Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የመኢአድ መልስ ለምርጫ ቦርድ – VOA

$
0
0

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ተከፋፍለዋል” ያላቸው የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት – መኢአድና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላት በሚቀጥሉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ የአመራር አባላቱ በአንድ ላይ ሆነው በችግሮቻቸው ላይ ጠቅላላ ጉባኤዎቻቸውን አስወስነው ለቦርዱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠቱ ተዘግቧል።

የቦርዱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በሰጡት መግለጫ ላይ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መልስ ሰጥቷል፡፡

እስክንድር ፍሬው የድርጅቱን ፕሬዚደንት አቶ ማሙሼት አማረን አነጋግሯል።

ለዘገባው የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡


ME EL


ፈረንሳይ ሌጋሲዮን በኢቦላ በሽታ ስጋት ተወጥራለች

$
0
0

• ከ10 በላይ ሰዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ በፖሊስ ታግተዋል

ebola(ዘሐበሻ) ሴራሊዮን ውስጥ በአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ ህይወቱ ያለፈውና በሽታው ኢቦላ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የደም ናሙናው ወደ ውጭ ለምርመራ የተላከው ኢትዮጵያው ጋር ግንኙነት አለው የተባለው የአምቡላንስ ሰራተኛና ከእሱ ጋር ተገናኝተዋል የተባሉ ሌሎች 10 ያህል ሰዎች የሚኖሩበት ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ የሚገኝ ግቢ በፖሊስ ተከቦ ነዋሪዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ተደርገዋል፡፡
ኢሳያስ የተባለና ህይወቱ ያለፈውን ኢትዮጵያዊ በአምቡላንስ ሲያመላልስ የነበር ወጣት ፈረንሳይ ሌጋሲዮን በተለምዶ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከራይቶ የሚኖር ሲሆን እሱን ጨምሮ ከእሱ ጋር የሚኖሩት እህቱና ባለቤቱ እንዲሁም ተከራይቶ በሚኖርበት ግቢ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ከ10 በላይ ሰዎች ከህዝብ እንዳይገናኙ በፖሊስ ታግተዋል፡፡ ግቢው በፖሊስ ተከቦ ሰው ከግቢው እንዳይወጣና ወደ ግቢው እንዳይገባ መከልከሉን ተከትሎ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ የሚኖረው ህዝብ በኢቦላ በሽታ ስጋት ተወጥሯል፡፡
የጤና ባለሙያዎችና ፖሊሶች ኢሳያስ የተባለው ግለሰብ ሟቹን በአምቡላንስ ሲያመላልስ እንደነበር ከትናንት ጠዋት ጀምረው ቢያረጋግጡም እስከ ትናንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ ከሰው ጋር እንዳይገናኝ ሳይከለክሉት ቆይተዋል ተብሏል፡፡ የአምቡላንስ ሾፌሩ በሚኖርበት ግቢ ውስጥ ከ20 በላይ ሰዎች የሚኖሩ ቢሆንም 10 ያህሉ ግለሰቦች ብቻ ከግቢ እንዳይወጡ የተከለከሉት ዛሬ ጠዋት ነው ተብሏል፡፡ ሆኖም ከግቢው ውጭ ከኢሳያስ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ግለሰቦች ላይ ምንም አይነት ክትትል ያልተደረገ ሲሆን ግቢው ውስጥ ከሚኖሩት መካከልም በጠዋት በስራና በሌሎች ምክንያች የወጡ ግለሰቦችም ተመልሰው ወደ ግቢ እንዳይገቡ ከመከልከላቸው ውጭ ክትትል እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ታውቋል፡፡
የአምቡላንስ ሾፌሩና ከእሱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉበት ግለሰቦች የሚኖሩበት ግቢ በርከት ባሉ ፖሊሶችና የደህንነት ሰራተኞች መከበቡን ተከትሎ ስጋት የገባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተሰባስበው ስለ በሽታው እየተወያዩ አስተውለናል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም የአንቡላንስ ሾፌሩ ከበርካታ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበረው መሆኑ፣ እንዲሁም ግቢው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችም ከግቢ ውጭ የሚገኙ በመሆኑ በሽታው ከተከሰተ ለአካባቢው ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱም አስጊ እንደሆነ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ በፖሊስና ደህንነት ከበባ ብቻ አንድ ግቢ ውስጥ ተከሰተ የተባለውን ጉዳይ በአግባቡ መያዝ አለመቻሉን ጠቅሰውም ‹‹መንግስት ዝግጅት ሳያደርግ ዜጎችን መላኩ ትክክል አልነበረም፡፡›› ሲሉ ተችተዋል፡፡
በፖሊስ ከታገቱት መካከል በስልክ አግኝተን ያነጋገርናቸው ሰዎች ደህንነቶች ‹‹ይህ የአገር ሚስጥር በመሆኑ ለማንም እንዳትናገሩ፡፡›› እብለው እንዳስጠነቀቋቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስና ደህንነቶች ሰው እንዳይወጣና እንዳይገባ በመከልከላቸው እስካሁን ምግብ እንዳልገባላቸውና ‹‹የሟቹ የደም ናሙና ነገ እስኪመጣ ድረስ ከግቢ መውጣት አትችሉም፡፡ ሌሎች ሰዎችም ወደ ግቢ መግባት አይችሉም፡፡ እስከነገ ለማንም መረጃ ባለመስጠት ተባበሩን፡፡›› እንደተባሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ፖሊስ ግቢውን በከበበት ወቅት የግቢው ነዋሪዎች ‹‹ችግር ካለ ባለሙያ መጥቶ ያረጋግጥ፡፡ ፖሊስ ለምን ያግተናል?›› በሚል ከግቢው እንወጣለን በማለታቸው ጭቅጭቅ ተፈጥሮ እንደነበርም የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

´ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ´ ዓብይ ጉዳይ!

$
0
0

ኣረጋዊ በርሄ

Gebru Asratኣቶ ገብሩ ኣስራት ´ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ´ በሚል ርእስ ትልቅ መፅሓፍ ፅፈዋል፤ ትልቅነቱ ሃገርን ያክል ዓብይ ስብስብ የሚንዱ ወይም የሚገነቡ ርእሰ ጉዳዮች – ማለት ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ- በኢትዮጵያችን የደረሱበትን ኣሳሳቢ ደረጃ ኣስመልክቶ እንድንመክርበት በጥልቀት መርምሮ ስላስቀመጠልን ነው። ከዚህም ኣልፎ ላሳሳቢው ችግር መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን ኣንኳር ፍሬነገሮች ግልፅ ኣድርገዋል። ከዚህ በመነሳት ይህ ትላልቅ ርእሶችን ያነገበ መፅሓፍ እንዴት መታየት እንዳለበት፤ ግድፈቶቹን ሳልተው የበኩሌን ኣስተያየት ኣጠር ባለ መልኩ ለማከል እወዳለሁ።

መፅሓፉ በ6 ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን የመጀመርያ 2ቱ ምዕራፎች ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ ኣሁን ለደረሱበት ኣሳፋሪ ደረጃ ማገናዘብያና ታሪካዊ መንደርደርያ ሲሆኑ፣ የተቀሩት 4ቱ ደግሞ የሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ መሸርሸር እንዴት እንደተከናወነና በኢትዮጵያ ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ይዘት ላይ ያስከተለው ኣሉታዊ ተፅእኖ ይተነትናሉ። በመጨረሻም የመፍትሄ ሓሳቦችን በመሰንዘር ያጠቃልላል።

ብዙዎቹ ጠበብት እንደሚስማሙት ሉዓላዊነት የኣንድን ሃገር መብትና ጥቅም ለማስከብር የሚያገለግል ከፍተኛው ሕጋዊ ስልጣን መጨበጥ ማለት ነው። ይህ ከፍተኛው ሕጋዊ ስልጣን ከሃገራችን እውነታ ኣኳያ ሲታይ በኣሁኑ ወቅት ምን ያህል እንደተሸረሸረና ያስከተለው ጉዳት በጥቅሉ ቢታወቅም በዝርዝር ማወቁና የደረሰው ጥፋት ይሽር ዘንድ፣ ብሎም እንዳይደገም የያንዳንዱ ዜጋ ተቀዳሚ ሓላፊነት በመሆኑ ይህ መፅሓፍ ለዚህ ሓላፊነት ንቁና ብቁ የማድረግ ተልእኮ ኣለው እላለሁ።

gebru-bookይህንን ሃገራዊ መብትና ጥቅም ማስከብር የመንግስት ተቀዳሚ ሓላፊነት ቢሆንም፤ ከ24 ዓመታት በፊት ስልጣን የጨበጠው ህወሓት/ኢህኣዴግ መንግስታዊ ስልጣኑ የተገለገለበት ሂደት ሲመረመር፣ ጭራሽ በሚገርም ሁኔታ የህዝቡን መሰረታዊ መብቶች በመጨፍለቅና የሃገሪቱን ኣንጡራ ጥቅሞች ለዘራፊዎች ኣሳልፎ በመስጠት እንደነበረና እንደሆነ እነሆ ኣቶ ገብሩ ከርቀት ሳይሆን በሓላፊነት ተቀምጦ ከውስጥ እንደተገነዘበው ያረጋግጥልናል። ገብሩ ይህን የኣፈናና የክህደት ቅንብር ሲታገለው እንደቆየና ዋጋ እንደከፈለበትም ከመፅሓፉ ጋር ስንከንፍ እንገነዘባለን።  የሃገር ሉዓላዊነት ሲደፈር የሃገሬው ህዝብ መጎዳቱና መቃወሙ ነባራዊ ስለሆነ፣ ይህን ፍትሃዊ ተቃውሞ ለማዳፈን ሲባል ደግሞ ዲሞክራሲያዊ መብቶች መጨፍለቅ ኣብሮ የሚሄድ የስርዓቱ ዋነኛ ፖሊሲም ተግባርም እንደሆነ በራሱ ጭምር ከደረሱ በደሎች በመነሳት ያብራራልናል። ይኸው በግልፅ የተቀመጠውን ሃቅ ደግሞ በበቂ መረጃዎች ስለታጀበልን ለመገንዘብ ኣይከብድም፤ ለግላዊ ምክንያት ዓይንን ካልጨፈኑ ወይም ህሊናን ካልሸጡ በስተቀር።

በመጀመርያው ምዕራፍ እንደተቀመጠው በኣንድ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ክብሩንና ዳር ድንበሩን ለማስከበር ከመሪዎቹ ጋር በመተባበር ባካሄደው መራራ ትግልና በከፈለው እጅግ ከባድ መስዋዕትነት የባዕዳን ወረራና ሴራ እንዳከሸፈና ሉዓላዊነቱን ኣስከብሮ እንደኖረ ሲታወቅ፤ በሌላው በኩል የመለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ ሚና ደግሞ ያንን በኣያሌ መስዋዕትነት የተገነባው ሉዓላዊነትን ለመሸርሸር ብቻ ሳይሆን ኣሳልፎ ለመስጠትም እንደነበረና፣ ምን ያህልም አክርረው እንደተረባረቡበት በንፅፅር ያስረዳል። በዓለም ዙርያ ይሁን በሃገራችን ታሪክም እንደሚታወቀው ሁሉ፣ መሪዎች የሚታወቁበት ትልቁ ሚናቸው የሃገር ሉዓላዊነትን በመጠበቅና ዳር ድንበርን በማስከበርና ሲሆን የመለስ ሚና ደግሞ የተገላቢጦሽ፤ ሉዓላዊነትን ኣሳልፎ በመስጠት በመሆኑ ልዩ ከሃዲ መሪ ያደርገዋል።

በ2ኛው ምዕራፍ በዋናነት የምንረዳው መለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ በትግሉ ወቅት ስውር ዓላማቸውን ለማሳካት የታጋይነት ካባ ለብሰው በማድፈጥ፣ ለህዝቦች መብትና ለሉዓላዊነት መከበር የቆሙትን ሃይሎች በተቀነባበረ ሴራ ከውስጥ እንዴት መምታት እንደቻሉ ይተነትናል። እራሱ ገብሩንና መሰሎቹን እንዴት ጠልፈው እንደጣልዋቸው ወደሁዋላ ቢያብራራልንም፣ በተመሳሳይ መልክ ቀደም ብለው ከተጠለፉት ታጋዮች ትምህርት ሳይወስድ ቀርቶ መዘናጋቱ ግን ሳይገርመኝ ኣልቀረም። ኣስመሳዮችና ከሃዲዎች ወደፊትም ሊኖሩ ስለሚችሉና እንደኣሁኑ ኣዘቅት ውስጥ ላለመዘፈቅ የዚሁን ሴራ ኣደገኛነት ተተንትኖ መቅረብ ትልቅ ትምህርት የሚገበይበት ነው። ይህ ኣውዳሚ ሴራ በሚገባ የተተነተነ ቢሆንም መለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ ራሱ ገብሩን እንዴት እንዳጠመዱትና ምን ድረስ እንደወሰዱት ቢያክልበት ኖሮ ትንተናውን በይበልጥ ያጠናክረው እንደነበር ጥርጥር የለኝም።

እነዚህ ሁለት ምዕራፎች እንደ መንደርደርያ ኣድርገን ብንወስዳቸው፤ የሚቀጥሉት 4 ምዕራፎች ሉዓላዊነት የተሸረሸረበትና ዲሞክራሲ የተረገጠበት ተግባራዊ ሂደት በማያሻማ ጭብጣዊ ኣገላለፅ በዝርዝር ያትታል። እዚህ ላይ ሉዓላዊነትን ማስደፈርና ዲሞክራሲን መጨፍለቅ ለምን ኣስፈለገ ? የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፤ ይገባልም። ዝርዝር ሂደቱን ስንመለከት የመለስ ዜናዊና ግብረ ኣበሮቹ የግል ስልጣን ጥም ማርካት ያስከተለው ረቂቅ በሽታ እንደሆነ ሊደረስበት ይቻላል። የግል ስልጣን በሽታ የተጠናወታቸው መሪዎች፥ በሌሎች መሪዎችም እንዳየነው፥ ለግል ስልጣናቸው መንከባከብ እስካገለገለ ድረስ ሉዓላዊነት ቢደፈር ፡ ዴሞክራሲ ቢጨፈለቅ ጉዳያቸው ኣይደለም። ለባዕዳን ሃይሎችም ተገዝተው የሚያገለግሉ “መሪዎችም” እንዳሉ ይታወቃል። ከነዚህኞቹ ኣንዱ መለስ ዜናዊ ሳይሆን ኣይቀርም። ይህ በተለያየ መልክ የሚንፀባረቀው ረቂቅ በሽታ ኣሁንም ወደፊትም ሊኖር ስለሚችል መድሓኒቱ የሚገኘው ከነቃና ከተደራጀ ህዝብ ብቻ ነው። ስልጣን በግለሰዎች እጅ እንዳይወድቅ፣ ህዝብ በየመልኩ ተደራጅቶ የስልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት ስርዓት ፈጥሮ መኖር ይኖርበታል።

ወደ ዝርዝር ጉዳዮች ስንገባ፤ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በይፋ መረገጥ የጀመረበት መቼና እንዴት እንደሆነ ገብሩ በማያሻማ ሁኔታ ያስረዳል። በ1983 ዓ/ም ሰንዓፈ – ኤርትራ ውስጥ በነመለስ ተረቆ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ ሆኖ ሳይመክርበት በላዩላይ የተጫነው ቻርተር ተግባር ላይ ሲውል ነው። ይህ ቻርተር ለህዝቡ ሳይሆን ለግላቸው የሚያገለገሉበት መንግስት እንዲፈጥሩ ኣስችሏቸዋል። “ኦነግ ፣ ሻዕብያና ህወሓት/ኢህኣዴግ የተስማሙበት ይህ ሰነድ በኢትዮጵያ የሚመሰረተው የሽግግር መንግስት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ኣሳድረዋል።” (ገብሩ፤ ገጽ 181) ካለ በኃላ ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ የዴሞክራሲ ጥሰቱን ኣያይዞ ሲያብራራው፤ ለሉዓላዊነት መከበር ሊቆሙ የሚችሉትን ህብረ-ብሄር ድርጅቶች “ኣስተሳሰባቸው በህዝቡ ውሳኔ መሸነፍ እስካልተረጋገጠ ድረስም ትምክህተኞችና ጸረ-ሰላም ሓይሎች ናቸው በሚል ከሚቋቋመው የሽግግር መንግስት እንዲገለሉ ማድረጉ ተገቢ ኣልነበረም” በማለት የህዝቡ ይሁን የድርጅቶቹ ዴሞክራሲዊና ፖለቲካዊ መብቶች በመርገጥ  ሃገሪቱን ለማያባራ ቀውስ እንደዳረጉዋት በተጨባጭ ያስገነዝበናል። ሰፊው ህዝብን የሚያገል ተግባራት ሁሉ ዞሮዞሮ ወደ ቀውስ ማምራቱ ኣይቀርም። ሃገር የጋራ እንደሆነ ሁሉ እነዚህ መብቶችም የሁሉም ናቸውና ይህን ሃቅ ማወላገዱ ሰላምን ማደፍረስ ብሎም ኣመፅን መጋበዝ መሆኑ በሁሉም ዘንድ እንደታወቅ የግድ ይላል።

ብዙም ሳይቆይ ቻርተሩ “ሕገ-መንግስት” ወደ ተባለው ሰነድ ተቀይሮ፤ በዚህ ሰነድ ከለላ ህዝቡን ያገለለ ግን ደግሞ በህዝቡ ስም በኣውዳሚነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሴራ ተፈፅመዋል። ከባሕር- በር ማጣት ጀምሮ የሃገሪቱን ኣንጡራ ሃብቶች እስከ ማስዘረፍ የደረሰ ክሕደት መፈፀሙ ገብሩ በዝርዝር ያስረዳል። በዚህ ወቅት 144000 (ኣንድ መቶ ኣርባ ኣራት ሺ) ኢትዮጵያዊያን ከኤርትራ በግፍ ሲባረሩ ጥብቅና የቆሙት ለወገናቸው፣ ግፍ ለደረሰበት ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ለግፈኛው ሻዕብያ መሆኑ ሲታይ (በሰነድም, EPRDF News Bulletin,…August 30, 1991. ላይ ሲያረጋግጡ) የብዙ ሰው ልብ ማድማታቸው ጠቅሸ ማለፍ እፈልጋለሁ።

ሓምሌ 1983 ሻዕብያ ኣስመራ ላይ በጠራው የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን የመዝረፍ ዕቅዱ ግልፅ እንዳደረገው፣ ገብሩና ባልደረቦቹ (ስብሓት ነጋን ጨምሮ) በታዛቢነት ተገኝተው ተገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ኣየር መንገድ፤ ባንኮች፤ ኣውራ ጎዳና ስራ፣  ወ.ዘ.ተ. ገብተው በራሳቸው ዕቅድ እንደሚሰሩ ተዝናንተው ግልፅ ኣድርገዋል። “የኤርትራን የእድገት ኣቅጣጫ ኣስመልክቶ የፖሊሲ መነሻ ሓሳብ የሚያቀርበው ምሁር፣ ኢትዮጵያ ገብተን ራሳችን መንገድ ቀይሰን መገንባት ኣለብን ሲል እብድ ይሁን ደንቆሮ ባይገባኝም ከሻዕብያ ኣመራር ያገኘውን መመሪያ መሰረት ኣድርጎ እንደተናገረ ግን ግልፅ ነበር” (ገብሩ፤ገፅ 193) ይለናል።

ይህ የዝርፍያ ዕቅድ እንዲሁ እቅድ ብቻ ሆኖ ኣልቀረም፣ በየዘርፉ ተግባራዊ ሆኖዋል። የኢትዮጵያ ከተማዎችን እየዳሰሰ ከኤርትራ ኬንያ የሚመላለሰው የኮንትሮባንድ ስምሪት፤ የውጭ ምንዛሪ ቅርምት፤ የቡና – ሰሊጥ- እንጨት ወዘተ ዝርፊያ፤ የጦር መሳርያና የኣልኮል መጠጥ ሸቀጡ ደርቶ እንደነበረ ያደባባይ ሚስጥር ነው። ሰውም ተዘርፈዋል / ታፍኖ ተወስደዋል። ለዚህ ማፍያዊ ስምሪት መሳካት መለስ ዜናዊ ተባባሪ ብቻ ሳይሆን ኣስፈፃሚም ነበረ። በህጉ መሰረት የሃገሪቱ መንግስት ምክር ቤት፤ ፓርላማ ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሳያውቁት በድብብቆሽ 1.2 ቢልዮን ብር ከኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ወጥቶ ለሻዕብያ እንዲሰጥ ማድረጉ (ገፅ 211) ኣንድ ኣብነት ነው።

ሻዕብያ የመለስና ስብሓት ተባባሪነት ብቻውን ኣላጠገበውም። ልቅ ምኞቱን ለማሳካት ወታደራዊ ሓይልን መጠቀም ፈልጎ የሰራዊት ምልመላና ስልጠና በገፍ ተያያዘው። የጦር ዝግጅቱ ያሳሰባቸው “ተወልደ፤ ኣውዓሎምና ገብሩ፣ ሻዕብያ ወደ ጦርነት እያመራ እንደነበር ቅንጣት ታኽል ጥርጣሪ ኣልነበረንም” ሲል ገብሩ፤ በኣንፃሩ ስብሓት ነጋ ግን መረጃው ሻዕብያ ወደ ጦርነት ማምራቱ ኣያመለክትም እያለ ሲቃወም እንደነበረ ያስረዳል። ቀጥሎም በባድመ ጦርነት ዋዜማ የህወሓት ማ/ኮሚቴና የኢህኣዴግ ስራ ኣ/ኮሚቴ በጋራ የኢትዮጵያ ጦር ኣስመራ ድረስ ዘልቆ የጠላትን ሓይል ማሽመድመድ ኣለበት ብሎ ሲወስን፣ (ገፅ 286) መለስ መቃወሙ ብቻ ሳይሆን በጠነጠነው ሴራ የብዙሃኑ ውሳኔ ግቡ ሳይመታ ከከባድ ኪሳራ ጋር ተኮላሽቶ እንዲቀር ኣድርገዋል። በፆሮና ግንባር ብቻው የነበረው ከባድ ኪሳራ ሲታይ መለስና ግብረ-ኣበሮቹ ለታጋዩ ወገን የነበራቸውን ደንታ ቢስነት በግልፅ ያረጋግጣል።

ገብሩ እንዳስጨበጠን፤ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጦሩን ሲደልብ፤ መለስ ዜናዊ ጦሩን ሲበትንና የተረፈውን ሲያኮላሽ፤ ስብሓት ነጋ ደግሞ የሁለቱን ሴራ ሲሸፋፍን በማህሉ ሃገርና ህዝብ ሲታመሱና ሲማቅቁ ማየቱ እጅግ ኣሳዛኝ ነበር። ዋናው ቁምነገሩ ግን ማሳዘኑ ኣይደለም። ከዚሁ ኣልፎ ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ መጠየቁ ኣግባብነት ያለው ዜግነታዊ ግዴታ መሆኑ ነው። ለዚህም ነው በግለ ሰዎች እጅ ላይ የወደቀች ሃገር እጣ ፈንታዋ ይኸው ኣሳዛኝ ተርእዮ የሚሆነው የምንለው። ባጠቃላይ እንደዚህ ዓይነቱ ግለ ሰዎች የሚቆጣጠሩት ስርዓት – የፈለገው ያህል ይመፃደቁ- በኣብዝሃው ስርዓት እስካልተተካ ድረስ ኣፈናው፣ ሰቆቃውና ውርደቱ ማቆምያ ኣይኖረውም።

መለስ በሓሳብ የተቃወሙትን የድርጅቱ ኣባላት ለመምታት ሲል 160 ዓመታት ወደ ኃላ ተጉዞ “ቦናፓርቲዝም” የሚባለው ፅንሰ ሓሳብ የመዘዘበትን መሰሪ ቅጥፈት ስንመለከት ደግሞ፣ ሃገሪቱና ህዝቡ ምን ያህል የኣንድ ግለ ሰብ መጫወቻ እንደነበሩ ያስረዳናል። ቦናፓርቲዝም ምን ማለት እንደሆነ ገብሩ (ገፅ 354-5) በግልፅ ኣስፍሮታል። እንዲያው በጥቅሉ ቦናፓርቲዝም የኣምባገነንነት ኣንዱ ገፅታ ሆኖ በተለይ የኣንድ ኣወናባጅ ሰው ፈላጭ ቆራጭነትን ያመለክታል። ሆኖም መለስ ይህ የራሱን ባህርያት ውስጥውስጡን ለተቃዋሚዎቹ በመለጠፍ ቀድሞ በህቡእ ከመታቸው በኃላ እራሱ  ምንደኛ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ኣረፈው። ይህን ተከትሎ የመጣው ኣሳዛኝና ኣሳፋሪ ድርጊቶቹም ገብሩ በማስረጃ ደግፎ ኣቅርቦልናል። ከብዙ በጥቂቱ፣

  • ለሃገር ሉዓላዊነት የቆሙትን “ኣፈንጋጮች” ብሎ በመሰየም በግሉ ውሳኔ ከስራቸው ማባረሩ (ገፅ 399)
  • በህዝብ ድምፅ ለብሄራዊ ምክር ቤት የተመረጡትን በግላዊ ጥላቻና ማን ኣህሎብኝነት የህዝቡን ውሳኔ ረግጦ ማገዱ (ገፅ 400)
  • “ኢንተርሃምዌ” በሚል የታወቀው የዘር ግጭት ቅስቀሳ ኢህኣዴግ እንዲጠቀምበት ውሳኔ ማስተላለፉ (ገፅ 434-5)
  • የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን “ሕገ-መንግስት መናድ” በሚል ክስ እስር ቤት እንዲወረወሩ ማድረጉ (ገፅ 442-3)
  • የሲቪል ማሕበረ ሰብ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ኣፋኝ ሕግ ኣስወጥቶ በስራ ላይ ማዋሉ (ገፅ 444)
  • ሓሳብን በነፃነት መግለፅ እንዳይዳብር ነፃ ፕሬሱን ጨምድዶ እጁ ውስጥ ማስገባቱና ጋዜጠኞችን ኣስሮ ማሰቃየቱ (ገፅ 445)
  • በፀረ-ሽብር ሽፋን ኣፋኝ ኣዋጅ ዘርግቶ ተቃዋሚዎችን በሰበብ ኣስባቡ መፍጀት (ገፅ 447-8) ሊጠቀሱ የሚችሉ የፀረ-ዴሞክራሲ ዘመቻው ኣብነቶች ናቸው።

 

እነዚህና ሌሎች ያልተጠቀሱ ፀረ-ዴሞክራሲና ፀረ-ሉዓላዊነት ድርጊቶቹ መለስን ተራ ኣምባገነን ሳይሆን ኣወናባጅ ኣምባገነን ያደርጉታል። የማወናበድ መሰሪነቱ ኣልታይ ያላቸው የዋሆች፣ የጥቅም ጉዳይም ተጨምሮበት፣ መታለላቸው ኣልቀረም። ለዚህም ነው ተከታዮቹ መለስን እንደ ብልጣብልጥ ሳይሆን እንደ ኣዋቂ የሚዘምሩለት። የገብሩ መፅሓፍ የመለስን ኣስመሳይ ገፅታ ፈጦ በግልፅ እንዲታይ ስለ ኣደረገ ተከታዮቹ ባሁኑ ጊዜ በመዝሙራቸው እያፈሩ ይገኛሉ። በኣድርባይነቱ የሚቀጥሉ ካሉም የባሰውኑ መዋረድ ኣይቀርላቸውም። ያም ሆኖ የመለስን ኣወናባጅ ባህርያት ሲያጋልጡና ሲቃወሙ የነበሩት የፖለቲካና የፕሬሱ ኣባላት እንደዚሁም የድርጅቱ ኣባላት (እነ ሓየሎምን ጨምሮ) የጥቃቱ ዒላማዎች ሆኖው እንዳለፉ መዘንጋት የሌለበት ሃቅ መሆኑ ላስታውስ እወዳለሁ። ለዚህም ነው በኢትዮጵያችን ዴሞክራሲ የተዳፈነው፤ ኣሁንም ተዳፍኖ የሚገኘው።

