ሄኖክ የሺጥላ
ሰሞኑን ወያኔ እንደ አናጤ ሱሪ አስር ቦታ ለጣጥፎ (በእንግሊዘኛው edit and copy paste ) አድርጎ ያቀረበልንን እና በፖሊስ ፕሮግራም ያስተላለፈልንን ቪዲዮ ተመለከትኩ። በጣም የገረመኝ ነገር ግን እኔ የማላውቀውን ፣ ወያኔ የሆነና አማሪካ ወይም አውሮፓ ሀገር የሚኖር ( እሱም ቢሆን ላያውቀው ይችላል ብዬ የማልገምተውን ነገር እንዳልተናግውሩ እሙን ነው )።
እጅግ የገረመኝ ግን ይሄን ሁሉ ቀን (ጊዜም አጥፍተው ) ከ ፍላሹ ላይና ሃርድ ድራይቭ ላይ ያገኙትን ነገር ሊያሳዩን አልፈቀዱም ? ለምን ? አንዳንድ አዳዲስ መረጃዎችን ጨመርመር አድርጎ ግንቦት ሰባትን ለመውቀስ ይሆን ? ( ምናልባት ግንቦት 7 ኢትዮጵያ ያለውን የአማሪካን እምባሲ ለማፈንዳት እንዳሰበ በማሳየት ፣ ደሞ እነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ተላልፈው የሚሰጡብትን ነገር እየቆፈሩ እንደሆነም ሹክ ተብየአለሁ )። አውሮፓ ያሉትንም እንዲሁ ! ግን ትንሽ ስለ ፎረንሲክ ሳይንስ እውቀት ያለው ታጋዳላይ ካለ ምክር ቢሰጣችሁ ከጉድ ትድናላችሁ !
የአቶ አንዳርጋቸው ቃለ መጠይቅ ግን ለኔ ምንም አዲስ ነገር አላየሁበትም ። ከዚያ ባለፈ ምንም ማለት አልፈልግም ። እንደሚሉን ግንቦት ሰባት አቅመ ቢስ ድርጅት ነው ወይ ? መልሱን ራሱ ወያኔው ይመልስ !