Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የትግራይን የበላይነት ለመገንባት የወጣ ስውር ደንብ ነው! |አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0

ኢትዮጵያ መንግስት የላትም። ከትግራይ ክልል በስተቀር ክልል የሚባሉትም በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቀዋል። ኢትዮጵያን እየገዙ ያሉት አራት ኪሎ ቤተ ሽፍታ [ቤተ መንግስት ላለማለት ነው] የሚገኙት ደም የተጠሙ የትግራይ ነውረኞች ናቸው።
acham
ደም የተጠሙት እነዚህ የትግራይ ነውረኞች ያወጡት አዋጅ ከትግራይ በስተቀር በሁሉም የአገሪቱን አካባቢዎች ተፈጻሚ ይሆናል።

አማራውም ሆነ ኦሮሞው በሰልፍ ወጥቶ መጀመሪያ የጠየቀው «የትግራይ የበላይነት ይብቃ» የሚል ህዝባዊ ጥያቄ ነበር። ነውረኞቹ የትግራይ ሽፍቶች ግን «የትግሬ የበላይነት ይብቃ» ሲል ለጠየቀው ህዝብ የሰጠውት መልስ ከትግራይ ውጭ ባሉት የአገሪቱ አካባቢዎች ለስድስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ አሁን ያለውን «የክልሎች» የኢኮኖሚ ልዩነት የበለጠ የሚያሰፋና የትግራይን የበላይነት በጽኑ መሰረት ላይ የሚስቀምጥ «መፍትሔ» ነው።
achamyeleh
በቤተ ወያኔ «የትግሬ የበላይነት በቅቶናል!» ለሚለው ህዝባዊ ጥያቄ የሚሰጠው ግብረ መልስ የትግሬን የበላይነት ሽቅብ ገንብቶ አማራውንና ኦሮሞውን ግን የበለጠ ቁልቁል የሚደፋ ነው። በርግጥ ለትግራይ የተነሳ ቡድን ከትግራይ ውጭ ያለውን የሌላውን ጥያቄ ሊመስል ባይችል አይገርምም። ለዚያም ነው አማራው ወያኔ የሚመልሰው ጥያቄ የለውም የምንለው። የአማራ ጥያቄ የሚመለሰው ወያኔ ሲወገድ ብቻ ነው የምንለው ለዚያ ነው።

የኮድ ስያሜ ተበጅቶላቸው የመለስ ራዕይ፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ «ግብጽ ተቃዋሚዎችን እየረዳች ኢትዮጵያን ልታፈርስ ነው» ወዘተ በሚል የሚቀርቡት ጉዳዮችን ሁሉ የትግራይን የበላይነት ለመገንባት የተፈጠሩ የተለያዩ ስልቶች ናቸው። እነዚህ የኮድ ስያሜዎች ሲፋቁ የሚነበበው ስንክሳር የሚነግረን የትግራይን የበላይነት ነው።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም ለስድስት ወር ያልህ ከትግራይ ውጭ ባለው የኢትዮጵያ ክፍል ቅንባ ተደፍቶበታል። ስድስት ወር ማለት ግማሽ አምት ማለት ነው። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዚህ የበጀት አመት ውስጥ ብቻ ትግራይ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል አንጻር ከግማሽ አመት በላይ ወደፊት እንድትገሰግስ የሚፈቅድ አዋጅ ነው። ለስድስት ወር ያህል ትግራይ ሰላም ሰፍኖ ብርሀን ሲበራ ቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል ግን ጦርነት ታውጆበች እየረገፈ በድቅድቅ ጨለማ ይማቅቃል። ወያኔ የታገለው የትግራይን የትግራይን ለማንበር ነበር። ይህንን በማረጋገጥ ረገድ አንድም ቀን አልቦዘኑም። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ያደረጉት ያንን ነው።

_____________________________
የወያኔ ነገር. . .
አቻምየለህ ታምሩ

ወያኔ የተወለደው በባንዶች ማህጸን ተጸንሶ ቢሆንም ያደገው ግን በኢትዮጵያ ጠላቶች አንቀልባ ታዝሎ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከምስረታው ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ አፍቃሪ የሆነ ነውረኛ ቡድን ቢኖር ወያኔ ብቻ ነው። ይህ ነውረኛ ቡድን ጫካ እያለ ያላንኳኳው የኢትዮጵያ ጠላት በር የለም። ከሶርያ እስከ ኢራን፤ ከሳውዲ አረቢያ እስከ ግብጽ፤ ከሊቢያ እስከ አልጀሪያ፤ ከሱዳን እስከ ሶማሊያ ያልረገጠው የኢትዮጵያ ጠላት ደጅ የለም። ወያኔ ከነዚህ መንግስታት ሁሉ ድጋፍ ያገኝ የነበረው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቃለ መሀላ እየፈጸመ ነው።
ጨካኙ የሰው አውሬ መለስ ዜናዊ ከመሀመድ ጋዳፊ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ዘሩን ሳይቀር ቀይሮ «እኛ ትግሬዎች አረቦች ነን፤ ኢትዮጵያዊ እንድንሆን ያስገደዱን አማሮች ናቸው» ብሏል። ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የራሷን ጦርነት በምታደርግበት ጊዜ አረመኔው መለስ ዜናዊ መሀል ሞቃዲሾ ዚያድ ባሬ ጉያ ጽህፈት ቤት ከፍቶ የትግራይ ተወላጆችን ሳይቀር ከወራሪው የሶማሊያ ጦር ጎን በማሰለፍ ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ጋር አብሮ ወግቷል። ሶማሊያ ወራን ኩባ ኢትዮጵያን በምትረዳበት ጊዜም ወያኔ ከሶማሊያ ጎን ቆሞ ኩባ ኢትዮጵያን በመርዳቷ በጥብቅ ያወግዝ ነበር።

ባለም ላይ ወያኔን ያልረዳ የኢትዮጵያ ጠላት የለም፤ ወያኔም ያለስስት የኢትዮጵያ ጠላቶችን ለማገዝ አብሮ ያልተሰለፈው ፀረ ኢትዮጵያ ግንባር የለም። የወያኔ ዶሴ ሲገለበጥ የሚነበበው ወያኔ ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያ ከውጭ ጠላቶች በላይ መውጋቱ ነው።

በኢትዮጵያ ታሪክ የሚጠላትን አገር ለመግዛት በኢትዮጵያ ጠላቶች ሙሉ ድጋፍ ተደርጎለት ለስልጣን የበቃ አገዛዝ ቢኖር ወያኔ ብቻ ነው። እንደወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በኢትዮጵያ ጠላቶች የተረዳ ኃይል የለም።

«ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ ይላል» እንዲሉ ይህ ወያኔ ነው እንግዲህ ዛሬ በኢትዮጵያ ጠላትነቱ ወደር እንደማይገንለት ምስክር የምትቀርበውን ግብጽን በኢትዮጵያ አፍራሽነት የሚከሰው።

ዛሬ ዛሬ በቤተ ወያኔ «አገር ማፍረስ» ማለት የትግሬ ነጻ አውጭ ቅኝ ገዢ ጥቅምን መንካት ማለት ነው። ከሁሉ አስቀድሞ አገር ለማፍረስ ጫካ የወረደው ዛሬ በስልጣን ላይ ያለው ነውረኛ ቡድን ነው። አገር ቆርሶ መስጠትን፤ አገርን ያለ ባህር በር ማስቀረትን፣ አገር የሚያፈርስ አዋጅን ህጋዊ ማድረግን የውጭ ግንኙነት መመሪያው ያደረገው ወያኔ የሞራል ልዕልና አግኝቶ ግብጽን በአገር አፍራሽነት ይከሳል። አገር በማፍረስ ረገድ ከሁሉ አስቀድሞ ኤርትራን የሸጠው መለስ ዜናዊ ነው። ኢትዮጵያን ያለ ባህር በር ያስቀረው ሽፍታው መለስ ዜናዊ ነው። የአገር የማፍረሻ አዋጅ የሆነውን ጎሰኝነት ህገ መንግስታዊ ያደረገው መለስ ዜናዊ ራሱ ነው።

ባጠቃላይ አገር ያፈረሰው፣ ታሪክ የደፈረው፣ ኢትዮጵያን ያለ ባህር በር ያስቀረው መለስ ዜናዊ የሚባለው የሽፍታ አለቃና የትግራይ ሽፍቶች ለግል ጥቅማቸው የመሰረቱት የቅሚያና የስርቆት ድርጅት የሆነው ፋሽስት ወያኔ ነው እንጂ ሌላ አካል አይደለም። ፋሽስት ወያኔና ደጋፊዎቹ [ግብጽንም ቢሆን] አፋቸውን ሞልተው ስለ ሀገር ሉአላዊነት ለመናገር የሚያስችል ስብእናና የሞራል የበላይነት የላቸውም!!

↧

↧

የአማራ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ 9 አዳዲስ የትግል ስልቶችን ይፋ አደረገ |ይዘነዋል

$
0
0

ከአማራ ክልል የሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና አዲስ የትግል ጥሪ

ቀጣዩ እቅድ አንባገነኑ መንግስት በአማራና በኦሮሚያ እንዲሁም በጋንቤላና በኮንሶ በሰላም ባዶ እጁን ለተቃውሞ በወጣ ህዝብ ላይ በአልሞ ተኳሽ ህዝብን መጨፍጨፍ ሥራ ብሎ ይዞታል። ዛሬም ወጣትነት እስኪጠላ ድረስ በጅምላ ይጨፈጭፋል ፤በጅምላ ያፍናል፤ በጅምላ ያስራል፤ አስሮም አድራሻ አጥፍቶ ይገላል፤ ወላጆችም በሞቱት ልጆቻቸው አንጀታቸው ተቆርጧል። ልጆቻቸው የታሰሩባቸውም በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ለማወቅ ተቸግረው ሌት ተቀን እያለቀሱ ይገኛሉ።

በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ ሰሞኑን በቢሾፍቱ የተፈጠረው ሁኔታ ሁላችንንም የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ አስገብቶናል። ጠንከር ያለ እርምጃ እንድንወስድም አስገድዶናል። በመሆኑም ባለን ውክልና በአማራ ክልል የወሎ፣ የጎንደርና የጎጃም የህዝብ ትግል አስተባባዎች የሆንነው አካላት አዲስ የትግል ጥሪዎችን አውጥተናል።

amhara
የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ትግል አስተባባሪዎችም እንዲህ አይነት የትግል ስልቶችን በመጠቀም ከወገኖቻቸው ጋር በመተባበር በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ በማሰቃያ ቤቶች የሚገኙ ወንድሞቻቸውን እና 40 ሚሊዮን የሚገመተውን የኦሮሚያን ክልል ህዝብ ከሌላው ወንድሙ ጋር በማስተባበር ፤ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እንድንተባበር ይህን የትግል ጥሪ ስናቀርብ፤ሌሎችም በህወሀት አገዛዝ ታፍነው የሚገኙት የደቡብ ፣የጋምቤላ፣ የሶማሌ፣ የሀረሪ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር እና የትግራይ ክልል ሕዝብ ከሌላው ወገናቸው ጋር በትግሉ በመተባበር ሁላችንም ነፃ ልንወጣ ይገባል የሚል እምነት አለን።
እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነጋዴዎችና አጠቃላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች፤ የንፁሀን ወገኖቻቸውን ያልተቋረጠ ስቃይ ለማስቆም የሌሎች ወንድሞቻቸውን ጥሪ ሊተገብሩ ግድ ይላቸዋል።
በመሆኑም እኛ የአማራ ህዝብ ትግል አስተባባሪዎች፣ አፋኙን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ህዝብን በማይጎዳ መልኩ ከዚህ በፊት ካካሄድነው የስራ ማቆም አድማ በበለጠ ጠንካራና ገዥውን ቡድን የሚያሽመደምድ ትግል የቀረጽን ሲሆን ህዝብም ይህን አንድ ሀሙስ የቀረው ቡድን አሽቀንጥሮ ለመጣል ይህን የትግል ስልት ያለፍርሀትና ያለመለያየት በጋራ ተግባራዊ ሊያደርገው ይገባል።

የትግል አይነቶች፦

የትግል ስልት1ኛ

-ለግል ድርጅቶች የ2008 ዓ/ም ግብር እስከ ተህሳስ 30 ታክስ አለመክፈል።
ከላይ እንደተመለከተው የወርሃዊ ቫት አለመክፈል ጥሪ ያስተላለፍን ሲሆን፤ አንድ ነጋዴ አገዛዙን ፈርቶ ታክስ እከፍላለው ካለ እስከ ታህስስ 30 ድርጅቱን የመዝጋት አማራጭ ቀርቦለታል። ምክንያቱም ህዝብ አንድ ከሆነ፤ አሸባሪው ቡድን ምንም ማድረግ አይችልምና።ይህን ጥሪ ጥሶ ለገዳዩ መንግስት ታክስ እየከፈለ ሌላውን የሚያሳጣውንና ለወንድሞቹ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ድርጅትም ለመፋረድ ዝግጅት አድርገናል።
ምክንያቱም እኛ ወጣቶች ለነፃነት የህይወት መስዋትነት እየከፈልን ባለበት ሁኔታ አንዳንድ ነጋዴዎች ለንብረት ሣስተው ለገዳዩ መንግስት የጥይት መግዣ የሚሆን ግብር ከከፈሉ እኛም ለነሱ ዋጋቸውን እንከፍላለን። ከሌላው ወገኑ ጋር ያልተባበረ ነጋዴንና ከህዝብ ያልወገነ የታክስ መስሪያ ቤት ሰራተኛንም ከገዳዩ የህወሀት ቡድን በምንም አይነት ለይተን የማናያቸው መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።

በተጨማሪም ነጋዴው ታክስ እንዳይከፍል የሂሳብ ባለሙያዎች ነጋዴውን በነፃ እንዲያማክሩት እናሣስባለን። ከምክሮቹም ውስጥ 1ኛ የወርሃዊ ቫት ሪፓርትና አመታዊ ታክስ ክፍያን ለወራት በማቋርጥ በወር በ2000 ብር ቅጣት ሳይከፍል እንደሚቆይ ማስገንዘብ፣ 2ኛ የአመታዊ የትርፍ ግብር የኪሳራ ሪፓርት ማቅረብ እና 3ኛ ተመላሽ ክፍያወችን መጠየቅ የሚሉት ይገኙበታል። ይህን በተመለከተ ለበጠ መረጃ የሂሳብ ባለሙያወችን ያማክሩ ።

እኛ የአማራ ክልል የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ከሌሎች ወንድሞቻችን እና ከሕዝባችን ጋር በመሆን በነዚህ ወራት ይህን ዘረኛና ገዳይ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እየጣርን ባለበት ሁኔታ የገዳዩን ቡድን እድሜ ለማራዘም ይህን ግብር ያለመክፈል ጥሪ የሚጥሱ ነጋዴዎችን ስምና አድራሻ የታክስ መስሪያቤት ሰራተኞች እንዲተባበሩን ጠይቀናል፣ አሁንም እንጠይቃለን።
በተጓዳኝ ከህዝብ ያልወገኑ የታክስ መ/ቤትና የንግድና ትራንስፖርት መ/ቤት ሰራተኞችን ስም ፣ የሥራ ቦታና እድራሻቸውን ነጋዴው ሊያደርሰን ይገባል።

የትግል ስልት 2ኛ

በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ተባባሪ ድርጅቶች ፦
ሀ- የጥረት ድርጅቶች ፣ለ- የሸህ ማህመድ አል አሙዲ ድርጅቶች፣ ሐ- በክልላችን የሚተላለፉ የህወሀት ተሽከርካሪዎችና ንግድ ድርጅቶች ስራችውን እንዲያቆሙ ጥሪ እያስተላለፍን፤ ይህን ጥሪ ከተላለፉ እርምጃ እንደምንወስድባቸው እናሳውቃለን!!!
የህወሀት ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ወንድሞቻችንም በክላችን እንዳትንቀሳቀሱ በውንድሞቻችን ደም እንጠይቃለን!!!