 

ኣቶ ገብሩ በመፅሓፉ በጥልቀት የመረመረው የሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ መረገጥ ኢትዮጵያን ምንኛ ኣዘቅት ውስጥ እንደከተታት ለመገንዘብ – የየዋሆቹና የኣድርባዮቹ መወድስ ወደ ጎን ትተን – ተገቢው (ለጂቲመት) የባሕር በር ማጣትና ያስከተለው ከባድ እዳ እና በተጨባጭ በየዓረብ ሃገር ኤምባሲ በራፍ የሚኮለኮለው ህዝብ ቁጥር ወይም በየባሕሩ የሚሰምጠውና በየምድረበዳው ቀልጦ የሚቀረው የወጣቱ ብዛት ማስተዋል ብቻውን በቂ በሆነ ነበር። ጥናታዊ መረጃ ካስፈለገም የተባበሩት መንግስታት ዕድገት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ. 2013) ብንመለከት ኢትዮጵያ በሰብኣዊ ዕድገት ኣመልካች ከ 187 ሃገሮች በ 173 ኛው ደረጃ ኣዘቅዝቃ ትገኛለች። ይህ ደግሞ የመናጢ ሃገሮች ተርታ ነው። 41% ህዝቧ ከድህነት ወለል በታች የሚኖርባት ሃገር ዕድገት ኣለ ብሎ ማውራት የዕድገት ትርጉም መሳት ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ኣሰቃቂ ሁኔታ ረስቶ በግለሰብ ኣምልኮ መጠመድ ነው። ኣድርባይነት ! ያውም ክላሲካል ኣድርባይነት ይሉታል።

 

ለዚህ ሁሉ ፍዳ ምክንያቱ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን ጨፍልቆ ኣምባገነንነትን ያነገሰው የመለስና ግብረ-ኣበሮቹ ሰንካላ ፖሊሲ መሆኑ መፅሓፉ በመረጃ ኣጅቦ ያስረዳል። የመፅሓፉ ዋናው ይዘት ይህ ሲመስል በመጨረሻም ከምንገኝበት ኣስከፊ ሁኔታ መውጣት የምንችልበትን ገንቢ ሓሳቦች ገብሩ በሚገባ ሰንዝረዋል።

 

የብዙ ሰው ዓይን ከፋች የሆነው፣ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን የሚያህሉ ትላልቅ ሃገራዊ ርእሰ ጉዳዮች በጥልቀት ተተንትነው መቅረባቸው ስለ ሃገሩ ሉዓላዊነትና ስለ ዴሞክራሲ ለሚጨነቅ ሁሉ ገብሩ ትልቅ ስጦታ ኣበርክተዋል። መፅሓፉ በዋናነት ለትውልድ የሚተርፍ ነው። ሆኖም፣ ማንም መፅሓፍ ፍፁም ኣይሆንምና ኣልፎ ኣልፎ ግድፈቶች መስለው የታዩኝን ኣንድ-ሁለት ነጥቦች ማንሳት እወዳለሁ።

 

1ኛ/ ቃለ-ምልልስ ኣለመጠቀም፣

ውስብስብ ታሪክ ያዘለና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መፅሓፍ በበርካታ ዋቢ መፃሕፍትና ጥቂት ሰነዶች ቢሸኝም ቅሉ፣ በዛ ረጅም ውጣ ውረድ ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊ የነበሩትን (ሃገር ቤትም ባእድ ሃገርም የሚገኙትን) ነባር ኣባላት በማነጋገር ለቀረበው ይዘትና ትንታኔ ቃላቸውን ቢያክሉበት፣ ሚዛናዊነቱን በይበልጥ ከማጉላቱ በላይ ግድፈቶችንም ይሞላ ነበር እላለሁ። ይህ ግድፈት የፈጠረው ክፍተት የራሴ ገጠመኝን በማውሳት በሁለት/ሶስት ኣብነቶች ላስረዳ፣

 

ለምሳሌ፣ በገፅ 71 “ ከኢዴሕ ጋር የተካረሩ ውግያዎችን በምናካሂድበት በ1969 ዓ/ም በጋ ላይ ኣረጋዊ በርሄ ሽሬ እንዳስላሴ ገብቶ ከደርግ ባለስልጣናት ጋር እንደተነጋገረ … ተኩሉ ሃዋዝ (ኣሁን በህይወት የሌለ) ነገረኝ …እስካሁን ከኣረጋዊ የቀረበ ይፋዊ መግለጫ የለም” ይላል። ገብሩ ከኣረጋዊ ጋር በዚህና በሌላ ትላልቅ ጉዳዮች ላይ ቃለ-ምልልስ ቢያድርግ ኖሮ እውነታውን በቀላሉ ሊያገኘው ይችል ነበር። ይሁንና ላነሳው ጥያቄ መልሱ ‘ኣዎን ተነጋግሬ ነበር’ ነው።

ሁኔታውን ማወቅ ለፈለገ ባጭሩ እንዲህ ነበር፣ በኢድሕ ግስጋሴ ስጋት ያደረበት፣  ሽሬ የመሸገው የደርግ ጦር ኣዛዥ እንገናኝ በሚል ያገሩ ሽማግሌ ላከብን። ምዕራብ ግንባር የነበርነው ኣመራር (ስብሓት ነጋን ጨምሮ) በጉዳዩ መከርን። ግንኙነቱ ትጥቅ ያስገኝልናል ከሚል መላምት እኔ እንዳገኘው ተወሰነ፤ ከተማው ጥግ ተገናኘን። ባጭሩ እሱ በተሎ ትጥቅ ሊያቀርብልን እንደማይቻለው፣ እኔም የሁለታችን ስምሪት ማቀናጀት እንደማይቻል ሓሳብ ተለዋውጠን በዚሁ ተለያየን፣ ግንኙነቱም እዛው ኣበቃ። ለገብሩ “በወቅቱ የማይታሰበው ውይይት” ለኛ ግን ታሳቢ ነበር።

 

በጭንቀት መኖር የተገደደው ደርግ ከዛ በኃላም ሊገናኘን ሞክሮ ኣልተሳካለትም። ዝርዝሩ የፈለገ ጠይቆ መረዳት መብቱ ነው።

 

2ኛ/ ቁምነገሩን የሚያስት የቃላት ኣጠቃቀም፡

እዚህ ላይ ተራ ቃላት የሚመስሉ 2 ኣምሮች (ኮንሰፕትስ)፣  ግርግር እና ማፈግፈግ (በሞራላዊ ወይም በዲፕሎማሲያዊ እሳቤ ተጠቅሞ ሊሆን ይችላል) ፣ ኣለቦታቸው ገብተው  እውነታውን እንዴት እንደቀየሩት ኣሳያለሁ።

 

ሀ/ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ታጋይ ተኽሉ ሃዋዝ “… በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ በእስር ቤት በተፈጠረ ግርግር ሕይወቱ ኣልፏል” ይላል (ገጽ 151)። በግርግር ሕይወቱ ኣልፏል ሲል እንደ ኣጋጣሚ፣ በትርምስ፣ ሳይታሰብ ሞተ ለማለት ይመስላል። ሃቁ ግን ሆን ተብሎ ነው የተገደለው። የተለየ ኣቛም ስለ ያዘ ተገደለ ማለቱ ይበቃ ነበር፣ ያልታሰበበት ከማስመሰል።

እንደገና የማእከላይ ኮሚቴ ተወካይ የነበረው ሸዊት ዳኘውም በዚሁ መልክ “… እስር ተበይኖበት እዛው በተነሳ ግርግር የድርጅቱ ሰለባ ሆነዋል” ይላል (ገጽ 90)። ሸዊት የግርግር ሰለባ ኣልነበረም፣ ሃቁ የመለስ ጥቃት ሰለባ እንጂ።

 

ለ/ በሶስት ቦታ (ገጽ 108፣ 113 እና 114) መለስ ዜናዊ ከጦርነት ማፈግፈጉና ሂስ እንደደረሰበት ይተርካል። ማፈግፈግ በወታደራዊ ስምሪት፣ ተመክሮበት የሚፈፀም ስልታዊ ንቅናቄ ነው፣ ሂስም ቅጣትም ኣያስከትልም። ከጦርነት ቀጠና መሸሽ ግን ሂስም ቅጣትም ያስከትላል። ተቀጥቷልም። በመለስ ላይ ኣመራሩ የበየነው ቅጣት ኣነሰ ተብሎ ያኔ ለተከሰተው ቀውስ (ሕንፍሽፍሽ) ኣንዱ ምክንያት እንደነበረም ማከሉ ሃቁን ያጎላዋል። ስለዚህ ታሪኩ እንዳይዛባ ኣለቦታው የገባው ኣፈገፈገ ፣ የሚለው ኣምር ሸሸ ወይም ሸሽቶ በሚለው ቃል መተካት ይኖርበታል።

 

3ኛ / በድርቅ ዙርያ ትልቅ ግድፈት

የ1977 ዓ/ም ድርቅ በህዝቦቻችን ላይ ያደረሰው ኣሰቃቂ እልቂት ፣ የሻዕብያ ኢ-ሰብኣዊነት ተጨምሮበት ምን ያህል ፈታኝ እንደነበረና የተደረጉ “ጥረቶች” በሰፊው ተብራርተዋል። ሆኖም እዚህ ላይ ሁለት የሚከነክኑ ዓበይት ጉዳዮች ተዘለዋል።

 

ኣንደኛው/ በዛ ቀውጢ ወቅት ማሌሊት ለተባለው ጤዛ ድርጅት ምስረታ ተብሎ ሁሉም የህወሓት ካድሬዎች ከነኣመራሩ ኣንድ ወር ሙሉ በድግስ ሲንንበሸበሽና ስንዘፍን መክረማችን፣ ኣፄ ሃ/ስላሴንና ደርግን በተመሳሳይ ኣስነዋሪ ድርጊት እንዳላወገዝን ሁሉ !!!

 

ሁለተኛ\ እና ዋናው ያኔ በድርቁ ምክንያት ከተሰበሰበው 100 (ኣንድ መቶ) ሚልዮን ብር 50% ማሌሊትን ማጠናከርያ፣ 45% ህወሓትን መደጎምያ፣ 5% ብቻ በድርቅ ለሚጠቃው ህዝብ በማእከላይ ኮሚቴው ስብሰባ መመደቡና ድርጊቱ የግፍ ግፍ መሆኑ ኣልተጠቀሱም። ይህ የበጀት ምደባ በኣብዝሃው ማ\ኮሚቴው ስብሰባ ጸድቆ፣  ቃለ ጉባኤውም በጽሑፍ ሰፍሮ፣ በቴፕ ተቀድቶ በህወሓት ሰነዶች ማእከል ይገኛል። ከህወሓት ፋይሎች ኣልፎም የዓለምኣቀፍ የረድኤት ማሕበራት፣ እንደነ ቢቢሲ የሚድያ ተቋማትን ኣሁንም እያተራመሰ ይገኛል። በግለሰብ ደረጃም ታዋቂው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ማርቲን ፕላውት፣  ዘፋኙ ቦብ ጌልዶፍ፣ ኢኮኖሚስቱ ፕሮፌሰር ደስታ ኣሳየኸኝ፣ ወዘተ ኣሁንም ይተቹበታል። “ኣህያውን ፈርተው ዳውላውን” እንዲሉ ገብሩ በጋራ ህዝባችን ላይ የደረሰው ጭካኔን ኣጉልቶ የሚያሳየው ትልቁ ነጥብ (ባእዳን ኣሁንም የሚነታረኩበት) ትቶ ስለተከናወኑ “መልካም” ነገሮች ብቻ መተረኩ ጭራሽ ኣልገባኝም።

 

ይህ ነውረኛ የበጀት ምደባ ኣስመልክቶ ኣምባሳደር-ነበር ኣውዓሎም ወልዱ ለኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ 27 ጥቅምት 2003 ዓ\ም ገጽ 21 ላይ ባሰፈረው መረጃ፣ “ 35% ለህዝቡ፣ 65% ለድርጅቱ ተከፋፍለዋል” ያለውን የተሻለ ጥቆማ ቢሆንም በቃለ ጉባኤው ከሰፈረው ሃቅ ጋር ግን ኣይጣጣምም። ስለዚህ ይህ ጉዳይ በድርቅ የተጠበሱት ሚልዮኖችን የሚመለከት፣ ላንዳንዱም መራር ትዝታ ስለሆነ ተስተካክሎ ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥበት ከወዲሁ ኣቶ ገብሩን ኣሳስባለሁ። ዋናው ቁምነገሩ ያለፈውን ጥፋት በግልፅ በማየት ይህ ዓይነት በደል ለወደፊቱ እንዳይደገም ለማድረግ ነው።

 

4ኛ/ ወደ ዝርዝር ሳልገባ፣ ከወደ ኃላ የተወራለት ወታደራዊ መመርያ (“ዶክትሪን”) በምንም መልኩ እንዳልታየ፣ በከተማ የተነደፈው የመጀመርያው የድርጅቱ ፕሮግራም እንደነበረና ቅጂው ኣሁንም እንደሚገኝ፣ ስለ የኢህኣፓ ምርኮኞች ኣያያዝ የቆየው የህወሓት ምርኮኛ ኣያያዝ ደንብ እንዳልተከተለ፣ ከግድፈቶች ተርታ ሊጨመሩ የሚችሉ ኣብነቶች ናቸው።

 

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ግድፈቶች ስጠቁም ዋናውን ርእሰ ጉዳይ፣  ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን ኣስመልክቶ ለቀረበው ሰፊና ጥልቅ ጥናታዊ ዘገባ፣ ላይ ምንም ዓይነት ኣሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራሉ ከሚል እንዳልሆነ ላረጋግጥ እወዳለሁ። እንዳውም ለዚህ ትልቅ ሃገራዊ ጉዳይ፣ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ ተብሎ ለተደረሰው መጽሃፍ ከሚቀርቡ ኣሉታዊ ትችቶች በተመለከተ ኣንድ ሁለት ነጥቦች ላክል።

 

የመጽሓፉ ርእስ ብሎም ይዘት ከጅምሩ እስከ ማብቂያው በሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ያጠነጠነ ሆኖ እያለ ኣንዳንድ ”ተቺዎች”፣ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ፣ በሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ላይ ኣንድም ቃል ሳይተነፍሱ በደራሲው ስብእና ላይ የባጡን የቆጡን ሲደረድሩ ይታያሉ።  ሃተታቸው ተጠቃሎ ሲታይ፣ ለምን ተሳስቸ ነበር ትላለህ ? ለምን ድርጅታችን ሲሳሳት ነበር፣ ኣሁንም እየሳሳተ ነው ትላለህ ? መሪዎቻችንን ለምን ታጋልጣለህ ? የሚሉ ናቸው። 1ኛ ነገር የማይሳሳት ድንጋይ ብቻ ነው፣ 2ኛ/ ስሕተትን ማየትና ሌላው እንዲማርበት ማድረግ ብልህነት ነው፣ 3ኛ/ ስሕተቱንና ችግሩን ተገንዝቦ እርማት የሚሰነዝር ሰው ኣርቆ ኣሳቢ ነውና ለነዛ ዓይነቱ “ተቺዎች” ዝርዝር መልስ ሳልሰጥ ባጭሩ ግን ለድርጅትና ለመሪዎቹ ጥብቅና ከመቆም ይልቅ ለሃገርና ለህዝብ ማስቀደም ይሻላል እላለሁ።

 

ጭራሽ የሚገርመው ደግሞ ሳያነቡ የሚተቹ “መሪዎች” መከሰታቸው ነው። ከነዚህ ኣንዱ –  ጠንቋይ ኣይሉት ነብይ  – ስብሃት ነጋ ነው። ለዚህ ሰውም የምለው ነገር ካለ “የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ኣላስደፈርኩም፣ ዴሞክራሲን ኣልረገጥኩም” ብለህ የኣንዲት ገፅ ፅሑፍ ኣቅርብ ብቻ ነው።

 

በቁምነገር መታየት ያለበት ሌላው ነገር፣ ገብሩ በመፍትሄነት ከሰነዘራቸው ዓበይት ነጥቦች ኣንዱ “ኢትዮጵያዊነትና የብሄረሰብ መብቶች ኣይነጣጠሉም” በማለቱ የሚወርዱትን የተቃውሞ ትችቶችን ይመለከታል። እነዚሀ ተቺዎች ጭራሽ የብሄረሰብ መብት ብሎ መነሳት የለበትም፣ የግለ ሰብ መብት መከበር ብቻ በቂ ነው። የብሄረሰብ መብት  ማስተናገድ ኢትዮጵያዊነትን ያዳክማል ወይም ይበታትናል ባዮች ናቸው። ይህ ዓይነቱ ሙግት በሌላ ጊዜም ተደጋግሞ ይሰማል። ፖለቲከኞችም ለተለያየ ዓላማ ይጠቀሙበታል። ሆኖም ይህ ኣመለካከት ማህበረሰባዊ ዕድገትን፣ ታሪክንና በመሬት ላይ ያለው ሃቅን ካለማንፀባረቁ ባሻገር የባሰ ብተና ወይም ቀጣይ ቀውስ እንጂ መፍትሄ ኣያመጣም። ለምን?

 

የግለሰብ መብት የግድ መረጋገጥ ያለበት ተፈጥሮኣዊም ፖለቲካዊም መብት መሆኑ ኣያጠያይቅም። ያለ የግለሰብ መብት መከበር፣ ዕድገት (ስልጣኔም ይሁን ፈጠራ) ኣይኖርምና። ይህ የግለሰብ መብት በኢትዮጵያችን ከተረገጠ ቆይተዋል። ዛሬ ግለሰቡ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሳይሆን የኢህኣዴግ ጢሰኛ (ሳብጀከት) ወደ መሆን ወርዷል። ለዚህም ነው ሁዋላ ቀርነት መለያችን ሆኖ ያለው።

 

የግለሰብ መብት ሲባል ግን ይዘትና መልክ የሰጠው ማን ነው ብሎ መጠየቅ የግድ ይላል። የግለሰብ መብት ይሁን እንደ ግለሰብ መኖር ራሱ ትርጉም የሚያገኘው በማሕበረሰቡ ከለላ ውስጥ ሆኖ ነው። ከማሕበረሰቡ ውጭ ግለሰቡ እንደ ሰው መኖርም ማደግም ኣይችልም። በእንሰሳት ማህል ያደገ ህፃን ከሰው የተወለደ ቢሆንም የእንሰሳቱ ጠባይ እንደሚይዝ ማስረጃዎች ኣልጠፉም። ስለዚህ ግለሰብና ማሕበረሰቡ ካስተሳሰብም ይሁን ከመብት ኣኳያ ነጣጥሎ ማየቱ ትክክል ኣይሆንም። የኢትዮጵያ ህዝብ ሲባል የተነጣጠለ ግለሰብ ድምር ማለት ሳይሆን ግለሰቡን ኢትዮጵያዊ ሰው ያደረገው ውስብስቡ ማሕበራዊው ስብስብ ጭምር ነው። የማሕበራዊው ስብስብ ኣንዱ ኣካል ብሄረሰብ (ወይም “ጎሳ”) ነው። ወረድ ካለም ቤተሰብ ይገኛል።

 

እንግዲህ ኣንድ ግለሰብ በሃገሩ መብቱን ሲነጠቅና መብቱን ለማስጠበቅ ዓቅም ሲያጣ፣ ተወደደም ተጠላ የሱን ዓይነት ችግር ከደረሰባቸውና ከሚመሳሰሉት ጋር ተሰባስቦ፣ ሓይል ፈጥሮ መብቱን ለማስከበር መፍጨርጨሩ ተፈጥሮኣዊም ዝንተሞገታዊም ሂደት ነው። ይህ ክስተት ድሮም ኣሁንም ኣለ። ኣድልዎ እስካለ ድረስ ወደ ፊትም ይኖራል። በዚህ ታሪካዊ ማዕቀብ (ኮንቴክስት) ስር ስንገነዘበው፣ የግለሰብና የማሕበረሰብ ትስስር እንደማይነጣጠሉ ሁሉ፣ ኢትዮጵያዊነትና የብሄረሰቦችዋ ህልውናም ይሁን መብት ተነጣጥሎ መታየት ኣይኖርበትም። ምናልባት የብሄረሰብ ወይም “ጎሳ” ህልውና ከነጭራሹ ካልካዱ ወይም ካልናቁት በስተቀር።

 

በማጠቃለል፣ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ዋናዎቹ የህዝብ እሴቶች እንደመሆናቸው መጠን እነዚህን እሴቶች ማእከል በማድረግ ባለፈው ሩብ ክፍለ-ዘመን ኢትዮጵያ ፊት የተደቀኑ ችግሮችና ህዝቡ ያጋጠሙት ፈተናዎች ኣቶ ገብሩ በጥልቀት ኣቅርበዋል። የሃገር ሉዓላዊነትና የህዝብ ዴሞክራሲ መብቶች የጋራ እሴቶች ሆኖው በጋራ ሓላፊነት ሊጠበቁ ሲገባ ነገር ግን ኣንድ ግለሰብና ግብረ-ኣበሮቹ እጅ ላይ ወድቀው የደረሰው ፍዳ ኣሁንም እንዳላበራ በስፋት ዘርዝረዋል። ከዚህም ባሻገር ከገባንበት የቀውስ ኣዙሪት መውጫውና ዘላቂ መፍትሄ የምንቀዳጅበት ብልሃቱ ኣመላክተዋል። ይኸውም ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲን የሚከበርበት ህዝቡ የሚቆጣጠረው የጋራ ስርዓት በቅድሚያ መመስረት ነው።

 

ኣቶ ገብሩ ለራሱ ሳይሳሳ፣ ሃገርንና ህዝብ በማስቀደም ለፍቶ ላቀረበልን ትልቅ መፅሓፍ ያን ያክል ምስጋና ይገባዋል።

 

ኣረጋዊ በርሄ

14.01.2015

ዘ-ሄግ

 

  የተውኔት አውራ –የሀገር ባንዴራ። -ከሥርጉተ ሥላሴ 1

$
0
0

16.01.2015 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/

„ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ሰው ያልተመለከተ ሰው ምስጉን ነው።“

/ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 40 ቁጥር 4/

እንደ እርእሱ ነው ተፈጥሮው። እንደ እርእሱ ነው ጸጋው። ውድ በጣም ውድ ነው ለሥነ ጥበብ ነፍስ። ክብር ልዩ ክብር ነው – ለታሪክ። ፍቅር ልዩ ፍቅር ነው – ለትውፊት። ጌጥ ልዩ ጌጥ ነው – ለትውልድ። ሩህ ነው ለጥበብ ዓውደ ምህረት – ለመድረክ። የታሪክ ዝማሬ ነው – ለመድረክ ድባብ። – አዛውንቱ የተግባር – ጋሼ ደበበ እሸቱ።

ግን እንሆ እንዲህ ሆነ ————በጦሮ።

ዘመኑ በካቴና፤ ምስጋናው – በእግር ብረት፤ ክብሩ – በስጋት፤ ዬጌጥነቱን – መንፈስ በምስማር – በችካል በመብሳት፤ ውለታው – በግዞት ተወራራደ በዘመነ እሾኽ – በወያኔ።

ታላቁ አርቲስት ጋሼ ደበበ እሸቱ መክሊቱ ቀንድ፤ ቀንድነቱ ደግሞ የአህጉር ሆኖ ሳለ እንደ ትቢያ ታይቶ በትዕቢት – ደቀቀ። ብቃቱ የሰማይ፤ ሥጦታው የመዳህኒተአለም ሆነ ግን በወያኔ አቧራ ለበሰ።

ውሰጡ ሻማ፤ ስጦታው የዘለዓለም – ማሾ፤ ህሊናው እራስ እግሩ ፍሬ ሆኖ፤ ነገር ግን በደፋሩ ወያኔ ታምሩ በዱላ ተቀጠቀጠ። ጋሼ ጸጋዬ የተውኔት አውራ ብቻ አልነበረም – የዘመንም እንጂ። ጋሼ ደበበ አውራነቱ ለሥነ ጥበብ ብቻ ሳይሆን ለሰብዕዊ መብት መከበርም ጭምር አንጂ። የሰብዕዊ መብት ተሟጋችነት ጸጋው በቁሙ ጻድቅ ነው። መከራን ለብዙኃን ፍቅር ሲል ፈቅዶ አብዝቶ የተቀበለ።

DEBEBE„የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ናት“ / ምሳሌ ምዕራፍ 20 ቁጥር 15/ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ ሞገዳማ ድምጹ የምህረት መሰላል ነበር። ያ ውስጥን ዳሳሽ ድምጹ የብሥራት ነጋሪ ነበር። ተናፋቂው ድምጹ የፈውስ ደወል ነበር። የማይጠገበው ድምጹ የምሽት ማህሌት ነበር። ድምጹ ከጸጋው ጋር ለኢትዮጵያ የኤዶም ሽልማት ነበር። ጋሼ ደበበና መድረክ፤ መድረክና ጋሼ ደበበ ደግሞ ሌሊኛ የቅኔ ግጥሞች – የመንፈስ ልዑቅ ቋንቋዎች ነበሩ። ለመደረክ ጋሼ ደበበ – ጋሼ ደበበን ደግሞ ለመደረክ ፈጣሪ መርቆና ቀድሶ ፈጣራቸው – ግን በፋሽስት ወያኔ የሰማይ ስጦታ ዕሴት አልባ ሆኖ እንሆ ጨለማ ተገመደለበት።

አዲስ አበባ ውስጥ ሰፊ ዬአማተር ከያንያን ክበቦች ነበሩ። እንዲያውም የታላቁ የሥነ ተውኔት ጸሐይ የጋሼ ወጋዬሁ ንጋቱ  የሙት ዓመት 5ኛ ዓመት ሲከበር እኔ „እሱ ማነው“ በሚለው ግጥሜ አሸንፌ ብሄራዊ ቲያትር የግጥሜን አቮል አቅርቤ ነበር። አዘጋጁ „የወጋዬሁ አማተር የተዋናይ ክበብ ነበር“ የውድድሩን ዕድሉ አቀናባሪው ደግሞ የአዲስ አበባ የባህልና ስፖርት ቢሮ ነበር። ዝግጅቱ እጅግ ማራኪና ውብ ነበር። በዛ በማይጠገበው የብሄራዊ ቲያትር አዳራሽ ታዳሚው ሙሉዑ ነበር። አዛውንት የጥበቡ አባና እማ ወራዎች በክብር ተገኝተውበትም ነበር። ታዲያ ያን ጊዜ ያን የመሰለ ተግባር ይፈጽሙ የነበሩ ክበቦች ዛሬ ምን በላቸው? ለመሆኑ አንድ ቀን ሰብሰብ ብለው ሄደው ግንዱን – ዋርካውን የሥነ ጥበብ ዋርካ አይተውት ያውቁ ይሆን? የጋሼ ደበበ ቀንን ለማክበርስ ምን አድርገው ያውቁ ይሆን? ጋሼ ደበበ አይደገመም። ኮፒ የለውም። ሥጦታ ነው የእኛ። በከፋው ቀን፤ ቀን በተደፋበት ጊዜ ከጎኑ ለመሆን ቀጣይ ከያንያን ምን ያስቡ ይሆን? የጥበብ ቤተኞች ቱግ ብለው የሚፈሉት ለእነሱ ሲቀርባቸው ሳይሆን ሥነ ጥበብ ከነ ሙሉአካሉ ሲታሰር፣ ሲንገላታ፣ ሲገደል፣ ሲሳደድ፣ ሲሞት፣ ሲቀበር፣ መራራን ዘመን ሲጠጣ  መሆን አለበት ባይም ነኝ – እኔው። ጸሐፍትም የጥበብ ቤተኛ ናቸው። እግር ብረቱ እነሱንም ዕለት – ተዕለት ሲለቅማቸው አደቡ እስከመቼ ይሆን? ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ጥበብ የሚባለው ነገርም ወይነ?! መገላበጥ መቼስ ዘመን ሰጥቶት ዬለ …

ዛሬ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ከያንያን – ህዝብ ለሚሳጣቸው አቻ የለሽ ፍቅር ውለታው እኮ ፈጣሪያቸው ለሰጣቸው ጸጋ መንገድ ጠራጊዎቻቸውን ዕንባ ሲጋሩ ነበር። ግን ኮሽ የሚል ነገር የለም። በቃ ጭር ጸጥ ረጭ። ጦሩ ለእኔ ካልተመዘዘ በማለት ዘግቶ  – መቀመጥን የመረጡ ይመስላል። አልፍ ብሎም ገዳይን ማወደስ ማድነቅ ማቆለበባስ ….ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል። ይህ እውነት ለመናገር ኢትዮጵያዊነት ተረግጦ ጎጠኛን ማሞጋገስ ለእኔ ኢትዮጵያን የመጠቅጠቅ ያህል ነው። ለዛውም ፍርፋሪ ለማይገኝበት – በጎሬጥ ለሚታይበት ዘመን። በአይመለከተኝም መስመርስ ተሂዶ የጥበብ ቤተኝነት አባልነት ወይንስ ደባልነት – ለሆድነት?

