እንደሚታወቀው የኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት በሁለቱም አገሮች ከባድ የሚባል መስዋእትነት ተከፍሎበታል። ይህ ጦርነት ሲጀመር ምክንያቱ ምን ነበር? ለመንስ ተደረገ? መቸና ለመን እንዲቆም ተደረገ? በግዜው ጦርነቱ ሲጀመር አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞችና ኢህአዴግ እንዳሉት ከሆነ የኤርትራ መንግስት ኢኮኖሚያዊ ችግር ነው ይላሉ። እውነቱ ይሀ ከሆነ ሆድ ይፍጀው። ለማነኛው ዛሬ ድረስ የእነዛን ጥያቄዎች መልስ ሳይፈታ ይሀው 16 ዓመታት አልፎ ቋጠሮውን ሳይፈታ ቀርቷል።
የሻዕቢያ ወረራ ገና ከመፈፀሙ በ1990 ዓ/ም በኤርትራ ይደረጉ የነበሩት ዝግጅቶችና ግልፅ የሆኑ የወረራ እቅዶች እንመልከት
1. ሻዕቢያ መጀመሪያ የመን ከዛ ሱዳንና ጅቡቲን በጦርነት መነካካት ከጀመረች ሰነባበታለች። በዚህ ግዜ በአካባቢው ከነበሩት አገራት የቀራት አንድ ኢትዮጵያ መንካት ብቻ ነበረ።
2. በኤርትራ የተለያዩ አገራዊ አጀንዳዎች ተነስተው ከኢትዮጵያ ጋር እያነፃፀሩ አስተያየትና ሃሳብ በግልፅ መስጠት የጀመሩት በመጋቢት 1990 ዓ/ም ነበር። በዛን ወቅት በተለይ በእምባ ትካላ በተባለው ቦታ ከሻለቃ አመራር በላይ በአጀንዳው እንዲወያዩበት ተደርጓዋል። በወቅቱ ኤርትራ በ 5 ኮር የተደራጀ ጦር አዘጋጅታ ነበር።
3. ሚያዝያ 29/1990 ዓ/ም ጀኔራል ስብሃት ኤፍሬም የኢትዮጵያ ሰራዊት ሁኔታ የሚገልፅ ደብዳቤ ለሁሉም የሻዕቢያ ክፍሎጦሮች በመላክ እንዲዘጋጁበት መልዕክት አስተላልፈዋል። በደብዳቤው የሚታይው መረጃ ኢትዮጵያ 30,000 ተዋጊ 20,000 እስታፍ ብቻ እንዳላት የሚገልፅ እስታቲክስ ጭምር ነበረበት።
4. ሻዕቢያ የተለያዩ ወታደራዊ መኪኖችንና ታንኮች ለጥገና በማስገባት አሉ የሚባሉ ሰዎች ከኢትዮጵያ ሳይቀር የቀድሞ የደርግ እውቁ የታንክ ባለሞያ ኮነሬል ተስፋማርያም ሳይቀር ጠርቶ ታንኮችንና ተሽከርካሪዎችን ማዘጋጀት የጀመረወ በዚሁ አመት 1990 ዓ/ም ነበር።
5. በ1990 ዓ/ም በጅማ ኢህአዴግ አዘጋጅቶት በነበረ ስብሰባና እንዲሁም ህወሓት ባደረገው ስብሰባ ሻዕቢያ ልትወረን ተዘጋጅታለች የሚሉ ሃሳቦች ቢነሱም የተሰጣቸው መልስ በፍፁም አይወሩኑም ነበር። እንደነ አበባ ፎሮ፣ ቄስ ጎነፅ፣ አቶ ተሰማ ስዮም ከትግራይና ኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ተወክለው ወደ ስብሰባ ስለመጡ ያዩትን ሁሉ ከነማስረጃ በማቅረብ አመራሩና ካድሬውን ለማሳመን ቢሞኩሩም የነ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር ብዱን አይሆንም ሻዕቢያ አይወሩንም ብለወ በእጅ ብልጫ ሃሳቡን ውድቅ አደረጉት።
