ሞት ማለት ተንጋሎ መተኛት ፣አለመንቀሳቀስ ፣ ፍፁም የእንቅልፍ ዓለም ፍፁም የሕይወት ቀውስ ፣ አለመደሰት ነው ፤ ተከፍቶ አለማልቀስ ፣ የሬሳ እኩልነት ፣ እርኩስ የለ ቅዱስ ፣ በኅብረት መበስበስ ፣ በየቀኑ መፍረስ ፣ ሞት አለመስማት ነው ፤ ጆሮ ዳባ ልበስ ፣ ክርስቶስ ሲሰቀል ፣ሲፈታ በርናባስ ። ሞት ማለት :- አለመናገር ነው ጭው ያለ ዝምታ፣ የመቃብር ሰላም የሬሳ ጸጥታ ፣ ደሀ በሰሌኑ ሳጥን ገብቶ ጌታ ፣ የውሸት ልዩነት ተጋድሞ በተርታ ፣ አይመሽ ወይ አይነጋ ፣ጠዋት የለው ማታ ። ሐዘን የለ ለቅሶ ፣ደስታ ፣ ፈገግታ ፣ ዘፈኑና ለቅሶው የምስጥ ሹክሹክታ ። ሞት ማለት:- አይረገዝበት ፣ አይወለድበት ፣ የመቃብር ዓለም ፣ጭንጋፍ ፣የጭንጋፍ ቤት የሰው
The post እንጉርጉሮ -ከ ፕ/ሮ መስፍን ወልደማርያም ገጽ 31-32 መስከረም 1967 ዓ. ም፡ ሞት ማለት appeared first on ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.