ያለፉት ሁለት ዕትሞቻችን በማተሚያ ቤት ችግር ምክንያት ቀናችንን ሳንጠብቅ እሁድ በመውጣታችን አንባቢዎቻችንን ጊዜ እንደተሻማን ቢገባንም ችግሩ የጋራችነው ብለቹ ገበያ ላይ ስንውል ለገዛቹሁንና አስተያየት ለሰጣቹን እናመሰግናለን፡፡ አዲስጉዳይ ሁልጊዜም ታማኝነቷ ለአንባቢዎቿ ነው፡፡
በሐተታ አምዳችን አገራዊ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር በአገራችን የፖለቲካ ትኩሳቱ እየጨመረ መሄዱ የተለመደ መሆኑን የቀደሙት ምርጫዎች ምስክሮች ናቸው፡፡ ሰሞኑን የታየው የሦስት ፓርቲ አመራሮች እስር ከእዚህ ጋር ተያያዥነት እንዳለው የተለያዩ ግለሰቦችና ምሁራኖች ይናገራሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ 2007 ምርጫ ከመድረሱ በፊት የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው ጨምሮ ጋዜጠኞችን በሽብተኛ ሕግ በማሰረ ምርጫውን ጠቅልሎ ለማሸነፍ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ጨምረው ይነጋራሉ፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን የምርጫ ዕዳዎች ምርጫ ሲቃረብ፣ውጥረቶች ሲባባሱና እስራቶች ሲበራከቱ ሲል በሽፋን ገፃችን አስፍረናል፡፡
አንድ ሀገር ተተኪ ትውልድ እንዲፈጠርባት ከተፈለገ በቤተሰብ፣በአካባቢና በትምህርት ቤት ልጆች እንዲያነቡ የሚያበረታቱ ለትውልድ ተቆርቋሪ የሆኑ ዜጎች ያስፈልጉናል፡፡ምክንያቱም ያላነበበ ትውልድ ስለራሱ፣ሰለ ሀገሩ ታሪክ የሚናገረው ያጥረዋል፡፡ በተጨማሪም የማያነብ ኀብረተሰብ እንደማይጽፍ ፣የማይጽፍ ኀብረተሰብ ደግሞ እንደማያብና ማንበብና መጻፍ፣አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን የሚዳስስ ጹሐፍ በዐብይ ጉዳይ ገጻችን “ኢትዮጵያ ታንብብ!! የዕውቀትና ያባህል ሕዳሴ በኢትዮጵያ” በሚል ሰፊ ትንታኔ የሚሰጥ ጹሑፍ አስተናግደናል፡፡
የሰሞኑን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እስርን አስመልክቶ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት ከሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፋራው እና ከሰማዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጋር በቃለምልልስ አምዳችን ተስተናግደዋል፡፡
80 ቀን ያስቆጠረው የስድስት ጦማሪያንና የሦስት ጋዜጠኞች እስር የፍርድ ቤት ውሎና የክሳቸውን ዝርዝር የሚያመልከት በሰሞነኛ አምድ ተስተናግዷል፡፡
በአንድ ጉዳይ ገጻችን እሁድ ከምሽቱ 3፡45 እልፈቱ የተሰማው ታዋቂው የወግ ፀሐፊ፣ደራሲ፣ ጋዜጠኛና መምህር የሆኑት መስፍን ሀ/ማርያም የሕይወት ታሪካቸውን የወግ ‘አባት በወግ’ በወግ ሲሸኝ ብለን አቅርበነዋል፡፡
አምደኞቻችን፡- ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ “ግራ እግርን ፍለጋ”፣ፊልፖስ ዓይናለም “የባልና ሚስት የእኩልነት መብት”፣ዳንኤል ክብረት “እንደገና እንጋባ”፣አሌክስ አብርሃም “ዘርፌ ቡቲክ!”፣በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር “የፓርላማው ኩንግ ፉ” እና ሰሎሞን ተሰማ ጂ. “መልሳይነት”! (ትናትና እና ዛሬ) የሚሉና ሌሎች በርካታ ጹሑፎች ተስተናግደዋል፡፡ —