Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በአምቦ የሃጫሉ አጎትን ጨምሮ አምስት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

$
0
0

ዛሬ [ረቡዕ] በአምቦ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እና የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከሚፈጸምበት ቦታ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች የሟቹን ድምጻዊ አጎትን ጨምሮ 5 ሰዎች መገደላቸውን ከቤተሰብ፣ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ቢቢሲ አረጋግጧል። ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውም ተነግሯል። የሃጫሉ ታናሽ ወንድም የሆነው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ሲናገር “አጎታችን ተገድሏል። በእድሜ ትልቅ ሰው ነው። ያሳደገን ነው። የአባታችን ወንድም ነበር” ብሏል። ከሟቾቹ መካከል የአንዱ የሃጫሉ አጎት መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከሃጫሉ አጎት በተጨማሪ ሶስት የቤተሰብ አባላት በጥይት ተመተው የተለያየ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። “የአጎታችን ሚስት እግሯን ተመታለች፣ የአጎቴን ልጅ የሚያገባም እጁን ተመቷል፣ የእህታችን

The post በአምቦ የሃጫሉ አጎትን ጨምሮ አምስት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.


እስክንድር ነጋ ‘ሁከትና ግጭት ለመቀስቀስ በመሞከር’ተጠርጥሮ መያዙ ተነገረ

$
0
0

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ውስጥ ሁከት ለመቀስቀስ በመሞከር ተጠርጥሮ እንደታሰረ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጸ። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምሽት ላይ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ጸጋ እንዳሉት በአዲስ አበባ ሁከትና ግጭት እንዲፈጠር በመቀስቀስ ተጠርጥሮ በሕግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳሉት አቶ እስክንድር በአዲስ አበባ ውስጥ ቡድን በማደራጀት ወጣቶችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመመደብ ሁከትን የሚያነሳሱ ቅስቀሳዎች ሲደረግ እንደነበር ጠቅሰዋል። በዚህም በሕዝቡ መካከል ግጭትን ለመፍጠር በሚችሉ ድርጊቶች ተጠርጥሮ በሕግ ቁጥጥር ሰር መዋሉን አቶ ፈቃዱ ጸጋ ተናግረዋል። የባልደራስ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ [ረቡዕ] ከሰዓት በኋላ አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ

The post እስክንድር ነጋ ‘ሁከትና ግጭት ለመቀስቀስ በመሞከር’ ተጠርጥሮ መያዙ ተነገረ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

ይታየኛል ( ዘ-ጌርሣም)

$
0
0

ይታየኛል ያ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር ማስተዋል ከቻለ የዕይታው መነፅር ስሜቴ ተውገርገር ድምፅህን አሰማ ህልምህን ተናገር ቅዠትክንም ደርድር ምኞትክን አስረግጥ አድማጭ ድንገት ካለ በአዕምሮው ያመነ የተደላደለ ከአጥናፍ እስከ አጥናፉ ሰላም ሰፍኖ በአገር ፖለቲካው ሰክኖ በውል ሲነጋገር ከጥፋት ዓለሙ ሁሉም ፊቱን ሲያዞር መተሳሰብ ሲነግሥ ልዩነት ሲወንስ ጠላትን ሲከፋው ወዳጅ ደስ ሲለው ይታየኛል ያ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር ማስተዋል ከቻለ የዕይታው መነፅር መለያየት ቀርቶ አንድነት ጎልብቶ በጋራ በመቆም ወገንን ለመጥቀም ሀገርን አልምተን ከልመና ወጥተን ዴሞክራሲ ሰፍኖ ጀብደኝነት በንኖ አንድነት ጠንክሮ ሁሉም ጠግቦ ሲያድር ተርፎትም ሲያካፍል ገበሬው አልፎለት ወጥቶ ከድህነት ተሜ ሲመራመር አዲስ ግኝት ሲፈጥር ይታየኛል ያ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር ማስተዋል ከቻለ የዕይታው መነፅር መጠፋፋት

The post ይታየኛል ( ዘ-ጌርሣም) appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

“የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን  ኢትዮጵያ የሁላችን እንጂ የኣንድ ባለኣርማ ቡድን ኣገር ኣይደለችም: ወደፊትም ኣትሆንም!”- በዩናትድ ኪንግድም ኢትዮጵያውያን

$
0
0

በኢትዮጵያዊው ወገናችን በታዋቂው ድምጻዊ በሃጫሉ ሁንዴሳ መሞት እጅግ ኣዝነናል:: ዬሃጫሉን ገዳዮች በብርቱ እያወገዝን የፍትሕ ኣካላት ሞያን መሰረት ባደረገ እውቀት ኣጣርተው በኣፉጣኝ ለፍርድ እንዲያቀርቧቸው እንጠይቃለን:: ሞትን ኣስመልክቶ ጥልቅ ሃዘንን መግለፅ የወረስነው የኢትዮጵያዊነት ባህል ብቻ ሳይሆን የሰብኣዊነታችንም መግለጫ ነው:: ይህንን በሚፃረር መንገድ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለው የሕይወትና የንብረት ጥፋት ግን መለኪያ የማይገኝለት ኣረመኒያዊነትና ሰብኣዊ ከሚባል ባህርይ ፍፁም የራቀ የጭካኔ ተግባር ነው::ከሃዘን መግለጫ እሴቶቻችን የተለየና ለሟቹ ኣርቲስት ክብርም የማይመጥን በሕይወቱ እያለ ኣይቶት ቢሆን ኑሮ እኔንና ኦሮሞነቴን የሚፃረር ድርጊት ነው የተፈፀመው በሚል ኣጥብቆ ያወግዘው የነበረ ኦሮሞ የሆንነውን ጭምር ኣንገት ያስደፋ ድርጊት ነው:: ሟቹ ኣርቲስት ለሁላችንም በጎና ደህንነት የቆመ የከፍተኛ ስብእና ባለቤት ነበር:: የእርሱን ከዚህ ዓለም

The post “የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን  ኢትዮጵያ የሁላችን እንጂ የኣንድ ባለኣርማ ቡድን ኣገር ኣይደለችም: ወደፊትም ኣትሆንም!”- በዩናትድ ኪንግድም ኢትዮጵያውያን appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

ኢትዮጵያዊ ሁሉ ንቃ! በወያኔና ግብጽ ቅጥር ኦሮሞ ነን ባዮች አትዘወር! –ሰርፀ ደስታ

$
0
0

  የሐጫሉ ሞት ኢትዮጵያዊ ነኝ በሚለው አመለካከቱ እንደጠላት ስለሚያስቡተ ታዋቂነቱና ስለሚነሊክ የተናገረውን ደግሞ ሕዝብነ ከሕዝብ ለማጋጨት እንደ ጥሩ ምክነያት ሊጠቀሙበት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው ነው ጠላቶቻችን የሠሩብን፡፡ ሥለዚህ ሁሉም ያስተውል፡፡ እነጀዋር ከመጀመሪያውም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነበር ዓላማቸው፡፡ የለንደኑን ስብሰባቸውን አትርሱት፡፡ ከቤተሰቡ (ከገዛ አባቱ) ፍቃድ ውጭ ይሄው አስከሬኑ እንኳን በተወለደበት ቦታ እነዳያርፍ ከቤተሰቡ እምነትና ባሕል ውጭ የቀበር ቦታ ወሳኝ ሆነው ወንጀለኞቹ እንደገና የወሳኝነት መብት አለን እያሉን ነው፡፡ ከዚህ በፊት የሳዕረን አስከሬን ከኢስ አበባ ወደመቀሌ ወስደው በዛ የሆነው እናስታውሳለን፡፡ በዚሁ ሳቢያ ዛሬ በአምቦ 7 ሰው ሞቷል፡፡ የሐጫሉ አጎትም የልጃችንን አስከሬን አትወስዱም በማለታቸው ቆስለዋል፡፡ መንግስት የሚባለው አካለ ይሄን እያወቀ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ካለማድረግ የሆነ

