Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አብርሀም ሊንከን እና ዶ/ር አብይ አህመድ –ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

$
0
0

አብርሀም ሊነከነ 16ኛው የአሜሪካ ፕረዛዳንት ሲሆን ሊንከን ፕረዛዳንት በነበረበት ጊዜ አሜሪካ በእርስ በርስ ጦርነት ላይ ነበረች፤ እንዲሁም ሀገሪቱ ከፍተኛ በሆነ በግብረ-ገብነት እና በፖለቲካ ቀውስ ትናጥ ነበር፡፡ በእንዲህ አይነት ቀውስ ውስጥ ሊንከን የአሜሪካን አንድነት በመጠበቅ፣ ተንሰራፍቶ የነበረውን የባሪያ ንግድን በማስቀረት፣ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማነቃቃት የተሳካለት መሪ ሁኖ ስሙ በመልካም ሲነሳ ይኖራል፡፡ ሊንከን በእርስ በርስ ጦርነት ደክማ የነበረን ሀገር ወደ ህብረት በማምጣት የተዋጣለት ታላቅ መሪ ሁኖዓል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ዶ/ር አብይ አህመድ መለስ ዜናዊ በጎሳ ፖለቲካ ሊበታትናት የተቃረበችን ሀገር እንደ አብርሀም ሊንከን አንድ ያደርጓታል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ በለውጡ የመጀመሪያዎቹ ወራት ‘ቲም ለማ’ እየተባለ የሚጠራው የለውጥ ቡድንም ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ የአብዛኛው ህዝብ ድጋፍ

The post አብርሀም ሊንከን እና ዶ/ር አብይ አህመድ – ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ appeared first on EthioPoint: Latest Ethiopian News and Point of View / ዘ-ሐበሻ 24/7.


የብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ አስቂኝ  ጭውውት በOMN –አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

$
0
0

ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ የሚባለው ዐይነ ደረቅ አክራሪ ብሔርተኛ “አማርኛ በኢትዮጵያ 29 በመቶ ብቻ ተናጋሪ ሲኖረው ኦሮምኛ ግን 71 በመቶ ነው፡፡” እያለን ነው፡፡ የት ሄዶና መቼ ይህን ጥናት እንዳደረገ አልገለጸም፡፡ ስድስት ሚሊዮኑን ትግሬ፣ ስድስት ሚሊዮኑን ሶማሌ፣ ስንት ሚሊዮኑን ደቡቤ፣ ስንት ሚሊዮኑን ሽናሻ፣ አገው፣ አኙዋክ፣ በርታ፣ ጉሙዝ ወዘተ. ከአማርኛው ይሁን ከኦሮምኛው የቋንቋ ቅርጫት በየትኛው ውስጥ እንደከተታቸውም አልጠቆመም – ፍጹማዊ የኅሊና መታወር ማለት ይቺ ናት እንግዴክ፡፡ በዚህ ሰውዬ ጥናት መሠረት – ይህንን ከእንስሳም የወረደ ስብዕና ሰው ብሎ መጥራት እንኳን ይቸግረኛል በውነቱ –  ከኢትዮጵያ ሕዝብ 71 በመቶው ኦሮሞ ሲሆን 29 በመቶው ደግሞ አማራ ነው፡፡ አዲዮስ ሸዋ! አዲዮስ የለማ አገር ቅምብቢት! አዲዮስ ትላልቅ ከተሞች!

The post የብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ አስቂኝ  ጭውውት በOMN – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) appeared first on EthioPoint: Latest Ethiopian News and Point of View / ዘ-ሐበሻ 24/7.

