Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሚሊዮኖች ድምጽ –የነጻነት ደዉል በአዲስ አበባ፣ በአዋሳ እና በደሴ ተደዉሏል!

$
0
0
MILLIONS OF VOICE FOR FREEDOM !

አንድነት ፓርቲ

የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፌዴራልም ሆነ የክልል ባለስልጣናት የተለያዩ ሕጎችና ደንቦች ሊያወጡ ይችላሉ። ነገር ግን ሕገ መንግስቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ መሰረታዊ የሕግ አንቀጾችን ማንኛዉም አካል ሊሽረው ወይንም ሊቀለብሰው አይችልም።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 ዜጎች ነፍጥ ሳይዙ የመሰባሰብ፣ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች የማድረግ፣ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሙሉ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።

“Everyone shall have the freedom, in association with others, to peaceably assemble without arms, engage in public demonstration and the right to petition. Appropriate procedure may be enacted to ensure that public meetings and demonstrations do not disrupt public activities, or that such meetings and demonstrations do not violate public morals, peace and democratic rights.”

ይላል አንቀጹ።

በአዲስ አበባ፣ በደሴና በአዋሳ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ። በሰልፉ የጥበቃ ኃይላት ያሰማሩ ዘንድ ለባለስልጣናት አስፈላጊዉ የማሳወቅ ደብዳቤ ተልኳል። በታሰበው ቀንና ቦታ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ካሉና በቂ የጥበቃ ኃይል ማሰማራት ባለስልጣናት ካልቻሉ፣ ቀኑ እንዲራዘም ወይንም የሰልፉ ቦታ እንዲቀየር ሊጠይቁ ይችላሉ። ከዚያ ዉጭ ሰልፎችን የመፈቀድም ሆነ የመከልከል መብት ባለስልጣናት የላቸውም። ይሄ መታወቅ አለበት። ከከለከሉ ወይንም መፍቀድ አለብን ካሉ፣ በቀጥታ የአገሪቷን ሕግ ያፈርሳሉ ማለት ነው። ሕገ ወጥ የሚሆኑት እነርሱ ናቸው ማለት ነው።

ሰልፍ ማድረግ አመጽ አይደለም። የአንድነት ፓርቲ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ላለፉት በርካታ ወራት የተለያዩ ሰልፎች አድርገዋል። በሰዉም ሆነ በንብረት ላይ አንድም ጉዳት አልደረሰም። ከፖሊሶች ጋር ምንም አይነት ግብግብ አልተፈጠረም። አንዲት ጠጠር አልተወረወረችም። ኢሕአዴጎች ይሄን ልብ እንዲሉ ያስፈልጋል። እነርሱ ሌላው ሕግ ማክበር አለበት እንደሚሉት፣ ሕግን ማክበሩ ያዋጣቸዋል።

እንግዲህ ሁላችንም እንዘጋጅ፤ ዉስጥ ውስጡን ማጉረምረም ይበቃናል። እርስ በርስ ማንሾካሾክ ይበቃናል። ከሚሊዮኖች ጋር ሆነን ድምጻችንን በድፍረት፣ በአደባባይ እናሰማ። ፈርተን እና ተስፋ ቆርጠን ከተደበቅን፣ ከሸሸን፣ ዝምታን ከመረጥን፣ በሙስናና በመልካም አስተዳደር እጦት የተዘፈቁት ገዢዎቻችን የደገፍናቸው ነው የሚመስላቸው። እንነሳ፣ እንቀሳቀስ። ሕገ መንግስቱ ይፈቅድልናል። ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታም አለብን።

እኛ ጥይት አንተኩስም ! ጠጠር እንወረወርም! ጥላቻን አንዘምርም። ክርስቲያን፣ ሙስሊም፣ ኦሮሞ፣ ትግሬም፣ አማራ፣ በብሄረሰቡ መታወቅ የማይፈልገው ቅልቅሉ..…ሁላችንም፣  በዘር፣ በኃይማኖት ሳንከፋፈል፣ ሚሊዮኖች ሆነን ድምጻችንን እናሰማለን። በርግጠኝነት የሚሊዮኖችን ጥያቄ ሊንቅ የሚችል ማንም ኃይል የለምም፣ ሊኖርም አይችልም።

እንግዲህ የነጻነት ደዉል በአዲስ አበባ፣ በአዋሳ እና በደሴ ተደዉሏል። ጥሪ ቀርቧል። ትኩረቱ ወደነዚህ ከተሞች ይሆናል!!!!!

በላስ ቬጋስ፣ በአትላንታ እና ዴንቨር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እነዚህ ሶስት ከተሞችን ስፖንሰር በማድረግ ድጋፋቸውን በመግለጻቸዉ ሊመሰገኑ ይገባል። ሌሎቻችንም ተደራጅተን፣ ሶሊዳሪቲ በማሳየት የሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !

 

እንበርታ ፣ እንጎብዝ ! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !

millionsforethiopia@gmail.com


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>