Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በምዕራብ አሪሲ ለትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት እየጠቆመ ታጋዮችን ሲያስጠቃ የነበረ የኦህዴድ ካድሬ መኖሪያ ቤት በነዋሪዎች ተቃጠለ

$
0
0


በምዕራብ አሪሲ ኮኮሳ ከተማ ለትግራይ ነጻ አውጪ እያቃጠረ የሚኖረውና በርካታ ልጆችን እየጠቆመ ሲያሳስርየኦህዴድ ካድሬ መኖሪያ ቤት በነዋሪዎቹ ተቃጠለ::


ኩሬአውያን –ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ትውፊታውያን የሀገራችን ሰዓሊዎች የማያመዛዝንን ሰው ሲስሉ አንድ ዓይና አድርገው ይስሉት ነበር፡፡ ሰፋ አድርጎ የማያይ፤ እውነትን በከፊል ብቻ የሚቀበላት፤ ከሚያውቀው ውጭ ሌላ ነገር ያለ የማይመስለው ነው ማለታቸው ነው፡፡ ‹እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል› የሚል አባባልም አለ፡፡ ዕውቀትህን፣ አመለካከትህንና አካሄድህን ባሻሻልክ ቁጥር ያላየኸውን ታያለህ፣ ያልሰማኸውን ትሰማለህ፤ ያልተገለጠልህ ይገለጥልሃል፤ የረቀቀው ይጨበጥልሃል፤ እውነት ነው ያልከው ውሸት፣ ውሸት ነው ያልከውም እውነት ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ሲሉ ነው፡፡
daniel

ቀደምት ሊቃውንት ሁለት ዓይን የተሰጠን በአንዱ የራሳችን በሌላው የሌላውን ለማየት ነው፡፡ ሁለት ጆሮ የተሰጠን በአንዱ የራሳችንን በሌላው የሌላውን ለመስማት ነው፡፡ ሁለት እጅ የተሰጠን በአንዱ ለመስጠት በሌላው ለመቀበል ነው፡፡ ሁለት እግር የተሰጠን በአንዱ ወደራሳችን በሌላው ወደ ሌላው ለመሄድ ነው ይሉ ነበር፡፡

ሞንጎልያውያንም ከዚህ ጋር የሚሄድ ብሂል አላቸው፡፡
በአንዲት የሞንጎልያ ትንሽ መንደር ውስጥ በምትገኝ ኩሬ አንዲት ዓይን ብቻ ያለቺው ዕንቁራሪት ይኖር ነበር፡፡ ለእርሱ ዓለም ማለት ያቺ ኩሬ፣ ንጉሥም ማለት እርሱ ነው፡፡ ከእርሱ ኩሬ የተሻለ ቦታ፣ ከእርሱም የበለጠ ዕድለኛ የለም፡፡ የሚመኘው ነገር ቢኖር እርሱ ያገኘውን ይህንን ታላቅ ነገር የሚካፈለው ጓደኛ እንዲያገኝ ብቻ ነበር፡፡

አንድ ቀን በአካባቢው ከባድ ዝናም ጣለ፡፡ ምድሪቱንም የሚገለባብጣት መሰለ፡፡ ዕንቁራሪቱ በዚያች ለእርሱ ምርጥ በሆነችው ኩሬ ውስጥ በመሆኑ ምንም ነገር አይመጣብኝም ብሎ አመነ፡፡ ዝናቡ ግን አካባቢውን ደበላልቆ ከኩሬው ማዶ የሚገኘውንና ዕንቁራሪቱ መኖሩን የማያውቀውን ኡቩስ ኑር የተባለውን ጨዋማ ባሕር እንዲሞላ አደረገው፡፡ ባሕሩ ሲሞላ በውስጡ የነበሩትን እንስሳት ተፋቸው፡፡ አንዱ የባሕር ዔሊም በጎርፉ ተወስዶ የማያውቀው ቦታ ወደቀ፡፡

ዔሊው የኡቩስ ኑር ባሕርን ሊያየው አልቻለም፡፡ የት ቦታ እንዳለም አላወቀም፡፡ ወደየት አቅጣጫ መሄድ እንዳለበትም ግራ ገባው፡፡ ነገር ግን በቆሙበት ቦታ ከመሞት እየሄዱ መሞት ይሻላል ብሎ መጓዝ ጀመረ፡፡ ቢሄድ፣ ቢሄድ፣ ቢሄድ መንገዱ ሊያልቅለት ባሕሩንም ሊያገኘው አልቻለም፡፡እንዲያውም እየደከመውና እየራበው መጣ፡፡ ሙቀቱንም መቋቋም አልቻለም፡፡ ወደ ኡቩስ ኑር ባሕር ሳልደርስ ልሞት እችላለሁ ብሎ ሠጋ፡፡

ወደ ባሕሩ በቀላሉ ሊደርስ እንደማይችል የተረዳው ዔሊ ነፍሱን ሊያድንለት የሚችል አንዳች ውኃ እየፈለገ ሳለ የዕንቁራሪቱን ኩሬ ተመለከተ፡፡ በዔሊ ፍጥነት ተንከላውሶ እዚያ ኩሬ ውስጥ ተወርውሮ ዘፍ አለ፡፡ ዔሊው ኩሬው ውስጥ ዘፍ ሲል የኩሬው ውኃ ከጥፋት ውኃ ባልተናነሰ ተናወጠ፡፡ ዕንቁራሪቱም ሰምቶት የማያውቀውን በመስማቱና አይቶት የማያውቀውን በማየቱ በድንጋጤ ልቡ ቀጥ አለች፡፡ ከሰዓታት በኋላ ሲረጋጋ አንዳች የሚያህል ፍጡር በኩሬው ውስጥ ሲንከላወስ ተመለከተ፡፡

‹ለመሆኑ ማነህ? ከየትስ መጣህ? እዚህስ ምን ታደርጋለህ?› የጥያቄ መዓት አወረደበት፡፡ ዔሊው ጥሙን የሚያስታግሥለትን ውኃ ከተጋተ በኋላ ‹እኔ ዔሊ ነኝ፡፡ የመጣሁትም ከኡቩስ ኑር ባሕር ነው፡፡ እዚያ በተከሠተ ጎርፍ ከባሕሩ ወጥቼ ጠፋሁ፡፡ ወደ ባሕሩ እመለሳለሁ ብዬ ስጓዝ በውኃ ጥም ልሞት ደረስኩ፡፡ ፈጣሪ ይመስገን እዚህ ኩሬ ውስጥ ጣለኝ› አለው፡፡

‹ታድያ አሁን ምን እያሰብክ ነው?› አለው ዕንቁራሪቱ፡፡ ‹እኔ ወደ ባሕሩ መመለስ ነበር የምፈልገው፡፡ ነገር ግን መንገዱን አላውቀውም፡፡ በመካከልም በውኃ ጥም እንዳልሞት ፈራሁ፡፡ እናም ካላስቸገርኩህ በጋው እስኪያልፍ እዚህ አንተ ጋ ብከርም ምን ይመስልሃል?› አለው፡፡ ለብዙ ዘመናት ብቻውን የኖረው ዕንቁራሪት ጓደኛ ስላገኘ ደስ ብሎት ፈነጠዘ፡፡ ይህን እርሱ በኩሬው ውስጥ ያገኘውን ልዩ ደስታና ርካታ የሚያካፍለው ጓደኛ አገኘ፡፡

ዔሊው የበጋውን ወቅት የሚያሳልፍበት ቦታ በማግኘቱ እፎይ ያለ ቢመስለውም ዕንቁራሪቱ ግን በጥያቄዎች ያጣድፈው ነበር፡፡ ከኩሬው ውጭ ያለውን ዓለም የማያውቀው፤ በዓለም የመጨረሻው፣ ትልቁና ምቹው ቦታ ኩሬው የሚመስለው ዕንቁራሪት የጥያቄ ናዳ አወረደበት፡፡ ‹ለመሆኑ ያንተ ባሕር እንደዚህ ኩሬ ውብና ምቹ ነው› አለው፡፡ ዔሊውም ዕንቁራሪቱን ላለማስከፋት ብሎ ‹ያንተ ኩሬ ውብና ምቹ ነው› አለው፡፡ ዕንቁራሪቱም በዚህ ተደሰተና ‹ለመሆኑ ያንተ ባሕር ከእኔ ኩሬ ይበልጣል› አለው፡፡ ዔሊውም ‹የኡቩስ ኑርን ባሕር ከዚህ ትንሽ ኩሬ ጋር ማነጻጻር የማይታሰብ ነው፡፡ ወርድና ቁመቱን ማንም ሊለካው አይችልም፤ አጅግ ሰፊ፣ ጥልቅና ምቹ ነው፡፡ አያሌ የባሕር እንስሳት ይገኙበታል› አለና መለሰለት፡፡

ዕንቁራሪቱ ደነገጠ፡፡ እዚህ ኩሬ ውስጥ የገባው እጅግ ውሸታም ዔሊ ነው ብሎ አመነ፡፡ ከዚህ ኩሬ የበለጠ ነገር በዓለም ላይ ሊገኝ አይችልም፡፡ ዕንቁራሪቱ በአንድ ዓይኑ ሲያያት የእርሱ ኩሬ ለእርሱ እጅግ ሰፊ፣ ማንም ሊደርስባት የማይቻላት ናት፡፡ ለመሆኑ በዓለም ላይ ከዚህ የሚበልጥ ምን ምቹ ቦታ ይገኛል? ብሎ አሰበና ‹የኡቩስ ኑር ባሕር የሚባል ነገር የለም፡፤ ቢኖርም ከዚህ ኩሬ ፈጽሞ ሊበልጥ አይችልም፡፡ አንተ ውሸታም ነህ፡፡ ሆን ብለህ እኔን ለማስደነቅና ከዚህ እንድወጣ ለማድረግ ነው እንጂ ከዚህ የሚበልጥ ባሕር ፈጽሞ የለም፡፡ በዓለም ላይ ያለው ብቸኛው፣ ታላቁና ምቹው ውኃ ይሄ ኩሬ ነው› አለው፡፡

ዔሊውም ‹ወዳጄ ሞኝ አትሁን፡፡ የማታውቀውን ነገር ሁሉ የለም አትበል፡፡ አንተ በአንድ ዓይንህ ስለምታያት ይቺ ኩሬ ትልቅ ትመስልሃለች እንጂ እንኳን ከዚህ ኩሬ ከኡቩስ ኑር ባሕር የሚበልጡም አሉ፡፡ እኔ የያዝኩት ብቻ የመጨረሻው ነው ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ዕውቀቴ የመጨረሻው ነው ብሎ እንደሚያስብ ፍጡር የሚጎዳ የለም› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ዕንቁራሪቱ ክፉኛ ተቆጣ ‹ሞኝ አልከኝ፡፡ አንተ ከሌላ ዓለም የመጣህ ፍጡር ነህ፡፡ ከዚህ ኩሬ የሚበልጥና የተሻለ ነገር አለ ብሎ የሚለኝ ለእኔ የመጨረሻው ውሸታም ነው፡፡ ይህን ኩሬ እስካሁን እኔ ዋኝቼ አልጨረስኩትም› እያለ አመናጨቀው፡፡

ዔሊው ይህንን ንግግር ለማመን አልቻለም፡፡ የዕንቁራሪቱን ደኅነኛ ዓይን እያየ ‹አንተ ይህቺን ኩሬ የዓለም መጨረሻ አድርገህ ማየትህ አይገርመኝም፡፡ ያለህ አንድ ዓይን ብቻ ስለሆነ፡፡ የሚገርመው በሁለት ዓይኑ የሚያየውን ሁሉ መቃወምህ ነው፡፡ ሁላችንም በአንተ አንድ ዓይን ልናይ አንችልም፡፡ ላንተ ያልታየህ ሁሉ የለም፤ አንተ ያልደረስክበት ሁሉ አልተፈጠረም፤ አንተ ያልኖርክበት ሁሉ ምቹ አይደለም ብለህ ታስባለህ፡፡ ዓለምን በልክህ ቀደህ ሰፍተሃታል፡፡ ሁላችንም ደግሞ ባንተ ልክ እንድናሰፋት ታስባለህ፡፡ ይህ የመጨረሻው ሞኝነት ነው፡፡ እኔ ብቻ እና የኔ ብቻ ትክክል ነው ብሎ ማሰብ ነው ከዚህ ኩሬ እንዳትወጣ ያደረገህ፡፡ ሁሉንም ነገር በኩሬው ልክ ታስበዋለህ፡፡ በእውነትም አንተ የመጨረሻው ሞኝ ነህ፡፡

ብልህ ብትሆን ኖሮ ስለ ሌላውና ሌላውንም ለመስማት ትፈልግ ነበር፡፡ ብልህ ብትሆን ኖሮ ካንተ የሚያንስም፣ ካንተ የሚስተካከልም፣ ካንተ የሚበልጥም መኖሩን አምነህ ትቀበል ነበር፡፡ ብልህ ብትሆን ኖሮ ስለ ሌላው ዐውቀህ ኅሊናህን ታሰፋው ነበር፡፡ ብልህ ብትሆን ኖሮ ካንተ የተለየ ዕውቀትና ልምድ ያላቸውን ታዳምጥ ነበር፡፡ ብልህ ብትሆን ኖሮ ለመናገር ብቻ ሳይሆን ለመስማት ዕድል ትሰጥ ነበር፡፡ በል ይመችህ፤ እዚሁ ኩሬህ ውስጥ ኑር፡፡ እውነትም ከዚህ የተሻለ ላንተ አይገኝም፡፡ እዚህ ኩሬ ውስጥ የምትኖረው ኩሬው ከሁሉም የሚበልጥ ስለሆነ ሳይሆን ላንተ ስለሚመጥንህ ነው፡፡ ቀሪ ሕይወቴን ከሞኝ ጋር ከምኖር ብልሆች ወዳሉበት እየሄድኩ ብሞት ይሻለኛል› ብሎ ከኩሬው ወጥቶ ሄደ፡፡

ዕንቁራሪቱም በአንድ ዓይኑ ሲያይ የኩሬውን ግድግዳ ተመለከተው፡፡ ‹ይህ የዓለም ዳርቻ አይደለምን፡፡ ለመሆኑ ይህ ዔሊ ከዓለም ዳርቻ ውጭ የት ሊሄድ ነው› አለ ይባላል፡፡
ኪችነር፣ ካናዳ

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ ከሌሎች የውጭ ምንዛሬ ምንጮች ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ያውቃሉን? |ጥብቅ መረጃ

$
0
0

screen-shot-2016-10-18-at-5-56-33-am
ዩኤስ አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ከሚረዱት በላይ የእርስዎና የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ የወያኔን ኢኮኖሚያዊ ጉልበት እንዳሳበጠው ደርሰውበታል? ከዚህ ጽሁፍ በስተግራ የተቀመጡትን መረጃዎች ይመልከቱ እና ፍርድዎን ይስጡ!!

በአገሬ ግድያ ይብቃ፣ መከራ ይቁም፣ እኩልነት ይስፈን ብለው ከምር ይጨነቃሉ? ምንስ ላደርግ እችላለሁ ብለው አስበዋል? በዚህ ጽሁፍ ዉስጥ የቀረበው መረጃ አቅመዎን ያሳየዎታል፤ በወያኔ ላይ ያለዎትን ጉልበት ያመለክተዎታል። ከእርሰዎ የሚጠበቀው ከወገኖችዎ ጋር ለመቆም ያለዎት ቁርጠኝነት ብቻ ነው።

ደክመው ያገኙትን ዶላር፣ ዩሮ ወይም ፓውንድ ወያኔ እንዳይደርሰው ካደረጉ ህወሓት የቆመበትን አንዱን የገንዘብ ምሰሶ ማዳከም ይችላሉ።

ሙሉውን መረጃ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ PDF

“አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !”ምን ማለት ነዉ?

