Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በአዲስ አበባ ከቧንቧ የሚፈሰውን ውሃ ይመልከቱ (ይናገራል ፎቶው)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ አተት ተከስቷል:: አሁን ደግሞ ኮሌራ:: በየሰፈሩ ከየቧንቧው የሚፈሰው ውሃ የሚሰቀጥጥ ነው:: በተለምዶ “ይህ ሕዝብ የሚኖርው በኪነጥበቡ ነው” እንደሚሉት አይነት ነው የሰው ኑሮ:: ይህ ከታች የምታዩት ፎቶ በአዲስ አበባ በተለምዶ ጎፋ ማዞሪያ በሚባለው አካባቢ ከሚኖሩ ወገኖች የተገኘ ነው:: ከቧንቧ ውሃውን ሲከፍቱት እንዲህ ያለ ቆሻሻ ውሃ ነው የሚፈሰው:: የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ በሆነችው ከተማ ንጹህ ውሃ ማቅረብ የተሳነው ስርዓት ሕዝቡን በውሃ ወለድ በሽታ እየፈጀው ነው::

gofa


የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ከሕዝብ ለተነሱት አስተያየቶች የሰጡት ማብራሪያ |ሊመደመጥ የሚገባ

$
0
0

Neamin Zeleke
(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ሰሞኑን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባደረጉት ንግግር ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቆይተዋል:: አቶ ነአምን በኢካዴፍ የፓልቶክ መድረክ ላይ በመቅረብ ከሰሞኑ ከሕዝብ ለተሰጡ አስተያየቶችና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል:: የአቶ ነአምን አስተያየት ለብዙዎች ጥያቄ ምላሽ ይሆናል ብለን እናምናለን – ሙሉውን ያድምጡት::

እኛና ጦርነት –ጊሼይ ጊሻ

$
0
0

ethiopia-eritrea-war-375x251

ጦርነት አስከፊ አውዳሚና ለሰው ልጆች በአጠቃላይ ሰቆቃ ውጤት ያለው ድርጊት መሆኑን በተግባር ያዩት ቀርቶ በፊልም የተመለከቱትም ቢሆኑ ሳይገነዘቡ የሚቀር አይመስለኝም። በአለም ላይ የተካሄዱ አስከፊ ጦርነቶችን ዛሬ የሆሊዉድ ሰዎች እነደመዝናኛ አድርገው በፊልም ሲያቀርቡት ትውልዱ ጦርነትን በመዝናኛ መልኩም ጭምር ቢመለከተው አስደናቂ አይሆንም። ዛሬ አሜሪካንና አውሮፓን በመሳሰሉ ሃገሮች እጂግ ዘመናዊ የሆኑ በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎችን ህይወት ለማጥፋት በሚያስችሉ መሳሪያዎች በየቀኑ የሽብር ተግባር ሲካሄድ የምናየው የጦርነት ፊልሞችና ያም የፈጠረው ለሰው ልጅ ክቡር ህይወት ደንታ ቢስነት ውጤት ነው። በጦርነት ሰበብ ያደጉ ማለትም (በቴክኒዎሎጂ)እንዳሉ ሁሉ ጦርነት ደግሞ ያቀጨጫቸው ሃገሮች በርካቶች ናቸው። ከነዚህ ሃገሮች አንድዋ ሃገራችን ኢትዮጵያ ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ታሪክ መመዝገብ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንኳን ከሽህ በላይ ጦርነቶችን አስተናግዳላች። አሁን እየደከመ ባለው ትውልድ ዘመን እንኳን ከንጉሱ ስርአት ጀምሮ ቢያንስ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ጦርነቶችን አስተናግደናል፥፥

አሁን ባለው ትውልደ እንኳን

በሻቢያና  በኢትዮጵያ መንግስት ( በንጉሱ በ ደርግ ዘመን የተካሄደው  ጦርነት )

በዋቆ ጉቱ የሚመራው የኦሮሞ ንቅናቄና በንጉሱ መንግስት የተካሄደው ጦርነት

ህዋሀት ኢሃዴግና በኢትዮጵያ መንግስት (ደርግ የተካሄደው ጦርነት

በኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጂትና  በደርግ መንግስት  የተካሄደው ጦርነት

በአፋር በሲዳማ ነጻአውጭዎችና በደርግ መንግስት  የተካሄደው ጦርነት

የታላቁዋ ሶማሊያ መስፋፋት አላማ በንጉሱ በደርግ ዘመን የተካሄደው ጦርነት

ኢህአፓና ኢዲዩ ከደርግ መንግስት ጋር ያደረጉት ጦርነትና እርስ በርሳቸውም ኢሃፓ ወያኔ እዲዩ ያካሄዱት ጦርነት

በወያኔ ኢሃዴግ የስልጣን ዘመን ደግሞ

በህዋሃት ኢሃዴግ መንግስትና  በ ኦ ኤል ኤፍ  መካከል የተደረገው ጦርነት ዛሬም የቀጠለው ጦርነት

በህዋሃት ኢሃዴግ መንግስትና በኦ ኤን ኤል ኤፍ  መካከል የተደረገው ጦርነት ዛሬም ያለው ጦርነት

በህዋሃት ኢሃዴግ መንግስትና በአልሻባብ እየተደረገ ያለው ጦርነት ዛሬም ያለው ጦርነት

በህወሃት ኢሃዴግ መንግስትና በሻቢያ በሚመራው የኢርትራ መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት

አርበኞች ግንቦት ፯ ( በኤርትራ መንግስት ድጋፍ  የጀመረውና ትኩሱ የርስ በርስ ጦርነት

እነዚህ ጎልተው የታዩና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን  የሃገራችንን ዜጎች የበሉ ይህ ትውልድ የሚያውቃቸው ጦርነቶች ናቸው

ከሁሉም በላይ በየስራቱ መሳሪያ አንግበው ጦርነት ውስጥ ሳይገቡ በአምባገነናቱ መንግስታት በተለይም  በደርግና ህወሃት ኢሃዴግ   በሰላማዊ ዜጎች ላይ  በየጊዜው የሚፈጸመው እልቂት ኢትዮጵያና ጦርነትን ደም ማፍሰስን  ለይቶ ማየት እንደማይቻል ይህ ትውልድ በሚገባ የሚገነዘበው የመስለኛል። የኢቲዮጵያውያን የሃገር ምንነት  ስነልቦና የጦርነት ስነልቦና ቢሆን አያስገርምም ። እድሚያችሁ በ ፷ አመት ወይም ከዚአም በላይ ወይም በታች የሆናችሁ ጦርነት የሌለባት ኢትዮጵያን ስለማናውቃትና የኢትዮጵያን እንደሃገር መኖር በደም መፍሰስ ብቻ ስለምናስባት የችግሮች መፍቻ ሌሎች አማራጮችን ማየት ባንችል አያስደንቅም። በኛ ዘመንና በቀደምት አባቶቻችን መካከል ያለው ልዩነት እነርሱ ከጣሊያን ከቱርክ ከእንግሊዝ በአጠቃላይም ከቅኝ ገዝዎች ሃገራችንን ለመጠበቅ የከፈሉት መስዋእትነት ሲሆን በዘመናችን ይህ መሰሉ ጦርነት በጅ አዙርም ይሁን በቀጥታ  ከውጭ ሃይሎች   ጋር ተመሳሳይ ጦርነት ያካሄድነው የመስፋፋት አላማ ዪዛ ከተነሳችው ሶምሊያ ጋር ብቻ ነው። የተቀረው ግን እኛው በእኛው የተጨራረስንበት ጦርነት ነው። ምናልባት ዛሬ ኤሪትራ ሌላ ሃገር እንድትሆን እኛው ወስነን እኛው ፈቅደን የሌሎች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጻረሩ ሃይሎች መሳሪያ  እንድትሆን አድርገን የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች እርስ በርስ እንዲጨራረሱ ያመቻቸነውም እኛው ነን ። ስለዚህ ጦርነቱ የእርስ በርስ ነው። በእርስ በርስ ጦርነት ደግሞ ሃገር ቂምበቀል የቋጠረ ዚጎችን ይዛ ወደፊት መራመድ እንደማትችል እሙን ነው። ስሞኑን በወጣው የአለም አስሩ ደሃ አገሮች ተርታና ረሃብተኛ ከሚባሉት ውስጥም  መገኘታችን ባያስገርምም ያለን ሃብትና ክምችት ለኛ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢያችንም የተትርፈረፈ እንደሆነ ብዙ ጥናቶች ያሳያሉ።

 

እነሆ ዛሬም የርስበርሱ ጦርነት አታሞ ከየአቅጣጫው እየተጎሰመ ነው። ለጦርነቶች ሁሉ ደግሞ መንስኤ አላቸው። በተለይ የርስ በርስ ጦርነት ትልቁ ምክንያት በአንድ ሃገር ውስጥ ያለው ስራት ኢፍትሃዊነት ኢዲሞክራሲያዊነት መሆኑ አያጠያይቅም ። በህዝቦች መካከል መተማመን በመንግስታትና በህዝብ መካከል ጤናማ ግንኙነት እስካለ ድረስ የርስ በርሱ ጦርነት አይታሰብም ። ምክንያቱም በተፈጥሮ የሰው ልጅ በሰላም ኖሮ በሰላም መሞትን ዪመርጣል። ከሰው ልጆች ውስጥ ጥቂቶች ከግል ስግብግበነት ወይም በስልጣን ጥቅም ታውረው ዜጎችን እርስበርስ በማባላት የስልጣን ዘመናቸውን ለማርዘም በሚያድርጉት ኢፍትሃዊ ጉዞ ለኢፍትሃዊነታቸው የተለያዩ ካባዎችን በሚደርቱ የፕሮፓጋንዳ ሰዎቻቸው እየታጀበ የሚከናውን ድርጊት ነው። የርስ በርስ ጦርነት እንዲካሄድ የሚያስችለው ደግሞ ሁሉም የርስ በርስ ጦርነቶች በህዝብ ጥቅም ስም ወይም በሃገር ሉዓላዊነት ስም መደረጉ ነው።

እኔ ለአንተ ከሱ የተሻልኩ ነኝ ወይም እኔ ከሱ የበለጠ ለሃገር ተቆርቁዋሪ ነኝ በሚሉ ወገኖች አነሳሽነት የሚፈጠር ቀውስ ነው። አንተ የሚሉትን ህዝብ ግን ማዳመጥ የማይችሉ ግብዞች ስራ ውጤት ነው። ካልሆነማ ሁላችንም ለህዝብና ለሃገር ካሰብንማ የህዝብን ደም ከሚያፈስ የመፍትሄ ሃሳብ ወጣ ባልን ነበር ። የፖለቲካ መፍቻችን የሰውን ልጆች ክቡር ህይወት ሊሰጥ የማይገባ እስከሆነ ድረስና በጋራ ሃገራዊ ጥቅምና ትርፍ እስካላስገኘ ድረስ ለሃገር ብዬ ነው ለህዝብ ብዬ ነው የሚሉት የፕሮፓጋንዳ ሃረጎች ትርጉም የላቸውም።

ስለዚህም ሃገራችንን የምንወድ ኢትዮጵያውያን ስለኢትዮጵያ ህዝብ ወይም ስለሃገራችን ህዝብ አንድነት የምንጨነቅ ሁሉ ዛሬ ከሁሉም አቅጣጫ  እየተመታ ያለውን የጦርነት ከበሮ ማስቆም ታሪካዊ ግዴታ አለብን ። የሚካሄደው ጦርነት ባህርይን ጠንቅቆ መገንዘብና በውንድማማቾች መካከል የሚደረገው ጦርነት ማንም በአሸናፊነት ቢወጣ ኢትዮጵያዊነት በቂምና በቁርሾ ላይ ሊያብብ እንደማይችል መረዳት ተገቢ ይሆናል። ጦርነት አምባገነኖችን ብቻ ከስልጣን አውርዶ የሚቆም ክስተት አይደለም ማህበራዊ እሴትን የማናጋት ባህርዩ ከፍተኛ ነው። በተለይ ምንም እንኳን በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖች በሚፈጥሩት ደባና የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በምክንያትም የተደገፈ ይሁን ያለምክንያት ጦርነቶችን መጫር ወይም መተናኮስ ባህሪያቸው ቢሆንም መንግስታቱ አምባገነኖች በመሆናቸው ብቻ በዘለቄታ ብሄራዊ ጥቅማችን ላይም ጭምር ከለየላቸው የሃገራችን ጠላቶች ጋር አለመቆማችንን    ማረጋገጡ አስፈላጊ ይሆናል፡

ስራቱ ከጊዜ ወደጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየዘቀጠና  በተለይም በተወሰኑ እኛ ብቻ አዋቂዎች ብለው በሚመጻደቁ ጥቂት ቡድኖች የማእከላዊነት አመራር  ወይም ሃላፊነት የጎደለው አክሂድ እየሄደ መሆኑ ግልጽ ነው። ሃላፊነት የጎደለው ስንል ደግሞ ለሰው ልጅ ህይውት ከሚሰጠው ክብርና ግምት አንስቶ ስለራሱም የወደፊት ህልውና ማሰብን ጭምር የሚያመለክት ቢሆንም በ እብሪትና በማን አለብኝነት የሚፈጥራቸውን ቀውሶች በሙሴ ህግ እጅን የቆረጠ እጅ አይንን ያጠፋ አይን ለሃገር ፖለቲካ መፍቻ ምላሽ ለመስጠት ከመሞከር ይልቅ ሃላፊነት የተሞላበትና የሚከፈለውም መስዋእትነት ዘለቂታና አስተማማኝ ውጤት ሊያመጣ እንዲችል ከጦርነት ባሽገር ያሉ ህዝባዊ ትግሎች እንደገና ሊፈተሹ ይገባል። ሊሎች የትግል ስልቶች የህይወት መስዋእትነት አያስከፍሉም ማለት እንዳልሆነ ባለፉት አመታት በተግባር አይተነዋል።  መስዋእትነቱ በጋራ መቆምን አስተምሮአል በጋራ በአንድ እስርቤት መከራን በመካፈል ለጋራ ትግል አነሳስቶአል። በህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት በሰከነ መንገድ ለማየት አስችሎአል። የስራቱ ደጋፊዎችን ጭምር ልባቸውን አሸፍቶአል። በተቃዋሚነት የተሰለፈው ጎራ ከድክመቱ አንሰራርቶ በጠንካራ አመራር  በስልት የተደገፈና  ህዝባዊ እምቢተኝነትን ትግል እያዳበረ ከሄደ የሃግራችን ትንሳኤ እሩቅ አይሆንም።

ስለዚህም በምንም መልኩ ቢሆን ለሃገራችን የምንጨነቅ ሁሉ ዳግም በሃገራችን የርስ በርስ ጦርነትም ሆነ በውጭ ሃይሎች በሚቃጣብን ወረራ  የኢትዮጵያዊ ወገን አስከሬን መሳለቂያችን ወይም ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በማዋል ሃገራችን የምንወድ ለህዝባችን የቆምን አድርገን እራሳችንን ከቆጠርነው አሁንም እራሳችንን መመርመር የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

የአምባገነኑን ስርዓት ለመታገል በተለያየ አቅጣጫ የተሰለፉ ወገኖች  ወይም በዚያች ሃገር ውስጥ  ማንኛውም አይነት ህዝብን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ክፍሎች ከሌሎች ተመሳሳይ ችግር ካላቸው ወገኖች ጋር ቢያንስ በጠረጰዛ ዙሪያ ተቀምጠው የጋራ ሃገራችንን እጣ ፈንታ ላይ ለመወያየት የሚያስችል ወኔና ድፍረት ከሌላቸው ከጦርነት የሚያገኙት ፍርፋሪ የወገኖቻቸውን ሰቆቃ ብቻ ነው።

እውነታው ዛሬ ህዝብ በስራቱ ተንገሽግሾአል። ስራቱም ብቻ ሳዪሆን ደጋፊው ጭምር ይህ ስራት መበስበሱንና መለውጥ ያለበት መሆኑን ዪፈልጋል።  ህዝብ ያጣው አንድ ነገር ነው፡ ስራቱን ተክቶ ሃገርን ለመምራት የሚችል የብዙዎችን ኢትዮጵያውያንን ጥያቀዎች ማእከል ያደረገና ሊዩነቶችን በበሰለ የፖለቲካ ጥበብ መፍታት የሚችል፡ የሃገሪቱን ሏላዊነት ለማስጠበቅና የኔ ብቻ መንገድ ከሚል እብሪት የጸዳ የፖለቲካ ሃይል ነው። ዛሬ ሁሉም እብሪተና በሆነበትና በኔ መንገድ ብቻ በሚል ፻ ድርጂት ወይም ስብስብ  ባለበት የሃገሩን ደህንነት በግርግር ለማንም አሳልፎ ላለመስጠት ሲል ብቻ በአምባገነኖች መዳፍ እየተደቆሰና መስዋእትነት እየከፈለ ይገኛል። በባህር ማዶ  ወይም በሃገር ውስጥ ተቀምጦ ተጨቁነሃል ተበድለሃል እያለ ብሶቱን የሚነግረውን አይደለም የሚፈልገው። ብሶቱን በህይወት ተሞክሮ ያውቀዋል፡ በዚህም ሆነ በዚያ ገፈቱን በቀጥታ እየተጎነጨው ነው። ያውቀዋል። ያጣው እምነት ነው። ብዙ ሲታለል የኖረ ህዝብ ነው። በስሙ ስንት ነገር እንደተሰራ ያውቃል። ዛረ ትውልዱም እየተቀየረ ሲመጣ የሃገር ፍቅር፡ የመስዋእትነት ልኩን እየተገነዘበም ይመጣል ። የኢንፎርሜሽን ዘመን በመሆኑም ብዙ ዪነጋገራል። በአጠቃላይም ትውልዱ የተሻለ ስራአት መምጣት እንዳለበት ቢፈልግም ስራቱን ለማምጣት በሚታገሉ ሃይሎች ላይ ኮንፊደንስ ገና አላደበረም ። እነሱም ቀልቡን በሚገባ አልሳቡትም። ለአንድ አላማ ቆመናል እያሉ በየቀኑ እየትማማሉ ተመልሰው እሳትና ጭድ ሆነው ሲታዩ እምነቱ ከየት ይመጣል፧ ለዚህም ነው መፍትሄው አንድብቻ የሚሆነው። በሃገራችን ለውጥ እንዲመጣ አምባገነኑም ስራት እንዲወገድ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ በየፊናቸው የሚያደርጉትን ሩጫ አቁመው በጠረጰዛ ዙሪያ ተገናኝተው የልባቸውን መነጋገርና መተማመን ሲፈጥሩ ብቻ ነው። መሪ ነን ባዮች በማይተማመኑበት መንደር ህዝብ እንዲያምናቸው መጠበቅ ሞኝነት ነው። ለዚህም ነው ይህ ባልለየበት ሁኔታ በየትኛውም በኩል የሚጎሰመውን የጦርነት አታሞ አጥብቀን ልናወግዘው የሚገባን።

ጦርነት ምንጊዜም የህዝብ ምርጫ አይደለም። ጦርነት ምንጊዜም በህዝብ ስም ተለውሶ የሚቀርብ መርዝና በጥቂቶች ለጥቂቶች ሲባል የሚደረግ እኩይ ተግባር ነው።

 

ጊሼይ ጊሻ

“3ቱ ሳጥኖች”ቁልፋቸው ተመሳሳይ ከሆነስ?(መልስ ለዲ/ን ዳንኤል)

