ክርስቶስ ተፈተነ መከራው ስቃዩ በዝቶ ደሙን በመስቀል ላይ አፈሰሰ፣ሞተ በ3ኛው ቀን በዚህች እለት ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ፣ሰማያዊ ክብሩን አሳየ ትንሳኤው እውን ሆነ።
የትንሳኤውን ታላቅ አውደ አመት በክብር በደስታና በፌስታ አልፋና ኦሜጋ በክብር እናስበዋለን ተመስገን።
ትናንት በጠበበውና በሚጨንቀው ክፍል ውስጥ ነበርኩ ዛሬ አነዚያ ክፉ ቀኖች አልፈው የተሻለ ከሚባለው ወህኒ እገኛለሁ።ግፍ ብሶት በደላቸውን ለአመታት እሰማና አሰማላቸው የነበሩ ግፉአን ኢትዮጵያውያንወገኖቼን በአካል አግኝቻቸዋለው።እኒህ ወገኖች የመንግስት ተወካዮቻቸውን ድጋፍ አተው አየገፉ ያሉት ህይወት አስደሳች ነው ባይባልም መራራውን ህይወት አሰልተችውን ውሎ አዳር እየተመለከትኩት ነው ።የዚህ ህይወት አስተምህሮቱ ዋቢ እማኝነቱ የወደፊት ህይወቴን እንደሚያደምቀው ሳስበው ክፉን ትዝታ አስፈንጥሮ ጥንካሬና ብርታትን ይሰጠኛል።
ዛሬ የሚከበረው የትንሳኤን በአል አለም በአንድ ቀን የሚያከብሩትን ልዩ አጋጣሚ ለኔ ቀኑን ልዮ የሚያደርገው የማከብረው በሺዎች ኢትዮጵያውያን ታሳሪዎች ታጉረው በሚገኙበት ማእከላዊ እስር ቤት ነው።
ለበአሉ ድምቀት ለመስጠት በአንድ የእስር ክፍል የምንገኝ
የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ገንዘብ አዋተናል።ፀሎተ ህማማት ከገባ ቀን አንስቶ በፆምና በፀሎት ለፈጣሪ ምልጃ በማቅረብ እንባቸውን አያዘሩ ፈጣሪያቸውንየሚለምኑ እስረኞች ከገቡበት ፈተና ፈጣሪ አንዲያወጣቸው ሲማፀኑ ሰንብተዋል።
ፍትህን እና ርትእን ተነፍገው ለወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የሚንገላቱ ዜጎች በመንግስት ተወካዮቻቸው ስለማይጎበኙ ከፍቶአቸዋል ፣አዝነዋል፣ተስፋ ቆርጠዋል።ፍትህን ከምድራዊ ባለስልጣን እናገኛለን አይሉም።እናም ፋታቸውን ወደ ፈጣሪ አዙረዋል።ከእለተ ህማማት እስከ ስቅለት እንባቸውን እያዘሩ ክአፉ ከመናገር ተገድበው አንገታቸውን ሰብረው ህማማቱን አሳልፈዋል።ከሴቶች እስር ቤትም ህማማትን በፆም በፀሎትና በስግደት የጌታችንን የመድሀኒታችንን የእየሱስ ክርስቶስ የመከራ ግዜ በማሰብ ከገቡበት መከራ ተገላግለው ወደ ሀገራቸው የሚገቡበትን የትንሳኤ ቀን ናአፍቀዋል።በአሉንም በሰላምና በደስታ ለማክበር ዝግጅት ማድረጋቸውን አውቃለሸሁ።
የትንሳኤን በአል በዚህ ሁኔታ በማከብርበት አጋጣሚ በመላው ሳውእዲ አረብያ ባሉ የህግ ታሳሪዎች የምህረት አዋጅ ከንጉስ አብደላ ፅህፈት ቤት ይለቀቃል የሚል ወሬ አየተዛመተ ይገኛል።ይህ የተስፋ የምስራች በብዙ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ታሳሪዎች ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ሆኑዋል።
ምህረቱን በሚመለከት በማእከላዊው እስር ቤት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሴቶች እስር ቤት ረብሻ ተነስቶ ሊያረጋጉ በሄዱበት አጋጣሚ የምህረት አዋጅ በቅርብ አንደሚደረግ በግላጭ መናገራቸው ተስፋውን አለምልሞታል።
የክርስቶስ የትንሳኤ በአል መልእክት ከጨነቀ ከጠበባቸው ወገኖች ጋር ሳስተላልፍ ፈጣሪ ከማያልቀው ምህረቱ ሁላችንን ይማልደን ዘንድ እንለምነዋለን።ድቅድቁ ጨለማ በክርስቶስ ይገፈፋል፣ይነጋልም።በምድራዊ ባለስልጣናት ምህረት ሳይሆን ዛሬ ሞትን ድል አድርጎ በተነሳው ክርስቶስ የመዳን ተስፋ ሰንቀናል።
መልካም የፋሲካ በአል
ነብዮ ሲራክ
ከአንዱ የሳውዲ ወህኒ።