Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር የሰውነት መለጠጥ ከወሊድ በኋላ ቋሚ ሆኖ እንዳይቀር 3 ዘዴዎች

$
0
0

pregnancy-facts04 በእርግዝና ወቅት የሚፈጠርብኝ የሰውነት መለጠጥ ቋሚ ምልክት እንዳያመጣብኝ ምን ላድርግ?

ጥያቄ፡- የማቀርበው ጥያቄ የ28 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ የዛሬ ዓመት የምወደውን ሰው አግብቼ አብሬ መኖር ጀምሬያለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ልጅ የመውለድ ፕሮግራሜን እውን ለማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ እናት መሆን በጣም የሚያስደስት ልምድ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በማረግዝበት ጊዜ ግን በእርግዝና ወር የሚፈጠረው የሰውነት መለጠጥ ቋሚ ምልክት እንዳያመጣ መከላከል እፈልጋለሁ፡፡ ምን ባደርግ ይሻለኛል?
ራሄል ወሰኑ

ውድ ራሄል፡- መልካሙ ዜና በእርግዝና አልያም በከፍተኛ የክብደት መቀነስ ምክንያት የሚከሰተው ሸንተረር ማጥፋት አስቸጋሪ በመሆኑ ሳይጀመር በፊት መከላከል መፈለግሽ ነው፡፡ ቆዳ ላይ የሚታየው ቀላ ያለ ትንሽ ቆይቶ አንፀባራቂ ወይንም ብራማ ቀለም ያለው ምልክት ወንድ ሴት ሳይል ማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በሆድ፣ በችን፣ በጡት፣ በታፋ ወይም በታችኛው ወገን ላይ ሊታይ ይችላል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪ ለተለያዩ ምክንያቶች በምንወስዳቸው መድሃኒቶች ምክንያት ጭምር ሊመጣ ይችላል፡፡
ሸንተረርን ለመከላከል የሚቻልባቸው ጥቂት መንገዶች መካከል የሚከተሉትን ልጠቁምሽ እወዳለሁ፡፡

1. ዘይት፣ ቅቤ፣ ሎሽን፣ ክሬም ወይም ለሸንተረር ተብለው የተሰሩ ልዩ ቅባቶችን ለቆዳችን የሚስማማውን በመምረጥ ሁሌም ያለመሰልቸት መቀባት፡፡ እርጉዝ ሴት ምንም አይነት ነገር ከመጠቀሟ በፊት ሐኪሟን ልታማክር የሚገባት ሲሆን ለጤናዋ የማይጎዳ መሆኑን ካረጋገጠች በኋላ በተፈገለው መጠን ያለማቋረጥ መቀባት ይኖርባታል፡፡
2. ‹‹ውሃ ጠጪ›› የሚባለው ተደጋጋሚ ምክር ለቆዳችን ጤናና ውበት በተራ ቁጥር አንድ ላይ ከሰፈረ ከርሟል፡፡ በመሆኑም ሸንተረር ከመከላከያ ዘዴዎች አንዱ ብዙ ውሃ መጠጣት መሆኑ ታምኖበታል፡፡ በቂ ውሃ ቆዳን በማለስለስ ሸንተረር በቆዳችን ላይ የመታየቱን እድል ዝቅ እንደሚያደርግ ጥናቶች የሚጠቁሙ ሲሆን፤ በብዛት የቡናና ሻሂ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች የጠጡትን ያህል ወይም ከዛ በላይ ውሃ በላዩ ላይ ቢወስዱበት ሸንተረርን ለመቀነስ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡

3. አትክልትና ፍራፍሬዎች በብዛት መመገብ

በሰለጠነው ዓለም ሰዎች ሸንተረርን ለማጥፋት ቀዶ ጥገና የሚያከናውኑ ሲሆን ውጤቱ በግለሰቡ ዕድሜ፣ የቆዳ አይነት እና የምግብ አወሳሰድ ይለያያል፡፡ በሀገራችን ይህንን መንገድ ተጠቅሞ ማስወገድ ስላልተለመደ ከላይ በተጠቀሱት ሁለት መንገዶች ተጠቅሞ መከላከል ይመረጣል፡፡ መልካሙን ሁሉ በእናትነትሽና በእርግዝናሽ መልካሙን ሁሉ እመኝልሻለሁ፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>