የትግል ስልት 3ኛ

ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ አባይ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ አማራ ብድር እና ቁጠባ ባንክ ተጠቃሚ የሆናችሁ የአማራ ክልል ነዋሪዎች በ15 ቀን ውስጥ ገንዘባችሁን እንድታወጡ እንጠይቃለን። ከ15 ቀን በሗላ ማንም የአማራ ክልል ህዝብ ገንዘብም በነዚህ ባንኮች እንዳይገባና እንዳይወጣ፤ እንዲሁም ከነዚህ ባንኮች የወሰደውን ብድር እንዳይከፍል፤ በነዚህ ባንኮች በእዳ የተያዙና ለጨረታ የቀረቡ የግለሰብ ቤቶችን እና ተሽከርካሪዎችንም ማንም እንዳይገዛ እናሣስባለን። ይህን ጥሪ ጥሶ በእዳ የተያዙ ንብረቶችን የሚገዛ፤ ነገ ጧት ሀብቱ የህዝብ እንደሚሆን ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!
በትጓዳኝ ሌሎች ባንኮችም ቅርንጫፎቻቸውን እንዲያሰፉ ባልተቋቋሙባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን እንዲከፍቱ እንጠይቃለን!
የንግድ ባንክ፣ የአንበሳ ባንክ፣ የዳሽን ባንክ፣ የአባይ ባንክ፣ የአበቁተ ባንክ ስራ አስኪያጆች፤ ገንዘቡን ወጭ የሚያደርገውን ህዝብ ያለምንም ችግር እንዲያስተናግዱ በሞቱት ወንድሞቻችን ስም እንጠይቃለን!ከዚህ በሗላ በነዚህ ባንኮች እየተጠቀመ ለወንድሙ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ግን እንፉረደዋለን!!!
ህዝብ ከከፈለው ግብር በአመታዊ በጀት ተመልሶ ለልማት ሊደርሰው ይገባ ነበር። የእኛ የአማራ ህዝብ ግን፦ “ሰነፍ ነው፤ አይሰራም” ተብሎ ግብር ከፍሎ ከተመደበለት 4.5 ቢሊዮን ብር (ልብ በሉ ሚሊዮን እይደለም)የአማራ ክልል ልማት ባንክ በጀት ገንዘብ፤ ወደ ትግራይ ተወስዶ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ ለህወሀት ወታደሮች ስልጠና እየተሰጠ ባለበት ወቅት እኛ በህወሀት በሚሽከረከሩ ባንኮች ገንዘባችንን ማስቀመጥ ፈጽሞ የለብንም!!!

የትግል ስልት 4ኛ

በመድን ኢንሹራንስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ ፣አንበሳ ኢንሹራንስ፣ አባይ ኢንሹራንስ ፣አፍሪካ ኢንሹራንስ ፣ተጠቃሚ የአማራ ህዝብ ከነዚህ ድርጅቶች ገንዘቡን ተመላሽ በማድረግ ሌሎች ኢንሹራንሶች እንዲገባ ጥሪ እናስተላልፉለን!!ሌሎች ኢንሹራንሶችም ለህብረተሰቡ የተመጣጠነ ዋጋ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን።

የትግል ስልት 5ኛ

በውጭ የሚኖረው ማህበረሰብ በወገኑ ላይ እየደረሰ ያለውን አይን ያወጣ ስቃይ እያየ ወደ ሀገር ቤት በባንክ ገንዝብ መላክ፤ ሕዝብን በተጋድሎው በማገዝ ፋንታ ወገንን ለማስገደል መንግስትን እንደማገዝ ይቆጠራልና ቢችሉ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ገንዘብ እንዳይልኩ እንጠይቃለን!!
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ግዴታ መላክ ካለበዎት በጥቁር ገበያ እንዲልኩ አለዚያም ዘመድዎ ሀገር ውስጥ ካለ ዘመድ ወይም ወዳጅ ተበዳድረው እንዲቆዩ ያደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን። ይህ ውጪ ላለው ወገናችን ለራሱ ህሊና የሚተው ጥሪ ሲሆን፤ ይህን ጥሪ ጥሶ በባንክ ገንዘብ የላከን ከአጋዚ ለይተን አናየውም።

የትግል ስልት 6ኛ

ማንኛውም ህዝብ ከዛሬ ጀምሮ የመሬት ሊዝ ማንኛውንም አይነት ክፍያ ለአማራ ክልል ለከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች እንዳይከፍል!!

የትግል ስልት 7ኛ

ትራፊኮች፣ አደጋዎችን ከመቆጣጠር ውጭ ተሽከርካሪዎችን በገንዘብ እንዳትቀጡ!

የትግል ጥሪ 8ኛ

የመንግስት ተላላኪዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ከህዝብ ጎን የማትቆሙ ከሆነ በናንተና በንብረቶቻችሁ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን!!

የትግል ስልት 9ኛ

የመንግስት ባለስልጣን እና ካድሬ ንብረቶችን ባልተጣሩበት ሁኔታ ከዛሬ ጀምሮ በእዳ መያዣም ይሁን በግዥ ማንም እንዳይገዛ ጥሪ እናቀርባለን! እነዚህን ንብረቶች ገዝቶ የተገኘ ፤ነገ ጧት ወደ ህዝብ ንብረትነት መመለሳቸው እንደማይቀር ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!

ከላይ የተዘረዘሩት ከዛሬ ጀምሮ የሚተገቡሩ የትግል ስልቶች ሲሆኑ ፤አሸባሪው ቡድን የህዝብን ጥያቄ የማይቀበል ከሆነ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው በየደረጃው ከዚህ የተሻሉ ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁ መኾኑን እናሳውቃለን።
የአማራ ክልል ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ!

↧

ሰሞኑን በጌዲዮ የዘረኝነት ጥቃት ለደረሰባችሁ የዲላ፣ ወናጎ፣ ቡሌ፣ ይርጋጨፌ፣ አንዲዳ፣ ጨለለቅቱ፣ ፍሰሀ ገነትና ወዘተ ተወላጆች የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

$
0
0

screen-shot-2016-10-16-at-9-07-35-am

ለመላው ወገኖች ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት:: ባለፉት ግዜያት እንደምታውቁት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ባለው የፖለቲካ ትኩሳት ብዙ ነገሮች በሚኖረው ህዝብ ላይ እየደረሰ ይገኛል፡፡ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ መነሻውና አላማው ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ተወልደን ባደግንበት ደቡብ ጌዴኦ አካባቢ ባሉ ወረዳዎች እና ከተሞች ላይ በዲላ፣ ወናጎ፣ ቡሌ፣ ይርጋጨፌ፣ አንዲዳ፣ ጨለለቅቱ፣ ፍሰሀ ገነት ወዘተ… በሚኖረው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተወልዶ አድጎ የልጅ ልጅ ያየውን የሚኖረውን ህዝብ ቦታህ አገርህ አይደለም በሚል እሳቤ ለፍቶ ባፈራው ንብረቱ ላይ ውድመት እንዲሁም የህይወት ዋጋ ጭምር ተከፍሎበታል፡፡ ይህ አይነቱ ክስተት ሲከሰት የመጀመሪያ ባይሆንም የአሁኑ የከፋ ሆኑዋል፡፡ከሁሉም ዞንና ብሄር ብሄረሰብ በጌዴኦ ዞን የተለየ ሲሆን ይታያል፡፡መላው ሀገራችን ማንም ዜጋ በነጻነት ሊኖርባት ይገባል፡፡የትኛውም ስፍራ ለዚህ ዘር ተብሎ አልተሰጠም ለሰው ልጅ ሁሉ ተፈጠረ እንጂ፡፡ሰው የሰው ዘር እንጂ ገለልተኛ የተለየ የማንነት መለያ የለውም፡፡ለዚህ ሁሉ ክስተት እና ለተጨማለቀ የዘር ፖለቲካ በህግም በታሪክም ያመጡት ይጠየቁበታል፡፡አሁንም እያዩት ይገኛል፡፡

ወገኖች ሁሉንም በግዜ ሂደት ምናየው ሲሆን አሁን ግን በአካባቢው ላይ ለደረሰው ጥፋት ለተጎዱት ወገኖች በምንችለው አቅም መድረስ እንድንችል እና ከጎናቸው እንድንሆን ባለው ሁኔታ ዙሪያ እንድንወያይ አስበናል፡፡ስለሆነም የአካባቢው ተወላጆችም ሆን የትኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወገን የሆነ ሁሉ ለወገኖቻችን እንድንደርስ ጥርያችንን እናስተላልፋለን፡፡ስለሆነም በመላው ዓለም ያላቹ ዛሬ እሑድ ጥቅምት 6,2009 (OCTOBER 16,2016)በ6pm በዋሽንግተን ዲሲ አቆጥጠር በስልክ ኮንፈረንስ ለማረግ ቀጠሮ ስለያዝን ሁላችንም እንድንገኝ ጥሪያችንን በትህትና እናቀርባለን፡፡

የመደወያ ቁጥር 5308811300 ሲሆን መግቢያው ቁልፍ 812195 ነው፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!

↧

የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ንቅናቄ መግለጫ: “የሕዝብን  ሕዝባዊ  ዐመፅ  ዐዋጅ  አያቆመውም!”

$
0
0

ባለፈው መስከረም ፪፪ ፣ ፪፻፱ በሰላም ፈጣሪን ለማመስግን በወጡ ንጹሃን ወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ ክፉኛ እናወግዛለን፡፡ በገዛ ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የመጨፍጨፍን ገፈት የቀመስነው እኛ የጋምቤላ ልጆች ዛሬ በኦሮሞ ወገኖቻችን ፣ በኦሮምያ እና በጎጃም ፣ በጎንደር አማራ ዜጎቻችን ላይ እየተደረገ ያለው የዘር ማጥፋት ክፉኛ አሞናል ለዚህም ነው ደማችሁ ደማችን ነው ስቃያችሁ ስቃያችን እያልን ከልብ የመነጨ ሀዘናችንን የምንገልጸው፡፡ ዛሬ ሀዘን ቢያቆራምደንም በአንድ በኩል ደግሞ ከጠላታችን ከወያኔ ጋር እየተናነቅ መስዋዕት የሚከፍል ትውልድ መፈጠሩን ስንመለከት እንባችንን አድርቆ ኢትዮጵያዊ ወኔያችንን ከፍ ያደርግልናል፡፡

Demonstrators chant slogans while flashing the Oromo protest gesture during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Bishoftu town, Oromia region, Ethiopia
ሀያ አምስት አመት ፣ ከጋምቤላ አኝዋክን በመፍጅት ጀምሮ ፣ ቤንሻጉልን ጠርጎ ፣ ኢሉባቡር ቴፒዎችን መሬት ለመንጠቅ ፈጅቶ ፣ አፋርን ትግራይ ለማድረግ እንደለመደው መንጥሮ ዛሬ ደግሞ ማንነቴን ያለውን የጎንደርን ወልቃይቶችን በግድ ትግሬ ካልሆንክ በሚል አይን ያውጣ አሳፋሪ ተግባር ላይ ተሰማርቶ ያለው ወያኔ ፣ የሕዝብ አመጽ በዐራቱም ማእዘን ተቀጣጠለበት፡፡ ከዚህ ቀደም ፣ ያለ ዐዋጅ እንዳልጨፈጨፍ ዛሬ አስቸኳይ ዐዋጅ አወጅኩ ቢል የጦር አዋጅህ ከሞት አያድንህም የሚል መልእክታችንን እናስተላልፍለታለን፡፡ እኛ በጋምቤላ በሁለት ሺ ስድስት ታህሳስ ሶስት በጅምላ የተጨፈጨፉ አኝዋኮችን መታሰቢያ አድርገን ለተቀሩትም ኢትዮጵያኖች አንድ ጠንከር ያለ መልእክት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምናስተላልፈው ፣ ማንም አጋር የሆነን የባእድ መንግስት በአለም ላይ የለንም እና ይህንን የሞት አፋፍ ላይ ያለን የወያኔ አገዛዝ ቀብረን ለመገላገል ያለን አንድ ሀይል በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ኢትዮጵያችንን አድነን ሕዝባችንን ከመጥፋት ታድገን በእኩልነት የተመሰረተች ኢትዮጵያን ስንመሰርት ብቻ ነው፡፡
የተለያዩ ሀይማኖት ልዩ ብሔር እና ቋንቋችንን ጉራማይሌ ቀለማችንን እንደ ውበት ቆጥረን ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው የሕብረት ትግል እኛም እንደ ዜጋ በአንድነት የሚከፈለውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን በሚሰዋው ሕዝባችን  በታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ስም ቃል እንገባለን፡፡ በየስርአቱ የተለያዩ በደሎች ቢኖሩም የበደሉን የየጊዜው ስርአቶች እንጂ ኢትዮጵያ አይደለችም እና የጋራ ሀገራችንን በጋራ እናድን እያልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

↧

የሶሴፑ አሊ ሁሴን የማያቆም የሰበዓዊ መብት ትግል ጀንበሬ

$
0
0

ali

ኦክቶበር 2016

በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ግፍ፣ ጭቆና፣ ባጠቃላይ ስለሰብዓው መብት ጥሰትና ዋልጌነት አጋጣሚው በፈቀደው ቦታና ሰዓት ሁሉ ሳይታክት ለዘመናት እየተሟጎቱ፣ እያጋለጡና ድምጽ አልባ ለሆኑት የሕሊና እስረኞች ሙሉ ድምጽ በመሆን ላይ ያሉት የኢትዮጵያ ፓለቲካ እስረኞች ኮሚቴ ማለትም የሶሴፕ ፕሬዚደንት አቶ አሊ ሁሴ ዛሬም ድንቅ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ። ሶሴፕ ድንበር፣ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ጾታ፣ ፓለቲካ ተጽዕኖ ሳይበግረው የሰብዓዊ መብት ሙግትናውን በየትም ቦታ ለተጨቆነ ሰው ሁሉ መብት መከበር ይታገላል። ለዚህም ነው “በየትኛውም ቦታ የሚሰራ ኢሰብዓዊ ድርጊት በሌላውም አካባቢ ቢሆን ኢሰብዓዊ ድርጊት ከመሆን አያመልጥም”።” – ማለትም በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ብቻ በመኮነን በሌላ አገር ለምሳሌ በኤርትራ ውስጥ የሚካሄደውን ግፍ እንዳላዩ ማለፍ ትክክል አይደለም።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

↧
↧

ሕወሓት በአሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊያሳካ ያሰበው ግልፅ እና ድብቅ ግቦች

$
0
0

ጉዳያችን / Gudayachn
ጥቅምት 7፣2009 ዓም
www.gudayachn.com
=====================

achamየአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ ላይ ከታወጀ ጥቂት ቀናት ውስጥም በሕወሓት ላይ የሚደረገው ተቃውሞ የመቀነስ አዝማምያ አላሳየም።በባህር ዳር የስራ ማቆም አድማ የተደረገው ከአዋጁ በኃላ ነው፣ አሁንም ከአዋጁ በኃላ በሰሜን ጎንደር የትጥቅ ትግሉ ቀጥሏል፣ ባለፈው ዓርብ በጎንደርም የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።ይህ ሁሉ የሚያሳየው የአዋጅ ጋጋታው ያመጣው ለውጥ አለመኖሩን ነው።እርግጥ የኢትዮጵያን ሕዝብ መስዋዕትነትን ሊጨምረው ይችላል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አዋጁ በወጣ በሳምንቱ አዋጁ ምን ምን እንደሚከለክል የመከላከያ ሚኒስትር በሚል ስም ስር በሚገኙ ግለሰብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገልጦለታል።እዚህ ላይ የተከለከሉ እና ያልተከለከሉ የተባሉትን የገዢው ስርዓት መገናኛ ብዙሃን ያሉትን መድገም አያስፈልግም።ባጭሩ አዋጁ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቦች ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር በላይ እንዳይርቁ ተነግሯል።በተጨማሪም መሰረታቸውን ውጭ ያደረጉ የቴሌቭዥን እና የራድዮ ጣብያዎችን ኢሳት እና ኦኤምኤን ጨምሮ መስማት የተከለከለ መሆኑም ተነግሯል።አሁን ጥያቄው ሕወሓት ይህንን አዋጅ ያወጣበት እና እግረ መንገዱን ሊያሳካው ያሰበው ግልፅ እና ድብቅ ግብ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ መመለሱ ነው።
ሕወሓት በአዋጁ ሊያሳካ ያሰበው ግልፅ እና ድብቅ ግቦች
1ኛ/ ግልፅ ግብ
አዋጁ በዋናነት ለሁሉም ግልፅ እንደሆነው የሚታየው ዓላማ የሕወሐትን የስልጣን ዘመን ማራዘም ነው።ይህም የሚቃወሙትን በሙሉ አንገት አስደፍቶ እና አሸማቆ በስልጣን ዘመኑ መቆየት ነው። ማሸማቀቅ እና አንገት ማስደፋት ብቻ አይደለም ጎን ለጎን በፈረሰው የኦህዴድ እና የብአዴን ድርጅቶች ምትክ አዲስ አሽርጋጆች እና መስሎ አዳሪዎችን ወደ መድረኩ እያመጣ የተቀባቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶችንም ይፈጥርበታል።ለእዚህም ነው እንደ ልደቱ አይነቶቹን መድረክ መስጠት የፈለገው።በእዚህ ሂደት ውስጥ ግን መንገዱ አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ በእርግጠኝነት አብዛኛው የሕውሓት አቀንቃኝ ያውቀዋል።ሆኖም ግን ተስፋ መቁረጥ እና ከወንጀል ነፃ ሆኖ ለመኖር እንደ ብቸኛ መፍትሄ የተወሰደው ዛሬ እየገደሉ እና እያሰሩ ነገን በተስፋ መጠበቅ ነው። ይህ ሁኔታ ግን ተቃውሞው እየጠነከረ ሲመጣ እና የበላይነት መያዝ ሲጀምር ለሕወሓት የበለጠ ወደ አዘቅት ብቻ ሳይሆን እርስ በርሱም የመከፋፈል ዕጣ እንደሚገጥመው የሚያጠራጥር አይደለም።
2ኛ/ ድብቅ ግብ
ሕወሓት በአዋጁ ዋናውን እና ግልፅ ግቡን ለማሳካት ከሚሄድበት መንገድ በተጨማሪ ሁለት ድብቅ ግቦችን ማሳካት ያስባል።

አሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደ አካባቢ ስጋት እንዳልሆነ የሚነገረው በትግራይ አካባቢ ነው።በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ከስጋት አልፎ ለበለጠ ትግል መነሳት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ብቸኛ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል።የአዋጁ አፈፃፀም ለምሳሌ የአደጋ ቀጠና ተብለው ከተጠቀሱት መንገዶች ውስጥ አንድም የትግራይ ክልል መንገድ የለም።ይህ ማለት ሕወሓት በአንደኛ ደረጃ ስጋት አለብኝ የሚለው ያውም ተቃዋሚዎች መሽገውባታል የምትባለው ኤርትራ ጋር የሚያዋስን መንገድ ለምን አንዱም ቀይ መስመር አልተባለም? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።ይህ ብቻ አይደለም አዲስ አበባ ዙርያን ለዲፕሎማቶች የስጋት ከተማ አድርጎ ያስቀመጠበት አግባብ እንደተባለው ሕዝባዊ ተቃውሞው የውጭ ሀገር ዜጎችን ኢላማ አድርጎ ነው? ባለፈው በሰበታ መስመር መገደሏ የተገለፀው አሜሪካዊት በእውነት በተቃዋሚ ሕዝብ ነው የተገደለችው? ከእዛ በፊት የሚኒባስ ጥቃት ያውም ተሳፋሪ ባለበት ተደብድቧል? እነኝህ ሁሉ ጥይቄዎች በአግባቡ መመለስ አለባቸው። በሌላ በኩልም መጠየቅ ያለብን ጉዳይ አለ በኦሮምያ እና በአማራ የተቃጠሉት ፋብሪካዎች እና እርሻ ቦታዎች በእውነት ሁሉም በተቃዋሚ ነው የተቃጠሉት? በጎንደር ገበያ ላይ የተፈፀመው እና በኃላም ሌላ የጎንደር ቦታዎችን ልታቃጥል ስትል የተደረስባት ከትግራይ የመጣች ነች የተባለችው ሴት ሰሞኑን ከሚቃጠሉት ቃጠሎዎች አንፃር ምን ይነግረናል? ይህችው ወንጀል ለመስራት ሙከራ ላይ እንደሆነች የተነገረው ሴት በወታደር ታጅባ እጇ ላይ ሰንሰለት ሳይገባ እንድትሄድ የሆነበት ጉዳይስ ምን ያሳየናል?

ከላይ ከተነሱት ጥያቄዎች አንፃር አዋጁ ሊያሳካ የሚያስባቸው ድብቅ አላማዎች እንዳሉት እና እነኝህ ድብቅ አላማዎች ደግሞ ከሕወሐት የረጅም ጊዜ ስልቶች ጋር ሁሉ የተቆራኙ እንደሆኑ መረዳት ይቻላል።በእዚህ አዋጅ ሕወሓት ግልፅ ከሆነው ስልጣኑን ማስጠበቅ በተጨማሪ ሁለት ድብቅ አላማዎች (ግቦች) አሉት። እነርሱም ; –
ሀ/ የመሃል ሃገሩን እና የደቡብ አካባቢን በአዋጁ አማካይነት ሙሉ በሙሉ በመምታት ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መሰረቱን ማናጋት እና የበለጠ ማደህየት።
በእዚህ አዋጅ መሰረት በሕወሓት መዘውር ውስጥ በሚገባ ያልገቡ የንግድ ድርጅቶች በሰበብ አስባቡ እና የሽብርተኛ ታቤላ እይተለጠፈባቸው ይዘጋሉ፣ይወረሳሉ ወይንም ከገበያ እንዲወጡ ይደረጋሉ።
በእዚህም የሕወሓት ሰዎች እንዲቆጣጠሩ ይደረጋሉ።የበለጠ ድሃ እንዲሆን የተደረገው ሕዝብ የበለጠ የእነርሱ ተገዢ እንዲሆን እና አመፁን ዝም ማሰኘት ይቻላል ብለው ያስባሉ።ለእዚህ ነው የሚቃጠሉት ድርጅቶች ሁሉ የሕወሓት ሳይሆኑ እንደ ጎንደር ገበያ ሕወሓት እራሱ የሚያቃጥላቸው ድርጅቶች እንዳሉ ማወቅ ያለብን።

ሌላው የማደህየት ሥራው የሚገልጠው የአዋጁ አስፈፃሚ ኮማንድ ፖስት ስር ያሉ ወታደሮቹ እንዲዘርፉ የውስጥ በጎ ፈቃድ አሳይቷል። ለእዚህም ማስረጃው በአዲስ አበባ በተደረጉ አሰሳዎች የውጭ ምንዛሪ እና ሞባይል ስልኮች መዘረፋቸው እና ወታደሮቹ በግላቸው መውሰዳቸው ነው።ይህ በትንሹ የተጀመረ ሂደት ነገ ኮማንድ ፖስቱ የእገሌ ድርጅት በሽብር ተግባር ሊሰማራ ሲል ተይዞ ድርጅቱ ተወረሰ ሲል እንደምንሰማ መጠራጠር የለብንም።
ለ/ የትግራይን ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ልዕልና በቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሚገባ መስፈኑን ዋስትና ለመስጠት
ሕወሓት ከመነሻው ዋና ግቡ መሃል እና ደቡብ ኢትዮጵያን ከቻለ ለሚገነባው የትግራይ ኢምፓየር በግብዓትነት እንዲያገለግሉ ማድረግ እና የተወሰነ ልማት እያሳዩ የቀረውን ግን ማጋበስ ነው።ይህ የሚሆነው ግን ሕዝብ በተቃውሞ እስካልተነሳበት ድረስ ነው።ሕዝብ በተቃውሞ ከተነሳበት ግን ሊያደርግ የሚያስበው መሃል ሃገሩን እና ደቡብን በብሄር ግጭት እና በምጣኔ ሀብት ቀውስ አተራምሶ ቀጥሎም ማውደም እና የትግራይ ምጣኔ ሀብት የመሳብ (puling role) ወይንም የማዕከላዊ ሚናውን(central role) እንድትጫወት ማድረግ ነው። ይህም የአዲስ አበባን የዋና ከተማነት እና የኢንዱስትሪ ማዕከልነት በተለያየ መንገድ አውድሞ ልማቱ ወደ ትግራይ ማዕከልነት እንዲቀየር ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ የእረጅም ጊዜ ሂደት ነው።ሆኖም ግን የእዚህ አይነቱ ግርግሮች እንደ አንድ አጋጣሚ ሕወሓት ይመለከተዋል እና የእረጅም ጊዜ ሂደቱን ያፋጥናል ብሎ ያስባል።

ባጠቃላይ ሕወሓት በአዋጁ ግልጥ እና ድብቅ ዓላማዎች እንዳሉት መረዳት ይገባል።ብዙ ሕዝብ የሚያወራው ስለ ግልጡ እና የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ነው የሚለውን እንጂ እግረ መንገዱ እየሰራ ያለው የእረጅም ጊዜ ግቡ የተከሰተለት አይመስለኝም።የፖለቲካ መፍትሄዎችን የማይሰጥበት ዋናው ምክንያት ድብቅ አላማውን እንደሚያሳኩለት ስለሚያምን ነው።የጎንደርም ሆነ የኦሮምያ ተቃውሞዎች ከመጀመርያው ፍፁም ሰላማዊ ነበሩ።በጎንደር በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ታሪካዊውን ሰልፍ ሲያደርግ አንዳች ኮሽታ አላሰማም።ነገር ግን ሕወሓት ቀላል መነሻ የነበራቸውን ጉዳዮች እያከረረ እና የህዝቡን ሰላም እየነሳ እዚህ አድርሶታል።በእዚህም የአማራ እና የኦርሞ አካባቢዎች የስጋት ቀጠና አድርጎ ትግራይ ግን ሰላማዊ ቀጠና አድርጎ አቅርቧል።ይህ ማለት አንድ ቱሪስት ጎንደር ከምትጎበኝ መቀሌ ብትሄድ የተሻለ ነው እያለ የሕዝብ ምጣኔ ሀብት እድገትን በማቀጨጭ የእረጅም ጊዜ የእድገት ማዕከልን የመቀየር ሂደቱን ያጧጡፍበታል።በተመሳሳይ መንገድም መሃል ሀገር ያለውን ባለ ሀብት ለ25 አመታት ያህል ከከተማ ይዞታው ከማፈናቀል ጀምሮ ከገበያ እንዲወጣ እያደረገ እና የንግድ መስመሮቹን በሙሉ በእራሱ ሰዎች በማስያዝ የምጣኔ ሀብቱንም ሆነ የማኅበረሰባዊ የበላይነትን ለመቆጣጠር ይጠቀምበታል።

ስለሆነም እንደ ኢትዮጵያዊነት መኖር ካለብን እኩልነት በቅድምያ መምጣት አለበት።ይህ እኩልነት ደግሞ የጥቂቶች (minority ) መንግስት የሆነው የሕወሓት መንግስት ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ እና የሁሉንም ሕዝብ ውክልና ያገኘ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ መመስረት የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው።ከእዚህ ውጭ አዋጁ በእራሱ ከፋሺዝም አዋጅ ያልተለየ እና ከፍተኛ ጦርነት የሚቀሰቅስ አደጋውም በበለጠ ለሕወሓት ህልውና ቆምያለሁ በሚለው ላይ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።ይልቁንም እነኝህ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት የሕወሓት ደጋፊዎች በመጨረሻው መጨረሻ ሰዓት ላይም ሆነው ሊያስቡበት ይገባል።የማይስኬድ መንገድ ለጊዜው የሚያራምድ ይመስላል እንጂ በማንኛውም ሰዓት ይርዳል።ይህ ደግሞ ያለፉት ጥቂት ወራቶችም በሚገባ አስተማሪ ናቸው።

 

↧

ወደ ሰሜን ጎንደር ሽንፋ እየገሰገሰ ያለውን የህወሀት ሰራዊት በተመለከተ ከአከባቢው የነጻነት ሃይሎች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት

$
0
0


ትጥቅ ለማስፈታት ወደ ሰሜን ጎንደር ሽንፋ እየገሰገሰ ያለውን የህወሀት ሰራዊት በተመለከተ ከአከባቢው የነጻነት ሃይሎች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት

↧

አርቲስት ሉሌ አሻጋሪ የመለከት ድራማ ቀረጻ ላይ አደጋ ደረሰባት

$
0
0


አርቲስት ሉሌ አሻጋሪ የመለከት ድራማ ቀረጻ ላይ አደጋ ደረሰባት

↧

Health: አብዝቶ መመገብ የሚያስከትላቸው 3 ጉዳቶች

$
0
0

foods
በምግብ እጦት መጎዳት እና የረሃብ ስሜትን ማስተናገድ መልካም ባይሆንም አብዝቶ መመገብም አግባብ እንዳልሆነ ነው የጤናና ስነ ምግብ ባለሙያዎች የሚያስገነዝቡት፡፡ የረሃብ ስሜትን ከመጥላት አንፃር አብዝቶ መመገብ ለጤነኛ ኑሮ አይመከርምና፡፡ ይህን ማድረጉ የራሱ የሆነ ጉት እንዳለው ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡ ከዚህ አንፃርም የጤና እክል እንደሚያስከትል ያስረዳሉ፡፡
አብዝቶ መመገብ ከሚያስከትላቸው የጤና ጠንቆች

የልብ እና ተያያዥ ችግሮች፡- 
ከፍተኛ የደም ግፊት፣ አላስፈላጊ የስብ እና ቅባት ክምችት መፈጠር እና ድንገተኛ የልብ ምት መቋረጥ ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች ናቸው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አብዝተው ሲመገቡ በርካታ እና ሰውነትዎ ማቃጠል ከሚችለው በላይ የካሎሪ መጠንን ይወስዳሉ፡፡ ይህ መሆኑና ሰውነትዎ በሚ ፈለገው ደረጃ የወሰዱትን ካሎሪ አለመፍጨት ደ ግሞ ከልክ በላይ ውፍረትን ያስከትላል፡፡ ከልክ በላይ ውፍረት ደግሞ ለልብ ጤና ዋናው ጠንቅ ነው፡፡

ለድካም ይዳርጋል፡- ሲመገቡ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከፍ ማለቱና ኃይልን ማበርታቱ አይቀርም፡፡ ይህ የስኳር መጠን ለሰውነት ጡንቻዎች ኃይልን በመስጠት አስፈላጊውን ስራ እንዲሰራ ያስችለዋል፡፡ ምናልባት ደግሞ ኃይል ሰጪ የሆኑ ጣፋጭ ምግቦችንና የተቀነባበሩ የጥራጥሬ ውጤቶችን አብዝቶ ወይም በአንድ ጊዜ መመገቡ ግን የበዛው ምግብ እንዳይፈጭ ያደርገዋል፡፡ ይህም ኃይል ለማግኘት ይጠቅም የነበረውን ንጥረ ምግብ የስኳር መጠንን ከመጠን በላይ በማብዛት ጥቅም ላይ እንዳይውል ያደርገዋል፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ ሰውነት ላይ ከፍተኛ ድካም እና መልፈስፈስ እንዲከሰት ያደርገዋል፡፡

የአጥንት ጥንካሬን ይጎዳል፡- ሰውነት መፍጨት ከሚችለው በላይ መመገብ ጫናው መልሶ ሰውነት ላይ እንዲወድቅ ያደርገዋል፡፡ ያ ማለት ደግሞ ያልተፈጨው ምግብ ለከፍተኛ ውፍረትና ውፍረቱን ለመሸከም የሚኖረው ጫና ደግሞ አጥንት ላይ ይወድቃል፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ አጥንትን አሰባጥረው የሚይዙ መገጣጠሚያ ክፍ ሎችን ከልክ በላይ ጫናውን በማብዛት አጥንት ጥንካሬውን እንዲያጣ ያደርገዋል፡፡በጊዜ ሂደትም የአጥንት ጥንካሬ በዚህ ሳቢያ ይጠፋና ልፍስፍስ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ይህም በጊዜ ሂደት የአጥንት መጉበጥና መሰል ጉዳቶችንም ያስከትላል፡፡ ከዚህ ባለፈም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ፍጥነትን ከመቀነስ ጀምሮ የተገደበ እንቅስቃሴን እስከማድረግ፡፡

ምናልባት ደግሞ ከልክ በላይ መመገብ በሚያስከትለው የሆድ ላይ ጫናም ይሁን አብዝቶ መወፈር እንደ ልብ እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ ስራዎ ላይ ተፅዕኖ ያስከትላል፡፡ ይህም ሌላው ጉዳቱ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ እናም አነስተኛ ወይም ተመጣጣኝ የካሎሪ መጠን በየቀኑ መውሰድ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ በአጠቃላይም ጤነኛ አመጋገብ መከተል ለዚህ ችግር መፍትሄ ነው ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ እርስዎም ቀላሉን መንገድ በመጠቀም ጤንነትዎን ይጠብቁ፡፡

Source: Zehabesha Newspaper
 
 
 
 
 

↧
↧

ኢትዮጵያዊቷ ሞዴል ሕይወት በቀለ ዶናልድ ትራምፕን እናግሬው ነበር በጓደኛዬም ይታማ ነበር አለች

$
0
0


ኢትዮጵያዊቷ ሞዴል ሕይወት በቀለ ዶናልድ ትራምፕን እናግሬው ነበር በጓደኛዬም ይታማል ነበር አለች

↧

በዚህ ሳምንት በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የተገደለውን ወጣት ለመቅበር በሜታ ሮቢ 100,000 ሕዝብ ወጣ | Video

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) በዚህ ሳምንት በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች በግፍ የተገደለውን ቀዘለአ ዳፈርሻ ረጋሳን ለመቅበር 100 ሺህ የሚሆን ሕዝብ በሜታ ሮቢ ወረዳ ወጣ::

በ2007 ዓ.ም በተደረገ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሜታ ሮቢ ወረዳ ውስጥ 140,627 ሰዎች ይኖራሉ:: ይህም ማለት በዛሬው ዕለት ይህን ወጣት ለመቅበርና መንግስትን ለመቃወም የወጣው ሕዝብ ብዛት የወረዳው ሕዝብ ግልብጥ ብሎ ለቀብርና ቁጣውን ለመግለጽ ወጣ ለማለት ያስችላል::

