Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ከገዥው ወገን የምንለይበት፤ አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘገጅ

$
0
0

ማክሰኞ፤ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት

tplfእኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለትግሬዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦሮሞዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአማራዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሶማሌዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአፋሮች ጥብቅና እቆማለሁ፣  እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦጋዴኖች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአኙዋኮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሲዳማዎች ጥብቅና እቆማለሁ፤ የሚል ግለሰብም ሆነ ድርጅት፤ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይልቅ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የበለጠ የጋራ የሆኑ መቀራረቢያ ጉዳዮች ስላሉት፤ ሰፈሩን ወደዚያ ቢያቀና ይቀለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር መሠረታዊ ልዩነቱ፤ እያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን፤ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። በሀገሬ በኢትዮጵያ የማደርገው ማንኛውም የፖለቲካ ተሳትፎ፤ በኢትዮጵያዊነቴ ብቻ ነው። በኢትዮጵያዊነቴ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ባልተለዬ ሁኔታ፤ እኩል በፖለቲካ ምኅዳሩ፤ የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቴ ተከብሮልኝ፤ በማንኛውም የሀገሬ ክልል፤ የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ በአካባቢውና በሀገር አቀፍ የፖለቲካ ሂደት ተሳትፎ የማድረግ ሙሉ መብት አለኝ።” ስንል፤ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ደግሞ፤ “የለም ኢትዮጵያ የትግሬዎች፣ የአማራዎች፣ የኦሮሞዎች፣ የደቡቦች፣ የሶማሌዎች፣ የአፋሮች፣ የአኝዋኮች ነች። ግለሰብ ኢትዮጵያዊ የሚባል የለም። እናም የፖለቲካ ተሳትፎ የሚደረገው በነዚህ ክልሎች ዙሪያ እንጂ፤ በኢትዮጵያዊነት አይደለም።” የሚለው ነው።

ከዚህ በመነሳት፤ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ አስተዳደሩን በዚህ ላይ ተከለ። በሂደቱም የተለያዩ ለየብቻቸው የተካተቱ ክልሎችን መሠረተ። አያንዳንዱ የዚህ ገዢ ቡድን ተቀጥላ ጥገኛ የክልል የፖለቲካ ድርጅት፤ የራሱን የክልሉ ተወላጆች ብቻ በክልሉ ለመክተትና ለማስተዳደር ሙሉ መብት አገኘ። እናም በገዥው ቡድን ፈቃድና ፍላጎት፤ ሌሎችን ከክልሉ ማባረር፣ ሀብታቸውን መዝረፍ፣ መግደል፣ አይቀሬ ሆነ። በተግባርም ተፈጸመ። ሀገራችንን ፍጹም ወደማትመለስበት አዘቅት ለመክተት፤ ይኼው ገዥ ቡድን ተሯሯጠ። ተከትለው የሚሄዱት የሕዝቡን ድምጽ ማፈን፣ ሀገሪቱን እስር ቤት ማድረግ፣ አንገቱን ሰብሮ የማይገዛውን ማሰር፣ ማባረርና መግደል፤ ተዥጎደጎዱ። ለዚህ ተቃውሞ፤ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ድርጅቶችን መሥርተው በመታገል ላይ ናቸው። እንግዲህ በዚህ ትግል፤ ሁለት ሰፈሮች ብቻ በገሃድ አሉ። አንደኛው የሕዝቡ ሰፈር ነው። ሌላው የአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሰፈር ነው። የግለሰብ ሆነ የድርጅት ጉዳይ እዚህ ቦታ የለውም። የግለሰብ እምነት ወይንም የድርጅት መርኀ-ግብር፤ ከሁለቱ መርጠን ባንዱ ሰፈር እንድንሰለፍ ያደርገናል። የሰልፉ መለያ ደግሞ፤ የፖለቲካ ፍልሰፍናችን እና ከዚህ የሚመነጨውና በተግባር ለማዋል የምንፈልገው የአስተዳደር መመሪያ ነው።

ይህ ነው የአሁኑ የሀገራችን የኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ። ይሄን በጁ ያልጨበጠ ማንኛውም ሂደት፤ መዳረሻው ተመልሶ ያው ነው። የድርጅት መሪዎችም ሆኑ ታጋይ ግለሰብ ኢትዮጵያዊያን፤ መሠረታዊ የሆነውን የልዩነት ነጥብ በማንገት፤ ትግሉን መልክ ሠጥተን መሄድ አለብን። አማራ ነኝና ከሌሎች የበለጠ ለአማራዎች እኔ ነኝ ተቆርቋሪ፣ ለኦሮሞዎችም፣ ለትግሬዎችም፣ ለሶማሌዎችም፣ ለአፋሮችም፣ ለአኙዎኮችም፣ ለሲዳማዎችም እኔ ነኝ ተቆርቋሪ የሚለው አባባል፤ የኢትዮጵያዊነት ጠላት ነው። እንደ ኢትዮጵያዊ ካላሰብን፤ ኢትዮጵያዊነት በውስጣችን የለም። እንደ ኢትዮጵያዊ ካልታገልን፤ ኢትዮጵያ የለችም። በሀገራችን፤ ለኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነት፣ ለሀገራችን ዳር ደንበር መከበር፣ ለያንዳንዳችን ዴሞክራሲያዊ መብት የምንታገለው በኢትዮጵያዊነታችን ነው። አንዳችን ከሌላችን ጎን የምንሰለፈው፣ የያንዳንዳችን ጉዳይ የሌላችን በመሆኑ ነው። አለዚያ፣ አንተም ለራስህ እኔም ለራሴ ከሆነ፤ ትግሉ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ሳይሆን፤ በየኪሳችን ለያዝነው ዘውድ ነው። መነሻችን ይሄ ከሆነ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ ናት።

ይሄን እንድጽፍ ያስገደደኝ፤ ስለሰላማዊ ትግል የመጀመሪያውን ክፍል ባቀረብኩበት ወቅት፤ ከሌሎች የተላኩልኝ አፀፋዎች ነው። የገዥውን ስም ለምን “ትግሬዎች” ትላለህ የሚለው በተደጋጋሚ የቀረበልኝ ቢሆንም፤ ባሁኑ ሰዓት ቁንጮው ላይ ደረሰ።

እናም ይሄን ጻፍኩ። እኔ ራሳቸውን እንዲጠሩበት በመረጡት ስም ነው የጠራኋቸው። ለኔ ካላይ እንደገለጽኩት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ነው። ኢትዮጵያ አንድ ናት። ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን ናት። በትግራይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን፤ ትግሬዎች ይባላሉ። በአፋር ያሉት ኢትዮጵያዊያን አፋሮች ይባላሉ። ታዲያ ትግሬዎችን ነፃ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ ግንባር፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ሲል፤ ሌላ ምን ብዬ ልጠራው ነው። የትግራይ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ካልኩማ፤ ሰፈሬ ከገዥው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አይሆንም ወይ? ለኔ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የትግራይ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ፣ የሶማሌ ሕዝብ፣ የሲዳማ ሕዝብ፣ የአኝዋክ ሕዝብ፣ የቤንሻንጉል ሕዝብ፣ የወላይታ ሕዝብ የለም። እናም፤ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ብዬ አልጽፍም። ለምን ይሄን ጽፍክ የሚለኝ ካለ፤ ሄዶ ስም ያወጣውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይጠይቅ።

በሀገራችን ያለው ትግል፤ ሀገርን ከአምባገነን ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ ጠላታችን አንጻር፤ ልዩነታችን በግልጽ ወጥቶ፣ ተሰላፊዎች ባደባባይ ታውቀን የቆምንለት እንጂ፤ አንዳችን ሌላችንን የምንለማመጥበት ጉዳይ አይደለም። ትግሉ የመላ ሕዝቡ እንጂ፤ የዚህ ወይንም የዚያ ወገን የግል ጉዳይ አይደለም። ታጋዩን የሕዝብ ወገን ወደ አንድ ማሰባሰቡ የትግሉ የመጀመሪያ ግዴታ ነው። በርግጥ መተባበር የዲፕሎማቲክ ሥራ እንጂ፤ አንተም ባፈተተህ የሚባልበት ሂደት አይደለም። በቅርቡ የተለያዩ ታጋይ ድርጅቶች ቢያንስ ተገናኝተው ለመነጋገር ይችሉ እደሆነ በማሰብ፤ ጥረት አድርጌ ነበር። ይሰበሰቡና መፍትሔ ያቀርቡልናል የሚል ብዥታ አልነበረኝም። ነገር ግን፤ በሂደቱ ሁላችን ሀገራችን ያለችበትን አደጋ በመመልከትና ቅድሚያ ለሀገር ብለን፤ በድርጅት ያሉትም ሆነ ግለሰብ ታጋዮች፤ የመሰባሰቡን ሂደት ያቀላጥፉታል ብዬ ነበር። አልተሳካም። ትግሉ ከገዥው አምባገነን ጋር የምንፋለምበትን ጉዳይ በቅርብ በልብ አንግተን፤ የጠራና ፀሐይ የሞቀውን ልዩነታችንን ባደባባይ አንግተን የተነሳንበት ግብግብ ነው። ይሄን ላስደስት፤ ያንን ላቆላምጥ የሚባልበት አይደለም። በተለይ በሥልጣን ላይ ያለን መንግሥት ለመለወጥ የሚደረግ ትግል፤ የጠራ አመለካከት ከሌለው፤ ትግሉ ውጤታማ አይሆንም። ጠላት ማነው፣ የምንታገለው ለምንድን ነው? ግባችን ምንድን ነው? መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች ናቸው። በዚህ ትግል፤ ጠርተው የሚወጡ ጽንሰ-ሃሳቦች አሉ። እኒህ የትግሉን ሂደት ይተረጉሙታል። ግንዛቤን ያዳብራሉ። በሥልጣን ላይ ያለውን ገዢ ቡድን ማንነቱን ለመግለጽ የምንጠቀምበት ስም፤ ራሱን ግልጽ አድርጎ የሚጠራበትና የሚጠራበት መሆኑ፤ በትግሉ ላይ ትልቅ አስተዋፅዖ አለው። የምናየው የትግል አሰላለፍ ትርጉሙ የሚመነጨው፤ ከግንዛቤያችን ላይ በመቆም ነው።

በአንድ በኩል ጠላታችን የሚታወቀው ራሱ ነኝ ብሎ ባወጣው ስም እንጂ፤ እኛ በምናወጣለት ስም አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ በመካከላችን እብሪተኛን እብሪተኛ ማለት ካልቻልን፤ ታጋዮች ሳንሆን ወሬኞች ነን። ከሁሉም በላይ የሀገሬ ጉዳይ ብሎ ያልተነሳ ታጋይ፤ የሕዝቡ ወገን ሊሆንም ሆነ ታግሎ የሕዝቡን ድል ሊያስገኝ አይችልም። ቢሳካለት ገዥውን መተካት ነው ሩጫው።

 

The post ከገዥው ወገን የምንለይበት፤ አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘገጅ appeared first on Zehabesha Amharic.


የሃይለማርያም ደሳለኝ የጃኪ ጎሲና የአርከበ የኤርትራ ጉዞ ወሬ

$
0
0

Hailemariam desalegn

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ አስመራ ድረስ ሄደዉ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆኑ ለአልጃዚራ በዲሴምበር 2012 ገልጸው ነበር:: ሰሞኑን ደግሞ የመለስ ራዕይ የሚባል ገደል ይግባ ያሉት አቶ አርከበ እቁባይ የመንግስት አቋም በሚንጸባረቅበት ዘመን መጽሔት “በኤርትራ ለውጥ ይመጣል; የኤርትራን ወደብ መጠቀም እንጀምራለን” ባሉ በነጋታው ድምፃዊው ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) አስመራ ሄጄ የሙዚቃ ኮንሰርት ማቅረብ እፈልጋለሁ ብሎናል:: የጃኪና የአርከበ ምኞቶች የተገለጹት በመንግስት ሚዲያዎች ነው:: ፎቶውን ይመልከቱና አስተያየትዎን ያስቀምጡ::

The post የሃይለማርያም ደሳለኝ የጃኪ ጎሲና የአርከበ የኤርትራ ጉዞ ወሬ appeared first on Zehabesha Amharic.

የጆሲ ኢን ዘሓውስ ምክር ለጃኪ ጎሲ (ጎሳዬ ቀለሙ) – Video

$
0
0

ከሊሊ ሞገስ

ጃኪ ጎሲ ከለቀቃቸው በጣት የሚቆጠሩ ዘፈኖች ውስጥ በጣት የሚቆጠሩትን ከሌሎች ዘፋኞች ካለፈቃድ ወይም ደግሞ አትውሰድ እየተባለ በጉልበት ወስዶ በመስራት ስሙ ይጠራል:: የተሾመ አሰግድ “የኔ አካል”, የኤርትራዊው ፍጹም ዮሐንስ ‘ፊያሜታ’ (ከዩቲዩብ እስከመታገድ ደርሶ ነበር)… እንዲሁም አሁን የአብርሃም አፈወርቂ ‘መለይ’ ዘፈኖች ክርክር አስነስተውበታል:: በርግጥ ጃኪ ምርጥ ድምጽ እና ስታይል ያለው ዘፋኝ ሆኖ ሳለ በሰው ዘፈኖች ላይ ሙጥጥ ማለቱን ብዙዎች እየወደዱለት አይደለም:: እያስተቸውም ይገኛል:: ለዚህም ነው ጃኪ መልካም የሆነ አማካሪ ቢኖረው ከነዚህ ትችቶች ሊያመልጥ ይችላል የሚባለው:: ቀጣዩ ቭዲዮ ጆሲ በአንድ ወቅት ከተሾመ አሰግድ ወስዶ በሠራው ሥራ ክርክር ውስጥ በገባበት ወቅት የመከረው ምክር ነው:: ጃኪ ያን ምክር በፊያሜታ እና በመለይ ላይ ባይተገብረውም አሁን ግን ከዚህ የበለጠ መካሪ የሚያስፈልገው ግዜ ላይ ይገኛል:: ያድምጡና የ እርስዎን አስተያየት ያስቀምጡ::


Jackey and Jossey

The post የጆሲ ኢን ዘሓውስ ምክር ለጃኪ ጎሲ (ጎሳዬ ቀለሙ) – Video appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ አይሲኤስን ለመቃወም ሰልፍ የወጣችው ወ/ሮ ንግስት ወንድይፍራው እስራት ተፈረደባት

$
0
0

nigist wendifraw

አረመኔው የሕወሓት መንግስት አይ ኤይ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰረችው ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ዛሬ ሰኔ 17/2007 ዓ.ም ቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርባ የ8 ወር እስራት እንደፈረደባት ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኘ መረጃ አመለከተ::

“የውጭ ሬሳ የአገር አንበሳ” እየተባለ የሚጠራው ይኸው አረመኔው የሕወሓት አስተዳደር አይሲኤስን ለመቃወም የወጡ በርካታ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኑን ያሰረ ሲሆንከነዚህም ውስጥ ንግስት ወንዲፍራው ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ያለ ማዘዣ ከ3 አመት ልጇ ጋር በፖሊስና ደህንነቶች ተይዛ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስራ መቆየቷ ይታወሳል::

The post በአዲስ አበባ አይሲኤስን ለመቃወም ሰልፍ የወጣችው ወ/ሮ ንግስት ወንድይፍራው እስራት ተፈረደባት appeared first on Zehabesha Amharic.

ሙታንን የከፋፈለው የህወሓት ‹‹ብሄርተኝነት››

$
0
0

hawzen
ከጌታቸው ሽፈራው

ጀርመን ውስጥ በነበረበት ወቅት ጠባብ ብሄርተኝነት ምን እንደሆነ በተግባር የተገነዘበው የሳይንሱ ሊቅ አልበርት አንስታይን ጠባብ ብሄርተኝነትን የሰው ልጅ አጥፊ በሽታ ነው ይለዋል፡፡ አውቁ ሳይንቲስት ይህን በሽታ በቀላሉ የማይድን፣ የሰውን መላ ሰውነት የሚያበላሽ እከክ አይነት ወረርሽኝ ጋር ያመስለዋል፡፡ የህወሓት በሽታም ይህ የኑክሊየር ፊዚክስ ቀመሩ ባለቤት የገለጸው ጠባብ ብሄርተኝነት ነው፡፡ ደርግ በትግራይ ጨምሮ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች ህዝብ ጨፍጭፏል፡፡ ይህን ጭፍጨፋ በኢትዮጵያውያን ላይ የተደረገ በደል አድርጎ ከመቁጠር ይልቅ በብሄር አይን መንዝሮታል፡፡ እናም ሰኔ 15 ‹‹የትግራይ የሰማዕታት ቀን›› በሚል ለ26ኛ ጊዜ አክብሯል፡፡

እንግዲህ ትግራይ ውስጥ ደርግ የጨፈጨፋቸውን ኢትዮጵያውያን ከሞቱ በኋላም እንደ ኢትዮጵያውያን እንዳናስባቸው በቋንቋ መስመር ታጥረናል ማለት ነው፡፡ በመላው አገሪቱ ጭፍጨፋዎች ነበሩና ሌሎች ከ80 በላይ ‹‹ብሄሮች››ም የየራሳቸውን ሰዕማታት ቀን ሊያከብሩ መሆኑ ነው፡፡ ደርግ አሁን ትግራይ ተብሎ በተከለለው የኢትዮጵያ ክፍል ባደረገው ጭፍጨፋ አፋርኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ….ሌሎችም ቋንቋ ተናጋሪዎች ለገበያ አሊያም በሌላ ምክንያት በአካባቢው በመገኘታቸው የጭፍጨፋው ሰለባ የሆኑት ነፍሳቸው የሰው ነፍስ አይደለም ማለት ነው፡፡

በተመሳሳይ በሌሎች አካባቢዎች በተደረጉ ጭፍጨፋዎች ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የጭፍጨፋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሆኖም ህወሓት ሀውዜንም ሆነ ሌሎች አካባቢዎች በተደረጉት ጭፍጨፋዎች ሰለባ የሆኑት ‹‹ትግሬዎች ብቻ ናቸው!›› ብሎ ለብቻው የሙት አመት እያከበረ ነው፡፡ በዚህም ትግራይ ውስጥ በደርግ የተጨፈጨፉ ሌላ ቋንቋ ተናገሪዎች ደመ ከልቦች ሆነዋል፡፡

ህወሓት ማንን ያስቀድማል?

