Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ሰበር ዜና: በስደት ያለው ሲኖዶስ ነገ ጠዋት የሚሰይማቸው 6 ኤጲስ ቆጶሳት ማንነት ከነታሪካቸው እጃችን ገባ

$
0
0

aba holy sinod
(ዘ-ሐበሻ) በስደት የሚገኘው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነገ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሬዎስ በሚገኙበት በካሊፎርኒያ በኦክላንድ መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አዲስ የተሰየሙ ኤጲስ ቆጶሳትን ይፋ ያደርጋል:: ዘ-ሐበሻ አዲስ የሚሾሙትን የኤጲስ ቆጶሳት ማንነትና ታሪካቸው እጇ ገብቷል::

ዘ-ሐበሻ አዲስ የተሾሙት ኢጲስ ቆጶሳት የጵጵስና ስማቸው ማን እንደሚሆን እና የት ሃገረ ስብከት እንደሚሾሙ እያጣራች ነው:: ሙሉ መረጃው እንደደረሰን ለአንባቢዎቻችን ትለቀዋለች::

ለጊዜው የአዳዲስ ተሿሚዎችን ማንነትና ታሪካቸውን ይዘናል – ይከታተሉት

1ኛ. የአባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ አጭር የሕይወት ታሪክ

አባ ወልደ ትንሣኤ

አባ ወልደ ትንሣኤ

አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ ከአባታቸው አቶ አያልነህ ጌጡ እና ከወይዘሮ ማንአህሎሽ ተበጀ በኢትዮጵያ ምድር በ1954 ዓ.ም ተወለዱ ። እድሜያቸው ለትምህርት እንደ ደረሰ በአካባቢው ከነበሩት የዜማ መምህር ከመሪጌታ ዲበ ኩሉ ዘንድ ተልከው ከፊደል እስከ ጸዋትወ ዜማ ተምረዋል ። የቅዳሴ ዜማ ከመምህር አባ ወልደ ትንሣኤ ጥሩነህ ፣እንዲሁም በጎጃም ክፍለ ሀገር በደምበጫ ወረዳ በብር ሸለቆ በደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ገዳም ከየኔታ ተክለ ጽድቅ ተምረዋል ። ቅኔ ለመማር ባላቸው ጉጉት የተነሣ ወደ ጎንደር ክፍለ ሀገር ደራ ወረዳ ዛራ ሚካኤል በመሄድ ፥ ብዙ ደቀ መዛሙርትን በማፍራታቸው ከሚታወቁት ከየኔታ ጥበቡ ባየ ቅኔ ከነአገባቡ ተምረዋል ። እንዲሁም ወደ ባሕር ዳር ከተማ በመጓዝ ከየኔታ መንግሥቱና ኋላም በዝዋይ ሐመረ ኖኅ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የቅኔ መምህር ከነበሩት ከመምህር አበበ ምሥጢር አደላድለዋል ።

በዘመናዊ ትምህርትም የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጎንደር ክፍለ ሀገር እንፍራዝ ከተማ እንፍራዝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፥ የመለስተኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጎንደር ከተማ በፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረው አጠናቅቀዋል ።

ስብከተ ወንጌልን በዘመናዊ መንገድ ለማቅረብ ከነበራቸው ጉጉት የተነሣ ፥ የስብከት ዘዴን ፥ የቤተ ክርስቲያን ታሪክንና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ለመማር ፥ በሸዋ ክፍለ ሀገር በሚገኘው የዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ በመግባት በዚያ የሚሰጠውን መንፈሳዊ ሥርዓተ ትምህርት ተከታትለው በመዐርግ ተመርቀዋል ።

በመቀጠልም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ገብተው ለአራት ዓመታት የሚሰጠውን የነገረ መለኮት ትምህርትና የስብከት ዘዴ ተከታትለው በዲፕሎማ ተመርቀዋል ።

የአሁኑ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ የቀድሞው አባ ጎሃ ጽባሕ የመጻሕፍትን ምሥጢር እንደ ገለጹላቸው ፥ በምክራቸውም እንዳነጿቸውና እንዳስተማሯቸው ፥ ከዚያም አልፎ ለአሁኑ ሕይወታቸው መሠረት እንደ ጣሉላቸው ይመሰክራሉ ።

አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ መዐርገ ዲቁና ፥ በወቅቱ የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ እንድርያስ በ1964 ዓ.ም ተቀብለዋል ። በመቀጠልም እንደ ኢትዮጵያ አቈጣጠር በ1978 ዓ/ም በጊዜው አሰብ ራስ ገዝ ተብሎ ይጠራ በነበረው ክፍለ ሀገር በአሰብ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከብፁዕ አቡነ በርናባስ መዐርገ ምንኩስናና ቅስና ተቀብለዋል ።

በአሰብ ራስ ገዝ በብፁዕ አቡነ በርናባስ ሥር በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊና ሰባኬ ወንጌል በመሆን ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል ። በመቀጠልም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ፥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ተመድበው በተንቀሳቃሽ ሰባኪነት አገልግለዋል ። አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ ፥ ሕይወታቸውን ለወንጌል አገልግሎት የሰጡ ፥ ታላቁንም ታናሹንም በትሕትና የሚያገለግሉ ፥ ቃላቸው ከግብራቸው የተስማማላቸው ፥ የሚኖሩትን የሚሰብኩ ፥ የሰበኩትን የሚኖሩ አባት ናቸው ። ይህም ሊታወቅ ፥ ስንቶች በሙስና የሚዋደቁለትን ሹመት ማለትም በአዲስ አበባ የቦሌ የኮተቤና የየካ አውራጃዎች ሊቀ ካህናት ይሁኑ ተብለው ሲሾሙ ፥ የኔ መዐርግ ወንጌል ናት ብለው በብዙ መከራ ውስጥ ወንጌልን የሰበኩ አባት ናቸው ።

በሚሊዮኖች የሚቈጠሩ ምእመናንን በሚስበው የስብከት አቀራረባቸው ፥ በቤተ ክርስቲያናችን ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ፥ ለዘመናዊ የስብከት ዘዴ ፋና ወጊ ተብለው ከሚጠቀሱት አባቶች አንዱ ናቸው ። በስብከታቸውም ብዙዎችን ለቅዱስ ቍርባን አብቅተዋል ። ብዙዎችን ከተሳሳተ መንገድና ትምህርት መልሰዋል ። እግዚአብሔር ለዚህ ዘመን ተስማሚ አድርጎ በሰጣቸው አንደበታቸው ከአህጉር አህጉር እየተንቀሳቀሱ መጽናናት ለሚያስፈልገውና ፥ ወንጌልን ለተጠማው ሕዝበ ክርስቲያን የወንጌልን ቃል በትሕትናና በቆራጥነት በመዝራት የብዙዎችን ልቦና አለምልመዋል ።

የመንግሥትን ለውጥ ተከትሎ በአገር ውስጥ ያለው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሁኔታ ለወንጌል አገልግሎት አመች አልሆን ሲላቸው ከሀገራቸው ተሰደው ወደ አሜሪካ ተጉዘው በሎስ አንጀለስ ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሰባኬ ወንጌልነት ተመድበው በማገልገል ዕለት ዕለት የሚያስተምሩትም ትምህርት እየተቀረጸ በሀገር ቤትና በመላው ዓለም በምትገኘዋ ቤተክርስቲያን እየተሰራጨ ትምህርታቸው ለአያሌ ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞችና እኅቶች መጽናኛና መማሪያ ብሎም በስሕተት ትምህርት ላሉት ሁሉ መልስ መስጫ በመሆን አገልግሎአል ።

አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ በአሁኑ ወቅት ፥ በመላው ዓለም በመዘዋወር ፥ በአሜሪካ፥ በካናዳ ፥ በአውሮፓ፥ በአፍሪካ ፥ በኒውዚላንድና በአውስትራሊያ እየተዘዋወሩ በማገልገል ላይ ይገኛሉ ። በዚህም አገልግሎታቸው ፥ አብያተ ክርስቲያናት በወንጌል እንዲታነጹ እንዲጽናኑ አድርገዋል ። አባ ወልደ ትንሣኤ ሕይወታቸውን ለወንጌል አገልግሎት የሰጡ አባት በመሆናቸው ፥ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዐተ ጉባኤው «ሐዲስ ሐዋርያ» በሚል ለቤተ ክርስቲያን የሰጡትን አገልግሎትና ድካማቸውን የሚገልጥ ስም ሰጥቶአቸዋል ።

ይህን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በመመልከት ፥ በማኅበረ ካህናቱ ፥ በማኅበረ ምእመናኑ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተጠቁመውና ተመርጠው ፥ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን መዐርገ ክህነት ለኤጲስ ቆጶስነት ተመርጠዋል ።

2ኛ. አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው አጭር የሕይወት ታሪክ

 አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው

አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው

አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው ከአባታቸው ከአቶ ደገፋው ዓለሙና ከእናታቸው ከወይዘሮ አየሁ ተመስገን ኅዳር 27 ቀን 1958 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተወለዱ ። አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው እድሜአቸው ለትምህርት እንደ ደረሰ ፥ በተወለዱበት አካባቢ በሚገኘው “ደብረ ኢየሱስ” ተብሎ በሚጠራው ታላቅ ገዳም ከሚገኙት የአብነት መምህራን ከመሪጌታ ዓለሙ ተገኘና ፥ ከመሪጌታ ርኁቀ መዓት ተፈራ ፥ ከፊደል እስከ ጸዋትወ ዜማ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሚገባ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ የዲቁናን መዐርግ ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ እጅ በ1970 ዓ.ም ተቀብለዋል ።
አባ ጽጌ ድንግል ኢትዮጵያ በሚገኘው በታላቁና ጥንታዊ ገዳም (ናዝሬት ኢየሱስ ገዳም) አገልግሎት ሲሰጡ ከቆዩ በኋላ ወደ ቅኔ ትምህርት ቤት በመሄድ በመጀመሪያ በመንግሥቶ ኪዳነ ምሕረት ከመሪጌታ ደጉ ፥ ከዚያም ወደ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም በመሄድ ከመሪጌታ ተስፋ ፥ እንዲሁም በደንበጫ ቅዱስ ሚካኤል ከመሪጌታ ብዙአየሁ ቅኔ ተምረዋል ። አገባቡን በሚገባ ለማሄድና ምሥጢር ለማደላደል ወደ ደብረ ወርቅ በመሄድ ከመሪጌታ ከብካብ ፥ በይጥባቆ ቅዱስ ሚካኤል ከመሪጌታ ዳንኤል ቅኔውን ከነአገባቡ አጠናቀው ተምረዋል ። የቅኔ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁም ወደ ታላቁ ገዳም በመመለስ በገዳሙ ሥርዓት መሠረት አበው መነኮሳትን በመታዘዝና በገዳሙ ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን አገልግሎት በመስጠት ከቆዩ በኋላ ፥ በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ እጅ በ1975 ዓ.ም ሥርዓተ ምንኩስናና የቅስና መዐርግ በተወለዱ በ17 ዓመታቸው ተቀብለው በገዳሙ ለሁለት ዓመታት አገልግለዋል ።

አባ ጽጌ ድንግል ወደ ዲማ ጊዮርጊስ በመሄድ የአዲስ ኪዳን ትርጓሜን ከታላቁና ታዋቂ ከሆኑት መምህር ከመምህር ማርቆስ ፣ እንዲሁም የውዳሴ ማርያምንና የቅዳሴ ማርያምን ትርጓሜ ከመምህር ዲሜጥሮስ ተምረዋል ። ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ፥ ከደገኛው አባት ከብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዘንድ ለጥቂት ጊዜ ከተቀመጡ በኋላ ፥ ወደ ዝዋይ ገዳም በመሄድ ገዳሙን እንዲያገለግሉና በገዳሙ ከሚገኘው የካህናት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ትምህርት እንዲከታተሉ ወደ ዝዋይ ተላኩ ። በማሠልጠኛው የሚሰጠውን ትምህርት ተከታትለው ፥ ከ63 ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መካከል በአንደኛ ደረጃ በመዐርግ ተመርቀዋል ። ከመምህር ዘሚካኤል የመዘገበ ቅዳሴን ትምህርት በሚገባ ተምረው እንደ ጨረሱ ለሦስት ዓመታት ያህል በዝዋይ ገዳም አገልግሎት ሰጥተዋል ።

አባ ጽጌ ድንግል ከእነዚህ ታላላቅ መምህራን የቀሰሙትን ዕውቀት በተግባር ላይ በማዋልም ፥ በብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ መልካም ፈቃድ በወለጋ ክፍለ ሀገር ነቀምት ከተማ በሚገኙት በመካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በቅስና እና በአስተዳዳሪነት ፣ በደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአስተዳዳሪነት ከመስከረም ወር 1979 ዓ.ም.እስከ ጥር ወር 1982 ዓ.ም.አገልግለዋል ። በእነዚህም ዓመታት ሁሉንም በሰላም በፍቅርና በአንድነት በመያዝ እንዲሁም ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራትና በማሠራት ለአብያተ ክርስቲያናት እድገትና ሰላም ፥ ለወንጌል አገልግሎት መስፋፋት ቅድሚያ በመስጠት በትጋት በታማኝነትና በቅንነት አገልግለዋል ። በተለይም በነቀምት ከተማ በምትገኘው በርእሰ አድባራት ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዋና አስተዳዳሪነት ባገለገሉበት ዘመን በታሪክ የሚመዘገቡና በምሳሌነት የሚጠቀሱ ቋሚ ሥራዎችን እንዲሠሩ በማድረግ ታላቅ አገልግሎት አበርክተዋል። በመቀጠልም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ፥ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊ በመሆን በደብሩ ቋሚ የስብከተ ወንጌል ፕሮግራም እንድቋቋም አድርገዋል።

በመቀጠልም የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሁነው በማገልገል ላይ ሳሉ በ1985 ዓ ም በጥር ወር በምዕራቡ ዓለም የምትገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባላቸው እውቀትና ሙያ እንዲያገለግሉ ከአምስት መነኮሳት ጋር ወደ ውጭ አገር ተላኩ ። አባ ጽጌ ድንገል ደገፋው በተላኩበት መሠረት የተሰጣቸውን አደራ ለመወጣት በካሪቢያን ደሴቶችና በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በመዘዋወር ለሁለት ዓመታት ያህል ሐዋርያዊ ተልእኮአቸውን ለመወጣት ከፍተኛ አገልግሎትን አበርክተዋል ። በዚህም ወቅት፥ አባት ከማጣት የተነሣ የተበተኑትን ሰብስበዋል ፥ የአካባቢው ተወላጆች የሆኑትን አስተምረው አጥምቀዋል ።

በመቀጠልም በአሜሪካ ወደ ሎስ አንጀለስ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመምጣት ቤተ ክርስቲያኒቱን ላለፉት 22 ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በትጋት አገልግለዋል ። በዋናነት ከሚያገለግሏት የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ባሻገር አገልጋይ ካህናት
በሌሉበት ቦታዎችና አብያተ ክርስቲያት ባልተቋቋመባቸው ቦታዎች አብያተ ክርስቲያናት እንዲቋቋሙ በማድረግና የወንጌል አገልግሎትን በማስፋፋት በውጭ ዓለም በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከቱ ታላቅ ሐዋርያ ናቸው ።

እንዲሁም ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ በአስተዳደር ልዩነት የቆየችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ለማድረግ በተጀመረው የሰላምና አንድነት ጉዞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የሰላም ሐዋርያ በመሆን ከሚጥሩ አባቶች ጋር በመሰለፍ ያደረጉትን ከፍተኛ ጥረት ታሪክና ትውልድ የማይረሳው ነው ።

በዘመናዊ ትምህርት ራሳቸውን አዘጋጅተው ትውልዱን ለማገልገል ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት መሠረት ፥ በአገር ውስጥ የአንደኛ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ፥ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከካሊፎርንያ እስቴት ዩኒቨርስቲ ኖርዝ ሪጅ በማኅበራዊ ጥናትና በቢዝነስ አስተዳደር (B.A.Degree in Sociology and Business Administration) ሁለተኛ ድግሪያቸውን ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ደሚንገዝ ሂልስ በማኅበራዊ ጥናት ማስተር (M.A.Degree inSociology) እንደ ገና በካሊፎርንያ ዩኒቨርስቲ እርቫይን በክሊኒካል ሳይኮሎጂ ማስተር ድግሪ (M.A. Degree in Clinical Psychology) የማስተርስ ድግሪ ተመርቀዋል ። በአሁኑ ሰዓት የመጨረሻ ድግሪያቸውን ለመያዝ በካሊፎርንያ ዩኒቨርስቲ እርቫይን የዶክትሬት ድግሪያቸውን በክሊኒካል ሳይኮሎጂ (Ph.D. in Clinical Psychology) የመመረቂያ ጥናታቸውን በመሥራት ላይ ይገኛሉ ።

በውጭ ዓለም በሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊ አመራር ሥር ላለቺው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፣ አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው ባላቸው የአስተዳደርና የአመራር ችሎታ ፥ እንዲሁም መፈሳዊና ዘመናዊ እውቀት የመጀመሪያው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሁነው በመሾም በስደት ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ለማደራጀትና በታማኝነት ለማገልገል ከፍተኛ ኃላፊነትን ተቀብለው ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የአስተዳደርና የመምሪያ ኃላፊዎችን በማቋቋምና በመሥራት ላይ ይገኛሉ ። በዚህም አግልግሎታቸው ወቅት የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤቱ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. እንዲገዛ ፤ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራበት ሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲዘጋጅና የተለያዩ የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲቋቋሙና የተደራጀ ሥራ እንዲሠራ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉ ታላቅ አባት ናቸው ።

ይህን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በማየት ፥ በማኅበረ ካህናቱ ፥ በማኅበረ ምእመናኑ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ተጠቁመውና ተመርጠው ፥ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን መዐርገ ክህነት ለኤጲስ ቆጶስነት ተመርጠዋል ።

3ኛ. የአባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ አጭር የሕይወት ታሪክ

አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ

አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ

አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ በሰሜን ኢትዮጵያ መስከረም 30 1950 ዓ.ም ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት እንደ ደረሰ ፥ በተወለዱበት አካባቢ ፥ በታላቁ ደብር በጉና ሚካኤል ደብር ከመሪጌታ ገበየሁና ከልጃቸው መሪጌታ ሙሉጌታ መዝሙረ ዳዊትና የቃል ትምህርት ተምረዋል ።
በመቀጠልም ፥ መሪጌታ አክሊሉ እና መሪጌታ ከሃሊ ከተባሉ መምህራን ምዕራፍና ጾመ ድጓ ተምረዋል ። ለቅኔ ትምህርት ወደ ጎጃም በመሄድ ከመሪጌታ ተከሥተ ፣ ኋላም በዛራ ሚካኤል ከሚገኙት ከታላቁ ሊቅ ከመልአከ ምሕረት ጥበቡ ቅኔን ከነአገባቡ ተምረዋል ። ከቅኔ መምህራቸው ከመልአከ ምሕረት ጥበቡ ጋር ያላቸው ፍቅርና ቅርርብ ልዩ በመሆኑ ፥ “አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ” ተብለው የሚጠሩት በዚህ ምክንያት ነው ።
የቅኔ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ፥ አቋቋም ለመማር በነበራቸው ጽኑእ ፍላጎት መሠረት ፥ በጎንደር ዓየር ማረፊያ አጠገብ በምትገኘው በማርያም ደብር ከመሪጌታ ኤርምያስ ሞላ ፣ ጉቢያ ኢየሱስ ደግሞ ከመሪጌታ ልዑል ፥ እንዲሁም በዋውቻ ዮሐንስ ከመሪጌታ መዝገቡ በሚገባ ተምረዋል ።
አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ ለስብከተ ወንጌልና የቅዱሳት መጻሕፍትን ዓለም ለመመርመር ከፍተኛ ፍቅር ስለ ነበራቸው ፥ ትርጓሜያቱን በሚገባ ለማሄድ ይመኙ ነበር። በመሆኑም ይህን ምኞታቸውን ፍጻሜ ለማድረስ ፥ የትርጓሜው ማዕከል ወደ ሆነው ወደ ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔ ዓለም በመምጣት ፥ ከታላቁ መምህር ከሊቀ ሊቃውንት መንክር መኮነን የመጻሕፍት ትርጓሜ ተምረዋል ።

ዘመናዊ ትምህርት ለመማር በነበራቸው ጉጉትም ፥ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርት ጎን ለጎን ፥ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጎንደር ኅብረት እና ደብረ ሰላም ትምህርት ቤቶች ፤ የመለስተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ጳውሎስ ትምህርት ቤት ፣ የሁለተኛ
ደረጃ ትምህርታቸውን በጎንደር ፋሲለደስ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል ።

የነገረ መለኮት ትምህርታቸውን በጥልቀት ለመከታተል በነበራቸው ጉጉት ፥ በአዲስ አበባ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ የነገረ መለኮት ሴሚናሪ በዲፕሎማ ተመርቀዋል ። ከአገር ከወጡ በኋላም በነገረ መለኮት ትምህርቱ እጅግ ታዋቂ በሆነውና በአሜሪካ በሚገኘው በቅዱስ ቭላድሚር የነገረ መለኮት ሴሚናሪ (St. Vladi- mir theological seminary የማስተርስ ኦፍ ዲቪኒቲ ድግሪያቸውን ። እንዲሁም ተጨማሪ የማስተርስ ድግሪያቸውን
በሃይማኖት ትምህርት በኒዮርክ ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል ። በአትላንታ ጆርጂያ በሚገኘው የኢሞሪ ዩንቨርስቲ በክሊኒካል ፓስቶራል ኢጁኬሽን የምስክር ወረቀት አግኝተዋል ። በሳንፍራንሲስኮ ቴዎሎጂካል ሴሚናሪ የዶክትሬት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ።

አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ መዐርገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ በደብረ ማርቆስ ከተማ በ1966 ዓ ም ። መዐርገ ቅስና ደግሞ ፥ በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ ከብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በ1983 ዓ ም ተቀብለዋል ።

አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ ፥ ከልጅነት እስከ እውቀት በገበዩት ሰፊ የሆነ የትምህርትና የሥራ ልምድ ቤተ ክርስቲያንን በብዙ አገልግለዋል ። ከእነዚህም መካከል በኢትዮጵያ 1ኛ/ በአዲስ አበባ የወልደ ነጎድጓድ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪ ፤ 2ኛ/ የጎንደር ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌልና የሰንበት ምህርት ቤቶች ክፍል ኃላፊ ፤ 3ኛ/ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፤ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሁነው አገልግለዋል ።

ወደ አሜሪካ ከመጡ በኋላም በአሜሪካ በሚገኙ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም በኒውዮርክ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዋና ካህንነት ፤ በሲያትል መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በሰባኬ ወንጌልነት ፤ በአትላንታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በክህነትና በስብከተ ወንጌል አገልግለዋል ።

አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለስደት ከተዳረጉበት ጊዜ ጀምሮ ፥ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር በሚያደርገው ጥረት በግንባር ቀደምነት የተሰለፉ ፥ የሲኖዶሱን ድምጽ በተለያዩ ሚዲያዎች በማስተላለፍ ፥ በማስተዋወቅ የደከሙ አባት ናቸው ። በስብከት ዘዴ አቀራረባቸውም የሰዎችን ሕይወት በጥልቀት የሚመረምር ሕይወታዊ ትምህርት በማቅረብ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ሰባኬ ወንጌል ናቸው ። በአሁኑ ወቅትም በአንታላንታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ካላቸው የስብከተ ወንጌል ኃላፊነት በተጨማሪ ፥ በቅዱስ ሲኖዶሱ ሥር በተቋቋመው የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምሪያ ዋና አስተባባሪ ሁነው እስከአሁን ድረስ በታማኝነትና በትጋት ያገለግላሉ ።
ይህን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በማየት ፥ በማኅበረ ካህናቱ ፥ በማኅበረ ምእመናኑ ፥ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ተጠቁመውና ተመርጠው ፥ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ለከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን መዐርገ ክህነት ለኤጲስ ቆጶስነት ተመርጠዋል ።

4ኛ. የመልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ዳኘው አጭር የሕይወት ታሪክ

አባ ሳሙኤል ዳኘው

አባ ሳሙኤል ዳኘው

አባ ሳሙኤል ዳኘው ከአባታቸው ከሊቀ ጠበብት ዳኘው በላይ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አመሁ ታደሰ በ1955 ዓም በቅድስት ሐገር ኢትዮጵያ ተወለዱ ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በተወለዱበት ደብር ከፊደል እስከ ዳዊት ከመሪጌታ መዝገቡ ለቃል ተምረዋል ። በመቀጠልም የድጓ መምህር ከነበሩት ከመርጌታ በቀለ ምሕረቱ ጾመ ድጓና ምዕራፍ ተምረዋል ። ከዚያም በጎጃም ክፍለ ሀገር በቀራንዮ መድኀኔ ዓለም የቅኔ መምህር ከነበሩት ከመምህር ተስፋ ተገኝ ቅኔ ተቀኝተው እስከ አስነጋሪነት ደርሰዋል ። ቅኔያቸውን ለማስፋት ባላቸው ምኞት ፥ ወደ ጎንጅ በመሄድ በጽላልሽ አማኑኤል ደብር የቅኔ መምህርት ከነበሩትና ብዙ የቅኔ መምህራንን በማፍራት በኢትዮጵያ ሴቶች ታሪክ ታዋቂ ከሆኑት ባለቅኔ ከእመይቴ ገላነሽ ዘንድ በመግባት ቅኔአቸውን አደላድለዋል ።

እርሳቸው ካረፉ በኋላም በዚሁ ደብር የድጓ መምህር ከነበሩት ከመርጌታ ድረስ ሽታ ድጓውን አሂደዋል ። ወደ አቋኋም ቤት በመሄድም በፎገራ ወረዳ በመነጉዘር ኢየሱስ ደብር የአቋቋም መምህር ከነበሩት ከመርጌታ ምሥራቅ ለአራት ዓመት አቋቋም በሚገባ ተምረዋል ። ከዚያም ወደ ዝማሬ መዋሥዕት ቤት በመሄድ በእስቴ ወረዳ በበር ጊዮርጊስ ያስተምሩ ከነበሩትና በርካታ ሊቃውንትን ካፈሩት ከመርጌታ ውብ አግኝ በመሄድ ዝማሬ መዋሥዕት አጠናቀው ተምረዋል ። በመቀጠልም ወደ ባሕር ዳር ከተማ በበዓታ ለማርያም ደብር የቅዳሴ መምህር ከነበሩት ከመምህር አክሊለ ብርሃን ኃይለ ሥላሴ ዘንድ በመግባት ቅዳሴ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል ።

ታዋቂ ከሆኑት የአገራችን ሊቃውንት የቀሰሙትን ትምህርት ዘመናዊ በሆነ አቀራረብ ማቅረብ እንዲያስችላቸው በማሰብ ፥ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ፥ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው ለሦስት ወራት ለካህናት የሚሰጠውን ኮርስ ተከታትለው የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል ። ከዚያም ዓይናማ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን በማፍራት ወደሚታወቀው ወደ ሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት ገብተው ለአራት ዓመታት የሚሰጠውን የነገረ መለኮት ትምህርት ተከታትለው በዲፕሎማ ተመርቀዋል ።

