Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም የወያኔን ጸረ-አገርና ሕዝብ ድርጊት በማወገዝ በሚኒሶታ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ።

$
0
0

የኢትዮጵያና የሕዝቦችዋ ደመኛ ጠላት የሆነው የወያኔ መንግሥት ሥልጣን ከወጣበት ከ1983 ዓም ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ ለነፃነት ፣ ለእኩልነት ፣ ለዲሞክራሲያው ሥርዓት የሚታገሉትን ከሕዝብ ልጆች በመግዸል ፣ በማሳር፣ ሰውሮ በማጥፋት፣በማሳቃየትና  መብታቸውን በመግፈፍ በጠመንጃ ኃይል በሥልጣን ላይ ተቆናጦ ይገኛል። ከዚህ በፊት ከሱዳን ፣ ከጅቡቲ ከኬንያ፣ ከሶማሌላንድ  መንግሥታት ጋር በማበር ኢትዮጵያውያንን አፍኖ በመውሰድ ለግድያና ለአስር ዳርጓቸዋል። ከሰሞኑ ደግሞ ከየመን መንግሥት ጋር  በመተባበር የግንቦት 7 ዋና ጻሐፍ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከሰናዓ አይሮፕላን ጣቢያ ወደ ኤርትራ ለመሄድ ትራንዚት በሚያደርጉበት  ወቅት አፍኖ በመውሰድ ማሳሩን እንዲሁም የየመንን የኣለም አቀፍ ድንጋጌ የጠሳውን ሕገወጥ ድርጊትና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ  ጣልቃ መግባቷን በመቃወም በሚኒሶታ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ስልፍ በሚኒሶታ ጠቅላይ ግዛት አስተዳደሪ ጽ/ቤት ፊት  ተካሄዷል። ሰልፈኛው በወክሎቻቸው አማካይነት ለአስተዳደሪው የተጸፈውን ደብዳቤ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ  መንግሥት የሚፈጽመውን የሰብአዊ መብት ረገጠና ሌሎች ወንጀሎች በዝርዝር አስረድተዋል።

ሰልፈኛው ከ10፡00AM- 12:30 PM ድረስ ለአስተዳደሪው ጽ/ቤት ሰራተኞና በአካባቢው ቆመው ሰልፉን ለሚመለከቱ አሜሪካውያን  የሰልፉን ምክንያት በማስረዳት ከአሜሪካ ሕዝብ በሚሰባሰብ ገንዘብ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ እየበደለ የሚገኛውን አምባገነን  መንግሥት መርዳት እንዲያቆም አሳስበዋል። ሰልፈኛው ግርማ ሞገሱ በሚያስፈራው የኢትዮጵያ ሰንዳቅዓላማ ተውቦ ብዙ  መፍክሮችንና ዜማዎችን በማዜም ወደ አስተዳደሪው ጽ/ቤት ደረሰ። ተይዘው ከነበሩት መፈክሮች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ነበሩ፡-

 

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
 ወያኔ የሕዝብ ጠላት ይወድማል!!
 የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸንፋል!!
 የዲሞክራሲ መብት ይከበር!!
 ዘረኝነት ይወገድ!!
 ሕዝብ ማፈናቀል ይቁም!!
 ወያኔ ገዳይ ነው!!
 ለትግል ቆርጠን እንነሳ!!
 የሕሊና እስረኞች በሙሉ ይፈቱ!!
 የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን መሰጠቱን በጥብቅ እንቃወማለን!!
 በቅርቡ በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ግድያ በጥብቅ እናወግዛለን!!
 Free Andargachew Tsige!
 Free Eskender Nega!
 Free Tsegaye Debteraw!
 Free All Political Prisoners in Ethiopia!
 Free Rhiot Alemu!
 Free Aberash Berta
 Free Muslim Peace Committee Leaders!!
 No Democracy!
 US stop helping the brutal regime in Ethiopia

 

ከዚያም ሰልፈኛው በመሰብሰብ የወያኔን የክክፍል ሴራ መቋቋም እንደሚያስፈልግ፣ ለዚህም መደራጀት እንደሚያስፈልግ ፣ ተደራጅተው የሚገኙ ድርጅቶችን መርዳት እንደሚያስፈልግ ፣ በወያኔዎች የንግድና ሌሎች ተቋማት ላይ እቀባ ማድረግ እንደሚያፈልግ  ፣ ወደፊት ለሚደረጉት ሁሉም ዓይነት እንቅስቃሴዎች አስቸኳይ መልስ በመስጣት የሥራ ግዴታዎችን መውጣትን በሚመለከት  ተነጋግሮ ከስምምነት ላይ በመድረስ ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል። የሚኒሶታ ግብረኃይል( Task Force in Minnesota

IMG_0406[1]   IMG_0405[1]   IMG_0411[1]   IMG_0410[1] 
  IMG_0412[1]


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>