6. ሻዕቢያ የመካናይዝድ ክ/ጦሩን ወደ ተኮምብያ፣ ሸላሎ፣ ሸንበቆ አስጠግቶ የመካናይዝድ ልምምድ ማድረግ ጀመረ። ከዚህ ልምምድ ጎን ለጎን የተለያዩ የስለያ ሰራተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ እንዲገቡ አደረገ። በወቅቱ ለመረጃ ስራ ከገቡት የሻዕቢያ ደህንነት ሰራተኞች በታህሳስ 1990 ዓ/ም በኢትዮጵያ ጃዊ ወታደራዊ ስለላ መስመር ውስጥ ገብተው ከተያዙተ ሰላዮች አንዱን በድምፅና በፅሁፍ የሰጠው መረጃ ሻዕቢያ ኢትዮጵያን ለመውረር በዝግጅት ላይ እንዳለች ግልፅ በሆነ መንገድ ያስረዳል። የተገኘውም ሪፖርት አሁኑም ለሟች ባለስልጣኑና አባላቱ ተሰጠ። ግን አሁኑም ሻዕቢያ አይወሩንም የሚል መልስ ተሰጠ።
7. ወረራው ከመጀመሩ በፊት በድንበር አከባቢ የነበረው አንዳአንድ የሻዕቢያ ተንኳሽነት የደረሰባቸው ገበሬዎች በወቅቱ የትግራይ ክልል መስተዳድር ባለስልጣናት ለነበሩት በሰጡት መረጃ መሰረት ከአካባቢው የኤርትራ ባለስልጣናት ጋር በሽሬ ከተማ ስብሰባ አድርገው ነበር። የስብሰባወ ሙሉ ይዘትና ተጨማሪ በድንበር ሲታዩ ነበሩት መረጃዎች በክልሉ ፕረዚዳንት ስም ለድርጅቱ መሪ ቢላክም እሳቸው ሻዕቢያ አይወረንም ነበር መልሳቸው።
የሚገርመው የቀድሞ የህወሓት መስራችና በ1967 የካቲት ወር ለስልጣና ኤርትራ ከሄዱት 9 ታጋዮች አንዱ የሆነው ታጋይ አውዓሎም ወልዱ በኤርትራ ሲደረገ የነበረው ሴራ ከፁሁፍ መረጃ ባሻገር በአይኑና አይቶ በጆሮው ሰምቶ ከኤርትራ ሳይወጣ ሪፖርት ሲያደርግ ነበር። ምክንያቱም በግዜው በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖ አስመራና ምፅዋ ሲንቀሳቀስ ከኢሰያስ አፍ ያመለጡትን ቃላት ሳይቀር ለማሳወቅ ሞክረዋል። ግን ሰሚ አጣ። በግዜው የትእምት ፕረዚዳንት የነበሩት ታጋይ ስየ አብርሃም በትግራይ እየሆነ የነበረውን ሁሉ በአካል አዲስ አበባ በመሄድ ሰዉየወን ለማስረዳት ቢሞኩሩም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይሆኑም አንተም አትሸወድ ኤርትራ አትወረንም ብለወ መልስ ሰጡት።
8. ወረራው ለማድረግ 10 ቀን ሲቀረዉ ከላይ ከተገለፁት 5 የሻቢያ ኮሮች የሰወ ሃይላቸው ለመጨመረ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዙር የሳዋ ሰልጣኞች ከተለያዩ ቦታዎች በልማት ስም በአስቸኳይ እንዲሰባሰቡ ተደረገ። በወቅቱ ሴት 54,202 ወንዶች ደግሞ 11,473 ብድምሩ 65,675 ወታደር በአጭር ግዜ ውስጥ ተስብስቦ የመዳራጀት ስራ ተጀመረ። የኛው መሪ አሁንም ዝምታን መረጡ
9. ወረራው ሊደረግ 2 ቀን ሲቀረው አዲስ አበባ ድረስ በመግባት ከሰውየውና ከቡዱኑ ጋር የሻዕቢያ ባለስልጣናት ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ ትልቅ ግብዣ ተደርጎላቸወ በባህርዳር እንዲሸኙ ተደርጓል።
