Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ተቃውሞ ገጠማቸው (ቪዲዮ ይዘናል)

$
0
0

አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰባቸው። በቪድዮ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሠረት ምዕመናኑ “ጎጃም ላይ የተሰረቀው ገንዘብ ሚኒሶታ ላይም አይደገምም” በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተውባቸው አንዳችም ንግግር ሳያደርጉ ከደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ እንዲወጡ መደረጋቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ሲያስተምሩ “በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ስር ካልገባችሁ ኢትዮጵያ መቀበር የለም”፣ የሚሶታውን መድሃኔዓለም ቤ/ክ “በረት” ሲሉ ገልጸውታል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰባቸው አቡነ ዘካሪያስ ከአቡነ ማርቆስ ጋር በመሆን ቤተክርሲያኑ በመንታ መንገድ ላይ ባለበት ሰዓት የመጡት ለመከፋፈል ነው በሚል ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ምዕመናን ይከሳሉ። የአቡነ ዘካሪያስን የአቡነ ማርቆስን የሚኒሶታ ደብረሰላም ቤ/ክ የተቃውሞ ውሎ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ፤ ከታች ደግሞ ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ም ዕመናን ያቀረቡትን ወቅታዊ ጽሁፍ ይመልከቱ አቡነ ዘካሪያስ የጎጃምን ሃገረ ስብከት በሚመሩበት ወቅት ስላጎደሉት ገንዘብ በቪኦኤ ሲጠየቁ “ገንዘቡ ጎሎብኛል፤ ለምኜ እከፍላለሁ” ማለታቸውን ብዙዎች ያስታውሱታል።

አቡነ ዘካሪያስን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ እንዳገኘናቸው ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን።

በእግዚአብሔር ስም አሜን። 4/5/2014

ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን
አንድነትን፣እርቅንና ሰላምን ከራሳችሁ ጀምሩ!

በኢተዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ዘመን ትልቁ ትንሽ የሆነበት ኃይማኖቱን በእለት ጥቅምና ሹመት ለውጦ ሁሉም ከትልቅ እስከትንሽ ለሆዱ ያደረበት ጊዜ የለም። የቀደሙት አባቶቻችን የቤትከርስቲያንን መብትና ሉአላዊነት ከማስከበር አልፈው ለአገራቸውም አርበኛና ሰማዕታት በመሆን
በታሪ የላቀች ሉዐላዊት ሃገርንና ርትዕት ኃይማኖትን አቆይተውልናል። ራቅ ያለውን ታሪክ ትተን የቅርቡን የጣሊያን ፋሺስት ወረራ ዘመን እንኳን ብናስታውስ ብዙ ካህናት አባቶች ከጀግኖት አርበኞች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ለአገራቸውና ለኃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል። ታላቁ ጻድቅና
አርበኛ ሰማእት ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ የሰሩት እጅግ አስደናቂ ታሪክ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።

መንጋውን እንዲጠብቅ በወንጌል የታዘዘ እረኛ ሕይወቱን እስከ ሞት ድረስ ለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣልና ኅዝቧም ምድሪቷም አይገዙልህ ብለው ጠላትን በማውገዝ በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የማይረሳ አኩሪ ተጋድሎን በደም ቀለም ጽፈውልን አልፈዋል። ዛሬስ? ንዑዳን ክቡራን የተባሉ አባቶች ለስማቸውና ለክብራቸው የሚገባ ሥራ እየሰሩ ይሆን?

በአደባባይ ቤተክርስቲያን በአላውያንና በመናፍቃን ሹማምንት ስትሰደብ፣ገዳማቶቿ ሲደፈሩና ሲቃጠሉ፣ ካህናትና ምእመናን ሲታረዱ፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነች ሃገርን ያቆየች ቤተክርስቲያን እንደወፍ ዘራሽ የትም ከበቀሉ ድርጅቶች ጋር ትቆጠሪያለሽ እንደ አዲስ ተመዝግበሽ ፈቃድ አውጥተሽ ብቻ ነው
መንቀሳቀስ የምትችይው ስትባል፣ ቤተክርስቲያን የነፍጠኛ ዋሻ ናት እያሉ በገሃድ አላውያኑ ሲሳደቡ፣ መለኪያው ኦርቶዶክስ የነበረውን ሰብረነዋል እየተባለ ሲፎከር የዛሬዎቹ አባቶች ጳጳሳት ምን እየሰሩ ነበር? ይሆን? እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ማለት ለምእመናን ብቻ የተጻፈ የወንጌል ቃል ነው እንዴ?

ሰሞኑን በዚህ በሜኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በጥቂት አማጽያን ግለሰቦች የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማደፍረስ ተጠንሶ እየተካሔደ ባለው ስርዓት አልበኝነት አንዳንድ ከኢትዮጵያ የመጡና እዚሁ የከረሙ ‘ጳጳሳት’ ቢመከሩና ቢዘከሩ እምቢ ብለው በእሳት ላይ ቤንዚን ለማርከፍከፍ መጥተዋል። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ ለ3 አመታት ያህል ሲለፋበትና ከፍተኛ ውጣ ውረድ ሲደረግበትቆይቶ ወደ ፍጻሜ ደርሶ የነበረውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲይያን የሰላምና የእርቅ ሂደት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ ካለው ኃይል ጋር በመሆን ካፈረሱ በኋላ አሁን ደግሞ የቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ፈላጊ መስለው ምእመናንን ለመከፋፈልና የቤተክርስቲያንን ችግር ከድጡ ወደማጡ ለማውረድ የሾማቸውን ኃይል ተልዕኮ ለመፈጸም እየዳከሩ እገኛሉ።

በቤተክርስቲያን አባቶች ዙሪያ ያለው ልዩነት በግልጽ በፖለቲካ ጣልቃገብነት የተፈጠረ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የችግሩን መንስዔ በመሸፋፈን ምእመናን እውቀት አንሷቸው የቤተክርስቲያን ስርአት የተበላሸ ይመስል የራሳቸውን ጥፋትና ችግር የችግሩ መንስ ኤ የሆነውን ኃይል
በሚቃወሙ ምእመናን ላይ በመላከክ ለማጭበርበር ሲሞክሩ ይታያሉ። ወያኔ ያበላሸውን ቀኖና ቤተክርስቲያን ወደጎን በመተው፤ ለሥልጣንና ለጥቅም አድረው ዋናውን ችግር ለመፍታት ከመንበርከክ ይልቅ እናንተም እንደእኛ ለሆዳችሁ እደሩ፣ ባንዳ ሁኑ እያሉ የማይገባ ነገር ሲናግሩና ሲሰሩ ማየት እጅጉን ያሳዝናል።

በመሰረቱ አባቶች እንደ አባቶች ሊከበሩና ሊታዩ የሚችሉት እንደ አባት ሆነው የሃገርና የቤተክርስቲያን ጠላት ከሆነው ኃይል ራሳቸውን ሲያገሉ አልያም ያልፍርሃት ክፉ ስራውን ሲቃወሙ ነው። ቄሱም ዝም መጽሐፉ ዝም ከሆነ ግን ቄሱም ቄስ አይደለም መጽሐፉም መጽሐፍ አየደለም!!!

በፖለቲካኖች ታቅዶ ቤተክርስቲያናችንን ለመንጠቅ እየተካሔደ ያለውን ታላቅ ሴራ ለማክሸፍ እየተደረገ ባለው ትንቅንቅ ላይሁላችሁም በመገኘት ምንደኞችን እንድናሳፍር ጥሪያችንን እናቀርባለን።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>