Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Sport: የዢሩ ‹‹ኑዛዜ››

$
0
0

የኦሊቪዮ ዢሩ ግምገማ ግልፅነት ይታይበታል፡፡ ከስቶክ ሲቲ ጋር ሲጫወቱ የፈፀሙትን ስህተት ለመናገር አላመነታም፡፡ የጨዋታውን እንቅስቃሴ በቪዲዮ ደግሞ ከተመለከተ በኋላ ማመንታት አላስፈለገውም፡፡ ‹‹ተሰጥኦ በቂ አይደለም፡፡ ተወዳዳሪ መሆን ያስፈልጋል፡፡ በዕለቱ የቁርጠኝነት ችግር ነበረብን፡፡ ስህተቶችን ስንፈፅም የነበረው እንደ ወጣት ተጨዋቾች ነው፡፡ ያንን በደንብ ተመልክተናል፡፡ መፈፀምም አይገባንም፡፡ ጠንካራ መሆናችንን እናውቃለን፡፡ ጥሩ ስብስብ አለን፡፡ ነገር ግን አልፎ አልፎ የቁርጠኝነት ችግር ይከሰታል፡፡ 100% ለጨዋታ ብቁ ሳትሆን የምትጫወትባቸው ጊዜያትም አሉ›› ፈረንሳዊው አጥቂ ሃሳቡን ማካፈል የሚጀምረው ይህን በመሰለው አስተያት ነው፡፡
Oliver Arsenal
የተሸነፈው ቡድን አካል የነበረው ተጨዋች የሰጠው መደምደሚያ ጥሩ መሰረት ያለው ነው፡፡ በሜዳ ውስጥ የነበረው መንትያ ወንድሜ ነው ሲልም ይቀልዳል፡፡ ከዚያን ዕለቱ ጨዋታ በኋላ ቡድኑ ጋላታሳራይን 4-1 አሸንፏል፡፡ የቼልሲን ያለመሸነፍ ጉዞ መቋጫ ያበጀለትን ኒውካስል ዩናይትድን ረትቷል፡፡

ነገር ግን የስቶኩ ሽንፈት ደስ የማይሉ ትዝታዎችን ጥሎ አልፏል፡፡ ተጨዋቾች ወደ ለንሰን ለመመለስ ባቡር በሚሳፈሩበት ወቅት በገዛ ደጋፊዎቻቸው ተጮሆባቸዋል፡፡ አርሰን ቬንገርም ከጥቃት አላመለጡም፡፡ እንዲያውም አጋጣሚው እጅግ የከፋ ስለነበር ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ ጋሪ ሲኒከር ‹‹አሳፋሪ እና ክብረ ነክ›› ሲል ድርጊቱን አውግዞታል፡፡

‹‹ሰዎቹን ሰምተናቸዋለ፡፡ የአርሰናል ደጋፊ እንደሆኑ የሚታሰቡ ሰዎች ተችተውናል፡፡ በተለይ አሰልጣኙን አንጓጠዋል›› ይላል ዤሩ፡፡ አባባሉ በአርሰን ቬንገር ላይ ያንን መሰል ያልተገባ ጥቃት  የሰነዘሩት ቡድናቸውን ለመደገፍ ከተጓዙ ደጋፊዎች መካከል አነስተኛ ድርሻ የሚይዙ መሆናቸውን ይጠቁማል፡፡ ‹‹አሳዛኝ ነበር፡፡ ያንን መሰሉ ውርጅብኝ ለእርሱ ይገባዋል ብዬ አላስብም፡፡ ጨዋታዎችን ስትሸነፍ እንዲህ ያለው ነገር ያጋጥማል፡፡ በእርግጥ እራስህን መፈተሽ ይጠበቅብሃል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም ነገር መቀየር አለባችሁ አይባልም፡፡ እንዲህ አይነቱን አጋጣሚ እንዴት መቋቋም እንዳለበት የሚያውቅ ሰው በመሆኑ እኛን ብዙ አያስጨንቀንም››

ዢሩ የደጋፊዎቹን ቁጣ ይረዳል፡፡ ‹‹ያንን የሚያደርጉት ጨዋታዎችን እንድናሸንፍ ነው፡፡ የምንጫወተው ለአርሰናል ነው፡፡ ቡድኑ ትልቅ ነው፡፡ ደጋፊዎች ብዙ ይጠብቃሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በውጤቱ እንደተከፉ እንገነዘባለን፡፡ ጥንካሬያችንን እና አፀፋችንን ለማሳየት የምንፈልገው ለዚያ ነው››

ያም ቢሆን ደጋፊዎቹ ቬንገር ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ በእጃዙር ቡድኑን እንደሚጎዱ ያምናል፡፡ ‹‹በሜዳ ውስጥ አንድነታችንን እና ጥንካሬያችንን እናሳያለን፡፡ በህብረት ለመፋለም ተጨማሪ ጉልበት ይሆነናል፡፡ እኛ ቡድን ነን፡፡ ከመካከላችን በአንዱ ላይ ጥቃት ቢሰነዘር ሁሉም የቡድኑ አባላት በጋረ በመሆን ይከላከላሉ፡፡ ይህ አሰልጣኙንም ይጨምራል፡፡ በስቶክ ያጋጠመን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ በተቻለን ፍጥነት ወደ ጥሩ አቋማችን እንመለሳለን›› ሲል የመድፈኞቹ አጥቂ ለአሰልጣኙ ጥብቅና ይቆማል፡፡ በቻምፒዮንስ ሊጉ ተሳታፊ የሚያደርጋቸውን ደረጃ ይዘው ለማጠናቀቅ እንደሚጥሩም ይጠቁማል፡፡

በአርሰናል ያሉ ተጨዋቾች በሙሉ የቬንገር ውለታ አለባቸው፡፡ ከፊሎቹን ከሌሎች ክለቦች አዘዋውረዋቸዋል፡፡ የተወሰኑትን ከታችኛው ቡድን አሳድገው የመሰለፍ ዕድል ሰጥተዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ከቬንገር ጎን የማይቆም የለም፡፡ ነገር ግን ዢሩ የተጨዋቾቹ ታማኝነት ምንጭ ከዚያም በላይ ስር የሰደደ ምክንያት እንዳለው ይናገራል፡፡ ‹‹ለእኔ መልካም የሚሆነው ስላስፈረመኝ ብቻ አይደለም፡፡ በጥሩ ሁኔታ ስጫወት ያሞግሰኛል፡፡ በመጥፎ ሁኔታ ስንቀሳቀስ ጉድለቴን ይጥቁመኛል፡፡ እርሱ ስላስፈረመኝ  ብቻ የተለየ እንክብካቤ አያደርግልኝም››

ዢሩ ተስፋ አልቆረጠም፡፡ በውድድሩ ረዥም ርቀት መጓዝ እንደሚችሉ ያምናል፡፡ ነገር ግን የአርሰናል ደጋፊዎች እና የውጪ ታዛቢዎች ይህንን ሁሉ ጉድለቶች ይዞ እና ገና ከአሁኑ ከመሪው ቼልሲ በ13 ነጥብ ርቆ ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ መቻሉን ይጠራጠራሉ፡፡

‹‹አልረፈደም፡፡ የውድድር ዘመኑ ገና አልተጋመሰም፡፡ በእርግጥ የቼልሲ አጀማመር ድንቅ ነው፡፡ ማንቸስተር ሲቲም ጥሩ ጊዜያት አሳልፏል፡፡ ነገር ግን ረዥም ጉዞ ይቀራል፡፡  የተወሰኑ መሻሻሎችን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ለጨዋታዎች ሙሉ ትኩረት መስጠት ያስፈልገናል፡፡ በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ይህንን ማድረጋችንን ከቀጠለን ከመሪዎቹ ተርታ መሰለፍ እንችላለን፡፡ እኔ ቡድኑን ከተቀላቀልኩ ወዲህ ባለፉት ሁለት እና ሶት ዓመታት ምርጦቹን ተጨዋቾቻችንን በቡድኑ ውስጥ ማቆየት ችለናል፡፡ ሆኖም ደጋፊዎች ሌሎች ታላላቅ ተጨዋቾች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ፈለጉ፡፡ አሰልጣኙም ሃሳባቸውን አደመጠ፡፡ ሜሱት ኦዚል፣ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ሌሎች ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቀለ፡፡ በብቃታችን ጫፍ ላይ መድረስ እንፈልጋለን፡፡ ተጨማሪ ዋንጫዎችንም ማንሳት እንሻለን፡፡

‹‹የባለፈው ዓመቱ የኤፍኤካፕ ድል የአስደናቂው ታሪክ መጀመሪያ ነው፡፡ ታላቅ ቡድን ለመገንባት ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ በስኳዱ ውስጥ ድንቅ ብቃት ያላቸው በቂ ተጨዋቾች አሉ፡፡ ወደ ቀድሞ ብቃታችን መመለስ መቻላችን የሚያስጨንቀን ለዚያ ነው›› በማለት የቀድሞው የሞንፒዬሌ ተጨዋች ልበ ሙሉነቱን ይገልጻል፡፡

ዢሩ ከዚህ ቀደም ወደ ጎን የተገፋበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ተስፋ ተጥሎበት እየተወደሰ ያደገ ተጨዋች አይደለም፡፡ በፈረንሳይ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ይጫወት ለነበረው ግሬኖብል እንደማይመጥን ተነግሮት ወደ ኤስትሬስ እና ቱርስ በውሰት ተሰጥቶ ነበር፡፡ ሁለቱም ክለቦች የታችኛው ሊግ ቡድኖች ናቸው፡፡ በግሬኖብል አሰልጣኙ የነበሩት መሐመድ ቤዝዳሬቪች በአንድ ወቅት ዢሩ በከፍተኛ ደረጃ ለመጫወት የማይመጥን አጥቂ መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡ እርሳቸው ከፍተኛ ብለው የገለፁት የፈረንሳይን ሁለተኛ የሊግ እርከን መሆኑን ልብ በሉ፡፡

ተጨዋቹ አርሰናልን የተቀላቀለው ከሞንፔሲዮ ጋር የፈረንሳይ ሊግ ሻምፒዮን ከሆነ በኋላ ነው፡፡ ከመድፈኞቹ ጋር የኤፍ.ኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን 23 ጎሎችን አስቆጠረ፡፡ በዓለም ዋንጫው እንደ ጎል በስሙ አስመዝገበ፡፡ እነዚህ ስኬቶቹ የቀድሞውን አሰልጣኙን አስተያየት ስህተት መሆን ጠቋሚዎች ናቸው፡፡ የቤዝዳሬቪችን አስተያየት ሲያስታውሱት ይስቃል፡፡ ‹‹የበለጠ የመጫወቻ ጊዜ ማግኘት ስለፈለግኩ ግሬኖብልን ለመልቀቅ ወሰንኩ፡፡ በውሳኔዬ ትንሽ ተበሳጭቶ ስለነበር መልቀቅ ፈለግኩ፡፡ ችግር የለውም ሂድ፡፡ ነገር ግን በፈረንሳይ ሊግ 1 ቀርቶ በሁለተኛው ዲቪዥን እንኳን የሚያቅፍህ ብቃት እንደሌለህ ልታወቅ ይገባል አለኝ፡፡ ሆኖም ወጣት እንደመሆኔ በሜዳ ውስጥ የማሳልፈው ጊዜ ፈለግኩ፡፡ በመሆኑም ክለቡን ለመልቀቅ ወሰንኩ፡፡ ከሞንፔሊዬ ጋር ሊጉን ሳሸንፍ እርሱ የሶቮ አሰልጣኝ ነበር፡፡ ከእርሱ ቡድን ጋር ያደረግነውን ጨዋታ 3-1 አሸነፍን፡፡

ሶስቱንም ጎሎች ያስቆጠርኩት እኔ ነኝ፡፡ ከጨዋታው በፊት ሰላም ብዬዋለሁ፡፡ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ግን ላገኘው አልቻልኩም፡፡ እንደዚህ ያሉ አጋጣሚዎች ያነቃቁሃል፡፡ ሜዳ ውስጥ ጠንካራ የአእምሮ ዝግጅት እንዳለህ ማስመስከር አለብህ›› በማለት አጋጣሚውን መለስ ብሎ ያስታውሳል፡፡

አሁን ላይ ፈረንሳዊው አጥቂ በቋሚነት ለመሰለፍ ከአሌክሲስ ሳንቼዝ እና ዳኒ ዌልቤክ ጋር ብርቱ ፉክክር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ እርሱም ቢሆን ዝግጁ ነው፡፡ ሁለቱም ተጨዋቾች የአርሰናልን የአጥቂ መስመር የተቀላቀሉት ባለፈው ክረምት ነው፡፡ ዢሩ ያለፉትን ሶስት ወራት በጉዳት ከሜዳ ርቆ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ደግሞ ሳንቼዝ እና ዌልቤክ በእርሱ እግር ተተክተው ድንቅ ብቃት አሳይተዋል፡፡ ፈተናውን ያከብዱበታል ተብሎ የተሰጋው ለዚያ ነው፡፡ የተጫወቹ ምላሽ ግን ፍፁም የተለየ ነው፡፡ ‹‹መሰለፍ አለመሰለፌ አያስጨንቀኝም፡፡ ዋናው ነገር የእኔ ቦታ አይደለም፡፡ ወሳኙ እያንዳንዱ ተጨዋች ለቡድኑ የሚሰጠው ግልጋሎት ነው፡፡ በጥሩ ብቃት ላይ ከሆንኩ እጫወታለሁ፡፡ ለዚህ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ችግሮች ሲኖሩብኝ ደግሞ ወደ ተጠባባቂ ወንበር እወርዳለሁ፡፡ ወሳኙ ለቡድኑ የምትሰጠው ነገር ነው፡፡ እንደምንደጋገፍ አስባለሁ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን የተሻለ ነገር እናሳያለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ችግሮቻችንን በጋራ በመቆም መጋፈጥ ይኖርብናል፡፡››

ዢሩ ያደገው በግሬኖብል አቅራቢያ ነው፡፡ ይህንን ቃለ መጠይቅ በሚሰጥበት ቀን የተማሪነት ጊዜውን የሚያስታውሰው አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ከኤምሬትስ ስታዲየም ብዙም በማይርቅ ስፍራ ላይ በሚገኘው ሴንት ማርክ ትምህርት ቤት ልምምድ በመስራት ላይ የነበሩ ተማሪዎችን ዢሩ ተቀላቀላቸው፡፡ አጋጣሚው የአርሰናል ፋወንዴሽን እያከናወነ ያለውን ስራ ጠቋሚ ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ የሚገኘው የ3G  የእግርኳስ መጫወቻ ሜዳ በክለቡ በከፊል ከሚደጉሙ 13 ተቋሞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ፈረንሳዊው አጥቂ ከታዳጊዎቹ ጋር ያሳለፈውን ጊዜ የወደደው ይመስላል፡፡ ያለበትን አካባቢ እንደወደደውም ፍንጭ ይሰጣል፡፡

‹‹ተማሪ ሳለሁ ይህንን በመሰለ ሜዳ አልተጫወትኩም፡፡ ያደግነው በአሸዋ ላይ እየተጨዋወትን ነው›› ይላል ዢሩ፡፡ በዚያን ወቅት የማርሴይ ደጋፊ ነበር፡፡ ነገር ግን ዕድሜው 10 ሲደርስ እርሱ እና የክፍል ጓደኞቹ ለሰሜን ለንደኑ ክለብ ፍቅር ማሳየት ጀመሩ፡፡ ‹‹በፕሪሚየር ሊጉ የምወደድደው ቡድን አርሰናል ነበር›› ሲል ቬንገር የተሾመበትን መንገድ እና ኢማኑኤል  ፐቲ እና ፓትሪክ ቪዬራ ፈጥረውት የነበረውን ጥምረት በማስታወስ ዢሩ ምላሽ ይሰጣል፡፡ ‹‹ታዳጊ ሳለሁ በአርሰናል ያሉ ፈረንሳውያንን እመለከት ነበር፡፡ አርሰናልን መቀላቀሌ ትልቅ ስሜት የፈጠረብኝ ለዚያ ነው፡፡ በፈረንሳይ የአሰልጣኙ ገድል ትልቅ ክብር ይሰጠዋል፡፡ ለአርሰናል መፈረም ምን ያህል ተጨዋቾችን እንደሚያሻሽልም ተመልክቼያለሁ››

አንዳንድ ጊዜ ቬንገር ምን ያህል የተከበሩ እንደሆኑ ይዘነጋል፡፡ ነገር ግን ሥራቸው ዘብ ቆሞ ይከራከርላቸዋል፡፡

The post Sport: የዢሩ ‹‹ኑዛዜ›› appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

↧

Health: የሰውዬው ‹‹ብታከመው ብታከመው ከውስጤ አልወጣልህ ያለኝን ጃርዲያን በምን ልከላከል?›› ጥያቄና የዶ/ሩ ምክር

$
0
0

ጃርዲያ የሚባል በሽታ ከምን ይመጣል? መከላከያውስ ምንድን ነው? ብዙ ጊዜ እየደጋገመ ይይዘኛል፡፡ ምን ላድርግ? ብታከምም እስከመጨረሻው ከበሽታው ልድን አልቻልኩም፡፡
ይማም አበበ ነኝ

giardia_web
የጃርዲያን ኢንፌክሽ /giardiasis/ የአንጀት ኢንፌክሽን ሲሆን የሚታወቀው በሆድ ቁርጠት፣ ሆድ መንፋት፣ ቋቅ ማለጽና ቀጭን ተቅማጥ የህመሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ በሽ በብዛት የሚመጣው በመላው ዓለም በሚገኝ ነገር ግን የፅዳት ችግር በሚታይባቸውና ለመጠጥ ብቁ ያልሆኑ ውሃ ተጠቃሚዎች ዘንድ ነው፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ ይህ በሽታ በውሃ ከሚታለለፉ በሽዎች ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ በአሜሪካንም ቢሆን በውሃ ከሚታለለፉ በሽታዎች እንዲሁ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ የጃርዲያ ኢንፌክሽን በምግብና ከሰው ወደ ሰውም ሊተላለፍ ይችላል፡፡
የዚህ በሽታ አብዛኛው ምልክቶች መጥፎ ጠረን ያለው ቀጭን ተቅማጥ አንዳዴ ለስለስ ያለ፣ አንዳንዴ ልፋጭ ያለው ሲሆን፣ ድካም፣ የሆድ ቁርጠትና መነፋት፣ ቋቅ ማለት እና የክብደት መቀነስ ናቸው፡፡

የዚህ በሽታ አምጪ ፓራሳይት /ተህዋስ/ ጃርዲያ ላምብሊያ /giardia lambila/ ሲባል ሁለት አይነት መልክ አለው፡፡ ይኸውም ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀስ ይባላሉ፡፡ ምርመራው የሰገራ ናሙናን በመውሰድ በማይክሮስኮፕ በማየት መለየት የሚያስችል ዘዴን በመጠቀም ነው፡፡

ይህ በሽታ በተለያዩ አንቲባዮቲክ መድሃኒቶች ሊታከም ይችላል፡፡ ነገር ግን ከምንም በላይ ንጽህና በመጠበቅ ሊጠፋ ስለሚችል ንፅህና ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረግ ይገባል፡፡ ከህክምናው በላይም ንፅህናቸውን የጠበቁ ምግቦችና ፈሳሾችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ንጽህና ሳይኖር ህክምናው ብቻውን ለህመሙ መፍትሄ አይሆንም፡፡

ነገር ግን እርጉስ ሴቶች በመጀመሪያው ሶስት ወራት ለጃርዲያ ተብለው የሚሰጡ መድሃኒቶችን መጠቀም አይገባቸውም፡፡ ይህንን በሽ በቀላሉ ለመከላከል እጅን ምግብ ከመብላት በፊት፣ ሽንት ቤት ከሄድን በኋላ፣ ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት በደንብ አሽተን በሳሙና መታጠብ ውሃን ማጣራትና ማፍላት /ነገር ግን በክሎሪን ብዙም መፍላት የለበትም/፣ ሰገራ በሜዳ ላይ መውጣት ካለበት መቀበር አለበት፣ ዋና በሚዋኝበት ጊዜ አፍን መዝጋት ያስፈልጋል፡፡

በቧንቧ ውሃም እንኳን አሜሪካንን የሚያክል ሀገር እንዲተማሙ አይመከርም፡፡ ምክንያቱም አልፎ አልፎም በአሜሪካም ሳይቀር የቧንቧ ውሃ በተለያየ ምክንያት ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ በአካባቢያችን የጃርዲያ በሽታ ከተቀሰቀሰ የታሸገ ውሃ መጠቀም ይመከራል፡፡ በጉዞ ጊዜ የታሸገ ውሃ መጠቀም ይመከራል፡፡ በፊንጢጣ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ይህንን በሽታ ስለሚያመጣው ይህ አይነት ድርጊት በስፋት በሚኖርባቸው ሀገሮች ኮንዶም መጠቀም ይመከራል፡፡ አልያም ከነጭራሹ ይህን ተግባር አለመፈፀም የተሻለ ነው፡፡

ጃርዲያ በጣም በከፍተኛ ደረጃ የሚተላለፍ በሽታ በመሆኑ ይህ በሽ ያለበት ሰው ጠያቂያችንንም ጨምሮ እጁን በሳና በደንብ አድርጎ ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ ዋና አለመዋኘት ከዋኙም ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩና ንፁህ ውሃ በተሞላ ገንዳ ወዘተ… መጠቀም ይመከራል፡፡

The post Health: የሰውዬው ‹‹ብታከመው ብታከመው ከውስጤ አልወጣልህ ያለኝን ጃርዲያን በምን ልከላከል?›› ጥያቄና የዶ/ሩ ምክር appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ከህወሃት ጉያ ስለ እናት ኢትዮጵያ ህወሃቶች ህወሃቶችን ሲያጋልጹ ክፍል ሁለት –በሳዲቅ አህመድ

$
0
0

ከህወሃት ጉያ ስለ እናት ኢትዮጵያ ህወሃቶች ህወሃቶችን ሲያጋልጹ ክፍል ሁለት – በሳዲቅ አህመድ

20140421_104421

 

 

The post ከህወሃት ጉያ ስለ እናት ኢትዮጵያ ህወሃቶች ህወሃቶችን ሲያጋልጹ ክፍል ሁለት – በሳዲቅ አህመድ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍትዊ ግደይ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተገደሉ፤

$
0
0

newsየአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን) አመራሮች በዛሬው እለት እንደገለጹልኝ ከሆነ የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍትዊ ግደይ ወረኢሉ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የአቶ ፍትዊ ባለቤት ባሉበት በአወጋን አባላት በጥይት መገደላቸው የታወቀ ሲሆን አቶ ፍትዊ የደቡብ ወሎን ሠው በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስሩ ሙስሊሙን «ፅንፈኛ»፣ ክርስቲያኑን «የድሮ ስርዓት ናፋቂ» በማለት በወሎ ክፍለ ሐገር ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የወሎ ሙስሊምና ክርስቲያንን ለመከፋፈል የሞከረ ግለሠብ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የአቶ ፍትዊን ግድያ ተከትሎ በወረኢሉ ከተማ ፍተሻው በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከሩን ለመታዘብ መቻሉን አመራሮቹ ይገልፃሉ።

በመጨረሻም የአቶ ፍትዊ ግደይ ግድያ ለሌሎች የህወሓት አመራሮች እና ጀሌዎች ትምህርት ይሆን ዘንድ የሟቹን ግለሠብ በሞተበት ሠዓት የተነሳውን ፎቶ ከነሙሉ መረጃው በድህረ ገፆች እና በማህበራዊ ሚዲያዎች እንደሚለቀቅ አስታውቀዋል።

~~ሁኔ አቢሲኒያ~~

The post በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍትዊ ግደይ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተገደሉ፤ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የምርጫ ቦርድን ልጓም ማን ይግታው???