ባዲሱ ዘመን ለሰው ልጅ ህይወት ክብር እንስጥ

$
0
0

የዘገየ ቢሆንም አሁንም ያለነው በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ወር በመሆኑ መልካም ምኞትን መግለጽ ትክክል ነው ብዬ ኣምናለሁ። በመሆኑም፣ አዲሱ ዘመን፡ የፈጣሪን ምህረት የምናገኝበት፣ ሰው ያለሃጢያቱ በርኩሳን የማይገደልበት፣ ሞትና መፈናቀል አንዳልታየ የማይታለፍበት፣ ፍትህ የሚሚገኝበት፣ የተጎዱ የሚካሱበት፣ ፈጣሪ በአምሳሉ የፈጠረውና ምድርን አንዲገዛ የፈቀደለት የሰው ልጅ፣ አንተ አንዲህ ነህ አንተ እንዲያ ነህ ተብሎ ተፈጥሯዊው የመኖር መብቱና አምላካዊ ስጦታው በሌላው እኩይ ሰው የማይነጠቅበት፣ የሚበላው ለሌለው ሰው ፊቱን ቅባት የማንቀባበት፣ የአገራችን ህዝብ በሁሉም የኣገራችን ስፍራ በሰላም ተኝቶ ያለሃሳብ የሚነቃበት፣ አንጋፎች መልካም አርአያነትን የሚያሳዩበትና የሚከበሩበት፣ የአገርና የህዝብ ወዳጆች የሚከብሩበትና አገርንና ህዝብን የሚጠሉ ከጨለማ የሚወጡበት ዘመን ይሁንልን። በኔ ምልከታ ያለፈው ዘመን በአገራችን ብዙ ጉዳቶች፣ ብዙ ስጋቶችና፣ ብዙ ያልተጨበጡ

The post ባዲሱ ዘመን ለሰው ልጅ ህይወት ክብር እንስጥ appeared first on EthioPoint: Latest Ethiopian News and Point of View / ዘ-ሐበሻ 24/7.

መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የአምስት አመት ረቂቅ የልማት እቅዱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

$
0
0

መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን መንግስት አገሪቱ ያላትን የመሬት ሃብት መረጃውን በአግባቡ በማደራጀትና ይዞታዎችን በማልማት እና በማስተደደር ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ጠቀሜታ እንዲያስገኝ ለማስቻል የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ ኮርፓሬሽኑ የእርምጃዎቹ አንድ አካል በመሆን የፈደራል መንግስት መስሪያቤቶች ስልጣንና ኃላፊነት ለማሻሻል በወጣው አዋጅ 1097/2011 ተቋቁሞ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 431/2ዐ11 መሰረት ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ኮርፓሬሽኑ በመላው ሃገሪቱ ያለውን የፌዴራል መሬት ይዞታን ለማልማትና ለማስተዳደር ያመች ዘንድ የመሬት መረጃዎችን ለማሰባሰና የይዞታ ካርታ ስራ ለማከናወን ስራ በፕሮጀክት ደረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡ በትላንት እለት መስከረም 13 2013 ዓ.ም መሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ረቂቅ የአምስት ዓመት የልማት

The post መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የአምስት አመት ረቂቅ የልማት እቅዱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ appeared first on EthioPoint: Latest Ethiopian News and Point of View / ዘ-ሐበሻ 24/7.

ሰልማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ፡ Sept. 25, 2020

የዐማራው ሕዝብ እልቂት ኢትዮጵያን ያጠፋታል (አክሎግ ቢራራ (ዶር))

$
0
0

“ዐማራን እየገደሉ ኢትዮጵያን መግዛት የከሰረ ፖለቲካ ነው” የጎንደር ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ያሰማው መፈክር “በእኔ ዘመን አሳዳጅና ተሰዳጂ አይኖርም” ጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ አሕመድ አሊ ክፍል አንድ ከፍተኛ ትኩረት ከሰጠሁት ከሕዳሴ ግድብ ትንተናና ሙግት ወጣ ብየ ይህን ግምገማና ምክሮቸን ለማቅረብ ምን አስገደደኝ? ሰሞኑን በመተከል አካባቢ፤ በቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ በዐማራውና በአገው ንጹህ ኢትዮጵያዊያን ላይ፤ ህጻናትን፤ ወጣት ሴቶችን፤ እናቶችንና ሽማግሌዎችን ሳይለይ የተካሄደው ዘውግ ተኮር እልቂት እጅግ አናዶኛል፤ አሳስቦኛል፤ አስቆጥቶኛል፤ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያለኝን ጽኑ እምነት ተፈታትኖታል። በእኔ ግምገማና እምነት ይህ እልቂት ሊወገድበት የሚያስችልበት እድል ነበር። ምክንያቱም፤ ማስፈራራቱ፤ ዛቻው፤ እንቅስቃሴው፤ አካባቢው የሽብርተኞች ምሽግ መሆኑ፤ በቀስትና በጦር በተደጋጋሚ የተደረገው የጭካኔ ግድያው፤ አፈናው ወዘተ ዛሬ የተጀመረ አይደለም። በሌላ

The post የዐማራው ሕዝብ እልቂት ኢትዮጵያን ያጠፋታል (አክሎግ ቢራራ (ዶር)) appeared first on EthioPoint: Latest Ethiopian News and Point of View / ዘ-ሐበሻ 24/7.

