Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ተሳታፊ አትሌቶች ምርጫና ውዝግቡ -VOA

$
0
0

F739E9C5-B01C-4303-A9A1-94F811BCD376_cx0_cy7_cw0_w987_r1_s_r1ብራዚል ውስጥ የሚካሄደው የዘንድሮው “ሪዮ ኦሎምፒክ 2016” ሊደረግ ሃምሳ ሰባት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እንደ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አገላለጽ ይህ ጊዜ ለአትሌቶች የመጀመሪያ ልምምድ ጊዜያቸውን አጠናቀው ለሁለተኛ ልምምድ የሚዘጋጁበት ነበር። በኢትዮጵያ ግን በአትሌቶችና በትሌቲክስ ፌደሬሽን መካከል በአትሌቶች ምርጫ በተፈጠረ አለመግባባት ውዝግብ ላይ ናቸው። ጽዮን ግርማ ዘገባ አላት።

ብራዚል ውስጥ የሚካሄደው የዘንድሮው “ሪዮ ኦሎምፒክ 2016” ሊደረግ ሃምሳ ሰባት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እንደ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አገላለጽ ይህ ጊዜ ለአትሌቶች የመጀመሪያ ልምምድ ጊዜያቸውን አጠናቀው ለሁለተኛ ልምምድ የሚዘጋጁበት ነበር። በኢትዮጵያ ግን በአትሌቶችና በትሌቲክስ ፌደሬሽን መካከል በአትሌቶች ምርጫ በተፈጠረ አለመግባባት ውዝግብ ላይ ናቸው።

ለውዝግቡ መነሻ ደግሞ ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ለምርጫ የሚያበቃውን መስፈርት ከአንድ ዓመት በፊት ማሳወቅ ሲገባው፤ አትሌቶቹ በቀደመው መስፈርት ዝግጅት ካደረጉና ለምርጫ ራሳቸውን ካዘጋጁ በኋላ ከምርጫው ውጤት እኩል አስታውቋል የሚል ነው። በተጨማሪም መስፈርቱም ከዚህ በፊት ያልነበረና ውጤት ለማምጣት ዋስትና የማይሰጥ ነው፣ እንዲሁም በአስር ቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ምርጫ መካሄዱን በመግልፅ በአጠቃላይ ምርጫውን ያካሄደው ኮሚቴ ብቃት የሌለውና በፌደሬሽን ውስጥ ያሉት አመራሮች የብቃት ማነስ ችግር አለባቸው የሚለው የበርካታ አትሌቶች ቅሬታ ነው።

አትሌት መሰለች መልካሙ

አትሌት መሰለች መልካሙ

ቅሬታ ካደረባቸው አትሌቶች መካከል አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት መሰለች መልካሙ ተጠቃሽ ናቸው። አትሌቶቹ 12 አባላት ያሉት አንጋፋ አትሌቶችን ስብስብ መርጦ ኮሚቴ አቋቁሟል። የዚህ ኮሚቴ

ሰብሳቢ ኃይሌ ገብረስላሴ ነው።

አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

ባልደረባችን ጽዮን ግርማ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴን፣አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት መሰለች መልካሙን ፣የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ ስለሺ ብስራትና እንዲሁም ታደለ አሰፋና ሰኢድ ኪያር የተባሉ ጉዳዩን በስፋት ሲከታተሉ የቆዩ ሁለት የስፖርት ጋዜጠኞችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።


በጾረና፣ ባድመና ዛላንበሳ ግምባር የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ተፋጠዋል |የቦምብ ፍንዳታ ተሰምቷል

$
0
0

ethio-ertria

(ዘ-ሐበሻ) በጾረና ግምባር በኩል የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች በብዛት እየሰፈሩ መሆኑ ተሰማ:: ከትናንት በስቲያ ምሽት ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው የሁለቱ ሃገራት ግጭት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ የተደረገበትና አብዛኛውም ጊዜ በስለላ ላይ ያተኮረ ግጭት እንደነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

ሞርታር እና አርፒጂን የተሰኙ በጦርነት ላይ በጣም ከባድ የማይባሉ መሳሪያዎች በዚህ የሁለቱ ሃገራት ግጭት ላይ በጥቅም ላይ እንደዋለ የደረሰን መረጃ ሲያስረዳ ዓዲ መስገነን; አሃራንንና ቁኒቁንቶን በተሰኙ ቦታዎች ከትናንት ጀምሮ የተኩስ ልውውጥና ግጭቱ እንደተካረረ ምንጮች ገልጸዋል::

ወታደራዊ ምንጮች እንደሚሉት ሁለቱም ሃገራት በአሁኑ ወቅት ጦራቸውን ወደ ድንበሮቹ አስጠግጠዋል:: ማምሻውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስተር ባወጣው ባለ 6 መስመር አጭር መግለጫው የሕወሓት መንግስት በጾረና በኩል ወረራና ጥቃት ፈጽሞብኛል ሲል ከሷል::

ከትግራይ ክልል ካሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች መረዳት እንደተቻለው በኢትዮጵያና በኤርትራ ወታደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ የተሰማው በጾረና በኩል ብቻ ሳይሆን በባድመ እና በዛላንበሳ ግንባሮችም ጭምር ነው:: በተለይም በባድመና በዛላምበሳ የቦምብ ድምጾች ሁሉ ይሰሙ እንደነበር ምንጮቹ አስረድተውናል::

ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት በጾረና በኩል ወረረኝ ስትል ብትከስም በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስትም ቢሆን በአንጻሩ የኤርትራ መንግስት በተለያዩ ድንበሮች በኩል እየተነኮሰኝ ነው ሲል መቆየቱ ይታወሳል::

ትናንት ማምሻውን በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን ሲያጓጉዝ እንደነበር የተመለከቱ የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

ዘ-ሐበሻ ይህን ጉዳይ እየተከታተለች ትዘግባለች | ይመላለሱ

Hiber Radio: ኤርትራ ሕወሓት አስቀድሞ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገች –አሜሪካ ኤርትራን አስታርቃለሁ አለች

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሰኔ 5 ቀን 2008 ፕሮግራም

<... ...> አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም መቀመጫውን ቤልጂየም ያደረገው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የሚሰራው ማህበር ዋና ዳይሬክተር የአገዛዙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ያወጣውን ሪፖርትና የፓርላማውን ውሳኔ በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<... ...> አቶ ነጌሳ ኦዶ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማህበር ሊቀመንበር የአገዛዙ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርትና የፓርላማ ውሳኔ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<...> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ ቲኬ ሾው አዘጋጅ በኤይ.አር.ኤስ ስም ስለሚያጭበረብሩ ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያድምጡት)

ሟቹ መለስ ዜናዊ የቀመሩት የተቃዋሚዎች እግሮችን የመቁረጥ እቅድ ከኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ(ኦፊኮ)ቢሮ ዘልቋል።በርካታ የኦሮሞ ታጋዮች በሰበብ ባስባቡ ወደ እስርቤት ሲወረወሩ የፓርቲው መሪው ዶ/ር መረራ ጉዲና ግን እስከ አሁን ድረስ ለምን አልታሰሩም ? ዶ/ር መረራ ለጥያቄው አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተውበታል (ልዩ ጥንቅር)

በፍሎሪዳ በኢሚግሬሽን እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን መካከል ከእስር ቤት ከወጣው ከአንዱ ጋር ያደረግነው አጭር ቆይታ(ያድምጡት)

በቬጋስ የሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎች ኩባንያዎቹ የገቡትን ቃል ለመፈጸም አልቻሉም ራሳችንን በማህበር ማደራጀት አለብን ብለዋል(መልዕክታቸውን ይዘናል)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የኤርትራ መንግስት በጾረና ግንባር የሕወሓት ወታደሮች ጥቃት ሰነዘሩ ሲል የኢትዮጵያው አገዛዝ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገ

የአገዛዙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰሞኑ ሪፖርትና የፓርላማ ውሳኔ በሕግ ፊት ተቀባይነት እንደሌለው ተገለጸ

በኢትዮጵያ አትሌቶች መካከል የመከፋፈል ደመና ማንጃበቡ ተሰማ

“ፌዴሬሽኑ ለብራዚሉ የኦሎምፒክ ውድድር የመረጣቸው አትሌቶች እራሳቸውን ከአነ አትሌት ሃይሌ እና ከእነ ቀነኒሳ እራቁ፣

“አትሌቶቹ ወደዚህ ለምን እንዳልመጡ ጠንቅቀን እናውቃለን”አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ

በአውስትራሊያ ሜልቦርን አቶ አባይ ወልዱ የተገኙበት ስብሰባ በተቃው ተበተነ

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኤርትራ መንግስት ላይ ያወጣው ሰሞነኛ ሪፖርት ምሁራኖችን እያነጋገር ነው

አሜሪካ ኤርትራ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንደትተባበር ጥረት አደርጋለሁ አለች

በኢትዮጵያ ውስጥ 5.5 ሚሊዮን ህጻናት ለጉልበት ብዛበዛ መዳረጋቸው ታወቀ

የተመድ እና ግብጽ በሶማሊያ ስለወደቁት 60 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የኢሕአዲግ መንግስት ግን “የሞተብኝ ሆነ የቆሰለብኝ ወታደር የለም ፣በአልሽባብ ላይም ድልን ተቀዳጅቻለሁ”ይላል

እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

“የኤርትራ ጦር ጥቃት የማድረስ አቅሙ የተዳከመ ነው”–የኢትዮጵያ መንግስት

$
0
0
የኢትዮጵያ ወታደሮች (ፎቶ ከፋይል)

የኢትዮጵያ ወታደሮች (ፎቶ ከፋይል)

(ዘ-ሐበሻ) የኤርትራ መንግስት ትናንት ማምሻውን የኢትዮጵያ መንግስት በጾረና ግምባር በኩል ጥቃት ፈጸመብኝ ያለበትን ዜና ማስነበባችን ይታወሳል:: ይህን ተከትሎ ትናንት ስለጦርነቱ የማውቀው ነገር የለም ሲል የነበረው ጠዋት የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ አውጥቷል::

“የኤርትራ መንግስት እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጠዋት በጾረና ግንባር ጥቃት ለመሰንዘር በመሞከሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአጸፋ እርምጃ ወስደናል” ያለው የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስተር መግለጫ “የኢትዮጵያ ሰራዊት በወሰደው በዚህ ተመጣጣኝ ዕርምጃም የኤርትራ ጦር ጥቃት የማድረስ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል” ብሏል::

ወደ ጾረና ግንባር የተንቀሳቀሰውን የኤርትራ ጦር ሙሉ በሙሉ ደምስሻለሁ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ

መግለጫው የኤርትራ መንግስት በራሱ ህዝብ ላይ የሚያካሂደው አስከፊ ጭቆናና የመብት ጥሰት፥ በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል የኤርትራ መንግስት ይህን ትንኮሳ የፈጸመው በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር የሚደርስበትን ጫና ለማስቀየስ ነው ብሏል::

ኤርትራ ካሁን በኋላ ጥቃት ማድረሷን ብትቀጥል የኢትዮጵያ ሰራዊትም የመልስ ምት እንደሚሰጥና የመከላከያ ሰራዊቱ የሚወስደው እርምጃም እንደ ኤርትራ መንግስት ባህሪ ይታያል ብሏል:: ይህም ማለት ኤርትራ ጥቃት ከፈጸመች እርምጃ እንወስዳለን እንደማለት ነው::

እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ ከሆነ በድንበር አካባቢ አሁንም ውጥረቱ እንዳየለ ነው:: መንግስት ለምን ከኤርትራ መንግስት ቀድሞ ለሕዝቡ መግለጫ አለመስጠቱም አነጋጋሪ እንደሆነ ነው::

አ. ግንቦት 7 መግለጫ አወጣ “ወያኔ ከገባበት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም”

$
0
0

በጥጋብና እብሪት የተወጠረው የህወሃት አገዛዝ በትናንትናው ዕለት ዕሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በኩል ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ቦታዎች ላይ ጦርነት ጀምራል፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ዜና አረጋግጠው ዘግበዋል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በወያኔ በኩል ስለጦርነቱ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም የኤርትራ መንግሥት በጾረና ግንባር በኩል ጥቃት እንደተፈጸመበት ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገ መግለጫ አረጋግጦአል።

ethio-ertria

የህወሃት ዘረኝነት በፈጠረው ኢፍትሃዊነትና አፈና የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞውን እያጠናከረ ባለበት በዚህን ሰዓት በሙስና የተጨማለቁ የህወሃት የጦር ጀነራሎችና በሲቪል ማዕረግ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሃይሎች ለምን ይህንን ጦርነት መጫር እንደፈለጉ ግልጽ ነው። በኦሮሚያ የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማፈን ከ400 በላይ ሕዝብ መጨፍጨፉና በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት መታጎራቸው የህወሃትን ዕድሜ ለማራዘም እንደ አንድ መሣሪያ ሆኖ ላለፉት 25 አመታት ሲያገለግል በኖረው ኦህዲድ ውስጥ እንኳን ከከፍተኛ አመራር እስከ ተራ ካድሬ ያሉትን አስኮርፎአል። የወልቃይት ህዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ ሌላኛው የህወሃት አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥ የማያባራ ክፍፍል ፈጥሮአል። የነጻነት ታጋዮች በቅርቡ አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ የፈጸሙት የጀግንነት ገድል የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያንቃቃና ለትግል የሚያነሳሳ አርአያነት እንደፈጠረ የህወሃት አገዛዝ ተረድቶአል። በቤኔሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአፋርና በሱማሌ ከመሬት ንጥቂያ ጋር በተያያዘ ወንጀል ህወሃት ከህዝቡ ጋር አይጥና ድመት ድብብቆሽ ውስጥ ከገባ አመታትን አስቆጥሮአል። በአዲስ አበባና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ቀድሞውኑም የድጋፍ መሠረት እንደሌለው ማወቁ ብቻ ሳይሆን ይኩራራበት የነበረው የትግራይ ምሽግነትም ከእጁ ሙሉ በሙሉ እያፈተለከ መምጣቱን ተገንዝቧል። በዚህም ምክንያት ፊቱን ወደሰሜን በማዞር የሕዝቡን ትኩረት አስታለሁ ብሎ ወያኔ አምኖአል። አባይ ጸሃይዬና ሳሞራ ዩኑስ መቀሌ ላይ በቅርቡ ባደረጉት የህወሃት ስብሰባ ላይ “ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ አይኖርም፤ ኢህአደግ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም” ማለታቸው ኤርትራን በመውረር በተለይም የትግራይን ህዝብ ድጋፍ መልሶ ያስገኛል የሚል እምነት በአገዛዙ መሪዎች ውስጥ መፈጠሩን ያመለክታል።

ሌላው ህወሃትን ወደ ጦር አጫሪነት እየነዳው ያለው እብደት መለስ ዜናዊ ከሞተ ወዲህ ድርጅቱ ውስጥ የነገሰው የእርስ በርስ የሥልጣን ሹኩቻ የፈጠረው ውጥረት እንደሆነ መገመት አያዳግትም። አንዱን ውጥረት ለማርገብ ሌላ የውጥረት ግንባር በመክፈት ለሚታወቀው ህወሃት ይህ የተለመደ ስትራቴጂ ነው።

አርበኞች ግንቦት7 ህወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ትኩረት ለመቀየር የሚያደርገው ማንኛውም አይነት ጥረት እንዳይሳካለትና የጀመረው ይህ የትኩረት ማስቀየሻ ስትራቴጂ የህወሃትን ውድቀት አፍጣኝ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ካሁን ቀደም ለአገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የሚሰጠው ፋይዳ ሳይመከርበትና ሕዝባዊ ስምምነት ሳይኖር ከአሥራ አንድ አመት በፊት ሱማሌ ውስጥ ዘፍ ተብሎ የተገባበት ጦርነት በየቀኑ የስንት ወንድሞቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ እያየነው ነው። ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን ሰሞኑ በሽብርተኛው አልሸባብ ሲጨፈጨፉ የወያኔ መሪዎች አንዲትም ወፍ የሞተቺባቸው ያህል እንኳ አልተሰማቸውም ። ይህንን ሁሉም ያገራችን ህዝብ ያውቃል። እስከዛሬ በሰላም አስከባሪነት ስም ወደ ሰው አገር እየተላኩ ደመ ከልብ እየሆኑ ያሉ ወገኖቻችን ህይወት እያንገበገበን ባለበት በዚህን ሰዓት ለወያኔ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ እንደ አገር የምንዋጋው ሌላ ጦርነት እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። በ1998ቱ የባድሜ ጦርነት ወቅት ህዝባችን የከፈለው ዋጋና ከባድሜ ጦርነት መልስ ጉልበቱን አጠናክሮ ለመውጣት ዕድል ያገኘው የህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ እስከዛሬ እየፈጸመው ያለው አፈናና ጭፍጨፋ ተረስቶ ሌላ ዕድል ለመስጠት ዳግም መሳሪያ የምንሆንበት ምክንያት የለም።

አርበኞች ግንቦት 7 ከአሁን ቦኋላ ወያኔ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘምና የተዘፈቀበትን የሃብት ዘረፋ አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያደርገውን የሞት ሽረት ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም አይነት ሁኔታ ማስተናገድ የለበትም ብሎ ያምናል። በዚህም ምክንያት በመላው አገራችን የተጀመረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለፍትህ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገው ትግል ከግቡ እንዲደርስ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ትግሉን ለማጠናከር እንዲረባረብ አርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል ። በመካሄድ ላይ ያለውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ ለማስለወጥ ወያኔ የሚያደርገውን የጦርነት እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የነጻነት ቀናችንን እንድናፋጥን ሁላችንም እንነሳ ።

አርበኞች ግንቦት 7 ወያኔ በሰሜን በኩል የጀመረውን ትንኮሳ እየተከታተለ ለህዝባችን ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

አርበኞች ግንቦት 7

ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም የተላለፈ ጥሪ |የሰኔ ሚካኤል ክብረ በዓልና በዓለ ጰራቅሊጦስ (ማስታወቂያ)

$
0
0

ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ ጥሪ | የሰኔ ሚካኤል ክብረ በዓልና በዓለ ጰራቅሊጦስ | የፊታችን እሁድ
4401 Minnehaha Ave Minneapolis, MN
sene michael

ሟቹ መለስ ዜናዊ የቀመሩት የተቃዋሚዎች እግሮችን የመቁረጥ እቅድ ከኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ቢሮ ዘልቋል |ልዩ ጥንቅር

$
0
0

ሟቹ መለስ ዜናዊ የቀመሩት የተቃዋሚዎች እግሮችን የመቁረጥ እቅድ ከኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ (ኦፊኮ)ቢሮ ዘልቋል።በርካታ የኦሮሞ ታጋዮች በሰበብ ባስባቡ ወደ እስርቤት ሲወረወሩ የፓርቲው መሪው ዶ/ር መረራ ጉዲና ግን እስከ አሁን ድረስ ለምን አልታሰሩም ? ዶ/ር መረራ ለጥያቄው አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተውበታል – ያድምጡት ቀጣዩን የታምሩ ገዳ ዘገባ::

ሟቹ መለስ ዜናዊ የቀመሩት የተቃዋሚዎች እግሮችን የመቁረጥ እቅድ ከኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ቢሮ ዘልቋል (ልዩ ጥንቅር)

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በጀርመን የሕወሓት ደጋፊዎች ስላደረሱባቸው ተቃውሞ ተናገሩ –“ደስ ብሎኛል”| Video

$
0
0

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ያደረጉትን ሙሉ ንግግር ማቴዎስ ፈቃደ በቭዲዮ ቀርጾ ለዘ-ሐበሻ ልኮልናል:: ሙሉ ንግግሩን ያድምጡት::


ኢትዮጵያ፤ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደ የሀይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል | HRW

$
0
0

ያለ አግባብ የታሰሩ ይፈቱ፤ በገለልተኛ ወገን ማጣሪያ ይደረግ

ናይሮቢ፤ ሰኔ 9 ቀን 2008 ዓ.ም (HRW) – ከህዳር ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከ400 በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ የሚቆጠሩትን ደግሞ ማሰራቸውን ሂዩማን ራይት ወች ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ እስራቶችንና ሌሎች የመብት ጥሰቶች በአስቸኳይ ተአማኒነት ያለውና ገለልተኛ የሆነ ማጣሪያ እንዲካሄድ ድጋፍ ማድረግ አለበት።

ይህ ባለ 61 ገጽ ሪፖርት “‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ” የተሰኘው ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት ተቃውሞሙን ለመቆጣጠር የተጠቀመውን ከመጠን ያለፈ ሀይል እርምጃና እስከ መግደል የሚያደርስ ሃይል፣ የጅምላ እስር፣ ጭካኔ የተሞላበት የእስር ቤት አያያዝ፣ እንዲሁም የተቃውሞ ሂደቶችን በተመለከተ መረጃዎች ለህዝብ እንዳይሰራጩ ማፈንን አጠቃሎ በዝርዝር አቅርቧል፡፡

ይህን ሪፖርት ለማጠናቀር ሂዩማን ራይትስ ዎች እ.ኤ.አ. ከህዳር ወር 2015ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም. ድረስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንዲሁም ሀሳባቸውን በነጻነት በሚገልጹ ዜጎች ላይ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን፣ ከ125 በላይ የሚሆኑ የተቃውሞ ሰልፎች ተሳታፊዎችን፣ ጉዳዩን በአንክሮ ሲከታተሉ የቆዩ ግለሰቦችን፣ በተለያዩ ጊዜያት የመብት ጥሰት የተካሄደባቸውና ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ያካተተ ቃለ መጠይቅ አድርጓል።

ከህዳር ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከ400 በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ የሚቆጠሩትን ደግሞ ማሰራቸውን ሂዩማን ራይት ወች ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ እስራቶችንና ሌሎች የመብት ጥሰቶች በአስቸኳይ ተአማኒነት ያለውና ገለልተኛ የሆነ ማጣሪያ እንዲካሄድ ድጋፍ ማድረግ አለበት።
“የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በቀጥታ በመተኮስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ ገበሬዎችን እና ሌሎች የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ገድለዋል።” በማለት የሂይውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ተናግረዋል። ሌፍኮው አያይዘውም “መንግስት ያለ አግባብ የታሰሩትን በአስቸኳይ መፍታት አለበት፣ ተአማኒነት ያለው እና ገለልተኛ የማጣራት ሂደት እንዲከናወን ድጋፍ ማድረግ አለበት፣ እንዲሁም ይህን ጥቃት የፈጸሙት የጸጥታ ሀይል አባላት ላደረሱት የመብት ጥሰት ተጠያቂ መሆን አለባቸው፡፡”

ሂዩማን ራይትስ ወች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ለወራት ያህል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄዱ ተቃውሞዎች ሰልፈኞችን ለመቆጣጠር ቀጥታ መተኮሱን እና በእያንዳንዱ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የተቃውሞ ሰልፈኞችን መገደላቸውን አረጋግጧል። ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች ድርጅቶች ከ300 በላይ የተገደሉ ሰዎችን ማንነት በስም ለይቷል እንዲሁም በተወሰኑት ጉዳይ ላይ በፎቶ ለማረጋገጥ ችሏል።

እ.ኤ.አ. የህዳሩ ተቃውሞ የተቀሰቀሰው መንግስት የዋና ከተማውን የማዘጋጃ ቤት ድንበር በአደሲ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን መሰረት ለማስፋፋት ማቀዱን ተከትሎ በተፈጠረ አሳሳቢ ሁኔታ ነው፡፡ ተቃውሞ አድራጊዎቹ ማስተር ፕላኑ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ያፈናቅላል እንዲሁም በአካባቢው የእርሻ መሬት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፤ የሚጠቅመው ጥቂት የበላዮችን ብቻ ነው የሚል ስጋት ያደረባቸው ሲሆን የማፈናቀል ተግባሩ ባለፈው አስር ዓመት እየጨመረ የመጣ ጉዳይ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በታህሳስ ወር ተቃውሞው ሲስፋፋ መንግስት ተቃውሞውን ለማፈን የጦር ሀይሉን በመላው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ አስፍሯል። የጸጥታ ሀይሎች ምንም አይነት ቅድመ ማስጠንቀቅያ ሳይሰጡ ወይም ጉዳት የማያስከትሉ የአድማ መበተኛ መሳሪያ ሳይጠቀሙ ወደ ሰልፈኖች በቀጥታ ተኩሰዋል። በዚህም አይነት ሁኔታ ከተገደሉት ሰልፈኞች መካከል አብዛኞቹ ተማሪዎችና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ እና የጦር ሰራዊት በጋራ በመሆን በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ሙዚቀኞችን፣ የተቃዋሚ አባላትን፣ የጤና ባለሙያዎችን፣ እንዲሁም ለተቃውሞ ሰልፈኞቹ እርዳታ ያደረጉ ወይም በፍርሀት በመሸሽ ላይ ለነበሩ ተማሪዎች መደበቅያ ያዘጋጁ ሰዎችን በሙሉ አስረዋል። በርካታ ታሳሪዎች የተፈቱ ቢሆንም አሁንም ድረስ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ እስረኞች ምንም አይነት ክስ ሳይቀርብባቸው፣ ከህግ አማካሪዎች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ፈጽሞ መገናኘት እንዳይችሉ ተደርገው ዛሬም ድረስ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ።

የአይን እማኞች የእስራቱን መጠንና ስፋት ‘ከዚህ በፊት ፈጽሞ ታይቶ የማይታወቅ’ ሲሉ ገልጸውታል። ነዋሪነቱ በወለጋ ዞን የሆነ ዮሴፍ የተባለ የ52 አመት ሰው “ሙሉ እድሜዬን እዚሁ ነው የኖርኩት። እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት የግፍ ድርጊት በህይወቴ አይቼ አላውቅም፡፡ በየቀኑ እስራት እና ግድያ በህዝባችን ላይ ይፈጸም የነበረ ሲሆን ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ቢያንስ አንድ ልጅ ታስሮ ነበር” ብሏል።

ከዚህ ቀደም ታስረው የነበሩ ግለሰቦች በእስር ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ስቃይና የሰባዊ መብት ጥሰቶች እንደተካሄዱባቸው እንዲሁም ሴት ታሳሪዎች አስገድዶ መድፈር እና ጾታዊ ጥቃቶች ይፈጸምባቸው እንደነበር ለሂዩማን ራይት ወች ተናግረዋል። ጥቂቶች እግራቸው የፊጥኝ ታስሮ የቁልቁሊት በመዘቅዘቅ መደብደባቸውን የገለጹ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በኤሌክትሪክ እግራቸው ስር መነዘራቸውን ገልጸዋል፤ እንዲሁም በዘር ፍሬያቸው (ብልታቸው) ላይ ክብደት ያለው ነገር ታስሮባቸው እንዲሰቃዩ መደረጋቸውንም ተናግረዋል። በዩኒቨርስቲ ካምፓሶች ውስጥ ታማሪዎች ሲደበደቡ እንደነበር የሚያሳይ ቪዲዮም ታይቷል።

ከጅምላ እስራቱ ባሻገር የመንግስት ባለስልጣናት በጥቂት ግሰቦች ላይ ክስ በመመስረት ፍርድ ቤት አቅርበዋቸዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እና ጋዜጠኞች በአወአዛጋቢው የኢትዮጵያ ጸረ ሽብርተኝነት ህግ የተከሰሱ ሲሆን

አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሞ ያደረጉ 20 ተማሪዎች በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ መሰረት ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በየትምህርት ቤቱ በመስፈራቸው እንዲሁም በርካታ መምህራንና ተማሪዎች በመታሰራቸውና ቀሪዎቹም ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ በፍርሀት በመዋጣቸው የተነሳ ተቃውሞው በተካሄደባቸው ብዙ ስፍራዎች ላይ የመማር ማስተማር ሂደቱ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። በአንዳንድ አካባቢዎችም ተቃውሞው እንዳይቀጥል በመስጋት ለስልጣን አካላት ትምህርት ቤቶችን ለሳምንታት ያህል እንዲዘጉ አድርጓል። በርካታ ተማሪዎች ለሂዩማን ራይት ወች እንደተናገሩት ወታደሮች በየትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሰፈሩ ከመሆኑም ባሻገር የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ለይተው ከመቆጣጠር አልፈው የመብት ጥሰት ሲያደርጉባቸው ነበር።

አንዳንድ ተአማኒነት ያላቸው ዘገባዎች እንደጠቀሱት በተቃውሞ ሰልፈኞቹም የተካሄዱ የወንጀል ድርጊቶች እንደነበሩ ተስተውሏል፤ ከእነዚህም መካከል የውጭ ሀገር ዜጎች ንበረቶች ወድመዋል፣ የመንግስት ህንጻዎች ተዘርፈዋል፣ እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ንብረቶች ወድመዋል። ይሁን እንጂ ሂዩማን ራይት ወች ባደረገው ማጣሪያ እ.ኤ.አ. ከህዳር ወር ጀምሮ በተካሄዱት ከ500 በላይ የተቃውሞ ሰልፎች አብዛኞቹ ፍጹም ሰላማዊ ነበሩ።

የኢትዮጵያ መንግስት በገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትና በመገናኛ ብዙሀን የጣለው ጽኑ እቀባ ምክኒያትችግሮቹ በሚታዩባቸው ስፍራዎች ላይ ስላለው ሁኔታ የሚወጡት መረጃዎች እጅግ አነስተኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የመገናኛ ብዙሀን ነጻነትን ለማፈን የሚያደርገውን ጥረት ጨምሯል። በዚህም ከመጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ ፌስ ቡክንና ሌሎች ማህበራዊ ድረ ገጾችን ገድቧል። ከዚህም በተጨማሪ መቀመጫቸውን ከሀገር ውጪ ያደረጉና በሀገር ውስጥ የሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን አፍኗል።

በጥር ወር ላይ መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን ይፋ አድርጓል። ይሁን እንጂ በወቅቱ መንግስት በወሰደው የሀይልና የግፍ እርምጃዎች ሳቢያ የተቃውሞው አድራጊዎቹ ብሶት ግንፍሎ ወጥቶ ነበር።
welencomi

የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከአዲስ አበባ 60 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኛው ኦሎንኮሚ ከተማ ዉስጥ በሰልፈኞች ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጣቸዉን በአደባባይ ላይ ሰልፍ ሲገልጹ። ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓም።

እንደ ሂዩማን ራይት ወች ጥናት ከሆነ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ይካሄዱ የነበሩ ተቃውሞዎች እየተቀዛቀዙ የነበረ ቢሆንም የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚፈጽሙት አፈና ግን ቀጥሏል። ላለፉት ሰባት ወራት ያህል የታሰሩት በርካቶች አሁንም በእስር ላይ ያሉ ሲሆን ሌሎች በመቶ የሚቆጠሩት ደግሞ የት እንደደረሱ ለማወቅ አልተቻለም፤ ይህም በሀይል እንዲሰወሩ ሳይደረጉ አይቀርም የሚል ስጋት ፈጥሯል። መንግስት ስለቀረበበት በዚህ ሁሉ ውንጀላ ምንም አይነት ተአማኒነት ያለው የማጣራት ስራ አልሰራም። ወታደሮች አሁንም በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች እንደሰፈሩና በአካባቢውም ከፍተኛ ፍርሀት እንደነገሰ ነው። ተቃውሞ አድራጊዎቹ ምንም እንኳ በመጠኑ አነስተኛ ቢሆንም እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ተነስቶ የነበረውን የተቃዎሞ ጥያቄ ነው ያስተጋቡት፣ እናም የመንግስት ምላሽ ለወደፊት ተቃውሞ የበለጠ እንዲባባስ ሊያደርግ እንደሚችል ሂማን ራይትስ ወች ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጭካኔ የተሞላው የግፍ አያያዝን በተመከተ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ምክርቤትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታት እና መንግስታዊ ተቋማት ጠንካራና የተቀናጀ ምላሽ የሚጠይቅ ነው በማለት ሂዩማን ራይት ዎች አሳስቧል። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ድርጊቱን በማውገዝ ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ ያወጣና ይሄው መግለጫም ለአሜሪካ መንግስት የተገለጸ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው የግፍ ድርጊት በአለማቀፍ ደረጃ በአብዛናው በዝምታ የታለፈ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክርቤት ይህን ከፍተኛ የመብት ጥሰት በአትኩሮት ሊያየው፣ ያለአግባብ ለእስር የተዳረጉት እንዲፈቱና አስቸኳይ ገለልተኛ የሆነ ማጣሪያ እንዲካሄድ ጥሪ ሊያደርግ ይገባል።

“የኢትዮጵያን መንግስት የሚደግፉ አብዛኛዎቹ የውጭ አጋር ተቋማት መንግስት በኦሮሚያ ክልል የወሰደውን አስከፊ አፈና በተመለከተ በዝምታ አልፈውታል፡፡” በማለት ሌፍኮው ተናግሯል። “የኢትዮጵያን ልማት የሚደግፉ ሀገራት በኢትዮጵያ በሁኒም መስኩ መሻሳሎች እንዲታዩ ጫና ማድረግ አለባቸው፤ በተለይም የንግግር ነጻነትና ለተጠቂዎች ፍትህ እንዲያገኙ መስራት ይጠበቅባቸዋል። ” ብለዋል።