አንድ ሀቀኛ ፓርቲ ከስልጣን ይልቅ ሊያስቀድመው የሚገባው ወክየዋለሁ የሚለውን ህዝብ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ፓርቲዎች በስም ወክለነዋል የሚሉትን ህዝብ እንዳስቀደሙ በማስመሰል ቅድሚያ የሚሰጡት ስልጣናቸውን ነው፡፡ ከዚህ ሲከፋ ደግሞ ስልጣናቸው በራሱ ወክየዋለሁ የሚሉትን ህዝብ ከመውደድ ይልቅ ሌላ ህዝብን በመጥላት ላይ ሊመሰረት ይችላል፡፡ አጠቃላይ የአገሪቱን ህዝብ የሚጠሉ ከሆነ ደግሞ የሚወዱት ስልጣንን ብቻ ይሆናል፡፡ የህወሓት ስልጣን የተመሰረተው ሌሎችን በመጥላት ላይ ነው፡፡ ህወሓት የትግራይን ህዝብ ቢወድ ኖሮ በጠባብ ብሄርተኝነት ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ባልጣረ ነበር፡፡ በመላ ኢትዮጵያ የሞቱትን ትግርኛ ተናጋሪዎች ሞት ረስቶ ክልሉ ውስጥ የሞቱትን የሚረሳበት አጋጣሚ አይፈጠርም ነበር፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር ቢኖረው ደግሞ ትግራይ ውስጥ የተጨፈጨፉትን ኢትዮጵያውያን ከሰው ሳይቆጥር የእኔ ነው ያለውን ህዝብ ብቻ በቋንቋ ለይቶ ባላስታወሰ ነበር፡፡

ህወሓት ይህን ጥላቻን መሰረት ያደረገ ጉዞውን አርበኝነት ይለዋል፡፡ ስሙ እንኳ ይህን ለትግራይ ህዝብ አርነት የቆመ መሆኑን ያስረዳል፡፡ የፈረንሳ ቻረለስ ዲ ጎል ህወሓትን አይነት አካሄድ አርበኝነት ሳይሆን በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ጠባብ ብሄርተኝነት አድርጎ ይወስደዋል፡፡ እንደ ቻረለስ ዲ ጎል አርበኝነት ማለት የህዝብን ፍቅር ስታስቀድም የሚመመጣ ነው፡፡ በተቃራኒው ጠባብ ብሄርተኝነት ለራስህ ህዝብ ያለህን ፍቅር በመቅደሙ ሳይሆን ለሌሎች ህዝቦች ያለህን ጥላቻ ስታስቀድም የሚመጣ ክስተት ነው፡፡ ይህ የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ህወሓትን በስርዓት የገለጸው ይመስለኛል፡፡ በመሆኑም ህወሓት ወክየዋለሁ የሚለውን የትግራይን ህዝብም አይደለም፡፡ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይማ ዲ ጎል እንደሚለው ጥላቸው የከረረ ነው፡፡ በዚህ መሃል የቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ስልጣን! ከሁሉም አስቀድመዋለሁ የሚለውን የትግራይ ህዝብም የስልጣን መጠቀሚያ ነው፡፡ ‹‹የትግራይ ሰማዕታ ቀን›› ብሎ ሲያውጅም ‹‹የሞትነው እኛ ነን፡፡ በመሆኑም ስልጣን ላይ መቆየት ያለብን እኛ ነን›› ብሎ ለስልጣን ምሽግ መቆፈሩ ነው፡፡
ኦስካር ስትራውስ የተባሉ ሌላ ሰውም እንደ ዲ ጎል ሁሉ ብሄርተኝነት አርበኝነት ሆኖ አያውቅም ይላሉ፡፡ ከብሄርተኝነት በእጅጉ የተሻለና ድንበርና ሌሎች መከለያዎች የማይገድቡት አርበኝነት አለ የሚሉት እኝህ ሰው አርበኝነትን የቋንቋም ሆነ ሌላ ድንበር ሊለየው አይገባም ባይ ናቸው፡፡ ይህ አርበኝነት ድንበር ሳይገድበው የሰው ልጅ ስልጣኔ የሰጠውን ተስፋ የሚያስቀጥለበት ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ድንበር የሚገድበው አርበኝነት ከዚህ በተቃራኒ የሰው ልጅን ስልጣኔ የሚያከስም እኩይነት ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ምሁራን እንደ ህወሓት ያሉትን የፖለቲካ ሀይሎች ላይ በተመሳሳይ የሚዘምቱ ናቸው፡፡

ለምሳሌ ያህል ቶርሰሪን ቬብለን ጠባብ ብሄርተኝነትን ሞራል ባጣ መንገድ የተወለደ እና ሰይጣናዊ በሆነ መንገድ የሚመለክ መሆኑን ያሰምሩበታል፡፡ አስቀጥለውም ይህ መስረቱ እኩይ የሆነ አስተሳሰስ የሰው ልጅን ተቋማትና አጠቃላይ ኑሮ በአለመግባባትና በጭንቀት ከመወጠር አልቆመመም ሲሉ ኢትዮጵያ ያለችበትን አይነት ሁኔታ ቀድመው የተገነዘቡ ያስመስላቸዋል፡፡

በአገራችን ብሄር ‹‹ከሲቪል›› ተቋማት አልፎ ቤተ እምነት ውስጥ አለመግባባትና አለመተማመን እየፈጠረ ቀጥሏል፡፡ ቀበሌ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ውስጥም ሳያዩ ያምናሉ በሚባሉት ኢትዮጵያውያን ላይ ‹‹ብሄር›› የልዩነት ምክንያት ሆኗል፡፡ ከአመታት በፊት ጳጳስ ከተቀናቃኞቻቸው ግብጽ ሲመጣ በፍቅር ይቀበሉ የነበሩት ኢትዮጵያውያን አሁን የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በ‹‹ብሄር›› አይን እንዲያዩ ተገድደዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ህወሓት ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ የድርጅቱ የቀድሞ ሊቀመንበር በመጽሃፋቸው እነ ስብሃት ነጋ ደብረ ዳሞን የመሳሰሉ ገዳማት ሳይቀሩ የህወሓትን አባላት አስርገው ሲያስገቡ መቆየታቸውንና በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ የሚሰራበት መሆኑን አምነዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንም የእምነት፣ የቋንቋና ሌሎችም ሳይወስኗቸው ከሚገናኙባቸው ነገሮች አንዱ ሀዘን ነው፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን የሆነን ልዩ ማህበራዊ መሰረትና ተቋማት መስርተዋል፡፡ አሁን ግን ሟች በ‹‹ብሄር›› አጥር ታጥሯል፡፡ ሁሉም ‹‹ሟችህን በየ ቋንቋህ አስብ›› ተብሎ መከለል ተጀምሯል፡፡ ይህ እንግዲህ ቶርሰሪን ቬብለን መሰረቱ አሉታዊ መሆኑን የሚገልጹት ጠባብ ብሄርተኝነት እስከ ለቅሶና ቀብርም ወርዶ የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ ትስስርና ተቋማት ማንኮታኮቱን ነው የምንረዳው፡፡

በአሁኑ ወቅት በርካታ ቀናት የሚከበሩት በአለም አቀፍ ደረጃ ነው፡፡ የሴቶች፣ የሰራተኞች፣ የጋዜጠኞች… ብቻ በርካታ ቀናት የሚታሰቡት በአለም አቀፍ ደረጃ ነው፡፡ ምክንያቱም ዘመኑ በአገር ብቻ የሚታጠርበት ባለመሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ በርካታ ህዝቦች በሩዋንዳና በሌሎች አገራት የተፈጸሙን ጭፍጨፋዎች ያወግዛሉ፡፡ ጭፍጨፋን በተመለከተም አለማቀፍ ቀናት ይከበራሉ፡፡ አሁን በአገራችን እየተደረገ ያለው ግን ከአለም አቀፍም ወርዶ በ‹‹ብሄር›› ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያውያን ቋንቋውን ካልተናገሩ በስተቀር የተጨፈጨፉ ወንድሞቻቸውን ቀን ለማስብ እንዳይችሉ የ‹‹ብሄር›› አጥር ታጥሮባቸዋል፡፡

The post ሙታንን የከፋፈለው የህወሓት ‹‹ብሄርተኝነት›› appeared first on Zehabesha Amharic.

የልኂቃኖቻችን ማንነትና ያደረሱብን ኪሳራ!!!

$
0
0

ከአምሳሉ ገ/ኪዳን (ሰዓሊ)
Amsalu በጥንት ዘመን ላይ ነው የምግብ ጉዳይ የሰማይ አእዋፍንና የምድር እንስሳትን ለሞት ሽረት ጦርነት ዳርጎ ነበር፡፡ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነባቸው ምክንያት እግዚአብሔር እንደ መና ያለ በጣም የሚጣፍጥና ተስማሚ መንጅ የሚባል ምግብ ለሁለቱም ወገኖች ባጠቃላይ ለፍጥረቱ ሁሉ በየዕለቱ ከሰማይ ያወርድላቸው ነበር፡፡ ታዲያ እላቹህ አንድ ወቅት ላይ መተሳሰቡ ጠፋና ሆዳምነት ሰፈነና የምድር እንስሳቱ አእዋፉን ሳያስቡ ድርሻቸውን ሳይተውላቸው ሁሉንም መንጅ ጠራርገው እየበሉባቸው አእዋፉ እጅግ በመቸገራቸው እራሳቸውን የምድር ታላላቅ እንስሳቱን ግልገሎችና እንደ እባብ አይጥ የመሳሰሉትን አነስተኛ እንስሳት እየሞጨለፉ በመውሰድ መብላት ጀመሩ፡፡ እንስሳቱ ደነገጡ በገዛ እጃቸው የማይቻል ባለጋራ እንደፈጠሩ ጠላት እንዳፈሩ ያኔ ገባቸው፡፡ ጥፋት እንደሠሩ ስሕተት እንደፈጸሙ አምነው ይቅርታ መበጠየቅ ከእንግዲህ የአእዋፉን ድርሻ እንደማይነኩባቸው ቃል በመግባት እርቅ እንዳያወርዱ በአራዊቱ ትዕቢትና እብሪት አሻፈረኝ ባይነት በእርቅ እናውርድ ጥያቄው ላይ መስማማት ባለመቻላቸው ምክንያት የእርቁ ጉዳይ ውድቅ ሆነና እጅግ ዘግናኙ የተራዘመ ጦርነት ተኪያሔደ፡፡ ከሁለቱም ወገን በርካታ ዝርያዎች ዝርያቸው ጨርሶ እስኪጠፉ ድረስ እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ ጦርነት ለተራዘመ ጊዜ ተደረገ፡፡ ማናቸውም ግን አሸናፊ ሆነው መውጣት አልቻሉም፡፡ የሁለቱም ቡድኖች ኃይላቸው ሲዳከም በራሳቸው ጊዜ ጦርነቱን እስከተውበት ጊዜ ድረስ ያንን ጦርነት ያደረጉ እንጅ መጨረሻ ላይ የደረሱበት ስምምነት ወይም እርቅ ኖሮ አልነበረም ጦርነቱን ያቆሙት፡፡

ፈጣሪም የሰጣቸውን ጸጋ በፍቅር በስምምነት በመተሳሰብ ሊጠቀሙበት ሊመገቡት ባለመቻላቸውና ለዘግናኙ እልቂት መንስኤም ስላደረጉት ወዲያውኑ ነበር መንጁን ከሰማይ ማውረዱን ያቆመው፡፡ ጦርነቱ ያንን ያህል ዘግናኝና አሰቃቂ ሊያደርገው የቻለው ከሰማይ የሚወርደው መንጅ ስለቆመና አንደኛው ሌላኛውን ለምግብነት ከመጠቀም አልፎ እዛው እርስ በርስም አንዱ ሌላውን ለምግብነት ፍጆታ የመጠቃቃት አዙሪት ውስጥም በመግባታቸውም ጭምር ምክንያት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ምግባቸውን ያቆመባቸው እሱ የሚገኘው ከመሀከልም የሚኖረው በረከትን ረድኤትን ጸጋውምን የሚሰጠው ፍቅር ስምምነት መተሳሰብ ባለበት ቦታና ሁኔታ እንጅ መለያየት ጸብ ክርክር ፍጅት ራስ ወዳድነት ስግብግብነት ባለበት ቦታና ሁኔታ እንዳልሆነ እንዲረዱ እንዲገነዘቡ ተገንዝበውም ሰላም ፍቅር ስምምነት መተሳሰብ እንዲያሰፍኑ ለማስተማር ለማሳወቅ ነበር፡፡ እነሱ ግን የሠሩት ስሕተት ምን ያህል ከባድ ማስተዋል አርቆ ማሰብ የጎደለው እንደሆነ በርካታ ዝርያዎቻቸው እስኪጠፉ ድረስ ከመተላለቅና ለምግብነት እራስበራሳቸው እስኪባሉ ድረስ የተጎዱበት እንጅ ምንም ያላተረፉበት እንደሆነ መረዳት ተስኗቸው እርቁን ስምምነቱን ሳያወርዱ ሳይፈጥሩ እንደቀሩ ቀሩ፡፡ ይሄው ይህ ሁኔታም እስከአሁን ድረስ ዘልቆ ለምግብ ፍጆታነት ሲባል እርስ በእርስ ይበላላሉ፡፡

ጦርነቱ ለከፋ መተላለቅ የዳረጋቸው ምክንያት ከሰማይ ይወርድላቸው የነበረው ምግባቸው በመቆሙ እርስ በራሳቸው ለምግብ ፍጆታነት የመጠቀም ግዴታ ውስጥ ከመግባታቸው በተጨማሪ ያ አስከፊ ጦርነት በዚያ መልኩ ተጠናቆ አስከፊ ውድመት ለመከሰቱ አንድ ሌላ ጠንቀኛ ምክንያት ነበር፡፡ እሱም ያ የተራዘመ ጦርነት በሚደረግበት ወቅት የኃይል ሚዛኑን ዕያየች ወደሚያደላው እየተሰለፈች እንስሳቱ ያሸነፉ ሲመስላት እንስሳ ነኝ፤ እእዋፉ ያሸነፉ ሲመስላት ደግሞ ወፍ ነኝ የምትል አንዲት ፍጥረት ነበረች፡፡ የሌሊት ወፍ ትባላለች፡፡ የሌሊት ወፍ ከወገቧ በላይ አይጥ ከወገቧ በታች ደግሞ ወፍ ናት፡፡ ይህች ወፍ ጦርነቱ እንደዚያ ዓይነት ውድመት ለማድረሱ ከፍተኛ ድርሻ ነበራት፡፡ እንዴት መሰላቹህ፡- አንድ ጊዜ ከአእዋፉ ሌላ ጊዜ ከእንስሳቱ በምትሆንበት ወቅት የአንደኛውን ቡድን የጦር አሰላለፍና የውጊያ ስልት (ስትራቴጂ) አቅድ ለሌላኛው እያቀበለች ነበር ጦርነቱ አሸናፊ ሳይኖረው ተራዝሞ በመኪያሔድ እንዲያ ዓይነት ውድመት ልታደርስ የቻለችው፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን መጽሐፉም እንደሚል “የማይታወቅ የተሰወረ የማይገለጥ የተከደነ ነገር የለምና” ሁለቱም ወገኖች የየሽንፈታቸውን ምክንያት በሚያጣሩበት በሚገመግሙበት ምሥጢራቸውን ማን አሳልፎ እንደሰጠ እንዳቀበለ በሚመረምሩበት ጊዜ የሌሊት ወፍ ሆና አገኟት፡፡ ሁለቱም ሞት ፈረዱባትና የሌሊት ወፎችን ማግኘት የቻሉትን ያህል ገደሉ፡፡ ሊያገኟቸው ያልቻሏቸውንና ያመለጡትን የሌሊት ወፍዘሮች ደግሞ የሁለቱም ወገኖት አረጋዊያን በየባሕላቸውና እምነታቸው የእርግማን መዓት አወረዱባቸው፡፡ ከዚያ በኋላ የሌሊት ወፍ ከሁለቱም ወገኖች ውጭ የተገለለች ስደተኛ የተነጠለች ሆና ጨለማ ለብሳ ጠቁራ የወፍ ሠራዊት በማይበርበት በማይኖርበት ሰዓት ሌሊት ሌሊት በራሪና ቀን ቀን ደግሞ በዋሻዎችና ዛፎች ላይ ተዘቅዝቃ ተንጠልጣይ ሆና ቀረች ይባላል፡፡

የዚህችን የሌሊት ወፍ ግብር ስታዩ ምን ተምሳሌትነት ያለው ይመስላቹሀል? የእሷን ማንነት የተላበሱ በርካታ ሰዎች በመሃላችን እንዳሉ ልብ አላላቹህም? አልታዩዋቹህም? እስኪ ዘወር ዘወር በሉና አማትሩ ብዙ ሳትቆዩ ከፍ ከፍ ያለ ቦታ የያዙ ከባለጸጋ እስከ ዳኛ ከምሁር እስከ የሀገር ሽማግሌ ከሃይማኖት መሪ እስከ የጎሳ መሪ ከሁሉም ዓይነት ጎራ ጎላ ጎላ ብለው የሚታዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች (ልኂቃን) በጭንቅላታቹህ ተግተልትለው ይመጡላቹሀል፡፡ በተለይ ይሄ ዘመን በርካታ የሌሊት ወፎችን ፈጥሯል፡፡ ብዙ አሉ ከወገባቸው በላይ ወያኔ ከወገባቸው በታች ሕዝብ ሆነው አንዱንም የሆኑ ሳይመስሉ በሕዝብ ሕይዎት ድራማ (ትውንተ ኩነት) የሚሠሩ የሚቀልዱ፣ ለወያኔ ምርኩዝ ድጋፍ እስትንፋስ በመሆን የሕዝብን የመከራ ዘመን የሚያራዝሙ፣ በሕዝብና በወያኔ መሀከል በሚደረገው ፍልሚያ የኃይል ሚዛኑን ዕያዩ ወያኔ ያየለ ሲመስላቸው ከወያኔ ጋር የሚለጠፉ ወያኔን የሚያገለግሉ ሕዝብ ያየለ ሲመስላቸው ደግሞ በአለብላቢት ምላሳቸው የሕዝቡን ዜማ የሚያቀነቅኑና “ካንተ ጋር እኮ ነን! ያንተ ደጋፊ እኮ ነን!” ለማለት ጥረት የሚያደርጉ፤ በዚህም የሌሊት ወፋዊ ማንነታቸውና ግብራቸው በሕዝብና በሀገር ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የከፋና የከበደ የሚያደርጉ፤ ከየማኅበራዊ አገልግሎቱ ኃላፊነትና ከየሙያ ዘርፉ በርካታ የሌሊት ወፎች አሉ፡፡ በዚህ ርካሽ ሰብእናቸው የጎደፈ የተመረዘ ሥራቸውን ዘወትር በየብዙኃን መገናኛው ተዘግቦና ተጽፎ ታገኙታላቹህ ሕዝብ በሚሰባሰብበት መድረኮች ሁሉ እራሳቸውን በአካል ሲቀባጥሩ ታገኟቸዋላቹህ፡፡

