በቃሊቲ እና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!! ህዝቡ በነቂስ በመውጣት የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል!! በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል የሰየመውና እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ከህዝብ ጎን ሆነን ድምፃችንን እንዳናሰማ በግፍ የተወረወርንበት እስር ቤት ቢያግደንም ከአርብ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እስከሚደረግበት እለት ድረስ የርሀብ አድማ በማድረግ ከህዝቡ ትግል ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳያለን ሲሉ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ህዝቡ ከየቤቱ በነቂስ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
↧