ጦርነቱ ተጀምሯል፤ አሸናፊውም በቅርብ ይለያል! –ይሄይስ አእምሮ

$
0
0

eritrea-border-claimአንድ ጊዜ በድብቅ ሌላ ጊዜ በግልጽ ለበርካታ ዓመታት ሲካሄድ የነበረው ጦርነት አሁን ለይቶለት ፈንድቷል፡፡ ብዙዎቻችን ስንጠብቀው የነበረ በመሆኑ አላስደነቀንም፤ እንዲያውም በጣም ዘግይቶ በመጀመሩ ምክንያት ሳንገረም የማንቀር ሰዎች እንደምንኖር እገምታለሁ፡፡ ኢሣይያስ ሣይቀር የዚህን የጦርነቱን መጀመርና የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ በሚመለከት በትንቢት መልክ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤ የሰማውና ከቁብ የቆጠረው ግን አልነበረም፡፡ ይሄውና አሁን ግን ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ግድ ሆነና በአራቱም ድንበሮች ማለትም አቅጣጫዎች ውጊያው ተጀምሮ እየተጧጧፈ ይገኛል፡፡

 

የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና አልቅሱ … እጅ ሁሉ ትዝላለች፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል፡፡ ይደነግጣሉ፤ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፤ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ … እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ ፣ ኃጢኣተኞችዋንም ከእርሷ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቁጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል፡፡ … ዓለሙን ስለክፋታቸው፣ክፉዎቹንም ስለበደላቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኩራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኩራት አዋርዳለሁ፡፡… ትንቢተ ኢሣይያስ 13፤ 6-16

 

የትኛው ጦርነት እንደተጀመረ አሁን ግልጽ ማድረግ አለብኝ፡፡ የተጀመረውና ተፋፍሞ በመቀጠል ላይ የሚገኘው ጦርነት አንባቢዎች እንደምትገምቱት የኢትዮጵያና የኤርትራ ሣይሆን በሰው ልጆችና በክፋት ሥራቸው መካከል ለዘመናት ሲግልና ሲቀዘቅዝ የመጣው የፍጻሜው ጦርነት ነው፡፡ የተለያዩ ስያሜዎችን መስጠት ይቻል ይሆናል፡- አርማጌዴዎን፣ ምፅዓት፣ የዓለም ፍጻሜ ወዘተ.፡፡ በየትኛውም ስሙ ጥሩት – የመጨረሻው መጨረሻ ግን በየበራችን ቆሞ እያንኳኳ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ባለፈው ሰሞን ስለ አበበ ተ/ሃይማኖት የጻፍኩትን መጣጥፍ በሚመለከት አንዳንድ አስተያየቶች በግል የኢሜል ሣጥኔም በድረ ገፅም ሣነብ የተሰማኝ ነገር አለ፡፡ ያም በተለይ የተቃወሙኝን በተመለከተ አንዳንዶቻችን ከእውነቱ ምን ያህል እንዳፈነገጥን የተገነዘብኩበት መራራ እውነት ነው፡፡ ጥቂት ድረ ገፆች እውነት እንደጦር እየወጋቻቸው ሣይሆን አይቀርም ስንት የደከምኩበትን ጽሑፌን የቅርጫት እራት አድርገው አስቀርተውብኛል፤ ትዝብት ይውረሱ፡፡ ይሄ ዘር የሚሉት ጣጣ ሲጠፋና (በቅርብ የሚጠፋ ከሆነ) ከዚያ ጠባብ ማዕቀፍ (shell) ሲወጡ አሁን ምን እየሠሩ እንደሆነ በማስታወስ ራሳቸውን ሊወቅሱ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ በተረፈ በዚያ ጽሑፍ ያልኩት ሁሉ መዛነፍ የሌለበት ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ ልጨምርልህ ከፈለግህ አሁንም፡፡

ትናንት ማታ አንድ ሰው ጋ ስንጫወት ይሄው የዘር በሽታ ተነሣና እንዲህ አለኝ፡፡ “እንዴ፣ ምን ማለትህ ነው ይሄይስ! የነዚህ ሰዎች ዘረኝነት እኮ ድንበር ብሎ ነገር አያውቅም፡፡ ለገሀር አካባቢ አንድ የአሸዋና ስሚንቶ መሸጫ ነበረ – ታስታውሰዋለህ? አሁን ትልቅ ፎቅ ተሠርቶበታል፤ ከሥሩም የነዳጅ ማደያ ተመርቆለታል፡፡ የዚያ ቦታ ባለቤት ምን እንደሆነ ሰምተሃል? … ለነገሩ ስንቱን ጉድ ልትሰማ ትችላለሀና፡፡ እናልህ ያ የቀድሞውን ባለቤት አንድ ትግሬ ቀምቶት ባዶ ሙልጩን ሰደደውና ሰውዬው በንዴት ራሱን ሰቅሎ ሞተ፤ ቤተሰቡም ተበተነ፡፡ ትግሬው አሁን እየተንጎማለለ ባለብዙ ሀብት፣ ባለብዙ ሚሊዮኖች ብር ሆኖልሃል፡፡ እንዲህ ያለ የጠነባ የዘረኝነት ግፍ አገር ምድሩን ሞልቶት ትግሬ ሲንቀባረር ሌላው አንገቱን ደፍቶ ሲዋትት ይኖራል ወንድሜ – መኖር ተብሎ፡፡ በዚህ መልክ ሀብት ንብረቱን፣ የሞቀ ትዳሩን፣ የማትተካ ሕይወቱን፣ ገንዘቡን ያጣው ዜጋ ቁጥር ሥፍር የለውም፤ ራሱን የገደለው ዜጋም እጅግ ብዙ ነው፤ ማርካቶን ከጉራጌ ያጸዱት እንዴት አድርገው እንደሆነ መቼም ሳትሰማ አትቀርም – ይሄውልህ – አንድን ነጋዴ ውጣ አይሉትም – እንዲወጣ ግን ያደርጉታል፤ ኪራዩን ሰማይ ይሰቅሉና፣ ግብሩን ሰማይ ይሰቅሉና፣ የዕቃ ቀረጡን ሰማይ ይሰቅሉና ምድረ ጉራጌና ሌላዋ ዜጋ በብስጭት የመርዝ “ዊስኪዋን” እያንደቀደቀች ስትሞትላቸው ወይም በእግር አውጪኝ ለስደት የመከራ ሕይወት ከሀገር ስትወጣላቸው ዌም ጨርቋን ጥላ ስታብድላቸው … እነሱ ያኔ በቆረጣ ሰዎቻቸውን ያስቀምጡበታል – ካላንዳች ግብር፣ ካላንዳች ቀረጥና ለስም በምትሆን ጥንጥዬ ኪራይ፡፡ ደስ ካላቸው ይቀሙህና አንተ በነሱው ፍርድ ቤት ስትንከራተት ትኖራለህ – በመጨረሻም በዘራቸውና በፖለቲካቸው ገብተው ያስፈርዱብሃል ፐ! እሱማ ቀላል ነው፤ ባንተ ላይ ማስፈረድ? በስማም፤ በተለይ ዐማራ ከሆንክማ የቆቅ ሥጋ ነህ – የምትጣፍጣቸው ግሩም ጣዕም ያለህ ፍጡር፡፡ ፈጣሪን ረስተው አንድያውን ለሰይጣን ስላደሩ ለማንም ሕይወት መንከራከስና የትም ወድቆ መቅረት ቅንጣት ታህል አያዝኑም፡፡ ትናንት ደግሞ አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሄጄ አንድ ጓደኛየ በክበባቸው ምሣ ሲጋብዘኝ የታዘብኩት ነገር በጣም የሚገርም ነው፡፡ የክበቡ ሠራተኞች በሙሉ፣ የክበቡ ተጠቃሚዎች በትንሽ ግምት 90 በመቶ የሚሆነው፣ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ከሞላ ጎደል ሁሉም ትግሬዎች ናቸው፡፡ ነገሩ የመከላከያ መሥሪያ ቤት በመሆኑ ሁሉም እነሱ ቢሆኑ አይፈረድም፡፡ ኧረ አለልህ እንጂ ማዘጋጃ ወይ ሌላ ተራ መሥሪያ ቤት … የትም ሂድ ብሔራዊ ቋንቋው ትግርኛ የሆነ ያህል እስኪሰማህ ድረስ እነሱ ናቸው ሠራተኞቹም ሆኑ አዛዥ ናዛዦቹ፡፡ ለዚህ ሳይሆን እኮ አይቀርም የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛ የማይችል ሰው አልቀጥርም እስከማለት የደረሰው – ያው እነሱስ ዘረኛ አይደሉ? ባለጌዎች፡፡ የሚገርም ትንግርት ነው እየታዬ ያለው፣ ይህን ቅጥ ያጣ አሠራር ማንና እንዴት እንደሚያስተካክለው ቆይቶ ማየት የሚችል ሰው ታድሏል ልጄ፡፡ እኔ በበኩሌ እስከዚህ ዐይናቸውና ሁለመናቸው የታወረ አይመስለኝም ነበር፡፡ ለይቶላቸዋልና እባክህን…” ሰውዬውን አስቆምኩት፡፡ በአሁኑ ሁኔታችን አንድ ሰው ብሶት መናገር ከጀመረ ማቆሚያ የለውም፡፡ እንደዶፍ ዝናብ ያዥጎደጉደዋል፡፡ ይሄ እንግዲህ ከማሰር መግደላቸው፣ በፍትህ ስም ግፍና በደል እየሠሩ ንጹሓንን ከማሰቃየታቸው፣ ሕዝብን በአስተዳድርና በኑሮ ውድነት ከማንገላታታቸው፣ ብዙኃንን ለስደት ከመዳረጋቸው፣ ዐይን ዐይን የከተማዋን ቦታዎች ለንግድም ሆነ ለመኖሪያ ለነሱ አባላት (ብቻ) ከመስጠታቸው … በተጨማሪ በኢኮኖሚውና በሀገራዊ ጥቅም ላይ የሚሠሩት የማንአለብኝነት በደል ነው፡፡ ይህን ስንናገር አላትምም የሚል ቢኖር የነሱን ዕጣ ይካፈል፤ እንደነሱ መጨረሻ የርሱም የሚያምር አይሁን – የሰዎችን ቁስል አናንቋልና፤ የወገኖቹን ስቃይ በዘረኝነት ቂጥኝ ለውሶ አድልዖዊ ውርዴነቱን በግልጽ አስመስክሯልና፡፡ አዎ፣ ይህን ግፍ መደበቅ ወይ ለመደበቅ መሞከር የግፉ ባለቤት የመሆን ያህል ነው፡፡ ወንድምህ ሰው ግድሎ አንተ ቤት ቢደበቅና ከሕግ ቢሠወር አንተም ከሱ ባልተናነሰ ወንጀለኛና አጥፊ ነህ፡፡ የሰማይና የምድር ሕግጋትና ሕገ ልቦና ተባብረው ፍትህን መታደግ ካልቻሉ ሰዎች ከዕቃነት አልተለዩምና ሰው አይባሉም፡፡ የወንድሙን ጥፋት የሚሸፋፍን የወንድሙን የበደል ዕጣ ይጋራ፤ በቃ፡፡ ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ መውጋቷ መቅረት አለበት፡፡ የአዳም ዘር ሁሉም አንድ ነው፡፡ ልዩነቶች በአብዛኛው ከቦታ ስፋትና ከጊዜ ሂደት ጋር ተያይዘው በኋላ የመጡ ናቸው፡፡ እንደመጽሐፉ ቃልም እነዚህ ልዩነቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይከስማሉ፡፡

እግዚአብሔርም አለ – ሰውን በመልካችን እንደምሣሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁሉ … ይግዙ፡፡ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፣ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1፣ 26 – 28

አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፡፡ ባርያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፡፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁና፡፡ እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ፡፡ ገላትያ 3፣ 28 – 29

መጽሐፉ እንዲህ እያለ ቀሣውስቱና አንዳንድ የዘረኝነት ውርዴ የሚያጠቃቸው ጠባቦች ከየት አምጥተውት ነው “የኔ ጎሣ ምርጥ – እኒህኞቹ ደግሞ እንጉላይ” የሚሉት? በዚህ የዘር መለኪያ መሠረት ዜጎች እየተሠፈሩ የአንዱን ገመና መሸፈን የሌላውን ገሃድ ማውጣት እንዴት የኅሊና ሚዛን ሊደፋ ይችላል? የሐጎስ ተስፋጋብር ነውርና ቅሌት ለፍትዊ ግደይ ምኑ ነው? የስንሻው ተገኘ ወንጀል ከአገሩ አበረ የትውልድ ሐረግ ጋር በምን ይያያዛል? ማንም ለራሱና ስለራሱ መጣ እንጂ ማንም የማንም ቅጣይ ወይም ማሟያ አይደለም፤ ልጄም ቢሆን በወንጀሉ ራሱ ይፈር እንጂ እኔን ምን አሸማቀቀኝ? ስለዚህ ይህን በዘር ጥላ ሥር ገመናን የመሻፋፈን ነገር እንተው፡፡ አለበለዚያ ሰውነታችንን በማይረባ ነገር እናረክሰዋለን፡፡

 

ለምን ወደ ተጀመረው ጦርነት አንሄድም?

 

እንጦስ ስለተባለ የወያኔ ጳጳስ ኢካድፍ ድረገፅ ላይ አንድ አስገራሚ ሀተታ ሰሞኑን አንብቤያለሁ፡፡ በአሜሪካን ሀገር በዚሁ ሰሞን በአንድ ግለሰብ የተፈጸመው የጅምላ ግድያም ገና ትኩስ ዜና ነው፡፡ መነሻየ እነዚህ ሆነው መድረሻየ ግን እንደምክንያት ሆኜ በትንሹ የአንድ ሰው ነፍስ መዳን ነው፤ “እሳት ተነስቷልና ራሳችሁን አድኑ፤ ሀብት ንብረታችሁንም አሽሹ” ብሎ መጮኽ ነውር የለበትም፡፡ የማይቀለበሰው ጦርነት ተጀምሯልና ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ ማለት ጤናማ ነኝ ብሎ ከሚያስብ ዜጋ የማይጠበቅ እንዳልሆነ በመገንዘብ ቀጣዩን ሀተታ በጥሞና እንመልከት፡፡

 

ስለዓለም ፍጻሜ የተጻፉና የተነገሩ መጽሐፍ ቅዱሣዊም (ሃይማኖታዊ)ም ይሁኑ ሰብኣዊ ትንቢቶች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ የድረገጽ ዳሰሳ ብናደርግ በሺዎች የሚቆጠሩ ንግርቶችንና መላ ምታዊ ግምቶችን በሴከንዶች ውስጥ እናገኛለን፡፡ አሁን “እከሌ ምን አለ” ወይም “ያ መጽሐፍ እንደዚህ አለ” የሚለው አካሄድ ጊዜ ያለፈበት ስለሚመስለኝ በምናያቸው አስቀያሚ ግን የሚጠበቁ እውነቶች ላይ ብቻ በመመርኮዝ የዘመናችንን ፍጻሜና የጦርነቱን መፋፋም ለቅጽበት ያህል እናስታውስ፡፡

በፍሎሪዳ ግዛት ሰሞኑን በሶዶማውያን የምሽት ክበብ ውስጥ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ ውጤቱ አሣዛኝ ቢሆንም ምክንያቱ ግን ተገቢና የፈጣሪ መቅሰፍት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡  የኖኅን የውኃ ጥፋትና የሎጥን የድኝ እሳት ዝናብ በሚያስታውሰን በዚህ ፍጅት ወደ ሃምሣ የሚጠጋ ሰው ሲገደል 53 አካባቢ ቆስሎበታል – ከነዚህም ስድስቶቹ በጽኑ የተጎዱ፡፡ ይህ አደጋ ያላሳዘናቸው ሰዎች ሞልተዋል፤ ያሳዘናቸውም እንዲሁ ብዙ ናቸው፡፡ ያላዘኑት ሰዎች ምክንያታቸው ሟቾቹ ዱሮውን በቁም ሞተዋል ከሚል ሃይማኖታዊ መነሻ ነው – ይህ እሳቤ ምናልባት የንስሃ ጊዜን ያለማሰብ ችግር ይኖርበት ይሆናል፡፡ በተረፈ ለሰይጣናዊ ድርጊትና እርሱን ተከትሎ ለተፈጠረ ቅጣት አቦካቶ ሆኖ መገኘት አጠያያቂ ይመስላል፡፡ እግዜር የፈቀደው ሆነ፤ የተገዳደሉት ደግሞ ጎልያድና ጎልያድ እንጂ ዳዊት በዚህ ትዕይንት የለበትም፡፡ ማለቴ ገዳዩም የዚያ ሥፍራ አዘውታሪና አባልም የነበረ መሆኑ በቀድሞ ባለቤቱ ተመስክሯል፤ ስለዚህ “አህያ ለአህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም” ነው፡፡

ወጣም ወረደ ይህ ክስተት የተጀመረው የታላቁ ጦርነት አካል ነው፡፡ የዓለም ሕዝብ በአሁኑ ወቅት እየተነዳ ያለው በዲያሎብስ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው – ሀፍረትን ለናቀው ድፍረቴ ግን ይቅርታ፡፡ እናም የታላቁ መሪያችን የሣጥናኤል ዘመን እየተገባደደ በመሆኑ ዐይኑን በጨው አጥቦ የዓለምን ዜጎች ወደግዛቱ ለማስገባት በተለይ ባለፉት 2000 ዓመታት የማያደርገው ጥረት አልነበረም፡፡ የተሳካለት ብዙ ነገር አለ፤ ያልተሳካለትም አለ፤ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡

ከተሳካለት ውስጥ ጥቂቶቹነ ማየት እንችላለን፡፡ ሰይጣን 500 ባልሞሉ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ዓለምን መቆጣጠር የምትችል ታላቅ ኃያል ሀገር ፈጥሯል፡፡ ይህ በራሱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ይህችን ሀገር የሚመሩ ኅቡኣኑ የዐውሬው ታዛዦች በአንዲት ሀገር ውስጥ ሁለት መንግሥታትን በማቆም ያሻቸውን እየሠሩና የዓለምን ሀገራት መሪዎች እንደፈለጉ እያሽከረከሩ ናቸው፡፡ በአንድ በኩል ዴሞክራሲ በጠራራ ፀሐይ የሚረሸንበትን ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር መሪዎች ሲሸልሙና ሲያሞግሱ ቢገኙ ወይም የዴምክራሲ ቃል ከናካቴው የማይጠራባቸውንና በተለይ የሴቶችን መብት የሚገፉ እንደሳዑዲ ያሉ ሀገራትን አቅፈውና ደግፈው ቢገኙ ለነሱ ምንም ማለት አይደለም፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝብ የሚወዳቸው መሪዎች ያሉባቸውንና በአንጻራዊ አነጋገር የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ የሚከተሉ ሀገራት መሪዎችን በሣተና ሰላዮቻቸው ቢያፍኑና ቢያስገድሉ ከማጉተምተም በስተቀር ወቃሽና ዳኛ የለባቸውም፡፡ አንዱ መንግሥት በግልጽ የሚታይና በዴሞክራሲ ጭምብል የዓለምን የኃይልና የፖለቲካ ሚዛን እንደፈለገው የሚያደርግ ነው፤ ሌላኛው ከ300 በማይበልጡና በማያንሱ ሥውር የቃል ኪዳን አባላቱ ዋናውን መንግሥት ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ በጥብቅ እየተቆጣጠረ የአባታቸውን የሣጥናኤልን ዓለምን ወደ አሃዳዊ የጨለማ ግዛት ለውጦ የመግዛት ህልም እውን ለማድረግ የሚጥር ነው፡፡ ይህ እውነት በሚዲያ እንዳይወጣ ከፍተኛ አፈናና ቁጥጥር ቢደረግም የፈለገ ግን አያጣውም፤ እኛ እዚህ ግቡ የማንባለው ውዳቂ ዜጎች እንኳን አላጣነውም፡፡

ቀደም ሲል በአዩኝ አላዩኝና እንደማፈርም እያሉ ህልማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ይሞክሩ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ድፍረታቸውና ዕብሪታቸው ወሰን አጥቶ መጣና ሌላው ቀርቶ ግብረ ሶዶማዊ “የዓለም መሪ” እስከመሾም በመድረስ “ምን ታመጣላችሁ?” እያሉን ነው፡፡ እኛማ ምን እናመጣለን ለነገሩ፡፡ ግን የሁሉም ሥልጣኔዎችና የሁሉም ድፍረቶች መጨረሻ ምን እንደሆነ ስለሚታወቅ ይህ ትዕቢታቸው የት ድረስ እንደሚወስዳቸው በጣም በቅርብ የምናየው ይሆናል፡፡

ሰይጣን ሰውን የሚያረክስበት ብዙ መንገድ አለው፡፡ ትልቁ ግን ፀረ-ተፈጥሮ ማድረግ ነው፡፡ ይህን ታዲያ ልብ እንበል፤ ከዚህ ትልቅ ፀረ-ተፈጥሮ ድርጊትም ራሳችንን እናርቅ፡፡ በዚህ ሰፊ ጎዳና ውስጥ የምንገኝ ሰዎች ካለን አሁኑኑ እንንቃና በአፋጣኝ እንመለስ፤ ይህ ነው የኔ መልእክት፡፡ ይህ ነው የኔና መሰሎቼ ወንድማዊ ጥሪ፡፡ “መብቴ ነው፤ ምርጫየ ነው፤ ምንም ማድረግ አልችልም – የተፈጥሮ ዝንባሌየ ነው …” ቅብጥርሶ ብንል አያዋጣም፡፡ ዘመኑም እጅግ ስለመሸ ጊዜ የለንም፡፡

 

… ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኩስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ … ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባህርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስህተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ፡፡ … እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤… ሮሜ 1፤ 24 – 28

 

መጽሐፍ አልጠቅስም ብዬ ነበርና ይቅርታ፤ ግድ ሆኖብኝ ነው፡፡ እናስ እንግዲህ ምንድነው የምንጠብቀው? የባለአንድዐይናውያኑ ዋና ተወካይ በሥርዓታቸው መሠረት ዕድገቱን አልፎ በግልጽ የሶዶማዊነት መንፈስ ዓለምን እየዞረ ስለነሱ መብት ሲከራከርና መብታቸውን ያልጠበቀ ሀገር ላይ ማዕቀብ እስከመጣል ወይም የተጣለን ማዕቀብ እስካለማንሣት ሲደርስ የኛን በመሰሉ ምሥኪንና ድሃ ሀገራት የሚገኙ የነሱው ተወካይ ቡችላ አጋንንት የሚገዙትን ሕዝብ በቁሙ እንጦርጦስ ሲከቱት ምን አሉ? አበረታቷቸው ወይንስ ተቆጧቸው? እውነቱ ይህ ነው – ገዢዎቻችን የነሰው ሎሌዎችና በምግባርም በጠባይምም የሚመሳሰሏቸው የሣጥናኤል ጭፍሮች ናቸው፡፡ እንደነሱ አለመሆን ታዲያ በምድር ቢቀር በሰማይ ማለትም በቀጣዩ ሕይወት ዋጋ አለው፡፡ ይህን ልብ እንበል!!

ሶዶማውያን ዓለምን እያበሻቀጧት ነው – ጥምብ እርኩሷን እያወጧት፡፡ ያቺ የትንቢት መፈጸሚያ ኃያል አገር እስካሁን ወደ 11 የሚደርሱ መሪዎቿ በዚህ ነገር እንደሚታሙ መዛግብት ይናገራሉ – በነገራችን ላይ ይህ ነገር ለነሱ ምንም ነውር የለበትም – ምክንያቱም አባታቸው እንዲሆኑለትና እንዲያስፈጽሙለት የሚያዛቸው ዋና ምሱ ነውና፡፡ ሰውን ማሳት በተለይ ትልልቅ የሚባሉትን ከመስመር ማስወጣት የዲያብሎስ ዋና መገለጫው ነው፡፡ አንድን ጳጳስ ማሳት አንድ ሺ ምዕመናንን ከማሳት ይበልጣል፡፡ ለምን ቢባል ጳጳሱን ፍየል እያየ የሚጠፋው በግ በብዙ መቶ ሺዎች ይቆጠራልና፡፡ የተያያዝነው ጦርነት እኮ በጣም ከባድና ሰው ያላወቀልን ነው ጎበዝ! ሆ!

ወደነኞች ስንመጣም እውነቱ ያው ነው – ሊያውስ ባይበስ አይደል? አንድ ወቅት እኔ በኃላፊነት እመራው በነበረ አንድ የግል ጋዜጣ  ውስጥ ይሠራ የነበረ ጋዜጠኛ የዱሮው ከርቸሌ ይታሰራል፡፡ ሲፈታ አንድ ግምኛ ጨዋታ ነገረኝ፡፡ ሁለት ካህናት እርሱ በታሰረበት ክልል ታስረው ነበር፡፡ የታሰሩበትን ምክንያት ሲነግረኝ የአሁኑን አያድርገውና በጊዜው በጣም ደነገጥኩ – አሁንማ እንኳን ቀሲስ ምድረ ባህታዊ፣ ጳጳስና ኤጲስ ቆጶስ ሁላ የተሰማራበት ቢያንስ ደግሞ በመደበኛው በኩል ያልሰነፈበት ተግባር ነው – ስንቱን ስናውቅ? እነዚያ ቄሶች የታሰሩት በግልጽ አማርኛ ሲሳረሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነበር – ግብረሶዶማውያን ነበሩ እያልኳችሁ ነው፡፡ መተፋፈር ዱሮ ቀረ ወንድሜ፡፡

ስለዚህ – የነአባ እንጦስማ ሚስት ማግባት ቀላል ነው፡፡ አባ ገብረ ሚካኤል የሚባሉ አሁን በማዕረገ ጵጵስና አቡነ እስጢፋኖስ የሚሰኙ እጅግ የተከበሩ ወያኔ ደግሞ አሥሬ እያገቡ የሚፈቱ መሆቸውን በቅርብ የሚያውቃቸው ሰው ነግሮኛል – ኃጢያቱ በኔ ይሁን ብያለሁ፤ እናንተ ባይሆን “አበስ(ኩ) ገበርኩ” እያላችሁ ሣር ቢጤ ባፋችሁ ያዙልኝ፡፡ አንድም ጳጳስ ከዚህ ውስልትና ነጻ የሚሆን ካለ በበኩሌ ይደንቀኛል፡፡ ከሟቹ ዱርዬ ፓትርያርክ ከጳውሎስ አንስቶ ሁሉም የሲኖዶስ አባል – ጃንደረባ(ስልብ) ካልሆኑ በስተቀር – ሴቱን እንደሸሚዝ ነው የሚለዋውጡት ይባልላቸዋል፡፡ የሰው ሚስት ሳይቀር እያፋቱ እንደሚያስቀምጡ የታወቀ ነገር እኮ ነው – ያን ታዋቂ አርቲስት ማን ነበር ባልቴት ሚስቱን ቀምቶ ባዶ ያስቀረው? ነውራቸው ተነግሮ ያልቃል እንዴ? እኔ በአንዲት ሚስት ከ30 ዓመታት በላይ ታስሬ ስኖር – በአንድ እጅ ጣት ከምትቆጠር የጥቂት ጊዜ ውስልትና ውጪ (ሸፋፋም ቢሆን ምክንያት ነበራት) – እነሱ ግን ቀዩዋን ከጠይሟ፣ ወጣቷን ቃ ካለችዋ እያማረጡ … የቀናሁ አስመሰለብኝ ይሆን እንዴ ይሄ ነገር?… ብቻ ይህን ሁሉ ጉድ መጽሐፉ አስቀድሞ ተናግሮታልና አዲስ ነገር የለም፡፡ የሚያሳዝነው ግን የእግዚአብሔርን መንገድ የሚከተል አንድም እረኛ ጠፍቶ ቤተ እግዚአብሔር የሰይጣን መናኸሪያና እንደልብ መፈንጫ መሆኗ ነው፡፡ በነዚህ አለሌዎች የምትመራ ቤተ አምልኮ ወደ ጥፋት እንጂ ወደጽድቅ መንገድ እንደማታስገባ ግልጽ ነው፡፡ እንዲያውም እስካሁን ድረስ ለይቶላት አለመጥፋቷና ምዕመናን አስልመውና ጴንጠው አለማለቃቸው ይገርመኛል፡፡ ሰው ሲጨነቅ እኮ የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ አንዳንድ ሞኝ ሰው ራሱን አንቆ የሚገድለው ወይም መርዝ ጠጥቶ ከዚህች ቆሻሻ ዓለም የሚሰናበተው ወዶ አይደለም፡፡…(በነገራችን ላይ ይህ ወሲባዊ ውስልትናና በዓለማዊነት የመጥፋት አባዜ በዘር የሚገደብ አይደለም|፡፡)

በመሠረቱ ጳጳሣትና መነኮሳት እግዚአብሔርን እያታለሉ በሰዎች ፊት እንዲህ ከሚዋረዱ የመጽሐፉን ቃል ሰምተው እያገቡ ቢኖሩ ይሻላቸው ነበር – ሊያውም በዚያም ከረጉና በአንዲት ሴት ብቻ ከተወሰኑ፡፡ ጳውሎስ የተናገረው ለሚችሉ እንጂ የሥጋ ፍላጎታቸውን መቆጣጠር ለሚያቅታቸው ወይም ፈጽሞ ለማይቻላቸው አስመሳዮች አይደለም፡፡

 

… ሰው ሁሉ እንደኔ ቢሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የፀጋ ስጦታ አለው፤ አንዱ እንደዚህ፣ ሁለተኛውም እንደዚያ፡፡… ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ – እንደኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው (በድንግልና እና/ወይም አለሩካቤ ሥጋ)፡፡ ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ፡፡…. የጳውሎስ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፤ 7-9

 

ይህ የጳውሎስ መልእክት የሚጠቁመን ምርጫ ያለን መሆናችንን ነው፡፡ ዘርን ከመተካት መለኮታዊ ትዕዛዝና ተፈጥሯዊ የተዋስቦ ህግ አንጻር ተገቢነቱ እጅግም ነው ብዬ በበኩሌ ባምንም  አለማግባት በመሠረቱ መጥፎ አይደለም፤ ማግባትም ጥሩ ነገር ነው፤ በምናብም ይሁን በእውን በአንዴ ሁለቱን መሆን ግን በጭራሽ አይቻልም፡፡ መሆንና አለመሆን በአንድ ጊዜ አንድ ቦታ ላይ የሚገኙበት ተጠየቃዊ ኹነት የለምና፡፡ እንዲያውም እሳትን በጉያ ይዞ እየነደዱ ከመኖር ይልቅ በህጉ መሠረት አንዲት አግብቶ እየተቃጠሉ ማነው እየወለዱና እየከበዱ መኖር የተሻለ አማራጭ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህን ጉዳይ በሚመለከት ሰዎች የማይችሉትን ቀምበር ለመሸከም የሚንደፋደፉትና ቅሌት ውስጥ የሚዘፈቁት ለምንድን ነው? ብለን መጠየቅ ደግሞ ይኖርብናል፡፡ ለእህል ውኃ ነው? ለክብር ነው? ለዝና ነው? ለየትኛው ክብርና ዝና? ክህነትን ያህል ትልቅ ማዕረግ፣ ጵጵስናን ያህል አቢይ መለኮታዊ ሥልጣን አፈር ድሜ አስግጦ ራስን ለማዋረድ ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ለምን አስፈለገ? አርሶና ቆፍሮ መብላት፣ ነግዶና ተቀጥሮ መሥራት እየተቻለ በእግዚአብሔር መቀለድ በምንም ሚዛን ቢለካ ከመቅለል አይተርፍም፡፡ ክህደት ነው? ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውሬን አያውቅብኝም ነው? ምንም አያደርገኝም ነው? ችግሩ ምን ይሆን? በየጥምጣሙ፣ በየጥንግ ድርቡ፣ በየካባውና ቀሚሱ ውስጥ ያለው ነገር ቢፈተሸ የእግዜርን ትግስት በእጅጉ እንድናደንቅ ያደርገናል፡፡ አዎ፣ ሞት ሲዘገይ የቀረ ይመስላል፤ ጥቂት እንፈላሰፍና – ምፅዓት የሞት ታላቅ ወንድም እንቅልፍ ደግሞ የሞት ታናሽ ወንድም ናቸው፡፡ ሁሉም ግን ጊዜያቸውን ጠብቀው መምጣታቸው አይቀርም፡፡ የማይመጡ እየመሰለን ግን ተሳስተን እናሳስታለን፡፡ ወዮ ለካህናት! ወዮ ለእረኞች! በጳውሎሳዊ ቃል “ወዮ! ቆሞ ያለ ለሚመስለው ዕቡይና ዝንጉ – የተቀመጠስ አንዴውኑ ተወዝፏል”፡፡ ትልቁን እግዚአብሔር ብንዘነጋ ትንሹን እግዚአብሔር ኅሊናችንን መርሳት የለብንም፡፡

