Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በመቀሌ ትግራይ ቤታችን ተነጥቆ ለካድሬዎች ተሰጠብን ሲሉ ተቃውሞ ያሰሙ ታሰሩ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በመቀሌ የፊሕ ገረብ ተፈናቃዮች መሬታችንን ተነጠቅን፤ አላግባብም ሕወሓት የኛን መሬት ነጥቆ ለካድሬዎቹ እየሰጠ ነው በሚል ትናንት አርብ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ በዛሬው እለት ይህን ተቃውሞ ያስተባብራሉ የተባሉ ሰዎች ተለቃቅመው እንደታሰሩ አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ባሰራጨው መረጃ ላይ አስታወቀ።

የመቀሌ ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የመቀሌ ከተማ (ፎቶ ፋይል)


በትናንትናው እለት በመቐለ የገፊሕ ገረብ ተፈናቃዮች “መሬታችን ለካድሬዎች አንሰጥም!” በሚል ምክንያት በአካባቢው ተሰባስበው ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን የትግራይ ክልል ፖሊስ ህገመንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ያሰሙትን እነዚሁኑ ወገኖች በሃይል መበተኑ ታውቋል።

ሕወሓት መሬታችንን ነጥቆ ከቀያችን እያፈናቀለን ነው፤ መሬታችንም ለካድሬዎች እየታደለ ነው በሚል የሚያማርሩት ወገኖች ሰብሰብ ብለው ሲያቀርቡት የነበረው አቤቱታ ከተበተነ በኋላ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 14, 2006 ዓም ጥዋት በፖሊስ እየታሰሩ ነው። አብርሃ ደስታ እስካሁን ባለኝ መረጃ መሠረት እስካሁን ህዝቡን ወክለው ለአባይ ወልዱና በየነ መክሩ አቤታቱ ሲያሰሙ የነበሩ ከ20-40 የሚሆኑ ኗሪዎች መታሰራቸው አረጋግጫለሁ ብሏል።

ከታሰሩት አንዱ “ይህን ያህል ለህዝብ ጥላቻ ካላቹ ለምን ገድላቹ በዚሁ አፈር አትቀብሩንም” ብሎ መናገሩ ተመስክሯል።

በተመሳሳይ ዜናም በአዲስ አበባ ለረዥም ጊዜ የኖሩበትን የቀበሌ መኖሪያ ቤት ካድሬዎች በመምጣት ልቀቁ እያሉ እንደሚያስፈራሩና ቤቱን አስለቀቀውም ለራሳቸው እንደሚያደርጉት የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይህን ጉዳይ ዘ-ሐበሻ በደንብ ተከታትላ ትዘግባለች።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>