በቭዲዮ ተደግፎ በተለቀቀው መረጃ ለመረዳት እንደተቻለው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቼ ሕዝብን አፍናለሁ ቢልም በሜታ ሮቢ ሕዝቡ የኦነግን እና የሜጫና ቱለማን ባንዲራ ይዞ በመውጣት ለትግራዩ መንግስት ያለውን ጥላቻና አልገዛም ባይነት አሳይቷል::

↧

አቶ አንዳርጋቸውን ጽጌን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ ሬፕሪቭ የተሰኘው ተቋም ገለጸ

$
0
0

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ደህንነት አድጋ ውስጥ እንደከተተ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሰኞ አስታወቀ።

andargachew new picture
መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው ሪፕሪቭ ተቋም የሃገሪቱ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ጉዳይ ግምት ውስጥ በመክተት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲያመቻችና ይፋዊ ጥያቄን እንዲያቀርብ አስቧል።
በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት ተቃዋሚ ናቸው ባላቸው አካላት ላይ የሚወደውን እርምጃ ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሃላፊ ማያ ፎዓ (FOA) ገልጸዋል።
ዜጋውን ለማስፈራት የተለሳለሰ አቋም ይዟል የሚል ትችት የሚቀርብበት የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ግምት ውስጥ በመክተት ዜጋውን ለማስለቀቅ አፋጣኝ ጥያቄን ማቅረብ እንደሚገባው ሃላፊዋ አስታውቀዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው ይኸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ወር የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች ለአቶ አንዳርጋቸው መጻፊያ እስክርቢቶና ወረቀት እንዳይገባላቸው እገዳ መጣላቸውን አውስተዋል።
በዚህም የተነሳ አቶ አንዳርጋቸው የህግ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማቅረብ ያልቻሉ ሲሆን፣ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ የብሪታኒያ መንግስት በኩል አቶ አንዳርጋቸው የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።
ሁለቱ ሃገራት ባልፈው አመት ሰኔ ወር በጉዳዩ ዙሪያ ስምምነትን ቢያደርጉም የኢትዮጵያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይግባኝ ለማቅረብ እንደማይችሉ ለብሪታኒያ መንግስት ማሳወቁን ሪፕሪቭ ማግኘት የቻለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
ጉዳዩ አሳስቦት እንደሚገኝ የገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የብሪታኒያ መንግስት የችግሩ አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በመግባት አፋጣኝ እርምጃን እንዲወስድ አክሎ ጠይቋል።

↧

በትግራዋይነታቸው ብቻ ተሹመው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደርን የሚዘውሩት 17 የትግራይ ተወላጆች ስም ዝርዝር

$
0
0

eliasየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት? [ ክፍል ፫]

ከአቻምየለህ ታምሩ

ከስድስት ቀን በፊት ማለትም እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2016 አ.ም. «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት?» በሚል ርዕስ ሙሰኛው «ፓትሪያርክ» «አቡነ» ማቲያስ ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዴት እንደሞሏትና የተሾሙት ዘራፊዎች የቤተክርስቲኗን አንጡራ እንዴት እንደገፈፏት የሚያሳይና በመረጃ የዋጀ ጥንቅር በሁለት ክፍል አቅርቤ ነበር። ቀጣዩና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን እንደሆነች የሚያሳየው ሶስተኛው ክፍል እነሆ።

ከታች የለጠፍሁት ዶሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር በነማን እንደተያዘ የሚያሳይ ሰነድ ነው። ልበ በሉ የቤተ ክርስቲያኗ መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር ማለት አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኗን የአገር ውስጥና የውጭ አገር አስተዳደር የሚቆጣጥር ነው።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደርን የሚዘውሩት የሚከተሉት የአባ ማቲያስ ሹሞች ናቸው፤
1. መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም — ትግሬ
መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም ታጋይ የነበረ ሰው ነው። ሰውየው በቅጽል ስሙ የቤተ ክህነቱ ስብሃት ነጋ በመባል ይታወቃል። መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም ወያኔ ትግራይን ሲቆጣጠር የትግራይ ቤተ ክህነት ሥራ ስኪያጅ የነበሩት ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ትግራይን ለቀው ሲወጡ ወያኔ የትግራይ ቤተ ክህነት ሥራ ስኪያጅ አድርጎ የሾመው ሰው ነው። ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ደግሞ አብሮ አዲስ አበባ በመግባት አዲስ አበባ ተሹሟል። ከዚያም ደግሞ ድሬዳዋ የተሾመ ሲሆን የተወረሱ የቤተ ክህነት ቤቶችን በማስመለስ ሰበብ በብዙ ቤችች ሙስና የሚታወቅ ዘራፊ ነው። ይህ ሰው አሁን የቤተክነቱ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ነው።
2. እስክንድር ገብረ ክርስቶስ — ትግሬ
እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የህወሀት ተመራጭ የነበረ ዋና ፖለቲከኛ ሲሆን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት አስተዳደር ዕቅድና ልማት መምሪያ ኃላፊ ነው።
3. አባ ሰረቀ ወልደሳሙኤል– ትግሬ
አባ ሰረቀ ወልደሳሙኤል አቡነ መርቆሪዎስን በማውረድ ሂደት ትልቅ ሚና የነበረው ሲሆን ወያኔ አዲስ አበባ ሳይገባ ከወያኔ ጋር መሳርያ ይዞ ይታገል የነበረ ታጋይ ሲሆን በኋላ ግን ቤተ ክህነት ውስጥ ገብቶ ትልቁን የፖለቲከኛነት ሚና የሚጫወት ሰው ነው። አባ ሰረቀ ወልደሳሙኤል የሚንቀሳቀሰው በዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ነው።
4. ዮሃንስ ኤልያስ – ትግሬ
ዮሃንስ ኤልያስ ትግሬ በመሆኑ ከመዝገብ ቤት ወደ አስተዳደር መምሪያ የተሾመ ሰው ነው።
5. እንቁ ባህርይ መለስ— ትግሬ
6. ሐዋዘብርሃን ጫኔ— ትግሬ
7. ዳን ኤል ወልደገሪማ—-ትግሬ
8. ተስፋጊዮርጊስ ኃይሉ —ትግሬ
9. አባ ገብረ ማርያም ትግራይ
10. መሀሪ ኃይሉ —ትግሬ
11. መኩርያ ደሳለኝ — ትግሬ
12. ሽመልስ ቸርነት — ኦሮሞ
13. አባ ኃይከማርያም – አማራ
14. ሰሎሞን ቶልቻ — ኦሮሞ
15. ሳሙኤል እሸቱ – ትግሬ
16. ብርሃኑ ካሳ—- ትግሬ
17. ኤርምያስ ተድላ —- ትግሬ
.
.
.
የወያኔዋ ኢትዮጵያ በመንፈሳዊነትም የከሰረች አገር ሆናለች። ከዚህ የጉድ ዘመን በፊት ግን ኢትዮጵያ ብዙ ጀግና መነኮሳት፣ ካህናትንና ቄሶችን አፍርታ ነበር። የሞራልና የመንፈሳዊነት ደረጃቸው ወደር የማይገኝላቸው አባቶች ተገፍተው የሀይማኖት ካባ የለበሱ የትግራይ ሽፍቶች በቤተ ክርስቲያኗ ነገሱና ቤተ ክርስቲያኗን የሽፍቶች መዲና አደረጓት።
ይቀጥላል!

↧
↧

በሃገር ቤት እየተቀጣጠለ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል እየመራ ያለው ማን ነው? ጀዋር ወይስ ዳዑድ? |ይህ የድምጽ ዘገባ ምላሽ አለው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አንደኛ ዓመቱን ሊደፍን ያለውን የኦሮሞ ሕዝብን ትግል በሃገር ቤት ወጣቶችን (ቄሮዎችን) በማደራጀት እየመራነው ያለነው እኛ ነን ሲሉ አቶ ዳዑድ ኢብሳ ለሰይፈነበልባል ራድዮ የሰጡትን ቃለምልልስ ዘ-ሐበሻ ጠቅሳ ዘግባ ነበር:: የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛዋ ጽዮን ግርማም ይህን ተከትላ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተርን አክቲቭስት ጀዋር መሐመድ “የኦሮሞን ሕዝብ እንቅስቃሴ እየመራው ያለው ማን ነው?” ስትል ጠይቃው ነበር:: በዚህ ቃለምልልስ የዳዑድ ኢብሳውን ኦነግ ሌላ አመራርም አካታለች:: ተከታዩ ዘገባ አሁን በሃገር ቤት እየተቀጣጠለ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል እየመራ ያለው ማን ነው? ለሚለው ምላሽ ይሰጣችኋል – ያድምጡት::

↧

ጎንደር የሥራ ማቆም አድማ ተጀመረ |ከተማዋ ጭር ብላለች

$
0
0

gonder
(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለሁና ካሁን በኋላ መስብሰብም ሆነ አድማ ማድረግ አይቻልም እያለ በተደጋጋሚ በቲቭና ራድዮ እንዲሁም የሚያዛቸው ድረገጾች አማካኝነት እየለፈለፈ ቢሆንም የአማራውና የኦሮሞ ሕዝብ ግን አሁንም አልገዛም ባይነቱ ላይ ቀጥሎበታል::

ትናንት በሜታ ሮቤ የተደረገውን እና ከ100 ሺህ ሕዝብ በላይ የወጣበትን ሰላማዊ ተቃውሞ ዘ-ሐበሻ የዘገበች ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ጎንደር የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ማስፈራሪያ ወደ ኋላ ጥላ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማዋን ጀምራለች::

በጎንደር ከተማ እየተደረገ ባለው የሥራ ማቆም አድማ ትራንስፖርት የቆመ ሲሆን ንግድ ቤቶችም ተዘጋግተዋል:: አንዳንድ የባጃጅ እና የታክሲ ሹፌሮች የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስትን መልካም ገጽታ ለመግንባት ሥራ ወጥተው የነበረ ቢሆንም በሕዝብ ማስጠንቀቂያ ለማቆም ተገደዋል::

በጎንደር ሕዝብ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ የተነሳ ከተማዋ ጭር ያለች ሲሆን በአደባባዩ የሚታዩት የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ብቻ መሆናቸውን ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቁሟል::

↧

በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የሚንገኝ የወላይታ ተወላጆች በወቅታዊ የሀገራችን አሳሳቢ ጉዳዮችን አስመልክተን የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ቀን ጥቅምት 6, 2008     ኦክቶበር 16, 2016

welyta-satenaw-news

እናት አገራችን ኢትዬጵያ የበርካታ ህዝቦች መኖርያ የሆነች ጠንካራ ሃይማኖቶች፤ ጥንታዊ ቅርሶችና፤የበለጸገ ታሪክ ያላት፤ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ናት። በኢትዮጵያችን ከሚኖሩ ህዝቦች አንዱ የሆነዉ የወላይታ ህዝብ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲሁም ለህዝቦች የጋራ መኖር ከፍተኛ አስተዋኦ ሲያደርግ የቆየ በደቡብ የሃገራችን ክፍል ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ህዝቦች አንዱ ነው። ከታሪክ እንደምንረዳው ወላይታ የሚለዉ የብሄረሰብ መጠርያ በወላይትኛ ቋንቋ “ወላሄታ” ወይም በአማርኛ “የተቀላቀለ” ከሚለዉ ቃል የተገኘ ሲሆን ይህም የወላይታ ህዝብ አንድ ዘዉግ ወይም የዘር ግንድ ሳይሆን ከኦሮሞ፤ ከአማራ፤ ከጋሞ፤ ከዳዉሮ፤ ከትግራይ፤ ከሃድያ፤ ከሲዳማ፤ ከአፋር፤ ከሶማሌና፤ ከተለያዩ አካባቢዎች በንግድ፤ በጦርነት፤ በጋብቻ፤ በስደት፤ ወዘተ የመጡ ሰዎች አካባቢዉን በለምነቱና ለኑሮ አመቺ በመሆኑ መርጠዉ ቀደም ሲል በስፍራዉ ይኖሩ ከነበሩ ሰዎች (natives) ጋር ተዋህደዉና ተዋልደዉ በአንድ ወላይትኛ ቋንቋ ተጠቅመው ጠንካራ ባህል ገንብተው የራሳቸዉን ንጉስ ተጠቅመው ቤተ መንግስት፤ የጦር ሃይል፤ የፍርድ ስርዓት፤ የመገበያያ ገንዝብ ፈጥረው ለብዙ ዘመናት የኖሩበት አካባቢ ነዉ።

በጥንታዊት በኢትዬጵያ አንዱን ንጉስ ሌላውን ንጉስ ለማስገበር አንደኛው መንገድ ጦርነት በመሆኑ በወቅቱ አፄ ምኒሊክ ማዕከላዊ መንግሥት ለመመስረት በነበራቸው ህልምና ምኞት ለማዕከላዊ መንግሥት  በሰላም አንገብርም ያሉትን በጦርነት ማስገበራቸው ይታወቃል ። በሄሆኑም የወላይታን ህዝብ ለማስገበር ጦርነት ከከፈቱ በኋላ በወቅቱ የወላይታ ንጉስ በነበሩት ንጉሥ ጦና የሚመራ የወላይታ ጦር 6 ጊዜ የሚኒሊክን ጦር አሸንፎ አባረረ። በዚህ ሽንፈት የተናደዱት አፄ ሚኒሊክ ራሳቸው ጦራቸዉን አጠናክረው በራስ አሉላ አባነጋ አዝማችነት ለ 7ኛ ግዜ ከወላይታ ህዝብ ጋር ተዋግተዉ በማሸነፍ ነጉስ ጦናን ማርከዉ የወላይታን ህዝብ ለማእከላዊ መንግስት አስገብረዋል። ጦርነቱ በህዝቡ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ከመሆኑ በላይ ሃብትና ንብረቱን ዘርፈዉ በአፄ ሚኒሊክ ፈቃድ የጦር ምርኮኞችንና ጉልበት ያላቸዉን ማንኛዉንም የወላይታ ተወላጆች ሠራዊታቸው የዘረፈዉን ንብረት አሸክመው እንዲወስዷቸው ተደረገ። በዚህም ሁኔታ በርካታ ወላይታዎች በመላዉ ኢትዮጵያ እንዲብትኑ ተደርጓል።ለመጥቀስም ያክል አዲስ አበባ ሲቆረቆር ከነበረዉ ነዋሪ ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የወላይታ ተወላጆች ነበሩ ። በደሴና አንዳንድ የኢትዮጵያ ከተሞችም የወላይታ ሰፈር እየተባሉ የሚጠሩት በጦርነቱ ተማርከዉ የተወሰዱት የወላይታ ተወላጆች ይኖሩበት የነበሩባቸዉ ሠፈሮች መጠርያዎች ናቸዉ።

አፄ ምኒሊክ ንጉስ ጦናን ማርከዉ ከወሰዱ ብኋላ የክርስትናን ሀይማኖት እንዲቀበሉ በማድረግ በመጥመቅና የክርስትና ስም በመስጠት ከእሳችዉ በፊት የወላይታ ነጉስ የነበሩት አማዶ ያገዱትን  የክርስትና እምነት ወደ ወላይታ እንዲገባየልዑላን ቤተሰብ የነበረችዉን “ሸዋንግዬ” የተባለችዉን ሴት ለንጉስ ጦና በመዳር የወላይታ ባላባት እንዲሆኑ መልሰዉ ልከዋቸዋል። የወላይታ ህዝብም ንጉሥ ጦናን ከተቀበለ በኋላ እንደሚስት ሆና አንድ ላይ የተላክችዉን ሴት “ሸንገቴ” ብለዉ ይጠሯት ነበር። የወላይታ ህዝብም የጣልያንን ወረራ ለመመከት በአድዋ ጦርነትንና  በግንባር ቀደምትነት በአዝማችነትና ዘማችነት ተዋግቷል ፣ የወላይታ ህዝብ በተለያዩ ወቅቶች ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሃገራችንን ሲወሩ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ተዋድቋል። በቅርቡ ኢሃዴግ ደርግን አሸንፎ የኢትዮጵያ ሰራዊትን ሲበትን በተካሄደዉ የቀድሞ ሠራዊት ምዝገባ የት እንደገቡ ያልታወቁትንና በጦርነቱ የተሰዉትን ሳይጨምር በቀይ መስቀል የተመዘገቡት ከተራ ወታደር እስከ ከፍተኛ መኮንን 75ሺህ የወላይታ ልጆች በመከላከያ ሠራዊትነት የኢትዮጰያን አንድነትና ዳር ድንበር ሲያስክበሩ ቆይተዋል። በቅርቡም ህወአት/ በኢሃዴግና በሻቢያ መካከል በተካሄደዉ ዉጤት አልባ የባድሜ ጦርነት ከ 10ሺህ በላይ የወላይታ ልጆች ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር በመሆን ትዋግተዋል።