በኛው ቤተ ክርስቲያን እንዲህ የጨከንኩ መሰልኩ እንጂ በካቶሊክም ሆነ በእስልምናውና በአይሁዳውያኑ ረገድም አጮልቀን ብናይ እውነቱ ከዚህ የተለዬ አይደለም፡፡ እኛ ጋ እነልደቱ አያሌውና እነ”አቡነ” እንጦስ ጽላት እየሸጡ እግዜርን በሰው ፊት “ሲያቀሉ”ና “ሲያዋርዱ” በአውሮፓ ደግሞ የገነት መግቢያ ካርድ(Indulgence Card?) ለምዕመናን እየሸጡ የሚከብሩና በፈጣሪ የሚቀልዱ ዚቀኛ ካህናትና ጳጳሳት ነበሩ – በመካከለኛው ዘመን አካባቢ፡፡ እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች አሁን አሁን ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገው – ጌታን በትክክለኛው መንገድ ማገልገሉን ሆን ብለው ትተውት –  ወንዶችና ሴቶች ሕጻናትን በማስገደድና በከረሜላ በማታለል መድፈር፣ እርስ በርስ በተመሳሳይ ፆታ የወሲብ ግንኙነት ተጠምደው ዲያብሎስን በሙሉ ልብ ማገልገል፣ በዘረፋና በማጭበርበር በሚያገኙት ገንዘብ የግል ሀብትን ማከማቸት… ዋና ሥራቸው በማድረግ በሥጋ ገበያ ጠፍተዋል – (አንድ የኢቫንጀሊካን ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ በጀርመን ሀገር የ42 ሚሊዮን ዶላር ቤተ መንግሥት መሰል መኖሪያ እንዳሠራና ከኃላፊነቱ እንደተባረረም ቀደም ሲል ሰምቻለሁ – ሁሉም ያው ቢሆኑም ለይምሰል ብለው በወቅቱ እርምጃ ወስደውበታል)፡፡ አብዛኛው ምዕመን በነዚህ ሰዎች ተስፋ በመቁረጥና በሕይወት ጨለምተኝነት በመሸነፍ ቤተ ክርስቲያንንና ሃይማኖትን እየተወላቸው መውጣቱን ተያይዞታል፡፡ ይህ አካሄድ ደግሞ እየገነነ ለመጣው ለሌላኛው ሰይጣናዊ ክንፍ ለአክራሪ እስልምና መስፋፋት የበኩሉን ድርሻ እያበረከተ ነው – ዛሬስ የጤና ያድርግልኝ፡፡ ምን ነካኘ ግን? ከስንቱ ጋር ነው “የምናጀሰው” በል?…

አዎ፣ እንግዲህ ያለንበት ሁኔታ በሁለትና ሦስት ዐረፍተ ነገሮች ሲገለጽ ይህን ይመስላል፡፡ በአንድ ወይ በሌላ መልክ ሁላችን ጠፍተናል፡፡ ከጠፋነው ይልቅ ደግሞ ልንጠፋ ያሰፈሰፍነው እንበልጣለን፡፡ ዓለማችንን ከያቅጣጫው ስንታዘባት አእምሮ ጠፍቶ ሕገ አራዊት የሚሉት ነገር ነግሦ እናያለን፡፡ ዓለማችን የአንድ ዓመትን ወንድ ሕጻን በቡድን የሚደፍሩ የታሊባን አክራሪ ሙስሊሞች፣ የሦስት ዓመት ወንድ ሕጻንን በቡድን የሚደፍሩና በመጨረሻ የሚገድሉ አክራሪ ሙስሊሞች በገፍ እየቀፈቀፈች ወደ ጨለማው የዲያብሎስ ግዛት ማስገባቷን ስንረዳ ምን ያህል እንደቆሸሸችና የመጽጃ ጊዜዋም ምን ያህል እንደቀረበ እንገነዘባለን፡፡ (ለነዚህ ወሬዎች ይህን ቦታ ፈልገው ያንብበቡ –  walidshoebat.com) ብዙ ጉድ እየፈላና እየተንተከተከ ነው፡፡ አይቀርልንም፡፡ እናም እንዘጋጅ፡፡

ዘረኝነትም አንዱ ከፈጣሪ የሚለየን መጥፎ ወረርሽኝ ነው፡፡ ለአንድ የሰው ልጀ ዘር ወደ ዓለም መጥቶ የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ትግሬ ወይ አማራ ወይም ኦሮሞ አልነበረም፡፡  ምንም እንኳን አንዱን የሰው ዘር መምሰል ስለነበረበት ክርስቶስ ኢየሱስ ከይሁዳዎች ዘር ቢፈጠርም ዓላማውና ግብሩ ግን ለመላው የሰው ዘር ነው፡፡ እነ መለስና አባቶቻቸው እነጳውሎስ ግን ቤተ ክርስቲያንን ለሰይጣን ማደሪያ በማድረግ ከቀደሙት አባቶች ባሱና ሕዝብን በቀበሮና በተኩላ ያስጨርሱት ገቡ፡፡ ሁሉም ዋጋቸውን ሊያገኙ ጦርነቱ መጀመሩ ተስፋ ይሆነናል እንጂ በዚህ በያዙት መንገድ ብዙ ዓመታትን መቀጠላቸው ግድ ቢሆን ኖሮ በእጅጉ እንናደድ ነበር፡፡ “ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም” የሚለቀውን የፈጣሪ ህግ አፍርሰው ከሁለት በላይ ለሆኑ ህግጋት አፈነደሱ – ለዘር፣ ለንዋይና ለሃይማኖታዊ ህፀፅ፡፡ የምድር ነገር ምድራዊ ነውና እንደጥላ ያልፋል፤ እንደጤዛም ይረግፋል፡፡ የሚቀረው ግን በቀላሉ የማይሽረው የታሪክ ጠበሳውና ስብራቱ ነው፡፡ ለወያኔ ዲያብሎስና ለእግዜር በአንዴ መገዛት እንደማይቻል ኅሊናን ትንሽ ከፈት አድርጎ ማየት ነው፤ እምብርት ላልተበጀለት ላስቲክ ሆድ ሲባል ሀገርንና ህዝብን ክዶ ለአንድ ዘረኛ ቡድን ማደግደግ ቀን ሲያልፍ ለሀፍረትና ለትልቅ ውርደት እንደሚዳርግ ማወቅ በተገባ ነበር – ጭንቅላት የለም እንጂ ቢኖር ኖሮ፡፡

ለማንኛውም ዛሬ እንዲህ ነው፤ ነገ ግን በርግጠንነት ይለያል፡፡ ተስፋ ሲሞት ሰው ይሞታል፡፡ ተስፋ ካለ ሰው አለ – እኛም አለን፡፡ ከሚተርፉት ከመደበን ጦርነቱ ሲያልቅ እንገናኝ ይሆናል፡፡ ሰላም፡፡

ቀጣዩን ነገር ከፈለጋችሁ አንብቡት – ልተረጉመው ብዬ አስቀመጥኩት – ግን ደከመኝና ተውኩት፡፡

 

Deviancy never resides in one desire, like murder; deviancy resonates in all desires, it becomes a part of one’s whole person. Deranged and disturbing lusts for blood resonates in one’s sexual urges, and these are always aberrant and debased. It all comes down to one’s religious beliefs. All deviancy originates from a disordered view of God. If one’s soul is loving, then that soul will treat his or her spouse with love. But if one’s soul is darkened by evil, then that person will not care for love, harmony, compassion, no, not even the natural order. Chaos is embraced, order is mutilated, and the entire divinely created system of nature is warred against. (source: walidshoebat.com)

ጦርነቱ ተጀምሯል፤ አሸናፊውም በቅርብ ይለያል! |ይሄይስ አእምሮ

$
0
0

ethio-ertria

አንድ ጊዜ በድብቅ ሌላ ጊዜ በግልጽ ለበርካታ ዓመታት ሲካሄድ የነበረው ጦርነት አሁን ለይቶለት ፈንድቷል፡፡ ብዙዎቻችን ስንጠብቀው የነበረ በመሆኑ አላስደነቀንም፤ እንዲያውም በጣም ዘግይቶ በመጀመሩ ምክንያት ሳንገረም የማንቀር ሰዎች እንደምንኖር እገምታለሁ፡፡ ኢሣይያስ ሣይቀር የዚህን የጦርነቱን መጀመርና የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ በሚመለከት በትንቢት መልክ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤ የሰማውና ከቁብ የቆጠረው ግን አልነበረም፡፡ ይሄውና አሁን ግን ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ግድ ሆነና በአራቱም ድንበሮች ማለትም አቅጣጫዎች ውጊያው ተጀምሮ እየተጧጧፈ ይገኛል፡፡

የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና አልቅሱ … እጅ ሁሉ ትዝላለች፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል፡፡ ይደነግጣሉ፤ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፤ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ … እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ ፣ ኃጢኣተኞችዋንም ከእርሷ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቁጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል፡፡ … ዓለሙን ስለክፋታቸው፣ክፉዎቹንም ስለበደላቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኩራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኩራት አዋርዳለሁ፡፡… ትንቢተ ኢሣይያስ 13፤ 6-16

የትኛው ጦርነት እንደተጀመረ አሁን ግልጽ ማድረግ አለብኝ፡፡ የተጀመረውና ተፋፍሞ በመቀጠል ላይ የሚገኘው ጦርነት አንባቢዎች እንደምትገምቱት የኢትዮጵያና የኤርትራ ሣይሆን በሰው ልጆችና በክፋት ሥራቸው መካከል ለዘመናት ሲግልና ሲቀዘቅዝ የመጣው የፍጻሜው ጦርነት ነው፡፡ የተለያዩ ስያሜዎችን መስጠት ይቻል ይሆናል፡- አርማጌዴዎን፣ ምፅዓት፣ የዓለም ፍጻሜ ወዘተ.፡፡ በየትኛውም ስሙ ጥሩት – የመጨረሻው መጨረሻ ግን በየበራችን ቆሞ እያንኳኳ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ባለፈው ሰሞን ስለ አበበ ተ/ሃይማኖት የጻፍኩትን መጣጥፍ በሚመለከት አንዳንድ አስተያየቶች በግል የኢሜል ሣጥኔም በድረ ገፅም ሣነብ የተሰማኝ ነገር አለ፡፡ ያም በተለይ የተቃወሙኝን በተመለከተ አንዳንዶቻችን ከእውነቱ ምን ያህል እንዳፈነገጥን የተገነዘብኩበት መራራ እውነት ነው፡፡ ጥቂት ድረ ገፆች እውነት እንደጦር እየወጋቻቸው ሣይሆን አይቀርም ስንት የደከምኩበትን ጽሑፌን የቅርጫት እራት አድርገው አስቀርተውብኛል፤ ትዝብት ይውረሱ፡፡ ይሄ ዘር የሚሉት ጣጣ ሲጠፋና (በቅርብ የሚጠፋ ከሆነ) ከዚያ ጠባብ ማዕቀፍ (shell) ሲወጡ አሁን ምን እየሠሩ እንደሆነ በማስታወስ ራሳቸውን ሊወቅሱ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ በተረፈ በዚያ ጽሑፍ ያልኩት ሁሉ መዛነፍ የሌለበት ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ ልጨምርልህ ከፈለግህ አሁንም፡፡

ትናንት ማታ አንድ ሰው ጋ ስንጫወት ይሄው የዘር በሽታ ተነሣና እንዲህ አለኝ፡፡ “እንዴ፣ ምን ማለትህ ነው ይሄይስ! የነዚህ ሰዎች ዘረኝነት እኮ ድንበር ብሎ ነገር አያውቅም፡፡ ለገሀር አካባቢ አንድ የአሸዋና ስሚንቶ መሸጫ ነበረ – ታስታውሰዋለህ? አሁን ትልቅ ፎቅ ተሠርቶበታል፤ ከሥሩም የነዳጅ ማደያ ተመርቆለታል፡፡ የዚያ ቦታ ባለቤት ምን እንደሆነ ሰምተሃል? … ለነገሩ ስንቱን ጉድ ልትሰማ ትችላለሀና፡፡ እናልህ ያ የቀድሞውን ባለቤት አንድ ትግሬ ቀምቶት ባዶ ሙልጩን ሰደደውና ሰውዬው በንዴት ራሱን ሰቅሎ ሞተ፤ ቤተሰቡም ተበተነ፡፡ ትግሬው አሁን እየተንጎማለለ ባለብዙ ሀብት፣ ባለብዙ ሚሊዮኖች ብር ሆኖልሃል፡፡ እንዲህ ያለ የጠነባ የዘረኝነት ግፍ አገር ምድሩን ሞልቶት ትግሬ ሲንቀባረር ሌላው አንገቱን ደፍቶ ሲዋትት ይኖራል ወንድሜ – መኖር ተብሎ፡፡ በዚህ መልክ ሀብት ንብረቱን፣ የሞቀ ትዳሩን፣ የማትተካ ሕይወቱን፣ ገንዘቡን ያጣው ዜጋ ቁጥር ሥፍር የለውም፤ ራሱን የገደለው ዜጋም እጅግ ብዙ ነው፤ ማርካቶን ከጉራጌ ያጸዱት እንዴት አድርገው እንደሆነ መቼም ሳትሰማ አትቀርም – ይሄውልህ – አንድን ነጋዴ ውጣ አይሉትም – እንዲወጣ ግን ያደርጉታል፤ ኪራዩን ሰማይ ይሰቅሉና፣ ግብሩን ሰማይ ይሰቅሉና፣ የዕቃ ቀረጡን ሰማይ ይሰቅሉና ምድረ ጉራጌና ሌላዋ ዜጋ በብስጭት የመርዝ “ዊስኪዋን” እያንደቀደቀች ስትሞትላቸው ወይም በእግር አውጪኝ ለስደት የመከራ ሕይወት ከሀገር ስትወጣላቸው ዌም ጨርቋን ጥላ ስታብድላቸው … እነሱ ያኔ በቆረጣ ሰዎቻቸውን ያስቀምጡበታል – ካላንዳች ግብር፣ ካላንዳች ቀረጥና ለስም በምትሆን ጥንጥዬ ኪራይ፡፡ ደስ ካላቸው ይቀሙህና አንተ በነሱው ፍርድ ቤት ስትንከራተት ትኖራለህ – በመጨረሻም በዘራቸውና በፖለቲካቸው ገብተው ያስፈርዱብሃል ፐ! እሱማ ቀላል ነው፤ ባንተ ላይ ማስፈረድ? በስማም፤ በተለይ ዐማራ ከሆንክማ የቆቅ ሥጋ ነህ – የምትጣፍጣቸው ግሩም ጣዕም ያለህ ፍጡር፡፡ ፈጣሪን ረስተው አንድያውን ለሰይጣን ስላደሩ ለማንም ሕይወት መንከራከስና የትም ወድቆ መቅረት ቅንጣት ታህል አያዝኑም፡፡ ትናንት ደግሞ አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሄጄ አንድ ጓደኛየ በክበባቸው ምሣ ሲጋብዘኝ የታዘብኩት ነገር በጣም የሚገርም ነው፡፡ የክበቡ ሠራተኞች በሙሉ፣ የክበቡ ተጠቃሚዎች በትንሽ ግምት 90 በመቶ የሚሆነው፣ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ከሞላ ጎደል ሁሉም ትግሬዎች ናቸው፡፡ ነገሩ የመከላከያ መሥሪያ ቤት በመሆኑ ሁሉም እነሱ ቢሆኑ አይፈረድም፡፡ ኧረ አለልህ እንጂ ማዘጋጃ ወይ ሌላ ተራ መሥሪያ ቤት … የትም ሂድ ብሔራዊ ቋንቋው ትግርኛ የሆነ ያህል እስኪሰማህ ድረስ እነሱ ናቸው ሠራተኞቹም ሆኑ አዛዥ ናዛዦቹ፡፡ ለዚህ ሳይሆን እኮ አይቀርም የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛ የማይችል ሰው አልቀጥርም እስከማለት የደረሰው – ያው እነሱስ ዘረኛ አይደሉ? ባለጌዎች፡፡ የሚገርም ትንግርት ነው እየታዬ ያለው፣ ይህን ቅጥ ያጣ አሠራር ማንና እንዴት እንደሚያስተካክለው ቆይቶ ማየት የሚችል ሰው ታድሏል ልጄ፡፡ እኔ በበኩሌ እስከዚህ ዐይናቸውና ሁለመናቸው የታወረ አይመስለኝም ነበር፡፡ ለይቶላቸዋልና እባክህን…” ሰውዬውን አስቆምኩት፡፡ በአሁኑ ሁኔታችን አንድ ሰው ብሶት መናገር ከጀመረ ማቆሚያ የለውም፡፡ እንደዶፍ ዝናብ ያዥጎደጉደዋል፡፡ ይሄ እንግዲህ ከማሰር መግደላቸው፣ በፍትህ ስም ግፍና በደል እየሠሩ ንጹሓንን ከማሰቃየታቸው፣ ሕዝብን በአስተዳድርና በኑሮ ውድነት ከማንገላታታቸው፣ ብዙኃንን ለስደት ከመዳረጋቸው፣ ዐይን ዐይን የከተማዋን ቦታዎች ለንግድም ሆነ ለመኖሪያ ለነሱ አባላት (ብቻ) ከመስጠታቸው … በተጨማሪ በኢኮኖሚውና በሀገራዊ ጥቅም ላይ የሚሠሩት የማንአለብኝነት በደል ነው፡፡ ይህን ስንናገር አላትምም የሚል ቢኖር የነሱን ዕጣ ይካፈል፤ እንደነሱ መጨረሻ የርሱም የሚያምር አይሁን – የሰዎችን ቁስል አናንቋልና፤ የወገኖቹን ስቃይ በዘረኝነት ቂጥኝ ለውሶ አድልዖዊ ውርዴነቱን በግልጽ አስመስክሯልና፡፡ አዎ፣ ይህን ግፍ መደበቅ ወይ ለመደበቅ መሞከር የግፉ ባለቤት የመሆን ያህል ነው፡፡ ወንድምህ ሰው ግድሎ አንተ ቤት ቢደበቅና ከሕግ ቢሠወር አንተም ከሱ ባልተናነሰ ወንጀለኛና አጥፊ ነህ፡፡ የሰማይና የምድር ሕግጋትና ሕገ ልቦና ተባብረው ፍትህን መታደግ ካልቻሉ ሰዎች ከዕቃነት አልተለዩምና ሰው አይባሉም፡፡ የወንድሙን ጥፋት የሚሸፋፍን የወንድሙን የበደል ዕጣ ይጋራ፤ በቃ፡፡ ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ መውጋቷ መቅረት አለበት፡፡ የአዳም ዘር ሁሉም አንድ ነው፡፡ ልዩነቶች በአብዛኛው ከቦታ ስፋትና ከጊዜ ሂደት ጋር ተያይዘው በኋላ የመጡ ናቸው፡፡ እንደመጽሐፉ ቃልም እነዚህ ልዩነቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይከስማሉ፡፡

እግዚአብሔርም አለ – ሰውን በመልካችን እንደምሣሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁሉ … ይግዙ፡፡ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፣ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1፣ 26 – 28

አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፡፡ ባርያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፡፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁና፡፡ እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ፡፡ ገላትያ 3፣ 28 – 29

መጽሐፉ እንዲህ እያለ ቀሣውስቱና አንዳንድ የዘረኝነት ውርዴ የሚያጠቃቸው ጠባቦች ከየት አምጥተውት ነው “የኔ ጎሣ ምርጥ – እኒህኞቹ ደግሞ እንጉላይ” የሚሉት? በዚህ የዘር መለኪያ መሠረት ዜጎች እየተሠፈሩ የአንዱን ገመና መሸፈን የሌላውን ገሃድ ማውጣት እንዴት የኅሊና ሚዛን ሊደፋ ይችላል? የሐጎስ ተስፋጋብር ነውርና ቅሌት ለፍትዊ ግደይ ምኑ ነው? የስንሻው ተገኘ ወንጀል ከአገሩ አበረ የትውልድ ሐረግ ጋር በምን ይያያዛል? ማንም ለራሱና ስለራሱ መጣ እንጂ ማንም የማንም ቅጣይ ወይም ማሟያ አይደለም፤ ልጄም ቢሆን በወንጀሉ ራሱ ይፈር እንጂ እኔን ምን አሸማቀቀኝ? ስለዚህ ይህን በዘር ጥላ ሥር ገመናን የመሻፋፈን ነገር እንተው፡፡ አለበለዚያ ሰውነታችንን በማይረባ ነገር እናረክሰዋለን፡፡

ለምን ወደ ተጀመረው ጦርነት አንሄድም?

እንጦስ ስለተባለ የወያኔ ጳጳስ ኢካድፍ ድረገፅ ላይ አንድ አስገራሚ ሀተታ ሰሞኑን አንብቤያለሁ፡፡ በአሜሪካን ሀገር በዚሁ ሰሞን በአንድ ግለሰብ የተፈጸመው የጅምላ ግድያም ገና ትኩስ ዜና ነው፡፡ መነሻየ እነዚህ ሆነው መድረሻየ ግን እንደምክንያት ሆኜ በትንሹ የአንድ ሰው ነፍስ መዳን ነው፤ “እሳት ተነስቷልና ራሳችሁን አድኑ፤ ሀብት ንብረታችሁንም አሽሹ” ብሎ መጮኽ ነውር የለበትም፡፡ የማይቀለበሰው ጦርነት ተጀምሯልና ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ ማለት ጤናማ ነኝ ብሎ ከሚያስብ ዜጋ የማይጠበቅ እንዳልሆነ በመገንዘብ ቀጣዩን ሀተታ በጥሞና እንመልከት፡፡

ስለዓለም ፍጻሜ የተጻፉና የተነገሩ መጽሐፍ ቅዱሣዊም (ሃይማኖታዊ)ም ይሁኑ ሰብኣዊ ትንቢቶች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ የድረገጽ ዳሰሳ ብናደርግ በሺዎች የሚቆጠሩ ንግርቶችንና መላ ምታዊ ግምቶችን በሴከንዶች ውስጥ እናገኛለን፡፡ አሁን “እከሌ ምን አለ” ወይም “ያ መጽሐፍ እንደዚህ አለ” የሚለው አካሄድ ጊዜ ያለፈበት ስለሚመስለኝ በምናያቸው አስቀያሚ ግን የሚጠበቁ እውነቶች ላይ ብቻ በመመርኮዝ የዘመናችንን ፍጻሜና የጦርነቱን መፋፋም ለቅጽበት ያህል እናስታውስ፡፡

በፍሎሪዳ ግዛት ሰሞኑን በሶዶማውያን የምሽት ክበብ ውስጥ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ ውጤቱ አሣዛኝ ቢሆንም ምክንያቱ ግን ተገቢና የፈጣሪ መቅሰፍት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡  የኖኅን የውኃ ጥፋትና የሎጥን የድኝ እሳት ዝናብ በሚያስታውሰን በዚህ ፍጅት ወደ ሃምሣ የሚጠጋ ሰው ሲገደል 53 አካባቢ ቆስሎበታል – ከነዚህም ስድስቶቹ በጽኑ የተጎዱ፡፡ ይህ አደጋ ያላሳዘናቸው ሰዎች ሞልተዋል፤ ያሳዘናቸውም እንዲሁ ብዙ ናቸው፡፡ ያላዘኑት ሰዎች ምክንያታቸው ሟቾቹ ዱሮውን በቁም ሞተዋል ከሚል ሃይማኖታዊ መነሻ ነው – ይህ እሳቤ ምናልባት የንስሃ ጊዜን ያለማሰብ ችግር ይኖርበት ይሆናል፡፡ በተረፈ ለሰይጣናዊ ድርጊትና እርሱን ተከትሎ ለተፈጠረ ቅጣት አቦካቶ ሆኖ መገኘት አጠያያቂ ይመስላል፡፡ እግዜር የፈቀደው ሆነ፤ የተገዳደሉት ደግሞ ጎልያድና ጎልያድ እንጂ ዳዊት በዚህ ትዕይንት የለበትም፡፡ ማለቴ ገዳዩም የዚያ ሥፍራ አዘውታሪና አባልም የነበረ መሆኑ በቀድሞ ባለቤቱ ተመስክሯል፤ ስለዚህ “አህያ ለአህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም” ነው፡፡

ወጣም ወረደ ይህ ክስተት የተጀመረው የታላቁ ጦርነት አካል ነው፡፡ የዓለም ሕዝብ በአሁኑ ወቅት እየተነዳ ያለው በዲያሎብስ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው – ሀፍረትን ለናቀው ድፍረቴ ግን ይቅርታ፡፡ እናም የታላቁ መሪያችን የሣጥናኤል ዘመን እየተገባደደ በመሆኑ ዐይኑን በጨው አጥቦ የዓለምን ዜጎች ወደግዛቱ ለማስገባት በተለይ ባለፉት 2000 ዓመታት የማያደርገው ጥረት አልነበረም፡፡ የተሳካለት ብዙ ነገር አለ፤ ያልተሳካለትም አለ፤ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡

ከተሳካለት ውስጥ ጥቂቶቹነ ማየት እንችላለን፡፡ ሰይጣን 500 ባልሞሉ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ዓለምን መቆጣጠር የምትችል ታላቅ ኃያል ሀገር ፈጥሯል፡፡ ይህ በራሱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ይህችን ሀገር የሚመሩ ኅቡኣኑ የዐውሬው ታዛዦች በአንዲት ሀገር ውስጥ ሁለት መንግሥታትን በማቆም ያሻቸውን እየሠሩና የዓለምን ሀገራት መሪዎች እንደፈለጉ እያሽከረከሩ ናቸው፡፡ በአንድ በኩል ዴሞክራሲ በጠራራ ፀሐይ የሚረሸንበትን ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር መሪዎች ሲሸልሙና ሲያሞግሱ ቢገኙ ወይም የዴምክራሲ ቃል ከናካቴው የማይጠራባቸውንና በተለይ የሴቶችን መብት የሚገፉ እንደሳዑዲ ያሉ ሀገራትን አቅፈውና ደግፈው ቢገኙ ለነሱ ምንም ማለት አይደለም፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝብ የሚወዳቸው መሪዎች ያሉባቸውንና በአንጻራዊ አነጋገር የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ የሚከተሉ ሀገራት መሪዎችን በሣተና ሰላዮቻቸው ቢያፍኑና ቢያስገድሉ ከማጉተምተም በስተቀር ወቃሽና ዳኛ የለባቸውም፡፡ አንዱ መንግሥት በግልጽ የሚታይና በዴሞክራሲ ጭምብል የዓለምን የኃይልና የፖለቲካ ሚዛን እንደፈለገው የሚያደርግ ነው፤ ሌላኛው ከ300 በማይበልጡና በማያንሱ ሥውር የቃል ኪዳን አባላቱ ዋናውን መንግሥት ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ በጥብቅ እየተቆጣጠረ የአባታቸውን የሣጥናኤልን ዓለምን ወደ አሃዳዊ የጨለማ ግዛት ለውጦ የመግዛት ህልም እውን ለማድረግ የሚጥር ነው፡፡ ይህ እውነት በሚዲያ እንዳይወጣ ከፍተኛ አፈናና ቁጥጥር ቢደረግም የፈለገ ግን አያጣውም፤ እኛ እዚህ ግቡ የማንባለው ውዳቂ ዜጎች እንኳን አላጣነውም፡፡

ቀደም ሲል በአዩኝ አላዩኝና እንደማፈርም እያሉ ህልማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ይሞክሩ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ድፍረታቸውና ዕብሪታቸው ወሰን አጥቶ መጣና ሌላው ቀርቶ ግብረ ሶዶማዊ “የዓለም መሪ” እስከመሾም በመድረስ “ምን ታመጣላችሁ?” እያሉን ነው፡፡ እኛማ ምን እናመጣለን ለነገሩ፡፡ ግን የሁሉም ሥልጣኔዎችና የሁሉም ድፍረቶች መጨረሻ ምን እንደሆነ ስለሚታወቅ ይህ ትዕቢታቸው የት ድረስ እንደሚወስዳቸው በጣም በቅርብ የምናየው ይሆናል፡፡

ሰይጣን ሰውን የሚያረክስበት ብዙ መንገድ አለው፡፡ ትልቁ ግን ፀረ-ተፈጥሮ ማድረግ ነው፡፡ ይህን ታዲያ ልብ እንበል፤ ከዚህ ትልቅ ፀረ-ተፈጥሮ ድርጊትም ራሳችንን እናርቅ፡፡ በዚህ ሰፊ ጎዳና ውስጥ የምንገኝ ሰዎች ካለን አሁኑኑ እንንቃና በአፋጣኝ እንመለስ፤ ይህ ነው የኔ መልእክት፡፡ ይህ ነው የኔና መሰሎቼ ወንድማዊ ጥሪ፡፡ “መብቴ ነው፤ ምርጫየ ነው፤ ምንም ማድረግ አልችልም – የተፈጥሮ ዝንባሌየ ነው …” ቅብጥርሶ ብንል አያዋጣም፡፡ ዘመኑም እጅግ ስለመሸ ጊዜ የለንም፡፡

… ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኩስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ … ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባህርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስህተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ፡፡ … እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤… ሮሜ 1፤ 24 – 28

መጽሐፍ አልጠቅስም ብዬ ነበርና ይቅርታ፤ ግድ ሆኖብኝ ነው፡፡ እናስ እንግዲህ ምንድነው የምንጠብቀው? የባለአንድዐይናውያኑ ዋና ተወካይ በሥርዓታቸው መሠረት ዕድገቱን አልፎ በግልጽ የሶዶማዊነት መንፈስ ዓለምን እየዞረ ስለነሱ መብት ሲከራከርና መብታቸውን ያልጠበቀ ሀገር ላይ ማዕቀብ እስከመጣል ወይም የተጣለን ማዕቀብ እስካለማንሣት ሲደርስ የኛን በመሰሉ ምሥኪንና ድሃ ሀገራት የሚገኙ የነሱው ተወካይ ቡችላ አጋንንት የሚገዙትን ሕዝብ በቁሙ እንጦርጦስ ሲከቱት ምን አሉ? አበረታቷቸው ወይንስ ተቆጧቸው? እውነቱ ይህ ነው – ገዢዎቻችን የነሰው ሎሌዎችና በምግባርም በጠባይምም የሚመሳሰሏቸው የሣጥናኤል ጭፍሮች ናቸው፡፡ እንደነሱ አለመሆን ታዲያ በምድር ቢቀር በሰማይ ማለትም በቀጣዩ ሕይወት ዋጋ አለው፡፡ ይህን ልብ እንበል!!

ሶዶማውያን ዓለምን እያበሻቀጧት ነው – ጥምብ እርኩሷን እያወጧት፡፡ ያቺ የትንቢት መፈጸሚያ ኃያል አገር እስካሁን ወደ 11 የሚደርሱ መሪዎቿ በዚህ ነገር እንደሚታሙ መዛግብት ይናገራሉ – በነገራችን ላይ ይህ ነገር ለነሱ ምንም ነውር የለበትም – ምክንያቱም አባታቸው እንዲሆኑለትና እንዲያስፈጽሙለት የሚያዛቸው ዋና ምሱ ነውና፡፡ ሰውን ማሳት በተለይ ትልልቅ የሚባሉትን ከመስመር ማስወጣት የዲያብሎስ ዋና መገለጫው ነው፡፡ አንድን ጳጳስ ማሳት አንድ ሺ ምዕመናንን ከማሳት ይበልጣል፡፡ ለምን ቢባል ጳጳሱን ፍየል እያየ የሚጠፋው በግ በብዙ መቶ ሺዎች ይቆጠራልና፡፡ የተያያዝነው ጦርነት እኮ በጣም ከባድና ሰው ያላወቀልን ነው ጎበዝ! ሆ!

