በያሬድ አማረ
ፍኖተ ነፃነት
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በውህደት ጉዳይ ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ጋር ሲደረግ የነበረው ውይይት በመጠናቀቁና ሁለቱ ፓርቲዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ምክንያት የቅድመ ውህደት ፊርማ ስነ-ስርዓት ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መላኩን የመኢአድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነው ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
እንደ ኃላፊው ገለፃ የቅድመ ውህደት ፊርማ ስነ-ስርዓቱን የሚያስፈፅሙ ከመኢአድ የተወከሉ የኮሚቴ አባላትንም ጭምር ያሳወቁ መሆኑንና በቀጣዩ ሳምንት የሚደረገው የቅድመ ውህደት ፊርማ ስነ-ስርዓትን በማካሔድ በአጭር ግዜ ውስጥ ሁለቱ ፓርቲዎች ወደ አንድ ውህድ ፓርቲነት እንደሚጠቃለሉና በቀጣይ ትግሉን በአንድነት ለመምራት የሚያስችል ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