$
0
0
2010-05-22T122316Z_783959720_GM1E65M1KO302_RTRMADP_3_ETHIOPIA-ELECTIONS_0_0በእኔ እምነት ምርጫ ቦርድ ልጓሙን በጥሶ መፈርጠጥ ጀምሯል፡፡ አዎ ምርጫ ቦርድም ሆነ ኢህአዲግ በህግ የበላይነት ሊያምኑና ህግን ሊያከብሩ ብሎም በተሰጣቸው ገደብ መሰረት ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ዴሞክራሲ፣የህግ የበላይነት ….ወዘተ እያሉ መደስኮሩ ጉንጭ ከማልፋት በተዘለለ ለዜጎች ጠብ የሚልላቸው ነገር አይኖርም፡፡ መንግስታት አንባገነን በሆኑበት አግባብ ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት አስቸጋሪ ነው፡፡
በሀገራችንም እየሆነ ያለው ይህ ሀቅ ነው፡፡ ምንም እንኳ የሀገሪቱ የይስሙላ ህገ መንግስት በአንቀፅ 102 1-2 ስለምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ተቋምነት ቢደነግግም፤ እውነታው ግን ከዚህ ፍፁም ያፈነገጠና ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ለመሆን ቀርቶ የመንግስት ክንፍ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ….እሺ ይኸንንም ይሁን ብለን እንቀበል፤…ኢህአዲግ ያላከበረውን ህገ-መንግስትና የህግ ማእቀፍ ምርጫ ቦርድ ያከብራል ብለን አንጠብቅ፤…ነገር ግን ምርጫ ቦርድ ከአንድ ተቋም ነኝ ከሚል መዋቅር የማይጠበቅና እጅግ የወረደ ተግባር ሲሰራ እየተመለከትንበት ያለው ሁኔታ በጣም የሚያሳዝንና ተቋሙንም ሆነ የተቋሙ አመራሮችን ከታሪክ ተጠያቂነት የሚያድናቸው ሆኖ አናገኘውም፡፡
ምርጫ ቦርድ እንደተቋም ያስፈፅማቸውና ሊተገብራቸው ዘንድ የሚጠበቁ ተግባራት በህግ ተለይተው ተቀምጠውለት ሳለ በፓርቲዎች አሰራርና የውስጥ ጉዳይ እንደርጎ ዝንብ ጥልቅ እያለ፤በማያገባውና በህግም ሆነ በአሰራር በማይመለከተው ተግባር ውስጥ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙ ምናልባትም የሀገራችን ህግ ምን ያህል እንደወረደና የምርጫ ቦርድ ማንአለብኝነት ከኢህአዲግ የጀርባ እጅ ጋር መያያዙንና የህወሀት/ኢህአዲግና/የምርጫ ቦርድን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታነት ቁልጭ አርጎ የሚያመላክት ነው፡፡
በህግ የበላይነት በሚያምኑ መሪዎችና ህዝቦች መካከል ፤…‹‹ህግ›› ማለት ልጓም ነው፡፡ አንድ ፈረስ በተፈቀደለት አቅጣጫና ፍጥነት በተገቢው ሁኔታ ይሄድ ዘንድ ልጓም ይበጅለታል፡፡ ልጓሙ ህግ ነው፤ ፈረሱ ከልጓም ከወጣ በሰውም ላይ ሆነ በራሱ ላይ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ …..ልጓሙን ይዞ ፈረሱ ላይ ተግባራዊ የሚያደርገው ደግሞ የጋሪው አሽከርካሪ ነው፡፡ ስለዚህ ባለጋሪው ከፍተኛ ሀላፊነት አለበት ማለት ነው፡፡…..በህዝብም ላይ ተመሳሳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ ተስማምተው ያወጡት ህገ-መንግስትና የየተቋማቱ ልዩ ልዩ ማስፈፀሚያ ህጎችና የህግ ማእቀፎች በሀገሪቱ ላይ ለሚደረገው ማንኛውም እንቅስቃሴና አሰራር ልክ እንደ ልጓሙ ሁሉ ገደብ አድርገውለታል፡፡ …..ከዚህ ልጓም የወጣ ደግሞ፤ …..ህገ-ወጥና የህግን የበላይነት የማያከብር ይባላል፡፡
በሀገራችን ያለው ሁኔታ በልጓም (በህግ) የበላይነት ማመን በወሬ ደረጃ ሆኖ የምናገኘው ኢህአዲግም ሆነ ሌሎች ተቋማት ህግንና አሰራርን በገሀድ ሲጥሱትና ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ሳይኖር ሲቀር ነው፡፡ …..ለነገሩ የሀገሪቱ መንግስት ነኝ ባይ ፓርቲ ህጉን እንዳሻው እየጣሰና እየረገጠ ባለበት ሁኔታ ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች ህጉን ቢጥሱ ምን ሊደንቀን ይገባል??? ……. ሰሞኑን እንደተከታተልነው ምርጫ ቦርድ ከተፈቀደለትና ከሚመለከተው ተግባር ውጭ በመውጣት በአንድነት ፓርቲ ላይ የጀመረው የውንብድናና የማንአለብኝነት ተግባር እጅግ አሳፋሪና የወረደ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ …….ምርጫ ቦርድ ‹‹ፅድቁ ቀርቶብኝ፣……›› እንደሚባለው ምንም እንኳ እንደአንድ ገለልተኛ ተቋም ለፓርቲዎች የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ከአድሏዊነት በፀዳ መልኩ ማገልገል ቢሳነውም በማያገባው ሁሉ ጥልቅ እያለ የሚፈፅመው የህግ ጥሰትና የአሰራር ዝቅጠት ድርጊቱ ሆን ተብሎና በኢህአዲግ ተልእኮ አስፈፃሚነት የሚሰራ ትወና ለመሆኑ ማስረጃ ነው፡.
ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ የከፈተው የተልእኮ ዘመቻ፤……. መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሊያውቀውና ሊገነዘበው የሚገባ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ እስካሁን በህዝብና በፓርቲዎች ላይ እየፈፀመ ያለው ደባ እንዳለ ሆኖ ልጓሙን የበጠሰው ይህ ተቋም በቀጣይነት ለፓርቲዎች ህግ ላውጣ፤ የፋይናንስ ጉዳያችሁን ላስተዳድር፤የዲሲፕሊንና ሌሎች የፓርቲው እርምጃ በኔ በኩል ይፈፀም፤…ለኢህአዲግ መስገድ በኔ በኩል የሚፈፀም የፓርቲዎች ግዴታ ነው፤የየፓርቲዎችን ፕሬዝዳንት በኢህአዲግ መልማይነት በእኔ አፅዳቂነት ይፈፀም ……. ወዘተ የሚሉ ወራዳና የወረዱ ተግባራትን እንደሚፈፅም አልጠራጠርም፡፡ይህ ተቋም በህዝብ ላይ ለፈፀመው ደባና ንቀት ተጠያቂ የሚሆንበት ቀን እሩቅ አይሆንም፡፡
አንድነት ፓርቲና ሌሎች የምርጫ ቦርድ መረን ለቀቅ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ፓርቲዎች ግን የህዝብን አደራ ተሸክመው፤በዚህ ተልካሻና የማይከበር ተቋም ሴራ ከትግሉ መራቅ እንዴሌለባቸው የሚታመን በመሆኑ፤…… በተባበረ ክንድ የምርጫ ቦርድንም ሆነ የኢህአዲግን ውጥን የሚያከሽፍ የትግል ስልት ነድፈው እንደሚንቀሳቀሱ አልጠራጠርም፡፡ ….ምናልባት ፓርቲዎች ባመጡት ጠንቅ ሳይሆን በኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ ሴራ ትግሉ ደም የሚያቃባና በመስዋትነት የታጀበ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ለዚህ ደም መፋሰስ ተጠያቂዎቹ ኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ መሆናቸውን መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው የሚገባ ሀቅ ነው፡
አመሰግናለሁ!!!
አንብበው ሲጨርሱ ሼር ማድረግዎትን አይርሱ!!!
ድል የህዝብ ነው!!!

The post የምርጫ ቦርድን ልጓም ማን ይግታው??? appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ሥርዓቱ የምርጫ ካርድ ያልወሰዱትን ስኳር በመከልከል ማስፈራራት ጀምሯል

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ የቦቀል ቀበሌ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ስልልወሰዳችሁ ስኳር አይሰጣችሁም መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በአካባቢው ስኳርን ጨምሮ ሌሎች አቅርቦቶች በስፋት እንደሚጠፉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ዛሬ ጠዋት የቀበሌ ካድሬዎች በድምጽ ማጉያ ‹‹ዛሬ ስኳር ስለመጣ ቀበሌ ድረስ መጥታችሁ እንድትወስዱ፡፡ የመጣው ስኳር ውስን በመሆኑ ሊያልቅ ስለሚችል ዛሬውኑ መጥታችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡ ከዛሬ ውጭ ላታገኙ ትችላላችሁ፡፡›› እያሉ ሲለፉ እንዳረፈዱ ተናግረዋል፡፡
election
ሆኖም መጥቷል የተባለው ስኳር ለማግኘት ወደ ቀበሌው ያመሩት ነዋሪዎቹ ስኳሩን ለመውሰድ ሲጠይቁ ‹‹የምርጫ ካርድ ወስዳችኋል?›› የሚል ጥያቄ እንደሚቀርብላቸው ግልጸዋል፡፡ የምርጫ ካርድ የሚያሳዩ ነዋሪዎች ስኳሩ ሲሰጣቸው፤ ያላወጡት በአስቸኳይ ምርጫ ካርድ አውጥተው እንዲመለሱና ስኳር እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ተብሏል፡፡ በአንጻሩ ስኳር ለመውሰድ የምርጫ ካርድ ማውጣት የለብንም ያሉት ነዋሪዎች ስኳር እንደማያገኙ የተነገራቸው ሲሆን ‹‹እንደዜና የምርጫ ካርድ ወሰድንም አልወሰድንም ስኳር የማግኘት መብት አለን›› ያሉ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበው እንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
በጠዋቱ የቀበሌ ነዋሪዎች ያሰሙት የነበረውን ለፈፋ ሰምቶ ወደ ቀበሌ ያመራ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ መምህር የምርጫ ካርድ ካላመጣ ስኳር እንደማይሰጠው ተነግሮት መመለሱን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ መምህሩ ‹‹የምርጫ ካድር የመውሰድና ያለመውሰድ መብት አለኝ፡፡ የማምንበት ፓርቲ ሲኖር የምርጫ ካርድ እወስዳለሁ፡፡ ካልሆነ ግን አልወስድም፡፡ ብወስድም ስኳር ለማግኘት ብዬ አይደለም፡፡ እንደማንኛውም ዜጋ ስኳር የማግኘት መብት አለኝ፡፡›› በሚል የቀበሌ ሰራተኞቹን ለማስረዳት ቢሞክርም ‹‹እኛ ስኳር ስጡ የተባልነው ካርድ ለወሰደ ብቻ ነው፡፡ ካርድ ካልወሰድክ አይሰጥህም›› ተብሎ እንደተመለሰ ገልጾልናል፡፡

The post ሥርዓቱ የምርጫ ካርድ ያልወሰዱትን ስኳር በመከልከል ማስፈራራት ጀምሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የሸለብታ (NAPPING) 6 ጥቅሞች

$
0
0

napping
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)
Dr Honilet
1) ንቃትን ይጨምራል
ድካም እየተሰማዎ የሚሰሩት ሥራ ውጤታማነት ስለማይኖረው ለትንሽ ደቂቃ ሸለብ አድርገው በነቃ አእምሮ ወደ ሥራዎ ቢመለሱ ይጠቅማል፡፡
2) የሥራና የትምህርት የማስታወሻ ችሎታን ያዳብራል
ሸለብታ የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡ ከባድና ውስብስብ ሥራዎችን በትኩረት እንድንሰራ ይረዳል፡፡
3) አዕምሮ በሥራ ብዛት እንዳይወጠር ይረዳል
የምንሠራው ሥራ ብዛት ካለው ዕረፍት እየወሰድን ከሠራን ውጤታማ ውጤታማነት እንጨምራለን፡፡ ለ30 ደቂቃ ሸለብ ካደረግን በአዲስ አዕምሮ ወደ ሥራ መመለስ ይቻላል፡፡
4) የፈጠራ ችሎታን ያዳብራል
ዕረፍት ያደረገ አዕምሮ አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠር ችሎታ ይኖረዋል፡፡
5) ጤናማ እንድነሆን ያደርጋል
ሸለብታ ለአዕምሮ ዕረፍት የሚሰጥ ሲሆን ሕመም የመከላከል አቅምን ይጨምራል፤ጭንቀት እና ፍርሃትን ይቀንሳል፡፡
6) ጥሩ ስሜትን ይፈጥራል
ሸለብታ በእንቅልፍ ውስጥ ሴሮቶኒን የሚባል ንጥረ ነገር እንዲመነጭ ስለሚያደርግ የእንቅልፍ ስሜት እንዲሁም የምግብ ፍላጎታችን እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡

እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!

The post የሸለብታ (NAPPING) 6 ጥቅሞች appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የማለዳ ወግ…አርቲስት ሜሮንና አስቴር ተናገሩ ፣ እኛስ ! * በስደት የግፉአኑን መከራ ለመቅረፍ ምን እየሰራን ነው ? * የውዴታ ግዴታ የለብንምን?

$
0
0

Meron Getenet
የማለዳ ወግ… አርቲስት ሜሮንና አስቴር ተናገሩ ፣ እኛስ !   * በስደት የግፉአኑን መከራ ለመቅረፍ ምን እየሰራን ነው ? * የውዴታ ግዴታ የለብንምን?
የማለዳ ወግ… አርቲስት ሜሮንና አስቴር ተናገሩ ፣ እኛስ !
* በስደት የግፉአኑን መከራ ለመቅረፍ ምን እየሰራን ነው ?
* የውዴታ ግዴታ የለብንምን?

ነቢዩ ሲራክ

ሜሮንና አስቴር …
ያን ሰሞን አርቲስት ሜሮን ጌትነት ” አትሂድ ” ባለችው የተዋጣለት ግጥሟ ታሸበሽብ ታረግድለት የነበረውን የኢህአዴግ አመራርና ስርአቱን በሰላ ብዕሯ መሸነቋቆጧ ከጫፍ እስከ ጫፍ የሃበሻ መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል ። የሜሮን ፋና ወጊ ፣ በጥበብ የተከሸነ ፣ ነፍስ አሽር ግጥም በድምጽ ብቻ ሲሰራጭ ገዥውን ፖርቲ የመከላከያ ሰራዊት መለዮ ከነኮፊያው ሳይቀር እየደነቀረች የተለያዩ ወቅታዊ ደጋፊ ዝግጅቶችን ስታቀርብ የምናውቃት አርቲስት ሜርን ጌትነት ድምጽ መሆኑን ለማመን ቸግሮንም ነበር ። ብዙም ሳይቆይ ግን ዛሬ በእሳት ዶግ አመድ በሆነው የጣይቱ ሆቴል ጥበብ ይዘንብበት በነበረው የጃዝ አንባ ዳራሽ መድረክ ላይ ግጥሙን ስታነብ የተቀረጸችው ፍንትው ያለ መረጃ ቀረበ ።

“ጉድ ” አልን … ” እውነት ሜሮን ናትን ” ስንል አይሆን መስሎን የተጠራጠርነው ገሃድ ሆኖ እውነቱ ተገለጠ ፣ ጥበቧን የወደዱላት ” ጥበብ የህዝብ ስሜት ጉዳት ሲገልጥበት እንዲህ ነው ፣ አበጀሽ ሜሮናችን ” በሚል የቆየ ብሽቀታቸውን ትተው የአድናቆት ፍቅር ስሜት ቀየሩት ፣ በቅኔ በውዳሴም በክብር ” ሜሮን ሜሮን ” እያሉ ከፍ ከፍ አደረጓት ! ሜሮን ጨክና ትደግፈው ይደግፉት የነበረውን የኢህአዴግ መንግስት ቅኔ ዘርፋ መሸንቆጧን ያልወደዱላት ምላሽ ቅኔ ሳይቀር ተቀኘን ብለው ትንታጓን ሜሮንን የስድብ ውርጅብኝ አወረዱባት ! ” ይህች ደግሞ ምን ጎደለብኝ ብላ ነው? ” ሲሉ የህዝብ ህመም ፣ የህዝብ ሮሮና ዋይታን የህዝብ ልጆች ጥበበኞች የመግለጽ ሃላፊነት እንዳለባቸው እያወቁት እንዳላቀቁ ሆነው ዘለፏት ፣ ተሳለቁባት !

የጥበብ ሰዎች እንደ ሃገሬው በከፋው የእኛ ፖለቲካ ዘባተሎ እየተገፉ ” ሃብታችን የህዝብ ፍቅር ነው! ” እንዳላሉ መሸነጋገላቸው አስተዛዛቢ ሆኖ መንጎድ ያዘ ፣ ህዝብና ጥበብ በፖለቲካ ቅኝት ተለያዩ ! አርቲስቱ ትዝብት ላይ ወደቁ … ይለይለት ያላ የሚመስለው መንግስት ያን ሰሞን ህወሃት ኢህአዴግ ያለፈበትን የትግል ጉዞውን ያዩለት ዘንድ አርቲስት የጥበብ ሰዎችን ወደ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የትጥቅ ትግል መጠንሰሻ ወደ ደደቢት ሲወስዳቸው ነገሩ ሁሉ ግልጥልጥ ማለት ያዘ !

በጉዞው ጉብኝቱ ስለሆነው ሁሉ አናወጋም …በዚያው በጉብኝቱ በተደረገው ውይይት የተነሱ በርካታ ውይይቶች አንዱ ግን እናነሳለን ! ቀልብ ሳቢ ከነበሩት ውይይቶች መካከል የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በተካፈሉበት አንድ ውይይት የሰላ ጥያቄ ለመከላከያ የበላይ ለጀኔራል ሳሞራ የኑስ የሰላ ጥያቄ ያቀረበችውን የአስቴር በዳኔ ጥያቄ ይጠቀሳል ፣ በእርግጥም የአስቴር በደኔ ጥያቄ ፍጹም ይሆንል ያልተናል ፣ ያልተጠበቀና ያልታሰበ ነበር ፣ የአስቴር ይህን ሁሉ አመት አውራ ሁናችሁ መግፋታችሁ ያዋጣ ይሆን የሚል አንድምታ ያለው ምክር የተቀላቀለበት ጥያቄ ለጀኔራል ሳሞራ ቀርቦ ምላሽ የተባለው ምልሽ ተሰጠው …

እናም የአስቴር ጉዳይ ፣ የአስቴርን እያንሾካሾከ ከራሱ ጋር የሚፋተገው የእኔ ቢጤ ፈሪ ጥያቄው የእሱ ጭምር ሆኖ እያለ የህዝብ ልጇ የብርቱዋ አርቱስት አስቴር በዳኔ ጥያቄ እያለ እንደ ሜሮን ሾተላይ ግጥም እየተቀባበለ መመልከቱ እውነት ነው ፣ በእርግጥም ጥያቄው የብዙሃን ጥያቄ ነበርና የአርቲስት አስቴር በዳኔ ጥያቄና መልስ የያዘው ተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፈ መረጃ እንደ ሜሮን ግጥም ከጫፍ እስከ ጫፍ በሰፊው ተናኘ !

እኛስ እንደ ዜጋ !

ከሜሮን ሰሞነኛ መነጋገሪያ ግጥም ለጥቆ አርቲስት አስቴር በዳኔ ለኢህአዴግ መንግስት ቁንጮ ባለስ ልጣናት ያቀረበችው ጥያቄ እንደ ሜሮን ሁሉ በድጋፍና በጥላ ቻ የታጀበ ነበር ። እኔ የምለው እኛስ የት ነው ያለነው ነው? ይህን ብየ የማጠይቀው ! መልስም አለኝ !

አዎ አርቲስት አስቴርና አርቲስት ሜሮን ያሻቸው የፈቀዱትን ተናግረዋል ፣ በቃ ! ሁለቱም እህቶች ስሜታቸውና ማስተላፍ ያለባቸው መልዕክት ያመኑበትን ሲሆን በአደባባይ ነው የተናገሩት ! እኛ ግን እነሱ ያመኑበትን ለመቀበል ምክንያቱ ግልጽ ሆኖ እያለ አግድመን እየተራኮትን ያለነው ! አርቲስቶች ባነሱት በብዙሃን የሃገሬ ሰው ውስጥ የሚንቀለቀል መሰረታዊ እውነትና ጥያቄ ውስጥ ራሳችን ማየት ተስኖናል ። እንደ ዜጋ በከባቢያችን ከእኛ የሚገባውን ጥቂቱን ሃላፊነት ሳንወጣ ማግለል ፣ ማንቋሸሽ ፣ ማጥላላትና መኮፈስን ለምደነዋል ! ግን ለምን ? አልልም ! እስከ መቸ እንዲህ ሁነን እንቀጥላለን ? ግን እላለሁ !

የሃገር ቤቱ ፖለቲካ እሳት ሆኖ ይፋጃል ቢባል ፣ በአረቡ አለም በስደት የሚገኙ እህቶቻችን መከራ እንዲያቆም በስደት ያለን የተሻለ ኑሮ የምንገፋው እንደ ዜጋ ለግፉአኑ የቻልነውን ማድረግ የሞራል ግዴታ እያለብን ለማድረግ ፈቃደኞች አይደለንም ! መከራና ሰቆቃው ከቀን ወደ ቀን እየከፋ መጥቷል ፣ የመንግስት ሹማምንት ከሞቀው ወንበራቸው ተነስተው ለተጎጅ ወገኖቻቸው እንዲተጎ እንኳ የሰላ ሂስ ሰንዝረን ቀርቶ ተሽቆጥቁጠን በየበአላቱ ስናጅባቸው ለተገፊው ወገን እንዲደርሱለት አንመክራቸውም ! በስደት የግፉአኑን መከራ ለመቅረፍ ምን እየሰራን ነው ? የውዴታ ግዴታ የለብንምን ?

