Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

5 የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ኤርትራ ገብተው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቀሉ

$
0
0

agazi
(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ 5 የአጋዚ ጦር አባላት የነበሩ የስርዓቱ ታጋዮች የሕወሓትን መንግስት በመክዳት አስመራ ገቡ:: እነዚሁ 5 ታጋዮች ኤርትራ የሚገኘውን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቅለዋል::

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰላማዊ ትግል ይታገሉ የነበሩም ሆነ የሕወሓት ጦርን ሲያገለግሉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን በመምረጥ ወደ ኤርትራ በመሄድ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን እየተቀላቀሉ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ::

ሰሞኑን ይህንኑ ንቅናቄ የተቀላቀሉት 5ቶ የአጋዚ ጦር አባላት

1ኛ. ግራማ ተላይነሕ
2ኛ. ሄኖክ እንዳልካቸው
3ኛ ስለሺ ተስፋሁን
4ኛ. ምርት ይሁን መንገሻ
5ኛ ስማቸው ካሴ ይባላሉ።

The post 5 የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ኤርትራ ገብተው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቀሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


የማለዳ ወግ…”ዱአ .. ዱአ ላይ …ነ …ኝ ”ጸሎት ላይ …–ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

nebeyu sirak

====================================

* በታላቁ የሮመዳን ወር እነሱና እኛ..
* የመረጃ እጥረት ይኖር ይሆን ?
* በጎ አድራጊዋ ጉብልና የአቡ ፈይሰል ቤተሰቦች…
* ” ዱአ .. ዱአ ላይ … ነ …ኝ “
የሮመዳን የመጀመሪያ ሳምነት …
=====================

የዘንድሮው ሮመዳን በሳውዲ በቀለጠ ሙቀት የታጀበ እንደሚሆን ማስጠንቀቂያዎች ጭምር ሲነገሩ ሰነባብተዋል ። እንደ መረጃው ከሆነማ በተወሰኑ ቀናት ሙቀቱ እስከ ሀምሳ ዲግሪ ይደርሳል ተብሎ ይታሰባል ። ይህ በተባለ ማግስት ሮመዳንን ከተቀበልን ሳምንት ሊጠጋ ቢሆንም ላያስችል የማይሰጠው ፈጣሪ ይመስገን የሚያስፈራ የሚያስበረግግ ሙቀት እስካሁን አልተስተዋለም !
ጾሙ የሳውዲን ትላልቅ ከተሞች የሞቀ የደመቀ እንቅስቃሴ ጾሙ እስኪፈታ ያለውን ጊዜ አቀዝቅዞት ይስተዋላል ። ያም ሆኖ የቀኑ ጾሙ ሊያከትም ሁለትና ሶስት ሰአታት እስኪቀሩት ከማለዳው እስከ ተሲያት ጸጥ ረጭ ብሎ የዋለው ከተማና በከተማው የከተመው ነዋሪ በውክቢያና ግርግሩ ይጨናነቃል ! ብቻ ሁሉም ተከባብሮ ያልፋል ፣ ለፈጥሩ ሰአት ገስግሶ ይደርሰናም አፍጥሮ ከጥድፊያው ላፍታ ይሰክናል … !
እነሱ በሮመዳን …
============
በሮመዳን የታደሉት የአረብ ወዛዝርትና ኮረዶችን ጨምሮ በሳውዲ ሰማይ ስር የከተመው ሙስሊማን በጾም ጸሎት የዋለውን ቤተሰቦቻቸው ጾም ለማስፈታት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን የሚያደርጉበት ልዩ ወር ነው ። በሮመዳን ቤት ያፈራው ተጠራርጎ የሚዘጋጅ የሚሰናዳበት ፣ ለተራራቀ ቤተሰብ እስከ ወዳጅ ዘመድና ጎረቤት ኩርፊያ ጥላቻን በይቅርታ አጽድቶ አብሮ ለመብላትና ለመጠጣት የሚገባበዝበት ድንቅ ወር ነው! በሮመዳን ለነፍሳቸው ያደሩ ባለጸጎችና እንዳቅማቸው የሞላላቸው ከቤት ቤተሰቦች አልፈው በአውራ መንገድ የሚተላለፈውን መንገደኛ ፣ በየስራ ቦታና በየመስጊዱ የተሰባሰቡትን ጾመኞች ድረስ ሔደው ጾማቸውን እንዲፈቱ ያለምንም ከፍያ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ደግሰው ያበላሉ ያጠጣሉ ። አንዳንዴማ አንቱ የተባሉ ዲታ ባለጸጎች ከመንገድ ከጽዳተኛ አሽከራቸው እኩል ማዕድ የሚቆርሱበት ፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሚያዩባት ወር የሮመዳንን የፍቅር ተግዳሮት መታዘብ ለመንፈስ የሚሰጠው እርካታ የትየ ለሌ ሆኖ እናገኘዋለን ! ባለጸጎችም ዝቅ የሚሉበት ወር ነው ለማለት እንጅ በሮመዳን ባለጸጎችም ብቻ ሳይሆኑ እንዳቅማቸው የሚያድሩት ጭምር በሮመዳን ብቻቸውን አይበሉም ፣ አይጠጡም ! በሮመዳን የሰፈር ድሃዎች ለይተው በቻሉት መጠን የሚበላ የሚጠጣ በማቅረብ ይደግፏቸዋል ። ከምግብ መጠጡ አልፎ የገንዘብ እርዳታና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በምክርና የተለያየ ድጋፍ የሚሰጥበት የደግነት መገለጫ ወር መሆኑን እየተዛብኩ ኑሬታለሁና እውነቱን እነግረችኋለሁ ! አብዛኛው የኖርኩበት ሀገር ታዳሚዎች በሮመዳን እንዲህ ናቸው ።

እኛ በሮመዳን …
============
በሳውዲ ሰማይ ስር ያለውን ሀበሾች ውሎ አዳር ስንቃኘው ደግሞ የምናስተውለው ሌላ መልክ አለው ። በሮመዳን በአብዛኛው ሀበሾች ሌላው ቀርቶ በየሆስፒታሉ ያለ ጠያቂ የወደቁ ወገኖቻችን ህብረት ፈጥረን በመጠየቁ ፣ በመርዳትና በመደገፉ ረገድ ነፍሳችን አልፈቀደም አልያም አላስተዋለ እንደሁ እንጃ አይንና ጆሯችን ትኩረት አልሰጠም ። ጅዳ ውስጥ ከኮንትራት ስራ ተባረው በመጠለያ ያሉትን ፣ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ ሆነው ቀን የጨለባቸውን እየረዳን ያለነው እኛ ሳንሆን አረቦች መሆናቸውን ሳስበው በሮመዳን መልካም በመስራት የመጣውን በረከት የነጠቁን ያህል ይሰማኛል በመንፈሳዊ ቅናት ድብን ያልኩባቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው !

በሳውዲ የጠረፍ ከተማና በትላልቅ ከተሞች ብዙ ወገኖቻችን የእኛን ሰብአዊ ድጋፍ ይፈልጋሉ ፣ ግን አያገኙም ! በጅዛን ሆስፒታል ለአመታት ከአልጋ ያለወረደው ካልድ በአዘቦትም ሆነ በሮመዳን ጎብኝ ወገን የለውም ። በመዲና ቤተሰቦቿ ከአመታት በፊት ሀኪም ቤት ወርውረዋት ሄዱ የተባለች ስሟ በውል የማትታወቅ እህት ከሰመመን አልነቃችም ፣ ይህች እህት ጎብኝ የላትም ፣ ቤተሰቧን ከማፈላለግ ጀምሮ ወደ ፈጣሪ በጸሎት አንለምንላትም ! በጅዳ ከአራት አመት በላይ በደረሰባት አደጋ በሰመመን ያለችው እህት ጉዳይ ተመሳሳይ ነው ቤተሰቧ አይታወቅም ፣ እኛም እንዲታወቅ አላደረግንም !

በመኪና ግጭት አካላቸው የተሰናከለው በየሀኪም ቤቱ ሞልተዋል ። ይህን ሰሞን እንዲረዳ ከምናነሳው ወንድም መሀመድ ሁሴን ካለበት ቁንፊዳ ሌላ በመኪና አደጋ አካሉ ብቻ ሳይሆን ጀሮው ማስማት የተሳነው በከፋ አደጋ የተሰናከለ ወንድም አለ ! ችግረኛ መኖሩ ሲታወቅ የሀገር ገጽታ ፣ የመንግስትን ስም ያበላሻል ብለው ለምን እንደሚሸፋፍኑት ባይገገባኝም የያዙትን ጉዳይ ከዳር ለማድረስ የገደዳቸውን ኃላፊዎች ተጽዕኖ እየፈጠርን ሰብአዊ ስራን መስራቱ ገዶናል ! ከሁሉም የሚያስገርመውጉዳዩን የያዙት መረጃው እንዲወጣ አለመፈለጋቸው ሲሆን ለመፍትሔ ፍለጋ የተጉ አለመሆናቸው ይባሱኑ ያማል !

ዝቅ ሲል አረቦች በሮመዳን ለጽድቅ እየነፈነፉ መሰራት የሚፈልጓቸው የበጎ አድራጎት ሰራዎች ከአጠገባችን ሞልተው ተርፈዋል ። እነሱ በሮመዳን ማህበራዊ መገናኛ መድረኮችን ሲጠቀሙባቸው “የተቸገረን እርዳ !” የሚለውን የፈጣሪ ትዕዛዝ እያስተላለፉ በተግባር እያደረጉትም ነው ፣ እኛ በየፊስቡክ ገጻችን መድረክ “የተቸገረን እርዳ !” ሌላም ሌላ መልካም ምግባርን ተገቢ ነው የሚለውን አሽቆጥቁጠን እንለጥፋለን ፣ በተግባር ግን ብዙዎች የለንበትም !

እኛ እነሱን እያየን አናያቸውም ! ስደቱ ከፍቶ ፣ ጊዜ ጠሞ የለከፋቸውን ውስጠ ፌደዌ በሽታ ለማስታገስ መድሃኒት እንኳ ለመግዛት ኑሮ አልሞላ ብሎ የከበዳቸው አሉ ፣ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን ጨምሮ ውስጣቸው ባዶ ሆኖ በውጫቸው የተዋቡ የወገኖቻችን ድረስ ባለው ሰፊ ምህዳር በሮመዳን የእኛን ድጋፍ ፣ የእኛን ጸሎት ፣ የእኛን አለኝታና ድጋፍ የሚሹ በርከት ያሉ ማህበራዊ ችግሮች በውስጣችን ቢኖሩንም እኛ ለዚያ ግድ የለንም አልያም ያላስተዋልነው ነገር አለ …
የመረጃ እጥረት ይኖር ይሆን ?

====================
ከላይ የጠቀስኩትን ወደ መንፈሳዊ መነቃቃት ያመጣን ዘንድ የሰነዘርኩት ወቀሳ ቢጤ ዋና አላማ ያለፈው ትምህርት ከሆነን በሚል ነው ። ከሁሉ አስቀድሞ በሮመዳኑ በሚጠበቅብን ቦታ ስላለመገኘታችን የመረጃ እጥረት ይኖር ይሆን ? ብለን ለምንጠይቅ ለአብዛኞቻችን ቅንነት ስላጎደለብን እውነታ ብዙ ጥቂት ማሳያዎችን ለመጠቃቀስ ልሞክር ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ወደ ቆዩ ማሳያዎችን አልሄድም ፣ በቅርብ እየተከወኑ ያሉ ሰሞነኛ ጉዳዮች መካከል አንድ ሁለት ልበል …
“ለመርዳት ለመደጋገፍ የተጎዳ እርዳታችን የሚሹ ወገኖችብ ለመርዳት መረጃ እጥረት የለንም!” እንዳይባል መረጃው አለ ። ቀዳሚው ማሳያየ የ9 ዓመቱ የአልጋ ቁራኛ የመሀመድን ፣ ብርቱ እናቱንና ቤተሰቡን ታሪክ ያልሰማ አለ አልልም ። ዳሩ ግን እኒህን የ9 አመት ግፉአን ወደ ሆስፒታል ጎራ ብለን ለማየት የቻልን ብዙዎች አይደለንም ! የእናቱን የፍትህ ፍለጋ ጩኸት እየተቀባበልን ብናሰራጨው ከፈጣሪ በታች ግፍ ፈጻሚዎችን ወደ ህግ ፊት የማቅረቡን ጉልበት ምስለኔ ሳይሻን እኛው ማፋጠን እንችላለን! …ይህ በሚጠበቅ ደረጃ እየተካሔደ አይደለም ! ቢያንስ ሳውዲ ያለ ሀበሻ የፊስ ቡክ ተጠቃሚ የብላቴናውን መሀመድ አብድልአዚዝ ፎቶናባ ቪዲዮ መረጃ ከፊት ገጹ ከማሰራጨት መቆጠብ የለበትም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ … ብዙዎች ሰፊውን ዝርዝር መረጃ ቀርቶ የመሀመድን ፍትህ ጥያቄ ለማስተጋባት ከፊስ ቡክ ገጻችን ፎቶውን አንድ ሰሞን መለያ የማድረጉን ሞራል ከድቶናል፣ እኛ ግን ብዙዎች የሚጠበቅብንን አላደረግንም ! የሰው ልጅ ሰጥቶ አያጠግብም ፣ በሞራል ፣ ለመሀመድ ቤተሰቦች በጸሎትና በመሳሰሉት ከጎናቸው መቆም በራሱ ከገንዘብ በላይ ነው ! …ይህ መረጃ አለን የሚጠበቅብንን እያደረግን ግን አይደለም!

ቀጣዩ ምሳሌ የክፉው ስደት አካሉን ያሰናከለውና በኩንፊዳ ከተማ ሆስፒታል የሚገኘውን የወጣት አባወራ የወንድም መሀመድ ሁሴን ጉዳይ ነው ። ምናልባት አሳዛኙን መሀመድን ለመጠየቅና ለመደገፍ ከጅዳ 300 ኪሎ ሜትር መሄድ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል ። እንደኔ አስፈላጊም አይደለም ! መሀመድን የተሰበረ አንገት ለማቅናት አንድም ከአንድ ቀኗ ፈጡር ( ቁርስ) አለያም የአንድ ምሳዋን ግማሽ ዋጋ ለመሀመድ መስዋዕት ማድረግ ሰው ዳተኛ ሆኗል ለማለት ጊዜው አይደለም ። ዳሩ ግና በቅርብ የማውቃቸው ለመሀመድ እርዳታ ቀናኢ ሆነው ስልክ ደውለው ” አስር ብር ለመሀመድ አዘጋጅቻለሁ! ” የሚሉኝ ቀን ናፍቆኛል ። በርካቶች በመሀመድ ታሪክ ቢያዝኑም በእስካሁኑ እርዳታ ከ10 ሽዎች የጅዳ ፊስ ቡክ ተጠቃሚ መካከል በተግባር እየደገፉ ያሉት ወደ 20 የሚጠጉ እህቶችና ሶስት አራት ወንድሞች ናቸው። ያም ሆኖ በቀጣይ ቀናት በርካታዎች እጅግ ጥቂት የእርዳታ ተሳትፎ በማድረግ የአባወራውን ወጣት ቤተሰብ ሊደግፍ የሚችል እርዳታ ይሰባሰባል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ! ከዚህ በተረፈ ያሌለው ያድርግ ብየ አልገፋም ፣ ወጭ ማድረጉ ከከበደን መሀመድ በስልክ ደውሎ ማጽናናት ማበረታታትና በጸሎት እንደሚያስቡት ማነጋገር ከገንዘብ በላይ የሚያክመው ሞራል ሊታሰብ የሚገባ ነው ባይ ነኝ ፣ ለመልካም ነገር መትጋት ዋጋው ከፍ ያለ ነውና !

በጎ አድራጊዋ ጉብልና የአቡ ፈይሰል ቤተሰቦች…
==============================
ትናንት ማምሻውን አንድ ባስደመመኝ ጉዳይ ወጌን ላክትም … የመሀመድ ገንዘብ እርዳታ እንድወስድ አንድ እህት መልዕክት አስቀምጣ ነበርና ስልክ ተደዋውየ ለመቀበል ከቤት የወጣሁት የአሱር ጸሎት እንዳከተመ ነበር ። ቀን ጸጥ ረጭ ብሎ የሚውለው ከተማ በሰውና መኪና የሚሞላ የሚተራመስበት ሰአት ነው ። በቀጠሮው ቦታ ደረስኩ ፣ ሀበሻዋ እህት ቦታዋን ካመላከተችኝ ከአሰሪዋ ጋር ወረደች ፣ እርዳታ የምታቀብለኝ እህት አጠር ያለች ፊቷ ክብ የሆነች ልጅ እግር ጉብል… የለመንኩትን እየሰጠች የተገላቢጦሽ አመስግናኝ ገንዘቡን ሰጠችኝ ! አሰሪዋም እጅጉን አመሰገኑኝ ፣ ይህ ሁሉ የሚሆነው ከግቢየቸው በር ላይ ነው “እቤት ግባ አፍጥር! ” ተብየ አሻፈረኝ በማለቴ ነው ግቢ በር እኔ በመኪናየ መስኮት እነሱ ለመኪናው አጠገብ ቆመው ተቀባበልን !
በልጅ እግሯ እህት ልጅነት ቀልቤ ተስቦ ተሰነባብተን ልንለያይ ልንቀሳቀስ ስል የቤቱ አባወራ ቴምር ውሃና ወተት ይዘውልኝ ሲንደረደሩ ወደ እኔ መጡ …
” ሰለም አሊኩ ፣ አቡ ፈይሰል መአክ ” አሉኝ በመልካም ምግባራቸው ተገርሜ ከመኪናየ ወርጀ ስሜን ማንቴስ ብየ አመስግኘ ያዘጋጁልኝን ለፍጡር የሚሆን ምግብ ተቀበልኳቸው ! ለካስ የእኛዋ ጉብል ሰራተኛቸው የመሀመድን ጉዳይ ነግራቸው ነበርና እርሳቸውም ” ጀዛከላህ !” ፈጣሪ ይስጥህ ብለው አመስግነውኝ የሰራተኛቸውን ደግነትና እንደልጅ እንደሚያዯት በቁሜ አጫወቱኝ ። ቀጥለው አጥር አስርገው ያወሩኝ ስለ ሀበሻው ቢላልና ነጃሽ ታሪክ በጥልቀት እንደሚያውቁና ሀበሻን እንደሚዎዱ ፈገግ እያሉ ጫወታውን አረዘሙት ፣ እኔም ተመስጨ መስማት ያዝኩ ” አየህ ወንድሜ ይህች የምታያትን ልጅ የመጣችው አሁን አደጋ ደረሰበት እንዳላችሁት ወንድም በመጣበት የየመን መንገድ ፣ በአሸጋጋሪዎች ነው። ገና የ 13 ዓመት ልጀ ነበረች ፣ የዛሬ 6 ዓመት ሮመዳን ስራተኛ ፈልገን ሰራተኛ ከሚያቀርብልን ሀበሻ ወደ ኪሎ 8 ሄድን ፣ ብዙ ሰራተኞች ደርድሮ ቢያሳየንም አንዲት እድሜዋ ወደ 20 የሚጠጋ ሰራተኛ መረጥን። ይህችን ልጅ ካስመረጡን ሰራተኞች ውስጥ ትንሿ ነበረች ። መስራት ባትችል ልጃችን ትጠብቃለች ብለንና ለነፍሳችንም ትሆናለች ብለን አመጣናት ። … ከመጣች በኋላ ግን እንኳን ልጅ ልትጠብቅ የእኛ ልጆች እሷን ጠባቂ ሆኖ ፣ ጥሩነቱ የቤተሰብ ናፍቆቱን ስትረሳው ከልጆቻችን እኩል እየቦረቀች ስትጫዎትና ፍቅር ስትሰጣቸው አድጋለች ፣ አላሀምዱሊላህ ዛሬ ያች ህጻን አድጋ ፣ መኖሪያ ፈቃድ አውጥተንላት ፣ ቤተሰቦቿን እየረዳች አብራን ስትኖር ሰራተኛ ሳትሆን ልጃችን ሆና ነው! ከእኛው ጋር በማደጓና መልኳም እንዳየሃት ቀይ በመሆኗ አረብ ነው የምትመስለው ፣ አረብኛም ቡልቡል ናት … ” ብለው የድሃ አደጓን ቤተሰብ ለማግኘት ያገጠማቸውን ክልትም አጫወቱኝ ፣ አቡ ፈይሰል ጫዎታቸው አይጠገብም …
” ዱአ .. ዱአ ላይ … ነ …ኝ ”
==================
ከአቡ ፈይሰል ጋር በነበረኝ ቆይታና ባየሁ በሰማሁት ተደስቻለሁ ፣ በድስታ መኪናየን አስነስቸ ወደ ሌላ ቀጠሮ እያመራሁ ያጋጠመኝን ደስ የሚል ታሪክ ላጫውተው ወደ ኩንፊዳው መሀመድ ስልክ ደወልኩ ። ስልኩ ደጋግሞ ቢጠራም አልተነሳም ፣ ደግሜ ደጋግሜ ደወልኩና ወደ መጨረሻው መሀመድ ስልኩን አነሳ ” ይቅርታ ወንድም ነብዩ ዱአ ላይ ነበርኩ !” አለኝ ። ረብሸው ከሆነ ይቅርታ ብጠይቀውም ጸሎቱን ጨርሶ ስልኬን ማንሳቱን አሳወቀኝ ! የስልኩ አለመነሳት ላጫውተው የነበረውን የእርዳታው ማሰባሰብ ያገናኘኝን የአቡ ፈይሰል ቤተሰብ ጉዳይ አስረስቶኝ የጅዳ ቆንስል ጉዳዩን እየተከታተልኩ እንደሆነ ተጫወትን ። ከዚያ ቀጥየ ስለ እርዳታው ሂደት ስጀመር የአቡ ፈይሰል ቤተሰብና የእኛ ጉብል ለስኬት የበቃ ታሪክ አጫወትኩት … ! …መሀመድ እጅግ በጣም ደስ አለው ፣ ሲቀጥልም እንዲህ አለኝ ” ዛሬ የገንዘቡ ነገር አላስጨነቀኝም ፣ ታሪኬን ከጻፍከው በኋላ ሰው ከአሜሪካ ፣ ከአውሮፖ ከሊባኖስና ከሳውዲ ይደውልልኛል ፣ አይዞህ ብለው እያበረታቱኝ ነውና የቀደቀው ሞራሌ እያንሰራራ ፣ ተስፋ የቆረጠው መንፈሴ በአላህ እትዳታና በሰው አይዞህ ባይነት እየታደሰ ነው ! በእኔ ላይ ለሆነው አላህ ምክንያት አለው ነቢዩ … እዚህ ሆስፒታል መድሀኒት ስለምንወስድ ለሁሉም ታማሚ ቁርስ ፣ ምሳ ፣ እራት በሰአቱ ይቀርባል ፣ እኔ ዘንድሮ ስለሆነልኝ ለማመስገንና ስለምህረቱ ልለምን መድኃኒቴ ዱአ ነውና በፍቃዴ እየጾምኩ ነው !… ለእናንተ ከጎኔ ለቆማችሁ ላልቆማችሁትም ፍቅር ስል ዱአ ላይ ነኝ ፣ እውነት እልሀለሁ ፣ ከልቤ አልቅሸ ፈጣሪየን አመሰግነዋሁ ፣ ዱአ .. ዱአ ላይ … ነ …ኝ !” የተቆራረጠ የሳግ ድምጽ ስሰማ የምሆነውን አጣሁ …በታደሰው የአባ ወራው መንፈስ ፣ በተገነባው የወንድማችህ ህይዎት ምክንያቱ ገንዘብ አለመሆኑን አሰብኩት … ” የሀበሻ ዘር ወገኔ ከሌለበት ቦታ ነው ያለሁ ፣ ሰው ይናፍቀኛል ፣ ወደ ሀገሬ ልግባ! ” ብሎ በምሬት የድሱልኝ ጥሪ ያሰማው የ9 ወር የአልጋ ቁራኛውን ወንድም ሳምንት ባልሞላ ቀን ተስፋውን ስለሞላለት ፋታሪ አምላክ ፣ ከአምላክ በታች የወንድማችን ጥሪ አሳዝኗችሁ በእርዳታና በሞራል ድጋፉ ለተሳተፋችሁ ምስጋናየ ከፍ ያለ ነው!
አሁንም ጊዜው ገና ነው ፣ አባወራውን መሀመድን የአቅማችን ያህል እንርዳው !
ስለሆነው ሁሉ ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓም

The post የማለዳ ወግ… ” ዱአ .. ዱአ ላይ … ነ …ኝ ” ጸሎት ላይ … – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ባክኖ የቀረ  አየር ኃይል –ክንዴ ዳምጤ –ሲያትል

$
0
0

ውስጥ ውስጡን በድብቅ ሲብላላ የሰነበተውና በኋላ ቀስ በቀስ ወደ አደባባይ የወጣው የሻብያና ህውሃት ወዳጅነት ላይ ያንዣበበው ጥቁር ደመና ሞትን አርግዞ እያስገመገመና እያስፈራራ ሰነባብቷል ። እዚህ አስመራ ውስጥ ከወትሮው የተለየ ነገር ባይታይም አዲስ አበባ ላይ የኢትዮጵያን ፓርላማ የክተት አዋጅ ተከትሎ የጦርነቱ ከበሮ ተሟሙቆ ቀጥሏል ።

ethiopian airforceህውሃት አዲስ አበባና ደ/ዘ እንደደረሰ እጁ ያስገባቸውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ወደ እስር ሲያግዝ እድል የቀናው ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ አገር ጥሎ ተሰደደ ። እዚህ አስመራ ደግሞ ሙያችንን ፈልገው አዲስ እየተዋቀረ ባለው አየር ኃይላቸው ውስጥ እያሰሩን ያለን ኢትዮጵያውያን ቁጥራችን ቀላል አይደለም ። እንዲያውም ከ80 % በላይ የአዲሲቱን አገር ኤርትራን አየር ኃይል እያቋቋምን የምንገኘው በትውልድ ኤርትራዊ የሆኑትና እኛ ኢትዮጵያውያን የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላቶች ነን ። (ኤርትራውያኖች የቀድሞ አየር ኃይል አባላት እድለኞች ናቸው ። ኢትዮጵያ እንደተደረገው መሰደድና መጋዝ አላጋጠማቸውም ። ሙያቸው ለአገሪቷ እንደሚጠቅም የሚረዳ የሙያው ባለቤት የሆነ አዛዥ አላቸውና በቀጥታ ወደ ስራ ምድባቸው እንዲገቡ ተደርጓል ።)

በዕለተ ዓርብ ግንቦት 27, 1990 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ሜይ 5, 1998 በፈረንጆች የአስመራ አየር ኃይል ቤዝን ለማውደም የተጀመረውን የአየር ድብደባ ተከትሎ የኤርትራ አየር ኃይል 100% የውጊያ ዝግጁነት ( 100 % Readiness ) ታዟል

ይህ የውጊያ ዝግጁነት እኛን ኢትዮጵያውያኖቹን የማይመለከተን ቢሆንም ከኰ/ል ታደሰ ሙሉነህ ጋር በነጋታው ጠዋት ወደ አስመራው የአየር ኃይል ግቢ አመራን ። (ኰ/ል ታደሰ ሙሉነህ ማለት ታዋቂ የአየር ኃይል ተዋጊ በራሪ የነበረና በኋላም የአርበኞች ግንባር መሪ ፣ በቅርቡ ደግሞ እዚያው ኤርትራ ውስጥ ለእስር ተጋልጧል የሚባለው)

አስመራ አየር ኃይል ቤዝ እንደደረስን በሁለት የኢትዮጵያ ሚግ – 23 ተዋጊ አውሮፕላኖች የደረሰውን የአየር ድብደባና በአካባቢው ላይ ያደረሱትን ጉዳት እየተዟዟርን ተመለከትን ።

አንድ የጥገና ጋራዥና አጠገቡ የነበረች ሻይ ቤት ሙሉ በሙሉ ወደመዋል ። ኰ/ል ታደሰ ተበታትነው ወደ ሚታዩት ፍንጣሪዎች በእጁ እያመለከተ “ ይሄ ክላስተር ቦምብ ነው ” አለኝ ። በድብደባውም ሻይ ቤቷ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ፣ ፍፁም የሚባል የቀድሞው አየር ኃይል ባልደረባም እንደሞተ ሰማሁ ።

አለፍ ብሎ ደግሞ ሁለተኛው የአውሮፕላን ጥገና ጋራዥ ላይ የወደቀውንም ቦምብ ተመለከትን ። ይህ ደግሞ “ ናፓል ቦምብ ” ነው አለኝ ኰ/ል ታደሰ ሙሉነህ በድጋሚ ። እኔ ሁለቱንም ዓይነት ቦምቦች ሳይ ይህ የመጀመሪያዬ ነበር ።

በመቀጠል በረራ መስመር ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማየት አውሮፕላኖቹ ወደቆሙበት ስፍራ ስንጠጋ አካባቢው በአደጋ መከለያ አጥር ታጥሯል ። አጥሩን አሻግሬ ስመለከት ኰንክሪቱን ወደ አንድ ሜትር ያክል ሰርስሮ የገባው ባለ 500 ኪ/ግ ቦምብ ሳይፈነዳ ከነነፍሱ ቁጭ ብሏል ። አደጋ እንዳይደርስ ተብሎም ወደ ቦምቦቹ መቃረብን ለመከላከል እንደታጠረ ተረዳሁ ።

 

ይህንን ግዳጅ የሰሩት ኢትዮጵያውያን በራሪዎች አስመራን ጠንቅቀው የሚያውቁና ፤ የሚደነቅም ችሎታ ያላቸው ስለመሆኑ እኔና ኰ/ል ታደሰ ተስማማን ። ለነገሩ የአገርን አንድነት ለመታደግ ከሻብያ ጋር ግብ ግብ እንደገጠሙ እዚሁ አስመራ አይደል ዘመናቸውን የፈጁት ? አስመራ የአየር ኃይል ቤዝ ለእነዚህ በራሪዎች አዲስ ሊሆን አይችልም ። በአገር ቤት ከእስርና ከስደት ተርፈው በስራ ላይ ያሉት በራሪዎች እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉም አሰብን ። በይበልጥ እኔ አብሪያቸው ስስራ የቆየሁ በመሆኔ ለመገመት ብዙም አልተቸገርኩም ።

አካባቢውን ተመልክተን እንዳበቃን ቁርስ በመቀማመስ ወደ ሆስፒታል በመሄድ የተጐዱ አባላትን ጠየቅን ። ኤርትራና ኢትዮጵያ ከመለያየታቸው በፊት በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ሁላችንም በአንድነት እንሰራ ነበርንና በአንድ እናት ልጆች መካከል የሚካሄድ ፋይዳ ቢስ ፀብ መሆኑ እየተሰማን የጦርነቱ አላስፈላጊነትና እየደረሰ ያለው መጐዳዳት በእጅጉ አሳዘነን ።

