Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሽንፍላ –ተንሳፎ የሚፈላ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ –  ሲዊዘርላንድ ዙሪክ

2

እያዘንኩ ብዕሬን አነሳሁ። የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን በፆማቸው እንኳን እንዲህ ሰላም ማጣታቸው የኢትዮጵያን መከራ ሃሞት ያደርገዋል። ፆም ላይ አኮ ምዕመኑ ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙበት የአደብ፤ የተደሞ፤ የጭምትነት ጊዜያቸው ነበር። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያን አጋድሞ እያረዳት ያለው ወያኔ ሽንፍላ በመሆኑ አቅል አልፈጠረለትም። ኑሮትም አያውቅም። ወያኔ በሁሉም መሰፈርት ከላይ ተነሳፎ የሚፈላ ሽንፍላ ነው። እርምጃው ሸውሻዋ፤ ትንፋሹ ከልካላ። አቅሙ ጭድ – ራዕዩ ንፋስ – አካሉ ብክነት – ህሊናው አሲድ ነው። ከንቱ!

የወገኖቻችን ዬአካሎቻችን ናፍቀውና ጓጉተው በምልዕት በሚታደሙት ፆመ – ሮመዳን የዛሬ ዓመት አሳርን አብዝተው የተቀበሉበት ወቅት ነበር። ዓውዳመታቸውም በደም ነበር የተወራረደው። በዐለም ላይ ያሉ ህዝበ እስልምና እምነት ተከታይ ሁሉ በሰላም ፍስካቸውን ሲከውኑ፤ ደስ ብሏቸው የተሰጣቸውን ጸጋ ለነድያን ሲራሩ፤ ኢትዮጵያ ላይ ግን በአደባባይ ዬዕምነቱ አዛውንታት የተደበደቡበት፤ ህፃናት ሳይቀሩ የተገደሉበት የመከራ ድቅድቅ የጨለማ ቀን ነበር።  ቀንበር! የኢትዮጵያ እስልማ እምነት ተከታዮች ከሌሎች ሀገር ሙስሊሞች በፍጹም ሁኔታ የተለዬ ሥነ ምግባርና ጨዋነት ያላቸው ሲሆኑ፤ በፋሽስቱ ወያኔ ግን በጠላትነት ተፈርጀው፤ መተንፈሻ ቧንቧቸውን ዘግቶና አስሮ አሳራቸውን – ፍዳቸውን እንሆ ቀን እዬቆጠረ ያበላቸዋል። ዬኢትዮጵያ የእስልማ ዕምነት ተከታዮች ሀገራችን ኢትዮጵያ በጠራቻቸው ማናቸውም ጊዜያት ሁሉ በግንባር ቀደምትነት እናታቸው ከእነሱ የምትጠብቀውን ግዴታ ሲወጡ ኖረዋል። ታሪካችን- ነፃነታችን፣ የጥቁር ገድላችን ሁሉ በዚህ ቅመም የተቀመመ ነው። በጠቀራው በወያኔ ዘመን ደግሞ የኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መብታቸው እንዲህ ተረገጦ፤ እንዲህ ተቀጥቅጦ በሰላምና በሥርዓት ሊፈታ የሚገባው ጥያቄዎቻቸው እንዲህ ባላፈለጉትና ባላሰቡት መልክ አቅጣጫውን እንዲቀይር ረብሻ የፈጠረው ፋሽስቱ ወያኔ እንጂ እነሱ በፍጹም ሊሆኑ አይችሉም። ይህ የፋሽስቱ ባህሬ መገለጫ በመሆኑ ደም መዲናዋ ላይ ስለጠማው ለዚሁ አቅዶ የተነሳበት እንጂ እነሱ ለምዕተ ዓመቱ የሰላማዊ ትግል ሐዋርያ ናቸው። ሰላማዊ ትግል ስልቱና አፈጻጸሙ፤ የሰላማዊ ትግል መሪና ተመሪ፤ የሰላማዊ ትግል ትሩፋትና ፋይዳ በስክነት አምሮበት የተከወነው ታሪክ አንድ የገደል መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን ተቋምም