እነኝህ ወገኖች እውነት ከየትኛው ወገን እንዳለች አጥተውት እንዳይመስላቹህ እንዲህ የሚሆኑት፡፡ ነገር ግን በተለያዬ ርካሽና ነውረኛ ምክንያቶቻቸው እውነቱ ካለው ከሕዝብ ጋር አያብሩም አስመሳዮችና አድር ባዮች ናቸው፡፡ እውነቱ ያለው የሕዝብ ወገን እንዳይቀየማቸውና ቀንቶት ያሸነፈ እንደሆነ ያኔ እንዳይገለሉ በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ በግልጽ ሳይሆን በቅኔ በተረትና ምሳሌ በሚናገሩትና በሚጽፉት ነገር ቁስሉን እያከኩ እያስተዛዘኑ አንጀቱን ለመብላትና ከሱ ጋር እንደሆኑ እንዲያስብ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ የፈለገ ቢሆን ግን የሚናገሩትንና የሚጽፉትን ተረትና ምሳሌ እንዲሁም ቅኔ በጥሬው ያስቀምጡታል እንጅ በምንም ተአምር እንደ ብሒሉ ተርጉመው በማስረዳት መልእክቱን የተሟላ አያደርጉትም፡፡ ተረትና ምሳሌውን ቅኔውን ተርጉመው ነገሩን ሊሉ የፈለጉትን ግልጽ ካደረጉት በሁለት ቢላ መብላቱ ስለሚቀርባቸውና እውነት በመናገራቸው ዋጋ ስለሚያስከፍላቸው ይህ እንዲሆንባቸው ደግሞ ፈጽሞ ስለማይፈልጉ ነው የሚናገሩትንና የሚጽፉትን ተረትና ምሳሌ እንዲሁም ቅኔ እዛው ላይ ተርጉመው በመናገር እንደ ጌታ ወንጌል እንደ ሊቃውንቱ ምክር የተሟላ የማያደርጉት፡፡

የሚሉትን በተረትና ምሳሌ በቅኔ ካሉ በኋላ ደግሞ በስውር አንዳንዴም በይፋ በሥራዎቻቸው ያኛውን ወገን (ወያኔን) ያወድሳሉ ያበረታታሉ ያከብራሉ ያገለግላሉ ሕዝቡ የሚጠቃበትን መንገድ ይጠቁማሉ ይመክራሉ፡፡ እራሳቸውን የማኅበረሰባችን ልኂቃን እንደሆኑ የሚቆጥሩ የእነዚህ እኩያንና እርኩሳን ግለሰቦች ድርጊት በሀገርና በሕዝብ ጥቅም ላይ ያደረሱትና የሚያደርሱት ጉዳት በዚህ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህ ርካሽ ነውረኛና ጸያፍ ማንነታቸው ወይም ሰብእናቸው እንደ ብልጠት ዘመናዊነትና አስተዋይነት ተቆጥሮ እንደ መልካም ነገር በሕዝባችን ዘንድ በአርዓያነት በምሳሌነት እየተወሰደ የሕዝባችን ባሕርይ ወደ እነሱው በመለወጡና ለመብቱ ደፍሮና እራሱን ገልጦ እንዳይታገል የአስመሳይነትን የአድር ባይነትን ሰብእና ሞያየ ብሎ እንዲላበስ እያደረገው በመሆኑም ጉዳቱን ድርብ ድርብርብ እያደረገው ይገኛል፡፡ እነኝህ ግለሰቦች እንደያዙትና እንዳለባቸው ማኅበራዊ ኃላፊነት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በታማኝነትና በቁርጠኝነት አለመወጣት በአዎንታዊ ጎን ምሳሌ አርዓያ ሆነው አለመገኘትና በአሉታዊ ጎን ምሳሌ አርዓያ ሆነው መገኘት ሕዝባችን በራሱ ጉዳይ ላይ የማያገባው አድርጎ እንዲያስብ ራሱን እንዲያገል በውጤቱም የምናየውን ያህል እንዲጎዳ አድርገውታል እያደረጉትም ይገኛሉ፡፡

ይህ ጉዳይም በአጭሩ “የፖለቲካ ጉዳይ አያገባኝም!” በሚል ድንቁርና የተሞላበት ቃል ይገለጻል፡፡ እኔ ይሄንን የሚሉ ሰዎች ፖለቲካ ማለት ምን ማለት መስሎ እንደሚታያቸው አይገባኝም፡፡ አንድ ዜጋ የሀገሩ የራሱ ጉዳይ ካላገባው ማን ይሆን ታዲያ የሚያገባው? አንድ ዜጋ በራሱ እጣ ፋንታ ላይ የሚወስነው መንግሥቱ ማንነትና ምንነት ጉዳይ ካላገባው ማን ነው እሱ የሚያገባው? የሰው ልጅ እስከበላ እስከጠጣ በዚህች ምድር ላይ ስፍራ ይዞ እስከኖረ ጊዜ ድረስ ራሱን ከፖለቲካ ገለልተኛ ወይም ነጻ አድርጎ ማኖር ይችላል ወይ? በዚህ ጉዳይ ላይ እጅግ በጣም የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ? የከፍተኛ ትምህርት ተማርን የሚሉ ሰዎች ሳይቀር እንዲህ ማሰባቸው ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ይቅር እነሱ አጭር ወይም ረጅም ጥቁር ወይም ነጭ እንትን ወይም እንትን በመሆናቸው ብቻ አላግባብ ከሕግ ውጪ የዜግነት መብታቸው ከሆኑ ጥቅሞች መገለላቸው ወይም እንዳያገኙ መደረጋቸው መከልከላቸው ከዚያም አልፎ እንዲጠፉ መደረጋቸው እንዴት ነው የማያገባቸው? “ፖለቲካ አያገባኝም” ማለት እኮ በዜግነቴ በሀገሬ ላገኝ ሊከበርልኝ የሚገባኝ ጥቅም ሁሉ ማለትም የመኖር፣ ሠርቶ የማደር፣ የመማር፣ በእኩል የመስተናገድ፣ ሰብአዊ መብቱን ያለማጣት የመሳሰሉት መብቶች ቢነፈጉኝ፣ ቢጣሱብኝ፣ ብከለከል አይገደኝም አይሰማኝም አያገባኝም አይመለከተኝም አይጨንቀኝም ማለት እኮ ነው፡፡ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ እነዚህን መሠረታዊ ጥቅሞቹንና መብቶቹን አጥቶ የማይከፋ ቅር የማይሰኝ የማይጎዳ እነኝህን ያጣቸውንም ጥቅምና መብቶቹን ለማስጠበቅ የማይፈልግ የማይጥር የማይመኝ ይኖራል? ካለ እሱ ሰው የሰው ልጅ ነኝ አይበል! ምን ነኝ እንደሚልም አላውቅለትም! “እንስሳ ነኝ” ይበል እንዳልልም እንስሳትም እራሳቸው እነኝህን መሠረታዊ መብቶችና ጥቅሞች አጥተው ዝም ጸጥ የሚሉ አይደሉምና ነው፡፡ ግዑዝ ነገር ድንጋይ እንዳልለውም ደግሞ ይተነፍሳል ይንቀሳቀሳል ይበላል ይጠጣል፡፡ ታዲያ ይሄንን ሰው ምን እንበለው?

እንዲህ የሚሉ ሰዎች ታግለው የፖለቲካ ምኅዳራቸውን ባስተካከሉ ሕዝቦች አይቀኑም ወይ? እንደነሱ ለመሆንስ አይመኙም ወይ? ከተመኙ ከፈለጉስ ይህ ስኬት በምን የሚመጣ መስሎ ነው የሚታሰባቸው? ፖለቲካ ሲባል ሌላ ምን መስሏቸው ነው? ግብግቡ ፍልሚያው ምን ሆነና? “የለም አይደለም እንዲህ መሆን የለበትም! ፍትሐዊ ሚዛናዊና ትክክል አይደለም ይስተካከል! በሚልና አይ! አይስተካከልም መብትህን እንጀራህን ነጥቄ ወደህ ሳይሆን ተገደህ ተረግጠህ እንደዜጋ ሳይሆን እንደ ባሪያ ትኖራታለህ!” በሚለው መሀከል አይደለም ወይ ግብግቡና ፍልሚያው? እነዚህ ሰዎች በዜግነታቸው በኢትዮጵያዊነታቸው የሀገሪቱንና የሕዝቧን ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ጨርሶ አያውቁም ማለት ነው? የአንዲትን ሀገርና ደኅንነት ዜጋዋ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ማን ከየት መጥቶ ነው የሚያስጠብቅላት? ይህችን ሀገርና ሕዝቧን እራሳቸው ዜጎቿ ካልሆኑ በስተቀር ሌላ ማን ከየት መጥቶ ነው ደህንነታቸውን የሚያስጠብቅላቸው? ይሄንን አለመረዳት ምን ይሉታል? ድንቁርና፣ አለቅጥ ከልክ በላይ የተጫነ ፍርሐት፣ የገዘፈ ራስ ወዳድነት፣ ሆዳምነት፣ አድር ባይነት፣ ኅሊና ቢስነት ወይስ ሌላ ምን?

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ፖለቲካ የምሁራን ተሳትፎ ምን ያህል መንማና እንደሆነና የዳር ተመልካቾች እንደሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ የተማሩ ፊደል የቆጠሩ ከባድ ማኅበራዊ ኃላፊነት የተጫነባቸው የተባሉ ሰዎች የፖለቲካን ምንነት በዚህ መልኩ ተረድተው ይሄንን ያህል ዘቅጠው እንዲህ ካሰቡ ያልተማረ በሚሉት ሕዝባችን ላይ በምንም ጉዳይ ላይ ቢሆን እንዴት ሆኖ ነው ጣት ለመጠቆም የሚያበቃ የሞራል (የቅስም) ብቃት አለን ብለው የሚስቡት? ወጣም ወረደ ፖለቲካ ማለት ሌላ ምንም ማለት ሳይሆን የዜጎች ሕይዎት የሀገር ደኅንነት ማለት ነው፡፡ አንድ ዜጋ እነኝህን ጉዳዮች አያገቡኝም ሊል አይችልም፡፡ ወይም ደግሞ የእነኝህ ነገሮች ምንነት የማይገቡኝ ደንቆሮ፣ ፈሪ፣ ራስ ወዳድ፣ አድር ባይ፣ ሆዳም፣ ኅሊና ቢስ ነኝ ብሎ በራሱ ላይ እየመሰከረ እንዲህ መሆኑን እያረጋገጠ ነው ማለት ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ “ከፖለቲካ ነጻ ወይም ገለልተኛ የሆነ” እየተባሉ የሚቋቋሙ ማኅበራት “ዋነኛ ሥራችን በቀጥታ ፖለቲካዊ አይደለም ማኅበራዊ ነው” ይበሉ እንጅ “ከፖለቲካ ነጻ ወይም ገለልተኛ” የሚባል ነገር ባለመኖሩና አማርኛው ፍጹም የተሳሳተና ቀደም ሲል ካወራነው መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር ፈጽሞ የማይጣጣም በመሆኑ ይሄንን ቃል ከመጠቀምና ሕዝብን ከማደንቆር ቢቆጠቡና ቢታረሙ መልካም ነው ለማለት እወዳለሁ፡፡ ማንኛውም ነገር ከፖለቲካ ነጻ ወይም ገለልተኛ በፍጹም ሊሆን አይችልም (physically impossible)፡፡ እውነት ከአንደኛው ወገን ላይ መሆኗ አይቀርምና ይሄ ከሆነ ዘንዳ ደግሞ የእውነት ደጋፊና ጠበቃ የመሆን ሞራላዊ (ቅስማዊ) ሃይማኖታዊም ግዴታ በሁሉም ሰው ላይ የተጣለ ነውና “ነጻ” ወይም “ገለልተኛ” የሚለው ቃል አያስኬድም ወይም ትክክል አይደለም፡፡ ምንጊዜም ቢሆን እውነት ከሕዝብ ጋር ናት፡፡ “ሕዝባዊ ወይም ማኅበራዊ ነን” የሚል ማኅበር የሕዝቡ የማኅበረሰቡ ደኅንነት ከምንም ጉዳይ በላይ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳትና ችግር የሚፈጥርበት ይህ ፖለቲካዊ ጉዳይ የማይመለከተው ሊሆን አይችልም አይገባምም፡፡ ማኅበራዊ ነው ብላቹህ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ስለ ሕዝባችንና ስለ ሀገራችን ደኅንነት ጉዳይ እኮ ማንሣታቹህ አይቀርም፡፡ ካነሣቹህ ደግሞ በቃ እኮ መሰላቹህ እንጅ ፖለቲካ ማለት እኮ እሱ ነው ሌላ አይደለም፡፡ በመሆኑም “ሕዝባዊ ወይም ማኅበራዊ ነን” ሲሉ “ከእውነት ጋር የቆምን ነን” እንዳሉ ያስቡ እንጅ “ከፖለቲካ ነጻ ወይም ገለልተኛ” እንዳሉ በማሰብ “አያገባንም” ሊሉ በምንም ተአምር አይገባም አይቻልምም፡፡ የቃሉ አጠቃቀም አስቀድሜ እንደገለጽኩት ማንም ሰው በዚህች ምድር እስካለ ጊዜ ድረስ ከፖለቲካ ነጻ ወይም ገለልተኛ መሆን ስለማይቻል የደነቆረና የተሳሳተ አገላለጽ በመሆኑ እንዲታረም ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም በእኩይ ነውረኛ ርካሽና ጠንቀኛ የማንነት ተግባሮቻቸው የመከራ ዘመናችንን ያራዘሙትን ጉዳታችንን ኪሳራዎቻችንን ያበራከቱብንን ያከበዱብንን እራሳቸውን እንደ የማኅበረሰባችን ልኂቃን (Elites) አድርገው የሚቆጥሩትን ከወገብ በላይ ወያኔ ከወገብ በታች ሕዝብ የሆኑ የሌሊት በራሪ የሌሊት ወፎቻችንን እረግሜ ልቋጭ፡- የዕውነት አምላክ ልዑል እግዚአብሔር እጣ ፋንታቹህን ዕድል ተርታቹህን መጨረሻቹህን እንደ የሌሊት ወፎቹ ያድርግባቹህ!!!

በአንጻሩ ደግሞ ሀገርን ከራስ በላይ ዐይታቹህ ሀገርን ከምንም ነገር አስቀድማቹህ መተኪያ የሌላት ነፍሳቹህን ሰጥታቹህላት ይህችን ጠብቃቹህ ያስረከባቹህንን ሀገር እንዳስረከባቹህን ጠብቀን ማስቀጠል ቢያቅተንምና ሀገር በየአቅጣጫው በሰሜን በምዕራብ በምሥራቅ ነገ ደግሞ በየት እንደሚቀጥል አናውቅም እንደቂጣ እየተሸራረፈች ስትሰጥ ስትሸጥ ጸጥ ብለን በማየት፤ ግን ምን እናድርግ? እናንተ እኮ! ነፍሳቹህን እስከመስጠት ቁርጠኛ ሆናቹህ መሥዋዕትነት ብትከፍሉ በዘመናቹህ ሀገር ወዳድ የሀገሩን ጉዳይ ፈጽሞ ለድርድር የማያቀርብ ከሀገራችንና ከሕዝቧ በላይ የሚያየው ምንም ነገር የሌለው ኢትዮጵያዊ መንግሥት ቢኖራቹህና ቢያዘምታቹህ ነው፡፡ እኛ እኮ! የተቸገርነውና አደራቹህንም ለመጠበቅ እንዳንችል ያደረገን ይህች ሀገር ዐይታው የማታውቀው ኢትዮጵያዊ ስሜት፣ ወኔ፣ የሀገር ፍቅር፣ ተቆርቋሪነት ቅንጣት እንኳ የሌለው ለሀገርና ለሕዝቧ ሳይሆን ለባዕዳንና ለጠላቶቻችን ታጥቀው ተግተው የሚሠሩ ከሀዲያን የእፉኝት ልጆች መንግሥት ሆን ብለው ተቀምጠውብን እንዴት ብለን በየት በኩል ማን አዝምቶን? ማን አስተባብሮን? ማን አስታጥቆን? ድንበራችንን ከጠላት እንከላከል? እንጠብቅ? እሱ ራሱ ጠላትና የጠላት ቅጥረኛ ሆኖብን?