ረፋዱ ላይ አገር ያናወጠ የአደጋ ማስጠንቀቂያ ጡሩንባ ( ሳይረን ) ደጋግሞ በረጅሙ አስተጋባ ። ይህ ሳይረን የጠላት ተዋጊ አውሮፕላኖች አደጋ ለማድረስ መቃረባቸውን የሚጠቁምና ማንኛውም ሰው መከላከያ ስፍራ እንዲይዝ የሚያስጠነቅቅ ነው ። በመሆኑም ሁሉም ሰው በደርግ የአስተዳደር ዘመን ወደተሰሩ የመሬት ስር ምሽጐች እየሮጠ መግባት ጀመረ ። እኔም ዘመቻ መምሪያ አቅራቢያ ወደ አለው ባንከር እየተጣደፍኩ አመራሁ ። ልክ ባንከሩ መግቢያ ደጃፍ ላይ ስደርስ በደርግ ዘመን ሻብያ ከርቀት የከባድ መሳሪያ አረሮችን ወደ አስመራው አየር ኃይል ካምፕ ያዘንብ በነበረበት ወቅት አንድ ም/መ/አለቃ ይኩኖ ታደሰ የሚባል ጓደኛችን ወደ እዚህ ባንከር ውስጥ ሊገባ ሲል ከእርቀት እየተተኰሰ ባለው የመድፍ አረር ፍንጣሪ አንገቱ ተቆርጦ መሞቱ ለአፍታ ወደ አዕምሮዬ በመምጣቱ ሰውነቴን ሁሉ እየዘገነነኝ እያማተብኩ ፈጠን ብዬ ወደ ባንከሩ ተወርውሬ ገባሁ ።  ወደ ውስጥ ስዘልቅ የአየር ኃይሉ ኰማንደርና የመከላከያ ሚንስትሩ ባንከሩ ውስጥ መኖራቸውን አስተዋልኩ ።

ደቂቃዎች ተከትሎ ለሰማይም ሆነ ለምድር የከበደ ከፍተኛ የተኩስና የፍንዳታ ጩሀት በተደጋጋሚ አገሩን አደበላለቀው ። የዓለም ፍፃሜ የሆነ ያክል ተሰማኝ ። በዚህ አስተማማኝ ባንከር ውስጥ ሆኜ ግን ሃሳቤና ስጋቴ ሁሉ አየር ላይ ሆነው ወደ ታች ስለሚተኩሱት በራሪዎች ነበር ። “ እነማን ይሆኑ ” ? ብዬ በረዥሙ እየተነፈስኩ እራሴን ጠየቅሁ ። ብርድ ቢጤ መላው አካላቴን ሲያንዘፈዝፈው ይሰማኛል ። ፓይለቶቹን በሙሉ አውቃቸዋለሁ ። ከሁሉም ጋር ከወዳጅነት የዘለለ ቅርበትና አብሮ መኖር አለኝ ።  በዚህ ቀውጢ ሰዓት በራሴው ወንድሞች ዒላማ ውስጥ መሆኔ እየተሰማኝ ቢሆንም መጥፎ ሃሳብ ወደ አዕምሮዬ ከቶ አልመጣም ፤ እንዲያውም ስለነሱ ደህንነት አብልጬ ተጨነቅሁ ። የአንድ እናት ልጆችን እርስ በርሳችን እያፋጁ ያሉትን ረገምኩ ።

 

መከላከያ ሚንስትሩና የአየር ኃይሉ አዛዥ ወደ አሉበት አካባቢ ቀረብ በማለት የሚያደርጉትን የሬዲዮ መልዕክት ልውውጦችን ማዳመጥ ጀመርኩ ። በትግሪኛ ቋንቋ መሆኑ ቢቸግረኝም እንዲሁ በደፈናው ግን ስለምን እንደሚያወሩ መረዳት ቀላል ነበር ። ከጥቂት የሬድዮ ንግግሮች በኋላ …. “አንዲት ሚግ -21 አውሮፕላን ተመታለች  ….. እየጨሰችም ነው ” የሚል መልዕክት ከወዲያኛው ጫፍ በሬዲዮው ውስጥ ጮክ ብሎ ተሰማ ። መድሃኒያለም ! እያልኩ ደጋግሜ ማማተቤን አስታውሳለሁ …. መላውን ሰውነቴን ነዘረኝ ፤ እንደፈራሁት ! አልኩኝ በውስጤ ።

ኰማንደሩም በመቻኰል ….” ወደቀች ! ” ? በማለት ጮክ ብሎ በጉጉት ጠየቀ ።

ከወዲያኛውም ጫፍ  “ አዎ ወድቃለች ” የሚል ተስፋ አስቆራጭ መልስ ሰጠ ።

ባንከሩ ውስጥ እኔ ካለሁበት በተቃራኒና ተማሪዎቹ ወደ አሉበት ጥግ የደስታና የጭብጨባ ድምፅ በከፍተኛው አስተጋባ ። የሚገርም ዓለም ነው ።  “ የአንዱ ቤት ሃዘን .. ለአንዱ ቤት ደስታ ነው ” አልኩኝ  አንገቴን ደፍቼ እያዘንኩ ። ሆዴ በእጅጉ ታወከብኝ …. አፌ በአንድ አፍታ ደረቀ ። ….. “ እግዚያብሄር ሆይ መጥፎ ነገር አታሰማኝ ! ” አልኩ በጉልህ በሚሰማ ድምፅ  ።

ኰማንደሩ በደስታ በሚመስል ፈጠን ያለ ድምፅ  …. “ ፓይለቱስ ? ”  ብሎ ጠየቀ ።

“ ፓይለቱ ዘሏል ! ”  የሚል ድምፅ ከወዲያኛው ጫፍ ከሬዲዮው ውስጥ አስተጋባ ። ቀጥሎም “ ወታደሮች ወደ ዘለለበት ስፍራ ተንቀሳቅሰዋል ”  አለ ።

…… “ የፈጣሪ ያለህ ! ” ….  አሁን እራሴን ማረጋጋት እንዳለብኝ ተገነዘብኩ ….. ነገሮች በቅፅበት እየተቀያየሩ ናቸው ።   ማን ሊሆን ይችላል ?  ብዬም ወደ ጥልቅ ሃሳብ ውስጥ ገባሁ ።

የማቃቸውን አራት የሚግ-21 በራሪዎችን ቆጠርኩ ። በእርግጥ ተፈትቶ ይሆናል ብዬ እንጂ አንዱ እስር ቤት እንዳለ አውቃለሁ ። ( እድለ ቢሱ መ/አ ደመላሽ መኰንን )

ለነገሩ እስር ቤቱማ የአገር ባለውለታ የሆኑትን የአየር ኃይል አባሎችን አጭቆ ይዞ የለ ? የነጠረ ችሎታ ፣ ለዘመናት የካበተ ልምድ ፣ በርካታ አዛውንት በራሪዎች በከንቱ ከተከረቸሙ 7ኛ አመታቸውን እያከበሩ አይደል ። በሃሳቤ የተሰደዱትንና በየሜዳው የተበተኑትን የአየር ኃይሉ ባለሙያተኞችን አስታወስኩ ። … “ያልታደለችና ባለቤት አልባ የሆነች አገር ”…. አልኩኝ ለራሴ ።

ከሁሉም ያስደነገጠኝ ነገር … ከቆጠርኳቸው አራት በራሪዎች ውስጥ ሶስቱ በወታደራዊው ስርዓት ዘመን ከሻብያ ጋር በጀግንነትና በቁርጠኝነት ሲዋጉ ( ዛሬ ያ ሁሉ መስዋዕትነት በዜሮ ቢባዛም ) በአማፅያኑ ተይዘው መጨረሻ ላይ ሻብያ ድል ሲያገኝ በምህረት የተለቀቁ ነበሩ ።

“ አምላኬ እባክህ ከሶስቱ መካከልስ አንዳቸውም አይሁኑ ” ….. ብዬ ፀለይኩ ። ከሶስቱ ውጪ ደግሞ አንዱ ወጣት በራሪ ነው …. የጊምቢ ልጅ ( ም/መ/አ እንደገና ታደሰ ) ።  በጣም ትሁትና ጨዋ ሰው ።

 

አንድ ጊዜ ባህር ዳር ከዚሁ ከጊምቢው ልጅ ም/መ/ እንደገና ጋር ከተማ ተያይዘን ወጣን ። የገበያ ዕለት በመሆኑ ብዙ ሰውና ግርግር በዝቷል ። አብዛኛው ሰው ጐስቋላና በየሚዲያው አማራ እየተባለው ከሚነገረው ፕሮፖጋንዳ ጋር በፍፁም አይጣጣምም ። መ/አ እንደገና የሚያየውና ስለ አማራ ነፍጠኛ ሲሰማ የነበረው ( ነፍጠኛ እየተባሉ የሚጠሩት አኗኗራቸው የተለየ ነው ብሎ ያምን ስለነበር ) አልገናኝ ብሎት ስሜን ጠርቶ … “ ወዳጄ ክንዴ ነፍጠኞቹ የታሉ … ? ” ብሎ ሲጠይቀኝ እነዚህ ሜዳው ላይ ፈሰው የምታያቸው ናቸው ብዬ በፈገግታ መለስኩለት ።  “ እነዚህ የማያቸውማ ከጊምቢ የባሱ ጐስቋላ ሰዎችን ብቻ ነው ….. ” ይልቅ ነፍጠኞቹን አሳየኝ ያለኝን አስታውሼ ነፍጠኛ ስለሚባሉት ምስኪን ህዝቦች ውስጤ አዘነ ።

ስለዚህ ቀደም ሲል ከሻብያ በምህረት የተለቀቁት በራሪዎች ክፉው ዕጣ የእነሱ እንዳይሆን የተመኘሁት በተቃራኒው ወጣቱ በራሪ ላይ ያሟረትኩበት መስሎኝ ተፀፀትኩ ።

እንዲሁ በሃሳብ እየባከንኩ ባለሁበት ቅፅበት ነበር “ ….. በራሪው በቁጥጥር ስር ውሏል ! ”  …. የሚል ጨካኝ መልዕክት በሬዲዮው ውስጥ የተሰማው ። ፈፅሞ የማላውቀው በራሪ እንዲሆን ተመኘሁ ። ለነገሩ የማላውቀው በራሪ ከየት ይመጣል ? ከማርስ …. ? እንዴት ሊሆን ይችላል ?

ኰማንደሩ ፈጠን ብሎ “  … ለመሆኑ ማን የሚባል ነው ? ” ብሎ ጠየቀ ። የልቤ ምት ተቀየረብኝ ….  ጆሬዬንና አፌን እንደከፈትኩ ከሬዲዮው ውስጥ የሚመጣውን መልዕክት ለማዳመጥ ጓጓሁ “ …. ያው ልማደኛው ነው …. ” አለ የሬዲዮው መልዕክት ። “ ….. ማ ! በዛብህ ?  …. ” …… “  በትክክል አውቀሀዋል …. ” አለ ያ ሟርተኝ ድምፅ በድጋሜ ።

ክፉኛ ደነገጥኩ …..  ። ኰ/ል በዛብህ ጴጥሮስ በእንደዚህ አይነት የልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ በሚመስል ፋይዳ ቢስ ጦርነት ውስጥ መሰለፍ እንደሌለበት ልቤ ያምናል ። ኰ/ል በዛብህ ለአገሪቷም ሆነ ለአየር ኃይሉ ትልቅ ኃብት ነው ። የአስተማሪዎች አስተማሪ ፣ እጅግ ልምድ ያለው አዛዥ መኰንን ነው ። የእርሱ አደጋ ላይ መውደቅ በእጅጉ ይጐዳል ። በእንደዚህ ዓይነት ኤርትራን በምታክል ገና ዳዴ በምትል አዲስ አገር ጋር በሚደረግ የጥጋበኞች ልፊያ ውስጥ ቢበዛ ወጣት በራሪዎችን ማሰለፍ ሲቻል ኰ/ል በዛብህን ከነሙሉ ልምዱና አዛዥነቱ በከንቱ ማጣት ምንኛ ያለመታደል እንደሆነ አሰብኩ ። ቀደም ሲል ስምንት ዓመታትን ሙሉ በሻብያ እስር ቤት አሳልፏል ። ከሻብያ ድል በኋላም በምህረት ተለቆ ወደ ቤተሰቦቹ በሰላም የተቀላቀለ ነው ። እግዚአብሄርም ዳግመኛ ባርኰት ልጅ ወልዶ ባላቤቱን እርጥብ አራስ ልጅ እንዳስታቀፈ ሳይመለስ የቀረውን ያልታደለውን ኰ/ል በዛብህን እንደገና አሰብኩ ? ለመሆኑ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ማነው ? የስንቱ ዜጋ ቤት ተዘግቶ ፣ ወጣት በራሪዎችን ሜዳ ላይ በትኖ ፣ አዛውንቶችን በየማጐሪያው እያሸ ያለ ጨካኝና ዘረኛ ስርዓት ። ፋይዳ ቢስ ጦርነት …. ከንቱ መስዋዕትነት …. ያልታደለችና እርግማን ያለባት አገር ።  አንጀቴ ተቃጠለ ።

 

በዛብህ ጴጥሮስ ሎዳሞ አልኩኝ አንገቴን እንደደፋሁ ። ምን ዓይነት ፍርጃ ነው ?  …. ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ “ አባት ሆይ … ፈቃድህ ቢሆን ይህቺ ፅዋ ከእኔ ትለፍ ” የሚለውን የመፅሃፍ ቅዱስ ትምህርት አሰብኩ ። ከምር ብርታትንና ፅናትን ተመኘሁለት ። የባለቤቱንና የልጆቹን ሃዘን አሰብኩ ። መጥፎ ቀን … መጥፎ ቦታ … መጥፎ አጋጣሚ ።

ቀና ስል ከአዛዡ ጋር ዓይን ለዓይን ግጥም አልን ። ለራሱ እየቀረበለት የነበረውን ቡና አስተናጋጇ ለእኔ እንድትሰጠኝ በጥቅሻ ወደ እኔ እያመለከተ ነበር ። አሁን ለእኔ ሁሉ ነገር መራራ ነው ፤ ነገር ግን የደረቀ አፌን ማርጠቢያ ባዶውን ቡና መጠጣት ጀመርኩ ። ሃሳቤን ግን ከኰ/ል በዛብህ ላይ ሊያነሳልኝ አልቻለም ። አሁን ምን ያስብ ይሆን አልኩኝ በውስጤ ።

በዛብህና የኤርትራው አየር ኃይል አዛዥ ኰማንደር ሃ/ፅዮን ሃድጐ ያላቸውን ጓደኝነትና ቀረቤታ አውቀዋለሁ ። አንድ ጊዜ አራት የኤርትራ አየር ኃይል የበረራ ተማሪዎች በኢትዮጵያ አየር ኃይል ስኰላር ሺፕ አግኝተው ወይም ለበረራ ስልጠና ዕድል አግኝተው ይመጣሉ ። ታድያ ተማሪዎቹን ደብረ ዘይት በረራ ት/ቤት አምጥቶ ያስረከበው አዛዡ ኰማንደር ሃ/ፅዮን ነበር ። ከስራ መውጫ ሰዓት እንደደረሰ ሃ/ፅዮን ለምን አንድ ላይ እራት አንበላም በሚል እዚያ ላለነው የበረራ አስተማሪዎች ግብዣ አቀረበ ። በሃሳቡም ተስማምተን ደ/ዘ ወደሚገኘው ሆራ ራስ ሆቴል አቀናን ። ኰ/ል በዛብህን ጨምሮ ስምንት የምንሆን የበረራ አስተማሪዎች ነበርን ። ሃ/ፂዮን ስለ ኰ/ል በዛብህ ተናግሮ አይጠግብም ። “ በጣም የምወደውና የማከብረው አስተማሪዬና ጓደኛዬ እያለ ያሞግሰዋል ። እኔ ጋ አስመራ ቢመጣ እንደዚህ ህውሃቶች እንዳደረጉት ተራ አስተማሪ አይደለም የማደርገው ። የአስተማሪዎች አስተማሪ በማድረግ ዘውድ ጭኜ በክብር የማስቀምጠው ሰው ነበር ” አለ ።

ታድያ አሁን በተፈጠረው አጋጣሚ ኰ/ል በዛብህን ምን ይለው ይሆን ? ። እንዴት ወንድምና ወንድም ፣ ጓደኛና ጓደኛ እንዲህ የመረረ የመጠፋፋትና የመተላለቅ ግጭት ውስጥ ይገባሉ ? በዚህስ ማን ተጠቃሚ ይሆናል ?  አድካሚ የሆኑ ከንቱ ሃሳቦችን ሳወጣና ሳወርድ ሰዓቱ መርፈዱንም ልብ ሳልል ቀረሁ ። ኰ/ል ታደሰ በሃሳብ ጭልጥ ብዬ ከሄድኩበት ቀስቅሶ እንሂድ ባይለኝ ኖሮ ምን ያክል እዚያው ፈዝዤ እንደምቆይ መገመት ይቸግረኛል ።

ከኰ/ል ታደሰ ጋር ተያይዘን እንደወጣን “ ቢ ዜድን አስበሉት አይደል ? ” አለኝ ኰ/ል ታደሰ ። (BZ ማለት ኰ/ል በዛብህ በረራ ምድብ ውስጥ የሚጠራበት የአህፅሮት ስሙ ነው) ። ለኰ/ል ታደሰ ምንም መልስ አልሰጠሁትም …. አሁንም ከራሴው የውስጥ ሃሳብ ጋር ሙግት ላይ ነኝ ። የኤርትራው አየር ኃይል ምክትል አዛዥን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ስታፎች የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባል በመሆናቸው ፣ በተጨማሪም እየተፈጠረ ያለው ግጭት በአንድ ወቅት አንድ ላይ በነበሩ ሰዎች መካከል በመሆኑ የሃዘኔታ መንፈስ ይታይባቸው ።

ከኰ/ል ታደሰ ጋር በዝምታ ተጉዘን ከቤቴ በራፍ ላይ ስደርስ ማ/ቴክ አርጃ ፔራን አገኘሁት ። (ማ/ቴክ አርጃ የታወቀ የአርማሜንት ስፔሽያሊስት ኢትዮጵያዊ ነው ፤ ነፍሱን በገነት ያኑራት አሁን በህይወት የለም) ።

ማ/ቴክ አርጃ ወደ ቴሌ ሄዶ ደ/ዘ ቤተሰቡ ጋ ስልክ ደውሎ እየተመለሰ ነበር ። ቤተሰብ እንዴት ነው ? ደ/ዘይትስ እንዴት ናት ? ብዬ ጠየቅኩት ። “ ቤተሰብ ደህና ነው …. ደ/ዘ ግን አንድ የሻብያ ሚግ አውሮፕላን መትተን ጥለናል ተብሎ እየተጨፈረ ነው ” አለኝ ። ሚግ ጥለናል የሚለው ጉዳይ ብዙም ትኩረቴን አልሳበም ፤ ምክንያቱም እዚህ ኤርትራ አየር ኃይል ውስጥ እየሰራ ያለ አንድም ሚግ የሚባል አውሮፕላን እንደሌላቸው አውቃለሁና ። ይልቅ የገረመኝ ከአንድ ቀን በፊት ዓርብ ዕለት እዚህ አስመራ ከተማ ውስጥ የመኪና ጥሩንባ እየተነፋ ቅልጥ ያለ ጭፈራና ደስታ ነበር ። ምክንያቱ ደግሞ ሁለት የኢትዮጵያ ሚግ-23 መትተን ጥለናል የሚል ነበር ። ሁለቱም ወገኖች አውሮፕላን መትተው እንደ ጣሉና ህዝባቸውም በደስታ እንዲጨፍር እያደረጉት ነው ። ሁኔታው ሁሉ ናላዬን እያዞረው በመሆኑ ሁሉንም ትቼ ወደ እቤቴ ገባሁና አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ እየተከሰተ ያለውን ትርምስ በአይነ ህሊናዬ እየመረመርኩ እንቅልፍ ጣለኝ ።

 

በነጋታው እሁድ ዕለት ማልጄ በመነሳት ኰ/ል ታደሰ በያዛት መኪና አስመራ አየር ኃይል ቤዝ ቀደም ብለን ደረስን ። የዘመቻ ጊዚያዊ ፅ/ቤት ከምድር በታች የተሰራው ባንከር ውስጥ ስለነበር ወደዚያው አመራን ። ዙርያውን መሬት ላይ በተደረደረው ፍራሽና ምንጣፍ ላይ ቁጥሩ በዛ ያለ ሰው ተኝቷል ። አዛዡ ኰ/ር ሃ/ፅዮን ወደ አለበት ጠጋ ብለን ሰላምታ አቀረብንለት ። አስከትዬም ውስጤን እያስጨነቀኝ ያደረውን ጉዳይ ኰ/ል በዛብህን አግኝቶት እንደሆነ ዓይን ዓይኑን እያየሁ ጠየኩት ። ሃ/ፅዮንም ቁጭትና ንዴት በተቀላቀለበት አንደበት “ አግኝቼዋለሁ …. የማይረባ ሰው ነው  ” አለኝ ። የኰማንደሩን ንዴት እንዳልገባኝ አልፌ “ ግን ደህና ነው ? ምን አለህ ለመሆኑ ” ? አልኩት ። “ በጣም ነው የተሳሳትከው …. እንዴት ትንሽ እንኳ አታስብም …. እንዴትስ በወያኔ ተልከህ ይህንን ትሰራለህ ” እንዳለውና  በዛብህም በበኩሉ “ አንተስ ብትሆን የሰራሀው ጥሩ ስራ ነው እንዴ ? አገር ጨርሰሃል እኰ ? ምን የተረፈህ ሰው አለ ? ብዙ ሰው ተጐድቷል ? አውሮፕላኖች ከጥቅም ውጪ ናቸው .. አንድም የተረፈ በራሪ የለም … ሁለታችን ብቻ ነን የተረፍነው … (እሱንና እንደገናን ማለቱ ነበር) ” እንዳለው ነገረኝ ።  ኰ/ር ሃ/ፅዮንም እየሳቀ መ/አ እንደገና (የኰ/ል በዛብህ ዊንግ ማን የነበረ ወይንም ከኰ/ል በዛብህ ጋር አስመራን ለመደብደብ አብሮት የበረረ ወጣት በራሪ) ትናንት ኰ/ል በዛብህ ተመትቶ ሲወድቅ ብቻውን ወደ መቀሌ ቤዝ ሲመለስ ወያኔዎች የሻብያ ሚግ መስሏቸው በሚሳኤል መትተው ጣሉት …. በጃንጥላ ወደ ምድር ከወረደም በኋላ የሻብያ በራሪ ያዝን ብለው ተሰብስበው ቀጠቀጡት …..  ” እያለ በጅልነታቸው ተገርሞ ጮክ ብሎ ይስቃል ። ማ/ቴክ አርጃ ፔራ ማታ ስለ ደ/ዘ የደስታ ጭፈራ የነገረኝን አስታወስኩና አሁን ኰማንደሩ ከሚነግረኝ አስቂኝ ሁኔታ ጋር አገጣጥሜ እኔም ሳልወድ በግድ ምን ያክል አየር ኃይላችን ወደ ኋላ እየወረደ እንዳለ እያሰብኩ ፈገግ አልኩኝ ። አዛዡ እንዲያውም “ ዘግይቶ የደረሰን ዜና ” በሚል በቴሌቪዥናቸውም አቅርበውታል ብሎ አከለልኝ ።

 

ኰማንደር ሃ/ፅዮን ከኰ/ል በዛብህ ጋር የተነጋገረውንና የሰማውን በመዘርዘር  .. አንድ ሚግ አውሮፕላን ለግዳጅ ወደ አስመራ እያቀና እያለ ባልታወቀ እክል በራሪው በጃንጥላ መውረዱንና አውሮፕላኑ መከስከሱን  የአብራሪው ስም ጨምሮ ነገረን ። 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከህውሃት በኩል 2 ሚግ-21 እና 1 ሚግ-23 አውሮፕላኖች መውደማቸውን ፣ በአየር በተደረገ ጥቃት ከህውሃት በኩል ሁሉም በራሪዎች መቁሰላቸውንና ከአሁን በኋላ አንድም በራሪ ግዳጅ ለመፈፀም የሚችል ያለመኖሩን ሲገልፅ በኩራትና በእርካታ ነበር ። አሁንም እያመነታሁ ቆይቼ “ አንተስ እንዴት ት/ቤት ትደበድባለህ ” ? ብዬ ጠየቅኩት ። ኰ/ር ሃ/ፂዮን ሲመልስም “ እናንተ ሰዎች መቼ እንደምትነቁ አይገባኝም ። እነዚህን ሰዎች (ህውሃት) አስከ አሁን አላወቃችኋቸውም ማለት ነው ። የመጨረሻ ውሸታሞች ናቸው ። የፖለቲካ ትርፍ የሚያስገኝ ከመሰላቸው ምንም ነገር ከማድረግና ከመናገር ወደ ኋላ አይሉም …. ማመዛዘን ፈፅሞ አልፈጠረባቸውም ። የሚያወሩትን ሁሉ ከሰማህማ አብደው ያሳብዱሃል ። እነሱ ያሰቡት የጦር ጀት የላቸውም እንደፈለግን እንቀጠቅጣቸዋለን ብለው ነበር ። እድሜ ለጆቤ ። ጆቤ አዛዥ መሆኑና ያንን አየር ኃይል እንዳልነበረ በማድረጉ ባለውለታችን ነው ። ከሁሉም በላይ የሚገርመኝ ግን እነ በዛብህ በጆቤ የመታዘዛቸው ጉዳይ ነው ። አዛዡ ታዛዥ …. ታዛዡ ደግሞ አዛዥ የሆነባት አገር ። አይነ ስውር አይን ያለውን እንደመምራት ማለት ነው ” አለኝ ። ቀጥሎም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን መበተን በጣም እቃወም ነበር ። አምርሬም አወግዝ ነበር ። ያለውን ዕምቅ ኃይል አውቀዋለሁና ። አሁን ግን እንኳንም አፈረሱልን ። እንኳንም በተኑልን ። ባይበተኑ ኖሮ ምን ይውጠን ነበር ? …. አፈር ከድሜ ያስገቡን ነበር ። ከታሰሩትና ከተሰደዱት ግማሽ ያክሉ እንኳ ቢኖሩ ኖሮ ማን ያድነን ነበር ? ሳይደግስ አይጣላም አይደለም የሚባለው ?

….. በአንድ ወቅት እንደውም የታሰሩት ምንም አላጠፉም ልቀቋቸው … ቢደበድቡም የደበደቡት ሻብያን ነው …. ስለዚህ ፍቷቸውና ለእኛ ስጡን ብያቼው ነበር ። እነሱን ባገኝ ደግሞ ለመላው አፍሪቃ የሚሆን የአቪዬሽን ሴንተር እከፍት ነበር ። እነሱም ያልፍላቸዋል …. ሙያቸውም ሜዳ ላይ እንዳልባሌ አይባክንም ነበር ። ስለዚህ ጆቤ ባለውለታዬ ነው ። በዛብህ ከነጆቤ ቤት ርካሽ ሆነ እንጂ .. የከበረ ዕንቁ ማለት ነው ። ነብይ በአገሩ አይከበርም …. ጆቤ ትልቅ ባለውለታችን ነው ….. የዕውር መሪ …. ” ብሎ ቃላቶቹን ሳይጨርስ ድንገት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ መጡና ጨዋታችን በዚሁ አበቃ ። እኛም ከኰማንደሩ ጋር የነበረንን ጥልቅ ስሜትን ያዘለ ጭጭውውት በዚሁ ቋጭተን ከኰ/ል ታደሰ ጋ ወደ አንድ ጥግ ተጠግተን የራሳችንን ጨዋታ ጀመርን ።

3 ሚግ አውሮፕላኖች ሃያ አራት ሰዓት ሳይሞላ ወደቀ የሚባለው ዕውነት ነው ? ብዬ ኰ/ል ታደሰን ጠየቅኩት ። ኰ/ል ታደሰም ሲመልስ “ትልቁ ኪሳራ ሚግ አይደለም ..  በዛብህ ነው ” አለኝ ። … በመቀጠልም “ መንግስቱ ካሳ የወደቀ ጊዜ አስታውሳለሁ .. አየር ኃይል ጨላማ የዋጠው ያክል ሃዘን ወሮት ነበር  አለኝ ። “ ጥሩ በራሪ ስታጣ ጉዳቱ የቤተሰቡ አይደለም …. የአየር ኃይሉ ነው … የተቋሙ ነው ” በማለት ከልቡ በተቆጨ ስሜት ተናገረ ። “ የሚገርምህ ግን አሁን ጆቤ ጉዳቱን የሚረዳውም አይመስለኝ አለኝ ኰ/ል ታደሰ እንደተቆጨ ።  ” በማስከተለም “ ለመሆኑ የእነ በዛብህ ግዳጅ ምን ለማጥፋት ነው ? ዒላማቸውስ ምንድነው ? ይሄ ሁሉ መስዋዕትነትስ አስፈላጊ ነው ? ”  ። በአጠቃላይ የአውሮፕላኖቹም ሆነ የበዛብህ ለሁሉም ኪሳራ ተጠያቂው ጆቤ ነው ።  በሙያው የተቀመጠ አዛዥ ቢሆን ኖሮ በዚህ ሁሉ ኪሳራ ምክንያት ወዲያው ስራውን መልቀቅ ነበረበት ። አለኝ ኰ/ል ታደሰ አምርሮ ።

ይህ የኰ/ል ታደሰ አባባል ለአስርተ ዓመታት ከአዕሮዬ አልወጣም ። እውነት ነው ደግሞ … ጆቤ በሙያው ሳይሆን በፖለቲካ አቋሙ ነው አዛዥ ሆኖ የተመደበው ። አመራሩም ሆነ ውሳኔው ሁሉ ሙያዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ነው ። እንዲያውም ጆቤ ዘረኛ እንጂ የሰከነ ፖለቲከኛም ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ ። ዘር በመሰረቱ የዜግነት እኩልነትን ያቃውሳል … መጨረሻውም ጥሩ አይሆንም ። ጆቤ በዘር በሽታ የተለከፈ ስለመሆኑ በስሩ በረዳትነት ያስቀመጣቸውን ሰዎች ለአፍታ በአይነ ህሊናዬ ቃኘኋቸው ዙርያውን የራሱን ቋንቋ ተናጋሪዎችን ብቻ ኰልኩሏል ። ይህ አደገኛ ዘረኝነት እንጂ ሌላ ስያሜ ሊሰጠው አይችልም ።

 

ያ ትውስታዬ ዛሬ 18 ዓመታትን አስቆጥሯል ። አስመራ ያለሁበትን ሁኔታ የተገነዘቡ ጓደኞቼ ሊታደጉኝ ወሰኑ ። በጉብኝት አሁን ወደምኖርበት ሰሜን አሜሪካ እንድመጣ ከፍተኛ እገዛ አደረጉልኝ ። ከመጣሁም በኋላ በአገር ቤት ተለይቻቸው እሩቅ ለእሩቅ እንኖር የነበሩትን ባለቤቴንና ልጄን አምጥቼ በሰላም እኖራለሁ ።

ኰ/ል በዛብህ የከፈለው ዋጋ ለአገሩ እንደሆነ አምናለሁ ። ቢያንስ ግን ክብር መስጠት አስፈላጊ ነበር ። በአንድ ወቅት አሉ የተባሉት አርቲስቶች ተሰብስበው አየር ኃይሉን እንዲጐበኙ ተደረገ ። አስጐብኚው ሻለቃም  “ የሞተና የበሰበሰ አየር ኃይል ነው የተረከብነው ” እያለ ደጋግሞ ይገልፃል ። ይህ አባባል እነ በዛብህን ሁለተኛ እንደ መግደል ይሰማኛል ። እንዲህ አይነቱን ሁኔታ አርቲስት ሜሮን ጌትነት “ ጠበል ጓሮ አግኝተው ቁርበት ነከሩበት ” በማለት ትቀኝበታለች ። ይህንን ታሪካዊ ስህተትና ዘለፋ ከአገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጪ ማንም ደፍሮ ቆሞ ሊሞግት ድፍረት ማጣቱ ቢያሳዝነኝም አርቲስት ታማኝ በየነ ረዥም እድሜ ይስጠውና እንባ እየተናነቀው ለቀድሞ የስራ አጋሮቹ እውነታውን በድፍረት አሳውቋል ። በዕለቱ አየር ኃይሉን እንዲጐበኙ የተጋበዙት አርቲስቶችም ይህንን እውነታ ሳይገነዘቡ ይቀራሉ የሚል እምነት የለኝም ። ቢያንስ እነ አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ እነ ጀነራል ፋንታ በላይን ከነሙያቸውና ዝናቸው ያውቁዋቸዋል የሚል እምነት አለኝ ። ጥላቻውና ዘረኝነቱ  ግን ልኩን ማለፉን በቀላሉ ማየት ይቻላል ።

 

በቅርቡም ገቢው ለአየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽን ይውላል የተባለው የአየር ኃይል ታሪክ መፅሃፍ (ስለ ቬትራን ማህበር ያለኝን ጥያቄ ላቆየውና) በአየር ኃይሎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረትን ስቦ ሰንብቷል ። አንድም ቀን ስለተሰደዱት ፣ በችግር ስለሚቆሉት ፣ ስለ ታሰሩት ፣ በእስር ላይ ህይወታቸው ላለፈ ፣ በስደት ህይወታቸው ላለፈ ፣ ስለ ተበተኑት ባለሙያዎች ድምፃቸውን አሰምተው የማያውቁት ሁሉ ዛሬ ሽር ጉድ ሲሉ ይስተዋላሉ  ። ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ .. ይህ ሁሉ የአገር ሃብት የፈሰሰባቸው ባለሙያዎች በከንቱ ሲበተኑ አንድም ቀን ያላስታወሱት ፤ እንዲያውም ሞትና እድሜ ልክ የተፈረደባቸውን የአየር ኃይል አባላት የፍርድ ሰነድ በፊርማቸው ያፀደቁት ፕሬዝዳንት አሁን የአየር ኃይሉ ታሪክ መፅሃፍ ሲመረቅ የክብር እንግዳና ፈራሚ መሆናቸው በእጅጉ የሚያስተዛዝብና ያስደነገጠኝ ክስተት ነው ።

በሸራተን የፊት መስመር ላይ የተሰለፉት ከፍተኛ የአየር ኃይል መኰንኖች አስተማሪዎቻችንና አለቆቻችን ሆነው ሳለ ምንም እንዳልተፈፀመ ፣ ዘግናኙ የብቀላ ጅራፍ ፈፅሞ እንደተረሳና የአየር ኃይሉን ጉዳይ ከብሄራዊ ጉዳይነት ወደ ተራ የግል ጉዳይ ዝቅ ያደረጉት በሚመስል ዓይነት በፕሬዝዳንቱ አማካኝነት የፖለቲካ ስሌት መጫወታቸው ታሪክ በትዝብት የሚመለከተው እንደሆነ ይሰማኛል ።  በመጨረሻም ለዚህ መፅሃፍ እውን መሆን ከመጀመሪያው ጀምሮ በቅንነት ጥረት ያደረጉትን ሁሉ ሳላመሰግን አላልፍም ።

 

ክንዴ ዳምጤ

 

The post ባክኖ የቀረ  አየር ኃይል – ክንዴ ዳምጤ – ሲያትል appeared first on Zehabesha Amharic.