አንዳንዶቹም ሹሞቻቸን ከማስተማር ከምመከር ወጥተን ጥሩ ነገር እንደሰሩ እናሞካሻቸዋለን ፣ የሰላ ሂስ የምናቀር በውን ” የግንቦት 7 ፣ የኦነግ ፣ የአረናና የማንቴስ ተቃዋሚ አባላት ” እያልን ለጥቅም ማግበስበሱ እኩይ ምግባር መትጋት ይቀናናል ፣ አድርባይ አጎብዳጅነቱን ትተንና ላንመለስበት ንስሃ ገብተን ፣ መቸ ይሆን ወደ ትክክለኛው መንገድ የምንጓዘው? መቸ ነው ለፖለቲካ ወገንተኛነትን ፈንግለን ለወገናችን መከራ መቆም ፣ ለሰብዕና ብለን እውነትን የምንከተለው ?

ከሰብአዊ ሰው በወጣ የአድርባይነት ካባ ደርበን የሚ ገፋውን ህይዎታችሁን መታዘብ ዘልቆ ያማል ! እንደ አርቲስት ሜሮን እውነትን ሸፋፍነን ብንከርምም ቀኑ ሲደርስ ፣ ውስጥ አልቀበል ሲል ለእውነት መስዋዕት ለመሆን የምንተጋበት ውበትን እውነት ብለን የምንገልጥበት ቀን ናፍቆኛል ። እንደ አርቲስት አስቴር ደፍረን የህዝብ የወገናችን “የህሊና ድምጽ ” መሆኑ ቢሳነን ፣ የሚፈሩትን ሹሞች ሳንፈራ በግምባር የምናጠይቅበት ስለ እውነት የምናፈጥበት ሞራል ባይኖረን … እንደ አቅማችን ፣ እንደ ራሳችን ፣ እንደ ቤታችም ፣ እንደ ጉዳታችን ሆነን የግፉአን ስደተኛ እህቶ ቻችን መከራ እንዲያቆም የምተጋበት ቀን ናፍቆኛል ! እውነቱን በገሃድ መገላለጥ ፣ ለየቸገረው ስደተኛ እርዳታን ድጋፍ የማድረጉ ሃላፊነት ከማናችንም የሚጠበቅ የውዴታ ግዴታ መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል ! ያ ሲሆን ማየት ደግሞ በጣሙን ናፍቆኛል !

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ጥር 12 ቀን 2007 ዓም

The post የማለዳ ወግ… አርቲስት ሜሮንና አስቴር ተናገሩ ፣ እኛስ ! * በስደት የግፉአኑን መከራ ለመቅረፍ ምን እየሰራን ነው ? * የውዴታ ግዴታ የለብንምን? appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ! –ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

$
0
0

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
nigatuasteraye@gmail.com
ጥር ፲፩ ፳፻፯ ዓ.ም.

kidus gebrielታህሳስ 19 ቀን በቅዱስ ገብርኤል ስም የሚታሰበው በዓል፤ እግዚአብሔር ሥነ ባህርይን
(ሞራልን) እንዲያከብር ቅዱስ ገብርኤልን የላከበት ቀን ነው።
ማሳሰቢያ፦ በቅዱስ ገብርኤል ስም በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን ከፍተው ህዝብን በመዝረፍ ላይ የሚገኙት ብዙዎቹ “ቅዱስ ገብርኤል ተከበረ እንጅ አከበረ” የሚለውን ሰምተውት ስለማያውቁ፤ “ቅዱስ ገብርኤል አይከበር አለ” እያሉ፤ አንብበው ከእውነቱ መድረስ የማይችሉትን አንዳንድ የዋሆችን ውዥንብር ውስጥ መክተታቸው አይቀርም። እኔ ኢትዮጵያን በመምራት ያሉ ፖለቲከኞችና በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን የሚከፍቱትን የአስመሳይ ነጋዴዎች ባህርይ፤ አባቶች ስለበዓሉ አላማና ምክንያት ካስተማሩኝ ጋራ ሳንጻጽረው፤ ቅዱስ ገብርኤል ካከበረበት ምክንያትና ዓላማ ጋራ ምንም ግንኙነት እንደሌለው ገለጽኩ እንጅ ቅዱስ ገብርኤልማ ክብር ይገባዋል ።

መግቢያ:­
ታሕሳስ 19 አስርቱ ቃላት የተጻበት ጽላት ከመንበሩ የሚንቀሳቀሰው ቅዱስ ገብርኤል ያከበረውን ሥነ ባህርይ (ሞራል) በቅርብና በሩቅ ላለ ሁሉ ለማንጸባረቅ ነው። ይሁን እንጅ ይህን ማስተጋባት የሚጠበቅባቸው መንፈሳውያን መሪዎችም ሆኑ ዓለማውያን መሪዎች በዚያ ወቅት በአገርና በወገን የፈጸሙት በደልና ግፍ፤ ለተከበረው በዓል ተቃራኒ ነበር።
1. የባህርዳርነዋሪህዝብለታቦትማንገሻየምንገለገልበትንአውደምህረትወደሌላአገልግሎት ልታውሉብን አይገባም አሉ። ወያኔ ግን ደበደባቸው፣ አሰራቸው ገደላቸው። ተብሎ በይፋ ተነገረ።
2. ህዝቡ ለጥምቀት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲሸርት መልበስ ፈለገ። ወያኔ እንዳይለብሱ ከለከላቸው ተብሎ በይፋ ተነገረ።
3. ወያኔም በሕዝብ ላይ የፈጸመውን በደል አስተባብሎ አቀረበ። ”ያካባቢው ብዙዎች ካህናት ወያኔ ከደበደበው፣ ካሰረውና ከገደለው ህዝብ ጎን መቆም ሲገባቸው፤ ከወያኔ ጋራ ተስማምተው በመቆም የወያኔን ሸፍጥ አስተጋቡ“ ተብሎ በይፋ ተነገረ።

እነዚህ ነገሮች የተፈጸሙበት ወቅት፤ ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይ (ሞራል) ያከበረበት ወቅት ነበር። በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለምሳሌ:­ በደብረ ማርቆስ፤ በወልቃይት ጠገዴ፤ በቤኒሻንጉል፤ በአርማጮ፤ በዑጋዴን ወገን በከንቱ ተገደለ የሚል ድምጽና ዋይታም ተሰማ። በዚሁ ወቅት “ሥነ ባህርይ (ሞራል) ክብር የምናስታውስብተን አውደ ምህረት ለሌላ ጉዳይ ልታውሉብን አይገባም” ብሎ የተሰለፈውን ህዝብ መምራትና መደገፍ የሚገባቸው ያካባቢው ጳጳስና ከካህናት ብዙዎች ወያኔ የፈጸመውን ግፍ ደግፈው ህዝቡን ጥፋተኛ አድርገው ካቀረቡ በኋላ፤ በዓሉን አከበርን ማለታቸው፤ ከመስመራቸው ውጭ አደረጋቸው። ከዚህ በታች በዘረዘርኳቸው አንቀጾች ከተሰለፉበት ተልእኮ ጋራ መጋጨታቸውን ለመግለጽ እሞክራለሁ።
❖ ፩ኛ. የበዓሉ ምክንያትና ዓላማ በጉባዔው ትምህርት
❖ ፪ኛ. ቅዱስ ገብርኤል ያከበረው ሥነ ባህርይ ከማለም ባሻገር፤ የተሰወረ ሕልም ፈች ብልጥ ያደርጋል።
❖ ፫ኛ. ወያኔ ሊደመስሳቸው የሞከራቸው፤ ያባቶች ህልም የተመሰረተባቸው፤ ኢትዮጵያውያን
የተወሀድንባቸው 4 መንገዶች
❖ ፬ኛ. ለጥምቀት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲ­ሸርት ባለመልበስ የሚጎድል ነገር የለም።
፩ኛ. የበዓሉ ምክንያትና ዓላማ በጉባዔው ትምህርት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መጻሕፍትን የሚተረጉሙበት ስልት አንድምታ ይባላል። አንድምታ ማለትም፤ “ይህም አለ። ያም አለ። እንዲህም ይባላል። እንዲያም ይባላል” ለማለት ንጽጽር (comparative) ነው። የበዓሉን ታሪክ በተሸከመው በዳንኤል መጽሐፍ፦
➔ 1ኛ “ብረቱን፤ ናሱን፤ ሸክላውን ብሩንና ወርቁን የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራ ወርዶ አደቀቃቸው” (2 ፡ 45) ተብሎ የተገልጸውን ድንጋይ
➔ 2ኛ “ግዛቱ የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው። መንግሥቱም የማይጠፋ ነው”(7፡14)የተባለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ለክርስቶስ ብቻ ከመስጠት በቅር፤ ቅዱስ ገብርኤል ባከበረው ሥነ ባህርይ ዙሪያ ያለውን ታሪክ፤ እንደ ሌሎች መተርጉማን በሮም፣ በባቢሎን፣ በፋርስና በግሪክ መንግሥታት ብቻ አይወስኑትም። አሁንም በየዘመናት የሚነሱትን የመንግስታትንና በነሱ ዙሪያ ተኮልኩለው በታላላቅ ወንበር ለይ የተቀመጡትን የሥነ ባህርይ ጉድለትና ብርታት ይለኩበታል።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ትእቢተኞችን በትኗል። ገዥዎችን ከዙፋናቸውም አዋርዷል። ትሁታንንም ከፍ አድርጓል። የተራቡትን ከበረከቱ አጥግቧል። ባለጠጎችን ባዷቸውን ሰዷቸዋል”(ሉቃ 1፡51­53) ብላ የተናገረችውንም፤ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት “ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል። መንግስታትን ያፈልሳል። ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ላስተዋዮች ይሰጣል” (2፡21) ከሚለው ጋራ ተፈጻጻሚ እንደሆነ ይናገራሉ። የዳንዔልን ንግግር ከእመቤታችን ንግግር ጋራ በማዛመድ፤ የክርስቶስ መንግሥት ሁሉንም እንዳልነበሩ እስኪያደርጋቸው ድረስ ይቀጥላል ብለው ስለሚያምኑ፤ ያፋችን መፍቻ በማድረግ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በቃላችን እንድንይዘው አደረጉ። በግልም፣ በማህበርም በየእለቱ እንዲደገም ስርዓት ሰሩ።

ታሪኩ ከዘመነ ሥጋዌ አምስት ምዕት ዓመታት በፊት በባቢሎን አገር የተፈጸመ ነው። በዚያ ዘመን የባቢሎን መንግሥት እንደ አሜሪካ ጥገኝነት ቢቅፈድና ሁሉም በችሎታው በእውቀቱ ለመኖር ሰፊ እድል ቢሰጥም፤ ሁሉም የፈለገውን እያመለከ ባህሉን እየጠበቀ እንዲኖር አሜሪካ የሰጠውን ዓይነት ነጻነት የናቡከደነጾር መንግሥት አልፈቀደም።

ድርጊቱ በተፈጸመበት አገር በምርኮ ይኖሩ የነበሩት ዳንዔልና ሶስት ወጣቶች፤ ከሆዳምነት ከፍርሀት ከጥርጥር የራቁ፤ ከመንግሥት አካባቢ በሚዘጋጁት በጥቅማ ጥቅም ንክኪ ላለመርከስ የወሰኑ የእምነትና የሥነ ባህርይ (ሞራል) ሰዎች ነበሩ (ዳን 1፡8)። እምነታቸውን ባህላቸውን ለቀው፤ የሚኖሩበትን ሃይማኖትና ባህል እንዲከተሉ በናቡከደነጾር ተገደዱ። እነሱ ግን “አምላካችን ያድነናል። ባያድነንም አንተ ላቆምከው ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ” ብለው መለሱ። በሥነ ባህርይ (ሞራል) ጽናታቸው “በጥበብና በማስተዋል በአገሪቱ ዙሪያ አሉ ከሚባሉት ምሁራን

ሊቃውንት አሥር እጅ የላቁ ሆነው ተገኙ”። (20)። የራሱ ህልም የጠፋበት ናቡከደነጾር በአካባቢያው አሉ ለሚባሉት ምሁራን ሊቃውንት ነን ለሚሉ ለሆዳሞችና ላስመሳዮች ህልሜን ከነትርጉሙ ካላመጣችሁ ትገደላላችሁ ብሎ ቀጭን ትእዛዘ ሰጠ (ዳን 2: 5) ። በዚህ ቀውጢ ሰአት እነዚህ የሥነ ባህርይ (ሞራል) ሰዎች ተገኙ።

እምነታችሁን ሞራላችሁን ልቀቁ ባትለቁ ወደሚንበለበለው እሳት ትጣላላችሁ የሚያድናችሁ የለም። (ዳን 3፡15)ተባሉ። እነሱ ግን “አምላካችን ያድነናል። ባያድነንም አንተ ላቆምከው ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ” የሚል ያሰፈሪውን የናቡከደነጾርን ትእዛዝ በትእዛዛቸው ሻሩት”(3፡18 19)። ባያድነንም”የምትለው ሁለተኛዋ ቃላቸው፤ ዋሽተው መስለው ረክሰው በዚህ ዓለም ከመኖር ይልቅ፤ ለሞራላቸው ሞትን በመምረጥ ገናናውን ናቡከደነጾር አስገረሙት። ለአምላካቸውም አምበረከኩት። የበዓሉ ምክንያትና ዓለማ ይህን ማንፀባረቅ ነው ። አዕምሯቸውን ባብነቱ ቅኔ አበልጽገው፤ ባንድምታው ትርጔሜ የሚዋኙ፤ አካባባያቸውን የታዘቡ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት “ልቡ ለጻድቅ ወኩሉ ከመ አንበሳ”(ተግሳጽ 4፡1)ብሎ ሰሎሞን የተናገረውን መንደርደሪያ በማድረግ፤ “በሶስቱ ወጣቶች የተንጸባረቀውን እምነትና ሥነ ባህርይ (ሞራል) እንዲያከብር እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ላከ” ይላሉ።
፪ኛ. ቅዱስ ገብርኤል ያከበረው ሥነ ባህርይ ከማለም ባሻገር፤ የተሰወረ ሕልም ፈች ብልጥ ያደርጋል።

ናቡከደነጾር ያለመው ህልም ጠፋበት፤ በዙሪያው የነበሩትም ሥነ ባህርይ የሌላቸው የሲኖዶስ አባል ነን እንደሚሉ እንደ እነ አባፋኑኤልና፤ አባ ፋኑኤል ያቆሞሷቸውን ፈቶችን የመሳሰሉ ነበሩ። የነ አባ ፋኑኤልን ሁኔታ መረዳት ከፈለጉ አባ ፋኑኤል ያቆሞሷቸውን ፈቶችን የመሳሰሉ ነበሩ የሚለውን ይጫኑ። ህልሙ ከተሰወረበት ከናቡከደነጾር በታች የወደቁ ነበሩ። የሥነ ባህርይ ሰዎች የተሰወረውን ህልምና ትርጉም ይዘው ብቅ አሉ። ከመካከላቸው አንዱን ዳንኤልን ናቡከደነጾር “ብልጣሶር” ብሎ ሰየመው። ጎዳና ለሚባለው የቅኔ ዓይነት ሊቅ፤ የደብረ ሊባኖሱ የኔታ አምዴ፤ ሰምን ግሥ በሚያደርገው ጎዳና ቅኔያቸው፤ ብልጣሶር የሚለውን ቃል፤ “አዋቂ ሆነ” ወደ ሚል ግሥ በመለወጥ የዘረፉትን ቅኔ አስታውሳለሁ። የዘረፉትን ቅኔ ሲያመሠጥሩም “ብልጥ” የምትለው አማረኛ ቅጽል የብልጣሶር ከፊል እንደሆነች የተናገሩትም ትዝ ይለኛል።

የኔታ አምዴ ከሳቸው በፊት ከነበሩ ከጥንታውያን ሊቃውንት አበው ስለበዓሉ ከገለጹባቸው ቅኔዎች ለምሳሌ ያህል አንዱን እጠቅሳለሁ። ይህ ቅኔ የሥነ ባህርይ (ሞራል) ልዕልና የሚያተርፈውን ክብር። የሥነ ባህርይ (ሞራል) ውድቀት የሚስከትለውን ውርደት ያንጸባርቃል። ቅዱስ ገብርኤል ይህንን ለማክበር እንደተላከ ይገልጻል። ቅኔው ከዚህ በታች ያለው ነው።
“በባቢሎን አመ ተሠርዐ፤ መስዋዕተ ገሞራ ነደ እሳት፤ እሳታውያን ደቂቅ ለኪፎቶ ዝንቱ ኢክህሉ። እሳት አማጣነ በላኢ ወመፍርህ ለኩሉ።

ላእካነ ባቢሎን ህዝብ ባህቱ አመ በእከይ ወዐሉ።
መቅሰፍቶሙ በልኡ ወተካፈሉ።
ላእከ ቤተ መቅደስ ገብርኤል ጊዜ በአሉ። እስመ ሠርዐ እሳተ ለኩሉ።”
ወደ ድርብርብ ጽንሰ ምሥጢሩ ሳንገባ፤ ቅኔው በቁሙ ሲተረጎም፦ ሥነ ባህርይን ለማክበር፤ የሥነ ባህርይን ጉድለት ለመደምሰስ በባቢሎን እሳታዊ ሚዛን በተዘረጋ ጊዜ፤ እሳታውያን ወጣቶችን የእሳቱ ነበልባል ሊበላቸው ይቅርና በእሳቱ ላይ የበለጠ እሳት ሆኑ። በነሱ ላይ የነደደው እሳት ሥነ ባህርይ የሌላቸውን በላቸው። ገብርኤል ይህን ድንቅ ሥነ ባህርይ (ሞራል) ለማክበር ተላከ። ማለት ነው።

የሊቁ ቅኔ የሚያንጸባርቀው “አምላካችን ከሞት ባያድነንም፤ ለእምነታችን፤ ለህሊናችን፤ ለቃላችን፤ ለባህላችንና ለታሪካችን እንሞታለን ብለው የወሰዱትን ቆራጥ ውሳኔ ነበር። ሶስቱ ወጣቶች በተማረኩበት አገር የማረካቸውን የናቡከደንጾርን አዋጅ ገሰሱ። “ባያድነንም እሳቱ ይብላን” ብለው እሳቱ ውስጥ ገቡ። እሳቱ በሰውነታቸው ላይ የሚፈስስ ወደ ወርቅ ጎርፍነት ተለወጠ። በወርቅ በብርና በዓልማዝ ፈርጥ የተንቆጠቆጠ የክብር ጌጥ ሆነላቸው። ከሰውነታቸው ሙቀት ጋራ ተስማማ፣ ተመቻቸው፣ ሞቃቸው። የራስ ወርቅ፤ የውርቅ ጫማ ሆነላቸው። እነሱን ወደ እሳቱ የወረወሯቸውን ሞራለ ቢሶችን እንደ ማግኔት እየጎተተ በመሳብ በላቸው። ሶስቱ ወጣቶች የናቡከደነጾርን ጭንቅላት ተቆጣጠሩት። የራሱን አምልኮ አስለቅቀው ለአምላካቻው አምበረከኩት (ዳን 3 28­30)። የቅኔ መምህራን የነ ሲድራቅን ሥነ ባህርይ (ሞራል) ሰም፤ የበላይ ዘለቀን ሥነ ባህርይ (ሞራል) ወርቅ፤ በማድረግ የዘረፉትን ቅኔ ተቀብያለሁ። እራሴም ቆጥሬ ነግሬበታለሁ።

“አምላካችን ያድነናል። ባያድነንም አንተ ላቆምከው ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ” ብለው ናቡከደነጾርን ሳይፈሩ ለእምነታቸውና ለሞራላቸው የበለጠ ክብር እንደሰጡ፤ በላይ ዘለቀም በመከራ በፈታኝ ጊዜ ለሞራሉ ክብር ለወሰደው ቆራጥ ርማጃ ሲቀኙለት የኖሩት የቅኔ መምህራን ብቻ አይደሉም። ክብረት በላይን የመሳሰሉ የዘመናችን አዘማሪዎችም፦
“ጀግንነት ወንድነት ለትውልድ አውርሶ
አለፈ ያ ጀግና የልቡን አድርሶ” እያሉ ለበላይ ዘለቀ ክብርና ልዕልና በመዘመር ላይ ናቸው።
ሳይፈሩ ሳያፍሩ “አምላካችን ያድነናል። ባያድነንም አንተ ላቆምከው ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ” በማለት ናቡከደነጾርን ሰለሰቱ ደቂቅ እንደተፋለሙት፤ በላይ ዘለቀም ሞሶለኒን ሳይፈራ ተፋለም። ክብረት በላይ
“የበረሀው ዳኛ የጫካው ንጉሥ፤
በላይ ሰው አይፈራም ያለ ክርስቶስ” እያለ በማዘመር ለበላይ ዘለቀ አንጸባረቀው። ሙሉውን ለማየት የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ። [ ክብረት በላይ ለበላይ ዘለቀ ሥነ ባሕርይ ልዕልና የዘመረለት ውዳሴ ]

አባቶቻችን በሰሩልን፤ በያመቱ በሚታወሰው ቅዱስ ገብርኤል ባከበረው ሥነ ባህርይ ሚዛን፤ ኢትዮጵያን በመምራት ላይ ያሉትን ብዙዎችን መንፈሳውያን መሪዎችን እና ወያኔዎችን ባንድ ረድፍ፤ በኢትዮጵያ ውስጥና ከኢትዮጵያ ውጭ በማፈለም ላያ ያሉትን የኢትዮጵያ ልጆች ደግሞ በሌላ ረድፍ ስንመዝናቸው፦ ወያኔ በወገን ላይ የሚፈጽመው በደልና ግፍ ፤ ናበከደነጾር ከፈጸመው ግፍና በደል እጅግ የከፋ ነው። በወያኔ ላይ የሚደርሰው ቅጣትም፤ በናቡከደነጾር ላይ ከደረሰው እጽፍ ድርብ የከበደ ቅጣት የሚጠብቀው ይመስላል። ”ናቡከደነጾር በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን በደል ትቶ ትክክለኛ የሆነውን ባለማድረጉ ክፋትን ትቶ ለተበደሉት ለተጨቆኑት ቸርነት ባለማድረጉ (4፡27)“እንደከብት ሳረ በላ ሆነ። የራሱ ጸጉር እንደንስር ላባ፤ ጥፍሮቹ እንደ ወፍ ጥፍር ሆኑ። በራሱ በደልና ኃጢአት ረግረግ ውስጥ ሰመጠ”(4፡33)እንደዚሁ ሁሉ፤ወያኔም በህዝብ ላይ በሚፈጽመው ደባ ወደ እመቀእመቃት በመስመጥ ላይ እንዳለ በሰፊው እየተነገረ ነው።

የወያኔ መንግሥት ሊቃውንት ብሎ በታላላቅ ማእረግ ላይ የሰየማቸው በናቡከደነጾር ዙሪያ እንደነበሩት ህልም መፍታት ማስታወቅ ያቃታቸው የሚቆረጡ ምቱርራን ሆኑ። (ዳን 2፡5)በዙሪያው ያሉት ምሁራን ጸሀፊዎች ጋዜጠኞች ነን የሚሉ ሁሉ በአገሪቱ ካሉት ሁሉ አዋቂዎች በሥነ ባህርይ (ሞራል) በጥበብ በማስተዋል አሥር እጅ በልጠው መገኘት (1፡20) ሲገባቸው፤ የህልም ምሥጢር ሊተረጉሙ ቀርቶ፤ በሞተው ባቶ መለሰ ህልም ተደናባሪና ህዝብ አደናባሪዎች ሆኑ።

