Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: የማን.ዩናይትዱ ዳረን ፍሌቸርና በአንጀት ህመም በተያዘበት ወቅት ያሳለፈው ስቃይ

$
0
0

በማንችስተር ዩናይትድ ካሪንግተን የልምምድ ማዕከል በአንዱ አነስተኛ የስብሰባ አዳራሽ አንድ ዝግጅት ተስተናግዶ ነበር፡፡ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬስ ቡድናቸውን በሚገነቡበት ማዕከል ስብሰባው ይደረግ እንጂ ከዩናይትድ አስቸጋሪ የውድድር ዘመን ጋር የሚያገናኘው ነገር አልነበረም፡፡ አስቸጋሪ በሽታን ለመዋጋት የተዘጋጀ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ራት ግብዣ እንጂ፡፡
Darren-Fletcher_2644581
ዳረን ፍሌቸር የግብዣው አንዱ ባለጉዳይ ነው፡፡ ‹‹Collitis›› በተሰኘው የአንጀት ህመም ሲሰቃይ ቆይቶ በቅርቡ በሙሉ ጤንነት ወደ ጨዋታ የተመለሰው የማንችስተር ዩናይትድ አማካይ ብቸኛው የህመሙ ሰለባ አይደለም፡፡ የቀድሞው የእንግሊዝ ራግቢ ብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋች ሉዊስ ሙዲም እንዲሁ በከባዱ ህመም አልፏል፡፡ ባለፈው ምሽት የተዘጋጀው ግብዣም በሁለቱ ሰዎች አስተባባሪነት የህመሙን ሰለባዎች ለመረዳት ምግባረ ሰናይ አላማ ያነገበ ነው፡፡

በግብዣው ላይ ፍሌቸር ከዚህ ቀደም ስቃዩን ከገለፀበት የበለጠ የችግሩን አስከፊነት ዘርዝሯል፡፡ ለረጅም ጊዜ አብሮት የቆየው ህመም የእግርኳስ ተጨዋችነት ህይወቱን ከፍፃሜ ሊያደርሰው ተቃርቦ እንደነበር ከዚህ በፊትም መግለፁ ይታወሳል፡፡ አሁንም ህመሙን እያስታወሰ ሲናገር ሳግ ይተናነቀዋል፡፡ ድምፁ ቁርጥ ቁርጥ ይላል፡፡ ህመሙን ውጦ በቡድን ጓደኞቹ ፊት ጤናማ መስሎ ለመታየት ሞክሯል፡፡ ደዌው እንደጀማመረው በነበሩት የመጀመሪያ ወራት ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን በስተቀር ለተቀሩት የቡድኑ አባላት በምስጢር ይዞት ነበር፡፡

‹‹ከልምምድ የምቀርበትን ምክንያት ለማወቅ ሲጠይቁኝ እዋሻለሁ፡፡ የፈጠራ ሰበቦችን ማዘጋጀት ነበረብኝ፡፡ በልምምድ ላይ ስገኝ መታመሜ ይታወቃል፡፡ ህመሜን ለመናገር ግን አልፈልግኩም፡፡ ወደ መፀዳጃ ቤት የምመላለስበትንም ምክንያት እንዲሁ የራሴ ምስጢር ነበር፡፡

‹‹ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋች ነኝ፡፡ በፕሪሚየር ሊግ እና በማንችስተር ዩናይትድ እጫወታለሁ፡፡ በቃ! እዚህ ደረጃ በመገኘቴ ከዓለም አናት ላይ የወጣሁ ይመስለኝ ነበር›› በማለት በህመሙ ብዙ መማሩን ፍሌቸር ያምናል፡፡ በፍሌቸርና በሙዲ እንደተተረከው ህመሙ ጨካኝና እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ አንጀት እንዲጉረበረብ ያደርጋል፡፡ ድውያን አሁንም አሁንም ወደ መፀዳጃ ቤት ለመመላለስ ይገደዳሉ፡፡ ‹‹በቀን ከ10 እስከ 30 ጊዜ ድረስ መፀዳጃ ቤት መግባት ግድ ያልል፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ብዙ ደም ከሰውነትህ ይወገዳል›› ይላል የ30 ዓመቱ ስኮትላንዳዊ፡፡

