ተናገር ማህደር ተናገር ዝክሩ በዚያች በኛ ሀገር ከቀየ እስክ ደብሩ ተናገሪ ቋራ አንች ትንሽ ሰፈር ማነን አንደወለድሽ ያስከበረ ሀገር ተናገሪ ደግመሽ ማን እንደገደለው የት ላይ እንደሞተ ለምንስ ሽጉጡን ወደ አፉ ከተተ ተናገር መተማ አንት ጨካኝ በረሃ ጀግናችን ያስቀላህ ሳታጠጣ ውኃ አንተ አውሊያም በረሃ ለድርቡሽ ያደላህ የቅዱሱን ንጉሥ አንገት ቆርጠህ በላህ የታሪክን መድበል በእሣት አስለበለብህ ተናገር አድዋ ሣልሳዊ ግፉን በምድር በሰማይ ወገን መደብደቡን ለሦስቱ ቀለማት ለኢትዮጵያ ባንዲራ ጀግና እንደ ጧፍ ሲቀልጥ ለሞቱ ሳይፈራ ጠላት አፍሮ ሲሄድ በምኒልክ ተራ ተናገር አድዋ ስንቱ ጀግና ሞቶ ስንቱ ተረፈልህ ባትናገር አንኳን መመዝገብ አለብህ ስማቸውን ዘርዝር በማዕረግ ለይተህ ተናገር ሳትደብቅ የሆነውን ሁሉ ምስክሮች የሉም አልቀዋል በሙሉ
The post ተናገር መጣጥፍ (ዘ-ጌርሣም) appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.