ወደነኞች ስንመጣም እውነቱ ያው ነው – ሊያውስ ባይበስ አይደል? አንድ ወቅት እኔ በኃላፊነት እመራው በነበረ አንድ የግል ጋዜጣ  ውስጥ ይሠራ የነበረ ጋዜጠኛ የዱሮው ከርቸሌ ይታሰራል፡፡ ሲፈታ አንድ ግምኛ ጨዋታ ነገረኝ፡፡ ሁለት ካህናት እርሱ በታሰረበት ክልል ታስረው ነበር፡፡ የታሰሩበትን ምክንያት ሲነግረኝ የአሁኑን አያድርገውና በጊዜው በጣም ደነገጥኩ – አሁንማ እንኳን ቀሲስ ምድረ ባህታዊ፣ ጳጳስና ኤጲስ ቆጶስ ሁላ የተሰማራበት ቢያንስ ደግሞ በመደበኛው በኩል ያልሰነፈበት ተግባር ነው – ስንቱን ስናውቅ? እነዚያ ቄሶች የታሰሩት በግልጽ አማርኛ ሲሳረሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነበር – ግብረሶዶማውያን ነበሩ እያልኳችሁ ነው፡፡ መተፋፈር ዱሮ ቀረ ወንድሜ፡፡

ስለዚህ – የነአባ እንጦስማ ሚስት ማግባት ቀላል ነው፡፡ አባ ገብረ ሚካኤል የሚባሉ አሁን በማዕረገ ጵጵስና አቡነ እስጢፋኖስ የሚሰኙ እጅግ የተከበሩ ወያኔ ደግሞ አሥሬ እያገቡ የሚፈቱ መሆቸውን በቅርብ የሚያውቃቸው ሰው ነግሮኛል – ኃጢያቱ በኔ ይሁን ብያለሁ፤ እናንተ ባይሆን “አበስ(ኩ) ገበርኩ” እያላችሁ ሣር ቢጤ ባፋችሁ ያዙልኝ፡፡ አንድም ጳጳስ ከዚህ ውስልትና ነጻ የሚሆን ካለ በበኩሌ ይደንቀኛል፡፡ ከሟቹ ዱርዬ ፓትርያርክ ከጳውሎስ አንስቶ ሁሉም የሲኖዶስ አባል – ጃንደረባ(ስልብ) ካልሆኑ በስተቀር – ሴቱን እንደሸሚዝ ነው የሚለዋውጡት ይባልላቸዋል፡፡ የሰው ሚስት ሳይቀር እያፋቱ እንደሚያስቀምጡ የታወቀ ነገር እኮ ነው – ያን ታዋቂ አርቲስት ማን ነበር ባልቴት ሚስቱን ቀምቶ ባዶ ያስቀረው? ነውራቸው ተነግሮ ያልቃል እንዴ? እኔ በአንዲት ሚስት ከ30 ዓመታት በላይ ታስሬ ስኖር – በአንድ እጅ ጣት ከምትቆጠር የጥቂት ጊዜ ውስልትና ውጪ (ሸፋፋም ቢሆን ምክንያት ነበራት) – እነሱ ግን ቀዩዋን ከጠይሟ፣ ወጣቷን ቃ ካለችዋ እያማረጡ … የቀናሁ አስመሰለብኝ ይሆን እንዴ ይሄ ነገር?… ብቻ ይህን ሁሉ ጉድ መጽሐፉ አስቀድሞ ተናግሮታልና አዲስ ነገር የለም፡፡ የሚያሳዝነው ግን የእግዚአብሔርን መንገድ የሚከተል አንድም እረኛ ጠፍቶ ቤተ እግዚአብሔር የሰይጣን መናኸሪያና እንደልብ መፈንጫ መሆኗ ነው፡፡ በነዚህ አለሌዎች የምትመራ ቤተ አምልኮ ወደ ጥፋት እንጂ ወደጽድቅ መንገድ እንደማታስገባ ግልጽ ነው፡፡ እንዲያውም እስካሁን ድረስ ለይቶላት አለመጥፋቷና ምዕመናን አስልመውና ጴንጠው አለማለቃቸው ይገርመኛል፡፡ ሰው ሲጨነቅ እኮ የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ አንዳንድ ሞኝ ሰው ራሱን አንቆ የሚገድለው ወይም መርዝ ጠጥቶ ከዚህች ቆሻሻ ዓለም የሚሰናበተው ወዶ አይደለም፡፡…(በነገራችን ላይ ይህ ወሲባዊ ውስልትናና በዓለማዊነት የመጥፋት አባዜ በዘር የሚገደብ አይደለም|፡፡)

በመሠረቱ ጳጳሣትና መነኮሳት እግዚአብሔርን እያታለሉ በሰዎች ፊት እንዲህ ከሚዋረዱ የመጽሐፉን ቃል ሰምተው እያገቡ ቢኖሩ ይሻላቸው ነበር – ሊያውም በዚያም ከረጉና በአንዲት ሴት ብቻ ከተወሰኑ፡፡ ጳውሎስ የተናገረው ለሚችሉ እንጂ የሥጋ ፍላጎታቸውን መቆጣጠር ለሚያቅታቸው ወይም ፈጽሞ ለማይቻላቸው አስመሳዮች አይደለም፡፡

… ሰው ሁሉ እንደኔ ቢሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የፀጋ ስጦታ አለው፤ አንዱ እንደዚህ፣ ሁለተኛውም እንደዚያ፡፡… ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ – እንደኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው (በድንግልና እና/ወይም አለሩካቤ ሥጋ)፡፡ ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ፡፡…. የጳውሎስ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፤ 7-9

ይህ የጳውሎስ መልእክት የሚጠቁመን ምርጫ ያለን መሆናችንን ነው፡፡ ዘርን ከመተካት መለኮታዊ ትዕዛዝና ተፈጥሯዊ የተዋስቦ ህግ አንጻር ተገቢነቱ እጅግም ነው ብዬ በበኩሌ ባምንም  አለማግባት በመሠረቱ መጥፎ አይደለም፤ ማግባትም ጥሩ ነገር ነው፤ በምናብም ይሁን በእውን በአንዴ ሁለቱን መሆን ግን በጭራሽ አይቻልም፡፡ መሆንና አለመሆን በአንድ ጊዜ አንድ ቦታ ላይ የሚገኙበት ተጠየቃዊ ኹነት የለምና፡፡ እንዲያውም እሳትን በጉያ ይዞ እየነደዱ ከመኖር ይልቅ በህጉ መሠረት አንዲት አግብቶ እየተቃጠሉ ማነው እየወለዱና እየከበዱ መኖር የተሻለ አማራጭ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህን ጉዳይ በሚመለከት ሰዎች የማይችሉትን ቀምበር ለመሸከም የሚንደፋደፉትና ቅሌት ውስጥ የሚዘፈቁት ለምንድን ነው? ብለን መጠየቅ ደግሞ ይኖርብናል፡፡ ለእህል ውኃ ነው? ለክብር ነው? ለዝና ነው? ለየትኛው ክብርና ዝና? ክህነትን ያህል ትልቅ ማዕረግ፣ ጵጵስናን ያህል አቢይ መለኮታዊ ሥልጣን አፈር ድሜ አስግጦ ራስን ለማዋረድ ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ለምን አስፈለገ? አርሶና ቆፍሮ መብላት፣ ነግዶና ተቀጥሮ መሥራት እየተቻለ በእግዚአብሔር መቀለድ በምንም ሚዛን ቢለካ ከመቅለል አይተርፍም፡፡ ክህደት ነው? ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውሬን አያውቅብኝም ነው? ምንም አያደርገኝም ነው? ችግሩ ምን ይሆን? በየጥምጣሙ፣ በየጥንግ ድርቡ፣ በየካባውና ቀሚሱ ውስጥ ያለው ነገር ቢፈተሸ የእግዜርን ትግስት በእጅጉ እንድናደንቅ ያደርገናል፡፡ አዎ፣ ሞት ሲዘገይ የቀረ ይመስላል፤ ጥቂት እንፈላሰፍና – ምፅዓት የሞት ታላቅ ወንድም እንቅልፍ ደግሞ የሞት ታናሽ ወንድም ናቸው፡፡ ሁሉም ግን ጊዜያቸውን ጠብቀው መምጣታቸው አይቀርም፡፡ የማይመጡ እየመሰለን ግን ተሳስተን እናሳስታለን፡፡ ወዮ ለካህናት! ወዮ ለእረኞች! በጳውሎሳዊ ቃል “ወዮ! ቆሞ ያለ ለሚመስለው ዕቡይና ዝንጉ – የተቀመጠስ አንዴውኑ ተወዝፏል”፡፡ ትልቁን እግዚአብሔር ብንዘነጋ ትንሹን እግዚአብሔር ኅሊናችንን መርሳት የለብንም፡፡

በኛው ቤተ ክርስቲያን እንዲህ የጨከንኩ መሰልኩ እንጂ በካቶሊክም ሆነ በእስልምናውና በአይሁዳውያኑ ረገድም አጮልቀን ብናይ እውነቱ ከዚህ የተለዬ አይደለም፡፡ እኛ ጋ እነልደቱ አያሌውና እነ”አቡነ” እንጦስ ጽላት እየሸጡ እግዜርን በሰው ፊት “ሲያቀሉ”ና “ሲያዋርዱ” በአውሮፓ ደግሞ የገነት መግቢያ ካርድ(Indulgence Card?) ለምዕመናን እየሸጡ የሚከብሩና በፈጣሪ የሚቀልዱ ዚቀኛ ካህናትና ጳጳሳት ነበሩ – በመካከለኛው ዘመን አካባቢ፡፡ እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች አሁን አሁን ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገው – ጌታን በትክክለኛው መንገድ ማገልገሉን ሆን ብለው ትተውት –  ወንዶችና ሴቶች ሕጻናትን በማስገደድና በከረሜላ በማታለል መድፈር፣ እርስ በርስ በተመሳሳይ ፆታ የወሲብ ግንኙነት ተጠምደው ዲያብሎስን በሙሉ ልብ ማገልገል፣ በዘረፋና በማጭበርበር በሚያገኙት ገንዘብ የግል ሀብትን ማከማቸት… ዋና ሥራቸው በማድረግ በሥጋ ገበያ ጠፍተዋል – (አንድ የኢቫንጀሊካን ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ በጀርመን ሀገር የ42 ሚሊዮን ዶላር ቤተ መንግሥት መሰል መኖሪያ እንዳሠራና ከኃላፊነቱ እንደተባረረም ቀደም ሲል ሰምቻለሁ – ሁሉም ያው ቢሆኑም ለይምሰል ብለው በወቅቱ እርምጃ ወስደውበታል)፡፡ አብዛኛው ምዕመን በነዚህ ሰዎች ተስፋ በመቁረጥና በሕይወት ጨለምተኝነት በመሸነፍ ቤተ ክርስቲያንንና ሃይማኖትን እየተወላቸው መውጣቱን ተያይዞታል፡፡ ይህ አካሄድ ደግሞ እየገነነ ለመጣው ለሌላኛው ሰይጣናዊ ክንፍ ለአክራሪ እስልምና መስፋፋት የበኩሉን ድርሻ እያበረከተ ነው – ዛሬስ የጤና ያድርግልኝ፡፡ ምን ነካኘ ግን? ከስንቱ ጋር ነው “የምናጀሰው” በል?…

አዎ፣ እንግዲህ ያለንበት ሁኔታ በሁለትና ሦስት ዐረፍተ ነገሮች ሲገለጽ ይህን ይመስላል፡፡ በአንድ ወይ በሌላ መልክ ሁላችን ጠፍተናል፡፡ ከጠፋነው ይልቅ ደግሞ ልንጠፋ ያሰፈሰፍነው እንበልጣለን፡፡ ዓለማችንን ከያቅጣጫው ስንታዘባት አእምሮ ጠፍቶ ሕገ አራዊት የሚሉት ነገር ነግሦ እናያለን፡፡ ዓለማችን የአንድ ዓመትን ወንድ ሕጻን በቡድን የሚደፍሩ የታሊባን አክራሪ ሙስሊሞች፣ የሦስት ዓመት ወንድ ሕጻንን በቡድን የሚደፍሩና በመጨረሻ የሚገድሉ አክራሪ ሙስሊሞች በገፍ እየቀፈቀፈች ወደ ጨለማው የዲያብሎስ ግዛት ማስገባቷን ስንረዳ ምን ያህል እንደቆሸሸችና የመጽጃ ጊዜዋም ምን ያህል እንደቀረበ እንገነዘባለን፡፡ (ለነዚህ ወሬዎች ይህን ቦታ ፈልገው ያንብበቡ –  walidshoebat.com) ብዙ ጉድ እየፈላና እየተንተከተከ ነው፡፡ አይቀርልንም፡፡ እናም እንዘጋጅ፡፡

ዘረኝነትም አንዱ ከፈጣሪ የሚለየን መጥፎ ወረርሽኝ ነው፡፡ ለአንድ የሰው ልጀ ዘር ወደ ዓለም መጥቶ የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ትግሬ ወይ አማራ ወይም ኦሮሞ አልነበረም፡፡  ምንም እንኳን አንዱን የሰው ዘር መምሰል ስለነበረበት ክርስቶስ ኢየሱስ ከይሁዳዎች ዘር ቢፈጠርም ዓላማውና ግብሩ ግን ለመላው የሰው ዘር ነው፡፡ እነ መለስና አባቶቻቸው እነጳውሎስ ግን ቤተ ክርስቲያንን ለሰይጣን ማደሪያ በማድረግ ከቀደሙት አባቶች ባሱና ሕዝብን በቀበሮና በተኩላ ያስጨርሱት ገቡ፡፡ ሁሉም ዋጋቸውን ሊያገኙ ጦርነቱ መጀመሩ ተስፋ ይሆነናል እንጂ በዚህ በያዙት መንገድ ብዙ ዓመታትን መቀጠላቸው ግድ ቢሆን ኖሮ በእጅጉ እንናደድ ነበር፡፡ “ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም” የሚለቀውን የፈጣሪ ህግ አፍርሰው ከሁለት በላይ ለሆኑ ህግጋት አፈነደሱ – ለዘር፣ ለንዋይና ለሃይማኖታዊ ህፀፅ፡፡ የምድር ነገር ምድራዊ ነውና እንደጥላ ያልፋል፤ እንደጤዛም ይረግፋል፡፡ የሚቀረው ግን በቀላሉ የማይሽረው የታሪክ ጠበሳውና ስብራቱ ነው፡፡ ለወያኔ ዲያብሎስና ለእግዜር በአንዴ መገዛት እንደማይቻል ኅሊናን ትንሽ ከፈት አድርጎ ማየት ነው፤ እምብርት ላልተበጀለት ላስቲክ ሆድ ሲባል ሀገርንና ህዝብን ክዶ ለአንድ ዘረኛ ቡድን ማደግደግ ቀን ሲያልፍ ለሀፍረትና ለትልቅ ውርደት እንደሚዳርግ ማወቅ በተገባ ነበር – ጭንቅላት የለም እንጂ ቢኖር ኖሮ፡፡

ለማንኛውም ዛሬ እንዲህ ነው፤ ነገ ግን በርግጠንነት ይለያል፡፡ ተስፋ ሲሞት ሰው ይሞታል፡፡ ተስፋ ካለ ሰው አለ – እኛም አለን፡፡ ከሚተርፉት ከመደበን ጦርነቱ ሲያልቅ እንገናኝ ይሆናል፡፡ ሰላም፡፡

ቀጣዩን ነገር ከፈለጋችሁ አንብቡት – ልተረጉመው ብዬ አስቀመጥኩት – ግን ደከመኝና ተውኩት፡፡

Deviancy never resides in one desire, like murder; deviancy resonates in all desires, it becomes a part of one’s whole person. Deranged and disturbing lusts for blood resonates in one’s sexual urges, and these are always aberrant and debased. It all comes down to one’s religious beliefs. All deviancy originates from a disordered view of God. If one’s soul is loving, then that soul will treat his or her spouse with love. But if one’s soul is darkened by evil, then that person will not care for love, harmony, compassion, no, not even the natural order. Chaos is embraced, order is mutilated, and the entire divinely created system of nature is warred against. (source: walidshoebat.com)

ኢትዮጵያ አዲስ ህገ መንግስት ያስፈልጋታልን? –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

alጥያቄ ሆኖ መቅረብ ያለበት ጉዳይ ኢትዮጵያ አዲስ ሕገ መንግስት ትፈልጋለችን የሚለው አይደለም፡፡

መጠየቅ ያለበት ግን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ሕገ መንግስት የሌላት ሀገር ስለሆነች ሕገ መንግስት ትፈልጋለችን? የሚለው ነው፡፡

“የ1995 የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት” እየተባለ የሚጠራው ሕገ መንግስት በዘ-ህወሀት ለዘ-ህወሀት የተዘጋጀ የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት ነው፡፡

ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ) በአሁኑ ጊዜ ስሙ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኝ የታወቀ የማፊያ አሸባሪ ድርጅት ነው፡፡

የዘ-ህወሀት ሀሳብ የለሽ፣ ጋጠወጥ እና ድፍረት የተሞላበት አውዳሚ የፖለቲካ ዓላማ ግልጽ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ በሕገ መንግስት ተብዬው ሰነድ ውስጥ በዝርዝር ተጽፎ ይገኛል፡፡

የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት የፌዴራል እና ዴሞክራሲያዊ የመንግስት መዋቅር ለመመስረት ዓላማ ያደረገ ነው፡፡

ይኸ የፌዴራል እና ዴሞክራሲያዊ የመንግስት መዋቅር እየተባለ የሚጠራው መንግስታዊ መዋቅር አንድ እና አንድ ዓላማ ብቻ አለው፡፡ ይኸውም የፖለቲካ ስልጣኑን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ በመያዝ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ሌሎችን የፖለቲካ ቡድኖች እና ድርጅቶችን አቅም የለሽ እና ምንም ነገር ለመስራት እንዳይችሉ ሽባ በማድረግ የፖለቲካ ስልጣኑን በብቸኝነት ዘ-ህወሀት ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር ማድረግ ነው፡፡

የዘ-ህወሀት የፌዴራል ሕገ መንግስት እ.ኤ.አ መጋቢት 1953 ከሞተው እና ደም ከተጠማው  የሶቪየት ህብረት ንጹሀን ዜጎች ጨፍጫፊ ከነበረው ከጆሴፍ ስታሊን የጽሁፍ ዘዬ እና የርዕዮት ዓለም ግፊት በቀጥታ ተኮርጆ የተጻፈ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1912 በቦልሸቪክ ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው ርዕዮተ ዓለማዊ እና ድርጅታዊ ቀውስ ምክንያት እርስ በእርሳቸው የሚሻኮቱ እና በጥላቻ የተሞሉ ተቀናቃኝ ቡድኖች ተፈጠሩ፡፡ በዚያን ወቅት በቦልሸቪክ ፓርቲ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነው እና የርዕዮት ዓለም አለመስማማት ጉዳዮች ዋና መነሻ ሆኖ የቀረበው “የብሄር ጥያቄ” ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1913 ስታሊን “ማርክሲዝም እና የብሄር ጥያቄ” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ ጻፈ፡፡ በዚያ ጽሁፍ ውስጥ ለብሄር ጥያቄ ጭቆና መፍትሄው ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች እያለ ለሚገልጻቸው ሁነቶች እውንነት እውቅና መስጠት እና ይህንን ጉዳይ በቦልሸቪክ ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም ውስጥ ማካተት ነው በማለት ሞገተ፡፡

ስታሊን እያራመደ የነበረውን የክርክር ጭብጥ ለመደገፍ በማሰብ ቁስ አካል/dialectical materialism የሚለውን የማርክስን ህልዮት በመውሰድ በስራ ላይ አዋለ፡፡ ስታሊን የብሄሮች እና የብሄር መንግስታት መነሳሳት እና የብሄራዊ ንቃተ ህሊና እውን መሆን ገበያዎችን ለማስፋፋት ሲባል በቡርዥዋው መደብ የሚመራ ልዩ የሆነ የካፒታሊስት ክስተት ነው በማለት የክርክር ጭብጡን አቀረበ፡፡

እ.ኤ.አ በ1914 ሌኒን “የእራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል” በሚል ርዕስ ጽሁፍ ካዘጋጀ በኋላ የስያሜውን ምክንያት እንዲህ በማለት አቀናበረው፡ “ቡርዥዋው የሀገር ውስጥን ገበያ መቆጣጠር አለበት፣ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ዓይነት ቋንቋ መናገር የሚችሉ ህዝቦች እና የፖለቲካ መስተጋብርን የፈጠሩ ግዛቶች መኖር አለባቸው፡፡”

በቅድመ ካፒታሊስት (ፊውዳሊስት) ማህበረሰብ  ውስጥ የጋራ የሆነ የጎሳ፣ የቋንቋ ወይም ደግሞ ባህልን መሰረት ያደረገ እውነተኛ ብሄራዊ የህብረተሰብ ንቃተ ህሊና አልነበረም፡፡ ቅድመ ካፒታሊስት ማህበረሰቦች የሚታወቁት በአጠቃላይ በፊውዳሉ የስልጣን ተዋረድ መሰረት የመንደሮች፣ የከተሞች እና የአካባቢዎች ባለስልጣኖች እና በይበልጥም ደግሞ በግዛቱ ውስጥ ያለውን መሬት በሙሉ ጠቅልሎ ለመያዝ ስልጣን ያለው ንጉሰ ነገስቱ ያሉበት ስርዓት የነበረ መሆኑ ነው፡፡

የካፒታሊስት ስርዓት ማቆጥቆጥ እና በቀጣይም የቡርዥዋው ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ አብዮት መከሰት ለብሄር መንግስታት መመስረት እና የብሄራዊ ንቃተ ህሊና እና የማንነት ጥያቄ መዳበርን አስከተለ፡፡ እንደ ስታሊን አስተሳሰብ ጥቂት የምዕራብ አውሮፓ መንግስታት የብሄር ጥያቄን አስወገዱ ምክንያቱም በካፒታሊስቱ አብዮት ጊዜ የብሄር መንግስታትን አቋቁመው ነበርና ነው፡፡ በምስራቅ አውሮፓ ቀደም ሲል የነበሩ ግዛቶች ለምሳሌ ያህልም የአውስትሮ ሀንጋሪ ግዛት የጎሳ ቡድኖች በአንድ የብሄር መንግስት ውስጥ ከመምጣታቸው እና የብዙ ብሄሮች መንግስታት ችግር ከመፈጠሩ በፊት ተከስቶ ነበር፡፡

የብሄር ጥያቄን ትንታኔ ለመስጠት ስታሊን የእራሱን የብሄር ትርጉም ሰጠ፡፡ እንዲህ በማለት ሞገተ፣ “ብሄር ቋንቋን፣ ግዛትን፣ የኢኮኖሚ ህይወትን እና የስነልቦናዊ ዘይቤን በማካተት የጋራ ባህልን መሰረት በማድረግ ታሪካዊ በሆነ መንገድ የተመሰረተ፣ የተረጋጋ ማህበረሰብ ነው፡፡“ እንዲህ የሚል አጽንኦም ሰጥቷል፣ “እነዚህ ሁሉ ባህሪያት በአንድነት ሲኖሩ ብቻ ነው ብሄር የሚኖረን፡፡“

እንደ ስታሊን እና ሌኒን ያሉ ጽንፈኛ የቮልሸቪክ አመራሮች ባሉባት ሩሲያ የሩሲያ የብሄር ጥያቄ (በሩሲያ ግዛት የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጭቆና) አስቸጋሪ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡

የሩሲያ ግዛት ሌኒን እንዳለው በርካታ ትናንሽ ብሄሮችን ወይም ደግሞ ህዝቦችን ማለትም ዩክሬኖችን፣ ፖሎችን፣ አርመኖችን፣ አዘርባጃኖችን፣ ፊኖችን፣ ጆርጃዎችን፣ ወዘተ አካትቷል፡፡ ሌኒን በሩሲያ ግዛት ውስጥ የብሄራዊ ነጻነት ንቅናቄዎችን በመደገፍ ብሄሮች ፍጹም አብዮታዊ በሆነ መልኩ የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል ጥያቄ እንዲያራምዱ ይቀበላል፣ ይደግፋልም፡፡ ሌኒን እንዲህ በማለት ይሞግታል፣ “በእኛ የፖለቲካ ቅስቀሳ የመገንጠል ጥያቄ መብትን መፈክር ለማራመድ እና ለመወትወት የማንችል እና የምንወድቅ ከሆነ በእጆቻችን ለቡርዣዎች እያጨበጨብን ብቻ አይደለም ያለነው፡፡ ሆኖም ግን ይህንን እያደረግን ያለነው ለፊውዳሎች እና ፍጹም ጨቋኝ ለሆነው ብሄር ጭምር እንጂ፡፡“ ከዚህም በተጨማሪ ሌኒን በቡርዥዋ ብሄራዊነት ስር ያለውን የብሄሮችን እና ብሄረሰቦችን ጭቆና ለማጥፋት ከሌላ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከሚጠየቅ አካሄድ የተለየ መሆን እንዳለበት ያምናል፡፡ በኋላ ግን ስታሊን ስሌታዊ በሆነ መልኩ እንዲህ በማለት ብዙ ጽፏል፡፡ “የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል መርህ ለሶሻሊዝም ስርዓት ግንባታ ለሚደረገው ትግል እንደ መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል እና ለሶሻሊዝም መርሆዎችም ተገዥ ሆኖ ሊያገልግል ይችላል“ ብሏል፡፡

ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና የማርክስ ህልዮት አቀንቃኝ የሆነችው ሮሳ ሉክስምበርግ የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚለው የሰራተኛው መደብ ትግል አስፈላጊ አይደለም በማለት ከሌኒን መርህ ጋር አትስማማም፡፡ ምክንያቱም ትላለች ምክንያቱም ያ አደሀሪ አካሄድ ነው፣ ይልቁንም የተጨቆኑ ብሄሮች ለባህል ነጻነት ዓላማ አድርገው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ ሉክሰምበርግ ሶሻሊስቶች ለዓለም አቀፋዊ የሰራተኞች ትብብር እንጂ ለብሄራዊ ነጻነት መታገል የለባቸውም ትላለች፡፡

ስታሊን እና ሌኒን “የብሄር ጥያቄ” በእራሳቸው አብዮት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን እንደምታ ተገንዝበዋል፡፡ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ሁለት አደገኛ ሁኔታዎችን አስተውለዋል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) አብዮትን ሊያጠፋ ይችላል፡፡ የሩሲያ ግዛት ፌዴራላዊ የአወቃቀር ዓይነት ያለው እንዲሆን እና የጥገናዊ ለውጥ አራማጅ በሆኑት በርካታ ብሄራዊ ፓርቲዎች የተደራጀ እና የሚመራ ስርዓትን ሊያቋቁሙ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነቶቹ የበርካታ ፓርቲ ስርዓት የእራሱን አብዮታዊ ባህሪነት በማሳጣት የነበረውን የሩሲያን የጭቆና አገዛዝ እንደነበረው ሊያስቀጥል ይችላል፡፡

2ኛ) የአብዮታዊ ሶሻሊስት ጉጉትን ውስጣዊ ስሜት በጨቋኙ የሩሲያ ግዛት ተሞክሮዎች የመተካት ወይም ደግሞ አንድ ላይ የማቀላቀል እውነተኛ አደጋ ነበር፡፡

በመጨረሻም ስታሊን እና ሌኒን የቦልሸቪክን አብዮት ለማፋጠን እና ስልጣንን በአስተማማኝ ሁኔታ ተቆጣጥሮ ለመቆዬት እንዲቻል የሩሲያን ግዛት ማፈራረስ እና ሕዝቡንም በብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መከፋፈል አስፈላጊ ነበር በማለት ደመደሙ፡፡

የብሄር ጥያቄን ለብሄራዊ የቡርዥዋ ጭቆና እና የባህል፣ የቋንቋ መብቶች ጭቆናን ከብዙ በጥቂቱ በማሳየት እንደ መደብ ትግል እንዲያገለግል ፈልገዋል፡፡

የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት አንቀጽ 39፣

የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት አንቀጽ 39 (1) (የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች መብት) የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፡

በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄር፣ ብሄረሰብ እና ሕዝብ የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል መብት አለው ይላል፡፡

አንቀጽ 47 የፌዴራል ዴሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ አባል መንግስታትን በሚከተለው ቅደምተከተል መሰረት አስቀምጧል፡

1ኛ) የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

2ኛ) የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

3ኛ) የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

4ኛ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

5ኛ) የሶማሊ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

6ኛ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

7ኛ) የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

8ኛ) የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

9ኛ) የሐረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

ከዚህም በተጨማሪ ድሬዳዋን እና አዲስ አበባን የፌዴራል ከተሞች በማለት ለየብቻ የከተማ አስተዳደር በማለት አዋቅሯቸዋል፡፡

አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ቦልሸቪኮች የሩሲያን የግዛት አንድነት እንዳፈራረሱት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በማፈራረስ ስልጣኑን ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ከስታሊን እና ከሌኒን ጽሁፎች ስለብሄር ጥያቄ እና የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚሉ ጠቃሚ የሆኑ ትምህርትችን ወስዶ በተግባር አውሏል፡፡

ቦልሸቪክ በሩሲያ ግዛት “የመደብ ትግል” እያለ የሚጠራውን ሀሳብ አምባገነኑ መለስ እንዳለ በመኮረጅ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ለኢትዮጵያ ግዛት “የጎሳ ትግል” እንዲተከል እና ዜጎች እርስ በእርሳቸው በጥርጣሬ እንዲተያዩ፣ የጥላቻ መንፈስ እንዲዘራ፣ ሀገራዊ ስሜት ጠፍቶ መንደርተኝነት እና ጎጠኝነት እንዲንሰራፋ በማድረግ ሀገርን እንዲያፈራርስ እሾሁን ተክሎ እና መርዙን ረጭቶ ተሰናብቷል፡፡

እንደ መለስ/ዘ-ህወሀት የዘልማድ ሀሳብ ትረካ “የኢትዮጵያ ግዛት” በተቀናቃኝ ፊውዳል የአማራ ነገስታት፣ መሳፍንት እና መኳንንት መካከል ለስልጣን የበላይነት እርስ በእርስ በተደረገ ትግል በ19ኛው ክፍለ ዘመን እውን ሆኗል፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ አጼ ቴዎድሮስ በሰሜን ኢትዮጵያ የሀገሪቱ ክፍል እራሳቸውን ንጉሰ ነገስት (የንጉሶች ሁለ ንጉስ) ብለው በመሰየም በሰራዊታቸው እየታጀቡ አዳዲስ መሬቶችን እየተቆጣጠሩ ወደ ደቡብ በመዝመት ብሄር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦችን አስገብረው ግዛታቸውን አስፋፍተዋል፡፡ የአጼ ቴዎድሮስን መሞት ተከትሎ ዳግማዊ  አጼ ምኒልክ ስልጣን በመያዝ ጦራቸውን በመምራት በርካታ መሬቶችን የተቆጣጠሩ ሲሆን ብዙ ብሄሮች፣ ብሄሮች እና ህዝቦችን አስገብረዋል ይላል፡፡

እንደ ዘ-ህወሀት አፈ ታሪክ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ፍጹም የተለያዩ “ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች”  በኃይል እና ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ አንድ እንዲሆኑ የተደረገ ጥረት ውጤት ናት፡፡

እ.ኤ.አ በ1993 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ እና የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፈላጭ ቆራጭ መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ቃለ መጠይቅ ላቀረበለት ጋዜጠኛ “ኢትዮጵያ የ100 ዓመት እድሜ ብቻ አላት:: ከዚህ ውጭ ሌላ ታሪክ የሚያራምዱ ካሉ እነርሱ እራሳቸውን ወደ አፈታረክ ጨምረዋል” ነበር ያለው፡፡

ስታሊን እና ሌኒን የብሄር ጥያቄን የቦልሸቪክ ፓርቲ ወደ ስልጣን እንዲወጣና የበላይነቱን እንዲያረጋግጥ እንደተጠቀሙበት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አምባገነኑ መለስ እና ዘ-ህወትም የብሄር ጥያቄን የተጨቆኑ ብሄረሰቦች በኃይል እና ጭካኔ በተመላበት መልኩ በኃይል አንድ እንዲሆኑ በማሳመን ስልጣናቸውን በማጠናከር እና የበላይነታቸውን በማረጋገጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

የተጨቆኑ ብሄረሰቦችን ችግር ለመፍታት ዘ-ህወሀት እንደ መፍትሄ የተጠቀመበት የጎሳ ፌዴራሊዝምን ሕገ መንግስታዊ እንዲሆን በማድረግ እራሳቸውን ነጻ በማውጣት የፖለቲካ፣ የባህል፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ወዘተ ድልን በመቀዳጀት ነጻ እና የራሳቸውን መንግስት ይመሰርታሉ የሚል ነበር፡፡

ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝምን በመሸጥ የተጨቆኑ ብሄረሰቦችን አታሏቸዋል፡፡ አምባገነኑ መለስ እና ዘ-ህወሀት ስለተጨቆኑ ብሄረሰቦች ደንታ አልነበራቸውም፡፡ ዘ-ህወሀት አንዱ እና ዋናው ፍላጎቱ ሆኖ የቆየው እና አሁንም ተጠናውቶት የሚገኘው የበላይ የመሆን አባዜ ነው፡፡

በእርግጥ ዘ-ህወሀት ስለ ብሄር ጥያቄ የሚያሰማው የከበሮ ጩኸት እውነተኛውን እና የተደበቀውን ነገር ሳይታወቅ ሰውሮ ለማቆየት ነው፡፡

የዘ-ህወሀት አጀንዳ ሶስት ዓላማዎችን ያካትታል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ዓላማው ለዘለቄታው በስልጣን ላይ ለመቆየት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ገዥዎች በመሆን እራሳቸውን መከላከልን ማረጋገጥ፣

2ኛ) ኢትዮጵያውያንን በጎሳ፣ በአካባቢያዊነት፣ በቋንቋ፣ በባህል እና በኃይማኖት መስመር በመከፋፈል የእነርሱን አገዛዝ የሚቃወሙትን ሁሉንም ተቃዋሚዎች የማዳከም እና ሽባ የማድረግ ዓላማ፣

3ኛ) “አማራዎች” ተመልሰው ወደ ስልጣን እንዳይመጡ እና አማራ ያልሆኑትን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦችን መልሰው ባሪያ እንዳያደርጓቸው ምናባዊ የሆነን የአማራን የጭራቅነት ሸፍጥ ፈጥሮ እና ፈብርኮ በማሳየት ለተጨቆኑ ብሄረሰቦች ተከላካይ ሆኖ የመቅረብ የአታላይነት ተውኔትን ማቅረብ ነው፡፡

ቀላል በሆነ መንገድ ለመግለጽ ዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝምን እንደ ሽፋን በመጠቀም ሆኖም ግን በድብቅ የማዕከላዊ መንግስቱን በመቆጣጠር እና በማጦዝ በሚስጥር በመንግስት ላይ መንግስት (ማፊያ አላልኩም) ለማቋቋም የሚያስችል ሕገ መንግስት አረቀቀ፡፡