በመንግሥት መዋቅር በመታገዝ በአማራና በአገው ተወላጆች የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ(Genocide)

$
0
0

ዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት 11303 Amherst Avenue, Suite 2 Silver Spring MD, 20902   መስከረም 14,  2013 ዓ/ም በህወሀትና ኦነግ እንዲሁም የዉጭ ኃይሎች አቀነባባሪነት በኦነግ ሸኔና በጉምዝ ታጣቂዎች በመንግሥት መዋቅር በመታገዝ በአማራና በአገው ተወላጆች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያደረሱትን እጅግ ዘግናኝና ኢሰባዊ የሆነ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ(Genocide) አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ ከጳጉሜ አንድ 2012  እስከ መስከረም ሦስት 2013 ዓ/ም  በመተከል ዞን፣ በቡለን ወረዳ፣ አጃር ቀበሌና በወምበራ ወረዳ መልካን ቀበሌ የኦነግ ሸኔና የጉምዝ ታጣቂዎች በክልሉ የመንግሥት መዋቅር በመታገዝ በአማራና አገው ተወላጆች  ላይ እጅግ ዘግናኝና ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ(Genocide) ፈጽመዋል፡፡ ከጭፍጨፋው የተረፉ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት እነዚህ ሽብርተኞች ሊገድሏቸው ያሰቧቸውን ሰዎች አስቀድመው የስም

The post በመንግሥት መዋቅር በመታገዝ በአማራና በአገው ተወላጆች የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ(Genocide) appeared first on EthioPoint: Latest Ethiopian News and Point of View / ዘ-ሐበሻ 24/7.

ሸገርና ምርጫ፣ ባልደራስና ፊርማ (አሁንገና ዓለማየሁ)

$
0
0

ሸገር ዳር እስከዳር ነዶ ሀገር ሞቋል ደምቋል የፈረንጅ ሣቅ መስሏል ሸገር ማሽላኛ ውስጡ ከስሎ በከበባው ተሸብሮ በወረራው ልቡ ቆስሎ ከተሰነይ ናቅፋ አፋፍ ከወለጋ ሐረር ጠረፍ ተወርውሮ የሮም ቋያ አራት ኪሎ ሲፈነዳ ማየት ሆኗል የርሱ እዳ ተፈራርቆ ሲጸዳዳ። ያሁኑ ግን መጥቶ አያልፍም ያልከሰለ ሳያከስል ያልፋመውን ሳያፋፍም እንዳለፉት መጥቶ አይሄድም ሁላችንን ሳያወድም። (ለምን? ካልሽኝ የኔ እህት ለምን? ካልከኝ የኔ ወንድም) ወራሻችን ባሕር ከቦ መሞቱ ነው ተቁለጭልጮ ቶሎ በሉ አታቁሙት ማቱን አምጡት እነ ሌንጮ* *ትውልዱንና አስተሳሰቡን የባእድ ተልእኮ ተሸካሚነቱን (ደቀ መዛሙርቱንም) ወክሎ የገባ ስም፣ ለቤት መምቻ እንዲመች የተመረጠ (አዎ ቅኔ ነው)። ምርጫ አህያና /ዱላ ይዘህ አንተ ስትሞት/ ተወዝውዘህ ዝሆን ጭኖ ጥሩር ለብሶ ሕግ

The post ሸገርና ምርጫ፣ ባልደራስና ፊርማ (አሁንገና ዓለማየሁ) appeared first on ዘ-ሐበሻ-ZeHabesha: Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.