“ድንበር የሚደፍር ሀገር የሚፃረር ጠላት መጥቶብሀል ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት!” ብሎ አውጆ ሀገራችንን ከጠላት እንድንጠብቅ ሊያስታጥቀን ሊያዘምተን ሊያስተባብረን የሚገባው መንግሥት ተብየ እሱ ራሱ ድንበር የሚያፈርስ መሬት የሚቆርስ ሀገር የሚያምስ አንድነታችንን የሚያፈራርስ በዘር በሃይማኖት እየከፋፈለ ሊያባላን ሴራ የሚጠነስስ ጉድጓዳችንን የሚምስ ጠላት ከጠላትም ጠላት ሲሆንብን እንዴትና በየት በኩል አደራቹህን እንጠብቅ? ችግራችን ይሄ መሆኑ ምንም እንኳን ከተጠያቂነት ባያድነንም የገጠመን ችግር እኮ እንኳን በሀገራችን በዓለማችን እንኳ አንድ መንግሥት በገዛ ሀገሩ ሲያደርገው ታይቶ የማይታወቅ በዐይነቱ የተለየና ትንግርት በመሆኑ እኮ ነው ነገሩን የባሰ አስቸጋሪ ያደረገው፡፡ ለማንኛውም ለውዲቷ ሀገራችን ነጻነትና ህልውና በአርበኝነት ከተጋደላቹህት ጀምሮ በጊዜና በቦታ ሳትወሰኑ መቸም የትም ለእውነት በመቆማቹህ እውነትን በመመስከራቹህ ልትከፍሉት የምትችሉት ዋጋ መሥዋዕትነት ሳያሳስባቹህ ሳያስጨንቃቹህ ሳያንበረክካቹህ ሰው የመሆንን ዋጋ በሚገባ ተረድታቹህ ሆድን፣ የግል ጥቅምን፣ ራስ ወዳድነትን፣ አድር ባይነት፣ ፍርሐትን አሸንፋቹህ ሥጋን ከነ ክፉ መሻቱ በመስቀል ለኅሊናቹህ ለእውነትና ለአምላክ ታላቅ ዋጋና ክብር በመስጠት ለዚህች ብርቅየ ሀገርና ለዚህ ውድ ሕዝብ ዋጋ መሥዋዕትነት የከፈላቹህ ዋኖቻችንን ጀግኖቻችንን ደግሞ ውኃ ሽቅብ አይፈስምና ምንም ብየ ልመርቃቹህ ባይቻለኝም ለከፈላቹህልን ዋጋና መሥዋዕትነት ላበረከታቹህልን ትሩፋት ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ይስጥልን!!! እጅግ እጅግ እጅግ እናመሰግናለን!!!

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እባክህን ለዚህች ብርቅ ሀገርና ውድ ሕዝቧ ልዕልና ነጻነት ደኅንነትና ህልውና ሲሉ መራር ዋጋ መሥዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖቻችን ዋኖቻችን ድካምና መሥዋዕትነት ከንቱ ሆኖ ይቀር ዘንድ አትፍቀድ? “የእሳት ልጅ አመድ” ሆነና ተረቱ ስንት ታሪክ የሠራ ሕዝብ ለስንቶች ስንት ያደረገ ስንት የሆነ ሕዝብ ጠላቶቻችን በምን በኩል እንዴት ሆነው ቢገቡብን ውጤታማ እንደሚሆኑ ተረድተው በደናቁርቱ በባንዶቹ በደካሞቹ ላይ ተጭነው በመግባታቸው ያ ታላቅ ሕዝብ ዛሬ ለራሱ እንኳን ሳይሆን ቀርቶ ለመፍረስ ገሐድ አደጋ በመጋለጡ ተጨነቅን ፍርሐትና ሥጋት እረፍት ነሳን፡፡ እውን ሥጋታችን ተግባራዊ ይሆናል? አንተን ከመበደላችን ከዐመፃ ሥራችን የተነሣ የጠላቶቻችን ጥረትና ምኞት ሠምሮ እውን ሀገራችን እንድትፈርስ ሕዝባችን እንዲጠፋ ትፈቅዳለህ?
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገብረ ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

The post የልኂቃኖቻችን ማንነትና ያደረሱብን ኪሳራ!!! appeared first on Zehabesha Amharic.

ጂ ሜይል በስህተት የተላከ መልዕክት ለማጥፋት የሚያስችል መተግበሪያ ጥቅም ላይ አዋለ

$
0
0

gmail
በሙለታ መንገሻ
ጂ ሜይል / Gmail/ በስህተት የላክነውን መልዕክት በ30 ሴኮንድ ውስጥ ለማጥፋት የሚያስችል /undo/ መተግበሪያ ጥቅም ላይ ማዋሉን አስታውቋል።

ይህም በስህተት የላክነው መልዕክት የላክንለት ሰው እንዳያየው የሚያስችል ነው ተብሎለታል።

የጂ ሜይል አካውንት ያላቸው ሰዎችም ሴቲንግ ውስጥ በመግባት undo የሚል ቦታ ላይ በመጫን የሴኮንዱን እርዝመት በመሙላት መጠቀም የሚቻል መሆኑን ኩባነያው አስታውቋል።

አዲሱ የጂ ሜይል አገልግሎትም በስህተት የላክነውን መልዕክት የላክንለት ሰው ጋር ደርሶ ከመታየቱ በፊት ለማጥፋት የሚረዳ በመሆኑ ሰዎችን ከስህተት የጸዳ ስራ እንዲሰሩ ያስችላልም ተብሏል።

ጂ ሜይል ከ11 ዓመታት በፊት አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፥ እስካሁንም በዓለም ዙሪያ ከ900 ሚሊየን በላይ የጂሜይል አካውት ያላቸው ሰዎች እንዳሉም ጎግል ባሳለፍነው ወር ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

ምንጭ፦ news.sky.com

The post ጂ ሜይል በስህተት የተላከ መልዕክት ለማጥፋት የሚያስችል መተግበሪያ ጥቅም ላይ አዋለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ ህይወት አዳነ

$
0
0

jersy
(አድማስ ዜና) ባህሬን ፦ አሲያ አብዱ ትባላለች፣ ባህሬን ከመጣች ሁለት ሳምንት ቢሆናት ነው፣ እሷ እንደምትለው ፣ የመጣችው ለደላላ 8ሺ ብር ከፍላ ሲሆን፣ የልብ ህመም አለባት፣ እናም ከመጣች በኋላ መስራት አልቻለችም። ስለዚህ አስሪዎቿን መስራት እንዳቃታትና ወደ አገሯ መመለስ እንደምትፈልግ ትነግራቸዋለች።

እነሱ ግን ፣ ያወጣነውን ወጪ መልሰሽ፣ ከዚያም የራስሽን ትኬት ገዝተሽ ነው እንጂ፣ እንዲሁ አንለቅሽም ይሏታል። ከዚያም ለአራት ቀናት ያህል በአንድ ክፍል ውስጥ ዘግተውባት ስታለቅስ ትከርማለች፣ ታዲያ በመካከል ከነበረችበት አራተኛ ፎቅ መስኮት ከፍታ ለመወርወር ስትዘጋጅ፣ ድንገት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ የለበሰ ወጣት ሲያልፍ በመመልከቷ በጩኸት ድረስልኝ ትላለች። ልጁም ያለችበት ተጠግቶ፣ ክፎቅ ላይ እንዳትወድቅ በመለመን አሳምኖ፣ እዚያው እንደቆመ፣ ለባህሬን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እና ለፖሊስ ይደውላል።

የኮሚኒቲው ተወካይ ከቦታው ደርሶም ጉዳዩን ካየ በኋላ፣ ፖሊስ እስኪመጣ ድረስ ከውጭው ከባድ ሙቀት ለመራቅ ጥግ ይዞ ሳለ፣ ከልጅቷ ቤት ጩኸት ይሰማል፣ ሮጦ ፎቁ ላይ በመውጣት ሲገባም፣ አስሪዋ ልጅቷን ማሰቃየቱና ጨለማ ቤት ማስቀመጡ እንዳይታወቅበት፣ በጓሮ ይዟት ሊወጣ ሲጎትታት ይደርሳል፣ ያን ጊዜ እሷን አስጥሎ፣ ወዲያውም ርዳታው ደርሶ ልጅቷ በህይወት ተርፋ የባህሬ ኮሚኒቲ ጽህፈት ቤት በአሁኑ ሰአት እንደምትገኝ ታውቋል።

The post የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ ህይወት አዳነ appeared first on Zehabesha Amharic.


የሚሚ ስብሃቱ እና የባሏ ዘሪሁን ተሾመ (ዛሜ ኤፍ ኤም)ሬዲዮ ሊዘጋ ነው ያላችሁ ተሸውዳችኋል

$
0
0

ከብስራት ወልደሚካኤል

ዛሜ ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ (የሚሚ ስብሃቱ እና የባሏ ዘሪሁን ሬዲዮ )ሊዘጋ ነው በሚል የዜና መረጃውን ለሰጡን እናመሰግናለን፡፡ ነገር ግን ይሄንን አምናችሁ ለምትቀበሉ ግን ተሸውዳችኋል፡፡ ምክንያቱም ሚሚ ስብሃቱና ባሏ ቀደም ሲል ከኢህአዴግም ለህወሓት ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩት በብሐረ ትግራይ ትስስርነት የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዛ ይልቅ ከህወሓት ያስተሳሰራቸው ለጣቢያው ፈቃድ ከማግኘታቸው ጀምሮ በህወሓት ከከፍተኛ ገንዘብ እስከ ህግ ከለላ የሚደርስ ድጋፍ ይደረግላቸው ስለነበር ነው፡፡ ለዚህም ከየትኛው ካዝና እንደሆነ ባይታወቅም ለዛሚ ኤፍ ኤም ብቻ በሕወሓት ባለስልጣናት በዓመት እስከ 15 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በጀት ይመደብላቸው እንደነበርስ ስንቶች ያውቁ ይሆን? ጣቢያውስ ለምን እንደተቋቋመስ ስንቶች ያውቁ ይሆን?
Mimi sebhatu
ጣቢያው (ዛሚ ፐብሊክ ኮኔክሽን/ዛሚ ኤፍ ኤም 90.7) በ1998 ዓ.ም. ሲቋቋም አዲስ አበባ በሙሉ የቅንጅት ደጋፊ ከመሆኑ በላይ ኢህአዴግን አምርሮ ይጠላልና ወጣቶችን በገንዘብና በልዩ ጥቅማጥቅም ከመደለል በተጨማሪ በአዲስ አበባ አካባቢ ያለውን መረጃ በአማራጭ ስም የህወሓትን የበላይነት ለማስጠበቅ እንደሚዛን ለመጠቀም የታለመ ነበር፡፡ ሚገርመው ከዛ በፊት በነ ዶ/ር ብርሃኑ እና ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም (ወደ ፖለቲካው ሳይገቡ በፊት) እና ጋዜጠኛ መለስካቸው እና ሌሎች ባለሙያዎች የተሳተፉበት በከፍተኛ በጀት የተመሰረተው አዲስ ብሮድካስቲንግ ካምፓኒ ትልቅ የሚዲያ ተቋም (ኤፍ ኤም ሬዲዮ፣ አጭርና መካከለኛ ሞገድ፣ ወደፊት ቴሌቪዥን ጣቢያ) ነፃ የብሮድካስ ሚዲያ ለማቋቋም ማመልከቻ አስገብተው ፈቃድ ተገኝቶ እጅግ ዘመናዊ የሬዲዮ ጣቢያ ማሽኖች ከገቡ በኋላ ተከልክለዋል፡፡ ከዛ በኋላ ዶ/ር ብርሃኑ እና ፕ/ር መስፍን በምርጫ 1997 ዓ.ም. የተደራጀ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ በመመስረት ቅንጅት እንዲመሰረት ዋነኛ ተዋንያን ነበሩ፡፡ በምርጫውም ቅንጅት አዲስ አበባን ከኢህአዴግ ጅቦች አፀዳ፤ከዛም የአዲስ አበባ ህዝብ የመስተዳደሩን መብት በቻርተር ስም ባንድ ለሌት ህግ ተቀማ፡፡ በዚህ ብቻ ሳያበቃ በቀለኛው ኢህአዴግም የአዲስ ብሮድካስቲንግ ካምፓኒ መሳሪያዎች በሙሉ ወረሰ፣ ሊቋቋም የነበረው ብሮድካስት ጣቢያ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሃ (አሁን የቪ ኦ ኤ ጋዜጠኛ) ታስሮ ከፍተኛ በደል ከተፈፀመበት በኋላ ተለቋል፡፡

የአዲስ አበባን እና አካባቢውን ህዝብ የመረጃ ፍሰት በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን እና በሬዲዮ ፋና ብቻ ሚዛን ማስጠበቅ (በኢህአዴግ መረጃን ማዛባት) ስለማይቻል በከተማው የተወሰነ ኤፍ ኤም ሬዲዮ በግል ስም ማቋቋምና ድጋፍ ማድረግ ወደሚለው ተመራ፡፡ ያኔ ቀዳሚ የሆኑት ሚሚ ስብሃቱ እና ባለቤቷ ዘሪሁን ዕቅዱን ለመፈፀም ፈቃደኝነታቸውን ገለፁ፤ወደስራም ገቡ፡፡ ከዛ በፊት ሚሚ ስብሃቱ ከመሰናበቷ በፊት የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጋዜጠኛ የነበረች ሲሆን፤ ባለቤቷ አቶ ዘሪሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአቶ መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ ቀጭን ትዕዛዝ ከተባረሩ መምህራን አንዱ ነበር፡፡

mimi sibehatuበመጨረሻም ለዛሚ ኤፍ ኤም በዓመት 15 ሚሊዮን ብር ከህወሓት ተመድቦ ወደስራ ሲገባ፤ ሚሚ ስብሃቱ በአስገራሚ ሁኔታ ለአንድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከሚገመተው በ4 እጥፍ የሚልቅ ጋዜጠኞች ቀጠረች፡፡ እነ ሚሚ ስብሃቱም ለጣቢያው የተመደበውን ብር በቀጥታ ሙሉ በሙሉ ወደስራ ከማስገባት ይልቅ አብዛኛውን ወደኪሳቸው በመወርወር ለተቀጠሩት ጋዜጠኞች በወቅቱ ደመወዝ መክፈል ሳይችሉ ይቀራሉ፡፡ ያኔ በአንድ ጊዜ 20 ጋዜጠኛ ከጀማሪው ዛሚ ኤፍ ኤም ስራ ይለቃሉ፡፡ ከዛም አቶ መለስ ዜናዊ በባለቤታቸው አዜብ መስፍን አማካኝነት እና በነ ስብሃት ነጋ የተመደበው ብር ዓመት ሳይሞላው የት ሄዶ ነው ይህ የተፈፀመውና እና ሌሎችም ጥያቄዎች ከአስገዳጅ ሁኔታ ጋር ካቀረቡ በኋላ የቀሩት ጋዜጠኞችን (የቅርብ ቤተሰብ የነበሩትን) ጨምሮ ሌላ ጋዜጠኞች እንዲቀጠሩ፣ የጣቢያውም የአየር ሰዓት በመዝናኛ እና ቴክኖሎጂ ላይ የሚያተኩሩ ወጣቶች ተወዳድረው እንዲሰሩ ዕድሉ እንዲፈጠር የሚል ሐሳብ ቀረበና ተግባራዊ ተደረገ፡፡ የፖለቲካና ማኀበራዊ ጉዳይ በነሚሚ ቁጥጥርና ክትትል የሚመራ ዜና እና ውይይቶች እንዲቀርቡ ሲደረግ መዝናኛዎች ላይ ተወዳድረው የሚገቡ ወጣቶች የአየር ሰዓቱን በመጋራት እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡

በጣቢያው መዝናኛ እና ቴክኖሊጂ ላይ የአየር ሰዓት ተጋርተው ይሰሩ ከነበሩት መካከል ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስ (በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እጮኛ) እና አሁን ከዞን 9 ብሎገሮች ጋር በእስር ላይ የሚገኘው የአዲስ ጉዳይ መፅሔት አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ሚገርመው እነ ሚሚ መዝናኛ ላይም ሳንሱር ይቃጣቸው ስለነበር እነዚህና ሌሎች ወጣቶች ባለመስማማት ስራቸውን በፈቃዳቸው አቁመው ወጥተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ቢኖርም ከእንግሊዝ ከሚያገኙት ርዳታ በተጨማሪ በህወሓት ቀጥተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ይደረግለት የነበረው የነ ሚሚ ዓመታዊ በጀት ግን እስከዛሬም አልቆመም፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ማንኛውም የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ በወቅቱ ከነበሩት 5ቱም) የአየር ሞገድ ኪራይና ግብር ለብሮድካስ ባለስልጣን በየዓመቱ የሚከፍሉ ቢሆንም የነ ሚሚ ግን በዝምታና ይታለፍ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ለአንድ ጉዳይ ሁለት የህግ ትግበራ የተለመደም አይደል?እንደዛ ነው፡፡ ጣቢያው አድማጭ ባለመኖሩ የኢህአዴግ ድርጅቶች እንኳ በግድ ከበላይ በሚሰጥ ግዴታ ካልሆነ በዚህ ጣቢያ መ፣ስታወቂያ እንኳ አያስነግሩም፡፡ ስለዚህ ከህወሓት ከሚመደብለት በጀት በቀር ገቢ እንኳ አልነበረውም፡፡ የኢህአዴግ አባላትም ቢሆኑ ጣቢያውን የሚወዱት አይደለም፡፡ አቀራረቡና የመረጃዎቹ ይዘት ምን እንደሆነ ለማወቅ የግድ ባለሙያ አያስፈልገውና፡፡ ስለዚህ ጣቢያው የተቋቋመው የአዲስ አበባን መረጃ ለማዛባት እና ለማስተንፈስ በሚል ቢሆንም እስካሁን ስኬታማ ሊሆን አልቻለም፡፡
የሚሳዝነው በዚህ ጣቢያ ህወሓት ሊያስራቸው ያሰባቸውን ዕጩ እስረኞች ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገፅ 3፣ አይጋ ፎረም፣ ትግራይ ኦን ላይን እና ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ቀጥሎ ይፋ የሚደረገው በዚሁ በነሚሚ ስብሃቱ (ዛሚ ኤፍ ኤም)ነው፡፡ ለዚህም አንድ ማስረጃ ብቻ ጠቅሼ ልለፍ፡፡ ረቡዕ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. በዚህ ዛሚ ኤፍ ኤም አንዱዓለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አመፅ ሊቀሰቅሱ ነው፣ ህዝብ ሊያሸብሩ ነው፣ መንግሥት እንዴት ዝም ይላቸዋል በሚል ሚሚ ስብሃቱ ፣መሰረት አታላይ፣ ዘሪሁን ተሾመ(የሚሚ ባል)፣…በጣቢያው የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ ውይይት ላይ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ ከዛም የጣቢያው ስርጭት እንዳለቀ በዕለቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አራጌ እና ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ታሰሩ፣ በምሽት የቴሌቪዥን ዜናም እንደወንጀለኛ ተቆጥረው የዕለቱ አብይ ዜና ሆነው አመሹ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን መንግሥት የከሰሳቸውና ከአንባቢ ውጭ ያደረጋቸው ፍትህ እና ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ፣ አዲስ ጉዳይ፣ ፋክት፣…እና ሌሎችም የተዘጉ መፅሔቶች አመፅ ሊቀሰቅሱ ነውና ዝም ሊባሉ አይገባም በሚል ሚሚ ስብሃቱና በልደረቦቿ በዛሚ ኤፍ ኤም ሲሞግቱ ነበር፤ተግባራዊም ተደረገ፡፡ ይህ የሚያሳየው እነ ሚሚ ስብሃቱ የተቋቋሙለት ዓላማ ምን እንደሆነ ትንሽ ፍንጭ ለመስጠት ያህል እንጂ ዝርዝር ሁኔታ እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡ እና ዛሬ የነሱ ሬዲዮ ዛሚ ኤፍ ኤም ሊዘጋ ነው…የሚለው ከጀርባው ሌላ አጀንዳ እንዳለ መርሳት የለብንም፡፡ ለዚህም የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ መፅሐፍ ላይ ስዕላይ ባራኺን እነ ሻዕብይ ለስለላ ተልዕኮ አሰማርተውት …በሚዲያቸው ያስተጋቡት ግን ይሄ ከሃዲ ጥሎን ሄደ፣ ድሮም አይረባም…ምናምን ፕሮፖጋንዳን ያስታውሰናል፡፡
በነገራችን ላይ ነገ ሸገር ኤፍ ኤምም ሆነ ሌሎቹ (ከህወሓት ሰወች ውጭ ) ያሉት የግል ጣቢያዎች የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በህግም ሆነ በሌላ የጉልበት መንገድ መዘጋታቸው የማይቀር ነው፡፡ በዕቅድ መልክ የተያዘ አዲስ መመሪያ(የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ፈርሰው ከመንግስት የአየር ሰዓት ተከራይተው እንዲሰሩ ሚያዝ) እየወጣ ነውና፡፡

