07/15/2014
ሰሞኑን ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ የነበሩትን የግንቦት 7 ድርጅት ዋና ጸሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ብትራንዚት ላይ የመን ከተማ ሰንዓ የአየር ማረፊያ እንዳሉ በየመን የጸጥታ ሀይሎች ታፍነው ለትግራይ ነጻ አውጭ ግንብር (ወያኔ) ተላልፈው እንደተሰጡና አሳዛኝና ከስብእና ውጭ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆ እየሰማን ሰንብተናል። በየመን መንግስት ተባባሪነት፣ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመባቸውና እየተፈጸመባቸው ባለው ግፍ፣ ድብደባና ሲቃይ ልሳን ግፉዓን አጥብቆ ያወግዛል። ለመሆኑም በውጭ ሀገር ታፍኖ መወሰድ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እንዳልሆኑ ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን በሙሉ ማስታወስ እንወዳለን። የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት የትግራይን የመስፋፋትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማ እንቅፋት ይሆኑኛል የሚላቸውን በሱዳን በስደት ላይ የነበሩትን ያሉትን የወልቃይት የጠገዴንና የአርማጭሆ አርበኞች፣ ድንበር ጠባቂዎች ከሱዳን የጸጥታ ሀይል ጋር በመተባበር በ1981 ዓ/ም ህዳር 5 ጀምሮ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ እየታፈኑ ተወስደው ጠፍተዋል፡፡ለምሳሌ ያህል
1. ሻለቃ ጌታቸው ይርጋ
2. ሻለቃ አጣናው ዋሴ (80 አመት አዛውንት በ2009 … ማእከላይ እስር ቤት በደረሰባቸው ጉዳት አረፉ)
3. አቶ ናሩ ገብረህይወት 4. አቶ መከታው አዛናው
5. አቶ አበጀ ፈለቀ 6. አቶ መላኩ ንጉሴ
7. አቶ ዘውዱ አልጣህ 8. አቶ ፈንቴ ገብሬ
9. አቶ ሀጎስ ጌታሁን 10. አቶ አስራደ በየነ ….ይቀጥላል
ሰሞኑንም ለሱዳን የጸጥታ ሀይሎችታስረው(ታፍነው) ለትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት እንዲሰጡ የሚፈለጉ ሰዎች ስም ዝርዝር የተሰጠ እንዳለ ማስረጃ ደርሶናል። ይህንን ህገ ወጥ ተግባርም አበክረን እናወግዛለን፡ እንቃወምም አለን።
ወድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤
የኢትዮጵያ ህዝብ ግፍና በደል ጽዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። ሀገር ውስጥ መኖር አልተቻለም፤ ውጭም በተለይ በኢትዮጵያ አጎራባች አገሮች ውስጥ በስደት ለመኖር አስቸጋሪ የሆነብት አጣብቂኝ ውስጥ ደርሰናል። ሀገርና መደበቂያ ያጣ ሆኖ መኖር እስከመቸ ነው? አይበቃንም!
ሀገርንና ወገንን ለማዳን አሁኑኑ በጋራና በአንድነት መነሳት የግድ ይላል!
ልሳነ ግፉዓን