አጠቃላይ የብሄር ጥያቄ ለአምባገነኑ መለስ እና ለዘ-ህወሀት ለዘላለማዊ የፖለቲካ የበላይነት ሲባል የህዝብን ቀልብ ለማስቀየስ እየተጠቀሙበት ያለ ታማኝነት የሌለው ሸፍጥ እና ተራ የማጭበርበር ዘዴ ነው፡፡ እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የዘ-ህወሀት ዋናው እና ቁልፉ ተልዕኮ ለሁልጊዜ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ማፈራረስ እና ማውደም ነው፡፡

የእነርሱ ዋናው መሪ ዕቅዳቸው በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እምነት የሌለው ማንም ኢትዮጵያዊ በእራሱ መሬት ላይ መኖር ይችላል፡፡ ዘ-ህወሀት ሌት ቀን እንደበቀቀን እየደጋገመ ለሚለፈልፍለት ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችን እና ሕዝቦችን ነጻ ለማውጣት ምንም ዓይነት ዕቅድ የለውም፡፡ ዘ-ህወሀት አንድ ጊዜ ስልጣን ከያዘ በኋላ የኢትዮጵያን ግዛት የተጨቆኑ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦችን ነጻ በማውጣት አስተባብራለሁ በሚል ማታለያ ለስልቱ ተግባራዊነት እንዲረዳው የብሄር ጥያቄን በማንሳት በማራገብ ላይ ይገኛል፡፡ ዋናው ዓላማቸው ግን አዲስ ስርዓት በመፍጠር የዘ-ህወሀትን ግዛት መመስረት ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ማንም ቁንጮ የዘ-ህወሀት ባለስልጣን አሁን በህይወት የሌለውን አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ጨምሮ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይም ደግሞ ኢትዮጵያን እወዳለሁ” በማለት የተናገሩት ካለ መቸውንም ጊዜ ቢሆን በኦዲዮ ወይም በቪዲዮ የተቀረጸ ማስረጃ አቀርባለሁ የሚል ሰው ካለ ፊት ለፊት ለመሞገት ዝግጁ ነኝ፡፡)

የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት በታሪክ አንዱ እና ዋናው የማጭበርበሪያ እርባናየለሽ ሰነድ ነው፡፡

እንዲህ የሚለው የብሩክሊን ድልድይ (ማለትም ላም አለኝ በሰማይ) የማጭበርበር ሸፍጥ ሁለተኛ ሊሆን ይችላል፡

“ ሄሎ ጌታዬ! እዚህ ያለውን አስደሳች እና ቀልብን የሚገዛ ድልድይ ሊገዙት ይችላሉን? ለዛሬ ብቻ በሽያጭ ላይ ይቆያል፡፡ ድልድዩን ለማቋረጥ ስለሚከፈለው ገንዘብ እስቲ ያስቡ፡፡“ ግራ የተጋበው ሰውዬ እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጠ፣ “እርግጠኛ ነህ ይኸ ድልድይ ይሸጣል?“  ሰውየው እንደገና እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጠ፣ “ታዲያ ለምን ይመስልሃል ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ  የተለጠፈበት?” አለ፡፡ ዘ-ሀወሀትም በብሄር ጥያቄ ስም ያደረገው ይህንኑ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም የብሩክሊን ድልድይን ለተጨቆኑ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ሸጧል፡፡ ይኸ የሚገኘው ከዘ-ህወሀት ብቻ ነው ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ በጎሳ ፌዴራሊዝም መኖር የምታገኙትን ነጻነት እስቲ አስቡት በማለት የዘ-ህወሀት ሸፍጠኛ አታሎች በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡

ያለምንም ጥርጥር የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት በአፍሪካ ውስጥ ከተጻፉት ሕገ መንግስቶች ሁሉ ታላቅ ማጭበርበር እና ሸፍጥን ያካተተ መናኛ ዉዳቂ ሰነድ ነው፡፡

የዘ-ህወሀት ሸፍጠኛ አጭበርባሪዎች ላለፉት 25 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ የተጨቆኑ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማታለያ የሸፍጥ ስም የማይነጥፍ ያጋተ የላም ጡት ወተትን በመጥባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ዘ-ህወሀት የሌኒንን አባባል በመዋስ የተጨቆኑ ህዝቦችን ከኢትዮጵያ ግዛት የብሄረሰቦች እስር ቤት ነጻ ለማውጣት ለ25 ዓመታት ያህል የሸፍጥ ህገ መንግስታቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡፡

በማስመሰያው ህገ መንግስት ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር እየተባለ የሚጠራ የማጭበርበሪያ እና የሸፍጥ ግንባር በመፍጠር የአማራ ጭቆና ሰለባ የሆኑትን ነጻ እናወጣለን በማለት በማደናገር፣ ልክ ስታሊን እና ሌሊን እንዳደረጉት ሁሉ ዘ-ህወሀትም በተመሳሳይ መልኩ የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚለውን መብት አረጋግጠዋል፡፡ ይህም ማለት ከኢትዮጵያ መንግስት ጥላ ስር በማንኛውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ በመገንጠል የእራስን መንግስት ማቋቋም ይቻላል የሚል ሆኖ ይገኛል፡፡ እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን ዘ-ህወሀት የእራሱን የፖለቲካ የበላይነት ለማቀላጠፍ እና ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ እንድትበጣጠስ የማድረጉ እውነታ ነው፡፡

እንደ ስታሊን ሁሉ አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፈላጭ ቆራጭ መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በየትኛውም መለኪያ የማይገናኙትን እና የማይዛመዱትን የጎሳ ቡድኖች በአንድ የጎሳ ግዛት ቅርጫት ውስጥ እንዲታጨቁ አደረገ፡፡ አምባገነኑ መለስ እና ዘ-ህወሀት የራሳቸውን የሸፍጥ የጎሳ ፌዴራሊዝም ለመፍጠር ያለምንም ሙያዊ ጥናት በዘፈቀደ የሸፍጥ የይስሙላ የድንበር ወሰኖችን ፈጥረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህልም በንጉሱ የአገዛዝ ዘመን የትግራይ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩት ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም አሁን በቅርቡ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት በሰጡት ቃለ መጠይቅ በትግራይ እና በቤጌምድር መካከል የነበረው ታሪካዊ የወሰን ድንበር የተከዜ ወንዝ ነበር፡፡ እናም ወልቃይት ጠገዴ መቸውንም ጊዜ ቢሆን በትግራይ አስተዳደር ውስጥ ገብቶ አያውቅም በማለት ቃለ መጠይቅ ሰጥተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በዘ-ህወሀት ህገ መንግስታዊ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የግዛት ምቹነት፣ የባህል፣ ወዘተ መስፈርት እንኳ ቢሆን ወልቃይት ጠገዴ በአማራ ክልል ውስጥ ሊካለል ይገባል፡፡ (እንዲያው ለታሪክ ያህል፡ በኢትዮጵያውያን ላይ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ወዘተ እየተባለ የመለያ ባጅ በመለጠፉ ዕኩይ ተግባር ላይ እምነቱ በፍጹም የለኝም፣ ከዚህ ቀደምም የለኝም ወደፊትም አይኖረኝም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመረጠው ቦታ የመኖር፣ ስራ የመስራት እና ቤተሰብ የመመስረት ፍጹም የሆነ መብት እንዳለው ሙሉ በሙሉ አምናለሁ፣ ለዚህም ተግባራዊነት በጽናት እታገላለሁ፡፡)

ላለፉት 25 ዓመታት ዘ-ህወሀት የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መፈክርን በማራገብ ውጤታማ በሆነ መልኩ ጥቂት ሰዎችን ለብዙ ጊዜ፣ አብዛኛውን ህዝብ ደግሞ ለጥቂት ጊዜ ለማታለል ተጠቅሞበታል፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም ህዝብ ለሁልጊዜ ሊያታልል አልቻም፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የተጨቆኑ ብሄሮች እና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እየተባለ ሌት ቀን እንደሚደሰኮረው ሳይሆን መቸውንም ጊዜ ከጭቆና ነጻ ሆነው አያውቁም፡፡ ዘ-ህወሀት በጎሳ ፌዴራሊዝም ስም ዝም ብሎ በተግባር የማይገለጽ የይስሙላ ነጻነት ፈቅዷል፡፡

እንደስታሊን ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አምባገነኑ መለስ እና ዘ-ህወሀት የእነርሱን አገዛዝ የሚቃወመውን እና የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚለውን የይስሙላ መብት ለመጠቀም የሚሞክረውን ቡድን ወይም ግለሰብ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ይጨቁናሉ፡፡

ሚሊዮኖችን እንዳጋዘው እንደ ስታሊን ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና ዘ-ህወሀትም የአማራ ሰፋሪዎችን ህገ ወጥ ሰፋሪዎች በማለት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙትን በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች እንዲጋዙ አድርገዋል፡፡

ዘ-ህወሀት የጋምቤላን እና የሌሎች አካባቢዎችን ህዝቦች በመንደር ማሰባሰብ በሚል ፈሊጥ ከቀያቸው በገፍ በማፈናቀል ከቀደምት አባቶቻቸው ጀምረው ሲጠቀሙበት የነበረውን መሬታቸውን እየነጠቁ ዓለም አቀፍ ለሆኑ አየር በአየር ነጋዴዎች የመሬት ቅርምት ሸፍጠኞች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ሲቸበችቡት ቆይተዋል፡፡

ዘ-ህወሀት ከአማራ አስፈሪ ጭራቅ ለመጠበቅ የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል ለሚለው ዕኩይ መርሆው እራሱን መልዓክ አድርጎ በማቅረብ ለመከላከል ይሞክራል፡፡ ዘ-ህወሀት የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚለውን ዕኩይ መርሆውን አማራን ለማሸማቀቅ እና አማራው በሀገር አንድነት እና ነጻነት ላይ ያለውን ቀናኢነት ለማዳከም በማስፈራሪያነት እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ብሄሮች እና ብሄረሰቦች በመጨቆን የግዛት ዕድሜውን ለማራዘም ይሞክራል፡፡

የዘ-ህወሀት ምዕናባዊ ጭራቅ ኢትዮጵያን በማሳደድ ላይ ነው፡፡ በኮሙኒስት ማኒፌስቶው ላይ የተቀመጠውን የማርክስን አባባል በመዋስ “ ይህንን እርኩስ መንፈስ ለማርከስ እና ፈውስን ለማምጣት ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረግ አለባቸው፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በማዕከል በእራሱ ቁጥጥር ስር በማዋል ስልጣን አልባ አድርጎ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት በማንኛውም ረገድ የፌደራል ስርዓት መዋቅሩን በበላይነት ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ምድር ላይ መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ወታደራዊ ኃይል፣ የደህንነቱን እና የፖሊስ መዋቅሩን  መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት ኢኮኖሚውን መቶ በመቶ በመቆጣጠር በደጋፊዎቹ እየታገዘ በመመዝበር የእራሱን የክሮንይ (crony) ካፒታሊዝም ስርዓት ፈጥሮ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት ቢሮክራሲውን እና የፍትህ ስርዓቱን መቶ በመቶ በእራሱ ቁጥጥር ስር አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ የውሸት ግዛት የሚበሳጩ ኢትዮጵያውን እውነተኛው እና ድብቁ የዘ-ህወሀት ግዛት መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ባምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና ወሮበላ የደናቁርት ስብስብ ጓዶቹ የጥላቻ አእምሮ የተፈጠረው የኢትዮጵያ ግዛት በፍጹም ህልውና የለውም፡፡

ያለምንም መደበቅ እውነተኛው ግዛት ግን የጥላቻ ግዛት፣ የኢፍትሀዊነት ግዛት፣ እኩልነት ያለመሆን ግዛት፣ የሙስና ግዛት እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ የመጠቀም የዘ-ህወሀት ግዛት ነው፡፡

የጎሳ ፌዴራሊዝም እና ዴሞክራቲክ ሬፐብሊክ እያለ ቢጮህም ዘ-ህወሀት በምዕናባዊዋ ኢትዮጵያ እውነተኛ እና ህልውና ያለው የዘ-ህወሀት ግዛትን በፈጠረው ሕገ መንግስት ለማቋቋም በቅቷል፡፡

እውነት ኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ትፈልጋለችን? 

ያለምንም ጥርጥር አዎ ትፈልጋለች! ያስፈለጋታለም!

ኢትዮጵያውያን በህዝብ የተዘጋጀ ለህዝብ የሆነ ሕገ መንግስት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ኢትዮጵ እንዲህ በሚሉ ቃላት የሚጀምር ሕገ መንግስት ትፈልጋለች፡ “እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች ፍጹም የሆነ አንድነትን ለመፍጠር…

ኢትዮጵያ ህዝቧን አንድ የሚያደርግ እና በህዝቦች መካከል ፍጹም የሆነ ፍቅር እና አንድነት እንዲፈጠር ትፈልጋለች፡፡

ለመሆኑ ፍጹም የሆነ አንድነት ማለት ምን ማለት ነው?

ለእኔ ፍጹም የሆነ አንድነት ማለት ስለግዛት አንድነት ጉዳይ አይደለም፡፡

ይልቁንም “ፍጹም የሆነ አንድነት” ማለት የኢትዮጵያ ህዝቦች የልብ እና አእምሮ አንድነት ማለት ነው፡፡

ኢትዮጵውያን በ40 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የአውሮፓን ኃይል ወታደራዊ ወራሪ ሰራዊት ሁለት ጊዜ በማሸነፍ ከቅኝ ገዥዎች የበላይነት እራሳቸውን ነጻ አድርገዋል፡፡ ምክንያቱም በልብ እና በአእምሯቸው አንድ ነበሩና ነው፡፡

በቅኝ ግዛት ሲሰቃዩ ለነበሩ ህዝቦች ሁሉ ኢትዮጵያውያን ለመላው የአፍሪካ ህዝብ የነጻነት ቀንዲል ተምሳሌት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ምክንያቱም በአንድ አእምሮ እና ልብ አንድ ሆነው ተነስተው ነበርና፡፡

ኢትዮጵያውያን በዘረኝነት እና በአድልኦ በመሰቃየት ላይ ላሉት ለአፍሪካ አሜሪካውያን ቤዛ ሆነዋል፡፡ ምክንያቱም ህዝብ እንደ አንድ ሆኖ ከተባበረ በምንም ዓይነት መንገድ ሊሸነፍ እንደማይችል በተግባር አረጋግጠዋልና፡፡

ኢትዮጵያውያን የነጻነት ቀንዲል መሆናቸው በጥቂት ታላላቅ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ገጣሚዎች ተወድሰዋል፡፡ ምክንያቱም እንደ አንድ ህዝብ ሆነው በመቆም በደም፣ በአጥንት፣ በላብ እና በእንባ መስዋዕትነት የሀገራቸውን ነጻነት ጠብቀዋልና፡፡

ለመሆኑ በኢትዮጵያ ህዝቦች አእምሮ እና ልብ ውስጥ እንዴት አድርግን ነው ፍጹም የሆነ አንድነት ለመፍጠር የምንችለው?

ጉዳዩ ቀላል ነው!

በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ፍጹም የሆነ አንድነት ለመፍጠር እኛ ህዝቦች (እያንዳንዳችን) ያለምንም መታከት ጠንክረን በመስራት የሕግ የበላይነትን፣ የኢትዮጵያን ህዝቦች ሰብአዊ መብት አጠባበቅ (የመናገር ነጻነት፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የኃይማኖት ነጻነት፣ ቅሬታን የመግለጽ መብት፣ የመሰብሰብ መብት፣ ወዘተ) መጠበቃቸው እና መከበራቸውን ማረጋገጥ አለብን፡፡

በስልጣን እና በኃላፊነት ቦታ ላይ ባሉ ባለስልጣኖች ላይ ፍጹም የሆነ የሕግ ተጠያቂነት መኖሩን፣ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ መኖሩን፣ የንብረት ባለቤትነት መብት በተለይም የመሬት ባለቤትነት መብት መጠበቁን እና መንግስት በንብረት የባለቤትነት መብት ላይ ጣልቃ እንዳይገባ በሕገ መንግስቱ መታገዱን እንዲሁም ጠንካራ እና ነጻ የሆነ የፍትህ ስርዓት መኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡

በኤሜሪካ በሲቪል መብቶች የትግል ምዕራፍ ወቅት መሪዎች የአንድነትን ጠቃሚነት እስከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ ለማስረዳት አምስቱን ጣቶቻቸውን በተመሳስሎ ይጠቀሙ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ኢትዮጵያውን ፍጹም የሆነ አንድነት ለመፍጠር በሚሰሩበት ጊዜ ከእነዚህ ተመሳስሎዎች በርካታ ቁምነገሮችን ሊማሩ ይገባል፡፡

በእያንዳንዱ እጅ ላይ አምስት ጣቶች አሉ፡፡ በሁለቱም እጆች ያሉት አስሩም ጣቶች በተናጠል ለየብቻቸው ሲዘረጉ ምንም ዓይነት ኃይል ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡

አስሩም ጣቶች ታጥፈው በአንድነት ቡጢን ከፈጠሩ ግን ለጠላት የማይበገሩ መሳሪያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ከእያንዳንዱ እጅ አንድ ጣት የሚነሳ ከሆነ በቡጢው ውስጥ ያለው አብዛኛው ኃይል ይቀንሳል፡፡

ሁለተኛው ጣት ከእያንዳንዱ እጅ ላይ የሚነሳ ከሆነ በቡጢው ላይ ያለው ሁሉም ኃይል ሙሉ በሙሉ ይጠፋል፡፡

ላለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአምባገነኑ እና በእብሪተኛው ዘ-ህወሀት በመጥረቢያ የመከተፍ፣ የመበጣጠስ፣ የባንቱስታናዊነት እና ክልላዊነት እኩይ ምግባሮች ሁሉ ተፈጽመውባቸዋል፡፡

ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን የተባበሩትን የጣቶች ቡጢ ኃይል በማድነቅ ታሪካቸውን እንደገና መለስ ብለው ማየት ይኖርባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ጣቶቻቸውን ሲያጥፉ እና ቡጢን በመፍጠር አንድ በሚሆኑበት ጊዜ ኃይለኛ የተባሉትን ጠላቶቻቸውን ድል ያደርጋሉ፡

ታሪክ እንዲህ በማለት ያረጋግጥ፡

ኦሮሞዎች ሀገራቸውን የወረረውን አንዱን ኃያል  የአውሮፓ (ጣልያን) ወራሪ ኃይል ብቻቸውን ድል አላደረጉትም፡፡

አማራዎች ሀገራቸውን የወረረውን አንዱን ኃያል የአውሮፓ (ጣልያን) ወራሪ ኃይል ብቻቸውን ድል አላደረጉትም፡፡

ትግራውያን ሀገራቸውን የወረረውን አንዱን ኃያል የአውሮፓ (ጣልያን) ወራሪ ኃይል ብቻቸውን ድል አላደረጉትም፡፡

ጉራጌዎች ሀገራቸውን የወረረውን አንዱን ኃያል የአውሮፓ (ጣልያን) ወራሪ ኃይል ብቻቸውን ድል አላደረጉትም፡፡

አፋሮች ሀገራቸውን የወረረውን አንዱን ኃያል የአውሮፓ (ጣልያን) ወራሪ  ኃይል ብቻቸውን ድል አላደረጉትም፡፡

ኢትዮጵያውያን  ሀገራቸውን የወረረውን አንዱን ኃያል የአውሮፓ (ጣልያን) ወራሪ ኃይል ብቻቸውን ድል አላደረጉትም፡፡

ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ትግራውያን፣ ጉራጌዎች፣ አፋሮች፣ ኦጋዴናውያን፣ ሀረሪዎች፣ ጋምቤላውያን እና ሌሎች ሁሉም በደቡብ፣ በሰሜን፣ በምስራቅ እና በምዕራብ ኢትዮጵያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንደ አንድ ህዝብ ሆነው ሀገራቸውን የወረረውን ታላቅ የአውሮፓ ወራሪ ኃይል (ጣልያን) ድል ለማድረግ በቁ፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ እያንዳንዳቸው በተናጠል በመዋጋት ዘ-ህወሀትን ድል ሊያደርጉ አይችሉም፡፡

እንደ አስሩ ጣቶቸ ሁሉ በየስራ መስኩ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ወደ አንድ በመምጣት ቡጢያቸውን በማጠናከር ኃያል የተባለውን የአውሮፓ ወራሪ ኃይል ድባቅ ለመምታት በቅተዋል፡፡

ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ላይ የጫናቸው 9ኙ ጣቶች (ክልሎች) በአሁኑ ጊዜ ወደ አንድ ቡጢ በመምጣት ለዘ-ህወሀት ትምህርት ሊሰጥ የሚችል ምት መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሕገ መንግስታዊ ወሮበላ እና ዘራፊነትን አይፈልጉም፡፡

ኢትዮጵያውያን የሰው ልጆችን ዘር አጥፊ እና የአእምሮ በሽተኛ በሆነው በጆሴፍ ስታሊን አእምሮ ውስጥ የበቀለ ሕገ መንግስትን አይፈልጉም፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለቄታው አንድነትን የሚያጠፋ፣ ጥላቻን የሚዘራ፣ ልዩነትን የሚፈጥር እና የሚበታትን መሪ ዕቅድ እና ሰነድ የያዘ ሕገ መንግስት አትፈልግም፡፡

ኢትዮጵያ የፖለቲካ መከፋፈልን፣ የስልጣን ማዕከላዊነትን፣ የህብረተሰብ ክፍፍን እና ህዝቦች በመልክዓ ምድር እና በግዛት እየተሸነሸኑ ለጨቋኝ አገዛዝ በሚመች መልኩ የሚበጣጠሱበትን መንገድ አትፈልግም፡፡

ኢትዮጵያ እኩልነትን፣ ወንድማማችነትን/እህትማማችነትን እና ነጻነትን መሰረት ያደረገ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ አንድ ብሄር፣ እንደ አንደ ብሄረሰብ እና እንደ አንድ ህዝብ የሚያስተሳስር ሕገ መንግስት ትፈልጋለች፡፡

ኢትዮጵያን ለማዳን የሚደረግ ትግል፡

ለእያንዳንዱ የኢትዮጵያ የጎሳ ቡድን እውቅና የሚሰጥ ሕገ መንግስት ሳይሆን የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ሰው የመሆን መብት የሚያረጋግጠው ሕገ መንግስት በኢትዮጵያ እውን እንዲሆን አልማለሁ፡፡

ኢትዮጵያውያን የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች አባል ከመሆናቸው በፊት በእግዚአብሄር አምሳል ነጻ ሆነው የተፈጠሩ ህዝቦች እንደሆኑ አምናለሁ፡፡ የኢትዮጵያውያን ሰው የመሆን ክስተት ከኢትዮጵያዊነት፣ ብሄራዊነት እና አፍሪካዊነት በፊት ቀድሞ የመጣ ነው፡፡

ነጻ ሆኖ እንደተፈጠረ ሰው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ክብር እና ሞገስ መጠበቅ እንዳለበት አምናለሁ፡፡ በቡድን መብቶች አላምንም፡፡ እርሱ ወይም እርሷ የአንድ ቡድን አባል ባለመሆኑ/ኗ እና ከዚያ ቡድን ጋርም ምንም ዓይነት ግንኙነት ስለሌው/ላት በምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን የሕግ ጥበቃ የመከልከል፣ የህግ የበላይነትን እና እኩል ዕድልን የማጣት ድርጊት ሊፈጸምበት/ባት አይገባም፡፡ አራት ነጥብ!

ኢትዮጵያውያን ለማንኛውም የቡድን መብቶች ጠቃሚ የሆኑ ግላዊ መብቶች አሏቸው፡፡

እያንዳንዱ ኢትዮጵዊ የእራሱን መንግስት እና የመንግስት መሪዎችን የመምረጥ መብት አለው፡፡

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በጫካ ወሮበላ ዘራፊዎች ባርነት እንዳይፈጸምበት መብት አለው፡፡

ከበርካታ ወጣቶች ጋር በመነጋገር እንደምገነዘበው ከሆነ ኢትዮጵያን የማዳን ትግሉ ከወሳኙ ምዕራፍ ላይ የደረሰ መሆኑን አምኛለሁ፡፡

በኢትዮጵያ “ቡጢ ለነጻነት” በማለት ለሁሉም ጀግኖች ኢትዮጵያውያን የተማጽዕኖ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን ቡጢያቸውን እንዲያስተባብሩ እኔ ከማቀርበው የነጻነት የተማጽዕኖ ጥሪ የበለጠ ሌሎች የማይቀሩ ነገሮች አሉ፡፡

ታላቁ አፍሪካ አሜሪካዊ የህዝብ ገጣሚ ላንግስተን ሁጌ እ.ኤ.አ መስከረም 1935 የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በወረረበት እና የጥቃት ዘመቻውን በጀመረበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት ቡጢያቸውን እንዲጠነክሩ እና ሁሉንም አፍሪካውያንን ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነጻ እንዲያወጡ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቹ አንዲህ የሚል የትግል ጥሪ አቅርቦ ነበር፡

ለኢትዮጵያ የቀረበ የትግል ጥሪ፣

 

የጀግና አገር ውድ ኢትዮጵያ፣
የነጻነት ቀንዲል እሳት ቋያ፣
የሳባውያን ዝርያ አቢሲኒያ፣
ትጉኋ ንብ ውብ ባለሙያ፣
የአፍሪካ እናት ውድ ኢትዮጵያ፡፡

ጨለማውን ጥሰሽ፣
በነፍጥ ተዋግተሸ፣
ለአፍሪካውን ተሰውተሸ፣
ባርነትን አስወግደሽ፣
ነጻነትን ተቀዳጅተሽ፣
ሰንደቅሽን ታውለብልቢያለሽ፡፡

በአስደማሚ ሳቢ ደኖች፣
የተዋብሽው በተራሮች፣
የጀግኖችሽ ቤት ንብረቶች፣
መጠለያ ለፋኖዎች፣
ላርበኞችሽ አለኝታዎች፣
የሚሰው ለብዙዎች፡፡

እብሪተኞችን አዋርደሽ፣
አይቀጡ ቅጣት ቀጥተሽ፣
ዘላለማዊ ትምህርት ሰጥተሸ፣
ድልን ብድል ላይ ተረማምደሽ፣
ነጻነትሽን ትቀዳጃለሽ፣
አፍሪካውያንን ታኮሪያለሽ
እናም ለነጻነትሽ ተነሽ፡፡

ሁሉም አፍሪካውያን ተነሱ

እናንተ ጀግኖች ደፋር ህዝቦች፣
ዓይነ ጉርጥርጥ ደመ ፍሎች፣
የንግስተ ሳባ ቅዱስ ዘሮች፣
የነጻነት ቀንዲል ተዋጊ ፋኖዎች፣
የአፍሪካ ኩራት ታጋይ አርበኞች፡፡

ኢትዮጵያ ነጻ ሁኝ!
እንደ እኔ ነጻ ሁኝ፣
ሰላም ምቾትን እድታገኝ፡፡
ሁሉም አፍሪካውያን፣
በአራቱም ማዕዘን፣

እጅ ለእጅ ተያያዙና፣
አንድነትን ፍጠሩና፣
ነጻ ሁኑ ተነሱና፡፡

እናንተ ጥቁር ህዝቦች ሁሉ፣
ከጫፍ እስከጫፍ በሙሉ፣
ወንድ ሴት ልጅ ሳትሉ፣
ለነጻነት ተጋደሉ፡፡

አሽከር በሪያ ሳትሆኑ፣
ለዘር መድልኦ ሳትወግኑ፣
ሰውን በቀለም ሳትኮንኑ፣
ታገሉና ነጻ ሁኑ! ነጻ ሁኑ፡፡

የጋና የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት እና ታላቁ የአፍሪካ ፓን አፍሪካኒስት የነበሩት ክዋሜ ንክሩማህ ሁሉም አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን በመጀመሪያ ኢትዮጵያ እንድተነሳ እንዲህ ሲሉ የግጥም ስንኝ ቋጥረው ነበር፡

ኢትዮጵያ ለነጻነት ቡጢዋን ታነሳለች፣

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዕንቁ፣
ታሪክ ያላት በደማቁ፣

በልምላሜ የተሸፈነች፣
የሰውን ቀልብ የሳበች፣
በጀግንነት የታወቀች፡፡

የዓባይ ውኃ መፍለቂያ፣
ጥንታዊ ሀገር አቢሲኒያ፣
የብልሆች ሀገር ኢትዮጵያ፣
ለም የትምህርት መፍለቂያ፡፡

የጥንት ታሪክ መገኛ፣
የአፍሪካ ኩራት ሁነኛ፣
የአምባገነኖች መጋኛ፣
የኩራት ሀገር የእኛ፡፡

የአፍሪካ ባህል ቅርሳችን፣
የእኛነታችን የአንድነታችን፣
የማንነት አሻራ የስብዕናችን፡፡

ሀገረ ምድር የፈላስፋ፣
የአፍሪካውያን ተስፋ፣
ትነሳለች በይፋ፣
አቧራዋን አራግፋ፡፡

ከወደቀችበት ትነሳለች፣
ከእኛ ጋር ትታደሳለች፣
በስልጣኔ ትጓዛለች፡፡
የአፍሪካ ተስፋ ቀንዲል፣
ባለታሪክ የአፍሪካ ዕድል፡፡

ኢትዮጵያ ከዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ እና የበላይነት በድል አድራጊነት ትነሳለች! 

ሁሉም ኢትዮጵያውያን የእራሳቸውን ዕድል በእራሳቸው በመወሰን ከዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ ነጻ እንዲወጡ ሁላችሁም በያላችሁበት እገዛ አድርጉ! 

ኢትዮጵያውያን ወንደሞቼ እና እህቶቼ፡ አንድ ሀገር፣ አንድ ብሄር፣ አንድ ሕዝብ ነን!