$
0
0
አሰፋ ከዳላስ
ጤና ይስጥልኝ ዲ/ን ዳንኤል
በ ‘ዘሀበሻ’ ድረ ገፅ ላይ በ June 19, 2016 የታተመውን መጣጥፎን አነበብኳት። የፅሁፎ መልክት ትንሽ ኮረኮረኝና ይህችን አጭር መልስ ለመፃፍ ወሰንኩ።
0184S-024321ሃሳብዎትን የሚያቀርቡባቸውን መንገዶች እወዳቸዋለሁ። እንደ አጫዋችነትዎ እና ማህበራዊ ተችነትዎ ሃሳቦችዎን እያዋዙና በምሳሌ እያስደገፉ ማቅረብዎ ጥሩ ነው። በዚህ ‘’3ቱ ሳጥኖች“ ብለው በሰየሟት መጣጥፍዎ ላይ በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ለሀሳብ የምንሰጠው ቦታ ዝቅተኛ መሆኑን መተቸትዎ ልክ ነው እላለሁ:: ለህሳብ እና ሀሳብን ለሚያፈልቁ ሰዎች ዋጋ የማይሰጥ ማህበረሰብ ጤናማ ነው አልልም። ያለመታደል ሆኖ እኛም የዚህ በሽታ ተጠቂዎች መሆናችንን ተችተዋል። እስማማለሁ:: ነገር ግን በኔ እይታ ትችትዎ ቁንፅል partial) ሆነብኝ።
ዲ/ን ዳንኤል  እንዳሉት ሰው በግል ነው የተፈጠረው:: የሚያስበውም ማሰብ ያለበትም በግል ነው:: በግል ማሰብ ግን ለግል ከማሰብ የተለየ ነው። በሌላ በኩል ሰው በነፃንትም ነው የተፈጠረው። በሚኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ እሴቶች ይህንን ከፈጣሪው ያገኘውን ነፃነት በበጎም ይሁን በመልካም የመቅረፅ ተፅእኖ እንዳላቸው እርሶም የሚስማሙበት ይመስለኛል። እነዚህ ተፅእኖ አድራጊ ተቋማት ታዲያ የሃሳብን ጣሪያ ብቻ ሳይሆን ይዘቱንና አቅጣጫውንም የመቅረፅ አቅም አላቸው። 
ከነዚህ ተፅእኖ ፈጣሪ ተቋማት ውስጥ ዲ/ን ዳንኤል “የምርጫ ሳጥን”  እና ”የገንዘብ ሳጥን“ ብለው የሰየሟቸው ይገኙበታል።  3ኛው ሳጥን ደግሞ “የህሳብ ሳጥን” ያሉት ነው። በኔ እይታ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ እነዚህ “3ቱ ሳጥኖች” ተደጋግፈው የሚሄዱ እንጂ ተነጣጥለው የሚታዩ አይደሉም። የትኛው የየትኛው ውጤት ነው ወይንም ትልቁን ስፍራ የሚይዘው የትኛው ነው የሚለውን ክርክር ለግዜው እንተወው። ነገር ግን አንድ ማህበረሰብ (ሀገር)“የምርጫ ሳጥኑን”  እና ”የገንዘብ ሳጥኑን“  የሚያስተዳድርበት ወይንም የሚይዝበት መንገድ በ3ኛው ሳጥን “የህሳብ ሳጥን” አያያዝ ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ ይኖረዋል እላለሁ። የዲ/ን ዳንኤል  እይታ ቁንፅል (partial) ሆነብኝ ያልኩት እዚህ ላይ ነው።
“በኢትዮጵያ ውስጥ  ሶስት ሳጥኖች አሉ። ሁለቱ ሳጥኖች በጣም ይፈለጋሉ። ስለሚፈለጉ ወይ ይዘረፋሉ ወይ ይሰረቃሉ። አንደኛውን ሳጥን ግን ዞር ብሎ የሚያየው የለም” ብለዋል ዲ/ን ዳንኤል  ። ታዲያ ሁለቱን ሳጥኖቹ “የምርጫ ሳጥን”  እና ”የገንዘብ ሳጥን“ሚዘረፉበትና  የሚሰረቁበት ሀገር ሀሳብስ ቢሰረቅ ምን ይገርማልምክንያቱም የሌባ ሀገር ነዋ። እንዲያውም የሃሳብ ሌባ በግልፅ ስለማይታይ  ለማወቅም ሆነ ለመከላከል ከባድ ነው። በግልፅ የሚታየውንስ ሌባ ማስቆም ወይንም መከላከል ያልቻለ ስውሩን ሌባ ሊገታው ይችላልን
ዲ/ን ዳንኤል  “የምርጫ ሳጥን” መዘረፍን በጨረፍታ ነክተው በማለፍ “የሃሳብ ሳጥን”  ግን ማንም ዞር ብሎ አያየውም ብለዋል። በኔ ግምት ይሄ አንድምታ “ሃሳብ” ለምንለው ነገር ያለንን ውሱን እይታ ያሳያል። ለመሆኑ ስለምርጫ ሳጥን ስናወራ ውስጡ ስለተቀመጠው ሀሳብ እንጂ ስለ ግዙፉ ነገር ወረቀቱን ወይንም እጨቱንማለታችን ነው እንዴእንደዚያ አልመሰለኝም። እኔ የምለው “የምርጫ ሳጥን”  አያያዝ  “በሃሳብ ሳጥን” አያያዝ ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል ብቻ ሳይሆን “የምርጫ ሳጥን”  ጉዳይ ራሱ የሃሳብ ጉዳይ ነው። ስለዚህ “የምርጫ ሳጥን”  ”የሚዘርፍ“ ወይንም ”የሚሰርቅ“ ሀሳብ ነው የሰረቀው። ሀሳብ ነው የዘረፈው። 
በኔ ግምት “የምርጫ ሳጥን”  እና ”የገንዘብ ሳጥን“ የሚዘረፍበት ሀገር ማህበረሰብአንድም ሌቦች ያለቅጥ በዝተውበታል። ወይንም ራሱ ሀገሩ ሌባ ሆኗል። ስለዚህ ጥያቄው ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል  ለይተውቆንፅለውእንዳቀረቡት የዋዛ አይመስለኝም። 
ስለዚህ ለወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል የምለው እኛ ማየት ስላልቻልን እንጂ ሁለቱን ሳጥኖች ሚዘርፉት እና የሚሰርቁት ሶስተኛውንም እየዘረፉና እየሰረቁት ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ግዜ በፎቶኮፒ መክፈት ቢቻልም፤ የሶስቱም ኦርጅናሌ ቁልፍ ግን አንድ ነው። ይህ ቁልፍ ምንድነው ከተባለ በሚቀጥለው ላብራራ እችላለሁ።

በሕዝብ ደም የሥልጣን ዕድሜ ማርዘም! –የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ መግለጫ

$
0
0

ሰኔ 13፣ 2008 (ጁን 20፣ 2016)

shengoበዓለም ላይ ከሚታዩት መንግሥታት ውስጥ ሁለት ዓይነት መንግሥታት ጎልተው የሚታዩ ሲሆን፤ ሁለቱም ወደ ሥልጣን እርካብ የሚወጡበት መንገድ የተለያየ ነው። አንደኛው በሕዝብ ምርጫና ፍላጎት፣ በዴሞክራሲ መንገድ ሥልጣኑን ለተወሰነ ዓመት የሚረከብ ሲሆን ሌላው ደግሞ በራሱ ፍላጎትና ውሳኔ፣ የሕዝብን ድምፅና ፍላጎት ሳይሰማና ሳይጠይቅ በመሣሪያ ኃይል አስፈራርቶና ደምስሶ የሥልጣኑ ባለቤት የሚሆን ነው። የመጀመሪያውን የስልጣን ባለቤትነትን የሚከተል የግድ የዲሞክራሲን ሕግና ባህል የተቀበለና በዛም የሚያምን መሆንን፣ ችሎታንና ሕዝባዊነትን፣አገር ወዳድነትን ይጠይቃል።በሁለተኛው የስልጣን አወጣጥ ግን ሃይልን፣  –– [ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]— 

ጠቡ የሻእቢያ እና የሕወሃት እንጂ የሕዝብ አይደለም |ግርማ ካሳ

$
0
0

solders ethiopian
(በአዲስ ገጽ መጽሄት እትም 13 የተወሰደ)

ሰሞኑን በሰሜኑ የአገራችን ግዛት ጦርነት ተቀስቅሷል። አስመራም፣ አዲስ አበባም ያሉ ገዢዎች ጦርነት መደረጉን ማመን ብቻ ሳይሆን “ይሄን ደመሰስን፣ ይሄን ያህል ገደልን” እያሉ በመማጸደቅ ላይ ናቸው። አለም የትናየት ደርሳለች፣ ትላንናት እኛ እየረዳናቸው ነጻ የወጡ የአፍሪካ አገራት እንኳን የትናየት ደርሰዋል፣ እኛ አሁንም መግደልን እንደ ጀብዱ አድርገን እናወራለን።

አንዳንድ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ከሻእቢያ ጋር የሚደረግን ጦርነት ከአንድ የዉጭ አገር ወራሪ ጋር እንደሚደረግ ጦርነት አድርገው ነው የሚያዩት። በኔ እይታ ይህ የተሳሳተ አመለካከት ነው። በሻእቢያ እና በኢሕአዴግ መካከል የሚደረገው ጦርነት ከኢትዮጵያ ህዝብ እና ከኤርትራ ህዝብ ጥቅም ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ጦርነቱ ፣ በዜጎች ደም የሰከሩ፣ የሁለት አምባገነን ቡድኖች ጦርነት ነው። የነርሱ ጣጣ ነው። ለጥቅማቸው፣ ለስልጣናቸው ሲሉ የሚያደርጉት።

ምንም እንኳን ላለፉት 25 አመታት ኤርትራ በፖለቲካ አስተዳደር፣ በሻእቢያ እና በሕወሃት ሴራ፣ ከኢትዮጵያ ብትለይም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኤርትራ ህዝብ ግን በመንፈስ የተለየ ህዝብ አይደለም። በታሪክ፣ በባህል፣ በስጋ፣ በሃይማኖት እርስ በርሱ የተሳሰረና የተዋለደ ወንድማማች ህዝብ ነው። እግዚአብሄር ፈቅዶና ህዝቡ በትግሉ በርትቶ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታት በአስመራና በአዲስ አበባ ቢመጡ እንደገና ተስማምቶ ሊዋሃድ የሚችል ህዝብ ነው።

ብዙዎቻችን ላለፉት 25 አመታት ከነበረው ፖለቲካ የተነሳ፣ ሻእቢያን ከህዝቡ መነጠል አቅቶን፣ ሻእቢያ ላይ ችግር ስላለብን፣ ኤርትራዉያን ላይ በጅምላ እንፈርዳለን። ይህ ሌላ ትልቅ ስህተት ነው። እስቲ ስለ ኤርትራ ህዝብ ትንሽ ላካፍላችሁ። የሰማሁትንና ያነበብኩትን ሳይሆን ያየሁትንና እና ያለፍኩበትን። የአስመራ ዮኒቨርሲቲ ተማሪ የነበሩኩኝ ጊዜ የማስታወሰዉን። (ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ሆና የመጨረሻዎቹ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ነበርን)

ኤርትራ፣ አስመራ ሲባል ብዙ ጊዜ ወደ አይምሯችን ከሚመጡት ነገሮች ጥቂቶቹ፣ ግፈኛው ሻእቢያ ሲሆን ሌላው ደግሞ ብዙ ጊዜ በፖስት ካርድ ላይ የምናየዉ፣ ዘንባባዎች በዳርና በዳር ያሉበት መንገድ በመሃከሉ የሚያልፈው፣ ፒያሳ ወይንም ኮምፖሽታቶ የሚባለዉን ሰፈር ነዉ። በዚያ መንገድ ብዙ ኬክ ቤቶችና ቡና ቤቶች ነበሩ። ትዝ ይለኛል በአምሳ ሳንቲም አንድ ኬክና ምን የመሰለ ካፑቺኖ እናዝ ነበር። በተለይም ሲመሽ ከመብራቶቿ ጋር ከተማዋ በጣም ታምር ነበር። (በነገራችን ላይ አሁን አስመራ ያኔ የነበራት ዉበት የላትም። የተንኮታኮተችና ያረጀች ከተማ ሆናለች። የቀድሞው የክፍለ ሃገር አወቃቀር ብንመለከት የትግራይ ክፍለ ሃገር ቢያንስ አራት ፣ ጎንደር ሁለት፣ ጎጃም ሁለት፣ ወሎ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች እያንዳንዳችው ሲኖራቸው፣ ኤርትራ የነበራት፣ እኛ የተማርንባት አንዱ ዩኒቨርሲቲ ተዘግቷል። ከከተማዉ ዉበት ባሻገር የማልረሳዉና በዉስጤ የተተከለ አንድ ሌላ ነገር ቢኖር የሕዝቡ ፈሪሃ እግዚአብሄርነትና ደግነት ነበር። እስቲ አንዳንድ ያጋጠሙኝን ላጫዉታቹህ።

አንድ ቀን በዮኒቨርሲቲ ዉስጥ ወዳለዉ ካፍቴሪያ እራቴን ለመብላት እየሄድክ ሳለ ጓደኞቼ አገኙኝና «አትሄድም እንዴ ? » አሉኝ። «የት ?» አልኳቸው። «ንግደት» አሉኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ያንን ቃል የሰማሁት። ጓደኞቼ ነገሩን ያውቁ ነበርና ምን እንደሆነ በኋላ አስረዱኝ። ያን ቀን በአስመራ በሰሜን ምዕራብ በኩል ቪላጆ የሚባል ሰፈር፣ የሚካኤል ይሁን የገብርዔል ቤተ ክርስቲያን አለ። (የቱ እንደሆነ አሁን አላስታወስም)። የዚያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት የሚወጣበት ቀን ነበር። ታዲያ ቤተ ክርስቲያኗ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ታቦቱ በነገሰበት ቀን ግብዣ አድርገዉ በአካባባዉ ያሉትን ሁሉ ይጋብዙ ነበር። ይሄ ስርዓት ነዉ እንግዲህ ንግደት የሚባለዉ።

ያኔ መኪና የለንም። በእግራችን ከአንድ ሰላሳ ደቂቃ በኋላ በቪላጆ ደረሰን። አራት ተማሪዎች ነበርን። በሰፈሩ ስንሽከረከር «ኑ ግቡ» ብሎ የሚጠራን ሰዉ አጣን። ለካ ኑሮ በጣም ስለተወደደ እንደድሮ በየመንገዱ እየቆሙ «ብሉልን ጠጡልን» ማለት ቆሟል። «መቼም የዩኒቨርሲቲ ካፍቴሪያ ምግባችንን ትተን ባዶ ሆዳችንን አንመለስም» ብለን ወደ አንዱ ቤት አመራንና አንኳኳን። «እንኳን አደረሳቹህ ? » ስንል ፣ አንዲት ያኔ ወደ አርባ አመት የሚጠጋት እናት፣ በእጇ አንድ ሕጻን ልጅ ታቅፋ ወጣችና «ግቡ፣ ግቡ » አለችን በፈገግታ። የቤቱ በር ጠባብ ነበር። ጎንበስ ብለን ገባን። የነበረችዋን ጠረቤዛ ከበብናት። በትልቅ ትሪ እንጀራ ቀረበልን። ሴትየዋ ድስቱን አመጣችና ወጡን እንዳለ እንጀራዉ ላይ ደፋችዉ። ብዙ ጊዜም አልፈጀብንም ትሪዉን ጠረግነዉ። ከዚያም በትላልቅ ጣሳዎች ጠላ አመጣች። ለኔ ዉሃ ተሰጠኝ። ምን ልበላቹህ ምን የመሰለ መስተንግዶ ተደረገልን።

አሰመራን ሳስብ፣ የአስመራ ነዋሪዎችን ሳስብ፣ ያቺን ሴት አስባለሁ። ለእግዚአብሄር ፍቅር ስትል፣ እንግዳን በደስታ የምትቀበል ! ችግረኛ ናት፣ ነገር ግን ከፊቷ ውስጣዊ ሰላም ያላትና ሰዉን የምትወድ ትልቅ ሴት ነበረች!! ያኔ በትግሪኛ አልነበረም ያናገርናት። «የኔ ዘር ናቸዉ» ብላ አልነበረም ያስተናገደችን። ነገር ግን ትልቅ ሴት በመሆኗ እንጂ።

የማያልፍ ነገር የለምና የዪኒቨርሲቲ ትምህርታችንን አጠናቀን የምረቃችን ቀን ደረሰ። ባጽእ (ምጽዋ) በሕዝባዊ ሀርነት ኤርትራ ግንባር ሥር ከወደቀ በኋላ በምጽዋና በአስመራ መሃከል ከሚገኝ አንድ የከፍታ ቦታ፣ «ግራፒ» እንለዉ የነበረ ከሩቅ የሚተኮስ መድፍ በየጊዜው አስመራ ከተማ ላይ ያርፍ ነበር። በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ መብረሩን አቁሞ ነበር። የጦር አይሮፕላን ግን ማረፉን አላቆመም። በወቅቱ ደግሞ ሕወሃት በትግራይ ጥቃቶች ያደረግ ስለነበረ ከአስመራ አዲስ አበባ ያለው መንገድ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቶ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለማይበርም ቤተሰቦቻችን ለምረቃችን ከአዲስ አበባ ሊመጡ አልቻሉም። ስለዚህ የምረቃ ስነ ሥርዓታችን ብዙ አልጓጓንለትም ነበር። የምረቃችን ስነስርዓት ቀን በወንዶች ሽንት ቤት ዉስጥ ትልቅ ፈንጂ ፈነዳ። ያን ሰዓት ትልቅ ድንጋጤ በዩኒቨርሲቲ ጊቢ ዉስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ተፈጠረ። ወዲያዉ ሻቢያ የደስታ መግለጫ መልዕክት ማስተላለፉ ነዉ ብለን ቀልደን አለፍን። ከሩቅ በሚተኮስ መድፍ በግራፒ ተምሮ በፈንጂ መመረቅ ይሉታል ይሄ ነዉ።

ያ ቀን ከፈንጂ ፍንዳታዉ ሌላ የማልረሳዉ፣ በጣም ልቤን የነካና ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ዘላቂ ፍቅር እንዲኖረኝ ያደረገ አስደናቂ ነገር ሆነ። ቤተሰቦቼ ከአዲስ አበባ ስላልመጡ የምረቃ ልብሴን አዉልቄ ወደ ዶርሚተሪ ለማምራት እየተዘጋጀሁ ሳለ ድንገት፣ አንዲት ሴትዮ አበባ ይዘዉ ብቅ አሉ። ትዬ ዘይዳ ነበሩ። ትንሽ እንደቆየዉ ደግሞ አንዲት አሮጊት ሴትዩ ሌላ እቅፍ አበባ ይዘዉ መጡ። አደይ ጸሃይቱ ነበሩ። ሁለቱም አይተዋወቁም። በአራት አመት የአስመራ ቆይታዬ የተወዳጀኋቸዉ እናቶች ናችዉ። ያኔ ብቻዬን የሆንኩኝ መስሎኝ ነበር። ግን ከአንድም ሁለት እናቶች እንደ እናቴ ሆነዉ አበባ ይዘዉ በምረቃዬ ተገኙ። እነዚህ ሁለት እናቶች ዶሮ አርደዉ ቤታቸዉ ድግስ አዘጋጅተዉ ነበር። ሁለቱም ወደ ቤታቸዉ እንድመጣ ፈለጉ። ግራ ገባኝ። በኋላ አንዳቸዉ ጋር ምሳ ሰዓት ፤ ሌላኛዋ ጋር ደግሞ ሲመሽ ለእራት ሂጄ ከጓደኞቼ ጋር የተዘጋጀልኝን ድግስ ተካፈልኩ።

አስመራን ሳስብ፣ የአስመራን ሕዝብ ሳስብ ትዬ ዘይዳና አደይ ጸሃይቱን አስባለሁ። እነዚህ እናቶች በስጋ እናቶቼ አይደሉም። እንደነርሱ ትግሬ አይደለሁም። እንደነርሱ የኤርትራ ተወላጅ አይደለሁም። ነገር ግን የእነዚህን እናቶች የዋህነት፣ ፍቅርና ያላቸዉን ፈሪሃ እግዚአብሄር የሞላባቸው ትልቅ ሴቶች ናቸው። ደጎችና ለዘር ቦታ የማይሰጡ። እግዚአብሄር ባሉበት ቦታ ይባርካቸው።

የመጨረሻ አመት ተማሪ እያለን በአንድ ሃይ ስኩል፣ ለሶስት ወር ማስተማር ነበረብን። ባርካ ተብሎ በሚታወቅ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመደብኩኝ። የተመደብኩበት ክፍል አስተማሪ ክፍሉ በጣም ረባሽ ክፍል እንደሆነ አስጠነቀቀኝ። በጣም ፈራሁ። ነገር ግን ማስተማሩን ስጀምር አስተማሪው ከነገረኝ የተቃረነ ሁኔታ ነዉ ያየሁት። ተማሪዎቹ በጣም የሚያዳምጡ፣ በአክብሮት ከታያዙ ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ሆነዉ ነበር ያገኘኋቸዉ። አስተማሪያቸዉም ብሆን ጓደኞቼም ሆነዉ ነበር የተለያየነዉ። ያኔ ከተማዋ ችግር ላይ ነበረች። እንደዚያም ሆኖ ግን ከፊታቸዉ፣ ከሁኔታቸዉ ያየሁት ፍቅርንና ደስታን ነበር።

አሰመራን ሳስበ፣ የአስመራን ሕዝብ ሳስብ፣ ያኔ ወርቃማ ዩኒፎርም ለብሰዉ የማስተምራቸዉን፣ ያዳምጡኝና ሳስረዳቸዉ ፊቴን ያዩ የነበሩትን የባርካ ተማሪዎችን አስታወሳለሁ። እርግጥ ነዉ ብዙ የሚያሳዝኑ ነገሮች በአስመራ አይቻለሁ። እርግጥ ነዉ ከተማዋ ያኔ መለስተኛ ጦር ግንባር ነበረች። እርግጥ ነዉ በየጊዜዉ ሳይታሰብ በሻቢያ የሚተኮስ መድፍ ባልተጠበቀ ቦታ ያርፍ ስለነበረ ብዙ ሰዎች አልቀዋል። እርግጥ ነዉ በደርግ ወታደሮች የተሰሩ ብዙ ግፎች ነበሩ። ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ፣ የሕዝቡ ፍቅር አሸንፎኝ ነዉ የጦር መሳሪያ በተሸከመ የጦር አይሮፕላን፣ መሳሪያ ላይ ተቀምጬ ከተማዋን የለቀኩት።