ነው። መጸሐፍ ተጽፎበት በት/ቤት ደረጃ ተማሪዎች ሊማሩት የሚገባ። ዜግነትንት አከበረ – ኢትዮጵያዊነትን ከበከበ – አብሮነት በተግባር ኳለ። አዎን! የፋሽስቱ ወያኔ መሰረታዊ የግለት መንገዱ  እንዲህ እሰኪ ላብራራው። ምሳሌ። ሀ/// ለ//// ሐ/// መ//// ሠ/// ቢኖሩ። የመጀመሪያ የጥቃቱ ሰለባ ሀ/// ከሆነ ወያኔ ለ – ለ/// ለ –  ሐ///  ለ – መ//// ለ – ሠ/// የተለዬ እንክብካቤና ግልብ ፍቅር ይለግሳል። ለ/// ሐ/// መ/// ሠ/// እውነት ይመስላቸውና በሀ/// ላይ ክንዳቸውን – ኃይላቸውን  - አቅማቸውን ከወያኔ ጋር አዳምረው ሀን//// ይከተክታሉ። ጦሩ ወደ እነሱ መዝመቱን ነገን ፈጽሞ አያቅዱትም። የወያኔ ዘመን ጠገብ እኩይ ረቂቅ መሰሪ ተግባሩ አንዱን ለማጥቃት ሌለውን በማስተባበር በሚያጠቃው ላይ ማናቸውንም ዬግለት ዘመቻ በመፈጸም ነው። ሽፍታው ወያኔ – ሀ/// ጥሩ ሁኖ መድቀቁን – ዳግም አገግሞ ሊነሳ አለመቻሉን ስያረጋግጥ ቀጣዩን  ዒላማ ለስለስ ብሎ እዬሰረሰረ ይጀምራል። በፋረሰው ሀ ላይ ሌላ ሸንኮፍ ሀን ይለብጣን ተለጣፊ ይፈጥራል። ይህም ቢሆን እዬተመነጠረ የሚወገድበት ቀን የሚጠብቅ የደለበ ሰንጋ ነው። የሆነ ሆኖ መተንፈሻ ቧንቧውን ከፍት አድርጎ እንዲያንቧርቅ ይፈቅድለታል – ለተለጣፊው። ከዚህ በኋላ ደግሞ ወደ ሌላው ጉልበታም የማንነት ተቋም ከዘራውን ይዞ ይዘምታል – አረሙ ወያኔ። ወደ ለ//// ይሄዳል። መጀመሪያ ለን/// ተርተር እያረገ አቅሙን ይሸረሽራል፤ እንደ ሥጋ ቀረምት በተመቸው መልክ ትናንሽ መደብ – ይሠራል። መደቡ በአፈር ሆነ በአሸዋ ይሆናል።። ከዛ በኋላ የለ/// አቅም መከፋፈሉን ሲያረጋግጥ ተለጣፊውን ሀን///  ከነተፈጥሯቸው ያሉትን  ሐ//// መ//// ሠ/// ያሰልፍና በእውነተኛው   ላይ ጦር ያውጃል። ሐ// መ/// ሠ/// ወደ እንሱ የሚመጣ ስለማይመስላቸው ጋሻ ጀግሬ ሆነው ጎሽ በርታ! እያሉ ሽፍታውን ይከብክቡና ዕውነተኛውን ለን//// በጠላትነት ፈርጀው አብረው ከጠላታቸው ጋር ይከተክቱታል። ለ/// የሚባል ነገር ድብዛው መጥፋቱን ሲያረጋግጥ ወያኔ ሌላ ተለጣፊ ለን/// ሞሽሮ የክህደት ካባ አለብሶ፤ ትንሽ እንደ ከብት አሞሌ መላሾ ሰጥቶ፤ ቀባብቶ ይጠፈጥፍና ያስጨፍረዋል። ለተወሰነች ጊዜ ያስዳንሰዋል። እሱ እራሱ ወያኔ እኮ  ቀፎውን አራት ኪሎ ልቡን ታላቋ ትግራይ ዶክተሪን ላይ አስቀምጦ በጅል አጃቢዎቹ ሸምቆ በቆረቆንዳ ተከታዮቹ ከትክት ብሎ ይስቃል። በዚህ መልክ አቅም ያለው ማናቸውም የማንነት ማማሳከሪያ ሰነድ ሆነ ውስጠት ሁሉ በዬተራ ደመራ የዶግ አመድ ይሆናል። ቲያትሩ ይህ ነው። ወያኔ አንድም የሚምረው ኢትዮጵያዊ ዘለላ አይኖርም ቁርጣችሁን እወቁ። የሚቀር የለም። ሆድ አደሩም ነገ ስሎ ወይንም ሰልቶ ወይንም ተስሎ በቀል ይጠብቀዋል። ልብሰህን እያወለቀ እርቃንህን ሲዘለዝልህ እያንዳንድህ ነገ ታገኘዋለህ። ብጣቂ ብናኝ እፍረት – ይሉኝታ ያልሰራለት የዘመኑ የአራዊት ተሰምሳሌት ቢኖር ወያኔ ብቻ ነው። የወያኔ ልብ በድንጋይ የተሰራ የበቀል ማሰሮ ነው። በዬትኛውም ዘመንን ትውልድ፤ በዬትኛውም ሁኔታ በህልም እንኳን የማይታሰብ ረግረግ ገደል ጉድጓድ ነው ወያኔ ማለት። የሚያረቃቸው አናቂ እሾኃማ ህግጋቶቹ የሚሞሽሩት ቋሳን ብቻ ነው። ነገር ግን በዚህ የቋሳ – ዝልል ጠማቂውም ጠጩም የነገ ተረኛ ተጠቂ መሆኑ ነው ሊመረምር የሚገባው ቁም ነገር። ሊፈተሽ የሚገባው እውነት። ሊታሰብበት የሚገባው አምክንዮ። ግን ህሊና ልብ ተግባራቸውን እንዲከውኑ ስንፈቅድ ብቻ። እማዝነው ለአፋሽ አጎንባሾች አሁንም ለወያኔ አንጣፊዎች ሆድ አደሮች ነው። ጅብ ዘመድ የለውም። እያንዳንዱ የወያኔ አባል ለህልውናው ተግቶ በተከታታይነት ይሠራል። በትጋት ሰይፉን በማናቸውም የወያኔ መንፈስን በሚጻረሩ ኃይሎች ላይ ይሰነዝራል። ትንሿን ነገር አይንቁም። የተሰባሰበ ፍላጎት ነው ያላቸው። ለማፍረስ ተልዕኮቻው ቃል ጠባቂዊች ናቸው። አጃቢው ደግሞ በማለቅለቅ ሸር ጉድ ይላል። ይህ ነው መፈታት ያለበት እንቆቅልሽ። የሰው ልጅ የቆመበትን መሬት ከመራመዱ በፊት አስተውሎ ሊያው ይገባል። መሬቱ ገደል ወይንስ ለጥ ያለ ሜዳ ስለመሆኑ? የወያኔ ማናቸውም እርምጃ በድልድይ ላይ ሳይሆን በገደል ላይ ነው። ድልድይ የሆኑት ደግሞ ከሌላ ብሄረሰብ የተወለዱ የባንዳ አበልጆች ናቸው። አሁን ደመ ነፍሱ  ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደስ አለኝ አንዱ አሻንጉሊት ናቸው። ቀን ወያኔ የሚጠብቅላቸው። ነገ ወያኔ ያሾልካቸዋል። አዋርዶና ጎራርዶ። አሁንም የተሰበረ ቅል ታውቃላችሁን ወገኖቼ? አዎን ለወያኔ ሃርነት ትግራይ አቶ ሃይለማርያም ማለት የተሰበረ ቅል ማለት ናቸው። ነገ ከጉብራቸው ላይ ሆኖ ወያኔ ያስተንፍሳቸዋል። ደመንፈስነታቸውን በሚገባ የተገነዘበው ወያኔ ዕቃ – ዕቃ እዬተጫወተባቸው ነው። ዝልብ! በተከበሩ የጀግና ጽላት አቶ አንዳርጋቸው እስር ላይ አቶ ሃይለማርያም እኮ ድርጊቱን ወያኔ ከፈጸመው በኋላ እኛ እንደሰማነው ነው የሚሰሙት። አሁንም ያሉበትን አያውቁም። የአቶ አንዳርጋቸውን ማናቸውንም የተከደኑ የበቀል እርምጃዎች ሲፈጸሙ ከጠባቂዎቻቸው ጀምሮ ከትግራይ ልጅ ውጪ ፈጽሞ ሊሆን እንዳማይችል በጣም በእርግጠኝነት መናገር እችላላሁ። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የታማኝነት መለኪያው ዘር ነው። ትግራዊነት። ከዚህ ያመለጡት እንደ ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ያሉት ደግሞ በእጥፍ የወያኔ ጭካኔ የሚጨቀጭቃቸው ለወያኔ የበቀሉ ቁርሾ ተጠቂዎች ናቸው። ስለምን? የወያኔን የናዚ መንገድ የተጸዬፉ ጀግኖቻችን ለእኛ  ስለሆኑ። በዚህ የባንዳ ዘመን የአሉላ ማሾ ስለሆኑ! ከመከራችን – ከችግሮቻችን – ከእንባችን ጋር ቤተኛ ስለሆኑ። የበቀልን የደም ጽዋ በአረመኔነት የሚያስፈጽሙ ባላሟሎች የፊት ለፊት ረድፈኞች የወያኔ ሃርነት አባላት ጭምር ናቸው። ነገም ለእያንዳንዱ የሚደርሰው የፈተና ጅረት ከዚህ አንጻር መፈተሽ አለበት።  