“ገዥዎች ሽብርን በህዝብ ላይ የሚዘሩ እንደሆኑ አድርገን ልናስብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን በተጻራሪው እነርሱ እራሳቸው በፍርሀት ሽብር ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሽብር የእራሳቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲሉ እርባናቢስ በሆኑ ቦቅቧቃ ፈሪዎች የሚሸረብ የሸፍጥ ድርጊት ነው፡፡“ እ.ኤ.አ በ1870 በፓሪስ ኮሚዩን ማርክስ ለኤንግልስ የጻፈው 

ይቀጥላል…

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም

 

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተመረጡ ተጫዋቾች አብዛኞቹ የዕድሜ ምርመራን ሳያልፉ ቀሩ

$
0
0

stadium

(ዘ-ሐበሻ) ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ወጣት(ከ17 ዓመት በታች) ብሄራዊ ቡድን በግብፅ ካይሮ ኦገስት 5 ለሚያደርገው ጨዋታ ልምምድ ይጀምራል፡፡

ለዚህ ጨዋታ እንዲረዳ ከሰሞኑ በጳውሎስ ሆስፒታል ተጨዋቾቹ ላይ የኤም አር አይ ወይንም እድሜን የማጣራት ምርመራ ተከናውኖ ነበር፡፡ በ3 ቡድን ተከፍለው ወደሆስፒታሉ የተጓዙት ተጨዋቾች ውጤት ይህን ይመስላል።
በመጀመሪያው ቡድን 40 ተጨዋቾች ተመርምረው 2ቱ ብቻ ምርመራውን ሲያልፉ በሁለተኛው ቡድን ከ19 ተጨዋቾች ውስጥ 7ቱ ማለፍ ችለዋል፡፡ በሶስተኛው ቡድን ደግሞ ከ35 ተጨዋቾች ያለፉት 15ቱ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
እነዚህን ተጨዋቾች ከመጡበት ቦታ ወይም ክለብ አንፃር ብንመለከት፡-
አዳማ ከ4/0፣
ወላይታ ዲቻ ከ5/1፣
ሀዋሳ ከ8/0፣
ሲዳማ ከ6/1
ቅ/ጊዮርጊስ ከ6/1፣
ደደቢት ከ9/2፣
ንግድ ባንክ ከ9/2፣
ኢትዮጲያ ቡና ከ11/2፣
ኤሌክትሪክ ከ9/3 ተጨዋቾች ያለፉ ሲሆን ተስፋ ከተጣለበተው አምቦ ጎል ፕሮጀክት 8 ተጨዋቾች ተመርምረው ምንም ማለፍ የቻለ ተጨዋቾች የለም፡፡ ከብሄራዊ አካዳሚ ደግሞ ከ10 በላይ ተጨዋቾች መጥተው ያለፈው 1 ብቻ ነው። በአጠቃላይ በ94 ተጨዋቾች ላይ እድሜ የማጣራት ምርመራ ተከናውኖ በትክክል እድሜያቸው ከ17 በታች ሆኖ የተገኙት 24 ብቻ ናቸው ማለት ነው፡፡

ኤርትራ “200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድዬ 300 አቆስለኩ”አለች

$
0
0

 

file(ዘ-ሐበሻ) ቢቢሲ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴርን ገልጾ እንደዘገበው ኤርትራ በ2 ቀን ጦርነት 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድላ 300 ማቁሰሏን አስታወቀች::

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በጾረና በኩል ጥቃት ፈጸመብኝ ማለቱ ይታወሳል::

እንደሚኒስትሩ መግለጫ እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተደረገው ጦርነት 200 ሰዎችን መግደሉን ይገልጽ እንጂ ከራሱ በኩል የተጎዱ ወይ የሞቱ ወታደሮች እንዳሉ የገለጸው ነገር የለም::

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለኤርትራ መንግስት እስካሁን ለፈጸመው ትንኮሳ ተመጣጣኙን እርምጃ ሰጥተነዋል:: ወደፊትም እንደ ኤርትራ መንግስት እንቅስቃሴ ጦራችንን እናንቀሳቅሳለን ማለቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫም ከኤርትራ ጋር ወደለየለት ጦርነት መግባት የኢትዮጵያ ምርጫ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል::

ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ1998 – 2000 ዓ.ም ድረስ ባደርጉት የድንበር ግጭት ከ100 ሺህ ሰዎች በላይ ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ::

Health: ህፃናት ከልክ በላይ መወፈራቸው ለምን ያሳስበናል? |ለህፃናት የሚመከሩ ምግቦች

$
0
0

 

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም | ለዘ-ሐበሻ

ዛሬ ላይ ሰዎች በሽታዎችና አደጋዎች ከሚያመጡባቸው ችግሮች እኩል ውፍረት ህይወታቸውን ሌላ መልክ እያስያዘው ይገኛል፡፡ እንደ አሜሪካ ባሉ ሀገራት ደግሞ የዜጎቸውን ህይወት በመንጠቅ ከቀዳማዊ ችግሮች አንዱ  ነው፡፡ ሰዎችን በተለይ አዋቂዎቹን ከቤት ውስጥ በማዋልና ተስፋ በማስቆረጥና በሌሎች ተፅዕኖዎቹ ከልክ ያለፈ ውፍረት ዋነኛው የዓለማችን ማህበራዊ ችግር ወደ መሆን እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ ችግሩ አሁን ላይ የወጣቶችና የህፃናትም ጭምር መሆኑ ነው አሳሳቢው ጉዳይ፡፡

baby fat

አንድ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ከ5 እስከ 11 ዓመት በሆናቸው ህፃናት መሀከል ከሚገኙ 3 ህፃናት ውስጥ አንዱ ከልክ ካለፈ የውፍረት ችግር ጋር የሚኖር መሆኑን አመልክቷል፡፡ ታዳጊዎች ከልክ በላይ በወፈሩ መጠን የዕድሜ እኩዮቻቸው ብዙ ጊዜ ተጋላጭ ባልሆኑባቸው አንዳንድ በሽታዎች የመጠቃት እድላቸው በእጅጉ ይጨምራል፡፡ እንደ ወላጅ ወይም እንደ አሳዳጊና እንደ መምህር በአንድ ህፃን ህይወት ላይ ሚናቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች አሉ በተለይ ጤናማና የተስተካከለ ክብደት እንዲኖራቸው ለማድረግ፡፡ በዚህ ረገድ ህጻናቱ ጤናማ ምግብ መመገባቸውን እርግጠኛ መሆንና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በማበረታታት ሊሆን ይችላል ሚናቸውን የሚወጡት፡፡

የህፃናት ውፍረት አደጋ በኢትዮጵያ

ልጅን በሚገባ ለማሳደጋቸውና የሚፈለገውን ለማሟላታቸው ብዙ ጊዜ ወላጆች እንደምስክርነት የሚያቀርቡት ድንቡሽቡሽ ያሉትንና ከልክ በላይ የወፈሩትን ልጆቻቸውን ነው፡፡ ታዛቢውም ቢሆን ‹‹እንዴት ቢንከባከቡት ነው እንዲህ የፋፋ ልጅ ያደረሱት?›› የሚለውን ጥያቄ መሰንዘሩ አይቀርም፡፡ በአጠቃላይ አቅሙና አቅርቦቱ እስካልተስተጓጎለ ድረስ ልጅን ማደለብ ባህል እንደሆነ አለ፡፡

በሀገራችን ወላጆች በውፍረት ሳቢያ በልጆቻቸው ላይ ሊመጡ ስለሚችሉ አካላዊና አዕምሯዊ ችግሮች ላይ በቂ ትኩረት ይሰጣሉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከልክ በላይ የወፈሩ በርካታ ህፃናትን እንደልበ እንድንመለከት ምክንያት እንደሆነ ነው የፊትነስና የጤናማ አመጋገብ ባለሙያዋ የትናየት ታምራት የምትናገረው፡፡ በግል የማማከርና ተግባር ልምምዶችን ስትሰጥ በቆየችባቸው ባለፉት 6 ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንኳን እርዳታዋን የሚፈልጉ ከልክ በላይ የወፈሩ ህፃናት ቁጥር በአስደንገጭ ቁጥር ጨምሯል፡፡ ወላጆች ግንዛቤ ጨምሯል፡፡ ወላጆች ግንዛቤ ኖሯቸው ይሁን ሳይኖራቸው ለልጆቻቸው ጤናማ አካላዊ ገፅታ ከፍተኛ ትኩረት እየሰጡ አይገኙም፡፡

ህፃናት ከልክ በላይ መወፈራቸው ለምን ያሳስበናል?

ልጆቻቸው ከልክ በላይ መወፈራቸውን ተከትሎ ወላጆችን ሊያሳስባቸው የሚገቡ በርካታ ተያያዥ ጉዳዮች አሉ፡፡ በከፍተኛ ውፍረት ውስጥ የሚመደቡት ህፃናት የመገጣጠሚያ እና የመተንፈሻ አካላት ችግሮች ይገጥሟቸዋል፡፡ በተለይ እነዚህ የጤና እክሎች ህፃናቱ እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው ማንኛውንም ተግባር እንዳሻቸው እንዳይፈፅሙ በመከልከል ከባዱ የአዕምሮ ችግር ውስጥ ይከታቸዋል፡፡

አንዳንዱ ህፃናት ደግሞ ከከፍተኛ ውፍረት ጋር ቀጥታ ተዛምዶ እንዳላቸው ለሚታወቁት የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ ደም ግፊት እና ከፍተኛ ኮሌስትሮል ይጋለጣሉ ዕድሜአቸው በተወሰነ ደረጃ እየጨመረ በመጣ ጊዜም የልብ ችግር እና በርካታ የካንሰር አይነቶች የጤና ስጋቶቻቸው ይሆናሉ፡፡

ህፃናት ጤናማ አመጋገብን እንዲዋሃዱ ምን ማድረግ ይገባል?

– የህፃናትን የተበላሸ የሚባል የአመጋገብ ልማድ ወደ ጤናማ መስመር ለማምጣት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴም እንዲያዘወትሩ የወላጆች እና የአሳዳጊዎች ሚና ዋነኛው ነው፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን ተግባራት መፈፀም ይመከራል፡፡

– ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የህፃናት አዕምሮ ያየውን ለመቀበል እና ለማመስመሰል የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለዚህ ወላጆችና አሳዳጊዎች በህፃናቱ ፊት ጤናማ የሚባሉትን ምግቦች ማዘውተራቸው በህፃናቱ አዕምሮ ላይ የሚፈለገውን ለውጥ ለማተም ይረዳል፡፡

– ሁሉንም ቤተሰብ ማሳተፍ፡- ከልክ በላይ ውፍረቱ የአንድ ህፃን ችግር ቢሆንም ዘላቂ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ ከሆነ ሁሉንም የቤተሰብ አባላት ያሳተፈ የአመጋገብ ባህል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ነው፡፡

– ከህፃናት ሊርቁ የሚገባቸው ምግቦችን መለየት

– በካሎሪ፣ ስኳር እና ጨው ክምችታቸው ከፍተኛ የሚባሉትን ምግቦችና መጠጦች ለምሳሌ ቺፕስ፣ ኩኪሶች፣ ጥብሶችና ከረሜላዎች የተቀነባበሩ ጣፋጭ መጠጦች ይገኙበታል፡፡ ከዚህ ባለፈ በፋብሪካ የተቀነባበሩትን እንደሩዝ እና ፓስታ ያሉትን ምግቦችም ህፃናቱን ማራቅ ይመከራል፡፡

ለህፃናት የሚመከሩ ምግቦች

ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች፣ ለውዝ እና ዝቅተኛ ፉት ያላቸውን ወተቶች እና የወተት ውጤቶች፣ ካልሲየም እና ቫይታሚን ‹‹ዲ›› የተጨመረባቸው ቢሆኑ ደግሞ ይበልጥ ይመከራል፡፡ ከዚህ ውጪ ስለ የሚባሉ ስጋዎችን አሳና ሌሎች የባህር ውስጥ ምግቦችን፣ ባቄላ፣ አኩሪአተር እና እንቁላልን ህፃናቶች እንዲያዘወትሩ ማድረግ በጤናቸውና አካላቸው ላይ የምንፈልገውን ለውጥ እንድንመለከት ይረዳል፡፡

ህፃናት ጤናማ አመጋገብን እንዲመርጡ እነዚህ የተቀመጡ አማራጮች ናቸው፡፡

– ህፃናት ስላጠኑ ወይም ለፈፀሙት አንድ ተግባር እንደማበረታቻ ሁልጊዜ ምግብን ባንጠቀም ይመከራል፡፡ ይሄ በተለይ ከልክ ያለፈ ውፍረት ለሚያሰጋቸው ህፃናት ይሰራል፡፡ በምግብ ማበረታታቱ አስፈላጊ ከሆነም ጤናማዎቹን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ለህፃናቱ በሽልማት መልክ ኬክን ጨምሮ ጣፋጮችን ማቅረቡ ከፍተኛ ችግር ያስከትላል፡፡

– ምግብን በትልቁ ከማቅረብ አነስ ባለ መጠን መጀመር፡፡ ህፃናቱ ተጨማሪ ምግብ ካስፈለጋቸው ጥያቄው ከእነርሱ እንዲመጣ መጠበቅ፡፡


በሻሸመኔ 7 ሰዎች ባልታወቁ ሰዎች ተወግተው ተገደሉ |“በምሽት የምትንቀሳቀሱ ጥንቃቄ አድርጉ”ጀዋር መሐመድ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፉት ጥቂት ቀናት በሻሸመኔ ጨለማን ተገን በማድረግ በትንሹ 7 ሰዎች በስለት ተወጋግተው መገደላቸው ተሰማ:: እንደ ዜና ምንጮች ዘገባ ከሆነ እነዚህን 7 ሰዎች ማን ወጋግቶ እንደገደላቸው ባይታወቅም ሆኖም ግን ሆን ተብሎ የብሔር ግጭት ለማስነሳት የታሰበ ይመስላል ተብሎ ተገምቷል::

ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ 7 ሰዎች ሲገደሉ ከነርሱም መካክል ትናንት ምሽት ባልታወቁ ሰዎች ተወጋግቶ ተገድሎ የተገኘው የሻሸመኔው ነዋሪ ወጣት ሃሩን ሃጂ ቱሱ ይህ ነው::

ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ 7 ሰዎች ሲገደሉ ከነርሱም መካክል ትናንት ምሽት ባልታወቁ ሰዎች ተወጋግቶ ተገድሎ የተገኘው የሻሸመኔው ነዋሪ ወጣት ሃሩን ሃጂ ቱሱ ይህ ነው::

ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በሻሸመኔ ከ7 ሰዎች ግድያ በተጨማሪ በርካታ ወጣቶች በጨለማ ተወግተው በህክምና ላይ ይገኛሉ::

በርካታ የሻሸመኔ ነዋሪ በዛሬው ዕለት በተለይም ከ7ቱ ሟቾች መካከል የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ሃሩን ሃጂ ቱሱ ቀብር ላይ በመገኘት በዛውም ተቃውሞውን ማሰማቱ ታውቋል::

በሻሸመኔ የተፈጸመውን የነብስ ማጥፋት በተመለከተ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል::

“ማስጠንቀቂያ ለሻሸመኔ ነዋሪዎች: ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስት ጭለማን ተገን በማድረግ በተፈጸሙ ጥቃቶች 7 ኦሮሞዎች ሲገደሉ ብዙዎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ይህን ጥቃት ማን እና ለምን እንደፈጸመው ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም ድርጊቱ ሆን ተብሎ ታልሞበት በህዝቦች መካከል ግጭት ለማስነሳት የተደረግ ሴራ እንደሆነ ይጠረጠራል። ይህንን ጥርጣሬ የሚያጠናክረው በአሁኑ ወቅት የመንግስት ሰዎች ‘ጥቃቱን የፈጸሙት የእከሌ ብሄር ተወላጆች ናቸው’ የሚል ሃሜት እና ወሬ እያናፈሱ መሆናቸው ነው። ነገሮችን ለማክረር ሲባል በሚቀጥሉት ቀናት ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊደርሱ እንደሚችሉ ይጠረጠራል። ስለዚህም በምሽት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የላቀ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል። ይህንን አደገኛ ሴራ በመረዳት ህዝቡ ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እንማጸናለን።”

እሱ ማነው ?

$
0
0

Screen Shot 2016-06-18 at 9.16.34 AM

      
“አቶ መለስ ዜናው በመተማ መሬት በምክር ቤት የሞገተ፣ እሱ ባሲያዘው አጀንዳ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ ከአቶ መለስ ጋር ከፍተኛ ክርክር በምክር ቤት ካደረጉት መካከል አቶ ተመስገን ዘውዴ ይገኙበታል”

                                                             (ይድነቃቸው ከበደ)

በ1997 ዓ.ም የህዝብ እንደራሴ በመሆን ቅንጅትን በመወከል በተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበር ።የቅንጅት መፍረስ ተከትሎ፣አንድነት ፓርቲ ሲመሰረት ፣የፓርቲው አባል በመሆኑ የሚጠበቅበትን ግዴታ ሲወጣ ቆይቷል።ይሁን እንጂ አንድነት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው መከፋፈል ከፓርቲው እራሱን ያገለለ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል በመሆን ፣ታህሳሥ 22 ቀን 2004 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ ምስረታዉን በይፋ ባካሄደበት ወቅት፣የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ሆኖ ተመረጠ። ለእስር እስከ ተዳረገበት ጊዜ ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን የጎንደር አስተባባሪ በመሆን ፣ከፓርቲው የተሰጠውን ኃላፊነትና ግዴታ በአግባብ ሲውጣ የቆየ ትጉህ ጓድ ነው።

እሱ ፣እጅግ በጣም ሲበዛ ትሁት እና ሰው አክባሪ ነው። ስለ-እሱ እሱን የሚያውቁት ሁሉ ይህን እውነታ ይመሰኩርለታል።ሰው አክባሪነቱና ትህትናው በሚያመቸዉ ቦታ እና ጊዜ ብቻ ሳይሆን የትም ለማንም ነው። ያለውን ለማካፈል የእሱ መስፈርት፣ የእሱ ኪስ ባዶ አለመሆኑን ብቻ ነው። ከእድሜው በላይ የአስታዋይ ሽማግሌ ባህሪና ሥራ አብዝቶ ይታይበታል፣ ለዚህም ነው በ23 ዓመቱ በሰሜን ጎንድር ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የህዝብ እንደራሴ ሆኖ የቅንጅት ተወካይ የሆነው። እሱ ልጅ ሆነ በ9 ዓመቱ የእነሱን ሰፈር አልፉ አዲስ አበባ የገባው ፣ አምባገነኑ የውያኔ ስብስብ፣ ለመቃውም የልጅነቱ ጊዜ ጨርሶ ፣ የወጣትነት ዘመኑ በጀመረ ማግስት ነው። ተፈጥሮ ካደለችው እሱም አጥብቆ ከያዘው የሰው ሰውኛ መልካም ባህሪ በተጨማሪ ፣ በትምህርቱ የሕግ ተመራቂ ነው።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበረው ቆይታ፣የአገዛዙ ስርዓት ዋና መሪ የሆነት ሟቹ አቶ መለስ ዜናው፣ በመተማ መሬት በምክር ቤት የሞገተ እሱ ነው። እሱ ባሲያዘው አጀንዳ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ ከአቶ መለስ ጋር ከፍተኛ ክርክር በምክር ቤት ካደረጉት መካከል አቶ ተመስገን ዘውዴ ይገኙበታል። ይሄን ጉዳይ አስመልክቶ የሆነውን ሁሉ ምስክርነታቸውን መስጠት ይችላሉ። በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ በፊት ገጹ፣ የአቶ መልስ ዜናዊ እና የሰሜን ጎንድር ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የህዝብ እንደራሴ የሆነዉ ፎቶ በመያዝ፤ ስለ መተማ መሬት ሰፊ ዘገባ ይዞ ቀርቦ ነበር ፣የጋዜጣው ሚዛናዊነት ማጋደሉ እንደተጠበቀ ሆኖ እንዳለ።

እሱ ፣የአገዛዙ ስርዓት እንዲለወጥ እስከ-ታሰረበት ጊዜ ድረስ ለ9 ዓመት ያህል በሰላማዊ መንግድ ፤ በቅንጅት ፣ በአንድነት እና በሰማያዊ ፓርቲ የሚቻለዉን ሁሉ አድርጓል ። ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከ በቃበት የእስር ዘመኑ ፣ባጠቃላይ ለ11 ዓመት ያህል ፣ በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ መስል የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን የአገዛዙን ሥርዓት ጠበንጃ አልባ በሆነ ትግል፤ በሰላማዊ መንገድ ሲገጥም ቆይቷል። አሁን ለእስር ከተዳረገ አንድ አመት ከ7 ወር ሆኖታል። የአገዛዙ ስርዓት ማሰቃያ ቦታ በሆነው መዓከላዊ እስር ቤት ለ5 ወር አስቸጋሪውንና ፣ችግሩ ይሄ ነው ተብሎ ለመግለፅ የሚክብድውን የስቃይ ጊዜ ያሳላፍ ሲሆን፣አሁን ደግሞ በቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ይገኛል።

ይህ ሰው፣ አሁን ላይ ለእስር የተዳረገው “የአርበኞች ግንቦት ሰባት ፣ዓላማና ተልእኮ ማስፈጸም ” የሚል ክስ ቀርቦበት ነው።የገዢው ስርዓት አስመሳይ የሕግ ሽፍን በመስጠት ፣የነፃነት ታጋዮችን በፍርድ ቤት አቅርቦ ለእስርና ለስቃይ የሚዳርገው አቃቤ ህግ፤በእዚህ ሰው ላይ ያቀረበው ክስ፤ 1ኛ.”ቀኑና ወሩ በትክክል ተለይቶ ባልታወቀበት በ2006 ዓ.ም አማረ ሽፈራው በተባለ የሽብር ድርጅት ተወካይ፣ስልጠና ለመውሰድ እና ተልእኮ ለመፈጸም መስማማቱ። 2ኛ.ቀኑ በትክክል ተለይቶ ባልታወቀ በጥር ወር 2006 ዓ.ም ከኢሳት ጋዜጤኛ መሳይ መኮንን ጋር (የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን፣ እያሰረና እያሰቃየ ነው) በማለት ከሽብር ድርጅት አባል ከሆነው ከመሳይ መኮንን ጋር ቃለ መጠይቅ በማድረጉ። 3ኛ.በየካቲት ወር 2006 ዓ.ም (ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንግድ መታገለ አይቻልም፤ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መንግሥት ተሰጥቷል) በማለት በኢሳት ተናግሯል የሚል ክስ ነው የቀረበበት። ክስ አቅራቢዎቹ በእዚ ሰው ላይ ምንም አይነት የሰው ማስረጃ ወይም ምስክር ማቅረብ አልቻሉም ፣አለን የሚሉት የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን ፤ ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር ቃለ መጠይቅ ማድረግ የሽብር ተግባር መሆኑ የአገዛዙ ልኬልሽ አምባገነናዊ ስርዓት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። አዎ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ መታገል ፣ ሕይወትን ያሳጣል ፣ለእስር እና ስቃይ ይዳርጋል! ይህን ማለት ሳይሆን፣ ይሄን ቀፋፊ ተግባር መፈጸም ነው ሽብር የሚሆነው። ይሁን እንጂ እነ ሽብሩ ሰላማዊ የነፃነት ታጋዩን አሸባሪ ብለው ከሰሱት።

እሱ፣ “የታሰርኩት የመተማ መሬት ለሱዳን መሸጡን በመናገሬ ነው፡፡ ትናንትም መሬቱ መሸጡን ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ ወደፊትም እናገራለሁ፡፡ የተከሰስኩት በመሬቱ ጉዳይ ነው እንጅ አሁን የተከሰስኩበትን ወንጀል ፈጽሜ አይደለም፡፡” ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን በፍርድ ቤት ፤ በሚገርም ወኔ በልበ ሙሉነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ በወቅቱ በፍርድ ቤት በመገኘት ይህን ለመታዘብ ችያለው። ግንቦት 11/2008 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ግፍ እያደረሰብኝ ነው፣ በማንነቴ ላይ በደል እየተፈጸመብኝ ነው ፣ እኔ ዘረኛ አይደለሁም ግን ፍጹም ዘረኛ በሆነ በማንነቴ ብቻ እያሰቃዩኝ ነው። በማለት አቤቱታ አሰምቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ‹‹ጨለማ ቤት እናስገባሃለን›› እያሉ እንደዛቱበትም በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡ እንዳለው ሆነና ግንቦት 17/2008 ዓ.ም ጀምሮ በሚታሰብ የሁለት ወራት ጨለማ ክፍል እስር ቅጣት አስተላልፈውበታል፡፡

ከግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከ በቃበት ድረስ፤ ቂሊንጦ በሚገኘው ጨለማ ክፍል ውስጥ ይገኛል።በቂሊንጦ ሁለት ጨለማ ክፍል የሚገኝ ሲሆን፣ እሱ የሚገኝበት ክፍል ከእሱ ውጪ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኛ የሌለ ሲሆን ፣እጅግ በጣም አደገኛ የሆኑ ወንጀለኞች የሚቀጡበት ክፍል ነው። በጨለማ ክፍል ውስጥ ከመታሰሩ በተጨማሪ በማንም እንዳይጠየቅ ክልከላ ተደርጎበታል።ከፍተኛ የሆነ ድብደባም እየተፈጸመበት እንደሆነ ከውስጥ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። ይህ ሰው ጨለማ ክፍል ውስጥ ከመግባቱ በፊት ፣ በእስር ቤት ሄደዉ ለሚጠይቁት ሁሉ ፣ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ አውርቶ አይጠግብም ፤ “አደራ ፓርቲያችን ጠብቁ” በማለት ተማጽኖ ጭምር የማይለየው የእሱ የሁል ጊዜ ትልቁ መልእክት ነው። ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ.ም በተከሰሰበት ክስ የመጨረሻ ብይን እንደሚሰጥ በፍርድ ቤት ቀጠሮ ተይዟል ። ሰኔ 13 ቸር ወሬ ፈጣሪ ያሰማን ፣አሜን።ይህ ሰወ አግባው ሰጠኝ ይባላል!!!

Health: ትዳር በሚያስቡ ፍቅረኞች መሀከል የዕድሜያቸው ልዩነት ስንት ይሁን?

$
0
0

በዕድሜ ጎዳና የሚደረግ ጉዞ ከልጅነት እስከ እርጅና ይዞን ይዘልቃል፡፡ በዚህ ሂደትም አንዱን የህይወት ምዕራፍ አጠናቀን ወደ ሌላው ስንሻገር ትዳር የመያዝ ወይም ያለመያዝ አማራጭ በጉዟችን ላይ ይገጥመናል፡፡ በሀገራችን በወርሀ ጥርና በወርሃ ሚያዚያ ብዙ ጥንዶች በዕድሜ ጎዳናቸው እኩሌታ ላይ ከጋብቻ ፌርማታ በመሆን ወደ ትዳር ለመሳፈር ዝግጁ የሚሆኑበት ወቅት ነው፡፡ ተፈጥሮ፣ ባህል፣ አቅም፣ ብስለት እንዲሁም ኃላፊነትን የመሸከም ዝግጁነት ሴቶችና ወንዶች ለትዳር የተለያየ አመለካከት እንዲኖራቸው አድርጎናል፡፡

Maza-wedding-bands

ሴቶች በሀገራችን በአብዛኛው ለመውለድ አልያም ‹‹ቆሞ ቀር›› ለሚባለው አሉታዊ የባህል ተፅዕኖ ላለመዳረግ ሲሉ ዕድሜያቸው 30 ከመሆኑ በፊት ትዳር የመያዝ ፍላጎት አላቸው፡፡ የትዳር ኃላፊነትን ከመሸከም አንጻር ወንዶች ከሴቶች ዘግይተው የመብሰል ነገር ስለሚስተዋልባቸው የወንደላጤነትን ነፃነት ላለማስረከብ ሲሉ እንዲሁም በየትኛውም የዕድሜ ክልል ልጅ መውለድ የመቻልን የተፈጥሮ ስጦታን ከቁጥር በማስገባት፣ ብዙ ወንዶች ትዳርን በለጋ ዕድሜ ከመያዝ ይቆጠባሉ፡፡

የህይወት መሰረታዊ ውሳኔ የሚባለው ትዳርም በሁሉም እምነቶች ዘንድ አይነተኛ ቦታ አለው፡፡ የትዳርም ትርጓሜ ሁለት የሚፋቀሩ ሰዎች ለመዋደድ፣ ለመደጋገፍ እና እስከ ህይወት ፍፃሜ አብሮ ለመኖር በሚያመልኩት ፈጣሪ ፊት ቃል የሚገቡበት እንዲሁም በህግ ፊት አስፈላጊውን ኃላፊነት ለመውሰድ ግዴታቸውን የሚቀበሉበት የጋራ ስምምነት ነው፡፡ በሰዎች ታሪክም የትዳር ፌርማታ አዲስ ገቢዎችን እንደሚያስተናግድ ሁሉ ጉዞን በቃል የሚሉ መንገደኞችንም ያስወርዳል፡፡ የትዳር ጓደኛ በአንድ ሰው የግል ምርጫ የሚወሰን ቢሆንም በአብዛኛው በፍቅር ምሰሶ የተዋቀረ ትዳር ዘላቂነት ይኖረዋል፡፡ በጥንዶች መካከል ያለ አካላዊ ግንኙነት ትዳር ውበቱ ሳይደበዝዝ እንዲቆይ ሲያደርግ የሥጋ ግንኙነትም በትዳር ውስጥ ብቸኛ ሳይሆን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ በአጠቃላይ ያለው ተፈጥሯዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ሁኔታ ወንዶች ትዳር እንዲፈሩና ሴቶች ጋብቻ እንዲፈልጉ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በሴቶች ፍለጋ እንዲሁም በወንዶች ማመንታት የሚፈጠርን ክፍተት ፍቅር፣ ፍቅረ ነዋይ ወይም የጋብቻ አባዜ በማጥበብ ሴቶችና ወንዶች ለጋብቻ ይበቃሉ፡፡

የሴቶች የዕድሜ ጣሪያና ዝቅታ!

ሴቶች በጋብቻ ውስጥ ቤተሰብን ማፍራት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ስለሆነ ልጅ መውለድ በሚችሉበት የዕድሜ ክልል የሚወዱትን የህይወት አጋር ማግኘትና ማግባት ይፈልጋሉ፡፡

ተፈጥሮ እንደ ወንዶች ለሴቶች በመሆኗ ትዳር በሴቶች ዘንድ 22-30 ባለው የዕድሜ ክልል እንዲፈፀም ይመከራል፡፡ የሴቶች የጋብቻ ዕድሜ እንደ ጊዜው እና እንደ አንድ ሀገር ባህል እሴት አንፃራዊ ነው፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ጥሩ የጋብቻ ዕድሜ ተብሎ የሚታሰበው 15 ዓመት እስከ 24 ዓመት ሲሆን፣ 22 ዓመቷ ያላገባች ሴትም ‹‹ቆሞ ቀር›› ትባላለች፡፡ በአንፃሩ በከተማው አንዲት ሴት ለምሳሌ 22 ዓመቷ ትዳር ብትይዝ ‹‹አልቸኮልሽም?›› ትባላለች፡፡ ስለዚህም 22-30 ያለው የሴቶች የጋብቻ ጊዜ በከተማ የሚስተዋል የአሁን ዘመን አማካይ ዕድሜ ሲሆን፣ 30 ገደብ እስከ 35 ሊበልጥም ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለች ሴት ትምህርት በመሟሯ፣ በስራ ዕድል ተወዳዳሪ በመሆኗ እና የራሷን ገቢ ማግኘት በመቻሏ በወንዱ ላይ ሊኖራት የሚችለውን የገንዘብ ጥገኝነት በከፊል ቀንሶላታል፡፡ ስለሆነም በስራዋ ማግኘት የምትፈልገውን የስኬት ደረጃ ላይ እስከምትደርስ የአሁኗ ዘመን ሴት በአንጻሩ እንደ በፊት ዘመን ሴቶች ትዳርን የማስቀደም አዝማሚያ ብዙም አታሳይም፡፡ በየተያያዥም 21ኛው ክፍለ ዘመን ካፈራቸው እሳቤዎች መሀከል አንዱ የሆነው የሴቶች ከወንዶች የእኩልነት ሃሳብ በሴቶች የጋብቻ ዕድሜ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ ጋብቻ ምርጫቸው ላልሆኑ ሴቶችም እንደ ድሮ ‹‹ቆሞ ቀር›› ከመባልም ይህ እሳቤ ገላግሏቸዋል፡፡ አንዲት ሴት የገንዘብ ነፃነቷን ካረጋገጠች በጋብቻ መታሰርን እና ነፃነቷን ልክ እንደ ወንዱ ላለማጣት ከፈለገች ትዳርን ያለመያዝ ወይም ‹‹ምን አጨቃጨቀኝ፣ እራሴን መቻል እንደው አይሳነኝ›› ብላ ትዳርን በተፈለገው አጋጣሚ የማፍረስ እድሉን የነጻው ኢኮኖሚ ነፃ አስተሳሰብ አመቺ አድርጎታል፡፡ በጥቅሉ ከባህልም፣ ከተፈጥሮም ከብስለትም አንፃር 22-30 ያለው ጊዜ ለሴቶች ወደ ትዳር የሚሳፈሩበት የዕድሜ ፌርማታ መሆኑን ብዙዎች የሚስማሙበት ሃሳብ ነው፡፡ 20ዎቹ፣ 30ዎቹ እንዲሁም 40ዎቹ የዕድሜ ክልል ጋብቻን ፈፅሞ ትዳር መያዝ በሴቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳትና ጥቅም አለው፡፡ 20ዎቹ መጀመሪያ ከወሊድ ጋር ተያያዥ ችግሮች በአነስተኛ ደረጃ ስለሚከሰቱ ለሴቶች የጋብቻ እንዲሁም ለወሊድ አመቺ ዕድሜ ተብሎ የሚታሰበው 24 ዓመት ነው፡፡ ሆኖም 20ዎቹ የዕድሜ ክልል ማግባት ለሴቷ የራሱ ተግዳሮቶች አሉት፡፡ አንዲት ሴት ከጋብቻ በኋላ 20ዎቹ መጀመሪያ ልጅ ብትወልድ ለራሷ ህይወት የምትሰጠውን ትኩረት በመቀነስ ወደ ህፃኑ ታደላለች፡፡ የኋላ ኋላ በባሏ የገንዘብ ድጋፍ ስር ትወድቃለች፡፡ ብዙሃኑ የጋብቻ ስነ ልቦና ባለሞያዎች የሚስማሙበት ግንባር ቀደም የፍቺ መንስኤ የገንዘብ ጉዳይ ነው፡፡ 20ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚከወነው ትዳር ለወሊድ ጥቅም ሲኖረው በተለይ በእኛ ሀገር ያሉ ልጅን የማሳደግ፣ ባልን የመንከባከብ እንዲሁም ትዳርን በፍቅር የማቆየት ኃላፊነቶች እጅጉን ፈታኝ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 30ዎቹ የዕድሜ ክልል ማግባት ለሴቷ ከወሊድ አንፃር እንደ 20ዎቹ የዕድሜ ክልል ሁሉ የወሊድ ሁኔታዎች ብዙም አመቺ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ሴቷም 20ዎቹ አንፃር በዕድሜ ስለምትበስል በቤት አያያዝና በስረዋ ዙሪያ ጥሩ ብቃት ይኖራታል ተብሎ ይታሰባል፡፡ 40ዎቹ እና ከዛ በላይ የሚፈፀሙ ጋብቻዎች ለሴቷ ከትዳር ከምትፈልገው ስኬት አንፃርም ሆነ ከወሊድ በአብዛኛው ተመራጭ አይሆንም፡፡

የወንዶች የዕድሜ ጣሪያና ዝቅታ

የወንዶች የጋብቻ ዕድሜ 24 አንስቶ የመጨረሻው ወሰን ገደብ የለሽ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ግማሾቹ ሴቶች ወንዶች ማግባት አለባቸው ብለው የሚያምኑት ዕድሜ 30-45 ዓመት ያለውን ጊዜ ነው፡፡ ወንዶች 20-30 ባለው ዕድሜ ትኩረት የሚሰጡት ጉዳይ ለትዳር ሳይሆን በተሰማሩበት ስራ ስኬታማ መሆን የሚያስችላቸውን የገንዘብ አቅም ነፃነታቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ 20-30 ያለው የዕድሜ ክልል ከሴቶች ትዳር የመያዣ ጊዜ ሲሆን፣ ለወንዶች ደግሞ የማንነት ጥያቄ የሚጎለብት መሆኑ በዕድሜ ጎዳና ላይ ሴቶችና ወንዶች ወደ ትዳር የሚያደርጉት አካሄድ አሰነዛዘሩና ፍጥነቱ እንዲለያይ አድርጎታል፡፡ ሴቶች የወንዶች ኃላፊነት የመውሰድ ዝግጁነት ብስለታቸው የሚመጣው በዕድሜ ሳይሆን በአፈጣጠራቸው እና በአስተዳደጋቸው ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ወንደላጤ ሆኖ መቆየት ለበሽታ ከማጋለጡ አንፃር ሲታይ አንዳንድ ወንዶች በጋብቻ የመወሰን ጥቅምን ተረድተው 20ዎቹ አጋማሽ ትዳር በመያዝ በለጋ ዕድሜያቸው አግብተው ስኬታማ ሲሆኑ የሚስተዋሉ ወጣት አባወራዎች አሉ፡፡ ከትዳር ጋር በተያያዘ የብዙዎቹ ወንዶች ጥያቄ የአቅም ጉዳይ ነው፡፡ በሴት እጅ መኖር አልፈልግም የሚል በማህበረሰባችን የሰረፀ አመለካከት በመኖሩ ሳቢያ ማንም ወንድ ትዳር ለመመስረት ብቁ የሚያደርገው የገንዘብ አቅም እስከሌለው ድረስ ጋብቻን ለመፈፀም ያመነታል፡፡ ወንዶች 30-45 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ቢፈፅሙ ትዳሩን ስኬታማ ከማድረግ አንፃር ጠቀሜታ እንዳለው ብዙ የትዳር ስነ ልቦና ባለሞያዎች ይስማማሉ፡፡ ከዘመነኝነት ጋር በተያያዘ የሴት ዕድሜ በመልኳ፣ የወንድ ዕድሜ በአመለካከቱና በአኗኗር ዘዬው ይለካል ብለው የሚያምኑ ወንዶች 40 ዓመትን እንደ 30 50 ዓመትን እንደ 40 በመቁጠር እና ‹‹50 ዓመቴ እንደ 30 ዓመት ወጣት ማሰብ እስከቻልኩ ችግር የለውም›› በማለት ትዳርን ማዘግየት ይመርጣሉ፡፡ እንደ መደመር የስሌት ህግ ህይወት አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ስለመሆኑ እርግጠኛ የማይኮንበት አጋጣሚን ስለሚፈጥር አንዳንድ ሴቶች 35-45 ባለው የዕድሜ ክልል ትዳርን ሲይዙ አንዳንድ ወንዶች 19 ዓመታቸው ወይም 60 ይፈፅማሉ፡፡

በትዳር አጋሮች መሀከል ሊኖር የሚገባ የዕድሜ ልዩነት ስንት መሆን አለበት?