አሁንም ለአስመራ ትልቅ ፍቅር አለኝ። አሁንም አሰመራን ከአዲስ አበባ ቀጥሎ እንደከተማዬ ነዉ የማያት። አሁንም ያንን ሕዝብ እንደ ሕዝቤ ነዉ የማየዉ። አሁንም ኤርትራዉያንን ከተቀረዉ ኢትዮጵያዊ እንደተለዩ ተደርጎ ሲታይ አያስደስተኝም። በዚህም ምክንያት ነዉ የኤርትራን መገንጠል አጥብቄ የተቃወምኩት። አሁንም የምቃወመዉ። ለዚህም ነዉ ከመረብ ደቡብ ይኖሩ የነበሩ ወደ ኤርትራ ፣ ከመረብ ሰሜን ይኖሩ የነበሩ ደግሞ ከኤርትራ በግፍ እንዲባረሩ መደረጉ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነዉ የምለዉ። ለዚህ ነዉ የባድመ ጦርነት የወንድማማቾች የርስ በርስ ጦርነት እንጂ ከዉጭ ኃይላት ጋር የሚደረግ ጦርነት አይደለም የምለዉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ መንቃት አለበት። የኢሕአዴግ መንግስት በባድመ ጦርነት እንዳደረገው አሁንም ኢትዮጵያዉያንን ለመገበር እየተዘጋጀ ያለ ይመስላል። በኦሮሚያ፣ በጎንደር በመሳሰሉት ቦታዎች እንዳየነው፣ ህዝባችን በኢሕአዴግ ታጣቂዎች የሚታረደዉና የሚገደለው አንሶ፣ እንደገና ከሻእቢያ ጋር በሚደረግ ጦርነት የሚማገድበት ምንም ምክንያት የለም። በመሆኑም ለኢሕአዴግ የጦርነት ጡሩምባ ጆሮዉን ይደፍን ዘንድ እመክራለሁ። ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለአገርና ለሕዝብ አስባለሁ፣ ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት እቆማለሁ የሚል ከሆነ፣ አገር ማለት መሬቱ ሳይሆን ህዝቡ ነውና ህዝብን መጀመሪያ ያክብር።

በሌላ በኩል ለዴሞክራሲ ቆመናል እያሉ፣ አለም በወንጀለኛነት የሚፈለገው የአረመኔው የኢሳያስ አፈወርቂን አገዛዝ መደገፍና እድሜዉንም ለማራዘም ደፋ ቀና ለሚሉ ተቃዋሚ ነን ባይዮችም ፣ መልእክት አለኝ። የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የሚቃወም፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሚነቀፍና በሻእቢያ የተዘጋጀ ፔቲሽኖችን ኢትዮጵያዉያን እንዲፈርሙ እንዳንድ እንደ ግንቦት ሰባት ያሉ ደርጅቶች የቅስቀሳ ዘመቻ መጀመራቸው በጣም የሚያሳፍር ነው። የሻእቢያ መንፈስ በአሁኑ ወቅት የኤርትራ ህዝብ ጠላት ነው። የሻእቢያ መንፈስ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው። የሰብዓዊነት ጠላት ነው። ከሻእቢያ ጎን በቆምን ቁጥር በሻእቢያ እጅ ለሚፈሱ ደሞች ሁሉ ተጠያቂ ነው የምንሆነው። በመሆኑም ከሻእቢያ ጋር የምናደረገውን ዳንኪራ በአስቸኳይ ማቆም አለብን።

የኢትዮጵያው እና የኤርትራው አምባሳደር በምን ተስማሙ? |ዜና ትንታኔ በታምሩ ገዳ (በምስልና ድምጽ)

$
0
0

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዲፕሎማቶች ኬኒያ ላይ ከሰሞኑ የድንበር ላይ ቁርቋሶ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜያት በግንባር በመገናኘት ስለ ውስጣዊ እና አካባቢያዊ ችግሮቻቸው በተመለከተ ከረር ያለ እና ከዲፕሎማቲክ ደረጃው የዘለለ የቃላት ልውውጥ አድርገዋል። ሁለቱ አምባሳደሮች በምን ጉዳይ ላይ ተሰማሙ? ሰሞነኛውን ጦርነትንስ ማን ጀመረው? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው ምንድን ነው? (የህብር ሬዲዮ ልዩ ጥንቅር) በታምሩ ገዳ


የኢትዮጵያው እና የኤርትራው አምባሳደር በምን ተስማሙ? | ዜና ትንታኔ በታምሩ ገዳ (በምስልና ድምጽ)

አሳዛኝ የመኪና አደጋ ወሎ ከመርሳ ከተማ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ |ይናገራል ፎቶው

$
0
0

በየቀኑ ዘ-ሐበሻ እንደምትዘግበው በኢትዮጵያ የሚደርሱ የመኪና አደጋዎች ለብዙ ንብረት እና ሕይወት መጥፋት ምክንያት እየሆነ ነው:: ይህ ከታች የምትመለከቱት ፎቶ ግራፍ የመጣው ከሃገር ቤት ነው:: እንደምትመለከቱት በሁለቱም ከባድ መኪናዎች ላይ አደጋ ደርሷል:: አደጋው የደረሰው ዛሬ ከቀትሩ 2 ሰዓት አካባቢ ወሎ ከመርሳ ከተማ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መንተላ አካባቢ ነው:: ከስፍራው የመጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት የሁለቱም መኪና ሹፌሮች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ናቸው:: ለጊዜው መጠኑ ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል::

ጋዜጠኞችን እና ተቃዋሚዎችን ለማሰር በ24 ሰዓት ውስጥ ህግ የሚያወጣው መንግስት ጫት እየቃሙ; መጠጥ እየነዱ ማሽከርከርን የሚያስቆም ሕግ መቼ ይሆን የሚያወጣው?

Photo


የቀድሞ አንድነት ም/ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ብሩ ቢርመጂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

$
0
0

Biru Bermijiየአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ፕሬዚዳንት የነበሩትአቶ ብሩ ቢርመጂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቶ ብሩ ዲሞክራሲና ፍትህ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ሲታገሉ የነበሩ፣ በ1997ዓ.ም ከሌሎች የትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ቅንጅትን ወክለው የተወካዮች ም/ቤት አባል በመሆን የበኩላቸውን የተወጡ፣ እንዲሁም አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሲመሰረትም ከመሥራቾቹ አንዱ በመሆን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ሆነው አገልግለዋል፡፡ አቶ ብሩ ቢርመጂ ለነፃነት ለፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን የበኩላቸውን ሲወጡ የነበሩ ጠንካራ ታጋይ ነበሩ፡፡ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለፍትህና ዲሞክራሲ ታጋይ ጉዋደኞቻቸው መጽናናትን ይስጣችሁ፡፡

የአቶ ብሩ ቢርመጅ የቀብር ስነስርዓት የሚፈፀመው ዛሬ ሰኔ 15/2008 ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መሆኑ መረጃው ለሌላቸው በማካፈል ተባበሩ፡፡ መኖሪያ ቤታቸው ገርጂ አካባቢ ወደ ፓርላማ ቤቶች መውረጃ በስተግራ በኩል በሚያስገበው መንገድ ሲሆን የቀበር ስዓቱም ዘጠኝ ሰዓት መሆኑ ከቤተሰቦች ተነግሯል፡፡ አስከሬኑ ከትግራይ ዛሬ ጠዋት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በረመዳን ወር የሕወሓት ሽብር –ሳዲቅ አህመድ ከጃዋር መሐመድ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ (ቪዲዮ)

$
0
0


በረመዳን ወር የሕወሓት ሽብር – ሳዲቅ አህመድ ከጃዋር መሐመድ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ (ቪዲዮ)
በረመዳን ወር የሕወሓት ሽብር –  ሳዲቅ አህመድ ከጃዋር መሐመድ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ (ቪዲዮ)

ሻሸመኔ ሕዝቡ የመረረ ተቃውሞውን አደባባይ ወጥቶ እያሰማ ነው –“የምሽት ግድያው ይቁም!”

$
0
0

shashemene 1

shashemene
(ዘ-ሐበሻ) በሻሸመኔ ከተማ በየዕለቱ ወጣቶች ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ የመገኘታቸው ዜና ያንገሸገሸው የሻሸመኔ ነዋሪ ዛሬ ብሶቱ ገንፍሎ ወጥቶ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ዋለ::

“በየምሽቱ እየተገደሉ የሚገኙት ወገኖቻችን ደም መፍሰሱ ይቁም” ሲሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የሻሸመኔ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን በአደባባይ ቢያሰሙም የፌደራል ፖሊስ እና አጋዚ ሕዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ ለመበተን ሞክረዋል::

በሻሸመኔ ማን እንደገደላቸው አይታወቅ እንጂ ከኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ጋር የሚገናኙ ወጣቶች ተገድለው እየተገኙ ነው:: ባለፈው ሳምንት ህዝቡ ለቀብር በወጣበት ወቅት በአደባባይ ተቃውሞውን ቢያሰማም ሰሚ አጥቶ እንደውም ግድያው እየተባባሰ መሄዱ ዛሬ ህዝቡ በአደባባይ ወጥቶ ብሶቱን እንዲያሰማ ምክንያት ሆኖታል::

በዛሬው ተቃውሞ ተማሪዎች እና ነዋሪው ሕዝብ በአንድ ላይ ወጥቷል::

በዛሬው የህዝብ ተቃውሞ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ዘ-ሐበሻ መረጃ ቢደርሳትም ስንት ሰው እንደተጎዳ ግን ለማረጋገጥ አልቻለችም::

አይሲስ ኢትዮጵያንን መግደሉን ለመቃውም ሰልፍ በመውጣቷ 6 ወር የተፈረደባት ሜሮን አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀለች

$
0
0

semayawi party

(ዘ-ሐበሻ) አይሲስ በሊቢያ ኢትዮጵያውያንን መግደሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ በመውጣት ‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች በሚል ተከሳ 6 ወር ተፈርዶባት የነበረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ሜሮን አለማየሁ አርበኞች ግንባርን በኤርትራ መቀላቀሏን አስታወቀች::

በአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ላይ ቀርባ ከአስመራ የሰማያዊ ፓርቲ አባልና የአዲስ አበባ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል ሀገር ቤትበነበረችበት ወቅት በሕወሓት መንግስት የደረሰባትን መከራ ያስረዳችው ሜሮን ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ያለው አማራጭ ቆርጦ ጫካ መግባትና ጠመንጃ መያዝ ነው ብላለች::

ሜሮን ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ያድምጡ

ዳግመኛ የመንግሥት ዋይታ በተቃዋሚዎች ላይ -ጣሰው አሰፋ)-

$
0
0
ግንቦት 7ን ለመቃወም ከውጭ የቆሙት የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችን እና የባለስልጣናት ዘመዶች

ግንቦት 7ን ለመቃወም ከውጭ የቆሙት የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችን እና የባለስልጣናት ዘመዶች

11 2016 በፍራንክፈርት ከተማ ላርበኞች ግነቦት7  የድጋፍ ማሰባሰቢያ (Fundraising) ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ስለነበር አንዳንድ ገጠመኞቼን በቦታው ላልነበሩ ለማሰማት የሚለው የዚህ ማስታወሻ መነሻዬ ነው። ዳሩ ግን፤  በሱ ላይ ትረካዬን ከመቀጠሌ በፊት፤ ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ፤ አንድ ከ 11 ዓመት በፊት የሆነና በ11.06. 2016 ከሆነው  ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነት የነበረው ድርጊትን ስላስታወስኩ እሱን ላስቀድም፤

 

ኖቬምበር 2005  ዓ.ም.  አንደኛ/ ኮማንደር መስከረም አታላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሊቀ-መንበር

ሁለተኛ/ አቶ ቱሃት ፖል ቻይ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር ሊቀመንበር፤ ወደጀርመን ሃገር መጥተው ስለኢ ትየጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ፤ ስለየድርጅቶቻቸውም አካሄድና እንዲሁም ሊደረግላቸው ስለሚፈልጉት ድጋፍ  ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ፐሮገራም ይዘጋጅላቸዋል፤ እነዚህን ሁለት ሰዎች ወደጀርመን አገር ጋብዘው ያስመጧቸው አቶ ከሳየ መርሻ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውጭ አካል የአመራር አባል ከሌሎች ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን ነበር።

 

ጉባዔው የተዘጋጀው ለኖቬምበር 18 . 2005 ሲሆን። ቦታው ከፍራንከፈረት ወጣ ያለች ሩሰልስሃይም የምትባል ትንሽ ከተማ ነች። ዕለቱ ቅዳሜ ነው፤ አዘጋጆች አዳራሹን ለመክፈት ወደ ስፍራው ይደርሳሉ፤ ስፍራው በፖሊስ ተወሯል። ምነው ሲባል፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ስብሰባ አድራጊዎቹ ጦርነት አውጀውብኝ ለዚያ ጦርነት ማራመጃ ገንዘብ ሊሰበስቡ የተዘጋጁ ናቸውና ስብሰባው እንዳይደረግ ይታገድልኝ ብሎ ስላመለከተ፤ ስብሰባው አይካሄድም ይላል ፖሊስ ነፍሴ፤

 

ልብ በሉ፤ ቀኑ የበዓል ቀን ነው አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፤ መስሪያ ቤት ሁሉ ዝግ ነው። በመሰረቱ ስብሰባው እንዳይደረግ ሲወሰን ለአዘጋጅዎቹ በቅድሚያ ማስታወቅ ሲገባ ፖሊስ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ብዙ የተደከመበትን ዝግጅት ሳይደረግ ቢቀር ለሚያደርሰው ኪሳራና ሌላም ጉዳት ማን ተጠያቂ እንደሚሆን ለማወቅ የሚቻል አልነበረም። ለተባለው ውንጀላም ይህን አሳማኝና ተጨባጭ መረጃ ባለመኖሩ፤ አራት ሰዓት የፈጀ ክርክረና ውጣ ውረድ ከተደረገ በዃላ አቶ ካሳዬ መረሻና ሌሎችም ባደረጉት ጥበብ የተሞላበት ደርድር  ፖሊስ በስብሰባው ላይ ተገኝቶ ውይይቱንና ሂደቱን ተከታትሎ መረጃውን ሊያሰባስብ እንደሚችል  ስምምነት ላይ ተደረሶ ከአራት ሰዓት መዘግየት በዃላ ስብሰባው እንዲጀመር ተደረገ። ፖሊስም ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁጭ ብሎ በአስተርጓሚ ከተከታተለ በሁዋላ ለቀረበው ውንጀላ ማዳበሪያ የሚሆን መረጃ የሚገኝ መስሎ ስላልታየው ጥሎን ወጣ፤ ስብሰባው ተካሄደ። የወያኔ መንግስት እንዳሰበውም ሳይሆን ቀረ።

 

እንደ ዕውነቱ ከሆነ፤ ጉባዔው በጥሩ ሁኔታ መካሄዱ ብቻ ሳይሆን፤ በተለይ አቶ ቱሃት ፖል ባደረጉት ሰፊ ንግግር ሲያጠቃልሉ፤ ያሉትን ብጠቅሰው ጥሩ መታሰቢያ ይሆነናል፤ “… ብሶት ተናጋሪዎች በመሆን ብቻ ተፈርጀን ታሪካዊ ሐገራችንና ሕዝባችንን በድቅድቅ የባርነት ጨለማና አዘቅጥ ውስጥ እንደምንከተው ተገንዝበን፤ ለወያኔ ዕድሜ ማጠር ከተፈለገ፤ ጠላትን ከህዝብ ነጥለን ለመምታት እንድንችል፤ በብሄረሰብ፤ በባሕል፤ በቋንቋ፤ በሃይማኖት፤ በጾታና በክልል የፈጠሩብንን ስነ-ልቦናዊ ችግሮች እርግፍ አድርገን በመተው፤ ብሔርተኝነትንና ትምክህተኝነትን ገድለን በመቅበር ወያኔ ሃገራችንና ህዝባችንን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ የባዕዳን ምንደኛ መሆኑን ተገንዝበን፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ በመተያየት ላለፉት 15 ዓመታት ወያኔ ለነሰነሰው መርዝ ሰለባ ሳንሆን፤ እጅ ለእጅ ተያይዝን የወያኔን ግብዓተ መሬት በሁለንተናዊ መለኩ በተቀነባበረ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ትግል በማፋጠን፤ በሱ ከርሰ-መቃብር ላይ አንድነቷና ሉአላዊነቷ የተከበረ፤ የግለሰቦች መብትና ነጻነት የተረጋገጠባት፤ የሁሉም ብሔር/ብሔረሰቦች የጋራ ቤት የሆንች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለተተኪው ትውልድ እናስረክበ!” ነበር ያሉትና፤ እንዳጋጣሚ ዛሬ ከ11 ዓመት በሁዋላም ይህንኑ እያልን እንደምንገኝ አስቡት።

 

በመጨረሻም ከተሰብሳቢው የገንዘብ ዕርዳታ ተሰብስቦ ለአቶ ቱሃት የተሰጠ ሲሆን፤ ውይይቱ ለወደፊቱም   መነቃቃትን የፈጠረ፤ ንቅናቄዎቹንም በቀጣይ ለመደገፍ የቀሰቀሰ አንደነበረና፤ ከዚያም በሁዋላ በጀርመን አገር ቀጣይ የሆነ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የሚሆን ፕሮጄክት ተነድፎ መንቀሳቀስ የሚቻልበትን ዘዴ ለመጀመር የሚያስችል ዘዴ ተቀይሶ ነበር። ዳሩ ግን አቶ ቱሃትም ከጀርመን  ከተመለሱ በሁዋላ ብዙም ሳይቆዩ ዱካቸው ይጠፋል፤ ኮማንደሩም እዚሁ ጀርመን አገር ቀርተው በችረቻሮ ንግድ ይተዳደራሉ የሚል ወሬ አለ። ስለዚያ ጉባዔ ሁኔታ ለማስታወስ ያህል ይህንን  አህል ካልኩ  በሁዋላ ወደ 11.06.2016 የፍራንክፈርቱ የአርበኞች ግንቦት7 ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ልመልሳችሁ፤

 

ይሄኛውም ስብሰባ ከ11 ዓመት በፊት እንደሆነው ለሁለተኛ ጊዜ የወያኔ መንግሥት ተቃውሞ ገጥሞታል። የተቃውሞው መንገድ ግን ከቀደመው የተለየ ነው። እንደሚመሰለኝ በቀደመው ሙከራ የተፈለገው ውጤት ባለመደረሱ አልተሞከረም፤ ወይም ጥያቄው በባለስልጣናቱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ፤ – ስለምክንያቱ መረጃ የለኝም –  ወይም ያ እርምጃ እንደጥፋት ተቆጥሮ እሱን መድገም አላስፈለገም። ጥፋት ስላለመድገም ጉዳይ ከተነሳ፤  መለስ በ2002 ዓ.ም. ምርጫ ጊዜ በ1997ቱ ምርጫ ሰለተፈጸመ ስህተት ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር ” ኢሕአዴገ? ዋና ልምዱ ጥፋቱን አይደግምም። በ97 ዓ.ም. ምርጫ የተፈጸመው ስህትት እንዳይደገም አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደረጓል” ብሎ ነበር። ፕሮፌሰር መስፍን ወያኔ “ገርበብ አድርጎ የከፈተውን በርግደን ገባን” እንዳሉት፤ መለስ ሲቀናጣ “እንከን የለሽ” እያለ ያሞካሸውንና ውጤቱ መርዝ እንደበላች ውሻ አቅለብልቦ ከሰውነት ወደ አውሬነት የለወጠውን ምርጫ ነበር እንደጥፋት ቆጥሮ አይደገምም ያለው። በርግጥም ታዲያ እንዳለውም ከዚያ በዃላ አልተደገመም። የሰውዬውን ሃቀኝነትም መጠራጠር አይቻልም።

 

በ11.06.2016ቱ ተቃውሞ በሰላማዊ ሰልፍ እንዲሆን ነበር የተደረገው። ወደ 15 የሚሆኑ ሰዎች ግንቦት7  የሻቢያ ተላላኪ ነው ከሚለው ያረጀውና ያፈጀው፤ እስከ ግንቦት7 የናት ጡት ነካሽ ነው እስከሚለው አዲስ መፈክር የተጠቃለሉ “ጥሩ ጥሩ” ቅሌት ያልበዛባቸው “የጨዋ” መፈክሮች ሲያሰሙ ውለዋል። ተሰላፊዎቹ አርበኞች ግንቦት7 የሚለውን ስም የሰሙ አይመስለኝም፤ ግንቦት7 ሲሉ ነበር የዋሉት፤ ግንቦት ሰባት ቴሬሪስት ነውና የጀርመን መንግስት እንዲከለክለው የሚልም ጥያቄ ነበር። ተሰላፊዎቹ በደንብ ማጥናት የነበረባቸውን ያሰጠኗቸው አልመሰለኝም። ምክንያቱም ኦባማም ግነቦት7ን ቴሬሪስት በልልን ተብሎ በወያኔ ተጠይቆ አይሆንም መባሉን አላወቁም።

 

