Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የሺመልስ አብዲሳ ግጭት ቀስቃሽ ንግግር !!

$
0
0
የኦዲፒ ባለስልጣናት ከሰሞኑ ኢሬቻ የሰላም እና የፍቅር ምልክት ነው ብለው በየሚዲያው እየቀረቡ ቢያደነቁሩንም የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንቱ ሽመልስ አብዲሳ ግን በአሉን የግጭት መቀስቀሻ እና የቂም መወጣጫ አድርጎታል። ሰውየው በፖለቲካ ስካር እየተደናበረ መስቀል አደባባይ ለተሰበሰበው ህዝብ እንዲህ አለ “የኦሮሞ ህዝብ እዚህ ነው የተሰበረው፣ እዚህ ነው ውርደት የጀመረው። እዚህ ነው ቅስሙ የተሰበረው። እነ ቱፋ ሙና እና ሌሎች የጊዜው […]

የህዝብ ብዛትን መሠረት አድርጎ የኃይል ሚዛንን ለማሳዬት የሚደረግ አጉል ፉክክር ወዴት ሊያመራ ይችላል?

$
0
0
(በመሐመድ አሊ መሀመድ) በመጀመሪያ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ – ወገኖቼ; እንኳን ለ2012 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡ ቅድም etv ላይ ዶ/ር ጉቱ የተባሉ ወጣት ምሁር ቀርበው በኢሬቻ በዓል ላይ ከስድስት እስከ አሥር ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ሊገኝ ይችላል ከሚለው ግምት በመነሳት; እያንዳንዱ ሰው በአማካይ 3,000 ብር ቢያወጣ በሚል ስሌት ከ18 ቢሊዮን እስከ 30 ቢሊዮን ብር ሊወጣ […]

በጎጠኝነት የታጀበ ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ በብአዴን መንደር አለ –መስከረም አበራ

$
0
0
አልበዛም ወይ መፋዘዙ??? **************************** የአማራ ክልልን የሚያስተዳድረው ብአዴን/አዴፓ የክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ በሚፈልገው ግራ ቀኝ የማየት ነገር ላይ የሚቀረው ብዙ ነው።ፓርቲው የህወሃት የስነ-ልቦና ማኮላሻ ለበቅ ያልገረፈው፣ከራስ መተማመኑ ያልተፋታ፣ወቅቱ የሚፈልገውን አይነት ሃሞተ ኮስታራ አመራር ማስገባት ግድ ይለዋል። ይህ የሆነ አልመሰለኝም። የስልጣን ጥም ብቻ ህዝብን ታዳጊ መሪ አያደርግም። በአዴኖች ክልሉን የመምራቱን ስራ በትርፍ ጊዜው እንደሚሰራ ሰው ከልባቸው የያዙት […]

ፍልስፍና፣ ኃይማኖትና አዲስ ኪዳን 

$
0
0
ፍልስፍናና ኃይማኖት ከክርስቶስ ልደት 361 ዓመት በፊት ፕላቶ (Plato) ከምዕራብ አቴንስ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኘውን የግል ዘመናዊ ቤቱን ጓሮውን ጭምር ለአምልኮው ማህበር (cult association) በስጦታ አበረከተ። ትምህርት ቤቱን በአካባቢው ተወዳሽ በነበረው አካዴሞስ (Akademos) ስም ሰየመው። ይህ ትምህርት ቤት ለሚቀጥሉት መቶ ዓመታት መላውን ኅዋና ጠፈር በሚያጠናው ሥነ–ትዕይንት (cosmology) ምርምርና የሥነ–አምላክ (theology) ትምህርት ማስተማርያ ሆኖ ቀጠለ። ከፕላቶ እልፈት በኋላ የእርሱ ተከታይ የሆኑት ስፔሲፖስና (Speusippos) ዜኖክራትስ (Xenocrates) ይህንኑ የፕላቶ ፈለግ ተከትለው ፕላቶናዊ (Platonism) ብለው የጠሩትን አስተምርሆ […]

ዋይት ሃውስ በአባይና በኅዳሴ ግድብ ላይ መግለጫ አወጣ

$
0
0
ቪኦኤ ዜና ዋሺንግተን ዲሲ — የኢትዮጵያን ታላቁን ኅዳሴ ግድብ ለመሙላትና አገልግሎቱንም ለማስኬድ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የትብብር፣ ዘላቂነት ያለውና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ ስምምነት ላይ ለመድረስ በግብፅ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል እየተካሄዱ ያሉትን ድርድሮች እንደምትደግፍ ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቀች። ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የፕሬስ ኃላፊ ማምሻውን የወጣው አጭር መግለጫ ”ሁሉም የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች የምጣኔኃብትና የብልፅግና መብት አላቸው” ይላል። በመቀጠልም “እነዚያን መብቶች […]