7 ኢትዮጵያውያን በደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ጥገኝነት ጠየቁ

$
0
0

airplane

ህጋዊ መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነድ አልያዙም ተብሏል
– የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአ/አ ስንነሳ ህጋዊ ሰነድ ነበራቸው ብሏል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየርላንድ ርዕሰ መዲና ደብሊን በኩል ወደ አሜሪካ ሎሳንጀለስ የጀመረውን አዲስ በረራ ለማስመረቅ ባለፈው ቅዳሜ ከአዲስ አበባ በመነሳት ባደረገው ጉዞ፣ ተሳታፊ የነበሩ 7 ኢትዮጵያውያን መንገደኞች፣ አውሮፕላኑ ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሲያርፍ ወደ ኢሚግሬሽን ክፍሉ አምርተው ጥገኝነት መጠየቃቸውን አይሪሽ ኢንዲፔንደንት ትናንት ዘገበ፡፡ሁለት ህጻናትን ጨምሮ ጥገኝነት የጠየቁት 7 መንገደኞች በአየር ማረፊያ ጣቢያው ሲደርሱ ምንም አይነት መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነዶችን አልያዙም ነበር ያለው ዘገባው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ግን፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በሙሉ ከአዲስ አበባ ሲነሱ ህጋዊ ሰነዶችን ይዘው ነበር፣ ስለ ጥገኝነት ጠያቂዎቹ የግል ጉዳይ ግን አስተያየት መስጠት አንፈልግም ብለዋል፡፡
አየር መንገዱ ላለፉት ከ40 በላይ አመታት ወደ አውሮፓ አገራት በረራ ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሱት ቃል አቀባይዋ፣ የምናጓጉዘው የተሟላ ህጋዊ የጉዞ ሰነድና ተገቢ ቪዛ ያላቸውን መንገደኞች ብቻ ነው ሲሉ መናገራቸውንም ዘገባው ገልጧል፡፡አንድ የአገሪቱ የህግ ክፍል ቃል አቀባይም የተለያዩ አገራት መንገደኞች በደብሊን አየር ማረፊያ ጣቢያ ሲደርሱ ጥገኝነት መጠየቃቸው የተለመደ የዘወትር ክስተት ነው፣ ባለፈው አመት ብቻ 221 መንገደኞች ለትራንዚት አርፈው ጥገኝነት ጠይቀዋል ብለዋል፡፡

The post 7 ኢትዮጵያውያን በደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ጥገኝነት ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

በምርጫው ውጤት ሊተላለፉ የተፈለገው መልእክት ምንድን ነው?። (ዳዊት ዳባ)

$
0
0

Friday, June 26, 2015

ዳዊት ዳባ

electionምርጫው ወያኔ በሚፈልገው እንደውም ባቀደው መንገድ አጠናቋል።  “እረጭ ያለ ምርጫ”። እስከቅርብ ጊዜ እንዲደርሰን የተደረገው መረጃ ምርጫውን በመቶ ፐርሰንት ማሸነፋቸውን ነበር። አሁን ለይቶለታል። በመቶ ፐርሰንት ማሸነፋቸውን ብቻ ሳይሆን በተወሰኑት ምርጫ ጣቢያዎች ላይ አገኘንም የሚሉት ድምጽም በተመሳሳይ መቶ ፐርሰንት እንደሆነም ነው። ሌብነቱ እንዳለ ሆኖ ምርጫውን ከዚህ በተሻለና በሚመስል መንገድ ከውኖ በመንግስትነት ለመቀጠል መሞከሩን  የሚያውቁት ነበር።  አልፈለጉትም እንጂ መቶ ከመቶ ከሚለው በተጓዳኝ አሁንም እንደ አንድ አማራጭ  አይተውት ነበር ብሎ በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። የሩቆቹ ነጮቹ አለቆቻችንም  የተሻለ ብለው የመከሩት ይህንኑ እንደነበረም እየሰማን ነው። ታዲያ ለምን? መቶ በመቶውን ምርጫቸው አደረጉት።

 

አንደኛው ምክንያት ነገሮችን ከተለመደው በጣም ባፈነገጠ መንገድ ማድረጉን ደጋግመው ተጠቅመውበት ፍቱን የሆነ መላ ሆኖ ስላገኙት ነው። አሁንም ይህው መላ ህዝብን ተስፋ በማስቆረጥ ተገዥነቱን ለማስቀጠል የጠቅማል ብለው ስላሰቡ ነው። ሁለት በአገር ውስጥ የሚደረገውን በይበልጥም ሰላማዊ የሆነውን ትግል ማከርከርያ ለመምታት ነው።

 

መታወቅ ያለበት ተገዥነትም ሆነ ገዥነት የጭንቅላት ጨዋታ አለበት። ትክክል ናቸው አይደሉም የሚለውን እናቆየውና  ለሀይሉ እራሱን ፍፁም በሆነ ሁናቴ ያስገዛው አገሬው ነው ብለው ሰዎቻችን ያምናሉ።  ይሄን ምርጫ ያከናወኑበት ጠቅላላ ሁናቴ ይህ እምነታቸው ምን ያህል ስር የሰደደና  ለውሳኔያቸውና ለድርጊቶቻቸው ሁሉ መሰረት  መሆኑን ነው የሚያሳየን። በዚህ 24 አመት ውስጥ ተመሳሳይነት ያላቸውን ድፍረትና ንቀት ያለባቸውን ተግባራቶች  ብንዘረዝር  ከአንድ ሚሊዬን ምክንያቶች ውስጥ የዚህ ምርጫ ውጤት አንዱ ብቻ ሆኖ  ነው የምናገኘው።  ስልሳ ጀነራሎች ካንድ ዘር ሶሙ ስንል ሌላ ስልሳ ጀነራሎች አሁንም ከራሳቸው ዘር ሾመዋል። ተገዥ አድረገንዋል የሚለው እሳቦት ለውሳኔ ዋንኛ መሰረት እስከሆነ  ተገዥ እንደሆንን እንድንቀጥል ጉልበታቸውን አግዝፈው ማሳየት ደግሞ  አለባቸው። መቼም ልናሸንፋቸው የማይቻለን እንደሆነም ደጋግመው ሊያስታውሱን ግድ ይላል። በተጓዳኝ ደግሞ የትኛውንም አይነት የኛመገዳደር ኮስሶ እንዲታይ  ማድረግ ደግሞ አለባቸው። አይቀጡ ቅጣት የሚያስቀጣም ተደርጎ እንዲወስድም ይፈለጋል። ለማንኛውም ይህ ሁሉ አዲስ አይደለም ሗላ ቀር ተብሎ የተተው ነው እንጂ ድሮ በባርያ ስረአት ዘመን ባርያ ለማሳደር ሲጠቀሙበት የነበረ ነው።

 

መቶ በመቶ አይነት እርምጃ በዋናነት ተገዝቶልናል ብለው ከሚያስቡት ህዝብ በላይም ማማ የሆናቸው ክፍል እንደተሸከመ እንዲቀጥል በእጅጉ አስፈላጊ ስለሆነም ነው። ጦሩ፤ካድሬው፤ የፓርላማ ምናምንቴው፤ አንድ ለአምስት የተደራጀው፤  አጋር በሚል በየዘሩ ያሰባሰቡት…። ፈቅደው ተጠቃሚ አደረጉት እንጂ  ያው ተገዥቸው አድርገው ነው የሚያዩት።

 

ይህ ሰው ያንድ አውራጃ አስተዳዳሪ ነው። ባለቤቱን ቀድሞ ውጪ ልኳል። አሁን ላይ እፎይታ ሊሰማው አልቻለም። በዚህ ምርጫ ሰበብ ስራ በዝቶበት ጭንቅም ላይ ነው የሰነበተው።  ከነልጆቹ ከቤቱ ለቆ በመሳርያ የሚጠበቅ ቦታ ከቶ ነበር። ልጆቹን በመሳራያ እያስጠበቀ ትምህርት ቤት ማመላለስ ድረስ ፈርቷል። በደወለ ቁጥር እነዚህን ልጆች ከዚህ በቶሎ ማውጣት እንዴት አቃተሽ። የዚህ አገር ሁኔታ አይታመንም። አስፈሪ ነው። አንድ እራሴን ሁኔታዎች ሲብሱ ወደጎረቤት አገር በቶሎ መሻገር እችል ነበር። እነዚህ ልጆች ግን ምን አድረጌ። ሲያለቃቅስ ነው የከረመው።

 

ስርአቱ ውስጥ የዚህ ግለሰብ አይነት እጅግ በዙ ናቸው። የዚህ አይነቶቹ በእርግጥም መቶ ከመቶ ካልሆነ ባነሰ ውጤት በጭራሽ አይፀኑም።  ዋናው ነገር ቁንጮዎቹ እዚህ ድረስ ያሳስባቸዋል። ያስባሉም። ልብ ልንለው የሚገባ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ትንሽ ለቀቅ አድርገው ቢሆን  ዘንድሮ እኛም የተዘረፍነው ድምፅ  ጨምረንም  ነፃነታችንን መጠየቃችን አይቀርም ነበር። በመቶ በርሰንት

 

እንዳሸነፉን ሲነግሩን ደነገጥን። መቶ በመቶው በዚህ አኳያም እንደሚጠቅም አስበውበታል ማለት ይቻላል። በተጨማሪም  በሰላማዊው ትግል ውስጥ ድርሻ እያደረጉ ካሉ ዜጎች ውስጥ የተገኘውን ያህል ተስፋ ቆርጠው አብዛኞቻችንን የሚመስሉ ከተገኙም የሚለው  አለበት።

 

Graham Peebles አሳምሮ ገልፆታል።

 

The recent election was an insult to the people of Ethiopia, who are being intimidated, abused and suppressed by a brutal, arrogant regime that talks the democratic talk, but acts in violation of all democratic ideals.

 

“ፈላጭ ቆራጭ አንባገነን ሆናችሁ ያለምህረት ስትቀጠቅጡ የኖራችሁትን ህዝብ ምርጫ ተደርጎ እኛን መረጠን ማለት ስድብ ነው። እናውቃችሗለን  ስለዲሞክራሲ ትቀደዳላችሁ ነግር ግን አንዳቸውን  የዲሞክራሲ እሴቶች እንኳ ማክበር የተሳናችሁ ደናቁርቶች ናችሁ።”

 

{ይሄ አሸነፍን ለዛውም በመቶ ፐርሰንት የሚለው ለይልቃል ወይ ለሰማያዊ፤ ለመድረክ ወይ ለመራራ ነው ካልን በትልቁ እራሳችንን እየሸነገልን ነው። ትግሉም ካኛ ጋር ነው። መልክቱም ለኛ ለዜጎች ነው።}

 

ሁለተኛው በአገር ውስጥ የሚደረገውን ሰላማዊውን ትግል ለማድቀቅ ከተቻለም እስከመጨረሻው ለማጥፋት ነው። ስርአቱ ድርጅቶችን እስከነብሳቸው እየበላ ነው። ብዙ ሺ ሰላማዊ ታጋዬች እስር ቤት ነው ያሉት።። በስቅላት መግደል ሁሉ ጀምረዋል። ባአጠቃላይ ሰላማዊ ትግሉን ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ታጋዬችን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ ነው የሚመስለው። ለነገሩ በቅጥቀጣ የሚጠፋ ቢሆን ኖር ድሮ ይጠፋ ነበር። ስለዚህም በተጓዳኝ አይሰራም ብለን እንድናምን ማድረግ አለባቸው። ይህንን ነው ያደረጉት።  የሚቀጥለውን የምርጫ ድራማ ካሁኑ የመስራትም ጉዳይ አለበት። ሰይብል ነው ያሉት ሰርተውታል ማለት ይቻላል።

 

ሰላማዊውን ትግል በተመለከተ ደግሞ ግማሹን ስራ በርትተን  ለረጅም አመታት እኛም ስንሰራበት ነው የከረምነው። ስለዚህም በቀላሉ ተፈጻሚ ሊሆን የሚችል ሆኖ ታይቷቸዋል። የድርሻችንን ማድረጉን ዛሬም ቀጥለናል። አጉልተን አገር ውስጥ የሚደረገው ሰላማዊ ትግል አይሰራም፤ አያስፈልግም ማለት የጀመርነው  ከምርጫ 97 ማግስት ነው። ይህው ላለፈው አስራ አንድ አመት አካባቢ እየተለዋወጥን ሰርተንበታል። አንዱ ቡድን ሲደክመው ወይ መሳሳቱን አውቆ ሲተወው ሌላው እየተቀበለ እስካሁን ቀጥሏል። ዛሬ የጉጀሌው የኛም ጥረት ተደምሮ ሰላማዊ ትግል አያስፈልግም የሚለው የብዙዎች እምነት ነው። እንደውም ሰላማዊ ትግል አይሰራም የሚለው ይዘቱን ቀይሮ መታገል አያስፈልግም ወደሚለው አድጓል። እግዚአብሔር እንዳመጣቸው እሱ አንድ ነገር ያድርግ ብቻ አይደለም በተፈጥሮ በሂደት ታመውና አርጅተው ይሞታሉ የሚባሉ አነጋገሮች መስማት የተለመደ ሆኗል።

 

የተዘራው ነው የሚታጨደው።

 

 

 

ደቡብ ኦሞ ደራሼ ውስጥ በጊዶሌ አውራጃ መምረጥ የሚችለው የህዝብ ቁጥር 11773 ለለምመረጥ የተመዘገበው 646 ነው። ንብን የመረጠ 431፤ ጃንጥላን 171፤ ሌላ ሰምቼው የማላውቅ ድርጅትን 44 ህዝብ ነው የመረጠው። በሌሎች ምርጫ ጣብያዎች ውጤት ቢገለጽ ከጊዶሌው ብዙም ልዩነት የሚታይበት አይመስለኝም። ምን አልባት በኦሮሚያ ክልል በተወሰነ ደረጃ ልዩነት ሊኖረው ይችላል።የምርጫው እለት በቀጥታ ስርጭት በፌስ ቡክ፤ በሳይቶች በመወያያ መድርኮች ስለምርጫው አፈፃፀም  ይተላለፉ የነበሩ የቀጥታ ምስክርነቶችን ስሰበስብ ነበር። ባብዛኛው ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ካርድ የወሰዱና ሊመርጡ የወጡት  አንድ ላምስት የተደራጁ ደጋፊዎች መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ነበር በብዛት የሚመጣው።

 

ይህ ስኬት ከተባለ መቼስ ማል ጎደኒ ብቻ ነው ማለት የሚቻለው።  ይሄ ቁጥር ግን የሚያስፈራ ነው። መጀመርያም ቢሆን የሀይሉ አማራጭ ውጤታማ የሚሆነው በሰላማዊው ትግል መቃብር ላይ ነው የሚለው በጥንቆላ ይሆናል እንጂ እስራተጃዊ ሆነ ፖለቲካዊ ፋይዳው ተሰልቶ የተደረሰበት አይደለም። ይህ ተስፋ መቁረጥን እንጂ ተሳትፎ በመንፈግ የማሳጣት ትግልም አይደለም። ሲጀመር ካገዛዙ ባህሪ አኳያ የማሳጣቱ ትግል በዋናነት ፋይዳው እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ በሁሉም ወገን ስምምነቱ አለ። ከባድ ያደረገው ይህንን አይነት አቋም እንድንወስድ ያደረጉን ገፊ ምክንይቶች የተሳሳቱ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ዘርፈ  ብዙ የሆኑ ተጓዳኝ ጉዳዬችን አካቶ የተያዘ አቋም ባለመሆኑ ነው። መስሎን ነው እንጂ የጎዳነው ባጠቃላይ ትግሉን ነው።  በዋናነት በሀይል የሚደረገውን ትግል። ንቁ ድርሻ ምርጫውላይና ሰላማዊው ትግሉ ላይ ከነበራቸው ዜጎች ነው የመሳርያውን ትግል እየተቀላቀሉ ያሉት። ሰላማዊ ትግሉን ዜጎች በሚሊዬኖች ጉዳዬ ብለው ይዘውትና ተሳትፈውበት ቢሆን ኖር ትግሉ ወደ ህዘባዊ እንቢተኛነት የማደግም የተሻለ እድል ነበረው። እረጭ ያለ ምርጫ ሲያቅዱ እረጭ ማድረግ ነው መዳኒቱ ትግል አይደለም።

 

ስለተጠያቂነት ከሆነ ምርጫ ያልነው ተጠያቂነትን በዋናነት መውሰድ ግድ ይልብናል።  ምርጫውን እንደ መብቱም እንደ አንድ ትግልም መወስድና ተሳትፎ ማድረግ ይገባቸው የነበሩ   ዜጎች በዚህ ደረጃ በማነሳቸው።  የነበሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ አስገብቶም  ቢታይ ልንሰራቸው ይገቡ የነበሩ ነገር ግን ያልሰራናቸው ስራዎች ብዙ መሆናቸውን አጋላጭ ነው። ተጠያቂነቱ በተዋረድ ይቀጥላል። ህዘብም ቢሆን በማኩረፍ ሆነ ተስፋ በመቁረጥ ጠብ የሚል መብት የለም። ቀላል የሆነው የዚህ አይነት ትግል ላይ እንኳ ድርሻ ለማድረግ አቅማችን የተሟጠጠ ዜጎች እዩት የሰራነውን።

 

“If there is no struggle, there is no progress. Those who profess to favor freedom, and yet depreciate agitation, are men who want crops without plowing up the ground. They want rain without thunder and lightning. They want the ocean without the awful roar of its many waters. This struggle may be a moral one; or it may be a physical one; or it may be both moral and physical; but it must be a struggle. Power concedes nothing without a demand.It never did and it never will.”
Frederick Douglass

 

“ትግል ከሌለ የሚሻሽልና የሚለወጥ ነግር የለም። ነጻነትን አብዝተው እያሹ ምንም አይነት አስተዋፆ ለማድረግ ተነሳሽነት የሌላቸው ሰዎች ሳያርሱ አዘመራን ማጨድ የሚጎመጁ አይነት ናቸው። ነጎድጓድና መብረቅ የሌለበትን ዝናብ ያልማሉ። ማእበል የሌለበትንም ውቂያኖስ እንዲሁ። ተገደው ካልሆነ ገዥዎች ፈቅደው የሚሰጡት ጠብታ ነፃነት የለም። አይኖርምም። መገደዱ አለባቸው። ማስገደዱ በሀይል ይሆናል ወይም ተሽሎ በመገኘት። ወይም በሁለቱም። የግድ ግን መታገል አለብን።”

 

ለነጻነት ለሚደረገው ትግል ወገንተኛ የሆኑ የበዙት መገናኛዎች ምርጫውን በሚመለከት ለጥፋቱ ድርሻቸው ከፍ ያለ ነው።  ሀላፊነት አለመወጣት ብቻ ሳይሆን አፍራሽ ሚናቸው የጎላ ነበር ባይ ነኝ። ይህንን ለማሳየት አስቤው የነበረው በትንሹ ከምርጫው ሶስት ወር በፈት ጀምሮ በጣም ካነሰም አንድ ወር ውስጥ ሽፋን የተሰጣቸውንና የተሰራባቸውን ቁምነገሮችን ሁሉ በዝርዝር በሰንጠረዥ ማስቀመጥ ነበር።  አንገብጋቢነቱ፤ አንድምታው፤ ህዘብ እንዲወስደው የተፈለገው የጠራው መልእክት። ቃላት ምርጫው። ሆን ብሎ ማንኳሰስ ነበር አልነበረም?። ተስፋ አስቆራጭ ነበር አበረታች?። ምርጫው ውስን በሆነ የጊዜ ሰሌዳ የሚካሄድ ነው። አጥኖትና ቀዳሚነት አግኝቷል አላገኘም?። በምርጫ ቅስቀሳው የነበረ ድርሻ ካለ። የመሳሰሉት ወሳኝ ጥያቄዎች  በማንስት መገናኛው የነበረውን  አስተዋፆ ማሳየት ነበር። በዚህ እሳቦት ሳዳምጠው ሳገላብጠው ስቦረብረው ስለነበር ተልቅ የሆነ የጥፋት ድርሻ እንደነበራቸው ግልጽ ብሎ ማየት ችያለው። ክሴን ከዚህ በላይ ላመረው እችል ነበር። ቢቸግር ነው እንጂ ይህም በራሱ ዱላ ማቀበል ነው። ልተወው።

 

አገር ውስጥ የሚደረገውን ትግል እንደግፋለን የሚሉ ድርጅቶችና ድጋፍ ማህበራትም ሀላፊነታቸውን ባግባቡ አልተወጡም። መሽኮርመም ይታይባቸው ነበር። ለታሪክ መዝገብ ቤት የሚቀመጥ አቋም መግለጫ ከመጻፍ የዘለለ አልነበረም አስተዋፆቸው። ይህን ያህል የሰው ድርቀት አለ ወይ ነው የሚያሰኘው። የተያዘውን አቋም እንኳ በካሜራ ፊት መናገር ታቡ ነበር። የፖለቲካ ትግል  መናገርን አብዝቶ ይፈልጋል።

 

እንደዚሁ ተጠያቂነቱ ይቀጥላል አብያተ እምነቶች ህዝብን ወደአምላክ መመለሱ አንድ ነገር ነው። የግድ የተራበና ነጻነት የሌለው  ባርያ መሆን ግን የለበትም። ይህ ክፉ ስራ ነው። አምላክም አይደሰትበትም።  ስርአቱን አያገለገላችሁ ያላችሁ ዜጎች በይበልጥም ቀለም የቀመሳችሁ ሁሉ  መቶ ፐርሰንት  ህዘብ አሸነፍኩህ እንዲባል አድርጋችሗል። ይህ ንቀት ነው። ይህ በህዝብ ላይ ማላገጥ ነው። ለዚህ ድርሻችሁ የጎላ ነውና የደረስንበትን ደረጃ እስቲ ቆም ብላችሁ እዩት።

 

ወያኔ እንዳቀደው ምርጫው እረጭ ያለ እንዲሆን እገዛ ያደረጉ ሌሎች አስተሳሰቦች።

  • ትግል መሆኑ ቀርቶ ምርጫ ስለተባለ ብቻ ፍታዊ ምርጫ ይደረግና ድምጽ ተሰጥቶ፤ ጠብ ሳይል ድምጽ ተቆጥሮ አብላጫ ድምጽ ያገኛ ስልጣን መያዝ አለበት። ይህ ካልሆነ ምን ያደርጋል። የሚገርመው ይህንን የምንጠብቀው ዛሬም ከወያኔ ነው።

 

  • የሚገለውም የገደለውም ምርጫ ጫወታ ውስጥ ስለምትገቡ ነው። ይህ ሲታገሉ የሞቱትንና የታሰሩትን ተጎጂ አድርጎ ማየትና ነገ የሚገደሉትን አስገዳይ አሳሳሪ አድርጎ መፈረጅ ድረስ ይሄዳል። ይሄ ፍርደ ገምድል መሆን ብቻ አይደለም ጭካኔም ነው።

 

  • በምርጫው የታሰተፉ እውነተኛ ተቃዋሚዎች የመጨረሻ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል እንዴትም እንደሚመጣ ምንም ብዥታ በጭራሽ አልነበራቸውም። አይደለም ለራሳቸው ለህዘብ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አስረግጠው ሲናገሩት በጥረታቸውም ሲገልፁት የነበረ ነው። ይህ በሆነበት እያወቁ ለምን ተሳተፉ የሚለውን ጥያቄ ቆም ብሎ ለሰከንድ እንኳ ለማሰብ አለመፈልግ። በቃ  ለስልጣን ነው ብሎ መደምደም።

 

  • ትግል የሚያካሂዱበትን ነባረዊ ሁኔታ በጭራሽ ግምት ውስጥ አለማስገባት። ፍቃድ ጠይቀው የሚሰለፉት ፈሪዎች ስለሆኑ ነው።  ትግሉን ከሰላማዊ ወደ ህዝባዊ እንቢታ ያላሳደጉት እየተቻለ ስለሚፈሩ ነው። በመንግስት ታውቀው በግላጭ እየሰሩ መሆኑ እየታወቀ በሚስጥር የማይደራጁት እየቻሉ ነግር ግን ጥቅሙ ስላልታያቸው ነው።  አቅምና ጉልበታቸውን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ በዛ ላይ ድርሻም እገዛም በሌለበት ውጤትና ተግባር አብዝቶ መጠየቅ። ሲጀመር ታጋዬች ለህዘብ ወይስ ህዘብ ለታጋዬች ነው ጉልበት መሆን የሚገባቸው። በሁለቱም አቅጣጫ ያስኬዳል ብንል እንኳ እስከ ድክመቶቻቸው እነሱ  መራራ መሰዋትነት  እየከፈሉ ትግሉን ቀጥለዋል። እኛስ?።

 

 

አገር ቤት ያሉ ሰላማዊ ታጋዬች ምርኩዝ የያዘ የተቀዳደደ ድሮቶ የለበሰ ባዶ እግሩን የሚሄድ ሽማግሌ ቢሆን እንኳ በርታትና ጉልበት ሆነነው፤ አፅድተን ሱፍ አልብሰነው አሸናፊ ማድረግ  መናቃችን ግድ ይለዋል። ፍቱንም ነው።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

The post በምርጫው ውጤት ሊተላለፉ የተፈለገው መልእክት ምንድን ነው?። (ዳዊት ዳባ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ፀሃፍ፦ አሰባሳቢ ማንነት፣ ባንድ ሃገር ልጅነት የኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ፀሃፊ፦ ዩሱፍ ያሲን ምስክርነት፦ (በጥላሁን አፈሣ)

$
0
0

Download (PDF, 162KB)

Yasu Yasinመንደርደሪያ ሃሳብ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ይመስለኛል። “For Love of Country: Debating The Limits of Patriotism” በሚል ርዕሥ እንደ ኤውሮፓ አቆጣጠር(“እ.ኤ.አ”)በ 1996 ዓ.ም፣ የተጻፈች አንዲት ትንሽ መጽሐፍ በርዕሷ ተስቤ፣ ከአሮጌ መጽሃፍት ተራ ገዝቼ ያነበብኩት። እዚች መጸሃፍ ላይ ለሰፈሩት የተለያዩ ምሁራን አስተያየቶች መንስኤ የሆነችው፤ Martha Nussbaum የተባለች ታዋቂ ምሁር፣ ከዚች መጽሃፍ እትመት ሁለት ዓመታት ቀደም ብላ፣ “Patriotism and Cosmopolitanism” በሚል ርዕስ በቦስተን ሪቪው ላይ ያሳተመቻት አንዲት 25 ገጾች ያዘለች መጻጽፍ ነበረች። ፕሮፌሰር ኑስቦም፣ በጽሁፏ ላይ ያሰፈረችው አሟጋች አስተያየት ባጭሩ ሲጠቃለል፦ ያለንባት ዓለም እየተዋሃደች በመጣችበት በአሁኑ ዘመን፣ በተለምዶ ከያዝነው ጠባብ የአገር ወዳድነት (patriotism)እምነታችን ተላቀን፣ እራሳችንን በሰው ዘርነታችን ብቻ የምንገልጽበት የአንዲቷ ዓለማችን ዜጎች (cosmopolitan)አርገን መቀበል ይገባናል ነበር የሚለው።

—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

The post ፀሃፍ፦ አሰባሳቢ ማንነት፣ ባንድ ሃገር ልጅነት የኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ፀሃፊ፦ ዩሱፍ ያሲን ምስክርነት፦ (በጥላሁን አፈሣ) appeared first on Zehabesha Amharic.