ከዚህ በተረፈ ስለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ እንድተርክ ካደረጉኝ ምክንያቶች፤  እውጭ በሰላማዊ ሰልፉ ዙሪያ የተደረጉ የሃሳበ ልውውጦችና በአዳራሹ ውስጥ ስለዴሞንሰትሬሽኑ የተሰጡ አስተያየቶች/ትችቶች ነበሩ። ውጭ በሰልፉ አካባቢ በሰልፍ አድራጊዎቹና ከድጋፍ ማሰባሰቢያው ፐሮግራም ታዳሚዎች መካከል አንዳንድ ግለሰቦች መሃከል  በተደረገ  እንካ ስላንቲያ አንድ ያስደነቀኝ ነገር ነበር። አንዱ ያዳራሸ ፐሮግራም ታዳሚ  ተናድዶ እየጮኸ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል፤ ይህን ያየ ሌላ ያዳራሹ ፕሮግራም ተሳታፊ  ምን ሆነሃል? ምን ያስጮህሃል? ይለዋል “አንዴ! አንተ ደርግ ነህ አለኝ እኮ!” ሲለው፤ ታዲያ ይሄ ምን ያናድዳል? ምርቃት እኮ ነው። ታስታውሳለህ? በደርግ ጊዜ እኮ አንድ ነበርን። አሁን እኮ ተበጣጥሰን እኛና እነሱ እያልን ነው ሲል በጣም አስደነቀኝ። ከዚህ ሌላ ደግሞ፤ በአዳራሹ ውስጥ ስለሰልፉ ከተሰጡ አስተያየቶች/ትችቶች ከማስታውሳቸው፤-

 

ከአዘጋጂዎቹ መካከል አንዱ ” መንግሥት የተቃዋሚዎች ስብሰባን ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አደረገ ሲባል በጣም ያሰጋል፤ የጤና አይመስለኝም፤ ሲል ሌላው አከታትሎ ዱሮ እኮ እነሱ እውስጥ ሆነው እኛ ነበርን እውጭ ሆነን የምንጮኸው ይህ የሚና ልውውጥ ትልቅ ድል ነው ብለን እንወስደዋለን ይላል። ብርሃኑ ነጋም “እኔ ኖረዌይ ከተደረገልኝ ሰፊ አቀባበል የበለጠ  በአውሮፓ ሌላ ቦታ ይገጥመኛል ብዬ አላስብኩም ነበር፤ ፍራንክፈርት ግን ከዚያም አልፎ  ወያኔም ጭምር ተሰልፎ ተቀበለኝ” ያለው የሰልፉ በጎ ገጽታ ነበር። ያም ሆነ ይህ መንግሥት በተቃዋሚዎች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ከወጣ መጽሃፉ “መንግስተሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ” እንደሚለው ዓይነት መሆኑ ይሆን? ማን ያውቃል? ስለሰለፉ አበቃሁ።

 

አንዲት ሃሳብ ላክልና ሃሳቤን ልቋጭ፤ ባሁኑ ጊዜ በዲያስፖራው አካባቢ የማጤነው አንድ ነገር ስላለ ምናልባት ይህንን ግንዛቤዬን ለአንባብያን ላካፍል ብያለሁ፤ ይኸውም የሰዎች በፖለቲካ ድርጅቶች የስብሰባ ጥሪ ላይ በስፋት የመገኘትንና ያለመገኘትን በተመለከተ ነው። ባለፉት አምስት ዓመታት ለኢሳት ድጋፍ ተብለው በጀርመን አገር በተደረጉት ስብሰባዎች የሚገኘውን የህዝብ ብዛት በስፍራው በመገኘት ተከታትያለሁ። በጣም የሚያስደስት ነው። አንዳንዴ ወደሺ ሰው የሚያስተናግድ አዳራሽ ተይዞ በቦታ እጥረት ምክንያት የሚመለሱ ሰዎች እንዳሉ አይቻለሁ። ይህ ሚዲያን በሚመለከት ነው። በፖለቲካ ድርጅት በኩል ደግሞ፤ አርበኞች ግንቦት7 የሚባለው ስብስብ ከተፈጠረ ወዲህ ድርጅቱ በየቦታው በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ የሚገኘውን የተሳታፊ ብዛት ስመለከት በጣም ጉድ የሚባል ነው።

 

ታዲያም በዲያስፖራ የሚንቀሳቀሱ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ያሉትን ያህል፤ የሚያሰሙት ተደጋጋሚ እሮሮ “ስብሰባ ጠርተን ሰው አልመጣልንም፤” የሚል ነው። እንደኔ ሮሮ ብቻ እያሰሙ ከመኖር ለመላቀቅ እንደመፍትሄ ሊረዳ ይችላል የምለው፤ ከላይ እንደጠቀስኩት  እነዚህ ብዙ ህዝብ የሚያሰባስቡ ድርጅቶችን በመመርመር እኔ የሌለኝ ሌላው ያለው ምንድነው? እኔ ለምን ሕዝብን መሳብ አልቻልኩም? የህዝብን ጆሮ ለምን አላገኘሁም? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት እራስን መጠየቅ። ይህን የምልበትም ዋና ምክንያት ድርጅቶች ሁሉ ለሕዝብ ጥቅም የቆምን ነን ብለው የሚንቀሳቀሱ እስከሆነ ድረስ አንዱ ከሌላው ሊማር የሚችለው ነገር ካለና ለመማር ቢሞክር፤ በምንም መመዘኛ ወደ “ሲኦል” የሚያወርድ መንገድ እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ።

 

ሰፊ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ እየተገኙ ሁኔታዎችን በማጥናት ሕዝብ ምን እንደሚፈልግ ለመረዳት ሞመከር፤ ከዚህ ግንዛቤ በመነሳትም፤ “እንደኔ የጠራ አቋም፤ መርህና ፕሮግራም ያለው የለም በማለት ብቻ እራስን አንቱ ከማለት ወጣ ብሎ፤ ህዝብ ምን እንዲደረግለት እንደሚፈልግ፤ የልቡ ትርታ ወዴት እንደሚመታ ማዳመጥና ከዚያ ተነስቶ አቅጣጫንና ሰትራቴጂን አቃንቶ መሄድ። የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ደግሞ ልብ ብለን ካየነው፤ ተባበሩ፤ ተቀራረቡ፤ ተባብራችሁ ስሩ ለሚለውም ጩኸት ምላሽ ለመስጠት አመቺ አጋጣሚ ሊሆን የማይችልበት ምክንያት አይኖርም። ይህም ማለት ዞሮ ዞሮ ሁሉም ፊቱን ወደ አንድ የሕዝብ ፍላጎት አቅጣጫ  ካዞረ፤ ይህ ወደ አንድ አቅጣጫ የሚመለከት ሃይልም በመጨረሻ  የትብብርንና የአንደነትን መንገድ ከመከተል ሌላ አማራጭ ሊኖረው እንደማይችል ግልጽ ነው። ለጥንቃቄ ያህል፤ አርበኞች ግነቦት7 የትጥቅ አመጽ ጭምር የሚያከሂድ በመሆኑ፤ ከስሙ ጋር ንክኪ ያለው መልዕክት የትጥቅ ትግልን ለማይቃወሙ ብቻ ይሁን።

 

ጣሰው አሰፋ

ጀርመን

 

tassat@t-online.de

 

 

 

“የኤርትራ ባለሰልጣናት እንደ ወያኔዎች ዘራፊዎች አይደሉም”–ነአምን ዘለቀ |“ከመለስ ዜናዊ እኩል ሊጠየቁ ለሚገባቸው ጥብቅና አንቁም ” –ያሬድ ሃ/ማሪያም

$
0
0

“የኤርትራ ባለሰልጣናት እንደ ወያኔዎች ዘራፊዎች አይደሉም …ኢሳያስን እንመርጣለን ይላሉ ”አርበኛ ነአምን ዘለቀ
“ከሟቹ መለስ ዜናዊ እኩል ሊጠየቁ ለሚገባቸው ጥብቅና መቆም አይገባም ” የ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ሃ/ማሪያም

ከታምሩ ገዳ

የአለማቀፉ ማህበረሰብን እንደሚወክል የሚነገርለት የተመድ የሰብ አዊ መብት አጣሪ ቡደን የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ የተለያዩ ኢ-ሰብ አዊ የሆኑ ድርጊቶችን የፈጽማል ፣ከ400 ሺህ በላይ የአገሪው ዜጎች ለተለያዩ የመብት ረገጣዎች ተዳርገዋል በማለት ሰሞኑን ያወጣው ጠንካራ መግለጫን ተከተሎ በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች እና ኤርትራዊያኖች የፖለቲካ መሪዎች፣ የመብት ተሟጋቾች እና የማህበረሰብ ክፍሎች ጎራ በመለየት በጉዳዩ ዙሪያ እየተናረኩበት የገኛሉ ።
Neamen zeleke zehabesha
የሰብ አዊ መብት አጣሪ ቡደን ዳሰሳን ከተቃወሙት ወገኖች መካከል የአርበኞች ግንቦት 7 የውጪ ጉዳይ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ነአምን ዘለቀ አንዱ ሲሆኑ የድርጅታችው አባላት ሆኑ ሰላም ወዳድ ወገኖች በሙሉ በተመድ የሰበዊ መብት አጥኚ ቡደን በኤርትራ ላይ ያለውን አቋም እንዲቀየር አልያም አሊያም የቡድኑን ወሳኔን ኣንዲቃወሙ ደጋፉቸውን በፊርማ እንዲያረጋግጡ ጥሪ ማቀረባቸውን ተከተሎ ከ ዋሽንግተን ዲሲ በአማሪኛ ፕሮግራም ከሚተላለፈው የ አዲስ ድምጽ ራዲዩ ባለቤት እና አቅራቢ ከሆነው አርቲስት እና ጋዜጠኛ አበበ በለው ጋር ባለፈው ሰኔ 12/ 2016 እ ኤ አ ባደረጉት ዘለግ ያለ ቃለ ምልልስ ድርጅታቸው ከ አሰመራ መንግስት ጋር ለመቆም ሶስት ጉዳዮች እንዳሰገደዱት የገለጹ ሲሆን እነርሱም” ኤርትራ ውስጥ እነደ ማንኛውም አገር በተለይ ከ ኢትዮ -ኤርትራ የድንበር ላይ ጦርነቱ በሁዋላ ከብሄራዊ ደህንነት አኳያ የሰበእዊ መብት ችግሮች አሉ፣የፖለቲካ አስረኞች አሉ፣ በብዙ መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች አሉ፣ለኢትዮጵያ ህዝብ የምመኘውን ሁሉ ለኤርትራ ሕዝብም እንዲሁ እመኛለሁ፣ ነገር ግን የተመድ አጣሪ ቡደን በኤርትራ ላይ ያለው አቋም ትክክል አይደለም፣ባለሁለት ፍርጅ አቋም/ደብል ስታንዳረድ ነው/፣አጨቃጫቂም ነው ።” በማለት አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመቀጠለም ይህንኑ አቋማቸውን ሲያብራሩት”የወያኔ አገዛዝ በተለያዩ ጊዜያት በጋምቤላ ፣ በኦጋዴን ፣በኦሮሚያ እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ውስጥ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቻን ላይ እጅግ ዘግናኝ የሆነ የመብት ረገጣ ሲፈጽም የተለያዩ የሰበዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጽኑ ሲያወግዙት ይህ በኤርትራ ጉዳይ እንዲያጠና የተዋቀረው እና የመብት ረገጣን አጣራለሁ የሚለው አለማቀፍ አካል ግን በወያኔ መንግስት ሰለ ተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ እሰከ አሁን ድረስ አንድም ያለው ነገር የለም።በኤርትራ ውስጥ የሚካሄደው የመብት ረገጣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚካሄደው የመብት ረገጣ የከፋ አለመሆኑን እኔ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ከኤርትራ መንግስት የበለጠ የከፋ የመብት ረገጣ የሚያድረጉ አገሮች እያሉ በአስመራ መንግስት ላይ የህ አይነቱ ጫና የበረታው የኤርትራ መንግስት ለውጪ ሃይሎች አጎብዳጅ ስላልሆነ ነው” ያሉት እቶ ነአምን ዘለቀ ለአባባላችው ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ እውቁ የሰብዊ መብት ተሟጋች ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም በአንድ ወቅት አሜሪካ ውስጥ “የድሮው የኢትዮጵያ ኩራት የቀረው ኤርትራ ውስጥ ብቻ ነው ማለታቸው ይታወሰልኝ” በማለት ለራዲዮኑ አድማጮች ደጋግመው አስታውቀዋል ።

ወደ ኤርትራ ለሶስት ጊዚያት እንደ ተጓዙ እና በዚያም ለአምስት ወራት መቆየታቸውን በተናገሩት በአቶ ነአምን ዘለቀ እምነት “ኤርትራ ውስጥ የማህበራዊ ፍትህ/ሶሺያል ጀስቲስ አለ፣የኢኮነሜ ፍትህ/ ጀስቲስ አለ፣ ኤርትራ ውስጥ የአኩልነት ፍትህ አለ ፣የኤርትራ ባለሰልጣናት እንደ ወያኔ ባለሰልጣናት እነደሆኑት አነ ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በጉቦ የተጨማለቁ ሳይሆኑ በከረከሱ አሮጌ መኪናዎች የሚሄዱ እና ያለ አጃቢ ከህዝቡ መሃል በነጻነት በጎዳናዎች ላይ የሚጓዙ ናቸው።የኤርትራ ባለሰልጣንት በህዝቡ ጭንቅላት ላይ ሆነው የሚቀልዱ አይደሉም ፣ይልቁንም የህዝቡን ኑሮ የሚኖሩ ናቸው፣ በኤርትራ የሶሻል ጀስቲስ የምንላቸው እንደ ነጻ ህክምና እና የነጻ ትምህርት እድሎች አሉ። ይሁን እንጂ ገና ያልተሟሉ ነገሮችም አሉ። እንደ ነጻ ፕሬስ የመሳሰሉት በኤርትራ ውስጥ እንዲያብቡ እፈልጋሁ።” ያሉት የአርበኞች ግንባር እና የግንቦት ሰባቱ ከፍተኛ ሹሙ አቶ ነአምን በሶስተኛ ደረጃ እና ዋንኛ የደጋፍ ፊርማው አሰፈላጊነቱ ማሳመኛ ሃሳብ ብለው ያቀረቡት “ እኛ የዲሞክራሲ ሃይሎች ከኤርትራ በሰተቀር ወዳጅ የሚባል የለንም ፣ከዚህም አኳያ የኤርትራ መንግስት መዳከም ማለት የአኛ ሃይል መዳከም ማለት ነው። ይህንን የወያኔ ጨቋኝ ስርአትን ለመዋጋት የኤርትራ መንግስት እና ህዝብ የሚያደርጉለን ድጋፍ ከፍተኛ ነው። ” በማለት ድርጅታቸውም ሆነ ደጋፊዎቻቸው ለምን ከወቅቱ የአሰመራ መንግስት ጎን ሙሉ በሙሉ መቆም እንዳለባቸው ለማስረዳት ሞክረዋል ።

የአቶ ነአምን አስተያየትን በመለጠቅ ከጋዜጠኛ አበበ በለው የቀረበው ጥያቂ”በአርሶ አቀራረብ የተመድ የሰበዊ መብት አጣሪ ቡድን በኤርትራ ላይ ያካሄደው የምርመራ አካሄድ የሚመሰለው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር በማነጻጸር ይመሰላል ፣ከአቶ ኢሳያስ መንግስት ደጋፊዎች በቀር በውጪ የሚገኙ የአገሪው ተወላጆች አንዳቸውም አገዛዙን የማይቃወሙ ይመሰላል” ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ”እኔ ወደ ኤርትራ በሄድኩበት ወቅት በብሄራዊ ውትድርናው ሳቢያ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጉረመርሙ ተቃዋሚዎችን አነጋግሬለሁ። ነጻ ምርጫ ቢመጣ ማን ትመረጣላችሁ? ብዩ ሰጠይቃቸው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂን እንመርጣለን ምክንያቱም አቶ ኢሳያስ ሃቀኛ ሰው በመሆናቸው ነው የሚሉ ወገኖች አጋጥመውኛል። ይህን ሁሉ ስልህ ግን በኤርትራ ውስጥ ችግሮች የሉም እያልኩ አይደለም ።የተመድ አጣሪው ቡድን ግኝት የፖለቲካዊ አንደምታ ያለው ፣በተወሰኑ ወገኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ፣ገለልተኝነት የጎደለው እና ኤርትራን ኢላማ ያደረገ ነው።የወያኔ መንግስትን ጨምሮ ላለፉት 25 አመታት በብዙ ሺህ ዜጎችን የጨፈጨፈ ፣ ሳይጠየቅ እንዲያውም ድጋፍ እየተደርገለት ፣ውንጀላው ደሃ እና ትንሽ በሆነችው በኤርትራ መንግስት ላይ ብቻ ለምን ተነጣጠረ?። ያ ነው የእኔ ጥያቄ።” በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል።

አርቲስት እና ጋዜጠኛ አበበ በለውም ጥያቄውን መወርወሩን አላቆምም”የ ወያኔ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚያደረሰውን ጭቆና እና እረገጣን ሁላችንም 100% እናወግዛለን ፣እዚህ ላይ ችግሩ ግን ተመሳስይ በሆነ ጉዳይ/የመብት ረገጣ ላይ ለምን የተለየ አቋም ተያዘ?’’ ሲል ላቀረበው ጥያቄ አቶ ነአምን ሲመልሱ”ተመሳስይ ግፍ የሚባል ነገር የለም ። በኤርትራ ውስጥ እንደ አትዮጵያ የዘር ማጥፋት /የጂኖሳይድ ወንጀል አይፈጸምም ፣በኢትዮጵያ ደረጃ የሚካሄደው ግፍ እና በደል በኤርትራ ውስጥ እንደማይካሄዱ አስረግጪ ልነግርህ አችላለሁ ። በኤርትራ በነበርበት ወቅት አገዛዙን እንቃወማለን የሚሉትን ሳይቀር ቁጭ ብዩ ለመጠየቅ እድሉ ነበረኝ።ሰለ ኤርትራ የሚነገሩት ሁሉ የተጋነኑ ናቸው ።ይህን ውንጀላን በተመለከተ ወደ ኤርትራ የተጓዙ ፍርንጆቹ ሳይቀሩ እያረጋገጡት ነው ።”በማለት ለአሰመራ መንግስት ያላቸው የደጋፍ አቋማቸውን አጠናክረዋል።