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ ዳይሬክተሮችን ጨምሮ በቅርቡ ጊዜ ብቻ ስራ የለቀቁ የ41 ሰራተኞች ዝርዝር (ከድርጅቱ የሰው ሀይል አስተዳደር የወጣ ደብዳቤ ያሳያል)

$
0
0
በእዚህ ውስጥ ያልተካተቱ በርካታ ሲሆኑ ከነዚህ አንዱ የኢንጂነሪንግ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዮሀንስ ይገኝበታል። የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አየር መንገዱን መደበቂያ አድርጎ ውሎ እና አዳሩን ሚዲያ ላይ አድርጎ ተአምር የሰራ ቢያስመስልም ብዙ የተበላሹ እና የተቀበሩ ነገሮች ነገ ላይ ሲመነዘሩ አየር መንገዱን አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች እንዳሉ የሚያውቁ እና ለውጥ ይመጣል ብለው ሲጠብቁ የነበሩ ሰራተኛ አቶ […]

ሰማህ ወይ የነፍጠኛ ልጅ! –በላይነህ አባተ

$
0
0
ነፍጠኛ ባቀናው አገር፤ አፉን እንደ ሊጥ ዕቃ ቦርግዶ፣ ስምንተኛው ሺ ሲቃረብ፤ አሳማም ነብር ናቀ አሉ፡፡ ነፍጠኛ ባያስከብረው፤ ጠላትን ደፍቆና አናፍጦ፣ ሥሙ ጆቫኒ በሆነ ነበር፤ ይኸ ገንፎ ዘረጦ! ቀን ዱብ እማያደርገው፤ ግዜ እማይሰቅለው ጉድ የለ፣ ነፍጠኛም በጓጉንችሮች፤ ሲታማ ሲረገም ዋለ፡፡ እንኳን የነፍጠኛን ልጅ፤ እግዜርስ እንዴት ይነደው? በደም አገር ጠባቂን፤ ድንፈፍ ሲያብጠለጥለው፡፡ ነፍጠኛ አርግ ተምድር፤ ውጣ ሽቅብ […]

ዲስኩሩና ፉከራው ይብቃ! (በጋዜጠኛ አበበ ገላው)

$
0
0
አዲሶቹ የአደባባይ ፎካሪዎች ለህወሃት አድረው ህሊናቸውን እንደ አሞሌ ጨው ለዳቦ ሸጠው ኦሮሞን ጨምሮ ጭቁን የድሃ ልጅ ሲገርፉና ሲያስገርፉ፣ ሲገድሉና ሲያስገድሉ ነበር። ይህን ሃቅ ችላ ያልነው ጠፍቶን ሳይሆን ለውጥ መጥቷል፣ እኩልነት ታውጇል በሚል የይቅርታ መንፈስ ነበር። እድል ይሰጣቸው ብለን የተከራከርነው የተስፋ ብርሃን ፈንጥቋል በሚል እምነት እንጂ ገና በተግባር ያልተፈተነ ሰበካ አስደስቶን፣ ዲስኩሩ አስደምሞን አልነበረም። ነጻት፣ እኩልነት፣ […]

 ዛሬስ ! ጉዞችን ወዴት ነው??? –መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

$
0
0
ኢትዮጵያን ፣ ብቻ ሳይሆን መላውን አፍሪካ ፣በዘር ና በጎሣ ከፋፍሎ ለብዝበዛ የማመቻመች ሥራ የተጀመረው፣ከባርያ አሣዳሪው ሥርዓተ ማህበር ጀምሮ ነው።   የታሪክ እውነት እንደሚያስረዳን ፣ ፀሐይ፣በሚናፈቅበት በበረዷማ አህጉር ፣ ባልተመቻቸ የአየር ንብረት ና የምግብ እጥረት ባየለበቱ አውሮፖ የሚኖረው የሰው ልጅ፣ለመኖር የሚያደርገው መፍጨርጨር “ጠያቂ፣አሳቢ ና ፈጣሪ”ስላደረገው ፣መርከብን  ሰርቶ፣ከሞት ወጥመድ የሚያመልጥበትን አህጉር ና ሀገር ለማሰስ ተነሳ። በነማጅላን እና […]

