ዳዊት ሰሎሞን
በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የኢኮኖሚ፣የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በተመለከተ የከተማይቱ ነዋሪ አደባባይ በመውጣት ድምጹን ከፍ ባለ መንገድ በዕሪታ እንዲያሰማ አንድነት ፓርቲ ለፊታችን እሁድ ጥሪ እያደረገ ይገኛል፡፡ነገር ግን ጥሪው በመብራት መጥፋት፣በንጹህ ውሃ አለመኖር፣በትራንስፖርት፣በቴሌ ኮም ኢንዳስትሪው ኋላ ቀርነትብቻ እንደሆነ በማስመሰል ለማንከኳሰስ የሚደረጉ ዘመቻዎች በፓርቲው ላይ ተከፍተዋል፡፡
እርግጥ ነው ለአንድነት
የኑሮ ውድነት፣የስራ አጥ ቁጥር መበራከትና እንደ ንጹህ ውሃ ፣መብራትና የቴሌ ኮም አገልግሎት ደካማነት አነገብጋቢ ጉዳዮች ተደርገው መወሰድ እንደሚገባቸው ያምናል፡፡
ሰልፉ ግን ከላይ ለመጥቀስ ከሞከርኳቸው ዐቢይ ጉዳዮች በተጨማሪ ‹‹የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ይመለከታል፡፡
የመልካም አስተዳደር እጦት ለእርስዎ ምንድን ነው?
የቢሮክራሲው መንዛዛት፣ሙስናው ፣ፍትህ ማጣቱ፣አድልዎ መደረጉ፣ስራ ለመቀጠር የድርጅት አባልነት መስፈርት መደረጉ፣በአስተሳሰብዎ የተነሳ ልዩነት እየተደረገብዎ መሆኑ፣የኑሮ ውድነቱ፣አፈናው፣እስራቱ ወዘተ አ