ዬት ይሆን ያሉት – አነዚህ ተተኪ የጥበብ ዕንቡጦች? ከቶ ዬት ይሆን አድራሻቸው? ለነገሩ ዝንቅንቅ ብሎ ጸጋ ሳይሆን ቅመሙ መለያው – መስፈሪያው – ማንዘርዘሪያው – ዘመንተኝነት ሆኗል። የሆኖ ሁኖ ግን አምልጠው የወጡት ግን ፊት ለፊት ወጥተው በሚገባም ተደራጅትው ገዢውን ስንክሳር – ሊሟገቱት ይገባል። ሰንደቃችን – ምሳሌያችን አባት ደበበን ሊያስቡት፤ ሊያስታውሱት፤ አውዳዓመት ሲደርስ ሄደው ሊጠይቁትና የተቀነባበረ ተግባር ሊከውኑ ይገባል። በተጨማሪም ማን ጌታ አለባቸው አካውንታቸው ላይ ፎቶውን ቢለጥፉት – ቤታቸው ውስጥ በፍሬም ቢያስቀምጡት ክብር ነው – ረድኤት ነው- አደራንም መወጣት – ምርቃትም።

ከሰሞናቱ ፈረንሳይ ውስጥ አንድ አስቃቂ ሀዘን ተፈጸመ – ለሶስት ተከታታይ ቀናት። በአንድ የህዝብ ልሳን በሆነ ላይ „አሸባሪዎች“ ወንጀል ፈጸሙ። በተከታታይ ሶስት ቀናት ፈረንሳይ በሃዘን – በምጥ ላይ ነበረች ከጥር 7 – 9። በ11.01.02 ከ50 በላይ የሚሆኑ የሌላ ሀገር ጠቅላይ ሚ/ሮች የመንግሥት ተወካዮች 100000 ታዳሚዎች ብሄራዊ ዓለምዐቀፋዊ የሶሊዳሪቲ ስልፍ ነበር „እኔም ሻርሊ ነኝ፤ እኔም ይሁዳዊ ነኝ፤ የሃሳብ ነፃነት ይከበር፤ የፕሬስ ነፃነት ይከበር፤ የሃይማኖት መቻቻል ይበልጽግ“ በማለት ከሁለኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የታዬ መጠነ ሰፊ የህዝብ ቁጣና የሀዘን ቀን ነበር። በህንድ፣ በጀርምን በተለዬ ሁኔታ፤ በእንግሊዚም ተማሳሳይ የወዳጅነት ሰልፍ ነበር … ይህን ጥቃት የደረሰበትን መጋዚን ለማጋዝም ሚሊዮኖች ተሰልፈዋል። እኛ ጋር ሲመጣ ሌላ ነው። በ2012 „ፍትህ“ ጋዜጣ 30000 ህትምት ስትቃጠል በጎኑ ዬመቆም አቅሙ ምን ያህል ነበር? የብዕር ውጤት ምርቶች ሲታገዱ አምራች ህሊናዎች ሲንገላቱ፤ ሲታሰሩ፤ ሲሰቃዩ ህዝቡም ሆነ ዋና የጥበብ ቤተኛው ታዳሚው ኮሽ አይልም። 30 ሺህ የፍትህ እትም መቃጠል ማለት በአማካኝ በስሌት አንድ ህትምት ቢያንስ በመዋዋስ 5 ሰው ያነበዋል። በማዕካለዊ ግምት ሲሰላ 150000 ሰው መንፈስ አብሮ ተቃጥሏል። ለዛውም የሆነውን እውነት ነገር በመጻፉ። ከዛም የተለያዩ ሙከራዎች አድርጎ ታታሪ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንፈሱ – ብቃቱ እግር ብርት ሆነ። ጭራሽ ስንቅ እንዳይገባለት ከቤተሰብ እንዳይገናኝ ተወሰነ። እውነት በቲያትር፤ በፊልም፤ በሙዚቃ፤ በሥነ ጹሑፍ በጸሐፊነት፤ በገጣሚነት፤ የተሰማራው ቤተኛ ሁሉ ጥበብ ቀብር ላይ ሆኖ እንዴት እንቅልፍ ወስዶት እንደሚያድር ሳስበው መተንፈስ ያቅተኛል – የእውነት። የጥበብን ጽኑ ጣር መስማት ያልቻለ ጆሮ ምን ይሁን ትላላችሁ – ክብሮቼ?

ሥነ – ጥበብ ዓለምነቷ የራሷመርህ ብቻ ሳይሆን የራሷ ፕላኔት ያላት ከመሆኑ ላይ ነው፤ ሥናዊቱ ሃይማኖት ጥበብ ህገመንግሥት ያላት፤ የሥምረት ማዕዶት ናት። ኪናዊቱ – ማናቸውንም ግርዶሽ ሁሉ ፈነቃቅላ እራሷን የመግለጽ የኤደን አቅም አላት። ልዕልት ጸሐይ ጉምን አሸንፋ ተወዳዳሪ የለሽ የኃይል ምንጭ እንደ ሆነች ሁሉ ጥበብ የአቅም ምጣኔ ባንክ ናት። የብቃት መጠለያ ናት። ኪዳን ናት – ውል። ማተብ ናት – ዕምነት። ሁሉን ለመጋራት የፈቀደች ወላጅ እናት ናት – አናት። ታዲያ አዛውንቱ አንድ ዕጣ ነፍሱን የቀረው ታላቅ ብርሃን – ዬትውልድ በ100 ዓመት ሊተካ የማይችለው የትዕይንት ንጉሥ ጨለማ ውስጥ ሆኖ እንዴት ስለእሱ ተቆርቋሪ ቀንጣ የሥነ – ጥበብ ክበብ፤ ቆራጥና ደፋር አርበኛ በባዕት ይታጣ?! አይጎረብጥም? ትንሺ ብጣቂ ሰለምታ በወል መላክ እንኳን ሳይቻል፤ ለተቋምነትህ እናመሰግንሃለን ሳይባል የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና አንድ ነገር ቢሆን ለወጣት ተዋናይ የህሊና ረመጥ አይሆንም?! ታሪክስ ትውፊትስ አይራገመሙም? አስተውሉ ….. እነ ኮበል እነ ሸበላ እባካችሁ ….. ን። ጥበብን አስቡ – መንፈሳችሁን – አነቃንቁት …. ለጥበብ ነፃነት አደባባይ ውጡ – ደጋፊዎቻችሁን፤ አድናቂዎቻችሁንም አሰልፉ — ዕልፍናችሁና ዕልፍነታችሁን በተግባር እልፍ አድርጉት እንጂ የምን ተኝቶ በለኝ ነው¡

ወያኔ እንደ ሆነ ድልድይ መስበር አመሉ ነው። የተፈጠረውም  ሆነ የሰለጠነው መንገድ ለማፈረስ ነው። ይህን ምኞቱን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይፈጽመዋል። ጋሼ ደበበ ባይታሰር ስንት ወጣቶች በብሄራዊ ስሜት ጥበብን አልቀው፤ ጥበብን እንደ ተፈጥሮው አቅልመው መቅረጽ የሚችሉ የነገ ጽጌረዳዎችን ባፈራ ነበር። ይህም ተፈርቶ ነው የታሰረው። ለአንድ ታላቅ ብልጹግ የሥነ ጥበብ አባዎራ – እማወራ አንድ ቀን ብዙ፣ እጅግ ብዙ ምርት የሚታፈስበት ዕለቱ ነው። እንኳንስ —- አስሉት ከ97 ጀምሮ ያሉትን ጊዜያቶች ….. ሥንት ዕንቡጥ የተውኔት ለጋ ኮሽ ብሎ ደርቆ እንደ ረገፈ፤ ተስፋ በግፍ ተነቀለ፤ ፍቅር ከፍቅረኛው ታገደ …. ያቆስላል። መድርክም ደም አማጣች! ይህን ፍሬ ነገር የነገ የተስፋ ተስፋዎች ከልብ ሆናችሁ አስሉት – አንሰላስሉት …. እናም ወስኑ ነገን ለማግኘት እባካችሁን ቁረጡ?! ለጥበብ አደራ ብቁ ወታደር ሁኑ። በራችሁ እሲኪንኳኳ ድረስ አትጠበቁ …. ተንቀሳቀሱ! ፍጠኑ! ትንሽ ተነቃነቁ ጅም ነገር አድርጉ! …. በትንሹ ጀምሩት … ይሄው ሰሞናቱ ዘመነ አስተርዮ ነው። ቃና ዘገሊላ ታምር የተመሰጠረበት።  …. እሰኪ ፖስት ካርድ ላይ ፊርማ አሰባስባችሁ እንኳን አደረሰህ አባታችን በሉት። የ5 ወይንም የ10 ወገኖቹ ሊሆን ይችላል። ብጣቂ ቁራሽ ሳቅ እስኪ ውስዱለት። እንወድሃለን፤ እናከብርሃለን ተክሊላችን ነህ እስኪ በሉት አፋችሁን ሞልታችሁ፤ ድፈሩ! መንፈሳችሁን አደላድላችሁ – ፍላጎታችሁን ፈጽሙ። ጨው አይዳላችሁ አትማሙ – እሰኪ ተስፋነታችሁን  ጀምሩት፤ እኛም ተስፋ እንዲኖረን አድርጉን። አሉልን – አሉልን – አሉልን እንበል። መታሰር ይኖራል፤ መገፋት ይኖራል፤ መሳደድ ይኖራል። „ከድምጽችን ይሰማም ተማሩ! ለሰማይው ጸጋችሁ ፍትኃት ቁረጡ – ወስኑ – ከድርጊት ጋር ከትሙ። ከመከራ በስተጀርባ ታላቅ ክብር አለ። መከራ በበዛ ቁጥር መጪው ቀን ብሩህ እንዲሚሆን ያበስራል።

ጥበብ ተናገረች – መርሄ ነው ብላ

ልቧነን አውጥቶ ካቴና ሲባላ፤

ጥበብ ታውጃላች – ተከተሉት ብላ

ሥነ ህግን – ገላ።

ጥበብ – ሠራች ባላ

የመሆን – አዝመራ!

እኔም ተቀበልኩኝ

እሺ አልኩኝ፤ እሺ አልኩኝ —-

ለእሱ  – ይሁንልኝ

ለመንፈስ ሁነኛ

መገኛ – መዳኛ፤

የሆነልን  – ዬእኛ – ለእኛ።  /05.01.2015 ሲዊዘርላንድ – ቪንተርቱር/

እንሆ – „የታላቋ ትግራይ ህልም“ ሁለመናን ያሳድዳል፤ ሁለንትናን – ይቀማል። ዘመቻው ጥልቅ ስትራቴጁም ስውር – ነውር። በተከታታይና በትጋት ዬትውልድን ውርርስ ሃብት ለመከተር ዋርካ ይነቀላል፤ የትውፊትን ቀንዱን ይሠበራል – ሴሉም ይገደላል። ድንበር ይጣሳል – ዘረፋም ይጎናል። ስለዚህ ሥር ሰደድ በደል ሥር ነቀል ለውጥን ማለም አለበት – እላለሁ – እኔው። የፍላጎት አቅም ሙያዊ ግዴታን በአግባቡ ከመወጣት ይታፈሳልና። በስተቀር እዬሞቱ መኖር እዬኖሩ መሞት —– ግን ይህ መኖር ወይንስ ምን?!

ጥበብ የእውነት አረበኛ ናት። ጥበብ ለማተቧ ሰማዕት ናት። ጥበብ ዘር ናት። ተከታዮቿ – ቤተኞቿ – አድናቂዎቿም – የዕውነት ሐዋርያ መሆን አለባቸው። ከዚህ ከወጡ ያረጡ ከንቱዎች ናችሁ ብላ ጥበብ እራሷ ትሰርዛቸዋለች። ከሰጠቻቸው እርእስት ሆነ ከጉልማ* መሬታቸውም ትነቅላቸዋለች። ጥበብ ካኮረፈች ወይንም ከተቆጣች ጸጋን እውሃ ሲሄድበት የከረመ አለት የማድረግ አቅሟ ብልህ ነው። ስለምን? ከዕውነት ውጪ ጥበብ አትታሰብም፤ ወይንም ቀና ብላ ጆሮ አትሰጥም። ጥበብ – ታማኝነትን ውጣ፤ ሃቅን አጣጥማ፤ ፈርኃ እግዚአብሄርን የጠበቀች ለ እውነት ያደረች ግማደ መስቀል ናት – ለኑሮ! ኑሮን ፈጥራ – ቀርፃ ጸሐይ ያደረገች የኑሮ ፈርጠ – ጉልላት።

ለሁሉ ዘመን አለው፤ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው“ /መጸሐፈ መክበብ ምዕርፍ 3 ከቁጥር 1 እስከ 2/

ቅኔያችን – ለእኛ የተከበረው የሰባዕዊ መብት ተሟጋችና ታላቁን የጥበብ ሰው  አርቲስት ደበበ እሸቱን አምላካችን ይጠብቅልን። አሜን! ዕድሜውን ሰጥቶት ጸጋውን ይምግበን ዘንድም አምላካችን አዶናይ ይርዳን። አሜን!

በተረፈ ነገ ጥር 17 ቀን ነው። የጀግና ኃይለመድህን አበራ 11ኛ ጀኔባ የገባባት የጀግንነት ወሩ ነው። እሱ የሳሳለት፤ ሁሉን የሰጠው፤ ለነፃነት መንፈስ ሲል ስለሆነ የእሱን ቀን ለተግባሩ ውለታ ለጋሼ ደበብ ይሁን ብዬ ወሰንኩ። ስለ ሀይልዬ ሆነ ቀልብን ሳብ አድርገው በሰነባበቱ ጥቂት ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ያቺው መቼም ቆራጣ ናት አንድ ሰዓት የሚሏት፤ የተቻለውን ያህል ትናንትና  በ15.01. 2015 በነበረው ፕሮግራም Tsegaye Radio ያለው ነበር። እሰኪ ገባ ብላችሁ አዳምጡት ከቻላችሁ። የሃይልዬም አምድ የበኩሉን ከውኗልና።

ይቋጭ – የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። አልገርምም ግን ስስናበት ሰላምታ። ይሁን። ለስላሳ ትህትና ለጀርጋዳ ስንብት እንሆ።

ውዶቼ አንድ ነገር – እሰኪ ሰንበትን በአካውንታችሁ የዚህን የዘመን አውራ ፎቶ መንበሩ ላይ የምትችሉ አስቀምጡት፤ ውስጡን በመንፈስ ብሌን ትክ ብላችሁ እዬት። በዕዝን ህሊና ከንፍርም በፍቅር ዳስሱት። ክብራችን – ጌጣችን – ግርማ ሞገሳችን – ውባችን – ተቆራቋሪያችን – አድባራችን – አለኝታችን – ትምህርት ቤታችን – ተቋማችን፤ የጥበብ ባዕታችን እስኪ በሉት — እንዲያምርባችሁ —– እንዲያምርብን — ሸበላ ሰንበት እንዲሆን ከመንፈሴ ተመኘሁኝ። ፍቅር ስለሆናቸውም ድንበር አልቦሽ – ነፍስ የሆነ ፍቅሬንም እንሆ! መሸቢያ – ሰሞናት- ኑሩልኝ።

*መፍቻ ጉልማ … ከሰፊው የምርት ማሳ ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጧቸው ቁራሽ የግል መሬት ሲሆን። ልጆችም ይህን መሬት በራሳቸው መንገድ አልምተው የፈለጉትን ዘርተው የሚያገኙት ገቢ ለራሳቸው የግል ጉዳይ መፈጸሚያ ወይንም ማስፈጸሚያ ያደርጉታል። ጎጆ ሲወጡም ጎጆ መውጫ ይሆናቸዋል። ሥነ ጥበብ ከሰፊው ማሳው ዘርፈ ብዙ የማይቋረጥ በብዙ መስመሮች ሊገለጽ የሚችል ረቂቅ ጥልቅ የሰማይ መክሊት ሲሆን ለሰው ልጆች የሰማይ ስጦታ ነው። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ የራሱን መክሊት ይዞ ይወለዳልና። እንደ መክሊቱም ህዝብን ዝቅ ብሎ ያገለግልበታል። ግን ችለናልን ወይንስ አደራ በይ ሆነናል ነው ጥያቄው ——

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የተውኔት አውራ –የሀገር ባንዴራ።

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 16.01.2015 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/

„ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ሰው ያልተመለከተ ሰው ምስጉን ነው።“
/ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 40 ቁጥር 4/

እንደ እርእሱ ነው ተፈጥሮው። እንደ እርእሱ ነው ጸጋው። ውድ በጣም ውድ ነው ለሥነ ጥበብ ነፍስ። ክብር ልዩ ክብር ነው – ለታሪክ። ፍቅር ልዩ ፍቅር ነው – ለትውፊት። ጌጥ ልዩ ጌጥ ነው – ለትውልድ። ሩህ ነው ለጥበብ ዓውደ ምህረት – ለመድረክ። የታሪክ ዝማሬ ነው – ለመድረክ ድባብ። – አዛውንቱ የተግባር – ጋሼ ደበበ እሸቱ።
ግን እንሆ እንዲህ ሆነ ————በጦሮ።

ዘመኑ በካቴና፤ ምስጋናው – በእግር ብረት፤ ክብሩ – በስጋት፤ ዬጌጥነቱን – መንፈስ በምስማር – በችካል በመብሳት፤ ውለታው – በግዞት ተወራራደ በዘመነ እሾኽ – በወያኔ።

ታላቁ አርቲስት ጋሼ ደበበ እሸቱ መክሊቱ ቀንድ፤ ቀንድነቱ ደግሞ የአህጉር ሆኖ ሳለ እንደ ትቢያ ታይቶ በትዕቢት – ደቀቀ። ብቃቱ የሰማይ፤ ሥጦታው የመዳህኒተአለም ሆነ ግን በወያኔ አቧራ ለበሰ።

ውሰጡ ሻማ፤ ስጦታው የዘለዓለም – ማሾ፤ ህሊናው እራስ እግሩ ፍሬ ሆኖ፤ ነገር ግን በደፋሩ ወያኔ ታምሩ በዱላ ተቀጠቀጠ። ጋሼ ጸጋዬ የተውኔት አውራ ብቻ አልነበረም – የዘመንም እንጂ። ጋሼ ደበበ አውራነቱ ለሥነ ጥበብ ብቻ ሳይሆን ለሰብዕዊ መብት መከበርም ጭምር አንጂ። የሰብዕዊ መብት ተሟጋችነት ጸጋው በቁሙ ጻድቅ ነው። መከራን ለብዙኃን ፍቅር ሲል ፈቅዶ አብዝቶ የተቀበለ።
„የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ናት“ / ምሳሌ ምዕራፍ 20 ቁጥር 15/ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ ሞገዳማ ድምጹ የምህረት መሰላል ነበር። ያ ውስጥን ዳሳሽ ድምጹ የብሥራት ነጋሪ ነበር። ተናፋቂው ድምጹ የፈውስ ደወል ነበር። የማይጠገበው ድምጹ የምሽት ማህሌት ነበር። ድምጹ ከጸጋው ጋር ለኢትዮጵያ የኤዶም ሽልማት ነበር። ጋሼ ደበበና መድረክ፤ መድረክና ጋሼ ደበበ ደግሞ ሌሊኛ የቅኔ ግጥሞች – የመንፈስ ልዑቅ ቋንቋዎች ነበሩ። ለመደረክ ጋሼ ደበበ – ጋሼ ደበበን ደግሞ ለመደረክ ፈጣሪ መርቆና ቀድሶ ፈጣራቸው – ግን በፋሽስት ወያኔ የሰማይ ስጦታ ዕሴት አልባ ሆኖ እንሆ ጨለማ ተገመደለበት።
አዲስ አበባ ውስጥ ሰፊ ዬአማተር ከያንያን ክበቦች ነበሩ። እንዲያውም የታላቁ የሥነ ተውኔት ጸሐይ የጋሼ ወጋዬሁ ንጋቱ የሙት ዓመት 5ኛ ዓመት ሲከበር እኔ „እሱ ማነው“ በሚለው ግጥሜ አሸንፌ ብሄራዊ ቲያትር የግጥሜን አቮል አቅርቤ ነበር። አዘጋጁ „የወጋዬሁ አማተር የተዋናይ ክበብ ነበር“ የውድድሩን ዕድሉ አቀናባሪው ደግሞ የአዲስ አበባ የባህልና ስፖርት ቢሮ ነበር። ዝግጅቱ እጅግ ማራኪና ውብ ነበር። በዛ በማይጠገበው የብሄራዊ ቲያትር አዳራሽ ታዳሚው ሙሉዑ ነበር። አዛውንት የጥበቡ አባና እማ ወራዎች በክብር ተገኝተውበትም ነበር። ታዲያ ያን ጊዜ ያን የመሰለ ተግባር ይፈጽሙ የነበሩ ክበቦች ዛሬ ምን በላቸው? ለመሆኑ አንድ ቀን ሰብሰብ ብለው ሄደው ግንዱን – ዋርካውን የሥነ ጥበብ ዋርካ አይተውት ያውቁ ይሆን? የጋሼ ደበበ ቀንን ለማክበርስ ምን አድርገው ያውቁ ይሆን? ጋሼ ደበበ አይደገመም። ኮፒ የለውም። ሥጦታ ነው የእኛ። በከፋው ቀን፤ ቀን በተደፋበት ጊዜ ከጎኑ ለመሆን ቀጣይ ከያንያን ምን ያስቡ ይሆን? የጥበብ ቤተኞች ቱግ ብለው የሚፈሉት ለእነሱ ሲቀርባቸው ሳይሆን ሥነ ጥበብ ከነ ሙሉአካሉ ሲታሰር፣ ሲንገላታ፣ ሲገደል፣ ሲሳደድ፣ ሲሞት፣ ሲቀበር፣ መራራን ዘመን ሲጠጣ መሆን አለበት ባይም ነኝ – እኔው። ጸሐፍትም የጥበብ ቤተኛ ናቸው። እግር ብረቱ እነሱንም ዕለት – ተዕለት ሲለቅማቸው አደቡ እስከመቼ ይሆን? ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ጥበብ የሚባለው ነገርም ወይነ?! መገላበጥ መቼስ ዘመን ሰጥቶት ዬለ …
ዛሬ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ከያንያን – ህዝብ ለሚሳጣቸው አቻ የለሽ ፍቅር ውለታው እኮ ፈጣሪያቸው ለሰጣቸው ጸጋ መንገድ ጠራጊዎቻቸውን ዕንባ ሲጋሩ ነበር። ግን ኮሽ የሚል ነገር የለም። በቃ ጭር ጸጥ ረጭ። ጦሩ ለእኔ ካልተመዘዘ በማለት ዘግቶ – መቀመጥን የመረጡ ይመስላል። አልፍ ብሎም ገዳይን ማወደስ ማድነቅ ማቆለበባስ ….ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል። ይህ እውነት ለመናገር ኢትዮጵያዊነት ተረግጦ ጎጠኛን ማሞጋገስ ለእኔ ኢትዮጵያን የመጠቅጠቅ ያህል ነው። ለዛውም ፍርፋሪ ለማይገኝበት – በጎሬጥ ለሚታይበት ዘመን። በአይመለከተኝም መስመርስ ተሂዶ የጥበብ ቤተኝነት አባልነት ወይንስ ደባልነት – ለሆድነት?

ዬት ይሆን ያሉት – አነዚህ ተተኪ የጥበብ ዕንቡጦች? ከቶ ዬት ይሆን አድራሻቸው? ለነገሩ ዝንቅንቅ ብሎ ጸጋ ሳይሆን ቅመሙ መለያው – መስፈሪያው – ማንዘርዘሪያው – ዘመንተኝነት ሆኗል። የሆኖ ሁኖ ግን አምልጠው የወጡት ግን ፊት ለፊት ወጥተው በሚገባም ተደራጅትው ገዢውን ስንክሳር – ሊሟገቱት ይገባል። ሰንደቃችን – ምሳሌያችን አባት ደበበን ሊያስቡት፤ ሊያስታውሱት፤ አውዳዓመት ሲደርስ ሄደው ሊጠይቁትና የተቀነባበረ ተግባር ሊከውኑ ይገባል። በተጨማሪም ማን ጌታ አለባቸው አካውንታቸው ላይ ፎቶውን ቢለጥፉት – ቤታቸው ውስጥ በፍሬም ቢያስቀምጡት ክብር ነው – ረድኤት ነው- አደራንም መወጣት – ምርቃትም።

ከሰሞናቱ ፈረንሳይ ውስጥ አንድ አስቃቂ ሀዘን ተፈጸመ – ለሶስት ተከታታይ ቀናት። በአንድ የህዝብ ልሳን በሆነ ላይ „አሸባሪዎች“ ወንጀል ፈጸሙ። በተከታታይ ሶስት ቀናት ፈረንሳይ በሃዘን – በምጥ ላይ ነበረች ከጥር 7 – 9። በ11.01.02 ከ50 በላይ የሚሆኑ የሌላ ሀገር ጠቅላይ ሚ/ሮች የመንግሥት ተወካዮች 100000 ታዳሚዎች ብሄራዊ ዓለምዐቀፋዊ የሶሊዳሪቲ ስልፍ ነበር „እኔም ሻርሊ ነኝ፤ እኔም ይሁዳዊ ነኝ፤ የሃሳብ ነፃነት ይከበር፤ የፕሬስ ነፃነት ይከበር፤ የሃይማኖት መቻቻል ይበልጽግ“ በማለት ከሁለኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የታዬ መጠነ ሰፊ የህዝብ ቁጣና የሀዘን ቀን ነበር። በህንድ፣ በጀርምን በተለዬ ሁኔታ፤ በእንግሊዚም ተማሳሳይ የወዳጅነት ሰልፍ ነበር … ይህን ጥቃት የደረሰበትን መጋዚን ለማጋዝም ሚሊዮኖች ተሰልፈዋል። እኛ ጋር ሲመጣ ሌላ ነው። በ2012 „ፍትህ“ ጋዜጣ 30000 ህትምት ስትቃጠል በጎኑ ዬመቆም አቅሙ ምን ያህል ነበር? የብዕር ውጤት ምርቶች ሲታገዱ አምራች ህሊናዎች ሲንገላቱ፤ ሲታሰሩ፤ ሲሰቃዩ ህዝቡም ሆነ ዋና የጥበብ ቤተኛው ታዳሚው ኮሽ አይልም። 30 ሺህ የፍትህ እትም መቃጠል ማለት በአማካኝ በስሌት አንድ ህትምት ቢያንስ በመዋዋስ 5 ሰው ያነበዋል። በማዕካለዊ ግምት ሲሰላ 150000 ሰው መንፈስ አብሮ ተቃጥሏል። ለዛውም የሆነውን እውነት ነገር በመጻፉ። ከዛም የተለያዩ ሙከራዎች አድርጎ ታታሪ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንፈሱ – ብቃቱ እግር ብርት ሆነ። ጭራሽ ስንቅ እንዳይገባለት ከቤተሰብ እንዳይገናኝ ተወሰነ። እውነት በቲያትር፤ በፊልም፤ በሙዚቃ፤ በሥነ ጹሑፍ በጸሐፊነት፤ በገጣሚነት፤ የተሰማራው ቤተኛ ሁሉ ጥበብ ቀብር ላይ ሆኖ እንዴት እንቅልፍ ወስዶት እንደሚያድር ሳስበው መተንፈስ ያቅተኛል – የእውነት። የጥበብን ጽኑ ጣር መስማት ያልቻለ ጆሮ ምን ይሁን ትላላችሁ – ክብሮቼ?

