Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live
↧

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

11889433_757998407659153_6814521236075663972_nአንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
ትናንት ነሀሴ 16/2007 ዓ.ም ጉባኤውን የጀመረው ፓርቲው በዛሬው ሁለተኛና የማጠቃለያ ውሎው የፓርቲውን ሊቀመንበር፣ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት ምርጫን አድርጓል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ ለቀጣዩ ሦስት አመታት ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን፣ አምስት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላትም በጉባኤው ተመርጠዋል፡፡ ጉባኤው የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም መርጧል፡፡
ለፓርቲው ሊቀመንበርነት ቀደም ብለው ፓርቲውን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ራሳቸውን በእጩነት ያቀረቡት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ብቻ ሲሆኑ፣ ጉባኤው ተጨማሪ እጩዎችን ለመቀበል ባቀረበው ሀሳብ መሰረት ራሱን በእጩነት የሚያቀርብ ይኖራል ተብሎ ቢጠበቅም በእጩነት ራሱን ያቀረበ አልነበረም፡፡
በመሆኑም በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት ጉባኤው ተጨማሪ እጩዎችን በጥቆማ ለማወዳደር ተገድዷል፡፡ በዚህም ጉባኤው ስድስት እጩዎችን የጠቆመ ቢሆንም አምስቱ ‹‹አንወዳደርም›› በማለታቸው ከተጠቆሙት መካከል አቶ ዮናታን ተስፋዬ ብቻ ለመወዳደር ፍላጎታቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፓርቲውን በህዝብ ግንኙነት ማገልገላቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ለሊቀመንበርነት መወዳደር ችለዋል፡፡

11143241_757998427659151_7139005276981892166_n
ለሊቀመንበርነት እጩ ሆነው የቀረቡት ሁለቱ እጩዎች በጉባኤው ፊት በተመደበላቸው ጊዜ ገደብ ውስጥ ራሳቸውን ካስተዋወቁና የምረጡኝ ቅስቀሳ ካደረጉ በኋላ ወደ ድምጽ መስጠት መግባት ተችሏል፡፡ በተሰጠው ድምጽ መሰረትም ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲን ለቀጣይ ሦስት አመታት እንዲመሩ በአብላጫ ድምጽ ተመርጠዋል፤ በዚህም ኢ/ር ይልቃል ከተሰጠው ድምጽ 136 ድምጽ አግኝተው ሲያሸንፉ፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በበኩላቸው 60 ድምጽ በማግኘት ፉክክር አድርገዋል፡፡
የምርጫ ውጤቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ንግግር ያደረጉት ተመራጩ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲ በሁለቱ ቀናት ጉባኤው ያነሳቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ውሎው ቀጣይ የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶም በጉባኤው አባላት አጠቃላይ ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህም ፓርቲው ወደፊት ማደራጀት ላይ አተኩሮ መስራት እንደሚገባው ጉባኤው አጽንኦት ሰጥቶበታል፡፡
ጠቅላላ ጉባኤው የብሄራዊ ምክር ቤትና የፓርቲው ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ሪፖርቶቹ የፓርቲው ሰነድ ሆነው እንዲፀድቁ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ያካሄደውን ጉባኤ ዛሬ ነሀሴ 17/2007 ዓ.ም አጠናቅቋል፡፡

118

↧

ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የበየነላቸው አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ እንዳይፈቱ እገዳ ተላለፈ

≫ Next: Hiber Radio : ኦብነግ በከፈተው ጥቃት አንድ ቻይናዊ ኢንጂነርን ጨምሮ የወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፣ኢ/ር ይልቃል በድጋሚ መመረጡና በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ክፍፍል የለም መባሉ ፣ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በወንድ አሰልጣኖቻቸው የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ተዘገበ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለፖለቲካ ስልጠና ተጠሩ፣የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ የፈጠረው ዓለም አቀፍ ስጋት፣ ቃለ መጠይቅ ከሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ ጋር እና ሌሎችም
$
0
0

Habtamu abrhayeshiwas daniel
(ነገረ ኢትዮጵያ) ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዳይለቀቁ ታግደዋል፡፡

አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ ማድረግ ከህግ ውጭ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡ ነጻ የተባሉት አመራሮች ባለፈው አርብ ከእስር ይወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ድረስ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

↧
↧

Hiber Radio : ኦብነግ በከፈተው ጥቃት አንድ ቻይናዊ ኢንጂነርን ጨምሮ የወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፣ኢ/ር ይልቃል በድጋሚ መመረጡና በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ክፍፍል የለም መባሉ ፣ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በወንድ አሰልጣኖቻቸው የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ተዘገበ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለፖለቲካ ስልጠና ተጠሩ፣የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ የፈጠረው ዓለም አቀፍ ስጋት፣ ቃለ መጠይቅ ከሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ ጋር እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 17 ቀን 2007 ፕሮግራም

<…ሰማያዊ ፓርቲ የሁለት ቀን ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል።የተለያየ ሀሳብ አስተናግዷል። ልዩነት መከፋፈል የሚባለው ሀሰት ነው ። ነገር ግን …> አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ

የፋይናንስ ሀላፊ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የፓርቲውን የመጀመሪያ ጉባዔ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…የጋሞ ብሔር ቅሬታና ተቃውሞ ይታወቃል። ጋሞ የለም የሚል ፣ብሄርን ከብሄር የኒያጋጭ ሕዝቡን የሚሳደብ መጽሐፍ ወጣ። መጽሐፉን የጻፈው ብቻ ሳይሄን ስፖንሰር ያደረጉት የዞኑ የፋይናንስ ቢሮ ነው? ለምን እነዚህም ተጠያቂ አይሆኑም ነበር ።ባለስልጣናቱ ሕዝቡን ጥገኛ ሕዝብ በሚል የተለያዩ ስሞች እየለጠፉ ነው። ሕዝቡ ግን…> አቶ ጉንጆ ዳርጌ በወቅቱ በአርባ ምንጭና አካባቢው ያለውን ውጥረት በተመለከተ ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የአሰብ ጉዳይ በኢትዮጵያ በኩል ጥቅሟን የሚያስጠብቅ መንግስት ሲመታ ሊነሳ የሚችል ነው።አሰብ ለሁለቱ አገራት ዘላቂ ሰላም እና ጥቅም የሚያመታው አስተዋጽዎ ትልቅ ነው። ወያኔ ግን በአሰብ ስም በሀሰት ዳግም ጦርነት ለመቀስቀስ የሚጠቀምበት ካርድ ሊሆን ይችላል። ይህን ካርዱን ቀደን መጣል አለብን።… ተወልደ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ወይዘሮ እማዋይሽን ጡቷን በምላጭ ሲተለትላት ምንድናት ብሎ ቢያስብ ነው? ብለን ካልጠየቅን በስተቀር ድርጊቱ ትርጉም አይሰጠንም። ገመቺስ ብልቱ ላይ ውሃ የተሞሉ ጠርሙሶች ታስረውበት ሁለት ቀናት ተንጠልጥሎ መሰቃየቱን ሲነግረን በሰማነው ነገር ስሜታችን ሲረበሽ እነ ተወልደ እነ ጉሽ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የማይሰማቸው ለምንድነው ብለን መጠየቅ አለብን? ገመቺስና ወ/ሮ እማዋይሽ የሰው ልጆች ስለሆኑ ነው ሰቆቃ ሊፈጸምባቸው አይገባም ያልነው ። እነ ተወልደና አለቃቸው ታደሰ መሰረት እኛም እንደእነሱ የሰው ልጅ መሆናችንን ቢያምኑ ኖሩ ይህን መሰሉን ሰቆቃ አይፈጽሙብንም ነበር።የዘር ፍጅት የደረሰባቸውን አገሮች ታሪክ ከመረመርን ጨፍጫፊዎቹ ተጨፍጫፊዎቹን እንደ እንስሳ እንጂ እንደ ሰው ልጆች እንዳልቆጠሯቸው በታሪክ ተመዝግቧል። እስከዛሬ ተናግሬ የማላውቀውን አንድ የደረሰብኝን ገጠመኝ ላንሳ …> አቶ ሙሉነህ እዩኤል የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር በቬጋስ ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ሕይወታቸውን ፣ደማቸውን እና አጥንታቸውን የገበሩላት ኮሪያ እንዴት ስነበተች? (ልዩ ዘገባ)

“ንጉሱ ለዘማቹ ጦራቸው ሰንደቃላማ ይሰጡና ከድል መልስም ያነኑ ሰንደቃላማውን ይዘው እንዲመጡ ትእዛዝ ያቀርቡ ነበር” የኮሪያው ዘማች ሻምበል ማሞ ሓብተወልድ ኮሪያን በትዛታ ለቢቢሲው ጋዜጠኛ እንዳስቃኙት (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኦብነግ በደገሃቡር በወሰደው ጥቃት በቻይናዊ ኢንጂነርና በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ጥቃት ማድረሱን ገለጸ

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲን በድጋሚ ለቀጣዩ ሶስት ዓመት ለመምራት ተመረጡ

ካቢኔያቸውን በቅርቡ ይፋ ያደርጋሉ ተብሏል

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለፖለቲካ ስልጠና ተጠሩ

ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በወንድ አሰልጣኞቻቸው የወሲብጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ተዘገበ

ከአቅም በላይ እየጨመረ የመጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከአቅም ባላይ መጨመር ለዓለም ሕዝብ ስጋት ፈጥሯል ተባለ

የቻይና ማፊያዎች ኢትዮጵያን ለመሸጋገሪያነት ተጠቅመው ዙሪክ ላይ ተያዙ

አገዛዙ አልገዛም ያለውን የጋሞ ብሔር በጅምላ በግንቦት ሰባትና በሌሎች ተቃዋሚዎች ስም በአደባባይ ከሰሰ

በቬጋስ ለአርበኞች ግንቦት 7 ማጠናከሪያ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ብር ተዋጣ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

↧

የተቃጠለ ካርቦን ነው ዬጥገና (Reform) ህልመኛነት መንፈስ (ሥርጉተ ሥላሴ)

≪ Previous: Hiber Radio : ኦብነግ በከፈተው ጥቃት አንድ ቻይናዊ ኢንጂነርን ጨምሮ የወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፣ኢ/ር ይልቃል በድጋሚ መመረጡና በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ክፍፍል የለም መባሉ ፣ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በወንድ አሰልጣኖቻቸው የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ተዘገበ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለፖለቲካ ስልጠና ተጠሩ፣የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ የፈጠረው ዓለም አቀፍ ስጋት፣ ቃለ መጠይቅ ከሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ ጋር እና ሌሎችም
$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.082015 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ጤና ይስጥልኝ እንዴትናችሁ ወገኖቼ። ከተለመደው ጊዜዬ ቀድሜ መምጣት ግድ አለኝ። ይህ የጥገና ወይንም የማሻሻያ Reform ለውጥ ህለመኝነት ከዚሕው ከቤቴ ከዘሃበሻ ተለጥፎ ማዬቴ ስላልተመቸኝ ነው ባልተራራቀ ቀን ብቅ ያልኩት።

reformዬወያኔ ሃርነት ትግራይ የታዛ ዕድሜ ለማኞች አዲስ ውሃ ያልነካው ወጀብ Reform ጥገናዊ ለውጥ አምላኪነትን ይዘው ከች ብለዋል። ትችቱም ከአንጀት ጠብ አይልም።ይህ ቅብ ወቀሳ የተለመደ ነው። እንዲህ መሰል የደካማቸው መንፈሶች እሳት መጫሪያ አጀንዳ አዘጋጅተው በዬጊዜው ነውጥ ፈጥረው የብሄራዊ ነፃነት ትግሉን አቅም ሲበሉ – ኖረዋል። አሁን ብሄራዊ ዬነፃነት ትግላችን በቆራጥ አርበኞቻችን ዱር ቤቴነት አብነት የመሠረቱ ፍላጎት መደላደል፤ ፍጹም ከማይችሉት ደረጃ ሲደርስ ደግሞ አዲስ ቅጥል ተስፈኝነት እያቆለማጡ ይገኛሉ – ይሄኛው እንዲህ እንዲያ ቢሆን ይሉናል። ይህን መሰሉን ዝል መንፈስ ተመገብው ደግሞ ያው የምናውቃቸው መደበኛ ሱቅ በደረቴያቸውን ከፍተው የሃሳብ ችርቻሮ – ይጀመራሉ። ቢገለባበጡም እነሱው ናቸው።

የአሜሪካው ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም በአዳዲስ አጀንዳዎች ዙሪያ በማር የተለወሱ መርዞችን ሰፋፊ ጊዜ እዬሰጠ አና ብሎ ተያይዞታል። ሰሞኑን ደግሞ የጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንቆቅልሽ – ምን አውቅልሽ ገባጣም አስደመጠን፤ ያው በአንድ ምዕራፍ ከፌስቡክ ደንበኛው ከዶር. ቴወድርስ አድሃኖም አንካሳ መንፈስ ጋር በአንድ ካሊም የሚጠቃለል ነው። መቼም ጠ/ሚሩ መደባቸው የትኛውን ህበረተስብ እንደሚውክሉ ግራ ነው። ስለ አብሮነት ስለ ዘውገ ተከል አስተዳደር ጠንቅነት እዬሰበኩን ነው። የዞረባቸው። ሥልጣኑን የሰጣቸው እኮ ይሄው ዘውገ መራሽ ማንፌስቶ መሆኑን ሙልጭ አድርገው – እረስተውታል። ይህን እንዲያስፈጽሙ እኮ ነው የተሾሙት። …. „ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኃል።“ ለነገሩ ከጤናቸው ጋር ስለመሆናቸው እጅግ – እጠራጠራለሁ። ነጋ መሼ ዝብርቅርቅ ባለ ግፋፎ – የጉሸ መንፈስ ላይና ታች ሲባዝኑ፤ በግድፈት ተንጠው ሲነዝሩ – ሲወድቁ፤ እላፊም ሲሄዱ ነው የሚታዩት …. ቢያንስ መካሪ የትዳር አጋርም የላቸውም እስኪያሰኝ ድረስ። እንጃ የሚያነቡትን ነገር ጋርም የሚተዋወቁ – አይመስለኝም። እውር ድንብሱን እኮ ነው የሚራመዱት። ቅጥ – አንብሩ ጠፍቶባቸዋል። ወረቀቱም ፈርዶበት በውልቅልቅ ፍላጎቶች ታጭቆ ተነበብ – ይባላል።

በሌላ በኩል የህግ ከፍተኛ ባለሙያው ከሆኑት ከተከበሩ ዶር. አበራ ደገፉም ስለ ህግ አፈጻጻም፤ ሥርዕተ ህገ መንግሥቱ ሞቶ ከተቀበረ ከስንት ዓመት በኋላ ሙያዊ የበቃ ትንተና ሲሰጡ እያዳምጥን ነው።  እኔ እንዲያውም ካነሱት ላይቀር በአዲስ አበባ ዩንቨርሰቲ የህግ ፋክሊቲ ስለሚባለው ለምን አይዘጉትም ስል ነበር – በግሌ። ፍትህ ለመቅበር ወጣቶችን ማስልጠን፣ መዋለ ንዋይ ማፈሰስ የሚያስፈልግ ስለማይመስለኝ። ጥቁሩን የክብር ልብስ ለመልበስ ከሆነ ምኞተኛው በግሉ አሰፍቶ መልበስ ይችላል። ሙያው ከተፈጥሮው ወጥቶ በዝርዝር የአፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ያተኮረ፤ ባለቤት የሌላው፣ ጎዳና አደር ከሆነ እኮ ዓመታት ተቆጠሩ። ለመሆኑ አሁን ነው የሚታያቸው የህግ ሥርዓት በኢትዮጵያ ከአፈር በታች መሆኑ ወይንስ አልኩ ለማለት ነው?! መጀመሪያ ከዛው ከዩንቨርስቲው ካለአግባብ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ የመምህራንና የተማሪዎችን የመብት ጥሰትን የመከላከል፣ የማስቆም አቅም ይኑረው የህግ ፋክልቲ – ተብዬው። በዩነቨርስቲው ቅጽር ግቢ በአስተዳደሩ ከህግ በላይ ያሉትን የህወሓት ካድሬዎችን መልክ ለማስያዝ ኩስሙን አቅሙን ያነጋግር፤ ይህቺን ለማድረግ ያልቻለ የህግ ሙያተኛ ለእኔ የሚፈጥራቸው አዲስ የህግ ሰልጣኞች ለገቢ ማስገኛ ስምሪት በጥቃቅን ሸቀጦች ተደራጅተው ለጉሮሯቸው ከማደር በስተቀር ከሙያው ሥነ – ምግባር ጋር ፍቺ ከተፈጸመ እኮ ከ20ዎቹ ዓመታት በላይ ተቆጠረ። የተኛ ነገር ነው በሁሉም ዘርፍ የሚታዬው፤ በቅድሚያ እስኪ ከራሱ ይነሳ ….. እራሱን በግልጽ ወቅሶና ገምግሞ አለሠራኝም ካለው የሙያ አካዳሚያዊ ነፃነት አፈና ጋር ፊት ለፊት ተሟግቶ „በቃኝን“ በተግባር ያስጊጥ። ይህ ነበር ግንባር ቀደም ተልዕኮው …። እራሱን ማሰከበር ይቀደም። ለማንኛውም መልካም ምኞት ከሆነም ሁሉን በእኩልነት አሳታፊ ሥራአት ሲደራጅ በራሱ ጊዜ ይህ መረን የለቀቀ ጋጠ ወጥ መስመር መልክ ይይዛል። በጥገናዊ ለውጥ – አይተሰብም፤ በሥር ነቀል ለውጥ እንጂ። እራሳችንም በአብዮታዊ መንፈስ ውስጥ አስገብተን እንሞራርደው።

እንዲሁም ስለነፃነት ተማጋችነቴ ማን ከእኔ በላይ የሚለን ለበጠኛው ባለድርጎ ተሰፋሪ ሪፖርትር ጋዜጣም ቢሆን የት ነበረ እስከ ዛሬ ድረስ?! ለአፓርታይድ ፋሽስታዊ ሥርዓት ድርና ማግ በመሆን በቃል አቀባይነት፣ በአቀንቃኝነት፣ በአፍቅሮተ ዘውገኝነት፤ በሙሉ ድጋፍ ሰጪነት፤ በሽፋን ጠገብ የህወሓት ሞሾሪነት በቆዬበት ግድፈት ዘለቅ ዘመን ለመሆኑ ምን ያህል ዓመት በህዝብ ሰቆቃ እንደ ተኛ ያውቀዋልን? ምን ያህል ሰዓትስ በግፍ የደም ፍስት ፍራሽ እንቅልፍ ላይ እንደ ነበርስ? አንዱ ቀን 24 ሰዓት አለው፤ በዐመታት ሲሰላ ደግሞ የት እዬለሌ ነው። ለመሆኑ አሁን ደግሞ አይዋ ሪፖርተር የሚተጋው ምን ፈልጎ ነው? ምን አምጣ ነው የሚለው የ90 ሚሊዮን የህዝብ ዕንባን? አለዬነም እሱ ብሎ መካሪ – ዘካሪ። ይልቅ በህዝብ ደምና ዕንባ ሲነግድና ሲያስነግድ የኖረበትን ዘመን አንድ … ሁለት እያለ ስሌቱን ቢያስኬደው ምን ያህል ከሰመጠ ጉድጓድ ውስጥ እራሱ እንደ በቀለ መስታውት ገዝቶ ቢያዬው መልካም ነው። ባንዳነት አድሮ የማይገኝ አሳፋሪ፤ ተላምጦ የተጣለ አገዳ ወይንም ውሃ ሲሄደበት የከረመ አለትነት ነው።

አዎን የዘር አጀንዳ፤ የታሪክ አጀንዳ፤ የሰፈር አጀንዳ፤ የሃይማኖት አጀንዳ፤ የከተማና የገጠር አጀንዳ ክርችም ሲል ሌላ ጊዜ መግዣ የጥገና ለውጥ Reform አጀንዳ ደግሞ አሁን ጅራቱን እዬቆላ ይገኛል በህወሓት አጋፋሪ በአይዋ ሪፖርተር። ቀጣዩ ደግሞ „ይኸው ይህን ህወሓት አሻሻለ፤ ይኸው ይሄኛውን ህወሓት ማሻሻያ ደገመ። ይኸው – ይኽኛው ተሰለሰ፤ ይኽው ይህን ያህል እስረኛ – ተለቀቀ፣ ህወሓት መማር ማስተካከል ጀመረ፤  በማለት አዘናግቶ ሌላ የራህብ፤ የሰቆቃ፤ የፍዳ፤ የዕንባ፤ የብሄራዊ ውርደት ዘመን አንድ ሁለት ሦስት አራት እያልን ወደ አይቀሬው ዬምርጫ ዙር ተብዬ ሽግግር – ይደረጋል። ከዛም 96 ፕርሰንት አሸነፈ ህወሓት ተቃዋሚውም ደግሞ 4 ፐርሰንት አግኝቷል በዚህች እንተክዝ …. በሚቀጥለው … በሚቀጥለው ደግሞ የአንድ ፐርሰንት ምራቂ ትኖረናለች“  ወዘተ ወዘተ ተረት – ተረት፤ ለዚህም ነው የአሁኑ ዓይን ያወጣ አዲስ ትጥቅ አስፈቺና አዘናጊ የጥገና Reform አጀንዳ … አና ብሎ ዕወጃ በዬአቅጣጫው ነጋሪቱን እዬጎሰመ ያለው። ቀልዱ ይቁም! ተረቡ ጠርዝ ይኑረው! በዕንባ ዘመናይነቱ ገደብ ይኑረው! ሪፎርምር ሪፖርተር ጋዜጣም ለከት ይኑርህ!