የፊርማ ማሰባሰቡ ዘመቻን በተመለከተ ከጋዜዘጠኛ አበበ በለው በኩል በተጨማሪነት የቀረበው ጥያቄ “ በእናንተ ምልከታ የኤርትራ መንግስት ብቸኛው አጋራችሁ/ረዳታችሁ መሆኑን ስትናገሩ በተቃራኒው ደግሞ የኤርትራው አገዛዝ አንገሽግሾናል ፣መኖር አልቻልንም የሚሉ ወገኖች መኖራቸው የታወቃል። ታዲያ እናንተ የየትኛው ኤርትራዊ ደጋፍን ነው የምትሹት? ፡(አፍቃሪ አቶ ኢሳያስ ወይስ ጸረ አቶ ኢሳይስ ) አቋምን ይዛችሁ ነው አላማችሁን የምታሳኩት?”የሚል ጥያቂ ሰንዝሮላቸው ነበር ። የአቶ ነአምን ምላሽም”እኔ ኤርትራ ውስጥ ጉደሉ የሚባሉ ነገሮችን ሁሉ እንዲሟሉ እፈልጋለሁ፣ ነገር ግን አሁን በአጣሪው ቡደን እንደችግር ትደረጎ የቀረበው በፖለቲካዊ ስሜት የተሞላ ነው ። እንደ እኔ አመለካከት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰበዊ መብት ረገጣ ከኤርትራ የሰበዊ መብት ረገጣ ጋር በጭራሽ አይወዳደርም ነው ያልኩት ።” ሲሉ መልሰዋል። አሰጣ ገባው ተካሮ ጋዜ ጠኛ አበበም የሚከተለውን የጠይቃል “እኛ ለኢትዮጵያ ነጻነት የምንታገል ሃይሎች ‘ኤርትራ እንድትነካብን አንፈልግም ‘ከሚለው አቋማችሁ በተቃራኒው የሚገኙ ወገኖች ለሚያነሱት ‘ለዚህ ሁሉ ችግራችን መነሻው እና መደረሻው የአቶ ኢሳያስ መንግስት ነው ‘ለሚሉ ወገኖች ምላሾት ምድን ነው?”ሲል የጠይቃል ። አቶ ነአምን ዘለቀም ሲመልሱ”ኤአርትራ ትንሽ እና ደሃ አገር መሆኑዋ የታወቃል ።ለዚህ ሁሉ የደህነነት፣ ኢኮኖሚ ፣የችግሯ ዋንኛ መንሰኤው ደግሞ የወያኔ መንግስት ነው ፣ስለዚህ የወያኔ መንግስት ከተወገደ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ከመጣ ኤርትራ ውስጥ ያለው ችግር ይወገዳል፣ ሰጋቶችም ይቀንሳሉ ።” ብለዋል።
በአቶ ነአምን ተቃራኒ የቆሙት ደግሞ በአወሮፓ/ቤልጂየም ብራሰልስ የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብት ጉዳይ ተሟጋች ድርጅት መሰራች የሆኑት አቶ ያሬድ ሃ/ማሪያም ሲሆኑ አርሳቸውም ለተቃውሟቸው ምላሽ ሲሰጡ”የአርበኞች ግንቦት 7 ሃላፊዎች ጭምር የእውቁ ጥቁር አሜሪካዊው የመብት ተሟጋቹ የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ታዋቂው ጥቅሱን የጠቀማሉ ።እርሱም፦’በአንድ ቦታ የፍትህ መጓደል ማለት ፣ በሁሉም ቦታ የፍትህ መጓደል ማለት ነው’ ይሄ አባባል የወያኔ ስር አት በዜጎቻቸን ላይ የሚያደረሰውን በደል እና ግፍ የሁሉንም ሰላም ወዳድን ስሜት የቆረቁራል፣ይነካል ብለን አቤት የምንልበት አቀራረብ ነው ።በሌላ በኩል ደግሞ ኤርትራዊያን ወገኖቻቸን እየደረሰባቸው ያለውን በደል እና ሰቃይን በተመለከተ አለማቀፉ አጣሪ ቡደን ሪፖርት ሲያወጣ አቶ ነእምን ቀደም ሲል የሰጡትን አስተያየት ሰምቻለሁ ።ከኤርትራ መንግስት ጋር አብሮ/ተባብሮ መስራት አንደ ነገር ሲሆን ፣ለዚያ ስርአት/ለሻቢያ ጥብቅና መቆም ግን በአንድ ግለሰብ ላይ እንኳን ግፍ እና በደል ቢፈጸም ወንጀሉን ከፈጸመው ወገን ጎን እኩል የመቆም ያህል ሆኖ ነው የሚታየው ። የፖለቲካ ጥቅምን ማየት፣ መደራደረ፣ አብሮ መስራት እና አብሮ መታገል እንዳለ ሆኖ በደል በየትኛውም ስፍራ ይፈጸም ቢቻል በደልን መቃወም ተገቢ ነው ፣ካልሆነ ደግሞ በሌሎች አስገዳጅ ሁኔታዎች እንኳን ተይዘን ከሆነ ከበዳዮች ጎን መቆማችንን በሚያሳይ እና በሚያጋልጥ ሁኔታ፣ እንደ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አይነቱ በንጹሃኖች ደም እጁ ለተበላሸ ለኤርትራዊያኖች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩ ብዙ ምስቅልቅሎች ተጠያቂ ለሆነ ፣ ከሟቹ መለሰ ዜናዊ እኩል ለመጠየቅ ወደ ኋላ ለማይባልበት ሰው/ለአቶ ኢሳይስ አፈወርቂ /ጥብቅና መቆም እና ለእርሱ ሲባል ፊርማ ማሰባሰብ በእኔ ግምት ከሞራልም ሆነ ለፍትህ እንታገላለን ከሚል አካል የሚጠበቅ አይመሰለኝም።”በማለት የአቶ ነአምንን አሰተያየትን በጽኑ ተቃውመዋል።

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።


የተመድ አጥኚው ቡደን ገለልተኛነትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ያሬድ ከልምዳቸው መልሱ”ቡደኑን የሚዘውሩት አካላት የፖለቲካዊ ዘንባሌ፣የመቧደን ያለው አካል ለመሆኑ ጥርጥር የለውም።የአንድ አገርን ጉዳይ የማክረር ፣ የሌላው ወዳጅ አገርን ጉዳይ ችላ የማለት እና ኢፈተሃዊ የሆኑ መደጋገፎች ለመኖሩ በግላጭ ነው የሚታየው ።ከዚህ አኳያ አቶ ነአምን ያሉት ጉዳይ በጥቅሉ እወነታነት አለው ።’ኤርትራ ብቻ ነች ኢላማ የሆነቸው’ የሚለው የአቶ ነአምን አሰተያየት ግን ትክክል አይደለም ለምሳሌ ደ/ሱዳን፣ ሶሪያ ፣ ብሩንዲ፣ ሰሜን ኮሪያ ፣የመን፣ ጋዛ(ፍልስም) ፣ሲሪላንካ፣ሊቢያ፣ባህሪን የመሳሰሉት አገሮች ላይ ጥናት አድርጓል።ተፈጸሟልም ባለው የመብት ረገጣ ዙሪያ እርምጃ እንዲወሰድ ይጠየቃል። ከዚህ አኳያ ኤ ርትራ ብቸኛ አገር አይደለችም።ለምን ኢትዮጵያ ሳትወቀስ እንዴት በኤርትራ ላይ ብቻ ተነጣጠረ? ለሚለው ጥያቄ እርሱ እራሱን የቻለ ጉዳይ ነው ።

ኮሚሽኑ ዝም ብሎ ላጥና አይልም ከኢትዮጵያ የበለጠ እነ አሚንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሁማን ራይት ዎች የመሳሰሉት ጠንከር ያለ ሪፖርት ማወጣታቸውን ተከተሎ ነው ጥናቱ የተካሄደው ።ኢትዮጵያን በተመለከተ በጭላንጭልም ቢሆን ሰለ ጅምላ ጭፈጨፋዎች በተለያዩ ወገኖች ሪፖርት የሚቀርቡ ሲሆን ፣ኤርትራን በተመለከተ ግን ምንም አይነት መረጃ ከአሰመራ ለማግኘት በጭራሽ አይቻልም። አቶ ነአምን በተፈጠረላቸው አጋጣሚ ተጠቅመው የተወሰኑ ሰዎችን አነጋግረው ‘ሰላም ነው’ ተብለው ሊሆን ይችላል።በአጠቃላይ በአገሪቱ ሰላለው የሰበዊ መብት አያያዝ በተመለከት ግን 45ሺህ ኤርትራዊያኖችን ጨምሮ እነ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል አጣሪ ቡድን ይቋቋም በማለት ጥሪ ሲያሰሙ ቁይተዋል።አቶ ኢሳያስ ለምእራባዊያኖች ተገዢ ባለመሆናቸው ነው የተባለው ጉዳይ እውነታነት ሊኖረው ሊሆን ይቻላል ። ለማንኛውም በኤርትራ ላይ ያነበብነው ሪፖርቱ ወጥቷል።”ብለዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ሲሞቱ እነሰማለን ኤኢርትራ ውስጥ ግን ሞቱ የሚባል ዜና የለም ከዚህ አኳያ የአቶ ነአምን መከራከሪያ ትክክል ነው አያስብልም ወይ?ለሚለው የጋዜጠኛ አበበ ጥያቄ አቶ ያሬድ ሲመልሱ”ኢህ አዲግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት ከስድስት ሺህ በላይ ሰላማዊ ዜጎችን ግድሏል።ታዲይ በኢ ህ አዲግ ላይ ለምን ማጣራት አይደረግም ለሚለው ጥያቁ እና አጥኚ ቡደኑንን ለመፋለም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ እና ፈተና ነው ።አቶ ነአምን እንዳሉት ኮሚሽኑ ሁለት ገጽታ/ደብል ስታንዳርድ ሊኖረው ይችላል።ከኤርትራ በከፋ የመብት ረጋጮች ሊኖሩ ይችላሉ።አጣሪ ቡድኑ ያጣራል።እኛም በአመት ሁለቴ ወደ ኮሚሽኑ ዘንድ የምንሄድው ለዚህ ጉዳይ ነው አሁን የኤርትራ ህዝብ እሮሮ ያገኘውን ማላሽ የሚስተካከል ምላሽ ለማግኘት ነው ። ኢትዮጵያን በተምለከተ ኮሚሽኑ እንዲያጣራ እጥብቀን መጎትጎት፣በማስረጃ የተደገፈ ሰለሆነ ምን ትጠብቃላችሁ ማለት ነው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመብት ረገጣ ሳታጣሩ በኤርትራ ላይ የማጣራት መብት የላችሁም፣ እርምጃውም ወዳጃችን አቶ ኢሳያሰን አትንኩ እንደ ማለት ነው ።አባባሉም ውሃ የሚቋጥር ምክንያት አይደለም ። በኢትዮጵያዊያኖች ዘንድ በቡደን/ቲፎዞ ፖለቲካ ምትክ የመቻቻል እና የመመካከር ባህል ሊጠነክር ይገባል ።”በማለት እግረ መንገዳቸውን ጥሪ አቅርበዋል ።

በተያያዘ ዜና የተመድ የሰብ አዊ መብት አጣሪዎች/ፓናሊስቶች በኤርትራ የወቅቱ አገዛዝ ላይ ያወጡትን የመብት ረገጣ ሪፖርት በተመለከተ ሪፖርቱን የሚቃወሙ(የአቶ ኢሳያስ አገዛዝን የሚደግፉ) እና በተቃራኒው አገዛዙን የሚቃወሙ(የአጥኚ ቡድኑ ሪፖርቱን የሚደግፉ) ወደ ሰባት ሺህ የሚገመቱ ከ አውሮፓ፣ ከካናዳ እና ከአሜሪካ የመጡ ኤርትራዊያኖች በትላንትናው እለት ሰኔ 21, 2016 አኤ አ የተመድ የሰብአዊ መብት ዋና ጸ/ቤት በሚገኝበት ጄኔቫ/ሲውዘርላንድ ታላቅ የድጋፍ/የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደዋል።ለተቃውሞ ሰልፍ ከወጡት እና ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ነጋሽ ኦስማን የተባሉ ሰለፈኛ ለ አልጀዚራ ቴሌቪዥን በሰጡተ አስተያየት “ምንም እንኳን በኤርትራ ውስጥ ያለው የሰብ አዊ መብት ረገጣው ለእኛ እንግዳ ባይሆንም የአጣሪው ቡድን ሪፖርቱን በተመለከተ የአለም ሕዝብ አሮሮአችንን ያዳመጡን መሰሎ ነው የታየኝ።”በማለት ለ ኮሚሽኑ ድጋፋቸውን ሰጠተዋል። የደጋፍ ሰልፉን ለመቀላቀል ካታላቋ ብሪታኒያ ወደ ጄነቫ የተጓዙት ሰላም ኪዳኔ የተባሉአክቲቪስት በበኩላቸው “ኢርትራ ውስጥ ለተፈጸምው የሰብ አዊ መብት ረገጣ አገዛዙ ሊጠይቅ ይገባል።” ብለዋል።

በተቃራኒው ጎራ( የአሰመራ መንግስትን በመደገፍ) ከወጡት መካከል ራሄ ል ወ/አብ የተባሉት የስውዲ ን ነዋሪ” ኮሚሽኑ የተከተላቸው የቃለመጠይቅ ቲክኒኮች የተዛባ ነው።” በማለት ወግዛታቸውን አቅርበዋል።

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ባቀረበው መቃወሚያ ላይ አቃቤ ህግ መልስ ሰጥቷል

$
0
0

Negere-Ethiopia-edtor-Getachew-Assefa-300x200-300x2001.jpgከሽብር ቡድን አመራሮች ጋር በፌስቡክና በስልክ ግንኙነት በመፍጠር መረጃዎችን አስተላልፏል በሚል የሽብር ክስ የቀረበበት የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ሰኔ 1/2008 ዓ.ም ላቀረበው የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ መልስ ሰጥቷል፡፡
የፌደራል አቃቤ ህግ ዛሬ ሰኔ 15/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ በተከሳሹ የክስ መቃወሚያ ላይ ለተነሱ ነጥቦች በጽሁፍ መልሱን ለችሎቱ አስገብቷል፡፡

ጋዜጠኛ ጌታቸው አቃቤ ህግ ያቀረበበት ክስ ‹‹በማናቸውም መልኩ በሽብር ተግባር መሳተፍ›› የሚለው፣ አንድ ሽብርተኛ ተብሎ የተሰየመን ድርጅት ስም መጥራት፣ የሽብር ድርጅቱ በሚጠቀምበት ሚዲያ መጠቀም ወይም የሽብር ድርጅት አባል ነው የተባለን ሰው ለሽብር ድርጅቱ አንዳችም ፋይዳ በሌለው ነገር ላይ ማነጋገር ሁሉ ይጨምራል በሚል ተለጥጦ መቅረብ እንደሌለበት ላቀረበው መቃወሚያ፣ አቃቤ ህግ ድንጋጌውና የወንጀል ዝርዝሩ በሚመጣጠን መልኩ ክሱ ቀርቧል ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡ ስለሆነም መቃወሚያው በአግባቡ ያልቀረበ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግለት ጠይቋል፡፡

ተከሳሽ አቃቤ ህግ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለነበሩ ክስተቶች የሽብር ድርጅት አመራር ናቸው ላላቸው ሰዎች መረጃ ማስተላለፍን በሽብር ድርጅቱ ውስጥ በማናቸውም መልኩ መሳተፍ እንደሆነ አድርጎ ማቅረቡ ስህተት ብቻ ሳይሆን ከህጉ አላማም በእጅጉ የራቀ ነው፣ የህጋዊነት መርህንም የተከተለ አይደለም በሚል ላቀረበው መቃወሚያ፣ አቃቤ ህግ ክሱ የህጋዊነትን መርህ ባከበረ መልኩ የቀረበ መሆኑን በመጥቀስ የወንጀል ድርጊቱ በማስረጃ የሚረጋገጥ ይሆናል በማለት መቃወሚያው ውድቅ ይደረግልኝ ሲል አመልክቷል፡፡
አንድ ድርጊት ወንጀል ነው አይደለም የሚለው ፍ/ቤት ማስረጃ ከሰማ በኋላ የሚወሰን ስለመሆኑ ጥር 27/2007 ዓ.ም ፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ ውሳኔ መስጠቱን በማስታወስ የወንጀል ድርጊቱ ላይ የተነሳው መቃወሚያ ከማስረጃ መሰማት በፊት ሊነሳ የማይገባው ነጥብ ስለሆነ ውድቅ ይደረግልኝ ብሏል፡፡ አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕጉ አንቀጽ 111 እና 112 መሰረት አድርጎ ተሟልቶ መቅረቡንም በመልሱ ላይ ገልጹዋል፡፡

ተከሳሹ ከሽብር ቡድኑ ተልዕኮ እንደተቀበለ ከመጠቀሱ በቀር ተልዕኮው ምን እንደሆነ፣ መቼ፣ ከማን እና በምን አይነት መንገድ ተልዕኮውን እንደተቀበለ ከሳሽ ግልጽ አላደረገም በሚል ለጠቀሰው መቃወሚያ፣ አቃቤ ህግ ‹‹ተልዕኮ መቀበል ሲባል የሽብር ቡድኑ አላማን በመቀበል የድርጅቱን አላማ በማራመድ በመንግስት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ህብረተሰቡን ለማስፈራራትና የሀገሪቱን መሰረታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ህገ-መንግስታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ…ተቋማትን ለማናጋትና ለማፈራረስ በሚንቀሳቀስ የሽብር ቡድን ውስጥ በማናቸውም መልኩ መሳተፍ›› እንደሆነ ገልጾ የመቃወሚያው መቅረብ የህግ መሰረት የሌለው በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ ሲል አመልክቷል፡፡
አቃቤ ህግ በአጠቃላይ ያቀረብኩት ክስ ህጉን መሰረት ያደረገና የክስ ዝረዝርና የህግ ድንጋጌውን ባጣጣመና በተገቢው መንገድ የቀረበ ስለሆነ በከሳሽ በኩል የቀረበው መቃወሚያ ውድቅ ተደርጎ ክርክራችንን እንድንቀጥል ሲል ጠይቋል፡፡

ችሎቱ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ላይ አቃቤ ህግ የሰጠውን መልስ አገናዝቦ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 8/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዛሬው የችሎት ውሎ 14ኛ ወንጀል ችሎት ቦታው በሙሉ በተከሳሾች ተይዟል በሚል ችሎቱን ለመታደም የቻለ የለም፡፡


ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተመለከተ ለእንግሊዝ መንግስት ስትሰጥ የነበረው መረጃ የተሳሳተ እንደነበር ተገለጸ

$
0
0

ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008)

andargachew Tisgeየኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ለብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሳሳተ መረጃ ሲሰጡ እንደነበር ዛሬ ረቡዕ የወጣ መረጃ አመለከተ።

ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አንዳርጋቸው ጽጌን ለመርዳት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ የብሪታኒያ ባለስልጣናትን ላይ እንቅፋት ሆኖ እንደቆየና፣ በሰውየው መለቀቅ ጉዳይ ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አጋልጧል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የት እንደታሰሩ ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩና የቆንስላ ጉብኝቶችን ጨምሮ ለመታሰራቸው መሰረታዊ የህግ አግባብነት ያላቸውን ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ሪፕሪቭ በመግለጫው አትቷል። የብሪታኒያው የውጭ ጉዳይ ሚስተር ፊሊፕ ሃመንድ አቻቸው የሆኑት የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም መሰረታዊ ጥያቄዎቻቸውን እንኳን በተደጋጋሚ ለመመለስ ባለመፈለጋቸውን ሲማረሩ እንደነበር መገለጹ ተመልክቷል።

በተመሳሳይ ሁኔታም የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያለቀለት በመሆኑ ጠበቃ እንደማያስልፈልጋቸው ለብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጻቸው ተመልክቷል።

የሪፕሪቭ ሪፖርት እንደተመለከተው፣ አቶ አንዳርጋቸው በታሰሩበት በሁለት የሰቆቃ አመታት፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል የገቧቸውን ነገሮች ሁሉ በተደጋጋሚ ሲያጥፉ እንደነበር ገልጿል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህግ መብት እንደሚጠበቅላቸው በቅርቡ ቃል የተገባላቸው ፊሊፕ ሃምንድ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ሰቆቃ ከማባባስ/ከማስረዘም ባለፈው ምንም መፍትሄ አያመጡም ሲሉ የሪፕሪቭ ዳይሬክተር የሆኑት ማያ ፎዓ መናገራቸው ተገልጿል።

ህጋዊው ሲኖዶስና ማህበረ ቅዱሳን –ዘማርያም

$
0
0

abune bernabasአክራሪ እስልምና የኢትዮጲያ ክርስትና አስቸጋሪው ፈተና በሚል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያቀረበው ሰፊ ማብራሪያ  በዩቲዩብ ሺዲዮ ለሁላችንም እይታ ቀርቧል ።እዛው ሀገራችን መሬት ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ስለሚዘረዝር ሁላችንም ብናዳምጠው ተገቢ ነው።ቢያንስ ከአስር አመት በፊት መምህር ልኡለቃል የግብፅ ጳጳሳት እስላማዊ ከሆነው የግብፅ መንግስት የተለያየ ጫና ምክንያት በይማኖታችን ላይ የነበራቸውን አሉታዊ ተፅእኖ በምሳሌነት ክርስትያናዊ ያልሆኑ መፅሃፍት በቤተክርስትያናችን መግባትን ጠቅሶ ያስተማረውን ዲን ዳንኤል ሌላ ከዚህ በፊት ያልሰማነውን ምሳሌ ማለትም ሰባት መስኪዶች ስላሰሩት በኢትዮጲያ የግብፅ ጳጳስ በማንሳት ይጀምራል።ቀጥሎም ስለ ኢትዮጲያዊቷ የመሃመድ ሞግዚት ስለ በረካ ፣ስለ ቢላል ፣ስለ ኢትዮጲያዊው ንጉሰ ነገስት አርማህ ወይም ነጋሲ፣ ስለ ሳውዲ ስደተኞችና ስለ እስልምናው ሀዲት ፣ስለ ፖለቲካ እስልምና ወይንም እስልምና ከሃይማኖት ይልቅ ለፖለቲካ ሀያልነት ጥቅም መዋል ይገልፃል።ዳር አልሂያንና ዳር አርቢእስላም የሚሉትን አመለካከቶች ይነካካና የእስልምናን መስፋፋትና የኢትዮጲያን ማእከላው መንግስት መዳከም መሃመድ ግራኝ ወረራና የነበሩትንም የግራኝ ደጋፊ አረብ መንግስታት አጣቅሶ ያብራራል።በኦርቶዶክሳውያን መሃከል የፀጋና ቅባት የሚል ክርክርና ልዩነት ምክንያት ህዝቡ በዘመነ መሳፍንት ሲታመስ ጥንተ ክርስትያን ህዝቦች በእስልምናና ፖርቱጋሎችም ባመጡት ካቶሊካው እምነት ጭምር መዋጣቸውን ያብራራል፣ ከዛም እስልምና በሀገራችን እንዴት እንደተስፋፋና ክርስትያኖችም ሃይማኖታቸውን  ለመጠበቅ እንዴት ይታገሉ እንደነበር፣ የመሃዲስቶችን ጥፋት፣የሱፊ እስልምናን በጎ ገፅታና ከክርስትያኑ ጋር የነበረውን ህብረት አጣቅሶ ወደ አሁኑ የእስልምና ፀባያት ይሸጋገራል።ቀጥሎም የሃረር ሰው የሆኑት ሼህ የሱፍ አብዱልራህማን ረጅሙን ጉዞ መጀመር አለብን ብለው ተነስተው አሁን በአለም አቀፍ ደረጃ የወሀቢው እስልምናና ባሁን ሰአት ያሉት አሸባሪ ድርጅቶች ሁሉ የበላይ መሪ መሆናቸውን፣ ኢትዮጲያዊው ሌላው የሃረሩ ሼክ አብደላ ኢብን መሃመድ ኢብን የሱፍ ደግሞ የወሃቢውን ሀይልና ክረት ያለው አስተምህሮ ተቃዋሚና የሱኒን አስተምሮ የሚያራምደው የአልሃበሹ መሪ መሆናቸውንና አስገራሚው የሁለቱም አስተምህሮ መሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጲያውያን መሆናቸውን ይጠቅስና ወሃቢዝም ባሁን ጊዜ ምን እየሰራ ነው ብሎ ይጠይቃል።