የዛሬ ሃምሳ በዓመት ገደማ ለለም መሬትና ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከጎንደር ፣ ጎጃም ፣ ከሸዋና ወሎ አካባቢዎች የመጡ ወገኖቻችን ወላይታ ውስጥ በአባያ ኃይቅ ዳርቻ አበላ በምትባል ለም አካባቢ ሰፍረው እዝያው ወልደው ፣ ተጋብተውና ከብረው ሃብትም አፍርተው ቋንቃውንም ለምደውና የራሳቸውንም ነዋሪውን አስለምደው እስከዛሬም ተባዝተው መኖራቸውና እንደዚሁም በሥራ ዝውውር የመጡ በርካታዎች ሁሉ ህዝቡንና አገሩንም በመውደድ ቤታቸው ማድረጋቸው የወላይታ ህዝብ ለኢትዬጵያዊነት ትስስርና አብሮነት ተምሳሌት  ስለመሆኑ ጥሩ ማሳያ ነው።

ዛሬም ታሪኩን አስከብሮ  ለዓመታት የተነዛውን የዘረኝነት አባዜ በመዋጋት ከሁሉም ወገኖቹ ጋር በትስስርና በፍቅርእንደሚቀጥል ሙሉ እምነታችንን ነው።

ከላይ ያስቀመጥነዉ የወላይታ ህዝብ ታሪክ የመጥፎም ሆነ የጥሩ የኢትዮጵያ ታሪክ አንዱ አካል መሆኑንና ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የአክሱም ሀዉልት ለወላይታ ምኑ ነው ብለዉ የተናገሩት ለወላይታ ህዝብ ከፍተኛ ስድብ መሆኑን ለመጥቀስም ጭምር ነው።

፩  በወያኔ አኢሃዴግ የሚመራው በወላይታው የኢሃዴግ ክንፍ “ወህዴድ” በወላይታ ህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍና በደል

1ኛ) 1985 በአረካ ገበያ ላይ ተኩስ በመክፈትና የእጅ ቦንብ በመወርወር ከ 100 በላይ ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ አካለ ስንኩል ሆነዋል። ይህም ሆኖ ወያኔ ወንጀለኞችንና ገዳዮችን ፈጥኖ ከአካባቢው እንዲሰወሩ በማድረግ ለሞቱትም ሆን ለቆሰሉ ተጠያቂ ሳይኖር በዋዛ ቀርቷል፤

2ኛ) በ 1991 ወጋጎዳ የተባለ በ 4 ቋንቋዎች የተዳቀለ አዲስ ቋንቋ በመፍጠር በሰላም ይማር የነበረዉን ተማሪና ወላጅ በማሸበር ከአጎራባች ጋሞና ጎፋ ህዝቦች ጋር ከማጋጨቱም በላይ በከፍተኛ የመንግስት ወጪ መጽሃፍ በማሳተም ህዝቡ በግድ አዲስ ቋንቋ እንዲማር ጫና በመፍጠሩ የወላይታ ህዝብ እምቢ በማለትና የዞን መስተዳድር ደረጃ ለመጠየቅ ሰልፍ በመውጣቱ የአጋዚ ጦር ታዞ የወላይታ አውራጃ ዋና ከተማ የሆነችዉን ሶዶ አፍንጫው በታጠቀ ሰራዊት በመክበብ የወላይታን ህዝብ ጨፍጭፏል፤ መምህራንና ሠራተኞች ከስራቸዉ አፈናቅሏል። ጉዳዩን እንዲከታተሉ በህዝብ የተመረጡትን ሽማግሌዎች በደህንነት በማደን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅሏል። የጉዳዪ ጠንሳሾች ናቸዉ ያላቸዉን አስሮ ከፍተኛ ቶርቸር በማድረግና በማሰቃየት በሽተኛ ሆነዉ እንዲሞቱ አድርጓል። የዞን ጥያቄ አቀራቢና የወላይታ ነጻነት ታጋይ አቶ ሰለሞን ሴታ ሲሆን በእስር ተሰቃይቶ ሞቷል። 12 ግለሰቦችም በአጋዚ ወታደሮች ጥይት ተገድለዋል። በርካታ ግለሰቦችም አካለ ስንኩል ሆነዋል። የዚህ ወንጀል ፈጻሚዎችና መመሪያ አስተላላፊዎች እስከ ዛሬ ድረስ በወላይታ ህዝብ ተወካይ ነን በማለት በወያኔ የስልጣን ኮርቻ ላይ ተቆናጠው ይገኛሉ።

3ኛ) በ 1997 ምርጫ ሰፊዉ የወላይታ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን በከፍተኛ ድምጽ ከመረጠ በኋላ በሶዶ በቦዲቲ፤ በሁምቦ፤ በባዴሳ ፤ በጋሱባ ፤ በአረካ ፤ በባሌ ከተማና በአንዳንድ ቀበሌዎች የአሸናፊዎች ስምና የቆጠራ ዉጤት ከተለጠፈ በኋላ በወቅቱ የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከአቶ መለስና በረከት ስምኦን በተሰጣቸዉ ትዕዛዝ በሌሊት በመላዉ ወላይታ ካድሬዎችን ከፍተኛ አበል ከፍለዉ በመንግስት ተሽከርካሪ በማሰማራት የወላይታ ህዝብ ድምጽ እንዲሰረቅና ኮሮጆ ተገልብጦ ኢህአዴግ እንዳሸነፈ ተደርጎ በህዝቡ ያልተመረጡ ግለሰቦች ሥልጣን በሌብነት እንዲይዙ ተደርጓል።  እነዚህ የዉሸት ባለስልጣኖች የወላይታ ህዝብ በጥቂቱም ቢሆን ብሶቱን እንዳይተነፍስ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ቢሮዎች በማሸግ አመረሮችን በማሰር የኑሮ ዋስትናቸዉን በማሳጣት ንብረታቸዉን በመቀማት እየተከታተሉ በማሳደድ አጥፍተዉ ለብቻቸዉ የወላይታን ፖለቲካ ጠቀልለዉ ይዘዋል።

  • በአሁኑሰአትወላይታዉስጥየኢህአዴግአባልወይምጆሮጠቢያልሆነግለሰብተምሮሥራአያገኝም፤ነግዶወደፊትእንዳይወጣይደረጋል፤አርሶበነጻነትእንዳይኖርበካድሬዎችጫናይደርስበታል።
  • ወላይታከፍተኛየህዝብብዛትያለበትናየመሬትጥበትያለበትመሆኑእየታውቀየገበሬዉይዞታለከተማመስፋፋትእየተባለአለበቂካሳክፍያይወሰዳል።በገጠርደግሞታዳጊማዘጋጃቤትእየተባለየገበሬዉመሬትይነጠቃል።የመሬትነጠቃዉንየተቃወሙግለሰቦችይታሰራሉይደበደባሉይባረራሉ።
  • የአርሶአደሩንመሬትበGPS እየለኩከአቅምበላይየሆነግብርበመጫንመክፈልካልቻለመሬቱንይነጥቃሉ።
  • ለገበሬዉበኮታማዳበሪያበማደልበአንድኩንታልክ 1 ሺህእስክ 2 ሺህበመተመንመክፈልካልቻለከብቱንነጥቀዉወደገበያበመዉሰድሸጠዉገንዘቡንለማዳበርያክፍያያዉላሉ።
  • በከተማዉነጋዴላይከአቀምበላይየሆነግብርበመጫንነግዶእንዳይበላያፈናቅላሉ፤ግብሩምእጅግየተጋነነነዉብሎየተናገረነጋዴየንግድፈቃዱተቀምቶቤቱይታሸጋል።
  • የከተማመሬትበከፍተኛዋጋበሊዝዝስለሚሸጥየመንግስትሠራተኞችምሆንአነስተኛኑሮያለዉዜጋየቤትባለቤትመሆንአቅቶአቸዋል።
  • በሌላዉየኢትዮጵያእንደሚፈጸመዉሁሉየወላይታህዝብበኑሮዉድነት፤በመኖርያቤትችግር፤በዉሃናበመብራትእጦት፤በመሬትዘረፋናንጥቅያ፤በኢህአዴግ“ወህዴድ”የፖለቲካጫናበድሮጉልተኛሥርዓትከደረሰበትጭቆናበላይወያኔበመደባቸዉየራሱንቋንቋበሚናገሩሆዳሞችታፍኖይገኛል።በሌላበኩልየወያኔጆሮጠቢዋችመዋቅርዘርግተዉህዝብንናመንግስትንበመዝረፍሰባዊመብቱንረግጠውናአፍነውይገዛሉ።

፪ በመላዉ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለዉ የህዝብ ንቅናቄና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምንስቴር ምላሽ በተመለከተ

አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከወላይታ ህዝብ ከመልካም ቤተሰብ የተወለዱ፤ በጥሩ ሥነምግባር ያድጉ፡ ከፍተኛ የቀለም ትምህርት የቀሰሙና ወጣት ሲቪል ፖለቲከኛ በመሆናቸው ህወሃት በጠቀላይ ሚኒስትርነት ሲመድባቸዉ ኢትዮጵያዉያን ወደተሻለ ዴሞክራሲ፤ የጋራ መግባባት ያለዉ የሰከነ ፖለቲካ፤ የህግ የበላይነት ያሰፍናሉ፤ የሰዉን ሰብአዊ መብት ያስከብራሉ፤ የህዝብን እምባ የሚያብስ ፖለቲካ ሥርዓት ያመጣሉ የሚል ተስፋ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደጣለባቸዉ እኛም የወላይታ ተወላጆች አንዳዶቻችን በግል ጓደኝነት ሌሎቻችን በአካባቢ ልጅነትና በትምህርትና በስራ አጋጣሚ ስለምናዉቃቸዉ ተደስተን ነበር። ሆኖም ቤተ መንግስት እንደገቡ ሙሉ በሙሉ ለህወሃት እጃችዉን ሰጥተዉ ህሊናቸውን ሸጠዉ የሟቹን ጠ/ሚኒስትር ራዕይ አሳካለሁ ማለት ጀመሩ።

የመጀመሪያዉ 2 የስልጣን ዘመን የዉከልና ነዉና ይሻሻላል በሚል ሲጠበቁ የመለስ ራዕይ የሚሉትን እንደ እግዚአብሄር ቃል ሙጭጭ አድርገዉ በመያዝ የመለስን የምርጫ ማጭበርበር፤ የተቃዋሚ ፓርቲ አፈና እስርና ግድያ፤ የጋዜጠኞች እስርና ስደት ደረጃዉን ከፍ አደረጉት። ኮሮጆ እየሰረቁም ቢሆን በመለስ ዜናዊ 10% ከዚያም አንድ ለእናቱ በሚል የሚታወቀዉን የፓርላማ ወንበር ጨፍልቀዉ ፓርላማዉን 100% ተቆጣጠሩት። በአረካ ከእርሳቸዉ ጋር የተወዳደሩትን እዉቁን ነጋዴ በካድሬዎቻቸዉ አማካኝነት የተቃዋሚ ደጋፊዎች የምረጡኝ ዘመቻቸውን በነፃነት እንዳያካሂድ በማዋከብና በማስፈራራት አሰናክለው ምንም ህፍረት ሳይሰማቸዉ 100 ለ 0 አሸነፍኩ አሉ። የህወሃትን የከፋፍለህ ግዛ ተልኮ ለመፈጸም በደቡብ የወላይታን ብሄረሰብ ከሲዳማ ጋር ለማጋጨት ከብላቴ ወንዝ ማዶ የነበረዉን የሲዳማ መሬት ብላቴን አሻግረዉ የወላይታ መሬት ለሲዳማ እንዲሰጥ በማድረግ ሁከት እንዲፈጠር አመቻችተዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉት የኦሮሚያ ህዝቦች፤ የመብት ጥያቄ ባነሱ የዓማራ ህዝቦች እንዲሁም በኮንሶ፤ በቁጫ፤ በአርባ ምንጭ፤ በቤኒሻንጉል፤ በጋምቤላና በቴፒ ወዘተ የተነሱትን የተነሱትን ጥያቄዎች የጥይት ምላሽ እንዲሰጥ የዉጭ ወራሪ ሃይል ባልተነሳበት ሁኔታ የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንዲውስድ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

የመሬት ባለቤትነት ቢረጋገጥ ገበሬዉ መሬቱን ሸጦ ወደ ከተማ ይፈልሳል የሚለዉን የህወሃት ፕሮፓጋንዳ ፍጽም መሠረት የሌለው መሆኑን እየጠቆምን ለመረጃም ያህል  በደርግ ዘመን መሰረታዊ የተማሪው ጥያቄ የነበረው የመሬት  ላራሹ ምላሽ በማግኘቱ ሠፊው ህዝብ ከመሬት ጭሰኝነት ተላቆ የመሬት በለቤትነት በሚገባ ተረጋግጦ ነበር ። ታድያ   ህወአት /ኢህአደግን የምናሳስበው የኢትዬጵያ አርሶ አደር መሬቱን ያለማል ለልጅ ልጅ ያወርሳል ፣ ህይወቱና የኑሮ ዋስትናው መሆኑን በማወቅ ይንከባከባል እንጁ በቀላሉ አይሸጥም ለምሳሌም ወላይታን ብንመለከት ሄምቤቾ ፤ የአድማንቾ ፤ የወይቦ ቀበሌ ገበሬዎች መሬታቸዉን ሸጠዉ አረካ ወርደዉ ነበር? የኦፋ ሴሬ፤ የዋጃ ቄሮ ፤የኮካቴና ሌሎችም አካባቢ  የሚኖረውረው  ገበሬ  መሬቱን ሸጦ ሶዶ ከተማ ወርዶ ነበር ? ገበሬዉ ቢቸገር እንኳን ዘመዱን ወይም ቅርብ ጓደኛዉን ፈልጎ ለአንድ ወይም ሁለት ዓመት ኮንትራት ይሰጣል ። የወላይታ ቀበሌዎችን እንደምሳሌ  አነሳን እንጂ የትም ቦታ ገበሬዉ የኑሮ ዋስትና የሆነዉን መሬት በቀላሉ አይሸጥም። ይህ እኛ እናዉቅልሃልን የሚሉ የህወሃት ፖለቲከኞች የኢትዮጵያን መሬት ተቀራምተዉ ለዘመድ አዝማድ በማከፋፈል በአቋራጭ ለመክበር ያወጡት ዘዴና አርሶ አደሩን አሳንሶ ማየት ነዉ። ከዛሬ 45 ዓመት በፊት  የወላይታ ተወላጅ የነበረዉ በወቅቱ ከቀዳማዊ ኃይለሥላስሴ ዩንበርስቲ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ጀግናዉ ሰለሞን ዋዳ ከዩንበርሲትው በሰርቢስ አገልግሎት ወይላታ ተመድቦ በዚሁ ህይወቱን የሰዋዉ መሬት ላራሹ የሚል መፈክር አንግቦ ነዉ። በታሪክ አጋጣሚ ከወላይታ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት በተቃራኑው የኢትዬጵያ ህዝብ እስትንፋሱና መሰረታዊ ጥያቄው የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ መሆኑን በመረዳት ከሰፊው ህዝብ ጎን መቆም ተስኗቸዋል ።

የኢትዮጵያ ህዝብ አንኳር ጥያቄ የአንድ ብሄር የበላይነት ይቁም ሲሆን እርስዎ ግን የብሄር የበላይነት የለም ይሞግታሉ ! በማሳያነትም በአጭሩ ቢገለጽ  የመከላከያ ኢንጂኔሪንግን የሰዉ ሀይል ብንወስድ ከዘበኛ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለስልጣን ቢመለከቱ  ከትግራይ አንድም ሰዉ የቀረ አይመስልም። የደህንነት መስርያ ቤትንና ማዕከላዊ ምርመራን ገራፊዉ፤ አሳሪዉ፤ አዛዡ ሲቪል ልብስ ለብሰዉ በየመንገዱ ዜጎችን አፍኖ ወዳልታወቀ ስፍራ ወሳጁ ከእርስዎ አጃቢዎች ጀምሮ እስኪ አስተውሉ! የኢትዬጵያ አየር መንገድ 80% ሠራተኞችስ? ቴሌኮም ፣ የኢትዬጵያ ቴለብዥንና ራድዬስ ?

