አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY
(UDJ)
ህግን እያከበርን የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን!!
——————————
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ በመጣው የማህበራዊ ግልጋሎት አቅርቦት እጥረትናአለመመጣጠን ምክንያት መንግሥት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድ ቢጠየቅም የወሰደው እርምጃ ባለመኖሩ ፓርቲያችን መጋቢት 28 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ‹‹የእሪታቀን›› በሚል መሪ ቃል ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ለህዝብ በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡
ሆኖም «የአዲስ አበባ ከተማ ሠላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍልበመጋቢት 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓም በቁጥር አ.አ ከስ/1ዐ/3ዐ.4/236 በላከልን ደብዳቤ ሠላማዊ ሠልፉን ለማድረግ በጠየቅንበት ቀን ተመሳሳይ የህዳሴ ግድብ ፕሮግራሞች ስላሉ ተለዋጭ ቀንእንድናቀርብ ጠይቆናል፡፡ በዚሁ መሠረት ለመጋቢት 28 ቀን 2ዐዐ6 ዓም ለማድረግ የያዝነውን ፕሮግራም ለማሸጋገር የህግ ግዴታ ስላለብን ለሚያዚያ 5 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ያዛወርን መሆኑንለኢትዮጵያ ሕዝብ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት
መጋቢት 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