ወሃቢዝም የኢትዮጲያ ክርስትና አስቸጋሪው ፈተና ነው ብሎ ከደመደመ በሁዋላ የወሃቢዎችንም እንቅስቃሴ በሀገር ውስጣና ከኢትዮጲያ ውጪ ብሎ በሁለት ይከፍላል፣ውጪ ሀገራት ተምረው እነደሚመጡ፣ የኢትዮጲያን ጠላቶች ሁሉ እንደሚደግፉ ፣የአል ኢትሃድን እንቅስቃሴ ይጠቅሳል፣ ንጉሰ ነገስት አርማህ ወይም ነጋሲ እስላም ነበረ የሚለውና የግራኝ መሀመድን ዘመቻ በኢትዮጲያ እስልምናን ለሚያስፋፉ አይነተኛ መሳሪያዎች መሆናቸውን ይጠቅሳል፣ ከዛ የእስላም ፍርድ ቤቶች ህብረት በሱማሌ እና ሀገራችን ውስጥ ስለነበረ የክርስትያኖች ጭፍጨፋ ግንኙነት፣ ወሃቢዝም በሃገራችን ስለፈጠረው ችግር ማለትም የክርስትያኖችና የእስላሞች የአብሮነቱ ስሜት መጥፋት መነሻ መሆኑን፣እስላሞች በእድር ሰርግ ንግድ ስራ ወዘተ ከክርስትያኖች መነጠል እንዳለባቸው እንደሚያስተምሩ፣በሃይል ክርስትያኖችን እንደሚያሰልሙ፣ክርስትያኖችን እንድሚገደሉና እንደሚደፈሩ፣ ቤተ ክርስትያናት እንደሚቃጠሉ ፣ጃራ አላ እስላሚያ በአሰቦት ገዳም አሰራ ሰባት መነኮሳት ማረዱ ፣በአርሲ ኮፈሌ ወረዳ በክርስትያኖች ላይ ስለተፈፀመ ግድያና ዝርፊያ ፣ሙስሊም አክራሪዎች ማናቸውንም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳይ ለሃሳባቸው ማራመጃ እንደሚጠቀሙ ለምሳሌ ክርስትያኖች ቅንጅት ናቸው ብለው ድብዳባ ዝርፊያ የጩቤ ውጊያ እንደፈፀሙ፣በአጋሮ ስለነበረ ጭፍጨፋ ይጠቅሳል፣የኦርቶዶክስና የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያናት መስቀል እየተነሳ ጨረቃ መሰቀሉን ይዘግባል፣ሻሽ ያደረገ ካህን መደብደቡ፣ዲያቆናት በግድ መስለማቸውና ቁራን እንዲያነቡ መደረጉ፣ሌላ ስድስት ዲያቆናት መገደላቸው፣አብያተ ክርስትያናት መቃጠላቸውና መዘረፋቸው፣ታቦታት ላይ ድንጋይ መወርወሩ ፣የገበሬዎች ክምር መቃጠሉ ፣በአንዳንድ ቦታዎች ክርስትያኖች ላይ ከሚደርሰው ጭቆና ብዛት ሁላችንም ከምንሰልም በሚል ከየቤቱ አንድ እንድ ልጅ እንዲሰልም መደረጉ ወዘተ ወዘተ በሚያስገርም ሁኔታ ይዘረዝራል።

ቀጥሎም በሀገራችን ውስጥ ያለውን የመስኪዶች መበራከት አሀዝ እየጠቀሰ ያብራራል።ከ1984-1987 ብቻ ኢትዮጲያ ውስጥ አምስት መቶ መስኪዶች መሰራታቸውን፣በመዲናችን በአዲስ አበባ 160 መስኪዶች ሲኖሩ 114 ቤተክርስትያኖች ብቻ መኖራቸውን። በአንፃሩ የኦርቶዶክሱ ቁጥር በመዲናችን 86 በመቶ ሲሆን የእስላሙ ግን 12 በመቶ ብቻ መሆኑን፣በአዲስ አበባ ካሉት 160 መስኪዶች 114 ቱ የተሰሩት ባለፉት 14 አመታት መሆኑን ሃሳቡ ከቀረበበት ጀምሮ ማለት ነው፣ይህ ሁሉ እየተደረገላቸው ወሃብያዎች ተጨቁነናል እያሉ በየአረቡ አለም መጮሃቸው፣ጀጎል ግንብ ውስጥ 99 መስኪድ ሲኖር ያለው አንድ ብቻ ቤተክርስትያን መሆኑን፣ሆነ ብለው ክርስትያኖችን በሚያስቆጣ ሁኔታ የመስኪድ እንስራ ጥያቄ ማቅረባቸው ለምሳሌ በአክሱም፣ በጥምቀተ ባህር፣ በመስቀል አደባባይ ወይም በደሴ በሀገረ ስብከቱ ፊት ለፊት፣በህዝብ ቆጠራ ዙሪያ ስላለ ግብግብ፣ተጨቁነናል በሚል የወሃቢን እንቅስቃሴ የነፃ አውጪ ቅርፅ ለመስጠት የሚደረግ ጥረት መኖሩን ሁሉ ይዘረዝራል።

ለህዝብ ሰላምና ፍቅር የቆመ ማንም ኢትዮጲያዊ ክርስትያን ይሁን እስላም በፅንፈኛ እስልምና ተከታዮች ምክንያት ይህ ሁሉ መአትና መከራ  በክርስትያኖች ላይ መድረሱን ሲሰማ የማይቆጣ የማያዝን ፍትህን የማይሻና የማይገረም የለም።በቅርቡ በሊቢያ ከታረዱ ወንድሞቻችንጋ አብሮ የታረደውንም እስላም ኢትዮጲያዊ እናስብ።ክርስትያኖች በመሆናቸው ብቻ ለታረዱ ለተደፈሩ ለተደበደቡና ለተዘረፉ በሰማይ እግዚአብሄር ዋጋቸውን እንደሚከፍላቸው እናምናለን። ግን ለዚህ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ይዘት ላለው ትልቅ ችግር የኢትዮጲያን የአካባቢ ሀገራትንና የአለምን የሃይማኖት የታሪክ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ያገናዘበና የመጠነ ሀይማኖታዊ የምን እናድርግ አቅጣጫ በዛ ዲስኩር ለነበሩ እድምተኞች ብሎም የተቀዳውን ሃሳብ በተዘዋዋሪ ለምናደምጠው ኦርቶዶክሳውያን ሊያሳየን ነው ብዬ ስጠበቅ  ዲያቆኑ እጅግ በጣም  የተሳሳተ ብቻ ሳይሁን የኮሰሰና የሾርባ ማንኪያ እንኲዋን የማይሞላ ድምዳሜ ላይ መድረሱን ስመለከት እጅግ እጅግ በጣም በመገረም ነው።በቤተክርስትያናችን እንዴት የማህበር የቡድንተኝነት ስሜት የንኡስ ኦርቶዶክሳዊነት ወይም ፅንፈኛ ኦርቶዶክሳዊነት ይሄን ያህል አድጎ በድፍረት ሊገለፅ ቻለ።

ያሁሉ ሀተታ በህዝብ ላይ የደረሰ ስቃይና መከራ ተዘረዘረ ።ከዛ ሁሉ ኩርኮራ በሁዋላ ለዚህ ተጠያቂው ማነው ሲባል መቼም አስተሳሰባችን እንደመልካችን ዥንጉርጉር ነውና አንዱ ሞኝ አሜሪካኖችና አውሮፓውያን ክርስትያኖች ሆነው እኛ ኢትዮጲያዊያን ክርስትያኖችን ስላልጠበቁን ብሎ ተጣያቂ ናቸው ሊል ይችላል፣ ሌላው የነበረው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ስራውን በአግባቡ ቢሰራ ሊል ይችላል፣ሌላው መንግስቱ ሀይለማርያም ባይፈረጥጥ፣ ሌላው ተቃዋሚ ድርጅቶች ባይኖሩ ወይም ቢያሸንፉ ፣ቅንጅቶች ባይኖሩ ወዘተ ወዘተ ማለት ይቻላል። ስለሃገራችን የፖለቲካ አቅጣጫ እንዳለን ግንዛቤ ከቀረበወ ዝርዝር በዚህ ወይም በዚያ መሄድ ያለ ነው። ይህ እንግዲህ ፖለቲካ የሚባለው ነው።ሀገር ውስጥ ለታየ ችግር አንዱ መንግስትን ተጠያቂ ያደርጋል መንግስት ደግሞ ሊጠየቅ የማይገባበትን ምክንያት ይዘረዝራል። ያም ፖለቲካ ነው።በመላው አለም ያለውን የአሸባሪዎች እንቅስቃሴና የሚታዩትንም በህዝብ ላይ የሚደርሱ ልዩ ልዩ ጥቃቶች እንኳን ቤተ ክህነት የኢትዮጲያ መንግስትም ብቻውን የመመከት ብቃት አለው ብሎ የሚያምን የለም።ሌላው ቀርቶ እንደ አሜሪካም ያሉ ሀያላን  መንግስታት እንኳን ካለአለም መንግስታት ትብብር የማይፈታ ችግር መሆኑን አፅናዕት እየሰጡ ሲናገሩ እናዳምጣለን እናያለን።ዲያቆን ዳንኤል ፊደል የቆጠረ ስለሆነ ይህን እውነታ የማያውቅ ሆኖ አይደለም። ግን በዛ ሁሉ የህዝባችን ችግር ስቃይ መከራና የፈሰሰ ደም ለማህበረ ቅዱሳን ቡድናዊ አላማ መገልገያ መነገጃ ሊያደርገው አሰበ በህዝብ ደም በክርስትያኖች ደም ነግዶም ለማህበሩ ሊያተርፍ።ለማህበረ ቅዱሳንም ርካሸ ድርጅታዊ ትርፍም ሲል በዋናነተ ተጠያቂ ያደረገው ከሀገር ውጪ ያለውን ሲኖዶስ በውስጡ ያሉ አባቶችና ምእምናን ነው። ያንን ሁሉ በህዝባችን ላይ የደረሰ መቅሰፍት ዘርዝሮ ሲይበቃ በስተመጨረሻው ምን ይደረግ ይልና የሚከተለውን ሃሳብ በቁጭት ድምፅ  ያቀርባል።ብዙ ሃሳቦች አቅርቧል በዋናንት የቀረበው ግን የሚከተለው ነው። እንዲህም ሲል ይደመጣል

‘ዛሬ የሰነበት ትምህርት ቤት ወጣቶች መዝሙር ከመዘመር ንግስ ከማንገስ አመታዊ በአል ከማክበር ያለፈ ግዳጅ ያስፈልገናል ብሎ ያንንም በመጠኑ ያብራራና ዋና ኢላማው ላይ እንዲህ ብሎ ይተኩሳል የሚያሳዝነው ቤተክርስትያን አንድ ሆና የውጭ ጠላቶችን መመከት ሲገባት ገና የውስጥ ስራችንን አለመጨረሳችን ነው።የሃሰት ሲኖዶስ ተቋቁሞ መንጋ የማይጠብቁ ጳጳሳት ተሾመዋል ቤተክርስትያንን እያዳከመ ለውጭ ጠላት ያመቻቻል ብሎ ወደ ሌላ ጉዳዮች ይገባና ከመፍትሄም የወንጌል ስርጭትን አስመልክቶ አቋም ያላቸው ሰባክያን መሰማራት አለባቸው ይላል።’

ለማንኛውም ሙሉ ንግግሩን ሁላችንም እናዳምጠው ። ችግሩ አለም አቀፋዊ ይዘት ያለውን የህዝብን ሰላም የመጠበቅ ሃላፊነት ከአለም መንግስታትና ከኢትዮጲያ መንግስትም አውርዶ የሀይማኖት መሪዎች ላይ ከዛም ዘቅጦ ውጭ ያሉ አባቶች ራስ ላይ መጫኑ ነው።

ኢትዮጲያ ውስጥ አቡነ ጳውሎስና አቡነ ማትያስ ማቆም ያልቻሉት አለም አቀፋዊ ይዘት ያለው የወሃቢያን እንቅስቃሴ ከነበረ ወይም ካለ አቡነ መርቆርዮስ ከሃገር ባይወጡ ክርስትያኖች አንድ ሆነን ወሃቢያንን መካላከል እንችል ነበር የሚል የቂል ድምዳሜ ላይ ዲያቆኑ ሲደርስ እንዴት የኢንጂንርና የምሁራን ስብስብ ነን የሚለው ማህበረ ቅዱሳን ተው ይሄ ስህተት ነው ማለት አልቻለም።ቤተክርስትያን አንድ ሆና የውጭ ጠላቶችን መመከት ሲገባት ? ጉድ የሚያሰኝ ነው። አባቶች በአስተዳደር ተለያዩ እንጂ አሁን ማህበሩ መጥቶ ቤትክርስትያናትን ከማውኩ በፊትኮ ህዝቡ አንድ ላይ ነው። ጦርነት መጣ ቢባል ይተባበራል፣ ህዝብ ተራበ ቢባል አባቶች ሀገራችሁን ህዝባችሁን አግዙ እያሉ ሲያስተባብሩ ነው የምናየው። አቡነ ጳውሎስና አቡነ ማትያስም ቢሆኑ መስቀልን ብቻ የያዙ ካህናት የእስልምና አሸባሪዎችን ምን ማድረግ ይችሉ ነበር።ጦር ሰራዊት የላቸው፣የስላላ መረብ የላቸው፣ፖሊስን አያዙ ፣መሬት አይመሩ ፣ፍርድ ቤትን አይቆጣጠሩ ባለስልጣናትን አይሾሙ ወይም አይሽሩም።ዲያቆኑ መስሎ አዳሪ ስለሆነ እንጂ ድፍረቱ ካለውና ለገንዘብ ሳይሆን ለፍትህ የቆመ ከሆነ መክሰስ የነበረት መንግስትን ነበረ። እውነቱ የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚንስትሮችን እንተዋቸውና የአሜሪካና የአውሮፓ መሪዎችም የሚይዙትና የሚጨብጡት ጠፍቷቸዋል።ይኸው ፎሎሪዳ ውስጥ ሀምሳ አሜሪካውያን ተገደሉ ሌላ ሀምሳ ቆሰሉ፣ ፈረንሳይ የሆነውን አስብ ቤልጂም የሆነውን አስታውስ። የትኛው ሲኖዶሳቸው ስለተከፈለ ይሆን?  ምነው ምነው በዚህ ማህበር እንደዚህ ጭልጥ ያለ የመሃይምና የደደበ ሃሳብ ይዘራል።የደደብ ያልኩት ያን የተሳሳተ ሃሳብ ነው ዲያቆኑን አይደለም።የተሰደዱት አባቶች ታረዱ ካልካቸው ዲያቆናት ጎን ስለሃይማኖታቸው ሲሉ የተሰደዱ ተብለው የሚደመሩ ሰለባዎች እንጂ የችግሩ ፈጣሪ ተብለው ከዋሀቢያን ጋር የሚታዩ አይደሉም።ይህ ቀጥተኛው እውነት ሆኖ ሳለ በሰሜን አሜሪካና በአጠቃልይ በወጭ ሀገር የሚንቀሳቀሰው ማህበር አላማው ውጪ ያለውን ሲኖዶስ መምታትና ማጥፋት ስለሆነ ከሰማይ በታች ላለ ችግር ሁሉ እንዚህን እድሜ ጠገብ አባቶች ተጠያቂ ያደርጋል።ዲያቆኑ ከመወለዱ በፊት ጀምረው እግዚአብሄርንና ቤተ ክርስትያናችንን ያገለገሉና የሚያገለግሉ በእግዚአብሄር ፊት ሲወድቁና ሲነሱ ያሉ አባቶችን መስደብ ማዋረድና ማሳደድ ክርስትያኖችን ከምንም አደጋ አይጠብቅም አያስተባብርምም።ጭራሽ በታኝና ከፋፋይ አካሄድ እንጂ።

ዲያቆኑ ሊያመልጥ የማይችለው አንድ እውነታ አለ።ሲያዳምጡት የሃይማኖቱ ጉዳይ የቆጨውና የከነከነው፣ ባመነበት የበኩሉን አስተውፅኦ ለማድረግ የሚጥር ይመስላል ግን የሚሄድበት መንገድ ጭልጥ በሎ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን ድብቅ አላማ ያለውና ሰይጣናዊም ነው።ሰይጣን ሄዋንን እፀ በለስ እንድትበላ ሲነግራት ዋና አላማውን ደብቆ መሁኑን ቅዱስ መፅሃፍት ያሳዩናል። ስለዚህ ዲያቆኑ እውነተኛ ሰው ከሆነ የአስተሳሰብና የግንዛቤ ደረጃው በጣም ዝቅተኛ ነው ማለት ነው።የግንዛቤ ደረጃው ከፍ ያለ ከሆነ የትምህርት ደረጃውና ስብከቱም ላይ ቅዱሳን መጳህፍትንና ታሪክን እያገናዘበ ያስተማረባቸውን የዩቲዩብ ሺዲዮዎች ይህንን ይመሰክራሉና የሚያደርገውን በሚገባ ያውቃል።ስለዚህ በዚህ በህዝብ ደም ንግድ ውስጥ የገባው ሆን ብሎ በሰይጣናዊ ማህበርትኝነት ከፋፋይና የልዩነት መንፈስ ተሞልቶ የተዋህዶ ምእምናንን ሊበታትን ቤተክርስትያናችንን ሊያዳክም እየተጋ ያለ የሰይጣን ምንደኛ መተተኛና ጠንቋይ ደብተራ ነው ማለት ነው።

መንጋ የማይጠብቁ ጳጳሳት ማለት ደግሞ ምን ማለት ነው? በውጭ ያለው ኢትዮጲያዊ የእግዚአብሄር መንጋ አይደለም ማለት ነው?በውጭ ያለው ኢትዮጲያዊ ምእምን መንጋ ካልሆነ ይህ ሁሉ የማህበሩ ሀሰተኛ ካህናት በአሜሪካና በአውሮፓ ምን ጉዳይ አላቸው ? እዛው ኢትዮጲያ አይቀመጡም? የክርስቶስ መንጋ መኖሩን እየካዱ በጎቹን አሁንም በኦሪት ህግ ከክርስቶስ እያራቁ ግን   የመነጋዎቹን የበጎቹን ቆዳ መግፈፍ  ብቻ- ዶላሩን ብቻ መሰብሰብ የሚፈልግ ማህበር በዚህ ክፍለ ዘመናችን ማየት ጉድ የሚያሰኝ ነው።አንድ መተተኛ ደብተራ ይሁን ምን ያልለየለተ ሀሰትን በማር አያላሰ እንደዚህ ካለእኩያው ሽቅብ እየተንጠራራ ታላላቅ ካህናትን ለመስደብና ለመወረፍ ሲቅበዘበዝ ምን ይባላል። እዚህ ሀገረ አሜሪካ ካለው ሲኖዶስና ጳጳሳቱ በእድሜ በቤተ እግዚአብሄር ግልጋሎትና በእውቀት ደረጃ የሚመጣጠኑት ኢትዮጲያ ያሉት ጳጳሳት ደፍረው ያላሉትን ይህን ሁሉ ወደላይ ተንጠራርቶ ካለእኩያው እንዲሳደብና ለኦርቶዶክሳውያን እስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የጦርነት የክተት ዘመቻ ፕላን ለማውጣትና መለከት ለመንፋት ለአንድ ደብተራ ስልጣን የሰጠው ማነው? ይህ ነው የማህበረ ቅዱሳን አላማ ?ዲያቆኑ በውጪ ያለውን ሲኖዶስ የሃሰት ሲኖዶስ ያለው በቤተክርስትያን ቀኖና ሳይሆን የግሉ ወይንም የማህበሩ የፖለቲካ አመለካከትና አቋም መሆኑን ከማሳየት ሌላ ምንም ፍሬ የለውም።