ድመቶች ብቅ ሲሉ አይጦች ተደበቁ (ዘ-ጌርሣም)

$
0
0

ማሳውን ዙሪያውን ሜዳ ተራራውን ቆፍረው ቆፋፍረው ቀንበጡን ቦጥቡጠው ዘሩንም አጥፍተው ሌሊት ጩኸታቸው ልፊያና ድሪያቸው አላስተኛ እያሉ አድረው እንዳልዋሉ ጊዜው ደረሰና ዘመን ተተካና ምድሯ ተንቀጥቅጣ ትራዋን ስትቀጣ ሁሉም ተጠራርተው ካዘጋጁት ቦታ ገቡ ጉድጓዳቸው ኑሮውን ለመልመድ ምንም ቢቸገሩ በቆፈሩት ግድጓድ በአንድ ላይ ታጎሩ ዳግም ሳይዳሩ በጠራራ ፀሃይ አንደውጡ ቀሩ ለሁሉም ጊዜ አለው ደረሰ ተራቸው ጠቢቡ ሰለሞን እንደተናገረው ጊዜው ባለ ጊዜ ሲቀየር አየነው ድመቶች ብቅ ሲሉ አይጦች ተደበቁ የሰበሰቡትን እንደሰለቀጡ ሆድ የገባ ነገር አይቀርም መውጣቱ መቆየት ተችሎ ከሰነባበቱ ማሳው ለመለመ ተመቸው አትክልቱ አይጦች ጉድጓድ ገብተው ቀሩ እንደታገቱ

The post ድመቶች ብቅ ሲሉ አይጦች ተደበቁ (ዘ-ጌርሣም) appeared first on ዘ-ሐበሻ-ZeHabesha: Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

$
0
0

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ! በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል የድልና የፈተና ምልክት ነው። አባቶቻችን ያለ ፈተና ክብር አይገኝም ይላሉ። መስቀሉም በአንድ በኩል እስከ ሞት የሚደርስ መሥዋዕትነትንና ፈተናን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ማንም ሊያስቀረው የማይችለውን ድል አድራጊነትን ያስታውሰናል። ሀገር ልቃ እንድትወጣ በሁለቱም ውስጥ ታልፋለች። በፈተናና በድል ውስጥ። ፈተናው ብቻ ቢሆን ተስፋ በቆረጥን ነበር። ግን ድል እንዳለ ስለምናምን መከራውን ተቋቁመን እናልፈዋለን። ድል ብቻ ቢሆንም ተዘናግተን በተቀመጥን ነበር። የምትፈለፈል ቢራቢሮ ከዕንቁላሉ ለመውጣት የምታደርገው ትግል፤ ለጥንካሬዋ አስፈላጊ እንደሆነው ሁሉ፤ በፈተና ውስጥ በጽናትና በትግል ማለፋችንም መሠረተ ጽኑ ያደርገናል። አንዳንዶች ስለፈተናው ብቻ ያወራሉ። ስለዚህም ተጨንቀው ሕዝብን ያስጨንቃሉ። ሰው ፈተናን ብቻ ካሰበ የዓለም መጨረሻ የደረሰ ይመስለዋል። ነገሮችን

The post ጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

‹‹የዕዳ ቦንብ!!! የኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ብድር የዕዳ መጠን!!! ››(ክፍል አንድ) –ሚሊዮን ዘአማኑኤል

$
0
0

አህመድ ሸዴ፣ግርማ ብሩ፣ሶፍያን አህመድ፣ተክለወልድ አጥናፉ፣ዮሐንስ አያሌው፣አብርሃም ተከስተ፣ይናገር ደሴ፣ አቤ ሳኖ፣በቃሉ ዘለቀ፣ባጫ ጊና የኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮችን የዕዳ መጠን ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም ዶክተር  ዐብይ አህመድ ለህዝብ ይፋ አድርገው ነበር፡፡ በ2012ዓ/ም ደግሞ ኮቪድ 19 ጣረ-ሞቱን በዓለማችን አህጉራቶች ላይ መረቡን ዘረጋ ዓለም አቀፍ ንግድ ድንበር ዘለል የኤሌክትሮኒክስ ንግድ  ሽያጭ ቢዝነስ ለሸማቾች Business-to-Consumer (B2C) እና የቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ/ የንግድ ለንግድ ልውውጥ (Business-to-Business (B2B) የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ  ተሸመደመዱ፡፡ የመጎጎዣና የጭነት አይሮፕላኖች ንግድ በኮቪድ 19 ቫይረስ ድባቅ ተመታ፣ ዓለም አቀፍ የጭነት መርከቦች ንግድ በቫይረሱ ጥቃት ሠጠሙ፣ ድንበር ዘለል አገር አቆራጭ የባቡር መስመሮች ተቆረጡ፣ የዓለም ስታዲየሞች ጩህት በካንቦሎጆ ዝምታ ተዋጡ፣ ትያትር ቤቶች፣ የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣  ገቢ ነጠፈ፣ የዓለም ሆቴሎችና