…. ያው የሳይበር አማሾች ደግሞ  እንደ ተለመደው አጀንዳቸው ሁሉ አይሆኑ ሆኖ አፈር ቅሞ ማርቶ አፈር ስለገባ። በለመደባቸውና በሰለጠኑበት የዕድሜ ለማኝነት አዲስ ነጠላ ዜማዋን ትናንሽ ኮርስ ይወስዱና ሰብሰብ ብለው „አይተን የመጣነው፤ ግን ሊስተካካል ይቻላል ተብሎ ቃል የተገባልን እዬሆነ ነው፤ ህወሓት ተሻሻለ¡ አሻሻለ አስተካከለ¡“ በማለት ይቀጥላሉ። ድሪቶ – በድሪቶ። አጃቢዎቻቸውም የእንኳን ደህና መጣችሁልን አቀባበላቸውን የሚገልጡበት መድርክ ይባልና በደማም ቃላት፣ በቀለም የተለቀለቁ ልስን አዳዲስ ብሎጎች፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት የተንቆጠቆጡ ድህረ ገፆች – በአዲስ፤ ጥገናዊ Reform የሚከበክብ የሚከብ፤ የሚያነጥፍ የሚጎዘጉዝ የመወያያ መድረክ – አዲስ ፓልቶክ፤ የተዘጉትም የውይይት መድረኮች በተሃድሶ መንፈስ – ይከፈታሉ። ራዲዮም አዲስ ይጀማመራል —- በዛው ልክ ፌስቡኩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች በስፋት ይዘረጋሉ። የተቃጠሉ ካርቦኖች። ጭስ!

አጅሬው – ህወሓት ደግሞ ዶላሩን በአፍ አፋቸው ያጎራርሳና አታሞውን ተመልካች – ይሆናል። በገፍ ያሰማራቸው ሰላዮችም በአዲስ የባንዳነት ቃና ጠብ እርግፍ – ይላሉ። ነገር ግን ሁሎቹም በረገበ አልጋ፤ በሰመጠ መርከብ ላይ መሆናቸው አይታያቸውም። እንዲያውም „አዲስ የኃይል አሰላለፍ ተፈጠረ በማለት ለዚህ ነበር የደከምነው – የታገልነው“ ይባልልናል። ልክ ለውሻ እንደሚጣለው ቅንጥብጣቢ ሥጋ ያን ከገዢያቸው ከትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ የሚወረውረውን ቅንጥብጣቢ ዬሥጋ ቁራጭ ለመንፈሳቸው አቀብለው ብሄራዊ ዘላቂ ዬነፃነት ፍላጎታችን ለመቦርቦር ዬዳንሱ አርንቋ ትዕይንት – ይያያዙታል።

የፖለቲካ ተንተኞቻቸውም „አደብ ገዝተን ማደመጥ ይገባል¡ ያጸደቁትን ህገ መንግሥታቸውን በራሳቸው ጊዜ እዬሸራረፉት ነው¡“ በማለት በብዕራቸው፤ በማይካቸው ተግተው ስብከታቸውን „ቀስ እዬተባለ¡ እዬተስተዋለ¡“ እያሉ የፕሮፓጋንዳ ጥፈት – ይለጣጥፋሉ። ይህ ለእኔ እርባናው ያለቀ የተቃጠለ ካርቦን አዲስ የምኞት መቃብር ድራማ ነው። የሚያሳዝኑኝ ግን ቅኖች ህሊናቸው ከዕለት ዕለት ታቱ ዥግራ ማለቱ ነው።

የሰው ልጅ እራሱን መተርጎም የሚችለው መቆም ቀጥ ብሎ ሲችል ብቻ ነው። መቆሙንም ማረጋገጥ ይኖርበታል። በዚህ ወጣ ገብ በሆነ ወጀብ መናጥ፤ መቆም አለመቻል የተፈጥሮ ሽሽት ወይንም የራስነት ውስት ብቻ ሳይሆን ከበታችነት የመነጨ ፍርሃትም ነው። በተለያዩ ክሮች ትስስር ከፋሽስቱ ወያኔ ጋር ጋብቻው አለ። እዬታዬ ያለው ያን ክር መበጠስ ድፍረቱን የሚቀማ የጥቅማጥቅም ድልድይ ወይንም የተስፈኝነት ሙት መንፈስ መንገታተገት ነው፤ የበሰበሰ ነገር መወገድ እንጂ ጥገናዊ ለውጥ በፍጹም ሁኔታ አያስፈልገውም። ጊዜው ያለፈበት ምግብ በሽታ ስለሆነ ዕጣ ፈንታው መደፋት ብቻ ወይንም ቆሻሻ ኮንቴይነር ውስጥ መጨመር ነው። ዬህወሓት መንፈስ ማርጀት አይደለም፤ ሞቷል። ደግሞ መነሳት ቀርቶ ዳግም ለመነሳት ማሰብም አይችልም። በቅቶታትል። ታሪክ – ተፍቶታል። ከውርርስ ቅርስነትም ውጪ ነው። ህወሓት ዕድሉን ያባከነው ዛሬ ሳይሆን ከ10 ዓመት በፊት በዘመነ ቅንጅት ወይንም ከዛ በፊት በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዘመን ነበር። ያን ጊዜ ታሪክ እራሱን አይቶ ከገደል ጫፍ የሚድነበትን ሁለት ትላልቅ መስተዋቶች ገዝቶለት ነበር። አሱ ግን ከመስታውቱ ላይ በመቆም ዕድሉን በመታበይ – ሰባብሮታል። የተቃጠለ ካርቦን።

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ሐገራችን ዘመነ መሳፍንትን፤ ዬዓፄ ሥርዓትን፤ የወታደራዊ ሥርዓት በሶሻሊስት – ርዕዮትዓለምን። እንደዬዘመኑ በተለያዩ ፈተናዎች ተወጥራ አስተናግዳለች። ከዘመን ባፈነገጠው በቬርሙዳ ትርያንግሉ ጠፍ አስተዳደር በህወሓት ደግሞ በዓለም የሌላ፣ ዘመንም የተፋው፣ ታሪክም የሚጸዬፈው፣ አደራም ያቃረው፤ ባህልም የፋቀው የዘውገ ሥርዓትን በአልባንያ አብዬት ጥንዝል ተመክሮ በፍዳ፣ በመከራ፣ በስቃይ ተቃጥላ፣ ተንገብግባ፣ ተርመጥምጣ አሳልፋለች። ሁሉንም – አይታለች። ለሁሉም መከራዊ ዘመን መፈተኛ ሆናለች።

አሁን ግን ዘመኑ የፈቀደላት ሌላ የፍትህ አዲስ የዲሞክራሲ የሽግግር ሥርዓት ያስፈልጋታል። በቅድሚያ እንዲያውም ብሄራዊ ነፃነት። ኢትዮጵያ ከጠላቷ ከህወሓት እስር ቤት መውጣት አለባት። ከዚያ በኋላ ሂደቱ ሁሉን ዜጎቿን በ እኩልነት ያሳተፈ አዲስ ሥርዓት አቅምና ህግ በድምጽ ብልጫ ሊመራት የሚችል ሀገር መሆን። ሰው የሚለውን ማዕከላዊ የተፈጥሮ አጀንዳ ተርጉሞ፤ በፈጣሪ አምላካችን የተሰጠው ዬሰው ልጅ ክብር ሙሉ መብት ሳይገፈፍና ሰይገሰሰ በዜግነት እኩልነት ላይ የተመሰረተ የተስፋ ሥርዓት መዝርጋትን ነው – የፍላጎቷ ህልመ – አስኳል። ለዚህ ደግሞ ዛሬ – የሞቀ የደመቀ ዬአብዛኛውን መንፈስ የገዛ አዲስ ብረሁኽ የለወጥ መንፈስ ላይ እንገኛለን። አቅማችን፣ ኃይላችን፣ አቅላችን፣ ህልማችን፣ ናፍቆታችን፣ ጸሎታችን እንደ ዕምነታችን ተማክሎ ከዛ ላይ በአርበኞቻችን ባረፈበት በአሁኑ ጊዜ የሪፖርትርን Reform የዕድሜ ልምና፣ የሱባኤ ነጋሪት ማስታመም፣ ማቆላመጥ ሆነ ማንቆላበስ ወይንም ማሽሞንሞን የተገባ አይመስለኝም። በምልአት ደምና ሰቆቃ መነገድ ነውም። የደም ንግድ ይቁም!

ሁሉመናን ለወሰደ – ቀማኛ ሽፍታ፤ ውሸታም፤ ዘራፊ፤ ይሉንታ ቢስ፤ ለበቀል ዞጋዊ ፖሊሲ አራማጅ አረመኔያዊ የህወሓት ሥርዓት ብጣቂ ጊዜ ልናውሰው ፈጽሞ – አይገባም። ይህ ያሰኘናል የሚሉ ሸጎሬዎች አብረው ድንኳን ጥለው ያስተዛዝኑ …. ሳልስቱንም፣ ሰባቱንም አርባውንም – ያውጡ። ይህ የእኛ መደባችን አይደለም። እኛን እኛን የማይሸት፣ ሰውኛ ያልሆነ የሳጥናኤልን ቀጠናን ቅብጥና ቅልጥ የሚያድርግ የራዕያችን ትንፋሽ ቅበረት ዘመቻ ስለሆነ „በቃን“ ልንለው ይገባል።

„በቃን“ ማለት እኮ እንዲህ አይነት የሚያላዝኑ ዝልብ – ስንጥቅ – ትርትር – ቀዳዳ ፍላጎቶቹን ማስፈንጠር ነው። ዬአሞሌ ጨው መላሾነት ለከብት እንጂ ለሰው ልጅ ክብር – አይመጥነውም። ለነገሩ ይህ „በቃን“ የሚለው ቃል ትርጉሙም የገባን አይመስለኝም። „በቃን“ ሲባል እኮ ማናቸውም ወያኔ ነክ መንፈሶችን ሁሉ መጸዬፍ፣ መገፍተር ማለት እንጂ እንደ ገደል ማሚቶ ደግሞ ማስተገባት አይደለም። ይህ በዕውነቱ 25 ዓመት የፈሰሰውን የወገኖቻችን ደም መርገጥ ነው። የእናት ኢትዮጵያን ዬኤሉሄዋ የምጥ ድምጽም እንደ መጠቅጠቅ ነው።

ለመሆኑ ስንት ጊዜ ነው ዕድላችን ለጆፌ አሞራ የምንቀልበው!? አይበቃም?!  በደል አይረሰም – ያገረሻል እንጂ። …. ይህ የፋታ ፖሊሲ ቃር ነው። ስለሆነም አንቅረን ልንተፋው – ይገባል። ንቀን ስንተዎው ወደ ገደሉ ተመልሶ – ይቀበራል። አፈሩን ተከናንቦም ለሽ ይላል። እኛን በእኛነት ሊያከብር ለተነሳው የአርበኝነትን መንፈስ ውስጣችን ገልጠን ለእሱ – እናስረክብ። ለመሆኑ እነዛ እስር ቤት ውስጥ ሆነው „እኔ ዬአርበኞች ግንቦት 7 ነኝ!“ ያሉን ቀንበጦች መልዕክት ከሰው አንደበት የወጣ ይመስላችኋልን?! የጀግና ጋዜጠኛ አበበ ገላው በሬግን ህንፃ በሀገረ አሜሪካ በፈጣሪ አምላኩ የተመረጠለት መክሊት ድምጽ አኮ ነው፤ ዛሬም በኢትዮጵያ ምድር በድፍረት በአራዊቶች ካቴና ላይ ሆኖ ድምጹን ለብላቴናዎቹ አምላካችን መዳህኒተዓለም አቀብሎ ያውም በህብረት አንደ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ብሄራዊ ጥሪ የላከልን። ጥሪው እኮ ዬፈጣሪ አምላካችን ዬአማኑኤል ነው። ፈጣሪያችን እራሱ በሳጥናኤላዊ ህወሓት አመራሩ ከምር – አዝኗል። ታምራትን የእኛ እንበለቸው።

ወገኖቼ ጊዜው ደርሷል። ማቄን ጨርቄን – አንበል። ቢያንስ የፈጣሪን ድምጽ ለማድመጥ – እንፍቀድ። –  ጥሪውንም እንቀበል! ታጥቦ ጭቃም አንሁን ልክ እንደ ሦስት ዓመት – ህፃን። ቢያንስ መንፈሳችን እንደ ዕድሚያችን የማሰብ አቅሙን – እናሳድገው። መዳህ መዳህ —- መሬት ላይ ለመቅረት መሆን አይገባውም። ዘመንም ጊዜም ማድመጥ መተርጎም አብሮ ለመሆን መፍቀድ – ያስፈልጋል። በስተቀር ድንጋይ ነው ተብሎ መወርወርም አለ ….. ይበቃል ግልምቷል ግምቷል ህወሓትና ፖሊሲው። መልካም ሰሞናት።

ምንጭ  –

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት ቦታ የለውም›› ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46121#sthash.S8L3yZti.dpuf

ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት! ጋዜጣው ሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽ – በጋዜጣው ሪፖርተር

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46125

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

↧

ርዕዮት አለሙ አራዳ ነች (ከተማ ዋቅጅራ)

$
0
0
(ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ)

(ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ)

አባቴ ሁሌ የሚነግረኝ ነገር ነበር አራዳ ማለት ይለኛል  አራዳ ማለት፡-  ለነብሱ ያደረ፣ እውነተኛ፣ ፈሪ ያልሆነ፣  አላማውን በእውነት የሚገልጽ፣ ታዛዥ፣ ህብረተሰቡን በቅን የሚያገለግል፣ የሚያውቀውን በቅንነት የሚያሳውቅ፣ የፍቅር ሰባኪ፣ የሰላም መዝሙረኛ፣ የጥበብ ቅኝት ተቀኚ፣ የፍልስፍና አባት፣ የተበላሹ መንገዶችን ጠራጊ፣ ማስተዋልና ጥበብን በልቡ አስቀማጭ፣ በእውነት የዘነጠ፣  ለውሸት ቦታ የሌለው፣ ስጋን አደላዳይ፣ ነፍሱን አዳኝ፣ ከፍ ባለ ማማ ተቀምጦ ከአትሮኑሱ ስር የሚገኝ፣ የእውቀት ጫፍ ላይ ደረሶ ከፊደል ቆጣሪወች ጋር ፊደል የሚቆጥር፣ ከራሱ ከፍታ የህዝቡ ከፍታን የሚወድ፣ ከራሱ ድምቀት የአገርን መድመቅን የሚናፍቅ፣ ለታናሹ ታዛዥ፣ ለታላቁ አገልጋይ፣ አባቶቹን አክባሪ፣ እናቶቹን አፍቃሪ፣ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል፣ ቢዘምር ላገሩ፣ ቅኔ ቢቀኝ ለህዝቡ፣ ለነብሱም ለስጋውም ያደረ ማለት ነው። ይለኝ ነበር

ሁሉም ሰው እኩል ተሰጥኦ አይሰጠውም ለአንዱ ድምጽ፣ ለሌላው ደራሲነት፣ ለአንዱ መካሪ፣ ለሌላው አስተማሪ፣ ለአንዱ ቀዳሽ፣ ሌሌላው አራሽ፣ ብቻ ሁሉም የራሱ ተሰጥኦ አለው ዋናው ነገር ተሰጥኦህን በአግባቡ እና በእውነተኛ መንገድ መጠቀሙ ነው። እናም ርዕዮት ንጽ አእምሮ፣ ቆራጥ ልቦና፣ እውነት የሚናገር ብዕር፣ ተሰጥቷታል። ለዚህም ምስክር የምትጽፋቸው ጽሁፍ ይናገራል። እስር ሳይበግራት ጥንካሬዋን ያሳየች ከስር ከወጣችም በኃላ የብዕሯ ቀለም ሳይነጥብባት ስራዋን የቀጠለች ንጹህ  ህሊና ያላት ያወቀችውን የምታሳውቅ የአገር አለኝታ የህዝብ መከታ የሆነች በኢትዮጵያዊያኑ ልቦና  ውስጥ የሴት ጀግና ሆና የተቀመጠች አራዳ ነች።

እንዲህም ሆኗል ሁለት ጓደኛሞች ቡና እና ጊዮርጊስ ሲጫወቱ አንድ የጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊ ሌላኛው  ደግሞ የቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊ ናቸው። ዘንድሮማ የደጋፊ ነገር ችግር የለብንም ንብ ደግፉ፣ ቢራቢሮን ደግፉ፣ ዝንብን ደግፉ፣ ጢንዝዛን ደግፉ፣ በግድም በእጅም ግንቦት20 ደግፉ፣ የሚባልበት ጊዜ ላይ ስለደረስን ድጋፌን በደንብ ትረዱታላቹሁ ብዬ እገምታለው። እናም የቡናው ደጋፊ ቡና ያሸንፋል  የጊዮርጊስ ደጋፊ ጊዮርጊስ ያሸንፋል በማለት በ 1000 ብር ያሲዛሉ።  ለማንኛው እንድንተማመን  ውል ተጻጽፈን እንፈራረም ይላሉ። በውሉ መሰረት እንደሚተገበር ይስማማሉ። እንዲህ ይል ነበር ውሉ፡-

እከሌ የተባለው እና እከሌ  የተባለው ዛሬ በዚህ ቀን ቡና እና ጊዮርጊስ በሚያደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ ቡና ካሸነፈም፣ ቡና ከተሸነፈ፣  እንዲሁም አቻ ከወጣ የቡና ደጋፊ የሆነው  2000 ብር የእከሌ መሆኑን በፊርማችን  እናረጋግጣለን ብሎው ተፈራርመው ወደ እስታዲዮሙ ይገባሉ። በጨዋታውም ጊዮርጊስ ያሸንፍና በል ብሬን ብሬን እኛ እንደዚህ ነን ይለዋል የጊዮርጊስ ደጋፊ። የጎርጊሱ ደጋፊ መጻፍና ማንበብ አይችልም ነበር።   ውሉን ምን እንደሚል ስላልተረዳው  ክርክር ተጀመረ። በኋላ ላይ ክርክሩ ሲያይል ወደ ጋደኞቻቸው ወሰዱት ዳኝነትን ጠየቁ ጋደኞቻቸው ውሉን ሲያዩት በጣም ሳቁ። ቡና ቢያሸንፍም ቢሸነፍም አቻ ቢወጣም እሱ ይውሰደው ብለህ ነው እኮ ነው የፈረምከው አሉት። የዚህን ጊዜ በጣም ተናደደ። ብር ከመቁጠርህ በፊት ፊደል ቁጠር አሉት። እስከአሁንም እንዲህ እየተባለ ይቀለድበታል።

የብዕር አርበኛዋ ርዕዮት አለሙ በአንድ ብእር 17 አመት ጫካ ነበርን፣ ጀግና ነበርን፣ የሚሉትን ያርበደበደ ታንክ አለን፣ አዳፍኔ አለን፣ የሚሉትን ያዳፈነች። እውነት በመጻፏ ሽብር የመሰላቸው፣ ብዕሯን ከወረቀትጋር በማዋሃዷ ጀግና ነን ብለው የተኮፈሱትን ያራደች፣ የድንጋይ መሰረት ሳይሆኑ የእንቧይ ካብ መሆናቸውን ያሳየች፣ ብዕርተኛ ነች። የእርዮት ብእር ሰለ ሕዝብ ነጻነት የሚናገር፣ ሰለ አገሯ ክብር ቀለምን የሚተፋ፣ አስተማሪ ብእር ነው።  መለስ ዜናዊ |<<ከሺ ጦር ባተሌ አንድ ብዕር የያዘ ሰው ለኛ ከባድ ነው>> ብለው እንደተናገሩት በአንዲት ብዕር ማንም አይደፈረንም ብለው  የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሲናገር የነበረውን የወያኔን ምሽግ ሚግ አብራሪ  ወይም ታንከኛ ሆና ሳይሆን ያራደችው፣ ብዕሯ አሁን ስልጣን ላይ ያለውን ገዥ ፓርቲ ምን እንደሚል ያልገባቸው አልያም እውነት ውስጣቸው ስለሌ  በብዕሯ ቀለም የተሸበሩት። እርሷ ግን  እውነትን በመግለጽ፣ አገርን በመውደድ፣ ህዝብን በማክበር ብዕራን ያነሳች አራዳ ነች። እናም ብር ከመቁጠር  ፊደል መቁጠር ይሻላል የሚለውን አባባል ጋብዥያቸዋለው። በእውቀት የበለጸገ እና በእውነተኛ መንገድ ላይ የቆመ  ብዕር ያስተምረዋል እንጂ አያስፈራውምና ነው በብዕር የሚሸበር ያልተማረ ወይም  በእውነተኛ መንገድ ያልቆመ ብቻ ነው።

እርዮት ስጋዋ የታሰረ ህሊናዋ ያልታሰረ ብዕርተና ነች። ገራፊን ገርፈሃል፣ አሳሪን አስረሃል፣ ገዳይን ገድለሃል፣ የምትል የእውነት ብዕር ያነሳች  በዕረኛ ነች። ስጋችን ሲያገኝ የሚወፍር፣ ሲያጣ ደግሞ የሚከሳ ነው። አእምሮአችን ግን እውነትን ስንሰጠው ብቻ ነጻ አድርጎ የሚያኖረን የራሳችን ፍርድ ቤት ነው። ለአእምሮዋ እውነትን ያስገባች፣ እውነትንም ያወጣች፣ ከዘላለም ጸጸት የጸዳች፣ ከራሳ ጋር የተስማማች ብዕርተኛ ነች። ሕዝብ ማለት እሷ፣  እሷ ማለት ሕዝብ፣ መሆኑን ያስመሰከረች የዘመኑ የሴት ተምሳሌት የሆነች አራዳ ነች።

