1. አጃ ጥሩ ጣዕም ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ ከተመገቡት በኋላ የረሀብ ስሜት እንዳይሰማዎት ያደርጋል፤ በፋይበር የበለጸገ በመሆኑምየኮልስትሮል መጠንን ያስተካክላል፡፡
2. እንቁላል እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ሆኖ የካሎሪ መጠኑ ግን አነስተኛ የሆነ ነው፡፡ እንቁላል ጡንቻዎችንና ጥሩውን የኮልስትሮል ዓይነት ለመገንባት ይረዳል፡:
3. አፕል በአንቲኦክሲዳንቶችና በሌሎችም የበለጸገው አፕል በተለይም በውስጡ የሚገኘው ፔክቲን የስብ መጠንን ይቀንሳል፡፡
4. አረንጓዴ ቃሪያ በአረንጓዴ ቃሪያ ውስጥ የሚገኘው ካፕሴሲን የአካላችን የእድገት ህዋሳት እንዲዳብሩ በመርዳት ስብ በፍጥነት እንዲቃጠል ይረዳል፡፡
5. ነጭ ሽንኩርት በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኘው አሊሲን የጸረ-ባክቴሪያ ባህሪአለው፣ ይህም ስብ እንዲቀንስና በደም ውስጥ የሚገኘው መጥፎው ኮልስትሮል እንዲወገ ድያደርጋል፡፡
6. ማር ስብን ለማቃጠል ማር ዋንኛውተመራጭ ነው፡፡ ለዚህም ማርን በሙቅ ውሃበጥብጦ ጠዋት ጠዋት መጠጣት ተገቢ ነው፡፡
7. አረንጓዴ ሻይ አረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው አንቲኦክሲዳንት የሰውነትን ክብደት ለማስተካከል ተመራጭ ነው፡፡ ለዚህም በየቀኑ ሁለት ብርጭቆ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት ይመከራል፡፡
8. ህዊት ግራስ (Wheat grass) የተሰኘው ተክል ስብ እንዲቃጠል ይረዳል፡፡
9. ቲማቲም ስብን በፍጥነት የማቃጠልብቃት ስላለው በምግባችን ውስጥ ብናካትተውተመራጭ ነው፡፡
10. ጥቁር ቸኮሌት በውስጡ የሚገኘው ፍላቮኖይድስ በደም ውስጥ የሚገኘውን ኮልስትሮል ለመቀነስ ይረዳል፡፡