$
0
0

ሸንቁጥ አየለ
ኢትዮጵያ በምልዓት ድና እና ተፈዉሳ ማዬት የምትፈልጉ ሀይላት “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የሚለዉን የአስተሳሰብ አድማስ እንዳትለቁ:: ለነገሩ ይሄ አስተሳሰብ ከተሸነፈ ቆዬ::የጸረ ኢትዮጵያዊነት ሀይላት በመጀመሪያ ወደ ምድር ከስክሰዉ በእግራቸዉ የረገጡት እና ያስረገጡት ይሄን አስተሳሰብ ሀሰት ነዉ በማለት ነዉ:: የአንድን ወገን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚነፋ ፕሮፖጋንዳ ነዉ በሚል ሀሰተኛ ቀመር ተነስተዉ ነዉ ዉድቅ ያደረጉት:: የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አንድነት የለዉም ብለዉ ተነስተዉ ይሄዉ ዛሬ ሀገሪቱን የህልዉናዋ ማክተሚያ ወደ ሆነ አፋፍ ላይ ገፍተዋት ከፍተኛ ትርምስ ዉስጥ ጥለዋታል::ከዛሬዉ ትርምስ ይልቅ የነገዉ ትርምሥምስ ይበልጥ አሳሳቢ ነዉ::

194679_239371246111935_1263846769_o

ሆኖም ሁሉም ቢተራመስ የመጨረሻዉ አሸናፊ እና ገዥ ሀሳብ ሆኖ የሚወጣዉ እና ህዝቡን የሚታደገዉ “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የሚለዉ አስተሳሰብ ነዉ:::: አቢዮት የሚባል ደንባራ ፈረስ በኢትዮጵያ ምድር ከተነሳበት ዘመን ጀምሮ ወያኔ እና ሻዕቢያ የፖለቲካዉን አስተሳሰብ ከተቆጣጠሩበት ዘመን ጀምሮ ይሄን የተቀደስ አስተሳሰብ ከሌሎች ጸረ ኢትዮጵያዉያን ጋር በመሆን አፈር አስግጠዉታል::መጀመሪያ እንዲሸነፍ እና ኢትዮጵያዉያን ለዘበተኛ ወይም ግዴለሽ አቋም እንዲይዙ የተደረገዉ በዚህ አስተሳሰብ ላይ ነዉ::ሲገፋም ይሄ “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የአንድን ብሄር ጥቅም ለማስጠበቅ እንደተነገረ ወይም እንደሚነገር በማስመሰል ጸረ ኢትዮጵያዉያን ብዙ አራግበዉታል:: አሁንም እያራገቡትም ነዉ::

ለመሆኑ “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” ምን ማለት ነዉ?

1. አንድ ሀገር ማለት የማይከፋፈል በአንድ የህግ የበላይነት ስር ያለ የተባበረ ሀገር ማለት::ወያኔ እንደ ቀመረዉ አንቀጽ 39 ግን አንድ ሀገር የሚባል የለም:: ማንም ተነስቶ ከፍቶኛል: ኢትዮጵያዊነት አስጠልቶኛል ብሎ ሀገሩን አፈራርሶ ይሄዳል::ለምን ኢትዮጵያዊነት ከትዳር እንኳን ያነሰ ዋጋ አለዉና::የመጨረሻዉ የጸረ ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ማለት ይሄ ነዉ::አሜሪካኖቹ የተባበረች አሜሪካ ሲሉ የማትከፋፈል አንድ እነቷ የተጠበቀ ታላቅ እና ማንም የማይደፍራት ሀገር ማለታቸዉ እንደሆነዉ ሁሉ መላዉ አለም የአንድ ሀገርን ጽንሰ ሀሳብ በማራመድ ነዉ የተከበረ እና ታላቅ ህዝብ ሆኖ የወጣዉ::ጸረ -ኢትዮጵያዊዉ ወያኔ እና የጸረ – ኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ ሀይላት ግን ይሄ አንድ ሀገር የሚለዉ ሀሳብ የኢትዮጵያ ነገስታት በተንኮል አንድን ወገን ለመጥቀም እንደፈጠሩት በማስመሰል አሁን ድረስ የሀስት መርዛቸዉን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይተፋሉ:: ከሞላ ጎደል ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳቸዉ በትዉልዱ ልብ ዉስት ቅቡልነት አግኝቷል::

2. አንድ ህዝብ
የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ ነዉ ሲባል ከዘረ መል (DNA) አንድነቱ ይጀምራል:: ቢገፋ የኢትዮጵ ልጅ ቢሄድም የዮቶር ልጅ ሄደም ከተባለ የኖህ ልጅ ነዉ::በፍሳሜዉም የአንድ የአዳም ልጅ ነዉ:: በመሃሉ ያሉት የቋንቋ ልዩነቶች በመሰረታዊነት የተለያዬ ህዝብ ነዉ የሚያስብሉት አይደሉም::የኢትዮጵያ ህዝብ ወንድማማች እና በደም የተሳሰረ: በባህል የተቆራኘ: በስነልቦና የተሰናሰነ ብሎም የጋራ ታላቅ የወደፊት ራዕይን ያነገበ ህዝብ ነዉ:: ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ የሚለዉን ሀሳብ/ህዝብ/ የመሰረተዉ ጸረ -ኢትዮጵያዉያን እንደሚሰብኩት ሰዉ ሳይሆን እግዚአብሄር እራሱ ነዉ::በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ ወይም በሰዉ ልጅ ታሪክ አላምንም ማለት መብት ነዉ::ሆኖም የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ እንደሚያስረግጠዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ የእግዚአብሄር ልጅ ነዉ::አንዳንዱ መርዙን ለመርጨት ሲነሳ ይሄ የቆዬ ተረት ተረት ነዉ ብሎ መተርተር እና መዋሸት ይጀምራል::ታሪክ እና እዉነት አዉቆም የቆዬ እና የጥንት መሆኑ ጠፍቶት ሳይሆን አንድ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለዉን እዉነት ለመካድ ስለሚፈልግ ነዉ::ጥላቻዉ እዉነትን ለመካድ ድፍረት ስለሚሰጠዉ ነዉ::
እናም ትንቢተ አሞጽ 9: 7 የእዉነታዉን ማስረገጫ እንዲህ ብሎ ያቀርበዋል:-

“የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፡፡”
እንደዚህ አይነት በርካታ እዉነታዎችን ጥንታዊዉ መጽሀፍ ያቅርብልናል::የኢትጵያዊዉ መልኩ: መልክዓምድሩ እና ስነምግባሩ ሁሉ በመጽሀፍ ቅዱስ በደንብ ግልጽ ሆኖ ተነግሯል::

3. እናም አንድ ኢትዮጵያ ! ዛሬ ጸረ ኢትዮጵያዉያን የኢትዮጵያዊነትን መሰረታዊ እዉነታዎች በሙሉ ክደዉ እና አስክደዉ የጮህታቸዉ ከፍታ አድማስ ጥጉን ተቆጣጥሯል:: “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የሚለዉ አስተሳሰብ ደግሞ ወደ ስርቻ ተገፍቷል::ሌላዉ ቀርቶ የአንድነት ሀሳብ እናቀነቅናለን የሚሉት ወገኖች እራሱ ይሄን ሀሳብ እና እዉነት ሽሽት ላይ ናቸዉ::ከታጠቡ እስከ አንገት ነዉ::ከታረቁ ከአንጀት እንዲሉ ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ጋር ነን የምትሉ ሀይሎች “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የሚለዉን የአስተሳሰብ መሰረት አትልቀቁ::ከዚህ አድማስ ላይ ወርዳችሁ ኢትዮጵያዊነትን በድፍረት ማራመድ ከቶም እንደማትችሉ እወቁት::

ጸረ ኢትዮጵያዉያንን መጀመሪያ በአስተሳሰብ ማሸነፍ ካልተቻለ ጸረ-ኢትዮጵያዉያንን በተግባር ማሸነፍ አይቻልም:: የጸረ ኢትዮጵያዉያን የአስተሳሰብ የበላይነት የሚከሽፍበት ዘመን ሲመጣ ያኔ የጸረ ኢትዮጵያዉያን ግብዓተ መሬት እዉን ይሆናል::ጸረ ኢትዮጵያዉያንን በአስተሳሰብ ማሸነፍ ሳይቻል ኢትዮጵያን ማዳን አይቻልም::

4. ጸረ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሰብኩት “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የሚለዉ አስተሳሰብ በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ያሉ የቋንቋ እና ሌሎች ልዩነቶችን የማቻቻያ ስልት የለዉም ይላሉ:: ይሄ ግን ያዉ የተለመደ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳቸዉ ነዉ:: በሀገሪቱ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ብሄራዊ ቋንቋዎች በማስፈን እንዲሁም ፌደራላዊ/አሃዳዊ/ወይም ምንም አይነት የመንግስት አወቃቀሮችን እዉን በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ በተሻለ የሚተዳደርበትን የተሻለ ስርዓት መገንባት “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የሚለዉን አስተሳሰብ ማሳለጫ ነዉ:: የህዝቡን አንድነት: የሀገሪቱን ህልዉና እና ህብረት መጠበቅ ብሎም የተሻለች የበለጸገች ሀገር መፍጠር የሚቻልበትን ማንኛዉንም ዘመናዊ አስተሳሰብ መከተል የሚያስችል ሰፊ መሰረት አለዉ::ግን ሁሉም ማጠንጠንጠኛዉ መሆን ያለበት “አንድ ኢትዮጵያ ! አንድ ሀገር ! አንድ ህዝብ !” የሚለዉ የጋራ መዳረሻ ሀገራዊ የአብሮነት ራዕይ ነዉ::

===================================
ማስታወሻ:-
የኢትዮጵያ ነገስታት “አንድ ሀይማኖት : አንድ ሀገር” የሚል ሀሳብ ያራምዱ ነበር ስለሚለዉ ሀሰተኛ ክስ
===================================

አንድ ኢትዮጵያ አንድ ሀገር አንድ ህዝብ የሚለዉን መርህ አንዳንድ ጸረ ኢትዮጵያዉያን ሆን ብለዉ ከሀይማኖት ጋር እያሳከሩ ኢትዮጵያዊነት ብሄረተኝነት እንዳያብብ ስለሚያደናብሩ አንድ ኢትዮጵያ አንድ ህዝብ አንድ ሀገር የሚለዉ ጽንሰ ሀሳብ ከሀይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለዉ ማብራራት ይገባል:: ጸረ ኢትዮጵያዉያን እና ሀሰተኞች ቆርጠዉ በመቀጠል ኢትዮጵያዊነት ላይ ያላቸዉን የጥላቻ መርዝ ለመትፋት ሲሉ ነገስታቱ “አንድ ሀይማኖት: አንድ ሀገር” የሚል ሀሳብ ያራምዱ ነበር በማለት ይከሳሉ:: ሳያፍሩ እና ሳይሸማቀቁ “አንድ ሀገር : አንድ ሀይማኖት” የሚል መፈክር የቀደሙ ነገስታታ ያራምዱ ነበር በማለት አይናቸዉን በጨዉ ታጥበዉ ይከሳሉ::አንዳንድ ሰዎች በራሳቸዉ ፈቃድ ተነስተዉ የሚናገሩትን አስተሳሰብ በኢትዮጵያዉያን ነገስታት ላይ በመለጠፍ የዚህን ዘመን ትዉልድ በጥላቻ ጭቃ ዉስጥ ይረግጥ ዘንድ ወያኔ እና ሌሎችም ጸረ ኢትዮጵያዉያን ብዙ ሀሰተኛ ወሬዎችን አናፍሰዋል:: እያናፈሱም ነዉ::

ሆኖም በአጼ ሚኒልክም ሆነ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ሀይማኖት የግል ሀገር የጋራ የሚል መፈክር እንደነበረ ማስታወስ ተገቢ ነዉ::ኢትዮጵያዉያን ነገስታት በአለም ላይ የነጻ ፈቃድ አስተሳሰብ አራማጅ ስለሆኑ ነዉ እስልምናን ከመጥፋት ያዳኑት:: እስልምናን ማዳን ብቻ ሳይሆን እስልምና በኢትዮጵያ ህዝቡ ፈቃድ ተቀባይነት ካገኘ እንዲስፋፋ በፈቃዳቸዉ ክርስቲያኖቹ ኢትዮጵያዉያን ነገስታቶች አዋጅ አስነግረዉ ሙስሊሞቹን አትንኳቸዉ ብለዉ የነብዩ መሃመድን ተከታዮች ሁሉ አክብረዉ ሀሳባቸዉን በነጻ እንዲያራምዱ ፈቅደዉ ነበር:: ዛሬ ምናምንቴዉ ትዉልድ አባቶቻችን ላይ ጣቱን ለመቀሰር እና በባለጌ መንፈሱ ለመሳደብ ምንም የሞራል ብቃት የለዉም::ወያኔዎች እና ሌሎችም ጸረ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ የሚያናፍሱት ወሬ ሀሰት መሆኑን እያወቁ ግን በሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳቸዉን ቀጥለዋል::

ክድህደት እና ሀሰት መገለጫዉ የሆነዉ የአቢዮቱ ዘመን እና ይሄኛዉ ትዉልድ ግን ሁል ጊዜ የቀደሙ አባቶቻችንን እዉነተኛ ማንነት መካድ ባህሪዉ ነዉ::እፉኝቱ ትዉልድ የቀደመዉን ዘመን በሙሉ በማጥፋት እና በእግሩ በመረጋገጥ ዘመናዊ የሆነ ይመስለዋል::ስለዚህ ይሄ ትዉልድ ስለአባቶቹ የቀደሙ ነገስታት በተገቢዉ ደረጃ ማወቅ አለበት:: የነበሩን አባቶች ማንንም ተነስተዉ በግድ ይሄ እምነት ይኑርህ አላሉም::የዚያን ዘመን በሚመጥን ደረጃ ብቻ ሳይሆን ከዚያኛዉ ዘመንም በዘለለ ደረጃ ነጻ ሀገር የመሰረቱ: የመሩ ብሎም ነጻ አስተሳሰብ ያራምዱ የነበሩ ነገስታት አባቶች ነበሩን:: እፉኙቱ ትዉልድ ይሄን ቢክድ ወይም ባይክድ ለዉጥ የለዉም::

የቅርቡን እንኳን ብናስታዉስ ፕሮቴስታንት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ አጼ ሀይለስላሴ የፕሮቴስታንት ሰባኪዎችን አትንኩ በማለት የስብከት አካባቢያቸዉንም ለህዝቡ አሳዉቀዉ በክብር በኢትዮጵያ ስብከታቸዉን ሲያከናዉኑ ኖረዋል::ይሄ ትዉልድ ግን ዉለታ መረጋገጥ መሰልጠን ስለሚመስለዉ የቀደመዉን ስራ ሁሉ ካላንቋሸሸ ከቶም አዲስ ሀሳብ የገለጸ አይመስለዉም:: ስለዚህ የዚህ ሁሉ አስተሳሰብ ሰለባ የሆነዉን ትዉልድ የአባቶቹን ታሪክ በማስተማር ማዳን ይገባል::

“አንድ ሀይማኖት አንድ ሀገር” የሚል አስተሳሰብን አባቶቻችን ነገስታቶች ፈጽመዉ አራምደዉ አያዉቁም::ይሄ የሀሰት ክስ በአባቶቻችን ላይ ከሚነዛዉ የፈጥራ ክሶቹ አንዱ መሆኑን ይሄ ትዉልድ ማወቅ አለበት::ሀይማኖት የሰማይ መንግስትን የሚያወርስ ሚስጢር ሲሆን ሀገር ደግሞ የምድር መንግስት ጉዳይ መሆኑን የቀደሙ ኢትዮጵያዉያን ነገስታት አባቶች ጠንቅቀዉ የሚያዉቁ በመንፈሳዊነታቸዉም የሰለጠኑ ሀይላት ነበሩ::ስለዚህ የምድሩን እና የሰማዩን መንግስት የሚቀላቅሉ አልነበሩም::ሁሉንም በየመልኩ እና በየፈርጁ መያዝ የሚችሉ ሀያላኖች ነበሩ እንጅ::

“መሠረተ-ልማቶች” “መሠረተ-ጥፋቶች” ሊሆኑ ስለመቻላቸው

$
0
0

ታደሰ ብሩ

በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትናትና ንግግር ውስጥ “ … ይህ የባርነት አዋጅና የአዋጁ ባለቤት ህወሓት/ኢህአዴግ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ መንገዶች “መሠረተ-ልማቶች” ሳይሆኑ መሠረተ-ጥፋቶች ናቸው፤ አውራ ጎዳናዎች አስጠቂዎቻችን ናቸው” የምትል ዓረፍተ ነገር አገር አለች።
“የተከበሩ” ኮካዎች “እንዴት አንድ የኢኮሚክስ ባለሙያ መሠረተ ልማቶችን መሠረተ ጥፋቶች ናቸው” ይላል ብለው እንደሚንጨረጨሩ እገምታለሁ።
“መሠረተ-ልማቶች” “መሠረተ-ጥፋቶች” ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያዊያን ያስተዋወቀው (እኔ እስከማውቀው ድረስ) ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ነው። የነጋድራስ ገብረሕይወትን ያህል የሕዝብ አስተዳደርና የኢኮኖሚ ግኑኝነትን የተረዳ ምሁር እንኳንስ ያኔ ዛሬም መኖሩ አጠራጣሪ ነው። ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት በ1916 ዓም በታተመው “መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር” በተሰኘው መጽሀፉ ውስጥ “መሠረተ-ልማቶች” “መሠረተ-ጥፋቶች” ሊሆኑ እንደሚችሉ ውብ በሆነ አገላለጽ ተንትኗል።
ነጋድራስ ገብረሕይወት በመጀመሪያ የአጴ ሚኒሊክ በኋላም የአጴ ኃይለሥላሴ ባለሟል ሆኖ ለፈጣን ልማት የታገለ ቢሆንም እንኳን ለሕዝቡ ደህንነት የሚጨነቅ መንግሥት በሌለበት አገር ውስጥ ዕውቀት አይሰፋፋም፤ ዕውቀት በሌለበት ደግሞ መሠረተ ልማት ቢስፋፋ ጥፋትን እንጂ ልማት አያመጣም በማለት በጣም ጠንካራ ቃላትን ተጠቅሞ ይተቻል።

