Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኢትዮጵያውያን ረዳት ፓይለቱን በመደገፍ በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ የፊታችን ሰኞ ሰልፍ ሊወጡ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰኞ ዕለት ሮም ላይ ማረፍ የነበረበትን አውሮፕላን ስዊዘርላንድ ላይ እንዲያርፍ ያደረገው ኢትዮጵያዊው ረዳት ፓይለት “የታፈነውን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለዓለም ያሳየ ጀግና ነው” የሚሉ ኢትዮጵያውያን የፊታችን ሰኞ ጠዋት ፌብሩዋሪ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ። የስዊዘርላንድ መንግስት ነገ ወይም ከነገ በስቲያ በረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ የተጣራው ይኸው ሰልፍ ረዳት አብራሪው አውሮፕላን ጠላፊ አሸባሪ እንዳልሆነና ድርጊቱን የፈጸመው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ በስርዓቱ ውስጥ የሰፈነውን የአንድ ብሔር የበላይነትን ለዓለም ለማሳየት የተጠቀመበት ዘዴ በመሆኑ የስዊዘርላንድ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄውን እንዲቀበለው እንደሚጠይቅ ከሰልፉ አስተባበሪዎች ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

“ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ይህ ወንድማችን ለኛ ነፃነት የታፈነውን ያገራችንን ህዝብ በአለም አደባባይ ያንድ ዘር ብቻ የነገሰው የዘረኛው ወያኔን ስራ ለአለም ያጋለጠ ጀግና ወንድማችን አሸባሪ ሳይሆን የነፃነት ታጋይ ወንድማችን መሆኖን ለመግለጽ ይህን ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል” ያለው የዋሽንግተን ዲሲው ሰልፍ አስተባባሪዎች ጥሪ ፍላየር ለዘ-ሐበሻ ደርሷታል። ሰልፉ የሚደረገው Embassy of Switzerland in the United States of America ሲሆን አድራሻውም ፦ 2900 Cathedral Ave., NW, Washington, D.C. ነው።

ረዳት ፓይለቱን በመደገፍ ተመሳሳይ ሰልፍ በስዊዘርላንድና በሌሎች ሃገራት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የስዊዘርላንድ መንግስት በረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ነገ ወይም ከነገ በስቲያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎም በርካቶች ጋዜጣዊ መግለጫውን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው።
dc


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>