በተለያ የብሮድካስት አየር ሞገድ ፈቃድ ሰጭው የኢትዮጵያ ብሮድካስ ባለስልጣን በነ ዘርዓይ አስገዶም (የኢቴቪ ስራ አስኪያጅ የነበረው) በነ ልዑል ገብሩ እየተመራ እነ ሚሚ ፈቃድ ተነጥቀው ጣቢያው ይዘጋል ማለት የዋህነት ነው፡፡ ምናልባት ሌሎችን ጣቢያዎች ለመዝጋት እንደምሳሌ ለመጠቀምና እን ሚሚን ወደ ሌላ ፋናም ሆነ ኢብኮ በማዛወር ተጨማሪ ተልዕኮ ለመስጠትና አቅጣጫ ለማስቀየር ታስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የነ ሚሚ ስብሃቱ (የህወሓት ሌለው የአዲስ አበባ ሚዲያ ክንፍ) በአገልግሎት ጥራትና ግብር ባለመክፈል በሚል የሚዘጋ የሚመስላቸውም ካሉ ተሳስተዋል፡፡ ምናልባት ሰሞኑን ሚሚ ስብሃቱ በየ አደባባዩ የፕሬስ ነፃነት ተዳፈነ ብላ ግር ግር እንድትፈጥር ሊደረግ ሁሉ እንደሚችል ጠብቁ፤ ግን እንዳትሸወዱ፡፡ ይህ የህወሓት ሉላው ስትራቴጂ መሆኑንም እንዳትዘነጉ፤ እንዳትሸወዱ፡፡ ጨወታው ሌላ ነውና አጀንዳ ባናደርገው ይመረጣል፡፡ ነገሩ አህያ ለአህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሰበርም ነውና…

The post የሚሚ ስብሃቱ እና የባሏ ዘሪሁን ተሾመ (ዛሜ ኤፍ ኤም)ሬዲዮ ሊዘጋ ነው ያላችሁ ተሸውዳችኋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ቆራጡ የዲሞክራሲ ታጋይ ዳዊት አስራደ ከሀገር ተሰደደ!!

$
0
0

እየጎመዘዘኝ የሰማሁት ዜና ነው!!

11659237_1018365658188047_2011915667152766052_nወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ የሚወዳቸውን ቤተሰቡንና ልጁን ትቶ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል፡፡ ዳዊት ከ13ቱ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የአንድነትን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድም ከሌሎች የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የነደፈ ሙሉ ማንነቱን ለሀገር ትግል የሰጠ ቁርጥ ኢትዮጵያዊ ልጅ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም በአማራ ክልል ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያለ በመኪና ተገጭቶ ለ6 ወራት ተኝቶ ከሞት ድኗል፡፡

በ97 ዓ.ም በቅንጅት ፓርቲ ውስጥ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን የጀመረው ዳዊት አስራደ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራች አባልም ነበር፡፡ ዳዊት በፓርቲው የተለያዩ ሓላፊነቶች ላይ የሰራ ሲሆን ለአብነትም

– በወጣቶች የትምህርትና ስልጠና ዘረፍ

– የብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ አባል

– የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ዋና ጸሀፊ

– የኢኪኖሚ ጉዳዮች ሃላፊና በተለያዩ የአድሆክ ኮሚቴዎች ውስጥ በሀላፊነትና በአባልነት ሰርቷል፡፡

የአንድነትን የ5 አመት እቅድና ስትራቴጂ ከነደፉት ሰዎች መካከልም ዳዊት አለበት፡፡ በ2002 ምርጫ አንድነት መድረክን ወክሎ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ተወዳዳሪ ነበር፡፡ ሆኖም በ2007 የአንድነት ፓርቲ በምርጮ ቦርድ ለነ ትግስቱ አወል መሰጠቱን በመቃወም ከፓርቲው ሙሉ በሙሉ ቢገለልም በገጠመው ተደጋጋሚ እስርና እንግልት ምክንያት ሀገሩን ትቶ ሂዷል፡፡

መንግስት በሽብር ቡድኖች በሊቢያ የተቀጠፉ ኢትዮጵያውያንን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ቪዲዮ ቀርጻሃል›› በሚል ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በፖሊስ ተይዞ ቄራ ፖሊስ ጣቢያ ገባ፡፡ ሰልፉን በሞባይል በቀረጸበት የ25000.00 ብር ዋስ እንዲለቀቅ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ምድብ ችሎት ወሰነ፡፡ ሆኖም አቃቢ ህግ ወዲያውኑ በ14 የተደረገውን ሰልፍ ለማወክ በ13 ከ200-300 የሚሆኑ ወጣቶችን አደራጅተሃል የሚል ተጨማሪ ክስ መሰረተበት፡፡ ይህን ክስ ደግሞ በ6000.00 ብር መያዣ ይፈታ ሲባል በእለቱ ስብሰባው ላይ ችግር ፈጥረሃል የሚል ክስ ታከለለት፡፡ ለዚህ ደግሞ 5000.00 ብር አስይዝ ተባለ፡፡

ሚያዚያ 14 በቄራ፣ ከሚያዚያ 15- 21 በፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስሮ ቆየ፡፡ ሚዚያ 21 ቀን ባስያዘው ገንዘብ ተፈቶ ሳይሰደድ ሲቀር ይምሰላል በግንቦት 3 ቀን ከፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ተደወለለት፡፡ ያስያዝከውን ንብረት ውሰድ ነጻ ነህ አሉት፡፡ ሲሄድ ግን ታሰረ፡፡ ሶስት ቀን ፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ከቆየ በኋላ ወደ ማእከላዊ ተወሰደ፡፡ ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዘያት እስከ ሰኔ 5 ቀን በማእከላዊ እስር ላይ ቆይቶ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ምድብ ችሎት በእለቱ እንዲፈታ ወሰነ፡፡ እስካሁን ያዝያዘው 36000.00 ያልተመለሰለት ሲሆን ሰኔ 19 ቀን ፍርድ ቤት እንዲገኘ ሌላ ቀጠሮ ተሰጠው፡፡

ዳዊት በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ባሉ መርማሪ ፖሊሶች ከኢህአዴግ ጋር እንዲሰራ ግብዣ ቀርቦለት ነበር፡፡

ዳዊት አስራደ በተለያዩ ባንኮች በተለያየ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሰርቷል፡፡ አገር ጥሎ በወጣበት ወቅትም በህብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የአንድ ክፍል ዋና ሓላፊ እና ጥሩ ደመዝ ተከፋይም ነበር፡፡ ዳዊት የአንድ ልጅ አባትና ባለትዳር ነው፡፡

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስርዓቱ እግር ተወርች አስሮ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ በዚህ ሳምንት አገሩን ጥሎ መጥፋቱ ተገልጧል፡፡

(ዛሬ የሰማሁት መራር ዜና ነው- የዳዊት አስራደ ስደት፡፡ ይህን ቆራጥ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ታጋይ በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ የሚወደውን ልጁን፣ የሚያፈቅራትን ሚስቱን እና ሀገሩን ትቶ መሰደዱን ስሰማ ከልቤ አነባሁ፡፡ )

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8067#sthash.3jr38q3y.dpuf

The post ቆራጡ የዲሞክራሲ ታጋይ ዳዊት አስራደ ከሀገር ተሰደደ!! appeared first on Zehabesha Amharic.

እነ ወይንሸት ሞላ ላይ ድጋሜ የቀረበውን መዝገብ ዳኞች አንቀበልም አሉ

$
0
0

9271_728586630600331_5995106938468341166_n
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በእነ ወይንሸት ሞላ የክስ መዝገብ መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ በእስር ላይ የሚገኙት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ላይ ፖሊስ በድጋሜ ያቀረበውን የምርመራ መዝገብ ዳኞቹ አንቀበልም ብለዋል፡፡
እነ ወይንሸት ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ቀርበው እንዲፈቱ ተወስኖ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፖሊስ ከእስር ሲወጡ በር ላይ በድጋሜ አስሮ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ይታወቃል፡፡

ዛሬ ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው ተመሳሳይ ‹ወንጀል› ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ይዞ ቀደም ብለው ውሳኔ ባገኙበት በተመሳሳይ ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበር ቢሆንም ዳኞቹ ‹‹እኛ ፈርደናል፤ እንዲለቀቁም ወስነናል፣ ከዚህ በኋላ ይህን ጉዳይ አናይም›› በሚል መዝገቡን እንደማያዩ ገልጸው መልሰዋቸዋል፡፡

ፖሊስ ፍርድ ቤቱ ክሱን እንደማያይ ከገለጸ በኋላ እነ ወይንሸትን ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የመለሳቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቱ የወሰነላቸው አራቱም እስረኞች ጉዳይ ምን ሊሆን እንደሚችል ግን ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም፡፡

The post እነ ወይንሸት ሞላ ላይ ድጋሜ የቀረበውን መዝገብ ዳኞች አንቀበልም አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቶ አስገደ ገ/ሥላሴ አዲሱ “የመለስ ራዕይ ሲፈተሽ”መጽሐፍ በአሜሪካ መሸጥ ጀምሯል – (የት እንደሚገኝ እንጠቁምዎ)

$
0
0

አቶ አስገደ ገብረሥላሴ የ’መለስ ራዕይ ሲፈተሽ’ የሚል መጽሐፍ ማሳተማቸው ይታወሳል:: መጽሐፉ በሰሜን አሜሪካም ለገበያ የቀረበ ሲሆን የት ቦታዎች እንደሚገኝ ፎቶ ግራፉ ላይ በመጫን ማየት ትችላላችሁ::
asegede gebresilase

The post የአቶ አስገደ ገ/ሥላሴ አዲሱ “የመለስ ራዕይ ሲፈተሽ” መጽሐፍ በአሜሪካ መሸጥ ጀምሯል – (የት እንደሚገኝ እንጠቁምዎ) appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለበት ይገኛል

$
0
0

Shimeles Kemal
<<ሰለፊስቶች ባሉበት ሁሉ ጦርነት፣ሁከት፣ብጥብጥ ይኖራል>> አቶ ሽመልስ ከማል ከተናገሩት!

 

አቡበከር አህመድ
መንግስት በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለ ሲሆን ከምርጫ ማግስት በአዳማው ቲታስ ሆቴል በተካሄደውና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴንና በተለይ ምክትላቸው አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ዘልቆ መግባቱን የሚያስረዱ ንግግሮችን አድርገዋል። አቶ ሬድዋን ሁሴን በዋናነት ሽብርተኝነት በተመለከተ በምዕራባውያን እይታና በኢትዮጵያ መንግስት እይታ መካከል ያለውን ልዩነት አብራርተዋል።
ምክትላቸው አቶ ሽመልስ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በእስልምና እምነት ስር ሰለፊዝም በሚባለው አስተምህሮት አማካኝነት ወደሽብር እየገባች እንደሆነ ያስረዱ ሲሆን በንግግራቸውም <<ሰለፊዝም ባለበት ቦታ ሁሉ ጦርነት አለ የሰለፊዝም አስተሳሰብ የሚያራምዱ አካላት ሁሉ ዓለማዊ መንግስት አይቀበሉም በሸሪዓዊ ስርዓት ብቻ ነው የሚያምኑት የሀገርን ህልውና ያፈራርሳሉ ለምሳሌ አይኤስአይኤስ (ISIS) የተባለውም ቡድን ይሄ ነው አላማው በሀገራችንም እነዚህ አካላት እራሳቸውን ማጠናከር ጀምረው እስከሚኖሩበት አከባቢም መነጠል ጀምረዋል ለምሳሌ ኮልፌና አየር ጤና ይሄንን አስተሳሰብ ልንከላከለው ይገባል ከዚህ ቀደም በሀገራችን የነበረው የሱፊዝም እስልምና ተከታዮች ከህብረተሰቡ ጋር አብረው መኖር ይችላሉ። አሁን የዚህ ተከታዮች እየጠፉ ነው አስተማሪዎቻቸውም እንዲጠፉ እየተደረገ ይገኛል ይሄንን አስተምህሮት ልንደግፈው ይገባል ለዚህ ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ያለው አንዱ የሰለፊዝም አካል ወሀቢዝም የሚባለው አስተምህሮት ነው። በሀገራችን ከ2004 ጀምሮ የተከሰተው የእምነት ችግር ከዚሁ ጋር ይያያዛል በወቅቱ ለዚህ ተጠያቂዎቹ አሁን በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ ወሀብዮችና ሰለፊስቶች አንድ ናቸው በአካሄድ ብቻ ልዩነት አላቸው እነዚህ አካላት ከዚህ በላይ ከተጠናከሩ እንደ ናይጄሪያ ትልቅ ቀውስ ማስከተላቸው አይቀርም በገንዘብ አቅም በኩል ጎልበተዋል በቴክኖሎጂም ሚፈልጉትን የሚፈፅሙበት ላይ ይገኛሉ>> በማለት በጥቅሉ መንግስት አሁንም በእስልምና ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደሚቀጥል የሚያረጋግጥ ንግግር አድርገዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች የተጠየቁ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ፓሊስ በህግ ስር ታራሚዎችን የሚይዝበት መንገድ አግባብነት፣ የፕሬስ ነፃነትና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
ምንጭ: ሪፓርተር

The post መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለበት ይገኛል appeared first on Zehabesha Amharic.