በሌላ በኩል በየፕሮጀክቶች ተቋራጭ የሆኑት፤ ዕቃ አቅራቢዎችና የመጓጓዣ ከባድ መኪና በለ ንብረቶች በሙሉ የአንድ ብሄር ተወላጆች አይደለምን? ለምሳሌ የወይጦ ስኳር ፋብሪካን እናንሳ አንድ የትግራይ ተወላጅ ግለሰብ እስከ 100 ከባድ መኪና ወይም ሎው ቤድ አለዉ። ይህ ከየት እንደመጣ ያጣራ ከፍል አለን?  ከጀቡቲ ወደብ መሃል አገር የኮንስትራክሽን ዕቃ የሚያመላልሱ የማን ተሽከርካሪዎች የማናቸው? አዲስ አበባ ካሉት ከፍተኛ ፎቆች አብዛኛዎቹ የህውሃት በለሥልጣንና ዘመድ አዝማዶቻቸው እንዲሁም በጋብቻና በአምቻ የተገናኙ ግለሰቦች ሀብት መሆናችው አይታወቅምን? ይህ ነው ይህች ሃገር የማን ናት አስብሎ የዜጎች እኩልነት የለም የሚያሰኘን። ከዚህም በላይ ኢህአዴግ እራሱ በየጊዜዉ በሚያካሂደዉ የምክር ቤትም ሆነ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባዎች ስለመልካም አስተዳደር እጦት ስለ ኪራይ ሰብሳቢነት ያነሳል ብልሹ አሰራረም እንዳለ በየመግለጫዎ በተደጋጋሚ ያስቀምጣል።

ኪራይ ሰብሳቢነት ችግር እንደሆነና ለመታገል አቅጣጫ ተቀምጧል ሲባል ቆይቷል። ሆኖም እየተሻሻለ ሳይሆን እየባስ ሄዷል። ኢሃዴግ ቁልፍ ችግር እንጂ ቁልፍ መፍትሄ ለኢትዬጵያ ህዝብ አልፈጠረም። ለህዝባችን ጥያቄ  ቁልፉ መፍትሄ 1ኛ) የመሬት ባለቤትነትና ንብረት ማፍራት 2ኛ) ነጻ ፕሬስ፤ 3ኛ) ነጻ ምርጫ፤ 4ኛ) የህግ የበላይነት፤ 5ኛ) በሰላማዊ ሰልፍም ሆን በተለያዩ መድረኮች ያለመሸማቀቅ ሃሳብን በነፃ መግለጽ  6ኛ) ከተቃዋሚ ፓለቲካ ድርጅቶች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መነጋገርና ፖለቲካ ምህዳሩንም ማስፋት፤ 7ኛ) የመንግስ ባለስልጣናትና የፖልቲካ ድርጅት አመራርና አሰራርን መለየት፤ 8ኛ) በአገሪቱ መተማመንን ለመፍጠር ሁሉንም የፓለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት ሌሎችን ማሸማቀቅና ማሰርን ማቆም።

፫) ዉድ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ በሆነ መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗን በመገንዘብ ካላይ ያስቀመጥናቸዉን ሁኔታዎች በጥልቀት አይተን የሚከተለዉን የአቋም መግለጫ አዉጥተናል።

1ኛ) ከአንደኛ  ደረጃ ጀምሮ በታሪክና በጂኦግራፊ ስንማር ወልቃይት ጠገዴ የጎንደር እንጂ የትግራይ ሆኖ ስለማያዉቅ ለበርካታ ግዜያት ከትግራይ ተወልደዉ የትግራይ ክፍለ ግዛት ገዠና አስተዳዳሪ የነበሩት ራስ መንገሻ ሰዩም በመሰከሩት መሰረት የወያኔ እንካ ሰላንተያ ቆሞ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ እንዲያገኝ እንጠይቃለን፤

2ኛ) የወያኔ ሰራዊትና የደህንነት ኀይል በሰላማዊ መንገድ እምነቱን ለመግለጽና የእሬቻ በአልን ለማክበር በወጣዉ  ህዝብ ላይ ያደረሰዉን ጭፍጨፋ የሰዉ ዘር ማጥፋት ድርጊት በመሆኑ በጣም አዝነን እያለቀስን ይህን አረመኔያዊና ሴይጣናዊ ተግባር አጥብቀን እናወግዛለን፤

3ኛ) የወያኔ ሰራዊት በአማራ፤ በኦሮምያ፤ በጋምቤላ፤ በኮንሶና፤ ወዘተ የሚያፈሰዉ የንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ደም የወላይታ ህዝብ ደም ስለሆነ ደርጊቱን እናወግዛለን፤

4ኛ) ሰሞኑንም በዲላና አካባቢው ብዙ ብሔረሰቦች በሰላምና በፍቅር ይኖሩ የነበሩት ሃያ አምስት ዓመታት ህዋአት ኢህአዲግ አገዛዝ በረጨው የዘረኝነት መርዝ ሳቢያ እርስ በርስ መጠቃቃታቸውንና በዚህም የንጽሐን ወገኖቻችን ህይወት  ማለፉና የአካልና የንብረት ውድመት መድረሱ እጅግም ልባችንን ነክቶታል ። አገዛዙም  የተቃጣበትን አገራዊ እምቢተኝነት ትኩረት ለማዛባት ሲል ራሱም ጭምር የለኮሰው መሆኑን በአሜሪካ ድምጽና ሌሎች መገናኛዎች ከሥፍራው ከተጠቂዎች አንደበት ስንሰማ በእጅጉ እያዘንን ድርጊቱን በጽኑ እናወግዛለን።

5ኛ) በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትርና የኢሃዴግ ሊቀመንበር የሆኑት የወላይታን፤ የሲዳማን፡ የጋሞን፤ የቁጫን፤ የኮንሶን ደም ያፈፈሱትን የመካላከያ ሠራዊት ሲያዙ ቆይተዉ ይህ ሳያንስ አሁን በመላ ኢትዮጵያ የተነሳውን የመብት ፣ የነጻነትና የህዝባዊ እምቢተኝነት ጥያቄ ለማዳፈን ጦር አዘዋል ፣ ይህንን ለማርገብ ያገባናል ከሚሉ ኃይሎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ  ውይይት አገሪቱን ከእልቂት ማዳን ሲቻል ይባሱኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት በህወአት ወታደራዊ መዳፍና የደህንነት ኮማንድ ፓስቴ አፈናውን ለማስፋት መወሰኑ ስላሳሰበንና ስላሳዘነን በእጅግ እርምጃውን  በጽኑ እናወግዛለን፤ኣ።

6ኛ) ከወላይታ ህዝብ አብራክ ወጥተው ለህዝባቸዉ ጥቅም ሳይሆን ለሆዳቸዉና ለስልጣናቸው አድረው ሰፊዉን ሕዝየሚያተራምሱ ካድሬዎች ነገ በታሪክና በህዝብ ፊት ተጥያቂ ከመሆናችሁ በፊት እጃችሁን ከጥፋት መንገድ በአስቸኳይ እንድታነሱ እንጠይቃለን፤

7ኛ) ሰፊዉ የወላይታ ሕዝብ ትናንትናም ዛሬም ነገም ጅግና ነህ፤ ሃጤሮ አንቼ  የተባሉ የወላይታ ጀግ የመልከኛው ሥርዓት  አንገሽግሾት ህዝብን አንቼ ድርባ በምባለው ተቃውሞ  ዘመቻ ለወላይታ ሕዝብ መብትና ክብር ታግሎ እንድተሰዋ ሁሉ ንብረታችሁንና መሬታችሁን ለመቀማት ለሚመጣውና ለሚያፍናችሁ የወያኔ ካድሬ ጸጥ ብላችሁ እንዳትገዙና ለኦሮሞ፤ ለአማራና፤ ለኮንሶ ሕዝቦች የአጋርነት ድምጻችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃለን። በህዝብ እገዛና ድጋፍ ተምራችሁ በተለያዩ የመንግስት ሥራ የተሰማራችሁ ወገኖች በኑሮ ዉድነት መከራችሁን እንድታዩና ልጆቻችሁን የማብላትና የማልበስ አቅም ያሳጣው በፕሮፓጋንዳ ሆዳችሁን እየሞላ ያለዉን የወያኔ ኢሃዴግ አገዛዝ ሕዝቡ እምቢ እንዲል የራሳችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፤

8ኛ) ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለዉን ጭፍጨፋ መልኩን ለማስቀየርና ሕዝባዊ ድጋፍ ያለው ለማስመሰል በየቦታው የሚጠራውን የድጋፍ ሰልፍ እንኳን ገደላችሁ ብሎ የሚወጣ የወላይታ ሰው አለመኖሩን በተግባር እንድታሳዩ እንጠይቃለን፤

9ኛ) አምባገነኑ ህወአት ኢህአደግ ሥርዓት በወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን መጠነ ሰፊ ሰቆቃ አስመልክቶ በአሁኑ ወቅት መላው ዓለም አገዛዙን በማውገዝ ላይ ይገኛል በዚህም ዓለም አቀፉ የሰባዊ መብት ድርጅቶች ፣ የተባበሩት መንግሥታት የአውሮጳ ህብረት ኃያላን መንግስታትን ጨምሮ አሜሪካና በሰሞኑ ኢትዬጵያን እግረመንገዳቸው የነበሩት የጀርመኗ ቻንስለር አንግላ ማርኬም አገዛዙን በመንቀፍ ለፓርላማው እንዲናገሩ የተጋበዙትን በአንድ ድርጅት ለተቀፈደደውየኢትዬጵያ ፓርላማ ንግግር አላደርግም በማለት ቅሬታቸውን ለማሳየት ውድቅ ማድረጋቸውን በጽኑ እንደግፋለን።

10ኛ) እኛም በአሜሪካና ካናዳ የምንኖር ( 69 ) ሰላሳ ዘጠኝ የምንሆን ኢትዮጵያዉያን የወላይታ ተወላጆች አገራችንችንን ከልባችን የምንወድ ከማንኛውም አፍራሽ ሃይል ጋር ግንኙነት ኖሮን ሳይሆን በአገር ቤት የሚገኘው ኢትዬጵያዊ ወገናችን ዛሬም በድጋሚ በአምባነኖችና ጨቋኞች መዳፍ ሥር በመውደቁና አፈናው ፣ ሰቆቃውና ግዲያው ህዝባችን ሊሸከመው ከሚችለው በላይ በመሆኑና ትዕግስታችንም በመሟጠጡ የወገናችን ሰቆቃ ሰቆቃችን መሆኑን በመገንዘብ የእዚአብሄር ቃል በመጽሃፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች ለተጎዱ ጩሁ በየቦታዉ ድምጻችሁን አሰሙ ባለዉ መሰረት ድምጽን ለለታፈነው የኢትዬጵያ ሕዝብ አንደበት በመሆን ይህንን መግለጫ በጋራ አውጥተናል።

ኢትዬጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

በአሜሪካና በካናዳ የምንኖር የወላይታ ተወላጅ ኢትዬጵያዊያን!

↧

እጅግ አሳዛኝ ዕለተ-ሰንበት በአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል

≫ Next: Hiber Radio: ሕዝቡ የሕወሓትን የአፈና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ጎን አድርጎ ተቀውሞውን ቀጥሏል፣የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ባለስልጣን በስልክ ሀይለማሪያም ደሳለኝን አስጠነቀቁ፣ የለንደኑ የኦሮሞ ጉባዔ ሁሉንም የኦሮሞ ድርጅቶች በአንድ ላይ እንዲቆሙ የተጠራና በጋራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር የተጀመረውን ትግል የሚያጠናክር እንጂ ወያኔ እንዳለው የሽግግር ቻርተር ለማርቀቅ የተጠራ አለመሆኑ ተገለጸ፣በአገዛዙ የቴሌቪዥን ጣቢያና የፓርቲ ዌብሳይት ላይ ለሰዓታት የዘለቀ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመ ሌሎችም
$
0
0

ጉዳዩ ከሚያንገበግባቸው የአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ኣባላት
ቀን፡ 6/2/2009 አ/ም (10/16216 እ.ኤ.አ.)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ: አሃዱ አምላክ: አሜን!!
የወያኔ ምልምል አባላት እና ድብቅ ደጋፊወችች ሴራም ግልፅ ሆነ
የቦርዱ ሰብሳቢ እና ግብረ አበሮቻቸው ብብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራውን ህጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደማይከተሉ በግልፅ በመናገር የወያኔ ተልዕኮ አስፈፃሚዎች እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡
የተወሰኑ የአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስትያን ቦርድ አባላት በእምባገነኖቹ አቶ አባተ ዘውዴ አና አቶ አየለ ገብሩ በመመራት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብን ከክርስትያናዊ እና አባታዊ አገልግሎታቸው ለማሰናበት እጅግ አሳዛኝ እና እንዲሁም ፈጣሪን እና ቤተ ክርስትያንን ከሚያገለግሉ ምዕመናን የማይጠበቅ የስንብት ወረቀት መፃፋቸውን ተከትሎ ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት የካቴድራሉ አባላት ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ዉለዋል፡፡ በዕለቱ፡ እጅጉን ያዘኑ ምዕመናን በከፍተኛ ለቅሶ እና ሃዘን ተዉጠው ብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብን ከብበው ፀሃይ እና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ሲዘምሩ እና ሲፀልዩ ዉለዋል፡፡
የዕለቱን ኣሳዛኝ ዉሎ በምስል ሲታገዝ ይህን ይመስል ነበር፡፡

ጠዋት ቤተ ክርስትያን ለምሳለም የመጡ ወገኖች የጠበቃቸው አባታችንን አቡነ ያዕቆብን የመሰረቷት ካቴድራል ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክሉ በወያኔ በሚመሩ የቦርድ አባላት የተቀጠሩ ፖሊሶች ነበሩ፡፡

ጠዋት ቤተ ክርስትያን ለምሳለም የመጡ ወገኖች የጠበቃቸው አባታችንን አቡነ ያዕቆብን የመሰረቷት ካቴድራል ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክሉ በወያኔ በሚመሩ የቦርድ አባላት የተቀጠሩ ፖሊሶች ነበሩ፡፡

ምዕመናኑ ገና በጠዋት ነበር እጅግ በሚገርም የአንድነት መንፈስ ቤተ ክርስትያን ቅፅር ግቢ ውስጥ የተገኙት፡፡

ምዕመናኑ ገና በጠዋት ነበር እጅግ በሚገርም የአንድነት መንፈስ ቤተ ክርስትያን ቅፅር ግቢ ውስጥ የተገኙት፡፡


ፍፁም አሳዛኝ እና ክርስትያናዊ ባልሆነ መንገድ ምእመናን እና አባታችን አቡነ ያእቆብ ሲንገላቱ አርፍደዋል፡፡

ፍፁም አሳዛኝ እና ክርስትያናዊ ባልሆነ መንገድ ምእመናን እና አባታችን አቡነ ያእቆብ ሲንገላቱ አርፍደዋል፡፡


እየነጋ ሲሄድም አባታችንን በመክበብ እየተዘመረ እና በብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብ የተመራ የፀሎት ቡራኬ ተደርጛል፡፡

እየነጋ ሲሄድም አባታችንን በመክበብ እየተዘመረ እና በብፁዕ አባታችን አቡነ ያዕቆብ የተመራ የፀሎት ቡራኬ ተደርጛል፡፡


በአንፃሩ ቤተ ክርስትያናችን ውስጥ ገብተው ከአምባገነኖቹ ወያኔዎች ጋር የበሩ እጅግ ጥቂት የሆኑ ግለሰቦች ይታዩ ነበር (ማሳሰቢያ፡ ፎቶው ዉስጥ የሚታዩት ሁሉም የነዚህ ህገዎጦች ደጋፊ ግን ኣይደሉም)፡፡

በአንፃሩ ቤተ ክርስትያናችን ውስጥ ገብተው ከአምባገነኖቹ ወያኔዎች ጋር የበሩ እጅግ ጥቂት የሆኑ ግለሰቦች ይታዩ ነበር (ማሳሰቢያ፡ ፎቶው ዉስጥ የሚታዩት ሁሉም የነዚህ ህገዎጦች ደጋፊ ግን ኣይደሉም)፡፡


የወከላቸውን የቤተ ክርስትያን ምዕመን እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተስፋ የሚጠብቁትን ቅዱስ ሲኖዶስ በማክበር ስራቸዉን በትጋት የሚሰሩት የቦርድ አባላት ስለተፈጠረው የወያኔ ሴራ ለምዕመናን ሲያስረዱ፡፡

የወከላቸውን የቤተ ክርስትያን ምዕመን እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተስፋ የሚጠብቁትን ቅዱስ ሲኖዶስ በማክበር ስራቸዉን በትጋት የሚሰሩት የቦርድ አባላት ስለተፈጠረው የወያኔ ሴራ ለምዕመናን ሲያስረዱ፡፡