አንድ ሁለተኛ ዲግሪ አለው የሚባል ሰው ልክ ዝሆንን በማይክሮስኮፕ እንደሚያይ ለደረሰው አለም አቀፋዊ የአሸባሪዎች አደጋ በውጪ ያለውን ሲኖዶስ እንዴት እንደ ችግር ፈጣሪ ወይንም እንደ ችግር ፈቺ ይመለከታል? ‘አንድ ሆና የውጭ ጠላቶችን መመከት ሲገባት’ ምን ማለት ነው? ኦርቶዶክሳዊ የጦር ሃይል እስላም ወንድሞቻችንን የሚገድል ሃይል እናቋቁም እያልከን ነው?  አቡነ በርናባስ የቀድሞው አባ ወልደተንሳይ ባሁኑ ዘመን ከማንም በላይ ኦርቶዶክሳዊ እምነትን በትምህርት ከሃሳውያን የመከቱ በሀፄ ገላውድዮስ ጊዜ አባቶች ያዘጋጁልን መንፍሳዊ የጦር መሳርያ ማለት ጦርና ጋሻ ሳይሆን ትክክለኛው ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት መሆኑን ሲያስተምሩ አላዳመጥክም? እሳቸውንም ተሃድሶ ብላችሗቸዋል አለም ቅንአቱን ሃይማኖት ያለብሳታል አሉ ይባላል ሃፄ ሀይለስላሴ ።በቅናትና በምቀኝነት ተነሳስታችሁ። እናንተ የምትፈልጉት ግን አቋም ያላቸው መምህራን ነው – ትርጓሜ ለማህበሩ ያደረ ። ለመሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ሀይማኖታዊ ድርጅት ነው ወይስ ፖለቲካዊ ድርጅት? የክርስቶስ ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን መከራ ይህ ድርጅት ማቆም እችላለሁ ካለ በእውን አባለቱ መፅሀፍ ቅዱስን አንብበዋል ብሎ መጠየቅ ተገቢ አይሆንምን? ግብፆች በግድ ሰለሙ ሮማውያን ባለማገዛቸው። ይህ የታሪክ ሳይንሳዊ ትንታኔ ሊሆን ይችላል ።ግን አንድ ዲያቆን ይህንን እንደ አማኒ ሁሉ ነገር ከእግዚአብሄር ፍቃድ ውጪ የሆነ ነገር አለመኖሩ ላይ ማተኮር የለበትምን? መንግስታት ምንም ይሁኑ ምን ህዝቦች በሰሙት ከፍርድ እንደማያመልጡ ያለንበትም የኢንፎርሜሽን ዘመን ወንጌልን ለመላው አለም በየቤቱና በየጓዳው አያደረሰ እንደሆነ። የቄሳርን ለቄሳር ነውና የክርስትያኖች ውጊያ ከፖለቲካዊው ሃይማኖት ራቅ ቅዱስ መፅሃፋችንን ጠበቅ አይደለምን? ንፁህ እምነታችንን ትታችሁ ወደ ፖለቲካ ቅልውጥና ማሀበረ ቅዱሳን የሚል በውሃቢያ አምሳያ ፅንፈኛ ኦርቶዶክሳዊ ቡድን ሴክት ማቁዋቁዋም ለምን አስፈለገ? በኦርቶዶክስ ስር ሆነው የራሳቸውን እምነተ መፃህፍት የሚፅፉ፣በየትኛውም ሲኖዶስ ሳይታይ በራሱ ኤዲቶርያል ቦርድ ኦርቶዶክሳዊ እምነትን የሚደነግግ፣ የራሱ ደሞዝተኛ ካህናት ያሉት፣የማህበረ ቅዱሳን ታማኝ ያልሆኑ የኦርቶዶክስ አብያት ክርስትያናትን እንደ ተራ ጠጅ ቤት የሚመለከት ምእምን ያለው የምናያቸው የአውደ ምህረት ብጥብጦች ምስክር ስለሆኑ፣ በቤተክርስትያን ውስጥ የሚደረግ ፍትሃትን ረግጠው የሚወጡ ፣ ምንም አይንት ፍቅር ልባቸው ውስጥ የማይታይ ፣ቃሉ ያልገባቸው፣ሰዎችን አፍቅሩ እየተባሉ የጥላቻና የፀብ አምበሎችን ማሰማራት፣ልክ እንደወሀብያን ከነሱ ባመለካከት ለተለየ የሰው ልጅ ፍቅር የሌላቸው፣ልክ እንደ ወሃቢዎች የራሳቸው የተለየ የነጠላ አጠማጠምና አለባበስ በመጠቀም ከሌላው ኦርቶዶክሳዊ መለየታቸውን በመላው አሜሪካና አውሮፓ በግልፅና በድፍረት የሚያሳዩ  ፅንፍኛ የባለጌዎች ማህበር መፍጠር ለምን አስፈለገ።

ድሮ የየሰፈሩ መሃይም ጉልበተኛ እየተሰበሰበ የማርያም ጠላት እያለ በድንጋይ ተከሳሽን በመውገር ኦሪታዊውን ስርአት ይፈፅም ነበር።አልፎ አልፎም ትክክለኛውን የተዋህዶ እምነት ለማስተማር የሞከሩ በነዚሁ አላዋቂ ሀይላት ተወግረዋል።ይሄ የአዲስ ኪዳን ወንጌል በቅጡ ያልገባው ኦሪታዊ ስብስብ አሁን በዘመነ መልኩ ማህበረ ምን በሚል ስም የተደራጀ የተሳዳቢና የባለጌ ቡድን ፍቅር፣ ይቅርታ ፣ህብረት ወዘተ የሚሉት የአዲስ ኪዳን ቃሎች በዞሩበተ አልዞረም። የሚመገበው ጥላቻና በለው ነው። ወሃብያን ገደሉን ስለዚህ ኦርቶዶክሳውያን ተባብረን እንመክት። ጉድ ነው። በማህበረ ቅዱሳን ስር ሌላ የጦር ሃይል ለማቋቋም ነው እቅዱ። ይህን ክርስትያናዊ ጦር ለማቋቋም እንቅፋቱ ደግሞ ተጠያቂው አሜሪካ ያለው ሲኖዶስ ነው ።ይህ ሲኖዶስ ሳይጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም ምክንያቱም የጦር ሃይል ለማቋቋም ኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን የተዋህዶ አማኝ በአንድ ማሰባሰብ ውጪ ባለው ሲኖዶስ ምክንያት አልቻልንም። ይህ ጉድ አያሰኝም? ዘቅጠን ዘቅጠን እዚህ ደረጃ መድረሳችን? አባቶች ይጥፋ ይውደሙ። ሰይጣናዊ የኮሚኒስቶች መፈክር።የማህበሩን ብልግና በአሜሪካ በአውሮፓና በደቡብ አፍሪካ በሺዲዮና በአይኔም አይቻለሁ። ኢትዮጲያ ውስጥ ደግሞ ድብደባና ግድያ ሁሉ ይህ ማህበረ በሀይማኖት ስም እንደፈፀመ ይነገራል። ጌታችንን ያገዘ መስሎት ሃዋርያው ሰይፉን ሲያነሳ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ምን አለ።አስትውሉ የማህበሩ አባላት።እኛ ክርስትያኖች እኛ የተዋህዶ አማኞች የምናምልከው አምላክ ደካማ አይደለም ።የኛን እርዳታ አይፈልግም።ሂዱ ጦር አቋቁሙ አላለም።ደካማ አምላክ የሚያመልኩ ደካማ አምላካቸውን ለማገዝ ሌሎችን ይገላሉ ይሳደባሉ ያሳድዳሉ ይቅርታ የሚባል ነገር ከቶውኑ አያውቁም። ለኛ ለተዋህዶ አማኞች ፖለቲካዊ ኦርቶዶክስ ወይንም ፅንፈኛ ኦርቶዶክሳዊ ሚሊሽያ አያስፈልገንም። እግዚአብሄር እራሱ የቄሳርን ለቄሳር ያለውን አስተውሉ።ህዝብን ከአሸባሪዎች መከላከል የመንግስታት ስራ ነው። አለዝያ ነገሩ ሆሉ ውሻ ምን አገባሽ ከእርሻ ይሆናል።

ግብፆቹ በሃገራቸው ከነበረባቸው የእስላማዊ መንግስት ተፅእኖ የተነሳ የራሳቸው ችግር ስለነበረባቸው እነሱ የኛ ቤተክርስትያን ላይ ያሳደሩትን አሉታዊ ተፅእኖ መረዳት ይገባናል። ይህ ሌላ ራእይ ነው። ከነሱም አልፈን የግሪክ የህንድና ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን አብያት ክርስትያናትን ተሞክሮ በተለይ የኦርየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናትን ተሞክሮ እያጣጣምን መሄድም ተገቢ ነው።ይህን ከግንዛቤ ወስደው ትክክለኛና ቀጥተኛውን ጥንካራ ኦርቶዶክሳዊና ወንጌላዊ ትምህርት የሚያስተምሩ ቤተክርስትያናችንን በትምህርት ከተሃድሶና ከመናፍቃን እንድንመክት የሚያስተምሩ የሚደክሙ አባቶችን ተሃድሶ እያሉ መሳደብ ጥቅሙ ምንድን ነው።ይህን ያህል ሲኖዶሱን በድፍረት የጎንደሬ ሲኖዶስ እያሉ መሳደብ ከምን የመጣ ነው።ጎንደሬ ባለመሆኑ ሹመት የተከለከለ ካለ ንገሩን።እውነታው ማህበሩ እንደመሳሪያ እያቀያየረ ከሚያራግባቸው ሰንካላ ምክንያቶች አንዱ መሆኑ እንጂ ከሲኖዶስ ውስጥ ጎንደሬ ባለመሆኑ ሹመት የተከለከለ ፈፅሞ የለም።በምእራቡ አለም በተለይ በአሜሪካ በከፍተኛ ሁኔታ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት እየተስፋፋ የአሜሪካውያኑ የኦርቶዶክስ አማኝ ቁጥር እየጨመረ ለምንድን ነው ባለፉት አስርት አምታት ብቻ ስድስት ሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጲያዊ ኦርቶዶክስ ወደ ጴንጤነት ተቀይሯል የሚል ዜና የምንሰማው?  ለምንድነው? ለምንድነው? ለምንድነው? ወሃብያን ናቸው ስድስት ሚሊዮኑን ኦርቶዶክሳውያንን ጴንጤ ያደረጉዋቸው? ጴንጤዎቹ ወይንም ምእራባውያኑ ዶላር ከፍለዋቸው ነው? ከምር ይህን ነው እውነት ብለን የምናምነው? በመጀመሪያ እኛ ማድረግ የሚገባንን በትክክል እያደረግን ነውን።እንዴት አንድ ካህን ከቤትክርስትያናችን ወጥቶ ጴንጤ ቤትክርስትያን ውስጥ ቆሞ ክርስቶስን እሰብካለሁ ሲል ይደምጣል። ቤተክርስትያናችን ክርስቶስን መስበክ ትከለክላለች እንዴ። ትክክለኛውን ኦርቶዶክሳዊውን የወንጌል ትምህርት በየቤተክርስትያናችን መምህራኖቻችን በጥልቀት ያስተምራሉን። ወደ ውጪ ጣትን ከመቀተር ወደ ውስጥ መመልከት የበለጠ ጠቃሚ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም።ደብተራው ግን የሚፈልገው አቋም ያላቸው መምህራን – ትርጓሜ ኦሪታዊ የማህበሩ ካህናት ፣ነገር ስለማህበር አባልነት መስበክ እንጂ በድፍረት ወንጌልን በመስበከ ክርስቶስን በመስበክ የማይታሙ።

እንኩዋንም ዘንቦብሸ እንዲያውም ጤዛ ነሸ እንዲሉ የኛ ካህናት በፊትም ተሃድሶ መናፍቃን ወዘተ የሚባሉትን መርዛም ስሞች በመፍራት ከወንጌሉ እንደሚርቁ እናውቃለን።ወንጌል አሁን ያለውን ቅርፅ እንዲኖረው ያደረገች ጥንታዊት ሀዋርያዊት ቤተክርስትያን ውስጥ ቁጭ ብለው ወንጌል የጴንጤ ነው አይነት የሚያስቡ። አሁን ጭራሸ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ የተሳዳቢ ሃይል ተፈጥሮ እንዴት ነው ካህናቱ በድፍረት ወንጌሉን የሚያስተምሩት።አሁንማ ትምህርቱም ይቅርና ማህበረ ቅዱሳን የሆነና ያልሆነ የሚል አተካራ ገብቶ ቤተክርስትያን እየተበጠበጠ ስለሆነ ምእምናኑ ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እያለ ነው። ትምህርቱም ቀርቶብን እሁድ ጠዋትን በሰላም ፀልየን ቤታችን በሰላም በተመለስን በሚል።ታድያ የተዋህዶ አማኞች ዋና የልዩነት አውራዎች መገልገያ የሆነው ማህበረ ቅዱሳን ገና የኦሪታዊውን የአሳማና የግርዘት ጉዳይ ያልተረዳ ቡድን እንዴት አድርጎ ነው ወደ አፍሪካና ሌላው አህጉር የክርስትያን ሃዋርያ ስለመሆን የሚያወራው።ዲያቆን ዳንኤል ካቶሊካዊ አስተምህሮ ቤተክርስትያናችን ውስጥ እንዲቆይ ቤተክርስትያናችን ከኦርየንታል ኦርቶዶክስ እንድትነጠል አባ ማትያስን ያሳሳተ መሆኑን እየሰማን ነው።ሌላው የማህበረ ቅዱሳን ሰው በዘው ሃበሻ በተባለው ድህረ ገፅ በድፍረት ሀዋርያው ጳውሎስ ተሳስቷል ማለት መፅሀፍ ቅዱስ ስህተት አለው ይለንና የአቡነ በርናባስ ወይም የቀድሞው የአባ ወልደተንሳይ ስህተት መፅሃፍ ቅዱስ መሳሳቱን ልብ አለማለታቸው ነው ይለናል።ይህ እንግዲህ የመጀመሪያው ተሃድሶ በወንጌል ውስጥ ያለው ሀዋርያው ጳውሎስ ሆነ ማለት ነው።በዛውም ፅሁፍ በማህበረ ቅዱሳን እምነት ወንጌል ሁለት ነች ለቅድመ ኦሪት አማኞችና ለሌሎች የተለያየ ትርጓሜ ያላት። ጉድ ነው።ጎረቤታችን ኬንያውያኖቹን  ሄደህ ብትጠይቃቸው አሁንም የኦሪት አማኞች እንመስላቸዋለን። ቢያንስ ቢያንስ ያንን 66 ጎዶሎውን መፅሀፋቸውን አንብበውታል።ታድያ አሁንም ኦሪታዊውን እምነት አዝለህ እንደ እንግሊዝ ወይም ፈረንሳይ ኮሎኒያሊስቶች ጠመንጃ ሳትሸከም ወይም በቅጡ ትክክለኛውና ቀጥተኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ላይ ሳትቆም በዚያም ኢትዮጲያዊውን ኦርቶዶክስ አንድ ሳታደርግ ከባህል እንቁልልጬ በስተቀር የሃገራት ስነ ልቦና የሚገባህ ከሆነ ታሪካችን ባህላችን ብለህ ሌላውን አፍሪካዊ መስበክ የምትችለው መስቀል ሳይሆን እንዳልኩህ ጠመንጃ ከተሸከምክ ብቻ ነው። የማህበሩ መሪዎች የሚሆነውንና የማይሆነውን ያውቁታል ።ግን ፕሮፕጋንዳ ስለሆን አርቆ አላሚ ለመምሰል ለአባላቱ ሚዛን የማይደፋ ሀሳብ ያቀርባሉ። በመጀመሪይ ወንጌሉን ተረዱ። እምነታችንን በመንፈሳዊና በትክክለኛው ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንመክት።ወንጌሉን የእለት ተእለት ህይወታችሁ አርጉት። ያኔ ፍቅር ልባችሁ ውስጥ ሲገባ ፣ልዩነት ሲጠፋ ፣ሁላችንም አንድ ስንሆን፣ አባቶች ሲከበሩ የአፍሪካ ሃዋርያነቱ ይታሰብበታል።

አለም ሁሉ የተረዳው የአሸባሪዎችን ጥቃት መከላከል የመንግስታት ስራ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ስራ አይደለም። የሃይማኖት ተቋማት በዚህ ጉዳይ ጦር አቋቁመው ከተንቀሳቀሱ ውጤቱ እጅግ ዘግናኝ የደም መፋሰስ በሃገራችን ማምጣት ብቻ ነው።በዚህ ፍልሚያ የሀይማኖት ተቋማት የመንግስታት አጋር መሆን አለባቸው። ከእስተምህሮዋቸው ውስጥ እንደደብተራ ዳንኤል ያሉ ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ  ግለሰቦች እንዳይኖሩ በመጠንቀቅና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ለመንግስት አካላት በመጠቆም።ካለ እስላም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ትብብር አሸባሪነትን መዋጋት አይቻልም።እኛ ኢትዮጲያ ውስጥ ከእስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንጋ በሰላም መኖራችን በግብፅ ለሚኖሩ በቁጥር አናሳ ኦርቶዶክሳውያን ሰላምና ደህንነት ዋስትና መሆኑን ማህበሩ የተረዳ አይመስልም። ቤተክርስትያን አንድ ሆና የውጭ ጠላቶችን መመከት ሲገባት ማለትህ አልሸባብንና አልኢትሃድን የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የጦር ሃይል ወይንም የሚሊሽያ ሃይል አዘጋጅታ ትዋጋ ማለትና ለዚህም ልዩ የጦር ሃይል መመስረት ውጪ ያለው ሲኖዶስ ችግር ፈጥሯል ማለትህ የሚያሳያው የማህበረ ቅዱሳን አመራርና አላማው ምን ያህል ፀረ ኦርቶዶክሳዊ ብቻ ሳይሆን ፅንፈኛ ፀረ ሰላም መሆኑን ብቻ ነው።በሁለቱ ሲኖዶሶች መሃከል እርቅ እንዳይወርድ አጥበቆ የሚሰራው ያንተው ማህበር መሆኑን እናውቃለንና ስለአንድነት አትስበከን ።ያ ያንተ ወይም የማህበርህ መክሊት አይደለም።ሀይማኖታችንን በጠንካራ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ከሃሳውያን የመከቱ አባቶች ይከበሩ።

ለጊዜው የእግዚአበሄርን መንጋ እየበተናችሁ የመንጋውን የበጎቹን ቆዳ ገፎ መብላቱን ማለትም ዶላር መሰብሰቡን ቀጥላችሁበታል ግን በወገኖቻችን ደም መንገዱን አቁም ደብተራው ።ከአባቶቻችን እራስ ውረድ።

ወስብሃት ለእግዚአብሄር

ዘማርያም

 

ተያያዥ ጉዳዮች

  1. አስገራሚው የአቡነ መቆርዮስ የኢሳት ቃለ መጠይቅ ይህ ህጋዊ ሆኖ በአሜሪካ የተቋቋመው ማህበረ ቅዱሳን የተባለ ስብስብ አባላቱን በየቤተክርስትያናቱ አስርጎ ያስገባል ወይም የቤተክርስትያን አባላትን ለማህበሩ ይመለምላል።አባላቱ በቂ ናቸው ሲል ብጥብጥ በማስነሳት መፈንቅለ ሲኖዶስ ያደርጋል። ከዛም ስደት ላይ ባለው ቤተክርስትያናት ስር ያሉ ካህናትን ለማህበሩ ካልተንበረከኩ ያባርርና አቋም አላቸው የሚላቸውን ማለት ኢትዮጲያ ካለው ሲኖዶስ በላይ ለማህበሩ ታዛዥ የሆኑ ልዩ የማህበረ ቅዱሳን ካህናትን ይቀጥርና መንግስትን ለማስደሰት እዚህ ቦታ ያለች የዲያስፖራ ቤተክርስትያን ሀገር ውስጥ ወዳለው ሲኖዶስ ተቀላቅላለች ብሎ ያውጃል። ልብ መባል ያለበት እዚህ እውጭ ሀገር ሲኖዶሶች የቤተክርስትያኖች ባለቤት አይደሉምና በፈለገው ቀን እንዚህን ቤተክርስትያናት አቋም አላቸው በሚላቸው ካህናቱና በአባላቱ ድጋፍ ቤተክርስትያንን ሀገር ውስጥ ካለውም ሲኖዶስ መነጠል ይችላል።በዚህ ስውር ደባ ምክንያት ውጪ ያለው ሲኖዶስ ማህበረ ቅዱሳንን ወራሪ ሃይል ብሎ አውግዞት በዚሁ አመት በማርች 4 2016 የማህበረ ካህናት ባለስምንት ነጥብ መግለጫ አውጥቷል።