የሸሪዓ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጣር በማእከላዊ (1)

$
0
0

የመፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የነበሩትና የቀድሞ የፌዴራል ሸሪዓ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ሸህ መከተ ሙሄ አሰቃቂውን የማእከላዊ ወህኒ ቤት ቆይታቸውን ወደ ኋላ እያጠነጠኑ ይተርኩታል… 

ferdየእኔ ተራ ደርሶ ስለነበር በኪሴ የነበረውን 500 ብር እና ቀበቶ፣ በብሔራዊ ፖስታ ቤት ሪኮማንዴ ያስገባሁበትን ደረሰኝ፣ ሰዓቴንና መታወቂያ ካርድ ተረከቡኝ። እጅግ የደቀቀ ፍተሻ ተደረገልኝ። ይህን እንደጨረስኩ ወደ ጨለማ ቤት ቁጥር 10 አስገቡኝ። የበሩን መዝጊያ ብረት በቁልፍ ከፍቶ ሲበረግደው ጩኸቱ እጅግ ያስደነግጣል። ‹‹ግባ!›› ብሎ ወደውስጥ ገፈተረኝ። ቤቱ ጨለማ ስለሆነ ከውጭ የሚገባ ሰው ምንም ማየት አይችልም። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ከቤቱ በረንዳ ላይ የመንገድ መብራት ስለነበር በእሱ ውራውርት የተወሰነ ነገር ለማየት እድል አገኘሁ። በበሩ ጩኸት ከእንቅልፍ ባነው ከተጋደሙበት የተወሰኑት ቀና ቀና አሉ። ሸህ ሱልጣን ከእኔ ቀድመው በዚሁ ክፍል ገብተው ስለነበር ተነስተው አቅፈው ‹‹አሰላሙ አለይኩም በሰላም መጣህ! አይዞህ! ለማንኛውም ሲነጋ እናወራለን። እዚህ ተኛ›› ብለው ወደቦታቸው መለስ አሉ። እኔ አገር አማን ብዬ ለመተኛት ጃኬቴን ሳወጣ ያዩኝ የነበሩት በግንቦት 7 ተጠርጠረው የታሰሩት መምሬ ደሳለኝ እንበአል በረጋ አነጋገራቸው ‹‹ወንድሜ አሁን መልሰው ስለሚጠሩህ ልብስህን አታውልቅ፤ አንተ ይህን ቤት የምታውቅ አይመስለኝም፤ ለማንኛውም እንዳትደናገጥ ጋደም በል›› አሉኝ። ይህንን ንግግር በጥርጣሬ ነበር የተቀበልኩት። ‹‹ኧረ ጉድ! መንግሥት እዚህም ሰላይ አስቀምጦ ቢሆን?›› የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ ውስጥ ተመላለሰ።*የሸሪዓ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጣር በማእከላዊ የመፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የነበሩትና የቀድሞ የፌዴራል ሸሪዓ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ሸህ መከተ ሙሄ አሰቃቂውን የማእከላዊ ወህኒ ቤት ቆይታቸውን ወደ ኋላ እያጠነጠኑ ይተርኩታል… የእኔ ተራ ደርሶ ስለነበር በኪሴ የነበረውን 500 ብር እና ቀበቶ፣ በብሔራዊ ፖስታ ቤት ሪኮማንዴ ያስገባሁበትን ደረሰኝ፣ ሰዓቴንና መታወቂያ ካርድ ተረከቡኝ። እጅግ የደቀቀ ፍተሻ ተደረገልኝ። ይህን እንደጨረስኩ ወደ ጨለማ ቤት ቁጥር 10 አስገቡኝ። የበሩን መዝጊያ ብረት በቁልፍ ከፍቶ ሲበረግደው ጩኸቱ እጅግ ያስደነግጣል። ‹‹ግባ!›› ብሎ ወደውስጥ ገፈተረኝ። ቤቱ ጨለማ ስለሆነ ከውጭ የሚገባ ሰው ምንም ማየት አይችልም። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ከቤቱ በረንዳ ላይ የመንገድ መብራት ስለነበር በእሱ ውራውርት የተወሰነ ነገር ለማየት እድል አገኘሁ። በበሩ ጩኸት ከእንቅልፍ ባነው ከተጋደሙበት የተወሰኑት ቀና ቀና አሉ። ሸህ ሱልጣን ከእኔ ቀድመው በዚሁ ክፍል ገብተው ስለነበር ተነስተው አቅፈው ‹‹አሰላሙ አለይኩም በሰላም መጣህ! አይዞህ! ለማንኛውም ሲነጋ እናወራለን። እዚህ ተኛ›› ብለው ወደቦታቸው መለስ አሉ።

እኔ አገር አማን ብዬ ለመተኛት ጃኬቴን ሳወጣ ያዩኝ የነበሩት በግንቦት 7 ተጠርጠረው የታሰሩት መምሬ ደሳለኝ እንበአል በረጋ አነጋገራቸው ‹‹ወንድሜ አሁን መልሰው ስለሚጠሩህ ልብስህን አታውልቅ፤ አንተ ይህን ቤት የምታውቅ አይመስለኝም፤ ለማንኛውም እንዳትደናገጥ ጋደም በል›› አሉኝ። ይህንን ንግግር በጥርጣሬ ነበር የተቀበልኩት። ‹‹ኧረ ጉድ! መንግሥት እዚህም ሰላይ አስቀምጦ ቢሆን?›› የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ ውስጥ ተመላለሰ።

እንደተባለውም የፖሊስ ጫማ ኮቴ ወደ ክፍሌ አቅጣጫ ተሰማ፤ በግምት ከ10 ደቂቃ በኋላ ነበር። የብረት መሸንጎሪያውን እንደጉድ አስጩኾ ‹‹መከተ ሙሔ ውጣ!›› አለ። ነገሩ እውነት ነው እያልኩ ፈጠን ብዬ ወጣሁ። ከዚያ 32 ቁጥር የምርመራ ክፍል ቢሮ አስገባኝና መርማሪ ሲሳይ የተባለው ፖሊስ በህይወቴና በንብረቴ ዙሪያ ጥያቄዎችን ጠየቀኝ። ከዚያም ለሌሎች መርማሪዎች አስተላለፈኝ። እነ አቡበከር የት እንዳሉና የስልክ ቁጥራቸውን ጠየቀኝ። እንደማላውቅ ሳስረዳው አንደኛው በቦክስ ለመማታት ቃጣው። ‹‹አቁመው!›› አለ። የእኔ ዋና መርማሪ ሆኖ የተመደበው አንዳርጋቸው በተረጋጋ መልክ ምርመራውን ለማስኬድ ፈልጎ እኛን ለመወንጀል ወዳሰቡበት ድርሰታቸው ገባ። ‹‹በህቡእ መቼ ተደራጃችሁ? ህገ-መንግሥቱን ለምን ማፈረስ ፈለጋችሁ? እስላማዊ መንግሥት ለመመስረት ትፈልጋላችሁ! የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ እያለ ለምን በአ.አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራችሁ?›› ወዘተ በማለት እስከ 8 ሰዓት አቆይቶኝ እኔም ለእያንዳንዱ ጥያቄ ስለጉዳዩ የማላውቅና ያልፈጸምን መሆኑን ምላሴ እስከሚደርቅ ላብራራ ሞከርኩ። መርማሪዎቹም ዙሪያዩን ከበው አንዱ በሐይል ቃልና ዘለፋ፣ ሌላው በተለሳለሰ ዘዴ ምርመራ ሲያደርጉ ከቆየን በኋላ መጨረሻ ‹‹እንዲህ በቀላሉ የምንላቀቅ አይምሰልህ! ለማንኛውም ለዛሬ ይብቃ›› አስወጡኝ። በእጄ ላይ ያለው ካቴና ጠብቆብኝ ስለነበር እጄን እያሻሻሁ ወደ ጨለማ ቤት ቁጥር 10 ተመልሼ ገባሁ።

ለመተኛት ሞከርኩ። እንቅልፍ ከየት ይምጣ? የቀኑ ጾም፣ የቤት ብርበራ፣ የ32 ቁጥር የምርመራ ቆይታ፣ ያልተያዙት ጓደኞቼ ነገር፣ በአጠቃላይ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ላይ እየተከፈተ ያለው ጦርነት… ነገሮችን በማውጠንጠን አላህን በዱዓና በዚክር እየተማፀንኩ ከአንድ ሰኣት በላይ አለፈ። በክፍሉ ውስጥ ባለው ውሃ ዉዱ አድርጌ ሰላተል ለይል በመስገድ ላይ እያለሁ ሸህ ሱልጣን ተነሱ። እሳቸውም ዉዱ አደረጉ። ሶላት እየሰገድን ፈጅር ተቃረበ። ሱብሂን ሰላት በጀመዓ ሰገድን። በረጅም ቁኑት በምርመራ የደከመው ቀልባችን በረጅም ቁኑት ወደነበረበት ተመለሰ።

ከነጋ በኋላ 12 ሰዓት አካባቢ የእስረኖች ቁርስ ከመቅረቡ በፊት ለማደር በሩ ተከፍቶ ሽንት ቤት ተራ በተራ የ(8) ክፍል ታሳሪዎችን አስወጡን። ከዚያ ቁርስ ከበረንዳው ላይ ተራ በተራ ተሰልፎ መታደል ተጀመረ። እኔና ሸህ ሱልጣን ረመዳን ወር 2ኛ ቀን ምንም ሳንቀምስ ቀጥለናል። በነበረው ሁኔታ ራብና ጥም ብዙም አልተሰማንም።

ይሁን እንጂ ከአስር በኋላ የውሃ ጥም ፍላጎት ስሜት ጠንከር ብሎ ተሰምቶናል። እኛ ክፍል የነበሩት ታሳሪዎች የሚከተሉት ነበሩ፡- 1ኛ. መምሬ ደሳለኝ እምቢያለ – የግንቦት 7 ተጠርጣሪ 2ኛ. አቶ ኦፔኝ የጋምቤላ ተወላጅ – የጋምቤላ የደኅንነት ኃላፊ 3ኛ. የኦፔኝ ጓደኛ – የጋምቤላ ፖሊስ አባል 4ኛ. አቶ ወንድ አምላክ – በፒያሳው ባንክ ዝርፊያ ተጠርጥረው የታሰሩ (ዘበኛ) 5ኛ. አንድ ወጣት የጎንደር ልጅ – የግንቦት 7 ተመልማይ ተጠርጣሪ

ሁሉም ተራቸው ደርሶ አንዳንድ ዳቦና ሻይ በኩባያ ታደሉ

The post የሸሪዓ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጣር በማእከላዊ (1) appeared first on Zehabesha Amharic.

ነገ አርብ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ ከተሞች የመሰባሰብና የሰደቃ ፕሮግራም እንደሚኖር ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ

$
0
0

sedeka

ጁሙዓ በአንዋር መስጂድ እና በክልል ማእከላዊ መስጂዶች ተሰባስበን በመስገድ ለወኪሎቻችን አጋርነታችንን እንግለጽ!
የአንድ ብር ሰደቃ መርሃ ግብር ይኖረናል!

እስካሁን ለወኪሎቻችን ያለንን አጋርነት በተለያዩ መንገዶች ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ የረመዳን ጁሙዓዎች ደግሞ አጋርነታችንን ለመግለጽ ከምንጠቀማቸው አመቺ ገጠመኞች ይመደባሉ፡፡ በእስካሁኑ የትግል ቆይታችን አንድነታችንን አጠንክረን ችግሮቻችንን በጋራ እንደተጋፈጥን ሁሉ አሁንም በዚሁ አንድነታችን እንደምንቀጥል ማረጋገጥ አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ይህን በተግባር ላይ ለማዋል የፊታችን ጁሙዓ በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ እና በክልል ደግሞ በማእከላዊ በሆኑ መስጂዶች ላይ ተሰባስበን የመስገድ እና በቀኑም ለችግረኞች በነፍስ ወከፍ የአንድ ብር ሰደቃ የመስጠት መርሃ ግብር ይኖረናል፡፡ በመሆኑም መርሃ ግብሩን ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ሁላችንም እንረባረብ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን!

የጁሙዓ ቀጠሯችን በአንዋር እና በክልል ማእከላዊ መስጂዶች ነው! ኑ…. ለወኪሎቻችን አጋርነታችንን እንግለጽ!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post ነገ አርብ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ ከተሞች የመሰባሰብና የሰደቃ ፕሮግራም እንደሚኖር ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.


የዘመቻ ጥሪ! –ከአበበ ገላው

$
0
0

Obama Ethiopia

ሰሞኑን ፕሬዚደንት ኦባማ ኬንያን ለመጎብኘት ሲሄዱ እገረ መንገዳቸውን ለዜጎቿ እስር ቤት እና ሲኦል ወደ ሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ ጎራ እንደሚሉ በይፋ ተገልጿል። ምንም እንኳን የማንንም ጉብኝት ባንቃወምም የፕሬዚዳንቱ ጉዞ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ይህንን አቋማችንን በስፋት ለአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናት ማሳወቅ ይገባናል። ስለዚህም ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ ቆም ብለው እንዲያስቡበት ለማስገንዘብና ለወንጀለኛው የወያኔ መንግስት አሜሪካ የምታደርገውን ድጋፍ በመቃወም ዋይት ሃውስን መጠነ ሰፊ በሆነ የስልክ ጥሪ፣ የፋክስ እና የኢሜይል መልእክት ለማጨናነቅ ከሰኞ ጀምሮ ልዩ ዘመቻ እንጀምራለን። ይሄ ጉዞ ከተቻለ እንዲሰረዝ ካልተቻለ ግልጽ አቋማችን እና ተቃውሟችንን ማሳወቅ የኛ ሃላፊነት ነው። ነጻነት ናፋቂው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ድምጽ የማሰማት እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን የአደራ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ይሄንን ዘመቻ በተቀናጀ መልኩ ለማድረግ የምናስተላልፈው መልእክት እንዲሁም ዝርዝር መረጃ ሰኞ ይለቀቃል።

The post የዘመቻ ጥሪ! – ከአበበ ገላው appeared first on Zehabesha Amharic.

የበረሃው ጂኒ ፣ የባህሩ ጋኔል  –በልጅግ ዓሊ

$
0
0

 

ብቻውን ሆኖ ከጥግ ቆሞ ይቆዝማል። ጸጉሩን እየፈተለ ይናደዳል . . . ብቻውን ያልጎመጉማል። ትንሽ ቆይቶ ያለቅሳል። ለጉድ! ያነባዋል። ሰው እንዳለ እንደሌለ አካባቢውን ይቃኛል። ገና ወደዚህ አካባቢ እንደመጣ ሲብስበት በሰው ፊት ያለቅስ ነበር። አሁን አሁን ግን ሲያለቅስ ሰው ሲያየው አይወድም። መጀመሪያ አካባቢ ጎረቤቶቹ ሲያለቅስ ሲመለከቱ ያጽናኑት ነበር። በኋላ ግን ቀውሷል ብለው ደመደሙ። እንዲያው በደፈናው ግማሾቹ ፍቅር ይዞት ነው ሲሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ የሳሃራ በረሃ ጋኔል አግኝቶት ነው. . . ወይም የባሕር ጂኒ ተጠናውታው ይሆናል ማለት ጀመሩ። በየሄደበት ሁሉም እብድ ነው፣ ቀውሷል  ብለው ደምድመዋል። ስለሚናገረው ነገር ግን ማንም ልብ ብሎ ያስተዋለውም፣ የጠየቀውም የለም። እሱም መናገር አይወድም። በእርግጥም ስለሱ የሚያውቅ ማንም የለም።

 

ብቸኝነቱን ሲያስብ፣ የውስጥ ሃዘኑ የአዕምሮውን ጣሪያ ሲነካበት ከቤት ተነስቶ ውልቅ ይላል። ባቡር ይሳፈርና ወደ ፍራንክፈርት ይሄዳል።  መሄጃ እንደሌለው የሚያውቀው ግን ፍራንክፈርት ሲደርስ ነው። ለምን ከቤቱ እንደወጣ ግራ ይገባዋል። ባቡር ጣቢያ ከሚገኘው ማክዶናልድስ ይገባና ቁጭ ይላል። እዛም ሆኖ በሃሳብ እንደገና ይወረሳል። ወዲያው ደግሞ እንባው ድቅን ይላል። የጸጋዬ ገብረ መድህንን ወንድ ልጅ ተደብቆ ነው የሚለቅሰው የሚለውን ግጥም በቃሉ ይወጣዋል።

 

ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ፣

አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ፣

ተሸሽጎ ተገልሎ ተሸማቆ ተሸምቆ፣

ከቤተሰብ ተደብቆ፣

መሽቶ የማታ ማታ ነው፣ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው ።

 

እውነት ነው! ወንድ ልጅ  በቀን አያለቅስም ብሎ ራሱን ያሳምናል።

 

በእንባ የጠበቡ ዓይኖቹን እየደጋገመ ጠረግ ጠረግ ያደርጋቸዋል።  ጭንቅላቱ ግን በሃሳብ እንደተወጠረ ነው። እዬ! ዬ! ብሎ . . . አልቅሶ ቢወጣለት ምንኛ በወደደ ነበር።  አካባቢውን ዞር ዞር ብሎ ይቃኛል። የሚያውቀው ሰው የለም። ማልቀስ እችላለሁ። ማን እንዳይታዘበኝ? ከማን ነው የምደበቀው? እዚህ አበሻ የለም . . .ቀውስ የሚለኝ የለም . . . እያለ ራሱን በራሱ በሚጽናኑ ቃላት ማባበል ይጀምራል። ብቻው ሲያለቅስ አበሾች አይተው ቀውሷል እንዳይሉት መፍራቱን ግን አልተወም።

 

ቁጭ ባለበት  በሃሳብ ይነጉዳል። እንቅልፍ እንደያዘው ሰው በመሃል እንደገና ከሃሳቡ ይባንናል። በቀስታ ድምጽ ማዕበል፣ ማዕበል ፣ ማዕበል ይላል። አጠገቡ ያሉት ሰዎች ቋንቁው ባይገባቸውም በትዝብት ይመለከቱታል፤ በመቀጠልም ጮክ ብሎ እጄን ያዢኝ ፣ እጄን ያዢኝ ፣ እጄን ያዢኝ እያለ ይጮኻል። ሁሉም ሰው ወደ እሱ ይመለከታል፣ እሱ ግን ሰው እንደሚመለከተው ከቶ አያስተውልም። ለምን ለቀቅሽኝ ፣ ለምን?. . . ለምን ለቀቅሽኝ ብሎ ይጮኻል። ከዚያም ወዲያው ፈቱን የእንባ ዘለላ ያርሰዋል። ያለቅሳል ፣ ይንሰቀሰቃል. . . በጉንጩ ላይ ከሚፈሰው ይልቅ ደረቱን ሰንጥቆ ወደ ውስጥ የሚገባው እንባ ይብሳል ።

 

ጥቂት ቆይቶ ራሱን የጸጋዬን ግጥም ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል። እሱም አልመች ሲለው ግጥሙን እያሰላሰለ ማን ነው . . . ወንድ ልጅ ተደብቆ ነው የሚያለቅሰው፣ የሚንሰቀሰቀው ያለው? . . . ስህተት ነው ፀጋዬ! ወንድ ልጅ የሚያነባው አደባባይ ላይ ነው እንጂ! . . . ፀጋዬ ተሳስተሃል! ግጥምህን አርመው! ባንተ ዘመን ይሆናል በምሽት ተደብቆ የሚያለቅስው፣ በእኛ ዘመን ግን ተቀይሯል። በእኛ ዘመን ወንድ ልጅ ሲደላው ብቻ ነው ተደብቆ በምሽት የሚያነባው፣ እንደዚህ ቀይረነዋል፣ አንተም ቀይረዋ!

