Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሕንድ ወደ ሃገሯ የሚገቡ ኢትዮጵያውያንን እና ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎቿን የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ አዘዘች

$
0
0

polio
(ዘ-ሐበሻ) ሕንድ ወደ ሃገሯ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ የሚያስገድድ ሕግ ማውጣቷ ተሰማ። ፖሊዮ ወይም የልጅነት ልምሻ በቫይረስ ምክንያት የሚነሳ በሽታ ሲሆን፣ አካልን ከማጉደል ባሻገር ህይወት እስከ ማሳጣት ያደርሳል። በሽታውም ቀጥታ የሚያድን መድኃኒትም የለውም።

ዘሒንዱ የተባለው የህንድ ጋዜጣ ዛሬ እንዳስነበበው ከመጪው ማርች 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ማንኛውም የፖሊዮ ተጠቂ የሆኑ ሃገራት ዜጎች ህንድ ከመግባታቸው በፊት የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ አዲስ የወጣው ህግ ያስገድዳል።

የሕንድ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከህንድ ወደ ፖሊዮ ተጠቂ የሆኑ ሃገራት ለሚጓዙ ዜጎቹም ለአንድ ዓመት የሚቆይ OPV የተባለ ክትባት (oral polio vaccine) ያዘጋጀ ሲሆን የአፍጋኒስታንን፣ የናይጄሪያን፣ የፓኪስታንን፣ የኢትዮጵያን፣ የኬንያን፣ የሶማሊያን እና የሶሪያን ሃገራት ከፖሊዮ ተጠቂ ሃገራት በመመደብ ወደነዚህ ሃገራት የሚጓዙ ዜጎችም ሆነ ወደ ህንድ የሚገቡ የነዚህ ሃገራት ዜጎች የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ ከማርች 1 ቀን ጀምሮ ያስገድዳል።

እንደ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ገለጻ የOPV ክትባት የወሰዱ ዜጎች ሰርተፊኬት የሚሰጣቸው ሲሆን ሰርተፍኬቱ ለአንድ ዓመት ያገለግላል። የOPV ክትባትን በየትኛውም ዕድሜ ክልል ያለ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከላይ ከተጠቀሱት 7 ሃገራት የሚመጡ ዜጎችም ሆኑ ወደዚያ ሃገር የሚጓዙ የህንድ ዜጎች መውሰድ አለባቸው ሲል የሂንዱ ዘገባ ጨምሮ ገልጿል።

ኢትዮጵያ በ2008 ዓ.ም ፖሊዮን ከኢትዮጵያ አጥፍቻለሁ ስትል ብታውጅም ባለፈው ኦገስት ላይ ግን በምስራቁ የሃገሪቱ ክፍል የፖሊዮ ተጠቂ መገኘቱ አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ባለሙያዎች እንደሚሉት በሶማሊያና በኬንያ እስካሁን ድረስ የፖሊዮ ቫይረስ ያልጠፋ በመሆኑ ወደ ምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል መግባቱ ብዙም ላያስገርም ይችላል ይላሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>