የህብር ሬዲዮ ግንቦት 24 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<... ኢትዮጵያውያን የዲሞክራሲ ሀይሎች መነቃቀፍ ትተው በአንድ ላይ ለጋራ ግብ መስራት ያለባቸው ወሳኝ ወቅት ላይ ነው ያለነው ...ህወሃት የወጠነልንን የከፋፍለህ ሴራ ትተን ለአገራችን የጋራ መፍትሄ ማበጀት አለብን ...>> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የቀድሞ የዓለም ባንክ አማካሪ እና ተመራማሪ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሸንጎ በሲያትል ላዘጋጀው ስብሰባ የሚያቀርቡትን የመፍትሄ ሀሳብ መሰረት አድርጎ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)
ኢትዮጵያውያን በምግባረ ሰናይ ተግባራቸው የሚዘክሯቸው የሰዎች ለሰዎች መስራች ካርል ሲዘከሩ (ልዩ ዝግጅት)
ግንቦት ሃያ ይዞት የመጣው ምስቅልቅል እና ሰብዓዊ ውርደታችን በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሪፖርት ሲዳሰስ( ልዩ ዘገባ አለን ሙሉውን ያዳምጡት)
<<...ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ለኢትዮጵያው አገዛዝ አሳልፎ አይሰጥም ከተባለ በሁዋላ በቅርቡ በይፋ በተከሰሰበት ጉዳይ ፍርድ ቤት ይቀርባል...>>
አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ የረዳት አብራሪውን ጉዳይ ከሚከታተሉት አንዱ ከሲዊዝ ጄኔቫ ለህብር ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
ውይይት እንደገና ዩኒየን እንደገና መደራጀት ?
ዜናዎቻችን
- በትግራይ አለመረጋጋት መኖሩ ተገለጸ
* የአረናን ልሳን ያደሉ ተደብድበው ሄስፒታል ገብተዋል
- ከአውስትራሊያ የሶማሌ ክልል ተወላጆች አዜብ መስፍን ከውጭ ኩባንያ ጋር ሆነው ከክልሉ ለተወሰደ መሬት ተጠያቂ መሆናቸውን ገለጹ
- ጅቡቲ አጥፍቶ መጥፋት በአገሬ ፈጸሙ ካለቻቸው ሁለቱ አንዱ ከኢትዮጵያ የሄደ መሆኑን ገለጸች
- የክርስትና እምነት ተከታይ በመሆኗ በሱዳን ሞት የተፈረደባት ትውልደ ኢትዮጵያዊትን የአገሪቱ ባለስልጣናት ልንለቅ ነው አሉ
- ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡትን ጦማሪያን ፖሊስ መንግስት ሊገለብጡ ነበር ሲል ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቀደለት
_ ፍርድ ቤቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ሽብር የለም ሲል ውድቅ ያደረገውን የ28 ቀን ቀጠሮ መቀበሉ ህጋዊ መሰረት እንደሌለው ታውቋል
_ ኤርትራ ወጣት ዜጎቼ በህገወጥ ደላሎች ሳቢያ ከአገር እየወጡብኝ ነው አለች
ሌሎችም ዜናዎች አሉ