Tadesse Biru
በቅድሚያ የመንግሥት ሥራ ምን መሆን እንዳለበት የገለፀበትን ለ 93 ዓመታት ሰሚ ያጣ አንቀጹን ላስቀድም
“በእያንዳንዱ መንግሥት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል። ስለሆነ መንግሥት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይዶለም። አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግሥት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው። መንግሥት ሕዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ካላሰበ መንግሥት በዙፋኑ ሊቆም አይችልም። ላንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግሥት የሚገባ ሥራው አይደለም።” ገጽ 14
ቀጥሎ ስለ መሠረተ ልማቶች ወደሰጠው ትንተና ልለፍ።
ነጋድራስ ይህን መጽሀፍ በፃፈበት ወቅት (ከሞተ በኋላ ነው የታተመው) የጅቡቲ- አዲስ አበባ የምድር ባቡር ግምባታ እና የአቢሲኒያ ባንክ መቋቋም የዛሬውን ህዳሴ ግድብና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ያህል በሥርዓቱ ባለስልጣኖች የሚወደሱ እንደነበሩ መገመት ይቻላል። ነጋድራስ ግን እነዚህ ፕሮጀክቶት ሳይቀር በሚከተለው መንገድ በድፍረት ተችቷቸዋል።
“ዕውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሠራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ፤ አይጠቅመውም። ጥቅሙ ከርሱ ጋር ለሚገበያዩ ዐዋቂዎች ሕዝቦች ነው” ገጽ 75
“የሚበላውንና የሚለብሰውን ያጣ ድኻ የተወለደበትን አገር የሚወድበትን ምክንያት ያጣልና ያገሩ መንግሥት ቢበረታ ለሕዝቡ ማሠልጠኛ የሚሆነውን ነገር ሁሉ የምድር ባቡር በፍጥነት ሲያመላልስ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ርስ በርሱ ሲለዋወጥና ባንኩም በሰበሰበው ገንዘብ ሲረዳ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሕዝቡን ለማሠልጠን ቢነሳ ማለፊያ አጋዦች ይሆኑት ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ ሐሳብ ከሌለው ግን የምድር ባቡርና ባንኩ ወዳገራችን አመጣጣቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ መቃብር ለመማስ እንደሆነ ጥርጥር የለውም።” ገጽ 127 -128
=====
NB: የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ለነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ የክብር ዶክሬት ሰጥቷል። እኔ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ከሰጣቸው የክብር ዶክሬቶች ተገቢ የምለው ብቸኛ የክብር ዶክሬትም ይህ ነው።

ወደ አማራ ክልል እንዲንቀሳቀስ የታዘዘው ጦር ማብራሪያ ጠየቀ።

$
0
0

ሚኒልክ ሳልሳዊ

የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ደህንነት ምንጮች እንደገለጹት ከእዙ የተለያዩ ቡድኖች ተዋቅረው የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ለመተግበር ወደ ኣማራ ክልል እንዲንቀሳቀሱ የታዘዙ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቃቸውን ጠቁመዋል። የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁ ከሕዝቡና ከሕገመንግስቱ ኣንጻር ያለውን ሃገራዊ እደምታ በተመለከተ እንዲሁም የግጭት ኣፈታትን በተመለከተ ከሕዝብ ጋር መወያየትን ያጣመረ ስራ ስለመሰራቱ ማብራሪያ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸው ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ በተላከ መመሪያ መሰረት በጎንደር በመተማ በባህርዳር በደብረማርቆስና በመተከል ያሉትን የወያኔ ኣግዓዚ ወታደሮች እንዲረዱ የታዘዙት የምስራቅ እዝ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቃቸውን ተከትሎ በዚህ ሳምንት ከመከላከያ ሚኒስቴር ኣንድ ቡድን ወደ ምስራቅ እዝ ይዘልቃል ተብሎ ይጠባቃል ሲሉ ወታደራዊ ደህንነቶች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።
በምስራቅ እዝ ያሉ ወታደሮችን ወደ ኣማራ ክልል ወስዶ በምትካቸው በምስራቅ በኩል ከሶማሊያ የሚመለሰውን ጦር ለማስፈር ያቀደው ወያኔ በወታደሮች እምቢተኝነት ጉዳዩ የዘገየበት ሲሆን ከሶማሊያ የተመለሱ ወታደሮችን በኣማራና ኦሮሚያ ክልል ለማስፈር ያሰበው እቅድን ያጠፈው የሰላም ኣስከባሪ ሃይሎች የሚላቸውን እና ስለ ወቅታዊ የትዮጵያ ጉዳይ በቂ መረጃ ያላቸውን ወታደሮች ሌላ ጥያቄ ስለሚያነሱ በሂደት ኣስፈላጊውን ለማከናውን ትልም የነደፈ ሲሆን ኣብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ከሶማሊያ እየተመለሱ በኣማራ ክልል ያለውን የኣግዓዚን ገዳይ ጦር መቀላቅላቸውም ምንጮቹ ገልጸዋል።

14695345_1794162264188302_509558195580423973_n

ህወሃት የሚመራዉ ወታደራዊ ጽንፍ ቡድን የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተንተርሶ በዉጭ ሐገራት በስደት የሚኖሩ ስደተኞች ላይ የሚመክር የመጀመሪያ ስብሰባዉን በደቡብ አፍሪካ ጠራ።

$
0
0

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሚገኘዉ የህወሃታዊያን ኢንባሲ በፍሪ ስቴት እና አካባቢዉ የሚኖሩ ደጋፊዎቹን በ 22/10/2016 ቅዳሜ እለት ስብሰባ ጠርቷል። የዚህ ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር እንቅፋት የሆኑ ከአርበኞች ግንቦት 7 እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር ትስስር ያላቸዉ ግለሰቦችን በተመለከተ ለመምከር መሆኑን ከዉስጥ ያገኘነዉ መረጃ ያመላከተ ሲሆን ስብሰባዉን በማቀናጀትና ድጋፍ በመስጠት የህወሃት ተወካዮች እና አቶ ታመነ ወንዳሮ የተባሉ ( 0027743822700 ) የፍሪ ስቴት አካባቢ የህወሃት አባልና ተጠሪ በግንባር ቀደምትነት ይገኙበታል።
Zehabesha-News.jpg

የስብሰባዉ ዋነኛ አላማ የሀወሃት ወታደራዊ ስርአት ያወጣዉን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በመደገፍ በደቡብ አፍሪካ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግና ሐገር በማበጣበት ከነጻነት ሐይሎች ጋር የሚያብሩ ግለሰቦችን የደቡብ አፍሪካ መንግስት አሳልፎ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ሲሆን መረጃዉ የደረሳቸው የነጻነት ታጋዮች ይህንን እኩይ የወያኔ ተግባር በማኮላሸት በኩል የአስቸኳይ ግዜ እርምጃ እንዲወስዱ መልእክት አስተላልፈዋል ”
በተጨማሪ መረጃ ወያኔ ህወሃት በኡጋንዳ በኬንያ በታንዛኒያ በማፑቶና እንዲሁም በአዉሮፓና በአሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ተመሳሳይ ስብሰባዎችን ለማድረግ እንቅስቃሴ የጀመረ በመሆኑ በመላዉ አለም የምትኖሩ ወገኖች ይህንን ወንጀለኛና ገዳይ የኢትጵያና የኢትጵያዊያን ነቀርሳ ከስር መንግላችሁ እንድትጥሉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን !
አንድነት ሐይል ነዉ !
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የጣሊያን ጀነራል የማረኩ ብርጋዴር ጀነራል ለማ ገ/ማርያም አረፉ

$
0
0

(ሙሉጌታ ኃይሌ)
ብርጋዴር ጀነራል ለማ ገ/ማርያም ይባላሉ፡፡ የማይጨው ዘማች ነበሩ፡፡ በተወለዱ በ99 አመታቸው መስከረም 23 2009 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ከማይጨው ዘመቻ ተርፈው እስካሁን በሕይወት ይኖሩ ከነበሩት የመጨረሻው እሳቸው ነበሩ፡፡
ከነፃነት በፊት ሜጀር የሚለው የወታደር ማዕርግ ያገኙ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ከነፃነት በኋላም የመጀመሪያውየአባዲና ፖሊስ ምሩቅ ሆነው የፖሊስ ሠራዊትን ወደ ዘመናዊነት ከአሸጋገሩትአንዱና ዋናው ነበሩ፡፡
በዘመናቸው ከሚታወቁበት ታሪካቸው አንዱ፣በ1934 ዓም ጎንደር ላይ የፋሽስትን የጦር መኮንኖች ለመማረክ በተደረገው የቤት ለቤት አሰሳ ላይ በአደረጉት አስተዋፆ ነው፡፡
ከነበሩበት አሳሽ ቡድን ፊት ቀደም ብለው ከሩቅ የነጭ ባንዲራ ወደሚውለበለብበት ባንኮ ዲሮማ ጠጋ ብለው በሩን ከፍተው ቢገቡ፣የጣሊያን ከፍተኛ መኮንኖች መሠሪያቸውን መሬት ላይ አስቀምጠው ጠረጴዛ ከበው ካርታ ሲጫወቱ ያያሉ፡፡ ይሄን ሁሉ መኮንን በአንድጊዜ መማረክ ስለማይችሉ እርዳታ ለመጠየቅ በሌላ በር ሊወጡ ሲሉ፤ በአንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ የሸዋ ገዢ የነበረውን ጀነራል ናዚን፣ቤተወደድ አስፋሐ ወ/ሚካኤል(ኤርትራዊው አስተርጎሚ) እና አቶ አሊ (የጀነራል ናዚ ልብስ አልባሽ)በአንድ ላይ አዝነው እንደተቀመጡ ይመለከታሉ፡፡ እነዚህን መማረክ እችላለሁ ብለው “እጅ ወደ ላይ”ሲሉ፣ቢትወደድ አስፋሐ “እንደ ጀነራል ናዚ አይነት ከፍተኛ መኮንን በአንተ ሳይሆን በእንግሊዝ ከፍተኛ መኮንን ነው መማረክ ያለበት”ብለውሲያንገራግሩ ወዲያው የእንግሊዝጦር ደርሶ ሁሉም አንድ ባንድ እጃቸውን ሊሰጡችለዋል፡፡
የእንግሊዝ ጦር ጄነራል ናዚን ማረከንብለው እንዳይኩራሩ በጎንደር ከተማ ለነበሩት ለልዑል አልጋወራሽ አሰፋወሰን ኃ/ሥላሴ ምርኩኞቹ በሙሉእንዲተላለፉ አድርገዋል፡፡
ይህም ስራቸው ልዑል አልጋወራሽ ከነፃነት በኃላ የሙሉ ጄነራልነት ማዕርግ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥምይሄ ሹመት ለመጀመሪያጊዜ መሰጠቱ ነበር፡፡
ለዚህ ታሪክ እውነታ ቢትወደድ አስፋሐ ወ/ሚካኤልለጀነራል ለማ በሰጡት የምስክርነት ደብዳቤ ላይ ተረጋግጦል፡፡

የጄነራል ለማ ገ/ማርያም አጭር የሕይወት ታሪክ
ጄነራል ለማ ከአባታቸው ከጎጃሙ ተወላጅ ከአለቃ ገብረ ማርያም አለምነህና ከእናታቸው ከቡልጋዋ ተወላጅ ከወ/ሮ ፋንታዬ ዘለሌ በ1910 ዓም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሥር በነበረችው የኬኒያ ሞያሌ ከተማ ተወለዱ፡፡ በኪኒያ የተወለዱበት ምክንያት አባታቸው በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መሐከል የነበረውን የወሰን ክልል አስከባሪ ስለነበሩ ነው፡፡
ጄነራል ለማ እድሜያቸው ለትምሕርት እንደደረሰ በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ገብተው በጊዜው ይሰጥ የነበረውን ትምሕርት አጠናቀዋል፡፡ በ1926 ዓ.ም. በውትድርና ተቀጥረው በምሕንድስናትምሕርትለሁለት ዓመት ሰልጥነው ተመርቀዋል፡፡ በ1928 ዓም የጣሊያን ጦር ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ ከመጀመሪያዎች እጩ መኮንኖች ጋር በመሆን በክብር ዘበኛ ጦር ውስጥ ማይጨው ዘምተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ተሸንፎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ፣ በመርዝ የተጎዳው ሰውነታቸው እስኪአገግም ድረስ በዘመዶቻቸው ቤት ውስጥ ተሸሽገው ተቀመጡ፡፡
የካቲት 12/1929 ዓም ግራዚያኒን ለመግደል በተደረገው ሙከራ ጣሊያን ለበለጠ በቀል የቤት ለቤት አሰሳ በሚያደርግበት ጊዜ ጄነራልበለሊት አምልጠው ወደ ጎጃም ሄዱ፡፡
ጎጃም ሲደርሱ ከአርበኛው ካሳ ብሩ እና ከራስ መስፍን ስለሺ ጋር ተቀላቅለው የአርበኝነት ሥራቸውመስራት ጀመሩ፡፡
ከእንግሊዝ ሀገር ከጃንሆይ ዘንድ የተላኩትን ፀሐፊ ትእዛዝ ሎሬንዞ መብራቱን አግኝተው አብረው ወደ ቤጌምድርና ጎጃም በመሄድ የመረጃ ስራ አሰባሰበው ተመለሱ፡፡
በመቀጠልም ሱዳን ከነበረው ከእንግሊዝ ጦር መሪ ሜጀር ቼዝማን በርካታ መሳሪያ በመረከብ እራሳቸውንና የጎጃምን አርበኞችን በተሻለ መሳሪያ አስታጠቁ፡፡
መስከረም 18/1932 ዓም በእንግሊዛዊው በጀነራል ሳንፎርድ በተቋቋመው ሚሽን 101 በተባለው የመረጃ ሰብሳቢ ኮሚቴ ውስጥ ተመድበው በሚስጥር ስራ ውስጥ ገቡ፡፡ በኮሮኔል ዊንጌት በሚመራው የጌዲዮን ጦር ውስጥ ሜጀር ተብለው የ5ሺ (እጁን የሰጠ የባንዳ ምርኮኛ) ሠራዊት መሪ ሆነው እስከ ቡሬ ከተማ ድረስ የነበረውን የጣላት ምሽጎችን አስለቀቁ፡፡
“ባንዶች ሀገራችሁን እንደጎዳቹሁ ዛሬ ደግሞ የምትክሶት ጊዜ ነው” እያሉ የሠራዊታቸውን ሞራል ይገነቡ ጀመረ፡፡የዚህ ምስክርነት ማስረጃ የተገኛው ክቡር አቶ ጌታሁን ተሰማ በፃፉት ማስታዋሻ ላይ ነው፡፡
ብ/ጄነራል ለማ የኢትዮጵያ ነፃነት ከተመለሰ በኋላ በየቦታው ደፍርሶ የነበረውን ሰላም ለማስከበር በወሎ፣ትግራይና ሐረር ተንቀሳቅሰዋል፡፡
gen-lema-1
በተለያዩ ጊዜያት የሚከተሉትን የሀላፊነት ግዴታዎችንአከናውነዋል፡፡
1. ከ1941-42 ዓ.ም. የወሎ ፖሊስ ዋና አዛዥ
2. ከ1942-49 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የወንጀል ምርመራ ሐላፊ
3. ከ1949-50 የመላው ወህኒ ቤቶች(እስርቤት)አዛዥ
4. ከ1952-53 የኤርትራ ፀጥታ አዛዥ
5. ለጥቂት ጊዜ የመተሐራናወንጂ ስኳር ሀላፊ
6. ከ1953-1956 የሕዝብ ደሕንነት ዋና ሐላፊ(የኮሮኔል ወርቅነህ ገበየሁ የነበረ ቦታ)