ይህ ሁሉ ሲሆን የወቅቱ መሪያችን ሻዕቢያ አትወረንም ብለወ ድርቅ አሉ። ግን ለምን? አሁኑም መልሱን ሳይሰጡን እሳቸውም ወደ ላየኛው አገር ሄደዋል። ግን የሳቸው አጨብጫቢ የነበሩት ቋጦሮውን ይዘወት ዛሬ ድረስ ዘልቀዋል።
ግዜው ደረሰ ሻዕቢያ ዝግጅቱን ጨርሶ ወደ ተግባር ተሸጋገረ ግንቦት 4/1990 ዓ/ም እንዲህ ሆነ
• ከሻዕቢያ በሜ/ጀ ገ/ሄር ገ/ማርያም ከሚመራው 2001ኛ ኮር አንድ ብርጌድና አንድ ታንከኛ ሻለቃ እንዲሁም በሜ/ጀ ፊሊጶስ ገ/ዮሃንስ ከሚመራው 161ኛ ኮር ተጨማሪ አንድ ሻለቃ 8 ታንኮች አሰልፈው ባድመን የነበረወን የኢትዮጵያ ፖሊሰና ሚሊሻ ጠራርገወ ከተማዋን ያዙ።
• ከዚያ በኋላ በሜ/ጀ ፊሊጶስ የሚመራው 161ኛ ኮር ከባድመ ጀምሮ ሰምበልን በመግባት እስከ ተከዜ መንገድ ዘግቶ ቦታውን ያዘ።
• በሜ/ጀ ዑመር ሐሰን ጠዊል የሚመራው 381ኛ ኮር በሜ/ጀ ገ/ሄር የሚመራውን 2001ኛ ኮርን በመረከብ ከሰምበል ወደ ምስራቅ በኩል በማስፈት እስከ መረብ ወንዝ አፋፍ ላይ ተዘርግቶ ቦታ ያዘ።
• በሜ/ጀ ገ/ሄር የሚመራወ 2001ኛ ኮር ቦታወን 161ኛ ኮር አስረክቦ ወደ ዛላምበሳ ግምባር በመቀየር ዛላምበሳ ከተማን ተቆጣጠረ።
• በሜ/ጀ ሃይለ ሳሙኤል/ቻይና/ የሚመራወ 419ኛኮርና 525ኛ ናደው ኮማንዶ ክ/ጦር የጅቡቲን መስመር ለመቁረጥ ቡሬ ከተማ ገብተው መሸጉ።
• 271ኛ ኮር በባድመና ዛላምበሳ አማካይ ቦታ በሆነው መንደፈራና አዲካላ አልፎ ወደ ራማ ከተማ በመጠጋት ቦታ ይዘዋል።
በኢትዮጵያ በኩል
ወረራወ ግንቦት 4/1990ዓ/ም ሲጀመር ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ ከማንም ቀድሞ ከተወሰነ ሃይል ጋር ወደ ባድመ ግንባር በሚወስዱት መንገዶች አከባቢ ደርሷል። በመቀጠልም ኢታማጀርሹም ፃድቃን ገ/ትንሳኤ፣ ስየ አብርሃ ሁኔታውን ላማጤን ዓዲ ሃገራይ ደርሰዋል።
ሜ/ጀ ብርሃነ ነጋሽና ሜ/ጀ አበባው ታደሰ 31ኛ ክ/ጦር ይዘወ ከሁመራ ቀን ከለሊት ተጉዘው ሸራሮ ከተማ ደረሱ።
ሜ/ጀ ኣብርሃ ወ/ማርያም 11ኛ ክ/ጦር ይዘወ ዛላምበሳ ግንባር ደረሱ።
ሜ/ጀ ስዓረ መኮነንና ሜ/ጀ ታደሰ ወረደ 12 ክ/ጦር ይዘው ቡሬ ግንባር ደረሱ።
ትናንትና ግማሹን ከህወሓት ጋር ሆኖ ሌላውም ደግሞ ከደርግ ጋር ሆኖ እንደጠላት ሲፋለም የነበረውን ታጋይና ወታደር አሁን በአገራዊ ጉዳይ አንድ በመሆን አብሮ ድሮ ወደ ተወው ምሽግ ውስጥ ገባ።
ግንቦት 13/1990 ዓ/ም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተራችን ከተደበቁበት ብቅ በለው እኛ ስላም ፈላጊ ነን። ስለዚ ችግሩን በሰላም መፍታት አለብን ብለወ ለውጭና አገር ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። ይገርማል “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” ይሉታል እንደዚህ ነው።