The post ኢትዮጵያዊ ሁሉ ንቃ! በወያኔና ግብጽ ቅጥር ኦሮሞ ነን ባዮች አትዘወር! – ሰርፀ ደስታ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

ኢሳት ልዩ ዜና July 2020

በአምቦ መረጋጋት የለም ፤ ወደ አምቦ መንገዶች ዝግ ናቸዉ

$
0
0

ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ የሚወስደዉ መንገድ በመዘጋቱ እና ማንንም ሰዉ ማለፍ ባለመቻሉ ጋዜጠኞች ወደ ቀብሩ ቦታ መድረስ አለመቻላቸዉ ተነገረ። ከአዲስ አበባ ወገን የፀጥታ ጥበቃዉ በጣም የጠበቀ ነዉ ። በአምቦ ግን በርካታ ወጣቶች አሁንም «የሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሪን ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ እና የክብር ሽኝት ተደርጎለት፤ የኦሮሞ እምብርት በሆነችዉ ፌንፌኔ መቀበር አለበት» እያሉ ከፍተኛ ተቃዉሞ እያሰሙ ነዉ ተብሎአል። ትናንት ረቡዕ ማምሻዉን የኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ ፤ በአምቦ የሚታየዉን ተቃዉሞ እና ከፍተኛ ዉጥረት ተከትሎ በመንግስት ብዙኃን መገናኛዎች ቀርበዉ በሰጡት መግለጫ «ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ መቀበር ያለበት ከትግል ጓዶቹ ጋር በአምቦ ነዉ ፤ ይህ ዉሳኔ የተሰጠዉ በቤተሰቦቹ ፍላጎት እንጂ በመንግሥት ጫና

The post በአምቦ መረጋጋት የለም ፤ ወደ አምቦ መንገዶች ዝግ ናቸዉ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

አስቸኳይ አገራዊ ጥሪ ለመላዉ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ!!

$
0
0

ቀን 24/10/2012 ዓም በቅድሚያ በሰኔ  22 ቀን 2012ዓ. ም. ምሽት ላይ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ እንዳለ በአሰቃቂ ሁኔታ በቅጥረኞች እጅ ህይዎቱ ያለፈዉ ወንድማችን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ድርጅታችንን እጅጉን ያሳዘነ እና ድርጊቱን በፅኑ የምናወገዘዉ ሲሆን ወንድማችን ላለፉት በርካታ  አመታት የሀገራችን የሙዚቃ ፈርጦች ዉስጥ አንዱ ነበር::  በዚህም ስራዉ መላዉ የሀገራችን ህዝብ ሲያስበዉ ይኖራል::  መንግስትም እነዚህን ወንጀለኞች እስካሁን እንደተደረገዉ በሆደ ሰፊነት በሚል ወንጀለኞች የፈለጉትን እየሰሩ የሚኖሩበት ዘመን ማብቃትና ሁሉም ሰዉ በህግ ስር መሆኑን ሊያሳይ የሚችል ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ አበክረን እንደ እሰከ ዛሬዉ እንጠይቃለን:: ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ብዙ ሽህ ዘመናት ዓለምን ያስደመሙ ስልጣኔዎችን፣ የታሪክ አሻራዎችን፣ የነፃነት ትግሎችን ለዘመናት ፈፅማለች ወደፊትም ትፈፅማለች::  በአንፃሩም እጅግ አስከፊ

The post አስቸኳይ አገራዊ ጥሪ ለመላዉ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ!! appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.


መከላከያ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ቢሮአቸዉ ናቸዉ

$
0
0

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር የአቶ ለማ መገርሳ በአዲስ አበባ በሚገኘዉ ጽ/ቤታቸዉ ሥራ ላይ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አረጋገጡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር የአቶ ለማ መገርሳ በአዲስ አበባ በሚገኘዉ ጽ/ቤታቸዉ ሥራ ላይ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አረጋገጡ። በአዲስ አበባም እንደ ወትሮዉ የፀጥታ ስምሪት በስተቀር ምንም አይነት ልዩ የጦር ኃይል ስምሪት አለመኖሩን ምንጮች ዳግም ተናግረዋል። አዲስ አበባ ሰላማዊ ግን ብዙም እንቅስቃሴ የማይታይባት ሆና ዉላለች ተብሎአል። DW