General Lemma

General Lemma

የ53ቱን የመንግስት ግልበጣ መሪ የነበሩትን ጀነራል መንግስቱ ነዋይን መርምረዋል(የዚህ ሙሉ ታሪክ በአቶ ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖ በተፃፈው ገድለ መፈንቅለ መንግስት ማግኘት ይቻላል)ከዘጠኝ ዓመት በፊት በ1942 ዓም ከጀነራል መንግስቱ ነዋይ ጋር ሆነው የቤተወደድ ነጋሽ በዛብህን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራን በጋራ አክሸፋዋል፡፡(የዚህ ሙሉ ታሪክ በአቶ በሪሁን ከበደ የአፄ ኃ/ሥላሴ ታሪክበሚለው መፅሐፍ ላይ ይገኛል) ጀነራል ለማ ከመንግስቱ ነዋይ በኋላ አራት የተለያዩ ያልተነገረላቸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎችን አክሸፋዋል፡፡ “ኩዴታ ደጋግሞ ያከሸፈ መልሶ ኩዴታ ከማድረግአይመለስም” በሚል ብሒል ጀነራል ለማ ወደ ጋምቤላ አገር አስተዳዳሪነት እንዲዛወሩ ተደርጓል፡፡
7. ከ1956-1962 ዓ.ም. የጋምቤላ አውራጃ ገዢ ሆነው ለረዥም አመታት ሠርተዋል፡፡
በአራጃው ዘመናዊ ትምህርት ቤት እና የጤና ክሊኒክ እንዲቋቋሙ አድርገዋል፡፡
ለዚህ መልካም አስተዳደራቸው የአለፋው ዓመት የጋምቤላ ፕሬዜዳንት ክቡር አቶ ኦልኤሮ ኦፒዮ በጋምቤላ በተደረገው የብሔር ብሔረሰቦች ክበረ በዓል ላይ በክብር እንዲገኙ ጥሪ አቅርበውላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን
በሐኪማቸው ትእዛዝ መሠረት በእዚህ እድሜ በአውሮፕላን መብረር አይችሉም ተብለው ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡
ታዋቂው የጋምቤላ የሥዕል ባለሞያ አቶ ሐሰን ኦፒዮ ለዛሬው ማንነቱ የጀነራል አሻራ እንዳለበት በአንድ ወቅት ሲናገር “ጀነራል ኒውሲክና ታይምስ የተባሉትን የእንግሊዘኛ መፅሔቶችን በረንዳቸው ላይ ቁጭ ብለው ሲያነቡ፣አንድ ቀን እንደሳቸው እሁናለሁ ብዬ እምኝ ነበር” በማለት የማይረሳውን የልጅነት ትውስታውን ገልፆአል፡፡
የጀነራል ዝና ከጋምቤላ አንስቶ አዲስ አበባ ደርሶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያስረዳል፡፡ እሳቸውየጋምቤላ አውራጃ ገዥ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ውስጥ ወጣቶች የጋምቤላን ተወላጅ ሲመለከቱ “ለማ!” ብለው ይጣሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡
አንዳንዶች ቃሉ ሲደጋገም ስድብ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን በጋምቤላ (በአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ) “ለማ” ለሚለው ፍቺካለጀነራል ስም በስተቀር ሌላ ፍቺ ያለው ቃልማግኘት አይቻልም፡፡
ጀነራል ለማ በ1960 ለመጀመሪያ ጊዜ የሱዳን ስደተኞች ወደ
ኢትዮጵያ በሚገቡበት ጊዜ ላደረጉት ከፍተኛ የሰብአዊ ርሕራሄ ሥራ የዓለም ስደተኞች ድርጅት UNCHR የልዩ እውቅና ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡ ዛሬከነዚህ ሰደተኞች መሐከል አብዛኞቹ ዛሬ ኢትዮጵያዊ ለመሆን በቅተዋል፡፡የዛሬ 50 ዓመት የደቡብ ሱዳን የነፃነት ታጋዮች የመረጃ አሰባሰብና የሬዲዮን ግንኙነት የተማሩት በጀነራል መኖሪያ ቤት ውስጥ እንደ ነበር የነፃነቱ መሪ የነበሩት ጀነራል ጋራንግ ስለ ኢትዮጵያ ውለታ ሲናገሩ ጠቅሰውታል፡፡
8. ከ1962-64 ዓ.ም. በሀገር ግዛት ውስጥ የወሰን አስተዳደር ም/ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል
9. 1964-68 ዓ.ም. የአሰብ አስተዳደር ዋና ሀላፊ ሆነዋል፡፡
ጀነራል ለማ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር መሪዎች የተለያዩ ኒሻኖችና ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል፡፡ ከነዚህ በጥቂቱ
1. የዳግማዊ ሚኒሊክ ሜዳይ
2. የክብር ኮኮብ ኒሻን
3. የአጥቢያ ኮኮብ ኒሻን
4. የረዥም ጊዜ አገልግሎት ኒሻን
5. የሰብአዊ አገልግሎት ኒሻን
6. ከእንግሊዝ መንግስት የተሰጠ ሁለት በአንገት ላይ የሚጠለቅ ኒሻኖች
7. ከይጎዝላቪያ ፕሬዚዳንት ማርሻል ቲቶ የተሰጠ ኒሻን
8. ከሱዳን መሪ ከጀነራል አቡድ የተሰጠ የሀገሪቱ ከፍተኛ ኒሻን
ጀነራል ለማ የዛሬ ሦስት ዓመትለቫቲካን መሪ ለፖፕ ፍራንሲስ የመጨረሻው ጸሎቴ በሚል ርእስ ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወቃል፡፡ የዚህ ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዞል፡፡
ጀነራል ለማ ሕይወታቸው ከማለፉ አንድ ሳምንት በፊት ጤናቸውና አእምሮቸው የተሟላ በሽታ የማያቃቸው እድለኛ አዛውንት ነበሩ፡፡ ዘወትር እሁድ ቤተክርስቲያን የማይቀሩ፤ ወርሐዊ የእድር መዋጮ ለመክፈል ወደ ፓሊስ ክበብ እና የጡረታ ገንዘባቸውን ለመቀበል በየወሩ የሚሄዱ ነበሩ፡፡(የጡረታ አበላቸው 1300.15 ሳንቲም ሲሆን በአሜሪካን ዶላር 54 ብቻ ነው፡፡ የዛሬ 45 ዓመት የጡረታ ገንዘባቸውን ማስቀመጥ ሲጀምሩ የአንድ ዱላር ምንዛሪ 2.15 ሳንቲም ነበር፤ ዛሬ 22 ወይንም 24 ብር ሆኖል፡፡) ለጀነራል መከፈል የነበረበት አበል በአሁኑ ምንዛሬ31,200 ብር መሆን ነበረበት፡፡ ጀነራል ስለ ሆኔታው ሲገለፁ “ያልታወጀ ጦርነት በሸማገሌዎች ላይ” ይላሉ፡፡
የዛሬ አራት ወር የጀርመን ሺፐርድ ውሻቸው ወልዳ ወንዶች ቡቻላዎችን በ900 ብር፣ ሴቶቹን ደግሞ በአንድ ሺ ብር ይሸጡ እንደ ነበር ታይተዋል፡፡ ምንአልባትም በ99 ዓመት ዕድሜ ገንዘብ የሚሠራየመጀመሪያው የዓማችን ሰው ሳይሁኑ አይቀርም፡፡
እኝህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ መቶ አመት ሊሞላቸው ሦስት ወር ብቻ ሲቀራቸው በድንገተኛ ሕመም መስከረም 23 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው መስከረም 25 ቀን በጳውሎስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን አስከሪናቸው በክብር አርፏል፡፡
እንዲህ አይነት ጀግና ሲያርፉያገለገሏት ሀገራቸው የጀግና አቀባበር ልታደርግላቸው በተገባ ነበር፤ ነገር ግን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያለፈው ታሪኳን እና ባለውለታዎቿን እረስታ እነሱም የዛሪቱን ኢትዮጵያ እረስተው በብቸኝነት ኖረው አንድባንድ ሁሉም በየተራ ለዘላለሙ
እየተለዩን ሄዱ፡፡
ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝነሸ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ

You can reach the writer at – mulugetahaile123@gmail.com


ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም -መወገድ ያለበት እንጂ ! ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

$
0
0

በገሀነም ውስጥ እጅግ የሚያቃጥለው ቦታ የተያዘላቸው የሞራል ቀውስ በሚታይበት ወቅት ለህዝብ ወገናዊነትን ለማያሳዩ ሰዎች ነው።“ Dante
tplf-ethiopian-leaders

መግቢያ

ሰሞኑን ወያኔ የሚያወናብደው ራሱን ለማደስ እንደተዘጋጀና ጊዜም እንደሚያስፈልገው ነው። በአገዛዙ ውስጥ የአስተደዳደር ብልሹነት አለ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ባህል ተስፋፍቷል፣ ሙስና ለቢሮክራሲው ማነቆ በመሆን ስራ አላሰራም በማለት የአገርን ዕድገት እየጎተተ እንደሆነ እየመላለሰ ይነግረናል። እነዚህንና ሌሎች የአስተዳደር ብልሹዎችን በየስብሰባውና በቴሌቪዢን „የውይይት መድረከ“ ላይ የሚያወሩልን የአገዛዙ የመሪ ቁንጮዎች በሽታዎቹ ከሰማይ እንደወረዱ እንጂ እነሱ ለአጋዛዛቸው እንዲያመቻቸው ሆን ብለው የፈጠሩትና ከተበላሸ ኢ-ሳይንሳዊና አገር አፍራሽ የአሰራር ዘዴ ጋር እንደተያያዘ አድርገው አይደለም የሚያቀርቡት። በሌላ አነጋገር፣ ለከፋፍለህ ግዛ እንዲያመች በፌዴራሊዝም መልክ ተዋቀረ የሚባለውና „የብሄረሰቦችን መብት የሚያስከብረው“፣ በመሰረቱ ግለሰብአዊ ነፃነትን በማፈን በክልል መልክ በተዋቀረው ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን አቀጭጮ የሚያስቀረው አስተዳደር ለሙስናና ለአስተስዳደር ብልሹ፣ እንዲያም ሲል ለአጠቃላይ ዕድገት ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ ወያኔ በፍጹም ሊያምን አይፈልግም። ከዚህም ባሻገር፣ ይህ ዐይነቱ የግለሰብ ነፃነትን አፋኝና ፈጠራ እንዳይኖር ያደረገው ስርዓት በየክልሉ ራሳቸውን ያደለቡ ዋር-ሎርዶችን እንደፈጠረና ለሁለ-ገብ ዕድገት እንቅፋት እንደሆነ ወያኔ በፍጹም የተገነዘበ አይደለም። በሁለተኛ ደረጃ በዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው ግፊት ወያኔ በ1993 ዓ.ም ተግባራዊ ያደረገው የተቅዋም መስተካከል ዕቅድ (Structural Adjustment Program)የሚባለው፣ አብዛኛውን ህዝብ በማደኽየት ጥቂቶችን የሚያደልበው የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በአገሪቱ ውስጥ የተዛባ ዕድገት ማምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱን የቆሻሻ መጣያ በማድረግ እንደ አንድ ህብረ-ብሄርና እንደ ህብረተሰብ እንዳትገነባ የሚያደርገው ፖሊሲ ዛሬ በአገራችን ምድር ውስጥ ለሚታየው አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ ቀውስ ተጠያቂ እንደሆነ ወያኔ በፍጹም ሊረዳ አይችልም። በሶስተኛ ደረጃ፣ የኢኮኖሚውን ቁልፍ ቁልፍ መስኮችን ለመቆጣጠርና ሀብት ለመዝረፍ እንዲያመች በአዲስ መልክ የተዋቀረው የመንግስት የመጨቆኛ መኪናና፣ በየጊዜው ፋሺሽታዊ መልክ እንዲይዝ እየተጠናከረ የሄደው የአገዛዝ መሳሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተዘረጋው የሚሊታሪ-ኢንደስትሪያል ውስብስብና(Complex) የፊናንስ ካፒታል ጋር በመቆላለፍ በአገራችን ምድር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ነፃነትን ማፈኑና፣ ለዕውነተኛ ዕድገትና ህብረተሰብአዊ ውህደትና ጥንካሬ ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ አገዛዙና ካድሬዎቹ በፍጹም የተገነዘቡት አይመስልም። ከዚህ ስንነሳ የብልሹ አስተዳደርና ሙስና ከላይ የተጠቀሱት፣ የክልል አስተዳደር፣ የኢኮኖሚው ፖሊሲና የመንግስቱ መኪና አወቃቀር ዕይንታዎች(Manisfestations) ወይም ውጤቶች እንጂ በራሳቸው እንደ ዋና ምክንያት ሊታዩ የሚችሉ አይደሉም።

ስለሆነም በአገራችን ምድር አማራ በመባል በሚታወቀውና በኦሮምያ ክልል የሚካሄዱትና በየቦታው እየተስፋፉ የመጡት ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች በመሰረቱ የነፃነት ጥያቄዎች ሲሆኑ፣ ወደ ውስጥ ገባ ብለን ስንመለከት ደግሞ ላይ በተዘረዘሩት መልክ በተዋቀረው ዘራፊና(Predatory State) ፋሺሽታዊ አገዛዝ ስር አንገዛም፣ ይህ ዐይነቱ አወቃቀር የአንድነታችን፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የማህበረሰብ ዕድገታችን፣ የህልውናችን፣ የብሄራዊ ነፃነታችን ፀር በመሆን ታሪክ እንዳንሰራ የሚያግዱን ናቸው በማለት የተነሱ ህዝባዊ አመጾች ናቸው። ስለሆነም ይላል ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ወያኔና ካድሬዎች የውጭ ኃይሎች ተጠሪዎች በመሆን የውክልና ጦርነት በማካሄድ እንደ ማህበረሰብና እንደ አገር እንዳንኖር እያደረጉን ነው፤ የውጭ ኃይሎች ገብተው እንዲፈተፍቱ መንገዱን በማዘጋጀት ርስ በርሳችን እንድንጨራረስ ሊያደርጉን ነው በማለት ነው በአገዛዙ ላይ በአንድነት ከዳር እስከዳር የተነሱበት። ይህንን አገር አፍራሽ ሂደቱን ግን ወደ ተራ የአስተዳደር ብሉሽነት በመቀየርና ለማስተካከል ይችል በማስመሰል ህዝቡን በማወናበድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ስንነሳ ተሃድሶ የሚለውን ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ አባባል ጠጋ ብለን እንመልከት። በእርግጥ ወያኔ እንደሚለው ራሱን ማደስ ይችላል ወይ? ፅንሰ-ሃሳቡ በየጊዜው እየተደጋገመ በመሰማቱ አብዛኛው ህዝብ ተሃድሶ ማለት ምን ማለት እንደሆን እንዲረዳው ትንሽ ማተቱ የሚከፋ አይመስለኝም።

ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው ?
በመሰረቱ ተሃድሶ ማለት ቀድመው የነበሩ ነገሮችን በአዲስ መልክ ከአንድ ሁኔታ ጋር በማቀናጀት ለአንድ ህብረተሰብ ልዩ ዕምርታን መስጠት ማለት ነው። ተሃድሶ የሚባለው ፅንሰ-ሃሳብ ቃል በቃል ሲተረጎም ሬናሳንስ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣሊያን ምድር በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ተግባራዊ የሆነና፣ የግሪክን ፍልስፍና፣ የማቲማቲክስን፣ የሳይንስን፣ የአርክቴክቸርና ሌሎችንም ግኝቶች ወይም ፈጠራዎች መሰረት ያደረገ ሁለ-ገብ የሆነ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ነው። ጸንሳሺዎቹም በ14ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ ላይ ኮንስታንቲኖፕል የሚባለውና ዛሬ ኢስታንቡል በመባል የሚታወቀው ከተማና ዛሬ ቱርክ የሚባለው ግዛት ሲወረር ሽሽተው ወደ ጣሊያን የሄዱ ቄሶችና ፈላስፋዎች፣ ወይም ደግሞ ኒዎ-ፕላቶናውያን(Neo-Platonic) በመባል የሚታወቁ ምሁሮች የአዳበሩትና የአስፋፉት ሰፋ ያለ የጭንቅላት እንቅስቃሴና ተግባራዊም የሆነ ነው። ይህ አዲሱ መንፈስን በማደስ የተጀመረው ምሁራዊ እንቅስቃሴ እነ ዳንቴ ካዳበሩት እንደ የአምላኮች ኮሜዲ ከመሳሰሉት ሌትሬቸሮች ጋር በመዋሃድ ልዩ ዕምርታን በማግኘት በዚያን ጊዜ በጣሊያን ምድር የተዘረጋውን አስከፊ ስርዓትና ብልሹ የሆነ የህዝብ የአኗኗርን ስልት በመቀየር የህዝቡን ጭንቅላት በማደስ ኋላ-ቀር ከሆነው አስተሳሰቡ በመላቀቅና ራሱን በራሱ በማግኘት ዕውነተኛ ነፃነትን እንዲጎናጸፍ በማድረግ ሁለንታዊ ዕድገት እንዲመጣ በር የከፈተ ሰፋ ያለ ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴ ነው። የዚህ ውጤት እነ ጋሊሊ፣ እነ ዳቪንቺና ሚካኤል አንጀሎና፣ እንዲሁም በሺህ የሚቆጠሩ ሳይንቲስቶችና የኦፔራ ሰዎችና ሰአሊዎች ብቅ እንዲሉ ያደረገ ነው። በሌላ አነጋገር፣ ሬናሳንስ ወይም ተሃድሶ የሚባለው መንፈስን ከዕውነተኛ ዕውቀት ጋር በማገናኘትና በማደስ የሰው ልጅ ዕውነተኛ ነፃነቱን በመጎናጸፍ ራሱን በልዩ ልዩ መልክ እንዲገልጽና፣ አንድ ማህበረሰብ እንዲመሰርትና በሰላምና በስምምነት እንዲኖር ያደረገና የሚያደርግ ሳይንሳዊና ፍልስፋናዊ ሂደት ነው። የሬናስን አፍላቂዎችና በመቀጠልም ያዳበሩትና ልዩ ዕምርታን የሰጡት ምሁሮች በመሰረቱ ምንም ወንጀል ያልሰሩና፣ መንፈሳቸውን ከእግዚአብሄር ጋር በማቀራረብ በኮስሞስ በማስመሰል በምድር ላይ ዕውነተኛ ገነትን ሊመሰርቱ የቻሉና፣ ማቴሪያላዊ ዓለምን ከመንፈሳዊ ጋር በማዋሃድ የሰው ልጅ በአርቆ አሳቢነት እየተመራ ሚዛናዊና ጥበባዊ ኑሮን እንዲኖር ሁሉን ነገር ያዘጋጁና ተግባራዊ ያደረጉ ታላቅ ምሁራን ናቸው። በሌላ አነጋገር፣ እንደ ወያኔ ከፋፋይ፣ ጨፍጫፊ፣ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጣላት አንድ ህዝብ በዘለዓለማዊ ትርምስ ውስጥ እንዲኖር ያደረጉ አይደሉም።

በዘራፊነትና ባልተስተካከለ ዕድገትም የሚታሙ ሳይሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውነተኛና ሃርሞኒየስ የሆነ የአርክቴክቸር ስራን ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉና፣ ለጠቅላላው የምዕራብ አውሮፓ ስልጣኔ መሰረት የጣሉ ናቸው። ከዚህም በመነሳት ነው በኋላ ካፒታሊዝምና የኢንዱስትሪ አብዮት ተግባራዊ መሆን የቻሉትና፣ በምዕራብ አውሮፓ ምድር ውስጥ ህብረ-ብሄሮች እንዲመሰረቱና እንዲጠናከሩ የተደረገው። ይሁንና ግን የሬናሳንስ መልዕክት ካፒታሊዝምን ማስፋፋት ሳይሆን፣ የየግለሰቦችን ዕውነተኛ ነፃነት በማወጅ በልዩ ፈጠራ ዘዴ ሚዛናዊ ዕድገትን ማምጣት ነው። የካፒታሊዝም በአሸናፊነት መውጣትና የሬናሳንስ መሰረተ-ሃሳቦች ቀስ በቀስ መደምሰስ ወይም መቀልበስ ከኃይል አሰላለፍ ለውጥ ጋር የተያዘ ነው ማለት ይቻላል።

ወደ ወያኔው ተሃድሶ ስንመጣ ግን በመጀመሪያ ደረጃ በድርጅቱ ውስጥ የተጠቃለሉት ግለሰቦች ከጦር ሜዳ ጀምረው በደም የተጨማለቁና የስው ልጅ ህይወትም ቅንጣት የማይሰጣቸው ሰይጣናዊ ባህርይ የተዋሃዳቸው ናቸው ማለት ይችላል። በዓለም ታሪክ ውስጥ በሰው ልጅና በህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ውስጥ ያልታየን ድርጊት የፈጸሙና ድርጊታቸው በሙሉ ህብረተሰብን ማከረባበትና አገርንም ማወደም ነው። ታሪክን ማፈራረስና፣ አንዱ የህብረተሰብ ክፍል ከሌላው ጋር እንዳይገናኛና እንዳይግባባ ልዩ ልዩ ፊደሎችን በመቅረጽ ቅጥ ያጣ ኑሮ እንዲኖር ባህላዊ ያደረጉና ፀረ-ዕድገትን ያስፋፋ ናቸው። በሌላ ወገን ግን እነ ዳንቴ በአስራአራተኛው ክፍለ-ዘመን ያደረጉት በዚያን ጊዜ የኢጣሊያን ህዝብ በተለያየ ዲያሌክት ይነጋገር ስለነበርና መግባባትም ስላልነበር፣ አንድ ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል ሰዋስውና ቋንቋ በመፍጠር ለጣሊያን ዕድገት ዕምርታን የሰጡ ናቸው። ይህም ማለት የወያኔው አካሄድ የዚህ ተቃራኒና የአንድን ህዝብ መተሳሰር በማፍረስ በእንግሊዞች የቋንቋ ምሁራን፣ በመሰረቱ ተንኮለኞች በመታገዝ በአገራችን ምድር ተግባራዊ ያደረገ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። ውጤቱ እንደምናየው፣ በተበላሸ ሁኔታ ወይም የአኗኗር ስልት፣ በተዝረከረከ የከተማ አወቃቀር፣ በአንድ የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ብቻ በመመካት በተለያየ የምርት ውጤት ሊገለጽ የሚችል የስራ-ክፍፍል እንዳይኖር ያደረገና፣ ብቃትነት ያላቸው ኢንስቲቱሽኖች እንዳይመሰረቱ በማድረግ በየአካባቢው የሰውና የተፈጥሮን ሀብት በማንቀሳቀስ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ዕውነተኛ ህዝባዊ ሀብት(National Wealth) እንዳይፈጠር ያደረገ ነው። በዚህም መሰረት በአንድ አካባቢና በአገሪቱ ምድር ውስጥ ስርዓት ባለው መልክ በኢንዱስትሪ ተከላ ላይ የተመሰረተ፣ ከሌሎች መስኮች ጋር የተያያዘ የውስጥ ገበያ(Home Market) እንዳይዳብር ያደረገ ነው። በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ በሌለበት አገርና፣ የውስጥ ገበያም እንዳይዳብር ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቆላለፍ ሻጥር በሚሰራበት አገር ውስጥ አንድ ጠንካራ አገር ወይም ህብረ-ብሄር መመስረት በፍጹም አይቻልም። የወያኔም ተልዕኮ ይህ ሲሆን፣ ከበስተጀርባ ሆነው የሚበውዙት፣ የእንግሊዝ፣ የአሜሪካንና የምዕራብ ጀርመን የስለላ ድርጅቶችና፣ በተራድዖ ስም የሚንቀሳቀሱት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ናቸው። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ምን ዐይነት ተሃድሶ ማካሄድ ይቻላል ?

ጭፈጨፋና ተሃድሶ እዚያው በዚያው ወይስ ማጭበርበር !
እንድምንከታተለው ወያኔ በአንድ በኩል ራሴን ለማደስ ዝግጁ ነኝ፣ በዚህም ላይ ዕቅድ በማውጣት ላይ ነን ይላል። እዚያው በዚያው ደግሞ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ ምስኪኑን ህዝባችንን ይጨፈጭፋል። በየቦታው የአጋዚ ወታደሮችን በመላክ ፋሺሽታዊ ጭፍጨፋውን ተያይዞታል። በዚያው መጠንም ሌሎች እምቢ ያሉትን ሰላማዊ ዜጎችን በማፈናቀልና ሀብታቸውን በመቀማት የቁም ስቅላቸውን ያሳያቸዋል። በሌላ አነጋገር፣ የወያኔ አገዛዘ በየቦታው እየጋለ የመጣውን ህዝባዊ ብሶትና ቆራጥ የተሞላበት ትግል በውጭ የስለላ ድርጅቶች በመታገዝና በመመከር ጭፍጨፋውን በየቦታው እያካሄደ ነው። ይሁንና ቆራጡ የጎንደርም የሆነ የኦሮሞ ወንድማችንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ዕምቢተኛነታቸውን በማስተጋባት ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ እየተፋለሙት ይገኛሉ። በአንዳንድ አካባቢዎችም ድልን እየተጎናጸፉ ነው።

በዚህ ዐይነት መልክና ቁልፍ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንድ አንድ ኩባንያ በተደራጀ መልክ ከአንድ ብሄረሰብ በተውጣጡ፣ ሰውነታቸው በደም በታጠበ ግለሰቦች በተያዘበት አገርና፣ በግለሰብ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሌለበት አገርና፣ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዳይቻል አንድ አገዛዝ በውጭ ኃይሎች እየታገዘ መንግስታዊ መኪናዉን ፋሺሽታዊ በሆነ መልክ ባዋቀረበት አገር እንዴት አድርጎ ተሃድሶን ማምጣት ይቻላል? በፍጹም የማይታለምና የማይቻልም ነው። አንድ በኮሜዲ መልክ የቀረበ ጥንቆላ፣ አንዷ ታማ ጠንቋይ ቤት ትሄዳለች። ጠንቋይዋ የመንፈስ በሽታ የተናወጣትን ለማዳን ያልሞኮረችው ነገር የለም። በመጨረሻ የደረሰችበት ድምዳሜ ከአቅሟ በላይ እንደሆነና መፈወስም እንዳማይቻል ነው። የወያኔም የጭንቅላት በሽታ እንደዚህ ነው። አጥፍቼ ልጥፋ በሚለው እርኩስ አስተሳሰብ የተለከፈ ስለሆነ መፈወሻ የሚገኝለት አይደለም። መፈወሻውም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂያዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴና በሱ ላይ የተመሰረተ በማያዳግም መልክ የሚያወድመው ርብርቦሽ ነው። በሌላ ወገን የወያኔን ነፍስ ለመዝራት በልደቱ አያልነህ የሚመራው ኢዴአፓና አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ነን ባዮች የማያደርጉት ሽር ጉድ የለም። ልደቱና ሌሎች ግለሰቦችና አንዳንድ ድርጅትን እንወክላለን የሚሉት በአገራችን ምድር ውስጥ እንደዚያ ያለ ጭንቅላትን የሚዘገንንና እንቅልፍ የሚያሳጣ ድርጊት በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ባለበት ወቅት ወያኔ በጠራው „የመወያያ ስብሰባ“ ላይ መገኘታቸው የቱን ያህል የህዝባችን ሁኔታ እንደማይመለከታቸው ነው የሚያረጋግጠው። እነዚህ „ተቃዋሚ“ ነን የሚሉ ኃይሎች እንደዕውነቱ ከሆነ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በአገራችን ምድር ምን እንደተካሄደ የገባቸውና የተገነዘቡም አይመስልም። ለመረዳትም የሚፈልጉ አይደሉም። የዲሞክራሲንና የነፃነትን ጉዳይ ከተራ ምርጫና ፓርላሜንት ውስጥ ተቀምጦ ከመዘባነን ጋር ነው የሚያያዙት። በዚህም መሰረት ማንም ውክልና ሳይሰጣቸው አሜሪካና አውሮፓ እየመጡ የዓለምን ህዝብ (International Community)እንወክላለን ለሚሉት የሚያሰሙት እሮሮ በመሰረቱ የህዝባችንን የዕውነተኛ የነፃነት ትግል የሚያጨናግፍ ነው። አካሄዳቸው በአገራችን ምድር ውስጥ ዕውነተኛ ዕድገት እንዳይመጣ የሚያደርግ ነው። እነዚህ ተቃዋሚ ነን ባዮች የዓለም ፖለቲካ አወቃቀርና ብወዛ በፍጹም የገባቸው አይመስልም።

ያም ሆነ ይህ፣ ወያኔ ተሃድሶ እያለ የሚያናፍሰው ወሬና የሚያካሄደው የእነወያይ ስብሰባ ማዘናጊያና ራሱን ማጠናከሪያ ዘዴ ነው። አገዛዙ የሚታደስም የሚታከምም አይደለም። ህፃናትን ሳይቀር በስናይፐር የሚገድልና ሴትን ቤንዚን በማርከፍከፍ አሰቃይቶ የሚገድል አገዛዝ በፍጹም ሊታደስ አይችልም። ዕውነተኛ ተሃድሶ ሊመጣ የሚችለው ከዚህ አገዛዝ ባሻገር በሀቀኛ አገር ወዳዶችና በተገለጸላቸው ምሁራን አማካይነት ነው። ይህም ቢሆን ከህዝብ ትግል ጋር መዋሃድና የህዝቡን ኃይልነት የሚያበስር መሆን አለበት። ከዚህም ጋር ተያይዞ የመንግስቱ የመጨቆኛ መሳሪያ እንዳለ በመንኮታኮት ለዕድገት በሚያመች መልክ ከማንኛውም የውጭ የስለላ ድርጅት ነፃ በሆነ መልክ መደራጀት አለበት። ከህዝብ ጋር የሚሄድና የሚዛመድ እንጂ በህዝቡ ላይ ጠበንጃውን የሚቀስር አገዛዝ አይደለም ህዝባችንና አገራችን የሚመኙት። ከዚህም ባሻገር ዕውነተኛ ተሃድሶ በሁለ-ገብ የትምህርት ዘመቻ የሚታገዝ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ፖሊሲዉም በመንግስትና በህዝብ መሀከል በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ ሁለ-ገብ(Holistic Economic Policy) የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ተግባራዊ የሚሆንበት ነው። በሌላ አነጋገር፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ የሚመራበትን የኢኮኖሚ ፖሊሲና የዓለም አቀፍ ኢንስቲቱሽኖችን ምክር በመጣል ርስ በርሱ የተሳሰረ የውስጥ ገበያን ሊያስገነባ የሚያስችል የኢንዱስትሪ ተከላና የቴክኖሎጂ ምጥቀትን የሚያመጣ ፖሊሲ የተሃድሶ መሰረተ-ሃሳብ ናቸው።
በመጀመሪያ ግን ይህን አገዛዝ ገርስሶ በመጣል፣ ህዝባችንን ለስራ በማንቀሳቀስ መሰረታዊ ፍላጎቶቹን(Basic Needs) ሊያሟላ የሚችልበትን ሁኔታ ማደራጀት አለብን። በዚህ መልክ ብቻ ነው ወደ ፊት መግፋትና ቀስ በቀስም ህዝቦቿን ማሰተናገድ የምትችልና የተከበረች ኢትዮጵያን መገንባት የሚቻለው። ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ በየቦታው በተሰበጣጠረ መልክ የሚካሄደው እንቅስቃሴ በአንድ የአስተሳሰብ ክልል ውስጥ(Unity of Thought) መካተት አለበት። ሁሉም በየፊናው ለስልጣን መታገሉን አቁሞ በአንድ ማዕከላዊ አመራር ስር በመመራት ወደ ድል ለማምራት መዘጋጀት አለበት። እየተሰበጣጠሩ መታገልና፣ የሚሆን የማይሆን ሰበብና ተንኮል እየፈጠሩ ዝናን ለማግኘትና ለመታወቅ መሞከር የህዝባችንን ሰቆቃ ያራዝመዋል። የአገራችንን መበታተን ያፋጥነዋል። ይህ ደግሞ የማንኛችንም ምኞትና ፍላጎት አይደለም። ስለዚህ ከመሰባሰብና ተወያይቶ በአንድ ሃሳብ ዙሪያ ከመታገል በስተቀር ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም።

