ኢትዮጵያ ሃገሬ ከጂዳ
ኢትዮጵያውያኑ የእረፍት ግዜያቸውን ዱባይ እና ባህሬን ለማስላፍ ተገደዋል!ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ለዕረፍት አሊያም ለተለያዩ አስቸኳይ የስራ ጉዳዮች በሚጓዙ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ መጡበት እንዳይመለሱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግመ ንግስት የጉዞ እገዳ መጣሉን ምንጮች አስታወቁ። የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት እየወስደ ያለው እርምጃ አያሌ ወገኖቻች በሰው ሃገር ያፈሩትን ቀዋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ያሳጣ ዜጎች ህጋዊ ሆነው ለመኖር የሚያስችሉ መብቶቻውን የነፈገ ከመሆኑም በላይ አብዛኛውን ተጓዥ ለምዝበራ እና ለተጨማሪ ወጪ የዳረገ አሰራር መሆኑንን የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች በባዕዳን ሃገር ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚኖረውን ወገናችንን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እርምጃ መሆኑ አክለው ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ኤርፖርት ላይ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ደህንነት ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው የጉዞ እገዳ ህጋዊ የሆነ መስረት የሌለው መሆኑን የሚናገሩ የእገዳው ሰላባዎች አንዳንድ ተጓዦች የቪዛ ግዜያቸው መቃጠሉን ተከትሎ ህገወጥ፡ በሆነ መንገድ ባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት መገደዳቸውን ተናግረዋል። መንግስት አዲስ አበባ ኤርፖርት ላይ እyeተፈጸመብን ያለው ወከባ ሳውዲያኑ ከሚፈጽሙብን ግፍ እና በደል የከፋ መሆኑንን የገለጹ አንድ ተበዳይ ለይለፍ 5 ሺህ ብር እጅ መንሻ መክፈላቸውን ጠቅሰው ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ህጋዊ በሆነ መንገድ መግባት የሚያስችለን ህጋዊ ቪዛ እያለን ከሃገር ሃገር የመጓጓዝ ህገ መንግስታዊ መብታችን በህገወጦች ተጭፍልቋል ብለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ለዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት እቅድ ይዘው የነበሩ ወገኖቻች በጉዞ እግደዳው ምክንያት የእረፍት ግዚያቸውን ጓረቤት ሃገራት ለማሳለፍ መገደዳቸውን በማውሳት ኤርትራውያንን ጨምሮ የሌላ ሃገር ዜግነት ያላቸው ተጓዦች ያለምንም ስጋት በነጻነት ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ኤርፖርት ላይ በደህንነት ሃይላቱ የሳውዲ የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) እንደማይጠየቁ ጠቅሰው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግንስት እገዳውን የጣለው በኢትዮጵያን ላይ ብቻ መሆኑንን አረጋግጠዋል ።
መንግስት የሳውዲን መኖሪያ ፈቃዱ (ኢቃማ) ያልያዘ ኢትዮጵያዊያን ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉ በጣም አሳፋሪ እና እርምጃው ጥናት ያልተደረገበት መሆኑንን የሚናገሩ ምንጮች የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.መንግስት በሳውዲ አረቢያ ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አኗኗር በቂ ግንዛቤ እና መረጃ የሌለው መሆኑንን ያሳያል ብለዋል ። በሳውዲ አረቢያ ህግ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋ የስራ ግዜውን ጨርሷ አሊያም ለእረፈት ወደ ሃገሩ ሲመለስ የመኖሪያ ፈቃዱን (ኢቃማውን) ለአሰሪው (ለከፊሉ) የማስረከብ ግዴታ እንዳለበት የሳውዲ አረቢያ ህግ ይደነግጋል ።