አባ ሳሙኤል ዳኘው ፥ መዐርገ ዲቁና የጎጃም ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጰስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በ1972 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር በሞጣ ከተማ ተቀብለዋል ። ሥርዓተ ምንኩስና በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የተቀሉ ሲሆን ፥ መዐርገ ቅስና ደግሞ፥ በ1986 ዓ ም የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም የበላይ ኃላፊ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ተቀብለዋል ።
አባ ሳሙኤል ዳኘው ፥ ባካበቱት ሰፊ ዕውቀት ቤተ ክርስቲያንን በብዙ አገልግለዋል። በመጀመሪያ በከንባታ ሀድያና ጉራጌ ሀገረ ስብከት የቅዳሴ መምህር ሁነው ለአምስት ዓመታት ያክል አገልግለዋል ።

በመቀጠም ወደ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ፥ በጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስደዳዳሪ በመሆን፥ በአካባቢው አብያተ ክርስቲያናትን በማቋቋም ፥ መጠነ ሰፊ ሥራ ሠርተዋል ። በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶሱ የመላው አፍሪካ ሊቀ ካህናት በመሆንም፥ በአፍሪካ ሀገሮች እየተዘዋወሩ በማስተማር ስደተኛውን ሕዝብ ለአሥራ አምስት ዓመታት በትምህርተ ወንጌልና በአባታዊ ጉብኝት አጽናንተዋል ።

ወደ አሜሪካ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በአሁኑ ወቅት ፥ የዴንቨር የዳግሚት ግሸን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል ላይ ይገኛሉ ።
አባ ሳሙኤል ዳኘው ለአገልግሎት በተሰማሩበት አካባቢ በሙሉ የፍቅርና የሰላም አባት በመሆን ፥ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሕዝቡን በመከራው በኀዘኑ የሚያጽናኑት አባት ስለ ሆኑ በምእመናን ዘንድ እጅግ ተወዳጅ አባት ናቸው ። በስብከተ ወንጌሉ ፥ በቅዳሴው፥ በማኅሌቱ ካላቸው እጅግ ታላቅ ከሆነው ዕውቀት ጋር ትሕትናቸውና አባታዊ አርአያቸው እንዴት ሕዝቡን በፍቅር አንድ አድርጎ እንዳኖረ ፥ በደቡብ አፍሪካና በሌሎችም የአፍሪካ አገሮች ያሉ ምእመናን ምስክር ናቸው ።

በመሆኑም ይህን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በማየት ፥ በማኅበረ ካህናቱ ፥ በማኅበረ ምእመናኑ ፥ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ተጠቁመውና ተመርጠው ፥ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን መዐርገ ክህነት ለኤጲስ ቆጶስነት ተመርጠዋል ።

5ኛ. መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ተሻገር አጭር የሕይወት ታሪክ

መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ተሻገር ከአባታቸው ከአቶ ተሻገር ተገኘ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ወርቄ ካሳየ በጎንደር ክፍለ ሀገር በእብናት ወረዳ ልዩ መጠሪያ ስሙ ደብረ ይባቤ ገዴ ማርያም በ1945 ዓ.ም ተወለዱ ።

አባ ሳሙኤል ተሻገር

አባ ሳሙኤል ተሻገር

እድሜያቸው ለትምህርት እንደ ደረሰ ፥ ብዙ ሊቃውንትን ካፈሩት ፥ ከመሪጌታ አግማስ / ቆሞስ አባ አበራ ዓለሙ ዘንድ ተልከው ከፊደል እስከ ዳዊት ተምረዋል ። በመቀጠል ቅራረም ኢየሱስ ከመሪጌታ ተሻገር ዘውዴ በመሄድ የግብረ ዲቁና ትምህርት እንዳጠናቀቁ ፥ ከታላቁ ምሁር ከመሪጌታ ጀምበር እና ከልጃቸው ከመሪጌታ ነጋ ጀምበር ፥ አዛሁር ኪዳነ ምሕረት ጸዋትወ ዜማ ማለትም ጾመ ድጓ እና ምዕራፍ ተምረዋል ።
መዐርገ ዲቁናን በ1966 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን በባሕርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ከተቀበሉ በኋላ ፥ ወደ ተወለዱበት ደብር በመመለስ ደብራቸውን በዲቁና ለሁለት ዓመታት አገለገለዋል ። ትምህርታቸውን ለማስፋት ባላቸው ፍላጎት ፥ ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር በመሄድ ደብረ ገነት ኤልያስ ከመሪጌታ ጥበቡ ዜማውን ከከለሱ በኋላ ፥ የቅኔ ትምህርት ከመሪጌታ መሠረት ተምረዋል ። ቅኔያቸውን ለማስፋት ወደ ደንበጫ ቅዱስ ሚካኤል በመሄድ ከመሪጌታ ብዙአየሁ ቅኔያቸውን አደላድለዋል ።

ዘመናዊ ትምህርትን በተመለከተ ፥ መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ተሻገር በ1972 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ታቦር መንፈሳዊ አዳሪ ትምህርት ቤት በመግባት ፥ የአንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ። በ1977 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በዲቁና እያገለገሉ ፥ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በምሥራቅ አጠቃላይ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቅቀዋል ። በመቀጠልም ፥ በብፁዕ አባታችን አቡነ መልከጼዴቅ መልካም ፈቃድና ትእዛዝ በ1983 ዓ.ም ወደ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በመግባት በዚያ የሚሰጠውን ሥርዓተ ትምህርት ተከታትለዋል ። በመቀጠልም ወደ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም የካህናት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመግባት በዚያ መዝገብ ቅዳሴ ተምረው በቅዳሴ መምህርነት ተመርቀዋል ።

መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ተሻገር ፥ በነሐሴ 24 ቀን 1987 ዓ.ም በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስናን ተቀብለዋል ፤ በመቀጠልም በ1988 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ መዓርገ ቅስናን ማዕረገ ቁምስናን ደግሞ ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ተቀብለዋል።

መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ፥ ቤተ ክርስቲያናቸውን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል ። በዚህም መሠረት ወደ አዲስ አበባ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ፥ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ፥ በዲቁናና በሊቀ ዲቁና አገልግሎት ለአሥራ ሦስት ዓመታት ፥ በቄሰ ገበዝነት ለአንድ ዓመት አገልግለዋል ። በቅድስት ሥላሴ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ በመሆን በመሆን አገልገዋል ። በዚህም ሕፃናት ልጆች በፈሪሃ እግዚአብሔር ታንጸው እንዲያድጉ በማድረግ የሃይማኖት አባትነታቸውን ተግባር ተወጥተዋል ። በዚሁ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ፥ በገንዘብ ቤት አገልግሎት ለሁለት ዓመት አገልገዋል ።

በ1989 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ መልካም ፈቃድ እና ተእዛዝ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ወደ ካናዳ በመምጣት ፥ በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ እና በሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ፈቃድ በቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ረዳት አስተዳዳሪ በመሆን ለአራት ዓመታት አገልግለዋል ። በመቀጠልም በኦቶዋ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በአስተዳዳሪነት ለአንድ ዓመት ፥ በካልጋሪ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በቅስና ለአራት ዓመታት አገልገዋል ።

ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለአሥራ አንድ ዓመታት በኤድመንተን ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በአስተዳዳሪነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ ።

ይህን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በማየት ፥ በማኅበረ ካህናቱ ፥ በማኅበረ ምእመናኑ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተጠቁመው ፥ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን መዐርገ ክህነት ለኤጲስ ቆጶስነት ተመርጠዋል።

6ኛ. የመልአከ ብርሃናት አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት አጭር የሕወት ታሪክ

መልአከ ብርሃናት አባ ገብረ ሥላሴ (ታደሰ) የኋላሸት በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ በደብረ ገነት አዛውር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ነሐሴ 16 ቀን 1958 ዓ/ም ተወለዱ ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ቦታቸው ከመጀመሪያው ክፍለ ትምህርት አንሥቶ በየደረጃው ምዕራፉን ፥ ጾመ ድጓውን ፥ ድጓውን ከታወቁት መምህር ከመሪጌታ ጀንበር ወንድም በሚገባ ተምረዋል ።

አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት

አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት

የቅኔ ትምህርታቸውንም በደጋ መልዛ ሹምዬ ማርያም ከምትባለው ደብር ከመሪጌታ ፍቅረ ማርያም ተምረዋል ። በተጨማሪም የቅኔ ትምህርታቸውን በሚገባ ለማጠንከር በነበራቸው ፍላጎት ፥ ወደ ታላቁ ደብር ደብረ ታቦር ኢየሱስ በመሄድ ከመሪጌታ ይኄይስ ፈንቴ ቅኔ ከነአገባቡ በሚገባ ተምረዋል ። ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የዝማሬና የመዋሥዕት ትምህርታቸውንም በአዲስ አበባ በገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ጠበብት ኅሩይ ለገሠ ተምረዋል ። የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜንም ውዳሴ ማርያም ፥ ቅዳሴ ማርያም እና የኪዳን ትርጓሜ ፤ ከሙሉ የቅዳሴ ዜማ ጋር በዚያው በገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከመልአከ ብርሃናት መምህር ተስፋ ወርቅነህ በሚገባ ተምረዋል ።
አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት ከቤተ ክርስቲያኑ ትምህርትና አገልግሎት ጎን ለጎን ፥ የዘመናዊውን ትምህርት በመከታተል ፥ የአንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ የጽጌ በሻህ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በዚያው በአዲስ አበባ በሚገኘው እቴጌ መነን ትምህርት ቤት ተከታተዋል።

የከፍተኛ ትምህርታቸውንም በአሜሪካ ዋሽንግተን ግዛት በሲያትል ቮኬሽናል ኢንስቲቲዩት በቢዝነስ ኮምፒውተር አካውንቲንግ የተመረቁ ሲሆን ፤ በሲያትል ዩኒቨርስቲ የፓስተራል ሊደር ሽፕ እና ካውንስሊንግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ።

አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት ፥ መዐርገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ እንድርያስ የጎንደር ሀገረ ስብክት ሊቀ ጳጳስ የተቀበሉ ሲሆን ፤ ሥርዓተ ምንኩስናን እና መዐርገ ቅስናን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ እጅ ተቀብለዋል ።

አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት ቤተ ክርስቲያን ከልጅነት እስከ እውቀት ባስተማረቻቸው እና ባገኙት ሰፊ የሥራ ልምድ ቤተ ክርስቲያንን በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል ። ከእነዚህም መካከል ፥ ባደጉበት ደብር በዲቁና ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በዲቁና ፥ በሊቀ ዲቁና ፥ በዋና ጸሐፊነትና በሰንበት ትምህርት መምህርነት ፣ በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በዲቁናና፥ በሊቀ ዲቁና ። በናይሮቢ ኬንያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዲቁና ፥ በሊቀ ዲቁና ፥ በዋና ጸሐፊነትና በሰንበት ትምህርት ቤት መምህርነት ፤ በኦክላንድ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በዲቁና ፤ በሲያትል ዋሽንግተን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ደግሞ በሊቀ ዲያቆንነት ፥ በዋና ጸሐፊነት ፥ በሰንበት ትምህርት ቤት መምህርነት ያገለገሉ ሲሆን ። በአሁኑ ወቅት ደግሞ የገዳሙ አስተዳዳሪ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ ።
ይህን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በመመልከት ፥ በማኅበረ ካህናቱ ፥ በማኅበረ ምእመናኑ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተጠቁመው ፥ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን መዐርገ ክህነት ለኤጲስ ቆጶስነት ተመርጠዋል።

ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ይቆየን ።

↧

↧

ለጠቅላላ ዕውቀት: አስሩ የዓለማችን ቆሻሻ ከተሞች

$
0
0

በቅርቡ ሜርሰን ሄልዝ ኤንድ ሳኒቴሽን (Mercen Health and Sanitation Index) የተባለ ተቋም 25 የአለማችንን ከተሞች ቆሻሻ ሲል ፈርጇቸዋል፡፡ ተቋሙ እንደሚለው እነዚህ ከተሞች ንጽህና የሌላቸውና አየራቸው የተበከለ እንዲሁም በውስጣቸው የሚያልፉ ወንዞች በቆሻሻ የተሞሉ ናቸው፡፡ ተቋሙ በቆሻሻነት የፈረጃቸውን የአለማችን ከተሞች በቅደም ተከተል ሲያስቀምጥ የአዲስ አበባ መገኛ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሆኗል፡፡ አስሩ ቆሻሻ ከተሞች በቅደም ተከተል እነዚህ ናቸው፡፡
zehabesha facts

1.ባኩ (አዘርባጃን)
የነዳጅ ሃብት እንዳላት የሚነገርላት አዘርባጃን በዋና ከተማዋ በኩል የቆሻሻነት ስሟን ተከናንባለች፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ በከፍተኛ የአየር ብክለት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህም ሳቢያ ለህይወት አደገኛ ተብላ ተፈርጃለች፡፡ በካስፒያን ባህር የተከበበችው አዘርባጃን በነዳጅ ማውጣት ሂደትና በመርከቦች እንቅስቃሴ ወቅት በሚወጣ ጭስ የታፈነች መሆኗን የከተሞቹን ደረጃ ያወጣው ተቋም ገልጾዋል፡፡

2.ዳካ (ባንግላዲሽ)
ወንዞቿ ተበክለዋል፡፡ አየሯ ቆሽሾዋል፡፡ በየጎዳናዎቿ ላይ የወዳደቁ ቆሻሻ ነገሮችን መመልከት ብርቅ አይደለም፡፡ ይህቺ ከተማ ዳካ ትባላለች፡፡ የባንግላዲሽ ርዕሰ መዲና፡፡
በዚህች ከተማ በርካታ ሰዎች በጣም በተጠጋጋ ሁኔታ የሚኖሩ ሲሆን በዚህም ሳቢያ ለበሽታና ለሞት የመጋለጥ እድላቸው ሠፊ ነው፡፡

3. አንታናናሪቮ
(ማዳጋስካር)
የህዝብ ቁጥሯ በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጊዜ ወደጊዜ ለአየር ብክለትና ለንጽህና ጉድለት እየተጋለጠች ነው፡፡ 8ኛዋ አህጉር በሚል ቅጽል ስም የምትጠራውና በህንድ ውቅያኖስ ላይ የሠፈረችው ማዳጋስካር ዋና ከተማዋ በቆሻሻነት 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

4.ፖርቶ ፕሪንስ (ሄይቲ)
ከአመታት በፊት ከባድ ርዕደ መሬት ያስተናገደችውና በርካታ ዜጎቿን ያጣችው ብሎም የመሠረተ ልማቷ የወደመባት ሄይቲ ዋና ከተማ ፖርቶ ፕሪንስ ቆሻሻ ናት፡፡ አየሯና ውሃዋ ተበክሏል፡፡ የአየር ብክለትን ለመከላከል የሚደረገው እንቅስቃሴ ደካማ መሆን ለከተማዋ መቆሸሽ ምክንያት ነው፡፡ በሙስና የሚታሙት የሄይቲ ባለስልጣናት ለህብረተሰቡ ጤና ግድ ያላቸው አይመስሉም፡፡

5.ሜክሲኮ ሲቲ
(ሜክሲኮ)
ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ካሉት ዋና ከተሞች ሁሉ የሜክሲኮ ሲቲን ያህል በአየር ብክለት የተጎዳ የለም፡፡ ለዚያም ነው ከተማዋ ሁሌም በጭስ ተሸፍና የምትታየው፡፡

6.አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ)
የኛዋ ከተማ አዲስ አበባ አፍንጫችን ይዘን የምናልፍባቸው አካባቢዎችና ለማየት የሚቀፉ ወንዞችን የያዘች ከተማ ናት፡፡ ከፍተኛ የንጽህና ጉድለት ያለባትና ከክልል ከተሞች እንኳ በእጅጉ ባነሰ ደረጃ ላይ የምትገኘው አዲስ አበባ ከአለማችን ቆሻሻ ከተሞች ጎራ ተመድባለች፡፡ ሜርሰር ሄልዝ እንደሚለው በአዲስ አበባ ለውሃ ወለድ በሽታ የመጋለጥ እድል ከፍተኛ ነው፡፡ ልጆች ያለ እድሜያቸው የሚሞቱትም ለዚህ ነው ብሏል፡፡

7.ሙምባይ (ህንድ)
የህንድ መንግስት የሙምባይ ከተማን የንጽህና ችግር ለመቅረፍና የአየር ብክለትን ለመከላከል 1 ቢሊዮን ዶላር መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የአለማችን ቆሻሻ ከተሞች ጎራ ከመሰለፍ አላዳናትም፡፡

8.ባግዳድ (ኢራቅ)
የኢራቅ ህዝቦች ችግራቸው ጦርነት ብቻ አይደለም፡፡ በየዕለቱ ድንገት በሚፈነዱ ቦንቦች ብቻ ሳይሆን በውሃ ወለድ በሽታ ጭምር ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ በተለያየ ጊዜ የኮሌራ በሽታ ተከስቶ በርካታ የባግዳድ ነዋሪዎችን ገድሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም እንደሚለው በሚቃጠል ነዳጅና ከጦር መሳሪያዎች በሚወጣ ጭስ ሳቢያ ባግዳድ በአየር ብክለትም የተጎዳች ከተማ ናት፡፡

9.አልማቲ (ካዛኪስታን)
ነዋሪዎቿ ግዴለሽ ናቸው፡፡ የቤታቸውን ቆሻሻ ሁሉ እያወጡ በየመንገዱ ሲወረውሩ እፍረት አይሰማቸውም፡፡ መርዛማ የሆኑ ገዳይ ኬሚካሎችን ሳይቀር በግዴለሽነት በየቦታው ይጥላሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም የካዛኪስታንዋ ከተማ አልማቲ ለኑሮ የማትመች ሆናለች፡፡

10.ብራዛቪል
(ኮንጎ)
የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ያለባት ብራዛቪል ለጤና የማይመቹ ከሚባሉ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ የንጽህና ጉድለትና የአየር መበከልም ሌሎች የከተማዋ ራስ ምታቶች ናቸው፡፡

Translated by Kumneger Magazine

↧

“የካናዳ ኢምባሲ ፓስፖርቴን መልሶልኛል.. ወደ ህክምና ልሄድ ነው”–ተወዳጁ ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አንጋፋው ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ ለህክምና ወደ ጣሊያን ሊሄድ ነው:: ዓለማየሁ እሸቴ ኮሌስትሮል ባስከተለበት የደም መዘጋት ሳቢያ በካናዳ ሊያደርገው የነበረውን ኮንሰርት ወደ ኦገስት አዘዋውሮ ወደ ህክምናው እንደሚሄድ ከታዲያስ አዲስ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ላይ ተናግሯል:: ያዳምጡት::

“የካናዳ ኢምባሲ ፓስፖርቴን መልሶልኛል.. ወደ ህክምና ልሄድ ነው” – ተወዳጁ ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ

↧

Sport: ኢብራሒም ጀይላኒ የረመዳን ሩጫ ቀናዉ

$
0
0

jeilan
ቢቢኤን ሰኔ 11/2008

ሶማሊ-እንግሊዛዊዉን ሙሐመድ ፋራህ በማሽነፉ የሚታወቀዉ ኢብራሒም ጄይላኒ አሸነፈ። በረመዳን ባለፈዉ ሀሙስ ስቶክሆልም ስዉዲን ዉስጥ በተደረገዉ የ5000 ሜትር የሩጫ ዉድድር ላይ ኢብራሒም ጅይላኒ አንደኛ ወጥቷል። ኢትዮጵያን ወክለዉ ከሚወዳደሩት ሯጮች መካከል የተለያ ማሊያ የለበሰዉ ኢብራሒም የአንደኝነት ቦታዉን ይዞ ይመራ የነበረዉን ዮሚፍ ቀጄልቻን በመቀድም ነዉ አንደኛ ለመዉጣት የቻለዉ። በዉጤቱም ዮሚፍ ቀጄልቻ ሁለተኛ ሲሆን ሙክታር እድሪስ ሶስተኛ ወጥቷል።

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ያለዉን ቦታ በመያዝ ኢትዮጵያዉያን እንዳሸነፉበት በታወቀዉ የዳይመንድ ሊግ ዉድድር ኢብራሒም ጀይላኒ፣ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ሙክታር እድሪስ፣ይገረም ደምመላሽ፣የኔነዉ አላምረዉ፣ሰለሞን ብርሃኑ ከአንድ እስከ ስድስት ያለዉን ቦታ ሲይዙ ጌታነህ ታምሬ ሰባተኛ ወጥቷል።

ኢብራሒምና ሙክታር ከድል በኋላ ስጁድ የወረዱ ሲሆን ሲተቃቀፉም ታይቷል።ቢቢኤን አትሌቶቻችንን እንኳን ቀናቹ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

↧

ሰበር ዜና: ዛሬ የተሾሙት ሊቀጳጳሳት የጵጵስና ስምና የተመደቡበት ሃገረስብከት እጃችን ገባ |በጥቅምት ተጨማሪ 7 ጳጳሳት ይሾማሉ

$
0
0

abune bernabas
(ዘ-ሐበሻ) ድረገጻችን ዘ-ሐበሻ ትናንት በሰበር ዜና ዛሬ በስደት የሚገኘው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለ6 ጳጳሳት ሹመት እንደሚሰጥ ዘግባ ነበር:: በዚህም መሠረት ዛሬ በኦክላንድ ካሊፎርኒያ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆርዮስ በተገኙበት ለነዚህ 6 ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተስጥቷቸዋል::

በትናንቱ ሰበር ዜናችን ላይ የአዳዲሶቹን ጳጳሳት የጵጵስና ስም እና እንዲሁም የት ሃገረሰብከት እንደሚመደቡ መረጃዎችን አሰባስበን ይዘን እንመለሳለን ብለን ቃል በገባነው መሰረት መረጃዎቹ ደርሰውናል::

1ኛ. አባ ወልደ ትንሳኤ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ በርናባስ የካሊፎርኒያ ጳጳስ
2ኛ. 
አባ ጽጌ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት ጳጳስ
3ኛ. አባ ገብረ ሥላሴ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአውስትራልያ ጳጳስ
4ኛ. አባ ሳሙኤል ብፁዕ – የጵጵስና መጠሪያቸው – አቡነ ናትናኤል የደቡብ አፍሪካ ጳጳስ
5ኛ. 
አባ ሳሙኤል – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኤድመንተን ጳጳስ
6ኛ. 
አባ ገብረ ስላሴ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የኦሪገን ጳጳስ

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳሉት በቀጣይ 7 ቆሞሳት የተመረጡ ሲሆን 
በኮሎቦስ ኦሃዮ በጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስርአተ ሲመቱ ይፈፀማል:: በስደት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ከመቸውም በበለጠ እድገት እያሳየ ነው የሚሉት ምንጮቻችን በቅርቡ ብዙ ስራዎችን የሚሰሩ ጳጳሳት እየተቀላቀሉት ነው ብለዋል::

↧
↧

ከማን አንሼ!!! –አገሬ አዲስ

$
0
0

በልጅነቴ እንደተረት የተነገረኝ ምሳሌ አሁን ካረጀሁም በዃላ በቁም ነገር ጨዋታ በሚመስል መልኩ ቀርቦ ለማዳመጥ በቅቻለሁ።ዕድሜ ደጉ!!
ተረቱ እንዲህ ነው።እንስሳት ጉባኤ ላይ ተቀምጠው ውይይት ሲያደርጉ የመናገር ቅድሚያ የሚሰጠው በአካሉ ጎልቶና ፈርጥሞ ለሚታየው አውሬ ወይም እንስሳ ነበር። የሌሎቹ ደቃቃና ቀጫጫ፣እንስሳት ድምጽ የመስጠቱ ዕድል እየተነፈጋቸው ሁል ጊዜ የትላልቆቹ አድማጭ፣ጭፍራና አድናቂ ብቻ ሆነው እንዲኖሩ ይገደዱ ነበር።ታዲያ በዚህ አይነቱ አለእኩልነትና የመብት ጥሰት የተበሳጨችው አንድ እንቁራሪት ከሌሎቹ መካከል በድፍረት ወጥታ “እንዴ ሁል ጊዜ የእኛ ድምጽ አይሰማም፣ለመናገርም መብት የለንም፣ቅድሚያ የሚሰጠው ሁል ጊዜ ለዝሁኑ ነው፤ ለምን እንደዚያ ይሆናል?ማን ከማንስ ያንሳል?” ብላ በምሬት ተናገረች።እሷን መሳይ እንስሳቶች የእንቁራሪትን ሃሳብ በመደገፍ አጉረመረሙ። ስብሰባውን ይመራ የነበረው አንበሳ ጥያቄና ተቃውሞው ወደ እራሱ እንደሚመጣ በማወቅ በመዳፉ መሬቱን ደበደበና ዝምታ እንሲፍን በማግሳት ሁሉንም ጸት እንዲሉ ካደረገ በዃላ “አዎ በእኛ በእንስሳቱ መካከል መከባበር የተገባ ነው።ትንሹ ለትልቁ አክብሮት መስጠት ይጠበቅበታል፤ታላቅነት ደግሞ የተፈጥሮ ስጦታ ነው።ታዲያ ከዚያ የተፈጥሮ ስጦታ ውጭ እራሱን ትልቅ የሚያደርግ እንስሳ አለ?”ብሎ ዓይኑን እያፈጠጠ ወደ እንቁራሪቷና ወደሌሎቹ ደጋፊዎቿ በመመልከት እንደተለመደው ካለምንም ተቃውሞ አሰራሩንና ባህሉን ተቀብለው እንዲያድሩ አስጠነቀቀ።እጄን አልሰጥም ያለችው እንቁራሪት “ማን ከማን ያንሳል?ማበጡንም ቢሆን እናውቅበታለን” አለችና ያለ የሌለ ሃይሏን ሰብስባና ትንፋሿን ውጣ ለመወጣጠር ስትሞክር አቅም ተሳናትና በተሰብሳቢው እንስሳት መካከል ፈንድታ ሞተች።

ይህ ነበር በልጅነቴ እንደሌሎቹ የዕድሜ አጋሮቼ ሲነገረኝ የነበረው ታሪክ።አቅምን ያለማወቅ ፣ከማን አንሼ ታሪክ።
ሰሞኑንም ይህን መሳይ ተረት በኢትዮጵያኑ የትግል ጎራ ውስጥ ከተሰለፉት መካከል የአንዱ ድርጅት አመራር አባል የሆነው ግለሰብ ነጻነት ለኢትዮጵያ በሚባለው ራዲዮ ስርጭት ቀርቦ የተናገረው የእንቁራሪቷን ታሪክ እንዳስታውሰው አደረገኝ።ለሙሉ ግንዛቤ ከዚህ በታች ያለውን የቪዲዮ የድምጽ ቅጅ በማዳመጥ መረዳት ይቻላል።
Neamin-Zeleke-1https፡//youtu.be/erPWBdb_U3Q
ይህንን ኢንተርቪው ከሰማሁ በዃላ ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ፣

በ2001 ዓ.ም.እ.አ.አ.አሜሪካ በአሸባሪዎች በተጠቃችበት ወቅት የአገሪቱ ፕሬዚደንት የነበረው ጆርጅ ቡሽ በቀል ለመመለስ ለጦርነት በሚዘጋጅበት ወቅት አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች መንግሥታት ስለተቃወሙት፣ እነሱን ከጥፋት ሃይሎች ጋር ለማዳበል “iether you are with us or with them” በማለት በጠባብ የምርጫ ሳጥን ውስጥ ለማስቀመጥ እንደሞከረ የሚያሳየው አባባሉ ነው።በዚያን ጊዜ ቡሽ ለሚያደርገው ጭፍን ጦርነትና ዕቅድ አለመተባበር ማለት ከሽብርተኞች ጋር መወገን ማለት ነበር።ሽብርተኞችንና የቡሽን አደገኛ መንገድ የሚቃወሙት ወገኖች በዚህ የጆርጅ ቡሽ አመለካከት የነጻ አቋምና አመለካከት መብታቸው የተገፈፈ ነበር።የፈሩት አልቀረም ይኸው የቡሽ መዘዝ አሁን ዓለማችን ካለችበት ከነበረው ለበለጠ ቀውስና አደጋ ውስጥ ተነክራ ትገኛለች።
ታዲያ የቡሽ ነገር ምን አነሳው ይባል ይሆናል።