ሥነ – ጥበብ ዓለምነቷ የራሷመርህ ብቻ ሳይሆን የራሷ ፕላኔት ያላት ከመሆኑ ላይ ነው፤ ሥናዊቱ ሃይማኖት ጥበብ ህገመንግሥት ያላት፤ የሥምረት ማዕዶት ናት። ኪናዊቱ – ማናቸውንም ግርዶሽ ሁሉ ፈነቃቅላ እራሷን የመግለጽ የኤደን አቅም አላት። ልዕልት ጸሐይ ጉምን አሸንፋ ተወዳዳሪ የለሽ የኃይል ምንጭ እንደ ሆነች ሁሉ ጥበብ የአቅም ምጣኔ ባንክ ናት። የብቃት መጠለያ ናት። ኪዳን ናት – ውል። ማተብ ናት – ዕምነት። ሁሉን ለመጋራት የፈቀደች ወላጅ እናት ናት – አናት። ታዲያ አዛውንቱ አንድ ዕጣ ነፍሱን የቀረው ታላቅ ብርሃን – ዬትውልድ በ100 ዓመት ሊተካ የማይችለው የትዕይንት ንጉሥ ጨለማ ውስጥ ሆኖ እንዴት ስለእሱ ተቆርቋሪ ቀንጣ የሥነ – ጥበብ ክበብ፤ ቆራጥና ደፋር አርበኛ በባዕት ይታጣ?! አይጎረብጥም? ትንሺ ብጣቂ ሰለምታ በወል መላክ እንኳን ሳይቻል፤ ለተቋምነትህ እናመሰግንሃለን ሳይባል የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና አንድ ነገር ቢሆን ለወጣት ተዋናይ የህሊና ረመጥ አይሆንም?! ታሪክስ ትውፊትስ አይራገመሙም? አስተውሉ ….. እነ ኮበል እነ ሸበላ እባካችሁ ….. ን። ጥበብን አስቡ – መንፈሳችሁን – አነቃንቁት …. ለጥበብ ነፃነት አደባባይ ውጡ – ደጋፊዎቻችሁን፤ አድናቂዎቻችሁንም አሰልፉ — ዕልፍናችሁና ዕልፍነታችሁን በተግባር እልፍ አድርጉት እንጂ የምን ተኝቶ በለኝ ነው¡

ወያኔ እንደ ሆነ ድልድይ መስበር አመሉ ነው። የተፈጠረውም ሆነ የሰለጠነው መንገድ ለማፈረስ ነው። ይህን ምኞቱን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይፈጽመዋል። ጋሼ ደበበ ባይታሰር ስንት ወጣቶች በብሄራዊ ስሜት ጥበብን አልቀው፤ ጥበብን እንደ ተፈጥሮው አቅልመው መቅረጽ የሚችሉ የነገ ጽጌረዳዎችን ባፈራ ነበር። ይህም ተፈርቶ ነው የታሰረው። ለአንድ ታላቅ ብልጹግ የሥነ ጥበብ አባዎራ – እማወራ አንድ ቀን ብዙ፣ እጅግ ብዙ ምርት የሚታፈስበት ዕለቱ ነው። እንኳንስ —- አስሉት ከ97 ጀምሮ ያሉትን ጊዜያቶች ….. ሥንት ዕንቡጥ የተውኔት ለጋ ኮሽ ብሎ ደርቆ እንደ ረገፈ፤ ተስፋ በግፍ ተነቀለ፤ ፍቅር ከፍቅረኛው ታገደ …. ያቆስላል። መድርክም ደም አማጣች! ይህን ፍሬ ነገር የነገ የተስፋ ተስፋዎች ከልብ ሆናችሁ አስሉት – አንሰላስሉት …. እናም ወስኑ ነገን ለማግኘት እባካችሁን ቁረጡ?! ለጥበብ አደራ ብቁ ወታደር ሁኑ። በራችሁ እሲኪንኳኳ ድረስ አትጠበቁ …. ተንቀሳቀሱ! ፍጠኑ! ትንሽ ተነቃነቁ ጅም ነገር አድርጉ! …. በትንሹ ጀምሩት … ይሄው ሰሞናቱ ዘመነ አስተርዮ ነው። ቃና ዘገሊላ ታምር የተመሰጠረበት። …. እሰኪ ፖስት ካርድ ላይ ፊርማ አሰባስባችሁ እንኳን አደረሰህ አባታችን በሉት። የ5 ወይንም የ10 ወገኖቹ ሊሆን ይችላል። ብጣቂ ቁራሽ ሳቅ እስኪ ውስዱለት። እንወድሃለን፤ እናከብርሃለን ተክሊላችን ነህ እስኪ በሉት አፋችሁን ሞልታችሁ፤ ድፈሩ! መንፈሳችሁን አደላድላችሁ – ፍላጎታችሁን ፈጽሙ። ጨው አይዳላችሁ አትማሙ – እሰኪ ተስፋነታችሁን ጀምሩት፤ እኛም ተስፋ እንዲኖረን አድርጉን። አሉልን – አሉልን – አሉልን እንበል። መታሰር ይኖራል፤ መገፋት ይኖራል፤ መሳደድ ይኖራል። „ከድምጽችን ይሰማም ተማሩ! ለሰማይው ጸጋችሁ ፍትኃት ቁረጡ – ወስኑ – ከድርጊት ጋር ከትሙ። ከመከራ በስተጀርባ ታላቅ ክብር አለ። መከራ በበዛ ቁጥር መጪው ቀን ብሩህ እንዲሚሆን ያበስራል።
ጥበብ ተናገረች – መርሄ ነው ብላ
ልቧነን አውጥቶ ካቴና ሲባላ፤
ጥበብ ታውጃላች – ተከተሉት ብላ
ሥነ ህግን – ገላ።
ጥበብ – ሠራች ባላ
የመሆን – አዝመራ!
እኔም ተቀበልኩኝ
እሺ አልኩኝ፤ እሺ አልኩኝ —-
ለእሱ – ይሁንልኝ
ለመንፈስ ሁነኛ
መገኛ – መዳኛ፤
የሆነልን – ዬእኛ – ለእኛ። /05.01.2015 ሲዊዘርላንድ – ቪንተርቱር/

እንሆ – „የታላቋ ትግራይ ህልም“ ሁለመናን ያሳድዳል፤ ሁለንትናን – ይቀማል። ዘመቻው ጥልቅ ስትራቴጁም ስውር – ነውር። በተከታታይና በትጋት ዬትውልድን ውርርስ ሃብት ለመከተር ዋርካ ይነቀላል፤ የትውፊትን ቀንዱን ይሠበራል – ሴሉም ይገደላል። ድንበር ይጣሳል – ዘረፋም ይጎናል። ስለዚህ ሥር ሰደድ በደል ሥር ነቀል ለውጥን ማለም አለበት – እላለሁ – እኔው። የፍላጎት አቅም ሙያዊ ግዴታን በአግባቡ ከመወጣት ይታፈሳልና። በስተቀር እዬሞቱ መኖር እዬኖሩ መሞት —– ግን ይህ መኖር ወይንስ ምን?!

ጥበብ የእውነት አረበኛ ናት። ጥበብ ለማተቧ ሰማዕት ናት። ጥበብ ዘር ናት። ተከታዮቿ – ቤተኞቿ – አድናቂዎቿም – የዕውነት ሐዋርያ መሆን አለባቸው። ከዚህ ከወጡ ያረጡ ከንቱዎች ናችሁ ብላ ጥበብ እራሷ ትሰርዛቸዋለች። ከሰጠቻቸው እርእስት ሆነ ከጉልማ* መሬታቸውም ትነቅላቸዋለች። ጥበብ ካኮረፈች ወይንም ከተቆጣች ጸጋን እውሃ ሲሄድበት የከረመ አለት የማድረግ አቅሟ ብልህ ነው። ስለምን? ከዕውነት ውጪ ጥበብ አትታሰብም፤ ወይንም ቀና ብላ ጆሮ አትሰጥም። ጥበብ – ታማኝነትን ውጣ፤ ሃቅን አጣጥማ፤ ፈርኃ እግዚአብሄርን የጠበቀች ለ እውነት ያደረች ግማደ መስቀል ናት – ለኑሮ! ኑሮን ፈጥራ – ቀርፃ ጸሐይ ያደረገች የኑሮ ፈርጠ – ጉልላት።

„ ለሁሉ ዘመን አለው፤ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው“ /መጸሐፈ መክበብ ምዕርፍ 3 ከቁጥር 1 እስከ 2/
ቅኔያችን – ለእኛ የተከበረው የሰባዕዊ መብት ተሟጋችና ታላቁን የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱን አምላካችን ይጠብቅልን። አሜን! ዕድሜውን ሰጥቶት ጸጋውን ይምግበን ዘንድም አምላካችን አዶናይ ይርዳን። አሜን!

በተረፈ ነገ ጥር 17 ቀን ነው። የጀግና ኃይለመድህን አበራ 11ኛ ጀኔባ የገባባት የጀግንነት ወሩ ነው። እሱ የሳሳለት፤ ሁሉን የሰጠው፤ ለነፃነት መንፈስ ሲል ስለሆነ የእሱን ቀን ለተግባሩ ውለታ ለጋሼ ደበብ ይሁን ብዬ ወሰንኩ። ስለ ሀይልዬ ሆነ ቀልብን ሳብ አድርገው በሰነባበቱ ጥቂት ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ያቺው መቼም ቆራጣ ናት አንድ ሰዓት የሚሏት፤ የተቻለውን ያህል ትናንትና በ15.01. 2015 በነበረው ፕሮግራም Tsegaye Radio ያለው ነበር። እሰኪ ገባ ብላችሁ አዳምጡት ከቻላችሁ። የሃይልዬም አምድ የበኩሉን ከውኗልና።

ይቋጭ – የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። አልገርምም ግን ስስናበት ሰላምታ። ይሁን። ለስላሳ ትህትና ለጀርጋዳ ስንብት እንሆ።
ውዶቼ አንድ ነገር – እሰኪ ሰንበትን በአካውንታችሁ የዚህን የዘመን አውራ ፎቶ መንበሩ ላይ የምትችሉ አስቀምጡት፤ ውስጡን በመንፈስ ብሌን ትክ ብላችሁ እዬት። በዕዝን ህሊና ከንፍርም በፍቅር ዳስሱት። ክብራችን – ጌጣችን – ግርማ ሞገሳችን – ውባችን – ተቆራቋሪያችን – አድባራችን – አለኝታችን – ትምህርት ቤታችን – ተቋማችን፤ የጥበብ ባዕታችን እስኪ በሉት — እንዲያምርባችሁ —– እንዲያምርብን — ሸበላ ሰንበት እንዲሆን ከመንፈሴ ተመኘሁኝ። ፍቅር ስለሆናቸውም ድንበር አልቦሽ – ነፍስ የሆነ ፍቅሬንም እንሆ! መሸቢያ – ሰሞናት- ኑሩልኝ።

*መፍቻ ጉልማ … ከሰፊው የምርት ማሳ ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጧቸው ቁራሽ የግል መሬት ሲሆን። ልጆችም ይህን መሬት በራሳቸው መንገድ አልምተው የፈለጉትን ዘርተው የሚያገኙት ገቢ ለራሳቸው የግል ጉዳይ መፈጸሚያ ወይንም ማስፈጸሚያ ያደርጉታል። ጎጆ ሲወጡም ጎጆ መውጫ ይሆናቸዋል። ሥነ ጥበብ ከሰፊው ማሳው ዘርፈ ብዙ የማይቋረጥ በብዙ መስመሮች ሊገለጽ የሚችል ረቂቅ ጥልቅ የሰማይ መክሊት ሲሆን ለሰው ልጆች የሰማይ ስጦታ ነው። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ የራሱን መክሊት ይዞ ይወለዳልና። እንደ መክሊቱም ህዝብን ዝቅ ብሎ ያገለግልበታል። ግን ችለናልን ወይንስ አደራ በይ ሆነናል ነው ጥያቄው ——

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የሰሜን አሜረካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር አንድነት ፓርቲ የምጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደማይቀበለው መግለፁን እንደሚደግፍ አስታወቀ

$
0
0

ከአንድነት  ድጋፍ ማህበር በሰሜን አሜሪካ  የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ  

ጉዳዩ፡  ፡ በቅርቡ  በኢትዮጵያ  ምርጫ  ቦርድና  በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በተመለከተ፡፡

 

udjእንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከምርጫ ቦርድ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ በ4 ቀን ውስጥ እንዲጠራና የፓርቲውን  መሪ በድምፅ አሠጣጥ መመሪያው መሠረት እንዲመርጥ ስለተገደደ አንድነት ፓርቲም በሆደ ሰፊነት በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ ባያምንበትም ሕግ ለማክበርና የሠላማዊ ትግሉን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ስለሚረዳ በሌለ አቅሙ በ4 ቀን ውስጥ በአስቸኳይና በታላቁ በገና በዓል ሣምንት የጉባዔ  አባላትን ከክ/ሃገር ጭምር ጉባዔ ጠርቷል፡፡  ምርጫ ቦርድ ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፋ በ4ቀን ጉባዔ እንዲጠራ ካዘዘ በኋላ በጉባዔው ተገኝቶ ምርጫውን ታዝቦ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጋብዞ ሣይገኝ ቀርቷል፡፡  ይህ ዓይነት የምርጫ ቦርድ ሕገ-ወጥነት በጥብቅ ሊወገዝ ይገባል፡፡  ይህ አልበቃ ብሏቸው ምርጫ ቦርድ አሁንም እጅግ በጣም በሚያሳፍርና ይሉኝታ በሌለው አካሄድ አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በድጋሜ ጉባዔ እንዲጠሩ ሕገ-ወጥ ትዐዛዝ ለማስተላለፍ ችሏል፡፡  ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ውስጥ ጉዳይ የመፈትፈት: ውሣኔ የመቀልበስ እንዲሁም የፓርቲዎችን አመራር የማፅደቅ ወይም ያለማጵደቅ መብት ጨርሶ ሊኖረው አይገባም፡፡  ምከንያቱም እንደዚህ ዓይነት ጣልቃ ገብነት ካለ የፓርቲዎች የበላይ አካል የሚሆነው የአባሎቻቸው ጠቅላላ ጉባዔ ትርጉም አልባ ይሆናልና፡፡

 

አንድነት ፓርቲ በምጫ ቦርድ በድጋሜ የተላለፈውን ጉባዔ የመጥራት ትዕዛዝ እንደማይቀበለው መግለፁን እኛም የሰሜን አሜረካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር ሙሉ በሙሉ እንደምንደግፍ እናረናገግጣለን፡፡  ምርጫ ቦርድ እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ለአገዛዙ ወገናዊነት በማረጋገጥ በአስተዳደሩ ኃላፊዎች በመታዘዝ በአንድነት ፓርቲና በሌሎች ተቃዋሚ አጋር ፓርቲዎች የሚያደርገውን ሕገ-ወጥነት አስተዳደራዊ ክፋ ሰራ እንቃወማለን! አንቀበለውም:: አገዛዙ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ከፈለገ ህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎችን በህገ-ወጥነት ሣይሆን በስርዓት :በአግባቡ የጨዋታ ሜዳውን ክፍት ማድረግ አለበት፡፡  የምርጫ ቦርድ የተደጋጋሚ ጉባዔ ጥሩ ትዕዛዝ ህገወጥነት ነው፡፡  ተቀባይነት የለውም አገዛዙ እንደዚህ ዓይነት እጅግ የዘቀጠ ፀያፍ ስራ ውስጥ ተነክሮ ያለው መጪውን ብሔራዊ ምርጫ ያለተቀናቃኝ ብቻዉን ተወዳድሮ ለማሸነፍ ካለው ጭፍን ፍላጐት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡  ሆኖም ግን ይህ አካሄዱ ሃገሪቱን ወደ ባሰ ምስቅልቅል ይወስዳታል እንጅ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡

 

በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ማለትም መኢአድ: ሰማያዊ: መድረክና ሌሎችም ፓርቲዎች ተቀራርበው ትግሉን በጋራ እንዲመሩት ጥሪ እናቀርባለን፡፡  ፓርቲዎቹ አገዛዙን በመቃወም ለሚያደርጓቸው ማንኛውም የሠላማዊ እንቅስቃሴዎች ከጐናቸዉ እንደምንቆም በዚህ እጋጣሚ ማሣወቅ እንወዳለን፡፡  አንድነት ፓርቲ በሚያደርጋቸው የትብብር ጥሪዎችና የአመራር ስልቶች በተናጠልም ወይም ከሌሎች አጋር ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርጋቸው ትግሎች ሙሉ በሙሉ የማቴሪያልና የሞራል ድጋፍ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብም የአገዛዙን ተንኮል በመረዳት ከአንድነትና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጐን በመሰለፍ የነፃነት ትግሉን እንዲያፋጥን ጥሪ አናቀርባለን፡፡

 

Health: ኤች.አይ.ቪ ኤድስን የሚያድኑ መድሃኒቶች ተፈጥረዋል የሚለው ምን ያህል እውነት ነው?

$
0
0

ውድ አዘጋጅ፡- የ21 ዓመት ወጣት ሴት ስሆን በአሁኑ ወቅት በግል ኮሌጅ ውስጥ በመማር ላይ እገኛለሁ፡፡ የምኖረው ጥሩ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦቼ ጋር ነው፡፡ ከወንድ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ የጀመርኩት ከአራት ዓመት በፊት ማለትም ገና የ17 ዓመት ወጣት በነበርኩበት ጊዜ ነው፡፡

በኤች.አይ.ቪ ኤድስ እንዴትና መቼ እንደተያዝኩ አላውቅም። ክብረ ንፅህናዬን ከገፈፈው ከመጀመሪያው የወንድ ጓደኛዬ በተጨማሪ እስካለፈው ዓመት ድረስ ከአራት የተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲባዊ ግንኙነትን ፈፅሜያለሁ፡፡ በስሜት የተሞላሁ በመሆኔ በግንኙነት ወቅት ኮንዶም የመጠቀም ጥያቄ አቅርቤ አላውቅም፡፡

HIVከአንድ ዓመት በፊት ሁለተኛው የወንድ ጓደኛዬ በጠና ታሞ መሞቱን በመስማቴና አንድ ጓደኛዬም ልጁ የሞተው በኤች.አይ.ቪ መሆኑን ስትነግረኝ ተጠራጥሬ በምስጢር ባደረኩት ምርመራ ቫይረሱ በደሜ ውስጥ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡
በአሁኑ ወቅት ሁሉንም ነገር በፀጋ ተቀብዬ ከቫይረሱ ጋር በመኖር ላይ እገኛለሁ፡፡ እንደ ቀድሞው መቅበጤንም ትቻለሁ፡፡

ውጤቴን ከሰማሁ በኋላ ላለፈው አንድ ዓመት ወሲባዊ ግንኙነት አላደረግኩም፡፡ ሲዲ ፎሬ በጣም ያልወረደ በመሆኑ በየጊዜው የምጎበኛት ሐኪም ፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት እንድጀምር አላዘዘችኝም፡፡ ያም ሆኖ በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ በቫይረሱ መጠቃቴ ሁሌም ያሳዝነኛል፡፡ በየጊዜው በኢንተርኔት አማካኝነት ስለ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ የሚወጡ ጥናታዊ ፅሑፎችንም እከታተላለሁ፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ፅሑፍ ቫይረሱ የሚጠፋበት እና ሰዎች ከኤድስ ነፃ የሚሆኑበት ጊዜ በጣም ሩቅ እንደማይሆን በመግለፁ ውስጤ በተስፋ ተሞልቷል፡፡ አሁን ልጠይቅህ የፈለኩትም ይህንኑ በሚመለከት ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ውስጥ ቫይረሱን በከፍተኛ ደረጃ ሊከላከሉ እና ሊያጠፉ የሚችሉ መድሃኒቶች ተፈጥረዋል ይባላል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው? እውን ከኤድስ መዳን ወይም መፈወስ የሚቻልበት ጊዜ እየመጣ ይሆን? ቫይረሱን በቅድመ ክትባት ለመከላከል የሚቻልበት ሳይንሳዊ ዘዴ ተገኝቷል የሚባለውስ እውነት ነው? እባክህን በእነኚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ስጠኝ፡፡
ሠላማዊት አስታጥቄ

ውድ እህታችን፡- ጥንቃቄ በጎደለው ወሲባዊ ግንኙነት ምክንያት በዚህ የወጣትነት ዕድሜሽ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በመያዝሽ አዝነናል፡፡ ይሁን እንጂ ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ ተገኘ ማለት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመኖር ወደ አለመኖር ትሸጋገሪያለሽ፣ ማለት እንዳልሆነ ተገንዝበሽ እንድትፅናኚ እንጠይቅሻለን። ይህንን የምንልሽ ከባዶ ሜዳ ተነስተን ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በመሰራጨት ላይ የሚገኙት የፀረ.ኤች.አይ.ቪ መድሃኒቶች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩትን ዕድሜ አስገራሚነትና ባልተጠበቀ መልኩ እያራዘሙት በመሆናቸው ነው፡፡ እናም በአሁኑ ወቅት አንድ ሰው በሚያደርገው ምርመራ ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እንደሚገኝ ቢያረጋግጥ እንኳን ስለ ሞት አይጨነቅም፡፡

በእርግጥ እስካሁን ድረስ ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ ከደም ውስጥ ማጥራት የሚችል መድሃኒት የለም፡፡ ይህም ማለት ቫይረሱን ከአንድ ሰው አካል ውስጥ ማጥፋት የሚችል እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማረጋገጫ የተሰጠው መድሃኒት አልተገኘም፡፡ ይሁን እንጂ በኤች.አይ.ቪ ህክምና ውስጥ በየጊዜው አስገራሚ የሆኑ ዕድገቶችና መሻሻሎች እየተፈጠሩ ሄደዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚደረጉት የህክምና ክትትሎችና መድሃኒቶች ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ህይወት እየታደጉት ይገኛሉ፡፡ እነኚህ ሁኔታዎች የታማሚዎችን አዕምሯዊ እና አካላዊ ሁኔታዎች በማደስ ላይ ናቸው፡፡

በአውሮፓ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ከቫይረሱ እየተፈወሱ ስለመሆናቸው የሚናፈሰውም ወሬ ቢሆን እውነትነት ያለው ይመስላል፡፡ ከእነኚህ ከኤች.አይ.ቪ መፈወሳቸው ከተነገረላቸው ሰዎች መካከል ‹‹የበርሊኑ ታማሚ›› (The Berlin Patient) በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው ራሞር ብራውን ይገኝበታል፡፡ በእርግጥ የበርሊኑ ታማሚ ጉዳይ በአውሮፓ ውስጥ በሚገባ የሚታወቅና ጥልቀት ያለው ጥናትም የተካሄደበት ነው፡፡ ታማሚው እንደተባለውም ከበሽታው መፈወሱ ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ሳይንስ ለዚህ ሰው የመፈወስ ጉዳይ እስካሁን ድረስ እውቅና ሊሰጠው አልፈለገም፡፡

የበርሊኑ ታማሚ ከበሽታው በመፈወሱ ምክንያት በአሁኑ ወቅት የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሃኒቶችን በመውሰድ ላይ አይደለም። በእርግጥም በቲሞቲ ብራውን ውስጥ የሚገኘው የቫይረሱ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱ ተረጋግጧል፡፡ ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙም እንደማንኛውም ጤነኛ ሰው የተሟላ ነው፡፡

ከበርሊኑ ታማሚ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ጉዳዮች እዚህም እዚያም በመታየት ላይ ናቸው፡፡ በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ የፀረ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ፈውስን ማግኘታቸው በስፋት ይወራል፡፡ በውጭ ሀገር ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ቫይረሱን በተሻለ ሁኔታ ማዳከም እና የሲዲ 4 መጠንን ለማሳደግ መቻሉ እየተነገረ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሳይንቲስቶች በእነኚህ ሁኔታዎች አልተዘናጉም፡፡ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ከደም ውስጥ ለማስወገድ የሚችለውንና ሳይንሳዊ ማረጋገጫ የሚሰጠውን መድሃኒት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት ሳይንቲስቶች የመፈወሻ መድሃኒቱ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡

በቅርቡ የተላላፊ ቫይረሶችና ተለዋጭነት ያላቸው ህመሞች 21ኛው ኮንፈረንስ በቦስቶን ከተማ ተካሂዶ ነበር፡፡ በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ሳይንቲስቶች የገለፁት ምንም እንኳን ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የሚችለው መድሃኒት እስካሁን ባይፈጠርም ህክምናውን በሚመለከት ከፍተኛ መሻሻሎች መታየታቸውን ገልፀዋል። እነኚህ መሻሻሎች የተገኙት ደግሞ ቫይረሱ በደም ውስጥ እንዴት ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደሚችል እና እንዴትስ ሊጠፋ እንደሚችል ተጨማሪ ዕውቀቶች በመገኘታቸው ነው፡፡

ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ፈውስ ያገኙ ሰዎችን በሚመለከት ከጀርመኑ ታማሚ በተጨማሪ ሌሎች አጋጣሚዎችም ተስተውለዋል፡፡ ከእነኚህም አጋጣሚዎች መካከል አንዲት በሚሲሲፒ ውስጥ የምትኖር ህፃን ትገኝበታለች፡፡

ዴቦራ ፔርሱር የተባለች በጆንስ ሆፕኪንስ ሆስፒታል ውስጥ የምትገኝ ሐኪም ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ ውስጥ ከሚገኝ እናት የተወለደችውን ህፃን በሚመለከት ስትገልፅ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በሚያደርገው የህክምና ጥበብ ባለመታገዟ በተወለደችበት ወቅት ህፃኗ በቫይረሱ መያዟን ታረጋግጣለች። በመሆኑም ህፃኗ በሚሲሲፒ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የህፃናት ሐኪም ቤት ውስጥ እንድትቆይና ከተወለደች ከ30 ሰዓታት በኋላ የአንታየርትሮቫይራል ህክምና እንድትጀምር ተደረገ፡፡
ከህፃኗ ጨቅላነት አንፃር ይህ ህክምና አደገኛነት ሊኖረው ይችል ነበር፡፡ ይሁንና ህይወቷን ለማትረፍ ይህንን ህክምና ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ ስላልነበረ ሕፃኗ ለ18 ወራቶች ያህል በሆስፒታሉ ውስጥ ተኝታ የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምናውን ስትከታተል ቆየች፡፡ በመጨረሻም ማለትም ከ18 ወራት በኋላ ቤተሰቧ በመልካም ጤንነት ላይ የምትገኘውን ህፃን ከሆስፒታሉ አውጥተው ወደ ቤታቸው ይዘው ሄዱ፡፡

