Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

« ፀሎታችን በቤታችን » የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የፀሎት ቦታ እና የመቃብር ስፍራ ጥያቄ በሳውዲ አረቢያ ።

$
0
0

Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ

« ፀሎታችን በቤታችን »   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የፀሎት ቦታ እና የመቃብር ስፍራ ጥያቄ  በሳውዲ አረቢያ ።

በተለያዩ ግዜያት   ህጋዊ እና ህገወጥ በሆነ መንገድ ተሰደው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከሚገቡ ኢትዮጵያውያን መሃከል ጥቂት የማይባሉ  የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የህዝብ ሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ደንብ እና ስረአት   አክበረው እንደሚኖሩ ይታወቃል ። እነዚህ  በሃገሪቱ  ግዛቶች ሪያድ ጅዳ ደማም እና ጅዛን በሚባል ክፍለ ግዛቶች ውስጥ በተለያዩ ስራዎች ላይ  ተሰማርተው  እንደሚኖሩ የሚነገረው  የእመንቱ ተከታዮች በደስታም ሆነ በሃዘን ግዜ ሃይማኖታቸው  የሚያዘውን የፀሎት ስረአት ሃይማኖታዊ ወግ እና ስረአት  ጠብቀው ለፈጣሪያቸው ጸሎት ማድረስ እንደማይቸሉ የሚገልጹ ምንጮች ሳውዲ አረቢያ በስላማዊ ህግ የምትመራ  የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ  እንደመሆኗ መጠን  ሌሎች ሃይማኖቶችን ማራመድ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ በመንግስት ዘንድ በይፋ ከሚታውቀው ሃይማኖት ውጭ  ምንም አይነት አማራጭ የጸሎት ስፍራዎች ባለመኖራቸው  በኢትዮጵያውያኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ ከፈተኛ መንፈሳዊ ተጸዕኖ እንዳሳደረባቸው ይናገራል።

comnity jeddእንደ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች እንዳሉ የሚጠቅሱ ምንጮች  እንደ ፊሊፒንስ ፡ ኔፓል ህንድ ወዘተ  የክርስትና  እምነት ተከታይ እና ሌሎች መንፈሳዊ እምናተ ተከታይ  የውጭ ሃገር ዜጎች በኤንባሲያዎቻቸው  በኩል በሚደረግላቸው ሁለንተናዊ ትብብር እና ድጋፍ ህይወቱ ያለፈች ዜጋን አስክሬን  ተባብረው ለሃሀገሩ አፈር ሲያበቁ ከፈጣሪው ተማጽኖ የራቀውን ፈሪሃ እግዝብሄር  በየሃገሮቻቸው ኮሚኒቲ ተቋማት  ሰር ተሰባስቦ በሳምንት አንዴ « ከፈጣሪው ጋር ተገናኝቶ » ፀሎት የሚያደርስበት   ስፍራ እንደተዘጋጀለት የሚገልጹ እንዚህ ወገኖች  በሪያድ እና በጅዳ የሚገኙ የመንግስት ተወካዮቻችን  ለዜጎቻቸው ደህነት የሚጨነቁ ከሆነ  በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በጂዛን የኮሚኒቲ ግቢ እና በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት ካፍቴሪያ አዳራሾች ለዚህ የተቀደሰ ተግባር የሚውል ቤቶቻቸው የማይለየው ግቢውስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የፀሎት ቦታ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ  ይናገራሉ  ።

በየአመቱ በኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ም ዕመናን ዘንድ የሚከበሩ በአላትን ከሳውዲ አረቢያ ህግ አንጻር አንድ ቦታ ተሰባስቦ ማክበር እንኳን  እንደማይችሉ የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች  ኤምባሲውን በበላይ ነት የሚቆጣጠሩት ዲፕሎማቶች አብዛኛዎቹ የእልምና ሃይማኖት ተከታዮች በመሆናቸው  ዲፕሎማቱ  ለኢትዮጵያውያኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ትኩረት እንደማይሰጦቸው ይገልጻሉ። ይህ በዚህ እንዳለ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መካነ መቃበር ባለመኖሩ በተለያየ ምክንያት ህይወታቸ የሚያጡ የዕምነቱ ተከታዮች እስከሬኖቻቸውን ወደ ሃገር ለመላክ አቅም ስለማይፈቀድ በዲፕሎማቱ ፊርማ እና ሃላፊነት ሆስፒታል «ተላጃ »ገብቷል እየተባለ  ሃይማኖታዊ ስረአትን ባልጠበቀ ምንገድ በአቦጀዴ እይተጠቀለለ ወደ አልታውቀ ስፍራ እንደሚወሰድ ምንጮች አክለው ይገልጻሉ።

