Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአቶ አንዳርጋቸውን መሰጠት የሚቃወሙ ሰልፎች ተደረጉ

$
0
0

E5F6E8FB-88FF-423B-8D16-867DF49C8288_w640_sየግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰንዐ – የመን ላይ ተይዘው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጣታቸውን በመቃወም ዋሺንግተን ዲሲ እና በአባባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የመን ሪፐብሊክ ኤምባሲ ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል፡፡

የመን ኤምባሲ ደጃፍ ላይ የተገኙት ኢትዮጵያዊያን የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷ ያስቆጣቸው መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ከኤምባሲው የሚወጡና የሚገቡ ተሽከርካሪዎችና ሠራተኞችን በብዙ ድምፅ፣ ጩኸትና መፈክር አውከዋል፡፡ የመን ሽብርተኛ፣ ሃፍረት ለእናንተ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ የየመንን ባንዲራና የፕሬዚዳንቷን ፎቶ አቃጥለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>