The post መከላከያ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ቢሮአቸዉ ናቸዉ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት በተወለደበት አምቦ ከተማ ተፈጸመ

$
0
0

የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት በተወለደበት አምቦ ከተማ ተፈጸመ። በከተማዋ በሚገኘው ስታዲዮም የሽኝት መርሐ ግብር ተካሒዷል። በሁለቱም ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አልተገኙም። በቀብር ሥነ ሥርዓቱም የተገኙ ሰዎች እጅግ ጥቂት ሆነው ታይተዋል። Posted by DW Amharic on Thursday, July 2, 2020 የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት በተወለደበት አምቦ ከተማ ተፈጸመ። በከተማዋ በሚገኘው ስታዲዮም የሽኝት መርሐ ግብር ተካሒዷል። በሁለቱም ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አልተገኙም። በቀብር ሥነ ሥርዓቱም የተገኙ ሰዎች እጅግ ጥቂት ሆነው ታይተዋል።

The post የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት በተወለደበት አምቦ ከተማ ተፈጸመ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

አቶ ጀዋርና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

$
0
0

አቶ ጀዋር መሐመድ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች ታሳሪዎች ሁሉ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ ባለዉ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀረቡ። በሌላ በኩል ፤ «በአዲስ አበባ የመከላከያ ሠራዊት ገባ ተብሎ የሚፃፈዉ ነገር ትክክል አለመሆኑ» ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል። በመረጃዉ መሰረት «ድሮም ቢሆን የመከላከያ ሰራዊት የነበረዉ አዲስ አበባ ዉስጥ ነዉ።» ቀደም ሲል «የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በሃገሪቱ ከ 80 ሰዎች በላይ በመገደላቸዉ፤ ልዩ የፀጥታ ኃይላት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸዉን የዉጭ ዘገቦች አመልክተዋል።» ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ መሰረት ግን አዲስ አበባ ከትናንትና በተሻለ መረጋጋት ላይ ትገኛለች። «ወደ አዲስ አበባ ልዩ ኃይል ገባ ፤ አልያም ተጨማሪ ሰራዊት ወደ

The post አቶ ጀዋርና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

ምክትል ጠቅላ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ያስተላለፉት መልዕክት

$
0
0

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በአሳዛኝ ሁኔታ መሞት ሁላችንንም ያሳዘነና የልብ ስብራት የፈጠረ ከስስተት ነው፡፡ ከዚህ ግድያ ጋር ተያይዞ በተደረገ የጥፋት ቅስቀሳ በተለያየ አካባቢዎች በአሳዛኝ ሁኔታ የብዙ ንፁኃን ህይወት አልፏል፡፡ ብዙ ንብረት እና ቅርስ ወድሟል፡፡ በዚህ ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት ህይወታቸው ለጠፋ ዜጎች የተሰማኝን ልባዊ ሃዘን እየገለፅኩ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን እመኛለሁ፡፡ የዚህ ዓይነት ጭካኔ የተሞላበት ግድያ በሃጫሉ ግድያ ለማቆም ሳይሆን ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጭት ሃገርን ወደ ለየለት ብጥብጥ እና ትርምስ በማስገባት በውጭና በውስጥ ላሉት የጥፋት ሃይሎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ነው፡፡ ከግድያ በኋላ የተላለፉት የጥፋት ጥሪዎች በአንዳንድ ቦታ በተግባር የተያዘው ድርጊት በቀጣይ የባሰ ጥፋት ለማቀጣጠል እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ይዘህ ማሳያ ነው፡፡ ይህን

The post ምክትል ጠቅላ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ያስተላለፉት መልዕክት appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

ሃጫሎን ማን ሊገድለው ይችላል ለምን?