በወንዶችና በሴቶች መሀከል በትዳር ውስጥ ሊኖር የሚገባው የዕድሜ ልዩነት እንደ ሰው ምርጫ ይለያያል፡፡ በሴቶች ዘንድ ተለቅ ያለን ወንድ የማግባት አዝማሚያ በፊትም እንዲሁም አሁን ላይ ያለ ድርጊት ነው፡፡ በፊት ጠና ያለ ወንድ የትዳር አጋር የሚሆንበት አጋጣሚ የባህል ተፅዕኖ ሲሆን በአሁኑ ዘመን ሴቷ ለስኬት፣ ለፍቅር ወይም የተደላደለ ህይወት ፍለጋ ከእርሷ ጠና ያለን ወንድ ለትዳር የምትመርጥበት አካሄድ ይስተዋላል፡፡ በጥቅም የሚመሰረት ትዳርም እድሜን ታሳቢ አያደርግም፡፡ የሀገራችን የቤተሰብ ህግ ‹‹ሀብትሽ ሀብቴ›› የሚል አሰራር ስላለው፣ ህጉም በጋብቻ ወቅት ያለውን የወንዱን ንብረት ሴቷ ከጋቻ በኋላ በሚኖረው ፍቺ እኩል የመካፈል መብትን ይሰጣታል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ ወጣት ሴቶች 20 ዓመት ታላቃቸው ጋር በፍቅር ጭምብል ሽፋን ለገንዘብ ብለው ትዳር ይፈጽማሉ፡፡ በሌላ እይታ ፍቺንና የንብረት ክፍፍልን ሰንቆ የተነሳ ትዳር መጨረሻው ምን እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡

ሆኖም በትዳር አጋሮች መሀከል ያለ የዕድሜ ልዩነት በትዳር ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ወንዱና ሴቷ ከተለያየ ትውልድ ውስጥ ከሚመደብ የዕድሜ ክልል ከሆኑ በቀላሉ ለመግባባት ይቸግራቸዋል፡፡ በፊተኛው ትውልድ ውስጥ ከሚመደብ የዕድሜ ክልል ከሆኑ በቀላሉ ለመግባባት ይቸግራቸዋል፡፡ በፊተኛው ትውልድ ውስጥ የነበረ ቀልድ በአሁኑ ትውልድ አመለካከት ከአዝናኝነቱ ይልቅ አናዳጅነቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ሌላው ችግር በወሲብ አለመጣጣም ሲሆን ለምሳሌ ያህል ሴቷን ወደ ሌላ የዕድሜ አቻዋ እንድታዘነብል ሊያደርጋት ይችላል፡፡ ይህንን ከግምት በማስገባት በትዳር አጋሮች መሀከል በአማካይ 3-5 ዓመት የዕድሜ ልዩነት ቢኖር ይመረጣል፡፡ በሴቶችም ዘንድ በዕድሜ የሚልቁትን ወንድ የማግባት አዝማሚያ አለ፡፡ በማዘዝና በመፍራት ያደገች ሴት ከእድሜ ታላቅ ይልቅ ታናሽዋን ለማግባት ትመርጣለች፡፡ ለአንዳንዶቹ ዕድሜ የብስለት መለኪያ ሲሆን ለአንዳንዶች ዕድሜ አንድ ብሎ እስከ መቶ እንደሚቆጠር አሃዝ ነው፡፡ በተለያየ የአመለካከት አድማስ ስር ባሉ ሰዎች ዘንድ በአሁኑ ጊዜ ዕድሜ ትዳርን ከመያዝ አኳያ ይህን ያህል ቦታ አይሰጠውም፡፡ ህይወት በቀመር ተካፍሎ ተባዝቶ ተደምሮና ተቀንሶ በትክክል የሚመጣ አይደለም ብለው ስለሚያምኑ አንዳንዶች ትዳርን ብዙሃኑ በሚስማማበት የወንድና የሴት የዕድሜ ክልል ጋብቻ ለመፈፀም አይጨነቁም፡፡ የህይወት ፍሰት በራሱ ጊዜ ከጋብቻ ፌርማታ አድርሶ ወደ ትዳር ዓለም ያሳፍራል ብለው ስለሚያምኑ ትዳርን በተጠቀሰው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ለመፈፀም አይጨነቁም፡፡ የህይወት ፍሰት በራሱ ጊዜ ከጋብቻ ፌርማታ አድርሶ ወደ ትዳር ዓለም ያሳፍራል ብለው ስለሚያምኑ ትዳርን በተጠቀሰው የዕድሜ ክልል ለመያዝ ሃሳብ አይገባቸውም፡፡

ከአሸወይና ማዶ

የሴቶችን እንዲሁም የወንዶችን አማካይ ዕድሜ ባገናዘበ ይሁን ባላገናዘበ መልኩ በአገራችን የሚስተዋለውን የጋብቻ ተሳፋሪዎች ቁጥር ማስተዋልአዳጋች አይሆንም፡፡ ይህም ቁጥር በተጨባጭ የሚታየው በየዓመቱ በየዕድሜያችን ጎዳና የሚፈራረቁት የወርሃ ጥር እና የወርሃ ከሚያዝያ የጋብቻ ፌርማታ ተሳፋሪዎች ብዛት ነው፡፡ በመኪና ጢሩንባ፣ በእጅ ጭብጨባ እና እልልታ እንዲሁም በሃይማኖታችን እስከ ህይወታችን ፍጻሜ በታማኝነት፣ በመቻቻል፣ በመደጋገፍ በመዋደድ ለመጽናት ምለን ጋብቻችን እንፈጽማለን፡፡ ከአሸወይናው ማዶ ያለውን የትዳር የህይወት ጎዳናን ፍቅር እና መቻቻል የተቃና እንዲያደርገው ከአባትና ከእናቶቻችን የምንለማው ነገር ነው፡፡

በዕድሜ፣ በፍቅር፣ በአመለካከት የልባችን ምርጫ የሆነችን እንዲሁም 20 ዓመታት በኋላም ቢሆን ልናፈቅራቸው እንደምንችል እርግጠኛ የምንሆንበትን አጋር ማግባት ትዳርን እንዲጸና ከማድረጉ ባሻገር በትዳር ፌርማታ ተሳፍረን ባለመግባባት ፌርማታ ከመውረድ ይታደገናል፡፡

ጄ/ል አበበ “የኢሳያስን መንግስት ማስወገድ ያስፈልጋል” አሉ –የአሰብ ወደብን እንዴት ማስመለስ እንደሚቻል ተናገሩ

$
0
0

abebe Tekelehianot

(ዘ-ሐበሻ) የቀድሞው የአየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖት  አበበ ተከለሃይማኖት ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ ከወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በሰሞኑ የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጊያ ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጡ:: በአስተያየታቸው “ፖለቲካዊ ጥናቶች ተጠንተው የኢሣያስ መንግስት መውደቅ አለበት፡፡ የኤርትራ ጉዳይ የራሣቸው የኤርትራውያን ጉዳይ ነው ይሄን እናከብራለን፡፡ ነገር ግን ለኛም ለነሱም ይሄ መንግስት ስጋት ነው፡፡ ” ብለዋል:: የአሰብ ወደብንም እንዴት ማስመለስ እንደሚቻል የሚናገሩበትን ቃለምልልስ እንደወረደ ያንብቡት::

መንግስት ሰሞኑን በኤርትራ ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡ አሁንም እንደ ቀድሞው ጭልጥ ወዳለ ጦርነት የምንገባ ይመስልዎታል? ለመሆኑ የሁለቱ አገራት የድንበር ግጭት እንዴት ነው ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኘው?
ሁለት ነገሮችን ማየት ያስፈልጋል፡፡ አንደኛ ከኤርትራ እንደ ኤርትራነቷ የሚመጣ ችግርን፣ በሁለተኛ ደረጃ ጂኦ ፖለቲክሱን መሠረት አድርጐ ማየት ይቻላል፡፡ አሁን መንግስት እየሰጠ ያለው መልስ ኤርትራን እንደ ኤርትራ በማየት ብቻ ነው። ያው እኛ እያደግን ነው፤ ኤርትራ በቀውስ ውስጥ ነው ያለችው፤ ስለዚህ ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ እየወሰድን እናቆመዋለን የሚል ነው፡፡ ይሄ እንደኔ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው፡፡ ኤርትራ ብቻ ለኢትዮጵያ ስጋት ወይም ጠላት አይደለችም። ግን አሁን ያለው የኤርትራ መንግስት ተላላኪ ነው፤ገንዘብ ያገኘበት የሚሄድ ነው፡፡ ገንዘብ ካገኘ ወደ ሣኡዲ ይሄዳል፤ ካላገኘ ደግሞ ወደ ኢራን፣ ብቻ ገንዘብ ወዳገኘበት የሚሄድና ተልኮ ፈፃሚ የሆነ መንግስት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኤርትራ ነፃ ሀገር ነች፤ በኤርትራ የውስጥ ጉዳይ መግባት የለብንም፤ ግን እሷም በኛ ጉዳይ እንድትገባ እድል መስጠት የለብንም፡፡ በተለይ በታጠቀ ሃይል ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሙከራ በሚደረግበት ጊዜ ይሄ መንግስት አቅም እንዲኖረው መፍቀድ የለብንም፡፡ ይሄ በኤርትራ ታጥሮ ሲታይ ነው። በአጠቃላይ ግን ከጂኦ ፖሊቲክስ አንፃር ሲታይ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ሱዳን ላይ ሠፊ ኢንቨስትመንት አላቸው፤ ድጋፍም እያደረጉ ነው። አረቦቹ በሶማሊያ፣ በጅቡቲም የራሣቸው እቅድ አላቸው፡፡ በኤርትራም የአሰብን ወደብ ከመጠቀም አንስቶ የራሣቸው እንቅስቃሴ አላቸው፡፡ ኤርትራ መረማመጃ ልትሆን ትችላለች፡፡ የኤርትራ መንግስት ይሄ ሁሉ ተልዕኮ እያለው፣የኛ መንግስት ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የምወስደው ማለቱ አስቂኝ ነው የሚሆነው፡፡ በአንድ በኩል ለ18 አመታት በዚያ በኩል እየደማን ነው ያለነው፡፡ ብዙ ሰው አልቋል። ጦርነት ሲከፍቱ ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን የሚሉት፣ እኔ እንደሚመስለኝ ከኛ ወገን 200 ሰው ከሞተ፣ ከነሱ 1000 ከገደልን ይበቃል እንደማለት ነው፡፡ እንዲህ እያደረግን እስከ መቼ እንቀጥላለን? ሃገራችንን ለማፍረስ በይፋ የተናገረ መንግስት፣ ኤርትራ ውስጥ እንዲኖርስ ለምን እንፈቅዳለን? መፍቀድ የለብንም፡፡
ምን ማድረግ ይቻላል…?
ፖለቲካዊ ጥናቶች ተጠንተው የኢሣያስ መንግስት መውደቅ አለበት፡፡ የኤርትራ ጉዳይ የራሣቸው የኤርትራውያን ጉዳይ ነው ይሄን እናከብራለን፡፡ ነገር ግን ለኛም ለነሱም ይሄ መንግስት ስጋት ነው፡፡ በረዥም ጊዜ ታቅዶ፣ ይሄ መንግስት የሚወድቅበት ነገር መፍጠር አለብን፡፡ ሶማሊያ አልሸባብን ለማስወገድ እንደገባነው ማለት ነው፡፡ ሶማሊያ ሄደን ካጠቃን፣ አስመራ ሄዶ ማጥቃት ሃጢያት አይሆንም። ራሳችንን መከላከል ነው፡፡ በቃ የኤርትራ መንግስት እንደ አልሸባብ ለደህንነታች ስጋት ነው ካልን፣ አልሸባብ ላይ ያረፈው ጡንቻ የሻዕቢያ መንግስት ላይም ማረፍ አለበት፡፡ በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲ፣ በወታደራዊ ስልት ጉዳዩን መመልከት አለብን፡፡
ይሄ ምን ያህል አዋጪ ነው? ኤርትራን የበለጠ ወደ ቀውስ አይከታትም?
መጀመሪያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች መሰራት አለባቸው፡፡ አንድ መገንዘብ ያለብን ጉዳይ፣ ኤርትራ ውስጥ ያለው መንግስት የወደቀ ነው፡፡ አሁንም በሆነ መንገድ ሊወድቅ ይችላል፡፡ የፈራነው መምጣቱ አይቀርም፡፡ እንደዚህ አይነት መንግስት ኤርትራ ውስጥ እንዲኖር መፍቀድ የለብንም፡፡ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የማትከጅል ሀገር መፍጠር አለብን፡፡ ከኤርትራ ህዝቦች ፀረ – አገዛዝ ትግል ጋር በመሆን፡፡
አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች “የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ ነው” የሚል አቋም በመያዝ፣ ሥልጣን ላይ ሲወጡ ወደቡን እንደሚያስመልሱ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ በአሰብ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አቋም ምንድን ነው?
እንግዲህ የማስተርስ ትምህርቴን አጥንቼ መመረቂያ ፅሁፌን እስክሰራ ድረስ የነበረኝ አቋም አሰብ የኤርትራ ነው የሚል ነበር፡፡ እኛ የማንንም ሀገር መሬት መውረር የለብንም የሚል አቋም ነበረኝ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ዳግም ኢትዮጵያ እንዳትወረር ጠቅላላ መደምሰስ አለብን፤አሰብን ግን መያዝ የለብንም የሚል ነበር አቋሜ፡፡ አሰብ ከተወሰደብን በኋላ የኛ መብት ምንድን ነው? የሚል ጥናት አደረግሁኝ፡፡ በጥናቱ ሂደት ግን አለማቀፍ ህግ እኛ በወደቡ የመጠቀም መብት እንዳለን አረጋግጦልኛል፡፡ ከህግ አኳያ መብት አለን፤በኔ ጥናት ሉአላዊ የሆነ መብት አለን፡፡ አሁን በዚህ ሃሳብ ውስጥ ነኝ፡፡
አሰብን እንዴት ነው ማስመለስ የሚቻለው?
መጀመሪያ የሻዕቢያን ጉዳይ መፍታት አለብን፡፡ በሁሉም የፖለቲካ ስራዎችና ድርድሮች፣ አለማቀፍ ህጎችን በመጠቀም ማስመለስ ይቻላል፡፡ በሰላም ብቻ ነው ማስመለስ ያለብን የሚለው አይሰራም፤ የሁሉም እንቅስቃሴ ውጤት ነው፡፡ ጡንቻ የዚያ አካል ነው፡፡ ለምሳሌ ኤርትራ ባድመ ተፈርዶላታል፤ ግን ጡንቻ ስለሌላት መብቷን ማረጋገጥ አልቻለችም፡፡ ግን ኪሳራውን ለመቀነስ ድርድርን ማስቀደም መልካም ነው፡፡
የኢትዮጵያና የኤርትራን ሰላም ለመመለስ እርቅ አማራጭ አይሆንም?
በእርግጥ ኤርትራና ኢትዮጵያ በኮንፌደሬሽንም በፌደሬሽንም አንድ የሚሆኑበት ሁኔታ ነበር። የኢሳያስ መንግስት ነው ኢትዮጵያን በመውረር ያንን እድል ያበላሸው፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ የሚሆኑበት ወርቃማ እድል ይፈጠር ነበር፡፡ ይህ የሚሆነው በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ፍላጎት ነው፡፡ ኢሳያስ ግን ይሄን ወርቃማ እድል አበላሽቶታል፤ስለዚህ የኢሳያስ መንግስት እያለ እርቅና ሰላም የሚኖር አይመስለኝም፡፡ እርቅ ስንል ኢሳያስና አቶ ኃይለማርያም እርቅ እንዲያደርጉ አይደለም፤ የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦች ናቸው። ይሄ ደግሞ የኢሳያስ መንግስት እያለ የሚሆን አይመስለኝም፡፡
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ኤርትራን በጦርነት ለመግጠም በቂ አቅምና ዝግጅት አላት ብለው ያስባሉ? ከወታደር ቁጥር ጀምሮ በጦር ስልጠና ኤርትራ እንደምትልቅ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የኤርትራ መንግስት ሌላውን አገራዊ ሃላፊነቱን ወደ ጎን ትቶ፣ ወታደራዊ አቅሙን ሲገነባ ነው የኖረው ይባላል——
በመጀመሪያ ፊዚካል የወታደር ወይም የአውሮፕላን አሊያም የታንክ ቁጥር አይደለም ጦርነት የሚያሸንፈው፡፡ ጦርነቱ ፍትሃዊ ነው አይደለም የሚለው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ኤርትራን ያለ አግባብ ለመውረር ከሄደች ለማሸነፍ ያስቸግራታል፤ ፍትሃዊ ስላልሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ የወታደራዊ ዶክትሪኑ ወሳኝ ነው፡፡ ማን ነው የሚያሸንፈው ለሚለው ጥያቄ፣ ፍትሃዊነት መልስ ይሰጣል፡፡ ፍትሃዊ ከሆንን፣ ኤርትራ ኢትዮጵያን መቋቋም አትችልም፡፡

