በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው እና ሰላማዊ ትግል 101 በሚል ስያሜ የሚጠራው አዲስ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ውሏል። ሰላማዊትግል 101 የተዘጋጀውበሰላማዊትግልየኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት እና የአገሩ ባለቤት በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲመውሰድየሚሹአገርወዳድኢትዮጵያውያንበተለይም ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ትምህርታዊየመወያያመጽሐፍእንዲኖረውታቅዶ ነው።ስለዚህ ሰላማዊ ትግል 101 በአቀራረቡም ሆነ በይዘቱ የውጭ አገር ቅጅ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ነው።
ሰላማዊትግል 101 ከአልበርትአነስታይንሰላማዊትግልምርምር ተቋምዘመናዊስራዎችውስጥ ጠቃሚዎቹን አቅልሎ አቅርቧል። መጽሐፉ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ህዝብ ነው የሚለው አባባል መሰረቱ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤትነቱ መሆኑን፣ የፖለቲካ ኃይል ድጋፍ ምሶሶዎች ሚና ምን እንደሆነ፣ የሲቪክ ድርጅቶች ሚና፣ ሴቶች ለሰላማዊ ትግል ያላቸው ተፈጥሮዋዊ ቅርበት፣ የሰላማዊ ትግል መፈጸሚያ መሳሪያዎች እነማን እንደሆኑ፣ ሰላማዊ ትግል ህዝብን እንዴት የራሱ ነፃ አውጭ እንደሚያደርገው እና የመሳሰሉትን የሰላም ትግል መሰረታዊ ጽንሰ አሳቦች አቅልሎ ይተነትናል።
መጽሐፉ ስለሰላማዊትግልእድገትታሪክይተርካል። ይህን ሲያደርግ ግን ከክርስቶስ ልደት ቀደም ብሎ ጀምሮ የሰው ልጅ በየክፍለ ዘመኑ በፍልስፍና እና በንድፈ አሳብ ደረጃ ካደረገው እድገት ጎን ለጎን የየዘመኑን ታሪካችንን በትይዩ በማመላከት አንባቢን ንፅፅራዊ ግንዛቤ ለማስጨበጥም ይሞክራል።
በኃይልየሚፈጸመውየመንግስትሽግግርባህላችንመለወጥ እንዳለበትለማስረዳትሰላማዊትግል 101 ከአክሱም ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ በተደረጉ የመንግስት ሽግግሮች የሆነውን፣ የተደረገውን እና የተፈጸመውን አሳዛኝ ታሪካችንን በአጭሩ ይተርካል። ሰላማዊትግል 101 ዴሞክራሲ በዳበረበት በምዕራቡ አለም እና አምባገነኖች በሚገዟቸው አገሮች ስለሚደረገው ምርጫልዩነት ዘርዘርአድርጎ አቅርቧል።የአሜሪካን፣የግብጽን፣የሰርቢያንናየዝምባቡዌንሰላማዊትግልናምርጫልምዶችምበየምዕራፉተንትኗል።ከኃይለስላሴዘመነመንግስትጀምሮለ80 አመታትያህልበኢትዮጵያየተደረጉትንምርጫዎችምይገመግማል ሰላማዊ ትግል 101።
ሰላማዊ ትግል 101 መጽሐፍ 232 ገጾች አሉት። ከፍ ብለው ከተጠቀሱት ቁም ነገሮች በተጨማሪ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ይዞ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ቀርቧል። በቅርቡ ደግሞ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በአውስትራሊያ ገበያዎች ይቀርባል። መልካም ንባብ። መልካም ውይይት።