ያየውን ህልም ረስቶ ህልሜን ከነትርጉም ንገሩኝ ካለው ከናቡከደነጾር ወያኔ እጅግ በጣም ተንኮታኩቶ ወደቀ። ናቡከደነጾር የሰጠው ትእዛዝ ፤ ከሱ በፊትና ከሱ በኋ ያሉ መሪዎች ያላደረጉትን እስካሁን ተሰምቶና ተደረጎ የማይታወቅ የጠፋብኝን ህልሜን ከነትርጉሙ ውለዷት የሚል የእብድ ትእዛዝ ነበር። የራሱን ህልም ከረሳው ከናቡከደነጾር ወያኔን የባሰ የሚያደርገው፤ ህልሜን ከነትርጉም ንገሩኝ አለማለቱ ብቻ አይደለም። ያቦቶቻችን ህልም የተመሰረተበትን የ ኢትዮጵያውነትን ህልም ሆን ብሎ እየደመሰሰ መምጣቱ ነው።

፫ኛ. ወያኔ ሊደመስሳቸው የሞከራቸው፤ ያባቶች ህልም የተመሰረተባቸው፤ ኢትዮጵያውያን የተወሀድንባቸው 4 መንገዶች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች እንደሚገልጹት የኢትዮጵያዊነት ህልም የተመሰረተባቸው ወያኔ የደመሰሳቸው አራት መንገዶች ናቸው።

● 1ኛ “ከ8ኛው ክፍለ ዘመን በፊት አክሱም የሰው ዘር መናሀሪያ ነበረች። ከጎረቤት አገሮች ከየመን ከግብጽ ከእስራኤል ከመካከለኛውና ከሩቅ ምስራቅ አገሮች ወደ አኩስም ከተማ ለንግድና፤ ከተማዋ ያፈራችውን ስልጣኔን ለመካፈል፤ በተለያዩ ምክንያያቶች ብዙ የተለያዩ የሰው ዘሮች ይጣለፉባት ነበር። በዚያ ወቅት በዚህ ሁኔታ ከየአቅጣጫዎች የተሰበሰቡ ሁሉ ተዋልደዋል። ተቀላቅለዋል።ተቀይጠዋል። አንድ ሆነዋል።

● 2ኛ:­ የተቀየጠው ህዝብ የሚኖርባትን የአኩስምን ከተማ በስምንተኛው ክፍለ ዘመን ዮዲት ስታፈርሳት፤ ከሞት የተረፈው ህዝብ ወደ መሀል ኢትዮጵያና ወደ ጠረፍ ወደ ባሌ፣ አሩሲ፣ ሀረር ድረስ ተበትኖ ካካባቢው ህዝብ ጋራ ተቀላቀለ። ተዋለደ በደም ባጥንት አንድ ሆነ።

● 3ኛ፦ በ12ኛ ክፍለ ዘመን ከምሥራቅ ኢትዮጵያ የተነሳው ግራኝ መሀመድ በዮዲት ወረራ ምክንያት በመላ ኢትዮጵያ ተበትኖ በየደረሰበት ትዳር እየያዘ ንብረት እያፈራ ኑሮ የጀመረውን ህዝብ ሠራዊት አድርጎ፤ ወደ መሀል ኢትዮጵያ እና ወደ ሰሜኑ ጠረፍ በማዝመት እንደገና መለሰው። ይህም ማለት ወደ ቅድመ አያቱ ቦታ በዘመቻ መልክ ተመለሰ ማለት ነው።

● 4ኛ፦እርሱ በርሱ እየተዋደደ እየተስማማ በመጋባት ተዋልዷል። ሆኖም በፍጥነት ከሚገናኙባቸው ቦታወች ራቅ ብለው ለብዙ ዘመን የቆዩት ወገኖች ያካባቢውን ቋንቌ በመናገርና በወንዝና በሸንተረር ቢወሰኑም።በሶስቱ መንገዶች ሳይቀላቀሉ ያመለጡ ምንም የደም ንክኪ የሌላቸው አይደሉም።

ጌታችን በወንጌሉ “ከኔ ጋራ ያልሆነ ጠላት ይበትነኛል” እንዳለው። ከህዝብ ጋራ ዝምድና የሌለው ጠላት፤ ህዝብ ይበትናል እንጅ አይሰበስብም። ህዝብ መበተን የሥነ ባህርይ ጉድለት ነው። የህዝብ አንድነት የኃይል ነው። የሥነ ልቡና ጉድለት ያለው ቅኝ ገዥ ነው። ቅኝ ግዛትን የሚወድ ደግሞ የአዕምሮ በሽታ ያጠቃው ነው። በዚህ ዓይነት በሽታ የተጠቃው ወያኔ ያቦቶች ስነ ልቡና የተመሰረተበትን ህዝቡ በደምና በአጥንት የተሳሰረበትን ህብረት እያፈረሰ መጣ።

በናቡከደነጾር ላይ የደረሰው መከራ “እንደከብት ሳረ በላ ” በመሆን በራሱ ላይ የቆመ አልነበረም። “የራሱ ጸጉር እንደንስር ላባ፤ ጥፍሮቹ እንደ ወፍ ጥፍር ሆነ”(4፡33። እንደተባለ፤ ወያኔ ኢትዮጵያን የሰነጠቀበት፤ የህዝቡን ገላ የሚቧጥጥባቸው ኃያላን መስለው የሚታዩ ኢትዮጵያውያንን በመደብደብ ላይ ያሉ ወታደሮች ጥፍሮቹ ናቸው። እነዚህ እንድንስር ላባ በነው ያልቃሉ። በዓሉ የሚነግረን ይህንን ነው።

የአባቶች ስነ ልቡና የተመሰረተበትን ህብረት እያፈረሰ የመጣውን፤ ባካባቢው ያሉት “ዘመናት ይለወጣሉ መንግስትም ያልፋል። ጥበብን ለጠቢባን እውቀትን ላስተዋዮች ይሰጣል”(2 ፡21)እያሉ መገሰጽ ሲኖርባቸው፤ በህልም አልባነቱ ተጨንቆ ህዝቡን በማስጨነቅ ላይ፤ መንፈሱም ታውኮ ህዝቡን በማወክ መኖሪያውን በማፍረስ ላይ ካለው ከወያን ጋራ ተባበሩ ። በናቡከደነጾር ዙሪያ የነበሩት “ህልሙን ከነፍቹ ባታሳውቁ ትቆረጣላችሁ። ቤቶቻችሁም የጉድፍ መጥያ ይሆናሉ” (2፡5)። እንደተባሉ፤ ህዝቡ ለስለት የሰጠውን ገንዘብ እየዘረፉ ንብረት ቤት የገነቡ በወያኔ ዙሪያ ያሉ ሆዳሞች ስግብግብ አስመሳይ ጳጳሳት ቆሞሳት ቀሳውስትና የሰንበት መምህራን የከፋ ፍርድ ይጠብቃቸዋል። ከበዓሉ እንደምንረዳው ከዚህ አይነት መከራ ተርፈው ሌላውን ማትረፍ የሚችሉት “ምህረትን ከሰማይ አምላክ የሚለምኑ”(ዳን 2፡18)የሥነ ባህርይ (ሞራል) ሰዎች ብቻ ናቸው። “ለጥምቀት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲሸርት እንዳንለበስ ወያኔ ከለከለን” የሚሉ ወገኖችም ያባቶቻቸውን ሥነ ባህርይ (ሞራል) እያንጸባርቀ ለረዥም ዘመን የኖረውን ቅዱስ ገብርኤል ያከበረውን ሥነ ባህርይ ማስተጋባት አያቁሙ እንጅ፤ ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲሸርት ባለመልበሳቸው የሚጎድልባቸው ነገር እንደሌለ በዚህ አጋጣሚ ሊገነዘቡ ይገባቸዋል።
፬ኛ. ለጥምቀት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲ­ሸርት ባለመልበስ የሚጎድል ነገር የለም።

የዚህ መንግሥት ተሳታፊዎች አንድነትን እያፈረሱ ባንዲራ እያቃጠሉ በኢትዮጵያ ላይ የመጡባት ጠላቶች ናቸው። መሪዎቻቸው ወደ አገራችን ሰርገው በገቡ፤ Only Jesus (ኢየሱስ ብቻ) በመሳሰሉ ሰባኪዎች ኢትዮጵያዊነታቸውን ከጭንቅላታቸው የታጠበባቸው ናቸው። እነዚህ ሰዎች ለጥምቀት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲሸርት መልበስ ቢከለክሉ የሚያስገርም አይደለም። ይልቁንስ ቅዱስ ገብርኤል ያከበረውንም ሆነ በጥምቀት በዓል የሚከበረውን በዓል ወደ መከልከሉ ደረጃ እንዳይደርሱ ጠንክሮ ለመታገል መዘጋጀት ነው። ጥምቀት ክርስቶስ ጽድቅን የፈጸመበት፤ ነፍሰ ገዳዮችን አረመኔዎችን “ከህገ አራዊት ተላቀቁ!ከህገ አረሚ ውጡ!እያልን የምናውጅበት፤ ስነባህርይ የጎደላቸውን የምንዋጋበት መሳሪያችን ነው።
ďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżź
ታላላቅ መንፈሳውያን በዓሎቻችን ”አምላካችን ያድነናል። ባያድነንም ለሆዳችን በመገዛት ከረከሰው መንግሥት ጋራ በመርከስ በዚህ ዓለም ከመኖር ይልቅ፤ ለስነ ባህርያችን መሞት ይሻለናል” እያሉ አባቶቻችን ኢትዮጵያውያን፤ ከገረቤቶቿና ከቀረው ዓለማት ልዩ አድርገው ነጻነቷንና ክብሯን የጠበቁባቸው ሥነ ባህርይ፤ በትውልዱ ልቡና መቀረጽ ያለባቸው ናቸው። Only Jesus (ኢየሱስ ብቻ) የመሳሰሉ ሰባኪዎች፤ ከኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የበለጠ የነገረ መለኮት እውቀት እንዳላቸው በመምሰል፤ “ከክርስትና ጋራ ምን አገናኛቸው“ እያሉ የሰበኴቸው ወገኖች” “እኛ ምን አገባን” እያሉ እየነቀፉ እየተቹ እየናቁ እያጥላሉ ያልተገነዘባቸውን ወገን በመስበክ ላይ ናቸው። ይህን ስርአት የዘረጉት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ወራሪዎች የሚሉትን ሳያውቁ ቀርተው አይደለም። ከወያኔ መንግሥት ጋራ በመተባበር፤ ተንቀሳቃሽ ያልሆኑትን ንብረቶች በማቃጠል፤ በመቅበርና በመናድ፤ ተነቀሳቃሽ የሆኑትን ቅርሶች በመሸጥ ላይ ናቸው። የዋሀን ጥቂት ወገኖቻችንን ከቋንቋቸው ከቀለማቸውና ከስማቸው በቀር ልባቸውንና ጭንቅላታቸውን አጥበው ባዶ ቀፎ በማድረግ እዚህ ውዥንብር ውስጥ ኢትዮጵያን ከተዋታል።

ይህን የተባበረ አፍራሽ ኃይል መቋቋምና ማሸነፍ የሚቻለው፤ ለጥምቀት እለት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲሸርት በመልበስ አይመስለኝም። “የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውን ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም”(ሮሜ 10፡3)። እንዳለው፤ ጠላት በቀላሉ የሚመታቸውን ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲሸርት የመሳሰሉትን በህዝቡ ደም ያልገቡትን ነገሮች ከመፍጠር ይልቅ፤ አባቶቻችን በእግዚአብሔር ጽድቅ በመሰረቱት ሥነ ባህርይ (ሞራል) ኢትዮጵያዊነትን ጠብቀው ያቆዩበትን ስርአት ወደ መሰረታዊ ትርጉሙ መልሰን በትውልዱ ጭንቅላት ሰርጾ እንዲገባ በማድረግ ብቻ ነው። ኢትዮጵያን ጠብቀው ያስረከቡን ዳዊት ደጋሜ የነበሩ አባቶች፤ ራሱን ዳዊትን እንደ ምሳሌ ይጠቅሱታል። ዳዊት ሳኦልን ታግሎ ያሸነፈው ከስነ ባህርዩ ጋራ በተዛመደለት በእጁ በነበረው ወንጭፍ ነበር (1 ሳሙ 17፡50)። እንደዚሁ ሁሉ፤ አገርን ወገንን እምነትን ለማዳን የሚያስፈልገው ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲ­ሸርት በመልበስ ሳይሆን፤ ከላይ እንደገለጽኩት ተጠብቀው በቀዩት ዓበይት በዓላት በሚንጸባርቁት ሥነ ባህርይ (ሞራል) ነው።

እንደ ሰለስቱ ደቂቂ ከሆዳምነት ከግል ጥቅምና ሥነ ምግባሩ ከረከሰበት መንግስት ንኪክ ከመርከስ ህሊና ማራቅ ነው። “ላቆምከው ምስል እንደማንሰግድ እወቅ”(3 ፡18 )ብለው ሶስቱ ወጣቶች ናቡከደነጾርን እንዳበረከኩት፤ እግዚአብሔር ይመስገን!ዛሬም የቀደሙ ኢትዮጵያውያን አባቶቻቸውን ምሳሌ በመከተል፤ ለጥምቀት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲ­ሸርት እንዳይለብሱ የተከለከሉ ወጣቶች፤ ከወያኔ ንክኪ ላለመርከስ እራሳቸውን ጠብቀው በያሉበት እየታገሉ ናቸው። ወያኔ ባነደደው እሳት(እስር ቤቶች)የገቡ፤ የሚደበደቡ የሚገረፉ ሁሉ እግዚአብሔር ስነ ልቡና አክባሪ የሆነውን ቅዱስ ገብርኤል በመላክ ሰውነታቸው ከሚችለው በላይ እንደማያደርግባቸው እናምናለን።

በኢትዮጵያ፡ በኢሮፕ፡ ባሜሪካ፡ በከናዳ በዓለም ዙሪያ ተበትናችሁ ወያኔን በመታገል ላይ ያላችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ!ለጥምቀት ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲሸርት እንዳይለብሱ ወያኔ በመከልከሉ ወያኔን ይታዘቡት ይናቁት እንጅ የሚጎድልባቸው ነገር እንደሌለ ለተከለከሉት ወገኖች ንገሩ!ይልቁንስ፤ በህገ አራዊትና፤ በህገ አረሚ ኢትዮጵያን በማመስ ላይ ያሉትን ሁሉ፤ ጽድቅን ለመፈጸም የክርስትና እምነት ባይኖራችሁም፤ “ከህገ አራዊት ተላቀቁ!ከህገ አረሚ ውጡ!“አትግደል አትዝረፍ“ ከምትለው ከኦሪት ለመድረስ ሞክሩ እያላችሁ በተባበረ ድምጽ መንገራችhሁን አትሰልቹ! በተረፈ፤ ጌታችን አምላካችን ጽድቅ የፈጸመበትን የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንኳን አደረሳችሁ በማለት፤ ቅዱስ ገብርኤል ስላከበረው ሥነ ባህርይ መግለጽ የጀመርኩትን ከዚህ ላይ በመግታት እሰናበታችኋለሁ።
ማሳሰቢያ፦ ስለ ሕገ አራዊት፣ሕገ ኦሪትና ሕገ ክርስቶስ የበለጠ ለመረዳት ከፈለጉየሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ :­ የጥምቀት በዓል
ለሌሎች ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ጦማሮች የሚከተለዉን ድረ­ገጽ ይመልከቱ:: http://medhanialemeotcks.org/
ďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżźďżź

The post ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ! – ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ካድሬዎች በየሜዳው የምርጫ ካርድ በግዳጅ እየሰጡ ነው

$
0
0

election
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ2 ምርጫ በፊት በ0 የተሸነፈው የገዢው ስርዓት ባለፈው ምርጫ 96.6% አሸንፍኩ ማለቱን ተከትሎ ምርጫው መሳቂያ እንደሆነበት ብዙዎች ሲተቹበት የቆየ ጉዳይ ነው:: በባለፈው ዓመት ምርጫ ብዙ ሰው “ብንመርጥም ስለሚጭበረበር ግዜዬን አላጠፋም” በሚል ካርድ ያልወሰደ ሲሆን ዘንድሮ በግድ እንዲወስዱ እየተደረገ ነው::

የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ያነጋገሯቸው ምንጮች እንደሚሉት ስርዓቱ ያዘጋጃቸው ካድሬዎች በየቤቱ እየሄዱ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ እያስገደዱ ሲሆን ከታክሲና አውቶቡስ መውረጃ ቦታዎች ላይ ወንበር እና ጠረጴዛ አስቀምጠው አላፊ አግዳሚውን በግድ የምርጫ ካርድ እንዲውስድ እያስገደዱት ነው::

የምርጫ ካርድ የሚሰጡት የኢህአዴግ ካድሬዎች በመሆናቸው ካርድ ሲሰጡ ኢሕ አዴግን ምረጡ እንደሚሉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

The post ካድሬዎች በየሜዳው የምርጫ ካርድ በግዳጅ እየሰጡ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ህወሓት ከወሎ ተጨማሪ መሬት ወደ ትግራይ ለመከለል ዝግጅት ላይ ነው

$
0
0

ናትናኤል መኮንን

740px-Afar_in_Ethiopia.svgከተመሰረተ 40 አመት ሊያስቆጥር ቀናት የቀረውና አሁንም በገንጣይነት ተግባሩ የቀጠለው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ከወሎ ተጨማሪ መሬት ለመከለል ዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ ለደሴ ሆስፒታል ባዛር በተደረገበት ወቅት ህወሓት አገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶች በባዛሩ እንዲገኙ ያደረገ ሲሆን በወቅቱም ወሎ ውስጥ ሰፊ መሬት እንዲሰጣቸው አድርጓል፡፡ በተለይም ከቆቦ ወደ ወልደያ በኩል 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አላውሃ የተባለ ቦታ ላይ በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደጋፊና አባል ባለሀብቶች መሬት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ውስጥ ለውስጥም ‹‹የትግራይ ድንበር አላውሃ ምላሽ ነው›› በሚል እያስወራ እንደሚገኝ የአካባቢው ነ…ዋሪዎች ገልጸዋል፡፡አላውሃን ጨምሮ ሌሎች የትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ የወሎ መሬቶች ላይ አርሶ አደሮቹን እያፈናቀሉ ለህወሓት ደጋፊና አባል ባለሀብቶች መሬት ለመስጠት ሰፊ እቅድ እንደተያዘና በሂደት በአካባቢው በርከት ያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች እንዲኖሩ በማድረግ ቦታውን ወደ ትግራይ ለመከለል ሴራ እየተሸረበእንደሚገኝ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል፡፡የቆቦና ሌሎች የትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ የወሎ መሬቶች ላይ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ተሰጥተው የአካባቢው ተወላጆቹ መሬት አልባ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህም ተከትሎ ሰሞኑን ወሎ ውስጥ ተጨማሪ መሬቶች ወደ ትግራይ ሊከለሉ ነው በሚል ህዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሯል፡፡ ህወሓት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የጎንደርና የወሎ መሬቶችን ወደ ትግራይ መከለሉ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ በስፋት የጀመረው መሬትን ለትግራይ ባለሀብቶች የመስጠት እቅድም ወደፊትም ሰፋፊ መሬቶችን ወደ ትግራይ ሊከልል እንደሚችል አመላክቷል፡፡

The post ህወሓት ከወሎ ተጨማሪ መሬት ወደ ትግራይ ለመከለል ዝግጅት ላይ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የትግራይ ነጻ አውጪዎች ኢትዮጵያን ማጥፋት ይችላሉን –ከሳሙኤል አሊ

$
0
0

tplfነብር ዠጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ሊቀይር አይችልም ይላል በታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ። ይህ ቃል የኔ ወይም የናንተ አልያም የወያኔዎች ቃል አይደለም ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ ሁሉን ማድረግ የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ኢትዮጵያዊ መልኩን ኢትዮጵያዊነትም ሊቀየር አይችልም ይላል እግዚአብሔር። ታዲያ  ወያኔ  ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳው ከምን ተነስቶ ነው? የሰው ልጅ መጋፋት የሚቻለው ከሰው ጋር ሊሆን ይችላል ወያኔ ግን ከፈጣሪ ዘንድ ነውና ኢትዮጵያን ማጥፋት ከቶውኑ አይችልም። ወያኔዎች ኢትዮጵያዊ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያወቁ አልመሰለኝም።

አዎ ኢትዮጵያዊ ማለት

እግዚአብሔር የመረጣት አገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ህዝብ የሚኖርባት መሬት.. በህገ ልቦና ገና  ህግ ሳይሰራ  ሊቀ ነብያት ሙሴም ህግን ከእግዚአብሔር ሳይቀበል በፊት እግዚአብሔርን በማምለክ የኖረች አገር ነች።

ኢትዮጵያ ማለት በህገ ኦሪት ሙሴ  ህግን ከእግዚአብሔ ከተቀበለ በኋላ ኢትዮጵያ በሙሴ አማካይነት ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ህግ ተቀብላ በህገ ኦሪት ስትመራ የቆየች አገር ነች።

ኢትዮጵያዊ ማለት በህገ ወንጌልም ግዜ ወንጌልን ተቀብላ የእግዚአብሔርን ቃል በአገሪቷ እያስነገረች ለአለም ምሳሌ የሆነች አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች አላወቁ ይሆን።

ክርስትናን ከእስራኤል በመቀጠል የተቀበለች አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች አልተረዱ ይሆን።

እስልምናን ከሳውዲ አረብ በመቀጠል የተቀበለች አገር እና አዛንን ለመጀመሪያ  በአደባባይ ላይ ያለው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ አላወቁ ይሆን።

ኢትዮጵያ ማለት በውስጧዋ የሚኖሩት የተለያየ ባህል ያላቸው እና ድንቅ መልከአ ምድር የያዘች አገር መሆኗን ዘንግተውት ይሆን።

ኢትዮጵያዊ ማለት ስም ብቻ ሳይሆን ስሜት የተቀላቀለበት እውነት የሚነገርባት ፈጣሪ የመረጣት ቅዱሳን የሚኖሩባት በደምስራችን የታተመች ለውጥ የማያሻት የታሪክ ማህደር የውበት መንደር እንደሆነች አላወቁ ይሆን።

ኢትዮጵያዊ ማለት አፍራሾች ቢከቧት የማትፈርስ ጠላቶች የማይተኟላት ግን የማይችሏት ታግለው የማይጥሏት የፈጣሪ ጥበቃ የማይለያት አገር መሆኗን ዘንግተውት ይሆን።

እናም ኢ..ት..ዮ..ጵ..ያ ማለት ዘር ቀለም ሳንል በሃይማኖት ሳንለያይ የምንኖርባት አገር እንደሆነች ማወቅ አለባቸው።

ገበሬው እያረስ ህዝብን የሚመግበውን ያለ  ምክንያት በግፍ በወያኔ ሆዳም አደሮች ከመሬቱ ሲፈናቀል ኢትዮጵያዊ ማለት ገበሬው ነው ገበሬው ሲነካ  ያመኛል።