የፀረ.ኤች.አይ.ቪ ህክምናውንም አቆመች፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ህፃኗ ወደ ሆስፒታሉ ተመልሳ ምርመራ ስታደርግ በደሟ ውስጥ የነበረው የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መጥፋቱ ተረጋገጠ፡፡ አሁን ህፃን ዲቦራ የሶስት ዓመት ህፃን ስትሆን ከቫይረሱ ነፃ ሆና ጤናማ ኑሮን በመኖር ላይ ትገኛለች፡፡ ይህም ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመካሄድ ላይ የሚገኙት የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምናዎች ፈዋሽ መሆናቸውና ህፃናት ጊዜው ከማለፉ በፊት ህክምናውን ካገኙ ከበሽታው ሊፈወሱ እንደሚችሉ ያመለክታሉ፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ ህክምናቸውን የተከታተሉ በርካታ ህፃናት እየተፈወሱ መሆናቸውም ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ በታች ያቀረብነው ቃለ መጠይቅ ደግሞ ሰዎች ከኤች.አይ.ቪ የሚፈወሱ ስለመሆናቸው የሚተርክ ነው፡፡

ዶ/ር ማስ አር ዩሱፍ የስሪ ላንግ ብሔራዊ የህክምና አገናኝ ተቋም ምክትል ዳይሬክተር እና የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው፡፡ በስሪላንካ ፒታ ኮቴ ሆስፒታል በፍልስፍና እና በነርቭ ህክምና ላይ ጥናት ያደረጉት ዶ/ር ዮሴፍ በናቹራፓዚ እና በማግኔቲያዊ ህክምና ሰፊ ዕውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ ዶክተሩ በቅርቡ ኮሎምቦን በጎበኙበት ወቅት ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጋር እየተካሄደ ያለውን ትንቅንቅ በሚመለከት ከአንድ የህክምና መፅሔት ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፡፡ እኛም ቃለ መጠይቁን በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፡፡ ጠያቂያችንም ከቃለ ምልልሱ ግንዛቤ እንደምታገኚ እንገምታለን፡፡

ጥያቄ፡- ኤች.አይ.ቪ ሰዎችን የሚያጠቃው እንዴት ነው?
መልስ፡- ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠቃው ተፈጥሯዊውን የበሽታ መከላከል ሲስተም ነው፡፡ ቫይረሱ የአምዩኒ ሲስተማችንን ካዳከመ በኋላ በተለያዩ በሽታዎች እንድንጠቃ ያደርገናል። አንድ ሰው ሁለት አይነት ቲ ሴሎች አሉት። አንደኛው ቲ ሴል ሲዲ 4 የተባለ ሞሉክዩል በላዩ ላይ የያዘ ሲሆን የዚህ ሞሉክዩል ተግባር ደግሞ ወደ ሰውነታችን የሚገባውን ቫይረስ በመከላከል ማስወገድ ነው፡፡ ሁለተኛው በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ሞሎክዩል ሲዲ 8 የተባለው ነው፡፡ የዚህኛው ሞሎክዩል ተግባር በበሽታ የተጠቁ ሴሎችን ማስወገድና ፀረ ቫይረስነት ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ማምረት ነው። እነኚህ ሁለት የሞሎክዩል አይነቶች ናቸው፡፡ በተቀናጀ መልኩ ሰውነታችን በአንድጀንስ፣ በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በፈንገስ እና ከመሳሰሉት ህመም አምጪ ህዋሳት እንዳይጠቃ የሚያደርጉት።

ኤች.አይ.ቪ በሲዲ 4 ሞሉክዩል ጋር በመጣበቅ ቫይረሱ ወደ ውስጥ ገብቶ ሴሎችን እንዲበክል ያደርጋል፡፡ በእርግጥ አንድ በውስጡ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ያለበት ሰው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይሰማው ለተወሰኑ ዓመታት በጤነኛነት ሊቆይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም በቫይረሱ በየቀኑ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የሲዲ 4 ቲ ሴልስ በቫይረሱ ቢደመሰስም የዚያኑ ያህል ቁጥር ያላቸው ሞሉክዩሎችን ሰውነታችን ስለሚያመርትና የተደመሰሱትን ስለሚተካ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ኤች.አይ.ቪ ያለ ጥርጥር ኤድስን ያስከትላል ማለት ይቻላል?
መልስ፡- አንድ አዋቂ ሰው ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ በኋላ ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይሰማው ለ8 ዓመታት ሊቆይ ይችላል፡፡ ለህፃናት ደግሞ አማካይ ጊዜ 2 ዓመታት ነው፡፡ ይህም ሆኖ አንዳንድ አማይዋሎጂስቶች ሞሎኪያሮች፣ ባዮሎጂስቶች፣ ቫይኖሎጂስቶች፣ ባዩኬሜስቶች እና ማይክሮባዮሎጂስቶች ኤች.አይ.ቪ ከመደበኛው በሽታ አስተላላፊ ቫይረስ ምንም የሚለይበት ነገር እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡ በእነኚህ ተመራማሪዎች እምነት መሰረት ኤች.አይ.ቪ ኤድስን አያከስትልም። ለዚህ እምነታቸው የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ኤድስ የባህሪ በሽታ እንጂ በኤች.አይ.ቪ የሚከሰት አይደለም የሚል ነው፡፡ በእነኚህ ጠበብቶች እምነት መሰረት ኤድስ የሚከሰተው በአሙዩኒ ሲስተም ውስጥ በሚከሰት በርካታ የመዛባት ሁኔታዎች ምክንያት ነው፡፡ እነኚህም ሁኔታዎች በወሲባዊ ግንኙነት ምክንያት በሚተላለፉ ህመሞችና በበርካታ የቫይረሱ ጥቃቶች ወዘተ… እንጂ በኤች.አይ.ቪ የሚከሰት እንዳልሆነ ለማሳመንም ይሞክራሉ። በዚህም ሆነ በዚያ አንድ ሰው በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ሲያዝ ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙ እየመነመነ ይሄዳል፡፡ ይህ ሁኔታም እንደ የሣምባ ምች፣ ካፓሲ ሰርኮም፣ ሰውነትን ለሚያከሳ በሽታ፣ ለተቅማጥ እና ለሌሎችም አደገኛ በሽታዎች ያጋልጠናል፡፡ እነኚህ በሽታዎች ደግሞ ሰውን የመግደል አቅም ያላቸው ናቸው፡፡
ጥያቄ፡- በእርስዎ ቲዩሪ መሰረት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ምክንያት ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅሙ የወረደውን ሰው የጤንነት ሁኔታ እንዴት ማሻሻል ይቻላል?

መልስ፡- የወደቀን የኢሚዩኒ ሲስተም ለማነቃቃት በሰው ላይ ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ መድሃኒቶችን በትንሹ እየሰጡ በማከም በሰውነት ውስጥ ያለውን ፊዚዮሎጂካል ሚዛን ማስተካከል የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ በመርፌ ነርቭን እየወጉ የማከም ዘዴ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ አንዴ ተስማሚ የሆነውን መድሃኒት ማግኘት ከተቻለ እና የአሲድ ጂኒክ ሁኔታን በሰውነታችን ውስጥ ወደ አልካሊ ጂኒክ መለወጥ ከተቻለ በሽታን የመከላከል አቅማችን እየተጠናከረ ይሄዳል፡፡ ይህንን ለውጥ መፍጠር የምንችለው ደግሞ በናቹር ፓቲክ ሳይንሳዊ ዘዴ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰውነታችን ማንኛውንም በሽታ ለመዋጋት የሚችልበትን ተፈጥሯዊ ጥንካሬ እያገኘ ይሄዳል፡፡

በመሰረቱ እኛ ሰዎች የምንኖረው በርካታ ጎጂነት ካላቸው እና ከሌላቸው ህዋሳት ጋር ነው። በሳይንሳዊ ግምት መሰረት አንድ ሰው በአንድ ሰዓት ውስጥ ከ14 ቢሊዮን በላይ ፓቶጂነሶችን ወደ አየር ይለቃል፡፡ ይሁንና በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው የአምዩኒ ሲስተም በየሴኮንዱ ውስጣችንን ከእነኚህ ህዋሳት የማንፃት ተግባር ያከናውናል። ኤች.አይ.ቪ ኤድስን በመዋጋቱ ሂደትም ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ መፈጠር አለበት።

ጥያቄ፡- እንደ ሆሞፓዚ፣ ፓልም ዲያግኖሲስ ቴክኒኮች፣ ማግኔቶራፒ፣ አዩርቪዳ እና ሌሎችም የህክምና አይነቶች ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ወደ ማዳን ሊያደርሰን ይችሉ ይሆን?

መልስ፡- በእርግጥ የመርፌ ነርቭን እየወጉ የማከሙ ዘዴ ከሌሎች ናውትሮፓቲክ የህክምና ዘዴዎች ጋር በመቀናጀት ቫይረሱ ባለበት እንዲቆምና የአምዩኒ ሲስተማችንንም ሊያሳደግ ይችላል። ሁሉም ችግር የሚመጣው በራሱ በቫይረሱ ሳይሆን ተፈጥሯዊው በሽታን የመከላከል አቅም ሲዛባ ነው፡፡ ፊዚዮሎጂያዊ የህክምና ዘዴ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅምን ካጠናከረ ቫይረሱ ራሱን እየወለደ ለመራባት አይችልም። ይህም ሁኔታ የመራባት ባህሪውን ያሳጣዋል፡፡ አንዳንድ ከኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጤነኛ እና የተረጋጋ ህይወት በመኖር ላይ የሚገኙትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ጥያቄ፡- በአጭሩ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ የመፈወስ ሁኔታ ይፈጠራል ማለት ነው?

መልስ፡- አንድን በኤች.አይ.ቪ ኤድስ የተያዘ ሰው የሚያድነው ብቸኛው መድሃኒት የገዛ ራሱ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም መጠናከሩ ነው፡፡ ሌሎች የህክምና ዘዴዎች አምዩኒ ሲስተምን ለመንከባከብና ቫይረሱ እንዳይራባ ለማድረግ ብቻ የሚከናወኑ ናቸው፡፡ ይህ ህክምና የህመምተኛው አምዩኒ ሲስተም ከቫይረሱ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመድሃኒቶቹም ጋር ተስማምቶ ያለ ችግር እንዲያድግ ያደርገዋል፡፡ ይህ እውነት ያለው ነገር ነው። በመሆኑም ሐኪሞች በቅድሚያ ማድረግ ያለባቸው ነገር የህመምተኛው ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም እንዲያድግ ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ህመምተኛው ወይም ህመምተኛዋ ወደ ሙሉ ፈውስ በሚያደርሳቸው ጎዳና ላይ እንዲጓዙ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አሚዩኒ ሲስተምን ሳያሳድግ የሚካሄድ ማንኛውም የህክምና ዘዴ ህመምተኛውን ከሞት ሊያድነው አይችልም፡፡

ጥያቄ፡- ነርቭን በመርፌ በመውጋት ከሚካሄደው ህክምና በተጨማሪ ሌላ ኤች.አይ.ቪ ኤድስን በተሻለ ሁኔታ ሊከላከል የሚችል መድሃኒት አግኝተዋል?

መልስ፡- በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ኪንግደም የሆምፓዝ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ፒተር ቻፕል የፈጠሩትን መድሃኒት በጥቅም ላይ ለማዋል በሙከራ ላይ እገኛለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ይህ መድሃኒት ከአሁን በፊት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህመምተኞች ላይ ተሞክሯል? ውጤቱስ ምንድነው?
መልስ፡- አዎን! ግን ሙከራውን ያደረኩት እኔ ሳልሆን ዶ/ር ቻፕል ናቸው። ዶ/ር ቻፕል በኢትዮጵያ ውስጥ ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጋር በሚኖሩ 200 ሰዎች ላይ ባደረጉት ሙከራ አስደናቂ ውጤት ተገኝቶበታል፡፡ በእርግጥ እስካሁን ያለውን ሁኔታ ከክሊኒካል ሙከራ የዘለለ አይደለም። ግን አዲሱ መድሃኒት እጅግ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ የሰውነትን የሲዲ 4 መጠን ከማንኛውም ጤነኛ ሰው ጋር ለማስተካከል የተቻለ ሲሆን የህመም ስሜቶችም መቀነሳቸው ተረጋግጧል፡፡

ጥያቄ፡- ይህ ከሆነ ታዲያ መድሃኒቱ ከሙከራ አልፎ በመላው ዓለም በስፋት ጥቅም ላይ ለምን አልዋለም?

መልስ፡- መድሃኒቱ እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ ያልዋለው ገንዘብና አስፈላጊው ትብብር ስለተነፈገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዶ/ር ቻፕል መድሃኒቱን የበለጠ ለማሻሻል ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ እኔም በዶክተሩ የተፈጠረውን መድሃኒት በማሻሻል ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ የሚፈውስ መድሃኒት የመፍጠር ሙከራዬን ገፍቼበታለሁ፡፡

Sport: ፌስቡክ እና ትዊተር በእግርኳስ ዓለም

$
0
0

ከጥቂት ዓመታት በፊት የፌስቡክ ኩባንያ ባለስልጣናት አንድ ትልቅ ጉዳይ ነበራቸው፡፡ የክርስቲያኖ ሮናልዶን ወኪሎች ማግኘት እና ተጨዋቹ የፌስቡክ ገፅ እንዲኖረው ማሳመን ዋና አላማቸው ነበር፡፡ ፖርቱጋላዊው ኮከብ የራሱን ገፅ አድራሻ ቢኖረው ‹‹10 ሚሊዮን ተከታዮች›› ሊያፈራ እንደሚችል እያስረዱ ወተወቷቸው፡፡

የሮናልዶን የምስል መብት ተያያዥ ጉዳዮች የሚያስተዳድረውን ፓላሪስ ስፖርትስ የተሰኘ ኩባንያ በሥራ አስኪያጅነት የሚመሩት ሉዊስ ኮሬያ በጊዜው የሆነውን ሁሉ ያስታውሳሉ፡፡ ሮናልዶ ይኖሩታል የተባሉትን የተከታዮች ቁጥር መቀበል ተቸግረው ነበር፡፡ ‹‹አላምናችሁም! የጠቀሳችሁት ቁጥር እና መላ ፖርቹጋልን ያህላል›› ሲሉ የማህበራዊ ድረገፁን ሰዎች ሞገቱ፡፡

cristiano-ronaldo-09
የሆነ ሆኖ በ2009 ሮናልዶ ብዙ ሳይወራበት የፌስቡክ ገፅ ኖረው፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ተጨዋቹ ማንነቷ ካልተገለፀ እንስት ወንድ ልጅ ማግኘቱን በዚሁ ገፁ አወጀ፡፡ ባለፈው ወር ሮናልዶ ከየትኛውም ስፖርተና ቀድሞ የተከታዮቹን ቁጥር 100 ሚሊዮን አድርሷል፡፡ በግለሰብ ደረጃ በአጠቃላይ በፌስቡክ ከሮናልዶ የሚልቅ አንድ ሰው ቢኖር ዘፋኟ ሻኪራ ብቻ ነች፡፡
ሶስት ዓመታትን ቆጥረን ወደኋላ ብንመለስ ብዙዎቹ ትልልቅ ክለቦች የፌስቡክም ሆነ የትዊተር ገፅ አልከፈቱም ነበር፡፡ ዛሬ ሁሉም ገብተውበታል፡፡ እንዲያውም በተለያዩ ቋንቋዎች ከአንድ በላይ ገፆች እየከፈቱ በየደቂቃው አዳዲስ ተከታዮችን መቀበል ቀጥለዋል፡፡ የማንቸስተር ዩናይትዱ የማህበራዊ ድረገፅ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሪቻርድ አርኖልድ ክለባቸው ከፌስቡክ ጋር ከየትኛውም ዝነኛ ግለሰብ ወይም በፕላኔታችን ከሚገኙ የስፖርት ክለቦች ሁሉ የላቀ ቁርኝት እንዳለው ይናገራሉ፡፡
ትልልቆቹ ክለቦችም ሆኑ ከዋክብት ተጨዋቾቻቸው ይህንን የሚያደርጉትበከንቱ አይደለም፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ በዓለም ዙሪያ 659 ሚሊዮን ያህል ደጋፊዎች እንዳሉት ይገለፃል፡፡ ይሁን እንጂ የእግርኳስ ትልቁ ችግር ክለቦች ደጋፊዎቻቸውን እንደሚፈልጉት የሚያገኙበት መንገድ አልነበራቸውም፡፡ አሁን ግን ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም፣ ቻይናስ ዌይቦ እና ሌሎችም ደጋፊዎች ለክለቦች እና ለተጨዋቾች እጅግ ቅርብ እንዲሆኑ አብቅቷቸዋል፡፡ ቀጣዩ ሥራ የደጋፊዎችን ፍቅር ወደ ገንዘብ መቀየር ይመስላል፡፡ ይህ የእግርኳስ ኢንዱስትሪ ቀጣይ ፍላጎት ነው፡፡

እግርኳስ ብዙዎች እንደሚያስቡት ትልቅ ቢዝነስ አይደለም፡፡ ባለፈው ዓመት ሪያል ማድሪድ ያገኘው 521 ሚሊዮን ዩሮ ገቢ በታሪክ ከየትኛውም የስፖርት ክለብ የላቀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ፊንላንዳዊው የፋይናንስ ተንታኝ ማቲያስ ሞቶላ የክለቡን ገቢ ብቻ እንደመመዘኛ ወስዶ አስገራሚ መረጃ ይሰጣል፡፡ ሪያል ማድሪድ በገቢው ብቻ ከተወዳደረ በፊንላንድ 120ኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ኩባንያ ይሆናል፡፡

እግርኳስ ተወዳጅ ስፖርት ነው፡፡ ትልልቅ ክለቦች ደግሞ ስማቸው ይገዝፋል፡፡ እንደ ኢኮኖሚክስ ባለሞያዎች እምነት እግርኳስ የአፍቃሪዎቹን ፍቅር ወደ ገንዘብ ለመቀየር እጅግ ይቸገራል፡፡ ለምሳሌ በኩዋላ ላምፑር የሚኖር እና ስሙ አብዱል የሚባል የማንችስተር ደጋፊን አስቡ፡፡ አብዱል እንኳን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም መታደም ቀርቶ አውሮፓን ረግጦ አያውቅም፡፡ ሆኖም በቅጂ የተሰራ የዩናይትድ ማሊያ ይለብሳል፡፡ የክለቡን ዜናዎች ከኢንተርኔት ያገኛል፡፡ ዩናይትድ ሲጫወት በአካባቢው በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት በቴሌቪዥን ይከታተላል፡፡ ይሁን እንጂ ክለቡ ከአብዱል የሚያገኘው ሰባራ ሳንቲም የለም፡፡ አብዱል የሚባል ሰው ስለመኖሩም ማንችስተር ዩናይትድ ጨርሶ አያውቅም፡፡

ማህበራዊ ሚዲያ ይህንን ሁሉ ይለውጣል፡፡ በፌስቡክ ገፅ በከፈቱ ከ1.3 ቢሊዮን ሰዎች መካከል 500 ሚሊዮን ያህሉ ለእግርኳስ ጠንካራ ስሜት እንዳላቸው የድረገፁ ሥራ አስፈፃሚ ግሌን ሚለር በቅርቡ በርሊን ውስጥ በተዘጋጀ አንድ ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል፡፡

በዓለም ዙሪያ የእግርኳስ አፍቃሪዎች ይበልጥ ጨምረዋል፡፡ የአውሮፓ ትልልቅ ክለቦች ዘግየተውም ቢሆን በቻይና፣ ህንድ፣ አሜሪካ እና ኢንዶኔዢያ በርካታ ደጋፊዎችን ማግኘት ችለዋል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያ ለዚህ ጥሩ ድልድይ ሆኗቸዋል፡፡
ይሁን እንጂ ማህበራዊ ድረገፅ ለእግርኳስ ክለቦች ዕድል ክፉ ሳይሆን ስጋትም ነው፡፡ በእግርኳስ ትልቁ የግብ ምንጭ የቴሌቪዥን መብት ክፍያ እንደመሆኑ ማህበራዊ ድረገፆች ይህንን እንዳያሳጣቸው ይፈራሉ፡፡ ወደ ስታዲየም የሚመጡ ደጋፊዎች ቁጥር እንዳይቀንስባቸውም ይሰጋሉ፡፡ በሌላ በኩል እንደሌሎቹ ኩባንያዎች ሁሉ የማህበራዊ ድረገፆቻቸው በህገወጥ ግለሰቦች ስወር ጥበብ እንዳይሰበሩ ለማረጋገጥ ይተጋሉ፡፡ በ2010 ፌስቡክን የተቀላቀለው ማንችስተር ዩናይትድ 615 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ሲሆን የገፁን ደህንነት በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ አርኖልድ መስክረዋል፡፡
Manchester united
ማህበራዊ ድረገፆች ከውዝግብ ነፃ አይደሉም፡፡ ተጨዋቾች በገፆቻቸው በሚፅፉት ነገር በተደጋጋሚ ራሳቸውን ለችግር ሲዳርጉ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ የኪውፒአሩ ሪዮ ፈርዲናንድ በቅርቡ በትዊተር ገፁ ባሰፈረው ያልተገባ ፅሑፍ ምክንያት በእግርኳስ ማህበሩ እገዳ ተጥሎበታል፡፡ ከ2011 ወዲህ ብቻ ማህበሩ 60 ሰዎችን ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ ቀጥቷል፡፡ የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር እነዚህን ድረገጾች በጥንቃቄ መጠቀም እንደሚያሻ ይናገራሉ፡፡ ‹‹የትዊተር እና ከክለቡ የሚወጡ ምስጢሮች ያሳስቡናል፡፡ ይህ ጉዳይ ቁጥጥር ይፈልጋል››

ተጨዋቾች በይፋ በሚፅፏቸው ጉዳዮች ጣጣ ውስጥ ሲያስገባቸው የተመሰለከተው ሮናልዶ ጥንቃቄ መርጧል፡፡ የፌስቡክ ገፁ በእንግሊዝኛ ነው፡፡ የእርሱ አፍ መፍቻ ቋንቋ ደግሞ ፖርቹጊዝ ነው፡፡ ስለዚህ መፃፍ የሚፈልገውን መልዕክት የፌስቡኩን ገፅ ለሚያስተዳድሩለት ሰዎች ይልካል፡፡ እነርሱ የተሻሉ አቻ ትርጉም ያላቸውን ቃላት ተጠቅመው ራሳቸው ገፁ ላይ ያስቀምጡለታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ራቱን እየተመገበ ከሚገኝበት ሬስቶራንት ፎቶዎችን የሚልክበት ጊዜ ቢኖርም የምስል መብቱን የሚቆጣጠርለት ኩባንያ በሚፈልገው መጠን ብዙ ፎቶ አይልክም፡፡ ክለቦች ተጨዋቾቻቸው በማህበራዊ ድረገፆች ላይ ስለሚፅፉት እና ስለሚያስቀምጡት ምስል እንዲጠነቀቁ አበክረው ማሳሰባቸው የፌስቡክ ባለስልጣናትን ብዙም አያስደስትም፡፡
ይሁን እንጂ እግርኳስ ማህበራዊ ሚዲያን እንደ ቢዝነስ መልካም አጋጣሚ ወስዶታል፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት የጀርመኑ በሩሲያዶርትሙንድ የአሰልጣኙን የርገን ክሎፕ ኮንትራት ማራዘም አስመልክቶ የሰውየውን ፎቶግራፍ በትዊተር ገፁ ላይ አስቀምጦ ነበር፡፡ በፎቶግራፉ ይበልጥ ጎልቶ የሚታየው ግን አሰልጣኙ ፊርማቸውን ያኖሩበት ስታቢሊ የሚል መጠሪያ ያለው ብዕር ነው፡፡ ይህንን በማህበራዊ ሚዲያዎች ያሉ የዶርትሙንድ ደጋፊዎች ሁሉ አስተውለውታል፡፡ በወቅቱ ብዕሩን አምራቹ ሼዋን ስታብሎ የተሰኘ ኩባንያ ባለስልጣናት በሁኔታው እጅግ ተደምመው ነበር፡፡

የማህበራዊ ሚዲያን ጥቅም የተረዳ ክለብ በስፖንሰርሺፕ ክፍያ ብዙ ሊጠቀም ይችላል፡፡ በ2012 ዩናይትድ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ተሳትፎ ማድረግ ከጀመረ በኋላ ከማሊያ ላይ ስፖንሰሩ ቼቭሮሌት ጋር ሪከርድ ሆኖ የተመዘገበ የ47 ሚሊዮን ፓውንድ ዓመታዊ ስምምነት ላይ መድረሱ የአጋጣሚ አይደለም፡፡

እንደ ማንችስተር ዩናይትድ ላለ ትልቅ ክለብ የማህበራዊ ሚዲያ ጥቅም ከስፖንሰርሺፕም ገቢ ይልቃል፡፡ ዩናይትድ እንደ አብዱል ያሉትን ደጋፊዎቹን ማግኘት ይችላል፡፡ የኦልድትራፎርዱ ክለብ እንዲህ አይነቶቹን አፍቃሪዎቹን መመዝገብ ከቻለ ይበልጥ ይገዝፋል፡፡ የተከታዮቹን ማንነት፣ ፍላጎት እና ምርጫ ማጥናት ቀጣይ ሥራ ይሆናል፡፡
በሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች የሚገኙ ኩባንያዎች ፌስቡክ እና ጎግልን በሚገባ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ የተከታዮቻቸውን ወይም የደንበኞቻቸውን ማንነት ይለዩባቸዋል፡፡ ድረገፆቹ አገልግሎታቸውን ለደንበኞቻቸው በነፃ ያቀርባሉ፡፡ ተጠቃሚው ስለ ማንነቱ በነጻ መረጃ ይሰጣል፡፡ በዚህ ሲስተም ውስጥ የእግርኳስ ክለቦች ከሌሎች ኩባንያዎች በተሻለ የመጠቀም ዕድል እንደሚኖራቸው የብራንዲን ባለሙያው ኦሊቨር ኬይዘር ይመሰክራሉ፡፡
ለምሳሌ ትልልቅ ክለቦች ከሌሎች ኩባንያዎች የበለጠ በማህበራዊ ድረገፅ ተከታይ ይኖራቸዋል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ ከናይኪ ወይም ማክዶናልድስ የላቀ ተከታይ አለው፡፡ በሌላ በኩል የእግርኳስ ክለቦች ከሌሎች ኩባንያዎች በተለየ ‹‹ፍቅር እና ታማኝነት›› ይኖረዋል፡፡ ‹‹እንደ ደጋፊ በስሜት የተሞላ አታገኙም፡፡ ማንኛውንም ነገር ያደርጋል›› ይላሉ ኬይዘር፡፡ ደጋፊ በኮምፒዩተር መስኮቱ ጨዋታ በሚያይበት ወቅት ብታገኙት በስሜቱ ጫፍ ላይ ትይዙታላችሁ፡፡ ‹‹ብልጥ የሆነ ክለብ ምናልባት ለወደፊቱ ሌላውን ኩባንያ እንዲህ ሲል ታደምጡ ይሆናል፡፡ ማነህ እኔን 25 ሚሊዮን ደጋፊዎች ፈልገህ ነው? እኛ ራሳችን እንፈልጋቸዋለን›› ይላሉ ኬይዘር፡፡

ክለቦች አሁን የተከታዮቻቸውን እና የደጋፊዎቻቸውን ማንነት የሚለዩላቸውን ሚዲያዎች እንዲሁም ድረገፆች ለመጠቀም በርት ያሉ ባለሙያዎችን እየቀረጠሩ ይገኛሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የክለቦች ባለስልጣናት ስለ ደንበኞች ጉዳይ አስተዳደር ደጋግመው ሲናገሩ መስማት ተለምዷል፡፡ የጁቬንቱስ የገቢ ጉዳዮች አስፈፃሚ ፈራንቼስኮ ካልቮ እና አንጋፋው የትምባሆ ኩባንያ ባለሙያ ፊሊፕ ሞሪስ በጋራ ደንበኞቻቸውን ለመጥቀም የተሻለውን ስትራቴጂ እንደሚከተሉ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ደጋፊዎችን እኛ ወደ አዘጋጀነው መዋቅር እንዲመጡ እንፈልጋለን፡፡ በዚያ መልኩ ይመዘገባሉ፡፡ ደጋፊዎቻችንን ለይቶ ማወቅ እና በእነርሱ ላይ ተፅዕኖ ማድረግ ከፍተኛ ገንዘብ ለማግኘት እጅግ ወሳኝ ነው›› ይላሉ፡፡
ክለቦች ደጋፊዎቻቸውን ማንነት ጠንቅቀው ማወቅ አለባቸው፡፡ በትዊተር ‹‹አብዱል ከኩሞላ ላምፑር›› ከሚለው አልፎ የ12 ዓመት ታዳጊ ነው? ወይስ የ42 ዓመት ጎልማሳ? ምን ያህል ገቢ ያገኛል? ምን ሊገዛ ይችላል? እነዚህ መረጃዎች አብዱልን ደጋፊ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ምንጭ ያደርጉታል፡፡