ሸኖ ላይ መንገድ በመዘጋቱ የግሸን መንገደኞችን ጨምሮ ብዙዎች እየተጉላሉ ነው

$
0
0
ከግሸን ተመላሾችን ጨምሮ በርካታ መንገደኞች ሸኖ ላይ ሲደርሱ “ቄሮ” ነን ባሉ የአካባቢው ወጣቶች መንገድ ተዘግቶባቸው እየተጉላሉ መሆኑን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ገልጸዋል። ይህን መሰሉን ተንኩዋሽ እርምጃ የወሰዱ ወጣቶች በአካባቢው የጸጥታ ሰዎች ጭምር እየተደገፉ መሆኑን የሚገልጹ ወገኖች ምክንያት ብለው ያነሱት በደብረ ብርሃን እሬቻ አክብረው ሲመለሱ የታሰሩ አሉ የሚል ቢሆንም እነማን እንደታሰሩ በዝርዝር የተገለጸ ነገር የለም። የፌደራል መንግሥት […]

የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ተከበረ

$
0
0
በዓሉ በሆራ አርሰዴ በዛሬው ዕለት ማለዳ ላይ በአባገዳዎች ምርቃትና ምስጋና ተጀምሮ በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል። ኢሬቻ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከበር ሲሆን፥ በበጋ ወቅት በከፍታ ቦታ ላይ የሚከበር ወይም ኢሬቻ ቱሉ እንዲሁም በጸዳይ ወቅት መግቢያ ላይ በወንዝ ዳር የሚከበረው ወይም ኢሬቻ መልካ በመባል የሚታወቅ ነው። በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ የተከበረው ኢሬቻ መልካ የኦሮሞ ህዝብ የክረምት […]

ግልፅ ደብዳቤ ለአቶ ሽመልሽ አብዲሳ፤ (ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)

$
0
0
የተወሰንን ግለሰቦች ኦሮአማራ እያልን ስንጮህ ሕውሃት እና የኦነግ አጋሮች ሲሰድቡን ከረሙ፡፡ የእነርሱ መንጫጫት እንብዛም አሳስቦን አያውቅም ነበረ፡፡ አሁን ደግሞ በሚያስደነግጥ እና በሚያሳፍር ትችት እና ዲስኮርስ የአማራን እና የኦሮሞን ግንኙነት ለማክሰም ሞከርክ፡፡ ሆኖም ግን ለብዙ ዘመናት በአብሮነት የኖሩት ህዝቦች፤ በፓርቲና በግለሰቦች ፈቃድ ቀድሞውንም ያልተመሰረተ በመሆኑ ሊፈርስ አይችልም፡፡ እንደዚህ አይነት ሕውሃታዊ፤ኦነጋዊ እና አክራራዊ ገለፃ አንተ ይዘህ በመቅረብህ […]

ሶደሬ–ዛሬና ትናንትና –መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0
መስፍን ወልደ ማርያም መስከረም 2012 ከሶደሬ ጋር የተዋወቅሁት የዛሬ አርባ አምስት ዓመት ግድም ነው፤ አብሮ አደጌ ጌታቸው መድኅኔ የየረርና ከረዩ አውራጃ ገዢ ነበር፤ እሱ ቤት እያደርሁ ሶደሬ እሄድ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሶደሬ ባዶ ቦታ ነበር፤ የጠበል ሙቅ ውሀ መታጠቢያ ነበረ፤ ባለቤት አልነበረውም፤ የሕዝብ ነበር፤ በጭራሮ ታጥሮ ማንም ሰው ደሀ ሆነ ጌታ ያለምንም ክፍያ ገብቶ በአግዚአብሔር […]

የኦህዲድ/ኦነግ ሰሞነኛ አፓርታዳዊ ጉዞ –ምሕረት ዘገዬ

$
0
0
“እጎድጓዳ ሥፍራ ይበቅላል ደደሆ፤ የፈራነው ነገር መጣ ድሆ ድሆ” ይባል ነበር በዘፈን፡፡ አሁን የምለውንም ነገር ዶ/ር አቢይ አህመድ አያውቅም በሉና እንደለመደብኝ ይግረመኝ፡፡ እ.አ.አ በ1990ዎቹ ከደቡብ አፍሪካ የተባረረው ነጮች በጥቁሮች ላይ ይፈጽሙት የነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ከነኮተቱ ወደ ሀገራችን ሰተት ብሎ በመግባት ቅርጹን እየለዋወጠ በመንግሥታዊ ተቋምነት የገዛ ቤተ መንግሥታችን ውስጥ ተገሽሮ ኅልውናችንን መፈታተን ከጀመረ እነሆ 30 ዓመታትን […]

ችግሩን ያልተቀበለ ስብስብ ለዐማራ ዋና የመፍትሔ አካል አይሆንም!