ፍሌቸርና ሙዲ ‹‹United fore Colitis›› የተሰኘውን የራት ፕሮግራም ያዘጋጁት በዩናይትድ ኪንግደም ለሚገኘው የኮሊቲስ ማህበር የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው፡፡ በመጪው ወር በኦልድ ትራፎርድም ተመሳሳይ የእርዳታ ዝግጅት ይኖራል፡፡

ፍሌቸር ከህመሙ እስኪፈወስ ድረስ በቅርብ ርቀት መፀዳጃ ቤት ወደሌለበት ቦታ አይጓዝም ነበር፡፡ ልጆቹን እንኳን ወደ መናፈሻ ወይም ስታዲም መውሰድ በማይችልበት ደረጃ ተፈትኗል፡፡ የራግቢው ተጨዋች ሙዲም በሽታውን ለሁለት ዓመታት ያህል ከቡድን ጓደኞቹ ደብቋል፡፡ ከራግቢው ክለብ የልምምድ ማዕከል 40 ደቂቃ ጉዞ ርቀት ላይ ይኖር ነበር፡፡ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ማዕከሉ ለመሄድ ሲያስብ ግን ስለ ጉዞው በጥልቀት ማሰብ ግድ ነበር፡፡ ‹‹ለዚያን ያህል ጊዜ በመኪና ውስጥ መቆየት በኮሊቲስ አልሰር ለተጠቃ ህመምተኛ ሰው የሚቻል አይደለም፡፡ በ40 ደቂቃው ጉዞ መካከል ለ10 ወይም 11 ጊዜ መኪናውን እያቆመ መፀዳጃ ቤት መፈለግ ግድ ይለዋልና›› ይላል፡፡

ያን ጊዜ ሙዲ ሌይስተር ታይገርስ ለተባለው የራግቢ ክለብ ይጫወት ነበር፡፡ እዚያ ለመድረስ የአምስት ደቂቃ ጉዞ ብቻ ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም በጉዞው ላይ ከሶስት እስከ አራት ጊዜ የመቆም ግዴታ ነበረበት፡፡ በችግሩ ምክንያት ለልምምድ ማዕከሉ በጣም የሚቀርብ መኖሪያ ቤት አግኝቶ መኖር ጀመረ፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ መፀዳጃ ቤቱ አምስትና ስድስት ሜትር ቅርብ ሆኖ ሳለ ሩቅ ይሆናል›› ሙዲ ያክላል፡፡

ፍሌቸር ግን ምስጢሩን ደብቆ መዝለቅ ተሳነው፡፡ ቁርጡ ቀን ሲመጣ ለቡድን ጓደኞቹ ችግሩን ነገራቸው፡፡ ‹‹ለካ ልትሞት ደርሰሃል›› ሲሉ በግምት አደመጡት፡፡ ህክምናውን እንዲከታተል መከሩት፡፡ (ምክራቸው) አበረታች ነበር›› ይላል ወቅቱን ሲያስታውስ፡፡ የፍሌቸር ህመም በይፋ ከታወቀ በኋላ መልዕክቱን ከፃፉት መካከል በተመሳሳይ ህመም በተጠቁ ልጆቻቸው ጤና ግራ የተጋቡ ወላጆች ይበዙበታል፡፡ በእንግሊዝ በበሽታው ብዙሃን ህፃናት ይጠቃሉ፡፡ በየዓመቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት በበሽታው ይያዛሉ፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ስለደረሰው ለተጨዋቹ ያዋዩታል፡፡ በትምህርት ቤት በኮሊቲስ ህመም ተይዣለሁ ከማለት ይልቅ እንደ ፍሌቸር ታምሜያለሁ ማለትን እንደሚችሉ ገልፀውለታል፡፡