 

ጣሩ ሲበዛበት ግፍ መከራው፣

በቀን በጠራራ ፀሐይ አደባባይ ሕዝብ ፊት ነው፣

ወንድ ልጅ የሚያለቅሰው፣ የሚንሰቀሰቀው።

 

ማንነቱ የተደፈረበት፣

እሱነቱን ያጣበት፣

ብሶቱን የሚገልጽበት፣

ቁጭቱን የሚያሳይበት፣

ብቸኝነቱን የሚወጣበት። 

 

ቀን ነው የሚያነባው፣

ሰው ፊት ነው የሚያለቅሰው፣

አደባባይ ነው ስቅስቅ የሚለው፣

 

ሕዝበ አዳም፣ የሃበሻ ዘር ብሶቱን እንዲያይለት ፣       

አይቶም እንዲያላግጥበት . . . ።  

 

ፀጋዬ ግጥምህን ቀይረው። . . . ይላል።

 

ወዲያው ቀና ብሎ ላፍታ ሰውን ሁሉ ከገላመጠ በኋላ፣ የአዳም ልጅ ሁላ አላግጥ . . . እኔን እያየህ ተዝናና ብሎ ከማክዶናልድ ይወጣል።  ነገር ግን፣ ውጭ ወጥቶ የሚሄድበትን አያውቀውም። መሃል መንገድ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቆሞ፣ እንደገና ለራሱ ብቻ በሚገባው ቋንቋ  ማልጎምጎም ይቀጥላል፡፡

 

ከዚያም ፈጠን ፈጠን እያለ በርካታ እርምጃዎች ይራመዳል ። ወዲያውም ዘው ብሎ አንዱ አበሻ ቡና ቤት ይገባል። እዚያም ላፍታ አይቆይም። ይወጣል። እንደገና ሌላው ጋ ይገባል። ከዚያም ይወጣል። ከረንቦላ መጫወቻ ቤት ይሄዳል። . . . እዚያም እንደደረሰ፣ ተጫዋቾቹንና የከረንቡላ መጫወቻወን ጠረንጴዛና ኳሶች ትኩር ብሎ ቆሞ ያስተውላል።

 

ይኽ ትዕይንት ለሱ የዕለት ተዕለት ኑሮው ነው።

 

ከእነዚህ ቀናት በአንዱ ግን፣ እንዲህ ሆነ። …. በዚው በለመደው ቤት የከንቡላ ጨዋታ እያስዋለ ሳለ፣ ድንገት ሳይታሰብ . . . “ማዕበል ! ማዕበል ! እጄን አትልቀቂ ! . . . ጀልባውን ይዤዋለሁ እጄን አትልቀቂ ! ሲል አንቧረቀ። በአንድ እጁ ጀልባውን፣ በሌላኛው እሷን እንደሚጎትት ያህል ሰውነቱ ተወጣጠረ። ጮኸ ! ተጣራ ! ከረንቦላ ቤቱ ላፍታም ቢሆን በጸጥታ ተሞላ። ሁላችንም በአንክሮ  ወደ እሱ ተመለከትን።  በአዕምሮው አንድ ነገር እንዳስታወሰ ዓይኖቹ ፈጠጡ። እንባው በፊቱ ላይ ቦይ ቀዶ ቁልቁል መንዠቅዠቅ ጀመረ። . . .  በከረንቦላው ጠረቤዛ ላይ ያሉትን ድንጋዮች በታተናቸው። ጨዋታውን ተረበሸ። ተጫዋቾቹ ጮኹበት። “ይህንን ቀውስ አስወጡት” ብሎ አንዱ ጮኸ ። ባለቤቶቹ “ውጣ! እንግዳ አትረብሽ” ብለው ገፍትረው አስወጡት።

 

የእሱን እግር ተከትሎ፣ በከረንቦላ ቤቱ ውስጥ የጦፈ ክርክር ተነሳ። “ይህንን ሰውዬ መምህር ግርማ ቢያገኙት ያድኑታል” አለ አንዱ። “እባክህ ተወን! በዓለም የታወቀው የጀርመን ሃኪም ያላዳነውን እንዴት ነው መምህር ግርማ የሚያድኑት?” አለ ሌላኛው።  ክርክሩ ከእሱ አለፈና ወደ መምህር ግርማ ሥራና ተዓምር ተቀየረ። አንዱ የእሳቸው አድናቂ ሌላው ደግሞ ጽኑ ተቃዋሚ ሆነው ይከራከሩ ጀመር።

 

እኔንም በውል የማላውቀው ስሜት ገፍትሮ ከውስጥ አስወጣኝ። ተከተልኩት። እንደተለመደው ለማጽናናት ሞከርኩ። “ፀሐፊ ነኝ ትል የለም እንዴ?” ሳላስበው ጠየቀኝ። መልሱን ሳይጠብቅ ቀጠለ። “እስቲ ጻፈውና እንይህ?  እስቲ ንገርልን ምን እንደደረሰብን ? አቦ  ጀግና ሁና ! እውነቱን ጻፈዋ ?  ቀውሷል እያሉ ከየአበሻው ቡና ቤት ከሚያባርሩኝ የደረሰብኝን ንገራቸው። ሳሃራን አየሁት. . . ባህሩን አየሁት ብለኸኝ የለም እንዴ ? ጻፈዋ እናንብበው ? ወይስ ሰሃራ ድረስ የሄድከው የአሸዋውን ማማር፣ የቴምሩን ጣእም፣ የፀሃዩን ግለት፣ የሙቀቱን ትእይንት  ለማያውቁት ልታሳውቅ ነበር? ወይንስ ዕረፍት አምሮህ ነው ? …. ጉድ እኮ ነው! የኛ ስቃይ ለእናንተ መዝናኛ መሆኑ አይገርምህም ! ” በማለት ሳላስበው በጥያቄ ላይ ጥያቄ እአደራረበ ጠየቀኝ።

 

“ለመሆኑ ኩፍራን ታውቀዋለህ ? ከሱዳን ተነስተን እስከ ሊቢያ ኩፍራ ድረስ ምን ያህል የሰው ልጅ ስቃይና መከራ እንዳለ ታውቃለህ ? ሳሃራን አቋርጠህ ሰዎች የሚኖሩበት ቦታ ስትደርስ የሚሰማህን ታውቃለህ ? አንተ አታውቅም ! መች ይህን ጉድ ቀመስክና ! አንተ ኤር ኮንድሽን ባለው መኪና ውስጥ ተቀምጠህ አይደል እንዴ ሳሃራን የጎበኘኸው ? እሱንም እንኳ ቢሆን ጻፍና አስረዳቸው. . . መቀወስ ይነሰኝ እንዴ ? ቀውስ ነው እያሉ የሚያሽሟጥጡኝን በውል አስረዳቸው እንጂ ? ዳሩ አንተ ብትጽፈው መች አንብበውት፤ ለእሱ መች ጊዜ አላቸውና፤ አንዳንዶቹም ማንበብ አይችሉም። መታወቂያቸው ላይ ያለውን ስማቸውን እንኳ በውል አያውቁትም እኮ ! . . . እኔ  ግን ቀውስ አይደለሁም። እነርሱ ናቸው አውቆ አበዶች። ሙሉ ቀን ድንጋይ ሲያፋትጉ የሚውሉ፣ ቤት ሞልተው በባዶ ሁካታ ሲንጫጩ የሚውሉ፣ ጫት እንደ ከብት እያመነዥኩ በቅዠት ምናብ የሚደሰኩሩ፣ በቁማር ፍቅር ሲነዱ ለሚያድሩ፣ የቡና ቅራሪ ሲጋቱ የሚውሉ፣ እነርሱ ናቸው እንጅ ቀውሶች። …. ህ’ ህ ! ….  የህሊና ሚዛናቸው የተዛባ፣ አዙሮ የሚያይ አንገት የሌላቸው፣ የመጡበትን የረሱ፣ የሚሄዱበት ካርታ የጠፋባቸው።” መድረሻቸው ከከንቱ የሆነ ።  “ሰው መሳይ በሸንጎ ማለት እነሱ ናቸው።”

 

“ደግሞ ንገራቸው. . . በሳር ውስጥ ተሸሸጎ፣ ታፍኖ፣ ከኩርፋ ትራቫሎስ ድረስ ያለውን መከራ።  ስለ ባሕሩም፣ ስለ ጀልባውም ንገራቸው ለእነዚህ አረመኔዎች። እኔን ቀውሷል እያሉ ከየቡና ቤቱ የሚያባርሩኝን ። ቀውስ ነው በላቸው። በፍቅር ነው ያበደው ይሉ የለም? አዎ በፍቅር ነው የቀወሰው በላቸው። ስለ ፍቅር ምን ያውቃሉ? በሃሳብ የሚገለሙቱ፣ በሥራ ቦዝነው ከረንቦላ የሚጫወቱ፣ ጫት እያመነዠኩ በከንቱ ፍልስፍና ለሚሟገቱ፣ የመንፈስ ድኩማኖች፣ ሲመሽ አንቡላ እየጋፉ በየጎዳናው ለሚጣለዙ ግብዞች፣ አስረግጠህ ንገራቸው። እኔ ሰው ወድጄ ስለሰው ነው ያበድኩት . . . እነርሱ ግን የራሳቸውን ጠልተው ሰለ ሆዳቸው አብደዋል። አዎ አሁን በእኔና በእነሱ መካከል ልዩነት አለ። ይኸውም እኔ ሰው ወድጄ ስለፍቅር እራሴን ሰጥቻለሁ፣ እነሱ ደግሞ ሞራል አጥተው ለሱስ ስብዕናቸውን ጥለዋል።”

 

“አይገርምም! ለሴት ፍቅር እንዴት ታለቅሳለህ ብሎ ጠየቀኝ እኮ አንዱ። እንዴት አላለቅስም? አለቅሳለሁ እንጂ! ሱዳን ነበር የተዋወቅነው። እዚያ ነው ያፈቀራት በላቸው።”

 

ሻይ የምትሸጥበት ቦታ ነው የተዋወቅነው። ገንዘብ አልነበረኝም። ርቦኝ ነበር ። ምንም ሳልፈራ መራቤን ነገርኳት። ዳቦና ሻይ ሰጠችኝ። እንደ እናቴም እንደ እህቴም ታየችኝ። ደግነትዋ እንድቀርባት አደረገኝ። በልቼ ስጨርስ ሲርብህ ሁል ጊዜ ና አለችኝ። እኔም ከእሷ አካባቢ መጥፋትን አልደፈርኩም። ስቀርባት ወደድኳት ። ስቀርባት ወደደችኝ ። ተዋደድን። እኔ ገንዘብ አልነበረኝም። ከውጭ ይልኩልኛል ብዬ የተማመንኳቸው ወንድሞቼና እህቶቼን በቃላቸው አላገኘኋቸውም። ታሪኬን ነገርኳት። አዘነችልኝና እኔ አለሁልህ አለችኝ። ገንዘብ ሠርተን አውሮፓ እንደርሳለን አይዞህ አለችኝ። ከወንድሞቼና ከእህቶቼ ያጣሁትን የሰው እምነት እንደገና የሰጠችኝን ካላፈቀርኩ ማንን ላፍቅር?”

 

“ንገራቸው ለእነዚህ ብኩኖች! ሻይ ሽጣ ነበር ወደ ሊቢያ የምንሄድበትን የከፈለችው። ያንን ሁሉ መከራ አልፈን አብረን ነበር ሊቢያ የደረስነው። ካንተ አልለይም ብላ አብራኝ የተሰቃየችው። ሳጣ ያጣችው፣ ሳገኝ የተደሰተችው፣ የፍቅር ማጀቴ ነበረች እኮ ። አንድ ለእኔ የተፈጠረች፣ ውብ ቆንጆ፣ ደግ ለሰው አዛኝ፣ ጠይቅ ድፍን ሱዳንን፣ ጠይቅ ድፍን ሊብያን፣ ማን እንደነበረች ይነግሩሃል። . . .  እርጉዝ እኮ ነበረች፣ የመጀመሪያው ልጄ እናት፣ አውሮፓ እናሳድጋለን ስንል ነው እኮ ጥላኝ የሄደችው፣ እንዴት አላብድ?  እንዴት አልቀውስ፣ እንዴት አላለቅስ፣ ለእሷ ያልታበደ ለሌላ ለማን ይታበድ?”

 

“እነዚህ  ስለ ፍቅር ምን ያውቃሉ? እነዚህ ከልጃቸው አፍ ቀምተው ለቁማር የሚገብሩ እብዶች እኔን እንዴት ቀውስ ይሉኛል? እነሱ አሉ አይደሉም እንዴ ጨርቃቸውን ያልጣሉ በቁም ሙቶች።  ይህንን ቀውስ አስወጡት ሲሉ በጫት አፋቸው ሲለፈልፉ አያፍሩም እኮ።”

 

ነገሩን ለማወቅ ቸኩዬ “. . .ታዲያ ለምን ተጣላችሁ? የትነች ያለችው? እናስታርቃችሁ እንጂ. . .?” ብዬ ጠየቅኩት። ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ አይቶኝ ። ቀጠለ።

 

“እኔ ጠቤ እንደነሱ ከሰው አይደለም። እኔ ጠቤ ከተፈጥሮ ነው። ከበረሃው ነው በልልኝ፣ ከማዕበሉ ጋር ነው በልልኝ። ያንን የሳሃራን በረሃ አቋርጠን ሊቢያ ስንደርስ ደስታችን ብዙ ነበር ። መለያያችን መድረሱን መች አስብንና። ሁለት ወር ሊቢያ ውስጥ ተደብቀን ኖርን። በተለይ እሷ ራሱዋን ደባብቃ አስቀያሚ ለመምሰል ትጥር ነበር። የእሷን ቁንጅና ያዩ ሊቢያኖች እሷንም እንደማይለቋት እኔንም እንደማይለቁኝ አውቀን ነበር። ለነገሩ ሁላችንም ተደብቀን አልነበረም የምንኖረው? እዛ ነበር እርጉዝ መሆኗን የነገረችኝ ። የመደንገጥም፣ የመደሰትም፣ የማዘንም ስሜት ተሰማኝ። እንደ ምንም ገንዘቡ ተከፍሎ፣ ጀልባው ተዘጋጀና ጉዞ ጀመርን። የሊቢያን የባሀር ክልል ስንወጣ ጀልባው ላይ ችግር እንዳለ ተረዳን። ከአንድ ወገን ያሉ ሰዎች በተፈጠረው ግርግር ወደ እኛ አካባቢ መጡ ። ጀልበዋ ተገለበጠች። ብዙዎቹ ሰመጡ። እኔ እጇን እንደያዝኳት እሷም እጄን እንደያዘችኝ ነበር ጀልባው መስጠም የጀመረው። በአንድ እጄ እሷን በሌላው ጀልባውን እንደያዝኩ፣ እሷ ደግሞ በአንድ እጇ እኔን በአንድ እጇ ባዶውን ጀርካን እንደያዘች ነበር። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሳይታሰብ ማዕበል ተነሳ። ይህንን ጊዜ ስትጸልይ ነበር። ፈጣሪ ላልተወለደው ልጃችን ብለህ ማረን፣ ማዕበሉን አቁምልን እያለች ነበር የምትጸልየው፣ ማርያምን ነበር የምትማጸነው።”

 

“በአንድ እጄ እሷን በአንድ እጄ ጀልባውን  ይዤ ነበር ማዕበሉን ለመቋቋም የታገልኩት። በከፍታ የተነሳው ማዕበል ውሃውን ፊታችን ላይ ስለረጨን አፈነን። እጄን ለቀቀችው። ለመያዝ ሞከርኩ አልቻልኩም። እሷም ታገለች። ስሜን እየጠራች ጮኸች።  ከአጠገቤ ድምጿ ራቀኝ። ድምጿ በአራቱም ማዕዘን ይሰማኝ ጀመር። ወዴት ልሂድ? ዋና አልችል። እዚህ ነኝ ብዬ መለስኩ። አበድኩ፣ በዚያ ጨለማ ምን ላድርግ፣ አበድኩ፣ ጮኩ፣ ምን ልሁን? ሌሊቱን ሁሉ ተጣራሁ፣ ድምጿ እየራቀ መጣ። እንዲሁ እንዳበድኩ ምሽቱ እየነጋ መጣ። ጠዋት ላይ የለችም፣ ትልቅ መርከብ መጥቶ እኛን አዳነን፣ ጀሪካኑን በሩቅ አየሁት። ፈለኳት ነገር ግን ላገኛት አልቻልኩም፣ የለችም። ከዚያ ቀን ጀምሮ መንፈሴ ታወከ፣ ህሊናየ ተነካ፣ ሰላሜና ፍቅሬ አብሮ በማእበል ዳግም ላይመለስ ተወሰደ፣ እኔም የሰውና የመንፈስ ደሃ ሆንኩ። አበድኩ፣ ቀወሰኩ። ንገራቸው ለምን እንደቀወስኩ። መቼም አይሰሙህም። ቁማር ተበልቶ አበደ ብትላቸው ነበር የሚሰሙህ!”

