Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ የቦርድ አባላት ከስልጣናቸው ወረዱ፤ ቤተክርስቲያኑም በገለልተኛነቱ እንዲቀጥል ተወሰነ

$
0
0

debereselam Minnesota

ይታየው ከሚኒሶታ

ከአንድ ዓመት በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ ሲያወዛግብ፣ ሲያነጋገር ቆይቷል። “ሃገር ቤት ያለው ሲኖዶስ እና ውጭ ሃገር ያለው ሲኖዶስ እስከሚስማሙ ድረስ ላለፉት 20 ዓመታት በገለልተኛነት እንደቆየነው መቆየት አለብን” በሚለው እና “ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ መቀላቀል ያለብን ጊዜ አሁን ነው” በሚለው ወገን በተነሳው እሰጥ አገባ ሲታመስ የቆየው የሚኒሶታው ደብረ ሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ዛሬ ምላሹን አግኝቷል፤ በድምጽ ብልጫም በገለልተኛነቱ እንዲቀጥል ተወስኗል።

ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲቀላቀል የሚፈልገው ወገን በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር ያሉ አባቶችን ጋብዞ የነበረ ሲሆን በተለይ አቡነ ማርቆስ የተባሉ አባት ለ21 ዓመታት የቆየውን ቤተክርስቲያን “ህንጻ’ እያሉ ሲያንቋሽሹ እንዲሁም “መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያንን አሳማ ያርቡበት” ሲል አሰድቧል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ሲደርስበት ነበር። (የቪዲዮ ማስረጃውን ለማየት ይህን ይጫኑ)

ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲቀላቀል የሚፈልገው ወገን በዚህ ወቅት ከወያኔ ጋር በመቆም አልተሳካም እንጂ በዘ-ሐበሻ ላይም ክስ መስርቶ ነበር። ይኸው ወገን በሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚጻፉትን አስተያየቶች እንዲታፈኑ በጠበቃቸው አማካኝነት ደብዳቤ ጽፈው የነበረ ቢሆንም ዘ-ሐበሻ ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ ቆይታለች። ጠበቃቸው ለከሰሰችው ክስም ምላሽ አግኝታለች።

በነዚህ ሁኔታዎች የቀጠለው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ዛሬ በሕግ አደባባይ እጣፈንታውን የለየ ሲሆን “እግዚአብሔር አሸንፏል” ሲሉ ምእመናኑ ይገልጻሉ። እንደምእመናኑ ገለጻ “የወያኔ መንግስት ፖለቲካ በማይገባቸው እህትና ወንድሞቻችን ውስጥ በሃይማኖት ተቆርቋነት ስም ገብቶ፤ ካህናቱን በገንዘብ አታሎ ደብረሰላም ውስጥ ያለውን ከ1.7 ሚሊዮን ዶላር እጁ ለማስገባት ያደረገው ጥረት ከሽፏል፤ የወያኔ እቅድ 1.7 ሚሊዮን ዶላሩን በእጅ አዙር ወስዶ ወገንን ለመግደያ ጥይት ማዋል እንደነበር ደርሰንበታል” ብለዋል።

(በማህበራዊ ድረ ገጾች እየተበተኑ ካሉ ፍላየሮች መካከል አንዱ)

(በማህበራዊ ድረ ገጾች እየተበተኑ ካሉ ፍላየሮች መካከል አንዱ)


“እግዚአብሄር ታላቅ ነው” የሚሉት አንድ እናት “ለሰላም እና ለአንድነት ቆመናል። ካህናቱ ሁሉ ከጎናችን እንዲቆሙ ለምነናል፤ በተለይ አባ ሃይለሚካኤል እንደባትነታቸው ብዙ ጠይቀናቸዋል፤ ግን እርሳቸው ‘ቤተክርስቲያኑን ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ መመለስ የቀደመ ህልሜ ነው’ ሲሉ ነግረውናል፤ ያን ግዜ አባ ሃይለሚካኤል ከማን ጋር እንደቆሙ አውቀናል ሲሉ ይናገራሉ።

“በዛሬው ምርጫ በተለይ ላለፉት 20 ዓመታት ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ቤተክርስቲያናችንን ከአራቱ የቦርድ አባላት በቀር ሌላው ለሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ሊያስረክብ የነበረው ወገን ከስልጣኑ ተጠራርጎ በሕዝብ ድምጽ መባረሩ አስደስቶናል” ያሉን አስተያየት ሰጪዎች የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ወያኔ ያወጣውን ከፍተኛ ገንዘብ በማክሸፍ ለዚህ ድል መብቃቱ አኩርቶናል ብለዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>