ጓዶች በአፅቢ ከተማ አራት የዓረና አመራር አባላት ከያዙት አልጋ እንዲለቁለት ጠይቆ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ፖሊስ ጠርቶ ያሳሰራቸው የፌደራል መንግስት ባለስልጣን አቶ ተፈራ ደርበው (የግብርና ሚኒስተር) ነው። የፌደራል ባለስልጣን ሊይዘው የሚገባ አልጋ ይዛችኋል ተብለው ነበር ታስረው ያደሩ። ከአፅቢ የዓረና ስብሰባ በኋላ በአባይ ፀሓየና ስብሃት ነጋ የሚመራ የፌደራል መንግስት ልኡኳን የአፅቢን ህዝብ ችግር ለመፍታት (ወይ ለማባባስ) ተልከዋል። መሬት የህዝብ ይሆናል፣ ብድር በነፃ ነው ወዘተ እያሉ ዓረና ሲያስተምረው የነበረውን ሲሰብኩ ሰንብተዋል። ዛሬ ሰኞ መጋቢት 06, 2006 ዓም ደግሞ አስራአለቃ ስንታየሁ ይመር የተባሉ የዓረና አባል “ዓረና” የሚል ፅሑፍ ያለው ቲ-ሽርት በመልበሳቸው ምክንያት በፖሊስ ታስረው ከሰዓታት በኋላ ተለቀዋል