የቤተ ክርስትያናችን አባላት ህጉን አክብረው የተዋህዶን ቀኖናን የጠበቁ የቦርድ አባላትን ንግግር በፅሞና ሲያዳምጡ፡፡

የቤተ ክርስትያናችን አባላት ህጉን አክብረው የተዋህዶን ቀኖናን የጠበቁ የቦርድ አባላትን ንግግር በፅሞና ሲያዳምጡ፡፡


በመጨረሻም፤ ምዕመናኑ የቦርዱን ህጋዊ ስርዓት ተከትለው የሚሰሩ የቦርድ ዓባላትን እንዲሁም አስተዋይ ሽማግሌወች ምክርን በማዳመጥ ለወደፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተነጋግረዋል፡፡ በተወያዩት መሰረትም፤
ከሶስት መቶ በላይ አባላት በፍጥነት ቦርዱ ስብሰባ እንዲጠራ የሚያስገድድ ፊርማ ሰብሰበዋል፡፡
አምባገነኖች የቦርዱ አባላት የተለመደውን ምእመናን ካለማክበር የመነጨ ንቀት በማሳየት ስብሰባ የማይጠሩ ከሆነ አባላቱ የቤተ ክርስትያንዋ ህልውና አደጋ ላይ በመሆኑ ምክንያት ፍፁም ህግን በተከተለ መንገድ እንዚህን የወያኔ ቅጥረኞች ከሀላፊነት ለማንሳት ተቀጣጥረው ተለያይተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የህግ የበላይነት ያለበት ሀገር የምንኖር እንደመሆናችን እና እውነትም ከኛ ጋር ስለሆነች በፍርድ ቤት የተጀመረውን ሂደት አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ አባላቱ ለራሳቸው ቃል ገብተዋል፡፡
ቅዱስ እግዚአብሄር ሀገራችንን ኢትዮጵያን እና ህዝባችንን ይባርክልን፡፡ አሜን!!
በእግዚአብሄር ስም፤
ጉዳዩ ከሚያንገበግባቸው የአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ኣባላት።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር!
↧
↧

Hiber Radio: ሕዝቡ የሕወሓትን የአፈና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ጎን አድርጎ ተቀውሞውን ቀጥሏል፣የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ባለስልጣን በስልክ ሀይለማሪያም ደሳለኝን አስጠነቀቁ፣ የለንደኑ የኦሮሞ ጉባዔ ሁሉንም የኦሮሞ ድርጅቶች በአንድ ላይ እንዲቆሙ የተጠራና በጋራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር የተጀመረውን ትግል የሚያጠናክር እንጂ ወያኔ እንዳለው የሽግግር ቻርተር ለማርቀቅ የተጠራ አለመሆኑ ተገለጸ፣በአገዛዙ የቴሌቪዥን ጣቢያና የፓርቲ ዌብሳይት ላይ ለሰዓታት የዘለቀ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመ ሌሎችም

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 6 ቀን 2009 ፕሮግራም

አክቲቪስት አቻሜለህ ታምሩ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቀጥታ ስርጭት ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ውይይት የተቀነቸበ(ሙሉውን ያድምቱት)

habtamu05

የደርግን ከ42 ዓመት በፊት የወጣ የመስከረም 2 ቀን 1967 አዋጅ በድምጽ ይዘናል አድምጡት የሕወሓት/ኢህአዴግ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የከፋ ነው ለንጽጽር በመጠኑ አስደምጠናል(ያድምጡት)

እየተገባደደ የመጣው የአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሰሞነኛ አስገራሚ ሂደቶቹ ሲዳስስ “ኢትዪጵያዊው ጨቅላው ከአሚሪክ ምድር እንዳይባረር ሰግቷል” እጩ ፕ/ት ሒለሪ ክሊንተን (ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የለንደኑ የኦሮሞ ጉባዔ ሁሉንም የኦሮሞ ድርጅቶች በአንድ ላይ እንዲቆሙ የተጠራና በጋራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር የተጀመረውን ትግል የሚያጠናክር እንጂ ወያኔ እንዳለው የሽግግር ቻርተር ለማርቀቅ የተጠራ አለመሆኑ ተገለጸ

የአውሮፓ ህብርት ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን በስልክ ደውለው አስጠነቀቁ

“ኢህአዲግ የፓለቲካ ምህዳሩን ማጥበብ የለበትም”ሚሲስ ፊዴሪካ ሞጋርኒ የህብረቱ ከፍተኛ ሹም

አስቸኳይ አዋጁን በመቃወም በአገዛዙ ኢቢሲ የቴሌቪዥን ጣቢያና የፓርቲ ዌብሳይት ላይ ለሰዓታት የዘለቀ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመ

በአዋጁ አገዛዙ በሕዝቡ ላይ ያሰበውን ተቃውሞ ማስቀረት አልቻለም

ኢህአዲግ የደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በውጭ ሚዲያዎች እይታ እና የፓለቲካ ተችዎች ስጋት

ህዝቡ የጸረ ልማት ዓላማ የለውም ነገር ግን የውጭ ባለሀብቶች ነገሮችን ቀደም ብለው ሊያጤኑ ይገባል”ዶ/ር መረራ ጉዲና

አውሮፓ ውስጥ በስርቆት ወንጀል የተጠረጠረው ኢትዪጵያዊ የዋስትና መብቱን ተነፈገ

ግለስቡ ግን በገዛ እራሴ ንብረት ሌባ ተባልኩኝ ባይ ነው

ግብጽ በአዲስ አበባና እና በካይሮ ግንኙነት ላይ ደንቃራ የሚፈጥሩ ወገኖችን ቸል አልልም አለች

በግብጽ የሚገኙ ኢትዪጵያዊያን ስደተኞች ዛሬ ለተቃውሞ ሰልፍ ወጡ

ፍርሃት ላይ የወደቀው የሕወሓት አገዛዝ በባህር ዳር በቴሌ አማካይነት በጥንቆላ ስም የስለላ ቴክስት መልዕክት በስልክ ልኮ ለመሰለል ሞከረ

ለመልዕክቱ ምላሽ ባለመስጠት ስለላውን ማክሸፍ ይቻላል ተባለ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

↧

ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም ! መወገድ ያለበት እንጂ !

≪ Previous: Hiber Radio: ሕዝቡ የሕወሓትን የአፈና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ጎን አድርጎ ተቀውሞውን ቀጥሏል፣የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ባለስልጣን በስልክ ሀይለማሪያም ደሳለኝን አስጠነቀቁ፣ የለንደኑ የኦሮሞ ጉባዔ ሁሉንም የኦሮሞ ድርጅቶች በአንድ ላይ እንዲቆሙ የተጠራና በጋራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር የተጀመረውን ትግል የሚያጠናክር እንጂ ወያኔ እንዳለው የሽግግር ቻርተር ለማርቀቅ የተጠራ አለመሆኑ ተገለጸ፣በአገዛዙ የቴሌቪዥን ጣቢያና የፓርቲ ዌብሳይት ላይ ለሰዓታት የዘለቀ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመ ሌሎችም
$
0
0

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) ጥቅምት 17 ፣ 2016„

በገሀነም ውስጥ እጅግ የሚያቃጥለው ቦታ የተያዘላቸው የሞራል ቀውስ በሚታይበት ወቅት ለህዝብ ወገናዊነትን ለማያሳዩ ሰዎች ነው።“ Danteመግቢያ ሰሞኑን ወያኔ የሚያወናብደው ራሱን ለማደስ እንደተዘጋጀና ጊዜም እንደሚያስፈልገው ነው። በአገዛዙ ውስጥ የአስተደዳደር ብልሹነት አለ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ባህል ተስፋፍቷል፣ ሙስና ለቢሮክራሲው ማነቆ በመሆን ስራ አላሰራም በማለት የአገርን ዕድገት እየጎተተ እንደሆነ እየመላለሰ ይነግረናል። እነዚህንና „ “ ሌሎች የአስተዳደር ብልሹዎችን በየስብሰባውና በቴሌቪዢን የውይይት መድረከ ላይ የሚያወሩልን የአገዛዙ የመሪ ቁንጮዎች በሽታዎቹ ከሰማይ እንደወረዱ እንጂ እነሱ ለአጋዛዛቸው እንዲያመቻቸው ሆን ብለው የፈጠሩትና ከተበላሸ ኢ- ሳይንሳዊና አገር አፍራሽ የአሰራር ዘዴ ጋር እንደተያያዘ አድርገው አይደለም የሚያቀርቡት። በሌላ አነጋገር፣ ለከፋፍለህ ግዛ እንዲያመች በፌዴራሊዝም መልክ ተዋቀረ „ “ የሚባለውና የብሄረሰቦችን መብት የሚያስከብረው ፣ በመሰረቱ ግለሰብአዊ ነፃነትን በማፈን በክልል መልክ በተዋቀረው ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን አቀጭጮ የሚያስቀረው አስተዳደር ለሙስናና ለአስተስዳደር ብልሹ፣ እንዲያም ሲል ለአጠቃላይ ዕድገት ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ ወያኔ በፍጹም ሊያምን አይፈልግም። ከዚህም ባሻገር፣ ይህ ዐይነቱ የግለሰብ ነፃነትን አፋኝና ፈጠራ እንዳይኖር ያደረገው ስርዓት በየክልሉ ራሳቸውን ያደለቡ ዋር- ሎርዶችን እንደፈጠረና ለሁለ- ገብ ዕድገት እንቅፋት እንደሆነ ወያኔ በፍጹም የተገነዘበ አይደለም። በሁለተኛ ደረጃ በዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው ግፊት ወያኔ በ 1993 ዓ.ም ተግባራዊ ያደረገው የተቅዋም መስተካከል ዕቅድ (Structural Adjustment Program)የሚባለው፣ አብዛኛውን ህዝብ በማደኽየት ጥቂቶችን የሚያደልበው የኒዎ- ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በአገሪቱ ውስጥ የተዛባ ዕድገት ማምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱን የቆሻሻ መጣያ በማድረግ እንደ አንድ ህብረ- ብሄርና እንደ ህብረተሰብ እንዳትገነባ የሚያደርገው ፖሊሲ ዛሬ በአገራችን ምድር ውስጥ ለሚታየው አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ ቀውስ ተጠያቂ እንደሆነ ወያኔ በፍጹም ሊረዳ አይችልም።
tplf-rotten-apple-1.jpg