ከላይ በቀረበው የራዲዮ ቃለምልልስ ላይ ነአምን ዘለቀ የተባለው የግንቦት ሰባት አመራር አባል ድርጅቱ በአስመራ ውስጥ ተቀምጦ በሻእብያ እየተመራና እየተረዳ የሚያካሂደውን ጦርነት በመደገፍ ሂደቱን የሚቃወሙትን እንደጆርጅ ቡሽ በማውገዝ ከኢትዮጵያ አንዱ ጠላት ከሆነው ከወያኔ ጋር ማስተሳሰሩ ተመሳሳይ ሆኖ አገኝቼዋለሁ። እውነት ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያ አንድነት፣ለዲሞክራሲ ስርዓት የሚታገል ከሆነ ትግሉን ከአምባገነኖች መዳፍ ውስጥ አላቆ፣በኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍና ተሳትፎ ፣በኢትዮጵያ ምድር ያድርገው ብለው የሚነቅፉትን ፣በትግል ስልት የሚለዩትን የአንድነት ሃይሎች በማውገዝ፣ ጆርጅ ቡሽ ”እኛን ያልደገፈ የጠላት ተባባሪ ነው እንዳለው ሁሉ “የሻእቢያን መንግሥትና የግንቦት ሰባትን ስልት መቃወም ጸረ ወያኔ ትግላችንን መቃወም ነው፤” “ከእኛ ጋር ወይም ከወያኔ ጋር የመሆን ጥያቄ ነው” በማለት ትችት ሰንዝሯል። የተለየ ስልት በሚከተሉትና ነቀፋ ባቀረቡት ላይ እንደጆርጅ ቡሽ የነጻ አመለካከትንና ተቃውሞን የማፈንና የማስፈራራት መልእክቱን አሰምቷል።እሱም ጆርጅ ቡሽን ለመሆን የጆርጅ ቡሽን አባባልና ዘዴ መጠቀሙ፣የቋንቋውና የአነጋገሩ ቃና ተመሳሳይ ከመሆኑም በላይ፣የወሮ በላውን የመንግሥቱ ሃ/ማርያምን ድንፋታ አስታወሰኝ።የሌለውን አለኝ ፣ያልሰራውን ሰራሁ ማለቱ ደግሞ ፈንድታ በሞተችው እንቁራሪት መልክ እንዳየው አደረገኝ።
ይህ ማለት ግን አቶ ነአምንም ሆነ ሌላው የየትኛውም አይነት ድርጅት አባል የመሆንና የሚከተለውን ስልት አላከብርለትም ማለት አይደለም።ባልቀበለውም አከብርለታለሁ።የእኔ አነሳስ በሰለጠነ የፖለቲካ ውይይት የምንለያይበትን ነጥብና መስመር በገሃድ ቁልጭ አድርጎ በማስቀመጥ አንዱ ከሌላው የሚማርበትን ዘዴና ከስህተቱ የሚወጣበትን፣የጋራ ትግሉ ስኬታማ የሚሆንበትን መንገድ መፈለግና ማሳየት ነው።በምጠረጥረው ሁኔታ በግንቦት ሰባት መሪዎች ላይ ተመሳሳይ ችግር ቢፈጠር ወይም አደጋ ቢደርስ ያንገበግበኛል፣ያሳዝነኛል።ለትግሉም ድርብ ክስረት ይሆናል።ያ ሳይደርስ ቀደም ብሎ አደጋው ሊከሰት የሚችልበትን መጠቆም ግን ሊከበር የሚገባው የወዳጅና የወገን ምክር ነው።በጭፍን እየጋለቡና እያጨበጨቡ ሰቅሎ ማውረድ አልወድም።ባለፉትም የትግል ታሪካችን የተፈጸመውና አሁንም በመፈጸም ላይ ያለው የዚሁ ካለመሰላል ሰቅሎ ካለመሰላል ጎትቶ የማውረድ ባህል ነው።ያ ደግሞ መቀየር አለበት።ፖለቲካችን

ከስሜት፣ከደምፍላት፣ከወገንተኝነት፣ከውሸት መላቀቅ አለበት።አገር የጋራ እንደመሆኑ የሁሉም ድምጽና ፍላጎት ሊደመጥ ይገባል።በጠላትነት ተመድቦ እውነትን በሃሰት መቀየር የጥፋት ጥፋት ከመሆኑም በላይ የሚጠፉበትን ጎዳና መቀየስ ይሆናል።

በጣም ያስገረመኝ ደግሞ ቃለምልልሱን ያዘጋጀውና ያስተላለፈው አቶ ዓለም ፈቃደ ያንጸባረቀው አቋም ነው።ዓለምን ለብዙ ዓመታት ከአቶ ነአምን ዘለቀ ጋር ካለው እውቅና ዘመንና በላቀ የትግል ተሳትፎ የማውቀው ጓዴና አሁንም ጋጓደኛ ነው።በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምን፣ጸረ ሻእቢያና ወያኔ አቋም የነበረው፣እራሱን ጥሎ ለትግል የቆመ መሆኑን እመሰክራለሁ፤የገረመኝ ነገር ግን በ2004 ዓ.ም.ኮሎኔል ታደሰ ፣የአርበኞች መሪ ዋሽንግተን በመጣ ጊዜ፣ዓለምና እኔ በተናጠል አግኝተነው የጠየቅነውና የተቃወምነው ነገር ቢኖር እንዴት ኢሳያስ አፈወርቂን አምነህ ኤርትራ ውስጥ ጸረ ወያኔ ትግል ታካሂዳለህ? ሻእቢያና ወያኔ እኮ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው ናቸው።የአሁኑ በጥቅም ዙሪያ፣ኢትዮጵያን በመዝረፍ ዙሪያ የተከሰተው ጊዜያዊ ጠባቸው ለነገው ትብብራቸው እንቅፋት አይሆንም፤የኢትዮጵያ አንድነትና አገር ወዳድ ሃይሉ ሲጎለብትና ሲጠናከር ተባብረው ከማጥፋት አይመለሱም፤ሻእቢያ አንተንም ድርጅትህንም ያጠፋችዃል የሚል ነበር።ያልነው አልቀረም፣ኮለኔል ታደሰም የት እንደደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም፣ ሻእብያ ደብዛውን አጠፋው።ድርጅቱም ኢትዮጵያዊነታቸውንና ኢትዮጵያን የሚያስቀድሙት ታጋይ አባላቱ ተገለውና ተገልለው ተሽመድምዷል። ታዲያ ዓለም በዛ ጊዜና እስከቅርብም ጊዜ ድረስ ይገፋ የነበረው አቋምና አመለካከት አሁን እንዴትና ለምን ተቀየረ?የፕሮፌሶር አስራት አክባሪና ደጋፊ የነበረው፣ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምነው፣ተገንጣይ ሃይሎችን ይቃወምና ይኮንን የነበረው ጓዴ በግንቦት ሰባቶች ላይ እንደ ኮሌኔል ታደሰ ለመተቸት ምን አንደበቱን ያዘው?ምን ነካውና ድፍረቱን አጣ?የአቋምና የአመለካከት ለውጥም ካደረገ ቢናገር ጥሩ ነበር፤ያንን ደግሞ አክብርለታለሁ እንዲከበርለትም ከጎኑ እቆማለሁ።በተገናኘን ቁጥር ግን በውይይት የማውቀው ጸረ ሻእቢያነቱንና ለኢትዮጵያ አንድነት መቆሙን ነው።

በግንቦት ሰባትም ላይ ያለኝ ልዩነት በስልት ደረጃ እንጂ ወያኔ በመወገዱ አስፈላጊነት በተነሳ ጥያቄ አይደለም። ልዩነቴ ወያኔን ለማሶገድ በተነደፈው የትግል ስልት ዙሪያ ነው።ስልቱን ባልቀበልና ብቃወመውም ድርጅታዊ መብቱን አከብራለሁ።እነሱ በሻብያ ድጋፍ ፣ተገንጣዮችን አስተባብረን ወያኔን እናሶግዳለን ባዮች ናቸው።በኢትዮጵያ አንድነት ጥያቄና ከወያኔ በዃላ ስለሚመጣው የስርዓት ለውጥ ግልጽ የሆነ ትንታኔ አይሰጡም።ብቻ በማንም ይሁን በማንም፣ ከጸሃይ በታች ባለ ሃይል ባገኘነው እርዳታ ወያኔን መጣል ነው ከሚል ባሻገር ለአገሪቱና ለሕዝቡ ቋሚ ችግር መፍትሔ የሚሆን መልስ አያቀርቡም።ከማንኛውም ጋር እንተባበራለን ሲሉ ግን ለኢትዮጵያ አንድነት ፣ለሕግ የበላይነት፣ለዲሞክራሲ ስርዓት መስፈን…ወዘተ ከሚታገሉት ኢትዮጵያኖች ጋር ግን አይደለም።የእነሱን የበላይነት፣አመራር፣ስልት የማይቀበል አይፈልጉም፣እንደጠላት ወይም እንደ ወያኔ አጋርና ደጋፊ አድርገው ይቆጥሩታል። ለዚህም ተደጋግሞ ለቀረበላቸው ጥሪ የሰጡት መልስና ዝምታ ማስረጃ ነው።ዝርዝሩ ካስፈለገ ወደፊት ሊቀርብ ይችላል። ወያኔ ብቻ ይውደቅ፣ከሱ የከፋ አይመጣም የሚለው ቅኝት ደግሞ ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ወያኔ ጸረ ደርግ ትግል ሲያካሂድ፣በአገሪቱ ላይ አሁን የምንቃወመውን ስርዓት እንደሚያሰፍን ሳንመለከትና ሳናገናዝብ ብቻ ደርግ ይውደቅ ከሚል ጥላቻ በመነሳት ከተወሰደውና አሁን ከሚቆጨን አቋም አይለይም።በወቅቱ ነገሮች ተስተካክለው፣ጎባጣው ቀንቶ ካልተራመድን የዃላዃላ ተቀምጠን የሰቀልነው ቆመን ለማውረድ እንደሚያዳግተን አሁን እያየነው ነው።ወደፊትም እንዳይደገም ትምህርት ልንቀስም ይገባል።

ለግንቦት ሰባትም ሆነ ሌሎቹ ለሚያካሂዱት ትግል የሚያዋጣው ዋሻና ደጀኑ የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ መሬት ነው።በዓለም አቀፍ ደረጃ፣በከባቢ ደረጃና በአገር ውስጥ የወገንና የጠላት ሃይልን አሰላለፍ ያላመዛዘነና ያላወቀ፣ወይም ከጠላቶቹ በአንዱ በጊዜያዊ ጥቅም የተታለለ ታጋይ የታሰረበትን ሰንሰለት ተሸክሞ እንደሚጓዝ እስረኛ ያህል ነው።እንደልቡ ሊንቀሳቀስና ካሰበበት የድል ጣቢያ ሊደርስ አይችልም።
ከሚጎዳ እሰጥ አገባ፣ውሸትና ትእቢት ተላቀን በጋራ ያገራችንን ችግር ለመፍታት ቅን፣ደፋር፣ ግልጽና እውነተኞች ሆነን እንነሳ፣ቅድሚያ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት እንስጥ!!

↧

እኔም  ጎንደሬ  ልሁንና ሹሙኝ  –ለተሰደደው የሲኖዶስ አባላት |ከመኳንንት  ታዬ

$
0
0

ይመስለኝ  የነበረው በክርስትናው አለም የመጀመሪያው ህግ እግዚያብሔርን ከመፍራት ጥበብ የሚነሳና በሌሎች ሰዋዊ ስነምግባር ታንፆ አንድ ሙሉ ሰው ሊያደርገው የሚችለውን ውህድ በማንነቱ ክህሎት ላይ ባለቤት ሊያደርጉት  የሚችሉትን  ባለመስመር ቀለሞች  ሰው ወደሚለው ምእራፍ  አልፈው ክርስቲያን  የሚያሰኘበውን መታወቂያ ያሰጡታል ብዬ አስባለሁ።በዚህ ሁሉ ውስጥ ሞራል  የሚባል ነገር  ደሞ  ትህትና ለሚሉት የባህሪያት ሁሉ የበላይ ለሆነው መልካምነት ውበት ሆኖ ይገለፃል የሚል እምነት  ነበረኝ ።ነበረኝ ለማለት ያነሳሳኝ  አሁን የለኝም ለማለት ሳይሆን ወደ ቤተክርስቲያን ጎራ ብዬ ለአበው ካህናት ከላይ  ያለኩትን አምነቴን  ማሻማት ስጀምር  ከመንገድ ሆኜ ሁሉ አንድ አደለም ቆብና ባለቤትነት  ይለያያሉ የሚለውን ካርድ ሳይ እምነቴን ቆም ብዬ  እንድፈትሽ አደረገኝ ።ለዚህም ነው ነበረኝ ለማለት የተገደድኩት ።

እስቲ ከላይ ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ ወደ ዝርዝር ጉዳዬ ልግባ ።ለመፃፍ ያነሳሰኝም አባይት ጉዳይ  ወደ አሜሪካው ገዳም  የተሰደዱ አባቶች መስመሩን በመርገጥ ለምን እንደሚፎርሹ  ሳስብ አለማው አልገባ ይለኝና  እቸገራለሁ።በደርግ መውደቂያ ማግስት ጎጠኛው የኢሃዲግ መንግስት ሐገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የቀድሞን ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሬዮስን ከስልጣን በማባረሩ ምክንያት እሳቸውም የስጋ ገዳም ወደሆነችው አሜሪካ እንደ እኛው ተሰደዱ።መልካም አባቶቻችን ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው  ሃገራቸውን ከጠላት ተከላክለው ለትውልዱ   አስረከቡ እንጂ ሐገር ጥለው መሸሸጊያ ፍለጋ  አልፈረጠጡም ።በርግጥ ሁሉም እኩል የሆነ ፀጋ የለውም ።ስለዚህ አባታችን  የኔ አቅም እስከዚህ ነው ካሉ ምንም ማለት አልነበረም።ማለት የሆነው እዚህ አሜሪካ ከመጡ በኋላ ተከወኑ ድርጊቶች ናቸው ።ሲጀመር አስተዳደር  አይሰደድም።ሲኖዶስ ማለት የግለሰብ ሐብት ሳይሆን  የ ኢ/ተ/ቤ/  መንፈሳዊ አስተዳደራዊ ስርአት ነው ።

ይህ    በእንዲህ እንዳለ ሆኖ   በስራ አጋጣሚም ይሆን ሆን ተብሎ ታስቦበት ከሀገር የወጡ የአንድ ሰፈር ልጆች በመሰባሰብ የቅድስት  ቤ/ክ አቁማዳ ፈተው  ትልቁን  ስርአት የልጅ ጫወታ በማድረግ  ሲኖዶስ ተሰዷል አሉን ።በዚህ እግዞ እግዞ ብለን ቀን እየቆጠርን በሐገር ቤት ያለችው ቅድስት  ቤተክርስቲያን  በዘረኛውና በጎጠኛው ወያኔ ስርአት እየደማች መኖሯአና ልጆቿ መስዋትነት እየከፈሉ መኖራቸው ሳያንስ ሲኖዶስ እኛ ነን ካላልን አባ አባ አንባልም በሚል  ሰበብ ይሁን መንፈሳዊ አባት መሆናቸው የሚያንሳቸው ስለመሰላቸው የነ አብነ መልከፀዲቅ  ጎንደር መራሹ የመለኩሴ አባቶች ስብስብ  ሳያሰልስ  በጥፋት ላይ ጥፋት  እየደገመ ይኸው ዘመናትን ተሻገርን ።አላማው ማንን ለመጥቀምና  ማንን ለመጉዳት እንደሆነ በፍፁም አይታውቅም።

ephrem

የሐገር ቤቱን አስተዳደር የሚከሱት  በጎጠኝነት ሆኖ እያለ እነሱ ግን ስሙን ብቻ ሳይሆን ልብሱንም ጭምር ጎጥ አድርገውታል።ቤተክርስቲያን አንድት ናት ።አስተዳደርም አንድ ነው ።አባቶች ግን ብዙ ናቸው ።በአባቶች ቁጥር ልክ ግን ሲኖዶስ  መኖር አለበት የሚል ስርዓትም ህግም የለም ።ከዚህ በፊት የተለያዩ እህት አባያተ ክርስቲያናት   በአንድም በሌላም መልኩ ችግር አጋጥሞአቸው ያቃሉ።ተሰደውም ኖረዋል ።ግን ሲኖዶስ ተሰደደ አላሉም ።ይህ ሁሉ ሆኖ ሐገራችን ኢትዮጲያ ከ80 በላይ ብሔረሰቦችን የያየዘች ሀገር ከመሆኗም በላይ አሁን ባለው መንግስት ጉዳት የደረሰበት ሰው ጎነደር ብቻ አደለም ።የጥቃቱ ሰላባ የትግራይ ወንድሞቻችንም ጭምር እንጂ።ስለ ክርስትናው ካነሳን ግን መስመሩ ሁሉ የመከራ መሆኑ የማይካድ ነው ።”የሚወደኝ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ ብሏል እና ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ  ማንም ቢሆን በማመኑ ለሚመጣበት መከራ መፍራት እንደሌለበት ኣስቀድሞ ተሰብኮልናል ።እንግዲህ በዚህ ሁሉ ወስጥ እጅግ ብዙ አብያተ ቤተክርስቲያናትና  ክርስቲያኖች በተለያየ ምክንያት በብዙ ችግር ውስጥ ተቀምጠው  የመሰባሰብና አንድ ሆኖ እነዚህን ችግሮች  ለመቀነስ ከመታግል ጀምሮ ስጋዊ ፍላጎትን ለማርካት ጎንደር ተሰብስብ እያሉ እርስ በእርስ መሿሿም ምን የሚሉት ነው ?።በውኑ የጎንደር መለኩሴ ክንፍ አለው ወይስ መንግስተ ሰማያትም  በጎነደሬነት ብቻ ነው የሚገባው?

አርግጥ እንደዛ ከሆነ ሌሎቻችን  አለቀልን።ምን አይነት ሞራል ነው ?ምን አይነት ክርስትና ነው ?ትምህረቱስ ከየት መጣ ? ይህን አለም አንፈልግም ብለው sign out  አደርገው ከወጡ በኋላ ለዚህ አለም ስልጣንና ምኞት መሽቀዳደም  እነማን ነበሩ ያሰኛል።ደግሞስ ከመንፈቅዱስ ያልሆነ ሹመት ሽልማት በውኑ መንገዱ አስከየት  ነው? ።የተሹሙት ሰዎች ብቃታቸው እና ትምህርታቸው የተለካው በፖለቲካ መስፈሪያ  ነው? ወይስ በመንፈሳዊ ትምርታቸው ?እነ አባ ወልደ ትንሣኤ  ማናቸው? እስቲ ከዚህ ሁሉ ጥያቄ በኋላ የሹመቱ ቃለ ማህላ ላይ ለምን ተዋህዶ የሚለው ቃል ተዘለለ? የ ኢ/ኦ/ተ/ የሚለው ቃል ስለከበደ ወይስ ስለተዘነጋ? ይህን በራሱ ለእነሱ እንተወውና  አስቲ የከዚ በፊት ሹመኞቹን አስበን  የዛሬዎችን እንመልከት ።

1. የአባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ       ትውልድ ሃገር   ጎንደሬ እና  በተለያየ ትምህርታቸው አፀፅ ያለባቸው

2.  አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው          ትውልድ  ሃገር ጎንደር 

3. የአባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ             ትውልድ ሃገር  ጎንደር

4.  የመልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ዳኘው   ትውልድ ሃገር ጎንደር

5.  መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል         ትውልድ ሃገር ጎንደር

6.  የመልአከ ብርሃናት አባ ገብረ ሥላሴ የኋላሸት    ትወልድ ሃገር ጎንደር

የህይወት ታሪካቸው  ላይ ሁሉንም ጎንደር ለማለት ፈርተው ይመስላል  በቅድስት ሃገር ኢትዮጲያ ተወለዱ። ብቻ ብለው ዝቅ ብላችሁ     የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን  የተማሩበት ቦታ ላይ ጎንደር እንደሆነ ተጠቅሶአል።በርግጥ እንኳን እኛ  እናንተም በስራችሁ  እንዳፈራችሁ በትልቁ ማሳያ ነው ። ነግር ግን መፅሃፍ ቅዱሳችን   በትንቢተ ኢሳያስ ምራፍ 30 ቁ15-18  እንዲህ ይላል፦ 

“የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥

ነገር ግን፦ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።  

ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፥ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፥ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ። 

እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። ውድ አባቶቻችን  ታዲያ በውኑ እንተ ቃሉ ተስቶአችሁ ወየስ ተረስቶአችሁ  ለሹመት ለሽልማት መጓጓታችሁ?ውይስ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል  እንዳለችው በቅሎ መሆኑ ነው ።በዚህ አጋጣሚ ይቀርታ የምላችሁ እናንተን አከብራለሁ ስለደፈርኩአችሁም አደለም  ከላይ ያለውን ሃሳብ ለመስጠት የተነሳሁት ።አንድም ዘረኝነትና ጎጠኝነታችሁ ከወያኔ የባሰ በመሆኑ አንድም  ትህትና ያልተከለበት ክወረስናትና የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምሮ ስላልሆነ ነው ።በፖለተካና በፖለተከኞች አፍ ህጋዊ ናችሁ። መንግስቱ ሐይለማርያምም  ህጋዊው ፕሬዘዳንት ነው።  ምክንያቱም  እሱም ተገዶ ነው ከስልጣኑ የወረደውና ። ግን እናንተ ጋ ሲሆን ህጋዊ ትባላችሁ እርሱ ጋር ሲሆን የቀድሞ ይባላል።ለምን  ጎንደሬ ስላልሆነ ወይስ  ሐራሬ ያለ ሰው ህጋዊ አይደለም  ?።ይህንና ይህን  የመሳሰለው  ጥፋታችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያንን  አንገት ያስደፋ ቢሆንም  ህዝበ ክርስቲያኑ ግን ቆም ብሎ የሚያስብበት  እና “አውነት ምንድነው ?” ብሎ የሚጠይቅበት  ግዜ ነው ።እግዚያብሔር ይታገሳል እንጂ አይቆጣም  አልተባለም ።አቡነ ጳውሎስንና  መለስ ዜናዊን  ያያ  በኢሳት አይጫወትም።ክብርአችሁ አምነታችሁ ና ትህትናችሁ ሆኖ ለትውልድ  መተላለፍ ሲኖርበት ማን አለበኝነታችሁንና ትውሉዱን  አሰፍስፎ ለሚጠብቀው ተሃድሶ መናፍቃን ለማስበላት  የምታደርጉት  እሩጫ  በእግዚያብሔር  ዘንድ ሳያስጠይቃችሁ የሚቀር አይመስለኝ ም።

በስተመጨረሻም:

እግዚያብሔር  በነብዩ በ ኢሳያስ  አንደበት  እንዲህ  ብሎ ተናግሮአልና “ከቃሌ የተነሣ ወደ ሚፈራ የዋህ ትሑትና ትግስተኛ  ወደሚሆን  ነው  እንጂ ወደ ማን  እመለከታለሁ?” ዳግመኛም ወንጌል  እንዲህ  ይላል “የዋሆች  ብፁዓን  ናቸው  እነርሱም ምድርን ይወርሳሉና “ዲድስቅልያ  አንቀፅ ፮ አና፯። በዚህ  ሁሉ ምሃል ለስልጣን የሚጓጉና  ጎጠኞች አላለምና አስቡበት ።

ችር እንሰንብት

↧

በጳጳሣት ሹመት ዙሪያ አንዳንድ ነጥቦች |ይሄይስ አእምሮ

$
0
0

ሰሞኑን ዘሃበሻ ድረገፅ በሰበር ዜናነት እንደዘገበችው በስደት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ስድስት ኤጲስ ቆጶሣትን በሙሉ የጵጵስና ማዕረግ ሾሞ በስድስት የዓለም ግዛቶች በሃይማኖታዊ የኃላፊነት ቦታ መድቧል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይቺ ቅመም የሆነች ዘሃበሻ የምትባል ድረገፅ ዜናውን ተከታትላ በወቅቱ ስላደረሰችን ከፍተኛ ምሥጋና ይገባታል፡፡ ሌሎቹ ድረገፆችም እንዲሁ፡፡ ሁሉም የዘጠኝ ወር ልጆቻችን ናቸውና ምሥጋናየ ለሁሉም ነው፡፡ “ከጣት ጣት ይበልጣል”ን አለቦታው ልተርት አልፈልግም፡፡ ቢሆንም….

abune bernabas

ይህ ሹመት በወያኔ ሤራ ምክንያት በካልቾ ተጠልዛ መሬት ላይ በመዘረር ነፍሷ አልወጣ ብሎ እያንቋረረች ለምትገኘው የሀገራችን ታሪካዊት ሃይማኖት ትንሣኤ የሚያበረክተው አወንታዊ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህ ማንሰራራት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ያደረጉና በማድረግም ላይ የሚገኙ አባቶች፣ ወንድሞች፣ እናቶችና እህቶች ታላቅ ክርስቶሳዊ ምሥጋና ይገባቸዋል፡፡ ይህችን የክርስቶስ መሠረት የሆነች ሃይማኖታችን በሁለት እግሯ እንድትቆምና የቀድሞውን ሕዝብን በአንድነትና በፍቅር የማሰባሰብ ሚናዋን እንድትጫወት እግዚአብሔር ያግዛት ዘንድ በበኩሌ እየጸለይኩ በሰሞኑ የሹመት አሰጣጥ ሂደት ላይ ከዜናው የታዘብኳቸውን አንዳንድ ነጥቦች ማንሳት ወደድኩ – እንዲያው አልሁ ለማለት ያህል እንጂ እስከዚህ ከባድ ሆነው አይደለም፡፡

ከአዲሱ ዜና ከዛሬው በመነሳት ስለስያሜያቸው ትንሽ ልበል፡፡ በአዲሱ ስያሜ አቡነ ቴዎፍሎስ የተባሉ አንድ አባት አሉ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም በደርግ ፋሽሽት (ደርግን ከወያኔ ጋር ሳነጻጽረው ይህንን ቃል መጠቀም ከብዶብኝ መቸገሬን ተረዱልኝ) የተገደሉትን ሁለተኛውን የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክርስቲያን ፓትርያርክን ያስታውሰናል፡፡ ቀደም ሲል ለሌሎች አባቶች የተሰጡ ሌሎች ተመሳሳይ ስያሜዎችም አሉ፡፡

እኔ እምለው ታዲያ አዲሱን አባት በሌጣው “አቡነ ቴዎፍሎስ” ብለን ከምንጠራ “አቡነ ቴዎፍሎስ ዳግማዊ(2ኛ)” ብለን ብንጠራ አይሻልም ነበር ወይ? ነው፡፡ አንድ ነገር ከታመነበት ምን ጊዜም ማስተካከል ይቻላልና የሚመለከታቸው ወገኖች ቢያስቡበት መልካም ይመስለኛል፡ ምክንያት አለኝ –  ምክንያቴ ደግሞ ለማንም ግልጽ ነው፡፡