እንጂ  አራዳ የሚለው ትርጉም እንደኛ ዘመን ትርጉም እንደተሰጠው  የቃመና ያስቃመ፣ ያጨሰና ያስጨሰ፣  የጠጣና ያስጠጣ፣ ከፍ ብሎ የዘለለ እና የወደቀ፣  የሰረቀና ያሰረቀ፣ ያመሸና ያስመሸ፣ የጨፈረ እና ያስጨፈረ፣ እስታ በል፣ ላሽ በል፣ ተቄ በል፣ ጩባ፣ ፍሉስ፣ ሼባው፣ ጌጃው፣ ማኛው ,… የሚለው የሚጠቀም እና የሚያደርግ አራዳ አይደለም። እንደዚ አይነቱ ከራስ መጣላት፣ ከቤተሰብ መጣላት፣ ከጎረቤት መጣላት፣ ከህብረተሰብ መጣላት፣ ከአገር መጣላት፣ ብሎም ከእግዛቤሔር ጋርም መጣላት ነው። ስጋውንም ነብሱንም የሚጎዳ አራዳ የሚለው ትርጉምን አይስማማውም።

ሁላችንም አራዳ ለመሆን የአባቶቻችንን ምክር እንስማ እላለው። አራዳ በኢትዮጵያ ምድር በዝቶ ይብቀልባት፣ ይውጣባት፣ ይታይባት፣ ያብብባት።  አራዳ ዶክተር ወላ እንጅነር፣ አራዳ ወታደር ወላ መምህር፣ አራዳ አርሶ አደር ወላ ኢንቨስተር፣ አራዳ ደራሲ ወላ ሃያሲ፣, አራዳ ሳይንቲስት ወላ ጂኦሎጂስት፣ አራዳ ፖለቲከኛ ወላ ዳኛ፣ አራዳ መሪ ..ሆኖ ታታሪ.. በህግ አዳሪ.. ህዝቡን አስከባሪ.. ያብዛልን ፈጣሪ።

 

ከተማ ዋቅጅራ

21.08.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

↧
↧

በሰቆጣ ከተማ ከፍተኛ የውሃ ችግር መከሰቱን ነዋሪዎች ገለጹ

$
0
0

rain-water-harvesting1ኢሳት ዜና :-በተያዘው ክረምት በአብዛኛው ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍሎች የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ የሰቆጣ ከተማና የአካባቢው ወንዞች በመድረቃቸው የውኃ እጥረቱ መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ነዋሪዎች ፣ በዝናቡ እጥረት የተነሳ የጉድጓድ ውሃ መጠን በማነሱ የሚጠጣ ውኃ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
“በከተማዋ በአጠቃላይ የውኃ ችግር ተከስቷል፡፡በከተማዋ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ ልማት ጽህፈት ቤት ምን እየሰራ እንደሆን አናውቅም የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ የውሃ መስመሩ በየሳምንቱ ተበላሽቷል እንደሚባሉ ይናገራሉ፡፡ በየቤቱ የሚገኘው የቧንቧ መስመር አገልግሎት በመቋረጡ የሚጠጣ ውሃ ለማግኘት ከሌሊቱ አስር ሰዓት በመነሳት ወረፋ በመያዝ የገደል ውሃ ለመቅዳት መገደዳቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በሌሊት ወጥተው እስከ ቀኑ አራት ሰዓት ድረስ አርፍደው ውሃ እንደሚያገኙ በምሬት ገልጸዋል፡፡
በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የውኃ ችግር እንዳለ የሚገልጹት ሌላው የከተማ ነዋሪ ከዝናቡ መጥፋት ጋር ተያይዞ የሚታይ ችግር መሆኑን ይናገራሉ፡፡በከተማው ውስጥ ለውስጥ የሚያቋርጡና በዙሪያው ያሉ ወንዞች መድረቅ ህብረተሰቡ ከወንዝ ቀድቶ መጠቀም እንዳይችል አድርጓል፡፡ዝናብ አንድ አንድ ጊዜ ሲዘንብ እንዲህ ያለ መጨናነቅ እንደማይከሰት የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢ አልፎ አልፎ በሚጥለው ዝናብ ከቆርቆሮ ላይ በመሰብሰብ የየዕለት ችግራቸውን ለመቅረፍ እንደሚሞክሩ ይናገራሉ። ዝናብ በወር አንዴ ብቻ መዝነቡንና ከዚህ ውጭ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሚቆይ ካፊያ ብቻ መሆኑ የውኃውን ችግር እንዳባባሰው ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ አስተድደር ከአሁን በፊት ውኃ በቦቲ በማቅረብ የህዝቡን ጊዜያዊ ችግር ለመቅረፍ ቢሞክርም፣ አሁን አገልግሎቱ በመቋረጡ የከተማው ህዝብ በችግር ላይ ነው፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚናገሩት በነሃሴ ወር ከአሁን በፊት እንደዚህ ዓይነት የውኃ ችግር ተከስቶ እንደማያውቅ ተናግረው፤አልፎ አልፎ በሚጥለው ዝናብ የደረቀውን መሬት ከማራስ አልፎ ወደ ከርሰ ምድር የሚዘልቅ ውኃ ባለመኖሩ ከመስከረም ወር በኋላ ከፍተኛ የውኃ ችግር ሊከሰት ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው አክለዋል።
የገዢው መንግስት አመራሮች ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠታቸው ህብረተሰቡ ለከፍተኛ የውሃ ችግር መጋለጡን የሚገልጹት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ የጉድጓድ ውኃ ለመቅዳት በወረፋ ሰበብ ህዝቡ እርስ በርሱ ሲጣላ እና ቀኑን ሙሉ አንድ ጀሪካን ውኃ ለመቅዳት ተሰልፎ ስራ ሲፈታ በዝምታ ከማየት ሌላ የፈየዱልን የመፍትሄ ነገር የለም በማለት ይናገራሉ፡፡
ከአሁን በፊት ለሃያ አመታት ያገለግላል ተብሎ በከፍተኛ ወጪ የተሰራው የቧንቧ ውኃ ፣ ሶስት ዓመት ብቻ አገልግሎ ደርቋል።

↧

Je Suis ኢትዮጵያዊ!

$
0
0

hailemariam

ገለታው ዘለቀ

ከብሄር ፖለቲካ እንውጣ!
የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገንባ!

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲናገሩ ኣገራችንን የሚበትኑ ኣጥፊ ዘሮች ያሏቸውን ሶስት ጉዳዮች ኣነሱ። ኣንደኛው ጠባብነት፣ ሁለተኛው ትምክህተኛነት፣ ሶስተኛው በሃይማኖት ሽፋን የሚራመድ ኣክራሪነት ናቸው ኣሉ። በመሰረቱ እነዚህን ጉዳዮች ኣቶ ሃይለማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሷቸው ጉዳዮች ኣይደሉም። በ”ኢህዓዴግ” ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚነሱ ሁሌም ሲባሉ የነበሩ ናቸው። ኣቶ ሃይለማርያም ኣዲስ ነገር ኣልተናገሩም ።
ለማናቸውም ግን እነዚህ ኣደገኛ ዘሮች ከየት መጡ? ኣገሪቱንስ ወዴት እየወሰዱ ነው? በርግጥ ከብሄር ፖለቲካው ኣዝማሪዎች ኣልፎ ወደ ታች ወርዶ የኔብጤው ተራው ህዝብ ኣካባቢ እነዚህ ዘሮች ጎልተው እየታዩ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይና ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ያለመቻሏ ጉዳይ፣ የሰብዓዊ መብት ኣያያዝ ጉዳይ ሃላፊነት ለሚሰማው ኢትዮጵያዊ፣ ለዓለማቀፍ ተቋማትና ለኢትዮጵያ ወዳጅ ሃገራት ዲፕሎማቶች በጣም ኣሳሳቢ ጉዳይ ሆኖባቸው ኣያለሁ።
ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግሩ እንመለስና በመጀመሪያ እሳቸው ራሳቸው ያመኗቸው እነዚህ ሶስት ጉዳዮች በሰፊው የሚታዮት በኣንድ ሃገር ውስጥ ፖለቲካው በጠባቡ ሲቀረጽ፣ ወይም በየቤትህ እደር ኣይነት የፖለቲካ ጨዋታ ሲጀመር ወይም የፖለቲካው ጥብቆ ሲጠብ ነው። ሳይንሳዊ በሆነ ኣገላለጽ የማንነት ፖለቲካ (Identity Politics) የሚባለው ሲሆን በተለይ ብዙህ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ይህ የፖለቲካ ስርዓት ሲዘረጋ የሚያመጣቸው ወይም ከዚያ የሚፈለፈሉ ችግሮች ብዙ ናቸው። የብሄር ፖለቲካ የማህበራዊ ካፒታል ምስጥ ነው። ለዚህም ነው ምሁሩ፣ ተማሪው፣ የተማረው፣ ያልተማረው ሁሉ ላለፉት ሃያ ዓመታት በላይ የብሄር ፖለቲካን ሲነቅፍ የነበረው:: የማንነት ፖለቲካ እነዚህን ኣደገኛ ነገሮች እንደሚያመጣ ብዙ ሳይንሳዊ ምርምር የሚጠይቅም ኣልነበረም። የብሄር ፖለቲካ ስነ- ልቦናው ራሱ ጠባብነት ነው። ከጎሳው ያላለፈ የፖለቲካ ስብእና ይዞ እንዲያድግ የሚያደርግ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ የተጫነው በመሆኑ የጠባብነት መነሻው ይሄው የብሄር ፖለቲካ ነው።

ትምክህተኝነት የሚባለውም ከዚሁ ከጠባብ ኣስተሳሰብ የሚመነጭ የኣንድ ዛፍ ቅርንጫፍ ነው። ሰው ጠባብ ሲሆን ነው የሚመካው። በወንዙ በጎሳው ሲመካ ጠባብ ሆኖ ነውና። ጠባቦች ሁል ጊዜም ትምክህተኝነት ኣያጣቸውም። ሁለቱም ባህርያት የተያያዙ ከኣንድ መራራ የብሄር ፖለቲካ ምንጭ የሚቀዱ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲናገሩ ተማሪው ላይ ተጽእኖው ይታያል እንጂ እነዚህን ዘሮች የሚዘራው ኣስተማሪው ነው ኣሉ። ማን ነው የጠባብነትን ፖለቲካ የሚያስተምረው? ህወሃት “ኢህኣዴግ” ኣይደለምን? ህወሃት “ኢህዓዴግ” ከመምጣቱ በፊት ትግሬው፣ዓማራው፣ኦሮሞው ወዘተ. ኣብሮ ቁጭ ብሎ ሲጫወት መች የብሄር ነገር ትዝ ብሎት ያውቅ ነበር? ቢታወሰውም እየተቀላለደ ከመኖር ውጭ መራራ ስር ኣልነበረውም። ለእነዚህ ኣደገኛ ዘሮች መፈጠርና ማደግ ጥሩ መፈልፈያ የሆነው ራሱ የፖለቲካው ቤት መሆኑን መረዳት ብዙ ምርምር ኣልጠየቀም።

ቡድኖች ለምንድነው የብሄር ወይም የሃይማኖት ማንነታቸውን ይዘው ወደ ፖለቲካ የሚሳቡት? ካልን የፖለቲካን ሃይል መሳሪያ በማድረግ የቡድንን የወል ጥቅምና የበላይነት ለማረጋገጥ ነው። የፖለቲካው ስልጣን የመሳሪያ ሃይል ያለውንና የኢኮኖሚውን ክፍል ስለሚያዝ ያንን ቡድኖች መቆጣጠር ከቻሉ ለቡድናቸው ኣቋራጭ እድገት ዓይነተኛ መሳሪያ ሆኖ ስለሚያዩት ነው። በዚህ የፖለቲካ ድባብ ውስጥ ኣክራሪነት፣ ልዮነትን ማድመቅ የመከሰታቸው እውነት ለምን ጥያቄ ውስጥ ይከተናል? ሃይማኖታዊ ኣክራሪነትም የሚከሰተው ኣጠቃላይ የፖለቲካው ቅርጽ በማንነት ላይ ሲረብብ ሃይማኖታዊ ማንነታቸውን ይዘው ወደ ስልጣን እንዲሳቡ የሚያደርግ ስነ ልቡናዊ ድባብ ሲፈጠር ነው። በመሰረቱ ሃይማኖትን ማጥበቅ ማለት ኣይደለም ኣክራሪነት ማለት። ሃይማኖታዊ ኣክራሪነት የሚፈጠረው በሃይማኖቱ መሰረት ላይ የቆመ ፖለቲካ ለመመስረት መጣርና በጋራ ህልውና (coexistence) ኣለማመን ነው። በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን እንዲህ ዓይነት ባህርያት ሲገለጹ ኣክራሪነት መጣ እንላለን። ይህ ኣክራሪነት በኢትዮጵያ ከታየ ኣካባቢያዊ ኣስተዋጾዎች እንዳሉ ሆነው ራሱ የፖለቲካው ተፈጥሮና የመንግስት ኣያያዝ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ማድረጋቸው ኣይካድም። በኣጠቃላይ ምንጩ የማንነት ፖለቲካ ሆኖ ሳለ ለምን የመንግስት ሰዎች እነዚህን ችግሮች እየጠቀሱ ኣጥፊዎች ናቸው እንደሚሉ ዶክተር ዳኛቸው በቅርቡ በ VOA እንዳስረዱት ለማንም ኣይገባም። “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል” ነው ያሉት?

ጠቅላይ ሚንስትሩ ራሳቸው እኮ ቢያንስ እንደ ብሄር ራሳቸውን የሚገልጹበት ታእታይ የፖለቲካ ስብእና ባይኖራቸውም በመልክዓምድር በተወሰነ የፖለቲካ ታእታይ ስብእና የታጠሩና ለፈጠራቸው ህወሃት ኣድርባይ ናቸው። የህወሃት ኣባላትም እንዲሁ የፖለቲካ ውስጣዊ ወይም ታእታይ ሰውነታቸው በብሄር ላይ የቆመ ጠባብ ነው። በርግጥ “ኢህዓዴግ” የሚባለውን ለብሰናል ለማለት ከሆነ ህዝቡ ኣይዋጥለትም። ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት “ኢህዓዴግ” የሚባል ድርጅትም በዓለም ላይ የለም። ለምን የለም? ከተባለ ከማንነት ፖለቲካ ተፈጥሮ ጋር ያለውን ፍልስፍናዊውን ጉዳይ ልተወውና ኣንድ ጥቂት ተግባራዊ ነገር በማንሳት ላሳይ።

የዛሬ 40 ኣመት ገደማ ሁሉም እንደሚያውቀው ህወሃት ይቋቋማል።በዚህ ወቅት ህወሃት ሲፈጠር የነበረውን ህልም ተግባራዊ ለማድረግ ውሎ ኣድሮ ያስባል። ወደዚያ የሚያደርሰው ኣድራሽ፣ ኣድራሽ ብቻ ሳይሆን እስከ ፈለገው ጊዜ እንዲቆይ፣ ጊዜ እንዲያገኝ የሚያደርገው፣ የሚያግዘው የፕሮጀክት ግብዓት ፈለገ። ጥሩ ኣድራሽና ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆነው የተለያዩ ብሄሮችን ስም የያዙ የፖለቲካ ድርጅቶችን መፈልፈል ሆኖ ኣገኘው:: በመሆኑም እንደ ኦህዴድ፣ ብዓዴን የመሳሰሉትን ሁሉ ፈለፈለ። እነዚህ ድርጅቶች የህዝብ ብሶት የወለዳቸው፣ ህዝብ የጠየቃቸው ኣይደሉም። ህወሃት ራሱ ለፕሮጀክቱ ግብዓት ይሆኑለት ዘንድ በኣምሳሉ የቀረጻቸው ናቸው። በሌላ ኣገላለጽ እነዚህ ድርጅቶች ራሳቸው ህወሃት ናቸው። ምንምን እንኳን የተለያየ ብሄር ኣባላትን ይዘው ቢመሰረቱም ተገትረው ብናይም በህወሃት ብሶት፣ በህወሃት ራእይ፣ በህወሃት እጅ የተፈጠሩ በህወሃት የህወሃት ናቸው። ኣንዳንዶቹ ድርጅቶች በተለይም ኦህዴድ እንደሚወራው ኣንዳንድ መሪዎቹ የህወሃት ኣባላት ስማቸውን እየቀየሩ ኣመራር ላይ የነበሩበት ሁኔታም ነበር።

ኣቶ በረከት ስምዖን በህወሃት 40ኛ ዓመት ላይ ንግግር ሲያደርጉ እንዲህ ኣሉ
“እኛ ብአዴኖችም ሁሌም ቢሆን ራሳችንን ከህወሓት ነጥለን ያየንበት ጊዜ የለም። ሁላችንም “ወየንቲ ኢና” (ወያኔዎች ነን) ነው የምንለው።”

(በረከት ስምዖን)

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም ደግሞ ይህንን ያስረግጡልናል።
“አንዳንድ ወገኖች …. ስድብ መስሏቸው “ወያኔ” አሉኝ ከጥቂት አመታት በፊት ለተመሳሳይ ጉዳይ በረከት ስምዖን ያለውን አስታወሱኝ “ሁላችንም ወያኔ ነን” አዎ አሁንም ሁላችንም ወያኔን ነን…..እኔ ወያኔ ኢህአዴግ ነኝ! Je Suis Woyane! …. በዚህም ኩራት ይሰማኛል፡፡ እኔ ወያኔ ነኝ! ሁላችንም ወያኔ ነን! ይህን ችግር የሚፈታውም በወያኔነት ነው! …እንበርታ፡፡”
(ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም)

በኣንጻሩ ከህወሃት ኣባላት መንደር ሁላችንም ኦህዴድ ነን ወይም ደህዴግ ወይም ብዓዴን ለማለት ጨርሶ ታስቦ የማያውቅ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ድርጅቶች እንደ ፖለቲካ ድርጅት በህወሃት ህሊና የሉምና። እንዴውም ኣቶ መለስ እንኳን ከዚህ ቡድን ተወለድኩ ብለው ጠባብና ትምክህተኛነታቸውን በኣደባባይ ሲናገሩ ተደምጠው ነበር። ይሄ ነው ጠባብነት፣ ትምክህትና ኣክራሪነት የሚባለው።
በኣጠቃላይ የሆነ ኣጀንዳ ይዞ የተነሳው ህወሃት ሲሆን በየመንገዱ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆኑትን የፖለቲካ ድርጅቶችን የፈለፈለ ሲሆን እነዚህን ግብዓቶች ይዞ ሁዋላ ላይ “ኢህዓዴግ” የሚል ስያሜ ይዞ ብቅ ይላል። “ኢህዓዴግ” የራሱ የህወሃት ፕሮጀክት ማስፈጽሚያ ሲሆን እንደ ፖለቲካ ድርጅት ግን ኣለ ማለት ኣይቻልም። ለዚህም ነው ራሱ በኣድራሽነት የተሰራውና የሚኖረውም። ግንባር በተፈጥሮው ኣድራሽ ሲሆን ይህ በግንባርነት የተዋቀረ ቤት የዚሁ የህወሃት ሌላው የኣዲስ ኣበባ ቤት ነው። በርግጥ ወደ ተራው ኣባል ኣካባቢ ስናይ የዋህነት ሊኖር ይችላል። ተሰብስበው ግምገማ ሲባል፣ እቅድ ኣውጡ ኣውርዱ ሲባል “ኢህዓዴግ” በህይወት ያለ ይመስላቸው ይሆናል። የለም። ተላላ መሆን ኣያስፈልግም። ህወሃት እነዚህን ድርጅቶች ሲያቆም ኣዲስ ኣበባን ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ከዚያ በሁዋላ ደህንነቱንና ወታደሩን እንዲሁም ኢኮኖሚውን እስኪቆጣጠር ግብዓት ስለሚሆኑት ነው። በርግጥም በኣሁኑ ሰዓት በነዚህ ድርጅቶች እገዛ ህወሃት እነዚህን ህልሞቹን ኣሳክቷል። ኣቅጣጫ ነው ያጣው። በመሆኑም የነዚህ ድርጅቶች ኣባላት መታለሉን ማቆም ኣለባቸው። መንቃትና ለለውጥ መነሳት ያስፈልጋል። በቂምና በበቀል ላይ ሳይሆን ሁሉን ነጻ የሚያወጣ የወደፊቱን በማሰብ ላይ የተመሰረተ ቢሆን ነው የሚሻለው።
በኣጠቃላይ የሚንስትሮቻችን የመሪዎቻችን ታእታይ የፖለቲካ መሰረት የወንዝ ፖለቲካ በመሆኑ ከዚህ የብሄር ፖለቲካ ዘር የሚወለደው ያው ጠባብነትና ኣክራሪነት ከመሆን ኣያልፍም።ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም ከፍ ሲል እንዳየነው እኔ “Je Suis ወያኔ ነኝ” ብለዋል። ይሄ እውነተኛ የፖለቲካ መሰረታቸው ሊሆን ይችላል። የሚገርመው ግን እኚህ ሰው ኣንድ ጊዜ ኒዮርክ በተደረገ ስብሰባ ላይ “ ኒውዮርክ ሜልቲንግ ፖት ናት” ብለው በስሜት ተናገሩ። መልቲንግ ፖት የህወሃት ኣስተሳሰብ ጸር ነው። ባህላዊ ውህደት ማለት ነው ሜልቲንግ ፓት ማለት። እኚህ ሰው ምን ኣልባት ተለውጠው ከሆነ ይህን ያሉት እንዳንል የኒውዮርኩን ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነው እኔ “ Je Suis ወያኔ ነኝ” የሚሉን። እሳቸው ይህን ይበሉ ፣ እኔ ደግሞ Je Suis ኢትዮጵያዊ! እናንተስ?

እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስትር ኣቶ ሃይለማርያም ይህን ዘር ኣጥፊ ነው ብለው ካመኑ በዚህ የወንዜ ፖለቲካ ቤት ውስጥ መዋል ማደር የለባቸውም። ሌሎች ምስጢሩ ያልገባቸው የዋህ የህወሃት፣ የብኣዴን፣የደህዴግ ወዘተ ኣባላት ከዚህ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ ወጥተው ጠባብነትን የህወሃትን የበላይነት መዋጋት ኣለባቸው። የጠባብነትና የትምክህት ዋና የሆነውን የብሄር ፓለቲካ ቤት ግድግዳውንና ጣራውን ለመንደል የውስጥ ኣርበኞች መሆን ኣለባቸው። ለለውጥ መነሳት ኣለባቸው።የተባበረችውን ኢትዮጵያን ለመገንባት ትውልዱ ሁሉ ኣምርሮ መነሳት ኣለበት።የተባበረችውን ኢትዮጵያን የምንገነባው ደግሞ ከብሄር ፖለቲካ ስንወጣ፣ ስምምነት ውስጥ ስንገባ ነው። ይህ ስምምነት የህዝብ ውክልና በሌላቸው በዚህ ኣርባ ኣመት ባፈራናቸው እዚህም እዚያም በተኮለኮሉ ፓርቲዎች መካከል ኣይደለም። ወደ ባህላዊ ቡድኖች ታች ድረስ ወርዶ ህዝቡ ተወያይቶ ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሉን ኣዋጥቶ ኣገሩን እንዲገነባ የሚያደረግ ሰፊ ስምምነት ነው።ለዚህ ደግሞ ኣገሪቱ የሆነ የጽሞናና የሽግግር ጊዜ የሚያስፈልጋት ሲሆን በዚህ ከፍተኛ ኣሳብ ላይ ሁሉም መጠቅለል ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ህወሃት የዘራው ዘር ከፍተኛ ኣደጋ ውስጥ ሊጥለን ይችላል።

ኣዲሲቱ የተባበረችው ኢትዮጵያ ከብሄር ፖለቲካ ወጥታ በተሻለ ውቅር ልትሰራ ይገባል። የማንነት ኪሳራ እንዳይመጣብን በኣንድ በኩል የተደራጀ የባህል መንግስት መስርተን ባህላችንን እየተንከባከብንና እየተደሰትን በሌላ በኩል ፖለቲካዊ ቤት መስራት እንችላለን። እንደ ኢትዮጵያ ብዙ መልካም ታሪክና ባህላዊ እሴቶች ያሉዋትን ኣገር ለማስተዳደር የዚህ ዓይነት ሲስተም መዘርጋቱ ሰላምን፣ ልማትና ዴሞክራሲን ያፋጥንልናል። ከዚህም በላይ ለዜጎች ርካታን ይሰጣል።
ከልጅነት ጊዜየ ጀምሮ በእድሜ የበሰሉ ሰዎች የሚሰጡት ትምህርት ይማርከኝ ነበር። ኣረጋውያን ሲያወሩ ጠጋ ብሎ ማዳመጥ ርካታን ይሰጠኛል ። ከእለታት ኣንድ ቀን እንዲሁ ኣንድ የእድሜ ባለጸጋ ኣገኘሁና በተፈታ ስሜት ወግ ጀመርን:: እኚህ ሰው ከሚናገሩት የሚበዛው ያለፈው ዘመን ምን ያህል የተሻለ እንደነበር ነው። ምን ኣልባት በኢኮኖሚ ጥንት የተሻሉ ነበሩ ማለት ነው፣ ኣሁን ኑሯቸው ኣሽቆልቁሏል ማለት ነው፣ ብየ እንዳላስብ ኣይደለም። ልጆቻቸው የተሻለ ገቢ ኣላቸው። እሳቸውም ድሃ የሚባሉ እንዳይደሉ ኣውቃለሁ። ምንድነው ወደ ኋላ የሚጎትታቸው? ምን ኣጥተው ነው? የሚል ጥያቄ ይዞኝ ነበር። በሳቸው የልጅነት ጊዜ በእግር ነበር ይጓዙ የነበሩት፣ ኣሁን በመኪና ይሄዳሉ፣ የተሻለ ልብስ ፣ የተሻለ ጫማ፣ የተሻለ ምግብ፣ የተሻለ ነገር…. እንዳላቸው መረዳት ችያለሁ። እኚህ ሰውም ይህንን ሁሉ ይደሰቱበታል። ይሁን እንጂ ያጡት ነገር ደግሞ ወደ ሁዋላ ሲጎትታቸው ኣየሁና ሁዋላ ላይ ለራሴ የተረዳሁት ነገር እኚህ ሰው ያጡት ባህል ነው ማለት ነው ብየ ደመደምኩ። በለውጥ ስም የሚወዱዋቸውን ባህሎቻቸውን ኣጥተዋል። ኣንቱ የተባሉ ሽማግሌዎችን ከሰፈራቸው ኣያዩም፣ ክብረ በዓላትን ሲያዩ ይገረማሉ፣ የጠፉ ባህላዊ ተቋማት ይናፍቋቸዋል፣ ወዘተ.

እኚህ ሰው ዘመናዊውን ዴሞክራቲክ የሆነ መንግስት ማየት ይፈልጋሉ። በርግጥ ደግሞ ባህላዊ ተቋሞቻቸው ቢያንስ ከነ ሙሉ ሃይላቸውም ባይሆን በቅርስነት በህይወት ማየት እንደሚፈልጉ ተማርኩ። እኚህ ሰው ኢትዮጵያን ቢወዱም ኣገራቸው የድሮ ሞገሷን የተገፈፈች ኣድርገው እንደሚያስቡ ገመትኩ። ርግጥ ነው ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ባህልን ማጣት እንደ ሃገርም እንደ ዜጋም ይከነክናል ይጎዳልም።ሌሎች የኢኮኖሚ ህይወታቸው እያደር እየደቀቀ የመጣ ሰዎችም እንዲሁ የድሮውን ጊዜ ሲናፍቁ ብዙ ጊዜ እሰማለሁ። ጥያቄያቸው ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ባህላቸውንም እንደናፈቁ መረዳት ይቻላል። ለዚህ ነው ኣዲሲቱ ኢትዮጵያ የተደባለቀውን ፖለቲካዊ ማንነትና ባህላዊ ማንነት በመለየትና በተለያየ ቤት እንዲያድሩ በማድረግ የተሻለ ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋታል የሚያስብለን ። የተባበረችውን ኢትዮጵያን የምንመሰርተውም እንዲህ በጠነከረ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መሰረት ላይ መሆን ኣለበት። ለዴሞክራሲ፣ ለለውጥ የምናደርገው ትግል ሁሉ Je Suis ኢትዮጵያ መርሃችን ኣድርገን የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገንባ። ኢትዮጵያውያን የተባበረችውን ኢትዮጵያን ገንብተን ትኩረታችንን ሁሉ በምግብ ዋስትና ላይ ልናደርግ ይገባናል። ተመልከቱ እስቲ። ኢትዮጵያ ባለፉት ኣስር ኣመታት ያለማቋረጥ በጥንድ ቁጥር እያደገች ነው ተባለ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ በምግብ በብሄራዊ ደረጃ ራሷን ቻለች ኣሉ። እነሆ በማግስቱ ዛሬ በጥቂት ወራት ውስጥ ለ4.5 ሚሊዮን ህዝብ ኣስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል ተባለ። የተባበሩት ህዝቦች ድርጅት የሰባዊ መብት ኣጋር ድርጅትና መንግስት ይህን ገልጸዋል። በእኔ እምነት ይህም ይፋ የሆነው በተባበሩት ህዝቦች ድርጅት ቅስቀሳ እንጂ መንግስት ይህ ነገር ወደ ኣደባባይ ሳይወጣ የሆነው ቢሆን የሚመርጥ ነው የሚመስለኝ። የሚገርመው ዛሬ በብሄራዊ ደረጃ ራሳችንን በምግብ ቻልን ያሉን ጠቅላይ ሚንስትር ለተራቡ ሰዎች ቀለብ ለመግዛት ከሚያስፈልገው ተጨማሪ $ 230 ሚሊዮን ውስጥ $33 ሚሊዮን የሚሆነውን ብቻ ነው መንግስት መሸፈን የሚችለው። ቀሪውን 200 ሚሊዮን ገደማ ዶላር ባስቸኳይ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ርዳታ እንዲያደርግ ልመና ጀምረናል። ይህ ማለት ደግሞ በምግብ በብሄራዊ ደረጃ ራሳችንን ኣልቻልንም ነበር ማለት ነው። ለብዙ ዓመታት በጥንድ ቁጥር ኣድጊያለሁ ዓለም ያጨብጭብልኝ ስትል የነበረች ኣገር ዛሬ ለጥቂት ወራት እንኳን ዜጎቿን መታደግ ኣልቻለችም። ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብስ ምነው ዛሬ ጠዋት በምግብ ራሳችንን ቻልን ብልችሁ የለም እንዴ? ቢለን ……ያሳፍራል። ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች በውነት ኣጃንዳቸው ሁሉ ይህ ነው ሊሆን የሚገባው። ይህቺን ኣገር በምግብ ራስዋን የማስቻል ስራ ነው መቅደም ያለበት። ሰው በሚራብበት ኣገር የብሄር ፖለቲካ ቅብጥርሴ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው። ለውጥና ሪፎርሜሽን ይመግበናል፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን ይፈታልና ለለውጥ ታጥቀን እንነሳ።

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

geletawzeleke@gmail.com

↧

የሕወሓት ሊቀመንበርነት ሽኩቻ እየተደረገበት ይገኛል

$
0
0

Arkebe Equbay - Ethiopia
አምዶም ገብረስላሴ እንደዘገበው

የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል።

ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ።

የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው።

ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የኣባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት ኣድርገዋል።

እንዲሳተፍ የተቀሰቀሰው ” ኣርከበ የመጣው ለሊቀ መንበርነት ሳይሆን በባቡርና ኢንዳስትሪ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ ነው። ስለዚ ቢሳተፍ ችግር የለውም ” የሚል ተነግሮሯቸው ነው።

“ኣባይ ደራ” የሚል የበረሃ ስሙ በመጥራት ” ከመለስ ሞት በሗላ ድርጅቱ ኣጋጥሞት የነበረው ከፍተኛ ችግር ያለ ኣባይ ደራ ምርጥ መሪነት ድርጅታችን ለመበታተን ይዳርጋት ነበር ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ተምረው ኣጥብቀው በመያዝ ኣሁንም ሌላ ኣማራጭ እንደሌለ ኣምነው ለማስፈፀም ተዘጋጅተዋል።

ወፍ የለም “ኣባይ ደራ ” የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ሲቆጣጠሩ የቴሌው ኔትወርክ ደግሞ ዶክተር ደብረፅዮን በእጃቸው ይገኛል።
ኣባይ ወልዱ የቴሌው ኔትወርክ ለመቆጣጠር ሞባይል ስልክ ወደ ኣዳራሽ እንዳይ ገባ ኣድርገዋል።

እነ ዶክተር ደብረፅዮን ደግሞ የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ እንዳይሰራ መበተን ይጠበቅባቸዋል።
ለውጥ ……………… የምትጠብቁ የዋሆች እርማቹ ኣውጡ።

በስብሰባው ኣንድ ተሳታፊ ህዝቡ ክፉኛ ተቀይሞናል፣ የመረጠንም ዕሬት ዕሬት እያለው ነው። ስለዚ ለውጥ የህልውናችን ጉዳይ ነው። ኣለበለዚያ ጥፋት ቅርብናት በማለት የተናገረው ደማቅ ጭብጨባ ኣስገኝቶለታል።

ስብሰባው ከተያዘለት ግዜ በላይ እንደሚፈጅ ታውቋል።
የመቐለ ከሓወልቲ እስከ ኣክሱም ሆቴል ያሉ ጎዳናዎች በቖልዑ ኣሸንዳ ምትክ ብሬን የጫኑ ፓትሮል የፌደራል ፖሊስና የክልል ልዩ ሃይል እየጠበቁ ነው።

↧

Health: በዕርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነቱ በምን መልኩ ሊቀጥል ይገባል?

$
0
0

እርግዝና እና ወሲብ
እስከየት ድረስ

በእርግዝና ወቅት ስለ ወሲብ ማሰብ ለነብሰጡር ሴቶች የመጨረሻው ከባድ ተግባር ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ በማቅለሽለሽ እና በማስመለስ እንዲሁም ድካም በሚበረታበት በዚህ ወቅት አንዳንድ ሴቶች የወሲባዊ ግንኙነት ፍላጎታቸው ሊቀስቅስ ይችላል፡፡ የወንድ ተጣማሪያቸውም በተመሳሳይ አንዳንዶች ግንኙነቱ ስሜትን በማስቀደም ብቻ ሊፈፅሙት ሲነሳሱ ሌሎቹ ወንዶች በአንፃሩ ህፃኑን እና ነብሰጡር ወዳጆቻቸውን ላለመጉዳት በማሰብ ወሲባዊ ግንኙነትን በዚህ ወቅት በእጅጉ የሚፈሩት ተግባር ይሆናል፡፡ አልጋ ለይቶ የማደር ሃሳቡ የሚመነጨውም ለዚሁ ሊሆን ይችላል፡፡ በአሜሪካ ኖርዝ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ አሶሽየት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ዳይና ሳለሰች ‹‹በእርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ ጥሩም መጥፎም ዜና ይዞ የሚመጣ ሊሆን ይችላል›› ይላሉ፡፡ የሴቶቹ እርግዝና ያልተወሳሰበ መሆን እና ዝቅተኛ አደጋ የሚያስከትል መሆኑ ሲረጋገጥ እንዲሁም የተጓዳኞች የግል አተያይ መሰረታዊ መሆኑን ከግምት እንድናስገባ ይመክሩናል፡፡ አንዳንዶች በዚህ ወቅት ወሲብን ይበልጥ ሲያጣጥሙት ሌሎች ደግሞ ዝቅተኛው የደስታ ምንጭ አድርገው ይወስዱታል፡፡
Premature Ejaculation 1
በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወቅቶች ማለትም ሴቶች የማጥወልወል እና የድካሙ ስሜት ውስጥ ሲሆኑ ብዙዎቹ ከፍተኛ ወሲብ ፍላጎት አያሳዩም ነው ባለሙያዋ የሚሉት፡፡ በሁለተኛው ዙር የእርግዝና ወቅት ደግሞ በአንፃራዊነት የተሻለ የሚባል ስሜት ውስጥ ይገባሉ፡፡ በተለይ የመራቢያ አካላቸው ላይ በተለየ ሁኔታ የሚመነጨው ዘይትም ለወሲባዊ ግንኙነት ይበልጥ እንዲሳቡ ምክንያት ይሆናል ባይ ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት ነብሰጡር ሴቶች ከወሲባዊ ግንኙነት ብዙ እንዲርቁ ከሚያደርጋቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ደግሞ ሆዳቸው በዚህ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ የክብ ቅርፅ የሚይዝ በመሆኑ ነው፡፡ ይሄ በሶስተኛው የእርግዝና ዘርፍ የሚጠበቅ አይደለም፡፡

ሆድ ሲገፋ እንዲሁም ድካምም በእጅጉ ሲበረታ የወሲብ ስሜቱ በዛው ልክ እየቀዘቀዘ ይመጣል፡፡

ዶ/ር ሳላሰች እንደሚሉት ባለቤት የፍቅር ጓደኛ ወደ መጨረሻዎቹ ወራት እየተቃረበች ከመጣችው ከነብሰጡር ጓደኛ ጋር ወንዱ ወሲባዊ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎቱ ከተነሳሳ ብዙ መጨነቅ አይገባም ይላሉ፡፡ በእንቁላሉ በሚገባ የተከለለ በመሆኑ ህፃኑ በምንም መልኩ ለአደጋ የተጋለጠ ሊሆን አይችልም እና፡፡ ባለሙያዎች ሴቶች በእርግዝና ምክንያት ለውጥ ውስጥ ሲያልፉ ለትዳር አጋራቸው አሁንም ያልበረደ ፍቅር እንዳላቸው ማሳየት፣ እርስ በርስ የመግባባት መስመሩም በተሻለ መንገድ እንዲቀጥል ማድረግ ይኖርባቸዋል ይላሉ፡፡

በዕርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነቱ በምን መልኩ ሊቀጥል ይገባል?

ሴቷ የእርግዝና ወቅቷ እየጨመረ እና ሆዷም እየገፋ ሲመጣ ባህላዊና የተለመደው ወሲባዊ ቅርፅ ማለትም ወንዱ ከላይ የመሆን አቅጣጫ ምቾት የሚሰጣት አይሆንም፡፡ በዚህ ምክንያት ሳልስቼን ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎች ከመሀል ወይም ፊት ለፊት የመተኛት የግንኙነት አቅጣጫዎችን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ ያስገነዝባሉ፡፡ ከዚያ ባለፈ ባሎቻቸው በጀርባቸው እንደተኙ አጠቃላይ የወሲባዊ ግንኙነትን ሂደት ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር በሚችሉበት አቅጣጫ ማለትም ከላይ እንዲሆኑ ይመከራል፡፡

በተወሰኑ ደረጃዎችም ነብሰጡር ሴቶች በጀርባቸው ብዙ እንዳይተኙ ይመከራሉ፡፡ ምክንያቱም የለብ ምት እና የደም ግፊትን ሊያስከትሉባት የሚችሉት ሰፓይን የሀይፐርቴንሲቭ ሲለንድሮምን ያስከትላልና፡፡ ችግሩ በተለይ ሴቷ በሶስተኛው እርግዝና እርከን ላይ ስትገኝ ይበልጥ የከፋ የመሆን ዕድል አለው፡፡
በግንኙነት ወቅት ምንም አይነት ችግር የማይገጥማት እናት ያለ ችግር በሂደቱ መቀጠል ትችላለች፡፡ ነገር ግን ከወሲብ በኋላ መድማትና ሌሎች ህመሞች የሚከተሉ ከሆነ የቀይ መስመሩ እየታለፈ ስለመሆኑ ማሳያ ነው እና በአፋጣኝ የህክምና ዶክተሮችን ማማከሩ ተገቢ ነው፡፡ ነብሰጡር ሴቶች በመሰል ግንኙነት ወቅት በትልቁ ትኩረት ይሰጡበት ዘንድ ባለሙዎች ከሚያስጠነቅቁት ሁኔታ መካከል አንዱ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት በሚተላለፉ በሽታዎች የተጠቃ የትዳር አጋር ካላቸው ኮንዶምን ጨምሮ ሌሎች መከላከያ መንገዶችን በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት እንዲጠቀሙ ነው፡፡
ባለሙያዋ ዶ/ር ሆፍማን በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ነብሰጡር ሴቶች በተቻለ መጠን ሰውነታቸውን ማዳመጥ እና ከጓደኛ ጋር ግልፅ የመሆንን አስፈላጊነት ያሰምሩበታል፡፡

በሌላ መልኩ ነብሰጡር እናቶች በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ሊያገረሹ የሚችሉ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ የመሆን ስጋት ካለባቸውና የተቃራኒ ፆታ አጋራቸው ትብብርም የሚፈልጉትን ያህል ካልሆነ በራሳቸው የሌቴክስ የሴቶች ኮንዶምን በግንኙነት ወቅት መጠቀም እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ሆፍማን ያስገነዝባሉ፡፡ ሌቴክስ ኮንዶሞች ውጤታማ ካልሆኑ ደግሞ ሌሎች የሴት ኮንዶሞችን መሞከር ጠቃሚ ነው፡፡
ደጋግመው ሁሉም ባለሙያዎች የሚያሳስቡት በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ምቾት የሚነሱ ሁኔታዎች ነብሰጡር ሴቶች ሲገጥማቸው በተቻለ መጠን ለተጣማሪያቸው ወዲያው ማሳወቅ ያለባቸው መሆኑን ነው፡፡ የወሲብ ስሜቱ ቢኖር እና በሌላ መልኩ በተለመደው መልኩ ግንኙነቱን ማድረግ አስቸጋሪ ከሆነ ደግሞ ሌሎች የስሜት መቆጣጠሪያና ኤሮቲክ ተግባራትን ማጤን ይመከራል፡፡ ከወሲብ እኩል ስሜታችንን ልናቀዘቅዝባቸው የምንችላቸው እንደ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ እና መተሳሰቡ በራሱ የተሻሉ መፍትሄዎች ናቸው፡፡
ወሲባዊ ግንኙነት በእርግዝና ወራትም የሚቀጥል ተፈጥሯዊ ጉዳይ ነው፡፡ ባለሙያዎቹም ደጋግመው ጤናማ እርግዝና የሚያሳልፉ ሴቶች መሰል ግንኙነት በራሳቸውም ሆነ በተሸከሙት ልጅ ላይ ሊከሰት የሚችል ችግር አይኖርም፡፡ በተፈጥሮ መጠበቂያ ግንቦች በሚገባ የተከለለ በመሆኑ፡፡
አንዳንዶቹ የህክምና ባለሙያዎች ነብሰጡሮች ወሲባዊ ግንኙነትን በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወራት እንዲያስወግዱ ይመክራሉ፡፡ ሊከሰት የሚችለውን ችግር በሚገባ በማስረዳት ረገድ ርቀው መሄድ ባይችሉም፡፡

በእርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነትን እንድናስወግድ የሚያስገድዱ ምክንያቶች
ሐኪሞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩና በእርግዝና ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮች ካሉብሽ ወሲብን እንዳትፈፅሚ ሊከለክልሽ ይችላል፡፡
– የመራቢያ አካል ላይ የሚከሰት የመድማት ችግር ካለብሽ
– መንታ አልያም ከሁለት በላይ ልጆችን እንደምትወልጂ ተነግሮሽ በዛ መሰረት የመውለጃ ጊዜሽን እየጠበቅሽ ከሆነ (ከ37 ሳምንታት በፊት) የመውለድ ስጋት እና ታሪክ ካለሽ
– የማህፀንሽ በር ያለ ጊዜ የመለጠጥ እና የመከፈት ምልክት የሚያሳይ ከሆነ…

ልጅሽን ከወለድሽ በኋላ መቼ ነው ወደ ግንኙነት መመለስ ያለብሽ?
ልጅሽን በተፈጥሮ መንገድ፣ በቀዶ ጥገናና ወይም በሌላ የህክምና እርዳታ ከወለድሽ በኋላ ሰውነትሽ ስለሚዳከም ለማገገምና ወደ መደበኛው የወሲብ ህይወት ለመመለስ ጊዜ መውሰድ ይኖርብሻል፡፡ ብዙዎቹ የጤና ባለሙያዎች ከወሊድ በኋላ ሴቶች በትንሹ እስከ 6 ሳምንት ከመሰል ግንኙነት መታቀብ አለባቸው በሚለው የጊዜ መመሪያ ላይ ይስማማሉ፡፡ የጊዜ ገደቡ ሴቷ የማህፀን በሯ ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመለስ ቁስሎችም እንዲሽሩ ይረዳል፡፡
ወደ መደበኛ ወሲባዊ ህይወትሽ ስትመለሺ ግንኙነቱን ቀስ ብለሽ መጀመር ይኖርብሻል፡፡ ያልተፈለገ እርግዝናን እና ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም የአባላዘር በሽታዎች የመጠቃት እድሉ አሁንም ያለብሽ እንደሆነም መድሐኒቶችን እና መከላከያዎችን መጠቀም ይኖርብሻል፡፡

↧
↧

በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ

$
0
0

ከኤልያስ ገብሩ

ሰኔ 01 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በነጻ እንዲሰናበቱ በችሎቱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ ከቂሊንጦ እስር ቤት መፈታት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ በዛሬው ዕለት ማረሚያ ቤቱ ላይ ክስ መቅረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ ከላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ፍርድ ቤቱ፣ በክሱ ከተራ ቁጥር 2-5 እና 7ኛ ተከሳሽ ክሱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የመፍቻ ትዕዛዙን በ15/12/2007 ዓ.ም ለማረሚያ ቤቱ ቢደርስም ተከሳሾቹ እስከአሁን ድረስ ከእስር ሊለቀቁ አለመቻላቸውን ይጠቅሳል፡፡
በመሆኑም ‹‹ፍርድ ቤቱ ይህንን ባደረጉ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ላይ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ጋር ተከሳሾቹን እንዲለቅ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ በማክበር አመለክታለሁ›› ሲሉ ለ2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም አዛናው እና ለ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ መሠረት ገ/ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ትዕዛዙን ለሰጠው ችሎት ክሳቸውን ማቅረባቸው ታውቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በነጻ ካሰናበታቸው ተከሳሾች መካከል አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ችሎት በመድፈር ወንጀል ሁለት ጊዜ ያህል መቀጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ሕግ በአምስቱም ተከሳሾች ላይ ይግባኝ ጠይቆ ከእስር እንዳይፈቱ ዕግድ አቅርቦ ነበር፡፡ እንዲሁም የተቀሩት አምስት ተከሳሾች እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

↧

የጋሞን ሕዝብ በሚያንቋሽሸው መጽሐፍ የተነሳ የደቡብ ክልል አመራሮች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው

$
0
0

ኢሳት ዜና :-በታደለ ቱፋ የተጻፈውን የጋሞን ህዝብ ማንነት የሚያንቋሽሸውን መጽሃፍ ፣ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች የገንዘብ ደጋፍ በማድረግ አስጽፈውታል በሚል ምክንያት ፣ በአርባምንጭና በተለያዩ የጋሞ ወረዳዎች የተቃውሞ ሰለፎች መደረጋቸውን ተከትሎ፣ በከፍተኛ አመራሩ እና በታች አመራሩ መካከል ያለው አለመግባባት ይፋ ሆኗል።
debub ethiopia

ለኢሳት የደረሰው የድምጽ ማስረጃ ከመጽሃፉ ጋር በተያያዘ ቀደም ብሎ ኢሳት በአመራሩ መካካል ልዩነት መፈጠሩን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ የሚያረጋገጥ ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬ፣ የጋሞ ጎፋ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የደኢህዴን ባለስልጣናት እጃቸው አለበት በሚል የሚያናፍሱት ወሬ ትክክል አይደለም በማለት፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጥፋታቸውን እንዲቀበሉ ጫና አድርገዋል። የወረዳ አመራሮች በተለይም የጨንጫ እና የአርባምንጭ የወረዳ አመራሮች ሂሳቸውን ወይም ጥፋታቸውን ለመቀበል ዝግጁ ካልሆኑ፣ የጥገኞች አስተሳሰብ አራማጆች ተብለው እንደሚፈረጁ በፕሬዚዳንቱ ተነግራቸዋል።
የወረዳ አመራሮች ከመጽሃፉ ጋር በተያያዘ ” ህዝቡ ከአመራሩ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኗል” ቢሉም፣ የክልል መሪዎች ” ሊቀበሉት ፈቃደኞች አልሆኑም።

ፕሬዚዳንቱ መጽሃፉን ደኢህዴን እንደላስጻፈውና እንዲያውም ሁሉም የድርጅቱ መሪዎች ደራሲውን ማውገዛቸውን ገልጸዋል። ምንም እንኳ ደራሲው ታስሮ በዋስ የተፈታ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንቱ ግለሰቡ ተመልሶ እንዲታሰርና ፍርድ ቤት የዋስትና መብቱን ጠብቆ የሚፈታው ቢሆን እንኳ፣ እርሳቸው እንደማይፈቱት በመናገር፣ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ከህግ በላይ ወይም ከፍርድ ቤት በላይ መሆናቸውን አስመስከረዋል፡፡

ይህ አንድ መጽሃፍ እርስ በርስ እንድንጠራጠርና እንዳንተማመን ካደረገን፣ እስከዛሬ አብረን የተጓዝነው ጉዞ የውሸት ነበር ያሉት መሪው፣ መጽሀፉ የድርጅቱን መዋቅር እንዲፈትሹ እና የደኢህዴንን የድርጅት ጥንካሬና በአመራሩ መካካል ያለውን መተማመንና መደጋገፍ እንደገና እንዲመረምሩ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል።
debub ethiopia1

በሌላ በኩል ዶ/ር ካሱ ኢላላ ከአመራር ቦታ ላይ ሲነሱ ዶ/ር ሽፈራው ደግሞ ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት ተነሱ::
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ደኢህዴን/ ጉባኤ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የድርጅቱ የስራ
አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን የመረጠ ሲሆን፣ በሕዝበ ሙስሊሙ ጠላት ናቸው የሚባሉትን ዶ/ር
ሽፈራው ተ/ማርያም ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት አሰናብቶ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ አድርጓቸዋል። ዶ/ር ካሱ ኢላላን በመተካካት ስም ሸኝቶአል፡፡

ጉባዔው 65 አባላት በማዕከላዊ ኮምቴ አባልነት የመረጠ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ዘጠኝ ያህሉ ማለትም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ ደሴ ዳልኬ ፣ ተስፋዬ በልጂጌ ፣ ሲራጅ ፈጌሳ ፣ ሬድዋን ሁሴን ፣ መኩሪያ ሀይሌ ፣ መለሰ አለሙ ፣ ተክለወልድ አጥናፉ እና ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚዎች ሆነዋል።

↧

Sport: ገንዘቤ ዲባባ ያሸነፈችው በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፖለቲካዊ አድሎ ፣ አድርባይነትን እና ቃላባይነትን ሁሉ ነው

$
0
0


BEIJING, CHINA - AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women's 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)

BEIJING, CHINA – AUGUST 25: Genzebe Dibaba of Ethiopia celebrates after winning gold in the Women’s 1500 metres final during day four of the 15th IAAF World Athletics Championships Beijing 2015 at Beijing National Stadium on August 25, 2015 in Beijing, China. (Photo by Cameron Spencer/Getty Images)

(ኢብራሂም ሻፊ)

ገንዘቤ ዲባባ ዛሬ ድልን ተጎናፅፋ የኢትዮጵያ ህዝብ ኩራት ትሁን እንጂ ቤይጂንግ ከመምጣቷ በፊት የተቀናጀ የስም ማጥፋት ሲካሄድባት እና የተለያዩ ውሃ የማይቋጥሩ ክሶች ሲቀርቡባት የከረመች አትሌት ናት፡፡ የዚህ የተቀናጀ የስም ማጥፋት እና ክስ አቀናባሪ ደግሞ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ (በዋናነት ዱቤ ጅሎ) ነበር፡፡ የቱታ እና ስኒከር ጫማ እርጥባን የሚጥልላቸው አንዳንድ “ጋዜጠኞች” ደግሞ የስም ማጥፋቱ እና የክስ ማርቀቁ ተባባሪዎቹ ነበሩ፡፡

ገንዘቤ ያለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፍቃድ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሆናለች ተብላ ተከሳለች፡፡ አዎን በእርግጥም ገንዘቤ ያለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፍቃድ ዳይመንድ ሊግ ሮጣለች፡፡ ሞናኮ ላይ የዓለም 1500 ሜትር ሪከርድ ያሻሻለችው አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ሳይፈቅድላት ነው፡፡ እዚህ ላይ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ “አትሩጡ” ቢልም ለምን አትሩጡ እንዳለ አጥጋቢ ምክንያት አልነበረውም፡፡ የቱታ እና ስኒከር እርጥባን ተቀባዮችን “ጋዜጠኞች” ምክንያትን ሰምተን የፌዴሬሽኑ ምክንያት ነው ካልን “ፋቲግ” (ድካም) እንደ ሰበብ ቀርቦ ነበር፡፡ እግዜር ያሳያችሁ ሞናኮ ላይ የዳይመንድ ሊግ ውድድሩ የተደረገው ጁላይ 17/2015 ነበር፡፡ ድካም እንደ ሰበብ የቀረበው ኦገስት 22/2015 ለሚደረግ ውድድር ነው፡፡ አንድ ውድድር ከወር በላይ ቀርቶት ገንዘቤን “አትወዳዳሪ……ትደክሚያለሽ” ማለት ምን ዓይነት ሙያዊ ውሳኔ ነው? አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ይሄን ሰበብ አድርጎ በዓለም ቻምፒዮንሺፑ 1500 ሜትር እንደማትሮጥ አሳውቆ ነበር፡፡ ገንዘቤ የግድ እንደምትሮጥ ስታሳውቅም ያደራጃቸውን ጋዜጠኞች ተጠቅሞ “ፋቲግ…..ፋቲግ……..” እያለ ውርድ ከራሴ የሚመስል አይነት ማስታወቂያም ሲሰራ ሰንብቷል፡፡ በጣም የሚገርመው አሁን የዓለም ቻምፒየንሺፑን ድሎች እየተቆጣጠሩ የሚገኙት ከሞናኮ በኋላ በለንደን ጁላይ 24/25 (ሁለት ቀናት) አሸናፊ የነበሩ አትሌቶች ናቸው፡፡ ሞ ፋራህ፣ ዩሴን ቦልት እና ዳቪድ ሩዲሺያ ለዚህ እንደማስረጃ መነሳት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች ከገንዘቤ በኋላ ዳይመንድ ሊግ ለሮጡ የውጪ ሀገር ሯጮች “ፋቲግ” ሲሉ አትሰሙም፡፡ የእነርሱ እኮ ርቀቱ አጭር ነው የሚል ሰበብ እንዳይቀርብ ደግሞ ሞ ፋራህ ለንደን ዳይመንድ ሊግ የሮጠው 3000 ሜትር ነው፡፡ ይኽን ርቀት 7፡34.66 ፉት ብሎት ኦገስት 22/2015 የዓለም 10000 ሜትር ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ የ5000 ሜትር ውድድሩን በድል ለመወጣትም ቀናት እየተጠባበቀ ነው፡፡ “ፋቲግ” የሚለው ቃል ሞ ላይ አይሰራም ገንዘቤ ላይ ግን ይደሰኮራል፡፡

ገንዘቤ ከጓደኞቿ (ኢትዮጵያዊያን ሌሎች አትሌቶች) ጋር አልተለማመደችም ተብላ ተከሳለች፡፡ እኔ ደግሞ ይኽች ዕፁብ አትሌት ለምን ብቁ ባልሆነ አሰልጣኝ ትሰለጥናለች? ለምን ከብቃቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ተቀባይነቱን በሚያስቀድም አሰልጣኝ ትሰራለች? ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ ገንዘቤ በሞስኮው የዓለም ቻምፒዮንሺፕስ 1500 ሜትርን ተወዳድራ ስምንተኛ ከወጣች ወዲህ የወሰነችው ምርጡ ውሳኔ ከታታሪው አሰልጣኝ ጃማ አደን ጋር መስሯቷ እና የልምምዷን አጠቃላይ መልክ መቀየሯ ነው፡፡ ጃማ አደን ሱዳናዊውን አቡበክር ካኪን (800 ሜትር) የዓለም ሻምፒዮን እንዲሁም ፤ አልጄሪያዊውን ቶውፊቅ ማክሉፊን (1500 ሜትር) የኦሊምፒክ አሸናፊ ማድረግ የቻሉ ድንቅ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በቤይጂንጉ የዓለም ሻምፒዮን ከገንዘቤ በተጨማሪ ሙሳብ ባላ (800 ሜትር) እና አያልነህ ሱሌይማንን (1500 ሜትር) የመሳሰሉ ምርጥ አትሌቶችን የሚመሩ ምርጥ አሰልጣኝ ናቸው፡፡

ገንዘቤ በእርሳቸው መሰልጠን ከጀመረች በኋላ ከቤት ውስጥ ውድድሮች አሸናፊነት ወደ ሁሉም መስክ አሸናፊነት ቀይረዋታል፡፡ የ2015 አንዳንድ ድሎቿን ብንመለከት ይሄን ይመሰክራሉ፡፡ ዩጂን፣ ኦስሎ እና ፓሪስ ላይ የተደረጉ ተከታታይ የ5000 ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ልዕልቷ ሳትቸገር አሸንፋቸዋለች፡፡ ሞናኮ ላይ እርሷ የአንድ ዓመት ህፃን ሳለች (ከ22 ዓመታት በፊት የተመዘገበ) በቻይናዊቷ ኩ ዩንዢያ የተያዘውን 1500 ሜትር ሪከርድ ሰብራለች፡፡ ከ2014 ጀምራ 1500፣ 3000 እና 5000 ላይ የተፎካከሯትን በሙሉ ረታለች፡፡ ታዲያ ይህን ድል እንድታስመዘግብ የረዳት አሰልጣኝን ጥላ ስራውን ከፖለቲካ ፓርቲ በተሰጠው መታወቂያ ወደሚያፀድቅ አሰልጣኝ ለምን ትጓዛለች?

ገንዘቤ የዛሬውን እና መጪዎቹን ድልሽን ለእልፍ ዓመታት ስንዘክረው እንከርማለን፡፡ ዛሬ ኬንያውያን እና ሆላንዳዊያንን ጭምር አላሸነፍሽም፡፡ በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፖለቲካዊ አድሎ፣ ፍርደ ገምድልነት፣ ምክንያታዊ ያልሆነ ውሳኔን፣ አድርባይነትን እና ቃላባይነትን ሁሉ አሸንፈሻል፡፡ በድጋሚ እንኳን ደስ ያለሽ ገንዘቤ……….!!!

↧

“ቴዲ አፍሮ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል”– (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

$
0
0

የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ቀጣዩን ስጋቱን በፌስቡክ ገጹ እንዲህ ነበር የገለጸው:: ተካፈሉት::

ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው::
teddy afro
ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ ባውቅም ትዕግስትም ልክና ድንበር አለውና የሰሞኑ ግፊትና ግፍትሪያ ከመራር ውሳኔ ሊያደርሰው እንደሚችል አምኜአለሁ::
ቴዲ ከእናቱ ቤት መሀል አዲስ አበባ እሱ ወደ ሚኖርበት ሲ ኤም ሲ በየጊዜው ሲመላለስ በደህንነቶች ታጅቦ: በመንገድ ላይ እያስቆሙ መከራውን አሳይተው በሚፈትሹት የህወሀት ሰዎች ተንገላቶ መሆኑ አስገራሚ ነው:: ቤቱ በደህንነቶች እጅ ላይ ወድቋል:: ዙሪያውን ይቆጣጠሩታል:: እንዳሻቸው እየጠሩ ያስፈራሩታል:: ከተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛለህ በሚል ክብረ ነክ ምርመራ ያደርጉበታል:: በቅርቡ ባለቤቱ ታማ ወደ ኬኒያ ይዟት ሊሄድ ሲል መንቀሳቀስ የጀመረን አውሮፕላን እንዲመለስ አድርገው እንደ ወንጀለኛ በተሳፋሪ ፊት እየገፈተሩ ወስደውታል:: በተደጋጋሚ የውጭ ጉዞዎቹ እንዲሰረዙ አድርገዋል:: በርካታ ሌሎች ጥቃቶችን ፈጽመውበታል:: ለፊታችን አዲስ ዓመት በላፍቶ ያዘጋጀው ኮንሰርትም ሊሰረዝ እንደሆነ ከውስጥ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል:: በአዲስ አበባ ለህወሀት የሚጮሁ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የላፍቶው ኮንሰርት የሚሰረዘው በስፖንሰር እጦት ነው በሚል ቢያራግቡም እውነታው ግን የምንመርጥልህን እንጂ የመረጥካቸውን ዘፈኖች አታቀርብም ብለው ጣልቃ በገቡ የደህንነት ሰዎች ግፊት ነው::

ቴዲን ህወሀት ከሀገር ገፍትሮ ሊያስወጣው እየሞከረ ነው:: መንፈሰ ጠንካራ የሆነው ቴዲ እስከአሁን በትዕግስት እየመከተ ነው:: ሰው ነውና መንግስትን የሚያክል ሃይል ተነስቶበት ብቻውን ይመክታል ማለት አይቻልም:: ከጎኑ መቆም ግድ ይላል:: ህወሀት ቴዲ ላይ አይደለም ሰይፍ የመዘዘው:: ትውልዱ ላይ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ላይ ነው::

↧
↧

Health: ለመልካም ትዳር 7 መልካም የንግግር ጥበቦች

$
0
0

sad couple

ባልና ሚስት ተፋቅረው እንደተጋቡ አንዳቸው ለአንዳቸው እምነት እንዳላቸው ያስባሉ፡፡ ስለዚህም አንዱ ለአንዱ መልካም ባል ወይም ሚስት መሆኑንን ወይም መሆኗን የትዳር አጋሩ ወይም አጋሯ እንደሚያምኑ ስለሚታሰብ ያንን በአንድም በሌላም መልዕክቶች ውስጥ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ

ሚስት ትጠይቃለች፥«ጉዳዩን ጨረስክ?»