ቲዮ ዋልኮት በአርሰናል መቆየቱ ያጠራጥራል * 18 ወራት ብቻ ቀርተውታል

$
0
0

ባለፉት ወራት ኢምሬትስ ስታዲየም አስደሳች ድባብ አልነበረውም፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ያልተጠበቁ ሽንፈቶች አስተናግዶ አሰልጣኙ አርሰን ቬንገርን የበዛ ጫና ውስጥ ያስገባቸው ቡድን ከመልካም ነገሮቹ ይልቅ እንከኖቹ ይበዛሉ፡፡ የተከላካይ ክፍሉ የጥራት ብቻ ሳይሆን የአማራጮችም እጥረት አለበት፡፡ አማካይ ክፍሉ በተጨዋቾች ጉዳት መታመሱን ቀጥሏል፡፡ በሜዳ ላይ በንፅፅር የተሻለው ነገር የአጥቂዎቹ ጥሩ የሚባል ብቃት ላይ መገኘት ይመስላል፡፡
walcote
ከጉዳት ገና ከመመለሱ ጎሎች ማስቆጠር የጀመረው ኢሊቪዬ ዢሩ ከመልካም ብቃት ላይ ይገኛል፡፡ ዳኒ ዌልቤክ ኳስ ከመረብ ያለማገናኘት ድክመቱ እንዳለ ሆኖ ከተቀሩት የቡድን ጓደኞቹ ጋር የፈጠረው ድንቅ ጥምረት ሁልጊዜም ለተጋጣሚ ቡድን አደጋ ፈጣሪ አድርጎታል፡፡ አሌክሲስ ሳንቼስ ባልዋዠቀ ብቃት መጫወት ብቻ ሳይሆን ወሳኝ ጎሎችን ማግኘት ቀጥሏል፡፡ ሌላው ቀርቶ ብዙም ተስፋ ያልተጣለበት ያሳኖጎ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የደጋፊዎችን ልብ ማግኘት ጀምሯል፡፡ በዚህ ላይ የአሌክስ ኦክስሌድ ቼምበርሌይን እየተሻሻለ መመጣት የመድፈኞቹን የማጥቃት ኃይል የማይናቅ አድርጎታል፡፡ እነዚህ ለውጦች በኢምሬትስ ቲዮ ዋልኮት እንዲዘነጋ እያደረጉት ይመስላሉ፡፡

በእርግጥ የአርሰናል ደጋፊዎች ዋልኮትን ጨርሰው ሊረሱት አይችሉም፡፡ ባለፈው ወር በርንሊን ሲገጥሙ ለ10 ደቂቃዎችም ቢሆን ወደ ሜዳ ተመልሶ አይተውታል፡፡ ወዲያው በኢንተርናሽናል ጨዋታ ወቅት ያስተናገደው የብሽሽት ጉዳት አሰልጣኙ እንዳሰቡት እንዳይጠቀሙበት ሰበብ ሆኗል፡፡

የዋልኮት ዳግመኛ ጉዳት የፈጠረው ችግር አስተዳደራዊ ፈተናም አለው፡፡ እንግሊዛዊውን በኤምሬትስ የሚያቆየው ኮንትራት ሊጠናቀቅ የሚቀሩት 18 ወራት ብቻ ናቸው፡፡ ቬንገር ቲዮን ለማቆየት ጥረት መጀመራቸውን ቢናገሩም ድርድሩ የት እንደደረሰ ወሬ የለም፡፡ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የክለቡ ደጋፊዎች ግን ሁኔታዎች እየሄዱበት ያለው መንገድ ስጋትፈ ጥሮባቸዋል፡፡ የዋልኮት ወቅታዊ የኮንትራት ሁኔታ በ2012 በካሪ ሳኛ ከነበረበት ጋር እጅጉን ይመሳሰላል፡፡ በጊዜው የአርሰናል ባለስልጣናት ዕድሜው 30 ሊሞላ ከተቃረበው ፈረንሳዊ ተከላካይ ጋር ውል ለማራዘም ብዙ እንደሚያስቸኩል አላመነበትም ነበር፡፡ በወቅቱ ሳኛ ልክ እንደ ዋልኮት ከከባድ ጉዳት መመለሱ ነበር፡፡ ስለዚህ የአርሰናል ሰዎች በሁለት እግሮቹ ላይ ከደረሰበት ስብራት ያገገመው ተጨዋች ወደ ብቃቱ መመለስ ስለመቻሉ ጊዜ ወስደው ማረጋገጥ ፈለጉ፡፡ ኮንትራቱን ለማራዘም መቸኮል እንደሌለባቸውም አመኑ፡፡ በዚህ ሰበብ ውሉን አዘገዩት፡፡ መድፈኞቹ አሁን የዋልኮትን ድርድር ቢቀጥሉ የተጨዋቹ አማካሪዎች ከበድ ያሉ ጥያቄዎች እንደሚያቀርቡላቸው አውቀዋል፡፡ ስለዚህም ምላሽ ከመስጠታቸው በፊት የዋልኮት የጉልበት ጉዳት በቀጣይ ውጤታማነቱ ላይ ችግር እንደሚያመጣ ማረጋገጥ ይሻሉ፡፡

በሳኛ ጉዳይ የክለቡ ሰዎች ዘግይተውም ቢሆን ፉልባኩ ወደ ብቃቱ መመለስ እንደሚችል አረጋግጠው ነበር፡፡ ኮንትራቱ 18 ወራት እየቀረውም አዲስ ውል አቅርበውለታል፡፡ ዋልኮት ግን ከወዲሁ እዚያ ቀሪ ጊዜ ላይ ደርሷል፡፡ ስለዚህም ተጨዋቹ ኮንትራትጉዳት አርሰናል ፈጣን እርምጃ መውሰድ ያለበት ይመስላል፡፡ ተጫዋቹ በመጪው ጃንዋሪ አርሰናልን የመልቀቅ እድል ባይኖረውም እስከ ክረምቱ በኮንትራቱ ዙሪያ የሚኖሩት ለውጦች የክለቡ ቆይታውን ይወስናሉ፡፡

በእርግጥ የጉልበት ጉዳት አደገኛ ነው፡፡ የተጨዋቾችን ቀጣይ የእግርኳስ ህይወት የሚወሰንባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ነገር ግን የዋልኮት ዕድሜ አደጋውን ለመቋቋም የተመቸ ነው፡፡ ቬንገር ቲዮን ለማቆየት የሚደረገው ድርድር ፈታኝ እንደሚሆን የተረዱ ይመስላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ብዙ የተጓተተው የተጨዋቹ ኮንትራት ፊርማ በስምምነት ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኙ የብዕሩ ቀለም መድረቁን የገቡለትን ቃል ወደ ጎን ማለታቸውን የሚናገሩ ወገኖች አሉ፡፡ በጊዜው ዋልኮት ውሉን ለማራዘም ያስቀመጣቸው ጠንካራ ቅድመ ሁኔታዎች በወቅቱ ቡድኑ ከነበረበት ችግር አንጻር አርሰናልን አቅመ ቢስ አስመስለውት ነበር፡፡

በ2012/13 ሮበን ቫን ፔርሲን አጥቶ የተቸገረው አርሰናል ሉካስ ፖዶልስኪን እና ኦሊቪዮ ዢሩን አምጥቶ ዠርቪንሆን ደግሞ በሀሰተኛ 9 ቁጥር ሚና እየሞከረ ይገኝ ነበር፡፡ ስለዚህም ዋልኮት የአጥቂነት ሚና ለማግኘት የበዛ ጫና መፍጠር ችሏል፡፡ ሆላንዳዊውን አምበላቸውን ሸኝተው ብዙ የተወቀሱት ቪንገርም በቀጣይ ዋልኮትን አጥተው ራሳቸውን ለተቺዎች ማመቻቸት አልፈለጉም፡፡ ስለዚህም የፊት መስመር ዕድል ለሰጡት ተስማምተው እንግሊዛዊው ፊርማውን አኑሯል፡፡

አሁን ግን ዋልኮት የቀደመ ጠንካራ ተፅዕኖው አዝኖት የለውም፡፡ ዌልቤክ እና ሳንቼዝን በአጥቂው ክፍል የጨመረው አርሰናል በቁጥር ብቻ ሳይሆን በጥራትም ተሻሽሏል፡፡ እንደቀደመው ጊዜ በዋልኮት ፍጥነት እና ሰብሮ የመግባት ብቃት ላይ ጥገኛ አይደለም፡፡ ቬንገር እነዚህ የዋልኮት ብቃቶች በፊት መስመር ከአንድም በሁለት ተጨዋቾቻቸው ላይ አግኝተዋቸዋል፡፡
ዘንድሮ በውድድር ዘመኑ ጅማሬ ይህ ሁሉ አልነበረም፡፡ በሴፕቴምበር ቬንገር ከቲዮ ጋር የሚደረገው ድርድር ቀላል አለመሆኑን ሲናገሩ ምክንያታቸው የገንዘብ ጉዳይ አልነበረም፡፡ ዋልኮት ደጋግሞ በይፋ እንደተናገረው የፊት አጥቂ መሆን ይፈልጋል፡፡ ባለፈው ጊዜ በንፅፅር የአጭር ጊዜ ኮንትራት ማራዘሚያ መፈረሙም ዋልኮት የተገባለትን ቃል ተፈፃሚነት ለማየት ጥንቃቄ ማድረግ መምረጡን ያሳያል፡፡

በእርግጥ ቬንገር እድሉን በጥቂቱም ቢሆን ሰጥተውት ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ግን ተጨዋቹን ወደ ቀድሞው ቦታው የመስመር አማካይነት መለሱት፡፡ በእርግጥ በእንቅስቃሴ መሀል አርሰናል ሲያጠቃ ወደፊት እየተጠጋ ዢሩን እንዲያጣምር ነፃነት ሰጥተውታል፡፡ አሁን የቲዮ እንቅፋት ዌልቤክ ይመስላል፡፡ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ልጅ ዋልኮት ሊሰራ የሚችለውን ባልተናነሰ መልኩ ይሰራል፡፡ ሳንቼዝ ስዋንሲ ላይ ጎል ሲያስቆጥር ያቀበለው ኳስ እና ሌሎችም ውጤታማ ሙከራዎቹ ይህንን ይመሰክራሉ፡፡

ዌልቤክ ከዋልኮት የሚሻልባቸው ነጥቦችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዳኒ የተሻለ ጉልበተኛ እና በመከላከል አጨዋወቱም ጥሩ የሚባል ነው፡፡ በዌስትብሮም ጨዋታ የትኛውም የአርሰናል ተጨዋች ዌልቤክን ያህል ሸርተቴ አልወረደም፡፡ በተለይ ዢሩ ወደ ሜዳ ከተመለሰ በኋላ ራሱ ዢሩ፣ ዌልቤክ፣ አሌክሳስ እና አሮን ራምሴይ ፍጥነት የቀላቀለ የአንድ ኳስ ቅብብል ሲፈፅሙ ተስተውለዋል፡፡ ዋልኮት ለቡድኑ ይህንን ያደርጋል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል፡፡

አርሰናል ሳንቼዝን ከጨመረ በኋላ የሚታወቅበትን በቡድን ቅብብል ላይ የተመሰረተ ጨዋታ በቺሊያዊው የአጨዋወት ባህርይ ምክንያት በጥቂቱም ቢሆን ተመሳሳይ ችግር የሚጨምርባቸውን ዋልኮት በተመሳሳይ ጊዜ በበላይኛው የቡድኑ መስመር እንዲገኛ ለመፍቀድ ሊያቅማሙ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ በአሌክሲስ፣ ዢሩ እና ዌልቤክ የሚቀናጀው የአርሰናል የፊት መስመር የሜዳውን ስፋት ያለመጠቀም ችግር ይስተዋልበታል፡፡ ዋልኮት ለዚህ ጥሩ መፍትሄ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ኦክስሌድ ቻምበርሌይንም ይህንን ማድረግ ይችላል፡፡

ይህ ሁሉ ግን ዋልኮትን በአርሰናል አላስፈላጊ ወይም ትርፍ ተጨዋች አያደርገውም፡፡ የቬንገር ቡድን እንደማንኛውም ለክብር የሚፎካከር ቡድን አማራጮች ያስፈልጉታል፡፡ በተለይ የውድድር ዘመኑ እየገፋ ሲመጣ ከተጠባባቂ ወንበርም ቢሆን እየተነሱ ውጤት የሚለውጡ ከዋክብት ይሻል፡፡ አርሰናል ሳውዛምፕተንን ለመርታት ብዙ ሲቸገር ዢሩ እና ፖዶልስኪ ከተጠባባቂ ወንበር ተነስተው ውጤት ሲለውጡ ታይተዋል፡፡

አጓጊው ነገር ክለቡ እና ተጨዋቹ የተሻለ ስምምነት ላይ መድረስ ይችሉ ይሆን? የሚለው ነው፡፡ ዋልኮት ከክለቡ ከፍተኛ ተከፋዮች ጎን የሚያስቀምጠውን ደመወዝ መጤቁ አይቀሬ ይመስላል፡፡ አርሰናል ስምምነት ላይ ለመድረስ ከተጨዋቹ የሜዳ ላይ አስተዋፅኦ ሌላ የምስል መብቱ ለክለቡ ገቢ የሚኖረውን ተፅዕኖ ከግምት ማስገባቱ እንደማይቀር መገመት ይቻላል፡፡ ዋልኮት በአውሮፓ ምስላቸው ለገበያ የተመቹ ከሚሰኙ ተመራጭ ተጨዋቾች መካከል ይጠቀሳል፡፡ ይህንን የተጨዋቹ ወኪሎችም አይነጉም፡፡ ስለዚህ እነዚህ እውነታዎች የአርሰናልን ተደራዳሪዎች ይበልጥ ይፈትናሉ፡፡

ምናልባት አንድ መረሳት የሌለበት ጉዳይ አርሰናል ዘንድሮ የጎል ዕድሎችን ፍሬያማ ለማድረግ እየተቸገረ ይገኛል፡፡ ቲዮ ደግሞ በዚህ በኩል የተመሰከረለት ምርጥ ጎል ጨራሽ ነው፡፡ ነገር ግን ጎል ጨራሽነት ለአርሰናል ቤት የተለየ ቦታ እንደሚያስገኝ በፖዶልስኪ ማየት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ብዙ የአርሰናል ደጋፊዎች አሁንም በወረቀት ላይ ያጓጓቸውን የሜሱት ኦዚል እና ዋልኮት አስፈሪ ጥምረት በሜዳ ላይ ማየት ይሻሉ፡፡ ምናልባት ቲዮ ራሱ ይህንን መጠቀም ከፈለገ እና በ2012/13 የፈጠረውን ተሰሚነት መልሶ ለማግኘት ከጓጓ የኮንትራት ድርድሩን ቀለል ያደርገው ይሆናል፡፡ በአርሰናል አጣሁት የሚለውን የፊት መስመር ሚና ከመድፈኞቹ ከፍ ባለ ደረጃ ላይ በሚገኝ ሌላ ክለብ በፍፁም እንደማያገኘው ክለቡም በኢምሬትስ መቆየትን ይመርጥ ይሆናል፡፡

Health: የቆዳ እርጅናን ለመከላከል 4 ጠቃሚ መመሪያዎች

$
0
0

ሊሊ ሞገስ

ቆዳችን ያለንበትን የጤና ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ መግለፅ የሚችል የአካላችን ክፍል ነው፡፡ ጤናማ ቆዳ አስተውላችሁ ከሆነ በተፈጥሮ በጣም ለስላሳ፣ የሚያበራ(Glow)፣ ከሁሉም ቦታ እኩል የውጥረት(Tone) ደረጃ ያለው፣ ከምንም አይነት ሽፍታና የቆዳ እክሎች የጠራ ሆኖ እናያለን፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው የተቆጣ ቆዳ በተለይ ለሌላው በሚታየው ክፍላችን ላይ ማለትም እንደ ፊትና እጅ የመሳሰሉት ላይ ሲታይ በጣም ያስጨንቃል፤ ይረብሻልም፡፡
israela-avitu
ግን ለምንድን ነው ቆዳ የሚታመመው? ባሉት መረጃዎች መሰረት ይህ ነው የሚባል አንድ መልስ የለም፡፡ ነገር ግን ለቆዳ መቆጣትና ለተለያየ የቆዳ ችግሮች እንደ መንስኤ ከሚጠቀሱት ውስጥ በዋነኛነት ዘመናዊ የአኗኗር ዘዴ የሚፈጥረው ጫና እና አካላዊ ውጥረት(Physical stress) ተፅዕኖዎች ቅድሚያ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል የአካባቢ ብክለት በስራችንና በኑሮአችን ምክንያት የሚፈጠር ውጥረት፣ በየምግቦቻችን፣ የመዋቢያና የመፀዳጃ ዕቃዎች ውስጥ የሚገቡ ከጤና አኳያ አላስፈላጊ የሆኑ ኬሚካሎች ወዘተ… ሲሆኑ ይህ ሁሉ ግብዓት እንደ ኮክቴል ሆኖ በአካላችን ስርዓት ላይ እንደ ውርጅብኝ ይወርዳል፤ የአካላችንን በሽታ የመከላከል አቅሙን ያዳክሙታል፡፡ በተለይ ደግሞ ስር የሰደዱ የጤና ችግሮች ካሉ ተደራርቦ የዚህ ሁሉ ጫና ውጤት በቆዳችን ላይ ይንፀባረቃል፡፡

ይህንን የቆዳ ችግር ለመፍታት ግን ይሄ ነው የሚባል አንድ የምግብ አይነት ብቻ እንዳለ ብነግራችሁ ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ጉዳዩ ግን ሌላ ነው፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ግን አመጋገብና የአኗኗር ዘዴአችን በቆዳችን ጤንነት ማለትም እንደአንዱ የአካላችን ትልቁ ክፍል ስራውን በትክክል መስራት እንዲችል፣ የማርጀት ፍጥነቱ ላይ የቆዳ ችግሮችን መበርታትና የመዳን ፍጥነት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንዳለው ነው፡፡

ስለዚህ ልክ እንደወትሮ ስለምግብ አይነቶችና ስለ አመጋገብ ከመግለፄ በፊት የቆዳችን ስራ ምን እንደሆነና እንዴት እንደሚሰራ በቅድሚያ መገንዘቡ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡

 

የቆዳችን አገልግሎት

ቆዳችን በሰውነታችን ውስጥ ከሚገኙ ክፍሎች ውስጥ እጅግ በጣም ትልቁ ሲሆን በአማካይ ወደ 2.7 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ ቆዳችን ከሚያከናውናቸው ስራዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. የመከላከል ሥራ (Protection) 

የመጀመሪያው የቆዳችን ሥራ የተለያዩ የአካላችንን ክፍሎች ከውጫዊው ዓለም ጥቃት መከላከል ነው፡፡ ቆዳችን ሙሉ ለሙሉ የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ስርዓት (immune sysetem) ዋና ክፍል ነው፡፡

በሚደንቅ ሁኔታ ቆዳችን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ከዓይን በማይታዩ ባክቴሪያዎች የተሸፈነ ነው፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች ምንም አይነት ጉዳት በቆዳችን ላይ ሳያስከትሉ በሰላምና በተድላ በቆዳችን ላይ ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች ታዲያ ምንድን ነው የሚሰሩት አትሉም? ስራቸውማ በሚገርም ሁኔታ ጎጂ ባክቴሪያዎችን መዋጋትና ጥቃት መከላከል ነው፡፡

ሌላው የመከላከል ስራ አካል የሆኑት ደግሞ በቆዳ ህዋሶች መካከል ተቀብረው አካላችንን የሚጎዱ ጎጂ ህዋሳቶች ሲመጡ ለበሽታ መከላከል ስርዓት መረጃ የሚያቀብሉ ላንገር ሐንስ (Langerhans) የሚባሉ የህዋስ አይነቶች አሉ፡፡ በእነዚህ ህዋሶች በመታገዝ የሰውነታችን በሽታ መከላከል ስርዓት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

2. የሰውነትን ሙቀት መቆጣጠር

ሌላው የቆዳችን ስራ እና ችሎታ ደግሞ የሰውነትን ሙቀት መቆጣጠር ሲሆን የአካባቢያችን ሙቀት በጣም በትንሹ ቢቀየር እንኳን በቀላሉ መለየት ይችላል፡፡ ታዲያ የአካባቢያችንን የሙቀት መጠን መረጃ ለአዕምሮአችን በመላክ የሰውነት የሙቀት ደረጃ እንዲስተካከል ይረዳል፡፡

በቅዝቃዜ ወቅት አዕምሮአችን ለቆዳችን ትዕዛዝ በማስተላለፍ በቆዳችን ስር ያሉትን የደም ስሮች እንዲጠቡ በማድረግና ከቆዳ የላይኛው ክፍል ርቀው ወደታች ዝቅ በማለት ሙቀት ከሰውነታችን እንዳይባክን ከማድረግ በተጨማሪ ቅዝቃዜው ቢበረታ ደግሞ ጡንቻዎቻችን እንዲቀጠቀጡ በማድረግ ሰውነታችን ራሱ ሙቀት እንዲያመነጭ ያደርጋል፡፡

በሙቀት ጊዜ ደግሞ በተቃራኒው ለቆዳችን መልዕክት በመላክ ቀጫጭን የደም ስሮቻችን እንዲሰፉ በማድረግ ከልክ ያለፈ ሙቀት በቆዳችን አማካኝነት እንዲወገድ ከማድረግ በተጨማሪ የላብ አመንጭ ዕጢዎች ላብ እንዲያመነጩ በማድረግ ሰውነት እንዲቀዘቅዝ ያደርጋል፡፡

3. እንደ የስሜት ህዋስ ክፍል ያገለግላል

በቆዳችን ላይ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ነርቮች ሲኖሩ በዋናነት አራት ነገሮችን እንድንለይ ያደርጋሉ፡፡ ሙቀት፣ ቅዝቃዜን፣ ንክኪን እና ህመምን፡፡ በንክኪ ላይ ብቻ ሻካራን፣ ለስላሳን፣ ግፊትን የመሳሰሉ የተለያዩ ንክኪዎችን የሚለዩ የነርቭ ህዋሶች አሉ፡፡

4. ቫይታሚን ማምረት

ሌላው የሚደንቀው የቆዳችን ስራ ደግሞ ፀሐይ ስንሞቅ ሙቀቱን ተጠቅሞ ቫይታሚን ዲ ማምረቱ ነው፡፡ ይህንን የሚሰራው  ጠቃሚ ኮሌስትሮልን ወደ ቫይታሚን ዲ 3 በመቀየር ከዚያም በጉበትና ኩላሊት እገዛ አማካኝነት ዲ 3 ወደ አክቲቭ ወደሆነው ስሬቱ እንዲቀየር ያደርጋል፡፡

የቆዳችን አወቃቀር ምን ይመስላል?

ጤናማ ቆዳ እንዲኖረን ከፈለግን የቆዳችንን አፈጣጠር እና ስራ ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ቆዳችን በሶስት ንብርብር ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡ እነርሱም የላይኛው ክፍል(ኤፒደርሚስ)፣ የመካከለኛው ክፍል(ደርሚስ) እና የታችኛው ክፍል(ሐይፓደርሚስ ወይም ሰብኩታንዬስ) በመባል ይታወቃል፡፡

1. የላይኛው የቆዳ ክፍል(ኤፒደርሚስ)

ይህኛው የቆዳችን ክፍል ከላይ የምናየው ክፍል ሲሆን ውፍረቱ በቆዳችን ላይ ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ያህል የተረከዝና የመዳፍ ቆዳ ላይ ይህ ክፍል ከ1-5 ሚ.ሜ ውፍረት ሲኖረው በዓይናችን ቆብ ላይ ደግሞ 0.5 ሚ.ሜ ያህል ውፍረት ይኖረዋል፡፡

ይህ ክፍል ብቻውን እስት ንብርብር ክፍሎች ሲኖሩት በዚህ ንብርብር ውስጥ አንደኛ የሚባለው በውጭ የሚታየው ነው፡፡ አምስተኛው ደግ የንብርብሩ የታችኛው ክፍል ነው፡፡ በአንደኛው ክፍል ውስጥ የሚገኙት ህዋሶች ጠፍጣፋና ከሞቱ ህዋሶች የተሰሩ ሲሆን በየጊዜው እየተሸረሸሩ የሚራገፉ ናቸው፡፡ ይኸውም በአማካይ በየሁለት ሳምንቱ በመርገፍ በአዲስ ይተካል፡፡ የመጨረሻውና አምስተኛው ደግሞ አዳዲስ ህዋሶች የሚወለዱበት ክፍል ሲሆን አዳዲስ ህዋሶች ተወልደው እስኪያድጉ ድረስ በንብርብሩ ውስጥ ከአምስተኛው ወደ አንደኛው ክፍል ሽቅብ ይጓዛሉ፡፡ በመጨረሻም አርጅተው አንደኛ ክፍል ላይ ይወገዳሉ፡፡

የቆዳችንን ቀለም የሚያመርቱ ሜላኖሳይት፣ ጎጂ ህዋሳትን ለይተው የሚጠቀሙ ላንጋርሐንስ የተባሉት ህዋሶችና ሌሎች ምንነታቸው የማይታወቁ ህዋሶችም የዚሁ የኤፒዲርሚስ የተባለው ቆዳ ክፍል አካሎች ናቸው፡፡

2. የመካከለኛው የቆዳ ክፍል(ደርሚስ)

ይኸኛው የቆዳ ክፍል ከላይኛው (ኤፒደርሚስ) ከ10-40 ጊዜ እጥፍ ውፍረት ያለው ነው፡፡ ይህ የቆዳ ክፍል ሲታይ ወጣ ገባ የበዛበት ሲሆን በውስጡም የተለያዩ የደም ስሮች፣ ነርቮች ኮላዲንና ኢላስቲንን የሚያመነጭ ፋይብሮ ብላስት የሚባሉ ህዋሶች፣ የወዝ ማመንጫ ዕጢዎች፣ ፀጉርና የፀጉር ስሮች፣ የላብ ማመንጫ ዕጢዎችና ቱቦዎቻቸውን ይዞ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የምናገኛቸውን ኮላጅንና አላስቲን በዋነኛነት የቆዳችንን ውጥረት፣ የመለጠጥ አቅም ወዘተ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

3. የታችኛው የቆዳ ክፍል(ሐይፓደርሚስ)

ይህ ክፍል ደግሞ ከሁሉም ክፍሎች ወፍራሙና ትልቅ የሆነ ሲሆን የተሰራውም በዋነኛነት ከኮላጅን ስሮችና ስብን ከሚያጠራቅሙ ህዋሶች ነው፡፡ በዚህ ክፍል የሚጠራቀመው ላብ በተወሰነ ደረጃ ስንቀመጥ ስንጋደም ምቾት ከመፍጠር በተጨማሪ የኃይልና የሙቀት ምንጭም ሆኖ ያገለግላል፡፡ የሰውነታችን ክብደት ሲጨምር በእነዚህ ህዋሶች ውስጥ የሚጠራቀመው የስብ መጠን ይጨምራል፡፡ ስለዚህ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ በማድረግና አመጋገብን በማስተካከል የላቡን መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡

የቆዳ እርጅና ሒደት

የቆዳን እርጅና ማስቆም ባይቻልም የእርጅናውን ፍጥነት(Aging Speed) ግን ማዘግየት ይቻላል፡፡

ቆዳ እንዴት እንደሚያረጅ ለማወቅ ከላይ የተብራሩትን የቆዳ አፈጣጠርና ዋና ዋና ክፍሎቹን ማወቅ ግድ ይላል፡፡ በዚህ መሰረት እያንዳንዱ የቆዳ ንብርብር ክፍሎች የሚያረጁበት አካሄድም ይለያያል፡፡

የላይኛው የቆዳ ክፍል(Epidermis) እርጅና

የቆዳ የላይኛው ክፍል ሲያረጅ የቆዳን ቀለም የሚፈጥሩ ህዋሶች ቁጥር መቀነስን ያስከትላል፡፡ እነዚህ ህዋሶች ሜላኒን የተሰኘውን የቆዳ ቀለም የሚያመነጩ ሲሆን የእነርሱ ቁጥር አነሰ ማለት የሜላኒን መጠን ቀነሰ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቆዳችን የፀሐይ ጨረርን(Ultraviolet ray) መቋቋም እንዲያዳግተው ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቆዳችን ላይ በሚገኙ ፍሪራዲካሎች መጠቃትና በቆዳ ካንሰር እስከ መያዝ ያደርሳል፡፡

ሌላው በዚህ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ላንገርሐንስ የተባሉ የተህዋሲያን መምጣትን የሚያሳውቁ ህዋሶች ቁጥር መቀነስ ሲሆን ይህም ተህዋሲያን በቆዳ ላይ ሲያርፉ በፍጥነት በሽታን የመከላከል ስርዓትን(Immune sysetem) የማሳወቅ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡

በተጨማሪ ይህ የላይኛው የቆዳ ክፍል ወዙን እና ውጥረቱን(tone) ያጣል፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የላይኛው የቆዳ ክፍል ከመካከለኛው(Dermis) ከሚባለው የቆዳ ክፍል ተነስተው ጫፋቸው በላይኛው የቆዳ ክፍል(Epidermis) ብቅ ብቅ ከሚሉት የደም ስሮች ውጭ የራሱ የሆነ በውስጡ የተዘረጉ የደም ስሮች የሉትም፡፡ በመሆኑም ቆዳ ሲያረጅ በዚህ ክፍል እና በመካከለኛው ክፍል መካከል መለያየት(መራራቅ) ይፈጠራል፡፡ በዚህም ምክንያት በቂ አየርና ንጥረ ነገሮች ስለማይደርሱት ህይወት አልባ ቆዳ ይሆናል፡፡ 

የመካከለኛው የቆዳ ክፍል (Dermis) እርጅና

በዚህኛው የቆዳ ጤና ላይ እርጅና የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ስንመለከት በዋነኛነት የቆዳን የመጠንና ባህሪ (የልጅ ቆዳ) የምንለውን ባህሪ የሚያሳጡት የኮላጅን እና ኢላስቲን መጠን መቀነስ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ኮላጅንን የሚያመርቱ ፋይብሮ ብላስት የተባሉ የህዋስ አይነቶች መኮማተር መጀመር ነው፡፡ ሌላው ኮላጅን ራሱ መቅጠን ይጀምራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሜታሎ ፕሮቲኔዝ የተባለ ኢንዛይም መጠን በቆዳ እርጅና ጊዜ መጠኑ ስለሚጨምር ኮላጅንን በመሰባበር የቆዳን የመለጠጥ ችሎታውን ይቀንሰዋል፡፡

ሌላው በዚህ ክፍል እርጅና ጊዜ የሚታየው ለውጥ ደግሞ የደም ዝውውር ስለሚቀንስ የአየርና የጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ማግኘትም ተያይዞ ይቀንሳል፡፡ ለዚህም ነው በእርጅና ጊዜ ቆዳ የመገርጣትና የመቀዝቀዝ ባህሪ የሚያሳየው፡፡

የታችኛው የቆዳ ክፍል እርጅና

ይህኛው የቆዳ ክፍል ደግሞ ላብ የሚከማችበት ክፍል ሲሆን በእርጅና ጊዜ የላብ ክምችቱ ይቀንሳል፡፡ ይህም የቆዳውን ሞላ የማለት ባህሪ ያዳጣዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቅዝቃዜን የመቋቋም አቅሙ ይቀንሳል፡፡

የቆዳን እርጅና የሚያፋጥኑ ነገሮች ምንድን ናቸው?

የቆዳን እርጅና ከሚያፋጥኑ ነገሮች ውስጥ በዋነኛነት የሚጠቀሰው የቆዳ ህዋሶች በፍሪ ራዲካሎች መጠቃት ነው፡፡ ስለ ፍሪ ራዲካሎች ባለፈው ወር እትም ላይ በዝርዝር ያየን ስለሆነ ጠለቅ ብለን አንገባበትም፡፡ ለማስታወስ ያህል ግን ፍሪ ራዲካሎች ያልተረጋጉ፣ የኤክትሮን ጥማት ያለባቸው ባዕድ ኬሚካሎች ሲሆኑ የሚፈልጉትን ኤሌክትሮን ለመስረቅ ሲሉ ከህዋሶቻችን ጋር ይጋጫሉ፡፡ በዚህ ሂደትም ህዋሶቻችን ይጎዳሉ፡፡ ይህም ጉዳት ህዋሶች ዳግመኛ በትክክል ስራቸውን መስራት እስኪያቅታቸውና ይህም የህዋሶች የመራባት ሂደትን አውኮ ወደ የካንሰር በሽታ እስከማምጣት የሚያደርሱ ናቸው፡፡

ፍሪ ራዲካሎች በተወሰነ ደረጃ በተፈጥሮ ሰውነታችን ውስጥ የሚመረቱ ሲሆን በብዛትና በአደገኛ ሁኔታ ደግሞ የሚመረቱት ሰውነት ጎጂና መርዛማ የሆኑ ነገሮችን በምግብ፣ በመጠጥ፣ በሲጋራና ሌሎች ሱስ አስያዥ ነገሮች፣ በመድሃኒት፣ በተለያዩ ኬሚካሎች አጠቃቀም ምክንያት ወደ አካላችን ሲገቡ እነርሱን ለመሰባበር በሚያደርገው ጥረት ፍሪ ራዲካሎች በብዛት ይመረታሉ፡፡ ይህንን የፍሪ ራዲካሎች ምርት ለመቀነስ ግን በዋነኛነት ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ስርዓትና የአኗኗር ዘዴ መከተሉ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፡፡

ሌላው የቆዳን እርጅና የሚያፋጥኑ ነገር ግን ብዙም የማይወራለት ነገር ደግሞ ጣፋጭ ምግቦችና መጠጦችን በተለይ የታሸጉ ምርቶችን መጠቀም ሲሆን እነዚህ የምግብ አይነቶች የሚይዙት የተጣራ የካርቦሃይድሬት ምግቦችን ጨምሮ አዘውትሮ መመገብ የቆዳን እርጅና ያፋጥናል፡፡

የተጣራ የካርቦሐይድሬት ምግቦች የምንላቸው ስንል ደግሞ ገለባቸው የወጣላቸው እንደ የነጭ ዱቄት ምርቶች ማለትም ነጭ ዳቦ፣ ነጭ ፓስታ፣ በፈጣን ሁኔታ የሚዘጋጁ ምግቦችን ያካትታል፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የምግብ አይነቶች በውስጣቸው ከልክ በላይ የሆነ ስኳር የያዙ ሲሆን በኢንሱሊን አማካኝነት ስኳር በፍጥነት  በሰውነታችን እንዲመጠጥ ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ከጊዜ በኋላ ሰውነታችን ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንዲጋለጥ ከማድረግ በተጨማሪ በቆዳችን ውስጥ ያሉትን የኮላጅንና ኢላስቲንን ስሮች በማስተሳሰርና በማጣበቅ የመለጠጥ ባህሪያቸውን ያሳጣል ብሎም የመሰባበር ባህሪ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ የቆዳ መሸብሸብን ያስከትላል፡፡ ስለዚህ ከተጣራ የካርቦሐይድሬቶችን ከመጠቀም ይልቅ እህሉን እንዳለ ፈጭቶ መጠቀም እንደዚሁ ጣፋጭ ምግብና መጠጦችን ቀንሶ በልክ ብቻ ማድረጉ ይመከራል፡፡

ገዥው ፓርቲ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና እየፈጸመ እንደሆነ በተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።

$
0
0

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል።

ከካድሬዎቹ ማስፈራሪያዎች መካከል፦<>የሚሉት ይገኙበታል። <>ተብሏልም።።

tplfበግድ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑና ኢህአዴግን እንዲመርጡ እየተገደዱ መሆናቸውንም የገለጹ በርካቶች ናቸው። ከዚህም በላይ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች ኢህአዴግ አንዳንድ ሰዎችን ያለፍላጎታቸው በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎቻቸው ጫና በመፍጠር ለሱ እንዲሰሩለት በማስጠንቀቅ በየምርጫ ጣቢያው በገለልተኛ ስም ማስቀመጡ የተጋለጠ ሲሆን፤ ሰዎቹ-ከተቃዋሚዎች ጥያቄ ቢቀርብላቸው <>የሚል ምላሽ ይሰጡ ዘንድ መመሪያ እንደተነገራቸው ተሰምቷል።

በተመሳሳይ ምርጫውን ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስርና ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል። ታህሳስ 27/2007 ዓ,ም በባህርዳር ከተማ የኢትዮጰያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መድረክ አባላት – በስርዓቱ አገልጋዮች ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።

ታፍነው ከተወሰዱት የመድረክ አባላት መካከል፤ አቶ ቴዎድሮስ መለስ፤ ወ/ሮ ሪዒማ ከድር፤ በባህር ዳር ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው አቶ ተፈራ ማሙና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን፤ የታፈኑበት ምክንያትም ሆነ ፤ያሉበት ስፍራ እስካሁን ድረስ አልታወቀም።

እንዲሁም ” ኢቲቪ ውሸታም ነው ፣ ኢህአዴግ ሌበ ነው”ብለሀል ተብሎ ክስ የተመሰረተበትና የሶስት ዓመት እስራት የተፈረደበት የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን፤ በእስር ቤት ከፍተኛ ድብደባና ግርፋት እየተፈጸመበት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። የደቡብ ወሎ የመኢአድ አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን ፍርደኛ እስረኛ ሆኖ ከድብደባና ግርፋት ማረፍ አለመቻሉ፤ በኢትዮጰያ እስር ቤቶች ለሚፈጸሙ የከፉ ሰብ ዓዊ መብት ጥሰቶች አንድ ማሳያ ነው ብለዋል-መረጃውን ያደረሱን የመኢአድ አባል።

ከሰሞኑ ብቻ ብቻ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አባላት የፐጻርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ወደቤታቸው ሲያቀኑ መደብደባቸው እና በወላይታ የሰማያዊ ፓርቲ አስተረባባሪዎች መታሰራቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ፓርቲና የኢትዮጰያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች ላይ በተለይም በሰማያዊ፣ በአንድነትና በ መ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ የሚፈጽሙትን ዛቻና በደል እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግቧል

ፓርቲዎቹ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ‹‹በምርጫ ዋዜማ በፓርቲዎች ላይ የሚደርሰው ደባና ዛቻ በአስቸኳይ ይቁም›› በሚል በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ ሰማያዊ ፓርቲ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ በመሆኑ፣ እንዲሁም መኢአድና አንድነት ብቃት ያላቸው ልሂቃንን ማፍራት በመቻላቸው ስጋት የተፈጠረበት ገዥው ፓርቲ – ፓርቲዎቹን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑን በመጥቀስ፤<> ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው-ገዥው ፓርቲ -በፓርቲዎቹ ላይ እየፈጸመ ካለው ድርጊት እንዲቆጠብ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድመረ ከገዥው ፓርቲ መሳሪያነት ወጥቶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ፤ አሣስበዋል፡፡

Source:: Ethsat

ደቡብ ኦሞ ውስጥ በአርብቶ አደሮችና በፖሊስ መካከል ግችት ተቀስቅሶ የነዋሪዎችና የፖሊሶች ህይወት ጠፋ፤ ግጭቱና ውጥረቱ ሊቆም አልቻለም።

$
0
0

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን አመር ወረዳ- ላላ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ አርብቶ አደሮችና- በፖሊስ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ነፍስ መጥፋቱን ነገረ ኢትዮጰያ ዘገበ፡፡

2000px-Southern_Nations,_Nationalities,_and_People's_Region_in_Ethiopia.svgጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ትናንት ጥር 7/2007 ዓ.ም <> በማለት ፖሊስ- አርብቶ አደሮቹ ገዳዩን አሳልፈው እንዲሰጡት በጠየቀበት ወቅት ነው ግጭቱ የተነሳው።

በአርብቶ አደሮችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ከሁለቱም ወገን የሰው ህይዎት መጥፋቱንና የቆሰሉም እንደሚገኝበት የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ገልጸዋል፡፡

ከዞኑ ፖሊስ ሻለቃ ለማ አሸናፊ የተባሉ የፖሊስ ባልደረባ በአርብቶ አደሮች ሲገደሉ፤ የዞኑ የፀጥታና የፍትሕ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጩመሬ የረር፣ እና የዞኑ የፖሊስ አባል የሆነው ወታደር ተሰማ መሰረት ቆስለው ደቡብ ኦሞ ዞን ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በግጭቱ ምክንያትም ከዲመካ ከተማ ቀይ አፈር ወደ ተባለው ከተማ የሚወስደው እንዲሁም ከቱሚ ወደ ዲመካ ከተማ የሚወስደው መንገድ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተዘግቷል። በአሁኑ ወቅት የዞኑ ዋና ከተማ በሆነው የጅንካ ከተማ እና ዲመካ፣ ቱኒ፣ ቀይ አፈር እና ኦሞራቴ ከተሞች ውጥረት መንገሱን አቶ ግርማ በቀለ ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲልም በአካባቢው ተመሳሳይ ችግሮች እንደሚፈጠሩ ያወሱት ሊቀመንበሩ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ ግጭቶች ሲፈጠሩ በባህላዊ መንገድ የሚፈቱ ሆነው ሳለ ፤ መንግስት ባህላቸውን ግምት ውስጥ ሳያስገባና የአገር ሽማግሌዎችን ሳያናግር በአርብቶ አደሮቹ ላይ እርምጃ በመውሰዱ፤ ታጣቂዎች የሆኑት የአካባቢው አርብቶአደሮች ምላሻቸውን በኃይል እንደገለጹ አስረድተዋል፡፡
‹‹በአብዛኛው ግጭት የሚከሰተው የአካባቢውን የግጭት አፈታት ወደጎን በመተው ችግሩን በኃይል ለመፍታት በሚጥረው መንግስት ነው›› ያሉት አቶ ግርማ የአሁኑ ግጭትም የተነሳው በመንግስት ችግር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አቶ ግርማ በቀለ አክለውም ‹‹ችግሩን በኃይል ለመፍታት የሚጥረው መንግስት ተጨማሪ የሰው ነፍስ እንዳይጠፋና ወደ እርስ በእርስ ግጭት እንዳያመራ አሁንም ከኃይል እርምጃው ተቆጥቦ ችግሩ በአካባቢው የግጭት አፈታት እንዲፈታ ማድረግ አለበት›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ትናንት ጠዋት ላይ የተጀመረው የአርብቶ አደሮችና- የፖሊስ ግጭት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልቆመም።

Source:: Ethsat

“አንድነትና መኢአድ ጋር ያለው ችግር ተወግዶ ወደ ምርጫው እንዲገቡ ያስፈልጋል።

$
0
0

unnamedምርጫ ቦርድም ነገሩን በቅንነት በማየት ጥቃቅን ግድፈቶችን ቸል በማለት ወደ ምርጫው እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን:: …. እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን ለሚገነባው የመድብለ ፓርቲ( multi-party) ሲስተምና ለሃገሪቷም ትልቅ ውድቀት ይሆናል።”

“ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት በባለስልጣኖች ይፈጸማል። ሳይውል ሳያድር በዜጎች ላይ በደል የሚያደርሱት ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።የሰብአዊ መብት ጥሰት ከባድ ወንጀልና ሃጢያትም ነውና።”

ዳንኤል ጣሰው በአለም ዙሪያ ወንጌልን የሚሰብኩ አለምቀፍ ወንጌላዊ ነው። ሰላምን መግባባት በአገራችን ኢትዮጵያ ይሰፍን ዘንድ፣ የፊታችን የ2007 ምርጫ ሁሉንም ባሳተፈና ፍትህዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ፣  እንደ ፍርድ ቤት ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማት ሁሉን በእክሉነት እንዲያስተናግዱና መንግስት የሚያደርጋቸው የልማት እንቅስቃሴዎች ቢደገፉም ሰብዓዊ መብት መርገጡን እንዲያቆም ጠይቋል። ወንጌላዊ ዳነልል ጥሰው በፌስ ቡክ የለቀቅትን ጽሁፍ ለማንበብ እንሆ

ፍትህና ሰላም በምርጫ 2007 –  ወንጌላዊ ዳንኤል ጣሰው

ክርስቲያኖች ለሀገር መሪዎችና ለሰላም እንድንጸልይ ታዘናል።እርቅን፥መግባባትን ማወጅ ሃላፊነታችን ነው፤የሚያስተራርቁ ብጹአን ናቸው ተብሎ ተጽፏልና::

በቅርቡ በሀገራችን ምርጫ ይካሄዳል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፉክክር፥ክርክር፥ውድድር ይኖራሉ።አንዳንዴም በሌላውም ዓለም እንደሚታየው መረር ያሉና መስመር ሊያስለቅቁ የሚችሉ ሽኩቻ ስድብና በጥላቻ ላይ የተመሰረታ ዘመቻ ይታያል።ከዚህም በፊት በሀገራችን ብዙ ሰዎች የሞቱበት አሳዛኝ ሁኔታ ተከስቶ ነበር።ያ እንዲደገም አንፈልግም።ለሰላምና ለመግባባት እንጸልያለን።

ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ውድድር ማድረግ እንዲችሉ ሜዳውን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ማመቻቸት ይጠበቅበታል። ምርጫ ቦርድ፥ፍርድ ቤትና ሚዲያው ሁሉንም እኩል የሚያስተናግዱ ሊሆን ይገባል።ኢትዮጵያ የምታድገው የተለያዩ ሃሳቦች ተፋጭተው ከውድድር በሚገኝ የነጠረ አስተሳሰብ ነው።ተቃዋሚ ሲኖር ለገዢው ፓርቲ መስተዋት ይሆናሉ፤ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋሉ፤ሙስናን ሌሎች ህገወጥነትን ያጋልጣሉ።ተወዳድረው ከተመረጡ ደግሞ ሀገር የመምራት እድል ያገኛሉ።

የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እንግልትና እስራት በተለያዩ ባለስልጣኖች ይደርስባቸዋል።እነዚህ በአግባቡ ታይተው መፍትሄ ሊበጅላቸው ይገባል።ወንጀል የሰሩና ያልሰሩ መለየት አለባቸው።ባልተጣራ ሁኔታና በግል ቂም በቀል ንጹህ ሰው በፍጹም መንገላታት የለበትም።

መንግስት ምንም አላደረገም ማለት አይቻልም።ሀገሪቷ ከቀደሙት መንግስታት የተሻለ የዲሞክራሲ ብልጭታ ታይቶባታል።ሆኖም ግን ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት በባለስልጣኖች ይፈጸማል። ሳይውል ሳያድር በዜጎች ላይ በደል የሚያደርሱት ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።የሰብአዊ መብት ጥሰት ከባድ ወንጀልና ሃጢያትም ነውና።
ሰሞኑን በአንዳንድ ፓርቲዎችና በምርጫ ቦርድ መካከል ያለው መቃቃር በሰላምና በመግባባት እንዲያልቅ እንጸልያለን።
እነዚህ ፓርቲዎች ክፍተኛ ዝግጅት አድርገው ለመወዳደር ተነስተዋል፤አንዳንድ ግድፈቶች አሉ ከተባለ በማለፍ በተቻለ መጠን ምርጫውን እንዲካፈሉ መንግስት መጣር አለበት።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመካከላቸው የሚነሱትን ልዩነቶች ብስለት በተሞላበት መንገድ በውይይት መፍታትና አንድነት መፍጠር ሀገራዊ ግዴታቸው መሆኑን በውሉ ሊያጤኑት ይገባል። በአንዳንዶች የምናየው ስር የሰደደ ጥላቻ፥ስድብ፥የሰውን ስብእና ማዋረድና ዘረኝነት መግባባትንና እርቅን ይጎዳልና በአስቸኳይ መቆም አለበት።
በሀገራችን የዲሞክራሲ ግንባታ ትልቅ ሚና የሚጫወቱና ባሁን ሰአት ካሉት ፓርቲዎች ሁሉ በተሻለ ደረጃ ላይ ካሉት ከአንድነትና መኢአድ ጋር ያለው ችግር ተወግዶ ወደ ምርጫው እንዲገቡ ያስፈልጋል። ምርጫ ቦርድም ነገሩን በቅንነት በማየት ጥቃቅን ግድፈቶችን ቸል በማለት ወደ ምርጫው እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን ለሚገነባው የመድብለ ፓርቲ( multi-party) ሲስተምና ለሃገሪቷም ትልቅ ውድቀት ይሆናል።እነዚህም ፓርቲዎች በሰላማዊ ትግል ላይ ተስፋ ይቆርጣሉ።እነርሱ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነት(Civil Disobedience) እንገባለን እያሉ ነው፤በዚህም ሀገሪቷ ወደ አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ የምትገባ ሲሆን ይህ ደግሞ የሚካሄዱትን የልማት ስራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያዳክም ይችላል።
ዛሬ በኢትዮጵያ አንዱ የጎደለው ነገር ቅንነት ነው።ቅንነት ከሌለ መጨቃጨቅ፥መካሰስ፥ፍርድ ቤት መንከራተት ብቻ ይሆናል።አንዱ አንዱን ለማጥቃት ሰበብና ምክንያት ብቻ ነው የሚፈልገው፤አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱትም አይነሳምና። ስለሆነም ችግሮች ሁሉ የሚፈቱት በመነጋገርና በመከባበር ነው።ያለፈውን በደል ይቅርታ በመጠያየቅ ህዝባችን ከድህነት የሚወጣበትን መንገድ ማፋጠን እንጂ እኛ ለስማችንና ለክብራችን ስንከራከር ህዝብ ማለቅ የለበትም።
እግዚአብሔርም ይሄን አይወድም፤ይቅር ተባባሉ፥ተከባበሩ፥ክፉን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አትሸነፉ ነው ያለው።ሌላ አማራጭ የለም።
“እርስ በርስ መግባባት፥ሀገርን መገንባት” መርሃችን ይሁን።
አብያተ ክርስቲያናትና የሃይማኖት ተቋማት እውነትን በፍቅር የመናገር ሃላፊነትና ግዴታ አለባቸው። ቅንነት ለኢትዮጵያ!
ፍቅርና ፍትህ ለኢትዮጵያ!
ዳንኤል ጣሰው
ከኢትዮጵያ ተነሺ አብሪ

ቁርሾ – (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

$
0
0

crime
ይህ ታሪክ ለብዙዎች ድራማ እስኪመስላቸው ድረስ ሲያስገርማቸው የኖረ ታሪክ ነው፡፡ በሀገራችን በአብዛኛው ብሔሮች ዘንድ ሰፍኖ የኖረው ቂም በቀልና የጥቁር ደም ባህል ምን ያህል የሰው ልጅን አርቆ አሳቢነት እንደሚፈትንና ከሰብአዊ አስተሳሰብ እንደሚያወጣ ጭምር የሚመሰክር የወንጀል ታሪክ ነው ይሉታል ብዙዎች፡፡ ከአስር ዓመት በፊት የተፈፀመ ቢሆንም ወንጀሉን መዝግቦ የተቀመጠው ሰነድ ግን አሁን ድረስ ለሁሉም መማሪያ የሚሆነውን ቁም ነገር አስቀርቷል፡፡

1980 ዓ.ም
ደራ
ሰሜን ሸዋ

ፍቼን ተሻግሮ ጀሊሳን አልፎ ወደ ጎሐፅዮን በሚወስደው መንገድ ላይ የሚመጣው ደራ ከተማ ለስሙ ከተማ ይባል እንጂ የመሰረተ ልማትም ሆነ ለከተማ ብቁ የሚያስብለው መዋቅር የተሟላለት ስፍራ አይደለም፡፡ ደራ የሚኖሩትን ሰዎ የታችኞቹን ህዝቦች ‹ደሮዬ› ብለው ይጠሯቸዋል በተለምዶ፡፡ ደሮዬዎች በአብዛኛው የአማራ ተወላጆች ሲሆኑ ‹ቆፍጣናና እንቢ ባይነት ባህሪያቸው የሆነ ነው› ይሏቸዋል ሲገልጿቸው፡፡ ከደገምና ከጀሊሳ አካባቢ ያሉ ሰዎች ሲመራቸውና ከሰው ተጣልተው ደም ሲቃቡ የሚሸሹት ወደዚህ ደራ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ደራ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ የነበረው ስፍራ በመሆኑ ለመሸፈት የሚመች አካባቢ ስለሆነ ነው፡፡ ደራ በአካባቢው ባሉ የኦሮሞ ተወላጆች ዘንድ እንደ ጀግና ምሽ የሚታይ ጫካ ነበር፡፡ (የዛሬን አያድርገውና)፡፡ ብዙዎች የጀግኖች ጀግና ነው እያሉ የሚያሞካሹትና በአፄ ኃ/ሥላሴ ጊዜ የነበረውን ግፍ ተቃውመው ከሸፈቱት የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጆች አንዱ የነበረው ሀገሬ ቱሉ መደበቂያ ቦታ ነበር ይላሉ፡፡ ሀገሬ ቱሉ በአብዛኛው የደገምና አካባቢው ነዋሪ ዘንድ ‹የድሃ ጠበቃ› ሲባል በሌሎች ዘንድ ደግሞ ዘራፊ ሽፍታ ነው ይሉታል፡፡ እዚያ ደራ ጫካ ውስጥ መሽጎ የአካባቢውን ጭቃ ሹሞችና ባለቤቶች ድንገት አደጋ ጥሎ እየገደለና እየዘረፈ ለሌሎች ያከፋፍል ነበር ይባላል- ሀብትና ከብት፡፡
በዚህ አካባቢ ልማድ ጥቃት ክፉ በትር ነው፡፡ ባለነፍጥ የሆነው ህዝብ በደም ከተፈላለገ ያንን የጥቁር ደም ሰንሰለት የሚበጥስ አንዳች ነገር የለም፡፡ የለገሰ በዳ ታሪክም የሚመዘዘው ከዚሁ የመጠላለፍና የመጠባበቅ ማህበራዊ ተራክቦ ውስጥ ነው፡፡ ለገሰ በዳኔ በ1980 ዓ.ም የ26 ዓመት ወጣት ሆኗል፡፡ ነገር ግን እሱ የ2 ዓመት ልጅ ሳለ በ1956 ዓ.ም አካባቢ አባቱ በዳኔ ቱፋ እንዴት ህይወታቸው እንዳለፈ በአክስቱ ሲነገረው የኖውን ዕውነት ነው ይዞ ያደገው፡፡ እነሆ ያ ታሪክ፡፡