ተራ ስሞችን ማንም ቢጠቀምባቸው ችግር የለውም፡፡ ለምሣሌ  በመቶዎች የሚቆጠሩ “ይሄይስ” የሚባሉ ስሞች በኢትዮጵያ ውስጥና ውጪ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ያ ምንም ችግር የለውም፡፡ የማዕረግና የሹመት ስሞች ግን አንዱን ከሌላው እንዳያምታቱ ተጨማሪ መግለጫ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ለምሣሌ ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ ዳግማዊ ምንሊክ፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ፣ አፄ ዮሐንስ አራተኛ፣ ሉዊስ 16ኛ፣ ጆን ፖል ሁለተኛ፣ ቤኔዲክት 16ኛ… እየተባለ የሚጠራው፡፡ አንድ ሰው ተነስቶ “አቡነ ቴዎፍሎስ እጅግ የተከበሩና በሕዝብ የተፈቀሩ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ በስማቸውም አንድ የበጎ አድራት አቋቁመው ደሞዛቸውን እንዳለ ወደዚያ ድርጅት ነበር ፈሰስ የሚያደርጉት፡፡…” ብሎ ቢጽፍ ስለየትኛው ቴዎፍሎስ እየተናገረ እንደሆነ ተጨማሪ መግለጫ ወይ ማብራሪያ በግርጌ ማስታወሻ መስጠት ይጠበቅበታል፤ አለበለዚያ አንባቢን ያደነጋግራል፡፡ ስለዚህ ሌላ አሳሳች መጠሪያ ያለባቸው አዲሶቹ ተሹዋሚዎች በስማቸው ላይ ቁጥር ቢደረብ ጥሩ ነው እላለሁ – ተለይተው እንዲታወቁ፡፡

በበቀደሙ ዜና ደግሞ በ10 ዓመታቸውና በ12 ዓመታቸው የዲቁና ማዕረግ የተሰጣቸው የቀድሞ ሕጻነት የአሁን አባቶች እንደነበሩ ተገልጾኣ፡፡ የአሥር ዓመት ልጅ የዲቁና ማዕረግ ይሰጠዋል? ከሆነ ጥሩ፡፡ ካልሆነ ግን መረጃው በውል መፈተሸ ነበረበት ወይም አለበት፡፡ የዕድሜ ነገር አወዛጋቢና አስተዛዛቢም ስለሆነ ይህ ዓይነቱ ነገር  ቢያንስ ለወደፊቱ ይታሰብበት፡፡

ከዚህ በተያያዘ አንድ አባት በ17 ዓመት ዕድሜያቸው መንኩሰው ለቅስና ክህነት እንደበቁ ተዘግቧል፡፡ በዚህ እኔም በጣም ግር ብሎኛል፡፡ ባለኝ ግርድፍ ሃይማኖታዊ ዕውቀት አንድ ሰው ቄስ ለመሆን ቢያንስ የ30 ዓመት ጎልማሣ ሊሆን ይጠበቅበታል – እንኳን ምንኩስና፡፡ ምንኩስና ደግሞ ብዙ የጥሞናና የእውነተኛ ጥሪ ማስተማመኛ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ “ነገሩ ካንገት ነው ወይንስ ካንጀት” – “ጥሪው መለኮታዊ ነው ወይንስ ሰይጣናዊ” ተብሎ መጣራት አለበት፡፡ “በ17 ዓመት ይመነኮሳል፣ በ17 ዓመት የቅስና ክህነት ይሰጣል” ብዬ ደግሞ አላምንም – ሆኖም ከሆነ አንድ ቦታ ላይ ስህተት መኖር አለበት፡፡ ይህም መረጃ ይጣራና ማስተካከያ ወይም ማስተባበያ ይሰጥበት – አንድ ዜጋ ጠየቀ -እኔ፡፡ የ17 ዓመት ታዳጊ ምን ያውቅና፣ ምንስ የሕይወት ተሞክሮ አለውና ነው ምንኩስና ላይ የሚደረብ ቅስና የሚሰጠው? አስረዱኝ፡፡

አንድ ዲያቆን ከደቆነ በኋላ በርከት ላለ ጊዜ በዚህ ማዕረግ ያገለግላል፡፡ ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት 30 ዓመት ሲሞላውና አስፈላጊውን ዕውቀትና ትምህርት አሟልቶ ሲገኝ የቅስና ማዕረግ ይጠይቃል፡፡ ይሄኔ አንድም ማግባቱ አንድም መመንኮሱ ይረጋገጥና ተፈትኖ ክህነቱ ይሰጠዋል፡፡ የ17 ዓመት ልጅ እንግዲህ አንድም ለጋብቻ አንድም ለምንኩስና አልደረስምና ጥያቄ ያስነሳል፡፡ (የቃል ፈተናው ላይ ሦስቱ ሥላሦችን አስረዳ የተባለ የቅስና ማዕረግ ለመቀበል ያመለከተ አንጋፋ ዲያቆን  የሥላሤ ጽላቶች የሚገኙባቸውን ሦስት ደብሮች እንደጠቀሰና ፈታኞቹን በሣቅ እንደገደላቸው ሰምቻለሁ – “ከመጠምጠም መማር ይቅደም” የተባለውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መሰለኝ፡፡)

የአራቱ አባቶች የትውልድ ቦታ በደምሳሳው “ኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ ዓመተ ምሕረት ተወለዱ” ይልና ሁለቱ ግን ከአራቱ በተለዬ የተወለዱበት ሥፍራ አንዱ በትክክል ሌላው “ሰሜን” በሚል በገደምዳሜ ተጠቅሷል፡፡ የአራቱ በጣም ተስማምቶኛል – ካህን ሀገር ስለሌለው፡፡ የሌሎቹ የሁለቱ ግን እንደሌሎቹ እንዳራቱ መሆን ነበረበት – ተለጣጣቂነቱ እንዳይፋረስ (consistence እንዲኖረው)፡፡ በቃ፡፡ አንዳንድ ነጥቦች አልኩ – እነሱንም እንደነገሩ ጨረስኩ፡፡

↧

Hiber Radio: የኤርትራው አምባሳደር “የሕወሓት መንግስት ወደ ልቦናው እንደሚመለስ ተሰፋ አደርጋለሁ”አሉ |የሩሲያ ኦርቶዶክስ መሪዎች ራሳቸውን አገለሉ |ዶ/ር መረራ እንተባበር አሉ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሰኔ 12 ቀን 2008 ፕሮግራም

እንኳን ለአባቶች ቀን አደረሳችሁ !

<... ...> ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<... ...> ኮ/ል ደረሰ ተክሌ የሰራዊቱ የቀድሞ የጥናትና ምርምር ክፍል ሀላፊ በኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዲፕሎማቶች ኬኒያ ላይ ከሰሞኑ የድንበር ላይ ቁርቋሶ በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜያት በግንባር በመገናኘት ስለ ውስጣዊ እና አካባቢያዊ ችግሮቻቸው በተመለከተ ከርረ ያለ እና ከዲፕሎማቲክ ደረጃው የዘለለ የቃላት ልውውጥ አድረገዋል።ሁለቱ አምባሳዳሮች በምን ጉዳይ ላይ ተሰማሙ? ሰሞነኛውን ጦርነትንስ ማን ጀመረው? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው ምንድን ነው? (ልዩ ጥንቀር)

<...> ዶ/ር ሙላቱ ውብነህ የማህበሩ የቦርድ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)

የእንግሊዝ ሕዝብ ከአውሮፓ ሕብረት አባልነት ለመውጣት ወይም አብሮ ለመዝለቅ ለሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ተቀመጠዋል። ለመሆኑ በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ነዋሪዎች ምን ይላሉ? የዓለማችን መሪዎች ህዝበ ውሳኔውን በተመለከተ ምን አሰተያየት እየሰጡ ይገኛሉ? የተለያዩ አስተያየቶችን አካተናል የሕብር ራዴዮ ልዩ ዘግጅትን ያድምጡ

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት(ጆቤ) የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራር የትግራይ ተወላጆች እርስት ሆኖ መቅረት የለበትም አሉ

ሳሞራን ሕዝብን ይቅርታ ይጠይቅ ብለዋል

የዓለም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች በታሪክ ታላቅ የተባለ ስብሰባ በግሪክ አካሄዱ | የሩሲያ ኦርቶዶምስ መሪዎች ራሳቸውን አገለሉ

የውጭው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ ለቅዱሳን አባቶች ሹመት ሰጠች

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከሰሞነኛው የጾረውና ግጭት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኬኒያ ውስጥ በግንባር ተገናኝተው ተወዛገቡ

“አናሳው የትግራይ ወያኔው መንግስት ወደ ልቦናው እንደሚመለስ ተሰፋ አደርጋለሁ” የኤርትራው አምባሳደር በየነ ርእሶም

“በአገሩ አንምዳችም የህዝበ ወሳኔ ያላድረገ መንግስት እንዴት ስለ አናሳዎች መብት ሊናገር ይቻለዋል?”የኢትዮጵያው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ዶ/ር መረራ ጉዲና ተቃዋሚዎች ስርዓቱን ማስገደድ የሚያስችል የጋራ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ

በሻሸመኔ በስለት ሰባት የኦሮሞ ተወላጆች ተገደሉ ሕዝቡ በወንጀሉ የሚጠረጠረው ስርዓት ሁኔታውን ለጎሳ ግጭት መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርገውን ቅስቀሳ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

13 የአለማያ ዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከዓመት በላይ ታገዱ

የዛምቢያ ባለስልጣናት ሰሞኑን 19 ሲሞቱ የ75ቱን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ህይወትን ከሞት ላተረፉት የኮንጎ ድንበር ጠባቂዎች ምስጋናቸውን አቀረቡ

እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

↧
↧

የአውሮፓ ሕብረት የኤርትራን ጨምሮ የ19 ሃገራት አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዳይበሩ አገደ

$
0
0

Eritrean Airlines
(ዘ-ሐበሻ) ሲሲቲቭ የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዛሬ እንደዘገበው የአውሮፓ ሕብረት በ12 የአፍሪካ ሃገራት አየር መንገዶች ላይ በሕብረቱ የአየር ክልሎች እንዳይበሩ እገዳ አስተላለፈ::

ሕብረቱ ኤርትራን ጨምሮ በ12 ሃገራት ላይ እገዳውን ሲጥል ሃገራቱም

1ኛ . ቤኒን
2ኛ. ኮንጎ ሪፐብሊክ
3ኛ. ዴሞክራሲያ ሪፐብሊክ ኮንጎ
4ኛ. ጅቡቲ
5ኛ. ኢኳቶሪያል ጊኒ
6ኛ. ጋቦን
7ኛ. ላይቤሪያ
8ኛ. ሊቢያ
9ኛ. ሞዛምቢክ
10ኛ. ሴራሊዮን
11ኛ. ሱዳን ናቸው::

የአውሮፓ ሕብረት የ214 አየር መንገዶችን የደህንነት ደረጃ የመረመረ ሲሆን ከአፍሪካ 12 እንዲሁም ከሌሎች ዓለም ሃገራት 7 በጥቅሉ የ19 ሃገራትን አየር መንገዶች አግዷል::

ለረዥም ጊዜያት እገዳ ተጥሎበት የቆየው የዛምቢያና የማዳጋስካር አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዲበሩ የተፈቀደ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት ሃገራት አየር መንገዶች ለመንገደኞች ደህንነት አስጊዎች ናቸው በሚል በክልሉ እንዳይበሩ መታገዱን ዘ-ሐበሻን ከሲሲቲቭ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል:;

↧

ሶማሊያዊው የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ ታሰረ

$
0
0

genzebe dibaba

(ዘ-ሐበሻ) የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ ጃማ ኤደን ስፖርተኞች ከሚወስዱት አበረታች ዕጽ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ስፔን ውስጥ መታሰሩ ተሰማ::

ገንዘቤ ከወራት ወዲህ በኢዩጂን፡ በኦስሎና ስቶክሆልም የሩጫ ውድድሮች የነበሯት ሲሆን ባልታወቀ ሁኔታ በነዚህ ውድድሮች ሳትሳተፍ መቅረቷ አይዘነጋም::

የዓመቱ ምርጥ አትሌትነትን እና ሌሎች ሽልማቶችን የጠቀለለችው ገንዘቤ የወቅቱ የ1 ሺህ 500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ስትሆን ሶማሊያዊ ዜግነት ያለው አሰልጣኟ በስፔን በካታሎኒያ አትሌቶችን ሰብሰበው በሚያሰለጥኑበት አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ መያዙን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘግቧል;:

ከሶማሊያዊው አሰልጣኝ ጋር እነማን አትሌቶች እንደተነካኩ የተዘገበ ነገር የለም::

↧

ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ሆይ፤ እባካችሁ ከናዚ ሐኪሞች የደም ታሪክ ከመዘፈቅ ታቀቡ!

$
0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ehtህሊናው ባሸነፈው ሐኪም አማካኝነት የሁለት መቶ አምሳ ልማታዊ ሐኪሞች ያየር ባየር ንግድ እንደገና አደባባይ ወጥቷል፡፡ ያያር ባየሩን ንግድ ከምድር ለማውረድ ከዚህ ህሊናው ካሸነፈው ጎበዝ በቀር ሁሉም ልማታዊ ሐኪሞች ኢትዮጵያውያኖች በወንጀል የሚከሱትን ቴድሮስ አድሃኖምን እሽኮኮ ተሸክመው ከወንበር ለመስቀል በውድም ሆነ በግድ ተስማምተዋል፡፡[1] ይህ ያየር ባየር ንግድና ወንጀለኛን በክትፎ ባበጠ ጫንቃ እሽኮኮ መሸከም የናዚ ሐኪሞችን ታሪክ አስታውሶኛል፡፡ በዘረኝነት በተገነባው የናዚ አገዛዝ ዘመን ከግማሽ በላይ የጀርመን ሐኪሞች ከሂትለር ጎን ተሰልፈው ነበር፡፡ [Nazi doctors list 2-4]. እንዲያውም ዶክተር ኢርነስት የተባሉ አይሁዳዊ ያልሆኑ ተመራማሪ “ያለ ሐኪሞች ተሳትፎ ሆሊኮስት እሚባለው የአይሁዶች እልቂት አይሳካም ነበር” ሲሉ በታወቀው የአለም አቀፍ የበሽታዎች ስርጪት መጽሔት (International Journal of Epidemiology) እ.ኤ.አ. በ2001 ዓ.ም ጽፈዋል፡፡ [5]

እንዳገራቸው ባህልና ሥርዓተ- አምልኮት ሐኪሞች የሚገቡት “ሂፖክራቲስ ኦዝ”[6] እሚባለው ቃል ኪዳን “ሥራዬን በንጹሕነትና በቅድስና ሳከናውን እኖራለሁ፤ ከአጭበርባሪነትና ሙስናዊ ተግባራት እቆጠባለሁ …” የሚሉ ፅንሰ-ሐሳቦች ይገኙበታል፡፡ እነዚህንና ሌሎችንም የቃል ኪዳን ፅንሰ-ሐሳቦች ብቻ ሳይሆን የሰውነትን ባህሪም ቡጭቅጭቅ አድርገው የበሉ ሐኪሞች ሂትለር እንደ መለስ ዜናዊ “ያይኑ ቀለም አላማረኝም” ያለውን ሁሉ አስፈጅተዋል፡፡ ሐኪሞቹ ሕዝብን ያስፈጁት ለናዚ አገዛዝ የሐሳብ፣ የመንፈስና የቁሳቁስ ድጋፍ ከመስጠት በተጨማሪ ሂትለር እሚጠላቸውን ዘሮች በማምከን፣ በጀርም በመበከል፣ በጋስ በማፈን፣ ጣጣቴ በመተኮስና በሌሎችም መንገዶች ሕዝብን በማሰቃየት ነበር፡፡ [7,8]

ከናዚው እልቂት ከአምሳ ዓመታት በኋላ በዘርኝነት ቦንብ የተገነባ አገዛዝ በኢትዮጵያ ተዘርግቷል፡፡ ይህ በዘርኝነት ቦንብ የተገነባ አገዛዝም በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በመተከል፣ በአምቦ፣ በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በአፋር፣ በሰቆጣ፣ በኮንሶ፣ በወለጋ፣ በሲዳሞና ሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች በዘራቸው ወይም በቋንቋቸው ምክንያት ዜጎች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ የዚህ እልቂት መረጃም በመላው የኢትዮጵያ ምድር ተቀብሮ ይገኛል፡፡ ከተቀበረው መረጃ ኢምንቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ጪሮ አውጥቷል፡፡ [8] እንደ ሂዩማን ራይትስ ዋች[9]፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል[10]፣ ፍሪደም ዋች[11] የመሳሰሉት ድርጅቶችም ኢምንቱን መዝግበዋል፡፡ የዘር ማጥፋትን ወንጀል የሚከታተለው ጀኖሳድ ዋችም ነፍሰ-ገድዮች ላለም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡[12] የጀርመኑ ዘረኛ አገዛዝ አይሁዶችን እንዳመከነው የኢትዮጵያው ዘረኛ አገዛዝም አማሮችን በማምከን ወንጀል ተከሷል፡፡ [14-16] አብዛኛው የዘረኝነት እልቂት መረጃ ግን ቆፍሮ እሚያወጣ ጋዜጠኛ፣ የቅሬት አካል ባለሙያ፣ የታሪክ ተመራማሪ፣ የሕግ  ባለሙያና ህሊናውን ያልገፈፈ ዜጋ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ዘርን ወይም ቋንቋን መሰረት አድርጎ በተለያዩ ዘዴዎች ያለቀው ሕዝብ ወደ ፊት በትክክል ሲቆጠር በሆሊኮስት ካለቀው ሕዝብ እንደሚበልጥ ይገመታል፡፡

ልማታዊ ሐኪሞች ሆይ! በጀርመን ሕዝብ  ከበረት ተከማችቶ እንደተጨፈጨፈው በኢትዮጵያም ሕዝብ በክልል ታጉሮ እየተጨፈጨፈ መሆኑን የምትገነዘቡ ይመስለኛል፡፡ ካልተገነዘባችሁም ጭፍጨፋውን ላለመረዳት አውቃችሁ ተኝታችኋል፡፡ ተገንዝባችሁ ጪጭ ካላችሁም ሳትሞቱ በሽንፍላ ከፈን ተከፍናችኋል፡፡ ጭፍጨፋ እንደሌለ የምትሰብኩትም እንደ መለስ ዜናዊና ቴድሮስ አድሃኖም ዓይናችሁን በጨው ታጥባችኋል፡፡ ዓይናችሁን በጨው የታጠባችሁት ሳይቀር በጮሌነት “አገዛዙ በድሎናል” በሚል ማመልከቻ የእንጀራ መጉረሻ መኖሪያ ፈቃዳችሁን በሰሜን አሜሪካ አግኝታችኋል፡፡ የማመልከቻችሁ ቀለም ሳይደርቅ በደሉን ካላችኋቸው ዘረኛ ነፍሰ-ገዳዮች ጀርባ በልማታዊ ሐኪምነት ቆማችሁ የሂፖክሪትስን መሐላ እንደ ናዚ ሐኪሞች ዘንችራችኋል፡፡

የሂፖክሪትስን መሐላ ከዘነቸራችሁት ሐኪሞች አንዳንዶቻችሁን ለምን ድሃ ከፍሎ ሊታከምበት የማይችል ዘመናዊ ሆስፒታል ከነፍሰ-ገዳዮች እግር እየወደቃችሁ እንደምትገነቡ ስንጠይቃችሁ “ውጪ አገር እየሄዱ የሚታከመውን ከበርቴዎች እዚያው ለማስቀረት” እሚል መልስ ሰጥታችኋል፡፡ ውጪ አገር እሚታከሙት ከበርቴዎች ደግሞ ነፍሰ-ገዳይዎች ወይም ከነፍሰ-ገዳይዎች ጋር የተሻረኩ ቱጃሮች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ነፍሰ-ገዳይዎችና ከነፍሰ-ገዳይ የተሻረኩ ቱጃሮች በድሃ ሥም የተረጠቡትንና ከድሃ ደም ሥር የመጠጡትን የደም ገንዘብ ለመካፍል ኪሳችሁን እንደ ካናዳ ኬሻ ከፍታችኋል፡፡ ከነፍሰ-ገዳዮች እየተዳራችሁ በጥይትና በግርፋት የሚያልቁትን ድሆች ረስታችኋል፡፡ ከአፋቸው እየሞለቀቁ በእንቁላልና በፍርፍር ያስተማሯችሁን እንጀራ ጋጋሪዋን ወይዘሮ ስለእናትን፣ እርፍ ጨባጩን አቶ አድማሱን፣ አምባሻ ጋጋሪዋን ወይዘሮ ሀዳስን፣ እንጨት ለቃሚዋን ወይዘሮ ዘይነባን፣ ቡና ለቃሚውን አቶ ረጋሳን፣ ቆሎ ሻጯን ወይዘሮ ሀሊማን፣ ጨጨብሳ አንጓቿን ወይዘሮ ጫልቱን፣ እንሰት ላጊውን አቶ ዘበርጋን፣ ጪቃ አቡኪውን አቶ ደሌቦን፣ ሸማ ሰሪውን አቶ ጫቦን ከድታችኋል፡፡

የናዚ ሐኪሞች የዘረኛውን የሂትለርን ጀኔራሎች እርካብ ሆነው ከፈረስ እንደሰቀሉ እናንተም በዘር  ከተለከፈው “መለስ ዜናዊ ጋር መስራት መባርክ ነው” ያለውን ቴድሮስ አድሐኖምን ባርጩማ ሆናችሁ ከወንበር ለመስቀል ትከሻችሁን ዝቅ አድርጋችሁ አጎብድዳችኋል፡፡ በነቴድሮስ አድሃኖም ጠባቂዎች ጭካኔ እየፈሰሰ ያለውን የአምቦዋን፣ የወልቃይቷን፣ የሁመራዋን፣ የጋንቤላንዋን፣ የወለጋዋን፣ የኮንሶንዋን፣ የኦጋዴኗንና የመተከሏን እናት እንባ ወደ ደም ቀይራችሁታል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሕክምና ጥበባቸውን የወረሳችሁትን ዳሩ ግን በቂ ሕክምና ተነፍጓቸው ያለፉትን ፕሮፌሰር አስራትን መቃብር ውስጥ በጦር ወግታችኋል፡፡ በነቴድሮስ ወታደሮች በመላ አገሪቱ በተረሸኑት ዜጎች ቀልዳችኋል፡፡

ሂትለርና አብረውት ዘግናኙን ወንጀል የፈጠሙት ሐኪሞች በስብሰው ፈራርሰዋል፡፡ በአድርባይነትና በሆዳምነት ድምጣቸውን አጥፍተው የነበሩት ሐኪሞችም ትቢያ ሆነዋል፡፡ እርግጥ ነው ስስታሙ አንጎላቸው፣ ጨካኙ እጃቸው፣ ሰፊው ከርሳቸውና አጎብዳጁ ወገባቸው ከገደል እንደ ወደቀ ሸክላ  ብትንትን ብሏል፡፡ አይሁዶችን በማምከን ሥራ ተጠምደው የነበሩት እንደነ ዶክተር ራይተር ያሉ ሐኪሞችም ከሞቱ በኋላ ክብራቸው ተገፏል፡፡ [17] ዘግናኝ ታሪካቸው ግን ዘመን በገፋ ቁጥር የበለጠ እየጎላና እየተንቀለቀለ ይሄዳል፡፡ እንደ ናዚ ሐኪሞች ሁሉ የእኔና የእናንተም ስስታም አንጎል፣ ሞጭላፊ እጅ፣ ቀላዋጭ ዓይን፣ ሰፊ ከርስ፣ አዙሮ እማያይ አንገትና አጎብዳጅ ወገብ ነገ ተበጣጥሶ ትቢያ ይሆናል፡፡ የማይበጣጠሰውና ትቢያ እማይሆነው እንዲያውም ዘመን በገፋ ቁጥር እየጎላ እሚሄደው ታሪካችን ይሆናል፡፡ እኛ እየተሽሎኮሎክን ያመለጥን ብንመስልም ታሪክ ድምጡን አጥፍቶ በመመዝገብና በመጠረዝ ላይ ይገኛል፡፡ በታሪክ መዝጋቢነትም  እንዳለመታደል እኛም እንደ ጀርመኖች የወንጀለኞችና ያልተባረኩ ሐኪሞች ዝርዝር ይኖረናል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ሆይ! ሕዝብን ደም ካስለቀሱ ወንጀለኞች ጋር መሽኮርመሙ ይቅርባችሁ፡፡ ስስትና አድርባይነት የሚያብከነክነውን ሥጋችሁን ለማርካት ስትሉ እባካችሁ ዓይናችሁን ጨፍናችሁ ከናዚ ሐኪሞች የደም ታሪክ ከመዘፈቅ ታቀቡ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ዋቢ

  1. ቃለ መጠይቅ ከዶክተር ግርማ መኮንን ጋር http://ethsat.com/esat-radio-wed-15-june-2016/ (Last accessed on June 18, 2016)
  2. List of Nazi MDS, https://en.wikipedia.org/wiki/List_of_Nazi_doctors (Last acessed on June 18, 2016)
  3. The Nazi Docotrs: http://www.auschwitz.dk/doctors.htm (Last accessed on June 18, 2016)
  4. Nazi doctors: http://faculty.webster.edu/woolflm/nazidocsandothers.html ((Last accessed on June 18, 2016)
  5. Earnest: The Third Reich—German physicians between resistance and participation, Int. J. Epidemiol.(2001)30 (1):37-42.doi: 10.1093/ije/30.1.37  http://ije.oxfordjournals.org/content/30/1/37.full
  6. Hippocratic Oath (400 BC) as translated by by Francis Adams (1849)http://www.britannica.com/topic/Hippocratic-oath ((Last accessed on June 18, 2016)
  7. The Nazi Doctors and the Nuremberg Code: Human Rights in Human Experimentation” Oxford University Press. May 7, 1992. Page 19 ((Last accessed on June 18, 2016)
  8. 13. Exhibition Examines Scientists’ Complicity In Nazi-Era Atrocities” The New York Times. Author, Warren E. Leary. November 10, 1992 ((Last accessed on June 18, 2016) (Last accessed on June 18, 2016)
  9. ሰብአዊ መብት ጉባኤ ሪፖርት 2008 ዓ.ም. http://ehrco.org/wp-content/uploads/2016/06/HRCO-141st-Special-Report-Amharic-Sene-01-2008.pdf (Last accessed on June 18, 2016)
  10. Protest Crack Down killed hundreds, Ethiopia, Human Rights Watch https://www.hrw.org/news/2016/06/15/ethiopia-protest-crackdown-killed-hundreds (Last accessed on June 18, 2016)
  11. Extrajudicial executions, Arbitray arests and detntions Amnesty International

 https://www.amnesty.org/en/countries/africa/ethiopia/report-ethiopia/ (Last accessed on June 18, 2016)

  1. Ethiopia, Police Open fire on Protesters https://freedomhouse.org/article/ethiopia-police-open-fire-protesters (Last accessed on June 18, 2016)

13 . Genocide watch documents on Ethiopia     http://www.genocidewatch.org/ethiopia.html (Last accessed on June 18, 2016)

  1. Three million Amhars Missing, Berhanu Abegaz https://www.youtube.com/watch?v=3-g-YWYBdbM ((Last accessed on June 18, 2016)
  2. Three Million Amara are Missing: An Analysis based on the 1994 and the 2007 Ethiopian Population Censuses, Berhanu Abegaz, http://ethiomedia.com/101facts/4513 9 ((Last accessed on June 18, 2016)
  3. Human right violation of Amharas Muluken Tesfaw http://video.ethsat.com/?p=24983 ((Last accessed on June 19, 2016)
  4. Experts Re-Examine Dr. Reiter, His Syndrome and His Nazi Past

https://partners.nytimes.com/library/national/science/health/030700hth-doctors.html ((Last accessed on June 18, 2016)

 

ሰኔ ሁለት ሺ ስምንት ዓ. ም.

↧

Sport: በሞሪንሆ ማን. ዩናይትድ ምርጥ 11 አሰላለፍ ምን ሊሆን ይችላል?

$
0
0

Morinuoማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ በደረጃው ሰንጠረዥ በ5ኛ ስፍራ ላይ ተቀምጦ ማጠናቀቁን ተከትሎ ባሰናበታቸው ሉዊ ቫንሃል ምትክ ፖቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ አዲሱ የቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩ በአሁኑ የዝውውር መስኮት በኦልድትራፎርድ ሰፊ የተጨዋች ዝውውር ሂደት እንዲጠበቅ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከወዲሁም በርካታ ምርጥ ብቃት ያላቸው ተጨዋቾች ስም ከማንችስተር ዩናይትድ ዝውውር ጭምጭምታ ጋር በመያያዝ ላይ ነው፡፡

የማንችስተር ዩናይትድ ቦርድም ለጆሴ ሞውሪኖ 200 ሚልዮን ፓውንድ የተጨዋች ግዥ በጀትን አፅድቆላቸዋል፡፡ ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም የስፖርት ሜይል የፉትቦል ተንታኞች ዘ ስፔሻል ዋን በማንቸስተር ዩናይትድ ስኳድ ከሚገኙት ተጨዋቾች የትኛዎቹን የቀጣዩ ሲዝን እቅዳቸው አካል ያደርጓቸዋል? የትኛዎቹን አዳዲስ ተጨዋቾችንስ ያስፈርማሉ? የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲረዳ በማሰብ የሞውሪንሆ የማንቸስተር ዩናይትድ ስራ የመጀመሪያው ሲዝን መደበኛ ቋሚ አሰላለፍ ከዚህ በታች ያለው እንደሚሆን ግምታቸውን ሰጥተውበታል፡፡

ግብ ጠባቂ

ዴቪድ ደ ሂአ

ስፔናዊው ኢንተርናሽናል ግብ ጠባቂ ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል በኃላፊነት የሚዘልቁ ከሆነ ማንቸስተር ዩናይትድን በአሁኑ የዝውውር መስኮት የመልቀቅ ሃሳብ እንዳለው ጠቁሞ ነበር፡፡ አሁን ግን ጆዜ ሞውሪንሆ የኦልድትራፎርድ ስራን በመረከባቸው የ25 ዓመቱ ዳሂአ ከእንግዲህ ስሙ ከሪያል ማድሪድ ዝውውር ጭምጭምታ ጋር እንዲነሳ በር ከፋች የሚሆንበት ምክንያት የሚኖር አይመስልም፡፡

ቀኝ ተመላላሽ

ማቲው ዳርሚያን

ጣሊያናዊው ኢንተርናሽናል የማንቸስተር ዩናይትድ የተሰለፈበትን የመጀመሪያውን ሲዝን ያሳለፈው በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ የአቋም አለመረጋጋት ችግር ተፈጥሮበት ነው፡፡ በአብዛኛው ችግር የታየበት በመከላከሉ ተግባር ላይ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾችን ችግር በመቅረፍ ደግሞ ከጆሴ ሞውሪንሆ የተሻለ ትክክለኛው ባለሙያ ባለመኖሩ ዳርሚያን በቀጣዩ ሲዝን የፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ መደበኛ ቋሚ አሰላለፍ እቅድ አካል ሆኖ በኦልድትራፎርድ ቢዘልቅ አስገራሚ አይሆንም፡፡

የመሃል ተከላካይ

ክሪስ ስሞሊንግ

እንግሊዛዊው የመሀል ተከላካይ የዘንድሮን ሲዝን በተሰናባቹ አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ስር የማይዋዥቅ ጥሩ አቋምን ይዘው ለማሳለፍ ከቻሉት የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ውስጥ ግንባር ቀደሙ በመሆኑ ከዚህ መልካም አጋጣሚ ሞውሪኖ ተጠቃሚ በመሆን ስሞሊንግን በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት እንዲጠቀሙበት እርግጠኛ ሆኖ ግምትን መስጠት ይቻላል፡፡

የመሃል ተከላካይ

ጆን ስቶንስ

የዛሬ ዓመት ጆሴ ሞውሪኖ በቼልሲ ስራቸው ሊያስፈርሙት ከፍተኛ ጥረትን ያደረጉበት እንግሊዛዊው ኢንተርናሽናል ተከላካይን ከኤቨርተን መግዛትን የአሁኑ የቅድሚያ አላማቸው እንደሚያደርጉት ይጠበቃል፡፡ ስቶንስ የዘንድሮው ሲዝንን ያሳለፈው አልፎ አልፎ የአቋም መሰረታዊ ችግር ታይቶበት ቢሆንም የመከላከል ስትራቲጂ ንጉስ በሆት ሞውሪንሆ ስር ግን ችሎታውን ለማሳመር ባይችል አስገራሚ ይሆናል፡፡

ግራ ተመላላሽ

ሉክ ሻው

እንግሊዛዊው ግራ ተመላላሽ በሴፕቴምበር ወር በእግር ስብራት ከሜዳ ከመራቁ በፊት ለማንቸስተር ዩናይትድ በተሰለፈባቸው ጥቂት ግጥሚያዎች በቦታው ላይ የተዋጣለት ብቃትን የተላበሰ ተጨዋች መሆኑን ያስመሰከረበት ታላቅ ፐርፎርማንስን ሞውሪኖ በምንም አይነት መልኩ ችላ እንደማይሉት ይታመናል፡፡ ገና በወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኝ ተጨዋች በመሆኑም ሞውሪኖ የእቅዳቸው አካል ያደርጉታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የመሀል ተከላካይ

ሳውል ሂጉዌዝ

የአትሌቲኮ ማድሪድ ከወዲሁ 54 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋን ያወጣበት ስፔናዊው ኢንተርናሽናል አማካይ ከወዲሁ በሞውሪኖ የግዥ ሊስት ከተካተቱት ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሳውል አትልቲኮ የዘንድሮው ሲዝን የቻምፒዮንስ ሊጉ ውድድር ዘመቻውን እስከ ግማሽ ፍፃሜ ለማድረስ እንዲችል በግማሽ ፍፃሜው በባየር ሙኒክ ላይ የግል ጥረት በታከለበት መልኩ አስገራሚ የማሸነፊያ ጎልን በማስቆጠር አበርክቷል፡፡

የመሃል አማካይ

ኔማኒያ ቪዲች

ለ27ቱ ሰርቢያዊ የመሀል አማካይ ብቃት እንደሞውሪኖ ሁሉ ሙሉ እምነት ያለው አሰልጣኝ አለ ለማለት አይቻልም፡፡ ማቲችም ከዚህ በፊት በሞውሪኖ ስር የነበረው ታላቅ ፐርፎርማንሱን በተሟላ ሁኔታ ለመመለስ በመመኘት ከማንቸስተር ዩናይትድ የሚቀርብለትን የግዥ ጥያቄን የመቀበሉ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ቀኝ ክንፍ

ሜምፊስ ዴፓይ

የዘንድሮው ሲዝንን ያሳለፈው ሊያስታውሰው በማይመኘው መልኩ ደካማ የጨዋታ እንቅስቃሴን በማሳየት ነው፡፡ ሆኖም ግን ዴፖይ የዘንድሮ ሲዝኑ ቁጭቱን በቀጣዩ ዓመት ማንነቱን በማስመስከር ወደኋላ ለመርሳት መጓጓትን ተናግሯል፡፡ ሞውሪኖም እንደዚህ አይነቱ ቁጭትን የሚያሳድሩ ተጨዋቾችን የመርዳት ባህል ያላቸውን በመሆኑ ሆላንዳዊ ኢንተርናሽናል ከእቅዳቸው ውጪ ሊያደርጉት አይመኝም፡፡

የአጥቂ አማካይ

ዋይኒ ሩኒ

ሩኒ የዘንድሮ ሲዝን ከተጋመሰ በኋላ የማንቸስተር ዩናይትድ የመሀል አማካይ ሚናን በመያዝ ውጤታማ እንቅስቃሴን ለማሳየት ቢችልም ሞውሪኖ ግን ለበርካታ ጊዜ ለቼልሲ ሊያስፈርሙት ምኞት አሳድረውበት የነበረው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበልን ከፊት አጥቂዎች ጀርባ ያለው ቦ እንደሚሰጡት ይጠበቃል፡፡

ግራ ክንፍ

አንቶኒ ማርሻል

ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል የማንቸስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች መሆኑን ያስመሰከረበት ሲዝንን ያሳለፈበት ሁኔታ በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ስር ተጠናክሮ እንደሚዘልቅበት ማበረታታችን ማግኘቱ የማይቀር ነው፡፡

የፊት አጥቂ

ዝላታን ኢብራሂሞቪች

ሞውሪኖ የቡድናቸው የማጥቃት ስትራቴጂን የሚመሩላቸው ትክክለናው የፊት አጥቂን የመያዝ ባህል አላቸው ለዚህ ተግባራዊነት ደግሞ ዝላታን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም የተሻለ አማራጭ ውሳኔ አይኖራቸውም፡፡ ከወዲሁም ስዊድናዊው ጎል አዳኝ በሞውሪኖ ስር የማንቸስተር ዩናይትድ አዲሱ ፈራሚ የመሆን ተስፋ የሰፋ ሆኗል፡፡

 

 

↧
↧

ትቸው ረስቸው 2 |እናንተው ፍረዱ! –አስፋ ጫቦ Dallas Texas USA

$
0
0
አቶ አሰፋ ጫቦ

አቶ አሰፋ ጫቦ

ቁጥር 1 ልንለው በምንችለው ትቸው! ረስቸው !ላይ ለዶክተር በየነ ጴጥሮስ ብዛት ያላቸው emails መላኬን ገለጬ ነበር። ከዚህ ውስጥ አንዱን October 10,2003 የጻፍኩትን አባሪ አድርጌ የላኩትን ይኸው አሁን አቅርቢያለሁ።

ሚስጥር (Confidential)ይላል። ስራዬ ብዬ ነው ሚስጥር ያልኩት። በኔ ግምት እዚህ email ውስጥ የሚታዩትን (የተገለጹትን) ውስብስብና የተቆላለፉ የሚመስሉትን የፈጠረው ራሱ በየነ ይመስለኛል። ይህንን የአካባቢ ማስረጃዎች ያረጋግጡልኛል። በጋሞ ዲሞክራቲክ ሕብረት አባላት መካከልና በኦሞቲክ ድርጀት አባላትመካከል የፈጠረው “ከፋፍለህ ግዛው ወይ አጋጨው “ማስረጃ ስለሚሆን ነው። በዚህ ምክንያት የላኩትንም email ማውጣቴ አይቀርም።

የዚህ email ሌላ ውስጠ ታዋቂ መልእክት እባክህ አሰራርህ ተደርሶበታልና ቀይረው ለማለት ጭምር ነው። ሌላው ትእዛዝ ወይም መመሪያ በማይመስል መልኩ በፖለቲካ ስራ መቻቻል ማቻቻል ሰውን እነደአመጣጡና ባህርዩ መስተናገድ ይገባል የሚል ትምህርት ያገኝበታል በማለት ነበር። 

ሳጥን ውስጥ (Box) ያስገባኋት ይህንን ሚስጥር የሚለውን ባለብዙ ገጽ ግምገማና ምክር አባሪ አድርጌ የለኩበት email ነው። እንዳልጨቀጨኩና (pestering) እንዳላጣብብህ (overwhelming) የሚል ተማጽኖ አለው። ምክንያት ፈልጎ ጠብ እንዳያነሳ መለማመጤ ነዉ ተብሎ ሊታይ ይቻላል። ወይም ዲፕሎማሲ!

የበየነ አንድ መሠረታዊ ባህይርይ መልስ አይሰጥም።ለማንም ለምንም ተጠያቂነት የለበኝም የሚል አመለካከት ሳይሆን አይቀረም።ጨለማን ተገን አድርጎ መስራት (ወይም አለማስራትም ልንለው እንችላለን )የሚወድ ይመስለኛል።

እዚህ ጽሁፍ ውስጥ የብዙ ሰዎች ስም ተጠቅሷል።ልደልዘው፤ልሰርዘው ወይም ልሸፋፍነው አልፈለኩም።አለአገባብ ስሜ ተነስቷል ለሚሉ ሁሉ አስቅድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ዋናው የበየንን ገጽ ለማሳየት ሙከራ እንጅ ሌሎችን ለመነካት ወይም ለመነካካትም አይደለም።ዘመኑ ይህ ከተጻፈበት ከ2003 ጀሞሮ 13 አመታት አልለፈዋል። የተቀበረው ተቀብሮ አሁንም እዚያ ያለው በየነ ጴጥሮስ ነው።

  ጣሊያንም መጣ፤ሔደ ተመለሰ፤

ሚናስ ብቻ ቀረ ቤት እያፈረሰን ያስታውሰኛል።

ለወጣቱም አንዳንድ መሠረታዊ የዲሞክራሲ ትምህርትም አያጣታም የሚል ተሰፋም አለኝ።ለሁሉም እናተው ፍረዱት!!

Points of View

A.CHABO gantagaro@yahoo.com   1017/03 11.51.AM.

To:abule2002@yahoo.com

Dear BeyenĂŠ

Hi!

I hope I am not pestering or overwhelming you

With Regards

Achabo

From: Achabo

Confidential

Tuesday, October 14, 2003

Dear Dr.Beyene

        Hi!

This is again about the SEPDC here in the USA I am not sure whether I am rushing you into something that you intentionally want to go slow.  Given the number of people who actually participated in one capacity or another at the Head Office of SEPDC in Addis and who now moved to the USA, I feel that it is possible to set up a better Core Office here in Washington, D.C.  II feel that there is enough material here to sift through the Good, the Bad and the Ugly and keep the Ugly out or on the sideline.

In the past few years, I intentionally kept away from SEPDC so as to avoid any vicariously liability on you and the SEPDC because of whatever I say and/or write.

As I have tried to explain to you in San Diego, California, the last time we met, I feel that the situation in Ethiopia in general and The SEPDC in particular has reached a crossroads.  I reached a decision to get engaged. And explained to you the highlights of the route my participation will follow. In that spirit I have been engaged in that endeavor since you left.

I anticipated some sort of at least token participation and nominal support from our SEPDC group here in Washington. I also anticipated some sort of resistance for one reason or another. In either case what I got is beyond what I bargained for. So far support real or nominal is not coming. On the contrary I sow a concerted effort in thwarting and/or outright hindrance.

I am not sure whether we will be able to say that there is a branch of SEPDC here except nominally and under questionable circumstances. Now there seems to be some sort of rush and scramble to set up an appearance of office of a sort. The effort does not appear genuine rather diversionary and to cover-up some mess and continue what they have been doing up to now.  The approach seems devoid of theory, practice and/or pragmatism. Rather there is an appearance of a desire to grab power or to thwart those who they think in power, especially you. From the minor glimpse that I took, I can safely say that it is not only Demissie Tsara that is out there to subvert your/our effort. There are many others here and I am not sure whether they have some root and following in Ethiopia.

I am not trying to complain or criticize anyone. I am just trying to pass over my empirical observation. Since you or no one, for that matter, gave me any insider view and background material on all our supporters or detractors here, I have to find out the hard way, that is, from conversations serious or casual that I had with the different ‘supporters’ and ‘functionaries ‘here. To my surprise, some of those whose names you gave me as supporters or activists are rather detractors. I would like to be informed if there are some more individuals on whom you have put some question mark. That will help and make my task easier.

As I had explained to you, I have started setting up a data bank of basic supporters.  It is supposed to be a starting point for creating a permanent Support Group. So far I have contacted about 40 people and the response has been positive. I expect geometric progression. The people I contact, as I have tried to explain to you, are not necessarily from the South. It includes people with “Goodwill” and “patriotism” from other areas of Ethiopian as well.

My approach thus far has been simple, direct, non-controversial, less political and more patriotic. I state that “…. the SEPDC has so far achieved more than its due. It intends to go to the next stage in its development. To that and other day-to-day activities it needs your support. If you have followed what has been achieved so far and have confidence in its future please support. The amount is a monthly contribution $10.00…” A lean body to be set up to oversee the raising of funds and disbursement.  A 3-person body will probably suffice. That is a coordinator, an accountant and an auditor. Transparency creates confidence. It is going to be carried out in cyberspace, e-mail extra. That is all and I wanted to keep it that way so as to avoid bickering and any string being attached with the $10.00 subscription.

Once the wheel starts moving, I intend to transform that Support Group into a non-profit organization. I am taking the American PAC as a model.  I hope you are familiar with it. The PAC (Political Action Committee) is a general support group that does not directly involve in political day-to-day activity. It maintains a facade of ‘neutrality’ and those who don’t have an appetite for politics are bound to support.

Eventually it will raise funds not only from Ethiopian Sources but also from far and wide. To do so it must be palatable to the taste of the Americans and other would/could be international support organizations. That is the Long Term Ideal!

The $ 10 subscription is simply to get started. The $10 is an arbitrary amount chosen by me in the hope that it will attract the larger number and money will not be an excuse not to join. They will always be encouraged to contribute more. Eventually it will go to asking support in kind for not only the office but for the victims of injustice and families as well.

I wanted this to be under the umbrella of SEPDC but politically as far removed as possible. This is to shield from any spillover of political bickering, infighting and the mood swings that usual accompany political ups and downs. That will probably will tend to have contaminating, hindering, frustrating or aborting effect on the Support Group. It will probably affect its longevity. Another reason for shield from political bickering, if any, is that there will probably be apolitical supporters to the Support Group and any political bickering will necessarily dampen their eager to support as a patriot.

That is how I at least view it.

I have shared this and other opinion a with some of the members of group and ‘leadership’ of SEPDC in the Washington D.C area I am sorry to say the reception by and large lukewarm, hostile, plagiarism and outright theft of my innovative idea and its perversion. Here are some to explain what I meant.

  • I had a domain paid for and registered in my name about six months ago as Awsa-Langano. My intention was to make it an Internet forum for brainstorming sometime in the future when the need and time arises. The idea came from the song of Melkamu Tebeje. I felt that the time is ripe now and shared this idea with Feleqe Eshete. He agreed reluctantly saying that he already had such an idea. I left that there because it was on the brainstorming stage. A week later he comes up with ta web site name Awassa and inviting me to join and participate in it. It was so brazen and shameful I got embarrassed. I will forward the registration to you to see.
  • The same thing happened to the Support Group Idea.  I shared the idea with some and all in the D.C area. The idea got truncated and turned upside down. They started collecting the sum of money and electing chairman and the rest from the same old group. The only thing remaining now of my idea is the $10 only. Fortunately I did not pass any of the names that I have approached. I asked if they had a list of supporters. What have been given, as supports are the names of who is who in the Washington area names like Fascia Belete. They have been a joke so far and want to make turn any innovative approach to farce. Felke Eshet spearheads this. I discussed why he is doing what he is doing. He was clear about it. He wants to have a control over you through that fund. “Since we are contributing, we must have a say as how Beyene runs the show. That is democracy” That is almost an exact quotation from Felq. You should have hinted to me that he is engaged in some sort of completion with you.
  • You will be having the cassette of the radio and will be the Judge of what transpired on the radio. I repeatedly asked Kedir to go on the air and refute all or part of the allegation and defamation of you and SEPDC. He categorically said No. The last time I brought about the subject about 3 weeks ago he hang up the phone on me.
  • Frustrated I arranged to go on the offensive so as to challenge, and at the same time to neutralize some of the audience for this diatribe. I told the intention to all of them and sent an email.  Feleqe Eshete insisted that I should not and Must Not at all take up the subject. He does not have any response to the why question but insisted that I should not get involved in it. Then they run like mad men and went on the air with the most embarrassing statement from the South. It was, I am afraid, Neamin who prepared it and told me that Assefa just left his office.

Why do they do these childish imbecile things? I am not sure and don’t want to venture into psychoanalysis. Here are some of my informed guesses from the bits and pieces that I get from here and there.

  • Kedir and Assefa don’t work for SEPDC. I don’t care about their loyalty to EPRP and they can keep their sentimental or ignorance based loyalty. What worries me most is the total betrayal of the SEPDC. That they work for EPRP is a public knowledge here. I have known about that for a long time now.
  • There is an undercurrent resentment simmering just below the surface against you.  I don’t know all the reasons. The resentment may be rooted simply in envy or instigated by others. It will appear that they want to keep you where you are for the moment but tarnish and politically damaged as much as possible. I have to the conclusion that is why they don’t want to refute the defamation against you even when I created an optimum condition.
  • Because of internal bickering the nature of which I am not sure, nothing has been accomplished so far. Even an attempt has not been made. When I just start mobilizing the whole world as Supporter they took it to be something exposing their incompetence and impotence real or induced. Hence the attempt to thwart and frustrate.

.

What can you do under the circumstances? I do not know. I say I don’t know because I am not privy of the relation you maintained with them. That is to say I don’t know the extent of influence you have to produce change. And in the absence of any knowledge on my part, I will take a guess and hope that you carry some weight here.  I will appreciate if you can convince them of the following; –

  • That I am not here to compete with them or anyone but simply to help and make available whatever asset I have. That I have no intention to compete here or anywhere else for whatever post there is.
  • Try to tell them that I am a friend not a threat and probably a very good tool to use rather than Shan
  • If you can, tell them that I have a right endowed by birth to do what I wanted to without requiring their, agreement consent or permission on the issue of the South
  • Try to set up a political core here. From bits and pieces of discussion I have, Getachew seems to be ok. He seems to have the ability to build consensus. He does not seem to have a big ego and appears to have outlived his EPRP past.
  • As I have mentioned Birhanu seems to possess common sense and exposure
  • Abebe Debotch  will be a good addition to the core. At least I have talked with him on the phone 3 or 4 times , and seem positively charged. His problem probably will be political maturity.
  • Asfa Yilma will be a new good addition. He has sober and penetrating intellect and low profile and does not create threat personality. He is not ambitious and doesn’t and will not compete for any position.
  • Dr. Bekele. I am not sure. One has to temper his politics and noise. I am not any surer of his alliance to the South any more.  He wants to eat his cake and still have it. Was he an EPRDF? Do you know whether he renounced that relation? That is some of the impression he created on me when I talked with him.
  • I also talked with Wondimagegn. I am not so sure of his tendencies. I hope he will not strength the Kedir group. If you know more about him communicate with Getachew.
  • I talked with Adnew in Atlanta Georgia and seems to have composed and aware. Apart from the physical distance, he could have made a good material for a Core.
  • .Hadiya Alemu does not want to participate in the Core Group. He gave me a reason but not satisfying.
  • Kedir and Assefa of course must be in it but with minimal influence. One has to create a position give them a high sounding name and PR with the Opposition Coalition
  • I will need some more time to suggest other names because I am still new and sifting through would always add one or 2 persons at a time.
  • Once the core is formed you and I must take from there and give at least an Interim Road Map that can officially be articulated on behalf of the South and whoever is to follow.
  • If at all they setup a Support Group outside the one intended by me, tell them to make it a separate entity from the political body.

As you can see the above is of people around the D.C area. There are some people that I need for the Support Group and eventually for executive office of a non-profit Organization should we reach that goal. The people that immediately come to mind are Haile Micheal from Minneapolis, Dr. Moges Mochana from Florida and Dr. Tektel Mulugeta from San Jose. Gideon Ersa is another name that comes up often. I intend to talk to him soon. I will appreciate if you call or e-mail Haile Michael and Gideon and tell to closely cooperate with me. I can take care of Tektele and Moges. I urge you to talk to Haile Michael on the phone and give this general idea.