ሻዕቢያ የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ከቁብ ሳይቆጥሩት ሰኔ 1/1990 ዓ/ም ውግያውን በከፍተኛ ሁኔታ ጀመሩት። በሁሉም ግንባሮች ሻዕቢያ እንዳሰበው ዓዲግራት ቁርስ መቐለ እራት ሳይበላ ኩፍኛ ተመቶ ተሸነፈ። አሁኑ ድሉ የኢትዮጳያ ሰራዊት ሆነ። መንግስታችን በአስቸካይ ሁኔታ በሚድያ ሁሉም በማሰራጨት የዘመቻ ጥሪ ያቀርባል። የኢትዮጵያ ህዝብ በአገሩ ጉዳይ ሁሌም የማይደራደር ህዝብ ስለሆነ ልክ ቆፎውን እንደተነካ ንብ ሆብሎ ወደ ነበሩት ማሰልጠኛ ማዕከሎች ጎረፈ። እንዲህ እንዲህ እየተባለ 1991 ዓ/ም ደረሰ።
በወቅቱ የአፍሪካ አንደነት መሪዎችና የተባበሩ መንግስታት መሪዎች ሁለቱም አገራት ለማስታረቅ ኡጋዲጎ ቢያገናኙዋቸው ሁለቱም ሳይስማሙ ቀሩ።
በዚህ መስረት እንደገና የካቲት ጀምሮ እስከ መጋቢት 16/1991 ዓ/ም የብዙ ሰው ህይወት የበላ ከባድ ውግያ ተደረገ። በዚህን ወቅት ፅሃይዋ ጠልቃ ባድመ ላይ የኢትዮጵያ ባንዴራ ተውለበለበች። ቢሆንም ግና በመካከለኛ ግንባር በተፈጠረው የውግያ ስልት ስህተት የኢትዮጵያ ሰራዊት ካባድ መስዋእትነት ከፈለ።
ቀጥሎም እንደገና ሰኔ የጦርነት ወር ናት የተባለ ይመስል 1991 ዓ/ም ሻዕቢያ ሰኞ ባድመ ብሎ ሓሙስ ቀን ከበድ ያለ ውግያ ጀመረ። አሁኑም ከመሸነፍና እፍረት ከመከናነብ አላመለጠም። የሰኔ ውግያ በጣም ከባድ ከመሆኑም ባሻገር ትልቅ ድል የተገኘበትና ብዙ መስዋእትነት የተከፈለበት ጭምር ነበር።
እንደዚህ እያለ 1991 ዓ/ም አብቅቶ 1992 ዓ/ም ተተካ። ኢትዮጵያ የሻዕቢያ ወረራ ከመመከት ወደ አጥቂነት ተሸጋግራ ሻዕቢያን ላይነሳ ለመጨረሻ ለመምታት አቋም በመወሰድ ሰፊ የስልጠናና ዝግጅት በማድረግ ግንቦት 4/1992 ዓ/ም ድንገተኛ ማጥቃት ሰነዘረች። ውግያው በተለየ ስልትና ዝግጅት ስለተደረገበት የኢትዮጵያ ሰራዊት በምዕራብ ትግራይ በኩል ተሰኔን አልፎ በረንቱ ከተማ በመግባት ሃይኮታን አልፎ አስመራን ለመግባት በጉጉት ይጠባበቅ ጀመር።
በመካከለኛ ግንባር ሻምበቆ በማለፍ ፆሮና ገብቶ አይቀሬው 95 ኪ/ሜትርን አልፋ የምተገኘውን አስመራን በርቀት ማየት ጀመረ። በምስራቕ ትግራይ በኩል ዛላምበሳ ከተማን አልፎ ሰንዓፈ ከተማ በመቆጣጠር እምባሴራ ተራራ ላይ ሆኖ አዲ ቀይሕና የአስመራ በር የሆነችሁ ደቀምሓሬን በርቀት እየተመለከተ መጣን መጣን ይላል።
በአፈር ክልል ባዳን አልፎ እንዳልጌዳ፣ ዓውዳ አልፎ የአሰብን መስመር ለመቁረጥ እየተፋለመ ይገኛል። በቡሬ ግንባርም የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ መስዋእትነት በመክፈል አይሞከር ምሽግን ደርምሶ የአሰብ ጨው ፋብሪካ ጋር ተጠግቶ የባህር በራችን ለመመለስ በስሜት እየተዋጋ ነበር።
በወቅቱ ከሻዕቢያ ከተማረኩት አንዱ ያለውን “ ዓስብ የነበረው ክ/ጦር ሁሉ ተነስቶ በዓፋር መሬት እንዳይቆረጥ ምፅዋዕ ላይ ተቀያሪ ምሽግ ሰርቶ ገብቷል። እዚህ ዓሰብ የቀረው አንድ ብርጌድ ነው። ይሀውም እኔ አንዱ የዛ ብርጌድ አባል ነኝ።” የሚል ቃሉን የሰማ ሰራዊታች ሺዎች ጓዶችን ወድቀው እያየ የነሱን መስዋት ከዳር ለማድረስ በደስታ ወኔውን ተነሳሳ።