$
0
0

በእኔ እምነት የአርቲሰቱ ሞት የታላቁ የእዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን ከማደናቀፍ ሴራ ጋር በእጅጉ የተጋመደ ነው።ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውኃ ማማ ናት።አፈሯም በዓለም ደረጃ ለም ከሚባሉት የሚመደብና የሰጡትን የሚያበቅል ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ተፈጥሮ የለገሰችንን ሀብት መጠቀም እንዳይችል በግብጽ ታላቅ ደባ ሲፈጸምብን ኖረናል። ግብጾች ሲመቻቸው በቀጥታ ወረራ በማካሄድ ጦርነቱ ሲሳናቸው በእኛ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት እያሰናከሉ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት በዋናነት ሲጠቀሙበት ኖረዋል። ግብጽ በሜዲትራንያን እና በቀይ ባሕር የተከበበች አገር ብትሆንም ውኃው ጨዋማ ስለሆነ ለመጠጥም ሆነ ለእርሻ አትጠቀምበትም። የግብጽ ሕዝብ የሕይዎት መሰረት የሆነውና አገሪቱንም በዓለም ደረጃ በግብርና በቀዳሚነት ከሚሰለፉት አገሮች ተርታ እንድትመደብ ያደረጋት በአባይ ወንዝ አማካኝነት  ከኢትዮጵያ  ታጥቦ በሚሄድላት አፈር ነው። በዚህ ከቀጠለ በተለይ

The post ሃጫሎን ማን ሊገድለው ይችላል ለምን? appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

የህወሓትና የፅንፈኛው ኃይል ዘመቻ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው አለመረጋጋት July 2020

ሐጫሉን ማን ገደለው?ለምን? መንግስት ሆይ ቁማሩ ይብቃ! –ሰርፀ ደስታ

$
0
0

አሁንም ያችው የተለመደች ነገርን አደበስብሶ ማለፍ ላትደገም አንዳቸውም ዋስትና የለንም፡፡ መንግስ የሚባለው አካል እኛ እሱም ባይነግረን የምንናገረውን ነው እስካሁም መልሶ እየነገረን ያለው፡፡ የጠቅለይ አቃቤ ሕጓ አበበች አቤቤ ለጋዜጠኞች የሰጠችው መግለጫ እንደምታወራው ነገሮች የሚፈጸሙ ከሆነ ጥሩ ነው፡፡ በቃ እንዳለቸው የዘመናት በሕዝብ ደም፣ ሞትና ሥቃይ ላይ መቆመር ሊበቃ ይገባዋልና፡፡ ሌሎች የሚያወሩትን ብዙም ትኩረቴን ሊስበው አልቻለም፡፡ አሁንም ማስመሰል እንደሌለበት ምንም ማረጋገጫ የለንም፡፡ በአብዛኛው የምንሰማቸው የባለስልጣኑ ንግግሮች የእኛን ስነልቦና ለመማረክ እንጂ ከውስጥ የሆነ ቁርጠኝነት ለመሆኑ ምንም ዋስትና የለም፡፡ የምንሰማቸው ድምጾች ከምናውቀው የማስመሰል ንግግራቸው ምንም የተለየ አደለም፡፡ ወሳኝ የሆነ በተግባር የተገለጠ እርምጃ ለማየታችን እጅግ እጠራጠራለሁ፡፡ አሁን ሁኔታው በጣም ስለተጋጋለ እንጂ ከአንድ ሶስት ቀን የመረጋጋት በኋላ

The post ሐጫሉን ማን ገደለው?ለምን? መንግስት ሆይ ቁማሩ ይብቃ! – ሰርፀ ደስታ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.