↧

ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል- ኖአሚን በጋሻው

$
0
0

ኖአሚን በጋሻው   (ሎንግ ቢች – ካሊፎርኒያ)

naominbegashaw@gmail.com

Ginbot-arbegnoch.gif
ሁለት ራዲዮ ጣቢያዎች አሉ። ከዲሲ የሚተላለፉ። የግንቦት ሰባት አመራር የሆኑትን አቶ ንአመን ዘለቀን አቅርበው አወያይተው ነበር። የነጻነት ራዲዮና የአቶ አበበ በለው አዲስ ድምጽ ራዲዮ። በሁለቱራዲዮዎች መካከል ትልቅ ልዩነቶች ይታያሉ። አንደኛው፣ የነፃነት ራዲዮ፣ የወያኔው ፋና ራዲዮ ነው የሚመስለው። የፕሮፖጋንዳ ራዲዮ። ገና አዳምጬ ሳልጨርስ ነው የዘጋሁት። ሁለተኛው የአዲስ ድምጽራዲዮ ግን፣ ለሁለት ሰዓት የተላለፈ ቢሆንም ሙሉዉን አደመጥኩት። የተለያዩ አመለካከቶች የተስተናገዱበት ዘመናዊ ራዲዮ ጣቢያ ነው።
በፕሮፖጋንዲስቱ የነጻነት ራዲዮ በተላለፈው ላይ ብዙ ጊዜ አላጠፋም። የአዲስ ድምጽ ራዲዮ ላይ ግን በተላለፈው ላይ አንዳንድ ሐሳብ መጨመር እፈልጋለሁ።
አቶ ንአመን፣ አቶ አበበ ጥያቄዎችን እንኳን እስኪጨርሱ ለመታገስ ትግስት ጎድሏቸው በመሃል ጣልቃ እየገቡ ፣ እየደጋገሙ ያቋርጡ ነበር። ዶናልድ ትራምፕን ነው የመሰሉኝ።
“በምን ምክንያት ነው ግንቦት ሰባት ሻእቢያን በመደገፍ ፔቲሽን ለማስፈረም የሚንቀሳቀሰው ?” የሚል ጥያቄ ነው መጀመሪያ አቶ ንአመን የቀርበላቸው። ሲመልሱም ሶስት ምክንያቶች አስቀምጡ። አንደኛውምክንያታቸው “በኤርትራ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ካለው አይበለጥም። Double standard ፣ hypocrisy አለ ” የሚል ነበር። “ኮሚሽኑ ፣ ኢትዮጵያ የሰዎች መብት የሚከበርባት አገር ናት ብሎቢናገርና እናንተ ያንን ብትቃወሙ እሺ። ግን ስለኢትዮጵያ የተናገረው ነገር የለም። ከኢትዮጵያ ጋር ምን ግንኙነት አለው ?” ብለው ሲጠየቁ አቶ ንአመን መልስ አልነበራቸው። በሻእቢያ ላይ የደረሰውማበረታቻ ሆኖን፣ “ወያኔዎችም ለፍርድ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የበለጠ መስራት አለብን፤ ከኤርትራዉያኖች መማር አለብን” ማለት ሲገባ “ወያኔዎች የሚሰሩት ግፍ ስላልተካተተ የሻእቢያግፍ ለምን ይነሳል” ብሎ መንጨርጨር አስፈላጊ አልነበረም።

 

ሁለተኛው አቶ ንአመን ያቀረቡት ምክንያት በጣም የሚያስቅና የሚያስተዛዝብ ነበር፡፡ “እንዴ …ምን ነካቸው አቶ ንአምን ? “ ብዬ እጆቼን ራሴ ላይ እስካደረግ ድረስ ነበር የደነገጥኩት። “ኮሚሽኑበኤርትራ ያሉ ጥሩ ነገሮችን ያላገናዘበ ነው። በኤርትራ ማህበረሰባዊ ፍትህ (social justice) አለ። እንደዉም እዚያ ሄጄ ያነጋገርኳቸው ኤርትራዉያን፣ ነጻ ምርጫ ቢደረግ ኢሳያስን ነው የምንመርጠውነው ያሉኝ” ሲሉ ነበር፣ ሰው በላውን ኢሳያስ አፈወርቂን፣ ሳያፍሩና አይናቸውን በጨው አጥበው እንደ መልአክ ሊያቀርቡልን የሞከሩት።

 

እነዚህ ሁለት ምክንያቶች ፈር የለቀቁና ዉሃ የማይቋጥሩ፣ ደካማ ምክንያቶች ናቸው። ግንቦት ሰባቶች በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ብቻ ሳይሆን ለስብእና ትልቅ ንቀት እንዳላቸው ነው ያሳዩት።

 

አቶ ንአመን ያቀረቡት ሶስተኛ ምክንያት፣ በኔ አስተሳሰብ ትልቁና ዋና ምክንያታቸው ነው። “ኤርትራ ብቸኛ ደጋፊያችን ናት። ሻእቢያ ተዳከመ ማለት እኛ ተዳከምን ማለት ነው” ሲሉ በትክክልጭንቀታቸውን ነው ለሕዝብ ይፋ ያደረጉት። በርግጥም ሻእቢያ ከተመታ ፣ ሻእቢያ ከሞተ፣ የግንቦት ሰባት መጨረሻ ነው የሚሆነው። ግንቦት ሰባት እድል ፈንታዉ ሙሉ ለሙሉ ከሻእቢያ ጋር ስላደረገባለው አቅሙና ጉልበቱ ሻእቢያ ከመጠበቅ ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖረዉም። ለነርሱ ሻእቢያን መደገፍ የሕልዉና ጉዳይ ነው። ለዚህም ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ በዲሲ ባደረጉት ስብስባ፣ ለሻእቢያ ድጋፍእንዲሰጥ፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን የሚቃወም ፊርማ እንዲፈረም፣ ተማጽኖ ያቀረቡት። ለዚህም ነው ግንቦት ሰባት እንደ ድርጅት፣ የወልቃይት ጠገዴ ፣ ለሱዳን የሚሰጠው መሬት የመሳሰሉትንበርካታ ኢትዮጵያዊና አገራዊ ጉዳዮችን ያካተቱ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሥራ በተሰራበት ወቅት፣ አንዳቸውም ጊዜ “ይሄን ፔቲሽን ፈርሙ “ ብሎ ፣ መግለጫ አውጥቶ የቀሰቀሰበት ሁኔታ ሳይኖር፣ ሻእቢያንለመደገፍ በአዝማችነት ፔቲሽኖችን እያስፈረመ ያለው። ለዚህም ነው፣ እንደ አቶ ንአምን ያሉ አመራሮች በተለያዩ ሜዲያዎች በመቅረብ (media blitz) ከፍተኛ “ሻእቢያዊ” ቅስቀሳ ማድረግ የተያያዙት።

 

በነገራችን ላይ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን የኤርትራ መሪዎችን በሰው ዘር ማጥፋት ቢከስም ዉሳኔው የመጨረሻ ዉሳኔ አይደለም። ዉሳኔው 47 አገራት ( ኢትዮጵያን ጨመሮ12 ከአፍሪካ፣ 8 ከአሜሪካ፣ 13 ከእሲያና 14 ከአዉሮፓ) ባሉበት በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባዬ ይታያል። ጉባዬዉም የአጣሪ ኮሚሽኑን ሪፖርት ተመልክቶ ዉሳኔ የሚሰጠው ከአንድሁለት ሳምንት በኋላ ሲሆን፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ ኤርትራዉያን ጉብዬው፣ የኮሚሽኑን ዉሳኔ እንዲያፀድቅ ግፊት ለማድረግ፣ በጄኔቫ በሂን 23 ቀን 2016 ዓ.ም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል።

 

ጉባዬው ዉሳኔውን ካጸደቀ፣ ወደ ተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ያመራል። የጸጥታው ምክር ቤትም የጉባዬዉን ዉሳኔ በማጽደቅ የአለም ፍርድ ቤት አቶ ኢሳያስን እና ጓዶቻቸዉን ለፍርድእንዲቀርቡ መመሪያ ይሰጣል። ክሱ በጸጥታው ምክር ቤት የሚወሰን በመሆኑም እነ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ከነሚሎሶቬች ምድብ ይቀመጣሉ።
በመጨረሻ አንድ ነጥብ ላስቀምጥ። ሻእቢያ ከተባበሩት መንግስታት ጋር በሰብአዊ መብት፣ በፍትህና በሕግ የበላይነት …ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ፍቃደኛ ከሆነ፣ ግንቦት ሰባቶችና ሻእቢያእንደተመኙት፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉብኤ፣ የአጣሪ ኮሚሽኑን ዉሳኔ ሊቀለብሰው ይችላል።

ሻእቢያዎች የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽኑን ለማነጋገርም ሆነ ወደ ኤርትራ ገብቶ ማጣራት እንዲያደርግ ፍቃድ ለመስጠት ከጅምሩ ፍቃደኛ አልነበሩም። ሪፖርቱ ከወጣ በኋላም፣ ኮሚሽኑን መሳደብናማውገዝ ነበር የመጀመሪያው ስራቸው። ሆኖም ጥቂት ቀናት እንዳለፉ፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ንግግራቸውን እያስተካከሉ የመጡ ይመስላል። በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ኦስማን ሣሌ በኩልለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባዬ በላኩት ደብዳቤ፣ አገራቸው በሰብዓዊ መብት መከበር ዙሪያ ለመወያየት ዝግጁ እንደሆነች ነው የገለጹት። “ I wish to assure the Council that Eritrea shall remain open and committed to constructive engagement to promote and protect human rights and fundamental freedoms and Eritrea will lend its hands to make this body more credible and relevant to all stakeholders.” ነበር ባለስልጣኑ ያሉት። ይሄ በሻእቢያ ታሪክ ተሰምቶ የማያወቅ፣ ሻእቢያአፍንጫው ተይዞ ፣ ተገዶ የደረሰበት አቋም ነው።

 

ይሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ሻእቢያ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉብዬ ጋር አብሮ ለመስራት ከወሰነ፣ እንደፈለገ ሊሆን አይችልም ማለት ነው። በተለይም በተባበሩት መንግስታት፣ በአፍሪካሕብረት በመሳሰሉት የማይወደዱና የሚያስነቅፉ ተግባራቱን ማቆም ይኖርበታል።

የጸጥታው ምክር ቤት እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 ያወጣው ፣ ” ሕግ 1907″ የተባለው፣ በኤርትራና በሶማሊያ ዙሪያ ያስቀመጣቸው ነጥቦች አሉ። አንዱ ኤርትራ በአካባቢዋ ያሉ አገራትመንግስታትን የሚቃወሙ የትጠቅ ትግል የሚያደርጉ ድርጅቶችን መደገፍና መርዳት እንድታቆም የሚጠይቅ ነው። ከዚህም የተነሳ ሻእቢያ፣ ፈልጎ ሳይሆን ተገዶ በኤርትራ ያሉ የትጥቅ ትግል የሚያደረጉተቃዋሚዎችን ሊያግድ ይችላል።

 

በመሆኑም በነ አቶ ኢሳያስ ላይ የተወሰነው ዉሳኔ፣ ተቀለበሰም፣ አልተቀለበሰም፣ ግንቦት ሰባትና ሌሎች አስመራ ያሉ ደርጅቶች፣ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነው የወደቁት። በኤርትራ በኩል እናደርገዋለንየሚሉት ትግል መጨረሻም ሊሆን ይችላል። ወይም አቶ ኢሳያስ ለፍርድ ቀርቦ ፣ ግንቦት ሰባቶች ወዳጃችን ያሉትን በማጣት ዜሮ ይገባሉ፤ አሊያም ኢሳያስ ለራሱ ሲል፣ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋርመስማማት ስላለበት ይሽጣቸዋል። በዚህም በዚያ ኤርትራ ያሉ ተቃዋሚዎች ቀለጡ ማለት ነው።

 

ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ለዉጥ ለማምጣት የሚደረገው ትግል፣ በምን አይነት ሁኔታ ከሻእቢያ ጋር መያያዝ የለበትም አይሉ ብዙ ሲከራከሩ የነበሩት። ሻእቢያ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደንታ የለውም።በማናቸዉም ጊዜ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከገደል ላይ ለጥቁሙ ሲል የሚፈጠፍጥ ነው። ታማኝነት ብሎ ነገር በታሪኩ አያውቅም።የኢሕዓፓ ወዳጅ ነበር፤ ወዲያው ተገልብጦ ወደ ወያኔ ሄደ። ብዙምሳይቆይ ደግሞ ከወያኔ ጋር ደመኛ ሆነ። ነገርም ግንቦት ሰባቶች እንደ ቁሻሻ ይወረወራቸዋል።

 

በተለይም በዳያስፖራ ብዙ ወገኖች ለግንቦት ሰባት ድጋፍ እንዳላቸው ይታወቃል። አብዛኛው የግንቦት ሰባት ደጋፊ ድጋፍ የሚሰጠው በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ተደረጎስለተነገረው ነው። አገሩን ከመዉደዱ፣ ለወያኔ ካለው ጥላቻ የተነሳ ነው።

 

ሆኖም ለሕዝቡ እየተነገረ ያለው ነገር ዉሸት ነው።ህዝቡ  በሂደት እዉነቱን ይረዳና አይኖቹን ከሻእቢያ አንስቶ ወደ ራሱ ይመልሳል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ”

ብዙዎች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዉጥ የሚመጣው በኢትዮጵያዉያን ነው። መመካት እና ማደራጀት የሚያስፈለገው የኢትዮጵያን ህዝብ ነው። እኛዉ ኢትዮጵያዉያን በቂ ነን።

 

( አቶ አበበ ከአቶ ንአምን ጋር ያደረጉትን ለመስማት 36 ደቂቃ ወደ ፊት ይሂዱ)

http://www.addisdimts.com/radio-show-for-june-122016-2/

 

 

 

↧

ትቸው ረስቸው 2 እናንተው ፍረዱ! –አስፋ ጫቦ

$
0
0

አስፋ ጫቦ Dallas Texas USA

አቶ አሰፋ ጫቦ

አቶ አሰፋ ጫቦ

ቁጥር 1 ልንለው በምንችለው ትቸው! ረስቸው !ላይ ለዶክተር በየነ ጴጥሮስ ብዛት ያላቸው emails መላኬን ገለጬ ነበር። ከዚህ ውስጥ አንዱን October 10,2003 የጻፍኩትን አባሪ አድርጌ የላኩትን ይኸው አሁን አቅርቢያለሁ።

 

ሚስጥር (Confidential)ይላል። ስራዬ ብዬ ነው ሚስጥር ያልኩት። በኔ ግምት እዚህ email ውስጥ የሚታዩትን (የተገለጹትን) ውስብስብና የተቆላለፉ የሚመስሉትን የፈጠረው ራሱ በየነ ይመስለኛል። ይህንን የአካባቢ ማስረጃዎች ያረጋግጡልኛል። በጋሞ ዲሞክራቲክ ሕብረት አባላት መካከልና በኦሞቲክ ድርጀት አባላትመካከል የፈጠረው “ከፋፍለህ ግዛው ወይ አጋጨው “ማስረጃ ስለሚሆን ነው። በዚህ ምክንያት የላኩትንም email ማውጣቴ አይቀርም።

 

የዚህ email ሌላ ውስጠ ታዋቂ መልእክት እባክህ አሰራርህ ተደርሶበታልና ቀይረው ለማለት ጭምር ነው። ሌላው ትእዛዝ ወይም መመሪያ በማይመስል መልኩ በፖለቲካ ስራ መቻቻል ማቻቻል ሰውን እነደአመጣጡና ባህርዩ መስተናገድ ይገባል የሚል ትምህርት ያገኝበታል በማለት ነበር።

ሳጥን ውስጥ (Box) ያስገባኋት ይህንን ሚስጥር የሚለውን ባለብዙ ገጽ ግምገማና ምክር አባሪ አድርጌ የለኩበት email ነው። እንዳልጨቀጨኩና (pestering) እንዳላጣብብህ (overwhelming) የሚል ተማጽኖ አለው። ምክንያት ፈልጎ ጠብ እንዳያነሳ መለማመጤ ነዉ ተብሎ ሊታይ ይቻላል። ወይም ዲፕሎማሲ!

 

የበየነ አንድ መሠረታዊ ባህይርይ መልስ አይሰጥም።ለማንም ለምንም ተጠያቂነት የለበኝም የሚል አመለካከት ሳይሆን አይቀረም።ጨለማን ተገን አድርጎ መስራት (ወይም አለማስራትም ልንለው እንችላለን )የሚወድ ይመስለኛል።

 

እዚህ ጽሁፍ ውስጥ የብዙ ሰዎች ስም ተጠቅሷል።ልደልዘው፤ልሰርዘው ወይም ልሸፋፍነው አልፈለኩም።አለአገባብ ስሜ ተነስቷል ለሚሉ ሁሉ አስቅድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ዋናው የበየንን ገጽ ለማሳየት ሙከራ እንጅ ሌሎችን ለመነካት ወይም ለመነካካትም አይደለም።ዘመኑ ይህ ከተጻፈበት ከ2003 ጀሞሮ 13 አመታት አልለፈዋል። የተቀበረው ተቀብሮ አሁንም እዚያ ያለው በየነ ጴጥሮስ ነው።

ጣሊያንም መጣ፤ሔደ ተመለሰ፤

ሚናስ ብቻ ቀረ ቤት እያፈረሰን ያስታውሰኛል።

ለወጣቱም አንዳንድ መሠረታዊ የዲሞክራሲ ትምህርትም አያጣታም የሚል ተሰፋም አለኝ።ለሁሉም እናተው ፍረዱት!!

 

 

Points of View

A.CHABO gantagaro@yahoo.com   1017/03 11.51.AM.

To:abule2002@yahoo.com

Dear BeyenĂŠ

 

Hi!

I hope I am not pestering or overwhelming you

With Regards

Achabo

 

 

 

 

From: Achabo

 Confidential

 

Tuesday, October 14, 2003

 

Dear Dr.Beyene

 

Hi!

 

This is again about the SEPDC here in the USA I am not sure whether I am rushing you into something that you intentionally want to go slow.  Given the number of people who actually participated in one capacity or another at the Head Office of SEPDC in Addis and who now moved to the USA, I feel that it is possible to set up a better Core Office here in Washington, D.C.  II feel that there is enough material here to sift through the Good, the Bad and the Ugly and keep the Ugly out or on the sideline.

 

In the past few years, I intentionally kept away from SEPDC so as to avoid any vicariously liability on you and the SEPDC because of whatever I say and/or write.

As I have tried to explain to you in San Diego, California, the last time we met, I feel that the situation in Ethiopia in general and The SEPDC in particular has reached a crossroads.  I reached a decision to get engaged. And explained to you the highlights of the route my participation will follow. In that spirit I have been engaged in that endeavor since you left.

 

I anticipated some sort of at least token participation and nominal support from our SEPDC group here in Washington. I also anticipated some sort of resistance for one reason or another. In either case what I got is beyond what I bargained for. So far support real or nominal is not coming. On the contrary I sow a concerted effort in thwarting and/or outright hindrance.

 

I am not sure whether we will be able to say that there is a branch of SEPDC here except nominally and under questionable circumstances. Now there seems to be some sort of rush and scramble to set up an appearance of office of a sort. The effort does not appear genuine rather diversionary and to cover-up some mess and continue what they have been doing up to now.  The approach seems devoid of theory, practice and/or pragmatism. Rather there is an appearance of a desire to grab power or to thwart those who they think in power, especially you. From the minor glimpse that I took, I can safely say that it is not only Demissie Tsara that is out there to subvert your/our effort. There are many others here and I am not sure whether they have some root and following in Ethiopia.

 

I am not trying to complain or criticize anyone. I am just trying to pass over my empirical observation. Since you or no one, for that matter, gave me any insider view and background material on all our supporters or detractors here, I have to find out the hard way, that is, from conversations serious or casual that I had with the different ‘supporters’ and ‘functionaries ‘here. To my surprise, some of those whose names you gave me as supporters or activists are rather detractors. I would like to be informed if there are some more individuals on whom you have put some question mark. That will help and make my task easier.

 

As I had explained to you, I have started setting up a data bank of basic supporters.  It is supposed to be a starting point for creating a permanent Support Group. So far I have contacted about 40 people and the response has been positive. I expect geometric progression. The people I contact, as I have tried to explain to you, are not necessarily from the South. It includes people with “Goodwill” and “patriotism” from other areas of Ethiopian as well.

 

My approach thus far has been simple, direct, non-controversial, less political and more patriotic. I state that “…. the SEPDC has so far achieved more than its due. It intends to go to the next stage in its development. To that and other day-to-day activities it needs your support. If you have followed what has been achieved so far and have confidence in its future please support. The amount is a monthly contribution $10.00…” A lean body to be set up to oversee the raising of funds and disbursement.  A 3-person body will probably suffice. That is a coordinator, an accountant and an auditor. Transparency creates confidence. It is going to be carried out in cyberspace, e-mail extra. That is all and I wanted to keep it that way so as to avoid bickering and any string being attached with the $10.00 subscription.

 

Once the wheel starts moving, I intend to transform that Support Group into a non-profit organization. I am taking the American PAC as a model.  I hope you are familiar with it. The PAC (Political Action Committee) is a general support group that does not directly involve in political day-to-day activity. It maintains a facade of ‘neutrality’ and those who don’t have an appetite for politics are bound to support.

 

Eventually it will raise funds not only from Ethiopian Sources but also from far and wide. To do so it must be palatable to the taste of the Americans and other would/could be international support organizations. That is the Long Term Ideal!

 

The $ 10 subscription is simply to get started. The $10 is an arbitrary amount chosen by me in the hope that it will attract the larger number and money will not be an excuse not to join. They will always be encouraged to contribute more. Eventually it will go to asking support in kind for not only the office but for the victims of injustice and families as well.

 

I wanted this to be under the umbrella of SEPDC but politically as far removed as possible. This is to shield from any spillover of political bickering, infighting and the mood swings that usual accompany political ups and downs. That will probably will tend to have contaminating, hindering, frustrating or aborting effect on the Support Group. It will probably affect its longevity. Another reason for shield from political bickering, if any, is that there will probably be apolitical supporters to the Support Group and any political bickering will necessarily dampen their eager to support as a patriot.

That is how I at least view it.

 

 

I have shared this and other opinion a with some of the members of group and ‘leadership’ of SEPDC in the Washington D.C area I am sorry to say the reception by and large lukewarm, hostile, plagiarism and outright theft of my innovative idea and its perversion. Here are some to explain what I meant.

 

  • I had a domain paid for and registered in my name about six months ago as Awsa-Langano. My intention was to make it an Internet forum for brainstorming sometime in the future when the need and time arises. The idea came from the song of Melkamu Tebeje. I felt that the time is ripe now and shared this idea with Feleqe Eshete. He agreed reluctantly saying that he already had such an idea. I left that there because it was on the brainstorming stage. A week later he comes up with ta web site name Awassa and inviting me to join and participate in it. It was so brazen and shameful I got embarrassed. I will forward the registration to you to see.

 

  • The same thing happened to the Support Group Idea. I shared the idea with some and all in the D.C area. The idea got truncated and turned upside down. They started collecting the sum of money and electing chairman and the rest from the same old group. The only thing remaining now of my idea is the $10 only. Fortunately I did not pass any of the names that I have approached. I asked if they had a list of supporters. What have been given, as supports are the names of who is who in the Washington area names like Fascia Belete. They have been a joke so far and want to make turn any innovative approach to farce. Felke Eshet spearheads this. I discussed why he is doing what he is doing. He was clear about it. He wants to have a control over you through that fund. “Since we are contributing, we must have a say as how Beyene runs the show. That is democracy” That is almost an exact quotation from Felq. You should have hinted to me that he is engaged in some sort of completion with you.
  • You will be having the cassette of the radio and will be the Judge of what transpired on the radio. I repeatedly asked Kedir to go on the air and refute all or part of the allegation and defamation of you and SEPDC. He categorically said No. The last time I brought about the subject about 3 weeks ago he hang up the phone on me.
  • Frustrated I arranged to go on the offensive so as to challenge, and at the same time to neutralize some of the audience for this diatribe. I told the intention to all of them and sent an email. Feleqe Eshete insisted that I should not and Must Not at all take up the subject. He does not have any response to the why question but insisted that I should not get involved in it. Then they run like mad men and went on the air with the most embarrassing statement from the South. It was, I am afraid, Neamin who prepared it and told me that Assefa just left his office.

Why do they do these childish imbecile things? I am not sure and don’t want to venture into psychoanalysis. Here are some of my informed guesses from the bits and pieces that I get from here and there.

 

  • Kedir and Assefa don’t work for SEPDC. I don’t care about their loyalty to EPRP and they can keep their sentimental or ignorance based loyalty. What worries me most is the total betrayal of the SEPDC. That they work for EPRP is a public knowledge here. I have known about that for a long time now.
  • There is an undercurrent resentment simmering just below the surface against you. I don’t know all the reasons. The resentment may be rooted simply in envy or instigated by others. It will appear that they want to keep you where you are for the moment but tarnish and politically damaged as much as possible. I have to the conclusion that is why they don’t want to refute the defamation against you even when I created an optimum condition.
  • Because of internal bickering the nature of which I am not sure, nothing has been accomplished so far. Even an attempt has not been made. When I just start mobilizing the whole world as Supporter they took it to be something exposing their incompetence and impotence real or induced. Hence the attempt to thwart and frustrate.

.

What can you do under the circumstances? I do not know. I say I don’t know because I am not privy of the relation you maintained with them. That is to say I don’t know the extent of influence you have to produce change. And in the absence of any knowledge on my part, I will take a guess and hope that you carry some weight here.  I will appreciate if you can convince them of the following; –

  • That I am not here to compete with them or anyone but simply to help and make available whatever asset I have. That I have no intention to compete here or anywhere else for whatever post there is.
  • Try to tell them that I am a friend not a threat and probably a very good tool to use rather than Shan
  • If you can, tell them that I have a right endowed by birth to do what I wanted to without requiring their, agreement consent or permission on the issue of the South
  • Try to set up a political core here. From bits and pieces of discussion I have, Getachew seems to be ok. He seems to have the ability to build consensus. He does not seem to have a big ego and appears to have outlived his EPRP past.
  • As I have mentioned Birhanu seems to possess common sense and exposure
  • Abebe Debotch will be a good addition to the core. At least I have talked with him on the phone 3 or 4 times , and seem positively charged. His problem probably will be political maturity.
  • Asfa Yilma will be a new good addition. He has sober and penetrating intellect and low profile and does not create threat personality. He is not ambitious and doesn’t and will not compete for any position.
  • Bekele. I am not sure. One has to temper his politics and noise. I am not any surer of his alliance to the South any more. He wants to eat his cake and still have it. Was he an EPRDF? Do you know whether he renounced that relation? That is some of the impression he created on me when I talked with him.
  • I also talked with Wondimagegn. I am not so sure of his tendencies. I hope he will not strength the Kedir group. If you know more about him communicate with Getachew.
  • I talked with Adnew in Atlanta Georgia and seems to have composed and aware. Apart from the physical distance, he could have made a good material for a Core.
  • .Hadiya Alemu does not want to participate in the Core Group. He gave me a reason but not satisfying.
  • Kedir and Assefa of course must be in it but with minimal influence. One has to create a position give them a high sounding name and PR with the Opposition Coalition
  • I will need some more time to suggest other names because I am still new and sifting through would always add one or 2 persons at a time.
  • Once the core is formed you and I must take from there and give at least an Interim Road Map that can officially be articulated on behalf of the South and whoever is to follow.
  • If at all they setup a Support Group outside the one intended by me, tell them to make it a separate entity from the political body.

 

As you can see the above is of people around the D.C area. There are some people that I need for the Support Group and eventually for executive office of a non-profit Organization should we reach that goal. The people that immediately come to mind are Haile Micheal from Minneapolis, Dr. Moges Mochana from Florida and Dr. Tektel Mulugeta from San Jose. Gideon Ersa is another name that comes up often. I intend to talk to him soon. I will appreciate if you call or e-mail Haile Michael and Gideon and tell to closely cooperate with me. I can take care of Tektele and Moges. I urge you to talk to Haile Michael on the phone and give this general idea.

 

 

↧

ኤርትራ በጾረናው ውጊያ 18 ወታደሮቼ በኢትዮጵያ ተገድለውብኛል አለች

$
0
0

Issayas Afewerki

(የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው) የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰኔ 5 ቀን በጾረና ግንባር ከኢትዮጵያ ጋር በተካሄደው ከባድ ውጊያ በኤርትራ በኩል 18 ወታደሮች እንደሞቱ ገለጹ። ፕሬዝደንቱ ሰኞለት የኤርትራ ሰማእታት ቀን ሲከበር ባሰሙት ንግግር በኢትዮጵያ በኩል ተገደሉ ስለተባሉት ወታደሮች ቁጥር የተናገሩት ባይኖርም፤ ባለፈው ሳምንት የኤርትራ የማስታወቂያ ምንስቴር ባወጣው መግለጫ ከ200 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውንና ከ300 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ይፋ አድርጎ ነበር።

“እሁድ የሰማእታትን የአደራ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው፤ የአስተማሪዎቻቸውን ፈለግ ለተከትሉ 18 ማስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖቻን ኩራት ይሰማችሁ በክብርም ይታወሱ” ብለዋል ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ።

የኤርትራ መንግስት የሰጠው አሃዝ በነጻ ምንጭ የተረጋገጠ አይደለም። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት “እኛ እያነባን ስላልሆነ” ቁጥሩን መግለጽ አያስፈልገንም ሲሉ፤ ከኤርትራ በኩል የተገለጸው ተዓማኒነት እንደሌለው ማስረዳታቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር ግርማ አስመሮም በኤርትራ በኩል “ማስረጃ አለ” ሲሉ ገልጸዋል።

የኤርትራ መንግስት ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ባወጣው መግለጫ ዩናይትድ ስቴይትስ ከኢትዮጵያ ጋር ወግና የድንበር ግጭቶችን “ትቆሰቁሳለች” ስትል ያወጣችው መግለጫ “እውነታ የለውም” ሲል የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ዝርዝር መረጃዎችና ማረጋገጫዎችን ሳያቀርብ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ምንስቴር ያወጣው መግለጫ ባለፈው እሁድ በሁለቱ ሀገሮች መካከል በተካሄደው ውጊያና በሌሎች የድንበር ጉዳዮች ዩናይትድ ስቴይትስ “በጦር መሳሪያ አቅርቦት የተጠናከረ ጥቃት እንዲደርስ አግዛለች” ብሏል።

“ዩናይትድ ስቴይትስ በሁለቱም ሀገሮች መዲናዎች ባሉን ወኪሎችም ሆነ በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልእክተኞቻችን ኢትዮጵያና ኤርትራ በትግስት ነገሮች እንዳይባባሱ እስንዲሰሩ ጥሪ አቅርባለች”
የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ

የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ “ዩናይትድ ስቴይትስ በሁለቱም ሀገሮች መዲናዎች ባሉን ወኪሎችም ሆነ በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልእክተኞቻችን ኢትዮጵያና ኤርትራ በትግስት ነገሮች እንዳይባባሱ እስንዲሰሩ ጥሪ አቅርባለች” ብለዋል።

↧
↧

የኢትዮጵያ-ኤርትራ የጦርነት ጨዋታዎች፣ –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ይህን አስቂ ኝ (አስለቃሽ) ትአይንት  (ትያትር)  ፊልም ከዚህ ቀደም አላየነውምን?

