ፍኖተ ነፃነት የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከትላንት በስቲያ የተያዙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በዛሬው እለት አራዳ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች እንደጠቆሙት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ም/ኃላፊ የሆነው አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ም/ሰባሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አራዳ ፍርድ ቤት ለጊዜ ቀጠሮ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ ጠበቆቻቸውን ጨምሮ ማንም ሰው እንዳይጎበኛቸው ክልከላ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ፖለቲከኞቹን ያሰረበትን ምክንያት እስካሁን ይፋ አላደረገም፡፡
↧
ኢሕአዴግ ለቃቅሞ ያሰራቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተባለ
↧