በሶስተኛ ደረጃ፣ የኢኮኖሚውን ቁልፍ ቁልፍ መስኮችን ለመቆጣጠርና ሀብት ለመዝረፍ እንዲያመች በአዲስ መልክ የተዋቀረው የመንግስት የመጨቆኛ መኪናና፣ በየጊዜው ፋሺሽታዊ መልክ እንዲይዝ እየተጠናከረ የሄደው የአገዛዝ መሳሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተዘረጋው የሚሊታሪ-ኢንደስትሪያልውስብስብና(Complex) የፊናንስ ካፒታል ጋር በመቆላለፍ በአገራችን ምድር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ነፃነትን ማፈኑና፣ ለዕውነተኛ ዕድገትና ህብረተሰብአዊ ውህደትና ጥንካሬ ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ አገዛዙና ካድሬዎቹ በፍጹም የተገነዘቡት አይመስልም። ከዚህ ስንነሳ የብልሹ አስተዳደርና ሙስና ከላይ የተጠቀሱት፣ የክልል አስተዳደር፣ የኢኮኖሚው ፖሊሲና የመንግስቱ መኪና አወቃቀርዕይንታዎች(Manisfestations) ወይም ውጤቶች እንጂ በራሳቸው እንደ ዋና ምክንያት ሊታዩ የሚችሉ አይደሉም። ስለሆነም በአገራችን ምድር አማራ በመባል በሚታወቀውና በኦሮምያ ክልል የሚካሄዱትና በየቦታው እየተስፋፉ የመጡት ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች በመሰረቱ የነፃነት ጥያቄዎች ሲሆኑ፣ ወደ ውስጥ ገባ ብለን ስንመለከት ደግሞ ላይ በተዘረዘሩት መልክ በተዋቀረው ዘራፊና(Predatory State) ፋሺሽታዊ አገዛዝ ስር አንገዛም፣ ይህ ዐይነቱ አወቃቀር የአንድነታችን፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የማህበረሰብ ዕድገታችን፣ የህልውናችን፣ የብሄራዊ ነፃነታችን ፀር በመሆን ታሪክ እንዳንሰራ የሚያግዱን ናቸው በማለት የተነሱ ህዝባዊ አመጾች ናቸው። ስለሆነም ይላል ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ወያኔና ካድሬዎች የውጭ ኃይሎች ተጠሪዎች በመሆን የውክልና ጦርነት በማካሄድ እንደ ማህበረሰብና እንደ አገር እንዳንኖር እያደረጉን ነው፤ የውጭ ኃይሎች ገብተው እንዲፈተፍቱ መንገዱን በማዘጋጀት ርስ በርሳችን እንድንጨራረስ ሊያደርጉን ነው በማለት ነው በአገዛዙ ላይ በአንድነት ከዳር እስከዳር የተነሱበት። ይህንን አገር አፍራሽ ሂደቱን ግን ወደ ተራ የአስተዳደር ብሉሽነት በመቀየርና ለማስተካከል ይችል በማስመሰል ህዝቡን በማወናበድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ስንነሳ ተሃድሶ የሚለውን ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ አባባል ጠጋ ብለን እንመልከት። በእርግጥ ወያኔ እንደሚለው ራሱን ማደስ ይችላል ወይ? ፅንሰ- ሃሳቡ በየጊዜው እየተደጋገመ በመሰማቱ አብዛኛው ህዝብ ተሃድሶ ማለት ምን ማለት እንደሆን እንዲረዳው ትንሽ ማተቱ የሚከፋ አይመስለኝም። ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው ? በመሰረቱ ተሃድሶ ማለት ቀድመው የነበሩ ነገሮችን በአዲስ መልክ ከአንድ ሁኔታ ጋር በማቀናጀት ለአንድ ህብረተሰብ ልዩ ዕምርታን መስጠት ማለት ነው። ተሃድሶ የሚባለው ፅንሰ- ሃሳብ ቃል በቃል ሲተረጎም ሬናሳንስ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣሊያን ምድር በ 15 ኛው ክፍለ- ዘመን ተግባራዊ የሆነና፣ የግሪክን ፍልስፍና፣ የማቲማቲክስን፣ የሳይንስን፣ የአርክቴክቸርና ሌሎችንም ግኝቶች ወይም ፈጠራዎች መሰረት ያደረገ ሁለ- ገብ የሆነ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ነው። ጸንሳሺዎቹም በ 14 ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ ላይ ኮንስታንቲኖፕል የሚባለውና ዛሬ ኢስታንቡል በመባል የሚታወቀው ከተማና ዛሬ ቱርክ የሚባለው ግዛት ሲወረር ሽሽተው ወደ ጣሊያን የሄዱ ቄሶችና ፈላስፋዎች፣ ወይም ደግሞ ኒዎ-ፕላቶናውያን(Neo-Platonic) በመባል የሚታወቁ ምሁሮች የአዳበሩትና የአስፋፉት ሰፋ ያለ የጭንቅላት እንቅስቃሴና ተግባራዊም የሆነ ነው። ይህ አዲሱ መንፈስን በማደስ የተጀመረው ምሁራዊ እንቅስቃሴ እነ ዳንቴ ካዳበሩት እንደ የአምላኮች ኮሜዲ ከመሳሰሉት ሌትሬቸሮች ጋር በመዋሃድ ልዩ ዕምርታን በማግኘት በዚያን ጊዜ በጣሊያን ምድር የተዘረጋውን አስከፊ ስርዓትና ብልሹ የሆነ የህዝብ የአኗኗርን ስልት በመቀየር የህዝቡን ጭንቅላት በማደስ ኋላ- ቀር ከሆነው አስተሳሰቡ በመላቀቅና ራሱን በራሱ በማግኘት ዕውነተኛ ነፃነትን እንዲጎናጸፍ በማድረግ ሁለንታዊ ዕድገት እንዲመጣ በር የከፈተ ሰፋ ያለ ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴ ነው። የዚህ ውጤት እነ ጋሊሊ፣ እነ ዳቪንቺና ሚካኤል አንጀሎና፣ እንዲሁም በሺህ የሚቆጠሩ ሳይንቲስቶችና የኦፔራ ሰዎችና ሰአሊዎች ብቅ እንዲሉ ያደረገ ነው። በሌላ አነጋገር፣ ሬናሳንስ ወይም ተሃድሶ የሚባለው መንፈስን ከዕውነተኛ ዕውቀት ጋር በማገናኘትና በማደስ የሰው ልጅ ዕውነተኛ ነፃነቱን በመጎናጸፍ ራሱን በልዩ ልዩ መልክ እንዲገልጽና፣ አንድ ማህበረሰብ እንዲመሰርትና በሰላምና በስምምነት እንዲኖር ያደረገና የሚያደርግ ሳይንሳዊና ፍልስፋናዊ ሂደት ነው። የሬናስን አፍላቂዎችና በመቀጠልም ያዳበሩትና ልዩ ዕምርታን የሰጡት ምሁሮች በመሰረቱ ምንም ወንጀል ያልሰሩና፣ መንፈሳቸውን ከእግዚአብሄር ጋር በማቀራረብ በኮስሞስ በማስመሰል በምድር ላይ ዕውነተኛ ገነትን ሊመሰርቱ የቻሉና፣ ማቴሪያላዊ ዓለምን ከመንፈሳዊ ጋር በማዋሃድ የሰው ልጅ በአርቆ አሳቢነት እየተመራ ሚዛናዊና ጥበባዊ ኑሮን እንዲኖር ሁሉን ነገር ያዘጋጁና ተግባራዊ ያደረጉ ታላቅ ምሁራን ናቸው። በሌላ አነጋገር፣ እንደ ወያኔ ከፋፋይ፣ ጨፍጫፊ፣ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጣላት አንድ ህዝብ በዘለዓለማዊ ትርምስ ውስጥ እንዲኖር ያደረጉ አይደሉም። በዘራፊነትና ባልተስተካከለ ዕድገትም የሚታሙ ሳይሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውነተኛና ሃርሞኒየስ የሆነ የአርክቴክቸር ስራን ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉና፣ ለጠቅላላው የምዕራብ አውሮፓ ስልጣኔ መሰረት የጣሉ ናቸው። ከዚህም በመነሳት ነው በኋላ ካፒታሊዝምና የኢንዱስትሪ አብዮት ተግባራዊ መሆን የቻሉትና፣ በምዕራብ አውሮፓ ምድር ውስጥህብረ- ብሄሮች እንዲመሰረቱና እንዲጠናከሩ የተደረገው። ይሁንና ግን የሬናሳንስ መልዕክት ካፒታሊዝምን ማስፋፋት ሳይሆን፣ የየግለሰቦችን ዕውነተኛ ነፃነት በማወጅ በልዩ ፈጠራ ዘዴ ሚዛናዊ ዕድገትን ማምጣት
ነው። የካፒታሊዝም በአሸናፊነት መውጣትና የሬናሳንስ መሰረተ- ሃሳቦች ቀስ በቀስ መደምሰስ ወይም መቀልበስ ከኃይል አሰላለፍ ለውጥ ጋር የተያዘ ነው ማለት ይቻላል። ወደ ወያኔው ተሃድሶ ስንመጣ ግን በመጀመሪያ ደረጃ በድርጅቱ ውስጥ የተጠቃለሉት ግለሰቦች ከጦር ሜዳ ጀምረው በደም የተጨማለቁና የስው ልጅ ህይወትም ቅንጣት የማይሰጣቸው ሰይጣናዊ ባህርይ የተዋሃዳቸው ናቸው ማለት ይችላል። በዓለም ታሪክ ውስጥ በሰው ልጅና በህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ውስጥ ያልታየን ድርጊት የፈጸሙና ድርጊታቸው በሙሉ ህብረተሰብን ማከረባበትና አገርንም ማወደም ነው። ታሪክን ማፈራረስና፣ አንዱ የህብረተሰብ ክፍል ከሌላው ጋር እንዳይገናኛና እንዳይግባባ ልዩ ልዩ ፊደሎችን በመቅረጽ ቅጥ ያጣ ኑሮ እንዲኖር ባህላዊ ያደረጉና ፀረ- ዕድገትን ያስፋፋ ናቸው። በሌላ ወገን ግን እነ ዳንቴ በአስራአራተኛው ክፍለ- ዘመን ያደረጉት በዚያን ጊዜ የኢጣሊያን ህዝብ በተለያየ ዲያሌክት ይነጋገር ስለነበርና መግባባትም ስላልነበር፣ አንድ ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል ሰዋስውና ቋንቋ በመፍጠር ለጣሊያን ዕድገት ዕምርታን የሰጡ ናቸው። ይህም ማለት የወያኔው አካሄድ የዚህ ተቃራኒና የአንድን ህዝብ መተሳሰር በማፍረስ በእንግሊዞች የቋንቋ ምሁራን፣ በመሰረቱ ተንኮለኞች በመታገዝ በአገራችን ምድር ተግባራዊ ያደረገ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። ውጤቱ እንደምናየው፣ በተበላሸ ሁኔታ ወይም የአኗኗር ስልት፣ በተዝረከረከ የከተማ አወቃቀር፣ በአንድ የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ብቻ በመመካት በተለያየ የምርት ውጤት ሊገለጽ የሚችል የስራ- ክፍፍል እንዳይኖር ያደረገና፣ ብቃትነት ያላቸው ኢንስቲቱሽኖች እንዳይመሰረቱ በማድረግ በየአካባቢው የሰውና የተፈጥሮን ሀብት በማንቀሳቀስ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ዕውነተኛ ህዝባዊ ሀብት(National Wealth) እንዳይፈጠር ያደረገ ነው። በዚህም መሰረት በአንድ አካባቢና በአገሪቱ ምድር ውስጥ ስርዓት ባለው መልክ በኢንዱስትሪ ተከላ ላይ የተመሰረተ፣ ከሌሎች መስኮች ጋር የተያያዘ የውስጥ ገበያ(Home Market) እንዳይዳብር ያደረገ ነው። በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ በሌለበት አገርና፣ የውስጥ ገበያም እንዳይዳብር ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቆላለፍ ሻጥር በሚሰራበት አገር ውስጥ አንድ ጠንካራ አገር ወይም ህብረ-ብሄር መመስረት በፍጹም አይቻልም። የወያኔም ተልዕኮ ይህ ሲሆን፣ ከበስተጀርባ ሆነው የሚበውዙት፣ የእንግሊዝ፣ የአሜሪካንና የምዕራብ ጀርመን የስለላ ድርጅቶችና፣ በተራድዖ ስም የሚንቀሳቀሱት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ናቸው። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ምን ዐይነት ተሃድሶ ማካሄድ ይቻላል ? ጭፈጨፋና ተሃድሶ እዚያው በዚያው ወይስ ማጭበርበር ! እንድምንከታተለው ወያኔ በአንድ በኩል ራሴን ለማደስ ዝግጁ ነኝ፣ በዚህም ላይ ዕቅድ በማውጣት ላይ ነን ይላል። እዚያው በዚያው ደግሞ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ ምስኪኑን ህዝባችንን ይጨፈጭፋል። በየቦታው የአጋዚ ወታደሮችን በመላክ ፋሺሽታዊ ጭፍጨፋውን ተያይዞታል። በዚያው መጠንም ሌሎች እምቢ ያሉትን ሰላማዊ ዜጎችን በማፈናቀልና ሀብታቸውን በመቀማት የቁም ስቅላቸውን ያሳያቸዋል። በሌላ አነጋገር፣ የወያኔ አገዛዘ በየቦታው እየጋለ የመጣውን ህዝባዊ ብሶትና ቆራጥ የተሞላበት ትግል በውጭ የስለላ ድርጅቶች በመታገዝና በመመከር ጭፍጨፋውን በየቦታው እያካሄደ ነው። ይሁንና ቆራጡ የጎንደርም የሆነ የኦሮሞ ወንድማችንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ዕምቢተኛነታቸውን በማስተጋባት ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ እየተፋለሙት ይገኛሉ። በአንዳንድ አካባቢዎችም ድልን እየተጎናጸፉ ነው። በዚህ ዐይነት መልክና ቁልፍ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንድ አንድ ኩባንያ በተደራጀ መልክ ከአንድ ብሄረሰብ በተውጣጡ፣ ሰውነታቸው በደም በታጠበ ግለሰቦች በተያዘበት አገርና፣ በግለሰብ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሌለበት አገርና፣ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዳይቻል አንድ አገዛዝ በውጭ ኃይሎች እየታገዘ መንግስታዊ መኪናዉን ፋሺሽታዊ በሆነ መልክ ባዋቀረበት አገር እንዴት አድርጎ ተሃድሶን ማምጣት ይቻላል? በፍጹም የማይታለምና የማይቻልም ነው። አንድ በኮሜዲ መልክ የቀረበ ጥንቆላ፣ አንዷ ታማ ጠንቋይ ቤት ትሄዳለች። ጠንቋይዋ የመንፈስ በሽታ የተናወጣትን ለማዳን
ያልሞኮረችው ነገር የለም። በመጨረሻ የደረሰችበት ድምዳሜ ከአቅሟ በላይ እንደሆነና መፈወስም እንዳማይቻል ነው። የወያኔም የጭንቅላት በሽታ እንደዚህ ነው። አጥፍቼ ልጥፋ በሚለው እርኩስ አስተሳሰብ የተለከፈ ስለሆነ መፈወሻ የሚገኝለት አይደለም። መፈወሻውም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂያዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴና በሱ ላይ የተመሰረተ በማያዳግም መልክ የሚያወድመው ርብርቦሽ ነው። በሌላ ወገን የወያኔን ነፍስ ለመዝራት በልደቱ አያልነህ የሚመራው ኢዴአፓና አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ነን ባዮች የማያደርጉት ሽር ጉድ የለም። ልደቱና ሌሎች ግለሰቦችና አንዳንድ ድርጅትን እንወክላለን የሚሉት በአገራችን ምድር ውስጥ እንደዚያ ያለ ጭንቅላትን የሚዘገንንና እንቅልፍ „ “ የሚያሳጣ ድርጊት በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ባለበት ወቅት ወያኔ በጠራው የመወያያ ስብሰባ ላይ መገኘታቸው የቱን ያህል የህዝባችን ሁኔታ እንደማይመለከታቸው ነው የሚያረጋግጠው። እነዚህ„ “ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ኃይሎች እንደዕውነቱ ከሆነ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በአገራችን ምድር ምን እንደተካሄደ የገባቸውና የተገነዘቡም አይመስልም። ለመረዳትም የሚፈልጉ አይደሉም። የዲሞክራሲንና የነፃነትን ጉዳይ ከተራ ምርጫና ፓርላሜንት ውስጥ ተቀምጦ ከመዘባነን ጋር ነው የሚያያዙት። በዚህም መሰረት ማንም ውክልና ሳይሰጣቸው አሜሪካና አውሮፓ እየመጡ የዓለምን ህዝብ (International Community) እንወክላለን ለሚሉት የሚያሰሙት እሮሮ በመሰረቱ የህዝባችንን የዕውነተኛ የነፃነት ትግል የሚያጨናግፍ ነው። አካሄዳቸው በአገራችን ምድር ውስጥ ዕውነተኛ ዕድገት እንዳይመጣ የሚያደርግ ነው። እነዚህ ተቃዋሚ ነን ባዮች የዓለም ፖለቲካ አወቃቀርና ብወዛ በፍጹም የገባቸው አይመስልም። ያም ሆነ ይህ፣ ወያኔ ተሃድሶ እያለ የሚያናፍሰው ወሬና የሚያካሄደው የእነወያይ ስብሰባ ማዘናጊያና ራሱን ማጠናከሪያ ዘዴ ነው። አገዛዙ የሚታደስም የሚታከምም አይደለም። ህፃናትን ሳይቀር በስናይፐር የሚገድልና ሴትን ቤንዚን በማርከፍከፍ አሰቃይቶ የሚገድል አገዛዝ በፍጹም ሊታደስ አይችልም። ዕውነተኛ ተሃድሶ ሊመጣ የሚችለው ከዚህ አገዛዝ ባሻገር በሀቀኛ አገር ወዳዶችና በተገለጸላቸው ምሁራን አማካይነት ነው። ይህም ቢሆን ከህዝብ ትግል ጋር መዋሃድና የህዝቡን ኃይልነት የሚያበስር መሆን አለበት። ከዚህም ጋር ተያይዞ የመንግስቱ የመጨቆኛ መሳሪያ እንዳለ በመንኮታኮት ለዕድገት በሚያመች መልክ ከማንኛውም የውጭ የስለላ ድርጅት ነፃ በሆነ መልክ መደራጀት አለበት። ከህዝብ ጋር የሚሄድና የሚዛመድ እንጂ በህዝቡ ላይ ጠበንጃውን የሚቀስር አገዛዝ አይደለም ህዝባችንና አገራችን የሚመኙት። ከዚህም ባሻገር ዕውነተኛ ተሃድሶ በሁለ- ገብ የትምህርት ዘመቻ የሚታገዝ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ፖሊሲዉም በመንግስትና በህዝብ መሀከል በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ ሁለ-ገብ(HolisticEconomic Policy) የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ተግባራዊ የሚሆንበት ነው። በሌላ አነጋገር፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ የሚመራበትን የኢኮኖሚ ፖሊሲና የዓለም አቀፍ ኢንስቲቱሽኖችን ምክር በመጣል ርስ በርሱ የተሳሰረ የውስጥ ገበያን ሊያስገነባ የሚያስችል የኢንዱስትሪ ተከላና የቴክኖሎጂ ምጥቀትን የሚያመጣ ፖሊሲ የተሃድሶ መሰረተ- ሃሳብ ናቸው። በመጀመሪያ ግን ይህን አገዛዝ ገርስሶ በመጣል፣ ህዝባችንን ለስራ በማንቀሳቀስ መሰረታዊፍላጎቶቹን(Basic Needs) ሊያሟላ የሚችልበትን ሁኔታ ማደራጀት አለብን። በዚህ መልክ ብቻ ነው ወደ ፊት መግፋትና ቀስ በቀስም ህዝቦቿን ማሰተናገድ የምትችልና የተከበረች ኢትዮጵያን መገንባት የሚቻለው። ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ በየቦታው በተሰበጣጠረ መልክ የሚካሄደው እንቅስቃሴ በአንድ የአስተሳሰብ ክልል ውስጥ(Unity of Thought) መካተት አለበት። ሁሉም በየፊናው ለስልጣን መታገሉን አቁሞ በአንድ ማዕከላዊ አመራር ስር በመመራት ወደ ድል ለማምራት መዘጋጀት አለበት። እየተሰበጣጠሩ መታገልና፣ የሚሆን የማይሆን ሰበብና ተንኮል እየፈጠሩ ዝናን ለማግኘትና ለመታወቅ መሞከር የህዝባችንን ሰቆቃ ያራዝመዋል። የአገራችንን መበታተን ያፋጥነዋል። ይህ ደግሞ የማንኛችንም ምኞትና ፍላጎት አይደለም። ስለዚህ ከመሰባሰብና ተወያይቶ በአንድ ሃሳብ ዙሪያ ከመታገል በስተቀር ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም።

↧

አማካሪው ማነው?

$
0
0

 

deb
ብቅሉሲጠነሰስጌሾምእንዲጨመር፤
እነማን ነበሩ ጠላ ጠማቂወቹ
ዜጎችእንዲጠጡበኢትዮጵያአገር።
ቦታውስ የትነበርየተማከሩበት፤
ጋኑንምበትንሽጠጠርየደጋገፉበት።
በሰላምሲሰለፍወጣትእንዲገደል
ወታደር ያዘዙእጃቸውንአጥፈው፣
እነማን ነበሩ አማካሪስ ማነው?
እስኪ እንጠይቃቸው!
አገሪኢትዮጵያምንመንግሥትአቋቋምሽ፤
በጥላውበርግጎላንችየቆሙትንየሚያሰቃይብሽ።
የዶሮ ብልቷ አሥራሁለት ነው
ተብሎስለሰሙየህዋሃትሞያተኞች፤
በጎሣበለቱየኢትዮጵያንልጆች።
ዚገኛን አዘዘ ሁሉእንዲበረግግ፣
እንዲህም አወጀ፣
አይንህ ብቻ ሳይሆን አዕምሮህን ዝጋ
በፍርሃትማነቆ፣እንዲያካለደረግህ፤
በአዋጅ ነግሪያለሁ አጋዚአለብህ።
በሰላምሲሰለፍወጣትእንዲገደል
ወታደር ያዘዙእጃቸውንአጥፈው፣
እነማን ነበሩ አማካሪስ ማነው?
እስኪ እንጠይቃቸው!
አገሪ ኢትዮጵያ ምኑን መርዝ ጠጣሽው?
እርሃቡስ ቤበዛ ምኑን ምርዝ በላሽው?
ለቀብርዳርጎሻልከሆድሽየወጣው።
እስኪ ሰላምልበልለኒያዘመዶቸ፤
ከአዲግራት፣መቀሌ፣ወልቃይትጎንደርውሥጥ
አርጎባ፣ ባሐር ዳር፣ አለፍ ብሎም ፍቸ።
ወደ ባሌም ልሂድ ሐረርንም ሳልተው አርሲም ሲዳማ፤
በረዲዮ ላስታውቅ ሁሉእስኪሰማ።
ግልጽአድርጌምልንገር፤
የለቱንግድያበኢትዮጵያእገር።
በሰላምሲሰለፍወጣትእንዲገደል
ፍትህ ለጠየቁት ጥይት ያበላቸው፣
ወታደር ያዘዙእጃቸውንአጥፈው፣
እነማን ነበሩ፣ አማካሪስ ማነው?
እስኪ እንጠይቃቸው!
አቤቱታላቅርብለራበውአባቴ፣
አቤቱታላቅርብለራባውወንድሜ፣
አቤቱታምላቅርብለራባትእህቴ፣
እንጀራ ብትሰጠኝ ያችኢትዮጵያእናቴ፤
ከታች ከላይ ስዞርስቆምለመብቴ።
© ለምለም ፀጋው፣October 17, 2016
በኢትዮጵያ ለምብታቸው ሲቆሙ ለተገደሉ ሁሉ መታሰቢያ
↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live