ይህ ሁሉ ሲሆን የሻዕቢያ መሪዎች በሬድዮና ቴሌቪዥን ላይ የድሮ የሳህልና የናቅፋ ዘፈኖች ለህዝቡ እንዲታዮ በማድረግ የነበራቸውን ትጥቅና ንብረት ወደ ናቅፍና ሳህል መጫን ላይ ነበሩ።
የሰኔው አስደንጋጭ ቋጠሮ ድንገት ሳይፈታ ዱብ አለ።
በወቅቱ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አስቸካይ ደብዳቤ በመፃፍ ወደ ሁሉም ግንባሮች እንዲበተኑ ከማድረግ በተጨማሪም በመገናኛ ሬድዮ ጦርነቱን አቁሙ የሚል መመሪያ ሰጡ። በእርግጥ በግዜው በእጃቸው ያልነበረው የጦሩ መሪነት ስልጣን ፓርላማውን ድንገት ስብሰባ ጠርተወ የመከላከያ ጠቅላላ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስተር እንዲሆን ካፀደቁት ትንሽ ወራቶች ብቻ ነበር የተቆጠሩት። ይህ አዲሱን ስልጣን ተረክበው ነገሩን ባልታሰበ ሁኔታ ቀየሩት። እነዛን ትላንትና ሻዕቢያ ሊወሩን ነው ሲሉዋቸው አልሰማም ብለው መልስ የሰጡዋቸው የህወሓት መሪዎች በ1992 ዓ/ም በታቀደው ጦርነት ሻዕቢያን አንዴና ለመጨረሻ መደምሰስ የሚል በአራት ኪሎ ቤተመግንስት የፀደቀውን እቅድ አሁን እንዴት ነው በግለሰብ ደረጃ ሊቀየር የሚችለው? ብለው ቆሽታቸውን አረረ። ይባስ ብሎ የታሰረውን ቋጠሮ አልፈታ ብሎ ሲያንገላታቸው ህሊናቸውን ሽጠው ከመኖር ሃቁን ይታወቅ በለው በስበስባ ማጋለጥ ሲጀምሩ 1993 ዓ/ም አንጃ ተብለው ከድርጅቱ እንዲወጡ ተደረጉ።
የሆነ ሆነና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ በጦሩ ከባድ ተፅእኖ አሳረፈ። ከተራ ወታደር እስከ ከፍተኛ አመራር በየግንባሩ በተደረጉት ስብሰባዎች አቋሙን ግልፅ በማድረጉ ግማሹ የታሰረ ግማሹ ተባረረ ብዙ ነው። የጦሩ ጥያቄ ተገቢ ነው። ምክንያቱም ከዚህ በፊት በተደረጉ ውግያዎች ማለትም:
ግንቦት 4/1990 ዓ/ም በባድመና ዛላምበሳ ያለቁት ፖሊሶችና ሚሊሻዎች በአይኑ አይቷል።
ሰኔ 3/1990 ዓ/ም ነባር የህወሓት ታጋይና የቀድሞ የደርግ ወታደሮች በባድመና ዛላምበሳ እንዲሁም በቡሬ መስዋእት ከፍለዋል።
የካቲት እስከ መጋቢት 16/1991 ዓ/ም ባድመ ለማስለቀቅ በተደረገው ውግያ 11ኛ ክ/ጦር በ6 ዙር ፈንጂ ገብታ አንድ ብርጌድ ሙሉ በሰላሞ የከፈለችሁ መስዋት የሚዘነጋ አይደለም። በተጨማሪም በፆሮና፣ እግሪ መኸል፣ ሻምበቆ 20ኛ ክ/ጦር፣ 21ኛክ/ጦር፣ 22ኛ ክ/ጦር፣ 13ኛ ክ/ጦር እና ኮማንዶ የከፈሉት መስዋእት ዘግናኝ ነበር። የሰውና የእንስሳት ድምና ስጋ የማይለይበት መጥፎ ውግያ የተደረገበት ነበር።
ከሰኔ 1እስከ 18/1991 ዓ/ም ጠላት ሰኞ ባድመ ብሎ ሲመጣ በባድመና መረብ ግንባር አከባቢ 31ኛ ክ/ጦር፣ 33ኛ ክ/ጦር፣ 23ኛ ክ/ጦር፣ 13ኛ ክ/ጦር እንዲሁም ኮማንዶ የከፈሉት መስዋትነት ከባድ ነበር።