እነዋሽንግተን ፖስት የኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት አብጠለጠሉ – Addis Admass

$
0
0

Obama Ethiopiaአለማየሁ አንበሴ

“የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ስለዲሞክራሲ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል”

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በቀጣዩ ሐምሌ ወር ኢትዮጵያን ይጐበኛሉ መባሉን ተከትሎ ታላላቅ አለማቀፍ ሚዲያዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቸ ተቋማት ተቃውሞአቸውን እየገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ ፕሬዚዳንቱን እንዲመጡ የሚያደርጋቸው የአገራችን የውስጥ ስኬት ነው ሲል ተቃውሞውን አጣጥሎታል፡፡ የኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትን ርዕሰ ጉዳያቸው ካደረጉ የአሜሪካ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው ዘ ዋሽንግተን ፖስት በርዕሰ አንቀፁ ባሰፈረው ተቃውሞ፤ “የኦባማ ኢትዮጵያን መጐብኘት ስለዲሞክራሲ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል” ብሏል፡፡ በእንግሊዝ ከፍተኛ ተሰሚነትና ተነባቢነት ያለው ዘ ጋርዲያንም ጉብኝቱን አስመልክቶ በርዕሰ አንቀፁ ባሰፈረው ሃተታ፤ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ዲሞክራሲያዊ ላልሆኑ ስርአቶች እውቅና መስጠት ነው ሲል ክፉኛ ተችቷል፡፡ ኦባማ ጋናን በጎበኙበት ወቅት፤ “መጀመሪያ የምንደግፈው የተጠናከረ ዲሞክራሲያዊ መንግስትን ነው” በሚል የተናገሩትን ዘንግተውታል ያለው ዋሽንግተን ፖስት፤ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ኢትዮጵያን የመሳሰሉ በሰብአዊ መብት ረገጣ ለሚታሙ ሃገራት እውቅናና ከለላ መስጠት ነው ሲል ተቃውሟል፡፡ “በቅርቡ ሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ የመንግስት ሽግግር ያደረገችው ናይጄሪያን የመሳሰሉ በዲሞክራሲ ጐዳና ላይ እየተጓዙ ላሉ ሀገራት እውቅና መንፈግ ነው” ሲልም የታቀደውን የኢትዮጵያ ጉብኝት ጋዜጣው አብጠልጥሎታል፡፡ ጉብኝቱ ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን የዘመናት ግንኙነት እንዲሁም ሃገሪቱ በቀጠናው ያላት የፀጥታ አስከባሪነት ሚናና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገቷን ታሳቢ ያደረገ ነው መባሉን ያስታወሰው ዋሽንግተን ፖስት፤ የሀገሪቱ መንግስት በዚያው ልክ ነፃ ሚዲያ የማያበረታታ እንደውም ያሉትንም እያጠፋና የፖለቲካ ጫናዎች እያሳደረ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሶ ጉብኝቱን ተቃውሟል፡፡

ባለፈው ዓመት ከሰኔ ወር ጀምሮ 34 ጋዜጠኞች ከሀገር እንዲሰደዱ መደረጋቸውን ጋዜጣው ጠቁሞ፣ ሃገሪቱ ጋዜጠኛ አሳሪ በመባል ከሚታወቁ የአለም ሀገራት በቀዳሚነት መሰለፏን ጠቅሶ የኦባማን ጉብኝት ተችቷል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዊንዲ ሸጋርማን በቅርቡ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት “ኢትዮጵያ ዲሞክራሲዋን እያጠናከረች ነው፣ የምታከናውነው ምርጫም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው” የሚል ምስክርነታቸውን በሰጡ ማግስት፣ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የምርጫ ውጤቱን ከ99.6 በመቶ ወደ መቶ በመቶ ማሳደጉ፣ ዲሞክራሲውን ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል ሲል ነቅቷል ዋሽንግተን ፖስት፡፡በዘንድሮ ምርጫ ተቃዋሚዎች እንግልትና እስራት እንደተፈፀመባቸው፣ አለማቀፍ ታዛቢዎች ምርጫውን እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን፣ በምርጫው ማግስትም ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩ ፖለቲከኛ እንደተገደሉ የጠቀሰው ጋዜጣው፤ ሆኖም መንግስት ስለተገደሉት ሰዎች ኃላፊነት አልወሰደም ብሏል፡፡ የተረጋጋ፣ ሰላማዊና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ያካሄደችው ናይጄሪያ እያለች ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ለለውጥ ላልተዘጋጀው የኢትዮጵያ መንግስትና ለአሳፋሪው
የምርጫ ውጤት እውቅና መስጠት ነው ያለው ዋሽንግተን ፖስት፤ ለአፍሪካውያንም ዲሞክራሲ ጠቃሚ አይደለም የሚል መልዕክት ያስተላልፋል ሲል ጉብኝቱን አጥብቆ ተቃውሟል፡፡ ታዋቂው የእንግሊዝ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን በበኩሉ፤ የኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት ለጨቋኝ መንግስት ስጦታ ነው ሲል ፅፏል፡፡ “ሃገሪቱ በኢኮኖሚ እያደገች ቢሆንም በዜጎች ሰብአዊ መብት አያያዝና በፕሬስ ነፃነት እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ በኩል ተወቃሽ ነች፣ የዲሞክራሲ ተምሳሌት ልትሆንም አትችልም” ብሏል ጋዜጣው በርዕሰ አንቀፁ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም የፕሬዚዳንቱን የኢትዮጵያ ጉብኝት አበክረው ተቃውመዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ምርጫ በአፈና ስር ያለ የፖለቲካ ልምምድ ነው”

ያለው ‹ፍሪደም ሃውስ› የተሰኘ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ቡድን፤ የኦባማ ጉብኝት ለፖለቲካና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መቀጨጭ አጋርነትን ማሳየት ነው ሲል በመግለጫው ተችቷል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ አንዳንድ ወገኖች የኦባማን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እየተቃወሙ መሆኑን እንደሚያውቁ ጠቁመው፤ ፕሬዚዳንቱን እንዲመጡ የሚያደርገው የሀገራችን የውስጥ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

“የኦባማ መምጣት ትልቅ ትርጉም አለው” ያሉት አቶ ሬድዋን፤ ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን ለመጐብኘት የማቀዳቸው ሚስጥር የኢኮኖሚ እድገቱ እንዲሁም ሀገሪቱ ለሠላም እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ ስኬታማና አይነ ግቡ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡ “በ112 አመታት የዲፕሎማሲ ታሪክ የአሜሪካ 44ኛው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን መጐብኘት ትልቅ የገጽታ ግንባታ ይኖረዋል፤ ቤታችን መጽዳትና መሞቅ መጀመሩንም ያረጋግጣል” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

Source: Addis Admass Newspaper

The post እነዋሽንግተን ፖስት የኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት አብጠለጠሉ – Addis Admass appeared first on Zehabesha Amharic.

መስፍን በዙ! የጥላሁን ገሠሠ ሌጋሲ ወራሽ ወይስ አደር-አፋሽ ?

$
0
0

tamagne beyeneስሜነህ ባዘዘው

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ እዚሁ አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ለሽልማት መታጨቱን ስሰማ በጣም ነበር ደስ ያለኝ። ይገባዋል!!! ብያለሁ።
ወዲያው ደግሞ በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ላይ “ታማኝ በየነ ሽልማት አይገባውም!” የሚሉ ሁለት የሱማሌ ወጣቶች ተቃዉሟቸውን ሲያሰሙ የሚያሳይ የቪዲዮ ክሊፕ አየሁና ገረመኝ። ተቃዋሚዎቹ “እንዳለቀ ቢራ ጠርሙስ” አንገት አንገታቸው ተይዞ እዳሪ ሲጣሉ ስመለከት ደግሞ ልቤ እስኪፈርስ ሳቅኩ። ከእንዲህ አይነቱ ውርደት ይሰውራችሁ….

የሱማሌዎቹ የተቃውሞ ምክንያት፤ የክልላችን ፕሬዝዳንት አሜሪካ በመጣበት ወቅት ተቃውሞ አደራጅቶ ያዋረደብን ታማኝ ነው ! የሚል ነበር ። ጉዳዩ ግን ሌላ ነው …
በዚሁ ክሊፕ ላይ ሱማሌዎቹ ወጣቶች ልብሳቸው የታኘከ እስኪመስል ተጨመዳደው ከአዳራሽ ከወጡ በኋላ ይህን ተቃውሞ ያቀነባበረው መስፍን በዙ የሚባለውን የወያኔ መሽሩፍ ተቀባይ ሰው እንደ ናዝሬት በርሜል እየገፉ ሲያስወጡት ተመለከትኩ። መስፍን የሚሉት ሰው ለምን ይሄን አደረገ? ለሚለው ወደ ኋላ ልመለስበትና በተቃውሞው ይዘትና በተቃዋሚዎቹ ማንነት ዙሪያ ጥቂት ልበል።

መስፍን በዙ የሱማሌ ወጣቶችን ቀጥሮ ለተቃውሞ ያሰማራው ሌላ ተባባሪ ስላጣ ይመስለኛል። ታማኝን ለመሸለም በታደመ ወገን መሃል ቆሞ በታማኝ ላይ ተቃውሞ ማቅረብ ምን ሊያመጣ፤ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ የተረዱ ሌሎች የወያኔ ቅጥረኞች መስፍንን ሊተባበሩት አልፈለጉም። ጎመን በጤና ብለውታል ።እናም “ጣጣ” የለንም የሚሉትን የሱማሌ መርቃኞች የበርጫ በጥሶ አሰማራቸው። እንዳሰቡት ሳይሆን ከጣጣም ጣጣ ገጠማቸው።

ይህ ሰው(መስፍን በዙ) የጥላሁን ገሠሠ የመጨረሻ የትዳር ጓደኛ (የመጀመሪያም ብቸኛም አለመሆኗን ለማመልከት ነው) ወንድም በመሆኑ ብቻ የጥላሁን ገሠሠ ሌጋሲ ወራሽ ሆኖ ለመታየት የሚያደርገው ሩጫ በጣም የሚገርም ነው። ሲጀመር፤ ጥላሁን የሕዝብ ልጅ ነው።ወራሹም አሳታዋሹም የኢትዮጵያ ህዝብ ነው።ሲቀጥል፤ የግድ የቅርብ ወራሽ ይኑር ከተባለም በመጀመሪያ ረድፍ የሚቀመጡት ልጆቹና የልጆቹ እናቶች በሙሉ ናቸው። ከመጀመሪያ የትዳር ጓደኛው እስከ መጨረሻዋ ..
መስፍን በዙ በመጀመሪያው ረድፍ ካልተቀመጥኩ ብሎ የሚሟዘዘው ለምን እንደሆነ የማይገባኝም ለዚህ ነው። የጥላሁን ገሠሠ የመጨረሻ ሚስት ወንድም መሆኑ ልዩ የአደር-አፋሽ ወራሽነት መብት ያሰጠው ይሆን?

mesfin-bezu-tg-tv ድሮ..! ድሮ..! ልጅ ሆነን ቆርኪና ብይ ደርድረን ስንጫወት፤ ተጫዋቹ ሁሉ በየተራ ይሞክር ይሞክርና እያንዳንዱ እንደችሎታው ያገኘውን(የበላውን) ይወስዳል። በመጨረሻ
ላይ የሚሞክረው ግን በሙከራው ካገኘው ውጭ ያደረውን(ሳይበላ የቀረውን) ቆርኪ ሁሉ ሰብስቦ ይወስዳል። እናም “መስፍን በዙ የጥላሁን ሌጋሲ አደር-አፋሽ ወይስ ወራሽ? ” የሚለውን ጥያቄ ለርዕስነት የመረጥኩትም ለዚሁ ነው። ሌላ ምን ልበል ….?
ለነገሩ ይህ ሰው የወያኔ ቅጥረኛ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች በገሃድ በማሳየቱ አካሄዱና እንቅስቃሴው ሁሉ ምንና ለምን እንደሆነ ለማንም ይጠፋዋል አልልም። ይሁንና እንደ መብት ካየነው ያሻውን መደገፍ መብቱ ነው። መብቱ ያልሆነው በጥላሁን ገሰሰ ስም በከፈተው የቴሌቪዥን ጣቢያ መነገድ ነው። የጥላሁን ቤተሰቦች(ልጆቹ) ቢያንስ የቴሌቪዥን ጣቢያውን ስም እንዲለውጥ ማስደረግ አለባቸው የሚባለውም ለዚህ ነው።

ጥላሁን የህዝብ ነው ስንል። በጥላሁን ጉዳይ ሁላችንም ያገባናል ማለታችን ነው። ስሙ እንዲከብር እንጂ ታሪኩ እንዲመዘበር አንፈቅድም። ጥላሁን እንባ ከጉንጮቹ እየተቀዳ ሃገሩን ዘክሯታል። ሃገሩም በክብር ትዘክረው ዘንድ ይገባል። ሃገር ማለት ደግሞ ህዝብ ነውና በጥላሁን ጉዳይ ኢትዮጵያዊው ሁሉ ያገባዋል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የአብራኩ ክፋይ የሆኑት ልጆቹ የበለጠ ያገባቸዋል። ለዚህም ነው የጥላሁን ልጆች ይህን “አደር አፋሽ” አድብ! የማይሉት ለምንድነው? የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው።
አደር-አፋሹ መስፍን ስለ ታማኝ በየነ ብዙ ብዙ ይላል። ታማኝ ጥላሁንን በድሏል ሲል ይወተውታል። እኛ ያየነው ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ በህይወት ሳለ “ታማኝ ከልጆቼ የማለየው ልጄ ነው” ሲል ለልጆቹ መመስከሩን ነው። የጥላሁን ገሰሰ ልጅ ንጹህ ብር ጥላሁን አባቷ የሰጣትን የጣት ቀለበት ለታማኝ በየነ አሳልፋ ስትሰጥ የመሰከረቺውም ይህንኑ ነው። ቀለበቱም የታማኝና የጥላሁን አባትና ልጅነት ቃልኪዳን ነው።

አደር-አፋሹ ፦ የሚነግረን ግን በጥላሁን የመጨረሻ ሰዓት የአማችነት ቅርበት ስለነበረው ወራሽም፤ አስታዋሽም፤ዘካሪም፤መስካሪም እሱ እንደሆነ ነው ። እኔ ደግሞ

• መስፍን በዙ ሆይ! አንተ የጥላሁንን ስም አስነዋሪ እንጂ ዘካሪ አይደለህም።
• የጥላሁን ሌጋሲ አደር-አፋሽ እንጂ ወራሽም አትሆንም።እለዋለሁ፦ አደራ እናተም እንደኔ በሉት!
መስፍን በዙ ጥላሁንን በዊልቸር ላይ ከዋለ በኋላ ኮንሰርት ሊያሰራው ፈልጎ ታማኝ በየነ “ጥላሁን በዊልቸር ላይ ሆኖ አይዘፍንም፤ ይዝፈን ከተባለም አርቴፊሻል እግር ገብቶለት ይዝፈን እንጂ በፍጹም ለገንዘብ ተብሎ ይህ አይሆንም” በማለቱ ከዶላር ወዳዱ መስፍን በዙ ጋ እንደተጋጨ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች አጫውተውኛል፡፤
መስፍን በዙ አፍቅሮተ-ንዋይ የተጠናወተው ስለመሆኑ ደግሞ ለነፍሰ ገዳዮች ተቀጥሮ በሚሰራው ሞራል የለሽ ስራ መረዳት አይከብድም። እናም አደር-አፋሹ መስፍን ጥላሁን በዊልቸር ላይ ተቀምጦ ኮንሰርት ቢሰራ የሚገኘውን ዶላር እንጂ በጥላሁን ላይ ሊደርስበት ስለሚቸለው የሞራል ጉዳት ሊያስብ እንደማይችል ስለምረዳ ከታማኝ ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባቱም አይገርምም።
የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው የወያኔ መንግስት በረጅም ሰንሰለት አስሮ ዲያስፖራ ውስጥ የለቀቃቸው ጥቂት የማይባሉ ውሾች የግንባር-ሥጋ ሆነው ሥርዓቱን በሚቃወሙ ወገኖች ላይ ሁሉ ለመጮኽ ሲሞክሩ በተለያዩ አጋጣሚዎች እያየን ነው። መስፍንም በታማኝ ሽልማት ላይ የሞከረው ነገር ከዚህ የተለየ አይደለም። ጌቶቹ የታሰረበትን ሰንሰለት አጠር ሲያደርጉበት የታማኝን ዱካ እየተከተለ ይጮሃል፤ ሰንሰለቱን አስረዝመው ሲለቁት ደግሞ ኢሳት ላይ ለመጮህ ይሞክራል(እንዳቅሚቲ)። ሰሚ አለው ወይ? ሌቦች ሊሰሙት ይችሉ ይሆናል። የውሻን ጩኽት ልብ ብሎ የሚሰማው ሌባ አይደል?

በመጨረሻም፦የጥላሁን ገሰሰ የአብራኩ ክፋይ ለሆኑት ልጆቹ አንድ ጥያቄ አለኝ? ለመሆኑ የአባታችሁን ከወርቅ ጸዳል የሚያበራ ታሪክና ስራ በአግባቡ መዘከር እንኳ ባትችሉ፤ ስሙ የፖለቲካ መነገጃ እንዳይሆን መከላከል ለምን አቃታችሁ? ችግሩ ምንድነው? ጥላሁንና ፖለቲካ ምን አገናኛቸው ብላችሁ ለምን አትጠይቁም?።ይህን “አደር-አፋሽ ወራሽ” ከጥላሁን ገሠሠ ራስ ላይ እንዲወርድ የማድረግ የደምም የሞራልም ሃላፊነት አለባችሁና ከተወቃሽነት ለመዳን አንድ ነገር ታደርጉ ዘንድ ይገባል እላለሁ። በተረፈ እመኑኝ የመስፍን በዙ ዕውቀትና ችሎታ አልባ ሩጫ ራሱንና ምናልባትም…. ከማዋረድ በስተቀር ማንንም አይጎዳም እያልኩ በነኚህ ስንኞች ልሰናበታችሁ!
ያቅበጠብጠዋል አዱኛ ርቆበት!
ማጀቱን ጠብቁ የእጅ አመል አለበት!

ቸር እንሰንብት
ስሜነህ ባዘዘው
semenehbazezew@gmail.com

The post መስፍን በዙ! የጥላሁን ገሠሠ ሌጋሲ ወራሽ ወይስ አደር-አፋሽ ? appeared first on Zehabesha Amharic.


የጓጐሉ –ጉሞች –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ  27.06.2015 / ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ /

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

የእስልማና ዕምነት ተከታይ እህቶቼ አሜሪካን ሀገር በነበራቸው ጉባኤ ላይ „የታሰርነው እኛ ነን“ ሲሉ ቅኔ – ተቃኙ። እውነታቸውን አኮ ነው። የፍላጎታችን አባጣ ጎራባጣነት የወጎኖቻችን ዕንባ እንዳይቆም ማነቆ ሆኗል። በዕዬለቱ የሚሰማው ባለቤት የለሹ መርዶ ትንፋሻችን – ሆኗል። በዬትኛውም የሀገራችን ችግር፤ በዬትኛውም የዓለም ክፍል ቤተ – ግፉዕኑ። ልብሷን የለበሰ፤ እናቴ እማማ ብሎ የጠራ ወንጀለኛ – አሸባሪ – አክራሪ – ጽንፈኛ ተብሎ – ይሞታል፤ ይታሰራል፤ ይደበደባል፤ ይዋረዳል፤ ይሰደዳል። የፍላጎታችን ቅንጡነት የወገኖቻችን ዕንባ እንዳይቆም ማነቆ መጋኛ ሆኗል። በዕዬለቱ የሚሰማው ባለቤት የለሹ መርዶ ትንፋሻችን – ሆኗል። በዬትኛውም የሀገራችን ችግር፤ በዬትኛውም የዓለም ክፍል ቤተ – ግፉዕኑ ኢትዮጵያውያን። ኢትዮጵያ ዛሬ ልጆቼ ብላ ከመከራው ሁሉ እትብቶቿን ልትታደግ እንዳትችል እሷም እስር ቤት ናት። ልብሷን የለበሰ፤ እናቴ እማማ ብሎ የጠራ ወንጀለኛ – አሸባሪ – አክራሪ – ጽንፈኛ ተብሎ – ይሞታል፤ ይታሰራል፤ ይደበደባል፤ ይዋረዳል፤ ይሰደዳል።

ዛሬ ኢትዮጵያ ባርነት ውስጥ በከፋ ቅኝ ግዛት ውስጥ ትማቅቃለች። ልጆቿ ዕንባቸውን ማፈሰስ ተክልክለው እንደ ልጅ ዋጥ! ዋ! ሱ! እዬተባሉ በስጋት ተሰንገው በዓለም የሌለ እውሃ ያዘለ መከራ ተሸከመው ይገኛሉ። ዛሬ ለኢትዮጵውያን በ21ኛው ምዕተ ዓመት ዴሞክራሲ የድሎት ጥያቄ ነው። የነፃነት ጥያቄ በባሩድ ነዶ አመድ እዬሆነ ነው። ቁጭ ብሎ አንገትን ደፍቶ ሰቀቀንን ታቅፎ ከመኖር – ይህም ሞት ሌላውም ሞት በመሆኑ የቆረጡት ትግላቸውን በስልታቸው መርጠው ሁሉን በመቀበል ላይ ይገኛሉ። ዘመናይነት ደግሞ የነፃነት ትግል የጫጉላ ሠረጋላ ስለሚመስለው አጋጣሚ እዬፈለገ ህይወቴን – ነፍሴን – ትዳሬን –  ወጣትነቴን እሰጣለሁ ያሉትን ደምና ሥጋዎች፤ ለሥነ – መንፈሳቸው ፍጹም ጥንቃቄ ሳያደርግ ያለ ርህራሔ በወረፋ፤ በፈረቃ ይደበድባቸዋል። ዘመናይነት በእጅ በሌለ ነገር ላይም – ለነገ በቀነ ቀጠሮ ባለ ዬምንዕብም ትልም ሙያተኛ (plan analyser) ሆኗል። ለነገሩ እሱም ነፃነት ፈላጊ ነኝ ባይ ነው።  – ሃቁ ግን እንቅፋት መፍጠር፤ በነፃነት ትግሉ ላይ የቅንጣት ታክል ጉድፍ ማስቀመጥ የነፃነት ትግል ፍላጎትን እራስን ብልዛም ውይባም ማድረጉን ካለማገናዘብ የመነጨ – ይመስለኛል። ሰው አካሉን እንዴት እንደ ተለጣፊ – ያዬዋል። ቀዝቃዛ። መንፈሱን ጠረኑን … በረዶ። ዋ! ኢትዮጵያ — ስለአንቺስ ማህፀኔ አለቀሰ – ደም።

ትኩረቱ በመሰረታዊ ምክንያታዊ ጉዳይ ሳይሆን በሳቢያ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ በዬወቅቱ የሚያነሳው ተዋጊ ሃሳብ መጠለያ ፈልጎ የሚለቀቀወ የተቀበረ ፈንጂ ሲሆን ዕንባን እንዲቀጥል እንጂ የቅንጣትም በጠላት ጎራ ላይ የሚስገኘው ትርፍ የለም። የዕንባው ስቃይ እርቆት ሆኖ ይሆን? አቅምን በይው ሃሳብ የውስጥነትን አቅም በባዕድነት ሲያስተናግድ? + ቁስለት። የነፃነት ትግሉን ካለ አቅሙ ካለወርዱ ቻል እዬተባለ እዬተጫነ ዘብጦ እንዲሰምጥ ለዛውም በዘመቻ – ተያይዞታል – በአድማ ፍታውራሪ ዘመናይ፤ ባላንባራስ ቅልጣን። ከቶ ህሊና የሚባለው ጸጋ ዬት ተደበቀ ይሆን? ከአቅሙ በላይ ነው የተሸከመው የነፃነት ትግላችን። ሌላ ዘመቻ ሌላ ጦር እንዴት ይታዘዝበታል —- ተስፋችን ? ? ? ይሄ ትናትን የበላ የበኽር ቁምነገር እዬጠፋ — እዬተረሳ … በገፍ የተሰጠ ዬነፃነት ትግሉ ቤተኛ ህዝበ – ፍቅር እዬተምዘገዘገ — ወይ ሐገር? ወይ ሰንደቅ? ወይ ማንነት? ወይ የህዝብ ፍቅር?

ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንደጦር የሚፈራው ነገር ለነፃነት ፈላጊው ጣዕሙ፤ ወዙ መሆን ይገባዋል እንጂ፤ እንደ ገደል ማሚቶ የጠላትን ፍላጎት መልሶ ማስተጋባት ከአደራ በይነት ምንም አይተናነስም። መራራውን ነገር ደፍሮ ኃላፊነት ወስዶ መጀመር ትርፍ ብቻ ይገኘዋል ተብሎ ሊታሰብም – አይገባውም። ከሙሉ ኪሳራ ጥቂት ኪሳራን መምረጥ – ብልህነት ነው። እርግጥ የዲሞክራሲ መንፈስ መለማመዱ የማይከፋ ቢሆንም፤ እራስን እንደ ድልህ እዬደቆሱ፤ በራስ ላይ አመድ ነስንሶ እራስን ወደ ቡላማ መለወጥ የተገባ – አይመስለኝም። የተሻለውን ለማግኘት በተሻለ አቀራረብ እራስን ሳይሰነጥቁ ወይንም ሳይፈልጡ ወይንም ሳይነጠቁ የዴሚክራሲን መንገድ መለማመድ – ይቻላል። ለነገሩ እኛ እኮ ውጪ ስላለን ባርነቱ ቀርቷልን መሰሎን ሊሆን ይችላል። ግን እኛም ባሮች – ጭቁኖች ነን። እንደ ፈለግን መኖር ያልተፈቀደልን፤ የተዋረድን ወጥ ሰንደቅዓላማ፤ ወጥ ብሄራዊ መዝሙር የሌለን። ሁሉን – የተቀማን። በማናቸውም ሁኔታ በወያኔ ሃርነት ትግራይ የዓይነ ቁራኛ ጥበቃ ሥር – የወደቅን። ስለዚህ መጀመሪያ እራሳችን ነፃ እናውጣ … ከዛ ዴሞክራሲ ከሚያስገኛቸው በረከት የተነፈግነውን ማንሳትና መጋፋት ይቻላል። ያም ሌላ የለውጥ አብዮት ነው። ለነገሩ ጊዜን ያላዳመጠ ክስተት ጊዜውን ጠብቆ አድራሻ ቢስ ሆኖ – ያከትማል። አጀንዳዎችም የፍቀት ታሪክ ባልደረባ – ይሆናሉ። አንድነት መድረክን በተቀላቀለበት ጊዜ የታዬው እሰጣ ገባ ዛሬ ደግሞ አገርሽቶ የግንቦትና የአርበኞች አሃቲነት በፈቃደ እግዚአብሄር መፍትሄ ሲያገኝ ቁርጥማት ሆነ። ውጋት ሆነ። መጋኛ ሆነ። አርበኞች ግንባር ይህን ተቀብሮ የኖረ ትብትብ ጥሶ የወሰደው እርምጃ ሁሉንም  በማዕከል ሆነን ለምንታዘብ ሰዎች ልዑቅ መሆኑን በሰማናቱ በተመዘዘበት ዘመቻና ግንባር ግብዕት ማወቅ ችለናል። ለምን በወጥ አመራር ሰከነ ነው – ጦርነቱ። „ስንተዋዋቅ …“ ይላል ጎንደሬ።

ሌላው ቀርቶ ከአዋሳኝ ቀያቸው ሁለመናቸውን ጊዜ በሰጠው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ እዬተነቀሉ ወደ ኤርትራ የሚሄዱት እንዛ ጭቃ ለበስ ድሃ ወገንህን እንዴት ጦር ታውጅባቸዋለህ?! ያሳፍራል አቤዋ። አፈር ቅሞ፤ አፈር ለብሶ፤ ራህብ የቆላውን፤ ንዳድ ያንገበገበውን ወገንህን ለመግደል ከዛ ድረስ ከምትሄድ አቤዋ በለው እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዝ አለሁልህ ና እና ድፍት አድርገኝ።  የእነሱን መከራ ፈቅጄ መቀበል ጽድቅ ነው – ለእኔ። በአንዲት ቁራጭ ሰኔል 6ቱ ተደራርበው ቀን የለበሷትን አፈርማ እራፊ ለብሰው የሌሊቱን ግርማ እንደሚያስታግሱ በዬቀያቸው ተገኝቼ – አይቸዋለሁና። ያ በዝቶባቸው ነው ዛሬ ቁሙ ተቀመጡ የሚባሉት – የሚሰደዱትም። እንዴት እንዳዘንኩብህ? እንደ አንተ አዝኘበት እማውቀው የነፃነት ትግል አባወራ የለኝም። ፆም ነው ሱባኤ – አለቀስኩ። ያ ህዝብ መቼ አልፎለት አውቆ ነውና አንተ ባሩድ ለማጉረስ የተዘጋጀኽው? ጎንደሬ በጋሻውን – አንብብ። ትንሽ መንፈስና ትንፋሽ ከቅድመ አያቶቻችን – ታገኝ ዘንድ። ተንትርሰው እንዳደሩት የሽንት ጨርቅ ኩፍትርትር – ጭምትርትር ያለውን የዘመቻህን መነሻና መድረሻ ጊዜ ወስጄ አዳመጥኩት – ለካንስ ለስቃይም አንተም ሆንክ መንፈስህ ሽፍታ ነበራችሁ ማለት ነውን? መተማ አዋሳኝ ላይ የሱዳን ሰራዊት ፊት ለፊት የወያኔ ሰራዊት በስተጀርባ ወገንህን ሲበላ በግፍ ረመጥ ከቶ ህመሙ ርቆህ ይሆን? የአርማጭሆ – ዬወልቃይት – የጠገዴ – የማይጸምሪ – የአዲረመጽ – የዋልድባ ወዘተ አፈር ገፊና ቅዱሳን ተነቅሎ ተገፍቶ መሰደዱስ? የመረቀዘ ምን እንደሚታፋ – ታውቀዋለህ። አዋሳኝህ ጓንጉም ሲሞላና ሲጎድልም ታውቀዋለህ …. በቅርቡ ያለውንም ረመጥ … ህሊናህን – ጠይቀው በአክብሮት። መብራትህን – አጠፋኸው፤ ታሪክህን  – ተዳፈርከው፤ አንተን – አጣኽው … ለመሆኑ ቦሌ ዱር ገደል ከሆነ አንተ ለምን ተሰደድክ? አሁንስ ማን አገደህ? በሞቴ ሞክረውና ተያዩ እንዴት እንደሚጥም —— ከዛ ጀግንነትህ በዝናር ሙሉ ገድል ይጣፍልሃል። ለመኮለሙ እኔ እህትህ ዬት ሄጄ?! ግን – ግን የተፈረደበህን የወያኔ ሃርነት ትግራይ አነሳልህን? ይህም እኮ አለ ለካ – አዬ! የእኔ ነገር ይህን ረስቼው ….  ህግ ወደ ኋላ ሄዶ አዬ አላዬ በህግ አልቦሹ ዘመን ቅጥ የለሽ ቅድ ነው – የዘበጠ። ሹክታ – በሽክታ ካለ ብዬ ነው። 80ውንም ቦጫጭቀህ ከመቅደድህ በፊት አንተ እራስህን ከልብህ ሆነህ  በመስታውት – አስተውለው! መልክህን ደግመህ እዬው – ትእዛዝ ግን አይደለም። እኔና እኔ አብረን ስንቀመጥ ፈራጁ ህሊና ይደኘናል። አበበ በለውን እንዴት አበበ በለው ከዳው? እንዴትስ አበበ በለው ከአበበ በለው አፈነገጠ? ጎሉን ያስገባኽው የመሰለኽ በአርበኞች ግንቦት ነው። አይደለም በዕንባ ላይ ነው የጥቃት ምት እዬሰነዘርክ ያለኸው። ሃሳቤን ታገሉት ብለህናል ምን እኛ ዕንባ – ዕራቁትነት – የሰብዕዊ ፍጡር አካል ጭስ የነሰማዕቱ ጋር የሃሳብህ የተሳለ ሰይፍ – ይፋለም። እንደ ከፋኝ እንደ አማጥኩኝም ያ … ጸጥተኛውና ያሳደግኽ ቻዩ ጣና የትእግስት መንፈሱን ያቀናልህ ዘንድ ተመኘሁ። በል አቶ ወንድም ሌሎቹ ተዛማጅ የተደሞ ዕዬታዎቼ መሄድ ግድ አለኝ —

ውዶቼ  የኔዎቹ እንሆ … በአክብሮት – በትህትና – በፍቅር – በናፍቆት። ጉሹን ጓጓላውን ያፍታታል ብዬ ወደ አሰብኩት ተዛማጅ የተደሞ ዕዬታዎቼ – አብረን።

ሰላማዊ ትግል አብቅቷልን?

