Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የኢዴፓ ሕዝብ ግንኙነት በሴት ተማሪያቸው በስለት ተወጉ

$
0
0

በታምሩ ጽጌ

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ በአንዲት ሴት ተማሪያቸው በስለት ሦስት ቦታ ወግተው ኮሪያ ሆስፒታል መግባታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
news
አቶ ወንድወሰን በሴት ተማሪያቸው የተወጉት ግንቦት 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ገርጂ በሚገኘው ኢትዮ ፖርት ትምህርት ቤት ሲሆን፣ ደረታቸውን፣ ሆዳቸውንና ጭናቸውን መወጋታቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

ድርጊቱን ፈጽማለች የተባለችው ተጠርጣሪ ተማሪ፣ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን፣ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ስትደርስ፣ የትምህርት ቤቱ መምህርና ዩኒት ሊደር የሆኑት አቶ ወንድወሰን፣ ቤተሰቧን እንዲጠሩላት ጠይቃቸው ወደ ምክትል ርዕሰ መምህር ክፍል ሄደው ስልክ በመደወል ላይ እያሉ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

በባህሪያቸው በትምህርት ቤቱ ተወዳጅ መምህር መሆናቸው የተገለጸው አቶ ወንድወሰን፣ በደረሰባቸው አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ቢሆንም፣ የኮሪያ ሆስፒታል ሠራተኞች ባደረጉላቸው የተፋጠነ ሕክምና ሕይወታቸው ሊተርፍ መቻሉንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪዋ ተማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏንና ቦርሳዋ ሲፈተሽ ሦስት የስለት መሣሪያዎች መገኘቱንም ምንጮቹ አክለዋል፡፡

በ60ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙት የኢዴፓ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነትና መምህር አቶ ወንድወሰን፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ረጅም ጊዜ ያገለገሉ መሆኑን የጠቀሱት ምንጮቹ፣ ከሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት በዚህ ዓመት በተዘዋወረች ተማሪ ድርጊቱ መፈጸሙ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎች በሥነ ምግባር የታነጹ መሆናቸውን የትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ ሊመሰክር እንደሚችል የገለጹት ምንጮቹ፣ ጉዳዩ በፖሊስ የተያዘ በመሆኑ ስለተማሪዋና ከድርጊቱ ጀርባ ሌላም ነገር ካለ በቅርቡ ይፋ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው አክለዋል፡፡

ተማሪዋ በቁጥጥር ሥር መዋሏንና በገርጂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኘ፣ ከባድ የግድያ ሙከራ በመሆኑ ገና በምርምራ ላይ መሆኗን አንድ የፖሊስ አባል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የኢትዮ ፖረንት ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሲሳይ መርዕድን ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው ‹‹በስልክ መግለጫ አልሰጥም›› ብለዋል፡፡

የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ ስለ አቶ ወንድወሰን ጠይቀናቸው ድርጊቱን ባለመስማታቸው ተደናግጠው፣ ግንቦት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ተገናኝተው ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. የአባላትን ስብሰባ እንደሚመሩ ከመነጋገር ውጭ ምንም እንዳልሰሙ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ሪፖርተር ጋዜጣ የእሁድ እትም


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>