ባል «ጨርሻለሁ»

«መፅሃፉን የት አደረግከው»

«መደርደሪያው ላይ አለ»

«ዛሬ አንድ ጉዳይ ነበረኝ ልጆቹን ከትምህርት ቤት ብታመጣቸው»

«እኔም አይመቸኝም»

ድርቅ ያለ ንግግር፣ የፍቅር ቅመም የጎደላቸው ቃላት፣ ወዳጃዊ ያልሆኑ አቀራረቦች::

የእናንተንስ ጎጆ ከስሩ ታውቃላችሁ? የመጠላላት የመኮራረፍ ያለመረዳዳት ያለመተጋገዝ የስልቸታ ሁሉ

ምንጩ የምትነጋገሩበት አግባብ፣ የምትነጋገሩበት ጊዜ፣ የምትነጋገሩበት ስሜትና የመሳሰሉት ተደማምረው የትዳራችሁን ደስታ ይነጥቃሉ ይላሉ የጋብቻን ጉዳይ የሚመረምሩ ምሁራን፡፡ በአነጋገር ስሜቶች ያለመጣጣም ደስተኛ ወዳልሆነ የትዳር ጎጆ ይመራል፡፡ መልካም ያልሆነ የንግግርና የስሜት አለመጣጣምም ለረጅም ግብ የታሰበውን ትዳር መራር ያደርጋል፡፡ በአንዳንድ ወዳጆቻችሁ ቤት ጎራ ትሉ ይሆናል፡፡ በቤቱ ወስጥ የሰው ህይወት የሌላ እስኪመሰል ድረስ በሚያስፈራ የፀጥታ ድባብ ተውጦ በባልና ሚስቱ ዘንድ ያለው የንግግርና የስሜት መራራቅ እንደተራራ ገዝፎ አይታችሁት ይሆናል፡፡ ድርቅ ያለና ጣዕም የሌለው ንግግር፣ ግዴለሽናትና ስልቸታን የተሞላ ምልልስ ትሰማላችሁ፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ፊት ለፊት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ጀርባ በሁለቱ መካከል ያለው የንግግርና የስሜት መጣጣም ጥያቄ ውስጥ መግባቱን ታያላችሁ፡፡

የግንኙነት ክህሎት በትዳር ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ብዙ የሥነልቡና ሊቃውንትም በዚህ ይስማማሉ፡፡ መቼም ትዳር ሲባል በሁለት ሰዎች ማለትም በወንድና ሴት መሀል ለዘላቂ ሕይወት የሚደረግ ተፈጥሮን መሠረት ያደረ ጥልቅ ግንኙነት ነው፡፡ በመሆኑም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ሐሳብ፣ መረጃ፣ ስሜትን እና የመሳሰሉትን ለኑሮአቸው የሚበጁ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በየዕለቱና በየሰዓቱ በቃል፣ በጽሑፍ ወይም በምልክት መልእክትን ይለዋወጣሉ፡፡ ግንኙነት ሲባልም ሁልጊዜም ታሳቢ የሚሆኑት መልእክት ሰጨው፣ መልእክት ተቀባዩና መልእክት ማድረሻ ምህዋር፣ በዚያ ላይ ተጽዕኖ የሚሳድሩ እንቅፋቶችና ግብረ መልሶች ናቸው፡፡

የትዳር አጋሮች አንዱ ለአንዱ በሚኖራቸው ግንኙነት ውስጥ መልእክትን ማለትም ሊያስተላልፉ የፈለጉት የሐሳብ፣ የስሜት ወይም የመረጃ ይዘትን ይመለከታል፡፡ በትዳር ውስጥ ለአጋራችን የምናስተላልፈው መልእክት ይዘት በትዳራችን ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ለፍሬያማ ግንኙነት ግን በምናስተላልፋቸው መልእክቶች ይዘት ምን መምሰል እንዳለባቸው የሚሠጡ አንዳንድ ምክሮችን ማስታወስ ይበጃል፡፡

7. የሚያበረታታ መልእክት

የትዳር አጋራችን ሊሰማው የሚመኘው የሚያስደስተውንና የሚጠብቀውን መልእክት ቢሆን መልካም ነው፡፡ ባልና ሚስት ተፋቅረው እንደተጋቡ አንዳቸው ለአንዳቸው እምነት እንዳላቸው ያስባሉ፡፡ ስለዚህም አንዱ ለአንዱ መልካም ባል ወይም ሚስት መሆኑንን ወይም መሆኗን የትዳር አጋሩ ወይም አጋሯ እንደሚያምኑ ስለሚታሰብ ያንን በአንድም በሌላም መልእክቶች ውስጥ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፡፡ እርሱን በማግባቷ ወይም በማግባቱ ደስተኛ መሆኗን/መሆኑን/ የሚገልጽ መልእክት ትዳርን የሚያንጽ ነው፡፡ በትዳር ውስጥ በራስ መተማመንን ያሳድጋል፡፡ ተዘውትሮ የሚታይ የመተቸት ዝንባሌ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ በቀጣዮቹ የትዳር ጊዜያት ላይ መተማመንን ያሳጣል፡፡ ተስፋ መቁረጥ ያስከትላል፡፡

አንድ ቢሊ የሚባል ሰው ናስቲ ስለተባለች ሚስቱ የግንኙነት ዘይቤ ሲናገር ያለው የምሬት ቃሉን ላስታውሳችሁ ‹‹ሚስቴ ሁሉን ነገር ማጥቂያ ታደርገዋለች፡፡ አነጋገሯ የሚያበሳጭና ለቁጣ የሚጋብዝ ነው፤ ለምን እንዲህ ማድረግ አልቻልክም? ለምን ይሄን አላደረግህም? ወዘተ በሚሉ ጥያቄዎች ልትጀምረው ትችላለች፤ ቃላቶቿ ብቻ አይደሉም የምትናገርበት ድምፀት ችግር ያለበት ነው፤ ናስቲ የማታከብርና በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ስህተት ፈላጊ ነች፡፡ ለምን እንዲህ ታደርጊያለሽ ስላት ያነሳሁትን ሐሳቤን ለማስቀየር ትጥራለች፤ ወዲያው ሌላ ስህተት ትሰራለች፤ ለዓመታት ያ ሆኖብናል፡፡ በችግሯ ላይ መወያየትንም ትቃወማለች፡፡ ስለዚህ ብወዳትም በዚህ ግንኙነት መንፈስ ከእርሷ ጋር መቆየት አልቻልኩም፤ በዚህ ጊዜ የፍቺ ጥያቄ ሳቀርብላት አላቅማማችም ምክንያቱም ስሕተት ሠራሁ ብላ አሁንም አታስብምና፡፡›› ብሏል፡፡

አንዳንዴ ትችት ብቻ ሳይሆን ሁሌ ተቃራኒ የመሆን ፍላጎቶችን ማሳየትም አንዱ የማያበረታታ ግንኙነት ነው፡፡ ሰማዩ ሰማየዊ ሆኖ ሳለ ሰማየዊ ሰማይ ነው ስትል አይ ዳመና አለው እያሉ በነገር ሁሉ ለመቃረን መሞከርም ዝንባሌው የግንኙነት እንቅፋት ነው፡፡

6. ገርነት ለመልካም ግንኙነት

እንዲህ ያሉ የሚያበረታቱ መልእክቶች ደግሞ የሰመረ የመልእክት ምህዋር በሆኑ መልካምና ልባዊነቱን በሚያመለክቱ አቀራረቦች ሲተላለፉ ለመልእክት ተቀባዩ የተረዳና የሚያረካ ይሆናል፡፡ ለመልካምም ግብረ መልስ ይጋብዛል፡፡ ከመልካም አቀራረብ ጋር አያይዘን የምናነሳቸው ተያያዥ የሆኑ የሚከተሉትን በጎ ልማዶችን መያዝ ጠቃሚ ነው፡፡ የመጀመሪያው ገርነት ነው፡፡ ኃይለኛ፣ ሸካራና ግትር መሆንን ከመሳሰሉ ለትዳር ጠንቅ የሆኑ ልማዶችን ማስወገድ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ጠንቆች ካሉ ከትዳር አጋር የሚወጡ መልእክቶች የሚያበረታቱ ሳይሆኑ በትችት የተሞሉ፣ አስቆጪና ተስፋ አስቆራጭ መልእክቶች ይሆናሉ፡፡

ትችት ግንኙነትን ይመርዛል፡፡ ከእያንዳንዱ ቃል ጀርባ ሐሳብ አለ፡፡ የትችት ቃላት የሚይዙት መልእክት ደግሞ የሚያበረታታ አይሆንም፡፡ ነገር ግን በገርነት ውስጥ ግንኙነትን የሚመሩ ሰዎች ለትዳራቸውና ትዳራቸውን የሚያንጽ ትችት በመሰንዘር አጋራቸውን በሚያበረታታ መንገድ መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡

Unhappy woman lying in couchUnhappy woman lying in couch

5. ንቁ አዳማጭነት ለመልካም ግንኙነት

የሚያበረታታ መልእክት ለማስተላለፍም ይሁን ለመቀበል ብቁና ንቁ ሆኖ የትዳር አጋርን ለመስማት/ለማዳመጥ/ መዘጋጀት ያሻል፡፡ የትዳር አጋሮች መልእክት በሚያስተላልፉ ጊዜ ሁሉ በንቃት ጆሮን መስጠት ማክበርን፣ ትኩረት መስጠትን ያመለክታል፡፡ ይህ የበለጠ የሚገለጸው የትዳር አጋር መልእክት ሲያስተላልፍ በቀጥታ ወደ እርሱ እያዩ መልእክት በመቀበል፣ ሌላ የሚፈጽሙት ጉዳይ ካለ ከትዳር አጋር በላይ እንዳልሆነ በሚገልጽ አግባብ ለጊዜው ተወት አድርጎ ለመስማት መሻትን በማሳየት ነው፡፡ ከተቻለም አክብሮ የትዳር አጋርን መልእክት በጉጉት ለመስማት መቻልን ለማረጋገጥ በቃላት ወይም በመልእክት በሚገለጽ ግብረ መልስ ማጀብ ብልህነት ነው፡፡

ማደመጥ የትዳር አጋር በሚስቱ ወይም በባሏ ዘንድ ዋጋ እንደሚሰጠው እንዲያስብ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ማዳመጥ የሰመረ ግንኙነትና ክብካቤ ማሳያም ነው፡፡ ለራሳቸው ብቻ እንደሚያወሩ የሚሰማቸው ከሆነ ከትዳር አጋራቸው ያገኙት አንዳችም ነገር እንደሌለ በማሰብ፣ ከዚህ ወይም ከዚህች ሰው ጋር የመኖሩ አስፈላጊነት ምንድነው ብለው እንዲጠይቁ ሊያደርግ ይችላል፡፡

4. ለጠንካራ ጎን እውቅና መስጠት

ከዚህ በተጨማሪ በሚተላለፉ መልእክቶች ውስጥ የሚያበረታታ መልክ እንዲይዝ የሚያስችለው ሌላው ነገር ጠንካራ ጎኖችን ወይም የትዳር አጋር ያገኛቸውን/ያገኘችውን ስኬት በጉልህና በተደጋጋሚ መግለጽና እውቅና መስጠት ነው፡፡ አንዳንዶች በድክመታቸውም ለመማር ለመታነጽ ዝግጁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ጠንካራው ሲነገራቸው የሚያውቁትን ደካማ ጎን ለማስተካከል እስኪችሉ ብርታት ያገኛሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የማያውቁትን ያላስተዋሉትን ደካማ ጎናቸውን በትዳር አጋራቸው እንዲነገራቸው እስኪጋብዙ ድረስ ፈቃደኝነት ሊታይባቸው ይችላል፡፡

3. የቃላት ኃይል በግንኙነት ውስጥ

ቃላት ያማሉ፤ ይፈውሳሉም፡፡ በትዳር ውስጥ ያላቸው ሚና እንዲሁ ነው፡፡ ትዳርን ያፈርሳሉ ወይም ያንጻሉ፡፡ የስድብ፣ የመመካት፣ የትምክህት፣ የሚያስቆጣ፣ የሽሙጥ፣ የምጸት፣ የጥርጣሬ፣ የቂም በቀል፣ የአድልዎ፣ የሚያገሉ፣ ወዘተ ቃላት እጅግ አደገኛና በትዳር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸው ናቸው፡፡ የርህራሄ፣ የፍቅር፣ የተስፋ፣ የሚያጽናና፣ የስኬት፣ የማክበር፣ የትህትና፣ የምስጋና፣ የግልጽነት፣ የይቅርታ ወዘተ ቃላት ደግሞ ትዳርን እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያንጹ ናቸው፡፡ ስለዚህ ባለትዳሮች አንዳቸው ለአንዳቸው የሚነጋገሩበትን ቃላት በግዴለሽነት ሳይሆን በጥንቃቄ በጭካኔ ሳይሆን በርህራሄ መንፈስ ከልባቸው መዝገብ አውጥተው መናገር ይገባቸዋል፡፡

በተለይ ከትዳር አጋር ጋር ወይም ከሌላ አካል ጋር በተፈጠረ አለመስማማት ውስጥ የሚነገሩ ቃላት በዘላቂ ግንኙነት ውስጥ የማይረሱ ጠባሳዎች ጥለው እንዳይቀሩ ቃላትን መርጦ በትዕግስት ውስጥ ሆኖ ራስን ተቆጣጥሮ መናገር አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በትዳር ውስጥ የሚያጋጩ ነገሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ምክንያታዊ የሆኑና ከቁጥጥር ውጪ የማይወጡ ግጭቶች መራር ቃላትን ሊያስተናግዱ አይችሉም፡፡ በአንጻሩ ግን ሆን ተብሎ ተዘውትሮ የሚፈጸም ምክንያታዊ ያልሆነ ወይም ከልኩ በላይ የሆነ የቃላት ጦርነትና ስሜታዊ በቃላት የሚፈጸም ረገጣ ውሎ አድሮ ትዳርን ለጥፋት ይዳርጋል፡፡

ቃላት ከፍተኛ ሐሳብን የተሸከሙ በመሆኑ በንግግራችን አንድን የትዳር አጋር አካልና መንፈስ የሚጎዳ መዘዝ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ብዙ የሕመም ዓይነቶች ሊተክሉ ይችላሉ፡፡ በርካቶች ከአጋሮቻቸው የተነገሩ ቃላትን እያሰቡ ምን ሊለኝ /ልትለኝ/ ፈልጎ ነው እያሉ ሲተረጉሙ የሚውሉ፣ ለምን እንዲህ ብዬ መልስ አልሰጠሁም የሚል የበቀልን የቁጭት ሐሳብ ተሸክመው የሚውሉ የሚያድሩ፣ ወዘተ ጊዜያቸውን የሚጨርሱ፣ ለሥራ ያላቸውን ትኩረት በማጣት ባዝነው የሚውሉ፣ ከረጅምና ተከታታይ ጭንቀት የተነሳም ለአእምሮና አካላዊ ህመም የሚዳርጉ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡

በአንጻሩ ደግሞ የአጋሮቻቸው የሚያበረታቱ ቃላት ከፍተኛ የመንፈስ ጥንካሬ የሚሠጣቸውና ስኬት በስኬት የሚሆኑ፣ ፍቅራቸውም ከጊዜ ጊዜ የሚጨምርባቸው በርካታ ሰዎችም ይኖራሉ፡፡

2. ዐውድን ያገናዘበ የቃላት ልውውጥ

ባለትዳሮች በሰዎች ፊት ሲወያዩና ለብቻቸው ሆነው ሲወያዩ የሚኖረው ዐውድ ሊለያይ ይችላል፡፡ በሰዎች ፊት ሲወያዩ የሚቀባበሉአቸው ቃላት በጥንቃቄ የተሞሉና የፍቅርና መከባበር መንፈስ በተሞላበት ሁኔታ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡ በሰዎች ፊት ሆነው ሲያወሩ ሊሰሟቸው የሚፈልጉአቸውና የማይፈልጓቸው ቃላት ይኖራሉ፡፡ ለብቻ ሆነው ሲወያዩ የሚነጋገሩባቸውን ቃላት መጠቀም ለአንዳንዶች ሊያስቆጣቸው ይችላል፡፡ ወይም አያስደስታቸው ይሆናል፡፡ በዚያም ምክንያት የትዳር አጋራቸውን በሰው ፊት ይዘው መቅረብ የማይፈልጉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በሌላ አንጻር ሁኔታዎችን ከግምት ያስገቡ የንግግር ቃላትን መጠቀም የሚችሉ፣ የትዳር አጋሮቻቸውን በማንም ፊት ይዘው ቢቀርቡ የማያፍሩ ምናልባትም ከትዳር አጋር ጋር ሆኖ መታደም ኩራት የሚፈጥርላቸውም በርካቶች ይኖራሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ችግርን ለመፍታት በሚደረጉ በአንዳንድ ጥብቅ ጉዳዮች ላይ ከተቻለም ለችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የሚደረጉ ውይይቶች የሚደረጉበትን ጊዜና ሁኔታ መምረጥ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ የትዳር አጋር በሌሎች ምክንያቶች ተቆጥቶ ሳለ ተበሳጭቶ ሳለ ወይም ተርቦ እያለ ቸኩሎ እያለ… ትኩረትና እርጋታ የሚፈልጉ ጉዳዮችን አንስቶ ለመነጋገር መሞከር በግንኙነት ሂደቱ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በሌሎች ሰዎች ፊት ሲሆኑ የትዳር አጋሮቻቸው እስከሚገረሙ ድረስ ደስ የሚያሰኙ ማራኪ ቃላትን የሚጠቀሙ ሰዎች ወደቤቶቻቸው ሲገቡ ተለውጠው ለትዳር አጋር እንደኮሶ የሚመሩ ቃላትን የሚያዘንቡም ይኖራሉ፡፡ እንዲህ ያሉት በልማዳዊ ንግግሮች ‹‹የውጪ አልጋ የቤት ቀጋ›› የሚባለው ዓይነት አቀራረብ ያላቸው ናቸው፡፡ በውጪ ምስጉንና የመልካም ቃላት ባለቤት ሆነው ሳለ በቤት ግን ትዳራቸውን ለማነጽ በማይጠቅሙ ኃላፊነት የጎደላቸው ንግግሮች የሚታጀቡ ይኖራሉ፡፡

1. የይቅርታ ኃይል በግንኙነት ክህሎት

ግንኙነት ሁልጊዜ የሰመረ ላይሆን ይችላል እንኳን ትዳርን በመሰለ የረጅም ዘመናት ተቋም ቀርቶ በየዕለት አጋጣሚዎቻችን በሚኖረን የሥራ፣ የንግድ፣ የማህበራዊ ኑሮ፣ ወዘተ ግንኙነት ውስጥ ታግሰን ልናልፋቸው ያልቻልናቸው ያልተሳኩ ግንኙነቶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ የግንኙነት እንቅፋቶች ከምንጠቀምባቸው የቃላት ጥራት፣ ከመልእክቱ ተቀባይ ግንዛቤ እጥረት፣ ወይም ከመስሚያና መናገሪያ አካላችን ችግር ጋር በተያያዘ ሳይሰሙ ወይም በደንብ ሳይናገሩ በሚፈጠር የግልጽነት ችግር የሚያጋጥሙ የግንኙነት እንቅፋቶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች በትዳር ውስጥ ባይዘወተሩም አልፎ አልፎ ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በምላስ ወለምታ፣ ባልሰማ ጆሮ፣ ወይም ባልሰከነ ሐሳብ ምክንያት መግባባት አለመቻል ከዚያም የመነጨ የተዛባ ግብረ መልስ መስጠት የሚያመጣው መዘዝ ሊኖር ይችላል፡፡

ሁልጊዜ አለመግባባት ራሱን በቻለ በሌላ አግባብ መታየት ሊኖርበት ይችላል፡፡ በአጋጣሚና አልፎ አልፎ በትዳር ውስጥ በምናስተላልፈው መልእክት ምክንያት የሚያጋጥሙ የግጭት ምክንያቶች ግን ስህተት ሲሆኑ የተሳሳተው ይቅርታን በመጠየቅ፣ የተበደለው ይቅርታ በማድረግ ግንኙነትን ወደነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ የባለትዳሮች ኃላፊነት ይሆናል፡፡ ይቅርታ የተሰበረ የግንኙነት ሁኔታን ለመቀጠል፣ ለመፈወስ እጅግ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

መሳሳትን ማጽናትም ሆነ መሳሳትን አለመፍቀድ ከጤናማ ግንኙነት ፈላጊዎች የሚጠበቅ አይሆንም፡፡ ሁሌ መሳሳትም ሆነ በአጋጣሚ የተፈጠሩ የግንኙነት ስህተቶችን በይቅርታ አለማየት የትዳር ግንኙነትን እጅግ ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉ የፍቺ ዋዜማዎች ናቸው፡፡

ማጠቃለያ

መልካም ግንኙነት ባለበት ሁሉ መልካም ትዳር አለ፡፡ የመልካም ግንኙነት መሠረት ደግሞ መልካም ቃላት፣ መልካም ስነምግባር፣ አስተዋይነት፣ ዕውቀትና ይቅርባይነት ናቸው፡፡ እነዚህ ለትዳር ሕይወትን ይሰጡታል፡፡ ከታመመ ይፈውሱታል፡፡ ስለዚህም በመልካም ባለትዳሮች ልብ፣ ቃልና ሥራ ውስጥ ሁሉ አይለዩም፡፡

↧

Sport: «ጦረኛው» –ኢቫንደር ሆሊፊልድ

$
0
0

ታምራት አበራ

ቦክስ ስፖርት ላይ ባሳየው ጠንካራ ብቃት «ሪል ዲል ወይም ጦረኛው» የሚል ስያሜ ሰጥተውታል፡፡እ.አ.አ ኅዳር 19 1962 በአሜሪካ ግዛት በአትሞር አላባማ ከተማ ተወለደ፡፡ ከድሃ ቤተሰቦቹ ዘጠነኛ ልጅ ሆኖ የተወለደው ቦክሰኛው ኢቫንደር ሆሊፊልድ ገና በ8 ዓመቱ የቦክስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ገብቶ የቦክስ ስፖርትን ተቀላቀለ፡፡ እስከ 11 ዓመቱ ድረስ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ በዝረራ ማሸነፍ የቻለ ቡጢኛ ነው፡፡ በ1984ቱ የሎሳንጀለስ ኦሎምፒክ በ22 ዓመቱ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ በመሆን አዲስ ክብረ ወሰን ጨብጧል፡፡
evander
የአራት ጊዜ የከባድ ክብደት ቦክስ ሻምፒዮኑ ሆሊፊልድ ባደገባቸው አትላንታ እና ጆርጂያ በሕፃንነቱ የቦክስ ልምምዶችን እያደረገ ነው ያደገው፡፡ በ1980 ወረቃማ ጓንት ለመውሰድ በሚደረገው ሻምፒዮና ላይ ገና በጨቅላ ዕድሜው በአማተርነት መሳተፍ የቻለው ሆሊፊልድ በ1984 የመጀመሪያውን የሀገሩን የወርቅ ጓንት አሸናፊ መሆን መቻሉ በወቅቱ ለአሜሪካ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ቡድን እንዲመረጥ አበቃው፡፡ በ1984ቱ የሎስአንጀለስ ኦሎምፒክ ሆሊፊልድ አሜሪካን ወክሎ ተጫውቶ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በድል ተወጥቶ ለሩብ ፍጻሜ ደረሰ፡፡ በሩብ ፍጻሜ ጨዋታው ከኒውዝላንዳዊው ኬቪን ባሪ ጋር ተገናኝቶ በሁለተኛው ዙር ከእረፍት መልስ እንደገቡ ፊሽካ ሳይነፋ መማታቱን ተከትሎ ለጊዜው ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡ ጉዳዩን የተመለከተው ኮሚቴ ስህተቱ የሆሊፊልድ ሳይሆን የዳኛው መሆኑን ስለደረሱበት ሆሊፊልድ ሦስተኛ ሆኖ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ እንዲሆን ተደረገ፡፡