ሰሞኑን መንግስት በሶማሊያ ከአልሻባብ ታጣቂዎች የተሰነዘረውን ጥቃት በአስተማማኝ ሁኔታ መክቻለሁ ብሏል … በሶማሊያ ያለው ሁኔታ መጨረሻው ምን ይመስልዎታል? የኢትዮጵያ ሰራዊት በሶማሊያ ያለውን እንቅስቃሴና ውጤቱን እንዴት ነው የሚገመግሙት?
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሶማሊያ ድረስ ዘልቆ የሀገራችንን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚደገፍ ነው፡፡ አሁን ብቻ ሳይሆን በ1998 እና 99 ዘልቆ በገባበት ጊዜ የኢትዮጵያን ደህንነት ለማረጋገጥ መዝመት ነበረበት፡፡ ያኔ እኔ በአሜሪካ ወታደራዊ ህግና አለማቀፍ ህግ እየተማርኩ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ በገባበት ጊዜ በተማሪዎችና በአስተማሪዎች መካከል ሰፊ ክርክር ነበር፡፡ ኢትዮጵያ መግባት አለባት የለባትም የሚለው ብዙ አከራክሮናል፡፡ በወቅቱ ባቀረብኩት ጽሁፍ ኢትዮጵያ ዘልቃ መግባቷ ተገቢ ነው የሚል አቋም ነበር ያንፀባረኩት፤አሁንም ያ አቋሜ እንዳለ ነው፡፡ ዛሬ በሰላም እንድንኖር እዚያ ያለው መከላከያ ኃይላችን እያደረገ ያለውን ነገር በክብር ነው የማየው፡፡
በቅርቡ እንግዲህ የተፈፀመውንም ሰምቻለሁ፤ የመከላከያ ኃይላችን ለወሰደው የአፀፋ እርምጃ ላመሰግነው እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ መሃል ግን እዚያ የተሰዉ የኛ ወታደሮችና የጦር አመራሮች አስክሬናቸው ወደ ሀገር መጥቶ በክብር እንዲቀበሩ መደረግ አለበት፡፡ ሌላው ሰራዊቱ ከሶማሊያ መቼ ነው የሚወጣው የሚለው ስልት ከወዲሁ መነደፍ አለበት፡፡ ይሄ ከሌለ ለረዥም ጊዜ ጦርነት ውስጥ መቆየት ሊኖር ይችላል፡፡
መንግስት በጦርነቱ የተሰዉ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ቁጥር ገልጾ አያውቅም፡፡ በኢራቅና አፍጋኒስታን ውጊያ ላይ የሞቱ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ አገራቸው ተወስደው በታላቅ ወታደራዊ ክብርና ሥነሥርዓት ነው የሚቀበሩት፡፡ የእኛ ምስጢራዊ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው?
ከትጥቅ ጊዜ ጀምሮ ያለው ልምድ፣ በክብር የሚያርፉት እዚያው በተሰዉበት አካባቢ ነው፡፡ በየሄዱበት የመቅበር ነገር ነው የነበረው፡፡ ትክክል ይሁን አይሁን ባላውቅም የተሰዉ ወታደሮች ቁጥር መግለፅ ከሞራል አንፃር አስቸጋሪ ነበር የሚል አመለካከት ነበር፡፡ ይሄ ልምድ እስካሁን ዝም ብሎ የቀጠለ ይመስለኛል፡፡ እኔ ግን ትክክል አይመስለኝም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ የተከፈለውን ዋጋና የተገኘውን ድል አውቆ ማመዛዘን ይኖርበታል፡፡ ይሄ መብት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ ቁጥሩን መደበቅ ተገቢ መስሎ አይታየኝም፡፡ በይፋ ቁጥሩ መታወቅ አለበት። ሁሉም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ድል ብቻ ሳይሆን ኪሳራውንም መመዘን አለን፡፡ ለህዝቡ ግልጽ መሆን አለበት፡፡ የሰው ህይወት ትልቁ ኪሳራ ነው፡፡ እዚህ መጥተውም በክብር አስከሬናቸው ማረፍ ይገባዋል። ለቤተሰቦቻቸውም ድጋፍ መደረግ አለበት፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተከታታይ በሚያቀርቧቸው ጽሁፎች፣ በመንግስትና በገዥው ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችቶች እየሰነዘሩ ነው፡፡ በመንግስት ላይ ጎልተው የሚታዩ ዋነኛ ችግሮች ምንድን ናቸው? እርስዎም የአቋም ለውጥ ላይ ያሉ ይመስለኛል—-
መቼም የአቋም ለውጥ የማያደርገው ድንጋይ ብቻ ነው፡፡ እኔ ከመጀመሪያውኑ ስታገልላቸው ለነበሩ አላማዎች፣አሁንም በፅናት ቆሜያለሁ ነው የምለው፡፡ ገዥው ፓርቲ ነው ከትግሉ አላማዎች ወደ ኋላ እየተንሸራተተ ያለው፡፡ የ25 ዓመት ጉዟችንን ስናየው፣ ይሄን ልንገመግም እንችላለን፡፡ ግን በቅርቡ እንኳ ያለውን የ10 ዓመት ጊዜ ብናይ፣ 97 ምርጫ ለኛ አንድ ወርቃማ እድል ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ የገባበት አጋጣሚ ነበር፡፡ በገዥው ፓርቲም በተቃዋሚውም በኩል በነበሩ ችግሮች ምክንያት ያ ተኮላሸ፡፡ በፊት ኢህአዴግ በተወሰነ ደረጃ ህዝቡን ያከብር ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ህዝብን መፍራት ጀመረና ህዝብን ማሳመን ሳይሆን መቆጣጠር የሚል አቅጣጫ ያዘ፤ ስለዚህ የተለያዩ ህጎች አወጡና ዲሞክራሲያዊ ሁኔታዎችን ማፈን ተያያዙ። እንግዲህ የኔ አቋም መነሻው ከዚህ ነው፡፡ ከህገ-መንግስቱ በመነሳት ነው አቋሜን የማንፀባርቀው። ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ መስፋት አለበት ነው የኔ አቋም፡፡ ኢህአዴግ የሚመዘነው በህገ-መንግስቱና በራሱ ፖሊሲ ነው፡፡ በኔ አመለካከት፤ ኢህአዴግ አሁን ህገ-መንግስቱንም እየሸረሸረ ነው፡፡ ህገ-መንግስቱን በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እያደረገ አይደለም፡፡ ለዚህ ደግሞ የሚካሄዱ ምርጫዎች ማሳያ ናቸው። በ1997 ምን አይነት ሁኔታ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ህዝቡ እድል ሲያገኝ ማንን እንዴት እንደሚመርጥ ያሳየበት ምርጫ ነበር፡፡ በ2002 ዓ.ም 96.6 በመቶ ነበር ገዥው ፓርቲ ያሸነፈው፡፡ በ2007 ደግሞ መቶ በመቶ ሆኗል፡፡
በ1997 የምርጫ ውጤት፤ ተቃዋሚዎች አዲስ አበባን ሲያሸንፉና በክልሎችም ያልተገመተ ድርሻ ሲያገኙ፣ ኢህአዴግ እንደ ድል ከመቁጠር ይልቅ ሽንፈት አድርጐ ቆጠረው፡፡ ከሕገ – መንግሥታችን ከራሱ ፕሮግራም አንፃር ድል ነበር። ግን ተደናገጠ፡፡ (ተቃዋሚዎቹም ቢሆኑ ያገኙትን ድል ተቀብለው፣ ለዚያ ያመቻቸላቸውን ህዝብና ኢህአዴግ አመስግነው እንደመቀጠል ተንጠራሩ። የመሪዎቻቸውን የግል ፍላጐት ለማሟላት ሲሉ በአቶ ልደቱ አያሌው የሚመራውን ኢዴፓ ምክር ትተው ተወራጩ፡፡ የአገሪቱን ሰላምና እድገት ከማሰብ ይልቅ በጊዚያዊ ስሜት ተነስተው ነጐዱ፡፡
በዚህም ከዴሞክራታይዜሽን አንፃር የተገኘውን ወርቃማ ዕድል የኢትዮጵያ ህዝቦች ተነጠቁ፡፡ ኢህአዴግ በመጀመሪያ የአዲስ አበባ ከተማን ስልጣን ወደ ፌደራል በከፊል ከመውሰድ ጀምሮ ያኛው ወርቃማ ዕድል ተመልሶ እንዳይመጣ የተለያዩ እርምጃዎች ወሰደ፡፡ የተቃዋሚ መሪዎችን ሰብስቦ ከማሰር ጀምሮ የተለያየ የህዝቦች አደረጃጀት እና አሰራር አመጣ፡፡
የፌደራል ተቋሞች የውጭ ጉዳይ፣ የመንግስት ሚዲያ፣ ወዘተ ዳኞችም ሳይቀሩ ከክልሎች አምጥቶ አስገባ፡፡ የሲቭል ሰርቫንቱን ሙያተኛነት የሚገድል ውሳኔ ነበር፡፡ ህዝብን ማሳመን ሳይሆን ህዝብን መቆጣጠር በመሆኑ የፓርቲ አባሎች ሲመለምል ከጥራት ይልቅ ብዛት ላይ በማተኮር በሚልዮኖች መለመለ፡፡ ሲቪል ሰርቫንቱ በብቃት ሳይሆን በአባሎቹ ተሞላ፡፡ ከዩኒቨርሲቲ “A” ከማምጣት ከኢህአዴግ “C” ማግኘት ይሻላል ተባለለት፡፡
አንደምታው መሰረታዊ ነው፡፡ ምርጫ ለመቆጣጠር የአንድ ለአንድ አሰራር ዘርግቶ፣ የያንዳንዱን ዜጋ መመዝገብ በተዘዋዋሪም ኢህአዴግን የመረጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ተንቀሳቀሰ። (አሁን አንድ ለአምስት ሆኗል፡፡)
በአጠቃላይ ሐቀኛ ተቃዋሚዎችና ተቃውሞን ለማፈንና ለማዳከም ልዩ ልዩ ስራዎች ተሰሩ፡፡ (የፓርላማ ስነ ስርዓት፣ የፓርቲዎች ሕግ) ወዘተ…ዴሞክራሲያዊ ምሕዳሩ እየጠበበ ሄደ፡፡
እርስዎ በብዕርዎ የሚታገሉት በዋነኝነት ምን ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ ነው?
ለሕገ መንግስቱ በተሟላ መንገድ መተግበር የአቅሜን ያህል እታገላለሁ፡፡ ምክንያቱም ሕገ – መንግስቱ የአገራችንን ችግር የሚፈታና የሁሉም ሕጐች የበላይ በመሆኑ የማክበርም ግዴታ ስላለብኝ ነው፡፡ በተጨማሪም ከወጣትነቴ ጀምሮ የታገልኩለትን ዓላማ የሚያንፀባርቅና የህዘቦች መስዋእትነት ውጤት ነው፡፡ በተለይም እኔ ስታገልበት የነበረው በህወሓት መሪነት የትግራይ ህዝብ በከፈለው እጅግ ከፍተኛ መስዋእትነት እንዲሁም፣ በተሰውት ጀግኖች፣ (በተደጋጋሚ በተቃጠሉ መንደሮች፣ በአውሮፕላን ድብደባ ወዘተ) የመጣ ውጤት በመሆኑ ሕገ መንግስቱን የማስጠበቅ ጉዳይ እንደሌላው ታጋይ ሞራላዊ ግዴታ አለብኝ ስለምል ነው፡፡
ኢህአዴግ የጀመረው መልካም አስተዳደር የማስፈን ዘመቻን በተመለከተ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
እኔ አንደኛው የምቃወመው፣ ለምሳሌ የመልካም አስተዳደር ጉዳይን መንግስት ከቢሮክራሲ ጋር ያየዋል፤ ይሄ ትክክል አይደለም፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግር ፖለቲካዊ ነው፤ የዲሞክራሲ ማጣት ውጤት ነው፡፡ ችግሩ የሚጀምረው ከላይኛው አመራር ነው፡፡ እላይ ከተስተካከሉ ከስር ይስተካከላል፡፡ የወረዳውንና የቀበሌውን እያሰሩ፣ እላይ ያሉት እርስ በእርሳቸው ሳይገማገሙ ሳይተጋገሉ ያሉበትን ሁኔታ አጥብቄ እቃወማለሁ፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ መተጋገል የለም፡፡
በቅርቡ በድረ-ገፆች በተሰራጨ ፅሁፍ፤ “ደርግነት እየመጣ ነው” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል…ምን ለማለት ፈልገው ነው?
ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ እየጠበበ ነው፡፡ በተለይ ከ97 ጀምሮ ያሉትን ነገሮች ስናያቸው፣ ህጎች የሚባሉት ተግባራዊ ሲደረጉ የሰውን ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት ለማፈን ነው። አንዳንድ ሰዎች የኢህአዴግን መንግስት በብዙ መልኩ ዝርክርክ ነው ይሉታል፡፡ አንድ ውጤታማ የሆነበት ጉዳይ ቢኖር፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብትን ማፈን ነው፡፡ የፕሬስ ነፃነት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ፣ የዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና ተቃውሟቸውን የማሰማት መብቶችን—ስናይ እየጠበበ ነው የመጣው፡፡ አሁን ደግሞ የሲቪል አስተዳደሩ አልቻለም፤ ተዳክሟል የሚባል ነገር ሲመጣ፣ አንዳንድ የወታደር መሪዎች፤ “እኛ እንሻላለን፤እኛ ጥሩ ነው ያለነው፤የደከመው ሲቪሉ ነው; እያሉ በአደባባይ መናገር ጀምረዋል፡፡ ደርግነት የሚመጣው እንግዲህ ሲቪሉ መግዛት ሲያቅተውና “ወታደሩ እኔ እሻላለሁ” ማለት ሲጀምር ነው፡፡ ከዚያ በኋላ እየጨለመ የመጣው ዲሞክራሲ፣ ወደለየለት አምባገነንነት ያመራል ማለት ነው፡፡
ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ እየጠበበ ደርግነት እያቆጠቆጠ፣ በመንግስትም ከመንግስት ውጪም ማፍያዎች እየታዩ ነው ስል፡ “ብዙ ሰዎች አንተ አትፈራም እንዴ? ሊገድሉህ ሊያስሩህ ይችላሉ” ይሉኛል፡፡ ለስጋታቸው አመሰግናለሁ፡፡ በተዘዋዋሪ መንገድ ግን መታገል አለብህ እያሉኝ ነው፡፡ ሃሳቡን በሠላማዊ መንገድ የገለፀ ሰው ጥቃት ይፈፀምበታል ካላችሁ፣ ይሄ ነገር ሊኖር እንደሚችል ሳላውቀው አይደለም ወደዚህ የገባሁት፡፡ መጀመሪያ በ “ካራክተር አሣስኔሽን”፣ ከዚያም የተለያዩ ጥቃቶች ሊፈፀሙ ይችላሉ፡፡ እንግልት… መሞት… መታሰር ያስፈራል፡፡ ያስጠላልም፡፡ እኔ ከሁሉም የምፈራው ፈርቶ በቁም መሞትን ነው፡፡ ፈርቶ የህሊና እስረኛ መሆንን ነው፡፡ በተለይ ወጣቶች ከዚህ የህሊና እስርና በቁም መሞት በላይ ምንም እንደሌለ ተገንዝበው መታገል አለባቸው፡፡
በትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሳተፈውን ሜቴክ በመጥቀስ፣ ኢኮኖሚውና ኢንዱስትሪው በወታደሩ ቁጥጥር ስር መዋሉ ትክክል አይደለም ብለው የሚቃወሙ ወገኖች አሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?
በመጀመሪያ ከህግ አኳያ ሲታይ፣ ሜቴክ ወታደራዊ ተቋም አይደለም፡፡ ወታደራዊ መሪዎች ያሉበት የሲቪል ተቋም ነው፡፡ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፡፡ ስለዚህ ወታደራዊ ተቋም ሳይሆን የራሱ ሰውነት ያለው ተቋም ነው፡፡ ግን በህብረተሰቡ ዘንድ ይህ ግንዛቤ የለም፡፡ አብዛኛው ሰው የመከላከያ ተቋም እንደሆነ ነው የሚያስበው፡፡ ለሰው ሜቴክ ተጠሪነቱ ለመከላከያ ነው የሚመስለው፡፡ በእርግጥ የመከላከያ ታንክና የሜቴክ ገንዘብ ከተጨመረበት በጣም አደጋ ነው የሚሆነው፡፡
ከዚያ በላይ ግን የሚያሳስበው ዝርክርክነቱ ነው፡፡ ባለፈው ፓርላማ፣ በስኳር ፕሮጀክቶች ላይ የቀረበው እንደ ቀላል ነገር መታየት የለበትም፡፡ ገና አንድም ነገር ሳይጀመር ሙሉ ገንዘብ መስጠት ምን ማለት ነው!? 2005 ላይ ማለቅ የነበረበት ፕሮጀክት እስካሁን ሲዘገይ፣ መንግስት ጉዳዩን በሚገባ ማየት አለበት፡፡ ስለዚህ ከፓርላማው ብዙ እንጠብቃለን። ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ብዙ እንጠብቃለን፡፡ ተጣርቶ ለህዝብ መቅረብ አለበት። ለመሆኑ ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ይሄ ሁሉ ሲሆን የት ነበር? ከዚህ ጉዳይ በመነሳት ጠቅላላ ስርአቱንም መገምገም ያስፈልጋል፡፡ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ማየት ይጠይቃል፡፡ እኔ እንደሰማሁት ሜቴክ ወደ 275 ቢሊዮን ብር ነው የሚያንቀሳቅሰው። ይሄ ነገር በህግና ስርአት ካልተመራ አደገኛ ነው፡፡ መንግስት ይሄን መገምገም አለበት፡፡ ጥሩ ከሰራ ጥሩ ሰርቷል ማለት፣ ካልሰራ ደግሞ ማስተካከል አለበት፡፡ ሜቴክ የመከላከያ ተቋም ነው የሚሉ ሰዎች፣ብዙ ጊዜ እንደ ስጋት የሚገልፁት፣ ጠመንጃና ገንዘብ ሲገናኙ አደገኛ መሆናቸውን ነው፡፡
ኢህአዴግ ያለፈውን ሥርዓት አስወግዶ ሥልጣን ሲይዝ፣ የደርግን ወታደራዊ ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ማውደሙ ተገቢ አልነበረም፤ባለው ላይ መቀጠል ነበረበት የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በተለይ አዲስ መንግስት በመጣ ቁጥር ሁሉንም አፈራርሶ ከዜሮ የመጀመር ባህል አገሪቱን ክፉኛ ይጎዳታል—-የሚል ሃሳብ ይንጸባረቃል፡፡ በዚህ ጉዳይ የእርስዎ አቋም ምንድን ነው?
እዚህ ላይ ሁለት ነገር ነው መታየት ያለበት፡፡ አንደኛው በሀገራች በአጠቃላይ ሲታይ፣ “ለውጥ” እና “ቀጣይነት” በሚለው መርህ አይደለም የምንሄደው። ደርግ የኃይለ ሥላሴን መንግስት ሲጥል ጠንካራ የነበሩትን ነገሮች በሙሉ አፍርሶ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ደርግን ስናስወግድ፣ ደርግና ሌላውን ነገር በተሟላ መንገድ ለይተን አይተነው ነበር የሚል እምነት የለኝም፡፡ መዋቅሩ አስቸጋሪ ስለነበር መቀየር ነበረበት፡፡ ነገር ግን የተሰሩ በጎ ነገሮችን ያየንበትና የተቀበልንበት መንገድ ችግር ያለበት ይመስለኛል፡፡ በአጠቃላይ ያለፈን ስርአት በጎ ነገር የመቀበል ልማድ በሀገሪቱ የለም፡፡ ይሄ መስተካከል ያለበት ነው፡፡
በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች፣እርስዎ በጀነራል ሳሞራ የኑስ ላይ የሰነዘሩት አስተያየት መነጋገሪያ ሆኗል …
አዎ! አንድ ጓደኛዬ፤ “ህወሓት ከሌለ ይሄ ህዝብ አይኖርም ይባላል” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “ኧረ እንዲህ ያለ ነገር የለም” አልኩት፡፡ “ኧረ የድሮ ጓደኛህ ነው ያለው” አለኝ፡፡ በእርግጥም ሊንኩን ነግሮኝ የተባለውን ሳነብ ማመን አልቻልኩም፡፡ ባለፈው የግንቦት 20 በዓል ላይም የቀረበው ነገር አጨቃጫቂ ነው፡፡ “የሀገራችን ችግር በህወሓትና በኢህአዴግ ብቻ ነው የሚፈታው” የሚል የምርጫ ቅስቀሳ ለምን እንደጀመሩ አይገባኝም። ድርጅት ድርጅት ነው፤ህዝብ ህዝብ ነው፡፡ ያ ድርጅት ከሌለ፣ ህዝብ የለም ማለት የሚያስኬድ አይደለም። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 87 ምን እንደሚል የታወቀ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ኢህአዴግ ከሌለ አይኖርም ማለት እብሪት ነው፡፡ ኢህአዴግንም ህወሓትንም የፈጠረው ህዝብ ነው እንጂ እነሱ ህዝብን አልፈጠሩም፡፡ በወቅቱ ጀነራሉ ይሄን ንግግር ሲያደርጉ፣ ከመድረክ ተሳስተዋል ያለ ሰው አልነበረም፡፡ ጀነራሉ የራሳቸው አስተያየት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ እንዲሉ ሕገ – መንግስት አይፈቅድላቸውም፡፡
በኔ አመለካከት ጀነራል ሣሞራ ለመንግስትና ለህዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ያለው ነገር የጠቅላይ አዛዡ የአቶ ሃይለማርያም ስራ ነው የሚሆነው። መተካት ካለባቸው ግን በጀነራል ፃድቃን መሆን የለበትም፡፡ እሣቸውም የሚፈልጉት አይመስለኝም፡፡ ጀነራል ፃድቃን በአመራር ብቃታቸው የተመሠከረላቸው፣ በሄዱበት ጥሩ አመራር መስጠት የሚችሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን በመከላከያ ውስጥ በጀግንነትና በብቃታቸው የተመሠከረላቸው ወጣት የጦር አዛዦች ስላሉ መተካት የሚያስፈልግ ከሆነም በነሱ ነው መተካት የሚኖርበት፡፡
እርስዎና አንዳንድ የቀድሞ አመራሮች፣በመንግስት ላይ ጠንካራ ትችት የምትሰነዝሩት ወደ ስልጣን ለመመለስ ፍላጎት ስላላችሁ ነው ይባላል፡፡ እርስዎ ተመልሰው ሥልጣን ለመያዝ ያስባሉ?
የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንዳንድ ጊዜ ኮንስፓይሬሲ ቲዎሪ ይበዛበታል፡፡ መስፍናዊ ዳራ አለው፡፡ ደርግ የፈጠረው ጫና አለ፡፡ አሁንም የሚፈጠር ጫና አለ። ስለዚህ ሰው በአገሩ ጉዳይ ላይ የመሰለውን ሃሳብ ሲያቀርብ፣ ቁም ነገሩ ምንድን ነው? የሚለውን በተሟላ መንገድ ሳያይ የራሱ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል፡፡ ለራሱ ስልጣን ፈልጎ ይሆን? የሚል ጥያቄም ያነሳል፡፡ በራሴ በኩል እኔ የማንም ከለላ የለኝም፤ የማንንም ከለላ አልፈልግም፡፡ የሀገራችን ሁኔታ ያሳስበኛል፤ ህገ መንግስቱ ያወጀልን መብት አለ፡፡ ይሄን መብቴን ተጠቅሜ በተቻለኝ መጠን ከጥናት ተነስቼ ያለኝን ሃሳብ አቀርባለሁ፡፡ በተረፈ እኔ ወደ ስልጣን የመመለስ ምንም አይነት ሀሳብ የለኝም፡፡ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ በምርምር ሀገሬን የማገልገል ፍላጎት ነው ያለኝ፡፡ ስልጣን ብፈልግ ኖሮ መሞዳሞድ ነበር የሚጠበቅብኝ፡፡
ጀነራል ሰሞራ በጄኔራል ፃድቃን መተካት አለባቸው ብለው አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች አሉ የእርሶ አስተያየት ምንድን ነው?
እንግዲህ 25 ዓመት ነው የቆየነው፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የሰራዊቱ የብሄር መመጣጠን እየተስተካከለ መጥቷል የሚል ግምት ነው ያለኝ። ወታደራዊ አመራሩም (chief of staff) የትግራይ ተወላጆች ርስት መሆን የለበትም፡፡ ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በብቃታቸውና በጀግንነታቸው እዚያ ደረጃ ላይ መድረስ የሚችሉ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ለትግራይ ህዝብ የሚጠቅመው ከብሄር ብሄረሰብ የተውጣጣ ብቁ አመራር ሲኖር ነው፡፡ የትግራይ ልጅ ስልጣን ላይ ስለተቀመጠ አይደለም፡፡
በዚህ ዓመት ከወትሮ በተለየ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ቀውሶች ተከስተዋል፡- በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በትግራይ—-ህዝባዊ ተቃውሞዎችና ግጭቶች ነበሩ፡፡ የእነዚህ ቀውሶች ምክንያት ምን ይመስልዎታል?
እዚህም እዚያም የሚታዩ ችግሮች ምንጫቸው፣ አንደኛው የዲሞክራሲ ጥያቄ ነው፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች መንግስት በተሟላ መንገድ መፍታት አልቻለም፡፡ ሁለተኛ ከሙስና ጋር በተያያዘ ያሉት ችግሮች ናቸው። እነዚህን ችግሮች ገምግሞ ማስተካከል ከተቻለ ሊፈቱ ይችላሉ፡፡ በመንግስት የላይኛው አመራር ያለውን ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ በሚገባ መፈተሽ ያስፈልጋል። ህገ-መንግስቱ እስከተከበረ፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ፣ ህገ-መንግስታዊ ተቋማት ስራቸውን በሚገባ መስራት እስከቻሉ ድረስ፤ ፓርቲና መንግስት የተለያዩ መሆናቸው ታውቆ አሰራሩ በዚህ እስከተለወጠ ድረስ ችግሮችን መፍታት አይገድም፡፡
ችግሮችን የቢሮክራሲ ብቻ አድርጎ ከታየ ግን አደገኛ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ በዋናነት ኢህአዴግ ከህዝቡ ጋር ሆኖ ተቃዋሚዎቹን አሳትፎ፣ አሁን ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍታት አለበት። የወታደሩ ተፅዕኖ መቆም አለበት፡፡ ወታደሩ ወደ ካምፑ መግባት አለበት፡፡ ይህ ሲሆን ቀውሱ የመፈታቱ እድል ከፍተኛ ነው የሚል እምነት አለኝ።
አሁን ለውጥ በሚፈልጉና በማይፈልጉ ኃይሎች መካከል ያለው ግጥሚያ ፍንትው ብሎ ወጥቶ መጥራት ይኖርበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በየጊዜው በሚያነሷቸው ሃሳቦች፣ ለውጥ ፈላጊ መሆናቸውን የሚያሳዩ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ በተግባር ግን የሚውሉ አይደሉም። በተግባር የማይውሉበት ምክንያት እነዚህን ሃሳቦች የሚያኮላሽ አንድ ያልተደረሰበት ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ይሄ መፈታት ይኖርበታል፡፡ ቀውሶቹ የመጡት ከዲሞክራሲ ጥያቄ፣ ከፍትህ ፍለጋ፣ ብልሹ አስተዳደርና ሙስናን ከመቃወም ነው። አንዱ ችግር ኢህአዴግ ህዝብ መስማት ማቆሙ ነው፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት ህዝቡን የግድ ማዳመጥ አለበት፡፡
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የብሄር ቅራኔዎች የሚፈጥሯቸው ግጭቶች በተደጋጋሚ ይታያሉ። የፌደራሊዝም መምህር እንደመሆንዎ፣መፍትሄው ምንድን ነው?
ህገ መንግስቱ ለአውሮፓውያን (እንደ ስፔን ላሉ ሀገራት) ተምሳሌት የሚሆን ጭምር ነው፤ ችግሩ ያለው ህገ መንግስቱን መተግበር ላይ ነው። ይህቺ ሀገር በ1983 ዋዜማ የነፃ አውጭዎች ሀገር ነበር የምትባለው፡፡ ይሄ ህገ መንግስት የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በማስከበርና ችግሮችን በመፍታት በኩል ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ የፌደራል ሥርዓቱ ሙሉ ለሙሉ በህገ መንግስቱ መሰረት ተግባራዊ ሳይደረግ ሲቀር ግጭቶቹ ሊመጡ ይችላሉ። ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ሽግግር ሲደረግ እነዚህ ግጭቶች ይኖራሉ፡፡ አሃዳዊ ስርአት ይሁን ቢባል ደግሞ የባሰ ነበር፡፡ እንደ ዩጎዝላቪያ መበታተን ሊመጣ ይችል ነበር፡፡ ይሄ ህገ መንግስት ዋና ችግሩ በሚገባ ተግባራዊ አለመደረጉ ነው፡፡ እስካሁን በመጠኑም ቢሆን ይሄን ፌደራላዊ ስርአት በእግሩ ለማቆም ጥረት ሲደረግ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ኋላ እየተመለስን ይመስለኛል፡፡
ለወደፊት ምን አይነት ስርዓት ይፈጠራል ብለው ነው ተስፋ የሚያደርጉት?
የኔ ተስፋ የተገኘውን ሰላም እና እድገት ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩ በቀጣይነት በማስፋት እንዲጐለብት ነው፡፡
አሁን በኦሮሚያ ይህን በሌሎች እየተቀጣጠለ ያለው የህዝብ መነሳሳት በሰላማዊ መንገድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና “ጠያቂ” ህዝቦች እንዲኖሩ ፀረ – ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩን እና ሙስናን እና ፍትሕ መጓደልን በጽናት የሚታገሉ ሲያስፈልግም ገዥው ፓርቲ እና በሱ የሚመራውን መንግስት በሰላማዊ ተፅእኖ ማስገደድ ሲችሉ ነው፡፡ ለዚሁም ሁሉም እንቅስቃሴ በሰላም እንዲሆን እና የነሱ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ለግላቸው ለመጠቀም ሁከት የሚጥሩትን ለመንግስት አሰልፎ በመስጠት ጭምር እንደታገሉ ነው፡፡
ሲብል ሶሳይቲ አሁን ካለው እንቅልፍ ተነስቶ ያለውን ሙሁራዊ ዓቅመ፣ ገንዘብ ትስስሩ መሰረት አድርጐ የተገኘውን በአምና እድገት የተጠናከረ መንገድ እንዲቀጥል በተሟላ መንገድ እንዲታገል ነው፡፡
ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ድርጅቶች ካላቸው Crisis ሰላማዊ መንገድ ተጠናክረው ወጥተው ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩ ለማስፋት ያለውን ሰላም እና እድገት እንዲቀጥል ነው፡፡
ወጣቶች በተለይ ምሁር በኛ ትውልድ የሚመሩት ድርጅት በወረራ በመቆጣጠር ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲሰይዙት አልያም የራሳቸው ድርጅት ፈጥሯል፡፡ Change and continustly በማመን የተገኘውን ሰላምና ዕድገት አስተማማኝ በሆነ መንገድ እንዲቀጥልበት ነው፡፡

የአገራችን ሦስቱ ሳጥኖች!! (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

$
0
0

“—- በገንዘብ መግዛት ሀብትን፤ በሥልጣን መግዛት ጉልበትን፣ በውበት መግዛት ፍትወትን፣ በመዋቅር መግዛት ሹመትን ያሳያል። በሐሳብ መግዛት ግን ልህቀትን ያመለክታል።

daniel-kibret-300x207ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ሳጥኖች አሉ። ሁለቱ ሳጥኖች በጣም ይፈለጋሉ። ስለሚፈለጉ ወይ ይዘረፋሉ፤ ወይ ይሰረቃሉ። አንደኛውን ሳጥን ግን ዞሮ የሚያየው የለም። ሁለቱ በውስጣቸው በጣም ተፈላጊ ነገር አለ ተብሎ ስለሚታመን፤ ሳጥኖቹ በፖሊስ በዘበኛ፣ አንዳንዴም በወታደር ይጠበቃሉ። አንደኛው ሳጥን ግን ጠባቂ የለውም። ውስጣቸው ያለው ነገር ሲጨምር የሚያመጡት ለውጥ አለ ተብሎ ስለሚታሰብ፣ ሁለቱ ሳጥኖች ቶሎ ቶሎ ይቆጠራሉ። አንደኛው ሳጥን ግን የሚያስታውሰው የለም።
ሁለቱ ሳጥኖች የምርጫ ሳጥንና የገንዘብ ሳጥን ናቸው። አንዱ ውስጥ ሥልጣን፣ ሌላው ውስጥ ገንዘብ አለ። ሥልጣን ያለበትን ሳጥን ፖለቲከኞች ይፈልጉታል። ስለዚህም ይሰብሩታል፣ ይገለብጡታል። ገንዘብ ያለበትን ሳጥን ሙሰኞች ይጓጉለታል። ይሰብሩታል፤ ይገለብጡታል። ሕዝቡም ስለ እነዚህ ስለ ሁለቱ ሳጥኖች ጉዳይ ይከታተላል። ሲዘጉና ሲከፈቱ ኮሚቴ ያቋቁማል። ሲቆጠሩና ሲመዘኑ ማወቅ ይፈልጋል። ሥልጣንና ገንዘብ ስላለባቸው።
ሦስተኛው ሳጥን ግን ከእነዚህ ሁሉ ይለያል። ዘጊ እንጂ ከፋች የለውም። ሠሪ እንጂ ተከታታይ የለውም። በውስጡ ያለውን ነገር ለማወቅ ባለቤቱም፤ ሕዝቡም አይጓጉም። ማንም እንደ ልቡ ያገኘዋል። ግን አይጠቀምበትም። ጥበቃ የለውም፤ ግን ማንም አይሰብረውም። ተመልካች ያጡ ወረቀቶችን በውስጡ እንደያዘ በየግድግዳው ላይ አርጅቷል። ሰዉም በዚህኛው ሳጥን ውስጥ ለማስገባት ብዙም አይፈልግም። እንደ ሁለቱ ሳጥኖች ፈላጊ የለውም ብሎ ያምናልና። ለምን?
ምክንያቱም ሦስተኛው ሳጥን ‹የሐሳብ መስጫ ሳጥን› ስለሆነ። ዓለምን የቀየረው ሐሳብ ቢሆንም እኛ ሀገር ግን ብዙም ፈላጊ የለውም። መሥሪያ ቤቶችም የተሰጣቸውን ርዳታ እንጂ የተሰጣቸውን ሐሳብ ሪፖርት አያደርጉም። ሀገር የምታድገው፣ የምትለወጠውና የምትሠለጥነው በሐሳብ ነው። ያውም በሰላ ሐሳብ። ያደጉ ሀገሮች ማለትም ታላላቅ አሳቢዎችና ታላላቅ ሐሳቦች ያሏት ሀገር ማለት ናት።
እስኪ አንድ እንኳን የሀገሪቱ መሪ፣ የፖለቲካ ልሂቅ፣ ባለ ሥልጣን፣ ሀገሪቱ ያፈራቻቸውን አሳቢዎች ከመጽሐፎቻቸው፣ ከንግግሮቻቸው፣ ከአባባሎቻቸው በንግግሩ ውስጥ ሲጠቅስ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? እውነት ዐሳቢዎች ሳይኖሩን ቀርተን ነው? ይህች ሀገርስ እንደ ሀገር ለዘመናት የኖረቺው ያለ ሐሳብ ነው? እንዴት ተደርጎ። ነገር ግን ለሐሳብና ለዐሳቢዎች የምንሰጠው ቦታ ኢምንት ስለሆነ ነው። በየቦታው የተጣሉት የሐሳብ መስጫ ሳጥኖች የሚነግሩንም ይኼንን ነው።
የአኩስምን ሐውልት ቆሞም ተጋድሞም አግኝተነዋል። ግን እነማን ነበሩ ያህንን ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ከአንድ ወጥ ድንጋይ ለመሥራት ያሰቡት? እንዴት ነበር ያሰቡት? ለምን ነበር ያሰቡት? ሐሳባቸውን በምን መንገድ ነበር የገለጡት? ጻፉት? ሞዴል ሠሩት? በሥዕል ገለጡት? በዜማ አቀረቡት? ከመላ ምት በቀር የምናውቀው ነገር የለም? ለዐሳቢዎች ቦታ ስለማንሰጥ። የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ቅዱስ ላሊበላ እንዴት ነበር ሊያስብ የቻለው? ሐሳቡን በምን ገለጠው? የሰው ኃይሉን፣ ቁሳቁሱን፣ በጀቱን፣ የሥራ ሂደቱን እንዴት ነበር ያደራጀው? ሕንጻውን እንጂ ሐሳቡን አላገኘነውም።
ፓል ሄንዝ አብያተ ክርስቲያናቱ ሲታነጹ ሊወጣ የሚችለው አፈር በአቡ ሲምባል የሚገኘው የግብጻውያን ታላቁ መቅደስ ሲሠራ ከወጣው አፈር አምስት እጅ የሚበልጥ ነው ይላሉ። ሥራውን ማንም ያከናውነው ፕሮጀክቱ ግን አያሌ የሰው ኃይልን ማንቀሳቀስን፣ የውቅሩን ሥራ እጅግ ሞያዊ በሆነ መንገድ መከታተልን፣ ያንን ግዙፍ የሥራ ኃይል እንዳለ ጠብቆ ለረዥም ጊዜ ለማቆየት የሚያስችል በቂ ሀብትን የሚጠይቅ ነው። በውቅሩ ላይ ምንም ዓይነት ስሕተት መሠራቱን የሚያመለክት ነገር የለም። ሞዴሎችና በጥንቃቄ የተዘጋጀ ዐቅድ መኖሩ አያጠራጥርም። አስደናቂው ደግሞ የውስጡን ቅርጽ ለመስጠትና ለማሣመር የተኬደበት መንገድ ነው። ይህ ሁሉ የተደረገው ደግሞ በችቦ መብራት ነው። (Layers of Time, 52) ያን ሁሉ ከየሥራው የወጣ አፈር የትና እንዴት ነው የደፉት? እርሱን ብናገኘው እንዲህ የግንባታ ቦታዎቻችን ሁሉ በቆሻሻ ባልተሞሉ ነበር። ታድያ የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት የሐሳብ መዝገብ ለምን አልደረሰንም? ሕንጻዎቹን ብቻ ለምን አገኘናቸው? ምናልባት ለሐሳብ ተገቢውን ቦታ ስለማንሰጥ ይሆን?
በዘመናዊቱ የኢትዮጵያ ታሪክ እንኳን ሀገሪቱን ሲመክሩና ሲዘክሩ የነበሩ፤ ከአውሮፓ እስከ ጃፓን አርአያ ይሆናሉ የሚባሉትን ሀገሮች መንገድ እየጠቀሱ፣ ሀገሪቱ በዚያ መንገድ እንደትጓዝ ሐሳብ ያቀረቡ፤ በኋላ የሚሆነው ቀድሞ ታይቷቸው የመንግሥትን አስተዳደር፣ የሕዝብን አመራር፣ የሥልጣንን ጉዞ፣ ሰላማዊ የለውጥን መንገድ የጠቆሙ አሳቢዎች ነበሩን። በተለይም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ችግሮች እየተባባሱ ሲመጡና ቁስሉ የበለጠ እያመረቀዘ መሆኑ ሲታይ ንጉሡንም ሀገሪቱንም ተነቃናቂ ተማሪዎቹንም ከማዕበል ለማትረፍ አያሌ ሊቃውንት ሐሳባቸውን አቅርበው ነበር። የሰማቸው ባለመኖሩ ግን ከለውጥ ይልቅ ለነውጥ ተዳረግን።
ዛሬም ድረስ ለሐሳብና ለዐሳቢዎች ቦታ እንደሌለን የሐሳብ መስጫ ሳጥኖቻችን በየግድግዳው ላይ ቆዝመው ቆመው እየመሰከሩ ነው።
ሰው በመዋቅር፣ በድርጅት፣ በኮሚቴ፣ በማኅበር ሊያስብ አይችልም። እነዚህ ሁሉ ሐሳብን በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚጠቅሙ እንጂ ማሰቢያዎች አይደሉም። ሰው በግሉ ያስባል፣ በጋራ ይመክራል፤ በጋራ ይሠራል። አሁን አሁን ግን በደርጅት፣ በማኅበር፣ በመዋቅር፣ በኮሚቴ ለማሰብ እየተሞከረ ነው።
ሰው የተፈጠረው በግል ስለሆነ የሚያስበውም በግል ነው። መላእክት የተፈጠሩት በማኅበር ነው። ስለዚህም ያለ ልዩነት በማኅበር ሊያስቡ ይችሉ ይሆናል። እንስሳትም የተፈጠሩት በወገን በወገን ነው። ስለዚህም ተመሳሳይ እንስሳት ተመሳሳይ ጠባይ ይኖራቸዋል። ሰው ግን በግለሰብ ደረጃ ነው የተፈጠረው። ስለዚህም ሐሳብ ግለሰባዊ ነው። የግለሰቦች ሐሳብ ተሞግቶ፣ ተሞርዶ፣ ዳብሮና በልጽጎ ሌሎችን እያሳመነ የማኅበር፣ የድርጅት፣ የፓርቲ፣ የተቋም፣ የኮሚቴ የጋራ ግንዛቤ፣ ዐቅድ፣ መግባቢያ፣ ዕውቀት፣ ልምድ ይሆናል እንጂ ሰው በጋራ ሊያስብ አይችልም። አንዳንድ ጊዜ ድርጅቶች፣ ኮቴዎች፣ ማኅበሮች፣ ፓርቲዎች ይመሠረቱና ሰዎች በዚያ ውስጥ ተሰብስበው ለማሰብ ይሞክራሉ። ምን እንሥራ? ይላሉ። መጀመሪያ ምን ለመሥራት ተሰበሰቡ? ለሐሳብ ድርጅት ከመፍጠር ይልቅ ለድርጅት ነው ሐሳብ እየተፈለገ ያለው። ለልጅ ስም ይሰጣል አንጂ፣ እንዴት ለስም ልጅ ይወለዳል? ሰዎች በጋራ ለማሰብ ከሞከሩ ላለማሰብ እየሞከሩ ነው ማለት ነው። ሐሳብም ቦታውን ለመግቦት ለቅቋል ማለት ነው።
መግቦት ማለት አንድ ሐሳብ ከሆነ ቦታ ይመጣል። አይጠየቅም፤ አይተችም፤ አይከረከርም፤ አይለወጥም፤ እንዳለ እንደ መድኃኒት ይወሰዳል። ይዉጡታል አንጂ አይገነዘቡትም። ይቀበሉታል እንጂ አይጋሩትም። ከበሮው አንድ ቦታ ይመታል። የሌላው ሰው ድርሻ ምቱን እየጠበቀ እስክስታ መውረድ ብቻ ነው። አሠልጣኙ የሆነ ቦታ ይቆማል፤ የሌላው ሰው ድርሻ ተቀመጥ ሲሉት መቀመጥ፣ ተነሣ ሲሉት መነሣት ብቻ ነው። ለምን ? ብሎ አይጠይቅም።
የሰው ልጅ መግነጢሳዊ ጠባይ እየተዘነጋ ነው። አንድ ሰው የአንድ ጎሳ ወይም ዘውግ አባል ስለሆነ ብቻ አንድ ዓይነት ሐሳብ ሊኖረኝ ይገባል ብሎ የሚያስብ ከሆነ ሰውነትን ያህል ክብር እየለቀቀው ነው። ትልቁ አንድነት የቀለም፣ የጎሳ፣ የቋንቋ፣ የትውልድ አንድነት አይደለም። ይህማ በተፈጥሮ የተቀበልከው፣ በሐሳብ የማትለውጠው ነው።
እነዚህ በምርጫ ያልመጡ አንድነቶች ስለሆኑ በአንድነቱ ውስጥ ያለውን ሰው ብቃት አያመለክቱም። ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱን አንድነት በእንስሳትም ውስጥ ስለምናገኘው።
ትልቁ የአንድነት ልህቀት የሐሳብ አንድነት ነው። ተከራክሮ፣ ተወያይቶ፣ ተሳስሎ፣ ተሞራርዶ ሐሳብን ገንዝቦ (ገንዘብ አድርጎ) አንድነት ሲመሠረት። የሰውን አንድነት ከአንድነትና ከኅብረት አውጥቶ ‹አሐተኒ› የሚያደርገው የሐሳብ አንድነት ነው። ይህንን የላቀ አንድነት ለማምጣት ደግሞ የሚገዛ መዋቅር፣ ድርጅት፣ ማኅበር፣ ፓርቲ ሳይሆን የሚገዛ ሐሳብ ያስፈልጋል። ትልቁ ገዥነት የሃሳብ ገዥነት ነው። በገንዘብ መግዛት ሀብትን፤ በሥልጣን መግዛት ጉልበትን፣ በውበት መግዛት ፍትወትን፣ በመዋቅር መግዛት ሹመትን ያሳያል። በሐሳብ መግዛት ግን ልህቀትን ያመለክታል።
የሀገር አንድነት ወደ አሐተኒ እንዲያድግ ከፈለግን፣ ልዕልና ያላቸውን ሐሳቦች የሚያቀርቡ፣ የሐሳብ ገዥዎች ያስፈልጉናል። ከተለያየ ዘውግ፣ ጎሳ፣ ብሔር፣ ባህል፣ እምነት፣ ልማድ፣ ክልል፣ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የእድሜና የጾታ ክልል የምንመጣ ሰዎችን እንደ ሥርዓተ ፀሐይ (Solar system) የሚያስተሣሥረን፤ እንደ ፍኖተ ሐሊብ (Milk way) ውጥንቅጣችንን በአንድ የተግባባ መንገድ የሚያስጉዘን፣ የምንገዛውና የሚገዛን ሐሳብ ያስፈልገናል። የሚገባንና የሚያግባባን ሐሳብ ያሻናል።
ለዚህ ደግሞ ለሐሳብና ለዐሳቢዎች ቦታና ክብር የሚሰጥ ማኅበረሰብና ሥርዓት መኖር አለበት። ለምርጫና ለገንዘብ ሳጥኖች የሰጠነውን ቦታ፣ ለሐሳብ ሳጥኖች መስጠት ካልጀመርን፣ ተፈጥሮ ለውበት የሰጠችንን ልዩነት እኛ ለማስጠሎነት እናውለዋለን። መዋቅሮችና አደረጃጀቶችም የታላላቅ ሐሳቦች ማስፈጸሚያዎች መሆናቸው ቀርቶ የማሰቢያ ‹ጭንቅላቶች› እንሁን ካሉ በሠራው ሠንሠለት እንደታሠረ አንጥረኛ እንሆናለን።
ዕድገትና ማዕዶትን (Development and Transformation) በፍጥነት ለማምጣት፣ የገንዘብና የምርጫ ሳጥኖች የያዙትን ቦታ የሐሳብ ሳጥኖች መረከብ አለባቸው።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live