ዳዊት ሰሎሞን
ጋዜጠኛ ነብዩና የአንድነት ሊቀመንበር ታሰሩ
ጋዜጠኛ ነብዩ ሃይሉ የቀስቃሾቹን እንቅስቃሴ ለመዘገብ በወጣበት ለእስር ተዳርጓል፡፡በካዛንቺስ ፖሊስ ጣብያ ከነብዩ ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ሊቀመንበር ዘካሪያስ የማነብርሃንና ዘላለም ደበበ ይገኙበታል፡፡የጣብያው ኃላፊዎች ‹‹ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል››የሚል ውንጀላ አቅርበውባቸዋል፡፡
ጋዜጠኛ ነብዩ ሃይሉ የቀስቃሾቹን እንቅስቃሴ ለመዘገብ በወጣበት ለእስር ተዳርጓል፡፡በካዛንቺስ ፖሊስ ጣብያ ከነብዩ ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ሊቀመንበር ዘካሪያስ የማነብርሃንና ዘላለም ደበበ ይገኙበታል፡፡የጣብያው ኃላፊዎች ‹‹ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል››የሚል ውንጀላ አቅርበውባቸዋል፡፡
ፖሊስ ህገ ወጥ እስሩን ቀጥሏል አንድነቶችም በእስሩ አልበረገጉም
ከአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ለተቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት አባላት በራሪ ወረቀት በማደል፣ፖስተሮችን በመለጠፍና በመኪና ቅስቀሳ ሲያደርጉ የእውቅናው ደብዳቤ እውቅና ግልባጭ የደረሰው ፖሊስ አባላቱን በማሰር ስራ መጠመዱ አስገራሚ ቢሆንም የፓርቲው አባላት ቅስቀሳውን ከማድረግ አልተቆጠቡም፡፡
ፖሊሶቹ ለያዟቸው የአንድነት አባላት ወረቀት ለመበተን፣ፖስተር ለመለጠፍና የመኪና ላይ ቅሰቀሳ ለማድረግ ፈቃድ አምጡ በማለት ይጠይቃሉ፡፡ነገር ግን ለሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ከሚሰጥ ወረቀት በስተቀር ለቅስቀሳ ተብሎ የሚሰጥ ወረቀት ባለመኖሩ የፖሊስን እስር አስገራሚም አስተዛዛቢም አድርጎታል፡፡
የአንድነት አባላት በአሁኑ ወቅት በካዛንቺስ፣በቦሌና ንፋስ ስልክ ፖሊስ ጣብያዎች ታስረው ይገኛሉ፡፡