ተማሪው ነገ አገር ለመረከብ ወደ ትምህርት ገበታው እውቀት ለማወቅ በሚሄድበት ግዜ ወያኔ  የኔን ፖሊሲ ተማር የኔን ፖለቲካ አራምድ ብለው በግድ ተማሪውን እያስገደዱ እውቀቱን የሚያጨናግፉ ኢትዮጵያዊ ማለት ተማሪው ነው ተማሪው ሲነካ  ያመኛል።

ኢትዮጵያዊ ማለት ፖለቲከኛው ነው። ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የፖለቲካ አመራር ለመወሰድ ፖለቲከኞች ለአገራቸው ሲሰሩ የግድ እንደ ቦይ ውሃ በአንድ መስመር መፍሰስ አለባችሁ ተብለው የገንጣይ አስገጣይ ፖለቲካ አራምዱ ሲባሉ እንቢ ኢትዮጵያዊ ማለት ኢትዮጵያዊ መሆን ነው እንጂ ዘረኛ መሆን አልያም መከፋፈል አይደለም ብለው ለእውነት የቆሙትን ሲታሰሩ እና ሲገደሉ ኢትዮጵያዊ ማለት ፖለቲከኛው ነው ፖለቲከኛው ሲነካ ያመኛል።

ኢትዮጵያዊ ማለት ጋዘጠኛው ነው። ጋዜጠኞችም እኛ የጻፍንላችሁን አንብቡ የጻፋችሁትንም እኛ ኤዲት አድርገን ካለፈ ብቻ ነው ማቅረብ የምትችሉት ብለው የጋዜጠኝነትን ሙያ አቃለው ስህተት ብቻ  እንዲዘግቡ ሲያስገድዷቸው የለም ጋዜጠኛ ማለት ትክክለኛውንና የተሰማውን የሚሰራና የሚያቀርብ ለህሊናው የሚኖር ለእውነት የሚገዛ እውነትን ወደ ህዝብ አቅራቢ እውነትን ዘጋቢ ነው የሚሉት ኢትዮጵያዊ ማለት ጋዜጠኛው ነው። ጋዜጠኛው ሲነካ ያመኛል።

ኢትዮጵያዊ ማለት ሰራተኛው ነው። አገር ለማሳደግ ጠዋት ወጥቶ ማታ የሚመለሰው ሳይሰለቹ ለለውጥ አገር ለማሳደግ የሚሰሩት ሰራተኛው ነው ኢትዮጵያዊ። ሰራተኛው ሲነካ ያመኛል።

ኢትዮጵያዊ ማለት መምህሩ ነው። የነገን አገር ተረካቢ ለማፍራት እውቀታቸውን ሳይሰስቱ ትውልድን ለመቅረጽ ብቁ ዜጋን ለማፍራት ሲደክሙ እውቀታቸውን ጨምቀው የሚያስተምሩ ኢትዮጵያዊ ማለት መምህሩ ነው። መምህሩ ሲነካ  ያመኛል።

ኢትዮጵያዊ ማለት አርቲስቶች ናቸው። በዜማ  በስነ-ጹሑፍ በስነ-ስዕል ስለ አገራቸው ክብርና ዝና ሲያቀርቡ የውስጥ ተሰጦአቸውን ለህዝብ ሲያቀርቡ እውነትን በጥበባቸው ሲገልጹ ህዝብን ሲያዝናኑ እና ሲያስተምሩ ኢትዮጵያዊ ማለት አርቲስቶች ናቸው። አርቲስቶች ሲነኩ ያመኛል።

ኢትዮጵያዊ ማለት ስፖርተኖች ናቸው። በዓለም መድረክ ድንቅ ችሎታቸውን በመጠቀም ከኢትዮጵያ  የበቀሉ አይበገሬ መሆናቸው ሲያሳዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ኢትዮጵያዊ ማለት ስፖርተኛው ነው። ስፖርተኛው ሲነካ ያመኛል።

ኢትዮጵያዊ ማለት ኢትዮጵያዊ ነው ከአምላክ የተሰጠን ድንቅ ስጦታ በምንም በማንም የማትለወጥ በልቦናችን ውስጥ የታተመች አገር ኢትዮጵያ።

ታዲያ  ይህቺን አገር ነው ወያኔ ሊያፈርሰው ሌት ተቀን የሚማስነው። ይህቺን ከፈጣሪ የተሰጠች አገር ሊያጠፋ ነው ሽር ጉድ እያለ  የሚገኘው። መስመር አበጅቶ ለመገነጣጠል እንዲያመቸው አንዱ ከሌላው ጋር የማያባራ  ጠላትነት እንዲመሰርት እና አንዱ ከሌላው ጋር እርስ በራስ እንዲጠፋፋ የማይሆን ታሪክ እየተናገረ  ያለው። አልቻለም እንጂ እንደ ውያኔ ሃሳብ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንድትኖር አይፈልግም አገር ብቻ  ሳይሆን በውስጧ የሚኖሩትንም ህዝብ እርስ በእርስ በማናከስ እና በማጥላላት ወደ ግጭት አምርተው እንዲጠፉ ነው የሚፈልገው ነገር ግን በእግዚአብሔር ጠባቆትነት ስር ስላለች መቼም ማፍረስ አይችልም።

እናም በአገራችን በሰላም ለመኖር እና የፈለግነውን እየሰራን፣ እየተናገርን በፍቅር ለመኖር ወያኔ የሚባለውን ጭራቅ በእግዚአብሔር ስም በአላህ ስም ተቀናጅተን እናጥፋው ያኔ  ኢትዮጵያ እንኳን ለኛ ለዓለም ሁሉ የምትተርፍ አገር ትሆናለች።

አርበኞች ግንቦት 7 መቼም ቢሆን በሰላማዊ ትግል ሊወርድ እንደማይችል ተገንዝበን ወደ  ትጥቅ ትግሉ ገብቷል። ኢትዮጵያን የመጠበቅ እና  የማስጠበቅ የሁላችንም ግዴታ ነው። የምንወዳትን አገር የማንም ሽፍታ መጥቶ  ማፍረስ ሲፈልግ ማንም እንደማይፈቅድለት ማሳወቅ ያለብን ሁላችንም ወደ አርበኞች ግንቦት 7 በመቀላቀል በአጭር ግዜ ውስጥ ወያኔን ደምስሰን ማጥፋት አለብን። ኢትዮጵያን የመጠበቅ ስራን ሁላችንም መወጣት እንዳለብን ማወቅ አለብን። በአገር ቀልድ የለም!! ወያኔ ከአሁን በኋላ በምንም መልኩ እያጭበረበረ የኢትዮጵያን ህዝብ እያሰረ እና እየገደለ  የሚኖርበት ዘመን ሳይሆን… ኢትዮጵያኖች ወያኔን ከነ  መርዙ ነቅለው ለማጥፋት  ሁሉም ኢትዮጵያ   ለትግል በአንድነት ይነሳ።

በኢትዮጵያ ቀልድ የለም። አገር ወዳድ ሁሉ በቆራጥነት በልበ ሙሉነት ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም።

ኢትዮጵያ  ለዘላለም ትኑር

ከ-ሳሙኤል አሊ

samilost89@yahoo.com

The post የትግራይ ነጻ አውጪዎች ኢትዮጵያን ማጥፋት ይችላሉን – ከሳሙኤል አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Article 7

$
0
0
Asrat Abrha

አስራት አብርሃ

አቶ አስራት አብርሃ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቀድሞው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነበሩ፡፡ አቶ አስራት አብርሃ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ፣ በግንቦቱ አገራዊ ምርጫ፣ ምርጫ ቦርድ እውቅና በሰጣቸው የአንድነት አመራሮች ዙሪያ እንዲሁም በአጠቃላይ ስለ ወደፊቱ የአንድነት ፓርቲ ዕጣ ፈንታ የየኛ ፕሬሱ ያዕቆብ ብርሃኑ አነጋግሯቸዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡ -–[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

The post appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

Health: ለራስ ምታት ህመም ፍቱን የሆኑ ምግብና የመጠጥ አይነቶች

$
0
0

የውጪ ሀገራትን ያህል ባይሆንም በርካቶች ለትንሹም ለትልቁም ህመም ክኒን ወደ አፋቸው ወርወር ማድረግን ከለመዱ ቆይተዋል፡፡ መድሃኒቶች በአግባቡ ሲወሰዱ የመርዳት አቅማቸው ከፍተኛ የመሆኑን ያህል ከበሽታ አምጪዎች ጋር ሲላመዱ ደግሞ ጣጣቸው ብዙ ነው፡፡ የጎንዮሽ ጉዳቶችንም ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ለህመሞቻችን ሁሉ ሁልጊዜ ክኒኖችን እንድንወስድም አይመከርም፡፡ ቀለል ያሉትን በአካባቢያዊ፣ አመጋገብ እና አጠቃላይ ጤናማ አኗኗር ብቻ ማስታገስ እና ማዳን እንደምንችል ባለሞያዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ለዛሬ ትኩረት ያደረግነው አንዴ ወይም ሌላ ጊዜ አብዛኞቻችን ገጥሞን በሚያውቀው ራስ ምታት ላይ ነው፡፡ መደበኛው ቀላል ራስ ምታት ወይም ጠንካራው ማይግሬይን ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ቀላል መፍትሄ አድርገው ሰዎች የሚወስዱት የራስ ምታት ክኒን ውጠው እንዲሻላቸው መጠበቅ ነው፡፡ ነገር ግን ከክኒኖች በተሻለ ያለጎንዮሽ ጉዳት በምግብና መጠጦች ራስምታቱን በፍጥነት ማስታገስና ማስቀረት እንደሚቻል በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ለመደበኛው ራስምታትና ማይግሬይን ፍቱን የተባሉት ምግቦችና መጠጦች የትኞቹ ይሆኑ?
ራስ ምታት የሚደጋግማት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዋ ማህሌት ግርማ ራስ ምታት ሲጀምራት ሰው ማት ራሱ ያስጠላታል፡፡ የለመደችውን ክኒን ካልዋጠች ፍፁም እረፍት አታገኝም፡፡ ክኒኑ ግን ሁልጊዜ በቅርብ ላይገኝ፣ የተፈገለውን ፈጣን ፈውስም ላይሰጣት ይችላል፡፡ ‹‹አንዳንዴ እናቴ ቡና ታፈላልኝና አንድ ስኒ ስወስድበት ቀለል ይላል፡፡ ምናልባትም ከክኒኑ ቡናው ፍቱን ሳይሆን አይቀርም›› ትላለች ማህሌት፡፡ የማህሌትን ሀሳብ አሁን አሁን የሚደረጉ ጥናቶችም ሳይንሳዊ ድጋፍ እየሰጡት ይገኛሉ፡፡ ቡና ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ተፈጥሯዊ ምግብና መጠጦች ከራስ ምታት ክኒኖች በተሻለ ለቀላሉ ራስ ምታትም ሆነ ከበድ ላለው ማይግሬይን ጥሩ የጎንዮሽ ጉዳት የሌላቸው መፍትሄዎች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ምስጋና የመጣላቸው ቡና እና የተለያዩ ፍራፍሬዎች በውስጣቸው የያዟቸው ንጥረ ነገሮች ለዚህ አብቅተዋቸዋል፡፡
watermalon

ቡና
ቡና በሳይንሱ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ከሚካሄድባቸው አነቃቂ መጠጦች አንዱ ነው፡፡ ለአንዳንዶች ቡና ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት ሲሆን ማይግሬይን ላለባቸው አንዳንድ ሰዎች ላይ በብዛት ሲወሰድ ማይግሬይኑን የሚቀሰቅስበት አጋጣሚ አለ፡፡ ሳይንሱ ሁሉንም የቡና ምስጢር ፈትቶ ባይጨርስም እስካሁን ባሉት ትናቶች መሰረት ግን ቡናን ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ መጠኑን በልክ ማድረግ አብሮ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ለከባዱ የራስ ምታት ማይግሬይን የሚታዘዙ ክኒኖች ውስጥ የቡና ዋና ንጥረ ነገር ካፌይን ይገኛል፡፡ ስለሆነም ቡና ለራስ ምታት በመፍትሄነት መቅረቡ አስደናቂ ነገር አይሆንም፡፡ ይሁንና መጠኑ በበዛ ቁጥር ራስ ምታትን ከማስታገስ ይልቅ ጭራሽ ሊቀሰቅሰው ይችላል፡፡ ማህሌት ‹‹ብዙ ጊዜ ይህን ሞክሬ ተሳክቶልኛል፡፡ ቡና መድሃኒቴ ነው›› ትላለች፡፡ ሳይንሱም ለዚህ ድጋፉን እየሰጠ ይገኛል፡፡ እጅግም ወፍራም ያልሆነ አንድ ወይም ሁለት ስኒ ቡና ከሁለት ክኒን የተሻለ ተፈጥሯዊ መድሃኒት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ሃብሃብ
ሃብሃብ ወይም በእንግሊዝኛው ወተርሜለን በውስጡ እጅግ ብዙ ፈሳሽ እና ማዕድናትን የያዘ ከፍራፍሬዎችም በትልቅነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬትና ሐዋሳ መስመር ሲሄዱ በመንገድ ዳር ተሸክመው ሲሸጡት እንመለከታለን፡፡ ሞክረውት እንደሆነ ባላውቅም በጉዞው ወቅት ለሚኖረው ሙቀት እና የውሃ ጥም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጥቅሙም ባሻገር ለራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት መሆኑ በባለሙያዎች ተጠንቶ ተቀምጧል፡፡ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት በቅርቡ ባሰፈረው ጽሑፍ ሃብሃብ ለራስምታት ፍቱን ያስባለው ከፍተኛ የውሃ እና ማዕድናት በተለይም ከፍተኛ የማግኒዚየም ማዕድን መጠኑ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ለራስምታት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ ያለመኖሩ ነው፡፡ ይህ ፍራፍሬ ደግሞ ይህን ችግር በደንብ ይፈታል፡፡ ከራስ ምታት ክኒን ይልቅ በቅርብ ሃብሃብ ከተገኘ በደቂቃዎች ውስጥ ከራስምታቱ እረፍትን ይሰጣል ብለው ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡

ዝንጅብል
ዝንጅብል ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ገና በቅርቡ የተጀመሩ ቢሆንም በውስጡ የደም ቧንቧዎችን መቆጣት እና ህመም የሚቀንሱ መድሃኒቶች ውስጥ ካሉ ኬሚካሎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ተመራማሪዎች ማግኘት ችለዋል፡፡ በተለይ በከባድ የራስ ምታት ወቅት የደም ቧንቧዎችን መቆጣት በማስከተል ራስምታቱ እንዲቀሰቀስ የማድረግ ተግባር ያላቸውን ፕሮስታግላንዲን የሚሰኙ ንጥረ ቅመሞች መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ራስ መታቱን እንደሚያስታግስ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት ይገልጣል፡፡ ራስ ምታቱን ሙሉ በሙሉ ባያቆመው እንኳ ከራስ ምታት ጋር የሚመጡ ደስ የማይሉ እንደ ማቅለሽለሽ አይነት ስሜቶችን በቶሎ ይቀንሳል፡፡ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ኢትዮጵያውያን ያለጥናቶቹ ውጤትም ቀድመው ለሆድ ህመም እና ማቅለሽለሽ ዝንጅብል አኝክበት ሲሉ የኖሩት!

ስፒናች
ትኩስ ስፒናች ጎመን ቅጠል በውስጡ የያዛቸው ቅመሞች ራስ ምታትን በማስታገስ ብቻ ሳይሆን የደም ግፊት መጠንን በመቀነስም በቀደመው ጊዜ ጥቅም እንደነበራቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ በርካሽ ለሚገኝባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ይህ ጥሩ ዜና ይመስላል፡፡ በውጪው ዓለም ስፒናችን አብስሎ ወይም በትኩሱ ከቲማቲም ጋር ከትፎ በመብላት ብቻ ሳይሆን ጨምቆ ከመጠጣትም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ደግሞ ይህ ፍቱን አትክልት ለራስ ምታትም ፈጣን መፍትሄ ይሰጣል ብለዋል፡፡ ቢፈልጉ ጨምቀው ከሻይ ጋር አለዚም ባዶውን ወይም ትኩሱን ቅጠል ሰላጣ እንደሚያዘጋጁት አዘጋጅተው ቢመገቡት ከራስ መታቱ ፋታ እንዲያገኙ እንደሚረዳዎት የተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡

ነገር ግን…
ለራስ ምታት ፍቱን ተብለው በጥናት ስር ያሉ በርካታ ተፈጥሯዊ ምግቦችና ፈሳሾች የሚገኙ ሲሆን በአንፃራዊነት ጥሩ ውጤት ካስገኙት መካከል ጥቂቶቹን አነሳሳን እንጂ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ በዋነኛነት ባለሞያዎች የሚመክሩት ራስ ምታቱን ከማስታገስ ባለፈ ዋናውን የራስ ምታት ምንጭ ፈልጎ መፍትሄ መስጠቱ ላይ ነው፡፡ እንደ ድርቀት፣ ውጥረት፣ ከፍተኛ ድካም መሰል ከስራ እና ማህበራዊ ምክንያቶች መነሻነት የሚመጣውን ራስ ምታት ከክኒን ይልቅ በተፈጥሮ መፍትሄዎች ማስታገስ ቢመከርም ከሰውነት የውስጥ በሽታዎች ምክንያት የሚነሳን ራስ ምታት ግን ምንጩን ካልታከሙት ማስታገስ ይከብዳል፡፡ አልፎ አልፎ ለሚከሰት ራስ ምታት ያነሳሳናቸው አይነት የቤት ውስጥ ቀላል መፍትሄዎች ጥሩ ናቸው፡፡ ተደጋጋሚ ራስ ምታት ግን የባለሞያ እርዳታን ይሻልና ቸል አይበሉት ይላሉ ባለሞያዎቹ፡፡ ራስ ምታት ይደጋግመኛል ስትል ሃሳቧን በመግቢያችን ያጫወተችኝ ማህሌት ከዚህ ምክር ሳትመደብ ትቀራለች ሰላም!

The post Health: ለራስ ምታት ህመም ፍቱን የሆኑ ምግብና የመጠጥ አይነቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የአዲስ አበባ ጉዶች: በማሳጅ ስም የወሲብ ገበያ ደርቷል * ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም ‹ማግኔት› በሚል በውጭ ሚድያዎች መጠራት ጀምራለች (ልዩ ዘገባ)

$
0
0

መነሻ
በቅርቡ ማክቤዝ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ኤች አይ ቪ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ(መታሻ) ቤቶች መስፋፋት በወጣቶችና በሴቶች ላይ የሚያስከትሏቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች በሚል ርዕስ አንድ ጥናት አሰርቶ ነበር፡፡ ወሲብና ወሲባዊ ተግባራት የሚፈፀምባቸውን ማሳጅ ቤቶች በተመለከተ bማህበራዊ ስነልቦና ባለሙያዎቹ አቶ በላይነህ ዘለለውና አቶ ዮሴፍ አህመድ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች ውስጥ ህገ ወጥ የሆኑ ማሳጅ ቤቶች በአሳሳቢ ደረጃ ተስፋፍተዋል፡፡ ማሳጅ ቤቶች ለወሲብ ቱሪዝም መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ethiopia massage
እንደሚታወቀው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶችና የውጭ ሃገር ድርጅት ሰራተኞች በብዛት ይኖራሉ፡፡ ትላልቅ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ጉባኤዎች በተደጋጋሚ ይደረጋሉ፡፡ በነዚህ ጉባኤዎች ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ የባህር ማዶ ሰዎች በአብዛኛው ጊዜ አዳራቸውን የሚያደርጉት በህገወጥ ማሳጅ ቤቶችና በትላልቅ ሆቴሎች ውሰጥ በግዥ ከሚቀርቡላቸው ሴተኛ አዳሪዎች ጋር አንዳንዴም በደላሎች አማካኝነት ከሚቀርቡላቸው የቤት ልጆች ጋር እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህ ሂደት በገንዘብ ተጠቃሚ የሚሆኑ በርካታ ሰዎች አሉ፡ ፡ በወጣት ሴቶች ስነልቦና እና ስነተዋልዶ ጤና እንዲሁም በማህበረሰቡ ግብረገባዊ አስተሳሰብ ላይ የሚነግዱ፣ ኢ – ሞራላዊና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ገንዘብ የሚሰበስቡ ማሳጅ ቤቶች ድርጊት በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላል ጥናቱ፡፡ ይሁንና ችግሩን ለመፍታት የተደረጉ እንቅስቃሴዎች የሉም ወይም አነስተኛ ናቸው፡ ፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ ጥናቱን ጨምቆ በማቅረብ የጉዳዩን አሳሳቢነት በማሳየት የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት ወደተግባራዊ እርምጃ እንዲገቡ ግፊት ማድረግም ነው፡፡

16ኛው “ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የአባላዘር በሽታዎች ጉባኤ በአፍሪካ” (16th International Conference on AIDS and STLs in Africa – ICASA) ከሦስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እንደተስተናገደ ይታወሳል፡፡ከዚያ ቀደም ብሎ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ያስደነገጠና ያወዛገበ አንድ ስብሰባ ሊደረግ ታስቦ ነበር፡፡ “የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን የቅድመ ኮንፈረንስ ማነቃቂያ ስብሰባ” የተባለው ይህ ስብሰባ በተለይ በሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ውግዘት ገጥሞት ነበር፡፡ በማህበራዊ ድረ ገጾችና በተለያዩ የሃገር ውስጥ ጋዜጦችና መጽሔቶች (ቁም ነገር መጽሔትን ጨምሮ) ብዙ ፅሁፎች በጉዳዩ ዙሪያ ወጥተው ነበር፡ ፡ ለግብረ ሰዶማውያን መስፋፋትና የወሲብ ቱሪዝም እየጨመረ እንዲመጣ ከሚያደርጉ አባባሽ ነገሮች አንዱ የህገ ወጥ ማሳጅ ቤቶች መኖር ነው፡፡ እንደ ታይላንድ ያሉ ሃገራት ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ፡፡

የወሲብ ቱሪዝም ‹ማግኔት›

በቅርቡ በወጣ አንድ ዓለም አቀፍ ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም እየተስፋፋባቸው ከመጡ ሃገራት አንዷ መሆኗን ‹‹Ethiopia has become a magnet for sex tourism›› (ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም ማግኔት እየሆነች ነው) በማለት ይገልጻታል፡፡ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባኤዎችንና ስብሰባዎችን ማስተናገዷ እያስገኘላት ከሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ገቢ በተጻራሪ ለማህበራዊ ችግሮች እየዳረጋት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ የውጭ ሃገር ጎብኝዎችና የጉባኤ ተሳታፊዎች ለመጤ ባህሎች እያጋለጧት ነው፡፡ በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የሚዘወተረው ወሲባዊ ንግድ ወደ መኖሪያ ቤቶችም ገብቷል፡፡ በተለይ የእንግዳ ማረፊያ ተብለው የተዘጋጁ አንዳንድ ቤቶች ለህገ ወጥ ማሳጅ ቤቶችና ለወሲብ ንግድ መፈጸሚያነት እየዋሉ ነው፡፡