ሆሊፊልድ በ1986 ዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር ደብሊው ቢ ኤን ክብር ያዘጋጀውን ፍልሚያ በውድድሩ ለረጅም ዓመት መንገስ የቻለውን ኋይት ኩዋይን በማሸነፍ ስኬታማነቱን አጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ሆሊፊልድ ልምምዱን ይበልጥ አጠናክሮ በ1990 የዓለም ከባድ ክብደት ተወዳዳሪ መሆን ቻለ፡፡ በመጀመሪያ ጨዋታውም በወቅቱ በተደጋጋሚ የዓለም ከባድ ቦክስ ሻምፒዮን የነበረውን ጄምስ በስተር ዳግላስን ሰባት ደቂቃ በፈጀ ፍልሚያ በዝረራ በማሸነፍ የከባድ ቦክስ ሕይወቱን ገፋበት፡፡ ሆሊፊልድ በ1992 እና በ1994 በማይክል ሙረር የሪዲክ ቦው ፍልሚያን ቢሸነፍም ስህተቱን አርሞ በ1993 ማሸነፍ ቻለ፡፡

ሆሊፊልድ በከባድ ክብደት የቦክስ ሕይወቱ በመላ ዓለም አነጋጋሪ የሆነ ክስተት ገጠመው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው። ከሀገሩ ልጅ ማይክ ታይሰን በተደጋጋሚ የእንፋለም ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡ በቦክሱ ዓለም መሸነፍን የማይወደው ሆሊፊልድ ከሀገሩ ልጅ ማይክ ታይሰን ጋር ለመፋለም ቀጠሮ ይይዛል፡፡ በ1996 ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱ የከባድ ቦክስ ባለድሎች ባደረጉት ፍልሚያ ሆሊፊልድ ያሸንፋል፡፡ በወቅቱም በቀጣዩ ፍልሚያቸው የሚከሰተውን ለመገመት ተቸገረ፡፡ ውድድሩ እንደተጀመረ በተደጋጋሚ በሚሰነዝራቸው ቡጢዎች ነጥብ መውሰድ የቻለው ሆሊፊልድ በታይሰን ላይ የበላይነትን ወስዶ ያሸንፈዋል፡፡

በቦክስ ሕይወቱ መሸነፍን የማይወደው እና በረባ ባልረባው መጣላትን እና ቦክስ መሰንዘርን ለሚወደው ማይክ ታይሰን ሽንፈቱ አልዋጥ ብሎት የሆሊፊልድን ጆሮ በንክሻ ይዘነጥለዋል፡፡ ከመዘንጠል ባለፈም የጆሮውን ቁራጭ ጭምር ይዞ ይሄዳል፡፡ ይህ ድርጊቱ በመላ ዓለም ከፍተኛ ትኩረት ያገኘው ታይሰን በዚህ አስነዋሪ ድርጊቱ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡

ከታይሰን ንክሻ አገግሞ ከጥቂት ወራት በኋላ የአይቢኤፍ ክብርን አንጋፋውን ማይክል ሙርን ስምንት ዙር በፈጀ ፍልሚያ በማሸነፍ ለሦስተኛ ጊዜ ዘውድ ደፋ፡፡ በ1999 ሆሊፊልድ ሌላ ፈተና ገጠመው፡፡ በወቅቱ በዓለም ከባድ ቦክስ ሻምፒዮንነት አቻ የሌለውን ሌኖክስ ሊዊስን ይገጥማል። ይህንን ውድድር ሆሊፊልድ በዝረራ ያሸነፋል ብሎ ያልገመተ አልነበረም፡፡ የመጀመሪያ ፍልሚያቸው በአቻ ነጥብ ተጠናቀቀ፡፡ ይሁን እንጂ ሊዊስ በዚያው ዓመት ሌላ ተወዳዳሪ ማሸነፉን ተከትሎ አሸናፊነቱ ጠቅልሎ መውሰድ ቻለ፡፡

ከ1990 እስከ 1992 እንዲሁም ከ1993 እስከ 1994 ለአራት ጊዜ የዓለም የከባድ ቦክስ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ብቸኛው ሆሊፊልድ ከቦክስ ሕይወቱ ውጪ መልካም አሳቢ እና በሥነ ምግባሩም አርአያ መሆን የቻለ ነው፡ ፡ከመድረክ ውጪ ታዳጊዎች እና አቅመ ደካሞችን በመርዳት የሚያሳልፈው አዛኙ ቡጢኛ «የሆሊፊልድ እርዳታ ተቋም» የሚል ተቋም አቋቁሟል። ድርጅቱ እርሱ በሚኖርባት አትላንታ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊዎች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

ሆሊፊልድ እስከ 2011 ድረስ 57 ያህል ፍልሚያዎችን አድርጓል፤ ከእነዚህ ውስጥ 44ቱን በድል ተወጥቷል፤ በ10ሩ ተሸንፎ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል፡፡ «ለአንተ ጠንካራ ቦክሰኛ ማነው?» ተብሎ የተጠየቀው ሆሊፊልድ ጆሮውን የነከሰውን ማይክ ታይሰን፣ በተደጋጋሚ ያሸነፉትን ጆኦርጅ ፎርማን፣ ሌኖክስ ሊዊስ ሪዲክ ቦው ወይስ ላሪ ሆልምስ በማለት መልስ ይሰጣል። የብዙዎች ግምት ነበር፡፡ ነገር ግን በአወዛጋቢ መልሱ ሆሊፊልድ ሁለት ጊዜ ተገናኝተው በሁለቱም ጨዋታ በዝረራ ያሸነፈውን መሀመድ ቃዊን መምረጡ በበርካታ የመገናኛ ብዙኃንን ዘንድ አግራሞት ፈጥሮ አነጋግሯል፡፡

↧

Sport: ኢትዮጵያዊያኑ 3 አትሌቶች በቤጂንጉ የ5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ላይ ይሳተፋሉ

$
0
0
The men's 5000m heats at the IAAF World Championships, Beijing 2015 (Getty Images) Š Copyright

The men’s 5000m heats at the IAAF World Championships, Beijing 2015 (Getty Images) © Copyright

በሙለታ መንገሻ

በ15ኛው የቤጂንግ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ በሶስት አትሌቶች ትወከላለች።

ሌሊት 10 ስአት ከ35 ላይ በተደረገ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሀጎስ ገብረ ህይወትና ኢማና መርጋ ፍጻሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ሀጎስ ገብረ ህይወት ከየምድባቸው አንደኛ በመውጣት ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ሲሆን፥ ኢማና መርጋ አምስተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ነው ያለፈው።

አትሌት ዮሚፍ ቀጄልጃ ውድድሩን 13:19.38. በሆነ ሰዓት የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ የነበረውን ሞህ ፋራህን ቀድሞ በመግባት የማጣሪያ ውድድሩን አጠናቋል።

ውድድሩ ዛሬም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን፥ 10 ስዓት ላይ በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ፥ አትሌት ህይወት አያሌውና ሶፊያ አሰፋ ኢትዮጵያን ከዚህ ያልተለመደ የውጤት ማሽቆልቆል ይታደጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ነገ ሌሊት 10 ስአት ከ40 ላይ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የማጣሪያ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ፣ አልማዝ አያና፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ጎይቶም ገብረ ስላሴ ይወዳደራሉ።

በዚሁ ቀን ሌሊት 11 ከ35 በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ አማን ወጤ፣ ዳዊት ወልዴ እና መኮንን ገብረ መድህን ይሳተፋሉ።

እሁድ ነሃሴ 24 2007 ዓ.ም 8 ስአት ከ30 ሌሊት በሴቶች ማራቶን ትርፌ ፀጋዬ፣ ማሬ ዲባባ እና ትእግስት ቱፋ የሚወዳደሩ ሲሆን፥ ቀን 8 ስአት ከ15 ላይ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር፤ 8 ስአት ከ45 ላይ ደግሞ የወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮች ይከናወናሉ።

ትናንት በተደረገው የ1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ በ4 ደቂቃ 08:09 ሰከንድ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ማስገኘቷ ይታወሳል።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን 1 የወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአለም 5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ገንዘቤ ዲባባ፣ በወንዶች ማራቶን የማነ ፀጋዬ እንዲሁም በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ገለቴ ቡርቃ ናቸው ሜዳልያዎቹን ያስገኙት።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአለም አቀፍ ሻምፒዮናዎች በወንዶች ውድድር ድል የራቃት ኢትዮጵያ፥ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ከበርካታ ዓመታት በኋላ ከሜዳልያ ውጪ ሆናለች።

ኢትዮጵያ በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ያልሆነችበት 15ኛው የቤጂንግ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአንፃሩ ለኬንያውያን ስኬታማ ነው ማለት ይቻላል።

ኬንያ እስካሁን 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ ሜዳልያዎችን በማግኘት ከአለም ሀገራት በቀዳሚነት ተቀምጣለች።

ብሪታንያ በ3 ወርቅ በ2ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ጃማይካ በ2 ወርቅ እና በ1 ነሃስ በ3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

↧

የ “ሀ”ን ዘር የ “ከ”ዘር እያጠፋው ነው:: –ይገርማል ታሪኩ

$
0
0

Amharic2በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ አልፎ ተርፎም ቀጥተኛ ግድያ አማሮች እያለቁ ቁጥራቸውም እየተመናመነ በመሄድ ላይ መሆኑን ሁሉም ያውቃል:: የአማራ ዘር ብቻ ሳይሆን የአማራ ባህል: ቅርስና ትውፊት ናቸው ተብለው በሚታመኑት የረጅም ጊዜ የታሪክና የእምነት አሻራወቻችን ላይም የማጽዳት እርምጃ በተለያየ መንገድ እየተወሰደ ነው:: ዛሬ አማራንና ኦርቶዶክስ ሀይማኖትን ለያይተው ማየት የተሳናቸው ግብዞች ኦርቶዶክስ ሀይማኖት አማራው የፈጠረውና የአማራ መሸሸጊያ እንደሆነ አድርገው በመስበክ: ቤተክርስቲያናቱን በማቃጠል: መጽሀፍቱንና የአምልኮ መገልገያ መሳሪያወችን ባህር እያሻገሩ በመሸጥ: ቤተክርስቲያን በነጻነት መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳትሰጥ ካድሬወችን በመሰግሰግ የወያኔ ጉዳይ ፈጻሚ በማድረግ: ጊዜ የማይሽረው በደል እየፈጸሙ ነው::

እንደሚታወቀው የአማራ ክልል የሚተዳደረው በዋናነት አማራ ሳይሆኑ አማራ ናቸው ተብለው በተቀመጡ የሌላ ብሄርና የሌላ ሀገር ሰወች ነው:: ከታች የተኮለኮለው አማራ ነኝ ባይ የአህያ ባል ሆኖ የመጣውን እየተቀበለ አድርግ የተባለውን እያደረገ የሚኖር ስለክልሉም ሆነ ስለ ህዝቡ የማይጨነቅ ለከርሱ ብቻ የቆመ ተራ ስብስብ ነው::

ቀደምት አማሮች በአራቱም ማእዘን በመዝመት አጥንታቸውን ከስክሰውና ደማቸውን አፍስሰው በየትኛውም የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ያልታየ ገድል በመፈጸም በምስራቅ ከጣሊያኖችና ከፈረንሳዮች በደቡብና በምዕራብ ከእንግሊዞች ጋር ድንበር ተካለው ኢትዮጵያን ለእኛ አስረክበዋል:: ያ ባይሆን ኖሮ ዛሬ ላይ በምስራቅ ያለው ኢትዮጵያዊ ከፊሉ ከጅቡቲ ቀሪው ደግሞ ከሶማሊያ ጋር: በደቡብ ያለው ኢትዮጵያዊ ከኬንያ ጋር: የሰሜኑ ከኤርትራ የምእራቡ ደግሞ ከሱዳን ጋር የመሆንና ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በታሪክ ብቻ የምትታወስ ሆና በቀረች ነበር::

የአፍሪካም ሆነ የኤዥያ ሀገሮች እንደሀገር የቆሙት በቅኝ ግዛት ጊዜ በነበራቸው አብሮነት መሰረት በመሆኑ በተለያዩ አገሮች በቅኝ ግዛትነት ተይዘው የቆዩት አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ተበታትነው በተለያዩ ሀገሮች የመኖር እጣ ደርሶባቸዋል:: እኛ ግን አያት ቅድመአያቶቻችን ባደረጉት የመረረ ተጋድሎ ረጅም ታሪክ ያላት ጥንታዊቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥቁር ዘር የነጻነት ፋና የልጆቿ መመኪያ በመሆን ከዘመን ዘመን ተሻግራ ለእኛ ተላለፈች:: ዛሬ ባለጊዜ ወያኔወች እንደፈለጋቸው የሚያደርጓት: ብዙሀኑም ፍዳ የሚያይባት: “ኢትዮጵያ” የምትባል ሁላችንንም ሰብስባ የያዘችዋ ሀገር ነጻነቷን አስጠብቃ ለእኛ እንድትደርስ የተከፈለው ደምና አጥንት ከ-እስከ የሚባል አይደለም::

ታዲያ እነዚያ ጠላት አይደፍረንም ብለው በቀዳሚነት ደምና አጥንት የከፈሉት ኢትዮጵያውያን ልጆች ዛሬ ላይ ራሳቸውን እንኳ ማስከበር አቅቷቸው በመጥፎ መንፈስ በተሞሉ የወያኔ ተኩላወች ፊታውራሪነት ለፈርጀ ብዙ ጥቃት ተጋልጠው ያለ አለሁ ባይ በየአካባቢው እየወደቁ ነው:: ከሁሉ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ተጣመው የተፈጠሩና ነፍስ ያላወቁ ከራሱ ከአማራው አብራክ የተገኙ ጥቂት ጉዶች ለወያኔ አድረው የጠላት መሳሪያ በመሆን እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ ከአዋራጆቹ ጋር ተስማምተው እያዋረዱት: ከአሳዳጆቹ ጋር እያሳደዱት: ከገዳዮቹ ጋር ተባብረው እየገደሉት በወገናቸው ላይ የሚደርሰው ግፍና ሰቆቃ ሳይጎረብጣቸው በድርጊታቸው ተኩራርተውና ረክተው መቀጠላቸው ነው:: በአማራው ላይ የሚደርሰውን ሁለንተናዊ ግፍ የሚቃወሙትን ፈጥነው በማጥፋት “ጎሽ” ለመባል የሚተጉት እኒህ ትንሽየ እንኳ እንጥፍጣፊ ህሊና የሌላቸው እፍኝ የማይሞሉ የእንግዴ ልጆች ያማራውን ክልል ለማስከበርና የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ መስራት ሲገባቸው መሬቱን በውጪ ለሱዳን: በውስጥ ደግሞ ለተለያዩ ክልሎች እያስቦጠቦጡ ከጊዜ ወደጊዜ መኖሪያውን እያጠበቡ ተስፋውን እያጨለሙበት ነው:: በየዳር ድንበሩ በውትድርና ዘምቶ በዚያው ሀገሬ ብሎ ከአካባቢው ህዝብ ጋር ተጋብቶና ተዋልዶ ለረጅም ጊዜ በኖረው ህዝብ ላይ የወያኔ የጥላቻ በትር ሲያርፍበት ለምን ብሎ እንደመከራከርና መብቱን እንደማስከበር “ከክልሉ የወጣ አማራ ጉዳይ አይመለከተንም” በማለት ወገኖቻችን በየሄዱበት ወድቀው እንዲቀሩ ድጋፋቸውን አበረከቱ:: እኒህ ከወያኔ ጉያ ተወሽቀው በሚያገኙት ዳረጎትና በወገናቸው ላይ በሚደርሰው ዘግናኝ ግፍ ተደስተው ሰላም አግኝተው የሚኖሩ የብአዴን ሰዎች የሚቆጭ ህሊና የሌላቸው ለሆዳቸው ብቻ የተፈጠሩ ትናንሽ ሰወች ለመሆናቸው ተግባራቸው ይመሰክራል::

በመሆኑም አማራው በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጭ እንደዜጋ መብቱ ተከብሮ ለመኖር ያልቻለ: በስውርና በግልጽ ደባ ቁጥሩ የተመናመነ: በቤተሰብ እቅድ ስም በርሱ ላይ ብቻ ያተኮረ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመበት ሆኗል:: የዚያ ታሪክ ሰሪ ህዝብ ልጆች ራሳቸውን መከላከል ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ወድቀው ያም ያም እንደፈለገው የሚያደርጋቸው እርካሾች ሆነው ሲታዩ እንዴት ያማል::

ወደርዕሴ ስመለስ.:- በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአሁኑ ትውልድ የሀን ዘር በከ ዘር በመተካት የሀን ፊደል ከፊደል ገበታ ለመሰረዝ በጉዞ ላይ ነው:: ፊደሎችን ካለወህል መጠቀም እንዴት ያስቀይማል! በተለይ ይህን የሚያደርጉት የስነጥበብ ሰዎች ሲሆኑ ደግሞ ከማስቀየም አልፎ ህመሙ ይጠዘጥዛል:: ጥሩ የታሪክ አወቃቀርና ፍሰት ያለው ድራማ/ፊልም ላይ ፊደላት ያለቦታቸው ሲገቡ ለሰሚ ይቀፋሉ: ታሪኩንም ያደበዝዛሉ:: አንድ ወይም አንዲት የአርት ሰው መሰረታዊውን የቃላት አወቃቀር በመቀየር እንዴት ነክ: እኔ እምልክ: የት ነክ: ወዘተ እያለ/እያለች ሲናገር/ስትናገር ለሰማ ጆሮን “ኩ-ር” ያሉት ያህል ይሰቀጥጣል::
የዱሮ                                                   የአሁን
ምን አደረግሁ                                              ምን አደረኩ
ማን ነህ                                                     ማን ነክ
የት ነህ                                                      የት ነክ
እኔ የምልህ                                                 እኔ የምልክ
ታምራለህ                                                   ታምራለክ
ተውበሀል                                                   ተውበካል
አምሮብሃል                                                 አምሮብካል
…….                                                       ———
በአንድ ወቅት ት/ቤት እያለሁ አንድ መምህር የተናገሩት ምን ጊዜም አይረሳኝም:: አንድ ተማሪ should የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል “ሹልድ” እያለ ሲያነብ ሰምተው በጣም ተቆጡና “ስማ! አንተ ሹድ ተብለህ ተምረህ ሹልድ እያልህ መጣህ የአንተ ልጆች ደግሞ ሹልዳ እያሉ ይመጣሉ”
ተከታዩ ትውልድስ የቱን የአማረኛ ፊደል ይገድፍ ይሆን!