የአባቶች ምክር – ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን

$
0
0

07/01/2020 የእስራኤል ጉባኤ ወደ ሮብዓም መጥተው “አባትህ ከባድ ቀንበር ጫነብን፣ አንተ ግን  አባትህ የጫነብንን ከባድ ቀንበር ብታቀልልን እንገዛልሃልን” አሉት፡፡የሮብዓም አማካሪ ሽማግሌዎችም  “ዛሬ አንተ ለዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆን፣ ብትገዛለትና ደስ የሚያሰኝ መልስ ብትሰጠው፣ይህ ሕዝብ ምን ጊዜም ያንተ አገልጋይ ይሆናል“አሉት።ሮብዓም ግን ከሽማግሌዎቹ ምክር ይልቅ የጓደኞቹን  ምክር ሰማ፣ “ከአባቴ ይልቅ አገዛዜን አከብድባችኋለሁ” በማለትም የሕዝብ ተወካዮችን አስፈራርቶ መለሰላቸው።በዚህም ድርጊቱ ሕዝቡን አስቆጥቶ፣ ከነገደ እስራኤል በአስሩ ላይ የንግሥና ሥልጣኑን አጣ። ይህ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ነው።ይሁንና የሰው ልጆች ሁሉ ፍላጎት  ተመሣሣይ ነው። አገልጋይ የሆነና መብቱን አክብሮ፣ በእኩልነት የሚያስተዳድረውን መሪ ነው የሚፈልገው።ሕዝባችንም እንዲሁ ጥያቄዎቹን ሰምቶ የሚፈታና ጭቆናዎችን አስወግዶ፣ በሰላምና በእኩልነት አስተባብሮ ወደ ብልጽግና ጎዳና የሚመራውን ነው የሚፈልገው ከዚሁ

The post የአባቶች ምክር – ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

ከአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

በአገራችን ኢትዮጵያ ለ27 ዓመታት በህወሓት የፓርቲ የበላይነት ሲመራ የቆየው የኢህአዲግ ድርጅት ከፍተኛ መስዋዕትነት ባስከፈለው የህዝብ ትግል ህወሓትን ከአራት ኪሎ የሚኒሊክ ቤተመንግስት ወደ መቀሌ እንድትኮበልል ሲያደርግ በምትኩ በህዝብ ትግል የመጣውን ለውጥ ከስርዓቱ ጋር በነበሩ አመራሮች የነበረ የጋራትግል ነው በሚል አስተሳሰብ ለውጡን እንዲመሩ እድል የተሰጣቸው አመራሮች በተመሳሳይ መንገድ ላለፉት 27 አመት በህዝብ ደም የተጨማለቁ አመራሮችን ከከፍተኛ እስከ መጨረሻው ዝቅተኛ የስልጣን እርከን ላይ መልሶ በመሾም ለውጡ ከህወሓት የአገዛዝ ዘመን በባሰ ሁኔታ ዜጎች ግፍ ሲፈፀምባቸው መቆየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው::በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና ኦሮሚያ የሚባል ሀገርን ለመመስረት ጫካ ገብቶ ሲታገል የነበረው ኦነግ ትጥቁን ሳይፈታ ወደ አገራችን በመግባቱ ምክንያትና በብልፅግና ውስጥ ከአሉ አመራሮች

The post ከአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

የሃዘን መግለጫ – የኢትዮጵያ ክፍላተሃገር ህብረት

$
0
0

ሰኔ 25 ቀን 2012ዓም(02-07-2020 የኢትዮጵያ ክፍላተሃገር ህብረት  ከሁለት ቀናት በፊት በገዳዮች እጅ ህይወቱ ባለፈው በታዋቂው ድምጻዊ አጫሉ ሁንዴሳ ሞትና ያንን ተከትሎ የወንጀለኞቹ ግብረአበሮች በንጹሃን ኢትዮጵያውያን በተለይም በአማራው ህብረተሰብ ተወላጆች ላይ በተለያዩ ቦታዎች ባደረሱት የጭፍን እርምጃ ህይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ይወዳል። በዚህ ተጠንቶና ታስቦበት በተቀነባበረ የፖለቲካ ግድያ ተካፋይ የሆኑት የተለያዩ ግን አንድ ዓላማ ማለትም የኢትዮጵያ መፈራረስና የሕዝብ እርስ በርስ እልቂት ያስተሳሰራቸው  የውጭ ሃይሎች አጀንዳ ፈጻሚዎች  እንደሆኑ ምልክቶችና ማስረጃዎች እዬወጡ ነው። እነዚሁ የጥፋት ሃይሎች በጭቁን ሕዝብ ስም ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ለአገራችን አንድነትና ነጻነት ለሕዝቡ አብሮነትና ዘላቂ ሰላም  እንቅፋት በመሆን  በተለይም ላለፉት ሃያ ዘጠኝ ዓመታት በፌዴራል፣ በክልልና በከባቢ ደረጃ ባሉት