ቀደም ሲል አንዲት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ  ግቢ በሚገኝ ግዜያዊ መጠለያ ውስጥ ታማ ያለህክምና እርዳታ ስትሰቃይ ከርማ  ህይወቷ በማለፉ በዲፕሎማቱ ት ዕዛዝ በሳውዲ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች አስከሬኗ የት እንደደርሰ እንደማይታወቅ የሚናገሩ የልጅቷ የቀርብ ቤተሰቦች  እናት  የልጃቸውን  ሞት ሳይረዱ  ሳውዲ አረቢያ ለስራ የሄደቸው ልጄ ከዕለታት አንድቀን ጥሪት ቋጥራ ትመጣልኛለች  በሚል ተስፋ  የ ልጃቸው ሬሳ  በወግ በመአረግ  ለአፈር መብቃቱን ሳይረዱ መቅረታቸውን በሃዘን የሚገልጹ  ምንጮች በተመሳሳይ መልኩ ህይወታቸው አልፎ መርዶ ነጋሪ ያጡ ኢትዮጵያውያን ወላጆች  ብዛት ቤት ይቁጠረው ብለዋል ።  ፀሎታችን በቤታችን በሚል መሪ ቃል ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጎናችን ሊቆም ይገባል የሚሉ   በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እስካሁን ሳውዲ አረቢያ ምድር ላይ ህይወታቸው አልፎ  የቀብር ስረአታቸው በወጉ ሳይፈፀም የቀሩ ወገኖችን ሰም ዝርዝር   ዲፕሎማቱ ለቤተሰቦቻቸው በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት በኩል ይፋ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸው  ወድፊት እንደዚህ አይነቱ አሳዛኝ ታሪክ በዜጎቻችን ላይ እንዳይደገም   ኤምባሲው ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር የጋራ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በአሰቸኳይ እንዲቋቋም ጠይቀዋል ። 

riyad ethioian comintyይህ በዚህ እንዳለ ቀደም ሲል ጅዳ ከተማ  እንድ የገል መኖሪያ ቤት ውስጥ ተሰባስበው በጋራ  ፀሎት ሲያደርሱ በነበሩ የኦርቶዶክ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች  ላይ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች  በወሰዱት እርምጃ ከ39 በላይ ኢትዮጵያውያን ለእስር መዳረጋቸው አይዘነጋም  ። ይህንን እምርምጃ የሚያስታወሱ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ የእመነቱ ተከታዮች  የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች በአመታዊ በአላትም ሆነ በሳምንት አንዴ ም ዕመናኑ ተስባስበው በጋር መንፈሳዊ ፀሎታቸውን ያለምንም ስጋት የምናደርሱበትንም ሆነ  የእምነቱን ተከታዮች  ሃይማኖታዊ ግንዛቤ እንዲዳበር የሚያስተምሩበት  መንፈሳዊ ማዕከል በኤምባሲው ስር ከሚገኙ ተቋማት ውስጥ ጅዳ ፤ ሪያድ ፤ እና ጂዛን ከተሞች   እንዲፈቀድላቸው ተማጽነዋል ። ለህዝበ ክርስቲያኑ ምዕመናን ጥያቄ መስካት በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከጎናቸው እንደሚቆሙ ከኢትዮጵያን ሃገሬ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።   ይህን ጉዳይ በተመለከተ  በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ የሁኑትን አቶ ሸሪፍ ኬሬ +96626653444 እና ተቀማጭነታቸው ሪያድ የሆኑትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በዚህ ዙሪያ ለመነጋገር ያደርኩት ሙከራ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን አልተሳካም ። 

Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>