በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። #Ethiopia የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ከባድ መሳሪያዎች ተወልውለው በድንበሩ ዙሪያ ተኮልኩለዋል።
የአንዳርጋቸው ጽጌ መያዝ ፡ የግንቦት ሰባት ጥሪ እና የትሕዴን ሰራዊት መመረቅን ትከትሎ በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ሰሜን ምስራቅ ድንበር ላይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ለሰሜን እዝ ቅርብ የሆኑ የሰራዊቱ ምንጮቻችን በደረሱን መረጃ አስታውቀዋል።እንዲሁም በአፋር ክልል ውስጥ ክፍተኛ ደህንነቶች በማፍሰስ ሕዝቡን እየሰለሉት መሆኑ ሲታወቅ ከፍተኛ አመጽ በክልሉ እንዳይነሳ ወያኔ መስጋቱ ታውቋል።
ወያኔ ተጠባባቂ ጦሩ ላይ እምነት ስለሌለው የትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ብቻ በተለያዩ ወረዳዎች በመሰብሰብ አስፈላጊውን መመሪያ የሰጠ ሲሆን በሁምራ ክዚህ በፊት ሰልጥነው የሰፈሩ እና መኖሪያቸውን እዛው ያደረጉ የወያኔ ልዩ ተጠባባቂ ጦር አባላት በነፍስ ወከፍ አዳዲስ ላውንቸር ክላሽንኮቭ እና ከበርካታ ጥይቶች ጋር እንደትድላቸው ታውቋል። እንዲሁም በትግራይ ውስጥ የሰለጠኑ ሚሊሻዎች ከነትጥቃቸው ድንበር አከባቢ ከዚህ ቀደም መሬት ተሰቷቸው የሰፈሩትም ለዚሁ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ተደርገዋል።ታንኮች መድፎች እና ከባባድ መሳሪያዎች ወደ ድንበሩ በመጠጋት አስፈላጊውን አሰሳ እያደረጉ ሲሆን የ24 ሰአት ልዩ ጥንቃቄ የተሞላበት ወታደራዊ የቁጥጥር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ምንጮቹ ጠቁመዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ መልክ በጎንደር በጎጃም እና በሰሜን ሸዋ ነዋሪዎችን መሳሪያ ማስፈታት ሊጀመር መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህም የሚያምለክተው አማራው ከግንቦት ሰባት ጋር ይሸፍታል የሚል ስጋት ስላላቸው መሆኑ ታውቋል። በዚህ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ይቀርባሉ።