ይህን የሲኖዶስ አቋም ደግፈን አባቶች አይሰደቡ በነፃነት መንፈሳዊ ስራቸውን ይስሩ እያልን የበኩላችንን ጥረት የምናደርግ ምእምናን አቡነ መቆርዮስ የስደተኛው ሲኖዶስ አባል ኢሳት ላይ ቀርበው ይህን ማህበር ሲያሞካሹ ስናደምጥ ከፍተኛ የመከዳት ስሜት ተሰምቶናል።የጠላቴ ጠላት የሚለውን ይዘው ከሆነ ማህበሩ በዋናነት በሃይማኖታችን ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት አልተመለከቱም ማለት ነው።ማህበሩ በዶግማና በቀኖና መሃከል ያለውን ልዩነት በማደብዘዝ ቀኖናን በየጊዜው በማሻሻል ቤተክርስትያናችን ጊዜውን የዋጀች እንድትሆን ህዝብና ሃይማኖታችን እንዲጣበቁ የሚጥር ሲኖዶስንና በስሩ ያሉ አባቶችን ይኽው ተሃድሶዎች እያለ በመሳደብ ቤተክርስትያን እንዳትጠናከር ቤተክርስትያን የባህል ባርያ እንድትሆንና የተዋህዶ አማኞች በዘላቂነት የፕሮቴስታንቶችና የካቶሊኮች ሲሳይ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል።የሲኖዶስ ሙሉ ስልጣን የሆነውን ለምሳሌ ቀኖናን ማሻሻልን በተሃድሶ መጣላችሁ ሰበብና በማህበሩ ረብሻ ስልጣንኑ ከሲኖዶስ ለመንጠቅ መሞከርና የመንግስት ተወካይ በሲኖዶስ አስገብቶ መንፈሳዊ ሳይሆን መንግስታዊ የሲኖዶስ ውሳኔዎች እንዲደረጉ ማድረግ ልዩነታቸው ምኑ ላይ ነው።ማህበረ ቅዱሳን ወይንም ዳንኤል ለሲኖዶስ ተሟጋች ሊሁኑ አይችሉም።ለምን ቢባል ማህበሩ ሲኖዶሳው ስላልሆነ ፣ሲኖዶስን አላሰራ በማለቱ ወይንም ሲኖዶስን ለመቆጣጠር እየሰራ ስለሆነ።

ተሃድሶ በእርግጥ አለ።ተሃድሶ ማለት የአምላካችንን ፍፁም ሰውነትና ፍፁም አምላክነት መካድ፣ሰማንያ አሀዱ መፅሀፍችንን አለመቀበል፣የቅዱሳን የፃድቃንና የሰማእታትን ተራዳኢነትና አማላጅነት መካድ፣የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ከነቢያትና ሌሎች ቅዱሳን በላይ ቅድስተ ቅዱሳንነትና ከፈጣሪ በታች መሆን አለመቀበል ፣የቤተክርስትያናችንን አእማደ ሚስጥራት መካድና ባጠቃላይ የቤተክርስትያናችንን ዶግማ አለመቀበል እንጂ ሲኖዶስ ቀኖናን ቢያሻሽል ወይንም ካህናትና ምእምናን በእኩይ ተግባሩ ምክንያት ለማህበረ ቅዱሳን አባልና ደጋፊ አንሆንም ማለታቸው በፍፁም ተሃድሶ አያደርጋቸውም።

  1. ከፕሮፌሰር መስፍን መጣ የተባለው ደብዳቤ

ይህ በመንግስት ድጋፍና በልዩ ልዩ ደባ የቤተክርስትያናችን የማህበራት ሞኖፖሊ የሆነው ብዙ ማህበራትን በመክሰስ በመወንጀልና የሃሰት ማስረጃዎችን ሁሉ በመጠቀም በማጥፋት በመብላትና በመዋጥ መሆኑ ይታወቃል።ታዲያ ለአትላንተ ሰአሊተ ማርያም ቤተክርስትያን አባለት ባሁን ሰአት እየተበተኑ ካሉ አሳፋሪ የማህበሩ ፕሮፖጋንዳዎች አንዱ ከፕሮፌሰር መስፍን ተፃፈ ተብሎ በኢሜይል የሚሰራጨው የሚከተለው መረጃ ሲሆን ፕሮፌሰሩ በእርግጥ የዚህ የፅንፈኛ ማህበር ሌላ የማናውቃቸው ሰባኪና አማካሪ ከሆኑ ከላይ በዋንው ፅሁፍ እንደተገለጠው በሀገራችን የሃይማኖት ጦርነት ለማነሳሳት አብረው እየሰሩ ከሆነ በታሪክ ተጠያቂ ላለመሆን እራሳቸውን ከዚህ ማህበር እንዲያገሉ መመከር አለባቸው።የመፅሀፍ ቅዱስ የተሞላው በልዩ ልዩ ስደቶች ስለሆነም ጭምር። ፖለቲካ ሲሆን ስደት ሌላ ትርጉም ሊኖረው ይችላል መፅሃፍ ቅዱስ ግን በብዙ የስደት ታሪኮች የተሞላ ነው። ለማንኛውም ደብዳቤው የሳቸው ካልሆነ ይህን የማህበረ ቅዱሳን እኩይ ተግባር ለህዝብ ግልፅ በማድረግ ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል።

________________________________________________________________________________________

ይድረስ ለስደተኞች ጳጳሳት ደጋፊዎች!

(ከፕ/ሮ መስፍን ወልደማርያም)

በመሠረቱ ስደት በምንም መልኩ አያምርም፤ አገርን ጥሎ ሄዶ በሰው አገር መሽጎ አገር አለኝ እያሉ በየአደባባዩ መጮህ ያሳፍራል፤ በተለይ ደግሞ መንኩሰናል፤ ለዚህ ዓለም ሞተናል፤ በእግዚአብሔር ሕግ እየተመራን የምንኖር መንፈሳዊ መሪዎች ነን ለሚሉ ሰዎች፣ በተለይ ደግሞ የአግዚአብሔርን ሕግ ለሕዝባችን ለማስተማር ግዴት አለብን ብለው የሚያምኑ ሰዎች፣ በተለይ የዚህ ዓለም ጣጣ ሚስት፣ ድስት፣ ጉልቻ፣ ልጆች የሌላቸው ሽማግሌዎች፣ ከሁሉም በላይ እዩልን-ስሙልን እያሉ መስቀል በግምባራቸው ላይ መስቀል በደረታቸው ላይ፣ መስቀል በቆባቸው ላይ ለጥፈው የመስቀሉ እውነተኛ መልእክት ከፍርሃት ነጻ መሆንና አለመሸሽ መሆኑን የማያምኑ ሰዎች ልክ እንደፖሊቲከኞቹ ሰውን ለማታለል አደባባይ ሲወጡ በልጅነታችን እንደምንለው እግዚአበሔር በቀዳዳ ያያችኋል በሏቸው፤ ጴጥሮስ ነው በሙቱ በቁማቸው የሞቱትን ደፍጥጦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት መሆኑን የምናምነው!

መስፍን ወልደ ማርያም ነኝ። (ሰኔ 12/2008)

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት

አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት

የሲኦል ደጆች አይችሏትም

ቤተክርስቲያን አ.ት.ታ.ደ.ስ.ም!

ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)

ለሌሎች እንዲዳረስ SHARE እና LIKE እንዲያደርጉ በሚጠፉትና በሚድኑት መሀል የክርስቶስ መአዛ በሆኑት በቅዱሳን ስም እንጠይቃለን!

ቤተክርስቲያን….

መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው

ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው

ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም

አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-ይቆየን።

____________________________________________________________

 

  1. በግሌ ከማህበሩ የምጠብቀው ምንድን ነው።

 

  1. ከሃይማኖተኛ ፅንፈኝነት እንዲርቅ ።እንደ ዳንኤል ያሉ ማህበሩን ወደፅንፈኝነት የሚወስዱ አመራሮችን ከተቻለ ማረም ካለዝያ ከማህበሩ ማግለል።ማንኛውም ሀይማኖት የራሱን እምነት ትክክለኛነት ማስተማር መብቱ ስለሆነ የተዋህዶን እምነት ማስተማር ፍፁም ትክክል ፍፁም ተገቢ ነው። ግን በምንም መልኩ ቢሆን የአንድን እምነት ተከታዮች በሌላ እምነት ተከታዮች ላይ ማነሳሳት ፅንፈኝነት ፣ አሸባሪነት ወይንም የሃይማኖት ጦርነት ማወጅ መሆኑን እንዲገነዘብ።

 

  1. ለቤተክርስትያናችን ከማህበረ ቅዱሳን የተለየ ግን ጥሩ ራእይ ያላቸው የተዋህዶ ልጆችም እንዳሉ መቀበልና ከኛ ወዲያ ላሳር ከሚል ግብዝነት በመታቀብ የሃሳብ መንሸራሸር እንዲኖር ማድረግ።

 

  • በስደት ላይ ያለውን ሲኖዶስና የሚሰጠውንም ማናቸውም ውሳኔዎች እንዲያከብር ከስድብና ከብልግና እንዲርቅ።ለሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅና መግባባት በዛም ለምእምናን ልዩነት ሳይሆን አንድነት ለሰላምና ለፍቅር ብቻ እንዲጥር።

 

  1. ስደት ላይ ያለውን ሲኖድስ የማይቀበል ከሆነ የማህበሩና የአባላቱ መብት ነውና ችግር የለውም። ግን በዚህ ህሳቤ ውስጥ ያሉ አባላቱና ደጋፊዎቹ በውጪው ሲኖዶስ ስር ካሉ ቤተክርስትያናት የውስጥ ጉዳይ እንዳይገቡ ወይም እንዲርቁ አባላቱን እንዲቆጣጠር ።ቤተክርስትያን ግን ለሁሉም ክፍት ነች።አንድ ህጋዊ ሆኖ በአሜሪካን ሀገር የተመዘገበ የረድኤት ማህበረ ሌላ ህጋዊ የረድኤት ማህበር ላይ ሲዘምትና ሲረብሽ ከህግ አንፃር ያለውን እንደምታ የህግ ባለሙያዎቻችን እንዲያስረዱን እንዲያስተምሩ  በዚሁ አጋጣሚ እጠይቃለሁ።

ይህ ሲሆን ሁላችንም የተዋህዶ ልጆች ማህበሩን እውነትም ማህበረ ቅዱሳን እንል ይሆናል።

 

 

የወያኔ ስርአት ዋነኛ የጀርባ አጥነት የብሔራዊ መረጃ በዘረፋና በሽሽት ተጠምዷል

$
0
0

Zehabesha-News.jpg

የልዑል ዓለሜ ዘገባ

እራሱን የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን እያለ የሚጠራዉ የወያኔ ስርአት ዋነኛ የጀርባ አጥነት የብሔራዊ መረጃ በዘረፋና በሽሽት ተጠምዷል።

በሰሞኑ ይኸው የብሔራዊ መረጃ 9 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የህወሃት የመረጃ ክንፍ ቀድሞ የሰየማቸዉንና በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዉ የነበሩ የሌላ ብሔር አባላቶችን በሙሉ መልሶ ወደ ሐገር ቤት በማስገባት በምትካቸዉ ከ 242 የሚጠጉ የአንድ ብሔር ብቻ ተወላጅ የሆኑ የመረጃ ሰራተኞችን እየተካ ይገኛል።

ጉዳዩን በትኩረት የተመለከቱት መረጃዎቻችን የመፍረስ ወይም የሽሽት መንፈስ እንዳለዉ የሚናገሩለት ይህ ዝዉዉር ድንገተኛና ያልተገመተ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ወጪ እየተደረገበት መሆኑ እጅግ እንዳሳሰባቸዉ ጠቅሰዉ እነዚህ ወደ ተለያየ ሐገር የሚላኩት የአንድ ብሔር የስለላ አባላቶች በትምህርት ፍቃድ ( Study Permit ) በንግድ ፍቃድ ( Business Permit ) በበቤተሰብ ጉብኝት ወይም ትስስር ፍቃድ ( Relation Permit ) በስራ ፍቃድ ( Work Permit ) በመንግስታዊ የስራ ወይም በዲፕሎማቲክ አገልግሎት ፍቃድ ( Diplomatic Travel documents ) ሲሆን በዋነኛነት የአሜሪካን ዋሺንግተን ዲሲ የአዉሮፓዎቹ ኖርዌይና ብሪታኒያ እንዲሁም የመሳሰሉት እና ደቡብ አፍሪካ አዉስትራሊያ የዝዉዉሩ ትኩረቶችእንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

የብሔራዊ መረጃ ከፍተኛ አመራሮች የህወሃት ባለስልጣን ቤተሰቦችና የትዳር ጓዶች ባጠቃላይ የተካተቱበት ይህ ሽሽት ወይም ዘረፋ ከዚህ ቀደም በሐገሪቷ ላይ ከታዩ አይን ያወጡ የዘረኝነት መንፈሶች ለየት ያለ እና እጅግ የተቻኮለ ሲሆን በተለያየ አለም ከሚገኙ የመረጃ ሰራተኞች ዉስጥ እስከ 23/06/2016 ወደ ሐገር ቤት እንዲመለሱ ከተጠሩት ዉስጥ በአብዛኛዉ እየተሰወሩ መሆኑና የመመለሻ ጊዜያቸዉም ማለፉን ታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

HIber Radio ጀዋር መሐመድ የሻሸመኔው ግድያ በሕወሓት የተቀነባበረ ነው አለ –የቀድሞው የአንድነት አመራሮች አዲስ ፓርቲ አልመሰረትንም አሉ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሰኔ 19  ቀን 2008 ፕሮግራም

 <...የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ በሁለቱም ፓርቲ አባላት  ሙሉ ድጋፍ የተቀበለው ለሴኔቱ ተመርቷል ይህ ሕግ ሆኖ ሲወታ የአሜሪካና የሕወሓትን ግንኙነት ይለውጣል። ይህ እንዲሆን ግን የተደረገው ስትራቴጂ..በእርግጠኝነት የምናገረው በወልቃይት፣በቅማንት ፣ለሱዳን በተሰጠው መሬት ሳቢአ የተገደሉት ንጹሃን ቁጥር በኦሮሚያ ተቃውሞውን ተከትሎ ከተገደሉት በእጥፍ ይበልታል።ይህን ግን ተከታትሎ በኦሮሚያ እንደተደረገው የእያንዳንዱ ሟች ብቻ ሳይሆን በተለይ የአካባቢው ፖሊስም ሆነ ልዩ ሔኢል በግድያ ሲሳተፍ የገዳዩ ማንነት ጭምር ቢወታ ኖሮ ከኦሮሚአው ጋር አንድ ላይ ማቀናጀት ይቻል ነበር ግን ያ አልሆነም። በአማራ የተፈጸመውን ግድያ ተከታትሎ የዘገበው የለም። ስራ አልተሰራም ይሄ ቢሰራ ኖሮ...> ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ  ከሰጠን  ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውንያዳምጡት)

በፍሎሪዳ የኢሚግሬሽን እስር ቤት ዛሬም የሚገኙ ወገኖቻችንን እንድረስላቸው  ቃለ መጠይቅ ከእስር ቤቱ ከወጣ ከአንዱ ጋር (ሙሉውን ያዳምጡት)

ሁለት ኩላሊቱን ያጣ ኢትዮጵአዊን ለመርዳት በቬጋስ የተጀመረ ወገን ለወገን ጥሪ

የአሜሪካ ፖለቲከኞችን ከማነታረክ እስከ ማፋጠጥ የሄደው ልዩ የሆነው የመሳሪያ ባለቤትነት መብትን የተቃወሙ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች ለሃአ አምስት ሰዓት የዘለቀ ተቃውሞና ውጤቱ ሲዳሰስ

በሕዝበ ውሳኔ ምክንያት ከአውሮፓ ሕብረት የወጣችው እንግሊዝ ከፍተኛ ተቃውሞና ድጋፍ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጠይቀዋል ልዩ ዘገባ

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

እስራኤል በኤርትራ ወታደራዊ ቤዝ እንደሌላት ተገለጸ

ጃዋር መሐመድ በሻሸመኔም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የሚደረገው ግድያ የሕወሓት የተቀነባበረ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ሴራ መሆኑን ገለጸ

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ እውነተና አመራሮች አዲስ ፓርቲ አልመሰረትንም አሉ

በስማችን አይነገድ ሲሉ ተቃውመዋል

የአማራ ወጣቶች ከሕወሃት ጥቃት ራሳቸውን አደራጅተው እንዲከላከሉ ጥሪ ቀረበ

የዛምቢያ መንግስት የ19 ኢትዮጵያውአን ስደተኞችን አስከሬን የኢትዮጵያ መንግስት ካልወሰደ በአገሬ እቀብራለሁ አለ

ለኢትዮጵያ የተለገሰ 68 ሚሊዮን ኮንደም ደረጃውን ባለመጠበቁ እንዲጣል ተጠየቀ

እና  ሌሎችም  ዜናዎች አሉን

የዛራና ቻንድራ ጉዳይ: “ፆተኝነት”* (sexism) ውስጤ ነው

$
0
0

(በፍቃዱ ሀይሉ፣ Weyeyet Magazine)

ምናልባት ራሴን “ውስጥ ውስጡን ፌሚኒስት ነኝ” እያልኩ ስገልጽ ሰምታችሁ ታውቁ ይሆናል። እውነት ነው። ነገር ግን ፆተኛም ነኝ።

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

‘ዛራ እና ቻንድራ’ በቃና ቲቪ እየታየ ያለ ተከታታይ ፊልም ነው። አልከታተለውም፤ ግን ርዕሱ ላይ የተጠቀሱት ሰዎች የተፋቃሪ ጥንዶች ሥሞች መሆናቸው ግልጽ ነው። እናም፣ በተደጋጋሚ ቻንድራን የሚለውን ሥም የሴቷ፣ ዛራ የሚለውን ደግሞ የወንዱ ሥም አድርጌ ስወስደው ነበር። ተራ ስህተት ነው ብዬ አልተቀበልኩትም። ውስጤ ያለው ፆተኝነት ቀድሞ የሚጻፈው የወንዱ ሥም ነው እያለ ስለሚነግረኝ ነው። በሕይወቴ ሲነገረኝ የነበረው በዚህ ቅደም ተከተል ነው፤ አዳም እና ሔዋን፣ ሮሜዎ እና ጁሊዬት… የወንዱ ሥም ሁሌ ቀድሞ ይመጣል።

በየለት ሕይወቴ፣ ፆታቸው ሳይገለጽልኝ ጎበዝ፣ የተማሩ እና ስኬታማ ስለሆኑ ሰዎች ሲነገረኝ ሳላስበው የማስበው ወንድ እንደሆኑ ነው። የቢሮ ጸሐፊ ሳስብ ሴት፣ ማናጀሩ ደግሞ ወንድ እንደሆነ አድርጌ ነው። ይህ የሆነው ጥሩ ሰው ስላልሆንኩ አይደለም። ይህ የሆነው ባለፉት ምዕተዓመታት አባታዊው ስርዓት የአደባባይ ሚናዎችን ለወንዶች ብቻ ገድቦ፣ ወንዶች ተወዳድረው ወንዶች እንዲያሸንፉ ስለሚያደርግ ነው። ቀልቤ ግምት የሚያሳልፈው ታሪክ አስልቶ ነው። ምክንያቱ – ያም ሆነ ይህ፣ ፆተኝነቴን አይቀንስልኝም።

ሌላው ቀርቶ ስለወሲብ ሳስብ ሳይቀር ለተወሳሳቢዎቹ ጥንዶች የተለያየ ሚና ሰጥቼ ነው። ወንዱን እንደአድራጊ፣ ሴቷን እንደተደራጊ። ብዙ ግዜ ‘ይች ሴት በብዙ ወንዶች ተደርጋለች’ ብዬ ሳስብ ራሴን ይዤዋለሁ፤ ነገር ግን ‘ይህ ሰው በብዙ ሴቶች ተደርጓል’ ብዬ አስቤ አላውቅም፤ ወይም ለወንዱ ሲሆን ጀብዱ ነው፣ ለሴቷ ሲሆን ሽርሙ*ና።

Saraswatichandra and Kumud

Saraswatichandra and Kumud

በአማርኛ ቋንቋ፣ ‘ወንድ’ የሚለው ቃል ‘ጎበዝ’ ከሚለው’ጋ አንድ ዓይነት ትርጉም ይሰጣል። ይሄን ቃል ላለመጠቀም እፈልጋለሁ፤ ነገር ግን የሆነ አሪፍ ነገር ያደረገ ሰው ሲገጥመኝ ለማበረታቻ ‘ወንዳታ’ እያልኩ ሳወድስ በተደጋጋሚ ራሴን ታዝቤዋለሁ። ስኬታማ መሆን ወንድ መሆን ይጠይቅ ይመስል!

ነገር ግን እኔ ብቸኛው ፆተኛ አደለሁም። ሁላችንም ነን። በየለት ተግባራችን ፆታዊ መድሎዎችን እንተገብራለን። የየለት ፆተኝነት አደገኛ ነው። ምክንያቱም ታግለን እንዳንቀርፋቸው እንኳን ጥቃቅንና ከመልመዳችን የተነሳ የማናስተውላቸው ናቸው። በቋንቋችን፣ በሐሳባችን፣ በቤት ውስጥ፣ በሥራ ቦታ፣ በመዝናኛ ቦታዎች እና በየለቱ እግራችን በሚረግጥባቸው ሥፍራዎች ውስጥ የሴቶችና የወንዶች ሚና ከፋፍለን ሳይታወቀን ፆተኝነትን እንድናራምድ ያደርገናል – የየለት ፆተኝነት።

ስለዚህ፣ ፆተኝነትን እየታገልኩ ከሆነ፣ በዙሪያዬ ያለውን ያክል በውስጤ ያለውንም ፆተኝነት መዋጋት አለብኝ።

(*ፆተኝነት – የሚለውን ቃል መጀመሪያ የተጠቀመበት Yohanes Molla ነው። ዘር (race) ብለን ዘረኝነት (racism) ካልን፣ ፆታ (sex) ብለን ፆተኝነት (sexism) ብንል ያስኬዳል በሚል መነሻ። 👌)

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>