ፈቃዱ በቀለ
fekadubekele@gmx.de

የዳሽን ቢራ አዲሱ ታክቲክ

$
0
0

GM Melaka

ዳሽን ቢራ ንብረትነቱ የህወሃት ነው። ለትግራይ ህዝብ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፋብሪካዎችን ገንብቶ በምትኩ የተከለብን የሹፈት የብቅል ፋብሪካ ነው።

bira_logo_dashen
ከፋብሪካው ትርፍ በተገዛ ጥይት ለጋ ወጣቶቻችን በወያኔ ትግሬ አልሞ ተኳሽነት ተመተው ወድቀው ደማቸው በጎንደር ፒያስ ወደ አውቶፓርኮ አቅጣጫ ያለማቋረት እንደጅረት ፈሷል።
የዳሽን ቢራ የሚቀልባቸው የወያኔ ትግሬ ወንበር ጠባቂዎች መፈክር አንግቦ የወጣን የባህርዳር ማርቆስ ዳንግላ ማርቆስና ፍኖተ ሰላም ወጣት ጭንቅላት ይሄው ራሱ ፋብሪካው በገነባው ማማ ላይ ተጠልለው ጭንቅላታቸውን አፍርሰዋል። የዳሽን ቢራ ጥይት ወልቃይትን ቢረሳ ቀኙ እንድትረሳው ቃል ገብቶ አደባባይ የወጣውን አበበ ገረመውን በአጭሩ አስቀርቶብናል።
ታድያ ይህ መቀመጫውን ዐማራ ክልል አድርጎ ለትግሬ ግብር የሚከፍል፥ ጥሬ እቃን እኛው ጋር በርካሹ አጋብሶ በትርፉ ለህወሃት የአብሪ ጥይትን የሚገዛው የቢራ ፋብሪካ እስካሁን ቆሞ መገኘቱ ሳያንስ ምርቴን ተጠቀሙልኝ የሚል ማስታወቂያ እየሰራ መሆኑን ከወደ ጎንደር እየሰማን ነው።
የሚከተለውን ያካፈለኝ ጎንደር የሆነውን የታዘበ በቅርብ የማውቀው ሰው ነው
“የዳሽን ቢራ የህወሃት ካድሬዎችን ስፖንሰር በማድረግ የተለያዩ ቡና ቤቶች እየዞሩ ዳሽን ብቻ እንዲያዙ፤ ሲጠጡም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው “የጎንደር ህዝብ ግን ምንኛ ሞኝ ነው ዳሽን እኮ ለጎንደር ብዙ ልማቶችን እየሰራ ያለ ፋብሪካ ነው” እያሉ እንዲያወሩ እየተደረገ ነው።
የምሰማውን ማመን አቃተኝ። የወንድሞቸ ደም የሆነውን ቢራ በፈለከው ቋንቋ ብትገልጸውም ጉሮሮየን ከፍቸ ልጠጣው አልችልም። በየማጎሪያ ቤቱ እየተሰቃዩ ያሉ ወንድሞቸ ሰቆቃ ላይ የሚያፌዙትን ካድሬዎች መስማት ስላልቻልኩ የነበርኩትን ቦታ ስቀይር ሌላኛው ቤትም ተመሳሳይ ሁኔታ ገጠመኝ።
የዐማራ ደም በውስጥህ ይዘህ እንዴስ ብለህ የዳሽንን ቢራ ትጠጣለህ? እንዴት ተደርጎ? ያለመጠቀም አድማችን እስከወዲያኛው መሆን ነው ያለበት!!
ይህን ሁሉ ግፍ ከተፈጸመብን በዃላ ዳሽንን የምንጠቀም ሆኖ ከተገኘ “የመንድሞቻችን አጥንት ይውጋን ደማቸውም እንደደራሽ ዉሃ ይውሰደን” በሚል ምህላ ተማምለን ምርታቸውን እስከወዲያኛው ማቆም አለብን።”

ኒውዮርክ፥ በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ውይይት እንዲደረግ ተጠየቀ

$
0
0

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገው የኢትዮጵያ መንግስት «መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን» እንዲያረጋግጥ ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን አስጠነቀቁ። ዋና ጸሐፊው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን ነገር «በጥልቅ» እየተከታተሉ መኾናቸውን የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱያሪች ትናንት አስታውቀዋል። የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን «ሁሉንም ቅሬታዎች ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ውይይት» እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዋል። ባለፈው ቅዳሜ ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአፈጻጸም መመሪያ፦ «ሽብርተኞች» ተብለው በመንግስት ከተጠቀሱ ማናቸውም ቡድኖች ጋር የሚደረግ ግንኙነትን ይከለክላል። ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ነዋሪዎች 60 በመቶ ይሆናሉ ያላቸው የአማራ እና የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ለአንድ ዓመት ግድም ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የጠቀሰው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ኤኤፍፒ የሀገሪቱ መንግስት በአብዛኛው በአናሳ የትግራይ ተወላጆች የተዋቀረ መሆኑንም አክሎ ዘግቧል።

Ban Ki-moon
Source:-dw.com

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ በአርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና በሌሎችም ጀግኖች መሰዋት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ መግለጫ አወጣ

$
0
0

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ

መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ አባል የሆነው አርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና የሌሎችም ጀግኖቻችን ነብስ ይማርልን!!!

የወያኔን የዘር ማጥፋት እኩይ ተግባርና የህዝብ ጥያቄን ከመመለስ ይልቅ እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመጨፍጨፉ ያማረረው ህዝባችን ከኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር መብቱን ለማስከበር በአንድነት የእንቢተኝነት ትግሉን ከወያኔ ጋር አንገት ላንገት መተናነቅ ከጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል ይህንን የሕዝባችንን እምቢተኝነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ቤሄራዊ ፓርቲ ከህዝባችን ጎን በመቆም የወያኔን ግብዓተ መሬት በማፋጠን ላይ ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ነው። በቅርቡም በጀግንነት (በዶጋአው በርሃ) በሞት ለተለየን ኮማንደር አርበኛ አበራ ጎባው እንዲሁም በህዝባችን እንቢተኝነት ትግል ውስጥ በሞት ለተለዩን ሌሎችም ጀግናና አርበኛ ወገኖቻችን ሞተቃቸው ሀዘናችን ቢሆንም ትግላችን በይበልጥ አጠናከረው እንጂ አላሣፈረንም።

በዚህ አጋጣሚ ለሟች ቤተሠቦች ሁሉ እግዚአብሄር ሙሉ ፅናቱን ይስጣቹሁ እንላለን። የኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ፓርቲ ከህዝባችን ጎን እንደተሠለፈ ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎናችን ተሠልፎ ይህን ዘረኛ መንግስት በአስቸኳይ እንድናስወግድ ጥሪያችንን እናቀርባለን

ድል የኢትዮጵያ ህዝብ ነው!!
epnp-002

በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ወጣ፤

$
0
0

ሙሉቀን ተስፋው

መኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንትና የሰሜን ምዕራብ ቀጠና ኃላፊ የነበረውና በቅርቡ ከወራት ስቅይት በኋላ ከእስር የተፈታውን አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ 78 በሚሆኑ የጎንደር ዙሪያ ወጣቶች ማደኛ መውጣቱን ዛሬ ሰምተናል፡፡ እነ ዘመነ ምሕረት ላይ የወጣው ማደኛ ግለሰቦቹን መያዝ ካልተቻለም በተገኙበት እንዲገደሉም ትዕዛዝ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከጎንደር አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአቶ ዘመነ ምሕረት ጋር በተፈላጊነት ስማቸው ከወጣው ዐማሮች መካከል 18ቱ የብአዴን አባላትና በአመራርነትም ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡

14724516_1336741063017170_9067649213559801039_n
አቶ ማሙሸት አማረን እና አቶ አብርሃም ጌጡን ጨምሮ የመኢአድ ሕጋዊ አመራሮች በተለያየ ጊዜ ታስረው የተሰቃዩ ሲሆን በቅርቡም ብዙ የፓርቲው አባላት በእስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከቀናት በፊት አቶ ጫኔ ዘየደ እና አቶ ኢዮብ ታስረው መፈታታቸው ይታወቃል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ በወገራ፣ በበለሳና አርማጭሆ አካባቢ ያሉ የዐማራ ገበሬዎችን ይቅርታ አድርገንላችኋል በሚል ትጥቃቸውን ለመቀማት አዲስ ስትራቴጂ መነደፉን ሰምተናል፡፡ መረጃውን ያቀበሉን ሰዎች እንደሚሉት ገበሬዎቹ ይቅርታውን ከተቀበሉ ለተሀድሶ በሚል ሰበብ ወደ ብር ሸለቆ ወስዶ ለማሰር እቅድ መኖሩን ጭምር ነግረውናል፡፡

በባሕር ዳር 67 ሆቴሎች የባንክ ብድር መመለስ አንችልም ብለዋል

$
0
0

በአገሪቱ የበጀት ውዥቀት ተከሰተ፤ በባሕር ዳር 67 ሆቴሎች የባንክ ብድር መመለስ አንችልም ብለዋል

(የባህር ዳር ከተማ File Photo)

(የባህር ዳር ከተማ File Photo)

መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ኪሳራ ውስጥ ገብቻለሁ አለ፡፡ የ2009 ዓ.ም የካፒተል በጀት እስካሁን ድረስ አልተለቀቀም፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለስራ ማስኪጃ እና ለፅህፈት መሳሪያዎች መግዥያ የሚገለገሉበት በሀገሪቱ የሚጠበቀው የካፒታል በጅት በ2009 ዓ.ም ሊለቀቅ አይችልም፡፡ ሲሉ የአማራ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አየነው በላይ ተናግረዋል፡፡
መንግስት በዚህ ስዓት ለድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ በሚል ከመንግስት በጀት ለሚልሻዎች ቀለብ እና ለወታደሩ የምግብ ሂሳብ ወጭ ያደረገ ሲሆን ይህም የወረዳዎችን በጀት እንዳናጋባቸው እና በአሰተዳደራዊ ስራው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን በበአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ላይ አንስተዋል፡፡
በተያያዘ በአማራ አካባቢ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት በክልሉ የሚገኙ ኢንቨስትምንት እና ሆቴሎች በቀን ሻሂ እንኳን መሸጥ አልቻልንም ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል፡፡
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ (ቴክስታይል)፣ ፒፒ የፕላስቲክ ቀረጢት ፋብሪክ፣ ፀሐይ ቀለም ፋብሪካ፣ አማራ ፓይፕ ፋብሪካ፤ በግብፆች እና በብአዴን የሚመራው ዳሸን ቢራ፣ አማራ ችፑድ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ገበያ ጠፍቷል አላመርትንም፤ መሸጥም አልቻንም ብለዋል፡፡
በባህ ዳር የሚገኙ ትልልቅ ሆቴሎች ደግሞ መንግስት ያበደረንን እስከ 300ሽህ ብር የሚደርስ ገንዘብ አሁን ምንም የመመለስ አቅም የለንም፡፡ በቀን ሻሂ እንኳን መሸጥ አልቻልንም ሠራተኞቻችንንም ለመበተን እየተገደድን ነው ብለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በባህር ዳር የስርዓቱ አቀንቃኝ ተብሎ በህዝባዊ አመፅ ጉዳት የደረሰበት ጋሳ ባለ አምስት ፎቅ ሆቴል፤ የወያኔ ተላላኪ እና የዳሸን ወኪል አከፋፋይ በመሆኑ፤ ህዝቡ ላለመጠቀም በወሰደው እርምጃ ሆቴሉ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠቱን አቆሞ፤ ሰራተኞችን እንደበተነ ከባለቤቱ አረጋግጠናል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የወሰድነውን ብድር መመለስ አልቻልንም ሲሉ ለመንግስት እንቅጩን በመናገር ቅሬታ ያሰሙ ሆቴሎች ዝርዝር 67 ሲሆኑ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1 ቦስተን ሎጂ ባ/ዳር 28 (የምኝታብዛት) 0582264868 0582264280
2 ፓፒረስ ሆቴል ” 100 0582205100 0582205047
3 ብሉ ናይል ሬስቶራንት (ጣና ሆቴል) ሆቴል ” 64 0582200554 0582202042
4 ብሉ ናይል ሆቴል ” 55 0582202028 0582263958
5 ጋሳ ሆቴል ” 31 0918766107 –
6 አዝዋ ሆቴል ” 41 0582203820 –
7 ኒውላይት ሬስቶራንት ” – 0918241801 –
8 ሌክ ሾር ሬስቶራንት ” – 0918340666 –
9 አባይ ምንጭ ሎጂ ” 44 0582281039 0582182223
10 ድብ አንበሳ ሆቴል ” 60 0582201436 0582201818
11 ሆምላንድ ሆቴል ” 28 0582204545 0582220209
12 ሰመርላንድ ሆቴል ” 40 0582206565 0582221091
14 ኢትዮስታር ሆቴል ” 68 0582202026 0582209442
15 ስታርባክስ ሬስቶራንት ” – 0918007370 –
16 ዴዘርት ሎጅ ሎጅ ” – 09218282575 –
17 አሉዋቅ ሆቴል ሆቴል ” 30 0582265565 –
18 አቫንቲ ብሉናይል ሆቴል ” 135 0582264566 –
19 ባ/ዳር ቁጥር 2 ሆቴል ” 36 0582203820 –
20 ኒውላንድ ፔኒሲዮንፔኒሲዮን “82 0582200876 /0918341054 –
21 አዲስ አምባ ሆቴል ሆቴል ” 69 0911220608 –
22 መነን ሆቴል ሆቴል ” 54 0582202800 –
23 ጃካራንዳ ሆቴል ” 28 ዐ5822ዐ9899 –
24 ጨጨሆ ሬስቶራንት ሬስቶራንት ” – ዐ911181937 –
25 ኢትዮ ላንድ ሆቴል ሆቴል ” 58
26 ራህን ሆቴል “ – ዐ5822ዐ7575 –
27 ቤተ ዳንኤል ሆቴል “ – ዐ582266161/22ዐ1414 –
28 ኤንጅጅ ሆቴል ሆቴል “ 42 ዐ5822ዐ6363 –
29 ጣና ሆቴል ጎንደር 18 ዐ918786132 –
3ዐ ሰሜን ፖርክ ሆቴል “ 32 ዐ58111ዐ3ዐዐ –
31 ግራንድ ሪዞርትና ሰፖ ሪዞርት ባ/ዳር – ዐ5822663ዐ3/ ዐ5822ዐ7833 –
32 አሲኗራ ሆቴል ሆቴል “ – ዐ5822ዐ7299 –
33 ኪትስል ሆቴል “ “ – ዐ5822663ዐዐ –
34 ዲላኖ ሆቴል “ “ – ዐ5822ዐዐ622 –
35 ታዬ በላይ ሆቴል “ 79 ዐ58111218ዐ ዐ581112175
36 አምባራስ ሆቴል “ 4ዐ ዐ581111181 –
37 ኩይንስ ሆቴል “ 18 0581141297 –
38 ጐሀ ሆቴል “ 66 ዐ58111ዐ634 ዐ58111192ዐ
39 ሴንትራል ጎንደር ሆቴል “ 18 ዐ581117ዐ2ዐ –
4ዐ አፄ በካፋ ሆቴል “ 24 ዐ581117711 –
41 ቋራ ሆቴል ጎንደር 5ዐ ዐ58111ዐዐ4ዐ ዐ581111144
42 ሰርክል ሆቴል “ 24 ዐ581111991 ዐ58112ዐ599
43 ሬድ ፎክስ ሆቴል “ 14 ዐ58114ዐ581 –
44 ህብረት ሆቴል “ 42 ዐ58112ዐ4ዐዐ ዐ58112ዐ4ዐ1
45 ጐልደንጌት ሬስቶራንት “ – ዐ58111769ዐ –
46 ኤልሼኘ ሬስቶራንት “ – ዐ91877ዐ272 –
47 ላመርጌር ሆቴል ሆቴል “ 2ዐ ዐ58112ዐ599 –
48 ኤጅ ሆቴል ሆቴል “ 45 ዐ581126ዐዐ7 –
49 ጃንተከል ሆቴል “ 39 ዐ918776ዐ68 –
5ዐ ሴንትራል ጎንደር ሆቴል ሆቴል “ 2ዐ ዐ58153762ዐ –
51 ተሜና ኪም ሎጅ ሎጅ ጎርጎራ 12 ዐ92ዐ336671 –
52 ዩኒክላንድ ስኬኘ ሆቴል ደባርቅ 21 ዐ58117ዐ152 –
53 ሰሜን ፖርክ ሎጅ “ 22 ዐ58231ዐ741 –
54 ጃይንት ሎቢሊያ ሆቴል “ 39 ዐ58117ዐ56ዐ –
55 እሚት ጐጐ ሆቴል “ 27 ዐ58117ዐ634 –
56 ጃስመን ሆቴል ሆቴል “ 27 ዐ58117ዐ563 –
57 ሰሜን ፖርክ ሆቴል ሆቴል “ 5ዐ ዐ58117ዐዐ55 –
58 ይምርሃ ሆቴል ላሊበላ 42 ዐ33336ዐ862 ዐ116299259
59 ማውንቴን ቪው ሆቴል “ 3ዐ ዐ33336ዐ8ዐ4 ዐ33336ዐ649
60 ፍቅሩሰላም ሆቴል “ 25 ዐ33336ዐዐ47 ዐ33336ዐ55ዐ
61 ሰቨን አላይቭስ ሆቴል ” 27 0333360020 –
62 ቤተአብርሃም ሆቴል ” 49 0333361065 0333361213/2
63 አያት ሮሃ ሆቴል ” 64 0333360009 0333360156
64 ሆሊ ላንድ ሬስቶራንት ” – 0911481948 –
65 ላል ሆቴል ” 210 0333660008 0333660008
66 አማን ሆቴል ” 56 0333360076 0333360214
67 ግራንድ ሪዞርትና ሰፖ ሪዞርት
68. ራህ ናይል

ሪያድ-ሳውዲው ልዑል አንገቱን ተቀላ፣ ጅዳ –ኢትዮጵያዊው ነጻ ተባለ !