The post የሃዘን መግለጫ –  የኢትዮጵያ ክፍላተሃገር ህብረት appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

ሃጫሉ ሁንዴሳ: ከሞቱ አሟሟቱ፣ ካሟሟቱ ቀብሩ፣ ከቀብሩ ሽብሩ –አሁንገና አለማየሁ

$
0
0

ሃጫሉ ሁንዴሳ እና ማልኮም ኤክስ መግቢያ “ከሞቱ አሟሟቱ፣ ካሟሟቱ ቀብሩ፣ ከቀብሩ ሽብሩ” ከሸገር ቀጥሎ ለአምቦ የተለየ ቅርበትና ፍቅር ይሰማኛል። በልጅነት እድሜ የቦረቅኩባት፣ ሌጣ ፈረስ ግልቢያ የተማርኩባት፣ በወንዝም በመዋኛ ገንዳም ውሃ የተምቦጫረቅኩባት፣ ጥንቸል አባርሬ ለመያዝ መከራዬን ያየሁባት የአምቦ ከተማና አካባቢዋ ትልቅ ትዝታ በውስጤ የተወችብኝ ናት። አዳሜ የልማት ጀግና እየተባለ በዘመነ ወያኔ የሚደረገውን ቀልድ ሳስብና በአምቦ ገና በኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ የምር የልማት አርበኛ የነበረውን መምህር ጋዲሳን ሳስብ የሚያቃጥል ቁጭት ይይዘኛል። የቀለም መምህር ብቻ ሳይሆን የተግባራዊ ኑሮና የልማት አስተማሪ የነበረው መምህር ጋዲሳ በአትክልት ልማት፣ በወተት ሀብት ልማት በእጁ ሠርቶ ገነትን የፈጠረ ሰው ነበር። የሚሠራ ሰው በመንግሥት እገዛ በማያገኝባት ሀገራችን ስንት እንቅፋቶችን እየታገለ ብዙ

The post ሃጫሉ ሁንዴሳ: ከሞቱ አሟሟቱ፣ ካሟሟቱ ቀብሩ፣ ከቀብሩ ሽብሩ – አሁንገና አለማየሁ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

የሀጫሉ ሀዘን መታሰቢያ! –ከአባዊርቱ

$
0
0

ይድረስ ለዝቃጮች ባላችሁበት ቦታ ሃጫሉን ለመድረስ ወጥታችሁ ከፍታ ጨለማን ለብሳችሁ ገላን ኮንዶ ሰፈር ልጃችን ተበላ አወይ የግዜር ነገር። ረስታችሁ  ከሆነ  የአምቦን ገጽታ እስቲ ላስታውሳችሁ ከያኔው ትዝታ። የጀግኖቹ አምባ ጅባትና ሜጫ መቁላት ያቅበታል ተልባን በሙቀጫ። ሃጫሉን ያፈራች ያች ፍል- ከተማ ብዙ ደጀን አላት ምን ” ወዩ” ቢግማማ። ጥንትም ታሪካቸው ሲነገር የኖረ ጀግኖችን ለመጣል አንድ ዘዴ ነበረ። ወይ ጽልመት ይለብሳል ከአይን ተሰውሮ ካልሆነም በሴት ነው የበጥራቆች ኑሮ። ይህን ጀግና ወጣት ሀሞተ ኮስታራ የወጣቶች ቁንጮ ምንም የማይፈራ በኦኤምኤን አውታር በክፉዎች ልሳን እንዲቀርብ አርጋችሁ  በዚያ ጁዋር ሰይጣን ሀጫሉ ጀግናው ልጅ ጥንትም ቀጥተኛ ላመነበት ጉዳይ ያልሆነ ዳተኛ ወጥመዳችሁ ገባ ወገንም ተንጫጫ ግን እኮ መብቱ ነው

The post የሀጫሉ ሀዘን መታሰቢያ! – ከአባዊርቱ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live