ሰላማዊ ትግል የዕድሜ ዘመን – የለውም። ሰላማዊ ትግል ሁልጊዜም ህያው ነው። የሰው ልጅ ከራሱ – ከመንፈሱ፤ ከራዕዩ፤ ከፍላጎቱ፤ ከገጠመኞቹ ጋር የሚያደርገው ግብግብ የሰላማዊ ትግል አካል ነው። እኔ ስጽፍ ከራሴ ጋር ቁጭ ብዬ መክሬ – ዘክሬ፤ እመሰርዘውን ሰርዤ፤ እማስተካክለውን አስተካካይ ስሜቴን ታግዬ ግን የታዳሚዎቼን ቀልብ አስልቼ ነው። የምፈልገውን ሁሉ – አልጽፈውም። ከድኜ ያስቀምጥኳቸው አምክንዮች አሉኝ። ስለምን? ወቅትን ማድመጥ የተገባ – በመሆኑ። ይህ ሳይሆን ሲቀር ደግሞ ግድ ሲል ትንሽ ገለል አድርጌ ወይንም ዘንበል አድርጌ – እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ሥርጉተና ብዕሯ፤ መንፈሷና ርዕዮዋም በሰላማዊ ትግል ማዕድ ላይ ናቸው ማለት ነው። ኑሮና መኖር ሁልጊዜ እንደተፋለሙ ነው። ውሳኔና ጭብጥም እንዲሁ … ፍ – ት – ጊ – ያ

በሰላማዊ ትግል ህዝቦች ከባርነት ከወጡ በኋላም የዴሞክራሲ ጥያቄ ያነሳሉ። የዴሞክራሲ ጥያቄ ከተመለሰላቸው በኋላም ቢሆን ወቅት በሚፈጠርባቸው ችግሮች ዙሪያ፤ የተዛቡ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን አንስተው በተናጠል – በግል – በጋራ ድምፃቸውን – ያሰሙበታል። በማይቋረጥ ሁኔታ የሰው ልጅ መንፈሱ ካፈለቃቸውና ዘመን ከለገሰው መልካም ነገሮች ሁሉ እኩል ዕድምተኛ ይሆን ዘንድ – ታዳሚዎችን ለማነቃቃት የሚካሄድ ትዕይንት ነው ሰላማዊ ትግል። ፈተና አለው ሁለገብ ግን … ይኬድበታል። ዕውቅና እስኪያገኝ ድረስ። ዓይነት የወጣለት – ደፋርም ነው።

ስለሆነም የአንድ ሀገር ህዝብ እንደ ህዝብ እንዲሻሻል የሚፈልገውን ህግ ሆነ የአፈጻጸም መመሪያ እንዲሁም በህዝብ ድምጽ ውሳኔ እንዲያገኝ የሚሻቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች ከመጠዬቅ ባሻገር፤ አፈፃጸማቸወን በባለቤትነት ከመከታተል ለአፍታም ቸል አይልም። ይህ ራሱ የሰላማዊ ትግል አካል ነው። አፈፃፀሙን – መከታተል። መቆጣጠር። ስለዚህ የሰላማዊ ትግል ሰዓት ማለት ነው። ሰዓት አያቆምም ሁልጊዜ – ይጓዛል። አይደክምም ሁልጊዜ – ይሄዳል። ተቆጣጠሪያችንም ነው። ሰላማዊ ትግልም ወቅት – ጠቀም፤ ህዝበ – ጠቀም፤ ዘመን – ጠቀም የምልዕት የተሳትፎ ማዕድ ሲሆን፤ የሰው ልጆች ፍላጎት ማለቂያ የሌለው በመሆኑ ልክ እንደ ሰዓት ደንበር ወይንም መከተሪያ ሥነ – አምክንዮ የለውም።። እንኳንስ በእኛ በጥቂቶች የብሄረሰብ የጭፍን አገዛዝ ወደ ምዕላቱ ፍላጎት ለመሸጋገር፤ ከባርነት ነፃ የመውጣት የመጀመሪያ የትግል ረድፍ ላይ የምንገኝ – ቀርቶ፤ የአደጉ ሐገሮችም፤ ዴሞክራሲን ተግባር ላይ ዘውድ ደፈተንለታል በሚሉት ሀገሮች ላይም በማያቋርጥ ሁኔታ የብዙኃኑ ጥያቄ ጎልቶና ጎልምሶ በህዝብ ትዕይንት – ይገለጽበታል። ትውናውም በሰላማዊ ትግል – ይፈረጃል። ሰላማዊ ሆኖ ግን ጉልበትና ብስጩነትንም ሊያስተናግድ ይችላል። ገዘፍ ያሉ ቁጣዎችን አንግቦ ቀለል ያሉ የቁስ ጥፋቶችን ሊያሰከትል – ይችላል። ከበድ ያለም ህይወትን ሊገብር – ይችላል፤

ሰላማዊ ትግል ሂደቱ እጅግ አስቸጋሪ የሚያደርገው ጉዳይ በሙት መሬት ላይ ትግሉን ስለሚያካሂድ ነው። ስለዚህም ዬዘርፈ ብዙ ጥቃቶች ሰለባ የመሆን ዕድሉም የሚመነጨው ሙት መሬት ላይ ሆኖ፤ ገዢ መሬት ላይ ያለውን ሃይል ስለሚታገል ነው። አብሶ እንደ እኛ በዘር በተቋጠረ ቂም – ተከል አስተዳደር ላይ የሚካሄደው ትግል እጅግ – አሰቃቂ፤ ሰቅጣጭ ሲሆን ኑሮው ሆነ ህይወቱ በመከራ – በመራር ሃዘን የተለወሰ – ጎምዛዛ።

ሰላማዊ ትግል ውስጥ የማይነኩ – የማይዳሰሱ –  የሚተዉ – ቀነ ቀጠሮ የሚያዝላቸው ዬህዝብ ፍላጎቶች አይኖሩም፤ ወይንም የሚዘነጉ ምንም ዓይነት የብዙኃን ጥያቄዎች፤ ወይንም ሙቅ ስሜቶች፤ ወይንም ጽኑ እምነቶች – አይኖሩም። ይህ በመሆኑ ጥያቄውን የሚፈራው ሥልጣን ላይ ያለው ሃይል ማናቸውንም እርግጫ፤ ማናቸውንም ኢ – ሰብዕዊ ጭፍጨፋ – ይፈጽምበታል። የታላቁ ፍጡር ዬሰው ልጅ ደም የመጀመሪያው በረከት ነው – መቋደሻ። አብሶ እንደ እኛ ባልሰለጠነ ቅድመ ሰው እድገት ደረጃ ላይ በሚገኝ ጫካዊ አስተዳደር በምትመራ ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄድ ትግል ዕለታዊው ስንቁ ነው – ደም መፍሰስ። አሳዛኙና እጅግ መራሩ ጉዳይ ደግሞ ከደብደባው፤ በስለት ከመወጋቱ፤ ከመሞቱ በላይ ተበዳዩ ተወቃሽ – ተነቀሽ ከመሆን አልፎ ሥሙ በግፍ – መገረፉ ነው። ሊቢያ ላይ የታረዱ ወገኖቻችን ሞተው እንኳን ዜግነታቸው፤ ሰማዕትነታቸው ከወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ ሥር ወድቆ ነበር የለመነው። መራር ነው። በማግሥቱም ባዕለ ሲመት ድምቅ ብሎ ተክብሯል። ሃሞት። ይህም ብቻ አይደለም ሀዘኑን የተጋራው ሁሉ ዜግነቱን በግፍ የተቀማበት የከሰለ ሂደት እያዬን ነው። ምግለት። ሃዘንን አምቆ ቢይዙት በሽታ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ውስጥን አሳርሮ – ያረግፋል። ወጥቶ ሲጋፈጡት ደግሞ ማገዶነት አይቀሬ ነው። የሆነ ሆኖ የሰላማዊ ትግል ከትንሹ ጥያቄ እስከ ግዙፉ የፖለቲካ ሥልጣን ጥያቄ ድረስ በሚያደርገው ጉዞ ሙት መሬት ላይ፤ በቅርበት ለችግሮች ስለሚገኝ አብዝቶ የመከራ፤ የፍዳ የስቃይ ህይወትን – ፈቅዶና ወዶ ይገፋበታል። ጥያቄው መልስ እስካላገኘ ድረስ ሰላማዊ ትግሉ – ይቀጥላል። በደሉ እስካለ ድረስ ሰላማዊ ትግሉ – ይቀጥላል። ህይወት እስከለ ድረስ፤ ኑሮ እስካለ ድረስ – እንዲሁ። ምርጫ ላይ ሰላማዊ ትግሉ ያቀደው አልተሳከም ተብሎ የሰላማዊ ትግሉ አባላት እጃቸውን አጣጥፈው – አይቀመጡም።

ነገ ሌላ አዲስ ቀን ነው። ማግሥት ሌላ ልዩ የተስፋ ቀን ነው። ስለዚህ የሰላም ታጋይ አርበኞች የቀደመውን መከራ አስተናግደው ለሌላ መከራ ደግሞ ትጥቃቸውን ጠበቅ አድርገው – ይሰናዳሉ። ለሌላ መስዋዕትነት – ይሰለፋሉ፤ ለሌላ ስቃይ – ይባትላሉ፤ ለሌላ አሳር – ይተጋሉ። ስለሆነም እነሱ የሰላማዊ ትግልን ሁለገብ መርህ ተከትለው ደከመን፣ ሰለቸን፣ መረረን፣ በቃን እሳካላሉ ድረስ እኛ ትግሉ አብቅቷል፤ የማለት ሞራሉም – አቅሙም የለንም። መከራን እንደ ስንቃቸው የተቀበሉት እነሱ እያሉ፤ እኛ የለም አቁሙ በማለት ለሰላማዊ ትግሉ የስንበት ወረቀት የመስጠት መብቱም ሞራሉም አይኖረንም። ይህ የጓጎለ ጉማዊ ፍላጎት ነው – ለእኔ። ሰላማዊ ትግል እንደ ዳቦ የሚያልቅ – አይደለም። የሰላማዊ ትግል ሩኹ የማያቋርጥ፣ ተከታታይነት፤ ተያያዥነትና ተወራራሽነት ያለው ሲሆን፤ በሁሉም ዘርፍ ሁለንትናዊ ፍላጎትን አማክሎ መጠነ ሰፊ ህዝብን በማስተባበርና በማደራጀት ለራዕዩ መትጋት ግድ – ይለዋል። ሰላማዊ ትግል ሁሉዬ – የሁሉዬም ነውና።

ዬምርጫ 2007 አለመሳካት፤ ወይንም እሱን ተከትሎ የደረሱ በደሎችና ግፎች የበለጠ ጥንካሬና እልህ ፈጥረው ለዘላቂ ነፃነት ስንቅና ትጥቅ በመሆን እውነትን ለትግሉ ለግሶ – ይገሰግሳል። በሂደቱ የሚሾልክ ሊኖር – ይችላል። ነገር ግን ቀጣይ ህይወቱን ጽኑ እምነት በመንፈሳቸው የሰነቁ ትጉኃን ትግሉን በመምራት ግብር ከፍለው፤ አስራት ሆነው ኢትዮጵያን ከትግራይ ወያኔ ሃርነት ባርነት የማላቀቁ ትግል ማቆሚያ ገደብ፤ መካተሪያ አውታር ሊበጅለት አይገባም ብለው፤ እንደሚቀጥሉት ተስፋዬ ብሩኽ ነው። በስልት – በብልሃት – በስልጡን መንገድ – ይቀጥሉታል። እርግጥ አጣብቂኞች በርከትም ከረርም – ሊሉ ይችላሉ። ነገር ግን በዝምታም አመጽ – ይኖራል። ባለመተባበር አመጽ ሊኖር – ይችላል። ፊት በመንሳት ማመጽ – ይቻላል። ፍቅርን በመንፈግ እንቢተኝነት ሊኖር – ይችላል። ልብንና መንፈስን በማሸፈት በቃኝን ኮትኩቶ ማሳደግ – ይቻላል። ቤተ እግዚብሄር ውስጥ በተመሳሳይ ደቂቃና ሰከንድ በደወል ማናወጽም፤ አላህ አክብርን በመሰሉ መከወንን ሊያካትት ይችላል። ሙቀቱ ግርፊያውን ቀጥሎ ከባህር የወጣው አሳው የጎሳ ድርጅት ወያኔ ሃርነት ትግራይ ትንፋሽም ነፍስም ያጣና ስምጠትን ሊጠመቅ ይችላል።

በሌላ በኩል ውጪ ሀገር የሚካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች፣ የሚሰበሰቡ ፊርማዎች፤ የሚላኩ ደብዳቤዎች፤ የሚዘጋጁ ውይይቶች፤ የሚደረጉ ቃለ ምልልሶች፤ ፊልሞች፤ ዶክመንተሪ – ዘገባዎች፤ ማህበራዊ ሚዲያዎች፤ ድህረ ገፆች ራዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፤ ሁሉ በሰላማዊ ትግል የሚታቀፉ ናቸው። አቁሙ ለማለት የማይስችሉ ጭብጦችም የሚነሱት ከነዚህ የፈለቁ የዕውነት ድባቦች አባልተኛ ስለሚሆኑበትም ጭምር – ይሆናል። ሌላ ጊዜ እርእስ አስይዤ ብመጣበትም ዛሬ ትውፊታችን፣ ሃብታችን፣ የእኛነታችን ሃምሌት የነበረው የሞራል ህግ ተሸርሽሮ – ተሸርሽሮ ድብዛው እዬጠፋ ነው። ሰላማዊ ትግል በነዚህ ሁሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የሆነ ኃላፊነት – አለበት። በተለይ የሰፊውን ህዝብ ኑሮውን – እዬኖሩ፤ መከራውን ሁሉ በቅንነት እያስተናገዱ የሚገኙት ሀገር ቤት የሚገኙት የሰላማዊ ትግል አርበኞቻችን አትኩረተ – አቅጣጫ ከበፊቱ በተሻለና በሰለጠነ ሁኔታ ዬትውልዱን መንፈስ በብሄራዊ ስሜት፤ በትውፊታዊ ቃናዊ ማዕዶት ላይ ያተኮሩ ህሊናዊ ተግባራት የመከወን ጉዳይ የሰላማዊ ትግል ልዩ ኃላፊነት ነውና በመርህ ደረጃ ሊያተኩሩበት ይገባል ባይም ነኝ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ያልዘረፈን አንዳችም ነገር የለም፤ አሁን በእንቁላል ውሃ የተገነባው የመተማመን፤ የጽናት በኽረ፣ ሥህን ናሙና የነበረው የአብሮ አደግነት የልጅነት ልዩ ፍቅር፤ ልዩ ጣዕም ያለው፤ ከቅዱስ ጋብቻ ያላነሰ የውል – የኪዳን ማርዳ ነበር። እሱን እንኳን አለስተረፈልንም፤ መሰሉን መልካም ገላጭ መለዮዋችነን ሁሉ – ተዘርፈናል። እንዲቆጠቁጠን – ከፈቀድንለት። አሳት ነው – ረመጥ፤ አውሎ ነው  – የሚለጋ። …. ጎርበጥባጣ፤

የሆነ ሆኖ አዘውትሬ እንደምገልጸው 90 ሚሊዮን ህዝብ ልሸፍት ቢል አይችልም፤ ልሰደድ ቢልም እንዲሁ፤ ስለዚህ ሰፊውና ጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ መኖር ለመጀመር ኑሮውን ከነጠቀው ጋር የሚያደርገው ዕለታዊ ግብግብ ቀጣይ – ይሆናል። ኦክስጅኑ ነው። መተንፈሻው ተዘግቶ መኖር አይችልምና። የታመቀ ስቃዩን – የሆዱን ለቅሶ – መተንፈሻ ቧንቧው – ሰላማዊ ትግል ነው። „አልተመቸህኝም“ ማለት ሲችል ይታገስለታል – ቃጠሎው። „በቅተህናል፤ አዬንልህ የበደል ድውለትህን፤ የቋሳ ብርንዶህን፤ የቁርሾ ክትፎህን“ ሲል ነዲዱ – ረብ ይልለታል። ትግሉን ማድረጉ ሆነ በውስጡ መኖር በራሱ ህሊና ለላው ዜጋ ጤና – ይለግሳል። የሰላማዊ ትግል የኩሬ ውሃ አይደለም። ስለዚህ በተሰራው የመንፈስ ሃብት ልክ ደጋፊ እዬገኘ ሲሄድ ቤቱን ገንብቶ ቤት አልባ፤ መጠለያ አልባ፤ ጥግ አልባ፤ ባለቤት አልባ በመሆን ለማንኛውም አደጋ እዳሪ ላይ የተጣሉትን ነፍሳት፤ ዜጎቹን ባለመጠለያ – ያደርጋቸዋል። ይህ አይቀሬ ነው። ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም – ይፈሳል።

ሽምቅ ውጊያና – መራራ ስክነቱ?

ሽምቅ ውጊያን ለዓለም ያሰተማረች ሀገር ኢትዮጵያ ናት። የጎሬው ኢትዮ አፍሪካዊው የጥቁር አንበሳ ታሪክ ነፃነታችን በማስገኘት ሂደት የታሪክ ባለቤት ነው። ዛሬ ግን ያነን እንተግብር ቢባል የሚቻል – አይሆንም። ዘመንን ወቅትን ያለጤነ አቤቱታ-  ይምጣል። አብዝቶ የሚደመጠው ጉዳይ በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ሃይሎች በሽምቅ ውግያ እርምጃ መውሰድ አለባቸው የሚለው ሲሆን፤ ለእኔ ሌላው የጓጎለው ጉም ነው። ሥልጣን ያለውን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ከሥሩ ለመንቀል በሽምቅ ውጊያ የሚሞከር – አይደለም። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩትም ዘመኑም – አይፈቅድለትም። ስለምን? በዘመኑ የሽምቅ ውጊያ ከሚያሰገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ አመዛኝ ስለሆነ። በሽምቅ ውጊያ ሰላማዊ ሰዎች በብዛት መስዋዕትነት እንዲከፍሉበት – ይገደዳሉ። ከተማ ውስጥ ያለው ኑሮ ጭፍቅፍቅ ባለ ሁኔታ የሰፈረ ነው – ህዝባችን። አንድ ቦታ እሳት ሲነድ በጥቂት ሰከንዶች ብዙ ንብረቶች፤ ብዙ ሰርቶ አደሮች ኑሯቸው አመድ የሚሆነውም በዚህው ምክንያት ነው። አድራሻ ቢስ ጉዳቶችም ህልቆ ናቸው። ሥርአተ – አልበኝነትም ብዙ አቅሞችን እንደ አሳማ ይውጣል። አብሶ ህጻናት፣ ነፍሰጡር ሴቶችና አዛውንታት ቀዳሚ – ተጠቂዎች ናቸው። ምክንያቱም ሽምቅ ውጊያው ድንገተኛ ስለሚሆን እናት ገብያ እንደ ሄደች፤ ልጆቿ ውጪ ሲጫወቱ እንደ ነበሩ፤ ወይ ትምህርት ቤት ላይ እንዳሉ የጥይት እራት ሊሆኑ ይችላሉ። ወይንም አንዲት ሴት ምጥ እንደተያዘች፤ ልክ እንደ መሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ማለት ነው ዬሽምቅ ውጊያ፤ እናትም እንደወጣች ልትቀር ትችላለች። ይህን እንደ አንድ ሰብዕዊ ፍጡር ለሚያዬው፣ ነፍሱ ከእሱ ጋር ላለች ፍጡር -ዘግናኝ ነው። በፓኪስታን ተዘውትሮ የሚታዬው አሰቃቂ ጉዳይም ይሄው ነው። አንድ ሰው እንደ ሰው ሊያስብ ይገባዋል። ይህ በችሮታ ሳይሆን ጸጋው ነው። መተርጎም – ከቻለ። የከፋውን የጎጥ አስተዳደር በደልን ለመቋቋም የሚመጥን ልዕቅና፣ ብልህነትና ሥልጣኔ ይጠይቃል። በስተቀር ትርፉ ድርብ ዕንባ ነው።

ከዚህም በላይ የህዝብ መገልገያ አገልግሎት መስጫ ድርጅቶች ሁሉ በድንገተኛው ጥቃት ከጥቅም ውጪ – ይሆናሉ። እኛ ደሃ ነን።አብሶ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በጥርሱ በያዛቸው ክልሎች ከሆነ፤ ከሥልጣን እስከሚወገድ ድረስ ባድማ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ለምሳሌ፤ … የጤና ክሊንክ፤ ድልድይ፤ ት/ቤት ላይ ቢሆን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዞር ብሎ አያያቸውም። እንዲያውም ብዙሃኑን በገፍ በማሰር ሠፈሩን በሰውም በአገልግሎትም ምድረ – በዳ እንደሚያደርገው – ይታወቃል። ወያኔ ጫካ በነበረበት ጊዜ ያዬሁት በዓይኔ ይሄውን ነበር። ዛሬም የአያያዙን አድሏዊነት – አላችሁበት። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖሊሲው ቂም፣ ቋሳና ቁርሾ ነው። ዛሬ ሳይወድ የተቀበላቸው ጉዳዮች አጋጣሚ አግኝተው ከፈረሱለት – እሰዬው ነው። ስለዚህ ጥያቄው የጓጎለ ጉም ነው – ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ። በተጫማሪም ትግሉ በሽምቅ ውጊያ ሳይሆን ከተደራጀ ሠራዊት ጋር የሚደረግ ስለሆነ፤ የሚፈልገው የሚመክተው የመደበኛ ውጊያ ሥርዓትን ነው። ይህም ታቅዶና አቅምን ለክቶ የሚከወን እንጂ፤ በነገ – በጣባ በግንፍል ፍላጎት ሊመራ ከቶውንም – አይችልም። ከሁሉ በላይ ጦርነቱ የእርስ – በእርስ ስለሆነ ሚስጥር ማሸነፍ ነውና እነኝህ ሁሉ አመክንዮዎች ግምት ሊሰጣቸው – ይገባል። ምን ያህል የተከደን እንደሆን ደግሞ – እናውቀዋለን። ከዚህም ባለፈ ዝርዝር የውጊያ ስልት ሪፖርት ካልቀረበ ብለን አካኪ ዘራፍ የምንል፤ ሳይኖረን እንዳለን – ደለቃቆችም አለን። ማሸነፍ – ሚስጢር ነው። ጥሬ ሃብቱ ደግሞ የሰው ልጅ ህይወት። ሰው! …. በቅፅበት ታልሞ ሰውን መፍጠር አይቻልም። የሰው ሥዕል ለመሳል እንኳን ጸጋን – ይጠይቃል።

አቅሙን የትጥቅ ትግሉን አላሳዬም ሌላው የኩነኔ ማሳ ነው፤

ጉድ በል ነው —- ባልተቋረጠ ሁኔታ የሚሰማው ጉዳይ የትጥቅ ትግሉ አንዲት ከተማ ይዞ በ24 ዓመት አላሰዬንም የሚል ነው። ይህ ገፊ ኃይል ከሦሰት አቅጣጫ ነው የሚከሰተው።  በቅንነት፤ ሌላው የትጥቅ ትግሉን በሚደግፉት ላይ ጫና ጥርጣሬና ተስፋ እንዲቆርጡ ለመሰንጠቅ ታስቦ የሚከወን ሲሆን፤ ሦስተኛው ግን ባልታቀዱ ሁኔታዎች ውድመትና ስቃይ የሚናፍቃቸው – ጠመዝማዞች – ልዞች አሉ። ሲፈጠሩ አዎንታዊነት የራቃቸው የአሉታ – ፍቅረኞች። ከሽንፈቱ ወይንም ከክሽፈቱ በኋላ ደግሞ የሰላ ገጀሟቸውን ይዘው ለመከትከት – ስለሚመቻቸው። እኛ እኮ ቃለ ምልልስን ለማድመጥ እንኳን አቅም – የለንም። እዬተሳቀቁ ነው እምናዬው። ትእግስቱ – ሸሽቶናል። እንኳንስ በድንገት በተነሳ ጊዜያዊ ወረራ፤ እልልታው ሳይሰክን መጠነ ሰፊ ዬዕንባ መራጨት ትዕይንት ሆኖ፤ በባዶ ሜዳ እንኳን ዘርፍ፣ ቅጥል፣ እንጥልጥል፣ እዬተፈጠረ – አሳር። ይህም ለእኔ የጓጎለ ጉም ተከል ነው።

አቅምን ለማሳዬት ብቁ አቅምን መገንባት – ይጠይቃል። አቅም ደግሞ ያለው – ከእኛው ነው። እኛ አቅም ልንሆን ቀርቶ አቅም መሰባሰብ ሲጀመር በፈረቃ በወበራ ወይንም በደቦ ስናጭድ ውለን – እናድራለን። በጥርሳችን የያዝነው አንድ ሥም ስንሞትም  ዬአጥንታችን ማህተም ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም፤ እኛ የምንፈልገው አቅም የሚመራትን ኢትዮጵያን ነው። በሌላ በኩል እሞታለሁ፣ መከራውን ሁሉ እቀበላለሁ የሚል ዜጋ ማግኘት ተራራ ላይ የሚገኝ ስንደዶ የሚመስለንም-  አለን። ወይንም አስፓልት ላይ የሚታፈስ – ጠጠር። ወይንም ሞድ ሱቅ ላይ አጭር – ረጅም – ቀይ – ነጭ – ጉርድ – ሙሉ ተብሎ ተመርጦ ለውጊያ ዝግጁ የሆነ የሰው ልጅ መሸመት። ዕብንነት! ተኝቶ መሄድ ታውቃላችሁን? እንደዛ —–

በሌላ በኩል ለሞት ለተዘጋጀው ደምና ስጋችን ስንል እንኳን ቆራጣ አክብሮት – በኗል፤ የመቻቻል ድህነት አብዝቶ – ይንጠናል። አንድ ነፍስ ለደቂቃ ትንፋሹን የሚሰበስብት ድንኳን ማግኘት የሰማይ ገነት ነበር። ግን መተላለፍ – ነው። ወቀሳም – አለበት። ውሃ ቅዳ እውሃ መልስ። ለማንኛውም የተደራጀ፤ የታጠቀ፤ የነቃ፤ ዓላማውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ተዋጊ ኃይል ለመፍጠር ጊዜ አብዝቶ – ይጠይቃል። የኢኮኖሚ አቅም – ይሻል፤ ህሊናን የማዘጋጀት ተቋም – ይጠይቃል። ከአንጎል ጋር ቁጭ ብሎ መወያዬትን – ይጠይቃል። ተባባሪ ሀገሮችን ለማግኘት መጣርን፣ በተከታታይ ያለመታከት መሥራትን – ይሻል። ሁልአቀፍ ድጋፍን – ይጠይቃል፤ ምክንያቱም የውጪዎቹ እነሱ በሚዲያቸው ካጣጣሉት በኋላ መልሶ የመገንባት ሂደቱ ቁልቁለት – አይደለምና። በሌላ በኩልም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሁኔታ የዓለም እንቅስቃሴዎች በስውር ስለሚከታተሉት ከእነሱ ቁጥጥር ውጭ ለመድረግ አለመቻል ሌላው የሳይንስና የቴክኖሎጂ ምጥቅ – አመክንዮ ነው። ትግሉ በግሎባል ደረጃ የማህበራዊ የኢኮኖሚ፣ ዬፖለቲካዊ ህይወትን ዕውቅና በቅንነት – ይፈልጋል። የሎጅስቲክስ ሁለገብ ድርጁነትን – ይሻል። የውጪ ሚዲያን አትኩሮትም – ይመኛል። የትጥቅ ትግል እኔ እንደማስበው ከባንቧ እውሃ የሚቀዳ አድርገን እንመለከተዋለን። እንኳንስ በህቡ ለተደራጀ፤ በመንግሥት ደረጃ ላለም ቢሆን የሰፊ መሰናዶ፤ ዬስልታዊ ሳይንስ ውጤት ወይንም ቀመር ነው – ውጊያ። ማሰብ – ይጠይቃል። ሂሳብ። የሰው ልጅ ጭድ አይደለም። ሰው ከመማገዱ በፊት በበቂ ሁኔታ በጥናትና በበቂ አቅም ተክህኖ ነው መጀመር – ያለበት። የትጥቅ ትግል እንጡሩብ የሚዘሉ ስሜቶች – አይገዙትም። ወይንም ከላይ ከላይ የሚፈላ – ግብዝነት።

አንድ ከተማ ቢይዝ ምን ያስፈልገዋል?