የፍሌቸር ጉዞ ምን ያህል የማይመች እንደነበር ድብቅ አይደለም፡፡ በተለይ ህመሙ በድጋሚ በተመለሰበት በ2010 ዙሪው ጨለመበት፡፡ ለፈውስ ለመብቃት ሶስት አይነት ቀዶ ጥገና አስፈለገ፡፡ ‹‹በተደጋጋሚ ባደረግኩት የደም ምርመራ ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የመድረሱን ውጤት አወቅኩኝ፡፡ እናም ለሁለት ጊዜ ያህል ጉልኮስ ተሰክቶልኝ በሆስፒታል ለመተኛት ተገደድኩ፡፡ ምክንያቱም በጣም አድክሞኝ ነበርና ነው፡፡

‹‹በጣም ፈርቼ ነበር›› ፍሌቸር ይቀጥላል፡፡ የህመሙን ሁኔታ አስመልክቶ ከዶክተሮች ቁርጡን ለመስማት እንኳን አራት ሳምንታት ፈጁበት፡፡ በኋላም በ2012 ለስድስት ወራት ከእግር ኳስ መራቅ አስፈለገው፡፡ ሰዎች እየመጡ ሀሳባቸውን ይሰጡታል፡፡ ‹‹የእግርኳስ አካላዊ ባህሪይ ለህመም ዳርጎሃል›› አሉት፡፡ ከዩናይትድ ርቆ ጤንነቱ ላይ አተኮረ፡፡ ልምምዱን ትቶ ጤናው አልተመለሰለትም፡፡ ህመሙ ቀጠለ፡፡ ልምምዱን ትቶ ጤናው አልተመለሰለትም፡፡ ህመሙ ቀጠለ፡፡ ልምምዱን ሰርቶም፣ ሳይሰራም መታሙ ግን የችግሩ መንስኤ እግርኳስ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ሆነለት፡፡ በዚህም ተደሰተ፡፡ ‹‹እግርኳስን ስለምወደውና ከቶም መጫወትን ማቆም ስለማልፈልግ ህመሙ መቀጠሉ አስፈላጊ ነበር፡፡ እግርኳስ ለህመሜ ምክንያት አይደለም፡፡ ለስቃይ የተዳረግኩት በህመሙ እንጂ በእግርኳስ አልነበረም፡፡
ሁለቱም ስፖርተኞች በህመሙ ምክንያት ጫማቸውን ሊሰቅሉ አልተገደዱም፡፡ ‹‹ከአካላዊ ህመሙ ይልቅ ስነ ልቦናዊ ጉዳቱ ያይላል›› ይላል ፍሌቸር፡፡

አሁን ጨለማው አልፏል፡፡ ፍሌቸርም ሙሉ ለሙሉ ተፈውሷል፡፡ በቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዙር ስኳድ ዝርዝር ውስጥም ተመዝግቧል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ ከአስቶንቪላ ጋር ባደረገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ሲመለስ ከተጫዋቾች አስደናቂ አቀባበል ተደረገለትት፡ ከጨዋታው በኋላም በመልበሻ ቤት የቡድን ጓደኞቹ በዝማሬና በጭብጨባ በጤና መመለሱን አበሰሩለት፡፡ ከስቶክ ሲቲ ጋር ሲወቱም ደጋፊዎች ‹‹ፍሌቸር ጎል ካስቆጠረ ወደ ሜዳ እንገባለን›› እያሉ አዜሙለትት፡

ሶስቱ ቀዶ ህክምናዎች ህመሙ እንዳያገረሽ ዋስትና እንደሚሆኑ ተጫዋቹ ይናገራል፡፡ በዚያች ሀገር ለሚኖሩት ፍሌቸር ተስፋ ነው፡፡ በራት ግብዣው ላይ ከተገኙት እንግዶች አንዱ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ናቸው፡፡ በዝምታ አልተደመሙም፡፡ የበኩላቸውን ሀሳብ እንዲህ ሲሉ ሰንዝረዋል፡፡ ‹‹የቡድን ጓደኞቹ ለማያውቁት ችግር ድጋፍ ሲያደርጉ መመልከት ለእኔ ትርጉሙ ብዙ ነው››


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>