ይህንን ያመረቀዘ – እጅግ የረቀቀ  - እጅግም በበቀል የበሰለ፤ እጅግም በበቀለ የተጠና፤ እጅግም በሳጥናኤላዊነት ግብር የተበከለ፤ የመርዝ ዘመን ከልብ ሆኖ መርምሮ፤ ቢያንስ አሁን ከ40 ዓመት ጥቃት በኋላ የጠላትን ጉርቦ አንቆ ደም ለማስተፋት መቁረጥ ያስፈልጋል። ቢያንስ ሥር ሰደዱ በቀል መነሻውና መድረሻውን በማስተዋል ማገናዘብ ያስፈልጋል። ንክኪ – ይሉኝታ – ዝምድና – ጋብቻ ይበቃ! ጥርት ብሎ የወጣው ጠላት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶና አራማጁ ፖሊሲ ነው። ሌላው ጭራሮ ነው። አሁንም የወያኔ ገበርዲን ለባሽ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የዛሬ የአካላችሁ ጥቃት ምንጩን ዕወቁት። ተራችሁ እስኪደርስ ከመጠበቅ አሁኑኑ ወያኔን አራግፋችሁ ከተጎዱ – ከተጎሳቆሉ – ከግፉዕን ጋር ሁኑ! ሌሎቻችሁም ብትሆን ተረኝነታችሁ የጊዜ ጉዳይ ነው። ከዛ በፊት መስመርን አስተካካሎ በጠላት ላይ አቅምን መሰንዘር ይገባል እላለሁ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባላት እኮ በጣም ነው የሌላውን ዝርያ የሚጸዬፉት። ምርጥ ዘሮች ናቸው። ደማቸው ተልይቶ የተፈጠረ¡ ማስጠጋትም አይፈልጉም። ከደማቸው ጋር እንዲቀራረብ አይሹም። እዬተጠላ የሚያጎነብስ – የሚያረብርብ ግልብ እንደ ሰው ለማዬት ይቀፋል። የሚያናድደኝ እኔ በግሌ ስጠላው የሚወደኝ ነው። አዎን የሌላ ዘር አባላትን የወያኔ አሽቃባጮችን የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባላት እንዴት እንደሚጠሏችሁ ማን በነገራችሁ?! አስተውሉ! ፉከራ አይደለም ከልባችሁ ሁኑ ለማላት ነው። አረም እያለ በወገኑ የሚስነቀለው ወገን ጠላቱ ወያኔ ነገ የነቀላው ተባባሪ የሆነውን አረም ብሎ መነቀሉን ፈጽሞ አስቦት አያውቅም። ትዝም አይለውም። እያንዳንዱ የወያኔ ጋሻ ጀግሬ የታላቋ ትግራይ ራዕይ አስፈጻሚ ስለመሆኑ ምን አልባት ከእንቅልፉ ሲነቃ – ሀገር አልባ ሆኖ አፈር ለማኝ ሲሆን – ይገባው ይሆናል። እስካ ዛ ድረስ ግን የወያኔ አሲድ አዚም ተጠቂ ነው …. እራስን ማቃጠል ….. ማንደድ ….. ለትምህክት ሰለባነት፤ ዘር ለማጥፋት ተልዕኮ አባሪና ተባባሪ መሆን። ነገም በተረኝነት እራስን እረስቶ ወይ ፍቆ መጠበቅ። ሃፍረት! ይቋጭ። እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ኢትዮጵያ ልጆች የእስልምና ዕምነት ወገኖቼ ሀዘኔ ከልብ፤ ዕንባዬም ከውስጥ ነው። እግዚአብሄር አምላክ ብርታትና ጥንካሬውን ይላክላችሁ። አሜን!   Radio Tasegaye or www.tsegaye.ethio.info aktuell sendung www.lora.ch.tsegaye   መራራውን ዘመን ጣፋጭ ለማደረግ ሁሉም በጠላቱ ላይ ይቁረጥ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>