እንደ ተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ‹‹ የቱሪዝምን ቅርጽ እና መረብ በመጠቀም በማንኛውም የወሲብ ነክ እንቅስቃሴ ላይ ለመሳተፍ የሚደረግ ጉዞ ›› የወሲብ ቱሪዝም ወይም ዘመናዊ የወሲብ ንግድ ነው ሲል ይገልጻል፡፡
በዓለማችን ከቅርብ አሥርት ዓመታት ወዲህ የወሲብ ቱሪዝምን ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖረው በማድረግ ለሃገሪቱ እንዲሁም ለዘርፉ ተዋንያን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሊያመጣ በሚችል መልኩ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህ ሃገራት ውስጥ ጀርመን፣ ብራዚል ፣ሞሮኮ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ እንዲሁም በምርጥ የእግር ኳሰኞቿ የምናውቃት ኔዘርላንድስ ከአጠቃላይ የሃገራቸው ኢኮኖሚ ከ ሁለት እስከ አምስት በመቶ የሚሆነውን ከዚሁ ዘርፍ ይሸፍኑበታል፡፡
ይህ ዘርፍ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በርከት ያሉ አገልግሎት ሰጪዎችን የሚያቅፍ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አየር መንገዶች፣ሆቴሎች የየብስ ትራንስፖርት ተቋማት የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡ ፡
ከዚህ በተጨማሪ እነዚሁ ሃገራት በድርጊቱ ለሚሳተፉት ሴት ዜጎቻቸው የማህበራዊ ዋስትናን እስከ ጡረታ ድረስ በመስጠታቸው ድርጊቱ የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ ዝቅተኛ ቢሆንም ሞራላዊ ተጠያቂነቱ ግን ከፍ ያለ ነው፡፡

በሃገራችን በተለይም በመዲናችን እና በተለያዩ የቱሪስት መናኸሪያ በሆኑ አካባቢዎች ከራቁት ጭፈራ ቤቶች የጀመረው ይህ የዘመናዊ የወሲብ ንግድ (የወሲብ ቱሪዝም) በአሁኑ ሠዓት በርከት ያሉ የወሲብ ንግድ ተቋማትን፣ ሰፊ የድርጊቱ መረብ፣ እሳት የላሱ ደላሎችን እንዲሁም ሰፋ ያለ ካፒታል የሚያንቀሳቅስ እና ወደ ኢንዱስትሪ ደረጃ ሊሸጋገር የደረሰ ተግባር ሆኗል፡፡ በተለይም የሃገራችን የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ እየተጠናከረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ያለውን የወጭ ሃገራት ዜጎችን ፍሰት ተከትሎ ዘርፉ ጠንከር ወደማለት እና የአደባባይ ሚስጥር በሚባለው ደረጃ ላይ ለመድረስ ችሏል፡፡

እነዚህ የወሲብ ንግድ ማዕከላት በዘርፉ ተዋንያን እና ቅርበት ባላቸው ወገኖች ዘንድ ‹‹ፍርድ ቤት ›› በመባል የሚታወቁ ሲሆን የድርጊቱ ተሳታፊ ሴቶች ደግሞ ከፈረንሳይኛ ቃል በተወረሰ ነገር ግን ከድርጊቱ ጋር ምንም ተዛምዶ በሌለው ‹‹ትራባዪ›› በሚል ስያሜ ይታወቃሉ፡፡

እነዚህን ‹‹ፍርድ ቤቶች›› እና ‹‹ትራባዪዎች›› ከውጭ ሃገራት ዜጎች ጋር በማገናኘት ረገድ የአንበሳውን ሚና የሚጫወቱት ደላሎች በተለምዶ ‹‹ጋይድ››የሚባሉ ሲሆን የትራባዪዎች (የወሲብ ንግድ ተሳታፊ ሴቶች) ማደሪያ እና መዋያ ቦታ የወሲብ ንግድ ማዕከላቱ ‹‹ፍርድ ቤቶቹ›› ናቸው፡፡
አንድ ፍርድ ቤት በውስጡ ከ 15-20 ለሚሆኑ ‹‹ትራባዪዎች›› ደንበኞቻቸው እስኪመጡ የሚገለገሉበት የማደሪያ አልጋ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን የሚያሟሉ ሲሆን ለሚጎበኟቸው የውጭ ሃገራት ዜጎችም በውድ ዋጋ የሚሸጡ መጠጦችን ለሽያጭ ያቀርባል፡፡

አንድ የውጭ ሃገር የወሲብ ደምበኛ የመረጣትን ‹‹ትራባዪ›› ከፍርድ ቤቱ ለአንድ አዳር ወይም ውሎ ይዞ ለመውጣት ከአንድ ሺህ እስከ አምስት ሺህ ብር የሚከፍል ሲሆን እንደየ ፍርድቤቱ ህግ ደግሞ ተጨማሪ የመውጫ የኮቴ የመሳሰሉትን ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል ፡፡
ለአንድ አዳር ወይም ውሎ የተስማማች አንድ ‹‹ትራባዪ›› ሊከፈላት ከተስማማችው የብር መጠን ውስጥ ከ50-70 በመቶ የሚሆነው በወሲብ ተቋሙ ባለቤት እና በደላሎች የሚወሰድ ነው፡፡
እነዚህ የወሲብ ንግድ ተቋማት በአብዛኛው በትላልቅ ቪላ ቤቶች የሚገኙ ሲሆን በተለይም ከቦሌ ድልድይ እስከ ደምበል፣ በሃያ ሁለት ፣ሲኤምሲ፣ መስቀል ፍላወር እንዲሁም የቱሪስት እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ተበራክተው ይገኛሉ፡፡

ይህ የወሲብ ቱሪዝም ወይም የወሲብ ንግድ ከወሲብ ንግድ ተቋማቱ ባለፈ መሸታ ቤቶችን፣የጫት ማስቃሚያ ቤቶችን ፣ የእንግዳ ማረፊያዎችን እንዲሁም ሌሎች መሰል ተቋማትን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እንደማስተሳሰሩ መጠን የሚያዘዋውረው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ ቢሆንም ከዚህ ዘርፍ መንግሥትም ሆነ የድርጊቱ ተሳታፊ ሴት እህቶቻችን የሚያገኙት ጥቅም ዘላቂነት ያለው እና ቀጥተኛ ባለመሆኑ በህብረተሰቡ ላይ የሚፈጥረው ማህበራዊ ቀውስ ከፍተኛ ነው፡፡

ምንም እኳን ይህ ተግባር በኢትዮጵያ ህጎች የተከለከለ ቢሆንም ድርጊቱን ከመቆጣጠር አኳያ የመንግሥት ጥረት ዝቅተኛ የሚባል ነው፡፡ለዚህም በከተማችን በርክተው የሚገኙት እነዚህ የወሲብ ንግድ ተቋማት ምስክሮች ናቸው፡፡

በዚሁ በወሲብ ንግድ ላይ በሁለት ጎራ የተከፈሉ አስተያየት ሰጪዎች የሚደመጡ ሲሆን በአንደኛው ወገን ድርጊቱ የሃገሪቱን መልካም ስም እና የማህበረሰቡን ሞራል የሚነካ በመሆኑ የቱንም ያህል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ቢያመጣ ሊወገዝ እና ቁጥጥር ሊደረግበት የሚገባ ተግባር ነው ሲሉ የሚሞግቱ አሉ፡፡ በሌላኛው ጎራ ይህን ተግባር ማስቆም ለሚጠይቀው ቁርጠኝነት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት አሊያም ድርጊቱ ይፋዊ በሆነ መንገድ ተፈቅዶ ከድርጊቱ ተዋንያን ከግብር እና ከሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን በመሰብሰብ የሚገኘውን ገቢ በመጠቀም ድርጊቱ የሚፈጥረውን ማህበራዊ ቀውስ መቀነስ ተገቢ ነው ባዮች ናቸው፡፡

የማሳጅ ታሪካዊ
ዳራ

የማሳጅ ታሪካዊ አመጣጥ በብዙ ሀገሮች የብዙ ሺህ ታሪክ ያስቆጠረ ነው፡፡ በጥንታዊ ጽሑፎች ላይ ተጽፎ እንደሚታየው በምስራቃዊያንና በምዕራባዊያን ስልጣኔ ሰዎችን ለመፈወስና ለማሻል ሰዎችን በመንካት/በማሸት/ እንደሚያደርጉ ታሪካዊ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ አብዛኛውን በአሁኑ ሠዓት የምንጠቀመው የማሳጅ ዘዴዎችና አቀራረቦች አጀማመራቸው ከጥንቱ የማሳጅ ዘዴዎች ነው፡፡በጥንት ጊዜም ቢሆን ማሳጅን የሰዎችን ህመም ለማሻል፣አደጋን ለማሻል(ጉዳቱን ለመቀነስ)፣ሰዎችን ሰውነታችውንና አዕምሮአቸውን ዘና ለማድረግ(ለማዝናናት) እንዲሁም ህመምን ለመከላከልና ለማዳን ሲጠቀሙበት ነበረ፡፡

በምስራቁ ዓለም የማሳጅ ታሪክ እንደሚያሳየው ማሳጅ እንደ መለኮታዊ ተዓምር/ Divinely- created system/ ተደርጎ የሚታይበት ሁኔታ ነበር፡፡በህንድ ሀገር ማሳጅን አይሩቨዳ / Ayurveda/ ብለው ይጠሩት የነበረ ሲሆን፣ይህም ህዝብ ይተገብርበት/ይገለገልበት የነበረው ከ3000 ዓ.ዓ ቀደም ብሎ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎችና ቦታዎች እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ ኢሲያ ሀገራትም ተስፋፋተው እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የማሳጅ ህክምና በጥንታዊት ቻይና የረዥም ዓመት ታሪክ ያለው ነው፡፡ይህም የህክምና አይነት ከ2700 ዓ.ዓ አካባቢ ተግባራዊ ይደረግ እንደነበረ የታሪክ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ጥንታዊ ቻይናዊያን ማሳጅን ለህክምና አገልግሎትና ራስን ለማዝናናት ይጠቀሙበት ነበር፡፡

ወደ አህጉራችን አፍሪካ ስንመጣም ይህ የማሳጅ ህክምና አይነት በተለያዩ ሀገሮች ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በሺ የሚቆጠሩ ዓመታት አስቆጥሯል፡ ፡ለምሳሌ በጥንታዊ ግብጽ የእራሳቸው የሆነ የማሳጅ አይነት ይጠቀሙ እንደነበር በፖፒረስ ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡የተለያዩ ተመራማሪዎች እንደሚገምቱት ሪፈሎኤሶሎጂክ/Reflexology/ የሚባለው ማሳጅ አይነት በግብጽ በ2500 ዓ.ዓ አካባቢ እንደተጀመረ ይገመታል፡፡ይህን የማሳጅ አይነት የተወሰነ የሰውነት ክፍልን ብቻ የማሻል ስራ ላይ ያተኩራል፡፡(በሀገራችን ወጌሻ ጋር እንደምንሄደው)
በተለያዩ ጊዜያት እንደሚታየው ማሳጅ የተለያዩ ጠቀሜታዎች እንዳለው ቢታወቅም ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ እየተነሳ የቆየበት ሁኔታ ስለነበረ አንዳንድ ባለሙያዎች በተለይም ከጥቂት መቶ ዓመታቶች በፊት ጠቀሜታው ወሳኝ እንደሆነ በመረዳት በ1600 ዓ.ም አከባቢ በምዕራባዊያን የህክምና ባለሙያዎች ድጋሚ ጠቀሜታውን በመገንዘብ ለአገልግሎት እንደ ገና ማዋል ተጀመረ፡ ፡ሆኖም ግን እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ማሳጅ ከፍተኛ እውቅና በማግኘት በብዛት ጥቅም ላይ መዋል ጀመረ፡፡

አዲሱ ጥናት

በቅርቡ ማክቤዝ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ኤች አይ ቪ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰራው ጥናት ዋና ዓላማ ‹በሀገራችን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች በተለይም የተለየ ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው መታሻ/Massage parlor/ ማረፊያ ማሳጅ ቤቶች መስፋፋት እያስከተለ ያለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፤የስነተዋልዶ ጤና እና ስነልቦናዊ ተፅዕኖዎች እና ቀውሶች በሚመለከት ለችግሩ መነሻ ፣ አባባሽ ምክንያቶች እና የምክረ ሀሳብ/ የመፍትሄ ሃሳቦችን ማቅረብ እንደሆነ› ይገልፃል፡፡
መጤ ባህልና ልማዳዊ ድርጊቶች በወጣቶችና ሴቶች ላይ የሚያደርሷቸው ተጽዕኖዎች በርካታ
መሆናቸውን የሚጠቅሰው ጥናቱ በአፍሪካ ሀገራትም መጤ ባህል በአምራች ትውልዱ ላይ አሉታዊ ተጽኖ እያሳደረው እንደሆነ እንደ አብነትም ለምሳሌ፡ -በግብጽ ፤በሊቢያ(ከጎረቤት ሀገር)፤በሞሮኮ(ወንደኛ አዳሪነት..)፤በኬፕ ቬርዴ(የወሲብ ቱርዝም)እንዲሁም በናይጄሪያ(በፍተኛ ወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ሴቶችን ወደ ሌሎች ሀገሮች በመላክ የቀዳሚውን ድርሻ ከያዙት ሀገራት ውስጥ እንደሆኑ ያብራራል፡፡

ጥናቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፤ ማለትም ከማሳጅ ማሰልጠኛ ተቋማት፣፤ ከማሳጅ ቤት ተጠቃሚዎች ፤ ከማሳጅ ቤት ሰራተኞች ጋር በርእሱ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ በማድረግ የተሰራ ሲሆን ከዚህ `በተጨማሪም በአሳታፊ የአካል ምልከታ ማሳጅ ቤቶችን በመቃኘት መረጃዎች ተሰብስበዋል ይላል ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አስር ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ክፍለ ከተማዎች ማሳጅ የሚከናወንባቸው ቦሌ187 ፣ጉለሌ 5 ፣የካ 20፣ አዲስ ከተማ 9 ፣አቃቂ ቃሊቲ 0 ፣ቂርቆስ 77 ፣አራዳ 10 ፣ንፋስ ስልክ 30 ፣ልደታ 3፣ ኮልፌ 8 ሲሆኑ በጠቅላላው 349 (ሶስት መቶ አርባ ዘጠኝ ) ማሳጅ ቤቶች ከአዲስ አበባ ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ፈቃድ አግኝተው በመስራት ላይ እንደሆኑ ጥናቱ ያመለክታል ፡፡ አብዛኛዎቹ የሚገኙትም ቦሌ አካካቢ በመሆኑ ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ ከሚገኙ 187 ማሳጅ ቤቶች ውስጥ 35 የሚሆኑ ማሳጅ ቤቶችን በመምረጥ ጥናቱ ተካሂዷል፡፡ የማሳጅ አገልግሎቱ የሚሰጥባቸውም ትላልቅ ህንፃዎች፣ ሰፋ ያለ ግቢ ያላቸው ቤቶች፣ አፓርታማዎችና በከተማዋ ዋና ዋና አካባቢዎች በሚገኙ ፎቆች ላይ የሚገኙ ቤቶች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ከእነዚህ ማሳጅ ቤቶች መካከል አብዛኞቹ ወደ ህገወጥ ተግባራት እየገቡ ሲሆን ጥናቱ እንደሚለው ለህገወጥ ማሳጅ ቤቶቹ መስፋፋት ተከታዮቹ ምክንያቶች በዋናነት ይነሳሉ፡-

– ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ለባለቤቱና ወሲባዊ ንግድ ለሚትፈጽሙ ሴቶች ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚያስገኝላቸው፣
– ተገልጋዮቹ የተሻለ ነጻነት እንዲሰማቸው ስለሚያደርግ፣
– ወሲባዊ ንግድ የሚፈጽሙ ሴቶች በሆቴልና በጎዳና ላይ ከሚያደርጉት ወሲባዊ ንግድ የማሳጅ ቤቱ በተሻለ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ስለሚያደርግላቸው፣
– ደላሎች ከዚህ ስራ የተሻለ ገንዘብ እያገኙበት ስለሆነ ስራውን እንዲስፋፋ አድርጎታል፣
– ወሲባዊ ማሳጅ ቤቶች ተጠቃሚ የማህበረሰብ ክፍል እየጨመረ መምጣቱና ሌሎችም ምክንያቶች እንዳሉት ጥናቱ ደርሶበታል፡፡

ከገቢ አንፃርም በእነዚህ ማሳጅ ቤቶች ውስጥ መስራት ስለሚያስገኘው ገቢ በጥናቱ ውስጥ የተካተተ አንድ ሰራተኛ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቶ እናገኛለን፡፡ ‹በአሁኑ ሰዓት በመዲናችን ስትዟዟር በተለይም ደግሞ ቦሌ ክ/ከተማ ዞር ዞር እያልክ ብታይ ልክ እንደ ካፌ በየአካባቢው ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ተከፍተው ታገኛለህ፡፡ለዚህ ስራ በዋናነት ምክንያት የሚሆነው ደግሞ ለተጠቃሚው የሚሰጠው ተጨማሪ አገልግሎት (ወሲብ) ነው፡፡ለምሳሌ እኔ እሰራበት የነበረው ቤት ወደ ስድስት ማሳጅ የሚደረግባቸው ክፍሎች ነበሩት፡፡ከእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ከምንሰራው ስድስት ወጣቶች ውስጥ እኔ ብቻ ነኝ ወንድ አምስቱ ሴቶች ናቸው፡፡እኛ ሁሌም ቀን ቀን ነው የምንሰራው፡፡ ማታ ፈረቃ የሚሰሩር በሙሉ ሴቶች ናቸው፡፡ እያንዳንዳችን በቀን ወደ 25 የሚጠጉ ደንበኞችን እናስተናግዳለን፡፡የማታ ፈረቃ ሰራተኞች ደግሞ ከ25 በላይ የሚሆን ሰው ያስተናግዳሉ፡፡በቀላሉ 50 ሰዎች ቢያስተናግዱ ለአንድ ሰው ዝቅተኛው ከ500 ብር እስከ 1200 ብር ያስከፍላሉ፡፡ በትንሹ 500 ብር ቢያስከፍሉ በአንድ ቀን 25,000 ብር ያገኛሉ ማለት ነው፤በወር ደግሞ 750,000 ብር ያገኛሉ፡፡ለሰራተኞችና ለአንዳንድ ወጪዎች 250,000 ብር ቢያወጡ ወደ 500,000 ብር ያገኛሉ፡፡በዚህም ምክንያት ማሳጅ ቤቶች እጅግ በፈጣን ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛሉ ፡፡›

እንደዚህ ያለው ስራ በአብዛኛው ሀገር እጅግ በጣም የሚያዋጣ የስራ ዘርፍ ነው፡፡ እንደ ታይላንድ ያሉ ሀገሮች በወሲብ ንግድ በዓመት ውስጥ ወደ 4.3 ቢሊየን ዶላር ያገኛሉ ከወሲብ ንግድ ብቻ፡ ፡ ይህም ብዙ ሰዎች በእንደዚህ አይነት ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም በአሜሪካ በተደረገ አንድ ጥናት መሰረት ወሲባዊ ንግድ ወደሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ስራ እንዲሰማሩ ምክንያት ከሆናቸው አንዱ ህጋዊ ማሳጅ ሲሰሩ የሚያገኙት ገንዘብ ዝቅተኛና ስራው አድካሚ ስለሆነ ወሲባዊ ንግድ ላይ ቢሰማሩ ግን በቀላሉ በዛ ያለ ገንዘብ ስለሚያገኙ ወደዚህ ስራ ይገባሉ ይላል ጥናቱ፡፡

የችግሩ ስፋት
በማህበራዊ ስነልቦና ባለሙያዎቹ አቶ በላይነህ ዘለለውና አቶ ዮሴፍ አህመድ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች በሴቶችና በወጣቶች ላይ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ስነ-ልቦናዊ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮችን እንደሚያስከትሉ ያሳያል፡፡ በአንድ ማሳጅ ቤት ትሰራ የነበረች ወጣት ከስራው ጋር በተያያዘ ስለሚያጋጥማት ችግር ምንም አይነት ዋስትና እንደሌላት እንዲህ ስትል ታስረዳለች‹አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣው ሰው በጣም የተለያየ ባህሪ ያለው ሰው ነው፡፡በዚህ ምክንያት ሁሉም የተለያየ ፍላጎት ስላለው፤አንዳንዱ ሰው ኮንዶም መጠቀም አይፈልግም፣ሌላው ደግሞ በፊንጢጣ የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈልጎ የሚመጣ አለ፡፡ ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ ግጭት የሚፈጠረው፡ ፡ በተለይም ማታ የሚመጡት ወንዶች አብዛኛዎቹ መጠጥ ጠጥተው ስለሚመጡ የጠየቁትን ወሲብ አይነት እንቢ ካልኳቸው በጉልበት ሊፈጽሙብኝ ይሞክራሉ፤ አንዳንድ ከውጭ የመጡ ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራ) ወሲባዊ ፍላጎታቸው የሚረካው እኔን በማሰቃየት፣በመምታት፣በመንከስ ስለሆነ የተለያየ ጊዜ አደጋ ደርሶብኝ ያውቃል፡፡ ግን ይህንን ችግር ለማን ትናገረዋለህ ለባለቤቱ ብትነግረው ቢዝነሱ እንዳይበላሽበት ስለሚፈልግ ለፖሊስ እንድንናገር አይፈልግም እንዲሁም ደንበኞችን ላለማጣት ሲል ምንም እርምጃ አይወስድም፡፡እኔ ተጎድቼ ብቻ ነው የምቀረው ብናገር ሊያባረኝ ስለምችል ዝም ነው የምለው፡፡ ›

እነዚህ ሴቶች ምንም አይነት ጥቃት ቢደርስባቸው ለህግ አስከባሪ አካላት ሄደው አይናገሩም፤ ምክንያቱም የሚሰሩት ስራ በማህበረሰብ የተወገዘና እራሳቸው እራሱ የማያምኑበት ስለሆነ ጉዳት ደረሰብኝ ብለው ለፖሊስ ሪፖርት አያደርጉም፡ ፡ይህ ደግሞ በእነሱ ላይ የሚደርሰውን የሀይል ጥቃት መጠን ለማወቅ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡የመፍትሄ እርምጃ እንዳይወሰድ ደብቆ ያስቀረዋል ከዚህም አልፎ በሴ ቶ ቹ ላይ የሚደርሰውን አካላዊና ስነ- ልቦናዊ ጉዳት ተገንዝቦ ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ያስተጓጉለዋል› ይላል፡፡