Wargames-Amharic
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 ዘ-ህወሀት የሕዝብን ስሜት ለማስቀየስ (ለማወናበድ ) ስለሚያካሂደው የጦርነት ጨዋታ  ትችት በጽሁፍ አቅርቤ ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት ማለት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተመዝግቦ የሚገኝ አሸባሪ ድርጅት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወሀት መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመለኮስ እና ከግብጽ ጋር ደግሞ የውኃ ጦርነት ለማካሄድ የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ስለጦርነት አይቀሬነት ድምጹን ከፍ አድርጎ በማጉላት የወሬ ክኩን ይሰልቅ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት ይኸው በአሁኑ ጊዜ እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 ወደለመድነው የጦርነት አረንቋ ተመልሰን ለመዘፈቅ አሀዱ/አንድ በማለት ጀምረናል፡፡

ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደገና በድጋሜ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ስለ”ጦርነት” ሰበካ፣ ስለጦርነት ሟርት እና ስለጦርነት ከበሮ ድለቃ ሌት ከቀን እየተለፈፈልን ሳንወድ በግድ እንድናዳምጥ በመደረግ ላይ እንገኛለን፡፡

እናም ይህንን የሕዝብ ስሜት/ቀልብ ማስቀየሻ ጦርነት እንደገና መመልከት ይኖርብናልን?

የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው “አፈ ጮሌው” ረዳ እንዲህ በሏል፣ “በሁለቱም ወገኖች በኩል ከፍተኛ የሆነ እልቂት ተፈጽሟል፣ በይበልጥ ደግሞ በኤርትራ በኩል ያለው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ስንወስድ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ እስከ አሁን ድረስ ስንወስዳቸው ከቆዩት እርምጃዎች በዓይነቱ እና በመጠኑ ከፍ ያለ እርምጃ መውሰድ በጣም ጠቃሚ ነገር ስለሆነ አስተማሪ የሆነ እርምጃ ወስደናል፡፡“

ኤርትራ በበኩሏ 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በመግደል ከ300 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ቁስለኛ አድርጊያለሁ የሚል መግለጫ ይፋ አድርጋለች፡፡

የካሊፎርኒያ ግዛት የዩኤስ አሜሪካ ታዋቂ የምክር ቤት አባል/ሴናተር የሆኑት ሂራም ጆሀንሰን ከብዙ ጊዜ በፊት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጦርነት በሚመጣበት ጊዜ የመጀመሪያው የጥቃት ሰለባ የሚሆነው “እውነት” ነው፡፡“

ሁለት የጦርነት ተፋላሚ ቡድኖች በአንድ ዓይነት “እውነት” ላይ የጋራ ስምምነት ሲያደርጉ የምመለከት ከሆነ “እውነት” የመጀመሪያ እና ብቸኛ የጥቃት ሰለባ ሆኖ ስለመቆየቱ መገረም የምጀምር ይሆናል፡፡

እንደዚሁም ሁሉ የጠነባን ዓይጥ ማሽተት እጀምራለሁ፡፡ የጠነባን ዓይጥ ገና ከ10 ሺ ሜትሮች ርቀት ላይ ማሽተት እችላለሁ፡፡ ያ ሽታም  በኢትዮጵያ-ኤርትራን ጦርነት በሚባለው ላይ ተንሳፎ ይገኛል! (እፍ እፍ እፍ!!!)

በእርግጥ የጆሀንሰን ቁም ነገር የጦርነት ሰለባ መርህ አነጋገር  በጦርነት ተጫዋቾች ላይ አይሰራም፡፡

ለበርካታ ዓመታት ሳስተውለው እንደቆየሁት የዘ-ህወሀት አመራሮች ከሕዝብ ጋር መጥፎ የሆነ የግንኙነት አባዜ ላይ እንደወደቁ አድርገው እራሳቸውን በሚቆጥሩበት ጊዜ ለዚያ ማስቀየሻ ዘዴ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡

ዘ-ህወሀት በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ሰብአዊ ወንጀል፣ ሙስና፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀም እና ሰላማዊ ዜጎችን መጨቆንን ለመደበቅ ሲያስብ የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ስሜት ለማስቀየስ የሚያጋልጡትን መጥፎ ዜናዎችን ማፈን እና የሕዝብን ስሜት የማስቀየስ መንገድ እንደሚጠቀም እገምታለሁ፡፡

ያለፉት ጥቂት ሳምንታት ለዘ-ህወሀት መጥፎ ዜናዎች እንደነበሩ ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡

ባለፈው ሳምንት የዩኤስ አሜሪካ የቦንድ እና የአክሲዮን ልውውጥ ኮሚሽን ዘ-ህወሀት ህገወጥ ወንጀለኛ በሆነ መልኩ ከደጋፊዎቹ እና ጥቅም አገኛለሁ ብለው ለቦንድ ግዥ ክፍያ ሲፈጽሙ ከቆዩት ኢትዮ-አሜሪካውያን 6.5 ሚሊዮን ዶላር በህገወጥ መልክ ዘርፎ በመገኘቱ ያወናበደዉን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲመልስ ቅጣት ጥሎበታል፡፡ ዘ-ህወሀቶች ኮሚሽኑ ለሚያቋቁመው አስተዳዳሪ እ.ኤ.አ ሀምሌ 8/2016 ከማለፉ በፊት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡

ይህ ድርጊት ለዘ-ህወሀት ትልቅ ውርደት እና የኢትዮጵያውያንን እና የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ኪስ በማራቆት በአፍሪካ ታላቅ ግድብ እሰራለሁ በማለት መቋጫ የሌለው ዲስኩሩን ሲያሰማ በነበረው እና አሁን በህይወት በሌለው በወሮበላ ዘራፊው መሪ በአምባገነኑ መላስ ትውስታ ላይ ታላቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ነገር ነው፡፡

ባልተመዘገበ እና ህገወጥ በሆነ የቦንድ ሽያጭ በማጭበርበር ግዙፍ የሆነ ግድብ በአፍሪካ እገነባለሁ ማለትን እስቲ አስቡት ጎበዝ! ቦንድ የማጭበርበር እኩይ ምግባሩን መከላከያ ዘዴ መሆኗ ነውን?

በዩኤስ አሜሪካ ሕግ መሰረት ያልተመዘገበ ቦንድ መሸጥ ሕገ ወጥ ነው በማለት ከሶስት ዓመታት ገደማ በፊት የተናገርኩ ሲሆን ከተናገርኩ ከሶስት ዓመታት በኋላ የዘ-ህወሀት መሪዎች የማጭበርበር አባዜ የተጠናወታቸው በመሆኑ ከማሰሮው ውስጥ እጃቸውን እንዳስገቡ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ማሰብ እችላለሁ፡፡

የሚሰማ ጆሮ እና የሚያስተውል አእምሮ የላቸውም እንጅ እ.ኤ.አ ግንቦት 8/2013 ፊት ለፊት እና በቀጥታ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ይህንን ነገር አታድርጉ! ያልተመዘገበ ቦንድ አትሽጡ! በዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል እና የአካባቢ መንግስታት ሕግ መሰረት ወንጀል ነው ብዬ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ወንጀልን አትስሩ፣ ከጊዜ በኋላ አደጋው የሚያንዣብብ እና የሚያስጠይቃችሁ ይሆናል በማለት በግልጽ ተናግሬ ነበር፡፡

እንደተናገርኩት ከሶስት ዓመታት በኋላ ያልተመዘገበ ቦንድ ሽያጭ (ወንጀል ነው፣ የ1933 የቦንድ ድንጋጌ ክፍል 20 (b)ን ይመልከቱ) ወንጀል ስለሆነ ማጅራታችዉን ተያዙ፡፡

ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት ያልተመዘገበ ቦንድ ዋና ሻጮች የወንጀል ቅጣቱን በማጭበርበር አንደተለመደው ሊያልፉት አልቻሉም፡፡

በእርግጥ አላለፉትምን?

የዘ-ህወሀት መሪዎች ለበርካታ ዓመታት ያህል ሰብአዊ መብቶችን እየደፈጠጡ ምንም ዓይነት ተጠያቂ ሳይሆኑ ደረታቸውን ነፍተው ተቀምጠው እንደሚገኙት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሜሪካ ሕጎች ላይም አፍንጫቸውን በመንፋት ከወንጀል ተጠያቂነት የሚያመልጡ መስሎ ታይቷቸዋል፡፡

በምንም ዓይነት መልኩ ሊሆንላቸው አልቻለም፡፡

ጉዳዩ በኮሚሽኑ (SEC) ግልጽ እና ይፋ ከሆነ በኋላ የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂዩማን ራይትስ ዎች (ሂራዎ)/Human Rights Watch (HRW) “ጭካኔ የተመላበት እርምጃ፡ ለኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ተቃውሞ የተሰጠ የግድያ እና እስራት ምላሽ“ በሚል ርዕስ ትልቅ ዘገባ አቅርቧል፡፡

ያ ዘገባ “ከመጠን ያለፈ እና አላስፈላጊ የሆነ የጥላቻ ኃይል መጠቀም እና ዜጎችን በጅምላ በቁጥጥር ስር የማዋል፣ መጥፎ የእስር ቤት አያያዝ፣ የሰላማዊ አመጽ እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት የመረጃ ምንጮችን መቆጣጠር“ በማለት ዝርዝሩን አቅርቧል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት የሂራዎ/HRW የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክር የሆኑት ሌዝሊ ሌፍኮው እንዲህ ብለው ነበር፣ “የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የሰው ልጆችን ህይወት ከቁብ ሳይቆጥሩ የጭካኔ ተኩስ በመክፈት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ አርሶ አደሮችን እና ሌሎችን ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል፡፡“

ለሰው ልጆች ህይወት ምንም ዓይነት ቁብ ሳይሰጡ በሰላማዊ ተቃዋሚ ስብስብ ላይ የጭካኔ ተኩስ መክፈት በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ሰብአዊ ወንጀል ነው፡፡ ይህንን የምለው ለታሪክ ምዝገባ ብዬ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 የዘ-ህወሀት ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በአመጹ ላይ የተገደሉት ሕዝቦች “ሁከት እና ብጥብጥን ዓላማ ያደረገ የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል በመፍጠር ሞዴል አርሰ አደሮችን፣ የህዝብ መሪዎችን እና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩትን የጎሳ ቡድኖች መግደል በመጀመራቸው ነበር” ብሏል፡፡

የሚገርም ነገር እኮ ነው ጎበዝ! በመንገድ ላይ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ የሁለተኛ ደረጃ እምቦቃቅላ ተማሪዎች እና የኮሌጅ ተማሪዎች በምን መስፈርት እና መለኪያ ነው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሊባሉ የሚችሉት? ወያኔ በእራሱ የፍርሀት ምዕናብ እየፈጠረ በህዝብ ላይ የሚነዛው ሽብር ካልሆነ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?

ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ የተባለው ድራጎን (ዘንዶ)፣ ሳንዲ እየተባለች የምትጠራውን ተንቀሳቃሽ ሲኒማ ልጃገረድ ውሸት እና ቅጥፈት ወደሚነገርባት ምድር የወሰደበትን ታሪክ  አስታወሰኝ፡፡ ሳንዲ እዚያ ከደረሰች በኋላ በሬ ወለደ እያለ የሚናገረውን ፕናክዮንን አገኘችው፡፡

ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ እና ሳንዲ ማንም አይቷቸው የማያውቅ ቀይ እና ሰማያዊ ላም እንዲሁም ቀይ እና ነጭ ዝሆንም አዩ፡፡

13 ወራት ሙሉ ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት በዘ-ህወሀት ቁጥጥር ስር ባለችው ኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ልጆች እና የኮሌጅ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር እንደተዘጋጀ ቡድን ተቆጥረው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሆነው ይታያሉ፡፡

ኢትዮጵያ 13 ወራት ሙሉ የፀሐይ ብርሀን የሚፈነጥቅባት ሀገር መሆኗን ነበር እኔ የማስታውሰው፡፡

በነገራችን ላይ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ሌሎች እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ ተደርጎ በነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ወደ 2000 ገደማ በሚሆኑ ሰላማዊ ኬንያውያን ዜጎች እልቂት ላይ እጃቸው አለበት በሚል የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እ.ኤአ. በ2012 ክስ መስርቶባቸው ነበር፡፡

ሂራዎ/HRW በኦሮሞ ሰላማዊ አመጸኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው እልቂት እንዲጣራ ነጻ የሆነ አጣሪ አካል እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት እንደተለመደው የዝሆን ጆሮ (የጅብ ሆድስ አለኝ) ይስጠኝ በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፡፡

ዘ-ህወሀት ወደ 20 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነውን ህዝብ እያሰቃየ ያለውን የረሀብ ሁኔታ አያያዝ በሚመለከት እያደረገ ስላለው ፍጹም የሆነ ብቃትየለሽነት እና ይኸ አውዳሚ የሆነ ረሀብ በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እይታ ደብቆ ለማቆየት እያደረገ ባለው አሳፋሪ ጥረት የህዝብ ግንኙነት ስራው በመጥፎ ሁኔታ ተበላሽቶበታል፡፡

ከዩኤስኤአይዲ/USAID እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች መጥፎ ሸፍጥ ጋር በመተባበር ዘ-ህወሀት ድርቁ ካጠቃቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት መረጃ እንዳይወጣ በማድረጉ እና ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ እውነታውን ለእራሳቸው እና ለህዝቡ ፈልፍለው እንዳያወጡ በመከልከሉ ደባ ተሳክቶላቸዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ዘ-ህወሀት ስለረሀቡ ሁኔታ ስለጠቅላላ ተጠያቂነቱ እና ግዴለሽነቱ፣ ለብቃትየለሽነቱ እና ወንጀለኛነቱ ምንም ነገር ባለመሆኑ ስኬታማ ሆኗል፡፡ (ለዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ለጋይሌ ኢ. ስሚዝ የጻፍኩትን ደብዳቤ ይመልከቱ፡፡)

ዘ-ህወሀት ሁሉንም መጥፎ ዜናዎች ሁሉ ፍጹም በሆነ መልኩ ለምን እንደሚያፍን ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡

ዘ-ህወሀት የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ መጥፎ ዜናዎችን በማፈን የጦርነት ወሬዎችን ከማምረት እና የጦርነት ነጋሪት ከመጎሰም የተሻለ ምን የተሻለ ስልት ሊኖረው ይችላል?

በዘ-ህወሀት እና በስተሰሜን በኩል ባሉት ጠላቶቹ መካከል የሚካሄደው ጦርነት በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው የጽጌረዳ ጦርነት ዓይነት ነው፡፡ የተለያዩ አባላት በሆኑት በአንድ ቤተሰብ መካከል የሚደረግ ጦርነት የውስጥ ጦርነት ነው፡፡

ዘ-ህወሀት እና ጠላቶቼ ናቸው እያለ የሚወነጅላቸው ኃይሎች በወንድማማችነት በአንድ ላይ ሆነው ለበርካታ ዓመታት በመዋጋት ወታደራዊውን አገዛዝ በማስወገድ ስልጣንን ተቆጣጠሩ፡፡ በወታደራዊ ኦፕሬሽን እና በህዝብ ግንኙት ስራ በአንድ ላይ ሆነው በመረዳዳት በወታደራዊ ጓደኝነት ሲታገሉ ቆይተው ነበር፡፡

በርካታ የዘ-ህወሀት አመራሮች ከጠላቶቻቸው ጋር የቤተሰብ እና የስጋ ዝምድና ትስስር እንዳላቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ አሁን እየከሰሷቸው ካሉት ጋር አስቂኝ በሆነ የመድረክ ላይ ተውኔት በደስታ ስልጣንን ተካፍለው እንደ አበደ ውሻ ጭራቸውን በመቆለፍ ቆዩ፡፡ ያ ሁኑታ ግን እ.ኤ.አ በ1993-94 ላይ ተቋረጠ፡፡

እ.ኤ.አ ከ1998-2000 ባለው ጊዜ ውስጥ ሁለቱ የጦር ጓደኛሞች በድንበር ጦርነት ተጠመዱ፡፡ ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት በመጣስ የኢትዮጵያን ግዛት ተቆጣጠሩ፡፡ ሆኖም ግን በግጭቱ ከ70 እስከ 120 ሺ የሚገመት የወታደሮች እና የሲቪል ዜጎች ህይወት ከተገበረ በኋላ ተቆጣጥረውት ከነበረው ግዛት በኃይል ተባረሩ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቡ አለቃ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወዲያውኑ የድል ዜናን አወጀ፣ እናም በዓለም አቀፍ የሽምግልና እርቅ ሰበብ በተሰላ የፖለቲካ የሸፍጥ ስሌት እና በሀገር ክዳት ወረውት የነበረውን የሀገሪቱን አንጡራ ግዛት ተመልሶ ኤርትራውያኖች እንዲወስዱት በመፍቀድ የተንበርካኪነቱን የመድረክ ላይ ተውኔት አከናወነ፡፡

አምባገነኑ መለስ ጠንካራ የሕግ መከላከል ጥረትን ማድረግ ሲችል የሽምግልና የዕርቅ ስምምነቱ የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ አያወጣም በማለት የሀገርን ጉዳይ እንደተራ ነገር በመቁጠር ጉዳዩን አጣጣለው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቀድሞ የጦር ጓደኛሞች በጦርነት ላይ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ የሌባ ጣቶቻቸውን አንዳቸው በአንዳቸው ላይ በመቀሰር የተለመደ ተራ ቅጥፈታቸውን በማራመድ ላይ ናቸው፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ ውሸት እንጅ እውነት በአፋቸው የማይገባ ኃይሎች በእርግጠኝነት ጦርነት ያካሂዳሉ ወይስ ደግሞ የጦርነት ጨዋታ በመጫወት ላይ ነው የሚገኙት?

ሆኖም ግን ለምን እርስ በእርሳቸው እንደሚዋጉ ትክክለኛውን ነገር አይናገሩም፡፡

አንድ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳቀረበው ውንጀላ ከሆነ የኤርትራ መሪዎች በሰው ልጆች ላይ የመብት ረገጣ ማለትም ማሰቃየትን፣ ግድያ እና በባርነት መያዝን ጨምሮ የሰብአዊ መብትን ይደፈጥጣሉ የሚል ዘገባ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የምታቀርበው ኢትዮጵያ ናት የሚለው የመድረክ ላይ ትወና የተተወነው በኢትዮጵያ ነው በማለት በኢትዮጵያ ከምስክሮች የሚሰበሰበው መረጃ እንዳትረጋጋ ለማደረግ ጥረት ለምታደርገው ሀገር ለኤርትራ ጥሩ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ እንድታገኝ አስችሏታል፡፡

የተመድ ዘገባ ለጦርነቱ መንስኤ መሆን ችሏልን?

“ሀገሮች ለምን እንደሚዋጉ“ በሚል ርዕስ ሪቻርድ ኔድ ሌቦው በ2010 በጻፉት መጽሐፋቸው ላይ አራት ታሪካዊ ዓላማዎች፡ ፍርሀት፣ ፍላጎት፣ ዝና እና በቀል በሚል መንግስታት ጦርነትን እንዲቀሰቅሱ ይመሯቸዋል በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ አብዛኞቹ ጦርነቶች ለዝና እና ቀደም ሲል አንዱ መንግስት በጠላቱ ላይ ድልን በመቀዳጀት ግዛቱን ያስለቀቀው ከሆነ ያንን ለመበቀል ሲባል የሚደረጉ ናቸው በማለት ይሞግታሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዝና፣ በቀል እና ግዛትን ለመያዝ ሲባል በሁለቱ መንግስታት መካከል ለጦርነት መንስኤ ሊሆን ይችላልን?

እኔ የማደርጋቸው የአምባገነንነት እና ጦርነት ጥናቶች በእነዚህ ነገሮች የሚቀሰቀስ ሌላ የተለዋጭ ገለጸ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡

“የጦርነትን ካርድ” ማውጣት በአምባገነኖች የእጅ መጽሐፍ ውስጥ ያለ አሮጌው የማጭበርበር ዘዴ ነው፡፡

የእጅ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፣ “የህዝብ ጥላቻ ሲመጣ ጦርነትን አውጅ፡፡ እውነተኛ ወይም ደግሞ የውሸት የማስመሰያ ጦርነት አውጅ፡፡ ምንም ዓይነት ችግር የለውም፡፡ ስለጦርነት አውራ፡፡ የጦርነት ቅስቀሳን ሆን ብለህ አሰራጭ፡፡ የጦርነት ከበሮ ምታ፡፡ የጦርነት ጨዋታዎችን ተጫወት፡፡“

ግን ለምን ጦርነት?

ምክንያቱም ጦርነት የተረጋገጠ እና በተግባር የተፈተነ የህዝብ ስሜት ማስቀዬሻ ፍቱን ዘዴ ነው!

ከሮማ ነገስታት ጀምሮ እስከ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ የጦርነት ጌቶች እና ትናንሽ አምላኮች የጦርነት ካርድን ተጫውተዋል፣ እናም በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት የግዛት ዘመናቸውን ለማስቀጠል ሲሉ በህዝቡ ልብ ውስጥ የአርበኝነት ትኩሳትን ይቀሰቅሳሉ፡፡

በምዕተ ዓመታት የጦርነት ቴክኖሎጂው ሊቀየር ይችላል ሆኖም ግን የማታለል ማሽኑ፣ ማጭበርበሩ፣ ሸፍጡ እና የጦርነት ናፋቂዎች የከበሮ ድለቃ ዜማ እና አፈጻጸም እስከ አሁንም ድረስ ያው ነው፡፡

አምባገነኖች ሁልጊዜ በጦርነት ቃላት ይጀምራሉ፣ እናም ህዝቦቻቸውን በጦርነት ውሸት ፕሮፓጋንዳዎች፣ ፍብረካዎች እና ስለጦርነት ዝርዝር መረጃዎች የሌለው እና አሳሳች መረጃዎችን በማቅረብ በፕሮፓጋንዳ ጎርፍ እንዲጥለቀለቅ ድርጋሉ፡፡

አምባገነኖች በጦርነት መጀመሪያ አካባቢ ሊተነበይ የሚችል የአካሄድ ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለጦርነቱ አስፈላጊነት ግዙፍ የሆነ መግለጫ ለህዝብ ያቀርባሉ፣ እንደዚሁም ሁሉ በሀገር ውስጥ ታላቅ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ተስፋን በመሰነቅ በጠላታቸው ላይ ግዙፍ የሆነ ጥላሸት የመቀባት ዕኩይ ምግባርን ያራምዳሉ፡፡

ታምራዊ በሆነ መልኩ የእናት ሀገር ፍቅርን ከመቅጽበት ይለብሳሉ፣ በሰንደቅ ዓላማዎቻቸው ውስጥ ይጠቀለላሉ እናም ኃያል አርበኞች ይሆናሉ፡፡ አርበኝነትን ለማነሳሳት በመሞከር የተወሰዱ ግዛቶችንም እናስመልሳለን በማለት ቃል ይገባሉ፡፡

አምባገነኖች የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ዓይን ባወጣ መልኩ በሀገር ወዳድ ብሄራዊነት እና የትምክህት እንቅስቃሴዎችን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለማይቀረው የጦርነት ጥቃት፣ ስለማይታዩ ጠላቶች፣ ሳይታሰብ ስለሚመጡ አሸባሪዎች፣ ስለሀገር ሉዓላዊነት መደፈር እና ስለሌሎች ነገሮችም ሁሉ ገደብ የሌለው ፕሮፓጋንዳ እና ቅስቀሳ በማካሄድ በህዝቡ ዘንድ ፍርሀት እንዲነግስ ያደርጋሉ፡፡

በሚያገኙት በማንኛውም አጋጣሚ ሁሉ ህዝቡ ስሜታዊ ሆኖ በጠላቶቻቸው ላይ በቁጣ እንዲነሳ በመቀስቀስ የህዝብን ድጋፍ ለማግኘት አሳፋሪ እና የሌለ ታሪክ በመፍጠር እነርሱ አገር ወዳድ አርበኛ የእነርሱ ተቃዋሚዎች እና ጠላቶች ደግሞ ምንም ዓይነት የሀገር ወዳድነት አርበኛነት የሌላቸው አድርገው ይፈርጃሉ፡፡

ሁሉም ነገር ሲከሽፍ እና ሲወድቅ አምባገነኖች በህዝቡ ላይ ፍርሀት እና ስሜታዊነት እንዲነግሱ በማድረግ የህዝብን ስሜት በማስቀየስ እነርሱ ከተዘፈቁበት ሰብአዊ ወንጀል እና አምባገነናዊ አገዛዝ ለማምለጥ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ የጦርነት ቃላት ስለአርበኝነት እና ስሜታዊነት በመቀስቀስ ከመክሰስ እና ጥላሸት ከመቀባት የበለጠ ኃይል የላቸውም፡፡ ወደ ሌላ ወደየትም ፈቀቅ ሳይሉ ስም በማጥፋት እና ጥላሸት በመቀባት ላይ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ፡፡

ሆኖም ግን አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በጦር ሜዳ አውድ ውስጥ የጥይት ጭሆት ካቆመም በህዋላ ስለጦርነት ማውራት እና የጦርነት ነጋሪት መጎሰምን አጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

ሆኖም ግን ጦርነት ለአምባገነኖች የማታለያ ሀሳብ ነው፡፡

የአምባገነኖች የመኖር ህልውና በጀመሩት ጦርነት የማሸነፍ ዝንባሌ የሚወሰን ይሆናል፡፡

በጦርነት የአምባገነኖች መሸነፍ ማለት የህልውናቸው ፍጻሜ ማለት ነው፡፡

የተሸነፉ አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት ወይም ደግሞ በሌሎች ህዝባዊ አመጾች ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ አምባገነኖች በሚሸነፉበት በእያንዳንዱ ጦርነት የመሰደድ፣ የመታሰር እና የመሞት ዕድላቸው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

ጥቂት የአፍሪካ አምባገነኖች ዓይን ባወጣ መልኩ ያለምንም ተጨባጭነት ሁኔታ በለኮሱት ጦርነት ቢሸነፉም ቅሉ ለበርካታ ጊዚያት በስልጣን ላይ ተጣብቀው ቆይተዋል፡፡ በእርግጥ ሽንፈታቸውን ለምክንያት እና ለይቅርታ በመጠቀም ህዝቦቻቸውን ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ለመግዛት ይጠቀሙበታል፡፡ ጠላቶቻቸውን እንደ ጭራቅ በመቁጠር በእራሳቸው ህዝቦች ላይ እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ህዝቡ ለጥ ገጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ይጠቀሙበታል ፡፡

አምባገነኖች ስለሚጭሩት የጦርነት እሳት እውነታነት የሂትለር ቀኝ እጅ ከነበረው ከኸርማን ጎሪንግ የበለጠ እውነታውን ያረጋገጠ በዚህ ዓለም ላይ የለም፡፡ ኸርማን እ.ኤ.አ በ1945 ኑረምበርግ በተሰየመው የዓለም አቀፍ ችሎት ላይ ቆሞ ሲጠየቅ እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡

“በተ%

↧

በሲኖዶስ የጳጳሳት ሹመት ላይ የተነሡ ተቃውሞዎች ሲፈተሹ!