  1. ከተማው ውስጥ ያሉ ማናቸውም ማህበራዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ አግልግሎቶችን በነበረው መልክ የማስቀጠል፤ ለደሞዝተኛው ደሞዙን፤ ለባለ ጡረታው – ጡረታውን፤ ለታማመው ህክምና፤ ለተጓዡ መጓጓዣውን፤ ለተማሪው ትምህርቱን ወዘተ …. በስተቀር አንድ ቀን ደሞዝ ቢያልፍ እራሱ ህዝቡ ተዋግቶ – ነፃ አውጪውን – ያስወጣዋል። መኖር አለበታ! እህል – እህል የሚሉ ልጆች ወይንም በሽተኛ ልጅ ወዘተ ይኖርበታል … ሸቅጦ መቅጦ አዳሪውም እንዲሁ … አሁንስ መቼ ተሟላለት ልትሉኝ ትችላላችሁ፤ የተሻለ ጠብቆ ያለውን ካጣ ዕዳው ከፍ ያለ ነው ዬሚሆነው። የ200 ዓመት ግዛት ምኞት ውሳኔው የወያኔ ብቻ ሳይሆን ህዝቡ በፊርማ የሚፈቅደው – ይሆናል። ባልተሟላ ዝግጅት አንድ ትንሽ ከተማ ቢያዝ – ትልቁ ቀርቶ ማለቴ ነው፤ እንዲሁም በቀጣይነት አጎራባች አካባቢዎችን ዬማስለቀቅ ሂደት መኖርም ግድ – ይላል። አካባቢው በጣም ነው የሚታወከው። ስለዚህ አዋሳኞችን እዬጨመረ መሄድ – ወሳኝ ቋት ነው – ለተስፋ። „ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው“ ይላል የሀገሬ ሰው። የሃይልና የአቅም፤ እንዲሁም የሥነ ልቦና የበላይነት ለውጊያ መሰረታዊ ጉዳይ – ስለሆነ በመደመር ላይ ማባዛት ትንፋሹ ሊሆን ይገባል። ለአዲሶችም የተሟላ አግልግሎትን ማስቀጠል ይኖርበታል። በስተቀር የሚከዳው ወዘተረፈ ይሆናል። ይናዳልም።
  2. ከተጠቂው ኃይል ጋር በሚደረግ ግብግብ የሚሰነዘርበትን የማናቸውንም ዓይነት የመልሶ ዬማጥቃት እርምጃን የመመከት ወይንም መልሶ የማደራጀት እርግጠኛ የሚያደርግ ተጨማሪ አቅም ማሟላትን አጥብቆ – ያስፈልገዋል። ቢያንስ የያዘውን ላለመልቀቅ። ኃላፊነቱ እጅግ ግዙፍ ነው። በልመና ገንዘብ ሲሆን ደግሞ የቁጥር ተማሪዎች ከሆናችሁ ስሌቱን እስኪዱት።
  3. ለቀጣዩ የማጥቃት ሂደት በሰው ሃይል፣ በማተርያል፣ በሎጅስቲክስ ሙሉ አቅም ላይ ሆኖ መገኘት – ይኖርበታል።
  4. ተጠባባቂ አቅም በሙሉ ዝግጁነት የማደራጀት ኃላፊነት – ይኖርበታል፤
  5. የደህንነቱ ጉዳይ በራሱ ፈተና ነው። እርስ በእርስ ነዋ – ፍልሚያው። ማን – የማን? ማን – ለማን? ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቅ። የማጣሪያው ወንፊት እራሱ ከአቅሙ በላይ የሚሆኑ ግብግቦች አሉበት – የነፃነት ትግላችን።
  6. በሂደቱ የሚገጥሙ ማናቸውንም ደራሽ ችግሮችን በአግባቡ ለማስተናገድ አብዝቶ መሰናዳት ይኖርበታል።
  7. በዲፕሎሎማሲ በኩል ትግሉን ሊረዱ ሊደግፉ የሚችሉ በርከት ያሉ ሀገሮች የሚኖራቸው አሉታዊ ዕይታ ወዘተ ታስቦና ታቅዶ በስልት መከወን ካልተቻለ ገብቶ ለመውጣት ከሆነ እግርም ጫማ ውስጥ ገብቶ ይወጣል። ወይንም ሰውነት ወንዝ ውስጥ ገብቶ ይወጣል። ምን ለማለት ነው የሚከፈለው መስዋዕትነትና የሚገኘው ድል ተመጣጣኝ መሆን መቻል አለበት። ስንዴ ወፍጮ ውስጥ እንደሚጨመረው – አይደለም። ሰው ነው ለውጊያ – የሚዘጋጀው። ድሉንም ለመስቀጠል በጣም እርግጠኛ የሚያድርግ በቂ አቅም መኖሩን ማረጋገጥ በጣም – እጅግ በጣም – ይስፈልጋል። ይህ ሳይሆን በውሽልሽል ወይንም በሞቅታ ፈረስ ጥቂቶችን ለማስደስት ተብሎ መጀመር አይደለም፤ ሙከራ ቢደረግ ከትርፉ ኪሳራው – ያመዝናል። ከዛ በኋላ እንዲያውም አገግሞ የመነሳት አቅሙ ሙት መሬት ላይ – ይወድቃል //// ቀጣዩ ዬድል ህልምም እሩቅ – እጅግ እሩቅ ይሆናል። አንጋጦ ዬማዬት ዕጣ ብቻ ይሆናል – የሚጠበቅው። እንስከን። ከወጣቶች በላይ ጎልማሶች በወጣት ፍላጎት እዬተናጥን – እንገኛለን። ጦርነት በጉርና ተገፍቶ እንደሚወጣው ወገሚትና ቅቤ – አይደለም።

ሳይሳካ ቢቀር ተከታዩ ምን ይሆናል? ወይንም ወደ ኋላ ሠራዊቱ ቢያሸገሽግ ….

  1. እጅግ ከአሁኑ በስፋትም በመጠንም የከፋ ተስፋ ቆራጭነት – ያይላል፤
  2. የሥነ ልቦና ውድቀት በከፍተኛ ደረጃ – ይከሰታል። ምክንያቱም የምንጠብቀው ፍላጎታችነን አስተልቀን ስለሚሆን፤
  3. የዕምነት መጓጎል አብዝቶ ትግሉን – ይፈታተነዋል።
  4. የሃይል መበተን በከፋ ሁኔታ ሊገጥም – ይችላል፤
  5. ዕምነት የማጣትና ኃላፊነትን የመሸሽ አደጋ ሊከሰት – ይችላል፤
  6. ዬሰው ህይወት ጥፋት – በትርፍ አልባነት – ይወራረዳል፣ ጡረታ የመክፈል አቅሙም – የለንም። ሌላው ቀርቶ ጀግናችን ለማለት እንኳን …. ?
  7. ዬንብረት ብክነት በዕሴተ – ቢስነት ይሰክናል፣
  8. ዬህዝቡን ትኩስ ስሜት መልሶ እንደገና ለማግኘት ዳገት ይሆናል፣
  9. እንደገና ለመልሶ ለመቋቋም ሌላ ተጨማሪ ዓመታትን – ይጠይቃል፣ ለዛውም ከተሳካ —- አደጋው እጅግ እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው፤ ምክንያቱ እኔ እንደማዬው ፍላጎታችን ሆነ ወቀሳችን ከአቅማች ሲነሳ አይቼ አላውቅምና። ፍላጎታችን በጣም የናጠጠ ዲታ ነው። አቅማችን ደግሞ – ስስ።
  10. በህዝብ ያለው ተቀባይነትና ፍቅር – ይደብዝዛል፤ ለዛውም ወፍ ካወጣው ነው፤ በስተቀር ጨርሶ – ሊተን ይችላል።
  11. የበቀል ጥቃቱ በተጨቋኝ ህዝብ ላይ በእጥፍ ድርብርብርብ ይጨምራል፤ ታዳጊ ወጣቶች – ይደፈራሉ፤ አዛውንታት – ይደበደባሉ፤ ቤተ አምልኮዖች – ይጠቀጠቃሉ፤ ባለትዳሮች ጥቃት – ይፈጽባቸዋል፤ ቁምጥ ያለነው እኛ ደግሞ ተጀምሮ ቢታይ ደጋፊ ይኖራል አውሎው ይሰክናል ወዘተ ወዘተ … ምንትስ ቅብጥርስ የምንለው ነገር „ከበሮ በሰው እጅ ሲይዙሽ“ ዓይነት ነው። የጦርነት ጉዳይ …. ነጠላ ገጥሞ መስፋት አይደለም።

የዲፕሎማሲ ሥራ ቀጣይነት አስፈላጊነት፤

በዲፕሎማሲ ትግል ቀጣይነትም የጓጎሉ ጉማዊ ዕይታዎች – አያለሁ። ምን ሲያደርግ? ምንስ ሲያተርፍ? የሚሉ ዕድምታዎች ይደመጣሉ። ዲፕሎማሲ አንዲት ሀገር ከሌላው ጋር ያላት ግንኙነት ወሳኝ ጉዳይ ነው። ህዋስም ነው። ትእግስትን አብዝቶ ይሻል። የዲፕሎማሲ ሥራ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም ወሳኝ ጉዳይ ነው። ስለሆነም በተከታታይነት መቀጠል ያለበት አምክንዮ መሆን አለበት። የዲፕሎማሲ ትግል አብዛኛው እጅ በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ቢካተትም ለትጥቅ ትግሉም ቢሆን ወሳኝነት ያለው ክስተት ነው። በነገራችን ላይ ለእኛ እንደ ሃጢያት፤ እንደ ወንጀል ይታይ እንጂ ትናንት ሻብያና ወያኔ ያለፉበት ህይወት ነው። ዛሬም ቢሆን እኛ ብቻ አይደለነም ለነፃነት ትግል የትጥቅ ትግልን እንደ አማራጭ – ያዬነው፤ እንደ ህንድ በርከት ያሉ ሀገሮችም እያካሄዱት – ይገኛሉ። ስለዚህ ለሁለቱም ስልት ደጋፊ ሀገሮችን ወይንም ግለሰቦችን ወይንም ተቋማትን ማግኘት ለነፃነት ትግል መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ስለዚህም ዘርፉን በታታሪነትና በቀጣይነት መከታታል በእጅጉ – ያስፈልጋል።

ይህም ማለት ከቀደመው በተሻለ፤ በጠነከረ ሁኔታ የዲፕሎማሲ ተግባርን ተግቶ ሥራ ላይ ማዋል – ያስፈልጋል። የዲፕሎማሲያዊ ትግል በተቆራረጠ መልኩ ከሆነ፤ ወይንም በትናንሽ የትርፍ ቅንጥብጣቢዎች ከተዘናጋ ውጤቱ የዚያን ያህል የከሳ ነው የሚሆነው። ነገር ግን ተከታታይነት ያለው፤ ሥልጡን፤ በታቀደ ተግባር በተደራጀ ሁኔታ ከተከወነ ከሁለቱ የትግል መስመሮች ባልተናነሰ በገዢው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እጅግ ጉልህ ነው። አጋርም ብረት መዝጊያ የሚሆን – ያስገኛል። በሌላ በኩል ተቀናቃኙ የጎጥ ድርጅት የወያኔ ሃርነት ትግራይ በፖሊሲ፤ በፋይናንስ፤ በመዋቅር፤ በዘመቻ የሚከውነውን የፕሮፖጋንዳ ተግባር ለማፍረስ ተሽሎና ቀድሞ መገኘትን ይጠይቃል። ይህም ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል፤ ግንኙነቶችን በሙሉ በፋክት ላይ የተመሰረቱ፤ እውነትን ያቀፉ ነገ ሊገኙ የሚችሉ ሃቆችን የተንተራሱ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መላኩ ሌላው የተስፋ ፍሬ አስገኝ ሃይልም ነው።

© internal character scope or reader (© የውስጣዊ ሥነ ባህሪ አጉሊ መነጸር ወይንም አንባቢ)

ቃሉን እራሴ ነው የፈጠርኩት። ይህን ሳይንቲስቶች ቢሰሩት መልካም በሆነ – በነበረ። ግን እስካሁን ድረስ አልሠሩትም። ይህ መሆኑ እዬታወቀ በአንድ ፓርቲ ወይንም ድርጅት ወይንም ንቅናቄ ወይንም ተቋም የሚፈጠሩ ጥቃቶችን ቀድሞ ማዬት ነበረበት የሚል ዕድምታ አለ። እንዴት ይለያል ከሰርገኛው ጤፍ ነጭኑ ለይቶ – ማውጣት። መልካችን አንድ፤ ደማችን አንድ፤ ዘራችን አንድ ነው። ቤቴ ብሎ ለሚገባ፣ ለመደራጀት የወደደውን ማናቸውም ተቋማት የአብርሃም ቤት ማለት ይኖርባቸዋል። ከመግባቱ በፊት ለእኛ ሲባል የተሠራልን የውስጥ ሥነ ባህሪ አጉሊ መነጸር ወይንም አንባቢ መሳሪያ internal character scope or reader እንዳለ ሁሉ ጠቅልለን፤ አንገዋለን ቀድሞውንም ማጣራት ነበረባቸው፤ ከመሃከላቸው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ወኪሎች ስላሉ እንዲህ ሆነ —- እንደዛ ሆነ እንላለን። ወይንም ችግርን አቅደን እንዲህ ሊሆን ይችላል —- እንዲያ ሊመጣ ይችላል እንላለን። በዕውነቱ ይህ ምናብ ነገር ነው – ለእኔ። እያመሰን ያለውም ጉዳይ ይሄው – ይመስለኛል። የመሬት መንቀጥቀጥ ወይንም አውሎ ቢነሳም የሚለካከከው እሚጨፈጨፈውም አንድ ንቅናቄ ብቻ ላይ ነው።

አንድነት ለፍትህና ለነፃነት ከመጨረሻው ጫፍ ደርሶ እንዲህ ሥሩ ተነቅሎ ሲፈርስ መነሻውም መደረሻውም ትግሉ የእርስ በእርስ ስለመሆኑ ከአምክንዮ ውጪ እንሆናል። ስለምን ማገዶዎቹ የአንድነት መሪዎች ተለይተው፤ ተለቅመው ጉድጓድ ውስጥ ተጨመሩ? ለምን? ይህን የሚመልስ ህሊና ለሌላውም ጥያቄ መልስ ሊኖረው – ይገባል። እንዳለ ድርጅቱን በሃጢያተኛነት ከመመደብ በፊት። ፍርዳችን፣ ዳኝነታችን፣ ወቀሳችን እራሱ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ባልተሻለ ሁኔታ በተመሳሳይ ወርድና ቁመና – የተጋደመ ነው። ምን የተጋደመ ብቻ የተኛም ነው – ለሽ ብሎ። ምክንያታዊ ጉዳዮችን እኩል በሰው ህሊና ለመርመር ቢያንስ ለራስ ህሊና ለመፈቅድ አለመቻል። መነሻቸውን ሆነ መድረሻቸውን ማዕከላዊ ሰቁ ላይ ቁመን ሙቀቱን እንለካው። አሉታዊውን – 1, – 2, – 3፣ ወዘተ ወይንም አዎንታዊውን + 1, +2, +3  ወዘተ … ደመ መራራው ድርጅት የትናንቱ ግንቦት 7 የዛሬው አርበኞች ግንቦት ከአካላቱ መንፈስና ህሊና ገና ያልተፈለሰፈ ሳይሆን ፈጽሞም ያልተሰበ መሳሪያ መግጠም ነበረበትን?

ከቶ ዛሬ ነፃ ነኝ የሚል የነፃነት ትግሉ ግንባር ቀደም ታጋይ ካለ እራሱን እረስቷል ነው የምለው። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ሁሉ ተጫማሪ ዬድርብ ሰው ጥላ አለ። ግን አናስተውለውም። እምንታገለው የራሳችን አካል ብቻ ነው፤ ቁሞ የምናዬውን። ነገር እዬለቀምን አቤቶ ስህተት እባክህን ናልን ብለን ተማጽነን ወጮፈዎን ወደ አንድ አቀጣጫ ብቻ – እንልከዋለን። በፓሊሲ ደረጃ ዕቅድ ተዘጋጅቶለት ለኢንባሲዎች የተበተነ ትዕዛዝ ነበር። በ6 ዓመት ቆይታው መሬት የያዘ ተግባር በጠላት የፈረጅነው የጎጥ ድርጅት ማንፌስቶ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ገቢራዊ – አድርጎታል። በገፍ ወደ ውጪ ከሁሉም ብሄረሰቦች – አስገብቷል። በህጋዊ – ፓስ። ፍጹም ስውር በሆነ ሁኔታ የእዝ ሰንሰለት አለ። አይደለም የሃበሻ – ተሃበሻ ግንኙነት ከዚህ ባለፈም የሄዱ – መረቦችም። አንድ ጹሁፍ ላይ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ስለምርጫ 2007 ከማህደር ራዲዮ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ያሰከኑት ከቆጮ ላይ ነበር። የሪስቶራንቱ ስም ሳይቀር ነበር የጻፉት። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የስለላ ተግባር ወጪውን በመቶ – ይቀንስለታል። ሳነበው እራሱ – ተንዘፈዘፍኩኝ። በቃ እንዲህ ምንም እንደሌለበት ሰው ነው እምትዝናኑት ማለት ነው?! ገረማችሁኝ።

መኪናንም ሞቅ አድርጎ አስነስቶ መሄድ ብቻ ነውን? በኪሱ ምን እንዳለ አትፈትሹትም ማለት ነው?  የገብያ ቦታዎቻችሁ የተለመዱ ናቸውን? በቃ! ኑልኝ ካለው ሁሉ ድግስ ቤት ትገኛላችሁን?! ፊት ለፊት ወጥታችሁ እዬታገላችሁ የሃበሻ ቤቱንም በልክ ለማድረግ አቅም አነሳችሁን?!  በጋብቻ – በአብልጅነት – በጓደኛ ወዘተ ያሉነን ግንኙነቶች በቃ እንደወረደ መቀላቀል ነውን? …. ጦርነቱ የእርስበርስ በመሆኑ አብዝቶ ጥንቃቄ – ያስፈልገዋል። ቢያንስ ለራስ ዘብ መቆም። ዝለናል ወይንም ተደግሞብናል። መንገድ ላይ እያለን ስልክ ቢደወልም ፈጥነን እናነሳ ይሆናልን?! በኋላችን መኪና እዬተከተለ አጣብቂኝ ቦታ ላይ ስንደርስ እራሱ ደወሉ ካነሳንለት – ድንገተኛ አደጋ ውስጥ እንድንገባ ሊታቀድ እንደሚችል ከቶ አይታያችሁምን?! ደም ከልብነትን አስታውሳችሁ አታውቁንም?! ተከታታያችሁ አቶ ‚ሀ‘ እሱ ደስ ብሎት አልፎን ይሄዳል። መሳሪያ አልያዘ፤ ግን በሥልጡን ሥልቱ በልጦ ድሉን ተጎንጭቶ በሰላም እፎይ ብሎ ቤቱን ይገባል። እሰቡ – በትንሽ። እህት ነኛና አብዝቼ ስለናንተ አስባለሁ።

እውነት ለመናገር የውስጥ ሥነ ባህሪ አጉሊ መነጸር ወይንም አንባቢ internal character scope or reader መሳሪያ በሌለበት ሁኔታ በግራ ቀኙ ተጠቂዎች እኛው ነን። ስለዚህ ለኑሯችንም ደንበር ይኑረው ነው ፍሬ ነገሩ። የሆኖ ሆኖ በታሠሩ ወገኖቻችን ሳቢያም ሁኔታ እዬተፈለገ እያሰገረ በሚነሳ አለሎ ትደቁሱታላችሁ እንደ – አደስ መከረኛውን። የትም ቦታ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ደጋፊዎች አሉ ከቤታችን ጀምሮ …. ማንገዋለያ መሳሪያ ደግሞ ዬለም። ስለዚህ ከሳሽም – ተከሳሽም ሊኖር አይገባም። ከጥንቃቄ ትርፍ እንጂ ኪሳራ ስሌለ በዬትም ሁኔታ ጠንቃቃ መሆን፤ ደወሎችን ማድመጥ፤ ምቾዎቶችን መቀነስ በእጅጉ ያስፈልጋል። ይቅርብኝ ብሎ መቁረጥና – መወሰን። በራስ ላይ መዕቀብ መጣል። የተቋማት ሁሉ ችግሩም ይሄው ነው። የነፃነት ትግል ማለት ከሁሉም ፍላጎቶች ጋር በስድ ሳይሆን በተዕቅቦ መኖር ማለት ነው። የነፃነት ትግል ኑሮ በልቅነት – አይታሰብም። ሥርዓት አለው።እራስን መቅጣት፤ ተፈጥሯዊ ስሜትን መግታት። ወጣትነትን አሳልፎ ፈቅዶ መስጠት፤ እናትነትን ሆነ አባትነትን በፈቃድ ማጣት፤ ተፈጥሯዊ ደስታዎችን መክዳት፤ በዳንኪራዎች ላይ መሸፈት … ወዘተ … የነፃነት ትግል ለእኔ የሱባኤ ጊዜ ነው።

ከውና – ነፃነት የፒክኒክ (picnic) ውሎ አይደለም። ወይንም – ቡፌ። መስዋዕትነትን ሰንቆ መከራን የፈቀዱትን ብቻ በአባልነት የሚቀበል ስለሆነ ቅንጦተኞች፤ ወይንም ቀለጤዎች ወይንም ዘመናዮች ክፍሉ አይደሉም። ነፃነት የራበው – ራህቡን የሚያስታግስበት ብትን መቆሚያ አፈር፤ ወስፋቱን የሚያሳርፍበት ቁራሽ እንጀራ፤ ጉሮሮውን የሚያረጥብበት ጭልፋ ጠብታ – ኤዶሙ ነው ለእሱ። ከፈኑን የሚሸፈንበት – ብጣቂ እራፊ …. እና ቀበቶ እና መቀነት —– ሌላውን ድለቃ ለምቾተኞች ለድሎተኞች

(no risk no fun) ይላሉ ፈረንጆቹ። ተደፍረው የሚገባባቸው በሮች ሁልጊዜ ላይሳኩ ይችላሉ ወይንም ሊሳኩ፤ ወይንም ተቆርጠው የሚቀሩ ህልሞችም ሊገጥሙ ይችላሉ፤ ተቆርጠው በሚገባባቸው መጠራቅቆች ተስፋን አምጦ ለመውለድ ምጥና ዳጥም ናቸው፤ ኮሶን – እንቆቆን፤ አሳንጋላን ደፍሮ ወስዶ ከኮሶ ትል መገላገል …. በስተቀር በህዝብ አደባባይ እዬሾለከ እዬወጣ ከእግሩ ሥር ይለጠፋል …. ትሉ። ውርዴት ጠጥቶ መኖር ? ? ?

የእኔ ጌጦቼ ለነበርን ሸበላ – መሸቢያ ሰሞናትን በፍቅር ተመኘሁ።

ሃሙስ ራዲዮ ፕሮግራም አለኝ በ2.07.2015 አዬር ላይ ከ15 እስከ 16 ወይንም በማግሥቱ አርኬቡ ላይም – ታገኙኛላችሁ።

Tsegaye Radio or www.tsegaye.ethio.info. Aktuelle Sendung

አንቺ እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ሰንድቅዓላማሽን ለብሼ አንችን የማይበት ቀን በእጅጉ – ናፈቀኝ! እባክሽን እማ ለወጉ – አድርሽኝ።

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

The post የጓጐሉ – ጉሞች – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

በድን –ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (ክፍል ፪) –አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

ሰኔ ፲ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህቱረት ( 6/17/2015 )

 

eskemecheበክፍል አንድ፤ የሰላማዊ ትግሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምን እንደሆነ ገልጫለሁ። በዚሁ ላይ፤ የሰላማዊ ትግሉ ከተወዳዳሪ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ልዩነት አሳይቻለሁ። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሰላማዊ ትግሉ የሚካሄደው በአንድ የሕዝባዊ ንቅናቄ ድርጅት ሥር ብቻ መሆኑንና፤ አማራጭና ተለዋጭ እንደሌለው አስምሬበታለሁ። በሂደቱ መሰባሰቢያ የሆኑትን ሀገር አቀፍ የትግል ዕሴቶች አስቀምጫለሁ። በዚህ ክፍል ሁለት ደግሞ፤ ስለተሳሳተው የሰላማዊ ትግሉ ግንዛቤያችን አስረዳለሁ። ባጠቃላይ፤ የሰላም ትግሉ ከትጥቅ ትግሉ አኳያ ለምን እንደሚመረጥ በግልጽ አሰፍራለሁ። በማጉላትም በአሁኑ ሰዓት፤ የሰላማዊ ትግሉ አማራጭ የሌለው ብቸኛ የትግል መንገዳችን መሆን እንዳለበት አመላክታለሁ።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ስለሚካሄደው ሰላማዊ ትግሉ ያለን ግንዛቤ ጉድለት አለው። አንዳንዶቻችን፤ ገዥው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ስለሚያስር፣ ስለሚገድል፣ ከሀገር ስለሚያሳድድ የሰላማዊ ትግሉ አይሠራም እንላለን። ሌሎቻችን ደግሞ፣ በምንም መንገድ፤ ገዥው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ወዶ ሥልጣኑን ስለማይለቅ፤ በምርጫ መሳተፉ ዋጋ የለውም፤ ስለዚህ የትጥቅ ትግሉ ብቻ ነው የሚያዋጣ፤ በማለት ሰላማዊ ትግሉን እናዋድቃለን። ይህ በመሠረቱ በሀገራችን ያለውን አስከፊ የፖለቲካ ሁኔታ ከመመልከትና ይህ የገዥ ቡድን ላንዴም ለሁሌም እንዲወገድ ከመፈለግ የተነሳ መሆኑ ግልጽ ነው። ችግሩ ግን ፍላጎት የታሪክን ሞተር አያሽከረክርም። ተጨባጩ የሀገራችን እውነታና ያንን ለመለወጥ በቦታው የዋለው ተግባር፤ ሂደቱን ይነዳዋል።

ትግሉ በአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ነው። ትግሉ ሀቅ ነው። ትግሉ አንድ ነው። በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በኢትዮጵያ ካለው ሰላማዊ ትግል ባሻገር ያለውን በማካሄድ ላይ ያሉት፤ አንድም የዚህ ወይንም የዚያ አካባቢ ነፃ አውጪ ግንባር ናቸው፤ አለያም ይህ ወይንም ያ ድርጅት ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ አሰባስቦ በአንድ ያሰለፈ ሕዝባዊ ድርጅትም ሆነ ጦር የለም። ስለዚህ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ወገን፤ የገዥው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በሌላ ወገን የተሰለፈበት ትግል አልተያዘም። እናም ይህ እስካልሆነ ደረስ፤ ትግሉ የሕዝቡ አይደለም ማለት ነው። በርግጥ ሁሉም ድርጅቶች የሕዝብ ነን ማለታችውና ለሕዝብ ነው የምንታገልው ማለታቸው አይቀርም። ከሆነ ለምን በአንድ አይሰባሰቡም? ይህ የሕዝቡ የነፃነት ትግል የማይሆነው፤ የሚታገሉት ለራሳቸው ጠባብ የግል የድርጅታቸው ዓላማና ግብ ስለሆነ ነው። በራሳቸው ጠባቡ የድርጅት ፍላጎትና በሕዝቡ ፍላጎት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። አለያማ ሁሉም የሕዝቡን ፍላጎት እንከተላለን ካሉ፤ በአንድ ይሆኑ ነበር። እንግዲህ በዚህ ጠባብ የድርጅት መነፅር ሁሉንም ነገር ስለሚመለከቱ፤ የድርጅቶች መፍትሔ ከዚሁ ይመነጫል።

የነሱን ድርጅት የበላይ አድርጎ የማያስቀምጥ ሂደት ሁሉ፤ “ትክክል” አይደለም። ለዚህ ነው ሰላማዊ ትግሉን የሚኮንኑት። በትክክለኛ መንገድ መኮነንም ተገቢ ይሆናል። ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ መኮነን ግን ተገቢ አይደለም። ሰላማዊ ትግሉ፤ ገዥውን ክፍል ለማስወገድ የሚደረግ ንቅናቄ እንጂ፤ ገዥውን ለመተካት የሚደረግ ሩጫ አይደለም። ሰላማዊ ትግሉ፤ ያለው የገዢ ቡድን መወገድ አለበት ብሎ የተነሳ ሕዝብ፤ የሚወስደው የፖለቲካ እርምጃ ነው። ማንኛውም የትግሉ እንቅስቃሴ፤ በመሳተፍ ተወዳድሮ ለማቸነፍ ሳይሆን፤ የውድድሩን መድረክ፤ ሕዝቡን ለመድረሻና ለመቀስቀሻ ለመጠቀም ነው። ሰላማዊ ትግል ሽርሽር አይደለም። መስዋዕትነት ይከፈልበታል። የኛ ታጋዮች እየከፈሉበት ነው። ሳሙዔል አወቀ ከፍተኛውን መስዋዕት ከፍሏል። ሌሎች ቀድመዉታል፤ ሌሎችም ይከተሉታል። ለዚህ ነው ይህ ገዥ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መወገድ ያለበት። እና “ምርጫ ተወዳደረን እንድንጥለው ካልፈቀደልን፤ ሰላማዊ ትግሉ አበቃለት!” ማለት፤ ሰላማዊ ትግልን አለማወቅ ሳይሆን፤ ሆን ብሎ ማደናገር ነው። ሰላማዊ ትግል፤ በምርጫ ለማቸነፍ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይደለም። በምንም መንገድ በምርጫ የሚቸነፍና ወዶ ሥልጣኑን የሚለቅ አምባገነን ጠላት የለም።

እኔ የሰላማዊ ትግሉን የምቀበለው፤ ፍጹማዊ ከሆነ ከትጥቅ ትግሉ ይበልጣል ከሚል ውሳኔ ተነስቼ አይደለም። በምንም መንገድ ትጥቅ ትግልን አልኮንንም። በአሁኑ የኢትዮጵያ የትግል አሰላለፍ፤ የቅንጣት ታክል ማመነታታት ሳይኖረኝ፤ የሰላማዊ ትግሉ ያላማራጭ ብቸኛ መንገዳችን መሆን አለበት እላለሁ። ለምን? አሁን አንድ የሆነ የትግል ማዕከል የለንም። እያንዳንዱ ድርጅት፤ ለድርጅቱ ግብ የሚታገልበት ሀቅ ነው ያለው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለግሉ ታግሎ ሥልጣን ጨብጧል። የያንዳንዱ ድርጅት ትግል፤ ያንን ለመተካት ነው። ውጪሰው ኢትዮጵያዊ ታጋዮች ደግሞ፤ አንድነት ከመመስረት ይልቅ፤ በመከፋፈልና እርስ በርስ በመነካከስ፤ ቁጥራቸው የበዙ ድርጅቶችን መሥርተን፤ በሕዝቡ ትግልና ድል ላይ ልናደርግ የምንችለው አስተዋፅዖ አመንምነነዋል። ዋናውን ጉዳይ ትተን በጠባብ ዕይታችን ታፍነን፤ ሩቅ ማየት አቅቶን ዓይናችን ስለጨፈን፤ የትግሉ ባቡር ጓዙን ጠቅልሎ ጥሎን እየሄደ ነው። እርስ በርስ መነኳኮሩ ጥሞናል። ከዕለት ዕለት መበጣጠስና መቀናነሱ አልቆረቆረንም።

አሁንም ባለንበት ስናዘግም፤ ትግሉ እኛን ታግሎናል። ይልቁንም ከኛ ተከትለው የትግሉን ችቦ የሚያበሩት ታጋዮች፤ መልሰው መላልሰው እንደኛው በተለመዱት፤ ሀገር ወይስ ድርጅት፣ የሰላማዊ ትግል ወይስ የትጥቅ ትግል፣ ከውጭ መደራጀት ወይስ በሀገር ቤት መንቀሳቀስ፣ ከኤርትራ መነሳት ወይስ ኤርትራን በጠላትነት የትግሉ አካል ማድረግ፣ በየግል ድርጅቶች መታገል ወይስ የትግል ማዕከል መፍጠር፤ በሚሉ አንድ ቦታ ላይ በማይደመደሙ ንትርኮች እንዳይጠመዱ ያሰጋል። ከዚህ ወጥተውና የእስከዛሬውን ትግል መርምረው፤ ትምህርት በመውሰድ፤ የአንድነት ትግል የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማስተካከል አለብን። ይኼን የማቀርበው፤ በትግሉ ሳይሆን፤ አሁን በውጭ ባለነው ታጋዮች ያለኝ እምነት እየመነመነ በመሆኑ ነው።

ሰላማዊ ትግል፤ ለሚታገሉለት ሕዝብና ሀገር፤ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ፤ የመጨረሻ ከፍተኛውን ቦታ በመሥጠት፤ ከግለሰብ የኔነት ጋር የተያያዙትን በሙሉ፤ የግል ጥቅም ሆነ የድርጅት ግብ ወደ ኋላ ገፍቶ፤ ቅድሚያ ለወገንና ለሀገር የሚሠጡበት ትግል ነው። ትግሉ፤ ገዥውን ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አምባገነን መንግሥትን ድል ማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ የሚከተለውን ሥርዓት ወሳኝ የሆነ ነው። ትግላችን ከፍተኛ ጥንካሬን ይጠይቃል። ትግላችን ወሰን የለሽ ትዕግስትን ይጠይቃል። ሞትን መናቅን ይጠይቃል። ይህ ሰላማዊ ትግል፤ የሕዝቡ ትግል ነው። ሰላማዊ ትግል፤ ታጋዮች በሕዝቡ መካከል ተገኝተው፣ የአካባቢው አካል ሆነው፣ የአካባቢው ብሶት የራሳቸው ብሶት ሆኖ፣ ከተባሰው ጎን ተሰልፈው፣ ከፍተኛውን መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚያካሂዱት ትግል ነው። የድርጅቶች ትግል አይደለም። ሰላማዊ ትግሉ በሕዝቡ የሚደረግ ነው። ሰላማዊ ትግሉ ሁሉን አስተባባሪ ነው። የማንም የግል ድርጅት ንቅናቄ አይደለም። ሰላማዊ ትግሉ ደጋፊው ብዙ ነው። ሰላማዊ ትግል የተወሰነ አባልነትን ብቻ ያነገበ የአንድ ክፍል ጥረት አይደለም። ሰላማዊ ትግሉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ዘንዳ ድጋፍና ተቀባይነትን ይሻል። በዚህ ዓይን ስንመለከተው ነው፤ የኛን አስተዋፅዖ ትርጉም የምናበጅለት።

የትጥቅ ትግሉ ተገቢ ቦታና ጊዜ አለው። አሁን ባለንበት ሀቅ፤ አንድ ማዕከል በሌለበት ሁኔታ፤ እያንዳንዱ ድርጅት ለራሱ መርኀ-ግብርና ግብ በቢታገልበት እውነታ፤ የታጠቀው ጦር የድርጅቶች መሣሪያ በሆነበት ጊዜ፤ የትጥቅ ትግሉ በጣም አደገኛ ነው። ሀገራችንን ወደ መበጣጠስ ያመራታል። በተለይም አብዛኛዎቹ የታጠቁት የነፃ አውጪ ግንባሮች መሆናቸው፤ አደጋዉን ያበዛዋል። እናም የሰላማዊ ትግሉ በጥረታችን አንድ ማዕከል አበጅቶ፤ ትግሉን እንድንቀጥልና ለድሉ እንድናበረክት ይጠራናል። ለሰላማዊ ትግሉ ቆርጠን እንነሳ። በሂደት አንድ ማዕከል ሲፈጠር፤ ሂደቱ ራሱ የሚያስከትለውን አዲስ ክስተት ከዚህ ሆኖ መገመት ከባድ ነው። በወቅቱ ግን ሂደቱን ተከትሎ እምነታችን መቀየር እንዳለበት ጥርጥር የለኝም።

eske.meche@yahoo.com  http://nigatu.wordpress.com

The post የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (ክፍል ፪) – አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ appeared first on Zehabesha Amharic.

የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው –ገለታው ዘለቀ

$
0
0

eprdfበድርጅት ከዚያም ከፍ ብሎ በመንግስት ደረጃና በሃገር ደረጃ ግምገማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉ ያምናል። የኣንድ ድርጅት ብቃትም በግምገማው ችሎታና ጥራት ሊለካ ይችላል።የኣንድ ሃገር የፖለቲካ መረጋጋት በፖለቲካ ለሂቆቹ የጠራ የሃገር የምናብ ስእልና ብስለት ሊለካም ይችላል። የፖለቲካ ቤቶች ሲኮለኮሉ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ ከፍ ያለ ግምገማን ይጠይቃል። ሃገሪቱ ያለፈችበትን የህይወት ጎዳና፣ የገጠማትን ችግር መንስዔና ውጤቶች በሰፊው መገምገም ለሚመሰረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረትና ለሚቀረጹ ፖሊሲዎች ጥራት ወሳኝ ነው። እንግዲህ በሃገራችን ኢትዮጵያ ግምገማ በሰፊው የተወራለት ጉዳይ የሆነው በዚህ መንግስት ጊዜ ነው።  ህወሃት በጫካ ኑሮው ጊዜ  የነበረው ማህበራዊ ህይወትና የትግሉም ባህርይ የየቀን ውሎውን እየገመገመ እንዲሄድ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ስለከተተው በግለሰቦች ድክመትና ጥንካሬ ዙሪያ ሲገማገም ነው ያደገው። የግምገማው ዓይነት ኣውጫጭኝ ኣይነት ግምገማ ተፈጥሮ ያለው ነው። በመርህ ደረጃ ግምገማ መኖሩ በራሱ ጥሩ ሆኖ ሳለ የግምገማውን ባህርይና ያመጣውን ፍሬ ማየት ግን ኣለብን።

ህወሃት “ኢሃዴግ” ስልጣን ከያዘ በሁዋላ የመጣው ይህ ግምገማ ከድርጅት ኣልፎ ታች በየመስሪያ ቤቱ እንዲሁም ገበሬው ድረስ ወርዶ እንደነበር ይታወሳል። ባህሪው ለየት ያለ በመሆኑና ያልተለመደ በመሆኑ ኣስተማሪዎችን፣ የህክምና ባለሙያዎችን፣ የግብርና ባለሙያዎችን ወዘተ ግራ ኣጋብቶ ነበር። ግራ ያጋባበት ምክንያት በሃሳብ ደረጃ መጥፎ ስለሚባል ኣይመስለኝም። ችግር ያመጣው ኣውጫጭኝ ኣይነት በመሆኑና ከሲስተምና ከፖሊሲ ይልቅ በግለሰቦች ባህርያትና ክህሎት ብቃት ላይ ያተኮረ በመሆኑ እንዲሁም የግምገማው መስፈርት የጠራ ባለመሆኑ የግለሰቦችን ግላዊ ህይወት ሳይቀር ኣደባባይ በማውጣቱ መዘበራረቅን ኣምጥቶ ነበር።

“ኢሃዴግ” ግምገማ ሲል በጣም የሚብከነከነው በኣክተሮቹ ፣ በሲስተሙ ተዋንያን ላይ በመሆኑ የግለሰቦቹን ድክመትና ጥንካሬ በኣደባባይ ኣውጥቶ መወያየት ኣንድን የስራ ሃላፊ ወይም ባለሙያ ያለውን ጠንካራ ጎንና ደካማ ጎን ኣብጠርጥሮ በገበያ ላይ ማውጣት ነው ትልቁ ግምገማ።  የሰውን ልጅ ይለውጠዋል የሚል እምነት ኖሮት እንደሆነ ኣላውቅም። የግምገማው ስነ ልቦና ትንሽ ለየት ይላል።ግለሰቦች ባህርያቸውን በጥልቀት ይገመገማሉ። በተለይ በፖለቲካ  ድርጅቶች ኣካባቢ የሚበሉበትን የሚጠጡበትን ቤት ሁሉ እያነሱ ማብጠልጠል ሁሉም በየማስታወሻው በኣንድ ኣባል ላይ የያዘውን እያወጣ ድክመት ነው ያለውን በጉባዔ ፊት ለዚያ ሰው መግለጥ ዋና ተግባር ነው።ህወሃት በግለሰቦች በተለይም በታችኛው ኣካል ኣካባቢ ግምገማውን ያብዛ እንጂ እንደ ድርጅት እንደ ሲስተም ሲበዛ ሚስጥረኛና ግልጽነት የጎደለው ድርጅት ነው።

“የኢህ ኣዴግ” ኣይነቱ ግምገማ በሌሎች ኣገሮች ከሚደረጉ ግምገማዎች ሁሉ የሚለይ ይመስላል።  በግምገማ ክህሎትን፣ ባህርይን ለማረቅ የሚሞክር ኣካሄድ ይመስላል። የድርጅት ኣባላት ሲናገሩ በኣንድ ሰው ዙሪያ ሁለት ቀን ድረስ የሚፈጅ ግምገማ የሚደረግበት ጊዜ ኣለ። ውሳኔ ያንስሃል፣ ትፈራለህ፣ ታዳላለህ፣ ከእከሊት ጋር ትወጣለህ፣ ብስለትና እድገት ኣይታይብህም፣ ሙስና ውስጥ ገብተሃል፣ ከእከሌ ጋር ያለህ ቅርበት በዝቱዋል፣ ከእከሌ ጋር ለምን ተኳረፍክ፣ ትኮራለህ፣ ኣድርባይ ነህ፣ ወዘተ ወዘተ…. እየተባለ የሚገመገም ብዙ ሰው ኣለ። ኣባላት ሁሉ እየተነሱ ግለሰቡን ቁጭ ኣርገው ያብጠለጥላሉ። ሂስህን ዋጥ፣ ኣልውጥም… ዋጥ፣ ኣልውጥም…  ብዙ ሰዓት ይፈጅና ተገምጋሚው “ውጫለሁ” ካለ ይታለፍና ሌላው በተራው ደግሞ እንዲሁ  ይብጠለጠላል። ኣንዳንዴም ኣባላት በሆነ ነገር ያናደዳቸውን ሰው ለማጥቃት ሲያስቡ በዚያ ሰው ዙሪያ ሲሰልሉ፣ ድክመት የተባሉትን ሲያሰባስቡ ይቆዩና በግምገማው ሰዓት  ኣንጀታቸውን የሚያርሱበት መድረክ እንደሆነም ይነገራል። በኣጠቃላይ እምነቱ ግን የሰዎችን ድክመት በተለይ በኣደባባይ በማውጣትና በመግለጥ የሰው ልጅ ይማራል፣ ምን ኣልባትም በግል በሱፐርቪዥን ከሚድረገው ግምገማ ይልቅ በኣደባባይ በቡድን ፊት መጋለጡ ለባህርይ ለውጥ የተሻለ ነው የሚል ነገር ይመስላል። ኣጠቃላይ ሂደቱ ባህርይንና ክህሎትን ለመቅረጽ ነው ብለን በቅንነት እንውሰድና በተግባር ግን በተለይ በሃገር መሪዎች ኣካባቢ ሰፋ ባለው በሃገር ደረጃ በርግጥ ይህ ኣካሄድ የሚፈለገውን ለውጥ ያመጣል ወይ? ህወሃት “ኢህዓዴግ” በዚህ የግምገማ ስልቱ የተሻሉ መሪዎችን ኣፈራልን ወይ? ኣገራችን መሪዎችን ኣገኘች ወይ? ግልጽነትና ተጠያቂነት እያደገ ሙስና ቀነሰ ወይ? ኣድረን ወደ ዴሞክራሲ ተመነደግን ወይ? የሚለውን መገምገም ተገቢ ነው።  ግምገማ ቀላል ነገር ኣይደለም። ፍርድ ነው። ለዚህ ደግሞ ከፍ ያለ ተመልካችነትን የሙያ ቅርበትን ይጠይቃል። “ኢህኣዴግ” ግምገማ የሚለው እርስ በርስ ከተሞሸላለቁ በሁዋላ ሂስ በመዋጥና ባለመዋጥ የሚቋጭ ነው ። ከዚህ በላይ ግን የግምገማው ውጤት  ከፍትህ ጋር  ጥብቅ ቁርኝት የሌለው ተገንጥሎ የወጣ ነው። ለማናቸውም ግን ግምገማው ጥሩ ነው ጥሩ ኣይደለም ከሚለው በላይ ለዛሬው ጽሁፍፌ መነሻ የሆነኝ ምን ትርፍ ኣገኘን? የሚለው ጉዳይ ነው ::

ከፍ ሲል እንዳልኩት “ኢህኣዴግ”  ከተፈጠረ  ጀምሮ ከዚያም በፊት በህወሃት ጊዜ ግምገማ በተለይም በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ግምገማ የሚካሄድ ሲሆን በርግጥ ከዚህ ፍሬ ኣግኝተን መሪዎችን ኣፈራን ወይ?  መሪዎቹ ክህሎት ጨመሩ ወይ? ትህትናና ዴሞክራሲ፣ የህግ የበላይነት በመሪዎቹ ኣካባቢ እያደገ መጣ ወይ? ብለን ኣጥብቀን መጠየቅ ኣለብን። ኣቶ ኣባዱላ ገመዳ ላለፉት ሰላሳ በላይ ኣመታት የሰላ ግምገማ ተካሂዶባቸው ኣሁን ክህሎት ጨምረዋል ወይ? ። “ኣዎ!” ከተባለ ከሰላሳ ዓመት በፊት ምን ዓይነት ሰው ነበሩ ማለት ነው? ብለን እንደመማለን። ለኣርባ ኣመት ገደማ የተገመገሙት እነ ኣባይ ጸሃየ፣ እነ ሳሞራ፣ እነ ስዩም ወዘተ በዓርባ ዓመት ግምገማ ውስጥ ኣልፈው ለምን የተሻለ ስብእና ኣላዳበሩም? እነ ኣዲሱ ለገሰና እነ ስብሃት ነጋ ሌሎች መሪዎች በዚህ ግምገማ ተወቅረው…. ተወቅረው …..ተወቅረው….. ምን ወጣቸው?  እንዴውም በተግባር የምናየው ህግን ሲጥሱ፣ ኣድረው ጭካኔ ሲያሳድጉ፣ ዴሞክራሲ እንዳያድግ ሲያደርጉ ነው። ይህን ስናይ የዚህ “የኢሃዴግ” ግምገማ ጉዳይ የሆነ ችግር ያለበት መሆኑን እንረዳለን። በዚህ ዙሪያ ነው ኣንዲት ትንሽ ኣስተያየት ለማቀበል  የፈለኩት። ቅን የሆኑ “የኢሃዴግ” ኣባላትም ይሰሙኛል ብየ ኣምኜ ነው።

በሃሳብ ደረጃ እንዲህ ኣይነቱ ግምገማ ጥሩ ቢመስልም የሳተው ትልቁ ነገር ግን ሊፈጥር ያሰበው ስብእና መያዣ ኣቁማዳ ተበጅቶለት ኣናይም። የግምገማው ሂደት “ኢሃዴግን”  ራሱን እንደ ድርጅት በሲስተምና በፖሊሲ ደረጃ ኣብጠርጥሮ ከመገምገም ይልቅ በኣክተሮቹ፣ በግለሰቦቹ የግል ባህርይና ክህሎት ላይ በማተኮሩ የሰላሳ ኣመቱ ግምገማ ፍሬ ኣላመጣም። ኣንዳንዶቹን እንዴውም በደንብ ኣድርጎ ያደነዘዛቸው ይመስላል። ግምገማን ከመልመዳቸው የተነሳ “ሂሴን ውጪያለሁ” ምንትሴ…… እያሉ ማለፉን መርጠው ለውጥ ሳይመጣ ቀርቶኣል። ኣንዳንዶቹም የሰው ሃጢያት ሲዘረዘር ደስ እያላቸው የግምገማ ጊዜ ሱስ የሆነባቸው ይህን ጊዜም የሚደሰቱበትም እንዳሉ ይሰማል። “የኢሃዴግ” ግምገማ ውጤታማ እንዳይሆን ያደረገው በግምገማ መድረኩ ለማጠብ የሞከረውን ኣባላቶቹን ኣጣጥቦ ኣመድ ላይ  መጎለቱ ነው።። ለምሳሌ ኣንድ የፖሊስ ተጠሪ ለህገ መንግስቱ ታዛዥ ኣይደለህም  ወዘተ….. ተብሎ ቢገመገምና ሂሱን ውጦ  ከመድረክ ቢመለስ ነገ የት ነው የሚገባው? መቼ ፖሊስ ራሱ ነጻ ተቋም ሆኖ ተፈጠረ?   የብር ዋጋው ሲወርድ (devaluate ሲደረግ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሃላፊ ሳያውቅ በሚወሰንበት ኣገር እንዴት ሆኖ ነው ይህ የባንክ ሃላፊ ውሳኔ ያንስሃል፣ ኣቅም ያንስሃል፣ ወዘተ እየተባለ ሊገመገም የሚችለው? በነጻነት መፍረድ በማይቻልበት ኣገር እንዴት ሆኖ ነው ኣንድ ዳኛ በሙያው የሚገመገመው? ዋናው ችግር ይህ ተቋም ነጻ ኣለመሆኑ ሲሆን ግለሰቡን ገምግመው ኣብጠልጥለው ሂሱን ኣስውጠው ቢልኩት ነገ ሄዶ የሚቀመጠው ኣመድ ላይ ነው። ለዚህ ነው ግምገማው ሲስተሙን ራሱን ጨክኖ የሚፈትሽ ባለመሆኑ የግለሰቦች ኣውጫጭኝ ሆኖ የሰላሳና የኣርባ ዓመት ፍሬው ባዶ የሆነው።

“ኢሃዴግ” ባለፉት ኣመታት ከግለሰቦች ኣውጫጭኝ ይልቅ ሲስተምን የሚያይ “የኢሃዴግን” ተፈጥሮና ፖሊሲዎቹን በሚገባ የሚገመግም ቢሆን ኣገሪቱ ወደ ተሻለ ዴሞክራሲና ልማት ታድግ ነበር። “ኢሃዴግ” ጨክኖ ራሱን እንደ ሲስተም እያየ ምርጫ ቦርድን ነጻ ኣድርገን ፈጥረናል ወይ? ወታደሩ ነጻ ነው ወይ? ፍርድ ቤት ውስጥ ጣልቃ ኣንገባም ወይ?  ባንኮችና ኣጠቃላይ የሃገሪቱ ተቋማት በነጻነት ይሰራሉ ወይ?  ህወሃት “በኢሃዴግ” ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ምን ኣደረገው? ይህ ትክክል ኣይደለም! የብሄር ፖለቲካ የመጨረሻ ግብ ኣለው ወይ?   እኛ ራሳችን ተሰባስበንበታል የምንለው “ኢሃዴግ” በርግጥ በዚህ ዓለም በህይወት ኣለ ወይ?  በኢትዮጵያዊነት ጽንሰ ሃሳብና “በኢሃዴግ” ተፈጥሮ መካከል ያለው ዝምድናና መስተጋብር ምን ይመስላል? የቱን ያህል ጥብቅ ነው? ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ ምንድነው? በህገ መንግስቱና በኣብዮታዊ ዴሞክራሲ መካከል ምን ዝምድና ኣለ? የብሄር ፖለቲካና የዴሞክራሲ መርሆዎች ኣብረው ይሄዳሉ ወይ? ህወሃት ለዖህዴድ ምኑ ነው? ወዘተ… ደግሞም ግምገማ በጣም በበዛበት ዘመን በሃገራችን የነበረ ጉቦ እንዴት ወደ ሙስና ያድጋል? እጅግ ብዙ ጥያቄ ለማኝ የሆኑ ጉዳዮች ስላሉ እነዚህ በሚገባ ቢገመግሙ የተሻለ ቤት መስራት ይቻል ነበር። ማህበራዊ ሃብትን የሚንከባከብ የህብረተሰቡን ኢነርጂ የማይቃረን ስርዓትና ፖሊሲ ከተፈጠረ በዚያ ውስጥ የሚኖረው ግምገማ የተሻለ ፍሬ ባመጣ። በመከላከያ ኣካባቢ በኢኮኖሚው ኣካባቢ የህወሃት የበላይነት መታየት የለበትም፣ ኣንድ ግለሰብ ሰረቀ ተብሎ ለሁለት ቀን የሚገመገም ከሆነ የህወሃት ድርጅታዊ ሙስና ለምን በሰፊው ኣይገመገምም?  የመሳሰሉትን ስናይ የዚህ መንግስት ትልቅ ችግር ግምገማው ሲስተሙን ጨክኖ  የሚገመግም ኣለመሆኑ፣ የሚፈራ በመሆኑ ነው። ሲስተምን ችላ ብሎ ሙስና በተጠናወተው ሲስተም ውስጥ ጥሩ መሪዎችን ለማውጣት መሞከር ኣይቻልም። ታጥቦ ጭቃ ነው የሚሆነው።በድርጅት ህይወት ውስጥ መጀመሪያ መታየት ያለበት ቤቱ ንጹህ ተደርጎ መሰራቱን ነው። ቤቱ ካልጸዳ በውስጡ ያሉት ኣይጸዱም:: ዝም ብለን ብንቀጥል ደግሞ እጥበቱ  ድብኝት ኣጠባ ነው የሚሆነው።

በሃገራችን ኣጠቃላይ የፖለቲካ ቅርጽ ኣካባቢ ይህ ችግር ይታየኛል። ሃገራችንን ኢትዮጵያን ተፈጥሮዋንና ማንነቱዋን በሚገባ መረዳት፣ ያለፈችበትን ህይወት በሚገባ መገምገም ችግሮቹን ኣንጥሮ ማውጣት የቀረን ይመስለኛል። ለዚህም ነው ዛሬ ኣንዱ የብሄር ጥያቄ ኣንዱ የግለሰብ እያለ በሁለት ውጥረት ውስጥ የወደቀችው። ችግርን በሚገባ ኣለመለየትና ኣለመገምገም ወደፊት ለምንሰራው የፖለቲካ ቤትም ሆነ ፖሊሲ ተጽእኖው ከባድ ነው። በመሆኑም “የኢሃዴግ” ኣባላት ጨክነው “ኢሃዴግን” ተፈጥሮውን የህወሃትን ግዝፈት የተቋማትን ነጻነት ኣብጠርጥረው ቢገመግሙ ነበር የምንለወጠው። ይህ ግን ኣልሆነም። ህወሃት በግምገማ ስም የበታቾቹን እያመሰ የሃገሪቱን ሃብት ሲቦጠቡጥ ነው የሚታየው። “ኢሃዴግ” በግለሰቦች ኣካባቢ ግምገማ ጊዜ ያለውን ጭካኔ በሲስተም ላይ ማሳየት ኣይፈልግም። እንዴውም ግምገማን የማይፈልገውን ሰው ለመቅጫም ጥሩ መሳሪያ ኣድርጎ በሚገባ ሲጠቀምበት ይታያል።

“ኢሃዴግ” ቁጭ ብሎ ግምገማውን ራሱን መገምገም ነበረበት። ኣርባ ኣመት የተገመገሙትን ሰዎች እያየ ለምን ወደ ፍጹምነት የተጠጋ ስብእና ኣላዳበራችሁም ብቻ ሳይሆን እንዴት በዚያ ግምገማ ውስጥ ኣልፋችሁ ክፋትንና ተንኮልን ትጨምራላችሁ? ብሎ መጠየቅ ካልቻለ  እሴት ኣልጨመረም። ነጻ ያልሆኑት ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ውሳኔ ላይ ደካማ ነዎት፣ ይህን ጉዳይ በሚገባ ኣልተወጡም ሊባሉ ኣይችሉም። ከዚህ ይልቅ “የኢሃዴግ” ኣባላት ቆራጥ ቢሆኑ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይል የላቸውም! እንደ ቃል ኣቀባይ ኣይነት ነው ስራቸው በሚል የህወሃትን ጣልቃ ገብነትና እጅ ኣዙር ኣገዛዝ መገምገም ፍሬ ያመጣ ነበር። ለኚህ ሰው የፈጀው ሰፊ የግምገማ ሰዓት ድራማ ከመሆን   የሚያልፈው ተገምግመው ሲያበቁ ነጻ በሆነ የሃላፊነት ወንበር ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ነበር። የቡድን ኣመራርን መቃወሜ ኣይደለም። ይሁን እንጂ በቡድን ኣመራር ስም የህወሃት ፈቃድ ብቻ በሚፈጸምበት ኣገር የኣቶ ሃይለማርያም ድርሻ ከቃል ኣቀባይነት ያለፈ ስራ ስለማይሆን ይህን ደፍሮ የሚሰብር ጠንካራ ግምገማ ያስፈልጋል።

 

በግምገማ ጊዜ ስለ ሙስና ተነስቶ ሰዎች ይወቀሳሉ። ኦዲተሮች ግን በነጻነት ኣይሰሩም። ኣንዳንዱ በሙስና የሚገመገመው ኦዲት በማይደረግ መስሪያ ቤት ነው። ኦዲት ተደርጎ የኦዲት ሪፖርቱ በማይታወቅበት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ኣንዳንድ ግለሰቦችን በግምገማ ላይ ማንሳቱ  ምን ኣልባትም በሙስና ስም ለማጥቃት ካልሆነ ፍሬ የሌለው መሆኑ ይታወቃል። ሳይንሳዊ ይሁን ስንልም በኣሰራርና ስራንና ሰራተኛን በማገናኘት ሊስተካከሉ የሚችሉትን በቡድን ኣውጫጭኝና ሂስህን ዋጥ ኣልውጥም ሊስተካከል ኣይችልም።

ከዚህ በፊት ኣንድ የብዓዴን ኣባል ኣናግሬ ኣውቃለሁ። ይህ ሰው በድርጅቱ ውስጥ ስልጣን ያለው ነው። እንዴውም የድርጅት ጉዳይ ሆኖ ነበር። እንዴት ነው እናንተ ብዓዴኖች ህወሃትን ኣታሙትም ወይ ? ብየ ጠየኩት::  በደንብ ነው ውጭ ውጭውን የምንንሾካሸከው ብሎኛል። ኦህዴድም እንደዚሁ ነው። ይህ የሚያሳየው በጣም በተበላሸ ሲስተም ውስጥ ነው ግለሰቦች እየተብጠለጠሉ ያሉት። ይህ ደግሞ  ለድርጅቱም ለሃገርም ለውጥ ኣያመጣም።

ኣንዳንዱ ሰው ደግሞ የሚወቀሰው ከተፈጥሮው ክህሎት ጋር በተያያዘ ነው። ውሳኔ ያንስሃል ሲባል ይህ ሰው  ወስን…. ወስን…. ወስን…… ስለተባለ ኣይደለም የሚወስነው።ውሳኔ  በኣብዛኛው መረጃን ከመረዳትና ከመገምገም ጋር ነው የሚያያዘው።በተለይ በከፍተኛ ስልጣን ላይ ያለ  ሰው ውሳኔ የሚያጥረው ብዙ ጊዜ የሚመጡ መረጃዎችን የመተንተንና  በኣእምሮ የመሳል ኣቅም ሲያጥረው ይመስለኛል:: ባለስልጣን ሆኘ ባላየውም። የውሳኔና ኣመራር ችሎታ በትምህርትና ከተፈጥሮም ጋር ከተያያዘ ተሰጥዖ ጋር ሊሄድ ይችላል። በስብሰባ ኣባላት ስለጮሁበት ኣይደለም። በዚህ መልኩ የመሻሻል እድል ጠባብ ነው የሚሆነው። ኣንዳንዱ ሰው ትላልቅ ፒክቸሮችን በኣይምሮው የማየትና የመደመም(a strong impression) ብሎም ውሳኔ የመስጠት ተሰጦ ላይኖረው ይችላል። ፖሊሲ ውሳኔ ነው። ሚሊዮን ህዝቦችን ተጽእኖ ሊያደርግ የሚችልን ፖሊሲ ሲያመጡ ወስነው ነውና ለዚህ ምናብ ኣስፈላጊ ነው። በሌላ በኩል ቴክኒካል የሆኑ ጉዳዮችን የመፈጸም ኣቅምና ፍላጎት ያላቸው ለዚህ ስራ ስሜታቸው የሚነቃቃ ሰዎች ደግሞ ኣሉ። በመሆኑም ስራና ሰራተኛን ማገናኘት የሚፈታውን ችግር “ኢሃደግ” ከየቦታው ታዛዞቹን ይሰበስብና የማይገባ ቦታ እየሰጠ እንደገና ደግሞ ኣቅም ኣነሰህ እያለ ይገመግማቸዋል። ስራና ሰራተኛን ማገናኘት በራሱ የሚፈታቸውን ጉዳዮች ችላ ማለት ኣገራዊ ኪሳራው ሰፊ ነው።