1956 ዓ.ም
መስከረም ወር

ደገም አካባቢ ባሉ የኦሮሞ ተወላጆች ዘንድ በታላቅ ጉጉት ይጠበቅ የነበረው የመስቀል በዓል እየተቃረበ ነው፡፡ ገና ነሐሴ አጋማሽ ላይ ክረምቱ ግም ብሎ እንደገባ ግም ብሎ እየወጣ ሳለ ነው አካባቢው በአደይ አበባና በለምለም ሜዳው ፍንትው ብሎ የሚታየው፡፡ ይህ የአዲስ ዘመን መምጫ ብስራት ለመቀበልና ለማቀባበል ወጣቶቹ ዱላቸውን ይዘው ጅራፋቸውን እያጮሁ ‹‹መስቀላ ሞቲን አያና›› ይላሉ፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ይህን የመስቀል በዓል ለማክበር ቀድመው የሚዘጋጁትና እየጨፈሩ የሚዘልቁት ቢያንስ ከ16 ቀን በላይ ለሆነ ጊዜ ነው፡፡ የመጨረሻው የመስቀል በዓል እስኪከበር ድረስ፡፡ ከዘመን መለዋጫ በዓለም በላይ የሆነ ክብር ያለውን ይህንን ቀን ለማክበር ወዲህ ወዲያ ሲሉ ከነበሩት ወጣቶች አንዱ ደግሞ በዳኔ ቱፋ ነው፡፡

በዳኔ የተዳረው ገና የ18 ዓመት ወጣት ሳለ ነው አባቱ ቱፋ ጎዳና በአካባቢያቸው የታወቁ ገበሬ ናቸውና በሰው ዘንድ ያላቸው ክብር የላቀ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ዘራቸው ከባላበትና ከፍ ካለው የኦሮሞ ብሔር ወገን ባይሆንም አቶ ቱፋ በኃይለኝነታቸው የሚነካቸውና የሚደርስባቸው የሌላቸው የተከበሩ ሰው ናቸው፡፡ እኚህ ሰው ከወለዷቸው አራት ልጆች መካከል አንደኛው ልጅ ብቻ ወንድ ሲሆን ሶስቱ ሴቶች ናቸው፡፡ በኦሮሞ ባህል ወንድ ልጅ ሲወለድ በከፍተኛ ስነ ስርዓትና በጥይት ተኩስ ነው ደስታ የሚገለፀው፡፡ ወንድ የወለደ አባት ‹‹የወንድ አባት›› ተብሎ ይከበራል፡፡ ይህ ኩራትም አቶ ቱፋ ቤት ገባ፡፡
ልጃቸውን በዳኔ አሉት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሙሉ መሆን የቻሉት የመሰላቸው፡፡ ለዚህ ነው በዳኔን በቶሎ የዳሩት፡፡ በዳኔ ወንድ ልጅ ወልዶ ለማየት የነበራቸው ህልም እንደተመኙት ከሁለት ዓመት በኋላ ተሳካላቸው፡፡ የ20 ዓት ልጅ ሳለ ካገባት ኮረዳ የመጀመሪያውን ልጅ አገኘ፡፡ በቤተሰቡ ዘንድ ደስታና ፌሽታ ሆነ፡፡ ለገሰ አሉት ይህን ልጅ፡፡ አቶ ቱፋ በዓይናቸው ሁለት ወንድ ልጆቻቸውን አይተው ደግሞ ሌላ እንዲመጣላቸው በመመኘት ላይ ሳሉ ነው ያልታሰበ ነገር የተፈጠረው፡፡ ልጃቸው በዳኔ አደጋ ውስጥ ወደቀ፡፡

በዚያን የፀደይ ወር መስከረም ጠብቶ መስቀል ሞቲን አያና ተከብሮ ሲያልቅ አንድ ሰው በበዳኔ ላይ ዓይኑን ጣለ፡፡ በዳኔ ገና የ22 ዓመት ወጣት ሳለ ሚስቱም ሁለተኛ ልጇን በፀነሰችበት ወቅት ቱሉ ሲጠብቀው የነበረው ቀን መጣለት፡፡ በዳኔን አብዝቶ ይጠላው ነበርና አንድ ቀን ከዚህች ዓለም ጋር ያለውን የኮንትራት ሕይወት ሊያቆራርጥበት አጥብቆ ይመኝ ነበር፡፡
የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የበዳኔ ሚስት ናት፡፡ ጊፍቲ በአካባቢው ጎልማሶች ዘንድ ዓይን ውስጥ የገባችና ያም ይሄም የኔ በሆነች ብሎ የሚሳሳላትና የሚመኛት ሴት ነበረች፡፡ ይህች ወጣት ገና በ16 ዓመቷ ሊያገቧት የሚራኮቱባትን ጎረምሶች በመፍራት ከቤቷ ሳትወጣ ያደገች ናት፡፡ ይህ የመጣው ደግሞ አባቷ የተላከባቸውን ‹ልጅዎን ለልጄ› የሚል ጥያቄ ሁሉ አይሆንም ብለው በመመለሳቸው ሳቢያ ነው፡፡ ከጎረምሶቹ ሁሉ አብልጦ ይወዳት የነበረው ቱቦ በአባቱ በተመረጡለት ሽማግሌዎች አማካኝነት ልጅቷን አስጠይቆ የግሉ ለማድረግ ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም፡፡ ምንም አማራጭ አልነበረውም፡፡ በቁጭትና በንዴት መሀል ሆኖ አንድ ቀን ውጪ ቢያገኛት እንደሚጠልፋት እያሰበ ሳለ አስደንጋጭ ወሬ ሰማ፡፡ በዳኔ ሊያገባት ነው ተባለ፡፡ በዳኔ በእኒያ ባለግርማ ሞገስ አባቱ የተነሳ የተመኘው ተሳክቶለት የጊፍቲን አባት ስምምነት አግኝቷል፡፡ የጊፍቲ አባት ለአቶ ቱፋ ‹ልጅን ለልጄ› የሚል ጥያቄ አሉታዊ ምላሽ የሚሰጡበት ጊዜ አልነበራቸውም፡፡

ለስንቱ ከልክዬ እችላለሁ ብለው ለሚያከብሯቸው ወዳጃቸው ልጅ ፈቀዱ፡፡ በአካባቢው ይህ ጉዳይ ወሬ ሆኖ ተሰማ፡፡ ቱሉ አንጀቱ አረረ፡፡ በበዳኔ ሰርግ ጊዜ የአጨዳ ስራ አለብኝ ብሎ በማሳበብ በሰርጉ ላይ ሳይገኝ ቀረ፡፡ ወደ ሌላ ከተማ ዘልቆ ነበር የጠፋው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እሱም ሳያገባ በዳኔም የወንድ ልጅ አባት ሆኖ ሁለተኛ ልጁን ሊደግም ሲጠባበቅ ሳለ ነው ቱሉ ንዴት የገነፈለበትና ራሱን መቆጣጣር ያቃተው፡፡ የመስቀል በዓል ተከብሮ እንዳለቀ መስከረም 22 ቀን የሆነው ሆነ፡፡
ቱሉ አደፈጠ፡፡ በዳኔ ደግሞ ጀሊሳ ወደተባለ መንደር የሚወርድበት ጉዳይ እንዳለው መረጃ ደርሶታል፡፡ ከ6 ሰዓት ያላነሰ የሚያስኬደው የእግር መንገድ ተከትሎ ብቻውን እያንጎራጎረ ወደ መንገዱ የገባው በዳኔ ከ30 ደቂቃ በላይ ሳይጓዝ ነው ድንገት ጭው ባለው አፋፍ ላይ ቱሉ ከች ያለበት፡፡ ቱሉ በዳኔ ፊት ለፊት ቺኮዝ ጠመንጃውን ወድፎ ሲቆም በዳኔ ዓይኑን ተጠራጠረ፡፡ ቱሉ ሊገድለው እስኪፈልግ ድረስ ቂም ይይዝብኛል ብሎ አልገመተም፡፡ ይህን ቢያውቅ አባቱ ለገሰን ሲወልድ የሰጡትን ጠመንጃ ይዞ በወጣ- ለዚያውም ውውል ጠመንጃ፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ተቀደመ፡፡

በአንድ ጥይት ደረቱን የበሳው ተኩስ የኋልዮሽ ቁልቁለቱ ላይ ዘረረው፡፡ የአካባቢው ወፎች በርግገው እስኪጠፉ ድረስ በድምጿ እየሰነጠቀችው ጥይት በበዳኔ ልብ ላይ ከተሳበች በኋላ ፀጥ አለች፡፡ ቱሉ ከአካባቢው ጫካ ጫካውን አቆራርጦ ተሰወረ፡፡ ከዚያ በኋላ አንድም ሰው አላወቀም፡፡ ቱሉ አረቄ ቤት ገብቶ ቀኑን ሙሉ ሲዘፍን ነበር የዋለው፡፡ የበዳኔ አስከሬን በነጋዴዎች ተገኝቶ ጉዳዩ ሲሰማ ጊዜ ግን አካባቢው ተተራመሰ፡፡

አቶ ቱፋ ጠመንጃቸውን ይዘው ወጥተው አገር ይያዝልኝ አሉ፡፡ ቱሉ ማንም ባይጠረጥረውም ሁኔታው ሲያስፈራው አመሻሹ ላይ ጠፋ፡፡ በማግስቱ የቱሉ ቀብር ላይ አለመኖር ሲታወቅ ነው ገዳዩ እሱ መሆኑ የተረጋገጠው፡፡ በዳኔ በታላቅ ስርዓት ታጅቦ በተኩስ ተጋግሎ በዋለ ቀብር ግብአተ መሬቱ ሲፈፀም የቱሉ ቤተሰቦችም በቁጣው ለመሸሽ ሀገር ለቀው ጠፉ፡፡ የበዳኔ ቤተሰቦች የቱሉን ወለጆች ቤትና ንብረት በእሳት አቃጥለው ከብቶቻቸውም ገድለው ጠፉ፡፡ አገሩ ተረባበሸ፡፡ ደራ ጫካ ቱሉ ተደብቆበታል ተብሎ ስለታሰበ ታመሰ፡፡ ልጁ ግን አልተገኘም፡፡

ከጊዜ በኋላ በቱሉ ጥፋት ወላጆች መቀጣት የለባቸውም ተብሎ ትልቅ ሽምግልና ተካሄደና የቱሉ ቤተሰቦች ወደቅያቸው እንዲመለሱ ተፈቀደ፡፡ ያም ሆኖ ስጋት ቤተሰቡን መጫኑ አልቀረም፡፡ ጥቁር ደም አንድ ዕለት ድንገት ለዚያ የፈሰሰ ደም በቀል ይህን ቤት ማንኳኳቱ እንደማይቀር ይታወቅ ነበር፡፡

ጊዜ የሁሉም ችግር መፍትሄ ነውና አቶ ቱፋ በልጃቸው ሞት የደረሰባቸውን ሀዘን መቋም ባለመቻላቸው ሳቢያ ህይወታቸው አለፈ፡፡ አሁን የቀሩት የሟቹ እህቶች ብቻ ናቸው፡፡ ዘመን እያለፈ በሄደ ቁጥር ወሬው የደበዘዘና የተረሳ መሰለ፡፡ ነገር ግን የሟችን ልጅ ለገሰ በዳኔን ባሳደገችው የሟች እህት ዘንድ ይህ ቂም አልረገበም፡፡

የቱሉን ቤተሰቦች ባየች ቁጥር ሁሌም ሟች ወንድሟ እየታሰባት እንደተሳቀቀች ኖራለች፡፡ ይህን ደግሞ ለህፃኑ ለገሰ እየነገረች አሳድጋዋለች፡፡ ‹‹የአባትህ ገዳዮች ቤት ያውልህ- የአባትህን ገዳይ አባት ይኸውል- ወደነርሱ አጠገብ እንዳትደርስ›› ወዘተ… እያለች ነበር ያሳደገችው፡፡ ለገሰ በዚህ የበቀል መርዝ ተመርዞ ነው ዕድሜውን የቆጠረው፡፡ አክስቲቱ አርፋ አልተቀመጠችም፡፡ አንዳንዴ ቱሉ እቤት መጥቶ ቤተሰቦቹ ጋር አድሮ ሌሊት ሄደ ሲባል እየሰማች- አንዳንዴ ታይቶበታል የሚባልበትን ቦታ እያጠናች ኖረች፡፡ አንድ ወቅት ግን ቱሉ ጫንጮ ውስጥ እንደሚኖር ደረሰችበት፡፡ ሚስት አግብቶ ቤት መስርቶ ይኖራል፡፡ ይህን የነገራት ደግሞ አንድ የደገም ተወላጅ የሆነ ወዳጇ ነው፡፡ አሁን የበቀል ጉማ የሚረከብበትን ወቅት አሰበች፡፡

1980 ዓ.ም

ለገሰ የ24 ዓመት ወጣት ሆኗል፡፡ አባቱን በዳኔን የመሰለ ጉብል፡፡ ፀጉሩና መልኩ ከእናቱ የተወረሰ ቁመናው ግን እንደ አባቱ የተዘነከተ ሰው፡፡ ይህን ጉልበትና በአባቱ በቀል ቂም የነደደ ልቡን ይዞ ተነሳ፡፡ አክስቱ መክራ ላከችው፡፡ በደንብ ያጠናችው የጫንጮን ከተማ አካባቢውን ሁሉ አስረግጣ ነግራ በመኪና ተሳፍራ ቦታውን አሳይታው ተመለሰች፡፡ የዘመናት ምኞቷ ሊሰምር መሆኑን አስባ በውስጧ ፈንድቃለች፡፡

1980 ሐምሌ ወር
ጫንጮ

አንድ ወጣት ኮስመን ያለ ገፅታውን ይዞ የነቱሉን ቤት አንኳኳ፡፡ የ48 ዓመት ጎልማሳው ቱሉ ነበር በር የከፈተው፡፡ በሩ ላይ የቆመው አሳዛኝ ገፅታ ያለው ወጣት በኦሮምኛ ‹‹እባካችሁ ከብት እረኛ ትፈልጉ ከሆነ ማደሪያ ስጡኝና አብሬያችሁ እየኖርኩ እረኛ ልሁን›› ብሎ ጠየቀ፡፡ ቱሉ በሩ ድረስ የመጣለትን ሲሳይ በዋዛ ሊያልፈው አልፈለገም፡፡ ልጁን አስገባው፡፡ ለእግሩ ውሃ ለሚባለው ደግሞ ትኩስ እንጀራ እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡
ከዚያም ስለ አመጣጡ ሁኔታ ጠየቀው፡፡ ወጣቱ ከገብረጉራቻ መምጣቱንና ሥራ ፍለጋ ሲንከራተት መኖሩን ተናግሮ መጠጊያ ብቻ እንደሚፈልግ በመግለፅ የሰውየውን ቀልብ ሳበ፡፡ ከዚያ በኋላ የእረኝነት ስራውን በሚገባው መጠን መፈፀም ጀመረ፡፡ የቤተሰቡ አባላት ወደውት ልጆቹ እንደ ወንድማቸው አይተውት ቱሉም አቅርቦት እረኝነቱ 2 ወር አለፈው፡፡ ይህ ወጣት ለገሰ ነው፡፡

ከአክስቱ ጋር የነጋገረው ቀን ደረሰ፡፡ መስከረም 22 ቀን፡፡ ልክ አባቱ የሞተበት ቀን፡፡ ቱሉ በዳኔን የገደለበት ቀን፡፡ በዚያን ዕለት ደግሞ ቱሉ ጫንጮ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን የሚሄድበት ጉዳይ ነበረው፡፡ ከዋናው መንገድ ራቅ ብሎ በማሳ ውስጥ ባለ ቀጭን መንገድ የሚያመራው የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ቱሉ ከሚኖርበት ስፍራ ራቅ ይላል፡፡ ለገሰ የዛሬው እረኝነቱ ነገር አለበት፡፡ ከብቶቹን ከቤት ያወጣቸው ገና በማለዳ ነው፡፡ 12፡00 ሰዓት በረት ከፍቶ ሲወጣ እነ ቱሉ ‹ጎበዝ› ብለውታል በልባቸው፡፡ ይህን ጉብዝናውን መስክረውለታል፡፡ እሱ ግን ዕቅድ አለው፡፡ ከብቶቹን በፍጥነት እያካለበ ሜዳ አደረሳቸው፡፡ ከዚያም ቶሎ ብሎ ተመለሰ፡፡ ወገቡ ውስጥ የሻጣት ጥልቆ መኖሯን አረጋግጧል፡፡ በጋቢው ሸፍኗታል፡፡ ቀኑ ጭጋግ ውጦታል፡፡ ይህ ደግሞ ለርሱ ተመችቶታል፡፡ በነቱሉ ቤት እና በቤተክርስቲያኑ መሀል የተዘረጋው መንገድ ላይ ዘወር ያለ ቁጥቋጦ የወረሰው ቦታ አለ፡፡ እዚያ ስፍራ ላይ ጥጉን ይዞ አደፈጠ፡፡ ለ1 ሰዓት ሩብ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ቱሉ ፈጠን ፈጠን እያለ በቆቅ ዓይኑ አካባቢውን ገርመም እያደረገ ዱላውን በትከሻው አንግቶ መጣ፡፡ ከሩቅ ይታየዋል፡፡ ጎፈሬ ፀጉሩ አሁንም አስፈሪ አድርጎታል፡፡ ለገሰ ተዘጋጀ፡፡ ቱሉ እዚያ ቁጥቋጦ ዘንድ ደረሰ፡፡ በውስጥ እየቆራረጠ ሲያልፍ ድንገት ከተደበቀበት እመር ብሎ ወጣ ለገሰ፡፡

ያቺን ጥልቆ በእጅ ይዟል፡፡ በፍጥነት ላዩ ላይ ተከመረበት፡፡ ቱሉ ሳይዘጋጅበት ስለነበር ወደ ኋላ ወደቀ፡፡ ለገሰ አልራራም ቱሉ ዓይኑ እያየው የአባቴ በዳኔ ገዳይ አገኘሁህ ብሎ በጥልቆው ጭንቅላቱን መታው፡፡ ግንባሩ ለሁለት የተከፈለው ቱሉ ወዲያው ነበር የሞታው፡፡ ለገሰ የቱሉን ጎፈሬ በእጁ ጎትቶ ነጩና ኪሱ ከትቶ እየበረረ ወደ ጫንጮ ከተማ አመራ፡፡ እዚያ በቀጠሯቸው መሰረት የምትጠብቀውን አክስቱን አገኘ፡፡
‹‹የወንድሜን ገዳይ ገደልከው?››
‹‹አዎ አዳዶ ገድዬልሻለሁ››
‹‹በምን ልመንህ?››
‹‹ይኸው ፀጉሩ››
ከኪሱ አውጥቶ አሳያት፡፡ አቅፋ ሳመችው ተያይዘው ወደ ሀገራቸው ሄዱ፡፡

ከ15 ቀናት በኋላ

ለገሰን ለመፈለግ ወደ ቤቱ የሄዱት የአካባቢው ታጣቂዎችና ፖሊሶች ገና የነለገሰ በር ሳይከፈት ነው የደረሱት፡፡ ዓለም ዘጠኝ ያሉትን እነለገሰንና አክስቱን በቤት እንዳሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ነበር እቅዱ፡፡ ውሻው ሲጮህ ግን የለገሰ አክስት በር ከፈተች፡፡ ተሰብስበው ስታያቸው ዘላ ገባችና በሩን ዘጋች፡፡ በዚህ መሀል የፀጥታ ኃይሎቹ በር ከፍተው ለመግባት ሲዘጋጁ ድንገት ከውስጥ የተኩስ ድምፅ ተሰማ፡፡ ያኔ ሁሉም መሳሪያቸውን አወጠና ጥግ ጥግ ያዙ፡፡ ለገሰ በጓሮ መስኮት ዘሎ ወጥቶ ጥሻው ውስጥ ሲመሽግ በጥይት አካባቢውን አመሱት፡፡ እሱም ተኮሰ፡፡ ብዙ አልቆየም ወዲያው ሲያቃስት ተሰማ፡፡ ተመታ፡፡ እዚያው የቤቱ ቢሮ ጓሮ ውስጥ ወደቀ፡፡ አልሞተም ነበርና ወደፍቼ ይዘውት መጡ፡፡ ይህን ሁሉ ቃል የተናገረው ሆስፒታል ሳለ ነው፡፡ ለ10 ቀናት ነበር በህይወት የቆየው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በጉዳቱ ሳቢያ አሸለበ፡፡ ፖሊሶች እዚህ ወጣት ላይ ያደረሱበት የቱሉ አባት የልጄ ገዳይ ለገሰ እንጂ ሌላ ማንም አይሆንም ብለው በማመልከታቸውና ለገሰ ለ3 ወር ከሰፈሩ ጠፍቶ መመለሱ በመታወቁ ነበር፡፡ አክስትየው ግን ለ3 ዓመታት ታስራ ተለቃለች፡፡ የበቀል ጦስ ሶስት ሰው ከዚህች ዓለም አሰናብቶ ተጠቃለለ፡፡ የሚቀጥል ይኖር ይሆን? ከ16 ዓመት በኋላም ቢሆን አሁንም የእነዚያ ሰዎች ቤተሰብ በስጋት መተያየቱን አላቆመም::

The post ቁርሾ – (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዲስ አበባ ግድግዳዎች በተቃውሞ ጽሑፍ አሸብርቀው አደሩ

$
0
0

addis ababa
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው:-

ቅዳሜ ጥር 9/2007አዲስ አበባ ዛሬ ሌሊት በትግሉ መፈክሮች አሸብርቃ አደረች! ተቃውሞውን እና ለትግሉ ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች ሲገልፅ የቆየው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁንም በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እየገለፀ ይገኛል።

የግራፊቲ መፈክሮቹ በቦሌ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በመካኒሳ፣ በቺቺኒያ፣ በአየር ጤና፣ በጦር ሀይሎች በሚገኘው መጅሊስ ቢሮ አካባቢ፣ በላንቻና በጎተራ፣ እንዲሁም በሌሎች ሰፈሮች ተፅፈው ያደሩ ሲሆን የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎችም በሁኔታው መደናገጣቸውን ማወቅ ተችሏል።

በግራፊቲው ከተፃፉት መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:–

«የጨለማ ፈራጆች!»
«ኮሚቴው የህዝብ ነው!»
«ሂጃብ መለያችን!»
«ትግሉ ይቀጥላል!»
«ፍትህ ለኮሚቴው!»

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post የአዲስ አበባ ግድግዳዎች በተቃውሞ ጽሑፍ አሸብርቀው አደሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


የኢ.ሕ.አ.ግ. ዓለም አቀፍ ኮሚቴ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት

$
0
0

ጥር:- 5 ቀን 2007 ዓ/ም
ለተከበራችሁ ለድርጅቱ ሥራ አመራር አባላትና በዱር በገድሉ ከጠላት ጋር ለምትዋደቁ ታጋይ ጓዶች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ፤ በማለት የአክብሮት ሰላምታችን እያቀርብን፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና በግንቦት 7 ለፍትህ ዴሞክራሲና የነጻነት ንቅናቄ መሀል የተደረገውን ውህደት በታወጀ ጊዜ
የተስማን ደስታ እጅግ የላቀ ነው::

ይህን የአንድነትና የወንድማማችነት ትስስር የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው በመሆኑ ይህ ውህደት ለህዝባችን ታላቅ የምስራች እንደሆነ እናምናልን::

ለዚህ ታላቅ ውህደት ለወድፊቱ ለምታደጉት የስራ እንቅስቃሴ ሁሉ ከጎናቸሁ የምንቆም መሆኑን እያረጋገጥን መጪው ጊዜ ይህ ሃገር ሻጭና ዜጋን ገዳይ የሆነ ዘረኛ የወያኔ ኢሃዴግ ጎጠኛ ድርጅት ተወግዶ ሰላምና ደስታ ህይወትና ብልጽግና የሰፈነባት ዜጎችዋ ሃገሪ ብለው የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለማየት እንድንበቃ ሁለንተናዊ አንድነት እና ኅብረት ለነጻነት በር ከፋች መሆኑን አምነን በጋራ ለመቆም ቃል እንገባለን !!
አንድነት ኃይል ነው!!
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዓለም አቀፍ ኮሚቴ

arbegnoch-427x264

 

The post የኢ.ሕ.አ.ግ. ዓለም አቀፍ ኮሚቴ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት appeared first on Zehabesha Amharic.

“ያልሰለጠኑ አሰልጣኞች” –የንጎቻው

$
0
0

‘ዋሻ ዘግተው’፤ ‘በዘር ቅኔ ደብትረው’ ደደቢት በድድብና ያደቆኑ፤
ብሔራዊ ካባ ቀደው የመንደር ቡትቶ ‘ውራጅ ጥብቆ’ የተጫኑ፤
ጥፋት፤ ድግምት ያጠነጠኑ፤ ‘በአበሻ ለምድ’፤ኮፈዳ ጣር፤ መከራ የለመኑ፤

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Woyanes shoud face justice

 

The post “ያልሰለጠኑ አሰልጣኞች” – የንጎቻው appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት የሕወሓት አባሉን ዳኛ ልኡል ገ/ማርያም በከፍተኛ ወጪ እያሳከመ ነው

$
0
0

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ልኡል ገ/ማርያም የተባለ የሕወሐት አባልና ዳኛ በከፍተኛ ወጪ በመንግስት እየታከመ መሆኑ ታውቋል። በዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት፣ በቅንጅት አመራሮችና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ እድሜ ልክና ሞት የፈረደ ነው።

newsዙቤር የተባለ ሃብታም የገዛ ጓደኛውን በውሻ እያስነከሰ በጥይት ደብድቦ ከገደለው በኋላ ጉዳዩ የቀረበው ልዑል ዘንድ ነበር። የፈርደበት 6 አመት በማለት ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብሎ ይህን ፍርድ ተብዬ እንዳስተላለፈ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ያስታውሱታል።

ይግባኝ የተጠየቀበት ዙቤር 22 አመት ፍርድ እንደተላለፈበትም ይታወሳል። ገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ ነክ ክሶችን በቀጥታ የሚመራው ወደ ልዑል ሲሆን አስቀድሞ ምን ፍርድ መስጠት እንዳለበት ተያይዞ ይነገረዋል። ዳኛ ተብዬው ልዑል ገ/ማርያም በልጆቹ እናት ላይ 5 ሴቶች በመወሸሙ ባለቤቱ ፍቺ ፈፅማለች። ባለፈው አመት በጠና በመታመሙ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኰ ከፍተኛ ህክምና የተደረገለት ሲሆን ለህክምናው 550ሺህ ዶላር ወጪ እንደተደረገ ተረጋግጧል። የስኳር ህመምተኛ የሆነው ልዑል በዘመኑ በሽታ ሳይለከፍ አይቀርም የሚሉ የቅርብ ምንጮች ቀደም ሲል የተደረገለት ህክምና በቂ ለውጥ ሊያመጣለት ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ታይላንድ ባንኮክ በህክምና ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ተችሏል።

በባንኮክ 7 ወሩ ሲሆን እስከአሁን 4ሚሊዮን 200ሺህ ብር ወጪ እንደተደረገለት ታውቋል። መንግስት አንድ የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እንኳ በአገር ውስጥ እንደማያሳክምና እንደማይረዳ እናውቃለን ያሉ የቅርብ ወገኖች ለሙሰኛውና ፍርደ ገምድሉ ልዑል ገ/ማርያም ይህን ያክል ወጪ መደረጉ አሳዛኝ ነው ብለዋል።

The post መንግስት የሕወሓት አባሉን ዳኛ ልኡል ገ/ማርያም በከፍተኛ ወጪ እያሳከመ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ታሥሮ የሚናከስ ውሻ –ተፈራ ድንበሩ

(ይናገራል ፎቶ) ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኤርትራ በርሃ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታጋዮች ጋር

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኤርትራ ከሚገኙ የኢትዮጵያውያን ታጋዮች ጋር ቆይታ አድርጓል:: ጋዜጠኛው እዚያው የሚገኙትንና ብረት አንስተው አሁን ያለውን የሕወሓት አስተዳደር ለመጣል ከሚታገሉት ታጋዮች ጋር የተነሳውን ፎቶዎች ይናገራል ፎቶ ስንል አቅርበንላችኋል::
mesay
mesay 2

The post (ይናገራል ፎቶ) ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኤርትራ በርሃ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታጋዮች ጋር appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live