Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ

$
0
0

Melaku-Fenta-and-Gebrewahid-Woldegiorgis የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ፡፡ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር በሚገኙት በእነ አቶ መላኩ ላይ የኮሚሽኑ

ዓቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የክስ መዝገቦች መካከል በመዝገብ ቁጥር 141356 ላይ ከቀረቡ 28 ክሶች መካከል 23 ክሶችን አሻሽሎ እንዲያቀርብ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15 ወንጀል ችሎት ብይን መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የፍርድ ቤቱን ብይን የተቃወመው የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የክስ መዝገቡን ማሻሻል እንደሌለበት በመጥቀስ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውንና ብይኑን መርምሮ የዓቃቤ ሕግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤቱን ብይን አፅንቶታል፡፡

የሥር ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ እንዲያሻሽል ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረው ዓቃቤ ሕግ በቡድን በቡድን ያቀረባቸው 23 ክሶችን ነጥሎ እንዲያቀርብ፣ ጊዜና ቀን ያልተጠቀሰባቸውን ክሶች ጠቅሶ እንዲያቀርብና ለክሶቹ ማስረጃነት ያቀረባቸው ሰነዶች ጥቅል በመሆናቸው የትኛው ማስረጃ ለየትኛው ክስ እንደሚያስረዳ ግልጽ ባለመሆኑ አስተካክሎ እንዲያቀርብ ብይን ሰጥቶ ነበር፡፡

ይህንን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ያፀናው በመሆኑ፣ ዓቃቤ ሕግ ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በችሎት ቀርቦ ክሶቹን አሻሽሎ የሚያቀርብበትን የጊዜ ትዕዛዝ ይቀበላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Source: Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>