$
0
0

sinod

ሲኖዶስ ብየ ስል “የትኛውን?” የሚል አይጠፋም፡፡ በአንድ ሀገር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሊኖር የሚችለው አንድ ሲኖዶስ ነው ሁለት ሲኖዶስ የለም፡፡ ሲኖዶስ ይሰደዳል ወይ?፣ እዚህ ሀገር ቤት ያሉትም ሲኖዶስ ነን ይላሉና የትኛው ነው ትክክለኛና እግዚአብሔር የሚቀበለው? ፣ ፓትርያርኩና ጳጳሳቱ መሰደድ ነበረባቸው ወይ? ስደታቸው ከወንጌልና ከሕገ ቤተክርስቲያን አኳያ ትክክልና የሚገባ ነው ወይ? ለሚሉ ጥያቄዎች ከተፈጠሩ ነባራዊ ሁኔታዎች አኳያ ወንጌልንና ሕገ ቤተክርስቲያን እየጠቀስኩ ትክክል መሆኑን ከዚህ ቀደም በሚገባ መልስ ሰጥቸበታለሁና አሁን ወደዚያው አልመለስም፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በስደት አሜሪካን ሀገር ያለው ነው፡፡ እዚህ ያሉት በእሱ ስር ሆነው በቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ (እያገለገሉ ከሆነ) አሜሪካ ያለው ሲኖዶስ አካል ናቸው እንጅ በራሳቸው ሲኖዶስ አይደሉም፡፡
ሰሞኑን ይህ በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ 6 ጳጳሳትን ከመሾሙ ጋር ተያይዞ ከያቅጣጫው ተቃውሞዎች ሲነሡ ነበር፡፡ እጅግ የገረመኝ ነገር ብዙዎቹ የዚህ የሲኖዶሱ ሹመት ተቺ ተቃዋሚዎች እዚህ ሀገር ቤት ያለአግባብና ያለ ቀኖና ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ነን ያሉት በወያኔ ታንቆ የተያዘው የጳጳሳት ቡድን የተጣለበትን ኃላፊነትና አደራ ባለመወጣት ቤተክርስቲያንን ለወያኔ ሸጦ የወያኔ መጫዎቻ መቀለጃ ሲያደርጋት፣ ዳግም ልታገኛው የማትችላቸውን በርካታ ጥቅሞቿን እንድታጣ ስትደረግ፣ መንጋዋ በገፍ ተበልቶባት ባዶዋን ስትቀር፣ ሥርዓቷ ቀኖናዋ ሕግጋቷ አልፎም ዶግማዋ ሲጣስ ሲሻር ሲፈርስባት በዝምታ ከመመልከት ውጭ ምንም ማድረግ ያልቻለ መሆኑን እያየ ትንፍሽ ብሎ የማያውቀው ሁሉ እየተነሣ በንዴት ጦፎ የማይገባ የነገር ዱላውን እየመዘዘ ምንም ባልገባው ጉዳይ ላይ የጳጳሳቱን ሹመት ሲቃወምና ሲያወግዝ ሳይ እጅግ ነው የገረመኝ፡፡ ብዙዎቹን ከሁኔታቸው እንደታዘብኳቸው ከወያኔ ቅጥረኝነታቸው የተነሣ ነው ያሉትን ሁሉ ሲሉ የነበረው፡፡ ስለሚናገሩት ነገር ሳያውቁ አግባብነት የሌለው ልፍለፋ ለመለፍለፍ አደባባይ ሲወጡ ሰው ይታዘበናል አለማለታቸው ግን በእጅጉ ገርሞኛል፡፡

እነኝህ ግለሰቦች ከጠቃቀሷቸው የተቃውሞ ምክንያቶቻቸው ዋናዎቹም፡-
1. ሹመቱ ተገቢ አይደለም
2. መናፍቅ ተሹሟል
3. ካንድ መንደርና ቤተሰብ ብቻ የተውጣጡ ናቸው፡፡ የሚሉ ናቸው፡፡ እነኝህ ተቃውሞ ትችቶች ስላላቸው ተጨባጭነት እያንዳንዳቸውን እንመልከት፡-
ሹመቱ ተገቢ አይደለም፡- ይሄንን የሚሉ ሰዎች ለዚህ ተቃውሞ ምክንያት ሲጠየቁ የሚመልሱት “በቤተክርስቲያን ላይ ያለውን መከፈል ዘላቂ እንዲሆን ያደርገዋልና እርቅ ነው እንጅ መፈጠር ያለበት ክፍፍሉን ቋሚ ሊያደርግ የሚችል ተግባር አይደለም” የሚል ነው፡፡ ይሁንና እነኝህ ወገኖች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግን አጢነው መረዳት ያለባቸውን ነገር መረዳት አልቻሉም፡፡ ዝምብሎ በምኞት የሚሆን ነገር የለም፡፡ ይሄንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ? ተብሎ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡
ምክንያቱም እዚህ ሀገር ቤት ያሉቱ ሊቃነ ጳጳሳት ይሄንን የእርቅ ሒደት ለመፈጸም በሚደክሙበት ጊዜ በወያኔ ከጥተኛ ጣልቃ ገብነት እርቁ እንዲቋረጥ በመደረጉና አሁን ደግሞ ወደፊት እንዳያስኬዱት በወያኔ ስለተከለከሉ ስለታገዱና “ይሄንን እርቅ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ቄሶችን እንሰቅላለን!” የሚል ከባድ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ከወያኔ ባለሥልጣናት ዘንድ ስለተሰነዘረባቸው እነኝህ ጳጳሳት ድፍረት አግኝተው እውነትንና ቀኖና ቤተክርስቲያንን መሠረት ባደረገና በጠበቀ መልኩ እርቁ እንዲፈጸም ማድረግ የሚችሉበትን ዕድል ባላገኙበት ቁርጠኝነቱም በታጣበት ሁኔታና ወያኔ እስካለ ጊዜ ድረስም ይህ ጉዳይ ሊፈጸም የማይችል በሆነበት ሁኔታ የሚፈለገው እርቅ እንዲፈጸም መጠየቅ ነባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያላስገባ ባዶ የየዋሀን ምኞት ከመሆን የሚዘል አይሆንም፡፡

“ሲኖዶስ ወያኔ እስኪወድቅ ድረስ ዝም ብሎ ይጠብቅ” እንዳይባልም የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚጎዳ ሆነ፡፡ ቤተክርስቲያን አገልግሎቷን ለማስፋት፣ ለማጠናከር፣ ለማሟላትና ለማሳለጥ የኤጲስ ቆጶሳቱና የጳጳሳቱ ሹመት የግድ አስፈላጊ ሆነ፡፡ በመሆኑም ሹመቱ መፈጸም ነበረበትና ሊፈጸም ቻለ፡፡ ስለዚህም ይሄንን ነጥብ በማንሣት በዚህ ጉዳይ ላይ የተነሣው ተቃውሞ ብስለት ቅንነትና ሙሉ ግንዛቤ የጎደለው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ሁለተኛው የተቃውሞ ነጥብ “በዚህ ሹመት ላይ መናፍቅ ተሸመዋል” የሚለው ነው፡፡ በእርግጥ ግን መናፍቅ ተካቷል ወይ? ብለን ስንጠይቅ መናፍቅ በተባሉ መነኩሴ ላይ የቀረቡ መረጃዎች በእጅጉ የዕውቀትና የግንዛቤ ማነስ ጎልቶ የሚታይባቸው በተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረቱ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ መናፍቅ በተባሉት በአባ ወልደትንሣኤ ላይ ቀረቡ የተባሉትን ክሶች እንይ፡-

አባ ወልደ ትንሣኤ አሳማ ይበላል ብለው ይሰብካሉ፣ በኦርጋን ያስጨፍራሉ፣ ሰንበቴን በቢራና በውስኪ እንዲወጣ ፈቅደዋል የሚሉ ናቸው፡፡ እስኪ እያንዳንዳቸውን ክሶች ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር እንያቸው፡-

በእርግጥ ግን አሳማ ይበላል? ይሄንንስ አባ ወልደትንሣኤ ብለዋል ወይ? ከተባለ አባ ወልደትንሣኤ አሳማን ብቻ ሳይሆን አይጡንም ጉርጡንም እባቡንም ፈረሱንም ውሻውንም ሁሉንም ነገር ይበላል እንደሚሉ እገምታለሁ፡፡ ይሄንን በማለታቸው ግን መናፍቅ የሚሏቸው ሰዎች ካሉ በአብነት ትምህርትቤቶች በመጽሐፍ ቤትና በቅኔ ቤት የሚሰጠውን የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ጨርሶ የማያውቁ እንደሆኑ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሄ ማለት ግን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እነኝህን እርኩስ ነገሮች እንዲበሉ ትሰብካለች ታበረታታለች ማለት አይደለም፡፡ የመልእክታተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት ስታስተምር ይሄንን ትምህርት የግድ ማስተማር ስላለባት እንጅ፡፡

ከገማልያል ስር የተማረው ሳውል (ጳውሎስ) እነኝህ እንስሳት በእግዚአብሔር ትዕዛዝ እርኩስና የማይበሉ መሆናቸውን እያወቀ ዘሌ. 11፤1-47 ዘዳ. 14፤4-21 እንዴት “በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና” 1ኛ. ቆሮ. 10፤25 በማለት ያስተምራል? ከተባለ “…እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። እኔ ደግሞ ብዙዎቹ ይድኑ ዘንድ ለጥቅማቸው እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ እንደማሰኝ፥ ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ” 1ኛ. ቆሮ. 10፤31-33 በማለት ይሄንን የሚያደርገው ክርስትና የሚሰበክላቸው አሕዛብ፣ አረማውያንና ኢአማንያን የለመዱትንና የሚወዱትን ነገር ሲከለከሉ ወንጌልን ከመቀበል ወደ ኋላ እንዳይሉ፣ ሁሉም እንዲድን ካለው ጉጉትና ስስት የተነሣ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ልብ በሉ ይህ የተደረገው ትምህርቱና ባሕሉ ስለሌላቸው፤ እንግዶች ስለሆኑት ስለ አሕዛብ አረማዊያንና ኢአማንያን ሲባል ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ሁሉም በክርስቶስ አምኖ ይድን ዘንድ ከመሻቱ የተነሣ “በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና” ሲል ግን “አትብሏቸው ያረክሳሉ” ብሎ የከለከለው እሱ እራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ዘሌ. 11፤1-47 ዘዳ. 14፤4-21 አውቆ ዘንግቷል፡፡ ምን ያድርግ? ቢቸግረው ነው፡፡ ነገር ግን “የጌታ ነውና” በሚለውማ ከሔድን ሰይጣንስ ቢሆን የሱ አይደል? ሌላ ፈጣሪ የለ!
እንግዲህ ጳውሎስን ከሐዋርያቱ ሁሉ ለየት የሚያደርገውም ይሄ ድፍረት የተሞላበት አኪያሔዱ ነው፡፡ በዚህ አኪያሔዱ የተነሣ ከሐዋርያት ጋር እስከመጣላት የደረሰበት ወቅትም ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ቅዱስ ጳውሎስ ይጠቅማሉ ይበጃሉ ከሚል ቀና አስተሳሰብ አንዳንድ ወጣ ያሉና የተለዩ ትምህርቶችን ሰጥቶ ሲያበቃ ግን “…እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም!” 1ኛ ቆሮ. 7፤12 “…የጌታ ትእዛዝ የለኝም፥ ነገር ግን የታመንሁ እሆን ዘንድ ከጌታ ምሕረትን የተቀበልሁ እንደ መሆኔ ምክር እመክራለሁ፡፡ እንግዲህ ስለ አሁኑ ችግር ይህ መልካም ይመስለኛል፤ ሰው እንዲህ ሆኖ ቢኖር መልካም ነው” 1ኛ ቆሮ. 7፤25 በማለት መደናገር እንዳይፈጠር ያስጠነቅቃል፡፡ ይሄንን ሲያደርግ በጎ አስቦ ነውና በእግዚአብሔር ዘንድ በደል እንደማይሆንበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

ይሄ ድርጊቱ የሚያሳየን ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር ምንድን ነው? ለካህናት የተሰጣቸው ሥልጣን ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡“እውነት እላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል” ማቴ. 18፤18 ይላልና፡፡ ኃጢአት ስለሠራ ኃጢአተኛ የሆነንና እንደ የእግዚአብሔር ቃልም ለኩነኔ ሊዳረግ የነበረ ሰው ካህኑ ስለፈታው ብቻ በሰማይም የተፈታ ወይም የጸደቀ ይሆናል፡፡ ይሄንን ያህል ነው ሥልጣናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የተጠቀመው ይሄንን ሥልጣን ነው፡፡

አባ ወልደትንሣኤ የአሁኑ አቡነ በርናባስ የሐዋርያው ጳውሎስን መንገድ የተከተሉ እየመሰላቸው የሚያደርጉትን ነገር እንደሚያደርጉ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መረዳት ይቻላል፡፡ ያልተረዱት ነገር ቢኖር ቅዱስ ጳውሎስ ያንን ያደረገው ጥቅም ቀርቶባቸው፣ ቁስልን ተሰቅቀው ወንጌልን ከመቀበል በክርስቶስ ከማመን ወደ ኋላ እንዳይሉ ባሕሉ ላልነበራቸው፣ አስተምህሮው ለሌላቸው ለአሕዛብ ለአረማዊያንና ለኢአማንያን እንጅ ይሄንን በማስተማሩ ለተቃወሙት አስተምህሮው ባሕሉ ለነበራቸው አይሁዶች ወይም ኦሪትን ለተቀበሉ አለመሆኑን ነው፡፡ ሁሉቱ ሰፊ መሠረታዊ ልዩነቶች አሏቸው፡፡

በየትኛውም መንገድ፣ ባሕል፣ አስተሳሰብና አስተምህሮ ቢሆን በኩርና ተከታይ፣ ብዙ የደከመ ባለመቶና በመጠኑ የደከመ ባለ ሠላሳ ወይም ምንም የሌለው እኩል ሊታዩ ሊመዘኑ ሊገመቱ የሚችሉበት አግባብና አሠራር የለም፡፡ አባ ወልደትንሣኤ ወይም አቡነ በርናባስ የሳቱት ይሄንን ነው፡፡

አባ ወልደትንሣኤ የቅዱስ ጳውሎስን አስተምህሮ ለነማን መስበክ እንዳለባቸው አላወቁም፡፡ ለነማን? መቸ? ለምንና እንዴት? ሳይሉ ዝም ብለው እንደወረደ ነው እያስተማሩት ያለው፡፡ ይሄ ደግሞ ስሕተት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳንስ አማኙ አረማዊውና አሕዛቡ እንኳ አሳማውን ፈረሱን፣ አይጡን ጉርጡን፣ እባቡን ውሻውን የመብላት ባሕል የለውም፡፡ ይሄ ባሕል ለሌለውና ለሚጸየፈው ብሉ ብሎ ማስተማር ቅዱስ ጳውሎስ ጌታ የሞተለትን ከማሰናክል በማለት“…ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም” 1ኛ ቆሮ. 8፤13 በማለት እጅግ የተጠነቀቀለትን ምስጢር አለማወቅ ነው፡፡ አባ ወልደትንሣኤ በዚህ አስተምህሯቸው ምክንያት ለተሰናከሉባቸው ነፍሳት የሚጠየቁ መሆናቸውን የማያውቁ ከሆነ ምንም የገባቸው ነገር የለም፡፡

ወደ ተከታዩ ክሳቸው ስንሔድ “በኦርጋን ያስጨፍራሉ” የሚለው ነው፡፡ አዎ በእርግጥ እሳቸው ይሄንን ያደርጋሉ፡፡ ይሄንን የሚያደርጉት ደግሞ “እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን!” የሚለውን ቃል አሳስተው ተርጉመው በመረዳታቸው ነው፡፡ “እስትንፋስ ያለው ሁሉ” ማለት ድምፅ የሚሰጥ ነገር ሁሉ ማለት መስሏቸዋል፡፡ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ማለት ሕይዎት ያለው ነገር ሁሉ ማለት እንጅ ሲመታ ድምፅ የሚሰጥ ግኡዝ ነገር ሁሉ ማለት አይደለም፡፡ እሳቸው ያልተባለውን በተሳሳተ አረዳድ እንደተባለ ቆጥረው ሥጋዊ የዘፈን ፈቃድንና ስሜትን ለማርካት የዘፈን መሣሪያዎችን ሁሉ እያንጫጩ ለመጠቀም መሞከር በእውነት እግዚአብሔርን አለመፍራትና አለማፈር ነው፡፡

ይሁንና አባ ወልደትንሳኤ ይሄንን በማድረጋቸው የምእራቡ ዓለም የዜማ ባሕል ምርኮኛ ወይም ዳንኪረኛ ናቸው ሊያሰኛቸው ቢችል እንጅ መናፍቅ ሊያሰኛቸው አይገባም፡፡ ምክንያቱም የአኃት (እኅቶች) አብያተክርስቲያናት የመዝሙር መሣሪያም ይሄው ነውና፡፡ ኦርጋን የአኃት አብያተክርስቲያናት የመዝሙር መሣሪያ ነው ስል ግን እኛም ኦርጋንን በመዝሙር መሣሪያነት እንቀበለው እንጠቀምበት እያልኩ አይደለም፡፡ መሆንም የለበትም፡፡ ከአኃት (ከግብጽ፣ ከአርመን፣ ከሶሪያ፣ ከህንድ) አብያተክርስቲያናት ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ በሥርዓትና ቀኖና ጉዳዮች ላይም እንኳ ሰፊ ልዩነቶች እንዳሉን መገንዘብ ይገባል፡፡

እነሱ የሐዲስ ኪዳን ልጆች እንደመሆናቸውና በኦሪቱ ዘመን እግዚአብሔርን አለማወቃቸው በኦሪት ሥርዓት እግዚአብሔርን አለማምለካቸው ለልዩነቱ መፈጠር ዐቢይ ምክንያት ነው፡፡ በመሆኑም አኃት አብያተክርስቲያናት እኛ በብሉይ ኪዳንም እግዚአብሔርን አምላኪዎች በመሆናችን ያሉን ጠቃሚና አስፈላጊ አገልግሎቶች፣ ሥርዓትና ሃይማኖታዊ ባሕሎች እነሱ የሏቸውም፡፡ ጉዳዩ እንዲያውም ከዚህም አልፎ እኛ ነባር እግዚአብሔርን አማኝ አምላኪ እነሱ አዲስ እንግዶች ከመሆናቸው የተነሣ ዶግማዊ ሊባል የሚችል ልዩነት የሚታይበት ሁኔታም አለ፡፡ ለምሳሌ እኛ ጽላትና ታቦት አለን፡፡ የጽላትና የታቦት አገልግሎት ለእኛ ቤተክርስቲያን ሊቀር ሊለወጥ ሊሻሻል የማይችል ዶግማ (አምደ እምነት) ነው፡፡ እነሱ ግን በስውራን ቅዱሳኖቻቸው ዘንድ ካልሆነ በስተቀር ጽላትና ታቦት የላቸውም፡፡

ከዚህም የተነሣ “ከስሩ ከመሠረቱ እንዴት ነው?” የሚያሰኝ ሥርዓት ወይም ጥያቄ በሚያስነሡ ጉዳዮች ላይ ያላቸውና የሚከተሉት ሥርዓት አስተምህሮና ሃይማኖታዊ ባሕል እንደመሰላቸው በዘፈቀደ የሚደረግ ከመሆኑ የተነሣ ብዙ ጊዜ የተሳሳተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህም ምክንያት “እነሱ ዘንድ እንዲህ ይደረጋልና እኛም ዘንድ እንዲህ ብናደርግ ችግር የለውም! ወይም ማድረግ ይኖርብናል!” ልንል የምንችልበት አግባብ አይኖርም፡፡ እነ አባ ወልደትንሣኤ ይሄንን ቁምነገር ነው የሳቱት፡፡
እናም የዚህ ኦርጋን የተባለው የዜማ መሣሪያ ጉዳይ እንዲያ ነው፡፡ በኦርጋን ዙሪያ ስላለው ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ባሕልና አስተምህሮ አንጻር ያለውን አጠቃላይ ጉዳይ “እውን ኦርጋን የመዝሙር መሣሪያ ነውን?” በሚል ርእስ ከጻፍኩት ጽሑፍ መረዳት ይቻላልና ይሄንን ይዝ (ሊንክ) ተጭነው ይረዱ፡፡

እውን ኦርጋን የመዝሙር መሣሪያ ነውን? – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሌላኛው ክስ ደግሞ “አባ ወልደትንሣኤ ሰንበቴን በቢራና በውስኪ እንዲወጣ ፈቅደዋል” የሚለው ነው፡፡ እንደ ይሄንን ክስ ያቀረቡ ምእመናን ግንዛቤ ሰንበቴም ሆነ ማኅበር የሚወጣው በጠላና በእንጀራ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ባለ መጠጥና ምግብ እንዳይደረግ በሕግ የተደነገገ ይመስላቸዋል፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ሕግና ድንጋጌ የሌለውና በተገኘው ነገር ሊፈጸም የሚችለው ብዙው ነገር ሁሉ እነሱ ከሚያውቁት በተለየ መንገድ ሲደረግ ሲያዩ ያ ለእነሱ ኑፋቄ ወይም ክህደት ነው፡፡
እንግዲህ እነዚህን ወገኖች ለዚህ የተሳሳተ ድምዳሜና ፍረጃ የሚዳርጋቸው አለማወቃቸው ነውና ተቆርቋሪነታቸውን ልናደንቅ የሚገባ ቢሆንም ይሄንን ተቆርቋሪነት ከቤተክርስቲያናችን ቀኖና ሥርዓት ሕግና ድንጋጌ አኳያ እያዩ እንዲያደርጉት እየመከርኩ ስሕተታቸውን በክፋት ሳንመለከት ማለፍ ይኖርብናል፡፡ ነገር ግን እንዲህ በቀላል በተሳሳተ ግንዛቤ የሰው ስም መጥፋቱና መሰበሩ ለእነሱም ቢሆን ዕዳ በደል ነውና የሚሆንባቸው በዚህ ስሕተታቸው ሊሰማቸውና ሊጠነቀቁም ይገባል፡፡ ንስሐም መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡

እና እንግዲህ አባ ወ/ትንሣኤን በመናፍቅነት ያስከሰሷቸውና የማውቃቸው እነኝህና ክሶቹም ተገቢ ያልሆኑ ናቸው፡፡ አባ ወ/ትንሣኤ ሌላ ዶግማን በተመለከተ ኑፋቄ እንዳለባቸው ወይም እንዲህ ብለው የተሳሳተና ኑፋቄ ሲያስተምሩ ሰምቻለሁ የሚል ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ እናም አባ ወልደትንሳኤ ከላይ የጠቀስኳቸው ሊያስተካክሏቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ሥልጣኑ ይገባቸዋል ስም ማጥፋቱ ተገቢ አይደለም እላለሁ፡፡
የኑፋቄ ጉዳይ ከተነሣ ግን አሁን ላይ በጵጵስና እንዳሉና እራሴን ምስክር አድርጌ በልጅነቴ ያየሁትንና የሰማሁትን በመጥቀስ በመናፍቅነት የከሰስኳቸው አቡነ ዮሐንስ ጉዳይ ቢጣራ መልካም ነው፡፡ ከኑፋቄያቸው ተመልሰው ከሆነ ለጵጵስና የበቁት እሰየው ነው፡፡ በእርግጥ አንድ ያጠፋ የተሳሳተ ሰው ንስሐ ገብቶ ሊመለስ የሚችልበት ሁኔታ ስላለ ያን ስሕተቱን አሁንም እየፈጸመ መሆኑ ካልታወቀና ካልታየ በስተቀር ቀድሞ በፈጸመው ስሕተት አሁንም መውቀስ መክሰስ ስሕተት ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ነው እንዲጣራ መጠየቄ፡፡

እንዲያው ልዑል እግዚአብሔር የማይመከሩ የማይገሰጹ የማይመለሱ እንደሆን እኒያን ሽማግሌ የዓለም ስማቸውን ባውቀው በዚያው ብጠራቸው ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር አቡነ መልከጸዴቅ የሚባሉትን ማለቴ ነው በቶሎ ንቅል አድርጎ ይውሰድልን እንጅ እሳቸው የሚሠሩት ሥራ ቤተክርስቲያንን እጅግ እያወከ ነው፡፡

ወደ ሦስተኛው ነጥብ ማለትም “ካንድ መንደርና ቤተሰብ ብቻ የተውጣጡ ናቸው” ወደሚለው ስናልፍ፡- መቸም ነገሮችን ማጋነንና ፈጥሮ ማውራት የሐሰተኛ ሰው ልማድ ነውና ልማድ ሆኖባቸው ካንድ ቤተሰብና መንደር የወጡ አደረጓቸው እንጅ እነሱስ አይደሉም፡፡ ከአንድ ክፍለ ሀገር ናቸው ቢሉ ግን ትክክል ናቸው፡፡ እሱም ቢሆን እንዲህ ሊሆን የቻለው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ጎንደሬ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ወገንተኝነት እየተሰማቸው ከእሳቸው ጋር ማበር መሰለፍ በወያኔ ዘንድ በጠላትነት ማስፈረጁን ሳይፈሩና ሳያፍሩ እየተቀላቀሏቸው ያሉት ካህናት ጎንደሬዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ሌሎቹ ወያኔን እየፈሩ የማይቀላቀሏቸው ሆነ እንዴት ይደረግ ታዲያ?

ምናልባት ግን ሲኖዶሱ የወያኔ ቅጥረኛ ያልሆነ፣ አሳልፎ የማይሰጣቸውንና የሚታመንን ሰው ሲፈልጉ የግድ የሚያውቁትንና የሚቀርቡትን ሰው ለመሾም ተገደው ከሆነና በዚህም ምክንያት የአንድ አካባቢ ሰዎችን የሚሰበስቡ ዘረኞች መስለው ታይተው ከሆነ ለዚህ ችግር ተጠያቂው የዘረኝነትን ከል ቤተክርስቲያን ላይ የጫነባት የመረዛት ወያኔ እንጅ ሲኖዶስ ሊሆን አይችልምና በዚህ ጉዳይ ላይ ሲኖዶስን እየከሰሳቹህ ያላቹህት ወገኖች ልብ ግዙ እላለሁ፡፡

ልዑል እግዚአብሔር የቤተክርስቲያንን ጋኔን ወያኔን አጥፍቶ፣ የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና ደኅንነት መልሶ፣ ቤተክርስቲያን ወያኔ ካመጣባት ደዌ ተፈውሳ ለማየት ያብቃን አሜን!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

↧

አበበ ባልቻ ጫማ ሰፊ ሆኖ ሊመጣ ነው

$
0
0

Blacha

(ዘ-ሐበሻ) አርቲስት አበበ ባልቻን ጨምሮ በርካታ የአገራችን ታዋቂ አርቲስቶች የሚተውኑበት ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማ ቀጣይ ክፍል ወደ30 ኤፒሶድ ተቀርፆ ተጠናቋል፡፡

 

በሰው ለሰው ድራማ ላይ የነበሩ ተዋናዮች በሙሉ የሚሰሩበት ይህ የቴሌቪዥን ድራማ ርዕሱ ‹‹ፊትና ኋላ›› የሚል ነው፡፡ ድራማውን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን(ኢቢሲ) ዘወትር ሰኞና ዕሮብ(በሳምንት ሁለት ቀን) ለማስተላለፍ ስምምነት ተደርሶ የነበረ ቢሆንም ባለቀ ሰዓት ኢቢሲ ሀሳቡን መቀየሩን ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ በመሆኑም የድራማው ፕሮዲውሰሮች ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር እየተደራደሩ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡

በ‹‹ፊትና ኋላ››ድራማ አርቲስት አበበ ባልቻ አዲስ ገፀ ባህርይ ተላብሶ ይጫወታል፡፡ አዲሱ ገፀ ባህርይው ደግሞ የጫማ ሰፊ ገጸ ባህርይ መሆኑን ከድራማው ስክሪፕት ለመረዳት ችለናል፡፡ አርቲስት አበበ ከተዋናይነትም በተጨማሪ የድራማውን ወጪ በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከፕሮዲውሰሮቹ አንዱ ነው፡፡

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images