Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ቴዲ አፍሮ ሚኒሶታ ገባ –ዛሬ ቅዳሜ ምሽት በሚኒያፖሊስ የሚያደርገው ኮንሰርት በጉጉት ይጠበቃል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዮተኛ ተብሎ በበርካቶች አድናቆትን የተቸረው ቴዲ አፍሮ ዛሬ ቅዳሜ ጁላይ 12 በሚኒያፖሊስ ለሚያደርገው ኮንሰርት ሚኒሶታ ገባ። ድምፃዊው ከአንድ ሰዓት በላይ በዘገየው በረራው ሚኒሶታ ሲደርስ በርከት ያሉ አድናቂዎቹ ባንዲራ ይዘው በመቀበል ያላቸውን ፍቅር ገልጸውለታል።
teddy afro arrived minnesota
ቴዲ አፍሮ በሚኒያፖሊስ-ሴንት ፖል ኤርፖርት እንደደረሰ በዘ-ሐበሻ አማካኝነት በተደረገለት አጭር ቃለምልልስ ዛሬ በሚኒያፖሊስ የሚያሳየውን ኮንሰርት በጉጉት እንደሚጠብቀው ገልጾ “በፍቅር እና በሰላም ሚኒሶታ ደርሰናል፤ የፍቅርና የሰላም ኮንሰርታችንን እናደርጋለን” ብሏል። በሚሚሶታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቴዲ አፍሮን መምጣት በጉጉት ሲጠባበቁት የነበረ ሲሆን በከተማዋ በሚገኘው ራስ ሬስቶራንት የራት ግብዣ ተደርጎለታል። በራት ግብዣው ወቅትም የቴዲ አፍቃሪዎች ፎቶ ግራፍ አብረው በመነሳት ድምፃዊውን “እንኳን በሰላም ወደ ሚኒሶታ መጣህ፤ የነገውን ዝግጅትህን በጉጉት እንጠብቃለን” ብለዋል።

በሚኒሶታ የሚደረገውን ይህን “የፍቅር ጉዞ” ኮንሰርት በተመለከተ አንዳንድ ሃገር ወዳድ መስለው ከበስተጀርባ ሌላ ዓላማ ያላቸው ድረገጾች አንዳንዶች ሊያውኩት ይችላሉ በሚል እያወሩ ቢሆንም ከሚኒያፖሊስ ፖሊስ እና ከሚኒያፖሊስ ከንቲባ ቢሮ ዘ-ሐበሻ ባገኘችው መረጃ መሠረት የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንደሚጠናቀቅ ነው። እንደ ፖሊስ ገለጻ በሚኒሶታ ነዋሪ ነን ያሉና የኦሮሞ ማህበረሰብ ተወካዮች ነን ያሉ 5 ሰዎች ለፖሊሱና ለከንቲባው ጽህፈት ቤት ኮንሰርቱ እንዲሰረዝ ጥያቄ አቅርበው ነበር። ሆኖም ግን ይህ ሳይሳካ ቀርቷል። በተለይም ሚኒያፖሊስ በኦል ስታር ጨዋታዎች ከሌላ ስቴት በመጡ እንግዶች የተነሳ በከፍተኛ ጥበቃ ሥር ያለች ሲሆን የሚኒያፖሊስ ፖሊስም አስፈላጊውን ጥበቃ ለዚህ ኮንሰርት እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ቴዲ አፍሮን “የፍቅር ጉዞ” ኮንሰርት ለመታደም ከሚኒሶታና አጎራባች የአሜሪካና የካናዳ ከተሞች በርካታ ወገኖች የገቡ ሲሆን ትኬቶችም በተለያዩ የኢትዮጵያውያን መደብሮች በመሸጥ ላይ ናቸው። ቅድሚያ ከሱቆች ለሚገዙ ዋጋው $37 ሲሆን በር ላይ $42 ነው። ከቴዲ አፍሮ ማናጀር አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው ባገኘነው መረጃም የቴዲ ኮንሰርት በጊዜ ስለሚጀመር በሩ ከምሽቱ 9 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከፈት አስታውቀዋል። ሁለት አዳዲስ ነጠላ ዜማዎቹንም በሚኒያፖሊሱ ኮንሰርት እንደሚያቀርባቸው ገልጸዋል።

የቴዲ ኮንሰርት በዳውንታውን ሚኒያፖሊስ Mill City Nights: 111 5th St N, Minneapolis, MN 55403, ይደረጋል። ለበለጠ መረጃ በ 651 955 6091 ወይም 612 226 8326 ይደውሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>