Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በአንዋር መስጊድ በተፈጠረ ግጭት የታሰሩ ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

$
0
0

-አንድ ጋዜጠኛና አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባልን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸው ተጠቁሟል ‹‹አብዛኛዎቹ ተለቀው ለግጭቱ ምክንያት የሆኑት ብቻ ታስረዋል›› ፖሊሶች

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ለጁምዓ (እለተ ዓርብ) ፀሎት መርካቶ በሚገኘው ታላቁ የአንዋር መስጊድ ተገኝተው የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሰሙት ጠንከር ያለ ተቃውሞ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት

demtschin yesema 2በመፈጠሩ፣ የተጎዱ የዕምነቱ ተከታዮች፣ የተለያዩ ግለሰቦችና የፖሊስ አባላት መኖራቸው ተገለጸ፡፡ በግጭቱ ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዕምነቱ ተከታዮችና በአካባቢው በግርግሩ ወቅት የነበሩ ሰዎች በፖሊስ ታስረው አንድ ቀን ካደሩ በኋላ፣ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀርበው ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡

ሐምሌ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በተለይ ሴት የዕምነቱ ተከታዮች ከድምፅ ያልዘለለ ተቃውሞ ማሰማታቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ የአሁኑ ከበድ ያለ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ግጭቱ በተፈጠረበት ወቅት በቦታው የጋዜጠኝነት ሥራዋን ስትሠራ ነበረች የተባለችው የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና ለግል ጉዳይዋ መርካቶ አካባቢ እንደነበረች በፓርቲው አመራሮች የተገለጸው የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ወደተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች መወሰዳቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡

በተለይ መሀል መርካቶ በሚገኘው አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ ኮልፌ ፖሊስ ማሠልጠኛ፣ ማዕከላዊና ኢትዮጵያ ትቅደም ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በርካታ ሰዎች ታስረው እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ተጠርጣሪዎች በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡

በወቅቱ በነበረው ግጭት የተፈነከቱ፣ የእጃቸው ጣቶች የተሰበሩ፣ የሚያነክሱና ራሳቸውን ስተው የወደቁ እንደነበሩ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸው፣ የፖሊስ ተሽከርካሪዎችና የቀይ መስቀል አምቡላንሶች ወደ ሆስፒታል ሲያመላልሱ መታየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ታሳሪዎቹ ‹‹ፍትሕ ናፈቀን፣ ፍትሕ ይከበር፣ የዕምነት ነፃነታችን ይከበር፣ የታሰሩ ይፈቱ፣ መንግሥት በዕምነታችን ጣልቃ አይግባብን፣ የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ…›› እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት በአንዋር መስጊድ ግቢ ውስጥ በማሰማት ላይ እያሉ፣ ከማን እንደተወረወረ ባልታወቀ ድንጋይ ፖሊሶች መጎዳታቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡

ለሥራ ወጥተው ምንም ሳያደርጉ ልጆቻቸው የት እንደደረሱ ማወቅ ያልቻሉ እናቶች፣ ቤተሰቦችና የሚመለከታቸው ወገኖች በየፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሲጠይቁ በቂ ምላሽ አለማግኘታቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ አንዳንዶቹ ወላጆች ደግሞ የልጆቻቸውን ስም እየተናገሩ የታሰሩበትን ፖሊስ ጣቢያ ለማወቅ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡና ምናልባትም በተለይ ሳያስቡትና በወጡበት ችግሩ የገጠማቸው በዋስትና ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡

በግጭቱ ወቅት በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ሰዎች ብዛትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ እንዲሁም የግጭቱ ዋነኛ መነሻ ምን እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና የፌዴራል ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ ማብራሪያውን ለማግኘት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፖሊስ አባላት እንደገለጹት፣ በግጭቱ ወቅት ቁጥራቸው በዛ ያሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ከበላይ ኃላፊዎች በመጣ ትዕዛዝ ሁሉም ማለት በሚባል ደረጃ ተለቀዋል፡፡ አሁን በቁጥጥር ሥር ሆነው በምርመራ ላይ የሚገኙት ለረብሻው ምክንያት የሆኑና በተደጋጋሚ ችግር ሲፈጥሩ የተገኙ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በደንብ በመደራጀት ሕዝብ ሰላም እንዳያገኝ በተደጋጋሚ ግጭት ሲያስነሱ የተገኙ ከ14 በላይ ግለሰቦች በተፋጠነ ችሎት እየቀረቡ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በግጭቱ ወቅት ፖሊሶች ሞተዋልና ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል ስለመባሉም ሐሰት መሆኑን ተናግረው፣ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ ግን አልካዱም፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ ለዓቃቤ ሕግ ካስረከበና የሚከሰሱ ከሆነም የፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲጠናቀቅ፣ የግለሰቦቹን የወንጀል ድርጊትና እንቅስቃሴ ከነማስረጃው ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>