$
0
0

* በንጹሃንን ላይ ወንጄል የሚፈጽም ከተጠያቂነት አያመልጥም
* ” ኢትዮጵያዊው የገደለው ራሱን ለመከላከል ነውና ነጻ ነው! ”
ሳውዲ አረቢያ የንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት ልዑል ቱርኪ ቢን ሳዑድ አል ቱርኪ በፈጸሙት የግድያ ወንጀል በተላለፈባቸው ውሳኔ መሰረት በትናንተናው እለት አንገታቸው መቀላቱን የሳውዲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል ። ሳውዲው ልዑል አንገታቸውን የተቀሉት አድል ቢን ሰልማን አብድልከሪም መሀመድ የተባሉ ሳውዲ ዜጋን መግደላቸው በመረጋገጡ መሆኑን መረጃው ያትታል ።: ልዑሉ ግድያውን የፈጸሙት ከሪያድ ወጣ ብሎ በሚገኝ አል ቱማማ al-Thumama በተባለ ስፍራ በተፈጠረ ግጭት መሆኑንም ተጠቁሟል። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫ በማከልም የግድያው ወንጅል ከተፈጸመ ጀምሮ በተደረገው ከፍተኛ ማጣራት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከሶስት አመት በፊት ልዑሉን ጥፋተኛነት አረጋግጧል ። ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረትም ጉዳዩ ለከፍተኛ የሳውዲ መንግስት አካላት ቀርቦ ይሁንታ ማግኘቱን ሲታወቅ የሟች አድል ቢን ሰልማን አብድልከሪም መሀመድ ቤተሰቦች ካሳ ቀርቦካቸው ፍርድ ሲፈጸም እንጅ የቀረበላቸውን ካሳ እንደማይቀ በሉ በማሳወቃቸው የልዑሉ አንገት በትናንትናው እለት መቀላቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሲያስረዳ በንጹሃንን ላይ ወንጄል የሚፈጽ ም ማናቸውም ሰው ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ መግለጫው አስታውቋል ።

14708301_10211194502324341_5902171941292942399_n
ይህ በእንዲህ እዚህ ጅዳ ውስጥ ከሁለት አመት በፊት ፈይሰልያ በተባለ አካባቢ የኢትዮጵያዊውን አባወራ ቤት ለመዝረፍ ሲመክር በተፈጠረ ግብግብ ነፍስ የጠፋው ኢትዮጵያዊ ኑረሁሴን ሀሰን ሙስ ጦፋ ከተከሰሰበት የግድያ ወንጄል ነጻ መሆኑ ታውቋል ። በመኖሪያ ቤቱ አገር ሰላም ብሎ ተቀምጦ እያለ ለዘረፋ ከመጡ ሳውዲ ወጣቶች ጋር ነበር የተጋጨው ። ዘራፊ ወጣቶች እሱን ወንድሞቹንና የቀሩትን ወንዶች በአንድ ክፍል በመዝጋት በቤቱ ያለውን ንብረት ከዘረፉ በኋላ ሚስቱን ሊደፍሩ ሲሞክሩ የተዘጋበትን ቤት ሰብሮ በመውጣት ከሳውዲ ወጣት ጋር ግብግብ የገጠመው ሁሴን ራሱን ለመከላከል ሳውዲው ወጣት ይዞት የነበረውን ስለት በመቀማት ሊገድለው እንደቻለ ለፍርድ ቤት አምኖ ነበር ።
ኢትዮጵያዊው ሁሴንን ከዚህ ቀደም ባቀረብኩት የማለዳ ወግ በሰጠን ቃለ ምልልስ ግድያ የፈጸመው ራሱ ለመከላከል መሆኑን በመግለጽ የሀገሩ መንግስት ተወካዮች ቀርበው ስለመብቱ መከራከር ባይችሉም ጉዳዩን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን አጫውቶን ነበር ። ከሳምንታት በፊት ጉዳዩን ለሁለት አመት ተኩል የመረመረው ከፍተኛ የሸሪያ ፍርድ ቤት ሁሴን ግድያውን ራሱን ለመከላከል ሲል መፈጸሙን በመግለጽ ከቀረበበት ወንጀል ነጻ እንዳለው በስልክ ባደረግነው ቃለ ምልልስ ግልጾልኛል ። አቅም ሲገቅድ ዝርዝሩን የጉዳዩ ባለቤት ሁሴን ሀሰን ያጫውቶኛል !

14670643_10211194502564347_8867902582509296800_n
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 2009 ዓም


ሰበር ዜና ! ! ! በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ዉስጥ የሚገኘዉ ህወሃት ለሐይማኖት አባቶች የመጨረሻ ጥሪ አስተላልፏል “””አድኑኝ “””! !

$
0
0

ህዝባዊ አመጹ ህወሃትን እያሽመደመደው ለመሆኑ መረጃዎች ብሐራዊ አገልግሎት ዉስጥ ከሚገኙ የዉስጥ አርበኛ ወገኖቻችን እየደረሰን ይገኛል።
የህወሃት የጎጥ ቡድን ለኢትዮጵያ የኦሮዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ሲኖዶስ ተጠሪ አቡነ ማትያስ እንዲሁም ለእስልምና ጉዳዮች ተጠሪ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተንተርሶ ህዝቡን እንዲያስተምሩ እንዲገስጹና እንዲመክሩ በተለይም በቤ/ክርስቲያንና በመስኪዶች አካባቢ በሚደረጉ እለታዊ እና ሳምንታዊ እንዲሁም ወርሐዊ በአላት ላይ ምንም አይነት አመጽ ቢነሳ እርምጃ እንደሚወሰድ የሕይማኖት አባቶች ህዝቡን እንዲያስጠነቅቁ እንዲያስፈራሩ መመሪያ ልኳል።
ህወሃት የሐይማኖት ተቋማት የአቸኵይ ግዜ አዋጁ ቀኝ እጅ እንዲሆኑ ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ አቡነ ማትያስ በሐገር ዉስጥና በዉጭ የሚኖሩ ጥሩ የመስበክ ችሎታ አላቸዉ የተባሉ ቀሳዉስትንና አባቶችን ወደ አዲስ አበባ ጠርተዋል።
በመሆኑም ይህንን የአቡነ ማትያስን ጥሪ በመቀበል በተለያየ ሐገር የሚኖሩ አባቶች የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ ሲሆን የደቡብ አፍሪካ የብሉም ፎንቴን ኪዳነ ምህረት አባት አባ ገ/ማርያም በ /16/10/2016 የደርሳቸዉን ጥሪ ተከትሎ ዉስጥ ዉስጡን ጫና መፈጠሩን ከታማኝ ምንጮች ስናረጋግጥ አቡነ ማትያስ በተለይም ከገር ዉስጥ ከተጠሩ የሐይማኖት አባቶች ማጉረምረም የተነሳ ከፍተኛ ተቃዉሞ ይደርስባቸዋል የሚል ግምትም ሐይማኖታዊ ተሳትፎዎችን ችግር ዉስጥ ከቷቸዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
Zehabesha-News.jpg

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጣጣሉት

$
0
0

(ቢቢኤን)በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ነቀፉ፡፡ ስርዓቱ ሲጨንቀው ያወጣው አዋጅ መሆኑን የጠቀሱት ሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ እና አረና ትግራይ ሲሆኑ፣ ሶስቱም ፓርቲዎች አዋጁ ለሀገር ሳይሆን ስርዓቱ ለራሱ ጥቅም ሲል ያወጣው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አረና ትግራይ ‹‹አዋጁ በሀገሪቱ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመምታት ወይም ለማዳከም የወጣ ነው›› ሲል ኮንኖታል፡፡
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር የነበሩት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ‹‹በሀገሪቱ ውስጥ አስቸኳይ አዋጅ የሚያስወጣ ነገር የለም›› ብለዋል፡፡ እንደ አ/ር ይልቃል አገላለጽ፣ አዋጁ ከመውጣቱ በፊትም ሰዎች ይታሰሩ ይገደሉ ነበር፤ አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ ዜጎች እየተገደሉ እየታሰሩ እንደሆነ ጠቅሰው ከአዋጁ በፊት እና በኋላ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ አክለውም፣ አዋጁ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች እና የሀገሪቱን ህገ መንግስት ጭምር የሚጥስ መሆኑን ከገለጹ በኋላ፣ ‹‹አዋጁ ከድጡ ወደ ማጡ ነው የሚወስደን፡፡›› ብለዋል፡፡
የአረና ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዶም ገ/ስላሴ በበኩላቸው ‹‹አዋጁ በአራቱ የኢህአዴግ ፓርቲዎች ውስጥ ያለውን ሽኩቻ ለመምታት ጭምር የወጣ ይመስላል፡፡›› ካሉ በኋላ፤ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰተው ችግር በውይይት እና በድርድር ካልሆነ በቀር በአዋጅ እንደማይፈታ ገልጸዋል፡፡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አክለውም፣ ገዥው ፓርቲ ጥያቄ የሚያነሱ ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች እና ባለድርሻ አካላትን ማደራደር እንዲሁም ሀገራዊ እርቅ መፍጠር እንዳለበት አስምረውበታል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙሉጌታ አበባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ አባሎቻቸው እየታሰሩ እና ከመንግስት ማስፈራሪያ እየተሰጣቸው እንደሆነ በመግለጽ፣ አባሎቻቸውም ከደቡብ ክልል፣ ከአማራ እና ከአዲስ አበባ መታሰራቸውን ተናግረዋል፡፡ ፓርቲያቸው መኢአድ በቀጣይ ቀናት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ መግለጫ እንደሚሰጥም ምክትል ሊቀ መንበሩ ገልጸዋል፡፡

14724372_915311031938393_4407987774672997179_n

ኢንተርኔት በመዘጋቱ ኢትዮጵያ ላይ የደረሰው ኪሳራ

$
0
0

ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ለ30 ቀናት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ማጣቷን መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው ጥናት ጠቋሟል።
የብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ዳረል ዌስት ባቀረቡት ጥናት በቅርብ ዓመታት ተጠቃሚዎች የሚገለገሉባቸውን የተወሰኑ አፕልኬሽኖች፤ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አሊያም መላውን የኢንተርኔት አገልግሎት መንግስታት ማቋረጥ እና መዝጋት እየተለመደ የመጣ ክስተት መሆኑን አትተዋል። ከእነዚህ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች። ከሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ለ30 ቀናት በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ይኸው ጥናት ጠቁሟል።

36005281_303
«መንግስታት ብሔራዊ እና የሕብረተሰብ ደሕንነት፤ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች» የኢንተርኔት አገልግሎትን ለመዝጋት እንደ ምክንያት የሚያቀርቧቸው ምክንያቶች መሆናቸውን የሚናገሩት ብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ዳረል ዌስት የመንግስት እርምጃ በውጭ ባለሐብቶች ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ይናገራሉ።

«በእርግጠኝነት በውጭ ባለወረቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። እንዲህ አይነት የአገልግሎት መስተጓጎል ከተመለከቱ ገንዘባቸውን በአገሪቱ በሥራ ላይ ከማዋል ሊታቀቡ ይችላሉ። የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋቱ የሚያስከፍለው ኤኮኖሚያዊ ዋጋ የከፋ ነው። ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን ያዳክመዋል። የገቢ ግብር ይቀንሳል። በንግዱ ሕብረተሰብ እና በመንግስት መካከል ያለውን መተማመንም ይጎዳዋል። ከዚህ በተጨማሪ በሸማቾች ላይም ተፅዕኖ አለው። ምክንያቱ በርካታ ሰዎች በሞባይል ገንዘብ ያንቀሳቅሳሉ።»በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት ከገጠመው ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ የኢንተርኔት አገልግሎቱን መገደብ ብሎም ማቋረጥን መርጧል። የአገልግሎቱ መቋረጥ በቅርብ ጊዜ መልስ የሚያገኝ አይመስልም። በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር የሆኑት ሜቴ ታይጌሰን በትዊተር የማሕበራዊ ድረ-ገፃቸው እንዳሰፈሩት የኢትዮጵያ መንግስት የሞባይል ኢንተርኔት እና የማሕበራዊ ድረ-ገፆች አገልግሎት መልሰው ግልጋሎት የሚጀምሩበትን ተጨባጭ ጊዜ ማስታወቅ አልቻለም። የመንግስት የኮምዩንኬሽን ፅ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው ማብራሪያ ነበር ይህን ያስታወቀው።

በኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች እንደ ዋትስአፕ እና ቫይበር ያሉ አገልግሎቶች ከተቋረጡ ሰነባብተዋል። ፌስቡክ እና ትዊተርን የመሳሰሉ የማሕበራዊ-ድረ-ገፆችም አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች አገልግሎታቸው ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል አሊያም ከፍተኛ ገደብ ተጥሎበታል። ዳረል ዌስት እንደሚሉት አብዛኞቹ መንግስታት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሲያቋርጡ የሚያስከትለውን ጣጣ ከግንዛቤ ውስጥ አያስገቡም። ዳረል በጥናቱ የተዘጋው ኢንተርኔት ከአገሪቱ ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ትስስር ለመፈተሽ ሞክረናል ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

«በጥናቱ መረጃውን ለማጠናቀር የተጠቀምኩበትን ሥሌት ይፋ በፅሁፉ አካትቼዋለሁ። በዋናኛነት የአገሪቱ አመታዊ የምርት መጠን፤ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ የሚቆይበትን ጊዜ ርዝመት፤የዲጅታል ኤኮኖሚውን ስፋት በኢትዮጵያ ያለውን የሞባይል ተጠቃሚ ብዛት እና ኢንተርኔት መዘጋት የሚፈጠረውን ተደራራቢ ተፅዕኖ ፈትሸናል።»
ቀድሞም እጅግ ደካማ የቴሌኮምዩንኬሽን መሰረተ ልማት እና ከአጠቃላይ የአገሪቱ የህዝብ ቁጥር አኳያ ውስን የኢንተርኔት ተጠቃሚ የሚገኝባት የኢትዮጵያ መንግስት አገልግሎቱን ሳንሱር ያደርጋል እየተባለ ወቀሳ ይቀርብበታል። የኢትዮጵያ መንግስት ከጎርጎሮሳዊው 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተጠቃሚዎችን የማሕበራዊ ድረ-ገፆች ይበረብራል መረጃዎችንም ያግዳል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ፍሪደም ሐውስ ይተቻል። ከኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ እንዳይደርሱ ገደብ የሚጣልባቸው ድረ-ገፆች መንግስትን የሚተቹ መረጃዎች እና የግለሰቦችን አስተያየቶች የሚያሰፍሩ መቀመጫቸውን በውጭ አገራት ያደረጉ ናቸው።