Top of Form

 

↧
↧

ሕወሓት መተካካቱ መገፋፋት ሆኗል በሚል የቀድሞ አርከበ እቁባይ ስዩም መስፍን ስብሃት ነጋን እና ብርሃነ ገ/ክርስቶስን መለሰ

$
0
0

ሪፖርተር ጋዜጣ ያስነበበው ዜና ከዚህ ቀደም ዘ-ሐበሻ የሕወሃት ምንጮቿን ጠቅሳ ስትዘግብ የነበረውን የሚያረጋግጥ ሆኖ አግኝተነዋል:: አቶ አርከበ “የመለስ ሌጋሲ በቃን” በሚል ተገፍተውበት የነበረውን ስልጣን ለመያዝ መስመራቸውን አሳምረዋል:: ሕወሓቶች ውስጥ ያለውን ክፍፍልም በይፋ አሳይቶናል:: መተካካቱ መገፋፋት ሆኖ ነበር ብለው የተሰናበቱትን መልሰዋል:: ዜናውን ያንብቡት::

metekakat

 

– ሦስቱ አባል ድርጅቶችም ጉባዔያቸውን አካሂደዋል

ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቐለ ሰማዕታት አዳራሽ እየተደረገ ባለው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ፣ በመተካካት ተሸኝተው የነበሩ የሕወሓት አመራሮች በጉባዔው እንዲመረጡና እንዲመርጡ ተወሰነ፡፡ አዘጋጅ ኮሚቴው የጋበዛቸው ያለ ድምፅ እንዲሳተፉ ነበር፡፡

ከ1,650 በላይ ጉባዔተኞች በታደሙበት ጉባዔ የተገኙ አንድ ተሳታፊ ከዚህ ቀደም ተገፍተው የወጡ ያሏቸው ነበር አመራሮች በድምፅ እንዲሳተፉ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ የመከረው ጉባዔ በጭብጨባ በሙሉ ድምፅ ጥያቄውን ተቀብሎታል፡፡ በዚህም መሠረት ዶ/ር አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይ)፣አምባሳደር ሥዩም መስፍን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣ አቶ ፀጋዬ በርኼን ጨምሮ 17 ነባር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ጉባዔው በእስካሁኑ ቆይታው በአንደኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በመልካም አስተዳደርና በመተካካት ላይ ተወያይቷል፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ክልሉ እየተጠቃ እንደሆነ በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ በተለይ በአንድ የሃይማኖት አባት የቀረበው የመልካም አስተዳደር እጦት ትኩረት የሳበ ነበር፡፡ የሕወሓት አመራሮች ድርጅቱ ቀድሞ አንግተውት የነበረውን ዓላማ እንደረሱ በአጽንኦት ገልጸው፣ ፍትሕ በገንዘብ እየተገዛ የክልሉ ሕዝብ የማያውቀው አዲስ ባህል በመጎልበቱ ይህንንም እንደሚዋጉት አመልክተዋል፡፡ ‹‹እሳት ያልፈራ ሕዝብ እናንተን የሚፈራ ይመስላችኋል?›› ሲሉም ጥያቄአቸውን አቅርበዋል፡፡ መተካካትን በተመለከተም ወደ መገፋፋት በመቀየሩ ያለ ዕድሜና አቅም ማነስ ዶ/ር አርከበና አምባሳደር ብርሃነ እንዲወጡ መደረጉን ተችተዋል፡፡ እንደ ድሮው መገማገምና አንዱ አንዱን ተጠያቂ ማድረግ በመሸፋፈንና በመጠባበቅ መቀየሩም ተገልጿል፡፡

የሕወሓት ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ የቀረበውን ቅሬታ ተቀብለው፣ የተሠራ ነገር ቢኖርም ትልቅ ዳገት እንደሚጠብቅ ገልጸዋል፡፡ የአመራር አባላት ራሳቸውን ማጥራትና ወደ ራሳቸው መመልከት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር አርከበ በጉባዔው ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፣ ሕዝቡ ቅሬታ እያቀረበ ያለው በፍትሕ አካላትና በፓርቲው አባላት መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ጉባዔው ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትን ይመርጣል፡፡

11ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በባህር ዳር በድርጅቱ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡ ጉባዔው በክልሉ የተመዘገበውን የኢኮኖሚና ዕድገትና የግብር ምርት ውጤታማነት የገመገመ ሲሆን፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ 10.4 በመቶ በመድረሱ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ መቻሉ ተገልጿል፡፡ የመጀመርያው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ መልካም አስተዳደር፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች መስኮችም በግምገማው ተካተዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን በተመለከተና በሥራ ፈጠራ ጉድለቶች መኖራቸውን የገመገመው ጉባዔው፣ የክልል ከፍተኛ አመራሮችም ለችግሩ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ አውስቷል፡፡ የድርጅቱ ጉባዔ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የብአዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን፣ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመምረጥ ማክሰኞ ምሽት ተጠናቋል፡፡ ማክሰኞ ምሽት የተመረጡት እነማን እንደሆኑ ግን አልታወቀም ነበር፡፡

ኢሕዴድ በአዳማ ከተማ 8ኛ ጉባዔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡ በጉባዔው በክልሉ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ለማምጣት የሚችሉ አዳዲስ ሐሳቦች እንደ ግብዓት ሲሰባሰቡ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በክልሉ የ11.2 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብና የኢኮኖሚውን መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡

የኦሕዴድን ድርጅታዊ ህልውና ይፈታተናሉ የተባሉት ትምክህትና ጠባብነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የተንዛዙ አሠራሮችና ፍትሐዊነት የጎደላቸው አመራሮች በጉባዔው ወቅት መነሳታቸው ታውቋል፡፡ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኦሕዴድ ጉባዔ ማክሰኞ ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር፡፡

የደኢሕዴን ጉባዔ በሐዋሳ ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ሲመረጡ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡ ጉባው በሦስተኛ ቀን ውሎው የመጀመርያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገምግሞ፣ በምግብ እህል ራስን መቻል ላይ አበረታች ውጤት መገኘቱን ተወያይቶበታል፡፡

አበረታች የተባሉ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ይቀራቸዋል የተባሉት ላይ ደግሞ በተጠናከረ ሁኔታ ርብርብ እንዲረደረግ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ የጤናና የትምህርት ዘርፍ ተደራሽነታቸው መልካም መሆኑ ተወስቶ፣ የጥራት ጉዳይ ግን እንዲታሰብበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ጠባብነት፣ ብልሹ አሠራርና ሙስና በድርጅቱ ውስጥ ቦታ እንደማይኖራቸው ውሳኔ ላይ መደረሱ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የደኢሕዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላትም ተመርጠዋል፡፡ የተሟላ ዝርዝር ግን ማግኘት አልተቻለም፡፡

በተያያዘ ዜና የብአዴን ነባር ታጋይና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሠ በክብር መሰናበታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ አቶ ዮሴፍ ረታም እንዲሁ ተሰናብተዋል፡፡ የደኢሕአዴን ሊቀመንበር፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ካሱ ኢላላ እንዲሁ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በክብር መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡

↧

ጃፓን የጣለችውን ማዕቀብ ካነሳች ከስድስት ዓመት በኋላ በቡና ጥራት አለመደሰቷን ይፋ አደረገች

$
0
0

–ግዙፉ የቡና ኩባንያ የጥራት ውድድር እዚህ ያካሂዳል

DSC_8247-425x282ከስድስት ዓመት በፊት ወደ ጃፓን በተላከ የቡና ጆንያ ላይ በተገኘ የኬሚካል ቅሪት ሳቢያ ጃፓን ከኢትዮጵያ የሚላከውን ቡና አግዳ ብትቆይም፣ አሁንም በሚላክላት ቡና ላይ የጥራት ጉድለት እየታየ በመሆኑ የቀድሞውን ያህል እየገዛች አለመሆኗ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የጃፓን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ካዙሂሮ ሱዙኪ ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ከስድስት ዓመት በፊት በፀረ አረምና ፀረ ተባይ ኬሚካል ሳቢያ ጃፓን ትገዛው የነበረው ቡና ለተወሰነ ጊዜ ከተቋረጠ በኋላ መልሶ ማገገም ቢጀምርም፣ ከስድስት ዓመት በፊት ወደነበረበት ደረጃ ሊመለስ አልቻለም ብለዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ ጥራት ያለውና ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው ቡና ተብሎ የሚላከው ጥራቱም ደረጃውም ዝቅተኛ ከሆነው ጋር እየተደባለቀ በመገኘቱ እንደሆነ አምባሳደር ሱዙኪ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያም የሚፈለገውን ያህል ቡና ወደ ጃፓን መላክ ባይቻልም በየጊዜው እያደገ መምጣቱ ግን ተነግሯል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚጠቁመው በዓመት ከ170 እስከ 190 ሺሕ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ ይቀርባል፡፡ ከዚህ መጠን ውስጥ የጃፓን ድርሻ ግን ከአሥር በመቶ እንደማይበልጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአንፃሩ ከስድስት ዓመት በፊት ወደ ጃፓን ይላክ የነበረው የቡና መጠን ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ኤክስፖርት እስከ 25 ከመቶ ይደርስ ነበር፡፡

የኬሚካል ንክኪውን ለማስቀረት የጃፓን ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጃፓን መንግሥት ድጋፍ የላቦራቶሪ ማዕከል ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና ከመደበኛው ቡና ጋር ተቀላቅሎ እየተላከ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ቡና የጃፓንን የጥራት ደረጃዎች ማሟላት ተስኖት እንደሚገኝ አምባሳደሩ ይናገራሉ፡፡ ይህ ቢስተካከል ግን ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ ጥራት ያላቸው ልዩ ቡናዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አምባሳደር ሱዙኪ አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከጥሬ ቡና ባሻገር አገር ውስጥ የተቀነባበረ ቡና የመላክ ሐሳብ እንዳላት ያስታወሱት አምባሳደሩ፣ ይህንን ለማድረግ ግን አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪው መዳበር እንደሚኖርበት ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በዓለም ግዙፉ የቡና ኩባንያ የሆነው ዩሺማ ኮፊ ካምፓኒ ሆልዲንግ ግሩፕ (ዩሲሲ) በኢትዮጵያ የቡና ጥራት ላይ ያተኮረ ውድድር ሊያካሂድ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ ኩባንያው በጅማ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙት በለጠና ጌራ አካባቢዎች የሚገኘውን የጫካ ቡና ሲገዛ መቆየቱም ይታወቃል፡፡ ኩባንያው በተደጋጋሚ በቡና ጥራት ላይ ከፍተኛ ጃፓናዊ ባለሙያ እያስመጣ ለአካባቢው አርሶ አደሮችና ቡና ላኪዎች ሥልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የኩባንያውን ማኅበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ስትራቴጂ እንደሆነ በተነገረለት በዚህ እንቅስቃሴም፣ ወደፊት በቋሚነት ሊካሄድ ይችላል የተባለውን የቡና የጥራት ውድድር ለማካሄድ ከአገር በቀሉ መታድ የግብርና ልማት ኩባንያ (ካቡ ኮፊ በተባለው ምርቱ ይታወቃል) ጋር የጥራት ውድድር እያዘጋጀ ይገኛል፡፡

በመጪው ዓመት መጋቢት ወር ይካሄዳል የተባለው ውድድር 24 ሺሕ አምራቾችን የሚያሳትፍ ሲሆን፣ አሸናፊ የሚሆኑት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ተወዳዳሪዎች ከመደበኛው የቡና ዋጋ ከአሥር እስከ 30 በመቶ ጭማሪ የሚደረግበት የስድስት ሺሕ ኩንታል ቡና ግዥ እንደሚፈጸምላቸው ኩባንያው አስታውቋል፡፡ ከጥር እስከ የካቲት ባለው ጊዜ ውስጥ ተወዳዳሪዎች ቡናዎቻቸውን ለውድድር ያቀርባሉ የተባለ ሲሆን፣ የመወዳደሪያ መሥፈርቶቹ ወደ ፊት ይፋ እንደሚደረጉ የዩሲሲ ኩባንያ ኃላፊዎች አስታውቀዋል፡፡

ጃፓን ከአሜሪካና ከጀርመን ቀጥላ በዓለም ሦስተኛ ቡና የምትገዛ አገር ስትሆን ከጣሊያን፣ ከፈረንሣይና ከእንግሊዝ በመቅደም በቡና ጠጪነት ከሚታወቁት አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ ዩሲሲ ኩባንያ በበኩሉ በጃፓንና በእስያ ቡና ቆልቶ በማዘጋጀት ግንባር ቀደምነቱን ተቆናጧል፡፡ በዓለም ሰባተኛ ደረጃ መያዙን የኩባንያው ወኪሎች ይናገራሉ፡፡ በተለያዩ ዘዴዎች ቡና አዘጋጅቶ ለጃፓናውያን፣ ለእስያውያንና ለአውሮፓውያን የሚያቀርበው ይህ ኩባንያ ቡናን በዱቄትና በፈሳሽ መልክ እንደ ለስላሳ መጠጦች አሽጎ በማቅረብም ስሙ የሚጠራ ተቋም ነው፡፡ በጃፓን የቡና ማሠልጠኛዎችና የቡና ሙዚየም ያለው ዩሲሲ በእንግሊዝ፣ በስፔን፣ በኔዘርላንድስ፣ በስዊዘርላንድና በፈረንሣይ አምስት የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች አሉት፡፡ ከተመሠረተ 80ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው ይህ ኩባንያ በሥሩ 62 ኩባንያዎችን በማቀፍ፣ በዓመት 185 ሺሕ ቶን ቡና በማገበያየት የ2.8 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ ያከናውናል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

↧

በደ/ጽጌ ቅ/ዑራኤል: የ6 ሚ. ብር የሕንፃ ገቢ ምዝበራ ጥያቄ ሳይመለስ ሌላ የሕንፃ ዕብነ መሠረት ሊቀመጥ ነው

$
0
0
  • የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር: “ባልተጣራ ሒሳብ እንዴት ሕንፃ ይሠራል?”
  • የግንባታ ጥናቱ ከክፍያ ነፃ እንደተሠራ ቢነገርም የብር 250,000 ክፍያ እያነጋገረ ነው
  • ሕግን መጣስ፣ ያለዕቅድ እና ያለጥናት ከፍተኛ ገንዘብ ማባከን የአስተዳደሩ መገለጫ ነው
  • በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ የተካሔደው የምዝበራ እና ብክነት ምርመራ ውጤቱ አልታወቀም
  • ነገ ዕብነ መሠረቱን የሚያስቀምጡት ፓትርያርኩ ኹኔታውን እንዲያጤኑት ተጠይቋል

st-urael-church-bld-complexብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ነገ ነሐሴ ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው፣የሕንፃ መሠረት ደንጊያ እንዲያስቀምጡ መርሐ ግብር ተይዞላቸዋል፡፡

በቀድሞው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የታቀደው ግንባታው÷ የካህናት ማረፊያ፣ የአብነት ት/ቤት እና የሰንበት ት/ቤት አዳራሽእንደሚያካትት ተገልጧል፡፡

የግንባታው ጥናት፣ የምሕንድስና ሞያ ባላቸው በአንድ የቀድሞው የሰንበት ት/ቤቱ አባል እና በሌላ ምእመን ከክፍያ ነፃ በበጎ አድራጎት መሠራቱ ቢነገርም፣ በስማቸው ቃለ ጉባኤ ተሠርቶ ወጪ ለማድረግ የታቀደው ብር 250,000 የወቅቱን የሰበካ ጉባኤ አባላት እያነጋገረ ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ የግንባታ ወጪው በዝርዝር እንዳልተሠራ እና በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሠረት በሀገረ ስብከቱ እና በሊቀ ጳጳሱ መመሪያ እንዳልተሰጠበት የደብሩ ሠራተኞች ጠቁመዋል፡፡ “መነሻ እና መድረሻው በማይታወቅ የገንዘብ ወጭ እንዴት ሕንፃው ይሠራል?” ሲሉ የሚጠየቁት ሠራተኞቹ፣ ግንባታው የሚታወቅ የጸደቀ በጀት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

የደብሩ ሒሳብ ሹም፣ የ2007 ዓ.ም የበጀት ዓመት ሊዘጋ ሰባት ቀናት ሲቀሩት ወደ ማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል መዘዋወራቸውን በመቃወም፣ ከመጋቢት/2005 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 22/2007 ዓ.ም. ድረስ ለ27 ወራት ከብር 54 ሚሊዮን በላይ ገቢ እና ወጪ የሠሩባቸው የሒሳብ ሰነዶች እና መዛግብት በገለልተኛ እና ሕጋዊ ኦዲተሮች በይፋ እንዲመረመርላቸው ፓትርያርኩን ጠይቀዋል፡፡

በሒሳቡ ሹሟ ጥያቄ መሠረት ሒሳቡ ሳይመረመር እና ሳይጣራ የሌላ ሕንፃ መሠረት መጣሉ አግባብነት እንደሌለው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምእመናን ተችተዋል፡፡ አያይዘውም፣ ለደብሩ ከፍተኛ ገቢ ለሚያስገኘው ሕንፃ ዕድሳት ባለመደረጉ ይዞታው እየተጎዳ ባለበት የሌላ ሕንፃ መሠረት መጣሉ ጥያቄዎችን የሚያስነሣ ነው፤ ብለዋል፡፡

ምእመናኑ እንደሚናገሩት፣ ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኘው የወቅቱ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር፣ እውነቱ መውጣቱን እንደሚሹ እና ሒሳቡ ተጣርቶ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ወደ ግንባታው መሔዱን ነው የሚመርጡት፡፡

በደብሩ ስለተፈጸመው የገንዘብ ብክነት እና ምዝበራ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እንደሚያውቁ የጠቆሙት ምእመናኑ፣ ከቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ ውጭ ስለተፈጸሙ የአስተዳደር እና የፋይናንስ አሠራር ችግሮች በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ሀገረ ስብከቱ ማጣራት ቢያካሒድም ውጤቱ እንዳልተገለጸላቸው አስታውሰው፣ ቅዱስነታቸው በነገው ዕለት ዕብነ መሠረቱን ከማስቀመጣቸው አስቀድሞ ስለ ግንባታው በተጨባጭ ያሉ እውነታዎችንና አግባቦችን በጥንቃቄ እንዲያጤኑት ጠይቀዋል፡፡

በአስተዳደሩ፣ ያለ ዕቅድ እና ያለጥናት የሚሠሩ ሥራዎች እና የሚፈጸሙ ክፍያዎች፣ የወጣባቸውን ከፍተኛ ገንዘብ ያኽል ጥራት እንደሌላቸው ተነግሯል፡፡ ለካህናት “ጊዜያዊ ቤት” በሚል እስከ ብር 600,000 ወጪ ቢደረግም ያለጥናት በመሠራቱ ክፍቱን መቀመጡ በአብነት ተጠቅሷል፡፡ ለደብሩ ዐይነተኛውን ገቢ ለሚያመነጨው እና በርካታ ሱቆች ላሉት ሕንፃ ጠርዝ የመሠረት ሥራ ከፍተኛ ወጪ ቢወጣም ጥራቱ ደረጃውን የጠበቀ እንዳልኾነ ተገልጧል፡፡

በአንጸሩ ጥቂት የደብሩ የአስተዳደር ሓላፊዎች፣ ውሳኔን በውሳኔ በመሻር ከሕንፃው የኪራይ ገቢ ላይ ከብር 6 ሚሊዮን በላይ ወደ ደብሩ ካዝና አለመግባቱን፤ በውል ላይ ውል በመዋዋል ከአንድ የሕንፃ ኪራይ ብቻ ብር 487,869.32 መመዝበሩን፤ የደብሩን የሕንጻ ኪራይ የአፈጻጸም ችግሮች ያጣራው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አጥኚ ኮሚቴ በሒሳብ ሹሟ አማካይነት ከመዝገብ ቤት በቀረቡለት ሰነዶች ማረጋገጡ ታውቋል፡፡

በኮሚቴው ጥናታዊ ሪፖርት እንደተዘረዘረው፣ በትክል ዘመኑ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቀደምት አብያተ ክርስቲያን አንዱ የኾነው የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን፡-

  • ሰፋፊ የንግድ ተቋማት ካሏቸው አጥቢያዎች መካከል በርካታ የንግድ ማእከላትን በማቀፍም ተጠቃሽ ቢኾንም አትራፊዎቹ ግን ግለሰብ ነጋዴዎች እና ከእነርሱ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት የአስተዳደሩ እና የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ናቸው፡፡
  • የደብሩ አስተዳደር፣ የንግድ ተቋማቱን የሚያከራየው ከሕጋዊ አሠራር ውጭ ያለጨረታ ነው፡፡ በደብሩ አካባቢ የሚከራዩ የግለሰቦች እና የደብሩ ሱቆች ኪራይ ዋጋ በእጅጉ የሚለያይ በመኾኑ ደብሩ ተጎጂ ኾኗል፡፡
  • ያለጨረታ የተከራዩት የንግድ ቤቶች የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ውስጥ ለውስጥ ስለሚሸጡ እና በሰፊው ለሦስተኛ ወገን ስለሚተላለፉ፣ ለደብሩ ገቢ መኾን የሚገባው የስም ማዘዋወርያ ብር 50,000 ገቢ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ ይህም ግለሰብ ነጋዴዎች እርስ በርስ እንዲጠቃቀሙ በማድረግ ደብሩን ያለአንዳች ጥቅም እያስቀረው ነው፡፡
  • ግለሰብ ነጋዴዎች ከደብሩ የተከራዩትን ሱቅ ሸንሽነው ለግሰለቦች በማከራየት ተጠቃሚ ሲኾኑ አስተዳደሩ በዝምታ አልፏል፡፡ ተከራዮቹ የኪራይ ውላቸው እንዲጸና በማድረግ እና ውል በመዋዋል ሱቆቹ በጨረታ ቢከራዩ ኖሮ ደብሩ ሊያገኝ ይችል የነበረውን ከፍተኛ ጥቅም አሳጥተውታል፡፡
  • አስተዳደሩ፣ በሕጉ መሠረት በካሬ ሜትር መክፈል የሚገባቸውን ክፍያ በአግባቡ የማይከፍሉትን በመከታተል እና በመቆጣጠር ማስከፈል አልቻለም፡፡ ለምሳሌ፣ የቅዱስ ዑራኤል ፋርማሲ ብር 167,552 ዕዳ እያለባቸው ተገቢው ክትትል ባለመደረጉና ተከራዮቹ ከአንዳንድ የደብሩ ሓላፊዎች ጋር በመመሳጠራቸው የተጠቀሰውን ገንዘብ ሳይከፍሉ ቤቱን ለቀው በመሔድ ደብሩን ተጎጂ አድርጎታል፡፡
  • በደብሩ ከሦስት እስከ ስምንት ሱቆች በአንድ ግለሰብ ስም ተከራይተው ይገኛሉ፡፡ ይህ በተናጠል ለተለያዩ ግለሰቦች በጨረታ እንዲከራይ ቢደረግ ኖሮ ደብሩ እጅግ በጣም ተጠቃሚ መኾን ይችል ነበር፡፡ ይህ ቀርቶ ተከራዩ ግለሰብ ለሌሎች በማከራየት ተጠቃሚ እንዲኾኑ ተደርገዋል፡፡

Source:: haratewahido

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>