በየደረጃው ያሉ ባለስልጣናት መረጃዎችን የሚያዩበት መጠነ ርእይ ይለያያል። የታችኛው ኣካል በተወሰነ ኣጥር ውስጥ የሚያይ ሲሆን ወደ ላይ ከፍ ያሉ ባለስልጣናት ደግሞ በሰፊ ስኮፕ ያዩታል። ከፖሊሲና ከማህበራዊ ተጽእኖ (Impact) ጋር ስለሚያዩት የሚደመሙት በዚህ ሰፋ ባለ ተጽእኖና  በዚያ ተጽእኖ ውጤት ላይ ነው።  ለዚህ የሚመጥኑ ሰዎችን በየደረጃው ማስቀመጥ የተሻለ ሲሆን በፖለቲካ ታማኝነት ብቻ ኣንዱን የቴክኒክ ሰው ሚንስትር ማድረጉ ኣገሪቱን በጣም ጎዳት። ከግምገማ ይልቅ በትምህርት ሊበለጽጉ የሚችሉትን መለየት፣ ግምገማውን ሳይንሳዊ ማድረግ ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን በተለይ ሲስተምን የማጽዳት ስራ መስራት ጠቃሚ ነበር። ስኮፕ የሌላቸውን ሰፋ ኣድርገው ማየት የማይችሉትን ኣጉሮ ኣጉሮ ምንም ለውጥ ማምጣት ኣይቻልም። በተበላሸ ፖሊሲ ስር የቱንም ያህል የግለሰብ ግምገማ ብናካሂድ ኣንለወጥም።ኢትዮጵያ ትታየናለች ወይ?  የጥንት ኣባቶች ድካም ይታየናል ወይ?  ስለ ሃገሪቱ ማንነት ስናስብ የጠራ ስእል ኣለን ወይ? እያልን የሚሾመው ቢሾም ይሻል ነበር።  ኣንድ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻን ሲለምን እኔ ተራው ሰውና ኣንድ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ሰው ብናገኝና ብናናግር የሁለታችን ምናብና መደመም መለያየት ኣለበት። እኔ ካለኝ ኣካፍየ ካልሆነ ኣዝኘ እሄዳለሁ። ያ ባለስልጣን ግን ከፍ ካሉ ሃገራዊ ጉዳዮች ጋር ኣገናኝቶ ኣገራዊ ተጽእኖ ሊፈጥር የሚችል ስእል ሊያይ ይገባል። በዚያ ጎዳና ተዳዳሪ ህጻን ምላሽ ፖሊሲን እስከማስቀየር በሚደርስ ሃይል ይህ ባለስልጣን ሊመሰጥበት ሊመታበት ይገባዋል። ስኮፕ እንዲህ ነው። ኢትዮጵያንም ኣጠቃላይ ኣካሉዋን በሚገባ የማየትና የመረዳት ብቃትን ይጠይቃል። ከዚህ ውጭ በኣካባቢያችን ያለችውን ችግር ኣይተን በዚያችው ዙሪያ የፖለቲካ ድርጅት መስርተን ለዚያች ችግር መፍትሄ ለማምጣት ብቻ የምንሞት ከሆነ ኢትዮጵያን ለመምራት ኣንመጥንም። መሪዎቻችን ባደጉበት ኣካባቢ ያዩትን ችግር በሰፊ ምናብ ካላዩት በብሄር ፖለቲካና በኢትዮጵያዊነት መካከል ውጥረት ውስጥ ገብተው ራእይ ኣጥተው ሊኖሩ ይችላሉ። ምናብ ለመሪዎቻችን በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ታላቁ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ኣንዱ ትልቁ ችሎታቸው ደቡብ ኣፍሪካን በይቅርታ መሰረት ላይ ቆማ በጠራ ምናብ ማየት መቻላቸው ነው። በጣም ግትር ከሆነ የፍትህ ኣስተሳሰብ ኣውጥቶ በዚህ ከፍታ ላይ ያስቀመጣቸው ምናባቸው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም እንዲህ ዓይነት መሪዎችን እንሻለን።

ትልቅ ችግር ያመጣው “ኢሃዴግ” እንደ ድርጅት ራሱን ኣለማየቱ ብቻ ሳይሆን ይህ ኣካል ስልጣን ላይ በመሆኑ ተጽእኖው ኣገራዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረጉ ኣሁን ላለንበት ውስብስብ ችግሮች ቀንደኛ ምክንያት ሆነ። የተቋማትን ነጻነት ለመገምገም ወይም የፓርቲውን ጣልቃ ገብነት ለመገምገም ባለሞሞከሩ ዛሬ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ገለልተኛ ኣልሆነም። ዛሬ “ኢሃዴግ”በኣምስተኛው ዙር “ምርጫ” በኦሮሚያ፣ በኣዲስ ኣበባ፣ በትግራይ፣ በኣማራ በደቡብ መቶ በመቶ ማሸነፉን ሲሰሙ “ኢሃዴጎች” ዴሞክራሲ ኣደገ ነው የሚሉት? ያ “ግምገማ” በርግጥ ሃቀኛ ከሆነ የዚህ ድርጅት ኣባላት እምቢኝ ማለት ነበረባቸው።ይህቺን ጽሁፍ ስጭር የቅርቡን የምርጫ ውጤት ሲሰሙ ኣንዳንዶቹ “የኢሕዓዴግ” ኣባላት ምን ይሉ ይሆን? ብየ ኣስቢያለሁ። እውነተኛ ለኣገር ኣሳቢ የሆነ ፓርቲ ውስጥ ነው ያለሁት የሚል ለኣገር ኣሳቢ የሆነ “የኢህዓዴግ” ኣባል በግምገማ ወጥሮ መጠየቅ ኣዲስ ምርጫ መካሄድ ኣለበት ኣለያ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ነበረበት፣ ኣልነበረበትም?::  በዴሞክራሲ የሚያምኑ ከሆነ ፣ ከዴሞክራሲ መገለጫዎች መካከል ኣንዱና ዋነኛው ምርጫ ሲሆን ውጥንቅጡ በወጣና ተዓማኒነት በጎደለው ምርጫ መቶ በመቶ ኣሸነፍኩ ሲለኝ በርግጥ ለዚህ መሞት ኣለብኝ።መቶ በመቶ ኣሸነፍኩ ብሎ “ኢሃዴግ” ሲያውጅ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የሆነ የዚህ ፓርቲ ኣባል ድግሱን ኣይበላም። ኣይበላም ብቻ ሳይሆን ይህ ታሪክ እንዲገለበጥ ኣጥብቆ ይሰራል። ኣለያ ቢሞት ይሻለዋል። ኣሁንም ቢሆን ሃቀኛ የሆኑ የኢህዓዴግ ኣባላት ለለውጥ መታገል ኣለባቸው። በስማቸው የሚነግዱትን ጥቂት የበላይ ኣካላት በመፍራት ዝም ማለት የለባቸውም። ለለውጥ ለተሻለ ስርዓት በቻሉት ኣቅም መታገል ኣለባቸው። ህዝባዊ እምቢተኝነት ሲነሳ ከህዝብ ጎን በመቆም ትግሉን ማፋጠን ይጠበቅባቸዋል። ፖሊሶች፣ ዳኞች፣ የባንክ ሰራተኞች፣ ወታደሮች፣ በኣየር ሃይል ኣካባቢ የሚታየውን ኣይነት ትግል ማፋፋም ኣለባቸው። ይህን በማድረጋቸው ከህሊና ፍርድ ነጻ መሆን ብቻ ሳይሆን ከለውጥ ባሻገር ኢትዮጵያ ትኮራባቸዋለች።

 

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

geletawzeleke@gmail.com

 

 

The post የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው – ገለታው ዘለቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕሬዝደንት ኦባማ ጉዞአቸዉን እንዲሰርዙ ለመጠየቅ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ

$
0
0

ቃልዎን ጠብቆ መገኘት

“እፍሪካ ጠንካራ የዲሞክራሲ ተቋም እንጂ ጠንካራ አምባገነን መሪ አያስፈልጋትም”

የአሜሪካ ፕረዝዳንት ባራክ ኦባማ በመጭው ሀምሌ ወር ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የያዙት ፕሮግራም ስለህዝቦች ሰብአዊ መብት መገፈፍ የሚናገሩት ለይስሙላ እንጂ በተግባር ግድ እንደማይሰጣቸው ያሳያል። ዜጎችን በመጨቆን፣ ጋዜጠኞችን በማሰር፣ የዉሸት ምርጫ በማካሄድ፣ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በማፈራረስ እና አባሎቻቸዉን በማሰር እንዲሁም በመግደል፣ የአገርን ሃብት ለጢቂቶች መበልጸጊያ በማድረግ፣ አብዛኛዉን ምስኪን ዘጋ ተስፋ አቶ ካገር እየተሰደድ ለሞትና ለባርነት በመዳረግ ወዘት የሚያዉቁትን የወያኔ ኢሃደግ ስርኣትን እንደመልካም የአፍሪካ አስተዳደር ቆጥሮ መጨባበጥ እና በቤተመንግስት መገባበዝ አግባብ እንዳልሆነ አስቀድሞ ለማሳሰብ እና ጉዞአቸዉን እንዲሰርዙ ለመጠየቅ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ

ቀን   አርብ ጁላይ ፫
ሰአት   ፱ ኤ ኤም
ቦታ   ሗይት ሃውስ

 

protest-against-obama-visit-628x941

The post ፕሬዝደንት ኦባማ ጉዞአቸዉን እንዲሰርዙ ለመጠየቅ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ የሚሳተፉ ከተለያዩ የካናዳና የአሜሪካ ከተሞች የመጡ ቡድኖች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ በፎቶ ግራፍ::

$
0
0

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ የሚሳተፉ ከተለያዩ የካናዳና የአሜሪካ ከተሞች የመጡ ቡድኖች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ በፎቶ ግራፍ::

11214209_897954850276722_4524430455891172151_n - Copy 11228121_897954766943397_4460564768293891951_n - Copy 1506069_897954783610062_4937945577979240180_n - Copy 11403234_897954980276709_8091184175990810284_n - Copy 11692648_897954726943401_22432999789610882_n - Copy 11659455_897954570276750_4538163869172761761_n - Copy

The post የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ የሚሳተፉ ከተለያዩ የካናዳና የአሜሪካ ከተሞች የመጡ ቡድኖች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ በፎቶ ግራፍ:: appeared first on Zehabesha Amharic.

32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በሜሪላንድ በድምቀት ተከፈተ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ በሜሪላንድ በርድ ስታዲየም በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በድምቀት ተከበረ::

ethiopia soccer 4

ethiopia soccer 3

ethiopia soccer 2

ethiopia soccer 1

ከአሜሪካ እና ከካናዳ የመጡ ከ30 በላይ ቡድኖች በስታዲየሙ በመገኘት በዚሁ በመክፈቻ ዝግጅት ላይ ራሳቸውን አስተዋውቀዋል:: በዚህ ዝግጅት ላይ ለእንግሊዙ አርሰናል ክለብ እየተጫወተ የሚገኘው ጌድዮን ዘላለም የተገኘ ሲሆን ከሕዝቡም ደመቅ ያለ አድናቆት ተችሮታል::

በዚሁ የመክፈቻ ዝግጅት የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ባሰሙት ንግግር የዘንድሮው ዝግጅት በርካታ ሕዝብ በመገኘት በመከፈቱ መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት ደማቅ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል:: እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ረቡዕ ምሽት የብሄራዊ ትያትር 60ኛ ዓመት በዓል በታሪካዊ ሁኔታ ይከበራል; የፊታችን ሐሙስ አርብና ቅዳሜም ከ እግር ኳሱ በተጨማሪ ታላላቅ አርቲስቶች የሚገኙባቸው ትልልቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንደተዘጋጁና ሕዝቡም በነዚህ ስፍራዎች እየተገኘ እንዲዝናና ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 32ኛ ዓመት በዓል መታሰቢያነቱ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ላለቁት ኢትዮጵያን መታሰቢያ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተወካይ ባሰሙት ንግግር የሊቢያውን ሰቆቃ አስታውሰው “እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አይረሳትም” ብለዋል::

የመድሃኔዓለም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተወካይ ቄስ በሪሁን መኮንን በሊቢያው ሰቆቃ ሊያስተምረን ስለሚገባ ነገር ተናግረዋል:: የሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ልዩነት ሳይበግራቸው በአንድነት በመቆም ሊሰሩ እንደሚገባ ይህ ሃዘን አስተምሮናል ብለዋል:: በሰሜን አሜሪካ የሙስሊም ኮሙዩኒቲ ተወካይ ሼክ ሱለይማን ነስረዲን በበኩላቸው በሊቢያ የተገደሉት ወገኖች የተገደሉት ክርስቲያን በመሆናቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሃይማኖቶች መከባበር ለመጠቆም ሞክረዋል::

በዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ የላስቬጋሱ አበበ ቢቂላ የሲያትሉን ዳሸን 2ለ0 – ዴንቨር የሚኒሶታውን ኒያላ 4ለ0 – ቺካጎ ፒላደልፊያን 2ለ1 – ኦሃዮ ቦስተንን 4ለ1 ሲያሸንፉ የሎሳንጀለሱ ዳሎል የዲሲው ዩናይትድ 1ለ1 እንዲሁም የሎሳንጀለሱ ስታርስ ከሜሪላንዱ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር 1ለ1 ተለያይተዋል::

ethiopia soccer 5
በሌላ በኩል የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሃፊ አቶ ያሬድ ነጋሽ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት በዛሬው የመክፈቻ ዝግጅት መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት በርካታ ሰው እንደሚገኝ ያላቸውን ግምት ገልጸዋል:: በሃይማኖት አባቶቹ መል ዕክት መደሰታቸውንም ገልጸዋል::

በድምቀት የተከፈተው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫልን በስፍራው የሚገኙት የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች በየቀኑ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይዘግቡላችኋል::

The post 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በሜሪላንድ በድምቀት ተከፈተ appeared first on Zehabesha Amharic.


የህብር ሬዲዮ ሰኔ 21 ቀን 2007 ፕሮግራም 32ተኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ቬስቲቫል በደማቅ ሁኔታ መከፈትን አስመልክቶ ውይይት ከጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ እና ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር የመክፈቻውን ስነ ስርዓት በተመለከተ ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡት)

$
0
0

Habitamu<…የእንግሊዝ መንግስት ያወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያውአን ያላሰለሰ አቤቱታ ውጤት ነው። ወያኔ ያንን ተከትሎ ደህና ነው ማለቱ የሚታመን አይደለም ደህና ከሆነ ለምን አያሳዩትም …ለመጀመሪያ ጊዜ ለእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት ደብዳቤ አስገብተናል ክርክራችን አቤቱታችን ከእንግሊዝ መንግስት ጋር ነው ይህንኑ ደብዳቤ ሰሞኑን…>  ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የአቶ አንዳርጋቸው ታላቅ እህት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ማስጠንቀቂያን ተከትሎ የኢትዮጵያው አገዛዝ በሰጠው ምላሽ ላይ አነጋግረናቸው ከሰጡን  (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ሕወሃት የፕ/ት ኦባማ መምጣት የምርጫችንን ዲሞክራሲያዊነት ያሳያል እያለ ሲቀሰቅስ ሕዝቡ ግድ አልሰጠውም …የኦባማ መምጣት የስርዓቱን አፈና የሚያበረታታ ነው ባይመጡ ጥሩ ነበር የግድ ከመጡ ግን ለስርዓቱ ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለባቸው። በውጭ ያለው ወገን ኦባማ እንዳይመጡ የሚያደርገው ጥረት መቀጠል አለበት…>

አቶ አምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ  የፕ/ት ኦባማ አፈና ወደ ነገሰባት ኢትዮጵያ ይሄዳሉ መባሉን በተመለከተ ከተናገረው( ሙሉውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ)

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄደው የሰብአዊ መብት ረገጣ በተመለከተ አርብ ዕለት ያወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ዳሰሳ

<<በኢትዮጵያ ውስጥ የጸጥታ ሀይሎች ከሕግ በላይ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ስለመብት መከበር መጠየቅ የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል >> የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት (ልዩ ዳሰሳ)

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ሕጋዊነት ማጽደቁ የአገሪቱን ማህበረሰብ ከሁለት ከፍሎ ማወዛገቡና ዓለም አቀፍ አንድምታው

አክራሪው አይሲስ ሰሞኑን አራት ግብረ ሰዶማውያንን በዘግናኝ ሁኔታ መግደሉን ይፋ ማድረጉ

<<ግብረ ሰዶሞችን ካልተቀበላችሁ እያሉ በእርዳታ ስም የሚያስፈራሩን እኚህ ፕ/ት ባራክ ኦባማን ለመሆኑ ማን ነው የወለዳቸው ? እዚህ አገር ዮሃንስን ከዮሃንስ ጋር ማሪያን ከማሪያ ጋር ማጋባት በጭራሽ አይሞከርም>> የዙምባብዌው ፕ/ት ሮበርት ሙጋቤ( ልዩ ጥንቅር)

የባሻ ይገዙ ትዝብት በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ላይ (ግጥም)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የሕወሓት መሪዎች የአዲስ አበባና የትግራይ በሚል በሁለት ተማድነው በስልጣን ሽኩቻ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

የአቶ አንዳርጋቸው ልጅ በወላጅ አባቷ መታሰር ዙሪያ ለንደን ውስጥ ተውኔት ተጫወተች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ከድል በሁዋላ በጉልበት ሰጭ እጽ ሳቢአ ከአውሮፓ ውድድር ታገደች

የታንዛኒያ ፖሊስ ከአምስት የተለያዩ ምዕራብ አገሮች የሄዱ ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር አዋለ

የፕ/ት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት እቅድ ላይ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

የሙስሊሙ ማህበረሰብ በአገዛዙ የፍርድ ቤት ድራማ ከዋናው የትግሉ መነሻ ጥያቄ እንደማያፈገፍግ ገለጸ

ሁበርና ሊፍት በቬጋስ በሴፕተምበር ስራ ይጀምራሉ ተባለ

የኬኒያ መንግስት ከኢትዮጵያ የሚያገኘውን የኤሌክትሪክ ሀይል ለጎረቤቶቹ አሳልፎ እንደሚሸጥ አስታወቀ

 ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት ህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

The post የህብር ሬዲዮ ሰኔ 21 ቀን 2007 ፕሮግራም 32ተኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ቬስቲቫል በደማቅ ሁኔታ መከፈትን አስመልክቶ ውይይት ከጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ እና ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር የመክፈቻውን ስነ ስርዓት በተመለከተ ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡት) appeared first on Zehabesha Amharic.

ጥያቄው ሻዕቢያን ማመን አለማመን ሳይሆን ከወያኔ አገዛዝ እንዴት እንላቀቅ ነው፡፡  –ይገረም አለሙ

$
0
0

 

eri_tigrayወያኔን በማያውቀው ሰላማዊ ትግል አሸንፈው  በህዝብ ለተመረጡበት ቦታ ሳይሆን ለወህኒ የተዳጉት ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ በሊቀመንበርነት የሚመሩት አርበኞች ግንቦት 7  ወያኔን ማነጋገር በሚገባው ቋንቋ ነው  ብሎ መዘጋጃና መነሻ ቦታውን ኤርትራ ውስጥ ማድረጉ በአንዳንድ ወገኖች እየተነቀፈ ነው፡፡ አንዳንዶች እንደውም  ከነቀፋና ተቃውሞ አልፈው ሀገር መሸጥ ነው እስከ ማለት ደርሰዋል፡፡

ሁሉም ድርጊቱን የሚኮንኑ የሚያወግዙ  ሰዎች ኢትዮጵያ ከወያኔ የግፍ አገዛዝ መገላገል አንዳለባት የሚያምኑ ናቸው፡፡ወይም ይመስላሉ፡ ግንቦት 7 የመረጠውን የትግል ስትራቴጂም በጥቅሉ ሲያወግዙ አይታዩም፡፡ ችግራቸው ሻዕቢያ አይታመንም፣ ሻዕቢያ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላት ነው ወዘተ የሚል ነው፡፡ እንዲህ አታድርጉ፣እንዲህ መሆን የለበትም የሚል በአንጻሩ መሆን አለበት የሚለውን መጠቆም ማመላከት ይኖርበታል፡፡

ወያኔ በአገዛዝ መቀጠል የለበትም ከተባለ ለዚህ የሚያበቃውን የትግል አይነትና ስልት ማሳየት ይገባል፡፡ ሻዕቢያ አይታመንም ከተባለ ወያኔን በሚገባው ቋንቋ አነጋግሮ ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ሊያወጣት የሚችል ትግል ከየት ሊጀመር እንደሚችል ማመላከት ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ በተቃውሞ ብቻ አማራጮችን ማጨለምና መንገድ መዝጋት የምናምነው ጎረቤት እስከሚገኝ ወያኔ ይግዛኝ ማለት ይሆናል፡፡

እኔ የሻዕቢያ አፍቃሪም አድናቂም አይደለሁም፤ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ነው፡፡ የኤርትራንና የኤርትራዉያንን ኢትጵያዊነት ግን በጥብቅ አምናለሁ፡፡ መሬቱም ሰዉም ማለቴ ነው፡፡ የበርሊን ግንብ ፈርሶ ጀርመኖችም አንድ ሆነዋል፡፡ ሻዕቢያና የኤርትራ ሕዝብ አንድና አንድ ናቸው የሚል እምነትም የለኝም፡፡አንዳንደ ሰዎች ሸዕቢያን ቅዱስ ኢሳይያስን መልዐክ ለማስመስል በሚቃጣ መልኩ የሚየሰሙት ድምጽም ተገቢም አስፈላጊም አይደለም እላለሁ፤

ሻዕቢያን ማመን አይገባም የሚሉ ወገኖች  የዛሬ ሰላሳና አርባ አመት ወደ ኋላ ተጉዘው ሻዕቢያ በኢህአፓ ላይ ፈጸመው ያሉትን ድርጊት በመከራከሪያነት ያቀርባሉ፡፡ ትናንት የነገረ የተደረገን  ነገር አስታውሶ ዛሬ መሰል ድርጊት እንዳይፈጸም መጠንቀቅ ብልህነት ነው፡፡ ሌሎች ከዛ እንዲማሩ መምከርም አርቆ አስተዋይነት ነው፡፡ ያን እያሰቡ በስጋት መፍራትና ፈርቶ ማስፈራራት ግን የሚጠቅም አይደለም፡፡

ትናንት ዛሬ አይደለም ነገም ዛሬን ሊሆን አይችልም፡፡ እያንንዱ ግዜ የራሱ ነባራዊ ሁኔታዎች ይኖሩታል፡፡ ያንን ተረድቶ ዓላማና  ፍላጎትን ለማሳካት የሚያስችሉ እቅድና ስትራቴጂዎችን ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞና መንገድን አመቻችቶ መሄድ ነው ከውጤት የሚያደርሰው፡፡

ሻዕቢያም ሆነ ወያኔ ኢህአፓን ሲያጠቁ አበይት ምክንያታቸው የዓላማ ልዩነት ነው፡፡ የኢህአፓ ዓላማ ከመገንጠል ማስገንጠል ዓላማቸው ተቃራኒ በመሆኑ ለትግላቸው ስኬትም ሆነ ተሳክቶላቸው ስልጣን ቢይዙ ለመንግስታቸው መርጋት እንቅፋት አድርገው ስላዩት ኢህአፓን ሳይቃጠል በቅጠል በማለት አጠቁት፡፡ እውነትን በድፍረት እንነጋገር ከተባለ ኢህአፓ የተጠቃው በወያኔና በሻዕቢያ ብቻ አልነበረም፡፡ ርስ በርስ በመጠቃቃትና በመከዳዳት ለሻዕቢያና ወያኔ ጥቃት ራሱን አመቻችቷል፡፡

ሻዕቢያና ወያኔ በየግል የፈለጉትን የሁለት ሀገር መንግስትነት ሲያገኙ በጋራ ያለሙት ኢትዮጵያን የመቦጥቦጥ  የጫካ ስምምነታቸው ግን በተለይ ወያኔ ቤተ መንግሥት ተቀምጦ ሊፈጽመው የሚችል አልሆን አለና ይሄው ሰበብ ሆኖ አያሌ ኢትዮጵያዉያን ( ኤርትራዉያንም  ማለቴ ነው) ላለቁበት ጦርነት ዳረጉን፡፡ ይህም ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅነትም ሆነ ጠላትነት የለም የሚለውን አባባል ትክክለኛነት ያሳያል፡፡

ስለሆነም አሁን ያለውን ሁኔታ መገምገምና የመፍትሄ ሀሳብ መለገስ  ኢትዮጵያን ከወያኔ አገዛዝ ለማላቀቅ ከምናካሂደው ትግል አንጻር የኤርትራ ጠቃሚነትና ጎጂነት በሚል ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር  ያለው ምርጫ ሁለት ነው፡፡ ወያኔ በሰላማዊ ትግል በምርጫ ሥልጣን መልቀቅ አይደለም አንድም የፓርላማ ወንበር ለተቀዋሚ እንደማይሰጥ አረጋግጧል፡፡ ይሄ ደግሞ የ ዛሬ ብቻ አይደለም እድሜ ከሰጠው የዛሬ አምስት አመትም ይደገማል፡፡ማስረጃ የሚፈልግ የወያኔን ልሳን አዲስ ራዕይ መጽሄት የሀምሌ 2002 ዕትምን ማንበብ ይችላል፡፡

“ጸረ ሕገ መንግሥታዊ አቋማቸውን እስካልቀየሩ ድረስ መብታቸውን በጥብቅ አክብረን በማያቋርጥ ዴሞክራሲያዊ ትግል አሁን ከደረሱበት ደረጃ አንዳያልፉና እንዳያንሰራሩም በርትተን መስራት ይጠበቅብናል” ይላል (አዲስ ራዕይ Ñê 27)

ይህ በምርጫ 2002 ማገስት የተጻፈ ነገር ምን ማለት አንደሆነ ዛሬ አሁን በምርጫ 2007 በተግባር ያየነው ይመስለኛል፡፡ስለሆነም ከላይ እንዳኩልት ያለው ምርጫ ሁለት ነው፡፡ከወያኔ አገዛዝ ለመላቀቅ ከምናደርገው  ትግል ጠቃሚነት አንጻር ኤርትራን  እንዴት በምን ሁኔታና እስከ ምን ድረስ  መጠቀም እንችላልን ብሎ የአጭርና የረዥም ግዜ ስትራቲጂ ነድፎ በጥንቃቄና በጥንካሬ ትግሉን መቀጠል፡፡ የወያኔ አገዛዝ ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ መቆየት የለበትም የሚል ወገን ሁሉ በሚችለው መንገድና አቅም  ትግሉን ማገዝ፤( ምክር መለገስ፣ ልምድ ማካፈል፣ ድክመትን መጠቆም፣ የመፍትሄ ሀሳብ መስጠት፣ መንገድ ማመላከት ወዘተ) ይህን ለማድረግ ፍላጎቱም ፈቃደኝነቱም ሆነ አቅሙ ከሌለ  ከማደናቀፍ መቆጠብ፡፡

ሁለተኛው ምርጫ ሻዕቢያ አይታመንም ብሎ ቀን እባብ ያያ ማታ በለልጥ በረየ እንዲሉ ሆኖ ለትግሉ መነሻ የሚሆን የሚታመን ጎረቤት ሀገር እስኪገኝ ወያኔ ይግዛኝ ብሎ  ቡራኬ መስጠትና ያዋጣል ብለው በአመኑበት መንገድ ትግል የጀመሩትን ወገኖች እያወገዙና እየኮነኑ መቀጠል፡፡ ይህኛው ተመራጭም አዋጭም አይመስለኝም፡፡

አንድየ የማሪያም ልጅ ኢትዮጵያን ይጠብቃት

The post ጥያቄው ሻዕቢያን ማመን አለማመን ሳይሆን ከወያኔ አገዛዝ እንዴት እንላቀቅ ነው፡፡  – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

‎ወኪሎቻችንን‬ በነጻ ከማሰናበት ያነሰ አንዳችም ብይን አንቀበልም! –ድምጻችን ይሰማ የተሰጠ ማሳሰቢያ!

$
0
0

11659418_872378946176521_8166061036471164171_nኮሚቴዎቻችን ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ ቀጣይ የትግል አቅጣጫችንን የሚቀርፅ ጉዳይ  ቢሆንም በራሱ ግን የትግላችን መዳረሻ አይደለም፡፡ ትግላችን ከመነሻው የተገነባው፣ በሂደትም የውድ ኮሚቴዎቻችንን እስርና እንግልት ጨምሮ በርካታ መስዋእትነት የተከፈለበት የተሸራረፉ መብቶቻችንን በማስከበርና የእምነት ነፃነታችንን በህገ መንግስቱ  መሰረት በማረጋገጥ ዓላማ ላይ ተመስርቶ ነው፤ ይህ ዛሬ አንስተነው ነገ የምንቀይረው  መፈክር፣ አልያም በሌሎች አጀንዳዎች የሚዋጥና የምንዘነጋው ጉዳይ ሳይሆን  ለተፈፃሚነቱ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋእትነት የምንከፍልበት ትግላችን የተጠረገበት ጎዳና ነውና! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማ! አላሁ አክበር!

The post ‎ወኪሎቻችንን‬ በነጻ ከማሰናበት ያነሰ አንዳችም ብይን አንቀበልም! – ድምጻችን ይሰማ የተሰጠ ማሳሰቢያ! appeared first on Zehabesha Amharic.

ለዋይት ሃውስ ይደውሉ፣ ፋክስ ይላኩ (የመጀመሪያ ዙር)

$
0
0

እንደሚታወቀው የአሜሪካኑ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በዚህ ወር መጨረሻ ለጉብኝት ወደ ኬንያ ሲሄዱ ኢትዮጵያ ጎራ የማለት እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል። ይሁንና የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ ነጻነት ናፋቂ የሆነውና በአለም ዙሪያ ተበትኖ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወደ ዋይት ሃውስ በመደወል እንዲሁም ፋክስ በማድረግ
በትህትና ፕሬዚዳንቱ ለዜጎቿ ምድራዊ ሲኦል እንድትሆን የተደረገችውን አገራችንን መጎብኘት አንባገነኖችን እንደማበረታታት ሊቆጠር ስለሚችል ድምጻችንን በስፋትና በተከታታይ እናሰማ። ከዚህ በታች ያለውን ደብዳቤ ስምና አድራሻችሁን በመጻፍ ፋክስ ብታደርጉ፣ እንዲሁም በማህበራዊ ድረገጾች በስፋት በማሰራጨት ትብብር እንድታደርጉ በትህትና እጠይቃለሁ።
ስልክ ለመደወል በስራ ሰአት በ +1 (202) 456–1414 ይደውሉ ask to talk to Denis McDonough, The President’s Chief of Staff / or leave a message
ፋክስ ለማድረግ +1 202-456-2461 በመጠቀም መልእክትዎን ያድርሱ።

Obama Ethiopia

 

 

The post ለዋይት ሃውስ ይደውሉ፣ ፋክስ ይላኩ (የመጀመሪያ ዙር) appeared first on Zehabesha Amharic.

አልሞት አለኝ –ወለላዬ

$
0
0

ወለላዬ ከስዊድን

በሥራው ላይ ልፈላሰፍ

ቅኔ ልቀኝ ግጥም ልጽፍ

ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ

የማደንቀው ሰው ነበረኝ

ሳይሞትማ ሳይቀበር

ስሙን ማንሳት እሱን ማክበር

መስሎ ታይቶኝ ልምድን መስበር

የማደንቀው ሰው እያለኝ

ልጽፍለት ተቸገርኩኝ

አቤት! ዕውቀት አይ! ቁመና

ብልህ ደፋር ቆራጥ ጀግና

ኃይማኖቱን አጠንካሪ

ደግ ለጋስ ሰው አክባሪ

ብዬ ልለው ቸኩያለሁ

አልሞት ብሎኝ ታሞ እያየሁ

 

ዛሬ ቢያጣ ዛሬ ቢርበው

በቁም ሆኖ ከምረዳው

ከማከብረው ከማደንቀው

እደርሳለሁ ሲሞትልኝ

ከምድር በታች ሲውልልኝ

ያንጊዜ ነው ስሙ ገኖ

የሚነሳው እሱን ሆኖ

የብዕር ጫፍ የሚመዘዝ

እንባ የሚረጭ የሚተከዝ

ሚጻፍለት ሚደነቀው

ታሪክ ገኖ ሚነበበው

ገንዘብ ከኪስ ሚመዘዘው

ለሟች በድን አካሉ ነው

ያን አይቼ ልምድ አብቶኝ

የቆየ ወግ አንቆ ይዞኝ

የማደንቀው ሰው እያለኝ

እንዳላደንቅ አልሞት አለኝ

Commentማስታውሻነቱ በአገራችን ላሉና ለነበሩ እውቅና ታላላቅ ሰዎች ይሁን።

ወለላዬ welelaye2@yahoo.com

The post አልሞት አለኝ – ወለላዬ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live