Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የሚያስከትላቸው 6 የጤና እክሎች

$
0
0

ከአድማስ ራድዮ አትላንታ የተገኘ (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
እንደሚታወቀው በቂ እንቅልፍ ያላገኘን ከሆነ የመነጫነጭ፣ ለስራ ተነሳሽነት ማጣት እና ድካም የመሳሰሉት ይከሰታሉ። ነገር ግን ከነዚህ ቀላል ከሚባሉ የዕለት ተዕለት ባህሪ ለውጦች በተጨማሪ የዕንቅልፍ እጦት ከፍተኛ የጤና ችግሮች እንደሚያስከትል ለማሳወቅ እወዳለው።

1. የእንቅልፍ እጦት ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል።
✔ የልብ ህመም
✔ የደም ግፊት
✔ ስትሮክ
✔ የስኳር ህመም

2. የመደበት ስሜትን ያስከትላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ለረጅም ጊዜ ለእንቅልፍ እጦት የሚዳረጉ ሰዎች የመደበት ስሜት ያጠቃቸዋል።

sleep disorder
3. የሰውነት ክብደት መጨመር
የእንቅልፍ ዕጦት የረሀብ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ሆርሞኖችን በሰውነታችን እንዲመነጩ ስለሚያደርግ እና ከፍተኛ የምግብ ፍላጎት እንዲኖረን ስለሚያደርግ የሰውነት ክብደታችን እንዲጨምር ያደርጋል።

4. ቆዳችን ያለ ዕድሜ እንዲያረጅ ያደርጋል
የአይን ማበጥና መቅላት ከዚህ በተጨማሪ በዓይን አካባቢ ጥቁር የሆኑ ቀጭን መስመሮችና የቆዳ መሸብሸብ የእንቅልፍ ዕጦት ከሚያስከትላቸው በቆዳ ላይ ከሚታዩ ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው።

5. ውጤታማነትን ይቀንሳል
በቂ እንቅልፍ የማያገኝ ሰው ማንኛውንም ስራ ለመተግበር አቅም ስለማይኖረውና የስራ ፍላጎቱ ስለሚቀንስ በስራ ወቅት የሚፈጠሩ ስህተቶች የጎሉ ይሆናሉ። በዚህም ምክንያት ውጤታማነት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።

6. ለአደጋዎች ያጋልጣል
እንደ አንዳንድ የጥናት ውጤቶች መረጃ የእንቅልፍ እጦት ለመንገድ ትራፊክ አደጋዎች፣ በስራ አካባቢ የሚደርሱ የማሽን አደጋዎች እና በቸልተኝነት ለሚከሰቱ የእሳት አደጋዎች ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል።

እንቅልፍ ማጣት ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች ጥቂቶቹ የገለፅኩላችሁን ይመስላሉ፣ ስለዚህም ለአንድ ሰው በቀን ውስጥ የሚያስፈልገውን የስምንት ሰዓት እንቅልፍ መውሰድ ለጤናማ ህይወት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ በቂ እረፍት እንድትወስዱ እመክራለው።
ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ እጦት የምትሰቃዩ ከሆነ ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ ሀኪምዎን በማማከር ተገቢውን እርዳታ ማግኘት ይኖርብዎታል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>