ይህ የስነ-ልቦና ችግር በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀይማኖታዊና ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ባለበት እነዚህ ወጣቶችና ሴቶች ከፍተኛ ለሆነ ለስነ-ልቦና ችግር ይጋለጣሉ፡፡በዚህም ምክንያት ወደ ጫትና ሺሻ ቤቶች በመሄድ ሱስ አስያዥ ዕፅና አልኮል በመጠቀም ችግራቸውን ለመርሳት ይሞክራሉ፡፡
የመፍትሔ
እርምጃዎች

ጥናቱ የተለያዩ የመፍትሔ ርምጃዎችን በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ለማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ መፍጠር፣ ባለድርሻ አካላት በጋራ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው፣ የተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ለተከታዮቻቸው ግንዛቤ መፍጠር እንዳለባቸው፣ ባለሀብቱ ኢንቨስትመንቱን ሀገር በሚጠቅም ነገር ላይ እንዲያውለው ተከታታይነት ያለው ትምህርት መሰጠት እንዳለበት፣ህጋዊ ማሳጅ ቤቶችን ማበረታታና ሌሎችም የመፍትሄ ሀሳቦች ተጨምረዋል፡፡ ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው በመስራት እየተፈጠሩ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የጋራ እቅድ በማውጣት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፤ ስነ-ልቦናዊ የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ከወሲባዊ ንግድ ከሚካሄድባቸው ማሳጅ ቤቶች ጋር ያላቸው ትስስር ጠንካራና ቀጥተኛ መሆኑንና እነዚህ ችግሮች አምራች የሆኑትን ትውልዶች ለሀገራቸው ማበርከት የሚጠበቅባቸውን እንዳያበረክቱ እያደረጋቸው እንደሆነ ጥናቱ አሳይቶል፡፡ በስተመጨረሻም በመጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች አሉታዊ ተፅዕኖ ምክንያት ላልተገቡ ባህሪያት እየተጋለጡ ያለውን ትውልድ ለመታደግ የተለያዩ እርምጃዎችን መወሰድ እንዳለበት ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

የተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ሰለወሲባዊ ንግድ አስነዋሪነትና መጥፎ ገጽታዎች ለተከታዮቻቸው በማስተማር ወጣቶችና ሴቶች ከእንዲዚህ አይነት ተግባር እንዲቆጠብ ትምህርት ቢሰጡ፣ ባለሀብቱ ማህበረሰብን የሚጎዱ ተግባራት ላይ ኢንቨስት እንዳያደርግና ሴቶችንና ወጣቶችን ዘለቀታዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ግንዛቤ መፍጠር ስራዎችን ማከናወን ይኖርበታል:: ለማሳጅ ቤት ባለቤትቶች ህጋዊ ሆነው ለህብረተሰብ ተገቢውን ማሳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ በየጊዜ ትምህራታዊ ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል :: በህጋዊነት እና የማሰጅን ስነምግባር ጠብቀው የሚሰሩ ማሳጅ ቤቶችን የተለየ ደጋፍ እና እረዳታ በደረግላቸው በቀላሉ ከገበያው የማይወጡ ይሆናሉ፡፡ ትምህርት ቤቶች አካባቢ የተከፈቱ እንዲሁም መኖሪያ አካባቢ የተከፈቱ የወሲብ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች በቶሎ ካካባቢው ቢነሱ እና በቦታው ለሌሎች የማህበረሰብን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የማያውክ ተግባረት የሚፈፀምባቸው በሆኑ ሀገርም ህብረተሰብንም የሚጠቅም ይሆናል :: ቤተሰብና ትምህርት ቤት በጋራበመጣመርየልጆቻቸውንናየተማሪዎቻቸውን ውሎ በቅርብ ሆነው መከታተል አለባቸው፡፡ በተለያዩ ጊዜ የልጆቹን ሁኔታ ለመገምገም ወላጅና ትምህርት ቤት በጋራ በመዋያየት የሚታዩ ችግሮችን
በእንጭጩ ለመቅጨት ይረዳቸዋል፡:

ይህ ዘገባ ቁምነገር መጽሄት ላይ ታትሞ የወጣ ነው::

The post የአዲስ አበባ ጉዶች: በማሳጅ ስም የወሲብ ገበያ ደርቷል * ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም ‹ማግኔት› በሚል በውጭ ሚድያዎች መጠራት ጀምራለች (ልዩ ዘገባ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Health: የስኳር ህሙማን ህክምና

$
0
0

Diabetes
ዋና ዋና የህክምና አይነቶች
1. ተመጣጣኝ የሰውነት ክብደትን ለመያዝ መስራት
2. ለስኳር ህመምተኛ ተስማሚ የሆነ አመጋገብን መከተል
3. መደበኛ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ ልምምድ
4. እንደ አስፈላጊነቱም የስኳር በሽታ መድሃኒቶችን መጠቀም

ማስታወሻ

አይነት 1 ህሙማን በኢንሱሊን መታከም አለባቸው፡፡ ምናልባት እርስዎ አይነት 2 የስኳር በሽተኛ ካልሆኑ ኢንሱሊን መውሰድ ላያስፈልግዎት ይችላል፡፡ ኢንሱሊን በእንክብል (ታብሌት) መልኩ ሊወሰድ አይችልም፡፡ ምክንያቱም መድሃኒቱን በምንውጥበት ጊዜ ስራውን ከመጀመሩ በፊት ሆዳችን (ጨጓራ) ውስጥ በዳይጀስቲቭ ሲስተም ተፈጭቶ ይጠፋል፡፡ ስለዚህ መድሃኒቱን ለመጠቀም ያለው ብቸኛው አማራጭ በመርፌ ወይንም በደም ስር መውጋት ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢንሱሊንን በኢንጄክሽን ለመስጠት የሚያስችሉ አዳዲስ መፍትሄዎች ተዘይደዋል፡፡ ከእነዚህ አንዱም ኢንሱሊን ፓምፕ የተባለ አሰጣጥ ነው፡፡

ተመጣጣኝ ክብደት
ተመጣጣኝ የሰውነት ክብደትን ለማረጋገጥ የሚከተለውን ፎርሙላ መጠቀም ይቻላል፡፡
ለሴቶች
ከቁመት 1.5 ክብደት 45.50 ይጀምሩ፡፡ ክብደትና ቁመትዎ ከዚህ በላይ ከሆነ በ5 ኢንች ከፍታ 2.2 ኪሎ ግራም ይጀምሩ፡፡ ቁመትዎ ከ1 ሜትር ተኩል በታች ከሆነ ከከብደትዎ 2.2 ኪ.ግ ይቀንሱ፡፡
ለወንዶች
ከቁመት 1.5 ክብደት 50 ኪ.ግ ይጀምሩ፡፡ ቁመትዎ ከዚህ በላይ ከሆነ በእያንዳንዱ 1 ኢንች ርዝመትዎ ላይ 3 ኪሎ ግራም ይጨምሩ፡፡ ቁመትዎ ከአንድ ሜትር ተኩል በታች ከሆነ ከክብደትዎ 3 ኪ.ግ ይቀንሱ፡፡

የስኳር በሽታ ህሙማን አመጋገብ

አመጋገብ ለስኳር በሽተኞች እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተቀመጠው የአመጋገብ ጥንቃቄ በአያሌ ጥናቶች የተፈተነ ነው፡፡

የአይነት 1 ስኳር በሽተኞች በየዕለቱ 35 ካሎሪ መጠን ያለው ምግብ በእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ክብደታቸው ብዜት መመገብ አለባቸው፡፡ ምሳሌ 50 ኪሎ ግራም የሰውነት ክብደት ሲባዛ በ35፣ 1750 ካሎሪ ይሆናል፡፡
የአይነት 2 ስኳር በሽተኞች ክብደታቸውን ለመቀነስ በየዕለቱ ከ1500 እስከ 1800 ካሎሪ መጠን ያለው ምግብ ሊመገቡ ይገባል፡፡ ከዚህም ሌላ ክብደት የመቀነስ ስኬታቸው የሚመሰረተው በዕድሜ፣ በፆታ፣ በአካላዊ እንቅስቃሴያቸውና በያዙት ወቅታዊ ክብደታቸውም ላይ ነው፡፡

ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ጡንቻዎች ስላሏቸው የአካል ብቃታቸውን ለማረጋገጥ ከፍተኛ የካሎሪ መጠን መመገብ ያሻቸዋል፡፡ ከፍተኛ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ የሰውነት ጡንቻዎች በየሰዓቱ ከፍተኛ የካሎሪ መጠን ሲያቃጥሉ አነስተኛ አካላዊ ንቅናቄ የሚያደርጉ ሰዎች የሚያቃጥሉት የካሎሪ መጠን ግን አነስተኛ ነው፡፡
በአጠቃላይ በየዕለቱ የምንመገበው ምግብ 50 በመቶ ያህሉ ካርቦ ሃይድሬት (ኃይል ሰጭ) ሊሆን ይገባዋል፡፡ (ተቀባይነት ያገኘው መጠን ከ40-60 በመቶ ነው) ነገር ግን ይህ የካርቦሃድሬት መጠን ያካተተው አመጋገብ በዛ ያለ ክብደት ያላቸው የስኳር በሽተኞች ላይ በደማቸው ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን እንዳያበዛው ወይም ከፍ እንዳያደርገው ከተፈለገ የአመጋገብ ዘይቤያቸውን አነስተኛ ፋት ወይም ካርቦሃይድሬት ባላቸው ምግቦች መለወጥ ያስፈልጋል፡፡

ስለ ምግብ አይነቶች መገንዘብ

1. ሶስት አይነት የምግብ ምድቦች አሉ፡፡ ካርቦሃድሬት፣ ፕሮን፣ ፋት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የግሉኮስ መጠን ከፍ የሚያደርገው ካርቦሃድሬት ስለሆነ ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡
2. ከምንመገበው ካርቦሃድሬት ውስጥ አብዛኛውን የያዙት የምግብ አይነቶች በሶስት ሲመደቡ እነርሱም ስታርች ስኳርነት ወይንም ጣፋጭነት ያላቸው ፍራፍሬዎች እና ወተት ናቸው፡፡

3. የቅጠላ ቅጠል ምግቦች ጥቂት ካርቦሃድሬት ሲኖራቸው ስጋና ቅባት ወይንም በስብ ምድብ ውስጥ ያሉ ምግቦች ግን የካርቦሃይድሬት ይዘታቸው በጣም አናሳ ነው፡፡

የሚመገቡት ምግብ በደምዎ ውስጥ የሚገኘውን የግሉኮስ መጠን ከመቆጣጠር ጋር በቅርብ የተገናኘ ወይንም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የካርቦሃይድሬት መጠን ያላቸውን ምግቦች የሚመገቡ ከሆነ በደምዎ ውስጥ የሚገኘውን የግሉኮስ መጠን ስለሚያበዛው ለስኳር በሽታ ይጋለጣሉ ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ከሚመገቧቸው ሁሉም ምግቦች ውስጥ የሚወስዱት ካሎሪ በደምዎ ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ያዛባዋል (ያበዛዋል)፡፡ ስለዚህ የስኳር በሽተኞች በየዕለቱ የሚመገቧቸውን የካርቦሃድሬት መጠን በጥንቃቄ መለካት እና መቆጣጠር እንዲሁም የአመጋገብ ጊዜውን ማራራቅ ግዴታችን ነው፡፡ ከዚህም በላይ በየዕለቱ የሚመገቡት ካርቦሃድሬት የደምዎን የስኳር መጠን ምን ያህል ከፍ እንዳደረገው መለካትና መቆጣጠር ያሻል፡፡

ካርቦሃድሬቶችን ከየት ያገኛሉ?

በታሸጉ ምግቦች ላይ የሚታተመው የኒውትሬሽን መግለጫ ስለ ምግቡ የካርቦሃድሬት መጠን ጥሩ መረጃ ይሰጣል፡፡ ነገር ግን ማወቅ የሚገባዎት ሁሉም ምግቦች የኒውትሬሽ መለያ የላቸውም፡፡ ለምሳሌ ሬስቶራንት የሚመገቧቸው ምግቦች፣ የፋስት ፉድ ምርቶች እና ሌሎችም የምግብ አቅርቦቶች ተገቢውን የካርቦሃይድሬት መረጃ አይሰጡዎትም፡፡ ስለዚህ እራስዎ የሚመገቡትን የካርቦሃድሬት መጠን መለካት ይኖርብዎታል፡፡

The post Health: የስኳር ህሙማን ህክምና appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“እከ ደከ ማን ችሎት በብልጠቱም ሆነ በጉልበቱ ከወንድ በላይ አበጀ”ይናገራል

$
0
0

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዩን አካባቢ አንቀጸ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡ በልጅነቱ ከገጠር በእንግድነት ወደ ቤታቸው የሚመጡ ሰዎችን ያነጋገር ዘይቤ ለማስመሰል በመጣር ለቤተሰብና ለት/ቤት ጓደኞቹ ሲያሳይ ጎበዝ በርታ የሚል አስተያየት በማግኘቱ ወደ ኪነ ጥበቡ እንዲሳብ ምክንያት እንደሆነው ይገልፃል፡፡ የዚህ እትም የመሿለኪያ አምድ እንግዳችን ሁለገብ አርቲስት የሆነው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅ እና ተዋናይ ንብረት ገላው ነው፡፡
nibret gelaw
በፈረንሳይ ኪነት ውስጥ የገጠሩን የሀገራችንን የቋንቋ ዘዬ ሲሰራ ያየው አንድ ሰው ከአብረሃም አስመላሽ ጋር እንዲገናኝ ያደርገውና ኢትዩጲያ ሬዲዩ ገብቶ ለመስራት እድሉን ይከፍትለታል፡፡ ከዚህ በኋላ በበርካታ በቴሌቭዥንና ሬድዮና የማስታወቂያ ስራዎች ላይ በድርሰት፣ አዘጋጅነትና በትወና ሰርቷል፡፡ ለአብነትም ሬድዮ ፋና ላይ በራሱ የቴአትር ፕሮሞሽን ስር በሚያቀርበው ‹ብሩህ ተስፋ› በተሰኘ አካል ጉዳተኞች ላይ በሚያተኩር ፕሮግራም ላይ ‹ጅረት› የተሰኘ ሃምሳ ሁለት ተከታታይ ክፍል ያለው ድራማ ደራሲ፣አዘጋጅ፣ተዋናይ በመሆን ፣ፖፕሌሽን ሚዲያ ሲያስተላልፈው በነበርው ‹መንታ መንገድ› የሬድዮ ድራማ ላይ በትወና፣ ኢትዮጲያ ሬድዎ የቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ከአብረሀም አስመላሽ ጋር ለረጅም ዓመት ጭውውት በማቅረብና በለያዩ የሲኒማ ፊልሞችና የመድረክ ቲያትሮች ላይ ሰርቷል፡፡

ንብረት ገላው በተለይም በህዝብ ዘንድ በደንብ ያስተዋወቀውና ተወዳጅ ያደረገው በአሁኑ ወቅት ማክሰኞ ማታ በኢትዮጲያ ቴሌቨዥን በሚቀርበው ‹ቤቶች› የቤተሰብ ኮሜዲ ድራማ ላይ በሚጫወተው ‹እከ› የተሰኘ ገፀ ባህሪ ነው፡፡ መጽሔታቸንም ‹ከእከ ደከ ማን ችሎት በብልጠቱም ሆነ በጉልበቱ ከወንድ በላይ አበጀ› ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡

ቁም ነገር፡- አንድ ሰው ምች መታኝ ቢልህ ምን ትመክረዋለህ?
ንብረት፡- ምስክር ነበር? ብዬ እጠይቀዋለሁ፡፡ ለመክሰስ! /…ሳቅ/፤ ወይም ከቻልከው ሂድና ግጠመው ነው የምለው ፤እና እኔ ሄጄ ልጣላለት ኖሯል!

ቁም ነገር፡- በሀገራችን የቤት ሰራተኞችና የጥበቃ ሠራተኞች የሚገባቸውን ያህል ቦታ ተሰጥቷቸዋል ብለህ ታምናለህ ?
ንብረት፡- በፍጹም! እኔ እንደውም አንዳንድ ጊዜ አረብ ሀገር ከፎቅ ላይ ተጣሉ ምናምን እያልን ስናማርር አንድ ቀን ግን ለምን ራሳችንን ዞር ብለን አናይም እላለሁ፡፡ እዚህም አገር ላይ እንኳ በገዛ ወገኖቻቸው ሰራተኛቸው ላይ ምግብ ቆልፈው የሚሄዱ፣የሚደበድቡና እንደውም ሰራተኛ ሊቀጥሩ ሲሉ ትማራለች ከተባሉ የማይፈልጉ ሞልተዋል፡፡ በጣም የሞላና የተረፋቸው ውሻቸውን በቂቤ እያሻሹ በጣም በሚያሳፍር ሁኔታ ለዘበኛቸው ከውሻ ያነሰ ምግብ የሚሰጡ አሉ፡ ፡ በዛው ልክ ደግሞ እጅግ በጣም ጥሩ ሰዎች እንደውም ለቤተሰባቸው እስከ መዳር የደረሱ ጥሩ ሰዎችም ገጥመውኛል፡፡ አሁን እኔ የምናገረው እንደ ሙያዊ አስተያየት አይወሰድብኝና ቤቶች ላይ የምናየው ግንኙነት ትንሽ ለቀቅ ይላል፡፡ ይህ ደግሞ የሆነው የሚሰራው የኮሜዲ ስራ ስለሆነ በታሪኩ ውስጥ የሰራተኞቹ ከቤተሰቡ ጋር ያላቸው ግኑኙነት እንደዚህመሆኑ ወሳኝ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ እንጂ እንደዛ መሆን አለበት ማለት አይደለም፡፡

ቁም ነገር፡- ገበጣ ፣ዳማ ፣ካርታ ልዩነታቸው ምንድ ነው ?
ንብረት፡- ምን አይነት የሚገርም ጥያቄ ነው የምጠይቂኝ? ገበጣና ዳማ የኢትዩጵያ ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡ በቅርቡ እንደውም አንድ ጥናት ላይ ተሳትፌ ነበር ፤‹የባህል ስፖርቶቻችን ለምን ቀሩ?› የሚባል እና ዳማም ኢትዮጵያ ውስጥ ጥንት ነገሥታቶች ይጫወቱት ነበር የሚልነገር አለ፤ ስለ ካርታ ግን አላውቅም፤ የሚመስለኝ የፈረንጆቹ ጨዋታ ነው ፡፡ እኔ እንደውም ካርታ ሲነሣ ቁማር ቀመስነቱ ነው ትዝ የሚለኝ (ይቅርታ ይደረግልኝና) /…..ሳቅ/፤ልዩነታቸው ካርታ በወረቀት ነው፡፡ ገበጣ በድንጋይ ነው በጠጠር፤ዳማም ጠጠር አለው፡፡

ቁም ነገር፡- ከቤቶች ድራማ ጋር በተያያዘ የገጠመህ ነገር አለ?
ንብረት፡- ምን የማይገጥመኝ ነገር አለ ?ብዙ ነው፡፡ ድንገት ስጠየቅ አይመጣልኝም እንጂ፤አሁን እኔ ቤቶች ድራማ ላይ ልክ በቀረፃ ወቅት ልብሱን አንዴ ከለበስኩ በኋላ እራሱን እከን የዘሩ ሞላ ዘበኛ ነኝ፤ ማንም ይምጣ ማንም
ትዕግስት ታደለ
በዚያ ገፀ ባህሪ ውስጥ ሁኜ ነው የማዋራው፡፡ እና አንዳንዴ በቀረፃ ወቅት ሐያት አካባቢ ነው የምንቀረጽበት ቤት፤እየሰራን እንዳለ ቁራሌው የሚሉ ይመጣሉ፣ ልዋጭ የሚል ይመጣሉ፤ የዛኔ ድምጹ ይረብሸናል፤ እኔ እረፉ ልል እወጣለሁ፤‹እባካችሁ ሥራ ይዘን ነው ዝም በሉ› ስላቸው ‹ባክህ አንተም ዘበኛ ነህ እኛም ቁራሌው› ይሉኛል፡፡ እንዲሁም እከን ሲያዩ በጣም የሚገረሙ ሰዎች አሉ፤በቅርቡ መኪናዬን አስነስቼ ስሄድ አንዲት ልጅ የእውነት በመገረም ዘበኛው እኮ ነው፡፡ በሚል ስትገረም አየኋት፤ ልክ ዘበኛ ሁኜ የባለቤቱን መኪና ሰርቄ እንደምነዳ አድርጋ ነው የቀወጠችው፤ እንደዚህ አይነት ነገሮች በተደጋጋሚ ይገጥሙኛል፡፡

ቁም ነገር፡- ሰዎች ወሽመጤን በጠሰው፤ ወሽመጤ ተበጠሰ ሲሉ እንሰማቸዋለን ፤ለመሆኑ ወሽመጥ የትኛው የአካላችን ክፍል ነው?
ንብረት፡- ብዙ ቦታ ወሽመጥ እንዳለ ላስብና፤ አንደኛው ብብት ላይ አለ ወሽመጥ /….ሳቅ/፤ ሁለተኛው ደግሞ እግርና እግር መካከል ውስጥ ወሽመጥ አለ፡፡
ቁም ነገር፡- በምድር ላይ ስትመለከተው እጅግ የሚያስደንቅህ ነገር ምንድ ነው?
ንብረት፡- ሰው ነው የሚያስደንቀኝ ነገር፡፡ እግዚአብሔር ሰውን እንዴት አድርጎ ፈጠረው የሚለው ነገር ያስደንቀኛል፡፡ በነገራችን ላይ እኔ ይሄ ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው የሚል ሳይንስ አይመቸኝም ፡፡ እንደዚህ አይነት ሳይንስን ሲያንስ ነው የምለው፤እግዚአብሔር ሰውን ምን ያህል ቢወደው ነው እንዲህ አድርጎ የፈጠረው እላለሁ፡፡ ከፈጠረው በኋላ ጥበብን ጥግ ድረስ ሰጠውና፤ አሁን አውሮፕላን ላይ ሆነን ስናይ አቤት የሰው ልጅ ስራ እንላለን፡፡ ግን ሰው መፍጠርና አንዲት ጣታችን እንኳን ተቆርጣ መልሶ መፍጠር አልቻልንም፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው መፍጠር ያስደንቀኛል፡፡

ቁም ነገር፡- እከን ብዙ ህፃናት ይወዱታል፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስልሀል?
ንብረት፡- አዎ እኔ ብዙ ጊዜ ሕፃናት ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ አውቃለሁ፤ ልክ ስገባ ይጮኻሉ፤ ይህንን እንግዲህ እኔ ክብር ለእግዚያአብሔር ብዬ ማለፍ ነው የምችለው፡፡ ምክንያቱም የእከን ገፀ ባህሪ አይተሽው እንደሆን የሚጮህ ነገር ነው፣ ጀው ጃዋ ዓይነት ነገር ነው፡፡ ሕፃናት ደግሞ እንደዚህ አይነት ሰውን የመፍራት ነገር ነው ብዙ ጊዜ የሚታይባቸው፤ የግርቢጥ ብዬ ልገልጸው እችላለሁ በአማርኛ እከን ወደውታል፡፡ እውነቱን ለመናገር ልጆች ላይ በትወና ግብት ማለት ይከብዳል፤እንደ አዋቂዎቹ አይደለም ነገሩ፤ማለት የምችለው ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ፕሮዳክሽኑን የጀመረው ጥላሁን ጉግሳ ወዳጄ በጣም ጀግና ሰው ነው ለኔ፤ወቅታዊ ኮሜዲ ተከታታይ ድራማን በድፍረት የጀመረ ሰው ነው፡፡ ከዛ ውጭ አዘጋጁ ይታገሱ ገስጥ ተጫኔና ሌሎችም ከፕሮዳክሽን ጀርባ ያሉት በሙሉ የነሱ አስተዋጽኦ እከን እንዲወደድ አድርጎታል፡፡