$
0
0
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት           እሑድ መስከረም ፳፭  ቀን ፪ሺህ፲፩ዓ.ም.               ቅጽ ፯ቁጥር ፲፭ አሁን በቅርብ ቀናት በሃገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተመሥርቶ ራሱን ዓለም አቀፍ የዐማራ ህብረት ( Global Amhara Coalition) በሚል ስም የተሰየመው ድርጅት መስከረም 18 ቀን 2019 እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር የድርጅቱን ምሥረታ አስመልክቶ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ማወጣው መግለጫ (ሙሉ ይዘቱን ለማንበብ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ […]

የ2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

$
0
0
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ ምደባ በመጠናቀቁ ከዛሬ ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ ተገለፀ፡፡ በዚህ መሰረት ተማሪዎች በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዌብ ሳይት www.neaea.gov.et በመግባት ማየት እንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን ጳጉሜን 6 ቀን 2011 ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ […]

አቶ አንዱአለም አራጌ በዋሽግተን ዲሲ ያደረገው ንግግር

$
0
0
አቶ አንዱአለም አራጌ በዋሽግተን ዲሲ ያደረገው ንግግር

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ም/ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው ድንቅ መልስ ለሽመልስ አብዲሳ

$
0
0
“የሰበረም ሆነ የተሰበረ/የሚሰበር ነፍጠኛ እንዲሁም የተሰበረ ሕዝብ አናውቅም። የተሰባበረች ሀገር ጠግነው በክብር ያቆሙ እንጅ የትኛውንም ሕዝብ የሰበሩም ሆነ በማንም የሚሰበሩ ነፍጠኞች አልነበሩም፤ የሉም፤ አይኖሩምም። ለሀገር ዳር ድንበር መከበር አጥንታቸው የተስበረና ደማቸው የፈሰስ እንጅ የራሳቸውን ወንድሞች የሰበሩ ነፍጠኞችን አናውቅም። እኛ የምናውቀው ነፍጠኛ መይሳውን አፄ ቴዎድሮስን ነው። እርሱ ቅስሟ ተሰባብሮ የተበተነችን ሀገር ለመሰብሰብ ላይ ታች ሲዋከብ በገዛ […]

ሽመልስ አብዲሣ… ኢጆሌ “እንኳዕ ካባኹም ተፈጢርና!” –ይነጋል በላቸው

$
0
0
ይነጋል በላቸው (yinegal3@gmail.com) እንኳን ለትዕይንተ ብዙው የመስከረም ወር – 2012ዓ.ም – አደረሳችሁ፡፡ መለስ ዜናዊ እንዳልሞተ ተዓምራዊ በሚመስል የነገሮች አካሄድና ምስስሎሽ እየተረዳን ነው፡፡ ብዙ ግልገል መለሶች ሀገር ምድሩን ሞልተውታል፡፡ መለሳዊ መምህራንም ከየዕድሜ ክልሉ በብዛት አሉ፡፡ ዶ/ር ገመቹ መገርሣ የተባለው ገልቱ አንዱና አንጋፋው ነው፡፡ እነሕዝቅኤል፣ ፀጋየ አራርሣ፣ ጃዋርና ሌሎች ጎልማሣና ታዳጊ የጥፋት ዘመቻው አባላትም አሉ፡፡ ስለዚህ መለሲስም […]

አንዷለም አራጌ በሕዝቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት እጅግ በጣም የላቀ እንደሆነ ነው- የኢዜማ የዲሲ ስብስባ በጣም የተሳካ ነበር 

$
0
0
ግርማካሳ የአንዷለም የዲሲ ስብሰባ በጣም የተሳካ ነበር። ያለፈው ጊዜ ብርሃኑ ስብሰባ በዲሲ ሲጠራ አራት ሰዓት ነበር ስብሰባው የወሰደው። ብርሃኑ ለአንድ ሰዓት ከአስር ደቂቃ ነበር ያወራው። መጨረሻ ላይ ለሃያ ደቂቃ፣ የሕዝብ አስተያየት ተጠየቀ። ዛሬ አንዷለም ወደ 10 ደቂቃ አካባቢ ነው ንግግር ያደረገው። የመጣሁት ልሰማ፣ ላዳምጥ ነው ብሎ ሰፊ ጊዜ የተሰጠው ስብሰባዉን ለማዳመጥ ለመጡ ነበር። ምም አይነት […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live