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መልእክት ኢንተርኔትን ጨምሮ በሞባይል፣ በፅሁፍ፣ በቴሌቭዥን፣ በፌድዮ፣ በማህበራዊ ሚድያ የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦችን አግዷል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ውሳኔ ከመድረሱ በፊት ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ጥቆማ ሰጥቶ ነበር።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 71ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ርዕሰ-ጉዳዮች መካከል የማሕበራዊ ድረ-ገፆች አጠቃቀም አንዱ ነበር። አቶ ሐይለማርያም በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚሰራጭ መረጃ በቀላሉ እንዴት እንደሚዛመት እና ሰዎችን በተለይም ወጣቶችን እንደሚያሳስት እየታዘብን ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እውነተኛ ጥያቄ ያላቸው ሰዎችን ለፅንፈኞች መጠቀሚያ እያደረገ ነው። ጥላቻን ለማስፋፋት እየተጠቀሙበትም ነው ብለው ነበር። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ኩባንያዎችም ይሁን ሥራ ፈጣሪዎች እድሉ የላቸውም። የአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በኢትዮቴሌኮም ቁጥጥር ሥር ነው። የአገሪቱ መንግሥት ዘርፉን ለውጭ ባለሐብቶች እንዲከፍት የቀረቡለትን ጥሪዎች ሁሉ ውድቅ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ባንኮች፤ አገር አስጎብኚ ድርጅቶች እና የገንዘብ ዝውውር ተቋማት ግልጋሎታቸውን ከኢንተርኔት ጋር በማቆራኘት ለማፋጠን ሲያደርጉ የከረሙት ጥረት በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ፈተና ይገጥማዋል። «በኢንተርኔት የሚሰጡ አገልግሎቶች በሁሉም አገሮች የአመታዊ የምርት መጠን ላይ እድገት እንዲፈጠር እያደረጉ ነው። ሰዎች በኢንተርኔት የሚያገኟቸው ግልጋሎቶች እና የሚያደርጓቸው ግብይቶችን እየወደዷቸው መጥተዋል።ብዙ ሰዎች ለመሰረታዊ ሸቀጦች ግብይት እና አገልግሎቶች ኢንተርኔትን መምረጥ ጀምረዋል። መንግስታት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሲያቋርጡ ራሳቸውን በዚያ ቦታ ላይ አድርገው መመልከት አለባቸው። ምክንያቱም የራሳቸውን የንግድ ሥራ እና ኤኮኖሚ እየጎዱ ነው።» ይላሉ ዳረል ዌስት
ብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ዘገባ መሰረት ባለፈው ዓመት በ19 አገሮች የተከሰተ የኢንተርኔት መቋረጥ የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ማድረሱን አትቷል። የዘገባው ጸኃፊ ዳረል ዌስት የኢንተርኔት መቋረጥ ወይም እንደ ዋትስአፕ እና ቫይበር ያሉ ማንቀሳቀሻዎች መታገድ ቤተሰብ፤ጓደኛሞች ያላቸውን ግንኙነት ላይም የከፋ ጫና እንደሚያሳድር ገልጠዋል። በአነስተኛ የገንዘብ አቅም አዳዲስ የሥራ ኃሳብ ይዘው ገበያውን ለሚቀላቀሉ ጀማሪ ኩባንያዎች የኤኮኖሚ እንቅስቃሴውን በማዘግየት አሊያም ጨርሶ በማቆም የሚያሳድረው ጫና አለ። በዳረል ዌስት ዘገባ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ የኢንተርኔት መዘጋት ወይም መቋረጥ ከሚከሰትባቸው እንደ ሕንድ እና ሳዑዲ አረቢያ ተርታ ተቀምጣለች።
የኢንተርኔት አገልግሎት በተቋረጠባቸው አገራት የደረሰው ኤኮኖሚያዊ ጫና በሕንድ ከፍተኛ ነው። አገልግሎቱ በመቋረጡ ሕንድ 968 ሚሊዮን ዶላር፤ ሳዑዲ አረቢያ 465 ሚሊዮን ዶላር፤ ሞሮኮ 320 ሚሊዮን ዶላር፤ ኢራቅ 209 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጥሟቸዋል። የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚዘልቅ በመሆኑ የኢንተርኔት ግልጋሎቱ ወደ ነበረበት መቼ እንደሚመለስ ማወቅ ይቸግራል። በዚሁ ከቀጠለ ግን ኪሳራው ከፍ ማለቱ አይቀርም።

እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ

source:-dw.com

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዐማራ ሊኖረው የሚገባ ዋቢ መጽሐፍ በሽያጭ ላይ ዋለ!

$
0
0

ምጽአተ ዐማራ፦
ተገድሎና ተገዳድሎ የማያልቅ፣ ተነቅሎ የማይደርቅ

mwao_%e1%88%a8%e1%89%a1%e1%8b%95-%e1%8c%a5%e1%89%85%e1%88%9d%e1%89%b5-9-%e1%89%80%e1%8a%95-2009-%e1%8b%93%e1%88%9d_%e1%88%9d%e1%8c%bd%e1%8a%a0%e1%89%b0-%e1%8b%90%e1%88%9b%e1%88%ab_s_20161019_122311

ይህ መጽሐፍ ባለ 657 ገፆች ነው። በዘጠኝ ምዕራፎች ተከፋፍሏል። እነርሱም፦
1. የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መከፋፈል፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዩና ዐማራው የከፈሉት ዋጋ
2. የኢትዮጵያ አንድነት ትንሣኤ፣ የዐማራው የአንድነትና የፀረ-አንድነት ትግል ውጤት
3. ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ የፍፁማዊ ዘውዳዊ አገዛዝ የአንድነት ግንባታ ሂደት ድምድም እና የኢትዮጵያ ዳግም ብተና ጽንስ
4. የለውጥ ፈላጊው ትውልድ የኃይል አሰላለፍ
5. ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ከ1972 እስከ 2007 ዓም ድረስ በዐማራው ነገድ ላይ ያደረሰው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል
6. ስለ ዐማራና ስለ ኢትዮጵያዊነት ምሑራን ምን ይላሉ?
7. የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)፦ ዐማራው ላይ የደረሰው ሰቆቃ የወለደው ነፍስ አድን ድርጅት
8. ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፦ የአሥራት ዘር ፍሬ
9. ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መግለጫዎች በከፊል የሚሉ ናቸው።

MWAO_ረቡዕ ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓም_ምጽአተ ዐማራ_s_20161019_122337.jpg

የመጽሐፉ አቀራረብ ከዚህ በፊት በተለምዶ በገበያ ላይ ከሚውሉት ለየት ያለ ነው። በውስጥ ይዘቱም ከዚህ በፊት ለአንባቢዎች ቀርበው የማያውቁ ጥሬ መረጃዎች፣ ታሪካዊ ትንታኔ፣ እና ዋቢ መጻሕፍት ተካትተዋል። የቀረቡት መረጃዎች በሠንጠረዦች፣ በፎቶግራፎች እና በልዩ ልዩ ካርታዎች አባሪነት የተብራሩ ናቸው።
ይህንን መጽሐፍ በመግዛት እና በማንበብ ስለአገርዎ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ተጨማሪ ዕውቀት ያገኙበታል። በተለይም ዐማራው የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያዊነትን ኅልውና ለማስቀጠል ስለከፈለው እና አሁንም ስለሚከፍለው መስዋዕትነት ለመረዳት ያስችልዎታል።
መጽሐፉን እንዴት እና ከዬት መግዛት እንደሚቻል፦
መጽሐፉ ከትላንት ማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ በገበያ ላይ ውሏል።
1. በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ለሚኖሩ፦ በእናት ኢትዮጵያ ገበያ (ዲሲ)፣ በአስኒ ገበያ (ቨርጂኒያ)፣ በናዝሬት ባልትና (ቨርጂኒያ)፣ በእንጦጦ ገበያ (ዲሲ) እና በሌሎችም የኢትዮጵያውያን መደብሮች ያገኙታል።
2. በመላው ዓለም ላሉት የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ኮሚቴዎች በቅርብ ቀናት ስለሚሠራጭ በየአካባቢው ካሉት የድርጅታችን አካሎች ተጠሪዎች መግዛት ይቻላል።
3. በፖስታ ቤት እና በሌሎችም መንገዶች የሚሠራጭበትን መንገዶች በቅርቡ እናሳውቃለን።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ወያኔ በመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምሕረት እና በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ቢያወጣ ህዝባዊዉን ትግል አይቀለብሰዉም

$
0
0

ሸንቁጥ አየለ
—————————————————————————————
በመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምሕረት እና በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ወያኔ አዉጥቷል:: ሆኖም ወያኔ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ቢያወጣ ህዝባዊዉን ትግል አይቀለብሰዉም:: ወያኔ ደንቆሮ ስለሆነ የመኢአድ ጀግኖችን በማደጥፋት ህዝባዊዉን ትግል የሚገታዉ መስሎት ነዉ::ይሄ ትግል ህዝባዊ ነዉ:: ህዝባዊዉን የህዝብ ጥያቄ የሚመልሰዉ እራሱ ህዝቡ ነዉ:::
ጽኑዓኑ የመኢአድ ጀግኖች 25 አመታት በሰላማዊ ትግል እሳት ዉስጥ ያለ ጫማ ስለ ኢትዮጵያዉያን መብት: ዲሞክራሲ እና ነጻነት በደስታ እና በጀግንነት ተረማምደዉበታል:: አሁንም ትግላቸዉን ቀጥለዋል:: የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከዳር በአሁኑ ሰዓት ህዝባዊ ጥያቄ ሲያነሳ እነዚህ ጀግና የህዝብ ልጆች ላይ ወያኔ ጣቱን መቀሰር ብቻ አይደለም ከምድረ ገጽ ሊያጠፋቸዉ ተነስቷል::

ወደ ሰሜን ጎንደር ሽንፋ እየገሰገሰ ያለውን የህወሀት ሰራዊት በተመለከተ ከአከባቢው የነጻነት ሃይሎች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት
የወያኔ ምርጫ 2007 ሲታወጅ መጀመሪያ የጥቃት ኢላማ የሆኑት እና ከምርጫ ዉጭ ያደረጋቸዉ እነዚህን ጽኑዓን የመኢአድ ጀግኖችን ነዉ:: ምርጫ 2007 ሲደርስበት ወያኔ በመኢአድ መልሶ መጠናከር እና አምስት ቦታ ተሰንጥቆ የነበረዉ የመኢአድ ሀይል ወደ አንድ መምጣቱ አስደንግጦት በአንድ ሳምንት ብቻ ከ250 (ከሁለት መቶ አምሳ) በላይ የመኢአድ አመራሮችን እና አባላትን ሰብስቦ እስር ቤት ከቷል:: በዚህም የድርጅቱን ፕሬዝዳት (አቶ ማሙሸት አማረን): ምክትል ፕሬዝዳንት (አቶ ዘመነ ምህረትን) እንዲሁንም በርካታ አመራሮቹን በጨካኝ እስር አሰቃይቷቸዋል::ለምን? ምክንያቱም እነዚህ የመኢአድ ጽኑዓን ጀግኖች ካነገቡት አላማ ሸብረክ የማይሉ እንደሆኑ ስለሚያዉቅ ነዉ::
ወያኔ ህዝባዊ አመጽ ኮሽ ሲልበት: ምርጫ ሲመጣበት: ምድሪቱ አልረጋጋ ስትለዉ የሚሮጠዉ ወደ መኢአድ ጀግኖች ነዉ::የመኢአድን ጀግኖች ወያኔ አስሮ ዘራቸዉን ይቆጥራል:: ከመላዉ ኢትዮጵያ የመኢአድን ጀግኖች እያጋዘ ወደ እስር ቤት ያጉራል:: በተለይ ደግሞ ከአማራ ህዝብ አብራክ የወጡትን የመኢአድ ጀግኖች ብልታቸዉን ያኮላሻል: ዘራቸዉን እየጠራ ይሳደባል: ይደበድባቸዋል: አስሯቸዉ እፊታቸዉ ቆሞ እንኳን በፍርሃት ይርዳል::
ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ የሆኑትን እና አማራ ያልሆኑትን የመኢአድ አባላት እና አመራሮች ደግሞ ከትምክህተኛ አማሮች ጋር ምን ህብረት አላችሁ: ከመኢአድ ዉጡ እያለ ጉቦ ለመስጠት ይሞክራል::ሆኖም ሁሉም ጽኑዓን የመኢአድ አባላት እና አመራር መልሳቸዉ የማይሰባበር እና የማይተጣጠፍ ቀጥ ያለ ነዉ:: “አንዲት ኢትዮጵያ: አንድ ሀገር: አንድ ህዝብ ነዉ የመኢአድ አላማ” የሚል:: “ስለዚህ የወያኔን የጎሳ ፖለቲካ እራሳችሁ አንጥፋችሁ ተኙበት” የሚል:: ወያኔን የሚያሳብደዉ እና የሚያርበደብደዉም ይሄዉ የመኢአድ ሀይላት የአስተሳሰብ የበላይነት ጭምር ነዉ::
ሆኖም ወያኔ በመኢአድ ጀግኖች ላይ አሁንም ይበልጥ ጦር ሰበቃዉን ቀጥሎበታል:: እናም አሁን ደግሞ በእብሪት በመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምሕረት እና በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ አዉጥቷል:: ዘመን ምህረት አንዱ ጽኑዉ የመኢአድ ልጅ ነዉ::የድርጅቱ መሪ::በጠላት ፊት ቆሞ በጠላት የሚሳለቅ የአናብስት ዘር:: የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን ሊያፈርሱ የሚላኩ የወያኔ ባንዳዎችን እራስ አስደፍቶ የሚልክ:: ሲናገር ነበልባል: ወኔዉ ሙሉ እና የኢትዮጵያዊነት እምነቱ ፍጹም::በማህበረሰቡ ዘንድ ያለዉ ተቀባይነትም እጅግ የታመነ ነዉ::
እናም አሁን ወያኔ መኢአድን እስከ መጨረሻዉ ለማጥፋት ሰዓቱ ነዉ ብሎ ተነስቷል:: ስለዚህ በሰሜን ጎንደር በመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምሕረት እና በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ቢያወጣ ምንም አይደንቅም::ወያኔ ማንንም ሰላማዊ ሰዉ እቤቱ ገብቶ ሊገድል ወይም ከቤቱ ጎትቶ ሊያስር የሚችል ወሮበላ ብቻ ሳይሆን ድንገት ብድግ ብሎ የራሱን ህገ መንግስት ወደ ተራ ወረቀትነት የሚለዉጥ ተራ የጎጠኛ እና የሽፍታ ስብስብ ነዉ::
የሚደንቀዉ ግን የብዙዉ ኢትዮጵያዊ ዝምታ ነዉ:: ጀግኖቻችሁን መቼ ነዉ የምትረዷቸዉ? መቼስ ነዉ የምትረዷቸዉ? 25 አመታት በእሳት ዉስጥ የተመላለሱት ስለማን ነዉ? ስለ ታላቂቱ ሀገራችሁ ኢትዮጵያ አይደለም? እናስ ? ምንድን ነዉ ከጎናቸዉ የማትቆሙት? ምንድን ነዉ ዝምታችሁ?
በመላዉ አለም ያላችሁ ኢትዮጵያዉያን አሁን ከጀግኖቻችሁ ጋር ለመቆም መነሳት አለባችሁ:: ጀግኖቻችሁን ለማገዝ ተነሱ:: የመኢአድ ጽኑዓን ጀግኖች አሁንም ስለ መላዉ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ: ነጻነት እና እኩልነት ለሃያ አምስት አመታት የቀጠለ ትግላቸዉን በደስታ: በወኔ እና በማይታጠፍ አላማ እያከናወኑ ነዉ::ወያኔም ያዉ እንደተለመደዉ የሀሰት ክሱን እየፈበረከ ጀግኖቹን ሊያጠፋ ተነስቷል::
መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አምስት አመታት በትግል እሳት ከተፈተኑት የመኢአድ ጀግኖች ጋር መቆሚያ ሰዓቱ አሁን ነዉ:: አንድ ሀገር : አንድ ህዝብ : አንድ ኢትዮጵያ የሚሉት ጀግኖቻችሁ ኢትዮጵያችሁን በምልዓት ከጥፋት የሚያድኑላችሁ እና ኢትዮጵያዉያንን ከጎሳ የእርስ በርስ መጠፋፋት የሚታደጉላችሁ ጽኑዓን መሆናቸዉን በደንብ ማስተዋያ ጊዜዉ አሁን ነዉ:: እናም ተነስታችሁ ከነዚህ ጀግኖች ጎን ቁሙ::
ወያኔም ጠንቅቆ ሊያዉቀዉ የሚገባዉ በመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምሕረት እና በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ቢያወጣ ህዝባዊዉን ትግል አይቀለብሰዉም::ይሄ ትግል ህዝባዊ ነዉና ህዝባዊዉን ትግል በድል የሚደመድመዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ነዉ::
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት !
አንድ ኢትዮጵያ: አንድ ህዝብ: አንድ ሀገር !
ሞት ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አይነት ጸረ ኢትዮጵያዊነት ህሳቤ አራማጅ ሀይሎች

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live