ቁም ነገር፡- ህይወትህን የምትመራው በዕቅድ ነው? ወይስ እንደ አመጣጡ?
ንብረት፡- እኔ ምን አስዋሸኝ? እንዳመጣጡ ነው የምኖረው /….ሳቅ/፤ የምን ዕቅድ ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ከሞት በኋላ ቀጣዩ ምዕራፍ ምን ይመስልሀል?
ንብረት፡- እኔ ሰማያዊቷን እየሩሳሌምን እወርሳለሁ፡ ፡ ምክንያቱም እየሱስ ሞቶልኛል፡፡
ቁም ነገር፡- ከሰማኸው ውሸት ውስጥ በጣም ያስገረመህ ውሸት አለ ?
ንብረት፡- እንዴ ብዙ ውሸት፤እኔም እራሴ ስኖር ውሸታም ነኝ፤ዓለም እንዳለች በውሸት የተሞላች ነች፤ ስለዚህ የትኛውን ውሸት ለይቼ ልንገርሽ?
ቁም ነገር፡- አይዶል ላይ ተወዳደር ብትባል በምን ብትወዳደር ይሳካልኛል ትላለህ ?
ንብረት፡- በድብድብ! /….ሳቅ/ የሚችለኝ ካለ ይምጣ ፡፡

ቁም ነገር፡- የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናድርግ ሲባል ምንድን ነው ወደ አዕምሮህ የሚመጣው?
ንብረት፡- ማድረግ ይቻላል፤ በጣም ቀላል ነው፡፡ እኔ ክርስቲያን ስለሆንኩ እግዚያአብሔር ሟችን በገነት አኑርልኝ እላለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ምን ይመጣብኛል መሰለሽ? ሰው አይደለሁ! ተንኮልም ወደ አዕምሮዬ ይመጣብኛል፡፡ በአካባቢሽ ያሉ ሰዎች ሀሳብሽን ሊሰርቁት ይችላሉ፤አንዳንዱ የሆነ ተመስጦ በራሱ ሙድ ውስጥ የሚገባ ሰው አለ፣ሀሜት የሚጀምርም ሰው አለ፤እነዚህ እነዚህ ነገሮች ሳይ ሐሳቤ ሊሰረቅ ይችላል፤ከራሴ ህሊና ጋር ስሆን ግን የሞቱትን ነፍስ ይማር እላለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- የዝና ጥቅሙ ይታወቃል፤ ጉዳቱስ ምንድን ነው?
ንብረት፡- እንደፈለጉ አለመሆን ፤ሰው በመሆን የምትፈጽሚያቸው ስህተቶች አሉ፤ አንዳንድ ጊዜ፤ያን ማድረግ አይቻልም፡፡ እኔ ግልፍተኛ ነበርኩኝ፤ያንን አሁን እህ….. ብዬ እተወዋለሁ፤ እንደምንም ችዬ እና ተወጣጥሬ፤ ይቺ በጣም ከባድ ነች፡፡ አንድ ጊዜ ከመገናኛ ጀምሮ አንድ መኪና መንገድ እየዘጋብኝ እየዘጋብኝ ይመጣል፤እኔም ችዬ ዝም አልኩት፡፡ መጨረሻ ላይ አልፌው ወደ ባልደራስ ጋር ልዞር ስል መልሶ ከፊቴ መጣና ተናገረኝ፤ተናድጄ የሆነ ኃይል ቃል ስናገረው በአካባቢው ከነበሩት ጎረምሶች መካከል አንዱ ‹ኧረ እከዬ አንተም ስድብ› ሲለኝ ‹ሂድ እኔ ሚካኤል ነኝ› አልኩት /..ሳቅ/ ይቺ ይቺ ናት ጉዳቷ፡፡

ቁም ነገር፡- ህይወት ምን አስተማረችህ ?
ንብረት፡- ብዙ ነገር፡፡ እኔ ነገን አላውቃትም ፤በእግዚያአብሔር ቸርነት እዚህ እንደደረስኩ አውቃለሁ፤ ተንገላትቼ ነው ያደኩት፤የረሐብ ጥጉን አውቀዋለሁ፤ከዛ ደግሞ አግኝቼ በግል ሄሊኮፕተር አልሄድኩም እንጂ የመዝናናት ጥጉንም አይቻለሁ፤ ስለዚህ ህይወት ከዚህ በላይ ምንም ልታስተምረኝ አትችልም፡፡ ከዚህ በኋላ ከኔ ምን ይጠበቃል የሚለውን ለማድረግ ነው የምጥረው፤ እንደሰው ስህተት ብሰራም አሁን ለህይወት ዋጋ እሰጣለሁ፤ታላላቆቼን አከብራለሁ፣ማህበራዊ ጉዳይ ላይ በደንብ እሳተፋለሁ፣እንደ አንድ አርቲስት በአካል ጉዳተኞች ላይ የኢትዮጵያ የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው ብሔራዊ ማህበር አምባሳደር ነኝ፤እንደውም በዚህ አጋጣሚ መጽሔታችሁን የሚያነቡ ሁሉ ብሔራዊ ማህበሩን እንዲጎበኙ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ምክንያቱም ማንም ሰው የአዕምሮ እድገት ውስንነት የሌለበት ልጅ ላለመውለድ ዋስትና የለውም፤ማንም ሰው ደግሞ ባጋጣሚ
ድንገተኛ አደጋ ይህ እንደማይከሰትበትም ዋስትና የለውም፤ ስለዚህ ብሔራዊ ማህበራችን ከዘሪሁን ህንፃ ጀርባ ይገኛል፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መስራት የሚፈልጉ ሰዎች መጥተው እንዲያናግሩኝና አብረን እንድንሰራ እላለሁ፡ ፡ እና ህይወት እነዚህን እነዚህን ኃላፊነቶቼን እንድወጣ አስተምራኛለች፡፡

ቁም ነገር፡- የመጀመሪያ ፍቅር ከሁለተኛው በምን ይለያል?
ንብረት፡- አዎ! ብዙ ሰው እንደዚህ ይላል፡፡ ስለዚህ እንደዚህ የሚሉትን ጠይቂያቸው እኔ አላውቅም /..ሳቅ/ ስለሁለቱም ፡፡

ቁም ነገር፡- በልጅነትህ በባህሪህ ምን አይነት ልጅ ነበርክ ?
ንብረት፡- በልጅነቴ ቀይ ልጅ ነበርኩ /…ሳቅ/፤በባህል ታንፆ የማደግ ነገር ነበር ቤተሰባችን ውስጥ፤ይህ ማለት ስማር እራሱ የመጀመሪያ ትምህርቴ ሀ. ሁ ነው ፤ፊደል ተማርኩት ለጥቆ አቦጊዳ ከዚያ መልዕክተ ከዚያ ደግሞ ዳዊት ደገምኩኝ፤ እንደዚህ እያልኩ መደበኛ ትምህርት ቤት ስገባ እንደ አሁኑ ዕውቀት ተኮር መመዘኛ ሳይሆን እጄን ጭንቅላቴ ላይ አድርጌ በእጄ ተቃራኒ በኩል ያለውን ጆሮዬን ንካ ተብዬ በቃ ደርሷል ተብሎ ነው የገባሁት፡፡ በባህሪዬ የተረጋጋሁ ልጅ አይደለሁም ፤ቶሎ አኩራፊ ነኝ፣ትንሽ ደግሞ ተደባዳቢ ቢጤም ነበርኩኝ፤ቶሎ ውጤት ፈላጊ ልጅ፣ ብዙ የምጠይቅ ነበርኩ በአጭሩ /..ሳቅ/፡፡

ቁም ነገር፡- ከዘሩ ሞላና አዛሉ ለቤተሰቡ ይበልጥ የሚያስበው ማነው?
ንብረት፡- ለኔ ሁለቱም እኩል ናቸው ፡፡ ዘሩ ሞላ ስናየው ዝም ብሎ ቋጣሪ ስግብግብ ይመስላል፤የሚንገበገበው ግን ለልጆቹ ነው ፡ ፡ ዘሩ በአሳማኝ ወጪ ብቻ የሚያምን ሰው ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን አሳማኝ ወጪዎችን ጭምር መሸወድ የሚፈልግ ሰው ነው /..ሳቅ/ ፤ለመኖር ደግሞ ይሄ አስፈላጊ ነገር ነው ፡ ፡ አሳማኝ ያልናቸውን ነገሮች ትተን ወደፊት ደግሞ በርከት ብሎ ከዛ ይበልጥ አሳማኝ ነገሮች ሲመጡ ለነዛ ልናውላቸው እንችላለን፤እና ዘሩ ሞላ እንደዚያ አይነት ሰው ነው ፡፡ ደግም ነው፡፡ እከን ያህል እንቅልፋም ሰውዬ፣ትርፌን ያህል ሆዳም ሴትዮ፣ሻሼን ያህል ምላሳም ይዞ መኖር እንደቤተሰብ አባል፤ የዘሩን ደግነት ነው የሚያሳየው፡፡ አዛሉንም ካየናት ቀለል ያለች እናት ነች፡፡

ቁም ነገር፡- ሀገራችን በቀላሉ ከድህነት መውጣት ያልቻለችው ለምን ይመስልሀል ?
ንብረት፡- ለምዳው ነዋ! /…ሳቅ/ ፤ ለምዳው ነው የሚለው ቃል ከማሳቅ አንፃር ይታይልኝና፤እኔ ትልቁ ምክንያት ብዬ የማስቀምጠው ሰው ላይ አልተሰራም ፡፡ ከድህነት ለመውጣት ሰው አለማም ፡፡ የመስራት ባህላችን የደከመ ነው፡፡ ድሮ ይህችን ሐገር ቅኝ ግዛት ሊያደርጓት የፈለጉ ፈረንጆች ስለቱን የሚሰራውን ቀጥቅጦ ጎራዴውን የሚያበጀው፣መቆፈሪያውን ፣ማልሚያውን የእርሻ መሳሪያውን የሚሰራውን ቀጥቃጭ እያሉት፣ ሸማ የሚሰራውን ቡዳ ነው እያሉ፣ሸክላ የሚሰሩትንም እንደዛው እያሉ ማንነታችንን ወሰዱት፤ እኛም እስካሁን ቁጭ ብለናል ስንሰዳደብና ስንጣላ እንዲሁ አለን፡፡ አሁን ያለው ትውልድ ደግሞ በዘመናዊ እውቀት ሄደዋል ለመረጃም ቅርብ ናቸው፤ግን የማንነት ችግር በጣም አለ፡፡ ኢትዩጵያዊ የሚባለው ነገር በጣም ያሰጋል፤ በኪ ነጥበብ ስራዎቻችን ላይም የራሳችን የሆኑ ብዙ የሚሰሩ ታሪኮች እያሉን የውጭ አድናቂ ሆነናል፡፡ ሙዚቃችን ፣ፊልሞቻችን ፣የመድረክ ቴአትሮቻችን በውርስ ትርጉም እየተጨናነቁ ነው ያሉት፡፡ እና እነዚህ ነገሮች ተንከባለው ተንከባለው የሆነ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳይደርሱ እፈራለሁ፡፡ ክፉ ትንቢትም እየተናገርኩ አይደለም ስለዚህ ሰው መልማት አለበት እላለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- በመጨረሻ የጠቅላላ ዕውቀት ጥያቄ ነው የቀረን፤ የመጀመሪያው የአጭር ልብ ወለድ መጽሐፍ ደራሲ ማናቸው?
ንብረት፡- አላቃቸውም፡፡
ቁም ነገር፡- አመሠግናለሁ፡

The post “እከ ደከ ማን ችሎት በብልጠቱም ሆነ በጉልበቱ ከወንድ በላይ አበጀ” ይናገራል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

በግማሽ ዓመት 47 ሺ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል * በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል

$
0
0

ሰሞኑን 35 ስደተኞች የያዘ ጀልባ የመን ሳይደርስ ሰጥሟል
በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል
“በህጋዊ ምዝገባ የስራ ጉዞ መታገዱ ህገወጥ ስደትን አባብሷል”

yemen

በህጋዊ ምዝገባ ወደ አረብ አገራት የሚደረግ ጉዞ ከታገደ ወዲህ፣ በየመን በኩል እየተሰደዱ ለአደጋ የሚጋለጡ ኢትዮጵያዊያን መበራከታቸውንና ባለፉት ስድስት ወራት 47ሺ ያህል ስደተኞች የመን እንደገቡ RMMS ሰሞኑን ገለፁ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን እና ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ ያቋቋሙት ይሄው ተቋም እንደሚለው፣ ዘንድሮ የስደተኞቹ ቁጥር ከአምናው በእጥፍ ይበልጣል፡፡ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ 250 ስደተኞች የመን ለመግባት ሲሞክሩ፣ በባህርና በበረሃ ጉዞ ላይ መሞታቸውን ተቋሙ ጠቅሶ ከስደተኞቹ መካከል ሰማኒያ በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ሰሞኑን በባህር ጉዞ ላይ በተፈጠረ አደጋ አንድ ጀልባ መስመጡን የዘገበው ኤኤፍፒ፤ ጀልባዋ 35 ስደተኞችን አሳፍራ ነበር ብሏል፡፡ ከጉዞ አደጋ በተጨማሪ ስደተኞቹ የመን ከገቡ በኋላም ግማሽ ያህሉ በወሮበላ ቡድኖች እንደሚታገዱ የገለፀው RMMS፤ ከእገታ ለመለቀቅ ከቤተሰብ ገንዘብ እንዲያስልኩ ይገደዳሉ ብሏል፡፡ ለስደት የሚገፋፉ ዋና ዋና ምክንያቶችን ለማወቅ በሺ በሚቆጠሩ ስደተኞችና በትውልድ አካባቢዎቻቸው ላይ ጥናት ያካሄደው ይሄው ተቋም፤ በኢትዮጵያ ዋናዎቹ መንስኤዎች የኑሮ ችግር እንዲሁም ህይወትን የሚያሻሽል ነገር ፍለጋ ናቸው ብሏል፡፡ የፖለቲካ ችግርም የተወሰነ ጫና እንደሚፈጥር ተቋሙ ጠቅሶ፣ የደላሎች ድርሻ ግን ብዙዎች እንደሚያስቡት አይደለም፤ ከመቶ ስደተኞች መካከል በደላላ ግፊት ለስደት የሚነሳሱት ከሁለት ወይም ከሦስት አይበልጡም ብሏል፡፡

ብዙ ወጣቶች ወደ ስደት የሚያቀኑት አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ባለማወቃቸው ነው ለማለት እንደሚያስቸግር ተቋሙ ሲያስረዳ፤ በአመት ውስጥ ወደ የመን ከገቡት ኢትዮጵያዊያን መካከል ሩብ ያህሉ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተባረሩና ካሁን በፊት ስደትን የሞከሩ ናቸው ብሏል፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ የስደተኞቹ ቁጥር የተባባሰበት ሌላው ምክንያት፣ በህጋዊ ምዝገባ ወደ ሳዑዲ አረቢያና ወደ ኩዌት ሲደረግ የነበረው የስራ ጉዞ በመንግስት መታገዱ ነው ብሏል – የተቋሙ ጥናት፡፡ በሌላ በኩል ሶማሊያ ውስጥ ከድህነት በተጨማሪ የሰላም እጦት ወጣቶችን ለስደት እንደሚገፋፋ ተቋሙ ገልፆ፤ በኤርትራ ደግሞ ከኑሮ ችግር ሌላ ዋነኛው ግፊት የመንግስት ከፍተኛ የፖለቲካ አፈና ነው ብሏል፡፡ በሊቢያና በግብጽ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ከሚሞክሩ ስደተኞች መካከል ከሶሪያዊያን በመቀጠል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ኤርትራዊያን መሆናቸውን የጠቀሰው ይሄው ተቋም፤ ባለፉት አራት ወራት 15ሺ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደተሰደዱ ገልጿል፡፡ ስደት የተባባሰው በድህነትና በአፈና ምክንያት አይደለም በማለት የኤርትራ መንግስት ሲያስተባብል፤ ወጣቶች እንዲሰደዱ በማድረግ አገሪቱን ኦና ለማድረግ አለማቀፍ ሴራ እየተካሄደብኝ ነው ብሏል፡፡

ምንጭ: አዲስ አድማስ ጋዜጣ

The post በግማሽ ዓመት 47 ሺ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል * በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ልደቱ አያሌው በቀጣዩ “ምርጫ”አልወዳደርም አሉ –“ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ምንም ነገር አይመጣም”ሲሉ ምርጫውን አጣጣሉት

$
0
0

lidetu ayalew
“ቴአትረ ቦለቲካ” የሚል መፅሃፍ ሊያወጡ ነው

በመጪው ግንቦት በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ካለፈው ምርጫ የተለየ ውጤት ቨመጣል ብለው እንደማይጠብቁ የተናገሩት የቀድሞው የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ ልደቱ አያሌው፤ በምርጫውም እንደማይወዳደሩ አስታወቁ፡፡ በ “ቴአትረ ቦፖለቲካ ፣ አሉባልታና የአገራችን ፖለቲካ ገመና” በሚል ርዕስ የፃፉት አዲስ መፅሀፍ በቅርቡ በገበያ ላይ እንደሚውልም ተናግረዋል፡፡

“የኢህአዴግን አካሄድና የተቃዋሚው ጎራ ያለበትን ሁኔታ ሳየው በግንቦቱ ምርጫ ካለፈው የተለየ ነገር ይመጣል ብዬ አላስብም” ያሉት አቶ ልደቱ፤ ኢህአዴግ ምርጫውን ሙሉ በሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር አድርጎ እንደቀጠለ ነው፣ ተቃዋሚው ጎራም ካለፉት ስህተቶቹና ድክመቶቹ ተምሮ ራሱን ለማሻሻል ያደረገው ብዙ ነገር የለም ሲሉ ምክንያታቸውን ገልፀዋል፡፡ “ድፍረት አይሁንብኝ እንጂ ተቃዋሚው ጎራ በፓርላማ ያለችውን አንድ መቀመጫ አስጠብቆ ይቀጥላል ወይ የሚለው በራሱ ለኔ ጥያቄ ነው” ሲሉም ጥርጣሬያቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በተቃዋሚ ፓርቲ ዙሪያ የተደረጉ የትብብር ሙከራዎች ትግሉን የጎዱ እንጂ የጠቀሙ አይደሉም ሲሉ የሚሞግቱት አቶ ልደቱ፤ ፓርቲዎች በእንተባበር ጥያቄዎች ባይዳከሙ ኖሮ በአሁኑ ወቅት ሁለት ወይም ሶስት ጠንካራ ፓርቲዎች ይኖሩን ነበር ብለዋል፡፡

“ቴአትረ ቦለቲካ፡ አሉባልታና የአገራችን ፖለቲካ ገመና” የተሰኘ ሶስተኛ መፅሃፋቸው በቅርቡ እንደሚወጣ የጠቆሙት አቶ ልደቱ፤ መፅሃፉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አሉባልታዎች ዙሪያ እንደሚያጠነጥን ተናግረዋል፡፡ አሉባልታ የተቃውሞ ጎራውን ትግል ክፉኛ እንደጎዳውም ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል፡፡

The post ልደቱ አያሌው በቀጣዩ “ምርጫ” አልወዳደርም አሉ – “ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ምንም ነገር አይመጣም” ሲሉ ምርጫውን አጣጣሉት appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ንብረት የሆነው መሬት በተጭበረበረ ካርታ ለባለሃብቶች መሸጡ ተነገረ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለየ ስሙና ቦታው እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ንብረት የሆነውን መሬት አዲስ የተመረጠው ሰበካ ጉባኤ ለባለሃብቶች በተጭበረበረ ሰነድ እየሸጠ ነው ሲሉ ምእመናን ብሶታቸውን አሰሙ::
news
“ለማን አቤት ይባላል? ለፈጣሪ እንጂ” የሚሉት እነዚሁ ተቆርቋሪ ምእመናን “በቅርቡ የተመረጡት የሰበካ ጉባዔ አባላት በቤተክርስትያን ስም ሁለት ማህተም በማሰራት የቤተክርስትያኑ ንብረት የሆነውን ቦታ በማጭበርበር እየሸጡት ነው፡፡” ነው ይላሉ:: ምዕመናኑ አክለውም “የቤተክርስትያኑ ሰንበቴ ቤት የነበረውን ክፍት ቦታ ለቤተክርስትያኑ ገቢ ማስገኛ በማለት ለግለሰብ ቢያከራዩትም ሰነዱን በማጥፋት ካርታ አስወጥተው እንደሸጡት ታውቋል:: አሁን ደግሞ የማቴዎስ ግቢ የሚባለውን የቤተክርስቲያኑን ቦታ አገልጋይ ካህናትን በማስወጣት ለግለሰብ ለ20 ዓመት ሊሸጡት እየተደራደሩ ነው:: ይህንንም ለማሳመን ሁለት ዓይነት የተጭበረበረ ሰነድ አቅርበዋል:: ስለዚህ የሚመለከታችሁ ሁሉ ይህንን የቤተክርስትያን ቦታ በመሸጥ ላይ የተመሰረተ እኩይ ተግባር በህግ አምላክ ብለን እናስቁማቸው::” ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርቧል::

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአዲስ አበባ መሬቶች ለሕወሓት ሰዎች እና ለውጭ ባለሃብቶች በልማት ስም ተቸብችበው ያለቁ በመሆኑና የመሬትም እጥረት ስላለ የቤተክርስቲያን መሬቶችን ወድ መቀራመቱ ተደርሷል:: በቅርቡ አዲስ አበባን በማስፋፋት በሚል ሰበብ በወጣው አዲስ ማስተር ፕላን የኦሮሚያ ገበሬዎች መሬት ተቀምቶ ለባለሃብት ሊሰጥ ነው በሚል በተነሳ የሕዝብ ጥያቄ በርካቶች የጥይት ራት መሆናቸው ይታወቃል::

እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ንብረት የሆነውን መሬት አለአግባብ ለባለሃብት ቸብችበዋል የተባሉትን የሰበካ ጉባኤ አባላት ዘ-ሐበሻ ለማናገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም:: እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ግን የቤተክርስቲያናችን ንብረት ሊሸጥ አይገባም የሚሉ ሰዎች ተቃውሟቸውን አደባባይ ይዘው ለመውጣት እየተዘጋጁ ነው::

The post እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ንብረት የሆነው መሬት በተጭበረበረ ካርታ ለባለሃብቶች መሸጡ ተነገረ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images