ግንቦት 4/1992 እስከ ሰኔ 7/1992 ዓ/ም በተሰኔ መግባትና እንዲሁም ሰራዊታችን ቦታውን ልቀህ ተመለስ የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ሰምቶ በሚወጣበት ግዜና እንዲሁም ሰራዊቱ በስሜት እንደገና ተመልሶ የተሰኔ ከተማ ሲቆጣጠር በነበረ ውግያ ከ15ኛ ክ/ጦር፣ 25ኛ ክ/ጦር፣ 27ኛ ክ/ጦር በተሰኔና በረንቱ መይዳዎች የክፈሉት መስዋእትነት ብዙ ነበር።
በግንቦት መጨረሻ ጀመሮ እስከ ሰኔ 15/1992 ዓ/ም በቡሬ በተደረገው ውግያ 39ኛ ክ/ጦር፣ 32ኛ ክ/ጦር፣ አግአዚ/ኮማንዶ/ ክ/ጦር የከፈሉት ከባድ መስዋእት በጠማ ከባድ ነበር።
ስለዚህ ሰራዊቱ በ1992 ዓ/ም ግንቦት ወር ውግያ ሲጀመር ሰኔ ላይ በሁሉም ግንባራት ማጥቃት ተሰንዝሮ አስመራ የሚለውን ዜማ ሊለቀቅ አፋፍ ላይ ነበር። ግን ይህ አልሆነም። ሌላው ከባድ መስዋእት የተከፈለባት በእጃችን መዳፍ ገብታ የነበረች አስብም ላትገኝ እንደገና አመለጠች።
በጣም በጣም የሚገርመው
ሰኔ 1990 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሰራዊት በሻዕቢያ ላይ ድል ተጎናፀፈ።
ሰኔ 1991 ዓ/ም ሻዕቢያ ባድመና ዛላምበሳን እንዲሁም ቡሬ ላያገኛቸው በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ገቡ።
ሰኔ 1992 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሰራዊት የኤርትራን ምድር 40 % የሚሆነውን ተቆጣጥሮ ውግያውን አቁም ተባለ።
ቆይሰቲ በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ በታዩት ሁለት ፍፌ ነገሮቸ ያዘለ ነበር
1. እኛ የሰው አገረ የምንገባ ወራሪዎች አይደለንም
2. የተባበሩት መንግስታት ማእቀብ ይጥሉብናል
ይገርማል ጨዋታው በሶማሌ ውግያ ያው እሳቸው በሰጡት መመሪያ የኢትዮጵያ ሰራዊት ባይዱዋን አልፎ ከፍተኛ መስዋእት ከፍሎ መቃድሸዎ ገብቷል። ይህ ወረራ አይደለም ማለት ነው። እንዲሁም የተባበሩ መንግስታት የኢትዮጵያ ሰራዊት ባይዱዋን አልፎ መቃድሸዎ ሲገባ ከማእቀብ ይልቅ ድጋፍና ዶላሮችን ቸበቸቡ። ጎማው ለብቻ መሪው ለብቻ ሆነብኝ።
ወይ ሰኔ ምን አይነት የማይፈታ ቋጠሮ ይዘሽ ነው እንደዚህ በሰው ህይወት የምትቀልጂ። ሻዕቢያ እንደሆነ ይሀው ዛሬም ነገም አሉ። ግን ለምን ያ ሁሉ ህይወት መጥፋት አስፈለገ እንዲህ ተመልሰው መምጣት የሚችሉበትን ዕድል ሰጥቶ? እኛስ ሰላም ፈላጊ ነን በአገር የመጣብንን ወደ ኋላ አንልም።
የኔ ጥያቄ ግን
ለምን በሚኒሊክ የነበረ ጥፋት
በሃይለስላሰ ያልተሰተካከለ
በኢህአዴግ ጭራሽ ላይነሳና ላይታሰብ በቋጠሮ የተዘጋ? ? ? ? ? ? ?
Source freedom4ethiopian Blog