 

“ለእነዚህ ሃይማኖት ለሌላቸው ግብዞች። ለእሷ ያላበድኩ ለማን ልበድ?. . . ለማን ልቀውስ? እንደነርሱ ለቁማር፣ ለጫት፣ ለዝሙት . . . ?  ጂኒ ባሕር ላይ መታው አይደል የሚሉህ? አዎ! የባህር ነውጥ ጭካኔና የሰው ፍቅር ማዕበል፣ የሳህራ በረሃ አባዜና የሰው ልጅ ውዴታውና ውለታው ነው እሱን ያቀወሰው በላቸው። እንደ እናንተ በየመሸታ ቤቱ ከበርቻቻና ጫት ቁማርና አደንዛዥ ዕጽ አይደለም እኔን ያሳበደኝ ብሏል በላቸው። መቼም ስለደነዘዙ አይሰሙህም እንጅ፣ ንገራቸው። ሰው ለሰው እንደ ተፈጠረና እንደሚኖር ሁሉ፣ ሰው ለሰው እንደሚሞትም ይወቁ።”

 

ካለኝ በሁዋላ፣ ጥሎኝ እያለቀሰ ሄደ። እያነባ፣ እየጮኸ፣ እያጉተመተመ፣ ሄደ . . .  የባህሩ ጂኒ፣ የባሕሩ ጋኔል ነው ፍቅሬን የወሰዳት እያለ ሄደ። ቀን ከሌሊት አነባለሁ፣ አለቀስሳለሁ፣ ለእንባና ለሃዘን ቀጠሮ የለውም ጸጋዬ አንተም አልተረዳኸውም እያለ ፈጠን ፈጠን እያለ ሄደ።

 

መከራ ሲመጣ አይነግርም አዋጅ ፡

ሲገሰግስ አድሮ ሌት ይደርሳል እንጅ 

 

እንዲሉ፣ ጸጋዬ ተሳስተሃል፣ እኔ ዛሬም ነገም አነባለሁ፣ ዓይኔ እስከሚከዳኝ አነባለሁ።  የሰው ልጅ አሳር ፍፃሜ እስከሚያገኝ፣ ፍቅር፣ ደግነት ልግስናና ርህራሄ ሚዛን እስከሚደፋ፣  ፣ የሰውልጅ ሃብቱ ሰው መሆኑ እስኪታወቅ ድረስ ዛሬም ነገም አነሆ አለቅሳለሁ.፣ማዕበሉ ፀጥ እስከሚል አነባለሁ . . እያለ እያጉተመተመ፣ ከዓይኔ ራቀ።

 

ተፈጸመ

 

(ግንቦት፡ 2015 ዓ.ም)

Beljig.ali@gmail.com

  • በፍራንክፈርት ከተማ የሊቢያንና የደቡብ አፍሪካን ሰማዕታት ለማስታወስ በተዘጋጀው የሐገር ፍቅር ሥነ ጥበብ ዝግጅት ላይ የቀረበ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልብ ወለድ።

comment pic

 

The post የበረሃው ጂኒ ፣ የባህሩ ጋኔል  – በልጅግ ዓሊ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኦባማን የኢትዮጵያ መንገዳቸው ቱሪናፋ አያደ ርጋቸውም ? –ከቢላል አበጋዝ

$
0
0

ጁን 25 ቀን 2015

ዋሽንተን ዲ ሲ ፡

ቱሪናፋ የሚለውን ቃል ሐበሻ የተባለው መዝገበ ቃላት: ወሬኛ።ጉረኛ።ወሬ የሚያበዛ ይለዋል።ይህ ጽሁፍ ለዘለፋ ሳይሆን በፕሬዚዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ለመወያየት ነው።እኒህን ነጥቦች እዩልኝ።

Obama Ethiopiaኦባማ ለምርጫ ሲቀርቡ “ይቻላል ፡አዎን ይቻላል” ብለው እኛንም አስብለውን ነበር።ለአሃጉራችንም በጎ ያደርጋሉ ብለንም ተመኝተን ነበርን።መመረጣቸውንም ኮርተንበትም ነበር።የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው የአገዛዝ ዘመናቸውን ጥላሸት የሚቀባው ነው።ይህ ደግሞ ለሳቸው ክፉ ነው። ወደ ስልጣን ሲመጡ የአፍጋኒስታንና የኢራቅን የውጭ ጉዳይ ችግሮችን ተረክበዋል።በስልጣን እያሉ ሶሪያ እና የመን ተጨምረዋል። እድላቸው ሆኖ የቋጠሩት ሁሉ የሚፈታባቸው ናቸው። ተቀናቃኞቻቸው ውሳኔ ላይ ቆራጥነት የለህም ይሏቸዋል።ስተተኛና ዳተኛ ያደርጓቸዋል። ይህ ጽሁፍም አፍቅሮ ህወሃት ተግባርዎ ስተት ነው ለማለት ነው። ከኢትዮጵያውያን በተረፈም ዓለም እየታዘበዎት ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ እምነቱ በኢትዮጵያ አምላክ ላይ ሲሆን የህወሃት እምነት በስዎ ላይ ነው። ለኢትዮጵያ ሁሌም መጨረሻው ላይ ይፈርድላታል።ህወሃት እንደ ጃፓን ሲኒ መሰባበሩ ግድግዳ ላይ ተጽፏል።

የኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ለማንም ግድ አይሰጥም። ስለ  ኢትዮጵያ ካሰብን እውነቱ ይህ ነው። የእስልምና ሃይማኖት ኢትዮጵያን አትንኩ ሲል መጽሃፍ ቅዱስ እጆችዋን ወደፈጣሪዋ ትዘረጋለች ይላል።ዛሬ ደግሞ ደካማ በጸሎቱ፡ብርቱው በጉልበቱ፡ በንብረቱ እግዜርን አለኝታ አድርጎ ኢትዮጵያን ከህወሃት መንጋጋ ሊያወጣት የቆረጠበት ስለሆነ “ኦባማ አላወቁበትም” ከማለት ሌላ፡ አምባገነኖች ጋር ጓይላ ቢጨፍሩ “እንታይ ገድሸኒ” እንላቸዋለን።

ካስተዋልነው ዛሬ የአፍሪካ አሀጉር  ከነዚያ የመንግስት ግልበጣ የዞትር ወግ ከነበረባቸው ዘመናት አልፎ ይገኛል።ስለዴሞክራሲ መስፋፋት የሚጽፉት አውራ ምሁራን  ፍራንሲስ ፉኪያማ እና አማርትየ ሳን እንደሚሉት  ጭቆና እየተገረሰሰ ነጻነት እያበበ ነው ባጠቃላዩ ሲታይ።በአሃጉራችን ናይጄሪያ፡ ጋና፡ ላይቤሪያ፡ ደቡብ አፍሪካ ፡ቦስዋና  ለምሳሌ ያህል ይጠቀሳሉ። የዚህ ሂደት ተቃራኒው ክሚታይባቸው አገራት አንድዋ ኢትዮጵያ ናት።

ኢትዮጵያ ከህዝብዋ ብዛት መልክአ ምድርን ይዞ የዓለም ፖለቲካ ሽኩቻ ላይ ያለችበቱ አቀማመጥዋ ዋና ቦታ እዲኖራት የግድ ነው።የምንወዳት ስለሆነ ልንክባት ሳይሆን እውነታው ይህ ነው።ሀያላን ከደጇ እማይጠፉትም ለዚሁ ነው።ሁሉም ለጥቅሙ።ታዲያ ሁለት አሳዛኝ ጉዳዮች አሉ።አንደኛውና ዋነኛው የገዛ ጥቅሟን የሚጻረር ፍጹም አምባገነን መንግስት ተንሰራፍቶባት ይሄው ዘመናት ፈጅቷል።ሁለተኛው ያለውን አደገኛ መንግስት በግዜ እንዳይተካው የተቃዋሚው ሀይል በህብረት ሆኖ ዛሬ አለመጎልበቱ ነው።ትልቅ መሻሻል እያየን መሆኑ የማይካድ ቢሆንም።

ይችን ዴሞክራሲና ፍትህ ቧልት የሆኑባትን ኢትዮጵያ  ፕሬዝዳንት ኦባማ ለምን ለጉብኝት መረጥዋት ? በመጀመሪያ የአስተዳደር ዘመናቸው “አምባገነኖች ወዮላችሁ !”ሲሉ ቆይተው የአምባ ገነኖች የንብ ቀፎን ያስመረጣቸውን ምክኛት መመርመር ድንቅ ነው።ዛሬ ኢትዮጵያ ትልቅ እስር ቤት ናት።የታሰረ ልጠይቅ ብለው ይሆን ? ዘር ማጥፋት የተካሄደባቸውን ስፍራዎች በዓይናቸው በብረቱ ለማየት? ሻል ያሉ ምክንያቶች እናስብ እንጂ! ጎበዝ! የአባታቸውን አገር የደፈረውን አል ሸባብን ከምድር ገጽ ለማጥፋት ?እግረ መንገዳቸው ደቡብ አፍሪካ ከመያዝ ያመለጠውን የሱዳኑን አል በሺር ጎራ ብለው ጋማውን ይዘው ዋንታናሞ ኩባ ሊሰዱት? ይህስ እንዴት ይረሳል። የአፍሪካ አምባ ገነኖችን አንድ ጋ አዲሳባ ሲማግጡ ሲያገኟቸው አንዱን በካልቾ! ሌላውን በኩርኩም! የቀረውን በቴስታ።ጉድ ሊያፈሉ ነው ለምርጫ ጊዜ እንደፎከሩት። ላቶ መለስ ለቅሶ ሊደርሱ? ይበቃል:: እኒህ የአስቂኙ ጓደኛዬ ወጎች ናቸው። አንድ ነገር እውነት ነው።ዋይት ሀውስ ከኦባማ ቤት በር ፊት ለፊት “ሚስተር ኦባማ! እረ ሚስተር ኦባማ ! አይሰሙም እንዴ ?”  እያለን እንጮህ ለነበርነው ልጅነታችንን አስጨርሰውናል።በፖለቲካ ትግል ይህ አቢይ ጉዳይ ነው።ካባቶቻችን አልማር ያልነውን እንድንማር አድርገዋል።ትግሉ ባገር ቤት ባሉ ኢትዮጵያውያንና፡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንድ ወገን ወያኔ በተቃራኒ መካከል ነው። ኦባማ ላሻቸው ወገን ቲፎዞ ይሁኑ።ባሻቸው በመሰላቸው ጊዜ። የመን የሆነው ይህ ነው። አሊ አብደላ ሳሊህ የኪሳቸው መሀረብ ነበር። የዛሬውን ሳይሆን።እኛ ኢትዮጵውያን  ከሚገድለን የበለጠ የናቀን ላይ ቂም እንይዛለን። አንረሳም።ዴሞክራሲ ሲሉ ወያኔ ያረገው ምርጫ ይበቃችኋል ነው። በዚህ እንተወውና ሌሎች ምክንያቶችን እናቋጥር።እኛ ምን ቸገረን ሲሻቸው ሰሜን ኮሪያም ሄደው ከዚያ ድንቡሼ የአገሩ መሪ ጋር ቅርጫት ኳስ ይጫወቱ።ያችን አፈነዳታለሁ የሚላትን ነገርም ቢቀሙት ለዚያ አካባቢ ሰላም ነው።ከዚህ የተረፈውን ያገራችን ሙያተኛ ቀልደኞች ይቀጥሉበት።ዋና ጭብጥ ነገሮችን ከፌዙ በተረፈ ከዚህ በታች እንወያይ:: አካባቢያችንን በተመለከተ።

ከአመታት በፊት አሜሪካ በሶማሊያ የማይታረም ስተት ሰርታለች።እንዲያው ከኢራቅም ከሌሎቹም የቀበሌው ችግሮች በፊት የሶማሊያ ይቀድማል።ከዚያ ወዲያ ዘሎ መግባት በኢራቅ።ዘሎ መግባት በየመን።ጎረቤት ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ ነው።በዚህ በኩል ሲያስቡት ይዘገንናል::ህወሃት ልትጨምረን የምትፈልገው ገደል የመንን ይመስላል። ቶሎ ህብረት ፈጥረን ጊዜ ሳንወስድ ወያኔን እናስወግድ የሚለው ዓላማ በተጨባጭ ከዚህ ምክንያት ይነሳል። አገር የማዳን ትግል ሲባል ይሄው ነው።ኢትዮጵያ ሌላዋ ስተት አንዳትሆን::

የሶማሊያን ችግር ለመፍታት አማሪካ ዘወር ማለት አለባት።ሌሎች አውሮፓ፡ቻይና ሩሲያ ህንድ እኒህ ብልሃትና ዘዴው ተቀባይነትም ስለሚኖራቸው የተሻሉ ሽማግሌዎች ይሆናሉ።አልሸባብን ከአልቃይዳ ጉያ ሊያወያወጡ የተሻለ እድል አላቸው። የተቀረው አረብ ገንዘብ ያልቸገረው ቲርኪሚርኪ ነው።ምንአልባት ትናንሾቹ የአረብ ኤሚሪቶች ቦታ ይኖራቸዋል።ከዚህ የሰላም ሙከራ ውጭ ወያኔን ወታደራዊ ሀይል አቅራቢ አድርጎ፤ሰው አልባ አውሮፕላን ይዞ ለመዝመት ከሆነ የፈሪ በትር ይሆናል።የኢትዮጵያ ሰራዊትም ከድንበሩ ተሻግሮ በከንቱ አይሞትም።ስለዚህ ህወሃትም መለስ ዜናዊ አንዴ በልቶበት የነበረውን ዘዴ መቀየር ይገባት ነበር።መለስ ትቶት የሄደው ግምብ ራስ ሁሉ ተመልሶ ከዚያው! አዲስ ብልሃት ከየት ይምጣ ? ከሶማሊያም ሌላ የመን ሄዶ የአገራችን ሰው ለምን ይማገድ?ያውም ድንበር በማያስከብር ከሃዲ ቡድን እየተመራ።ማሃይም የህወሃት ጄኔራሎች ቀድመው ይግቡበት።ገንዘቡ ወደነሱ ኪስ ሞቱ ለተራው ወታደር መሆኑ ፍትሃዊ አይሆንም።

የየመንም ጉዳይ ውሉ ከተፈታ ቆየ። አሁን ተተብትቧል።የአየር ድብደባ አይፈታውም።የአየር ድብደባ ቀድሞ ቬትናም በኋለ አፍጋኒስታን አልፈየደም።በዚህም ግጭት የአውሮፓ፡ቻይና ሩሲያና የህንድ ሚና ካአሜሪካ ይሻላል።ላሁን ፍጥጫው የጥይት ድምጹ ሞቱ ስደቱ መቆሚያው አይታይም።

ቻይና የዛሬ አርባ አምስት ዓመታት፡ እኤአ 1970 መጀመሪያ ታንዛም የባቡር መስመርን በምስራቅ አፍሪካ ዘርግታለች።ይህ የባቡር መስመር ታዛንያን እና ዛምቢያን የሚያገናኝ  1710 ኪሎ ሜትር የሚደርስ በስድስት ዓመት ያለቀ ነው። ይህን ተግባር የምናነሳው የቻይናን አፍሪካን በጇ ማድረግ ስራ ቀደም ያለ እቅድ ያለው እንዳአማሪካ አንዴዚህ  አንዴዛ እንዳልሆነ ለማሳየት ነው።ዛሬ ቻይና በአፍሪካ ተንሰራፍታለች።ለአምባ ገነኖች የጡት እናት እየሆነችም ቢሆን። ስለዚህ ኦባማ የአፍሪካን ወዳኝነት ለማግኘት ከሆነ ዉሻ ከሄድ ጅብ ጮኸ ነው።አምባ ገነኖቹንም ብዙ ገንዘብ ስላስለመደቻቸው ክፍያው ይበዛባቸዋል።ቻይናን ካፍሪካ ዘወር በይ የሚል የማን ወንድ፡ ነው?

ታዴያ የዲሞክራሲያዊ እና የሰብአዊ መብት ረገጣው ላይ ከመሳለቅ በተቀረ ከላይ ባነሳናቸው ጭብጦች ተነስተን የኦባማ ጉዞ ምን ይፈይዳል?ኬንያ ዘመድ ጥየቃ ቢያደርጉ መልካም ነው።ናይሮቢ ኤሌትሪክ አለ ስልክ ይሰራል ውሃ አለ። በጠቅላላው ካአዲሳባ ይልቅ ይመቻቸዋል። እዚያ ብቻ ቢሄዱ መልካም ነበር። ቱሪናፋን በስዋሂሊ ብችለው ደስ ይለኝ ነበር።

 

ኢትዮጵያን አምላክዋ ይጠብቃታል:: እብሪተኞችን ያንበረክካል!

በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች፡የሀይማኖት መሪዎችን፡ የፖለቲካ መሪዎችን ለማስፈታት እንጩህ! የፍርድ ያለህ ! የነጻነት ያለህ!

ህወሃትን ከምድር ገጽ አጥፍተን ሽብርተኛ ዝር እማይልባትን ኢትዮጵያ እንገነባለን!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

 

The post ኦባማን የኢትዮጵያ መንገዳቸው ቱሪናፋ አያደ ርጋቸውም ? – ከቢላል አበጋዝ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ –ኮርኩማ አፍሪካ

$
0
0

የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዮተኛ ቴዲ አፍሮ አዲሱን ነጠላ ዜማ ለሕዝብ ለቀቀ:: ቴዲ በዋሽንግተን ዲሲ የፊታችን ሐሙስ ጁላይ 2 ያለው ሲሆን አዲሱ ነጠላ ዜማው ከወዲሁ የሶሻል ሚዲያውን አጥለቅልቆታል::

በስጋት ቀፎን ተይዞ እስራት
አዋቂው ሸሽቶ ረሃብ ነግሶ ርዛት
በምድሯ ሊቆይ ማንስ ይደፍራል
ታንኳ ላይ ወጥቶ ወንዝ ይሻገራል
አለቀ ሰዋ ባህር ገብቶ ሄዶ(4×)
………

ውሃ ቢገባ በአፍሪካ መርከብ
አቤት ቢል ተጓዥ ሃሳብ ለማቅረብ
ይሰምጣል እንጂ ከባህር አብሮ
ቀዛፊው ላሳብ አይሰጥም ቶሎ
……….

ዮንጂ ከረ
ቤቴ ኖረ
ወጥቶ ቀረ
ግዶ ግዶ
ወይ ግዶ ወይ ግዶ
………..

ኮርኩማ ኮርኩማ ወንዝ አሻገረችው
ኮርኩማ አፍሪካ
የንን የሰው ጫካ
ኮርኩማ አፍሪካ
ባዶ አደረገችው
ኮርኩማ አፍሪካ
የሚለውን አዲሱን የቴዲ ነጠላ ዜማ ዘ-ሐበሻ እነሆ ትላለች::

teddy afro

The post ቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ – ኮርኩማ አፍሪካ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአንዋር መስጊድ ደማቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲሰማ ዋለ * “ኮሚቴውን በነጻ ከመልቀቅ የተሻለ አማራጭ የለም”

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ትናትም ዛሬም “ኮሚቴው ነፃ ነው.. በነፃ ይሰናበት” እያሉ ፍትህን የሚጠይቁ ሙስሊሞች በአንዋር መስጊድ ደማቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ:: በተያዘው የረመዳን ጾም የሕወሓት መንግስት ካንጋሮው ፍርድ ቤት እስር ቤት ባሉት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ፍርድ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ መዘገቡ ይታወሳል::

ዛሬ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ የክልል ከተሞች በተደረገው በዚሁ የድምፃችን ይሰማ ተቃውሞ ሕዝቡ መፈክሩን በመያዝ በየመስጊዱ ኮሚቴውን በነጻ ከመልቀቅ የተሻለ አማራጭ የለም ሲል በአንድ ድምጽ ሲያሰማ ውሏል::

“የተከሰሰነው ነው እኛ ነን:: በነፃ ከማሰናበት ውጭ ያነሰን ብይን ያለ አማራጭ አንቀበልም” ያሉት ሕዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት መንግስትን አሁንም በሰላማዊ መንገድ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል::
muslim addis abeba

muslim addis 2

muslim addis

muslim

The post በአንዋር መስጊድ ደማቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲሰማ ዋለ * “ኮሚቴውን በነጻ ከመልቀቅ የተሻለ አማራጭ የለም” appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live