The post ‹‹የዕዳ ቦንብ!!! የኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ብድር የዕዳ መጠን!!! ››(ክፍል አንድ) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ከእውነት ጋር በመራመድ  ከጠ/ሚኒሥትራችን ነፍሥ ጋር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከቆምን ነጋችን እጅግ ያማረ ይሆናል። –መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

$
0
0

 አሁን ያለው  የሀገሬ መንግሥት ፣አሻጋሪ መንግሥት ነው። ይህ አሻጋሪ የሆነው “የለውጥ መንግሥት” በህዝባዊ ተቃውሞ ታግዞ  ከ27 ዓመት በፊት የነበረውን  ፣በወያኔ ኢህአዴግ  የሚመራውን  መንግሥት እርካቡን በዘዴ ተቆናጦ መንበሩ ላይ የተቀመጠ። መንበሩ ላይ የተቀመጠው” አሻጋሪው የለውጥ “ ፣መንግሥትም በእቅድ፣በዘዴ ና ጥበብ በተሞላበት ብልሃት ሀገርን እየመራ ነው። ይህ እውነት ነው።  የአሻጋሪው መንግሥት መሪ ሀገርን ከጥፋት ያዳነ መንግሥት ነው።የለውጡ መንግሥት  ሀገሬ በባንዳዎችና ሤረኞች እንዳትገነጣጠል ና ጥንታዊ ታሪኳ ከምድረ ገፅ እንዳይደመሠሥ ጥበብ በተሟላበት ዘዴ  ተጠቅሞ የፀረ-ኢትዮጵያ ሴራዎችን ግንባር ቀደም ሆኖ  አክሽፏል።  ይህንን እውነት መካድ አይቻልም። አሁን ያለው የሀገሬ መንግሥት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር መሆኑን በተግባር ያሥመሠከረ መንግሥት ነው።በመሆኑም ሀገሬ በለውጡ ፣ጥንቃቄ በተሟላበት  ሂደት ና ዛሬ

The post ከእውነት ጋር በመራመድ  ከጠ/ሚኒሥትራችን ነፍሥ ጋር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከቆምን ነጋችን እጅግ ያማረ ይሆናል። – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

መልካም የመስቀል በዓል –እሳት ወይ አበባ ከ ሎሬት ፀጋዬ

$
0
0

A tribute to my late brother, written some two years ago, now a part of my anthology at amazon: የወንድም ፍቅር ============= ዓመታት አልፈው ዘመን ሲተካ፤ ጥሎልን ያልፋል የሃሳብ ዱካ፤ እንድንከተል መንገዱን ሳንስት፤ ሁሌ ስንደክም ሁሌም ስንዋትት፤ ቤት ለመመለስ ከተጓዝንበት፤ ጊዜ ይነጉዳል ፈጥሮ ትዝታ፤ የማይደበዝዝ ህያው ደስታ፡፡ ጓደኛ ወንድሜ የምትኖር በልቤ፤ የማትለየኝ የምትኖር በሃሳቤ፤ ፋናዬ ነበርክ መንገዴ ለዝንተ ዓለም፤ መንፈስህ ይመራኛል፣ አይዞህ ይለኛል ዛሬም፡፡ ያኔ የድሮው የልጅነትህ ፈገግታ፤ አሁንም ደማቅ ነው በሞት የማይገታ፤ በጊዜ የማይፈታ፡፡ ካንድ ማህጸን ወጥተን፣ አንድ ላይ ኖረን፤ አንድ ልብ ይዘን፣ አንድ አካል ሆነን፤ ደስታና ሃዘን ባንድ ተጋርተን፣ አብረን ተምረን፣ አንድ ላይ አድገን፤ ኖረናል ህይወት ስቀን፣ ተጫውተን፣

