Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሰበር ዜና- ምዕራብ ወለጋ ከጊምቢ እና ቄሌም (እንፍሌ ወረዳ አሽ ቀበሌ) በሺህ የሚቆጠር የአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ተፈናቀሉ።

$
0
0

ጉዳያችን

Amhara woman lalibelaበሺህ የሚቆጠር የአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ እና ቄሌም በኃይል አካባቢውን እንዲለቁ ከመደረጉ በላይ ድብደባ እና ግድያ እንደተፈፀመባቸው ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሰኔ 12/2006 ዓም ምሽት ባስተላለፈው ዘገባ ገለፀ።

ዘገባው የተፈናቃዮችን ምስክርነት እንዳስደመጠው ድብደባው እና ግድያው በከተማው ሕዝብ እና ፖሊስ የታገዘ መሆኑን እና ህይወታቸውን ያተረፉት በኮርኒስ እና ጫካ በመደበቅ መሆኑን ሲገልጡ፣አንድ ምስክርነታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ተፈናቃይ አክለው እንደገለፁት ከጊምቢ ከተማ ብቻ ከሶስት ሺህ በላይ የአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።ሌላው ምስክርነት ሰጪ ደግሞ ቁጥሩን ከስምንት ሺህ ሕዝብ በላይ አድርሶታል።

አምስት ልጆች የነበራቸው መሆናቸውን የተናገሩት ሌላ ተፈናቃይ የነበራቸው መደብር መዘረፉን እና ካለምንም ሀብት መቅረታቸውን፣ጉዳዩን አቤት ለማለት ወደ ባለስልጣናት ቢሄዱም ሰሚ ማጣታቸውን አስታውቀዋል።

የቪኦኤ ጋዜጠኛ ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ብሎ የአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ኃላፊ የተባሉ እሳቸው ግን የኦሕዴድ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ነኝ ያሉ አቶ አወቀ የተባሉ የክልሉ ባለሥልጣን ስለጉዳዩ ሲናገሩ ”ያባረረ የለም’ ሲሉ ተደምጠዋል።

የኦሮምያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ራቢያ ኢሳ ”ሰዎቹ የሄዱት ፈርተው ነው” ካሉ በኃላ ”ቁጥራቸው ”መቶ አይሞሉም ” ማለታቸው ግርምትን ፈጥሯል።የቪኦኤ ጋዜጠኛ አቶ ሰለሞን በመቀጠል ” ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ አንድም ሰው ቢሆን ለምን ተፈናቀለ? ደግሞስ ምን ያስፈራቸዋል? ያብራሩልኝ ” ብሎ ለጠየቃቸው ወ/ሮ ራቢያ አጥጋቢ መልስ መስጠት ለመስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል።

የኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቡን በአካል መለብለብ ከጀመረ ሰነበተ።ሺዎች የእዚህኛው ሌሎች የእዝያኛው ናችሁ እየተባሉ ተፈናቅለዋል።በተለይ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጉርዳፈርዳ፣ከበንሻጉል፣ከኢልባቦር እና ከወለጋ አሰቃቂ ግድያ እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት እየተነጠቁ መባረራቸውን ያመለከቱ ዘገባዎች ሲወጡ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

voa amharic voice ቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት የድምፅ ዘገባ ለመስማት ይህንን ይጫኑ 

ሰኔ 12/2006 ዓም (ጁን 20/2014)

Source: gudayachn


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>