The post መልካም የመስቀል በዓል – እሳት ወይ አበባ ከ ሎሬት ፀጋዬ appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ይድረስ ለቀድሞ የወያኔ አመራር ቡድን አባሎች

$
0
0

አክሱም ሆቴል መቀሌ፡ ትግራይ ክልል ኢትዮጵያ “ባድመ ለኛ ተወሰነ: የጠየቅነውን ብቻ ሳይሆን ያልጠየቅነውን ጭምር ተፈረደልን”  (ስዩም መስፍን፡ ሚያዝያ 15 2002)  የዚህ መግለጫ ምንጩ ምንድነው? በዚሁ ጉዳይ የአፍሪካዊው ዲፕሎማት ሚናስ ምን ነበር? ግልጽ ደብዳቤ ጉዳዩ፡- በኤርትራና በንፁህ ኤርትራዊያን ላይ የፈፀማችሁትን ታሪካዊ ስህተቶችና ግፎችን ስለ ማስታወስ በቅድሚያ የኛ ባህል በሚጠይቀው ጨዋነት መሠረት ሰላምታዬን አስቀድማለሁ። ከስልጣን ከተባረራችሁና አራት ኪሎ ከሚገኘው ቤተ መንግስት ጠቀልላችሁ ወጥታችሁ መቀሌ መመሸጋችሁን ከሰማሁ ሁለት ዓመት አልፎታል፡፡ሆኖም እስከዛሬ በተእግስት ምንም ሳልል ቆይቼ አሁን ትዝ ያላችሁኝ ባለፉት ሶስት ወራት በትግራይ ቲቪና ድምፂ ወያኔ በተደጋጋሚ ብቅ እያላችሁ ኤርትራን በተመለከተ የምትሰጡትን መግጫ ከተከታተልኩ በኋላ ነው። ስለ ኤርትራ ብዙ አበይት ጉዳዮች አንስታችኋል። የኤርትራ ሕዝብ

The post ይድረስ ለቀድሞ የወያኔ አመራር ቡድን አባሎች appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.

ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፡ ሐሙስ ሌሊት በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ተገደሉ

$
0
0

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንገዝ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ሐሙስ መስከረም 14/2013 ሌሊት ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። ጥቃቱ የተፈጸመበት የበንገዝ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደምለው ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ቢያንስ 14 ሰዎች በጥይት መገደላቸውንና ከሰለባዎቹ መካከልም ወንድማቸው እንዳለበት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ አርብ ምሽት ባወጣው መግለጫ ላይ “በድጋሚ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉ” ገልጾ፤ ሁኔታው በእጅጉ አሳሳቢነቱ እንደጨመረ መሆኑን አመልክቷል። የቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ ደምለው እንዳሉት “ጥቃቱ የተፈጸመው ሌሊት 10 ሰዓት ነው። ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልንም። የጥይት ተኩስ ብቻ ነበር በአካባቢው የሚሰማው፤ ብዙ ሰው ነው ያለቀው” በማለት “የእኔ

The post ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፡ ሐሙስ ሌሊት በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ተገደሉ appeared first on ዘ-ሐበሻ-Latest Ethiopian News and Point of View 24/7.


“ህወሓት ከፌዴራሊስት ሃይሎች ጋር እየሰራሁ ነው”በሚል የትግራይ ህዝብን እያወናበደ ነው ሲል የፌዴራሊስ ሃይሎች ጥምረት አስታወቀ

$
0
0
ጥምረቱ “በሂልተኑ ጉባኤ ያባረርነው ህወሓት የእኛን አርማና ሎጎ ያለአግባብ በመጠቀም እየነገደ ነው” ሲልም ከሷል ህወሓት ከፌዴራሊስት ሃይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በሚል የትግራይ ህዝብን እያወናበደ ነው ሲል የፌዴራሊስ ሃይሎች ጥምረት አስታወቀ። ጥምረቱ ለዝግጅት ክፍላችን ዛሬ (መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም) በላከው መግለጫ ላይ እንደገለጸው፤ ህወሓት ከፌዴራሊስት ሃይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በሚል ወክየዋለሁ የሚለውን የትግራይ ህዝብ እያወናበደ ይገኛል። “የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሂልተኑ ጉባኤ ከጥምረታችን ያባረርነው ህወሓት በስማችን በተለመደው የማምታታትና የማፍያነት ባህሪው የእኛን አርማና ሎጎ በመጠቀም እየነገደ ስለሆነ ይህንን ቡድን ከእኛ ጋር በጋራ በመቆም እንድትታገሉ እንጠይቃለን” ሲልም ጥሪውን አቅርቧል። ጥምረቱ በመግለጫው እንዳተተው፤ ህወሓት ህዝቡን በፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ስም እያወናበደ ይገኛል። ስለሆነም የፌዴራሊስት

አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች

$
0
0
በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች። ለሳምንታት በህመም ላይ የነበረችው አርቲስቷ ዛሬ ማለዳ ነው ማረፏ የተሰማው። የአርቲስቷ ስርዓተ ቀብር ነገ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል። በሶፎኒያስ ዋሲሁን

የመስቀል በዓል በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል። በመጠኑ በፎቶ እንየው

$
0
0
የመስቀል በዓል በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል። በመጠኑ በፎቶ እንየው

በኢትዮጵያ የብልጽግና ፓርቲና የብልፅግና ወንጌል !!! ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

$
0
0
www.Prosperity church logo የብልፅግና ፓርቲና የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል ቢጫ፣ሰማያዊና ቀይ ሰዎች እጃቸውን ወደ ላይ ዘርግተው የሚዘሉ ሰዎች አናት ላይ መስቀል ከነ ፈነጠቀው ጸዳሉ ይስተዋላል፡፡ በአንፃሩ የብልፅግና ፓርቲና ሁለት እጆች ተዘርግተው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ሰዎች በሰማየ ሰማያቱ ላይ የፈነጠቀውን የፀሐይ ብርሃን አይተው ሲጨፍሩ ይስተዋላል፡፡  የሁለቱም ቀለማቶች አንድ ዓይነት መሆናቸው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት መሆናቸውና ሦስት እጃቸውን ወደላይ አድርገው የሚዘሉ  ሰዎች መሆናቸው ዝም ብሎ ገጠመኝ ሊሆን አይችልም እንላለን፡፡ የብልፅግና ቤተክርስቲያን የተጀመረው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን የአዲስ ሃሳብ አፋላቂዎች ንቅናቄ ሲሆን በ1950 እኤአ በሃገረ አሜሪካ በመዳን ቅሪቶች ዘመን የብልፅግና ቤተክርስቲያን ነገረ መለኮት ተጀመረ፡፡ (www.Prosperity church logo)1 ድረ-ገፅ አይተው ትዝብትዎን ያጋሩ፡፡ የብልፅግና

አዲስ አበባ ሆይ! የማነሽ ይሉሻል የማን ልበላቸው፣ –ደረጀ ከፊትበር (የግል ምልከታ)

$
0
0
አዲስ አበባ ፊትበር ላይ፣ እኔ አዲስ አበባ ፊትበር ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ተወልጄ ነው ያደኩት። ሰፈራችን ለታላቁ ቤተመንግስት (ምኒልክ ቤ/መ) ቅርብ በመሆኑ የደርግ ቅልብ ወታደሮችም ሆኑ የወያኔ አጋዚ ጦር የአካባቢውን ጸጥታ ለማስከበር ብቻ ሳይሆን ኮረዶችንም ለማሽኮርመም እኛ ሰፈር አይጠፉም ነበር። አንድ ነገር ኩሽ ባለ ቁጥር የደርግ ቅልቦች፣ በኋላ ደግሞ የወያኔ አጋዚ ጦር እና የውጭ ጉዳይ ፌዴራሎች ክላሻቸውን እያቀባበሉ መጀመሪያ የሚመጡት እኛ ሰፈር ነው። ልጅ እያለን ሰፈራችን በሚገኘው መናፈሻ ውስጥ ስንጫወት በየዛፉ ስር በጥይት የተገደሉ ወጣቶችን እናይ ነበር። በደርግ ወቅት ሶስት የሰፈራችን ወጣቶች 31 ቁጥር አውቶቡስ ማቆሚያ ፌርማታ አጠገብ ያለውን የጣውላ አጥር ተደግፈው እያወሩ ነበር። አንደኛው መርከብ ወ/ጊዮርጊስ የሚባል ሲሆን የዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>